Telegram Web Link
ስፔን ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከጣልያን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

ለስፔን ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቧን ሪካርዶ ካላፊዮሪ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ አሳርፏል።

በዘንድሮው የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር እስካሁን በተደረጉ ጨዋታዎች ብቻ አምስት ግቦች በራስ መረብ ላይ ተቆጥረዋል።

ሪካርዶ ካላፊዮሪ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ በራሱ ላይ ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ሆኗል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ስፔን :- 6 ነጥብ

2️⃣ ጣልያን :- 3 ነጥብ

3️⃣ አልባንያ :- 1 ነጥብ

4️⃣ ክሮሽያ :- 1 ነጥብ

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ የፊታችን እሁድ ስፔን ከአልባንያ እንዲሁም ጣልያን ከክሮሽያ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Poland - Austria
Netherlands - France
Spain - Italyለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
" ሁሉም ተጋጣሚዎች ከእኛ ጋር በተለየ መንገድ ይጫወታሉ " ሊዮኔል ሜሲ

ተጠባቂው የ2024 የአሜሪካ የኮፓ አሜሪካ ውድድር ትላንት ምሽት አርጀንቲና ከካናዳ ጋር ባደረጉት የመክፈቻ ጨዋታ ጀምሯል።

የመክፈቻ ጨዋታውን አርጀንቲና በጁሊያን አልቫሬዝ እና ላውታሮ ማርቲኔዝ ግቦች ካናዳን 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።

አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በጨዋታው በኮፓ አሜሪካ ውድድር ሰላሳ አምስት ጨዋታዎች በማድረግ በሌላ ተጨዋች ተይዞ የነበረውን ብዙ ጨዋታ የማድረግ ሪከርድ ሰብሯል።

ሊዮኔል ሜሲ በኮፓ አሜሪካ ውድድር አስራ ሰባት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል እሱ በውድድሩ መካፈል ከጀመረ ወዲህ ከአምስት በላይ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል የቻለ ተጨዋች የለም።

ከጨዋታው በኋላ አስተያየቱን የሰጠው ሊዮኔል ሜሲ " ጨዋታው ከባድ እንደሚሆን እናውቅ ነበር ፣ አስቸጋሪ ጨዋታ ነበር የጠበቅነው ሁሉም ቡድኖች እኛን ሲገጥሙ ከሚጠቀሙት በተለየ መንገድ ነው የሚጫወቱት።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ስፔን ማሸነፍ ይገባታል " ስፓሌቲ

የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ በምሽቱ የምድብ ጨዋታ ስፔን ማሸነፍ እንደሚገባት በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

" በጨዋታው ውጤት አልተበሳጨሁም " ያሉት አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ እነሱ በጨዋታው ከእኛ የበለጠ ብልህ ነበሩ ስፔን ጨዋታውን ማሸነፍ ይገባታል በማለት ተናግረዋል።

" ኳስ በአጋጣሚ ስናገኝ እንኳን ማቆየት አልቻልንም በፍጥነት እንቀማለን ፣ ራሳችን ላይ አስቆጥረናል ሌላም ሊቆጠርብን ይችል ነበር ለመጨረሻው ጨዋታ በደንብ መዘጋጀት አለብን።" ስፓሌቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከእኛ የሚበልጥ ቡድን የለም " ሉዊስ ዴ ላፉንቴ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላፉንቴ በአሁን ሰዓት ከስፔን የሚበልጥ ቡድን እንደሌለ ከምሽቱ የጣልያን ጨዋታ በኋላ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

በድሉ መደሰታቸውን የገለፁት አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላፉንቴ " በተጨዋቾቼ በጣም ኮርቻለሁ በመላ ሀገሪቱ ደስታን አንግሰዋል ፣ ያለኝ በጣም ጥሩው ነገር ተጨዋቾቹን በደንብ አውቃቸዋለሁ " ብለዋል።

አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላፉንቴ ቀጥለውም በአሁን ሰዓት ከስፔን ብሔራዊ ቡድን የበለጠ ቡድን አለ ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኒኮ ዊሊያምስ ወደ ባርሴሎና ?

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ስፔናዊውን የአትሌቲክ ቢልባኦ የፊት መስመር ተጨዋች ኒኮ ዊሊያምስ የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

ባርሴሎና በቀጣይ ለማስፈረም የሚፈልገውን አቅም ያለው ወጣት እና ወደፊት ታላቅ ተጨዋች መሆን የሚችል የክንፍ አጥቂ መስፈርት ኒኮ ዊሊያምስ እንደሚያሟላ ተነግሯል።

ይሁን እንጂ ባርሴሎና ኒኮ ዊልያምስን ለማስፈረም በቀጣይ ያለባቸውን የፋይናንስ ችግር ማስተካከል እንዲሁም ተጨዋች መሸጥ ሊጠበቅባቸው እንደሚችል ተገልጿል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እና ቼልሲ በበኩላቸው ኒኮ ዊሊያምስን ለማስፈረም በዝርዝር ውስጥ የያዙ ክለቦች መሆናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮቤርቶ ባጅዮ ጥቃት እንደደረሰበት ተገለጸ !

የቀድሞ ጣልያናዊ ታሪካዊ ተጨዋች ሮቤርቶ ባጅዮ ትላንት ምሽት በመኖሪያ ቤቱ የጣልያን እና ስፔንን ጨዋታ በመመልከት ላይ እያለ ጥቃት እንደደረሰበት ተገልጿል።

የቀድሞ ተጨዋቹ በመኖሪያ ቤቱ ከቤተሰቡ ጋር ጨዋታውን በመመልከት ላይ እያለ አምስት የሚደርሱ መሳሪያ የታጠቁ ዘራፊዎች ሰብረው ሲገቡ ለመከላከል ሲሞክር ጥቃት እንዳደረሱበት ተነግሯል።

ሮቤርቶ ባጅዮ ዘራፊዎቹን ለማስቆም ሲሞክር ጭንቅላቱ ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ተከትሎ ወደ ሆስፒታል ማምራቱ ተገልጿል።

ዘራፊዎቹ መላው ቤተሰቡን በአንድ ክፍል ውስጥ በመቆለፍ ጌጣጌጥ እና ገንዘብ ይዘው መሄዳቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Samsung Galaxy S22 Ultra
256 GB - 67,000 ETB
512 GB - 78,000 ETB

Samsung Galaxy S23 Ultra
256 GB - 92,000 ETB
512 GB - 109,000 ETB

Samsung Galaxy S24 Ultra
256 GB - 109,000 ETB
512 GB - 124,000 ETB

Exchange Available
🏍️ Free Delivery

Contact us :
0925927457 @eBRO4
@Heyonlinemarket
Forwarded from WANAW SPORT
📢 ፈጣን እና አስተማማኝ አቅርቦት ከ #ዋናው!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ዌልስ ከአሰልጣኟ ጋር ተለያየች !

ለአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ሳያልፍ የቀረው የዌልስ ብሔራዊ ቡድን ከዋና አሰልጣኙ ሮበርት ፔጅ ጋር መለያየታቸው ይፋ ተደርጓል።

አሰልጣኝ ሮበርት ፔጅ የዌልስ ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት እየመሩ ከሰልሳ አራት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በኳታሩ አለም ዋንጫ ውድድር ማሳተፋቸው ይታወሳል።

የዌልስ ብሔራዊ ቡድን በአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያ ጥሎ ማለፍ በፖላንድ በመለያ ምት ተሸንፎ ለውድድሩ ማለፍ ሳይችል መቅረቱ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ምባፔ ለኔዘርላንድ ጨዋታ ላይደርስ ይችላል ! ትላንት ምሽት በአፍንጫው ላይ ከባድ ጉዳት ያጋጠመው ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ለአርቡ የኔዘርላንድ ጨዋታ ላይደርስ እንደሚችል ተገልጿል። ፈረንሳይ ከፖላንድ ጋር በምታደርገው የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ኪሊያን ምባፔ የመድረስ እድል እንደሚኖረው ተዘግቧል። ኪሊያን ምባፔ በጉዳቱ ምክንያት በቀሪ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር…
" ምባፔ በኔዘርላንድ ጨዋታ ሊሳተፍ ይችላል " ዴሻምፕ

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ  ኪሊያን ምባፔ በዛሬ ምሽቱ የኔዘርላንድ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ይሳተፋል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ልምምዱን በጥሩ ሁኔታ እንደሰራ የገለፁት አሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ " በምሽቱ የኔዘርላንድ ጨዋታ ይሳተፋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት አፍንጫው ላይ ጉዳት ያጋጠመው ኪሊያን ምባፔ ወደ ሜዳ የሚመለስ ከሆነ ተመሳሳይ ቀለም ያለው የፊት ጭምብል አድርጎ እንደሚጫወት ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

10:00 ስሎቫኪያ ከ ዩክሬን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
17 '

ስሎቫኪያ 1 - 0 ዩክሬን

ሽራንዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ስሎቫኪያ 1 - 0 ዩክሬን

ሽራንዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባሕር ዳር ከተማ ድል አድርገዋል

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባሕር ዳር ከተማ ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የጣና ሞገዶቹን የማሸነፊያ ግቦች የአብስራ ተስፋዬ ፣ ወንድወሰን በለጠ እና ፍቅሩ አለማየሁ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥረዋል።

የአዳማ ከተማን የመሪነት ግቦች ዮሴፍ ታረቀኝ እና ኤሊያስ ለገሰ ማስቆጠር ችለዋል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

3️⃣ ባሕር ዳር ከተማ :- 49 ነጥብ

5️⃣ አዳማ ከተማ :- 44 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

- ሀዋሳ ከተማ ከ ባሕር ዳር ከተማ

- አዳማ ከተማ ከ መቻል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
54 ' ስሎቫኪያ 1 - 1 ዩክሬን

ሽራንዝ ሻፓሬንኮ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
80 ' ስሎቫኪያ 1 - 2 ዩክሬን

ሽራንዝ        ሻፓሬንኮ
ያሬምቹክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች በድምቀት ቀጥለዋል!

ዛሬ ምሽት፡

⚽️ Netherlands vs France ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት | 10፡00 PM በSS Football 225 ጎጆ ፓኬጅ በSS Euro2024 222 በሜዳ  ፓኬጅ

🤔ዋንጫው የማን ነው? የእርሶን አስተያየት ያጋሩን                        

በጀርመን የሚደረጉትን ደማቅ ጨዋታዎች በቀጥታ በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ቻናሎች በወር ከ350 ብር ከጎጆ ፓኬጅ ጀምሮ ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ዩክሬን ወሳኝ ድል አሳክታለች !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የዩክሬን ብሔራዊ ቡድን ከስሎቫኪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

ለዩክሬን ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ሻፓሬንኮ እና ያሬምቹክ ሲያስቆጥሩ ለስሎቫኪያ ብሔራዊ ቡድን ኢቫን ሽራንዝ ከመረብ አሳርፏል።

ሮማን ያሬምቹክ በሶስት ግቦች በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ላይ ብዙ ግብ ማስቆጠር የቻለ ቀዳሚው ዩክሬናዊ ተጨዋች መሆን ችሏል።

ኢቫን ሽራንዝ በሁለት ተከታታይ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሮች ላይ ግብ ማስቆጠር የቻለ የመጀመሪያው ስሎቫኪያዊ ተጨዋች መሆን ችሏል።

ወቅታዊ የምድብ ደረጃ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ሮማንያ :- 3 ነጥብ

2️⃣ ዩክሬን :- 3 ነጥብ

3️⃣ ስሎቫኪያ :- 3 ነጥብ

4️⃣ ቤልጂየም :- ምንም ነጥብ

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ እሮብ ስሎቫኪያ ከሮማንያ እንዲሁም ዩክሬን ከቤልጅየም ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 14:29:55
Back to Top
HTML Embed Code: