Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ሆሴሉ ለሪያል ማድሪድ በቋሚነት ይፈርማል ! ሪያል ማድሪድ በውሰት እየተጫወተ የሚገኘውን ስፔናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሆሴሉ ለሚቀጥለው የውድድር አመት በቋሚነት ለማስፈረም መወሰናቸው ተገልጿል። ሎስ ብላንኮዎቹ ሆሴሉን ባለፈው ክረምት በውሰት 500,000 ዩሮ በማውጣት ያስፈረሙት ሲሆን ተጫዋቹም በወሳኝ ጨዋታዎች ግብ በማስቆጠር ለክለቡ ጥሩ ግልጋሎት መስጠት ችሏል። ሪያል ማድሪዶች ተጫዋቹን በውሉ…
ሆሴሉ ሪያል ማድሪድን ሊለቅ ነው !

ስፔናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሆሴሉ በሚቀጥለው የውድድር አመት ከሪያል ማድሪድ ጋር ላለመቀጠል ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድ በሆሴሉ የውሰት ውል ውስጥ የተካተተውን አማራጭ ተጠቅመው 1.5 ሚልዮን ዩሮ ወጪ በማድረግ በቋሚነት ለማስፈረም መወስናቸው ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ሆሴሉ ኪሊያን ምባፔ እና ኢንድሪክ ወደ ሪያል ማድሪድ መምጣታቸውን ተከትሎ ሎስ ብላንኮዎቹን ለመልቀቅ ማሰቡ ተገልጿል።

ሆሴሉ በቀጣይ የኳታሩን ክለብ አል ጋራፋ ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 በጥራት የተዘጋጁ #ቢብሶች!

🔥 አሁኑኑ #ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
Forwarded from HEY Online Market
Samsung Galaxy S22 Ultra
256 GB - 67,000 ETB
512 GB - 78,000 ETB

Samsung Galaxy S23 Ultra
256 GB - 92,000 ETB
512 GB - 109,000 ETB

Samsung Galaxy S24 Ultra
256 GB - 109,000 ETB
512 GB - 124,000 ETB

Exchange Available
🏍️ Free Delivery

Contact us :
0925927457 @eBRO4
@Heyonlinemarket
" በእግርኳስ ካሰብኩት በላይ ማሳካት ችያለሁ " ሜሲ

አርጀንቲናዊው የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በእግርኳስ ህይወቱ ካሰበው በላይ ስኬታማ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

" አመታት እየሄዱ እንደሆነ እና በእግርኳስ ውስጥ የቀሩኝ አመታት ጥቂት መሆናቸውን አውቃለሁ " ያለው ሊዮኔል ሜሲ በእግርኳስ ህይወቴ ካለምኩት በላይ ማሳካት ችያለሁ " ብሏል።

የኢንተር ሚያሚው የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በዛሬው ዕለት 37ኛ አመት የልደት ቀኑን በማክበር ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤምሬትስ ካፕ የሚደረግበት ቀን ተገለጸ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በቅድመ ውድድር ዝግጅት ወቅት የሚያዘጋጀው ኤምሬትስ ካፕ የተሰኘው  ውድድር ነሐሴ 5 እንደሚካሄድ ተገልጿል ።

አርሰናል የዚህን አመት የኤምሬትስ ካፕ ጨዋታ እሁድ ነሐሴ 5/2016 ዓ.ም ከፈረንሳዩ ክለብ ኦሎምፒክ ሊዮን ጋር እንደሚያደርግ ይፋ ተደርጓል።

በተጨማሪም መድፈኞቹ ከሊዮን ጨዋታ አራት ቀናት ቀደም ብለው ከጀርመኑ ክለብ ባየር ሌቨርኩሰን ጋር በኤምሬትስ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል።

ስዊዘርላንዳዊው የቀድሞ የመድፈኞቹ ተጨዋች ግራኒት ዣካ ከአንድ አመት በኋላ ወደ ኤምሬትስ ስታዲየም ተመልሶ የቀድሞ ክለቡን ይገጥማል።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
" ኪሊያን ምባፔ መጫወት ይፈልጋል "

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ የቡድኑ አምበል ኪሊያን ምባፔ ካጋጠመው ጉዳት እየተሻለው መሆኑን በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ዲዴ ዴሻምፕ አያይዘውም ኪሊያን ምባፔ በነገው የፖላንድ ጨዋታ ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን እና በጨዋታው መሰለፍ እንደሚፈልግ ገልጸዋል።

ኪሊያን ምባፔ በቀጣይ ጨዋታዎች የሚያደርገው የፊት ጭምብል ለመተንፈስ አስቸጋሪ ባይሆንበትም እይታውን በመጠኑ ሊቀንሰው እንደሚችል አሰልጣኙ አያይዘው ስጋታቸውን ገልጸዋል።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 አልባንያ ከ ስፔን

4:00 ክሮሽያ ከ ጣልያን

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
#EURO2024

በምሽቱ የጣልያን እና ክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ 38,000 ተመልካች በሚይዘው የሌፕዚግ ስታዲየም 25,000 ገደማ የክሮሽያ ደጋፊዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

የፊት መስመር ተጨዋቹ ኢቫን ፔርሲችን ተጠባባቂ ያደረገችው ክሮሽያ የአጥቂ አማካዩ ክራማሪችን በፊት መስመር ቦታ ላይ አሰልፋለች።

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው ያለ ተፈጥሯዊ አጥቂ ሲገቡ 4-6-0 የሆነ የጨዋታ አሰላለፍ ሊጠቀሙ ይችላሉ።

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ በምሽቱ የክሮሽያ ጨዋታ የሶስት ተጨዋቾች ለውጥ አድርገው ወደ ሜዳ ይገባሉ።

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው የ3-5-2 የጨዋታ አሰላለፍ ይዘው እንደሚገቡ ይጠበቃል።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
13 '

አልባንያ 0-1 ስፔን

ቶሬስ

ክሮሽያ 0-0 ጣልያን

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
31 '

አልባንያ 0 - 1 ስፔን

         ቶሬስ

ክሮሽያ 0 - 0 ጣልያን

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
#እረፍት

አልባንያ 0 - 1 ስፔን

         ቶሬስ

ክሮሽያ 0 - 0 ጣልያን

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
54 '

ክሮሽያ 1 - 0 ጣልያን

ሞድሪች

አልባንያ 0 - 1 ስፔን

         ቶሬስ

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
77 '

ክሮሽያ 1 - 0 ጣልያን

ሞድሪች

አልባንያ 0 - 1 ስፔን

         ቶሬስ

*ወቅታዊ የምድቡ ደረጃ ሰንጠረዥ

1️⃣ ስፔን :- 9 ነጥብ

2️⃣ ክሮሽያ :- 4 ነጥብ

3️⃣ ጣልያን :- 3 ነጥብ

4️⃣ አልባንያ :- 1 ነጥብ

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
90+8'

ክሮሽያ 1 - 1 ጣልያን

ሞድሪች ዛካኚ

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
ጣልያን ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለት የመጨረሻ ጨዋታ ስፔን አልባንያን 1ለ0 በሆነ ውጤት ስታሸንፍ ክሮሽያ ከጣልያን ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ለስፔን ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቧን ፌራን ቶሬስ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ለክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ሉካ ሞድሪች ማስቆጠር ሲችል ለጣልያን ዛካኚ በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃ የአቻነት ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን መታደግ ችሏል።

ጣልያን አቻ መውጣቷን ተከትሎ ስፔንን በመከተል አስራ ስድስቱን መቀላቀሏን አረጋግጣለች።

ሉካ ሞድሪች በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ ለክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን አራት ግቦችን በማስቆጠር የኢቫን ፔሪሲችን ታሪክ መጋራት ችሏል።

የ 38ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ግብ ማስቆጠር የቻለ በታሪክ በእድሜ ትልቁ ተጨዋች መሆን ችሏል።

የአልባንያ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁን ተከትሎ ከአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/06/25 05:20:44
Back to Top
HTML Embed Code: