Telegram Web Link
“ ትልቅ ዋንጫዎችን ማሸነፍ መጀመር አለብን “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው በቀጣይ ትልቅ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንዳለበት ገልፀዋል።

ቡድናቸው ወደ ስኬት እጅግ እየቀረበ ስለመሆኑ እርግጠኛ መሆናቸውን የገለፁት ሚኬል አርቴታ “ በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ ምርጡን ቡድን እየተፎካከርን ነው አሁንም ግን ብዙ መስራት ያለብን ነገር አለ።“ ብለዋል።

“ አሁን ትልቅ ዋንጫዎችን ማሸነፍ መጀመር አለብን ወጥነት ማሳየት አለብን ሊሻሻሉ የሚገባቸው ቦታዎችም አሉን “ ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሮማ ስራ አስፈፃሚ ከሀላፊነት ለቀቀች !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ሮማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሊና ሶሎኮ ከክለቡ ሀላፊነቷ በፍቃዷ መልቀቋን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

ሀላፊዋ ስራዋን ለመልቀቅ የወሰነችው የአሰልጣኝ ዳንኤል ዲ ሮሲን መሰናበት ተከትሎ ከሮማ ደጋፊዎች ማስፈራሪያ ደርሷት መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም በአሁን ሰዓት እሷ እና ልጆቿ በፖሊስ ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑ ተነግሯል።

ሮማ ከቀናት በፊት ዳንኤል ዲ ሮሲን በማሰናበት አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪችን በሀላፊነት መሾሙ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አርሰናል ለአቻ የሚጫወት ይመስለኛል “ ጄሚ ጋራገር

የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ጄሚ ካራገር አርሰናል ዛሬ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ለአቻ የሚጫወት ይመስለኛል በማለት ተናግሯል።

" አርሰናል ዛሬ አቻ ለመውጣት የሚጫወቱ ይመስለኛል ኢትሀድ ስታዲየም ላይ ነጥብ ይዘው ከወጡ የሚደሰቱ ይመስለኛል።" ሲል ጄሚ ጋራገር አስተያየቱን ሰጥቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የማንችስተር ሲቲ እና አርሰናልን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 12:30 ሰዓት ብቻ ነው።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
Forwarded from WANAW SPORT
🎁 #ይገምቱ፣ ዛሬም #ይሸለሙ!

🏆  በዛሬው ምሽት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ተጠባቂ ፍልሚያ ማን ያሸንፋል?

⚽️ ማንቺስተር ሲቲ
ወይስ አርሰናል ⚽️

💬 ግምትዎን #በገፃችን ኮሜንት ላይ ብቻ ያስቀምጡልን!

⚠️ የውድድሩ ህጎች፦
👉🏾 የጨዋታውን አሸናፊ ክለብ እስከ የግብ መጠኑ #በትክክል ቀድመው የሚገምቱ #2 ተከታታዮቻችን የዋናውን ማልያዎች ይሸለማሉ።
👉🏾 የዋናውን ማህበራዊ ገፆች መከተል፣ መወዳጀትና ማጋራት ይጠበቅቦታል።
👉🏾 የተስተካከሉና ተደጋጋሚ መልሶች በፍፁም ተቀባይነት የላቸውም።
👉🏾 አንድ ተሳታፊ ከሁለት ጊዜ በላይ አይሸለምም፡፡

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የጨዋታ አሰላለፍ !

12:30 ማንችስተር ሲቲ ከ አርሰናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የዴብሮይን ጉዳት ከባድ አይደለም “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ወሳኝ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን በጉዳት ምክንያት ከዛሬው የአርሰናል ጨዋታ ውጪ ሆኗል።

ኬቨን ዴብሮይን ያጋጠመው ጉዳት “ ከባድ አይደለም “ ሲሉ የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል

“ ሚኬል አርቴታን የአርሰናል ተጨዋቾች እና ደጋፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ማለት እፈልጋለሁ “ ሲሉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አያይዘው ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የባርሴሎና እና ቪያሪያልን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 1:30 ሰዓት ብቻ ነው።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
የጦና ንቦቹ አመቱን በድል ጀምረዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን ወላይታ ድቻ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የጦና ንቦቹን የማሸነፊያ ግቦች ተስፋዬ መላኩ ፣ ካርሎስ ዳምጠው እና ጌታሁን ባፋ በራሱ ግብ ላይ ማስቆጠር ችለዋል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች እዮብ ገ/ማርያም እና አቤል ሀብታሙ ከመረብ አሳርፈዋል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

አርብ ⏩️  ኢትዮጵያ ቡና ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

ቅዳሜ ⏩️ ድሬዳዋ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ከጨዋታው በፊት ምን ተባለ ?

በተንታኝነት እያገለገሉ የሚገኙ የቀድሞ ተጨዋቾች ከደቂቃዎች በኋላ በሚጀምረው የማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል ጨዋታ ዙሪያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ከእነዚህም መካከል :-

ኮሎ ቱሬ :- “ አሁን ላይ ማንችስተር ሲቲን ማሸነፍ የሚችለው ብቸኛው ክለብ አርሰናል ብቻ ነው።“

ፖል ሜርሰን :- “ እውነት ለመናገር አርሰናል ዛሬ ማንችስተር ሲቲን ማሸነፍ የሚችል አይመስለኝም።

ሮይ ኪን :- “ አርሰናል ከሰሞኑ ያሳየው እንቅስቃሴ ዛሬ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በቂ አይሆንም።"

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ለጨዋታው ዝግጁ ነን “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ከደቂቃዎች በኋላ ለሚደረገው የማንችስተር ሲቲ ጨዋታ መጓጓቱን ገልጸዋል።

“ ለጨዋታው ዝግጁ ነን በደንብ መዘጋጀታችንን እናውቃለን ለጨዋታው ጓጉተናል “ ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከጨዋታው በፊት ተናግረዋል።

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በበኩላቸው “ አርሰናል ጥሩ የሆኑት በመከላከል ብቻ አይደለም በመልሶ ማጥቃትም አስፈሪ ናቸው “ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀመረ

ማንችስተር ሲቲ 0-0 አርሰናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TikvahGoal

የጨዋታውን አጫጭር ቪዲዮች እና ጎሎች በጎል ቻናላችን መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
8 ' ማንችስተር ሲቲ 1-0 አርሰናል

ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
18 ' ማንችስተር ሲቲ 1-0 አርሰናል

ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
21 ' ማንችስተር ሲቲ 1-1 አርሰናል

ሀላንድ ካላፊዮሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
26 ' ማንችስተር ሲቲ 1-1 አርሰናል

ሀላንድ                ካላፊዮሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
35 ' ማንችስተር ሲቲ 1-1 አርሰናል

ሀላንድ               ካላፊዮሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/28 15:33:15
Back to Top
HTML Embed Code: