Telegram Web Link
Forwarded from WANAW SPORT
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሩበን አሞሪም የራሽፎርድን ሁኔታ በራሳቸው ይፈታሉ !

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የማርከስ ራሽፎርድን ሁኔታ በራሳቸው እንዲፈተቱ ከክለቡ ሀላፊዎች ፍቃድ እንደተሰጣቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

ሰር ጂም ራትክሊፍም ሆኑ የክለቡ ሀላፊዎች በማርከስ ራሽፎርድ የወደፊት ቆይታ ዙሪያ ጣልቃ እንደማይገቡ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማርከስ ራሽፎርድን በተከታታይ ሶስት ጨዋታዎች ከቡድናቸው ስብስብ ውጪ ማድረጋቸው አይዘነጋም።

ማርከስ ራሽፎርድ በ 350,000 ፓውንድ ከክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ ተጨዋቾች አንዱ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኦስካር ወደ ብራዚል ሊመለስ ነው !

ብራዚላዊው የቀድሞ የቼልሲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኦስካር ወደ ቀድሞ የልጅነት ክለቡ ሳኦ ፓውሎ ለመመለስ መቃረቡ ተገልጿል።

የ 33ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኦስካር ከቻይናው ክለብ ሻንጋይ ፖርት ጋር ከተለያየ በኋላ ያለ ክለብ ይገኝ ነበር።

ኦስካር በቻይና ሊግ በነበረው የሰባት አመታት ቆይታ 175 ሚልዮን ፓውንድ መሰብሰቡ ተገልጿል።

ኦስካር አሁን ላይ ሳኦ ፓውሎን ለሶስት የውድድር አመታት ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በኦልድትራፎርድ አይጦች ማስቸገራቸው ተገለጸ !

በማንችስተር ዩናይትዱ ኦልድትራፎርድ ስታዲየም አይጦች ማስቸገራቸውን ዴይሊ ሜይል አስነብቧል።

የአካባቢው የንፅህና ተቆጣጣሪዎች በኦልድትራፎርድ ጉብኝታቸው ወቅት በስታዲየሙ አይጥ ማግኘታቸው ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ክለቡ ከነበረው የንፅህና ቁጥጥር አምስት ኮከብ ደረጃ ሁለት ደረጃዎች መቀነሳቸው ተዘግቧል።

አብዛኞቹ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች አምስት ኮከብ የንፅህና ጥራት ደረጃዎች እንዳሏቸው ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ ችግሩን ለማስተካከል ከአካባቢው የፀረ ተባይ ተቆጣጣሪዎች ጋር እየሰሩ መሆኑ ተነግሯል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል በሳካ ቦታ ማንን ሊጠቀም ይችላል ?

እንግሊዛዊው የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዩ ሳካ በጉዳት ምክንያት ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል።

የቡካዩ ሳካን ጉዳት ተከትሎ ወደ ዝውውር ገበያው ይገቡ እነደሆነ የተጠየቁት ሚኬል አርቴታ “ ያሉንን ተጨዋቾች ለመጠቀም ነው ሀሳቤ “ ብለዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አክለውም የቡካዩ ሳካ ጉዳት ከባድ ሊሆን እንደሚችል በመጠቆም ከውድድር ዘመኑ መጠናቀቅ በፊት ይመለሳል ብዬ እጠብቃለሁ ብለዋል።

በቀጣይ ጨዋታዎች ቡካዩ ሳካ በሚሰለፍበት የቀኝ የፊት መስመር ቦታ የተለያዩ ተጨዋቾች መሰለፍ እንደሚችሉ አሰልጣኙ ጠቁመዋል።

በቀጣይ በቀኝ የፊት መስመር ቦታ ጄሱስ ፣ ሀቨርትዝ ፣ ትሮሳርድ ፣ ማርቲኔሊ እና ንዋኔሪን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አርቴታ ተናግረዋል።

ጋብሬል ማርቲኔሊ የመጀመሪያ ተመራጭ ሊሆን እንደሚችል የጠቆሙት አርቴታ “ እሱ ከዚህ በፊት ተሰልፎ ጥሩ ነገር አሳይቷል ጥሩ አማራጭ ነው “ ብለዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
🔹Mackbook M2 Air

•02 CC 139,000 Birr
•15 CC 129,000 Birr
•50 CC 119,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile

@Heyonlinemarket
🎁🎁 የቤቲካ የገና ስጦታዎች 🎁🎁

💰 የአቪዬተር የበአል ሽልማት 225,000 ብር ይዞ መቷል !
💰

ብዙ ማባዣዎች(x) የሚሰበስቡ ደንበኞች 225,000 ብር ይካፈላሉ!

ታዲያ ምን ይጠብቃሉ?
ይወራረዱ፣በትልቁ ያሸንፉ፣ከስጦታ እና ጉርሻዎቹ የድርሻዎን ይውሰዱ።


ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት
“ ትኩረቴ ራሽፎርድን ማሻሻል ላይ ነው “ አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማርከስ ራሽፎርድ የሰጠውን ቃለምልልስ ወደ ጎን በመተው አቋሙ ላይ ብቻ እያተኮሩ መሆኑን ገልጸዋል።

“ አሁን ላይ ትኩረት እያደረኩ ያለሁት ራሽፎርድን ማሻሻል ላይ ብቻ ነው “ ያሉት ሩበን አሞሪም "  እንደሱ አይነት ተሰጥኦ ያለው ተጨዋች ያስፈልገናል " ብለዋል።

" እሱ ያደረገውን ቃለምልልስ ረስቼ ሜዳ ላይ የማየውን ነገር ብቻ እየተመለከትኩ ነው “ ሲሉ ሩበን አሞሪም ተናግረዋል።

አሰልጣኙ አክለውም “ እንደ አሰልጣኝ ትኩረት የማደርገው የእሱ አቋም እና ልምምድ ላይ ነው ሌላው ጊዜው ሲደርስ ቢሆን ለእኔም ለክለቡም ጥሩ ነው።“ ብለዋል።

“ እንደዚህ አይነት ተጨዋቾች በዙሪያቸው ብዙ ሰዎች እንዳሉ እረዳለሁ አንዳንድ ጊዜ የራሳቸው ሀሳብ ያልሆነ ውሳኔም ይወስናሉ።“ ሩበን አሞሪም

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሌክስ ኢዎቢ በነፃ የሚያገለግል ሱቅ ከፍቷል !

ናይጄሪያዊው የፉልሀም የፊት መስመር ተጨዋች አሌክስ ኢዎቢ ለንደን ውስጥ በነፃ የሚያገለግል የራሱን ጊዜያዊ ሱቅ መክፈቱ ተገልጿል።

የቀድሞ የአርሰናል ተጨዋች አሌክስ ኢዎቢ በጊዜያዊ ሱቁ ለገና በዓል ምግብ ለመግዛት አቅም ለሌላቸው ሰዎች በነፃ ምግብ ማከፋፈሉ ተነግሯል።

“ የገና በዓልን ደስተኛ ሆነው እንዲያሳልፉ መርዳት ከቻልኩኝ ለምን አላደርገውም “ ሲል አሌክስ ኢዎቢ ሰዎችን በመርዳቱ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል።

“ ሰዎች ቤተሰባቸውን ይዘው መጥተው የሚፈልጉትን ይዘው መሄድ የሚችሉበትን ቦታ መፍጠር እፈልጋለሁ “ አሌክስ ኢዎቢ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዴቪድ ኩት ይግባኝ መጠየቅ አይፈልጉም !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዳኛ የነበሩት ዴቪድ ኩት የፕርሚየር ሊጉ ፕሮፌሽናል ዳኞች ማኅበር ከስራቸው እንዳሰናበታቸው ይታወቃል።

ዋና ዳኞው በቅርቡ በተሰራጨ የቪዲዮ ቅጂ ሊቨርፑልን እና የቀድሞ አሰልጣኛቸውን የርገን ክሎፕን ሲሳደቡ እና ሲተቹ ተስተውለው እንደነበር ይታወሳል።

የ 49ዓመቱ ዳኛ ዴቪድ ኩት አሁን ላይ ከስራቸው የተባረሩበትን ውሳኔ ለመቀበል ማሰባቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ዋና ዳኛው ውሳኔውን ተተቃውመው ለእንግሊዝ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች ማኅበረ ይገባኝ መጠየቅ እንደማይፈልጉ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ዋና ዳኛውን ከዚህ በኋላ በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች የማንመለከታቸው ይሆናል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
ቶተንሀም ተጨዋች ማስፈረም ይፈልጋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም በጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት አዲስ ተጨዋቾች ማስፈረም እንደሚፈልግ አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ተናግረዋል።

ቶተንሀም ወሳኝ ተጨዋቾቹ ቫን ዴቪን ፣ ክርስቲያን ሮሜሮ እና ግብ ጠባቂው ቪካርዮን ጨምሮ ሰባት ተጨዋቾቹ በጉዳት ላይ ይገኛሉ።

" በአንዳንድ የሜዳ ክፍሎች ስብስባችን የሳሳ ነው ቦታውን በጥር ማጠናከር አለብን " ሲሉ አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ተናግረዋል።

ቶተንሀም በሊጉ ሀያ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
ባርሴሎና ተጨዋቹ ጉዳት አጋጥሞታል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋቹ ፌራን ቶሬስ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።

ስፔናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፌራን ቶሬስ ባርሴሎና በአትሌቲኮ ማድሪድ በተሸነፈበት ጨዋታ ጉዳት እንዳጋጠመው ክለቡ አስታውቋል።

ባርሴሎና ተጨዋቹ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ የሚመለስበትን ጊዜ በግልጽ አላስቀመጠም።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
ሲቲ የተጫዋቹን ግልጋሎት አያገኝም !

ማንችስተር ሲቲ ሐሙስ ከኤቨርተን ጋር በሚያደርገው የሊግ መርሐግብር የተጫዋቹን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አረጋግጠዋል።

እንግሊዛዊው ተከላካይ ጆን ስቶንስ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ መሆኑን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

ቡድናቸው ዛሬ የልምምድ መርሐግብር እንዳለው የገለፁት ፔፕ ጋርዲዮላ ምንያህል ተጨዋቾች ዝግጁ እንደሆኑ ገና አላወቅኩም ብለዋል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
" አሁን ላይ ለእኛ ቀላል ተጋጣሚ የለም " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ሐሙስ ከኤቨርተን ጋር ከሚያደርገው የሊግ መርሐግብር በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ምን አሉ ?

- ኤቨርተን ቀላል ተጋጣሚ ነው ብለን አናስብም አሁን ባለንበት ሁኔታ ለእኛ ቀላል የሚባል ተጋጣሚ የለም።

- በጨዋታው ወደ አሸናፊነት መመለስ እንፈልጋለን ጊዜ ይወስዳል ነገርግን በቻልነው ፍጥነት ነጥብ ማግኘት አለብን።

- ኤቨርተን ጥሩ አቋም ላይ ሆኖ ነው የምንገጥመው ጥሩ መሆናቸውን ቁጥሮች እና እንቅስቃሴያቸው ያሳያል።

- ኤርሊንግ ሀላንድ ለእኛ ወሳኝ ተጨዋች ነው እሱን በጥሩ መንገድ ለመጠቀም የተሻሉ ነገሮችን ማድረግ አለብን።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
ያልተጠበቁ ውጤቶች ያስተናገደው የዘንድሮ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አሁንም እንደቀጠለ ነው!

ቦክሲንግዴይ ፍልሚያ ደግሞ ታህሳስ 17 እና 18 ይካሄዳል! የሊጉ መሪ ሊቨርፑል የነጥብ ልዩነቱን ያሰፋል ወይስ ቼልሲ፥ አርሰናልና ማን ሲቲ ልዩነቱን ያጠቡታል?

ያጓጓል!

👉እነዚህን ድንቅ ፍልሚያዎች ጨምሮ ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ይመልከቱ።

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

#PremierLeagueallonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
“ ጠንካራ መሆን አለብን “ ሩበን አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድናቸው ጥሩ ያልሆነ ጊዜ ላይ ቢሆንም ጠንካራ መሆን አለብን ሲሉ ገልጸዋል።

“ አሁን ያለንበት ሁኔታ ከክለባችን አስከፊ ጊዜያት አንዱ ሊሆን ይችላል “ የሚሉት ሩበን አሞሪም ጠንካራ መሆን እና ሁኔታውን መጋፈጥ አለብን ብለዋል።

“ አሁን ስለ በዓል አላስብም ጨዋታ ስለማሸነፍ ብቻ ነው ሀሳቤ ሙሉ ትኩረታችን ቀጣዩን ጨዋታ ስለማሸነፍ ብቻ ነው “ ሲሉ ሩበን አሞሪም ተናግረዋል።

“ ምቾት የሚሰማኝ ጊዜ ላይ አይደለሁም አስቸጋሪ ወቅት ላይ ነን ነገርግን ችግሮችን ቀስ በቀስ በመፍታት ለሁሉም ጥያቄዎች መልስ እናገኛለን።“ ሩበን አሞሪም

ሰለ ራሽፎርድ ሁኔታ ያነሱት አሰልጣኙ እሱ ቡድኑን ለማሻሻል ትልቅ ሀላፊነት አለበት “ እዚህ ብዙ አመት የቆዩ እና ትልቅ አቅም ያለባቸው ተጨዋቾች ትልቅ ሀላፊነት አለባቸው “ ብለዋል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
“ ሲቲ ወደ ዋንጫ ፉክክሩ ይመጣል “ ማሬስካ

የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ስለ ዋንጫ ፉክክር ያለማሰባቸው ምክንያት “ ጫና ሳይሆን እውነት ነው " በማለት ተናግረዋል።

የዋንጫ ፉክክር ውስጥ የለንም ማለታቸው ጫና በመፍራት አለመሆኑን ያነሱት ኢንዞ ማሬስካ “ እንደዚህ አይነት ጫናዎች መቋቋም እንፈልጋለን ነገርግን የተናገርነው እውነታ ነው “ ብለዋል።

ኢንዞ ማሬስካ አክለውም “ ማንችስተር ሲቲ በመጨረሻ ሰዓት ወደ ዋንጫ ፉክክሩ ይመጣል “ ሲሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

“ ማንችስተር ሲቲ ከዚህ በፊት ገጥሟቸው በማያውቅ ችግር ውስጥ እያለፉ ነው በየጨዋታው ጉዳት እያጋጠማቸው ነው አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ናቸው።“ ማሬስካ

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
2024/12/25 02:38:56
Back to Top
HTML Embed Code: