Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
" ከአርሰናል ሲሆን የማሸነፍ ፍላጎታችን ይጨምራል " ቴን ሀግ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት በአሜሪካ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ቡድናቸው ከአርሰናል የሚያደርገውን የወዳጅነት ጨዋታ በቁምነገር እንደሚመለከት ገልጸዋል። “ እኛ ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ እንፈልጋለን “ የሚሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ " በተለይም ከአርሰናል ጋር ሲሆን የማሸነፍ ፍላጎታችን ይጨምራል" ብለዋል።…
“ ዩናይትድ ከአለም ምርጥ ቡድኖች አንዱ ነው “ አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ዛሬ ሌሊት የሚገጥሙበት ማንችስተር ዩናይትድ ከአለም ምርጥ ቡድኖች አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

" ዛሬ ለእኛ ትልቅ ቀን ይሆናል " ያሉት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከአለም ምርጥ ቡድኖች አንዱ ከሆነው ማንችስተር ዩናይትድ ከአለም ውብ ስታዲየሞች አንዱ በሆነው እንጫወታለን ብለዋል።

“ በቀጣይ ሊጉን ለማሸነፍ 114 ነጥቦች ያስፈልጉናል “ ሲሉ ከሲቲ ጋር ጠንካራ ፉክክር እንደሚኖር የገለፁት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የመጀመሪያው አላማችን ይህንን ማድረግ ነው " በማለት ተናግረዋል።

አርሰናል ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በአሜሪካው ሶፊ ስታዲየም የሚያደርጉት የወዳጅነት ጨዋታ ዛሬ ሌሊት 9:00 ሰዓት ላይ ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሜሲ የማበረታቻ መልዕክት ልኮልናል “ ጁሊያን አልቫሬዝ

የአርጀንቲና ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን አባል የሆነው ጁሊያን አልቫሬዝ የዋናው ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ የማበረታቻ መልዕክት እንደላከላቸው ተናግሯል።

በሞሮኮ ከተሸነፉበት ጨዋታ በኋላ ሊዮኔል ሜሲ የማበረታቻ መልዕክቱን እንደላከላቸው የገለፀው  አልቫሬዝ " ያለፈውን ጨዋታ ረስተን በቀጣዩ ጨዋታ ላይ እንድናተኩር ነግሮናል" ብሏል።

ጁሊያን አልቫሬዝ አክሎም ሊዮኔል ሜሲ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ እንዲሆኑ እንደሚፈልግ እና ጠንካራ መሆን እንዳለባቸው ማሳሰቡን ገልጿል።

የአርጀንቲና ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ የኢራቅ አቻውን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የመጀመሪያ ድሉን ማሳካቱ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
  🆕 አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

📌 https://www.tg-me.com/sellphone2777

📞  0929008292

📩 inbox @bina27

📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
TIKVAH-SPORT
ካናዳ የኦሎምፒክ ቡድኗን አሰልጣኝ አገደች ! የካናዳ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሀገሪቱን ሴቶች እግርኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ቤቭ ፕሬስትማን ከኦሎምፒክ ቡድኑ ማገዱን አስታውቋል። ካናዳ አሰልጣኟን ያገደችው ከቀናት በፊት የትላንት ተጋጣሚዋ ኒውዝላንድን ልምምድ በድሮን ለመሰለል በተደረገው ሙከራ ጋር በተያያዘ መሆኑ ተገልጿል። የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ የካናዳ እግርኳስ የበላይ ቦርድ ሁኔታውን መርምሮ የመጨረሻ…
ፊፋ ካናዳ ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳለፈ !

የአለም እግርኳስ የበላይ ፊፋ የካናዳ ሴቶች እግርኳስ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ቤቭ ፕሬስትማን ለአንድ አመት ከእግርኳስ ማገዱን አስታውቋል።

በተጨማሪም የካናዳ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን ስድስት ነጥቦች እንዲቀነሱበት እና 200,000 የስዊዝ ፍራንክ እንዲከፍል የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን ይፋ አድርጓል።

ፊፋ ቅጣቱን ያሳለፈው ካናዳ ከቀናት በፊት ተጋጣሚዋ ኒውዝላንድን ልምምድ በድሮን ለመሰለል በመሞከሯ ምክንያት መሆን ተገልጿል።

የካናዳ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የብሔራዊ ቡድኑን ዋና አሰልጣኝ ቤቭ ፕሬስትማን ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ ማድረጉ እና ኒውዝላንድን ይቅርታ መጠየቁ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሳሞኣ የቦክስ አሰልጣኟ ህይወቱ አለፈ !

የሳሞኣ ኦሎምፒክ ልዑክ ብሔራዊ ቡድን የቦክስ አሰልጣኝ የሆኑት ሊዮኔል ፋቱ ኤሊካ በአትሌቶች መንደር ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።

የ 60ዓመቱ አሰልጣኝ ሊዮኔል ፋቱ ኤሊካ በብሔራዊ ልዑክ ቡድኑ ማረፊያ ባሉበት ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አረጋግጧል።

አሰልጣኙ በምን ምክንያት ህይወታቸው እንዳለፈ የሀገሪቱ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በይፋ ለመገናኛ ብዙሃን አላሳወቀም።

ይሁን እንጂ አሰልጣኙ ህይወታቸው ያለፈው ከልብ ጋር በተያያዘ ህመም ሳይሆን እንዳልቀረ ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ደቡብ አፍሪካ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች !

በ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ደቡብ አፍሪካ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት የቻለች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር መሆን ችላለች።

ደቡብ አፍሪካ በራግቢ ውድድር አውስትራሊያን 26 ለ 19 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የነሀስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆናለች።

በራግቢ ውድድር ለወርቅ ሜዳልያ በተደረገ ፍልሚያ ፈረንሳይ ፊጂን በማሸነፍ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት መሆን ችላለች።

አዘጋጇ ፈረንሳይ ባለፉት ሁለት የኦሎምፒክ ውድድሮች የራግቢ አሸናፊ የነበረችውን ፊጂ በመርታት የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳልያዋን አሳክታለች።

እስካሁን የወርቅ ሜዳልያ ያሳኩ ሀገራት እነማን ናቸው ?

🥇🥇 ቻይና
🥇 ቤልጅየም
🥇 ጃፓን
🥇 አውስትራሊያ
🥇 ካዛኪስታን
🥇 ፈረንሳይ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

ስፔናዊዎቹ የሜዳ ቴኒስ ተጨዋቾች ራፋኤል ናዳል እና ካርሎስ አልካራዝ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጣመሩበትን የኦሎምፒክ የጥንድ ውድድር በአሸናፊነት መወጣት ችለዋል።

የቀድሞው እና የወቅቱ የሜዳ ቴኒስ ኮከቦች ራፋኤል ናዳል እና ካርሎስ አልካራዝ በመጀመሪያው ዙር አርጀንቲናዊያኑን ሞልቴኒ እና ጎንዛሌዝ 7ለ6 እና 6ለ4 መርታት ችለዋል።

ራፋኤል ናዳል ሁለት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ባለቤት ሲሆን ወጣቱ ካርሎስ አልካራዝ የመጀመሪያ ኦሎምፒክ ተሳትፎውን በማድረግ ለመጀመሪያ ሜዳልያው ይፋለማል።

ራፋኤል ናዳል እና ካርሎስ አልካራዝ በሁለተኛው ዙር ከኔዘርላንዳዊዎቹ ዌስሌይ ኮሎፍ እና ግሬክስፖር ወይም ከሀንጋራዊያኑ ማሮዛን እና ፉሶቪክስ አሸናፊ ጋር ይጫወታሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Arsenal #ManchesterUnited

በአሜሪካ ለሊቱን በነበረው ተጠባቂ የወዳጅነት ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ መደበኛውን ዘጠና ደቂቃ በአርሰናል 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ቀያይ ሰጣኖቹ በጨዋታው ሽንፈት ይግጠማቸው እንጂ በዕለቱ በነበረው የመለያ ምት አርሰናልን 4 ለ 3 ማሸነፍ ችለዋል።

በጨዋታው የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ጋብሬል ጄሱስ እና ማርቲኔሊ ሲያስቆጥሩ የዩናይትድን ብቸኛ ግብ ራስሙስ ሆይሉንድ አስቆጥሯል።

የጨዋታውን አጫጭር ቪድዮዎች በጎል ቻናላችን https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk ይመልከቱ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
"ፔፕ እንድቆይ እንደሚፈልግ መናገሩ አስደስቶኛል" ኤደርሰን

የማንችስተር ሲቲ ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ ኤደርሰን በክለቡ ስለሚኖረው የወደፊት ቆይታ ከውሳኔ ላይ እንዳልደረሰ ተናግሯል።

ማንችስተር ሲቲ በአሜሪካ ሌሊቱን የቅድመ ውድድር ዝግጅት ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን ከኤሲ ሚላን ጋር አድርጎ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊያመራ ይችላል ተብሎ ስሙ በስፋት እየተነሳ የሚገኘው ኤደርሰን "ምንም የወሰንኩት ውሳኔ የለም “ ሲል አጭር ምላሽ ሰጥቷል”

ኤደርሰን አያይዞም “ፔፕ ጋርድዮላ እንድቆይ እንደሚፈልግ መናገሩ አስደስቶኛል" ብሏል።

በመጀመሪያው ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች የተሸነፈው ማንችስተር ሲቲ በቀጣይ ከሁለት ቀናት በኃላ ከ ባርሴሎና ጋር ሌላ የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
"የተቆጠረብን ግብ ከጨዋታ ውጪ ነበር" ቴን ሀግ

የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ከአርሰናል ጋር በነበራቸው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ የተቆጠረባቸው የመጀመሪያ ግብ ከጨዋታ ውጪ እንደነበር ተናግረዋል።

"የአርሰናልን የመጀመሪያ ግብ ተመልክቼዋለሁ ከጨዋታ ውጪ ነበር" ያሉት ቴን ሀግ በመጀመሪያ አጋማሽ ቡድናቸው በጥሩ መልኩ መጫወቱን ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ አክለውም በጨዋታው ጉዳት ያስተናገዱትን ሌኒ ዮሮ እና ራስሙስ ሆይሉንድ ሁኔታ ለማወቅ በሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ውስጥ ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ ከስፔኑ ክለብ ሪያል ቤቲስ የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
"ደጋፊዎቻችንን በውጤቱ እንደተደሰቱ ተስፋ አደርጋለሁ " ሚኬል አርቴታ

የአርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ባስመዘገበው ውጤት ደጋፊዎች ደስተኛ እንደሚሆኑ ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

"እኛን ለማየት የመጡትን ደጋፊዎች ማመስገን እፈልጋለሁ" ያሉት ሚኬል አርቴታ " ደጋፊዎቻችን በጨዋታው በነበረን ውጤት እንደተደሰቱ እና እንደተዝናኑ ተስፋ አደርገዋለሁ" ብለዋል።

"እረፍት ላይ የነበሩ ተጨዋቾች ወደ ቡድን ስብስቡ መመለሳቸው ለእኛ ተጨማሪ ሀይል እና ጥንካሬ ሰጥቶናል “ ሲሉ ተደምጠዋል።

በጨዋታው ላይ በርካታ የሁለቱ ክለቦች ደጋፊዎች የተገኙ ሲሆን ታወቂው የሙዚቃ አቀንቃኝ ጀስቲን ቢበርም ጨዋታውን በስታዲየሙ በመገኘት መከታተሉ ተነግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ፓሪስ ከፍተኛ የሀይል መቋረጥ አጋጥሟታል !

የፓሪስ ኦሎምፒክ ከመጀመሪያ ቀን ውድድር ፍፃሜ በኋላ ሌሊቱን ከፍተኛ የሆነ የሀይል ማቋረጥ በከተማው መከሰቱ ይፋ ሆኗል።

የሀይል መቋራረጥ ምክንያቱ ያልተገለፀ ሲሆን እውቁ ኤፍል ታወርን ጨምሮ በርካታ የሀገሪቱ ከተሞች በጨለማ ተውጠው ታይተዋል።

በጉዳዪ ላይ የተሰጠ ማረጋገጫ ባይኖርም በርካቶች በተንቀሳቃሽ ስልካቸው የሀይል መቋረጥ ማጋጠሙን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ይፋ አድርገዋል።

ትችትን እያስተናገደ የሚገኘው የፓሪስ ኦሎምፒክ በመክፈቻ ዝግጅቱ ላይ ፖለቲካዊ ይዘቶቹ ፣ የተመሳሳይ ፆታ ድጋፎቹ እንዲሁም የሀይማኖት ዝግጅቶቹ በርካቶችን አስቆጥቷል።

አለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የመክፈቻ ሙሉ ዝግጅቱን ከ “ YouTube “ ላይ ማንሳቱም ተዘግቧል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Genk - St. Liege
FC Copenhagen - Aarhus
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ኔዘርላንድ ተጨዋቿ ተቃውሞ ገጠመው !

ከአመታት በፊት ከ 12ዓመት ታዳጊ ጋር ፆታዊ ግንኙነት አድርጓል በሚል ወንጀል እስር ላይ የነበረው ኔዘርላንዳዊው የቮሊ ቦል ተጨዋች ሀገሩን በኦሎምፒክ ለመወከል ፓሪስ መገኘቱ ተገልጿል።

ስቴቨን ቫን ዴ ቬልዴ የተባለው ተጨዋቹ እ.ኤ.አ 2016 እንግሊዝ ውስጥ የአራት አመት እስር ተፈርዶበት ከአንድ አመት እስር በኋላ ተለቆ ወደ ሀገሩ መሸኘቱ ተነግሯል።

ተጨዋቹ ከአመታት በፊት  ከ 12ዓመት ታዳጊ ጋር ፆታዊ ግንኙነት ሲያደርግ በወቅቱ 19ዓመቱ እንደነበር ተገልጿል።

ተጨዋቹ በፓሪስ ቆይታው ከኔዘርላንድ ብሔራዊ ልዑክ ቡድን ጋር በአትሌቶች መንደር #እንደማያርፍ ሲነገር እንዲሁም መገናኛ ብዙሃን እሱን ማግኘት እንደማይችሉ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲቀርቡ ከኦሎምፒክ ውጪ እንዲሆን ድምፅ መሰባሰቡ ሲገለፅ ከ 89,000 በላይ ሰዎች ድምፅ መስጠታቸው ታውቋል።

የኔዘርላንድ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ተጨዋቱ ሙሉ የኦሎምፒክ መስፈርት አሟልቶ ፓሪስ መገኘቱን ሲገልፅ አለም አቀፉ የቮሊ ቦል ፌዴሬሽን በበኩሉ ይህንን ለማስቆም ስልጣን #ማጣቱን አሳውቋል።

ተጨዋቹ የኦሎምፒክ ተሳትፎውን ባገኘበት ወቅት ከአመታት በፊት የተፈጠረው አደጋ " የህይወቴ ትልቁ ስህተት ነበር " ሲል " የሚዲያዎች ቀልብ እንደምስብ አውቃለሁ ነገር ግን መቀየር አልችልም መቀበል አለብኝ " ብሏል።

ተጨዋቹ ዛሬ ኔዘርላንድን በመወከል ከቡድን አጋሩ ማቲው ኢመርስ ጋር የጣልያን አቻቸውን ይገጥማሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ሁለተኛ ቀን በዛሬው ዕለት ሲቀጥል ዛሬም እንደትላንቱ በተመሳሳይ አስራ ሶስት የወርቅ ሜዳልያዎች ለአሸናፊዎች ይበረከታሉ።

የመጀመሪያውን ቀን የኦሎምፒክ ውሎ አውስትራሊያ በሶስት ወርቅ ሜዳልያዎች የሜዳልያ ሰንጠረዡን በበላይነት እየመራች ማጠናቀቅ ችላለች።

ዛሬ ከሚጠበቁ ውድድሮች መካከል ምሽት 12:15 ሰዓት በሊብሮን ጄምስ የሚመራው የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ቡድን በኒኮላ ጆኪች ከሚመራው የሰርቢያ አቻው ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ አንዱ ነው።

በዛሬው ዕለት የዋና ፣ ቀስት ፣ ካያኪንግ ፣ ብስክሌት ፣ ፌንሲንግ ፣ ጁዶ ፣ ሹቲንግ እና ስኬትቦርዲንግ ለሜዳልያ የሚደረጉ ውድድሮች ናቸው።

ወቅታዊ የሜዳልያ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

🥇🥇🥇 አውስትራሊያ
🥇🥇 ቻይና
🥇 አሜሪካ
🥇 ፈረንሳይ
🥇 ደቡብ ኮርያ
🥇 ካዛኪስታን ፣ ቤልጂየም ፣ ጃፓን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ውድድር ብራዚልን በ " Surfing " ውድድር የሚወክለው ተጨዋች መንሸራተቻ ሰሌዳውን እንዳይጠቀም እንደታገደበት ተገልጿል።

አለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የተጫዋቹን የውሀ ላይ መንሸራተቻ አነስተኛ ቦርድ ያገደው የኦሎምፒክ ደንብን የጣሰ ሃይማኖታዊ መልዕክት ይዟል በሚል መሆኑ ተነግሯል።

የአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ህግ በኦሎምፒክ ውድድር ላይ ሃይማኖታዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ዘርን መሰረት ያደረጉ መግለጫዎች እና መልዕክቶችን ማንፀባረቅ የተከለከለ ስለመሆኑ ይደነግጋል።

አለምአቀፍ የሀይማኖት ተቋማት እና የእምነት ተከታዮች ውድድሩ የሃይማኖት እምነቶችን ያንቋሸሸ እና ከክብራቸው ያወረደ ነው በሚል ቅሬታቸውን በማቅረብ ናቸው።

በመክፈቻ ዝግጅቱ ላይ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ሴቶች ሂጃብ ለብሰው መሳተፍ እንደማይችሉ በአዘጋጆቹ መከልከላቸው የውድድሩን አዘጋጆች ያስተቸ ሁነት ነበር።

በአነጋጋሪ ሁነቶች የታጀበው የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ውድድር ሁለተኛ ቀኑ ላይ ሲደርስ ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው ውድድሮች ከቀናት በኋላ ሐሙስ ይጀምራሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥⚽️ ትኩስ የስፖርት ዜናዎችን በቀላሉ በSMS እናግኝ! 💬

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30001 SMS በመላክ አሁኑኑ Elite ስፖርትን እንቀላቀል ! በቀን 2ብር ብቻ!

በElite ስፖርት በሽ ዜናዎች⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን
https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
2024/10/04 21:17:44
Back to Top
HTML Embed Code: