Telegram Web Link
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 ዋናው × ኬሮድ ሩጫ × ሳሬም ጂም 🇪🇹

🏃🏾‍♂ ታላቁ የኬሮድ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ! 🏃🏾‍♀

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የኦሎምፒክ መክፈቻ ዝግጅት የእምነት ተቋማትን አስቆጣ !

ከቀናት በፊት አርብ ምሽት የተካሄደው የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር መክፈቻ ስነ ስርዓት ብዙ የእምነት ተቋማትን ማስቆጣቱ ተገልጿል።

በመክፈቻ ዝግጅቱ ላይ የቀረበው ትዕይንት " የክርስትና እምነት ላይ ያፌዘ እና ክብረ ነክ ነው " በሚል የእምነቱን አባቶች ጨምሮ የሀገራት መሪዎችን አስቆጥቷል።

በዝግጅቱ ላይ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ " የኢየሱስ የመጨረሻው እራት " በሚል የሚታወቀው ስዕለ አድኖ ያለአግባብ ቀርቧል በሚል ቅሬታ እንደቀረበ ተገልጿል።

በአሜሪካ የሚገኙ የግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች ባወጡት ይፋዊ መግለጫ ኦሎምፒክ ኮሚቴን የወቀሱ ሲሆን ኮሚቴው ይቅርታ እንዲጠይቅም በመግለጫቸው ጠይቀዋል።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የፈረንሳይ ጳጳሳት ጉባኤ በበኩሉ በድርጊቱ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ “ ይህ ስነ ስርዓት በሚያሳዝን ሁኔታ በክርስትና ላይ የሚሳለቁ እና በጣም የምንጸየፋቸውን ትዕይንቶችን አካትቷል” ብሏል።

እንደ ሮይተርስ ዘገባ በአውሮፓ እና አሜሪካ የሚገኙ የቀኝ አክራሪ ፖለቲከኞች በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ድርጊቱን አውግዘዋል። 

አሜሪካዊ ቢልየነር ኤለን መስክ በሰጠው አስተያየት " ድርጊቱ ለክርስቲያኖች አክብሮት የጎደለው ነው " በማለት ትችቱን አቅርቧል። 

ጣልያናዊው ፖለቲከኛ ማትዮ ሳልቪኒ በበኩላቸው “ በዓለም ላይ ያሉ በቢልዮን የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን በማንቋሸሽ ኦሎምፒክን መክፈት በእውነት በጣም መጥፎ  ጅምር ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጠው የመክፈቻ ዝግጅቱ ዳይሬክተር ቶማስ ጆሊ " ለማሾፍ አላሰብኩም ነበር " ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

“ ለማስተላለፍ የፈለግኩት የተለየ መልዕክት አልነበረኝም ፣ ፈረንሳይ ውስጥ የምንፈልገውን መውደድ እና አማኝ ያለመሆን መብት አለን እንዲሁም ብዙ መብቶች አሉን ማስተላለፍ የፈለግኩት ይህንን ነው “ ቶማስ ጆሊ

የፓሪስ ኦሎምፒክ መክፈቻ ዝግጅት ከተደረገ ሁለት ቀናት ቢሆኑትም የአለም ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ምንም አይነት ምላሽ አልሰጡም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ደቡብ ሱዳን ውድድሯን በድል ጀመረች !

የበርካቶችን አድናቆት እያገኘ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ቅርጫት ኳስ ብሔራዊ ቡድን የኦሎምፒክ ውድድሩን ከደቂቃዎች በፊት አድርጎ በአሸናፊነት አጠናቋል።

የመጀመሪያ ምድብ ጨዋታውን ከፑኤርቶ ሪኮ አቻው ጋር ያደረገው የደቡብ ሱዳን ቅርጫት ኳስ ቡድን 90ለ79 በማሸነፍ ምድቡን መምራት ጀምሯል።

በ2023 የአፍሪካ ምርጥ የቅርጫት ኳስ ቡድን በመሆን ያጠናቀቀው የደቡብ ሱዳን ቅርጫት ኳስ ቡድን የመጀመሪያ የኦሎምፒክ ተሳትፎውን በማድረግ ላይ ይገኛል።

እ.ኤ.አ ከ1996 ወዲህ የአፍሪካ ቅርጫት ኳስ ብሔራዊ ቡድን የኦሎምፒክ ጨዋታ ሲያሸንፍ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

የደቡብ ሱዳን ቅርጫት ኳስ ቡድን በቀጣይ የኦሎምፒክ ሩብ ፍፃሜውን የሚቀላቀል ከሆነ በታሪክ የመጀመሪያው የአፍሪካ ቅርጫት ኳስ ብሔራዊ ቡድን ይሆናል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከሳምንታት በፊት ኦሎምፒክን ደጋግማ በማሸነፍ ከምትታወቀው አሜሪካ ጋር ባደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያሳየው አስደናቂ ፉክክር የብዙዎችን ቀልብ መሳቡ ይታወሳል።

በጨዋታው ደቡብ ሱዳን ድንቅ የሚባል ፉክክር ስታደርግ በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረባት ነጥብ በአሜሪካ 101-100 ነበር የተሸነፈችው።

ደቡብ ሱዳን በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በምድብ ሶስት ከውድድሩ የ16 ጊዜ ወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ አሜሪካ ፣ ሰርቢያ እና ፑኤርቶ ሪኮ ጋር ተደልድላለች።

የደቡብ ሱዳን ቅርጫት ኳስ ቡድን ሁለተኛ ጨዋታውን የፊታችን እሮብ ከአሜሪካ አቻው ጋር ረፋድ 4:00 ሰዓት የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፊፋ ካናዳ ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳለፈ ! የአለም እግርኳስ የበላይ ፊፋ የካናዳ ሴቶች እግርኳስ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ቤቭ ፕሬስትማን ለአንድ አመት ከእግርኳስ ማገዱን አስታውቋል። በተጨማሪም የካናዳ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን ስድስት ነጥቦች እንዲቀነሱበት እና 200,000 የስዊዝ ፍራንክ እንዲከፍል የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን ይፋ አድርጓል። ፊፋ ቅጣቱን ያሳለፈው ካናዳ ከቀናት በፊት ተጋጣሚዋ…
የካናዳ መንግሥት ለእግርኳስ የሚሰጠውን ገንዘብ ያቋርጣል !

የካናዳ መንግሥት ከሰሞኑ ከፊፋ በሴቶች ብሔራዊ ቡድን ላይ የተላለፈውን ቅጣት ተከትሎ ለሀገሪቱ እግርኳስ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያቋርጥ አሳውቋል።

በኦሎምፒክ እየተሳተፈ የሚገኘው የካናዳ ሴት ብሔራዊ ቡድን ተጋጣሚውን በመሰለል ክስ ቀርቦበት የስድስት ነጥቦች ቅነሳ እንዲሁም የአሰልጣኞች የአንድ አመት እግድ ቅጣት እንደተጣለበት ይታወቃል።

የሀገሪቱ ስፖርት ሚኒስቴር ካርላ ኳልትሩፍ በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት " መንግሥት ለእግርኳስ የሚያደርገውን ድጋፍ ቅጣቱ እስከሚያልቅ ይቋረጣል " ብለዋል።

የሀገሪቱ ስፖርት ሚኒስቴር አክለውም በካናዳ እግርኳስ ውስጥ አሳሳቢ የሆነ ስርዓት አልበኝነት ተንሰራፍቷል ሲሉ ተችተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
  🆕 አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

📌 https://www.tg-me.com/sellphone2777

📞  0929008292

📩 inbox @bina27

📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
TIKVAH-SPORT
ደቡብ ሱዳን ውድድሯን በድል ጀመረች ! የበርካቶችን አድናቆት እያገኘ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ቅርጫት ኳስ ብሔራዊ ቡድን የኦሎምፒክ ውድድሩን ከደቂቃዎች በፊት አድርጎ በአሸናፊነት አጠናቋል። የመጀመሪያ ምድብ ጨዋታውን ከፑኤርቶ ሪኮ አቻው ጋር ያደረገው የደቡብ ሱዳን ቅርጫት ኳስ ቡድን 90ለ79 በማሸነፍ ምድቡን መምራት ጀምሯል። በ2023 የአፍሪካ ምርጥ የቅርጫት ኳስ ቡድን በመሆን ያጠናቀቀው የደቡብ…
የደቡብ ሱዳን ተጨዋቾች ቅር መሰኘታቸውን ገለጹ !

የደቡብ ሱዳን ቅርጫት ኳስ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ቅሬታቸውን ያሰሙት ከዛሬው የኦሎምፒክ ጨዋታ አስቀድሞ በስህተት የሱዳን ብሔራዊ መዝሙር በመከፈቱ መሆኑ ተገልጿል።

የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋች ማጆክ ዴንግ በሰጠው አስተያየት " ይህ የአለም ትልቁ መድረክ ነው የተሻለ መሆን ይገባቸዋል ፣ ይህ ክብር የሚነካ ነው ጥሩ ስሜት አልተሰማንም " ሲል ተደምጧል።

የጨዋታው አዘጋጆች ባወጡት ይፋዊ መግለጫ " የስህተቱን ክብደት በሚገባ በመረዳት ለተፈጠረው የግለሰብ ስህተት ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን ስህተቱ በፍጥነት ታርሞ ትክክለኛው ተካሂዷል በድጋሜ አይከሰትም " ብለዋል።

ደቡብ ሱዳን እ.ኤ.አ 2011 ራስ ገዝ ሀገር መሆኗን ማረጋገጧ የሚታወስ ሲሆን ሀገሪቱ በ2016 የመጀመሪያ የኦሎምፒክ ውድድር ተሳትፎዋን ማድረግ ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ራፋኤል ናዳል በነጠላ ሜዳ ቴኒስ ባለድል ሆነ !

ስመ ጥሩ ስፔናዊ የሜዳ ቴኒስ ተጨዋች ራፋኤል ናዳል ከደቂቃዎች በፊት ባደረገው የነጠላ ሜዳ ቴኒስ ውድድር ሀንጋራዊውን ማርተን ፉሶቪችስ በመርታት ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል።

መጠነኛ ጉዳት እንዳለበት ሲነገር የነበረው ራፋኤል ናዳል ከማርተን ፉሶቪችስን ጋር ያደረጉት ጨዋታ 6-1 ፣ 4-6 እና 6-4 ተጠናቋል።

የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ አሸናፊው ራፋኤል ናዳል በሁለተኛው ዙር ከሰርቢያዊው ኖቫክ ጆኮቪች ጋር ተጠባቂ ፍልሚያውን ያደርጋል።

ራፋኤል ናዳል ትላንት ምሽት ከካርሎስ አልካራዝ ጋር የተጣመረበትን የቡድን የሜዳ ቴኒስ ውድድር በአሸናፊነት መወጣታቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሰራተኞች ሲቀነሱ ማየት ከባድ ነው " ጆኒ ኢቫንስ

የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ጆኒ ኢቫንስ ክለቡ በቀጣይ በርካታ ሰራተኞችን ለመቀነስ የጀመረውን እንቅስቃሴ " ለማየት ከባድ የሆነ " ሲል ገልፆታል።

ማንችስተር ዩናይትድ ወጪውን ለመቀነስ በሚል ከ250 በላይ የሚሆኑ የክለቡን ሰራተኞች ለመቀነስ እንዳሰበ መግለፁ አይዘነጋም።

በማንችስተር ዩናይትድ ቤት በርካታ አመታትን ያሳለፈው ጆኒ ኢቫንስ የክለቡን ውሳኔ " ለማየት ከባድ ነው " ሲል የገለፀ ሲሆን በርካታ ሰዎች ስራቸውን ሲያጡ መመልከት ከባድ ሆኖብኛል ብሏል።

“ የክለቡ ባለቤቶች የሚሄዱበት መንገድ ጥሩ መሆኑን ያስባሉ በተመሳሳይ ሰዓት ደግሞ ለሁሉም ሰው ቀላል አልነበረም “ ሲል ጆኒ ኢቫንስ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሂጃብ መልበስ የሃይማኖቴ አካል ነው በመልበሴም እኮራለሁ "

አውስትራሊያዊቷ ቦክሰኛ ቲና ራሂሚ ፈረንሳይ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ሴት አትሌቶቿ ሂጃብ እንዳይለብሱ ያደረገችውን ክልከላ በይፋ ተቃውማለች።

ፈረንሳይ በኦሎምፒክ ውድድር የሚሳተፉ ሁሉም አትሌቶቿ ሃይማኖትን የሚያንፀባርቁ ነገሮችን እንዳይጠቀሙ መከልከሏ ተገልጿል።

“ ሴቶች መልበስ የሚፈልጉትን መርጠው የመልበስ መብት አላቸው “ ስትል የገለፀችው ቲና ራሂሚ “ ሂጃብ መልበስ የሃይማኖቴ አካል ነው በመልበሴም እኮራለሁ " ብላለች።

ቲና ራሂሚ አውስትራሊያን በቦክስ ስፖርት በኦሎምፒክ ውድድር የወከለች የመጀመሪያዋ የእስልምና እምነት ተከታይ ቦክሰኛ መሆኗ ተገልጿል።

“ ከሃይማኖት እና ከስፖርት እንድትመርጥ መገደድ ተገቢ አይደለም “ ስትል አክላ የገለፀችው አትሌቷ “ የፈረንሳይ አትሌቶች ላይ የሚደረገው ይህ ነው “ ብላለች።

ሀገሪቱ ሂጃብን ጨምሮ ያሳለፈቻቸው ሌሎች ክልከላዎች ለራሷ አትሌቶች ብቻ መሆኑ እና በኦሎምፒክ ውድድር ለመሳተፍ የመጡ የሌሎች ሀገራት አትሌቶችን እንደማይመለከት ተነግሯል።

በቅርቡ አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ አለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በጋራ እገዳውን አውግዘው አለምአቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጣልቃ ግብቶ እንዲያስቆም አሳስበው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፊፋ ካናዳ ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳለፈ ! የአለም እግርኳስ የበላይ ፊፋ የካናዳ ሴቶች እግርኳስ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ቤቭ ፕሬስትማን ለአንድ አመት ከእግርኳስ ማገዱን አስታውቋል። በተጨማሪም የካናዳ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን ስድስት ነጥቦች እንዲቀነሱበት እና 200,000 የስዊዝ ፍራንክ እንዲከፍል የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን ይፋ አድርጓል። ፊፋ ቅጣቱን ያሳለፈው ካናዳ ከቀናት በፊት ተጋጣሚዋ…
ካናዳ አሰልጣኟ ይቅርታ ጠይቀዋል !

የተጋጣሚ ቡድን ልምምድን በድሮን ለመሰለል በመሞከር በፊፋ እና በካናዳ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እገዳ የተጣለባቸው አሰልጣኝ ቤቭ ፕሬስትማን በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል።

“ ካናዳን ይቅርታ እጠይቃለሁ የቡድኑ መሪ እንደመሆኔ ለጉዳዩ ሃላፊነት መውሰድ እፈልጋለሁ “ ያሉት አሰልጣኝ ቤቭ ፕሬስትማን በጉዳዩ ላይ እየተደረገ ባለው ምርመራ ውስጥ እተባበራለሁ ብለዋል።

እንግሊዛዊቷ አሰልጣኝ ቤቭ ፕሬስትማን አክለውም “ አሁን ላይ ብዙ መናገር ብፈልግም ምርመራውን እና የይግባኝ አቤቱታውን ላለማደናቀፍ ዝምታን እመርጣለሁ “ ሲሉ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ቤቭ ፕሬስትማን ከድሮን ስለላው ጋር በተያያዘ በፊፋ የአንድ አመት ቅጣት እንደተጣለባቸው ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ራፋኤል ቫራን ወደ ኮሞ ? በቅርቡ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የተለያየው ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን ጣልያኑን ክለብ ኮሞ ለመቀላቀል በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል። ራፋኤል ቫራን አሁን ላይ ከክለቡ ቦርድ እና ከክለቡ አሰልጣኝ ሴስክ ቫብሬጋስ ጋር ለመነጋገር ወደ ጣልያን ኮሞ ማምራቱ ተነግሯል። በዚህ አመት ወደ ጣልያን ሴርያ ማደጉን ያረጋገጠውን የአሰልጣኝ ሴስክ ቫብሬጋሱ…
ራፋኤል ቫራን በይፋ ኮሞን ተቀላቀለ !

በቅርቡ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የተለያየው ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን የጣልያኑን ክለብ ኮሞ በይፋ ተቀላቅሏል።

ራፋኤል ቫራን በኮሞ ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የሁለት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

የ 31ዓመቱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን የጣልያን ሴርያ በእግርኳስ ህይወቱ የተጫወተበት አራተኛ ሊጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ለጃፓናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዋታሩ ኢንዶ ከማርሴይ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተገልጿል።

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኘው የፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ ለዋታሩ ኢንዶ 14 ሚልዮን ዩሮ አቅርበው እንደነበር ተነግሯል ።

በተጨማሪም በርካታ የጀርመን ክለቦች ተጫዋቹን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ሲገለፅ ሊቨርፑል በበኩሉ የመሸጥ ፍላጎት እንደሌለው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቨርቹዋል ጨዋታዎች የሚጨበጡ ሽልማቶች, ዳጎስ ያሉ የገንዘብ ሽልማቶችን በቤቲካ ቨርቹዋል!
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
TIKVAH-SPORT
የኦሎምፒክ መክፈቻ ዝግጅት የእምነት ተቋማትን አስቆጣ ! ከቀናት በፊት አርብ ምሽት የተካሄደው የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር መክፈቻ ስነ ስርዓት ብዙ የእምነት ተቋማትን ማስቆጣቱ ተገልጿል። በመክፈቻ ዝግጅቱ ላይ የቀረበው ትዕይንት " የክርስትና እምነት ላይ ያፌዘ እና ክብረ ነክ ነው " በሚል የእምነቱን አባቶች ጨምሮ የሀገራት መሪዎችን አስቆጥቷል። በዝግጅቱ ላይ በክርስትና እምነት ተከታዮች…
ኦሎምፒክ ኮሚቴ በይፋ ይቅርታ ጠየቀ !

የ 2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ከውድደደሩ የመክፈቻ ፕሮግራም ጋር ተያይዞ ለተነሱ ከፍተኛ ቅሬታዎች ይቅርታ ጠይቋል።

ባወጣው መግለጫም " የትኛውንም የእምነት ተቋም ዝቅ አድርጎ የማሳየት ፍላጎት የለንም ፣ የመክፈቻው ዝግጅት የማህበረሰቡን መቻቻል ለማሳየት ሞክሯል " ይላል።

"ይህን አላማችንን አሳክተናል ብለን እናምናለን ፣ በድርጊቱ ለተከፉ ሁሉ ይቅርታ እንጠይቃለን " ማለታቸው በመግለጫው ታይቷል።

የፓሪስ ኦሎምፒክ ቃል አቀባይ የሆኑት አና ዴሻምፕ በጋዜጣዊ መግለጫቸው እንደተናገሩት በተሰበሰበ ድምፅ 86% የሚሆነው ፈረንሳዊ የመክፈቻ ዝግጅቱ ስኬታማ ነው ማለቱን ገልፀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

ሶስተኛ ቀኑን የያዘው የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በዛሬው ዕለት ሲቀጥል ዛሬ አስራ ዘጠኝ የወርቅ ሜዳልያዎች ለአሸናፊዎች ይበረከታሉ።

በሁለተኛው ቀን ውሎ ጃፓን የወርቅ ሜዳልያ ቁጥሯን ወደ አራት ከፍ በማድረግ የሜዳልያ ሰንጠረዡን በበላይነት እየመራች ማጠናቀቅ ችላለች።

አውስትራሊያ በተመሳሳይ አራት የወርቅ ሜዳልያ ስታሳካ በሌሎች ሜዳልያዎች ተበልጣ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

በሜዳልያ ብዛት አሜሪካ አጠቃላይ አስራ ሁለት ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ ቀዳሚ መሆን ችላለች።

በዛሬው ዕለት በሹቲንግ ፣ ዳይቪንግ ፣ የፈረስ ግልቢያ ፣ ብስክሌት ፣ ጁዶ ፣ ስኬትቦርዲንግ ፣ ቀስት ፣ ጂምናስቲክ ፣ ታንኳ ፣ ዋና እና ፌንሲንግ ለሜዳልያ የሚደረጉ ውድድሮች ናቸው።

ወቅታዊ የሜዳልያ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ጃፓን :-🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥉

2️⃣ አውስትራሊያ :- 🥇🥇🥇🥇🥈🥈

3️⃣ አሜሪካ :- 🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥉🥉🥉 

4️⃣ ፈረንሳይ :-🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥉🥉

5️⃣ ደቡብ ኮርያ :-🥇🥇🥇🥈🥈🥉

6️⃣ ቻይና :-🥇🥇🥇🥈🥉🥉

*የኢትዮጵያ ብሔራዊ ልዑክ ቡድን ሐሙስ ውድድሩን ማድረግ ይጀመራል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ግዙፍ ስታዲየም መገንባት ይፈልጋል !

ማንችስተር ዩናይትድ አዲስ ስታዲየም ለመገንባት የመጨረሻ ውሳኔ የሚደርሱ ከሆነ ግዙፍ ስታዲየም መገንባት እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

ኦልድትራፎርድ ስታዲየምን ለማደስ ወይም አዲስ ለመገንባት በማሰብ ላይ የሚገኙት ቀያዮቹ ሴጣኖች አዲስ ከሰሩ 100,000 ተመልካች ማስተናገድ የሚችል ለማድረግ ማሰባቸው ተነግሯል።

ክለቡ 100,000 ተመልካቾች የመያዝ አቅም ያለው ስታዲየም ለመገንባት ያሰበው እየተስተዋለ የሚገኘውን ከፍተኛ የትኬት ፍላጎት ለማሟላት መሆኑ ተዘግቧል።

እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ ኦልድትራፎርድን ከማደስ ይልቅ ከአዲስ መገንባት እንደሚመርጡ ተነግሯል።

ክለቡ አዲስ የሚገነባ ከሆኑ በኦልድትራፎርድ አጠገብ በሚገኝ የመሬት ይዞታው ላይ እንደሚያደርግ እና ግንባታው እስኪጠናቀቅ ቡድኑ በኦልድትራፎርድ መጫወት እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

የስታዲየም ግንባታው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ስድስት አመታትን ሊወስድ እንደሚችል ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናይጄሪያ አዳራብዮ ለቡድኗ እንዲጫወት ጠይቃለች !

ናይጄሪያ በቅርቡ ከፉልሀም ቼልሲን የተቀላቀለው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቹ ቶሲን አዳራብዮ ለብሔራዊ ቡድኗ እንዲጫወት ለማሳመን በመጣር ላይ መሆኗ ተገልጿል።

እንግሊዝ ውስጥ የተወለደው ተጨዋቹ እስካሁን በኢንተርናሽናል ደረጃ የወከለው የአዋቂዎች ብሔራዊ ቡድን እንደሌለ ተነግሯል።

ቶሲን አዳራብዮ ከዚህ በፊት ለሱፐር ኤግሎቹ እንዲጫወት ከናይጄርያ ሁለት ጊዜ ጥያቄ ቀርቦለት ሳይቀበል መቅረቱ ሲገለፅ ሀገሪቱ አሁንም ጥረቷን መቀጠሏ ታውቋል።

በተጨዋቹ በኩል እስካሁን መወከል የሚፈልገው ብሔራዊ ቡድን ዙሪያ ከውሳኔ እንዳልደረሰ አሳውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቪቶር ሮኪ የአል ሂላልን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

ብራዚላዊው የባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋች ቪቶር ሮኪ ከሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተገልጿል።

አል ሂላል አሁን ላይ ቪቶር ሮኪ ጥያቂያቸውን አለመቀበሉን ተከትሎ የአስቶን ቪላውን ተጨዋች ጆን ዱራን ለማስፈረም በመመልከት ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

ኮሎምቢያዊው የአስቶን ቪላ የፊት መስመር ተጨዋች ጂጆ ዱራን ዌስትሀም ዩናይትድን መቀላቀል እንደሚፈልግ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 23:28:28
Back to Top
HTML Embed Code: