Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
የዋልያዎቹ ተጋጣሚ በይፋ አሰልጣኝ ሾመች ! በቀጣይ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታውን የሚያደርገው የጊኒ ቢሳው ብሔራዊ ቡድን በይፋ ዋና አሰልጣኝ ሾሟል። ጊኒ ቢሳው ፖርቹጋላዊውን የፉልሀም ምክትል አሰልጣኝ ሉዊስ ቦ ሞርቴ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጋ በሀላፊነት መሾሟን አስታውቃለች። የቀድሞ ፖርቹጋላዊ ተጨዋች ሉዊስ ቦ ሞርቴ በኤቨርተን እና ፉልሀም…
ጊኒ ቢሳው ስብስቧን አሳውቃለች !

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታዋን የምታደርገው ጊኒ ቢሳው የምትጠቀመውን የቡድን ስብስብ ይፋ አድርጋለች።

በቀድሞ የፉልሀም ምክትል አሰልጣኝ ሉዊስ ቦ ሞርቴ የምትመራው ጊኒ ቢሳው ለሀያ አምስት ተጨዋቾች ጥሪ ስታቀርብ ሁሉም ተጨዋቾች ከሀገር ውጪ የሚጫወቱ መሆናቸው ታውቋል።

ለፖርቹጋሉ ክለብ ፋሬንሴ የሚጫወተው የመሐል ሜዳ ተጨዋቹ ኤልቬስ ባልዴ ብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ያቀረበለት ብቸኛ አዲስ ተጨዋች ነው።

የፈረንሳዩ ክለብ ኦሎምፒክ ሊዮን የፊት መስመር ተጨዋች ማማ ሳምባ ባልዴ እና የሜትዙ ተከላካይ ፋሊ ካንዴ በብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውስጥ ተካተዋል።

በአመቱ ውስጥ በክለባቸው ጥሩ ጊዜን ማሳለፍ ከቻሉ ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ከቀረበላቸው ተጨዋቾች መካከል ለዴንማርኩ ክለብ ሚድላንድ የሚጫወተው ፍራንኩሊኖ ጁ አንዱ ነው።

19ዓመቱ ተጨዋች ፍራንኩሊኖ ጁ ለክለቡ ተሰልፎ በተጫወተባቸው ሰላሳ ሁለት ጨዋታዎች አስራ ስድስት ግቦች አስቆጥሮ ስድስት ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ ማቀበል የቻለ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሽሊ ያንግ በኤቨርተን መቆየት ይፈልጋል !

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች አሽሊ ያንግ በመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ቤት በሚቀጥለው የውድድር አመት መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

ኤቨርተን ባለፈው አመት በነፃ ዝውውር ቡድናቸውን የተቀላቀለውን አሽሊ ያንግ በሚቀጥለው የውድድር አመት በክለቡ ለማቆየት የአንድ አመት ውል ማቅረባቸው ተገልጿል።

የ 38ዓመቱ የመስመር ተጨዋች አሽሊ ያንግ መጫወት እስከቻለ ድርስ መጫወቱን እንደሚቀጥል በሰጠው አስተያየት አያይዞ ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዋንጫውን ለማሸነፍ ሁሉንም እናደርጋለን " ዣካ

የዘንድሮው የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በጣልያኑ ክለብ አታላንታ እና በጀርመኑ ክለብ ባየር ሊቨርኩሰን መካከል ዛሬ ምሽት ይደረጋል።

ከጨዋታው በፊት አስተያየታቸውን የሰጡት የአታላንታ አሰልጣኝ ጂያን ፔሮ " ከባድ ጨዋታ ይሆናል ባየር ሊቨርኩሰን በዚህ አመት አልተሸነፉም ፣ እነሱ ላይ ነገሮችን ከባድ ለማድረግ እና ዋንጫውን ለማሸነፍ ከባድ ፍልሚያ እናደርጋለን።"ብለዋል።

" ለዚህ አይነት ቅፅበት አመቱን ሙሉ ስንዘጋጅ ነበር ፣ ድንቅ ቡድን አለኝ ለአታላንታ ክብር አለን ነገርግን አመቱን ሁሉ እንዳደረግነው በከፍተኛ የራስ መተማመን ነው የምንጫወተው።" ያሉት ደግሞ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ናቸው።

" ዋንጫውን ለመውሰድ ሁሉንም ነገር ከማድረግ ወደኋላ አንልም " ያለው ግራኒት ዣካ በበኩሉ በእኔ ሀሳብ በፍፃሜ ጨዋታ ተጋጣሚን ዝቅ ማድረግ አያስፈልግም ያላቸውን ጥራት እናውቃለን በራሳችን ላይ ማተኮር አለብን ብሏል።

የሁለቱ ክለቦች የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት በአየርላንድ ደብሊን አቪቫ ስታዲየም ምሽት 4:00 ሰዓት ይደረጋል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንተር ሚላን አዲስ ባለቤት ማግኘቱ ተገለጸ !

የአሜሪካው የፋይናንስ ተቋም ኦክትሬ ካፒታል የጣልያን ሴርያውን ክለብ ኢንተር ሚላን ባለቤትነትን ከዛሬ በኋላ ከቻይናው ሱኒንግ ሆልዲንግ ግሩፕ መውሰዱን በይፋ አሳውቋል።

ተቋሙ የክለቡን ባለቤትነት የወሰደው በቀድሞ የኢንተር ሚላን ፕሬዝዳንት ስቴቫን ዣንግ የሚመራው የክለቡ ባለቤት ከኦክትሬ የወሰደውን ብድር በሰዓቱ ባለመክፈሉ እና ከስምምነት ባለመደረሱ መሆኑን ገልጿል።

ኢንተር ሚላን በባለቤትነት የያዘው የቻይናው ሱኒንግ ሆልዲንግ ግሩፕ ከኦክትሬ ካፒታል ከሶስት አመታት በፊት የተበደረው 395 ሚልዮን ዩሮ እንደነበር ተቋሙ አሳውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ኪሊያን ምባፔ እኛን አያስፈራንም " ሌዋንዶውስኪ

የባርሴሎናው የፊት መስመር አጥቂ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ የፈረሳዊው ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ሪያል ማድሪድን መቀላቀል እንደማያስፈራቸው ተናግሯል።

" ኪሊያን ምባፔ እኛን አያስፈራንም " ሲል የተደመጠው ሌዋንዶውስኪ እሱ አስደናቂ ተጨዋች ነው ማድሪድን ከተቀላቀለ ጠንካራ ይሆናሉ ነገርግን እኛ በጋራ ከሰራን እንደ ቡድን እነሱን ማሸነፍ እንችላለን ብሏል።

" ሪያል ማድሪድ በዚህ አመት በሊጉ ጥሩ ሳይጫወት ብዙ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችሏል እኛ በቀጣይ ማሻሻል ያለብን አንዱ ነገር ነው ፣ እኔ ቢያንስ ለሁለት ተጨማሪ አመታት በትልቅ ደረጃ መጫወት እችላለሁ።" ሌዋንዶውስኪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Tecno #Camon30Pro5G

Tecno Camon 30 pro 5G  በአስገራሚ ቴክኖሎጂዎች እና በአገልግሎቱ ልቆ የቀረበ የዘመኑ ምርጥ ስልክ!

#Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
Forwarded from WANAW SPORT
📢 ለስፖርት ዝግጅቶችና ፌስቲቫል አዘጋጆች በሙሉ!

👉🏾 በሀገራችን፣ በአፍሪካ ብሎም በተለያዩ የዓለማችን ክፍላት የተለያዩ የስፖርት አልባሳትን እያቀረበ የሚገኘው ዋናው ስፖርት ለስፖርት ዝግጅቶችና ፌስቲቫል አዘጋጆች ጋር ለተለያዩ የስፖርት ውድድሮች የሚሆኑ አልባሳትን በ5% ቅናሽ ከማቅረብ ጀምሮ በጋራ አብሮ ለመስራት ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቋል።

👉🏾 #ያናግሩን#ውድድርዎን ከእኛ ጋር ያከናውኑ!

🔥 #ውድድር ካለ #ዋናው አለ! 🔥

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
የደጋፊዎች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር ( ፒኤፍኤ ) የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የደጋፊዎች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች #ስምንት እጩዎችን ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት ፊል ፎደን ፣ ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ ማርቲን ኦዴጋርድ ፣ ኮል ፓልመር ፣ ዴክላን ራይስ ፣ ሮድሪ ፣ ዊሊያም ሳሊባ እና ኦሊ ዋትኪንስ በእጩነት መቅረብ ችለዋል። የአመቱ ምርጥ…
የደጋፊዎች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር ( ፒኤፍኤ ) የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የደጋፊዎች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ኮል ፓልመር የፒኤፍኤ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የደጋፊዎች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።

ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር አመት የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች በመሆን መመረጡም አይዘነጋም።

ኮል ፓልመር በዘንድሮው የውድድር አመት በሊጉ ለቼልሲ ሀያ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ሲችል አስራ አንድ ለግብ የሆኑ ኳሶችንም አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ካሜሮን አዲስ አሰልጣኝ ሾማለች ! አሰልጣኝ ሪጎበርት ሶንግን ከአፍሪካ ዋንጫው ውድድር በኋላ ያሰናበተው የካሜሩን ብሔራዊ ቡድን አሁን ላይ አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል። ብሔራዊ ቡድኑ ቤልጂየማዊውን የ 61ዓመት አሰልጣኝ ማርክ ብራይስ በሀላፊነት መሾሙን ይፋ አድርጓል። አሰልጣኝ ማርክ ብራይስ በቤልጅየም ፣ ኔዘርላንድ እና ሳውዲ አረቢያ በነበራቸው የአሰልጣኝነት ቆይታ አስራ አምስት…
ካሜሮን አዲስ አሰልጣኟን ማሰናበቷ ተገለጸ !

በቀድሞ ተጨዋች ሳሙኤል ኤቶ የሚመራው የካሜሮን እግርኳስ ፌዴሬሽን ከወር በፊት የሾሙትን አዲስ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ማርክ ብራይስ ምንም ጨዋታ ሳያደርጉ ማሰናበታቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሪጎበርት ሶንግን ከአፍሪካ ዋንጫው ውድድር በኋላ ያሰናበተው የካሜሩን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስን የሾመው በሀገሪቱ ስፖርት ሚንስቴር በኩል ነበር።

በአዲሱ አሰልጣኝ ሹመት ውስጥ እንዳይሳተፉ የተደረጉት የካሜሮን እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ኤቶ ብስጭት ውስጥ ገብተው እንደነበር ሲገለፅ አሁን ላይ አሰልጣኙን ማሰናበታቸው ታውቋል።

አሰልጣኙ አሁን ላይ ከፊፋ ድህረ-ገጽ ላይ ስማቸው መሰረዙ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ካሜሮን ወቅታዊ ሁኔታውን ካላስተካከለች ከፊፋ የእግድ ቅጣት ሊጠብቃት እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቪንሴንት ኮምፓኒ ወዴት ሊያመራ ይችላል ?

ቤልጂየማዊው የበርንሌይ ዋና አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በቀጣይ ታላላቅ ክለቦችን በሀላፊነት ለመረከብ ንግግር መጀመሩ በመዘገብ ላይ ይገኛል።

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ ቪንሴንት ኮምፓኒን በሀላፊነት ለመሾም እንደሚፈልጉ እና የክለቡ ሀላፊዎች ተደጋጋሚ የስልክ ልውውጥ ማድረጋቸው ተነግሯል።

በትላንትናው ዕለት ከማውሪስዮ ፖቼቲኖ ጋር የተለያየው ቼልሲ በበኩሉ ስሙ ከቪንሴንት ኮምፓኒ ጋር እየተያያዘ የሚገኝ ቢሆንም አስካሁን ምንም አይነት ንግግር አለማድረጋቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በቀጣይ አመታት የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ የት ይደረጋል ?

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የሚያዘጋጃቸው የክለብ ውድድሮች በሚቀጥሉት አመታት የፍፃሜ ጨዋታቸው የሚደረግበትን ቦታ እና ስታዲየም ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት :-

- የ2026 ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ :- ቡዳፔሽት - ፑሽካሽ አሬና ስታዲየም

- የ2027 ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ :- ጣልያን - ሳን ሲሮ ስታዲየም

- የ2026 ዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ :- ኢስታንቡል - ቤሺክታሽ ፓርክ

- የ2027 ዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ :- ጀርመን ፍራክፈርት - ዶቸ ባንክ ፓርክ እንደሚደረጉ ተገልጿል።

የዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ በዌምብሌይ ስታዲየም እንዲሁም የቀጣዩ የ2025 ፍፃሜ ጀርመን አሊያንዝ አሬና ስታዲየም እንደሚደረጉ ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዋንጫ የማሸነፊያ ጥሩ እድል አግኝተናል " ማጓየር

እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሀሪ ማጓየር አስቸጋሪ የውድድር አመት ያሳለፈው ቡድናቸው ዋንጫ የማሸነፊያ ጥሩ እድል እንዳለው ገልጿል።

" ለማንችስተር ዩናይትድ መጫወት ሁልጊዜ ዋንጫ ማሸነፍን ይጠይቃል " የሚለው ሀሪ ማጓየር ባለፈው አመት አድርገነዋል አሁንም አስቸጋሪ አመት ካሳለፍን በኋላ ዋንጫ የምናሸንፍበት ጥሩ አጋጣሚ አግኝተናል ብሏል።

ሀሪ ማጓየር ቀጥሎም በተደጋጋሚ የጡንቻ ጉዳት ሲያጋጥመው የዚህ አመቱ የመጀመሪያ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ለኤፌ ካፑ ፍፃሜ ለመድረስ ተስፋ እንደሚያደርግ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ኤፌ ካፑን ለማሸነፍ ሁሉንም እንሰጣለን " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ቅዳሜ የኤፌ ካፕ ዋንጫውን በድጋሜ ለማሸነፍ ያለውን ሁሉ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

" የኤፌ ካፕ ዋንጫውን በድጋሜ በማሸነፍ የማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎችን ለማኩራት ያለንን አቅም ሁሉ በጨዋታው እንደምንጠቀም ቃል እገባላችኋለሁ።"ሲሉ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

" በዚህ አመትም በኤፌ ካፕ ፍፃሜ ላይ በመሆናችን ትልቅ ክብር ነው ይህንን ውብ ዋንጫ የማሸነፍ እድል አግኝተናል ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ እናውቃለን ተጨዋቾቹ ዝግጁ ናቸው ጓጉተናል።" ጋርዲዮላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ የኤሲ ሚላን ቆይታ ?

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን በውድድር አመቱ መጨረሻ አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊን ከሀላፊነታቸው ለማሰናበት በወሰነው ውሳኔ መፅናቱ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ በቅርቡ ስለወደፊት ቆይታቸው ተጠይቀው " በውድድር አመቱ መጨረሻ ከክለቡ ጋር እነጋገራለሁ አሁን አስተያየት መስጠት አልፈልግም።" ብለው ነበር።

ኤሲ ሚላን አሁን ላይ አሰልጣኙን የማሰናበት ውሳኔውን እንደማይቀይር ሲገለፅ አዲስ ተተኪ አሰልጣኝ ለመሾም በማፈላለግ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ የፊታችን ቅዳሜ ኤሲ ሚላን በስታዲዮ ጁሴፔ ሜዛ ከሳለርኒታና ጋር በሚያደርገው የሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ክለቡን ይሰናበታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኤሲ ሚላን በቀጣይ የአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ተተኪ ለማድረግ ፖርቹጋላዊውን የሊል አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካን ማነጋገራቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኤሪክ ቴንሀግ የዩናይትድ ቆይታ ?

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ክለቡ በአመቱ ውስጥ ባሳየው ደካማ እንቅስቃሴ ምክንያት በቀጣይ አመት በክለቡ የሚኖራቸው ቆይታ አጠራጣሪ ሆኗል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት የሚኖራቸው የወደፊት ቆይታ አስተማማኝ እንዳልሆነ የተገለፀ ሲሆን ሁኔታው 50/50 መሆኑ ተዘግቧል።

አሰልጣኙ የመሰናበት አደጋ ውስጥ መውደቃቸው እርግጥ ቢሆንም በክለቡ በኩል እስካሁን በግልጽ የተነገረ ውሳኔ #እንደሌለ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ታማኝ የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ቅዳሜ በኤፌ ካፑ የሚያስመዘግበው ውጤት ክለቡ በአሰልጣኙ ዙሪያ የሚያሳልፈው ውሳኔ ላይ ለውጥ እንደማያመጣ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 አታላንታ ከ ባየር ሊቨርኩሰን ( ዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ ስብስባቸውን አሳውቀዋል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ላሉበት ሁለት የአለም ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ጨዋታዎች የሚጠቀመውን የቡድን ስብስብ አሳውቋል።

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ለሀያ ስድስት ተጫዋቾች የመጀመርያ ጥሪ ማድረጉን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

ብሔራዊ ቡድኑ ግንቦት 29/2016 ዓ.ም ከጊኒ ቢሳው እንዲሁም ሰኔ 2/2016 ዓ.ም ከጅቡቲ ጋር ከሜዳው ውጪ ጨዋታውን ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ታሪክ መፃፍ እንፈልጋለን " ዣቢ

ከደቂቃዎች በኋላ የዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታቸውን ከአታላንታ ጋር የሚያደርጉት ባየር ሌቨርኩሰን አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ቡድናቸው ታሪክ መፃፍ እንደሚፈልግ ተናግረዋል።

ከጨዋታው በፊት አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ " አታላንታ ጨዋታውን ከባድ እንደሚያደርጉብን እናውቃለን ነገርግን ለእሱ ጓጉተናል ፣ ታሪክ መፃፍ እንፈልጋለን።"ሲሉ ተደምጠዋል።

ግራኒት ዣካ በበኩሉ " ማመናችንን መቀጠል አለብን አሰልጣኛችን ሁልጊዜም ያለንን ሁሉ እንድንሰጥ ይፈልጋል ።"በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
12 ' አታላንታ 1 - 0 ባየር ሊቨርኩሰን ( ዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ )

ሉክማን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 07:23:44
Back to Top
HTML Embed Code: