Telegram Web Link
📢 Calling all our international customers!

👉🏾 Get ready to elevate your game with our professional kits at WANAW SPORTSWEAR!

👉🏾 Enjoy our free worldwide #DHL_Delivery and affordable prices. Whether you're in Europe, Asia, or even the United States, we've got you covered!

🛍 Order now and experience the ultimate in comfort, style, and performance.

🔥 Don't miss out, join the WANAW FAMILY today!

📞  For orders and further information contact 0901138283, 0910851535 and 0913586742.

📲 You can also order via Telegram @Wanawsales by directly talking to our sales team or via our Telegram bot @WANAWSbot.

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የክሎፕ ሽኝት የብዙዎችን ትኩረት ስቦ ነበር !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በተጠናቀቀበት ምሽት አብዛኞቹ የውድድሩ ተከታታዮች ከማንችስተር ሲቲ የዋንጫ ድል ስነ-ስርዓት ይልቅ የአሰልጣኝ የርገን ክሎፕን ሽኝት ሲከታተሉ እንደነበር ተገልጿል።

ሰባ በመቶ የሚሆኑት የውድድሩ የብሪቲሽ የቴሌቪዥን ተከታታዮች እሁድ ምሽት የአሰልጣኝ የርገን ክሎፕን የሽኝት ስነ-ስርዓት ሲከታተሉ እንደነበር ተነግሯል።

በተጨማሪም በማህበራዊ ሚዲያዎች ከአርባ አራት በመቶ የሚሆኑ ተከታታዮች የአሰልጣኝ የርገን ክሎፕን የሽኝት ለመመልከት መምረጣቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቤን ቺልዌል ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ አይቀርብለትም !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የመስመር ተጨዋች ቤን ቺል ዌል የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ለአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሪ እንደማያቀርብለት ተገልጿል።

ተጨዋቹ በዘንድሮው የውድድር አመት በጉዳት ምክንያት ለክለቡ ብዙም ግልጋሎት መስጠት ሳይችል መቅረቱ ይታወሳል።

የክሪስታል ፓላሱ አማካይ አዳም ዋርተን እና የፊት መስመር ተጨዋቹ ኢዜ ከብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ሊቀርብላቸው እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶኒ ክሩስ ጫማውን እንደሚሰቅል ይፋ አደረገ !

ጀርመናዊው የሪያል ማድሪድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ ከ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር በኋላ በይፋ ከእግርኳስ ራሱን እንደሚያገል አስታውቋል።

" በጣም ለረጅም ጊዜ አስቤበታለሁ ነገርግን ባለፉት ጥቂት ቀናት ይህ አመት ትክክለኛው ጊዜ መሆኑን ተረድቻለሁ ብቸኛው ምርጫዬ እግርኳስን በሪያል ማድሪድ ማጠናቀቅ ነው።"ሲል ቶኒ ክሩስ ተናግሯል።

ቶኒ ክሩስ በማድሪድ ቤት ምን አሳካ ?

4️⃣ ሻምፒየንስ ሊግ

4️⃣ የላሊጋ ዋንጫ

4️⃣ ሱፐር ኮፓ

3️⃣ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ

5️⃣ የክለብ አለም ዋንጫ

1️⃣ ኮፓ ዴ ላሬ ማሳካት ችሏል።

ቶኒ ክሮስ በተጨማሪም በእግርኳስ ህይወቱ አንድ የአለም ዋንጫ ፣ ሶስት የቡንደስሊጋ እና ሶስት የጀርመን ካፕ ድሎችን መጎናጸፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ራሽፎርድ ከብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውጪ ሆነ !

የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ በእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የአውሮፓ ዋንጫ ስብስብ ውስጥ አለመካተቱ ተገልጿል።

የ 26ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ በዘንድሮው የውድድር አመት በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ጥሩ የሚባል አመት ማሳለፍ አልቻለም።

ማርከስ ራሽፎርድ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ስልሳ ጨዋታዎች ማድረግ ሲችል አስራ ሰባት ግቦችን ማስቆጠርም ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እንግሊዝ እነማንን በስብስቧ ታካትታለች ?

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ዛሬ ከሰዓት የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ስብስባቸውን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አሰልጣኙ ነባር የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾችን መቀነሳቸውን እና አዳዲስ ተጨዋቾችን ማካተታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮች በመዘገብ ላይ ናቸው።

በማንችስተር ሲቲ ቤት በዚህ አመት በቂ የጨዋታ ጊዜ ሳያገኝ አመቱን ያጠናቀቀው ጃክ ግሪሊሽ በአሰልጣኙ ስብስብ ውስጥ መካተቱ ተዘግቧል።

ከብሔራዊ ቡድኑ እነማን ተቀነሱ ?

- ጆርዳን ሄንደርሰን

- ማርከስ ራሽፎርድ

- ሪስ ጄምስ

- ቤን ቺልዌል

እነማን ይካተታሉ ተብሎ ይጠበቃል ?

- ከርትስ ጆንስ                   - አዳም ዊርተን

- ጃሬል ኳንሳህ                  - ጃክ ግሪሊሽ

- ኢቫን ቶኒ                         - ኢዜ

- ጄምስ ትራፎርድ 

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፖርቹጋል ስብስቧን አሳውቃለች !

በአሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ የሚመራው የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ለቀጣዩ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የሚጠቀመውን ስብስብ ይፋ አድርጓል።

የ 41ዓመቱ የፖርቶ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ፔፔ ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለታል።

በጉዳት ላይ የሚገኘው የባየር ሙኒክ ተጨዋች ራፋኤል ጎሬሮ ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ሳይቀርብለት ቀርቷል።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
እንግሊዝ እነማንን በስብስቧ ታካትታለች ? የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ዛሬ ከሰዓት የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ስብስባቸውን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። አሰልጣኙ ነባር የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾችን መቀነሳቸውን እና አዳዲስ ተጨዋቾችን ማካተታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮች በመዘገብ ላይ ናቸው። በማንችስተር ሲቲ ቤት በዚህ አመት በቂ የጨዋታ ጊዜ ሳያገኝ…
እንግሊዝ ስብስቧን ይፋ አድርጋለች !

በአሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት የሚመራው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ለቀጣዩ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የሚጠቀመውን ስብስብ ይፋ አድርጓል።

ማርከስ ራሽፎርድ ከስብስቡ ውጪ የሆነው በእሱ ቦታ የተሻለ አመት ያሳለፉ ተጨዋቾች መኖራቸውን ተከትሎ መሆኑን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ገልጸዋል።

ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ከሚያደርጋቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች በኋላ ሰባት ተጨዋቾችን በመቀነስ ወደ አውሮፓ ዋንጫው ያመራል።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዋልያዎቹ ተጋጣሚ በይፋ አሰልጣኝ ሾመች !

በቀጣይ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታውን የሚያደርገው የጊኒ ቢሳው ብሔራዊ ቡድን በይፋ ዋና አሰልጣኝ ሾሟል።

ጊኒ ቢሳው ፖርቹጋላዊውን የፉልሀም ምክትል አሰልጣኝ ሉዊስ ቦ ሞርቴ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጋ በሀላፊነት መሾሟን አስታውቃለች።

የቀድሞ ፖርቹጋላዊ ተጨዋች ሉዊስ ቦ ሞርቴ በኤቨርተን እና ፉልሀም ቤት ከአሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ ጋር በምክትል አሰልጣኝነት ለስድስት አመታት ማገልገል ችለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአስራ አምስት ቀናት በኋላ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታውን ከጊኒ ቢሳው ጋር ቢሳው ላይ የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቶኒ ክሩስ ጫማውን እንደሚሰቅል ይፋ አደረገ ! ጀርመናዊው የሪያል ማድሪድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ ከ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር በኋላ በይፋ ከእግርኳስ ራሱን እንደሚያገል አስታውቋል። " በጣም ለረጅም ጊዜ አስቤበታለሁ ነገርግን ባለፉት ጥቂት ቀናት ይህ አመት ትክክለኛው ጊዜ መሆኑን ተረድቻለሁ ብቸኛው ምርጫዬ እግርኳስን በሪያል ማድሪድ ማጠናቀቅ ነው።"ሲል ቶኒ ክሩስ ተናግሯል። ቶኒ…
ጫማውን ስለሚሰቅለው ቶኒ ክሩስ ምን ተባለ ?

በእግርኳስ ህይወቱ ስኬታማ ጊዜን ያሳለፈው ጀርመናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ ከአውሮፓ ዋንጫ በኋላ ጫማውን እንደሚሰቅል ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

ቶኒ ክሩስ ራሱን ከእግርኳስ ለማግለል መወሰኑን ተከትሎ የቡድን አጋሮቹ እንዲሁም ሌሎች ተጨዋቾች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ተጨዋቾች ስለ ቶኒ ክሩስ ምን አሉ ?

- ክርስቲያኖ ሮናልዶ :- " ለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ ቶኒ ከአንተ ጋር ሜዳ ላይ መጫወት ትልቅ ክብር ነው መልካሙ ሁሉ እንዲገጥምህ እመኛለሁ።"

- አንድሬ ሉኒን :- "ዛሬ ለአለም እግርኳስ የሀዘን ቀን ነው በጣም ትናፍቀናለህ ጀግናችን እንወድሃለን።"

- ሰርጂዮ ራሞስ :- " ከልዩ ተጨዋች እና ድንቅ ሰው ጋር አስደናቂ ቅፅበቶች እና ስኬቶችን ማስመዝገብ አስደሳች ነበር በአዲሱ ህይወትህ እና ቀሪ ጨዋታዎች ደስተኛ ሁን።"

- ብሩኖ ፈርናንዴዝ :- "በዚህ ትውልድ ከታዩ ምርጥ ተጨዋቾች አንዱ ነህ በእነዚህ ሁሉ አመታት አንተ ስትጫወት መመልከት አስደሳች ነበር።"

- ቹዋሜኒ :- " አንተን ለማመስገን አስራ አምስተኛ ሻምፒየንስ ሊግ የምናሳካበት ተጨማሪ ምክንያት አግኝተናል ፣ ከአንተ ጋር መጫወቴን መናገር ስለቻልኩ ደስተኛ ነኝ ፣ ከምንጊዜውም ምርጦች አንዱ ነህ።"

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ብዙ እይታ በማግኘት ቀዳሚው ክለብ ሆኗል !

ጥሩ የውድድር አመት ማሳለፍ የቻለው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በተጠናቀቀው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ውድድር ጨዋታዎቹ ብዙ ጊዜ የታዩለት ቀዳሚው ክለብ መሆን ችሏል።

ይህንንም ተከትሎ መድፈኞቹ ከሌሎቹ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች የበለጠ የቴሌቪዥን መብት ክፍያን እንደሚያገኙ ተገልጿል።

አርሰናል በዘንድሮው የውድድር አመት በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቁ እና በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ሩብ ፍፃሜ በመድረሱ ምክንያት 253 ሚልዮን ፓውንድ ገቢ እንደሚያገኙ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🏆የአውሮፓ ሊግ የዋንጫ ፍልሚያ🏆

🔥 ነገ ረቡዕ ግንቦት 14 ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት የአውሮፓ ሊግ ፍፃሜ የመጨረሻ ጨዋታ አታላንታ ከ ሌቨርኩሰን ጋር ያደርጋሉ!

ያለ ምንም ሽንፈት የቡንደስሊጋን ዋንጫ ያሸነፈው ሌቨርኩሰን ለዓመቱ ሁለተኛ ጊዜ ዋንጫ ለማሸነፍ እየገሰገሰ ነው!

🤔 ዋንጫው የማን ነው? የእርሶን አስተያየት ያጋሩን             

👉 ጨዋታውን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
የሴርያ የአመቱ ምርጦች እነማን ይሆናሉ ?

በኢንተር ሚላን አሸናፊነት የተጠናቀቀው የጣልያን ሴርያ የዘንድሮው የ2023/24 የውድድር አመት በየዘርፉ የአመቱ ምርጥ እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት :-

- የአመቱ ምርጥ አጥቂ እጩዎች :- ፓብሎ ዲባላ ፣ ራፋኤል ሊያኦ እና ቭላሆቪች

- የአመቱ ምርጥ አማካይ :- ካልሀኖግሉ ፣ ኮፕሜነርስ እና ክርስቲያን ፑልሲች

- የአመቱ ምርጥ ተከላካይ :- ባስቶኒ ፣ ብሬመር እና ካላፍዮሪ በእጩነት መቅረብ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ከቼልሲ ጋር ሊለያዩ ነው !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከአርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ጋር ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ እንደሚለያዩ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ከቼልሲ ጋር በጋራ ስምምነት ለመለያየት ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

ቼልሲ በቀጣይ ከሚመለከታቸው አሰልጣኞች መካከል የጂሮናው አሰልጣኝ ሚቼል ፣ የኢፕስዊች ታውኑ ኬራን ማኬና እና የሌስተር ሲቲው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ፖቼቲኖ እንደማይቀጥሉ ሰምቻለሁ " ፈርዲናንድ የቀድሞ እንግሊዛዊ የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪዮ ፈርዲናንድ አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ከቼልሲ ጋር እንዳማይቀጥሉ መስማቱን ገልጿል። ሪዮ ፈርዲናንድ ከውስጥ ሰምቼዋለሁ እንዳለው መረጃ ከሆነ አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ በሚቀጥለው አመት " በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ቤት አይቀጥሉም " ብሏል። …
ቼልሲ ከአሰልጣኙ ጋር መለያየቱን ይፋ አደረገ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከአርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ጋር ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ በጋራ ስምምነት መለያየቱን በይፋ አስታውቋል።

አሰልጣኙ ለክለቡ ለሰጡት ግልጋሎት ምስጋናውን ያቀረበው ክለቡ በመግለጫው በሚቀጥለው የአሰልጣኝነት ቆይታቸው መልካሙን እንመኛለን ብሏል።

ማውሪስዮ ፖቼቲኖ በበኩላቸው " የዚህ ታላቅ ክለብ ታሪክ ተጋሪ እንደሆነ እድሉ ስለተሰጠኝ አመሰግናለሁ፣ ክለቡ አሁን አቋሙን ለማስቀጠል በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•MacBook Air, M1
•MacBook Pro, M1

•MacBook Air, M2
•MacBook Pro, M2

•MacBook, M1 Pro
•MacBook, M2 Pro

•MacBook, M1 Max
•MacBook, M2 Max

Contact Us
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
ክላውዲዮ ራኔሪ ራሳቸውን ከእግር ኳስ አገለሉ !

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኔሪ ራሳቸውን ከእግር ኳስ የስልጠና አለም ማግለላቸውን ይፋ አድርገዋል።

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ከሌስተር ሲቲ ጋር ታሪካዊ ዋንጫን ማሳካት የቻሉት ራኔሪ ለመጨረሻ ጊዜ የሴርያውን ክለብ ካግሊያሪ በማሰልጠን ላይ ነበሩ።

የ 72ዓመቱ አንጋፋ አሰልጣኝ የሆኑት ክላውዲዮ ራኔሪ በ እግር ኳስ ከ 50ዓመታት በላይ መስራት ችለዋል።

ከ 1400 ጨዋታዎች በላይ በአስራ ዘጠኝ የተለያዩ ክለቦች የቆየው የክላውዲዮ ራኔሪ የአሰልጣኝነት ዘመን ካግሊያሪን ከመውረድ
ባተረፉበት ቀናቶች በኋላ ተገባዷል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ ሆነ !

ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲ ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሊጉ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በመባል መመረጣቸው ይፋ ሆኗል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ይህን ሽልማት ሲያሸንፉ ካለፉት ሰባት አመታት ውስጥ ለአምስተኛ ጊዜ ነው።

ጋርዲዮላ ከሽልማቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት “ ይህን ሽልማት አስደናቂ ስራን እስከ መጨረሻው ሳምንት ከሰራው አርቴታ ጋር መጋራት እፈልጋለሁ “ ብለዋል።

በተጨማሪም ፔፕ ጋርዲዮላ “ ከየርገን ክሎፕ ጋር ላሳለፍናቸው የማይረሱ ፉክክሮች ይህን ሽልማት ማጋራት እፈልጋለሁ “ በማለት ተናግረዋል።

“ ይህን ሽልማት ማሸነፍ ለእኔ ክብር ነው ፣ ይህ ሽልማት ማንችስተር ሲቲ በሁሉም ደረጃ ምን ያህል ጠንካራ ስራ እንደሰራ ያሳያል። “ ፔፕ ጋርዲዮላ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
2024/10/05 09:21:49
Back to Top
HTML Embed Code: