Telegram Web Link
" ከአርሰናል ሲሆን የማሸነፍ ፍላጎታችን ይጨምራል " ቴን ሀግ

ለቅድመ ውድድር ዝግጅት በአሜሪካ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ቡድናቸው ከአርሰናል የሚያደርገውን የወዳጅነት ጨዋታ በቁምነገር እንደሚመለከት ገልጸዋል።

“ እኛ ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ እንፈልጋለን “ የሚሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ " በተለይም ከአርሰናል ጋር ሲሆን የማሸነፍ ፍላጎታችን ይጨምራል" ብለዋል።

ቴን ሀግ አክለውም " አርሰናልም በተመሳሳይ ጨዋታውን እንደ ወዳጅነት ጨዋታ አይመለከቱትም " ያሉ ሲሆን “ ይህ ለእኛ ትልቅ ፈተና ይሆነናል “ ሲሉ ተናግረዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናል በአሜሪካ የሚያደርጉት የወዳጅነት ጨዋታ ዛሬ ሌሊት 9:00 ሰዓት ላይ ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 ዋናው 🤝 ድሬዳዋ ከተማ 🤝 አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ 🇪🇹

በዋናው ስፖርት አዘጋጅነት በሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደ የፊርማ ስነስርዓት እና ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የቀድሞ የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ የነበረውን አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለን በትናንትናው ዕለት በዋና አሰልጣኝነት ሾሟል። ክለቡ አሰልጣኙን በይፋ ለአራት አመታት ከቡድኑ ጋር ለማቆየት መስማማቱን የገለፀ ሲሆን፣ አሰልጣኝ ይታገሱ በወጣቶች የተገነባ የድሬዳዋ እሴትን የሚያስጠብቅ የጨዋታ ፍልስፍናን በመከተል ክለቡንና የድሬዳዋ ወጣቶችን ከፍ ወዳለ የእግር ኳስ ደረጃ ለማድረስ እንሚሰራ በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገልጿል።

ዋናው ስፖርት ይህን ታሪካዊ የፊርማ ስምምነት በአጋርነት በማዘጋጀቱ ታላቅ ኩራትና ክብር ይሰማዋል።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሀገር ታወቀ !

በትላንትናው ዕለት ጅማሮውን ያደረገው የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ውድድር የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሀገር ቻይና መሆን ችላለች።

በመጀመሪያው የፓሪስ ኦሎምፒክ ቀን ውሎ ቻይና በ10 ሜትር የጠመንጃ አልሞ መምታት የቡድን ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆናለች።

ቻይና ደቡብ ኮሪያን 16 ለ 12 በሆነ ድምር ውጤት በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያው ባለቤት መሆን እንደቻለች ተገልጿል።

እንዲሁም ደቡብ ኮርያ የብር ካዛኪስታን የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በዛሬው ዕለት በፓሪስ ኦሎምፒክ ሜዳሊያ የሚያስገኙ የዳይቪንግ ፣ የብስክሌት ፣ የጁዶ ፣ የስኬትቦርዲንግ ፣ የራግቢ እና የዋና ውድድሮች እንደሚኖሩ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤንድሪክ በይፋ ማድሪድን ተቀላቅሏል !

ሪያል ማድሪዶች ከፓልሜራስ ላስፈረሙት ብራዚላዊው የፊት መስመር አጥቂ ኤንድሪክ ይፋዊ አቀባበል እያደረጉ ሲሆን ተጨዋቹ ውሉን መፈረሙ ተገልጿል።

የ 18ዓመቱ ኤንድሪክ በክለቡ የህክምና ምርመራውን በማድረግ የሎስ ብላንኮዎቹ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ በተገኙበት የስድስት አመት ኮንትራት ፈርሟል።

በተጨማሪም ተጨዋቹ በሪያል ማድሪድ ቤት አስራ ስድስት ቁጥር ማልያን እንደሚለብስ ይፋ ተደርጓል።

ሪያል ማድሪድ ከሰዓታት በኃላ በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም የክለቡ ደጋፊዎች በተገኙበት ለኤንድሪክ ይፋዊ አቀባበል ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእስራኤል አትሌቶች ማስፈራሪያ ደረሳቸው !

የእስራኤል መንግስት የኢራን አሸባሪዎች በእስራኤል አትሌቶች ላይ ጥቃት ያደርሳሉ የሚል ትልቅ ስጋት እንዳለው ለፈረንሳይ መንግስት በይፋ ማሳወቁ ተገልጿል።

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ ጥቃቱ መረጃ እንዳለው ለፈረንሳይ አቻው በፃፈው ደብዳቤ ማሳወቁ ተዘግቧል።

የኦሎምፒክ ውድድራቸውን ለማድረግ ፓሪስ የሚገኙ የእስራኤል አትሌቶች የኢሜል እና ስልክ ማስፈራሪያዎች እየደረሷቸው እንደሆነ ተገልጿል።

ኢራን በቅርቡ የእስራኤልን የኦሎምፒክ ተሳትፎ በመቃወም “ እስራኤል በጋዛ ንፁሃንን እየገደለች ነው በፓሪስ በሚካሄደው ውድድር መሳተፍ የለባትም “ ብላ ነበር።

ሀገሪቱ የእስራኤልን በኦሎምፒክ መሳተፍ ባወገዘችበት መግለጫዋ “ የአፓርታይድ ሽብርተኛውን አገዛዝ አትሌቶችን መቀበልና መጠበቅ ማለት የህፃናትን ግድያ ህጋዊ ማድረግ ነው" ማለቷ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኤንድሪክ በይፋ ማድሪድን ተቀላቅሏል ! ሪያል ማድሪዶች ከፓልሜራስ ላስፈረሙት ብራዚላዊው የፊት መስመር አጥቂ ኤንድሪክ ይፋዊ አቀባበል እያደረጉ ሲሆን ተጨዋቹ ውሉን መፈረሙ ተገልጿል። የ 18ዓመቱ ኤንድሪክ በክለቡ የህክምና ምርመራውን በማድረግ የሎስ ብላንኮዎቹ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ በተገኙበት የስድስት አመት ኮንትራት ፈርሟል። በተጨማሪም ተጨዋቹ በሪያል ማድሪድ ቤት አስራ ስድስት ቁጥር…
" እዚህ መሆን ህልሜ ነበር " ኤንድሪክ

ሎስ ብላንኮዎቹ ለብራዚላዊው ወጣት የፊት መስመር ተጨዋቻቸው ኤንድሪክ በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም በደጋፊዎቻቸው ፊት ይፋዊ አቀባበል አድርገውለታል።

" እዚህ መሆን የሁልጊዜ ህልሜ ነበር " ሲል በአቀባበሉ ላይ የተናገረው ኤንድሪክ ለሪያል ማድሪድ መጫወት ሁልጊዜ ስመኘው ነበር የሚሰማኝን ስሜት መግለጽ አልችልም “ ብሏል።

" ወደ አዲሱ ቤትህ እንኳን ደህና መጣህ " በማለት የተናገሩት የክለቡ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ በበኩላቸው የመጣኸው ከምናከብረው ሀገር ብራዚል ነው ብራዚላዊ ተጨዋቾቻችን ስለ ማድሪድ እንደነገሩህ አልጠራጠርም ብለዋል።

የኤንድሪክን ይፋዊ አቀባበል ስነ ስርዓት 43,000 የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች እንዲታደሙ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
አርጀንቲና ያቀረበችው ቅሬታ ተቀባይነት አላገኘም !

የአርጀንቲና ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን ከቀናት በፊት ከሞሮኮ አቻው ጋር ባደረገው ጨዋታ ጋር በተያያዘ ያቀረበው ቅሬታ በፊፋ ውድቅ መደረጉ ተገልጿል።

አርጀንቲና በጨዋታው ከሁለት ሰዓታት በኋላ ግቧ ከጨዋታ ውጪ በሚል በመሸሩ እንዱሁም ሌሎች ቅሬታዎችን ለፊፋ አስገብታ ነበር።

አርጀንቲና ከደቂቃዎች በኋላ ሁለተኛ የኦሎምፒክ የምድብ ጨዋታዋን ከኢራቅ ጋር የምታደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

የአለምአቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ቶማስ ባህ የደቡብ ኮርያውን ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዬኦልን በቀጥታ ለማነጋገር ማሰባቸው ተገልጿል።

በትላንቱ የኦሎምፒክ መክፈቻ ስነ ስርዓት የደቡብ ኮርያ ብሔራዊ ልዑክ የሰሜን ኮርያ ልዑክ በሚል በቀጥታ መተዋወቁን ተከትሎ ከፍተኛ ተቃውሞ መቅረቡ ይታወሳል።

አለምአቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ለተፈጠረው ስህተት በደቡብ ኮርያ ብሔራዊ ቋንቋ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ደቡብ ኮርያን ይቅርታ ጠይቋል።

በተጨማሪም የአለምአቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ቶማስ ባህ የደቡብ ኮርያውን ፕሬዝዳንት በቀጥታ ስልክ በመደወል ይቅርታ ለመጠየቅ እና ለማነጋገር ማቀዳቸው ተነግሯል።

የደቡብ ኮርያ ስፖርት ሚኒስቴር በበኩሉ በተፈጠረው ስህተት ሀገሪቱ ማዘኗን ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አስታወቆ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

በዛሬው ዕለት ጅማሮውን ባደረገው የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በመጀመሪያው ቀን ውሎ አስራ ሶስት የወርቅ ሜዳልያዎች ለውድድር አሸናፊዎች እንደሚበረከቱ ተገልጿል።

የሀገሪቱ የፈጣን ባቡር መስመር ትላንት ጥቃት የተፈፀመበት መሆኑን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ
አትሌቶች በጀልባ ለመጓጓዝ መገደዳቸው ተነግሯል።

ቻይና የመጀመሪያውን የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሀገር መሆን ችላለች።

በዛሬው ዕለት በዋና #አራት ፣ በብስክሌት ፣ ፌንሲንግ ፣ ጁዶ ለእያንዳንዳቸው #ሁለት እንዲሁም በዳይቪንግ ፣ ራግቢ እና ሹቲንግ ለእያንዳንዳቸው #አንድ የወርቅ ሜዳልያ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🎁 በተወዳጆቹ ሜጋ ጥቅሎች በሽ በሽ እንበል! ለ90 እና ለ180 ቀን የሚቆዩትን ልዩ የኢንተርኔት ጥቅሎች በM-PESA በመግዛት እስከ 500 ብር የሚደርስ ቅናሽ አግኝተን ፏ እንበል! 🌐🤳 ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት!

🤖 የቴሌግራም ቦታችንን https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!
  
🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ: https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
ስፔን ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀለች !

በ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ እግርኳስ ውድድር የስፔን ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን የምድብ ሁለት ጨዋታዎችን በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜ መድረሱን አረጋግጧል።

ስፔን ዛሬ ከዶምኒካን ሪፐብሊክ ጋር ያደረገችውን የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።

የአርጀንቲና ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ከኢራቅ አቻው ጋር ያደረገውን የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ 3ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 23:16:38
Back to Top
HTML Embed Code: