Telegram Web Link
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ፖላንድ ከ ኦስትሪያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የፖላንድ ብሔራዊ ቡድን በኔዘርላንድ ከተሸነፈበት የመጀመሪያ ጨዋታ የአራት ተጨዋቾች ለውጥ በማድረግ ወደ ሜዳ የሚገቡ ይሆናል።

የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ በፈረንሳይ ከደረሰበት ሽንፈት የሶስት ተጨዋቾች ለውጥ አድርገው ወደ ሜዳ ይገባሉ።

የኦስትሪያ አሰልጣኝ ራልፍ ራኚክ በራሱ ላይ ግብ ያስቆጠረውን ዎበር ጨምሮ በፈረንሳይ ጨዋታ በመሐል ተከላካይነት የተጠቀሟቸውን ሁለት ተከላካዮች ተጠባባቂ አድርገዋል።

የፊት መስመር ተጨዋቹ ማርኮ አርናቶቪች በበኩሉ ሚሼል ግሪጎራሽን በመተካት በቋሚ አሰላለፍ ተካቷል።

የፖላንድ ወሳኝ ተጨዋች ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በምሽቱ ጨዋታም በጉዳቱ ምክንያት ለብሔራዊ ቡድኑ በቋሚ አሰላለፍ ገብቶ ግልጋሎት አይሰጥም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
10 ' ፖላንድ 0 - 1 ኦስትሪያ

ትራውነር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
31 ' ፖላንድ 1 - 1 ኦስትሪያ

ፒያቴክ                  ትራውነር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ፖላንድ 1 - 1 ኦስትሪያ

ፒያቴክ                  ትራውነር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀድያ ሆሳዕና ድል አድርገዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሀድያ ሆሳዕናንን የማሸነፊያ ግቦች ግርማ በቀለ ፣ ቃለአብ ውብሸት እና ሰመረ ሀፍተይ ከመረብ ሲያሳርፉ ለድሬዳዋ ከተማ አድናን መኪ አስቆጥሯል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

8️⃣ ድሬዳዋ ከተማ :- 40 ነጥብ

9️⃣ ሀድያ ሆሳዕና :- 38 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
67 ' ፖላንድ 1 - 2 ኦስትሪያ

ፒያቴክ              ትራውነር
ቡምጋርትነር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
78 ' ፖላንድ 1 - 3 ኦስትሪያ

ፒያቴክ              ትራውነር
                              ቡምጋርትነር
አርናውቶቪች

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ኔዘርላንድ ከ ፈረንሳይ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኦስትሪያ የመጀመሪያ ድሏን አሳክታለች !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን ከፖላንድ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

ለኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ትራውነር ፣ ቡምጋርትነር እና አርናውቶቪች ከመረብ ሲያሳርፉ ለፖላንድ ፒያቴክ አስቆጥሯል።

የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን በአንድ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጨዋታ ከሶስት በላይ ግቦች ሲያስቆጥር በታሪኩ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

በጨዋታው ኦስትሪያ የመጀመሪያ ሶስት ነጥቧን ስታሳካ ፖላንድ ምንም ነጥብ ማስመዝገብ ሳትችል ቀርታ የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች።

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ሐሙስ ፖላንድ ከፈረንሳይ እንዲሁም ኔዘርላንድ ከኦስትሪያ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ኦሊሴን ለማስፈረም ንግግር ጀመሩ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በፈረንሳዊው ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ዝውውር ዙሪያ ክለቡ ክሪስታል ፓላስን ማነጋገራቸው ተገልጿል። ሰማያዊዎቹ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴን በግል ጥቅማጥቅም ዙሪያ ለማነጋገር ከክሪስታል ፓላስ ፍቃድ መጠየቃቸው ተነግሯል። ባየር ሙኒክ እና ኒውካስል ዩናይትድ በበኩላቸው ተጫዋቹን ለማስፈረም ክሪስታል ፓላስን ማነጋገራቸው…
ቼልሲ የኦሊሴን ዝውውር ማቋረጣቸው ተገለጸ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴን ለማስፈረም የሚያደርጉትን ጥረት ማቋረጣቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ በዚህ ሳምንት ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴን እንዲሁም ክለቡ ክሪስታል ፓላሴን አነጋግረው እንደነበር ተነግሯል።

ይሁን እንጂ ቼልሲ ለተጨዋቹ የሚያወጡት የውል ማፍረሻ ካሳ ክፍያ ፣ ደሞዝ ፣ የፊርማ ጉርሻ እንዲሁም ሌሎች አጠቃላይ ክፍያዎች ከፍተኛ ናቸው በማለት ዝውውሩን ማቋረጣቸው ተገልጿል።

ባየር ሙኒክ ፣ ኒውካስል ዩናይትድ እና ማንችስተር ዩናይትድ በበኩላቸው ተጫዋቹን ለማስፈረም አሁንም ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ኔዘርላንድ 0-0 ፈረንሳይ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ የኦሊሴን ዝውውር ማቋረጣቸው ተገለጸ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴን ለማስፈረም የሚያደርጉትን ጥረት ማቋረጣቸው ተገልጿል። ሰማያዊዎቹ በዚህ ሳምንት ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴን እንዲሁም ክለቡ ክሪስታል ፓላሴን አነጋግረው እንደነበር ተነግሯል። ይሁን እንጂ ቼልሲ ለተጨዋቹ የሚያወጡት የውል ማፍረሻ ካሳ ክፍያ ፣ ደሞዝ ፣…
ባየር ሙኒክ ኦሊሴን ለማስፈረም ተስማማ !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የክሪስታል ፓላሱን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር በግል ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ከክሪስታል ፓላስ የቀረበለትን አዲስ ውል ውድቅ በማድረግ ባየር ሙኒክን ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ኦሊሴን ለማስፈረም ሲያደርጉ የነበረውን ሙከራ ማቋረጣቸው መዘገቡ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
70 '

ኔዘርላንድ 0 - 0 ፈረንሳይ

*ኔዘርላንድ በዣቪ ሲሞንስ አማካኝነት ያስቆጠረችው ግብ ከጨዋታ ውጪ በሚል በቫር ተሽሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ንጎሎ ካንቴ በመጀመሪያዎቹ ሁለት የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች የጨዋታው ኮከብ ተብሎ መመረጥ ችሏል።

ውጤቱን ተከትሎ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎችን የተሸነፈው የፖላንድ ብሔራዊ ቡድን ከውድድሩ የተሰናበተ የመጀመሪያው ቡድን መሆኑ ተረጋግጧል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ኔዘርላንድ :- 4 ነጥብ

2️⃣ ፈረንሳይ :- 4 ነጥብ

3️⃣ ኦስትሪያ :- 3 ነጥብ

4️⃣ ፖላንድ :- ምንም ነጥብ

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ሐሙስ ፈረንሳይ ከፖላንድ እንዲሁም ኔዘርላንድ ከኦስትሪያ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Samsung Galaxy S22 Ultra
256 GB - 67,000 ETB
512 GB - 78,000 ETB

Samsung Galaxy S23 Ultra
256 GB - 92,000 ETB
512 GB - 109,000 ETB

Samsung Galaxy S24 Ultra
256 GB - 109,000 ETB
512 GB - 124,000 ETB

Exchange Available
🏍️ Free Delivery

Contact us :
0925927457 @eBRO4
@Heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ መቼ ይደረጋል ?

በሞሮኮ አዘጋጅነት የሚካሄደው የ2025 አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የሚደረግበትን ወቅት የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በትላንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት የ2025 የሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከታኅሣሥ 12/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 10/2018 ዓ.ም ለማድረግ መታቀዱን ካፍ አስታውቋል።

ውድድሩ ከሚቀጥለው አመት ክረምት ወር ወደ ጥር ወር የተዘዋወረው ቀጣይ ክረምት ከሚደረገው አዲሱ የፊፋ የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ጋር እንዳይደራረብ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ካፍ በተመሳሳይ በሞሮኮ የሚካሄደው የ2024 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ውድድር በሚቀጥለው ክረምት ሐምሌ ወር እንደሚደረግ ይፋ አድርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 12:16:39
Back to Top
HTML Embed Code: