Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ራሽፎርድ ወደ ጣልያን ሊያመራ ይችላል ! እንግሊዛዊው የተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ ባለፉት ጨዋታዎች በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም አለመመረጡን ተከትሎ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ሲገለፅ ነበር። አሁን ላይ ዘ አትሌቲክ ባወጣው ዘገባ ማርከስ ራሽፎርድ በዚህ ወር የጣልያን ሴርያ መዳረሻው ሊሆን እንደሚችል አስነብቧል። ጆሽዋ ዚርኪዜ በበኩሉ በጁቬንቱስ እየተፈለገ ቢሆንም በጥር ማንችስተር ዩናይትድን መልቀቅ…
ዶርትመንድ ራሽፎርድን ለማስፈረም ሊጠይቁ ነው !

የጀርመኑ ክለብ ቦርስያ ዶርትመንድ ማርከስ ራሽፎርድን በውሰት ለማስፈረም ጥያቄ ሊያቀርቡ ማሰባቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።

የማንችስተር ዩናይትዱ ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ በተጨማሪም በኤሲ ሚላን እና ጁቬንቱስ እየተፈለገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች እንዲሁ ማርከስ ራሽፎርድን በውሰት እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ለማስፈረም ማሰባቸው ተነግሯል።

ጋላታሳራይ በተመሳሳይ የተጨዋቹ ፈላጊ ቢሆኑም ማርከስ ራሽፎርድ በአምስቱ ታላላቅ ሊጎች ብቻ መጫወት እንደሚፈልግ ተዘግቧል።

@Tikvahethsport   @kidusyoftahe
“ ያስመዘገብነው ውጤት የሚገባን ነው “ አርኔ ስሎት

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ከነገው የቶተንሀም የካራባኦ ካፕ ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኙ በንግግራቸውም :-

- " በቡድኑ ውስጥ ያለ ሁሉም ተጨዋች ለመጫወት ብቁ እና ዝግጁ ነው ይሄ ጥሩ ነገር ነው ሁሉም ነገ መጫወት ይፈልጋሉ።

- በማንችስተር ዩናይትድ ጨዋታ ሁላችንም ባሳየነው እንቅስቃሴ እና በውጤቱ ተበሳጭተናል በአርኖልድ ብቻ አይደለም።

- ቡድኑን ከባለፈው የውድድር ዘመን ጋር ማነፃፀር ከባድ ነው የማውቀው ነገር ቢኖር ምንም ነጥብ እንዳልሰረቅን ነው ያገኘነው ነገር በሙሉ የሚገባን ነው።

- ከቶተንሀም ጋር በነበረን ጨዋታ ብዙውን የጨዋታ ጊዜ ራሳችንን አሳይተናል ነገርግን እነሱም በተወሰነ ጥሩ ነገር አስመልክተውናል።" ብለዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ኤለን መስክ ሊቨርፑልን መግዛት ይፈልጋል !

አሜሪካዊው ቢሊየነር ኤለን መስክ የመርሲሳይዱን ክለብ ሊቨርፑል የመግዛት ፍላጎት እንዳለው ወላጅ አባቱ ኤሮል መስክ አረጋግጠዋል።

የኤለን መስክ ወላጅ አባት በንግግራቸውም “ ልጄ ሊቨርፑልን መግዛት ይፈልጋል አያቱ ከሊቨርፑል ነች እዛ ቤተሰብ አለን “ ሲሉ ተደምጠዋል።

የእንግሊዝ ጋዜጦች ከሰሞኑ ኤለን መስክ ሊቨርፑልን በ 6️⃣ ቢልዮን ፓውንድ ለመግዛት አቅዷል የሚል መረጃ በፊት ገፆቻቸው ይዘው ወጥተው ነበር።

የ “ X ” ፣ ቴስላ እና “ SpaceX " ባለቤቱ ኤለን መስክ ሊቨርፑልን የመግዛት ሀሳቡ በዩናይትድ ኪንግደም ያለውን ተፅዕኖ ለማሳደግ እንደሚረዳው ተዘግቧል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ስኬታማው የቻይና ክለብ ከሊጉ ውጪ ሆነ !

ስኬታማው የቻይና ክለብ ጉዋንጆ እግርኳስ ክለብ በሚቀጥለው የቻይና ሱፐር ሊግ ውድድር እንደማይሳተፍ ተገልጿል።

ክለቡ በገባበት የፋይናንስ ችግር ምክንያት ያለበትን እዳ መክፈል ባለመቻሉ በአዲሱ የውድድር አመት መሳተፍ እንደማይችል ተነግሯል።

የቻይና ሱፐር ሊግን 8️⃣ ጊዜ በማሸነፍ ስኬታማው የቻይና ክለብ የሆነው ጉዋንጆ ክለብ አሁን ላይ በሊጉ ለመሳተፍ ከቻይና እግርኳስ ፌዴሬሽን ፍቃድ አላገኘም።

ክለቡ በእስያ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለት ጊዜ ባለክብር ሲሆን በአለም ክለቦች ዋንጫ አንድ ጊዜ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀ ነው።

ጉዋንጆ በአለም ክለቦች ዋንጫ አራተኛ ደረጃን ይዞ ባጠናቀቀበት አመት ከሪያል ማድሪድ ጋር በአካዳሚ አጋርነት ለመስራት ስምምነት መፈፀም ችለዋል።

በተጨማሪም 100,000 ተመልካች መያዝ የሚችል ስታዲየም ለመገንባት ማቀዳቸውን አስታውቀው ነበር።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ባርሴሎና የሜሲን አልባሳት ማስቀመጫ ሊሸጥ ነው !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የአርጀንቲናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ አልባሳት ማስቀመጫ በጨረታ ሊሸጡ መሆኑ ተገልጿል።

ባርሴሎና የታሪካዊ ተጨዋቾቻቸውን አልባሳት ማስቀመጫ በ 350,000 ዩሮ በጨረታ ለሽያጭ እንደሚያቀርቡት ተነግሯል።

የአልባሳት ማስቀመጫ ሽያጩ ባርሴሎና ካለበት የፋይናንስ ችግር እንዲወጣ እንደሚያግዘው ተገልጿል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የቤቲካ የገና ስጦታ ተመልሷል!
ጨምሯል፣አድጓል፣ያንበሸብሻል!!
በየሳምንቱ ጓደኞቻችሁን በዕለተ ሰኞ በምንለቀው የፌስቡክ ፖስታችን ስር ታግ ያድርጉ፣ ይሸለማሉ!
በየሳምንቱ 5 አሸናፊዎች!
በየሳምንቱ ስማርት ስልክክክክክ እንዲሁም በመጨረሻም ለ2 ደንበኞች የ50,000 ብርርርር ሽልማት!! ሌሎችም ብዙ ስጦታዎች ከቤቲካ!

ለዚህ ሳምንት ፣ በየፌስቡክ ፖስታችን ስር ብቻ ያሉ ታግ የተደረጉ ቁጥሮች የሚመዘገቡ ይሆናል!
አሁኑኑ https://web.facebook.com/BetikaET ላይታግ ያድርጉ!

ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
TIKVAH-SPORT
“ ሳውዲ ሊግ ከፈረንሳይ ሊግ ይበልጣል “ ሮናልዶ የአል ነስሩ የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳውዲ አረቢያ ሊግ በትልቅ ለውጥ ላይ መሆኑን ገልጿል። “ የሳውዲ አረቢያ ሊግ በማደግ ላይ ነው “ የሚለው ሮናልዶ አሁን ላይ የሳውዲ አረቢያ ሊግ ከፈረንሳይ ሊግ የበለጠ ነው በማለት ተናግሯል። ሮናልዶ አክሎም “ እኔን አትመኑ ነገርግን ወደ ሳውዲ አረቢያ ሄዳችሁ ተመልከቱት “ ሲል አስተያየቱን…
“ በሮናልዶ ሀሳብ እስማማለሁ “ ኔይማር

“ የአለም ዋንጫ ለማሸነፍ ያለኝን ሁሉ እሰጣለሁ “

ብራዚላዊው የአል ሂላል ተጨዋች ኔይማር ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳውዲ አረቢያ ሊግ ከፈረንሳይ ሊግ የተሻለ ነው ባለው ሀሳብ እንደሚስማማ ተናግሯል።

“ የሳውዲ አረቢያ ሊግ እያደገ ነው “ የሚለው ኔይማር አሁን ላይ ሮናልዶ በተናገረው ነገር እስማማለሁ የሳውዲ ሊግ ከፈረንሳይ ሊግ የተሻለ ነው ብሏል።

የፈረንሳይ ሊግ ጠንካራ መሆኑን አያይዞ የገለፀው ኔይማር አሁን ግን ሳውዲ ሊግ የተሻሉ ተጨዋቾች አሉ በማለት ተናግሯል።

ስለወደፊት ቆይታው የተናገረው ኔይማር በእግርኳስ የሚፈጠረው አይታወቅም ነገርግን አሁን ላይ በሳውዲ አረቢያ በጣም ደስተኛ ነኝ “ ብሏል።

“ የ 2026 አለም ዋንጫ የመጨረሻዬ እንደሆነ አውቃለሁ ፣ የመጨረሻ እድሌ እና ሙከራዬ ነው ለማሳካት ሁሉንም አደርጋለሁ።“ ኔይማር

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሲቲ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት ማንችስተር ሲቲዎች የወርሀ ታህሣሥ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት :- ናታን አኬ ስቴፋን ኦርቴጋ እና ሳቪንሆ የማንችስተር ሲቲ የወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል። የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? @tikvahethsport      @kidusyoftahe
የሲቲ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት ማንችስተር ሲቲዎች የወርሀ ታህሣሥ የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሳቪንሆ የማንችስተር ሲቲ የወርሀ ታህሣሥ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

በዚህ አመት የማንችስተር ሲቲን የወሩ ምርጥ ተጨዋች ሽልማት

- ኤርሊንግ ሀላንድ 2x
- ጆን ስቶንስ
- ማቲውስ ኑኔስ እና
- ሳቪንሆ ማሸነፍ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው።

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

5:00 አርሰናል ከ ኒውካስል ዩናይትድ

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
ተጀመረ

አርሰናል 0 - 0 ኒውካስል ዩናይትድ

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
13 '

አርሰናል 0 - 0 ኒውካስል ዩናይትድ

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
27 '

አርሰናል 0 - 0 ኒውካስል ዩናይትድ

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
39'

አርሰናል 0 - 1 ኒውካስል ዩናይትድ

አይሳክ

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
እረፍት

አርሰናል 0 - 1 ኒውካስል ዩናይትድ

                አይሳክ

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
52 '

አርሰናል 0 - 2 ኒውካስል ዩናይትድ

                አይሳክ
ጎርደን

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
69 '

አርሰናል 0 - 2 ኒውካስል ዩናይትድ

                አይሳክ
                 ጎርደን

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
80 '

አርሰናል 0 - 2 ኒውካስል ዩናይትድ

                አይሳክ
                 ጎርደን

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
90 '

አርሰናል 0 - 2 ኒውካስል ዩናይትድ

                አይሳክ
                 ጎርደን

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
መድፈኞቹ ሽንፈት አስተናግደዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከኒውካስል ጋር ያደረገውን የካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የኒውካስል ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች አሌክሳንደር አይሳክ እና አንቶኒ ጎርደን ከመረብ አሳርፈዋል።

ሁለቱ ቡድኖች የካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታቸውን ከአንድ ወር በኋላ በኒውካስሉ ሴንት ጄምስ ፓርክ የሚያደርጉ ይሆናል።

አርሰናል ከአስራ ሶስት ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ በኋላ ሽንፈት አስተናግደዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
2025/01/08 01:32:51
Back to Top
HTML Embed Code: