Telegram Web Link
" አሁንም ለዋንጫ ለመፎካከር ዝግጁ አይደለንም " ማሬስካ

የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬሳካ ቡድናቸው አሁንም የሊጉን ዋንጫ ለማሸነፍ ለመፎካከር ዝግጁ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

የምሽቱ ጨዋታ አስቸጋሪ እንደነበር የገለፁት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ትልቅ ድል ነበር ያሳካነው “ ማሸነፍ ይገባን ነበር " በማለት ተናግረዋል።

አሰልጣኙ አክለውም “ አሁንም ቼልሲ የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ ለማሸነፍ ዝግጁ ነው ብዬ አላስብም " በማለት ገልፀዋል።

ስድስተኛ ተከታታይ ድላቸውን ያሳኩት ሰማያዊዎቹ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል በሁለት ነጥቦች ዝቅ ብለው በ 3️⃣4️⃣ ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ዲያጎ ሚሊቶ በፕሬዝዳንትነት ተመርጧል !

የቀድሞ የኢንተር ሚላን ተጨዋች ዲያጎ ሚሊቶ የአርጀንቲናው ክለብ ሬሲንግ ፕሬዝዳንት በመሆን ማሸነፉ ተገልጿል።

የ 45ዓመቱ ዲያጎ ሚሊቶ እስከ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ማሸነፍ የዘለቀው የእግርኳስ ህይወቱ የጀመረበትን የልጅነት ክለቡ ሬሲንግ በፕሬዝዳንትነት የሚመራ ይሆናል።

ዲያጎ ሚሊቶ የምርጫውን ስልሳ በመቶ ድምፅ ማሸነፉ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ አራት አመታት ክለቡን በፕሬዝዳንትነት የሚያገለግል ይሆናል።

“ ህልሜ እውን ሆኗል ለመሆን ሳልመው የነበረው ቦታ ላይ ሆኛለሁ “ ሲል ዲያጎ ሚሊቶ ከድሉ በኋላ ተናግሯል።

አርጀንቲናዊው የቀድሞ የፊት መስመር አጥቂ ዲያጎ ሚሊቶ በኢንተር ሚላን ቤት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እና ሴርያ ዋንጫዎችን አሳክቷል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

የማንችስተር ዩናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ

1ኛ. @eliabte
2ኛ. @AGarnacho17
3ኛ. Tame dan

የቼልሲ እና ብሬንትፎርድ

1ኛ. @adugna25
2ኛ. @Dua_Lipa1223
3ኛ. @Miko_Ye_Michael

 የባርሴሎና እና ሌጋኔስ

1ኛ. @Sa_aved
2ኛ. Faris kemal
3ኛ. Misael/cheru

🔴 አሸናፊዎች @Kidusyoftahe ስልክ ቁጥር በማስቀመጥ ሽልማታቸውን መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ሽልማቱ በነገው ዕለት የሚደርሳቸው ይሆናል።

@tikvahethsport
ቼልሲ ተጨዋቾቹ በቀጣይ ይመለሳሉ !

የሰማያዊዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፊሊክስ ሐሙስ በሚደረገው የኮንፈረንስ ሊግ ጨዋታ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ገልጸዋል።

ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጇ ፊሊክስ በጉዳት ምክንያት ያለፉት የቡድኑ ጨዋታዎች እንዳመለጡት ይታወሳል።

ቤልጂየማዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች በበኩሉ በሚቀጥለው የፕርሚየር ሊግ መርሐግብር ወደ ሜዳ እንደሚመለስ አሰልጣኙ አረጋግጠዋል።

ቼልሲ በቀጣይ ሐሙስ በኮንፈረንስ ሊግ ከሻምሮክ ሮቨርስ እንዲሁም እሁድ በሊጉ ከኤቨርተን ጋር ይጫወታሉ።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
ሀሪ ማጓየር ውሉን ለማራዘም ንግግር ላይ ነው !

እንግሊዛዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሀሪ ማጓየር በአዲስ ኮንትራት ዙሪያ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ንግግር ላይ እንደሚገኝ አረጋግጧል።

ሀሪ ማጓየር በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ያለው ለአንድ ተጨማሪ አመት የመቆየት አማራጭ ያካተተው ውል በውድድር አመቱ መጨረሻ ይጠናቀቃል።

ኮንትራቱ ሊጠናቀቅ የስድስት ወራት እድሜ የቀረው ሀሪ ማጓየር በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ሳምንታዊ 190,000 ፓውንድ እንደሚከፈለው ይታወቃል።

“ ቀሪው የውድድር አመት እና ለተጨማሪ አመት የመቆየት አማራጭ አለኝ እየተደረገ ያለው ንግግርም በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል “ ሲል ሀሪ ማጓየር ተናግሯል።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
ኪሊያን ምባፔ ወደ ልምምድ ተመልሷል !

በጉዳት ላይ የነበረው ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ወደ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል።

ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት የራዮ ቫዬካኖ ጨዋታ ያመለጠው ኪሊያን ምባፔ በዛሬው ዕለት በግሉ ልምምድ መስራቱ ተነግሯል።

ተጨዋቹ በቀጣይ ለፊፋ ኢንተርኮንቲኔንታል ካፕ ጨዋታ ከሪያል ማድሪድ ስብስብ ጋር ወደ ኳታር እንደሚያመራ በይፋ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ኪሊያን ምባፔ በፊፋ ኢንተርኮንቲኔንታል ካፕ ጨዋታ ላይ ይሳተፋል ተብሎ እንደማይጠበቅ ተጠቁሟል።

ሪያል ማድሪድ የፊታችን እሮብ ምሽት 2:00 ሰዓት ከሜክሲኮው ክለብ ፓቹካ ጋር የኢንተርኮንቲኔንታል ካፕ ፍፃሜ ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
🔥 ይጋብዙ ፣ ይሸለሙ 🔥

👉🏽አሁንም መሸለማችንን እንደቀጠልን ነው 🎁💥

ከእናንተ የሚጠበቀው የሳፋሪኮም መስመራችሁን በመጠቀም የተጠቀሱትን ቅደም ተከተሎች መተግበር ነው🫰🏽

ያስተውሉ 👉🏽 በእርስዎ ጋባዥነት የሚቀላቀለው ሰው ቁጥር ሲጨምር የሽልማቱም መጠን እየጨመረ ይሄዳል 😱 እንዲሁም ተጋባዦቻችሁ ገፁን ከተቀላቀሉ በኃላ “back” የሚለውን ተጭነው “check subscription” እንዲያደርጉ ያሳስቡ 💥

የቴሌግራም ቻናላችን 👉🏽 https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC

የቴሌግራም ቦታችን👉🏽 https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot

መልካም እድል 🎁

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit
#Furtheraheadtogether
ላሚን ያማል ጉዳት አጋጥሞታል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል የቁርጭምጭሚት ጉዳት እንዳጋጠመው ክለቡ አስታውቋል።

ተጨዋቹ ትላንት ምሽት ባርሴሎና በሌጋኔስ በተሸነፈበት ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ መውጣቱ አይዘነጋም።

ይህንንም ተከትሎ ስፔናዊው ተጨዋች ላሚን ያማል በጉዳት ምክንያት ቢያንስ ለአንድ ወር ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ተገልጿል።

የዘንድሮው የጎልደን ቦይ ሽልማት አሸናፊው ላሚን ያማል በዘንድሮው የውድድር አመት ተደጋጋሚ ጉዳቶች እያጋጠሙት ይገኛሉ።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሾመ !

የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን በዛሬው ዕለት ራፋኤል ሎዛንን የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አድርጎ መሾሙ በይፋ ተገልጿል።

የ 2030 አለም ዋንጫ ውድድርን በጣምራ እንድታዘጋጅ ከቀናት በፊት በይፋ የተመረጠችው ስፔን አዲስ የእግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አግኝታለች።

ራፋኤል ሎዛን ብቸኛ ተቀናቃኛቸው የነበረውን ሳልቫዶር ጎማን በመርታት የፌዴሬሽኑን ፕሬዝዳንትነት ምርጫ ማሸነፍ ችለዋል።

የ 57ዓመቱ ፕሬዝዳንት ራፋኤል ሎዛን እ.ኤ.አ ከ 2019 ወዲህ በስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ነበሩ።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
#CAFAwards2024

የ 2024 የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ሽልማት ስነስርዓት ዛሬ ምሽት በሞሮኮ ማራካሽ “ Palais des Congrès " ይካሄዳል።

በስነ ስርዓቱ የሚጠበቁ ሽልማቶች የትኞቹ ናቸው ?

- የአመቱ ምርጥ ተጨዋች
- የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ
- የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ
- የአመቱ ምርጥ ብሔራዊ ቡድን
- የአመቱ ምርጥ ክለብ

የሽልማቱ የመጨረሻ እጩዎች እነማን ናቸዉ ?

የአመቱ ምርጥ ተጨዋች :-

አሽራፍ ሀኪሚ
ሴርሁ ጁራሲ
ሲሞን አዲንጋራ
አዴሞላ ሉክማን
ሮንዌን ዊልያምስ

የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ :-

አንድሬ ኦናና
ያህያ ፎፋና
ሮንዌን ዊልያምስ

የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ :-

ኤሜርስ ፋኢ
ሴባስቲያን ዴሳብሬ
ሁጎ ብሩስ

የሽልማት ስነስርዓቱ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ በሞሮኮ መካሄዱን ይጀመራል።

እነማን ያሸንፋሉ ?

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
ዴሊ አሊ ወደ ልምምድ ሊመለስ ነው !

እንግሊዛዊው ተጨዋች ዴሊ አሊ ከሚቀጥለው ጥር ወር ጀምሮ ከጣልያኑ ክለብ ኮሞ ጋር ልምምድ መስራት ሊጀምር መሆኑ ተገልጿል።

በአሰልጣኝ ሴስክ ፋብሬጋስ የሚመራው ኮሞ ዴሊ አሊ ከቡድኑ ጋር ልምምድ በመስራት ወደ አቋሙ እንዲመለስ ለማገዝ መስማማታቸው ተነግሯል።

የቀድሞ የቶተንሀም አማካይ ዴሊ አሊ ባለፈው አመት ከኤቨርተን ጋር ያለው ኮንትራት ከተጠናቀቀ በኋላ ያለ ክለብ ይገኛል።

ዴሊ አሊ ባጋጠመው የረጅም ጊዜ ጉዳት ምክንያት ላለፉት አስራ አንድ ወራት እግርኳስ ጨዋታ ማድረግ አልቻለም።

ዴሊ አሊ በቀጣይ በኮሞ ተጨዋችነት ሊቀጥል እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሳውዝሀምፕተን አሰልጣኙን አሰናበተ ! ትላንት ምሽት በቶተንሀም በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈው ሳውዝሀምፕተን አሰልጣኝ ሩሴል ማርቲንን ከሀላፊነት ማሰናበቱ ይፋ ተደርጓል። ክለቡ ካደረጋቸው አስራ ስድስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ሲሆን በአስራ ሶስቱ ተሸንፏል። ሳውዝሀምፕተን አሁን ላይ በሊጉ በአምስት ነጥቦች የመጨረሻውን ደረጃ ይዘው ይገኛሉ። ስኮትላንዳዊው አሰልጣኝ ሩሴል ማርቲን…
“ አሰልጣኙ መሰናበት አልነበረበትም “

የሳውዝሀምፕተኑ ተጨዋች ታይለር ሀርውድ ክለቡ አሰልጣኝ ሩሴል ማርቲንን ማሰናበቱ ትክክል እንዳልነበረ ተናግሯል።

በውጤት ማጣት ውስጥ የሚገኘው ሳውዝሀምፕተን ከትላንት ምሽቱ የቶተንሀም ከባድ ሽንፈት በኋላ አሰልጣኝ ሩሴል ማርቲንን ማሰናበቱ ይታወቃል።

ሩሴል ማርቲን መሰናበታቸው ትክክል እንዳልነበረ የገለፀው ታይለር ሀርውድ “ ተቃውሞው ወደ አሰልጣኙ መሆን አልነበረበትም “ ሲል ተናግሯል።

“ ተጠያቂነቱ የእኛ ተጨዋቾቹ እንጂ የአሰልጣኙ አይደለም “ የሚለው ተጨዋቹ ሜዳ ላይ ስህተት የሰራነው እኛ እንጂ አሰልጣኙ አይደለም ብሏል።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
TIKVAH-SPORT
#CAFAwards2024 የ 2024 የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ሽልማት ስነስርዓት ዛሬ ምሽት በሞሮኮ ማራካሽ “ Palais des Congrès " ይካሄዳል። በስነ ስርዓቱ የሚጠበቁ ሽልማቶች የትኞቹ ናቸው ? - የአመቱ ምርጥ ተጨዋች - የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ - የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ - የአመቱ ምርጥ ብሔራዊ ቡድን - የአመቱ ምርጥ ክለብ የሽልማቱ የመጨረሻ እጩዎች እነማን ናቸዉ ? የአመቱ…
#CAFAwards2024

የ 2024 የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ሽልማት ስነስርዓት በአሁን ሰዓት በሞሮኮ ማራካሽ “ Palais des Congrès " በመካሄድ ላይ ይገኛል።

እስካሁን ባለው የሽልማት ስነስርዓት በተለያዩ ዘርፎች አሸናፊዎች ይፋ ሲደረጉ ከእነዚህም መካከል :-

የአመቱ ምርጥ የወንዶች ብሔራዊ ቡድን :- የኮትዲቫር ብሔራዊ ቡድን

የአመቱ ምርጥ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን :- የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን

የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች :- ላሚን ካማራ

የአመቱ ምርጥ ክለብ :- አል አህሊ

በሌሎች ዘርፎች በቀጣይ ይፋ የሚደረጉ ይሆናል።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ታወቀ !

የ 2024 የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ከደቂቃዎች በፊት በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው የሽልማት ስነስርዓት ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ናይጄሪያዊው የአታላንታ የፊት መስመር ተጨዋች አዴሞላ ሉክማን የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።

አዴሞላ ሉክማን በ2024 ባደረጋቸው 5️⃣7️⃣ ጨዋታዎች 2️⃣7️⃣ ግቦችን አስቆጥሮ 1️⃣3️⃣ አመቻችቶ ማቀበል ችሏሌ።

በተጨማሪም ከአትላንታ ጋር የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ሲያሳካ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ ተፋላሚ እንዲሆንም አግዟል።

ሉክማን የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማት ያሸነፈ ሰባተኛው ናይጄሪያዊ ተጨዋች መሆን ችሏል።

ሌሎች አሸናፊዎች እነማን ናቸው  ?

የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ :- ሮንዌን ዊሊያምስ

የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ :- ኤሜርስ ፋኢ

የአመቱ ምርጥ ሴት ተጨዋች :- ባርብራ ባንዳ

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
ይቅናዎት!
ኦዶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ተደርገዋል።
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
Forwarded from HEY Online Market
-Mackbook Air M3 (2024)
16GM RAM
256GB SSD Storage

175,000 birr

Contact us :
0953964175 @heymobile

Facebook |Instagram |Telegram

@Heyonlinemarket
2025/01/08 15:48:37
Back to Top
HTML Embed Code: