Telegram Web Link
41 ' ማንችስተር ሲቲ 1-1 አርሰናል

      ሀላንድ               ካላፊዮሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
45 ' ማንችስተር ሲቲ 1-2 አርሰናል

      ሀላንድ               ካላፊዮሪ
ጋብሬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእረፍት ሰዓት !

በሳምንቱ ተጠባቂ መርሐ ግብር አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት እየመሩ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

የመድፈኞቹን የመሪነት ግቦች ካላፊዮሪ እና ጋብሬል ሲያስቆጥሩ ለማንችስተር ሲቲ ሀላንድ ከመረብ አሳርፏል።

🟨 የቢጫና ቀይ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ በማንችስተር ሲቲ በኩል ኤደርሰን እና ሩበን ዲያስ እንዲሁም በአርሰናል በኩል ቶማስ ፓርቴ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል።

🟥 የመድፈኞቹ ተጨዋች ትሮሳርድ ቀይ ካርድ ተመልክቷል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ ማንችስተር ሲቲ 66% - 34% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

የጨዋታውን አጫጭር ቪዲዮች እና ጎሎች በጎል ቻናላችን መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
48 ' ማንችስተር ሲቲ 1-2 አርሰናል

      ሀላንድ               ካላፊዮሪ
                                     ጋብሬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
60 ' ማንችስተር ሲቲ 1-2 አርሰናል

      ሀላንድ               ካላፊዮሪ
                                     ጋብሬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊያንድሮ ትሮሳርድ ለምን በቀይ ወጣ ?

የ አርሰናሉ የፊት መስመር ተጨዋች ሊያንድሮ ትሮሳርድ ሁለተኛ የቢጫ ካርድ " ቀይ ካርድ " የተመለከተው ጨዋታውን ለማዘግየት በመሞከር መሆኑን ሊጉ አሳውቋል።

ማይክል ኦሊቨር በበኩላቸው ሰባተኛ ቀይ ካርዳቸውን ለአርሰናል ተጨዋች መዘዋል።

ዋና ዳኛው ለአርሰናል ተጨዋቾች የመዘዙትን ሰባት ቀይ ካርዶች ያህል ለየትኛውም ክለብ ተጨዋቾች አልመዘዙም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
70 ' ማንችስተር ሲቲ 1-2 አርሰናል

      ሀላንድ               ካላፊዮሪ
                                     ጋብሬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የኢንተር ሚላን እና ኤሲ ሚላንን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 3:45 ሰዓት ብቻ ነው።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
80 ' ማንችስተር ሲቲ 1-2 አርሰናል

      ሀላንድ               ካላፊዮሪ
                                     ጋብሬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 ' ማንችስተር ሲቲ 1-2 አርሰናል

      ሀላንድ               ካላፊዮሪ
                                     ጋብሬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90+7 ' ማንችስተር ሲቲ 2-2 አርሰናል

      ሀላንድ               ካላፊዮሪ
       ስቶንስ               ጋብሬል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ነጥብ ተጋርተዋል !

በአምስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የአርሰናልን ግብ ጋብሬል ማግሀሌስ እና ሪካርዶ ካላፊዮሪ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለማንችስተር ሲቲ ኤርሊንግ ሀላንድ እና ጆን ሴቶንስ አስቆጥሯል።

ኤርሊንግ ሀላንድ በ 105 ጨዋታዎች 100 ግቦችን በማስቆጠር ፋጣን ተጨዋች በመሆን የክርስቲያኖ ሮናልዶን ሪከርድ መጋራት ችሏል።

ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጋብሬል ማግሀሌስ አስራ ስድስተኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን ለአርሰናል አስቆጥሯል።

የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በአራት ጨዋታዎች አስረኛ የሊግ ግቡን አስቆጥሯል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ማንችስተር ሲቲ :- 13 ነጥብ
4️⃣ኛ አርሰናል :- 11 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ ኒውካስል ከ ማንችስተር ሲቲ

ቅዳሜ አርሰናል ከ ሌስተር ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አፄዎቹ አመቱን በድል ጀምረዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የአፄዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ቢኒያም ላንቃሞ እና ምኞት ደበበ ከመረብ ሲያሳርፉ ፍፁም ጥላሁን በፍፁም ቅጣት ምት ለፈረሰኞቹ አስቆጥ

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

ሐሙስ ⏩️  ፋሲል ከነማ ከ መቐለ 70 እንደርታ

አርብ ⏩️ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጎሉን በማስቆጠሬ ደስ ብሎኛል “ ጆን ስቶንስ

የማንችስተር ሲቲን የአቻነት ጎል በመጨረሻ ደቂቃ ያስቆጠረው ጆን ስቶንስ “ ደስተኛ ነኝ “ ሲል ከጨዋታው በኃላ ተደምጧል።

በቋሚ አሰላለፍ ጨዋታውን አለመጀመሩ ያላስደሰተው ስቶንስ “ ተቀይሬ ወደ ሜዳ የገባሁት ብልጫ እንድንወስድ ነው ፣ ያገኘሁትን አንድ እድል ወደ ግብነት ቀይሬያለሁ “ ብሏል።

ፔፕ ጋርድዮላ ያለውን መተግበሩን የተናገረው ስቶንስ “ ፔፕ ከሀላንድ ጋር በቅርበት እንድጫወት እና የአየር ላይ ኳሶችን እንድጠቀም ነግሮኛል “ ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
በተጫዋቾቼ ኮርቻለሁ “ ሚኬል አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድኑ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ባሳየው ብቃት “ ኮርቻለሁ “ ሲሉ ተጫዋቾቻውን አወድሰዋል።

“ በተጫዋቾቼ ኮርቻለሁ “ ያሉት ሚኬል አርቴታ “ ከአለማችን ምርጡ ክለብ ጋር የተደረገ መርሐ ግብር ነበር “ በማለት ተናግረዋል።

አሰልጣኙ በዕለቱ ስለነበረው የዳኝነት ሁኔታ ሲጠየቁም “ ስለ ዳኝነቱ ማውራት ጥቅም የለውም “ ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ቡድናችን በአስር ተጫዋቾች ለብዙ ደቂቃ መምራታችን ተአምር ነው “ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ባርሴሎና በአሸናፊነቱ ቀጥሏል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የስፔን ላሊጋ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብሩን ከቪያሪያል ጋር አድርጎ 5ለ1 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።

የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦች ሮበርት ሌዋንዶውስኪ 2x ፣ ፓብሎ ቶሬ እና ራፊንሀ 2x ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለቪያሪያል ፔሬዝ አስቆጥሯል።

ባርሴሎና በመጀመሪያ ስድስት የሊግ ጨዋታዎች በተጋጣሚዎቹ ላይ ሀያ ሁለት ግቦችን አስቆጥሮ ሁሉንም ማሸነፍ ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ባርሴሎና :- 18 ነጥብ
5️⃣ኛ ቪያሪያል :- 11 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሮብ ባርሴሎና ከ ሄታፌ

ሐሙስ እስፓኞል ከ ቪያሪያል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ቀጣይ ተጨዋቾቼ ዳኛው ሲጠራቸው እንዳይሄዱ እነግራቸዋለሁ “ ጋርዲዮ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አርሰናሎች በመከላከል ላሳያችሁት ጥንካሬ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ተናግረዋል።

ስለ አርሰናል የመጀመሪያ ግብ ያነሱት ፔፕ ጋርዲዮላ “ በቀጣይ ለተጨዋቾቼ ዳኛው ጠርቶ ኑና አናግሩኝ ሲላችሁ መሄድ የለባችሁም እነሱ ይምጡና ያናግሯችሁ ብዬ እነግራቸዋለሁ “ ሲሉ ተደምጠዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቀጥለውም “ ቡድናችን አሁንም ለሊጉ ዋንጫ ለመፎካከር ፍቅሩ አለው “ በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዳኛው ስራ የጨዋታውን ውበት መጠበቅ ነው “

በአርሰናል መለያ በሊጉ የመጀመሪያ ጎሉን ያስቆጠረው ሪካርዶ ካላፊዮሪ ከጨዋታው በኃላ በዕለቱ ዳኛ ላይ ትችቱን ገልፆል።

“ የዳኛው ስራ የጨዋታውን ውበት መጠበቅ እና ሁለቱን ቡድኖች እኩል መርዳት ነው ፣ ይህ ግን በዛሬው ጨዋታ አልሆነም “ ሲል ካላፊዮሪ ተናግሯል።

ካላፊዮሪ በቀይ ካርድ የወጣው የቡድን አጋሩ ትሮሳርድ “ የዳኛውን ፊሽካ አልሰማም ነበር “ ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኤሲ ሚላን ድል አድርጓል !

በጣልያን ሴርያ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኤሲ ሚላን ከኢንተር ሚላን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የኤሲ ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ክርስቲያን ፑልሲች እና ማቲኦ ጋብያ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለኢንተር ሚላን ፌዴሪኮ ዲማርኮ አስቆጥሯል።

ኤሲ ሚላን ከሁለት አመታት በኋላ ከኢንተር ሚላን ጋር ያደረገውን የዴላ ማዶኒና ደርቢን ማሸነፍ ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ?

6️⃣ኛ ኢንተር ሚላን :- 8 ነጥብ
7️⃣ኛ ኤሲ ሚላን :- 8 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

አርብ ኤሲ ሚላን ከ ሊቼ

ቅዳሜ ዩዲኔዜ ከ ኢንተር ሚላን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/28 13:18:52
Back to Top
HTML Embed Code: