Telegram Web Link
ማንችስተር ዩናይትድ ድል አድርጓል !

ማንችስተር ዩናይትድ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ተጠባቂ የፕርሚየር ሊግ መርሐግብር 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች አማድ ዲያሎ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከመረብ ሲያሳርፉ ለማንችስተር ሲቲ ቫርዲዮል አስቆጥሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ በዘንድሮው የውድድር አመት የተቆጠሩበት አርባ ሁለት በመቶ ግቦች ከቆመ ኳስ የተቆጠሩ መሆናቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከአሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በኋላ የመጀመሪያ የማንችስተር ደርቢ ጨዋታቸውን ያሸነፉ የመጀመሪያው የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሆነዋል።

ማንችስተር ሲቲ ካለፉት አስራ አንድ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ነው።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

5️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 27 ነጥብ
1️⃣2️⃣ማንችስተር ዩናይትድ :- 22 ነጥብ

ቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ?

ቅዳሜ - አስቶን ቪላ ከ ማንችስተር ሲቲ

እሁድ - ማንችስተር ዩናይትድ ከ በርንማውዝ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ድሉ የሚገባን ነው “ ሩበን አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የምሽቱ ድል የሚገባቸው መሆኑን ከጨዋታው በኋላ ተናግረዋል።

ቡድናቸው አሁንም መሻሻል እንደሚገባው የገለፁት አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም “ ነገርግን ለደጋፊው ትልቅ ድል ነው “ ሲሉ ቡድናቸው ጥሩ መስራቱን ጠቁመዋል።

በጨዋታው ልዩነት ፈጥረናል የሚሉት አሰልጣኙ “  የተመዘገበው ድል ይገባናል “ ሲሉ ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የባርሴሎና እና ሌጋኔስን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 5:00 ሰዓት ብቻ ነው።

🔴 ይነበብ

አንድ የቤተሰባችን አባል ግምት ማስቀመጥ የሚችለው #አንዴ ብቻ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ የመለሰ ቤተሰባችን ሽልማት አይደርሰውም።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
3 '

ቼልሲ 0-0 ብሬንትፎርድ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
15 '

ሳውዝሀምፕተን 0-3 ቶተንሀም

ማዲሰን
ሰን
ኩሉሴቭስኪ

ቼልሲ 0-0 ብሬንትፎርድ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
" እንደ 15ዓመት በታች ልጆች ነው የተጫወትነው " በርናርዶ ሲልቫ

የማንችስተር ሲቲው ተጨዋች በርናርዶ ሲልቫ ቡድናቸው በመጨረሻ ደቂቃዎች እንደ ታዳጊ ቡድኑ ደረጃ መጫወቱን ገልጿል።

" በመጨረሻ ደቂቃ የተጫወትነው እንደ 15ዓመት በታች ተጨዋች ነው " ያለው ሲልቫ ዋጋም አስከፍሎናል የተፈጠረው ነገር ይገባናል በማለት ተናግሯል።

ቡድኑ ራሱን መመልከት አለበት ሲል የተደመጠው ተጨዋቹ የማንችስተር ሲቲ ደረጃ ላይ አይደለንም ብሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
27 '

ሳውዝሀምፕተን 0-4 ቶተንሀም

                  ማዲሰን
                  ሰን
                  ኩሉሴቭስኪ
ሳር

ቼልሲ 0-0 ብሬንትፎርድ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
37 '

ሳውዝሀምፕተን 0-4 ቶተንሀም

                  ማዲሰን
                  ሰን
                  ኩሉሴቭስኪ
                  ሳር

ቼልሲ 0-0 ብሬንትፎርድ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
" መፍትሔ መፈለግ አልቻልኩም " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው የዚን ያህል የከፋ ችግር ውስጥ ይገባል ብለው ጠብቀው እንዳልነበረ ገልጸዋል።

“ በአመቱ መጀመሪያ አስቸጋሪ የውድድር አመት እንደሚሆን አውቅ ነበር “ ያሉት ጋርዲዮላ " የዚን ያህል ከባድ ይሆናል ብዬ ግን አላሰብኩም ነበር " ሲሉ ተናግረዋል።

" አሰልጣኝ እኔ ነኝ መፍትሔ የማፈላለግ ሀላፊነት የእኔ ነው ነገርግን ማግኘት አልቻልኩም እኔ በቂ አይደለሁም እውነታው ይሄ ነው።“ ጋርዲዮላ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
43'

ቼልሲ 1-0 ብሬንትፎርድ

ኩኩሬላ

ሳውዝሀምፕተን 0-4 ቶተንሀም

                  ማዲሰን
                  ሰን
                  ኩሉሴቭስኪ
                  ሳር

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
እረፍት

ቼልሲ 1-0 ብሬንትፎርድ

ኩኩሬላ

ሳውዝሀምፕተን 0-4 ቶተንሀም

                  ማዲሰን
                  ሰን
                  ኩሉሴቭስኪ
                  ሳር

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
47 '

ቼልሲ 1-0 ብሬንትፎርድ

ኩኩሬላ

ሳውዝሀምፕተን 0-5 ቶተንሀም

                  ማዲሰን
                  ሰን
                  ኩሉሴቭስኪ
                  ሳር

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
80 '

ቼልሲ 2-0 ብሬንትፎርድ

ኩኩሬላ
ጃክሰን

ሳውዝሀምፕተን 0-5 ቶተንሀም

                    ማዲሰን
                  ሰን
                  ኩሉሴቭስኪ
                  ሳር

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
90 '

ቼልሲ 2-1 ብሬንትፎርድ

ኩኩሬላ ምቤሞ
ጃክሰን

ሳውዝሀምፕተን 0-5 ቶተንሀም

                    ማዲሰን
                  ሰን
                  ኩሉሴቭስኪ
                  ሳር

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ሰማያዊዎቹ ጣፋጭ ድል ተቀዳጅተዋል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐግብር ቼልሲ ከብሬንትፎርድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሰማያዊዎቹን የድል ግቦች ኒኮላስ ጃክሰን እና ኩኩሬላ ከመረብ አሳርፈዋል።

ቼልሲ ማሸነፉን ተከትሎ ከፕርሚየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #ሁለት ማጥበብ ችለዋል።

ኢንዞ ፈርናንዴዝ ባለፉት ሰባት ጨዋታዎች ሰባት የግብ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የቼልሲው ተጨዋች ኩኩሬላ ቀይ ካርድ ተመልክቷል።

በሌላ ጨዋታ ቶተንሀም ከሳውዝሀምፕተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የቶተንሀምን የማሸነፊያ ግቦች ጄምስ ማዲሰን 2x ፣ ሰን ፣ ኩሉሴቭስኪ እና ፓፔ ሳር ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ሰን ሁንግ ሚን በፕርሚየር ሊጉ የቶተንሀም የምንግዜም ብዙ አመቻችቶ ማቀበል የቻለችው (68) ተጨዋች መሆን ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ ቼልሲ :- 34 ነጥብ
1️⃣0️⃣ ቶተንሀም :- 23 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ?

እሁድ - ቼልሲ ከ ኤቨርተን

እሁድ - ቶተንሀም ከ ሊቨርፑል

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ባርሴሎና ሽንፈት አስተናግዷል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የስፔን ላሊጋ የአስራ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብሩን ከሌጋኔስ ጋር አድርጎ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የሌጋኔስን የማሸነፊያ ግብ ሰርጂዮ ጎንዛሌዝ ከመረብ አሳርፏል።

ባርሴሎና በውድድር ዘመኑ አራተኛ የሊጉ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

በጨዋታው የባርሴሎናው የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል ጉዳት አጋጥሞታል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ባርሴሎና :- 38 ነጥብ
1️⃣5️⃣ኛ ሌጋኔስ:- 18 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ ባርሴሎና ከ አትሌቲኮ ማድሪድ

እሁድ ሌጋኔስ ከ ቪያሪያል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሳውዝሀምፕተን አሰልጣኙን አሰናበተ !

ትላንት ምሽት በቶተንሀም በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈው ሳውዝሀምፕተን አሰልጣኝ ሩሴል ማርቲንን ከሀላፊነት ማሰናበቱ ይፋ ተደርጓል።

ክለቡ ካደረጋቸው አስራ ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ሲሆን በአስራ ሶስቱ ተሸንፏል።

ሳውዝሀምፕተን አሁን ላይ በሊጉ በአምስት ነጥቦች የመጨረሻውን ደረጃ ይዘው ይገኛሉ።

ስኮትላንዳዊው አሰልጣኝ ሩሴል ማርቲን ከአሰልጣኝ ስቲቭ ኩፐር ፣ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ እና ጋሪ ኦኔል በመቀጠል አራተኛው ተሰናባች የፕርሚየር ሊግ አሰልጣኝ ሆነዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ይቅናዎት!
ኦዶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ተደርገዋል።
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
Forwarded from HEY Online Market
-Mackbook Air M3 (2024)
16GM RAM
256GB SSD Storage

175,000 birr

Contact us :
0953964175 @heymobile

Facebook |Instagram |Telegram

@Heyonlinemarket
2025/01/07 17:58:02
Back to Top
HTML Embed Code: