Telegram Web Link
Forwarded from HEY Online Market
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Norrkoping - Djurgarden
Al Ittihad - Pyramids
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
" ከሜዳችን ውጪ መጫወት እመርጥ ነበር " ካይሴዶ

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሞይሰስ ካይሴዶ ባለፈው የውድድር አመት መጀመሪያ በሜዳቸው መጫወት አስቸጋሪ ሆኖባቸው እንደነበር ገልጿል።

ሞይሰስ ካይሴዶ በንግግሩም " መጀመሪያ አካባቢ በአቋማችን ምክንያት ከደጋፊዎች በሚደርስብን ጫና መጫወት ከብዶን ነበር ፣ በስታምፎርድ ብሪጅ ከመጫወት ይልቅ ከሜዳ ውጪ መጫወት እመርጥ ነበር " ሲል ተናግሯል።

" ብራይተን ውስጥ ሁሉም ነገር በታክቲክ ነው ቼልሲ ውስጥ ሁሉም ነገር መሮጥ እና መሮጥ ነበር ይህ በጣም ከብዶኝ ነበር ብራይተን ሁልጊዜም ኳስ ይቆጣጠር ነበር ቼልሲ ውስጥ የተለየ ነው።" ካይሴዶ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሞራታ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ሊያገል እንደሚችል ገለጸ !

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ሞራታ ከአውሮፓ ዋንጫው ውድድር በኋላ ራሱን ከብሔራዊ ቡድን ለማግለል ሊያስብ እንደሚችል ጠቁሟል።

" አሁን ላይ ኢንተርናሽናል ጨዋታ ስለማቆም ብዙም ማውራት አልፈልግም " ያለው ሞራታ ነገርግን ከአውሮፓ ዋንጫው በኋላ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ራሴን ላገል እችላለሁ ብሏል።

" ከስፔን ውጪ መጫወት ደስተኛ አድርጎኛል " የሚለው ተጨዋቹ ምክንያቱም እዚህ የሚያከብሩኝ ሰዎች አሉ ስፔን ውስጥ ለምንም ነገር እንዲሁም ለማንም ክብር የሚባል የለም ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የአማድ ዲያሎን ውል ማራዘም ይፈልጋል !

ማንችስተር ዩናይትድ የአይቮሪኮስታዊውን የፊት መስመር ተጨዋች አማድ ዲያሎ ኮንትራት የማራዘም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በተጨዋቹ እግርኳሳዊ አድገት ደስተኛ መሆናቸው ሲገለፅ በሚቀጥለው ወር ውሉን ለማራዘም ንግግር ይጀምራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

አማድ ዲያሎ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድን ውስጥ አስፈላጊ ከሚባሉ ተጨዋቾች መካከል አንዱ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኒኮ ዊሊያምስ ወደ ባርሴሎና ? የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ስፔናዊውን የአትሌቲክ ቢልባኦ የፊት መስመር ተጨዋች ኒኮ ዊሊያምስ የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል። ባርሴሎና በቀጣይ ለማስፈረም የሚፈልገውን አቅም ያለው ወጣት እና ወደፊት ታላቅ ተጨዋች መሆን የሚችል የክንፍ አጥቂ መስፈርት ኒኮ ዊሊያምስ እንደሚያሟላ ተነግሯል። ይሁን እንጂ ባርሴሎና ኒኮ ዊልያምስን ለማስፈረም በቀጣይ ያለባቸውን…
" ኒኮ ዊሊያምስን የማስፈረም አቅም አለን " ላፖርታ

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ ክለባቸው አሁን ላይ በአውሮፓ ዋንጫው ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኘውን ኒኮ ዊሊያምስ ማስፈረም እንደሚችል ገልጸዋል።

ኒኮ ዊሊያምስን በጣም አደንቀዋለሁ በማለት የገለፁት ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ " ባርሴሎና በአሁን ሰዓት እሱን የማስፈረም አቅም አለው " ብለዋል።

የ 21ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ኒኮ ዊሊያምስ በአትሌቲክ ቢልባኦ ቤት ያለው የውል ማፍረሻ 50 ሚልዮን ዩሮ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩናይትድ ምክትል አሰልጣኞች ካሪንግተን ተገኝተዋል !

የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን የአሰልጣኞች ቡድን እንደሚቀላቀሉ የሚጠበቁት የቀድሞ የክለቡ ታሪካዊ ተጨዋች ሩድ ቫን ኔስትሮይ እና አሰልጣኝ ሬኔ ሀኬ ዛሬ በክለቡ ልምምድ ማዕከል ተገኝተዋል።

ኔዘርላንዳዊው የቀድሞ የፊት መስመር ተጨዋች ሩድ ቫን ኔስትሮይ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት የሁለት አመት ውል መፈረሙ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ በተጨማሪም ኔዘርላንዳዊውን የጎ አሄድ ኤግልስ ዋና አሰልጣኝ ሬኔ ሀኬን በአሰልጣኞች ቡድን ውስጥ ለማካተት መስማማቱ ይታወቃል።

ማንችስተር ዩናይትድ ዛሬ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ልምምዱን እንደሚጀምር ተገልጿል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎችን እነማን ይመሩታል ?

ማክሰኞ እና እሮብ የሚደረጉ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎችን የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል።

ማክሰኞ ምሽት 4:00 በፈረንሳይ እና ስፔን መካከል የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ስሎቬኒያዊው የ 42ዓመት ዳኛ ስላቭኮ ቪንቺክ በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።

እንዲሁም እሮብ ምሽት 4:00 ሰዓት የሚደረገውን የእንግሊዝ እና ኔዘርላንድ ጨዋታ ጀርመናዊው ዳኛ ፌሊክስ ዝዋየር በመሀል ዳኝነት እንደሚመሩት ተገልጿል።

እነማን ለፍፃሜ ይደርሳሉ ?

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
" እዚህ የተገኘሁት ቡድኑ አቅም እንዳለው ስለማምን ነው " ማሬስካ

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የክለቡ ደጋፊዎች በቡድኑ እምነት እንዲኖራቸው እና ከጎኑ እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

" እዚህ የተገኘሁት ቡድኑ አቅም ባላቸው ተጨዋቾች እንደተሞላ ስለማምን ነው " ያሉት ኢንዞ ማሬስካ ቼልሲ በአለም ምርጡ ክለብ እንደሆነ አምናለሁ እዚህ ስለሆንኩ ኩራት ይሰማኛል ብለዋል።

የራሳቸው የሆነ የአጨዋወት መንገድ እና ስልት እንዳላቸው የጠቆሙት አሰልጣኙ የክለቡ ደጋፊዎች በሂደቱ እንዲያምኑ እና ከጎን እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
ሊቨርፑል የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ለተከላካዩ ናት ፊሊፕስ ከቱርኩ ክለብ ትራብዞንስፖር የቀረበለትን 4 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ውድቅ ማድረጋቸው ተገልጿል።

የ 27ዓመቱ የመሐል ተከላካይ ናት ፊሊፕስ በዚህ ክረምት ሊቨርፑልን እንደሚለቅ የሚጠበቅ ሲሆን ሊቨርፑል ለዝውውሩ እስከ 8 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

ተጫዋቹን ለማስፈረም በተጨማሪም በርንሌይን ጨምሮ በርካታ የሻምፒዮ ሺፕ ክለቦች ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
ግሪንውድ ካሪንግተን ተገኝቶ ተነጋግሯል !

አመቱን በውሰት በሄታፌ ያሳለፈው እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ዛሬ ካሪንግተን ልምምድ ማዕከል መገኘቱ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በክለቡ የተገኘው ልምምድ ለመስራት ሳይሆን በቀጣይ ክለቡን ስለሚለቅበት ሁኔታ ከክለቡ ሀላፊዎች ጋር በግልጽ ለመነጋገር መሆኑ ተዘግቧል።

ሜሰን ግሪንውድን በቀጣይ ለማስፈረም ማርሴይ እና ላዝዮ በንግግር ላይ መሆናቸው ሲገለፅ ማርሴይ ዝውውሩን ለመፈፀም የተሻለ እድል እንዳለው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎችን እነማን ይመሩታል ? ማክሰኞ እና እሮብ የሚደረጉ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎችን የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል። ማክሰኞ ምሽት 4:00 በፈረንሳይ እና ስፔን መካከል የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ስሎቬኒያዊው የ 42ዓመት ዳኛ ስላቭኮ ቪንቺክ በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል። እንዲሁም እሮብ ምሽት 4:00 ሰዓት የሚደረገውን የእንግሊዝ እና ኔዘርላንድ ጨዋታ ጀርመናዊው…
#EURO2024

እንግሊዝ ከ ኔዘርላንድ ጋር የሚያደርጉትን የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ጀርመናዊው ዳኛ ፌሊክስ ዝዋየር በመሀል ዳኝነት እንዲመሩት ተመርጠዋል።

ዋና ዳኛው ፌሊክስ ዝዋየር ከዚህ በፊት በጨዋታ ማጭበርበር ተከሰው ለስድስት ወራት ከዳኝነት ታግደውም እንደነበር ተገልጿል።

ዳኛው በወቅቱ ጉቦ መቀበላቸው ተረጋግጦ እንደነበር ሲገለፅ እንግሊዛዊው ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም በበኩሉ ጀርመን እያለ " ጨዋታ አጭበርባሪ " ሲል ጠርቷቸው እንደነበር ተዘግቧል።

በዚህ ምክንያት ዋና ዳኛው ለጨዋታው መመደብ ከእንግሊዝ መገናኛ ብዙሃን ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ማስነሳቱ እየተነገረ ይገኛል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 ልዩ ቅናሹ 1 ቀን ብቻ ቀረው!

📌 በቀሩት ሰዓታት በዋናው አዲስ የቴሌግራም ቦት የስፖርት ትጥቆችን በማዘዝ ልዩ የ5% ቅናሽን ያግኙ።

🤖 @WanawSportBot 🤖

👉🏾 #ዛሬውኑ እንዳያመልጥዎ፣ ይዘዙን!

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
" ለጨዋታው ብቁ እንደሆንኩ ይሰማኛል " ሉክ ሾው

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የመስመር ተጨዋች ሉክ ሾው በእሮቡ የኔዘርላንድ የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ብቁ እንደሆነ እንደሚሰማው ተናግሯል።

ባለፉት አራት ወራት አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንደነበር የገለፀው ሉክ ሾው " በእሮቡ የኔዘርላንድ ጨዋታ በቋሚነት ለመሰለፍ ብቁ እንደሆንኩ ይሰማኛል " ብሏል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በማንችስተር ዩናይትድ ስለመቆየታቸው አስተያየቱን የሰጠው ሾው " በመቆየቱ ሁሉም እንደተደሰተ አስባለሁ ፣ ብዙም አልተገረምኩም በየአመቱ ዋንጫ አሸንፏል በቀጣይ ብዙ እንደሚሆን አስባለሁ " ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አለምአቀፍ የኦሎምፒክ ደንቦች ተጥሰዋል " ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በቅርቡ በዝግ ባደረገው ምርጫ አለምአቀፍ ህጎችን መጣሱን በመግለፅ " ህግ መከበር አለበት " ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

በኦሎምፒክ ኮሚቴው ምክትል ፕሬዝዳንት ሆኖ የተመረጠው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ " የኦሎምፒክ ኮሚቴው መሪዎች ስራ መልቀቅ ከነበረብን ከሶስት አመታት በፊት በቶኪዮ ኦሎምፒክ አንድ ወርቅ ይዘን ስንመጣ ነበር " ብሏል።

አትሌት ኃይሌ ቀድሞም ሆነ አሁን የኦሎምፒክ ኮሚቴው ውስጥ ተመርጠሃል ሲሉኝ ለምን እና እንዴት ብዬ ጠይቄያለሁ ነገር ግን እንድታገለገል ነው የሚል ምላሽ ነው የተሰጠኝ ብሏል።

“ ህግ መከበር አለበት የዓለም አቀፉ ደንቦችም ተጥሰዋል” የሚለው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በቀጣይም በኦሎምፒክ ኮሚቴው ጉዳይ መሄድ እስካለብን ርቀት ድረስ እንሄዳለን " ብሏል፡፡

የፓሪሱ ኦሎምፒክ ሊደረግ በተቃረበበት ወቅት ይህንን ማንሳት ስፖርተኞች ላይ ተፅዕኖ ከመፍጠር ይልቅ ብልሹ አሰራሮችን ማጋለጥ ያነቃቃቸዋል የሚል እምነት እንዳለው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ጨምሮ ገልጿል።

ኮሚቴው ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ከሚደረጉ እርምጃዎች አንዱ ኦዲት ማስደረግ ነው ያለው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ  ሂደቱን በጠበቀ  እና ህግን በተከተለ መንገድ ደግሞ ምርጫ መከናወን ነበረበት ሲል አስረድቷል።

በምርጫው ከተሳተፉ አካላት መካከል የተቀመጡ መስፈርቶችን የማያሟሉ ይገኙበታል በማለት ፤ ስፖርት በፖለቲካ ተሳትፎ ባላቸው እና የስፖርት እውቀት በሌላቸው ሰዎች ሊመራ እንደማይገባ በማንሳት ይህንንም ልንፈትሽ ይገባል ብሏል።

ምንጭ - EBC

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ላሚን ያማልን ምቾት ለማሳጣት እንሞክራለን " ራብዮ

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ራብዮ በነገው የስፔን ጨዋታ ላሚን ያማልን ሜዳ ላይ ምቾት ለማሳጣት ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጿል።

አድሪያን ራብዮ በንግግሩም " ላሚን ያማል በጨዋታው ምቾት እንዳይሰማው ለማድረግ እንጥራለን ፣ ለፍፃሜ መጫወት የሚፈልግ ከሆነ ከዚህ በፊት ካደረገው የበለጠ ማድረግ አለበት።"ብሏል።

" ስፔን በውድድሩ የሚጫወተው ምርጥ ቡድን እንደሆነ አይተናል ፣ እነሱ ላይ ምን ማድረግ እንዳለብን እናውቃለን ፣ ተጋጣሚዎቻቸው በነፃነት እንዲጫወቱ ፈቅደውላቸው ነበር።" ራብዮ

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊቨርፑል ከግብ ጠባቂው ጋር ሊለያይ ነው ! ስፔናዊው የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ግብ ጠባቂ አድርያን ከአምስት አመታት በኋላ ክለቡን ሊለቅ መሆኑ ተገልጿል። የ 37ዓመቱ ግብ ጠባቂ አድሪያን ከሊቨርፑል ውሉን እንዲያራዝም ጥያቄ ቢቀርብለትም ለመልቀቅ ከውሳኔ መድረሱ ተዘግቧል። ግብ ጠባቂው በቀጣይ የቀድሞ ክለቡን ሪያል ቤቲስ ለመቀላቀል መቃረቡ ተነግሯል። በአሰልጣኝ አርኔ ስሎት የሚመራው ሊቨርፑል…
አድርያን ሪያል ቤቲስን በይፋ ተቀላቀለ !

ስፔናዊው ግብ ጠባቂ አድርያን ከአምስት አመታት በኋላ ሊቨርፑልን በመልቀቅ የቀድሞ ክለቡን ሪያል ቤቲስ መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

የ 37ዓመቱ ግብ ጠባቂ አድሪያን ከሊቨርፑል በነፃ ዝውውር ለሪያል ቤቲስ እስከ 2026 የሚያቆይ የሁለት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

ሊቨርፑል በሚቀጥለው የውድድር አመት ሶስተኛ ግብ ጠባቂ አድርገው ቪቴሽላቭ ጃሮስን ወደ ዋናው ቡድን የሚያሳድጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አሜሪካዊውን የአትላንታ ዩናይትድ ወጣት የግራ መስመር ተጨዋች ካሌብ ዊሌይ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ተጫዋቹን እስከ 2031 በሚቆይ የሰባት አመት ኮንትራት በ8.5 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተዘግቧል።

የ 19ዓመቱ የመስመር ተጨዋች ካሌብ ዊሌይ በቀጣይ የውድድር አመት በውሰት ወደ ስትራስቡርግ ሊያመራ እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሜሲ በነገው ጨዋታ ይሰለፋል " ስካሎኒ

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ሊዮኔል ሜሲ ለነገው የኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

ከመጠነኛ ጉዳት የተመለሰው ሊዮኔል ሜሲ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን የገለፁት አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ " በነገው ጨዋታ መሰለፍ ይችላል ዝግጁ ነው " ብለዋል።

አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ አያይዘውም በነገ ሌሊቱ ጨዋታ ሊዮኔል ሜሲ እና አንሄል ዲማርያ አንድ ላይ ተሰልፈው እንደሚጫወቱ ጠቁመዋል።

አርጀንቲና ነገ ሌሊት 9:00 ሰዓት የኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዋን ከካናዳ ጋር የምታደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማንችስተር ዩናይትድ የዝውውር ጥያቄ አቀረበ ! ማንችስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የመሐል ተከላካይ ጃሬድ ብራንዝዌት ለማስፈረም ለኤቨርተን ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። ቀያዮቹ ሴጣኖች ለ 21ዓመቱ ተጨዋች ጃሬድ ብራንዝዌት ዝውውር የመጀመሪያ 35 ሚልዮን ፓውንድ ማቅረባቸው ተነግሯል። የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን በበኩሉ የቀረበው የዝውውር ሒሳብ ከሚጠበቀው በታች ነው ብለው እንደሚያምኑ…
ዩናይትድ አዲስ የተሻሻለ የዝውውር ሒሳብ አቀረበ !

ማንችስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የመሐል ተከላካይ ጃሬድ ብራንዝዌት ለማስፈረም ለኤቨርተን አዲስ የተሻሻለ የዝውውር ሒሳብ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ለ 21ዓመቱ ተጨዋች ጃሬድ ብራንዝዌት ዝውውር አሻሽለው 45 እና ታይቶ የሚጨምር 5 ሚልዮን ፓውንድ ሒሳብ ማቅረባቸው ተነግሯል።

የዝውውር ሒሳቡ ኤቨርተን ከሚፈልገው ክፍያ ጋር እንደማይቀራረብ ሲገለፅ በቀጣይ ውድቅ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

ዩናይትድ ከሳምንታት በፊት ያቀረበውን 35 ሚልዮን ፓውንድ ውድቅ ያደረጉት ኤቨርተኖች ለተጨዋቹ ዝውውር እስከ 70 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚፈልጉ ተጠቁሟል።

ማንችስተር ዩናይትድ በዚህ ክረምት የተከላካይ ክፍሉን ለማጠናከር ማትያስ ዴሊትን እና ጃሬድ ብራንዝዌትን ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 18:20:13
Back to Top
HTML Embed Code: