Telegram Web Link
52 ' ቱርክ 1 - 0 ኔዘርላንድ

         አካይዲን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
70 ' ቱርክ 1 - 1 ኔዘርላንድ

         አካይዲን ዴ ቭሪጅ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
76 ' ቱርክ 1 - 2 ኔዘርላንድ

     አካይዲን     ዴ ቭሪጅ
ሙልዱር ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኔዘርላንድ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ !

በአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከቱርክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜ መድረስ ችለዋል።

የኔዘርላንድን የማሸነፊያ ግቦች ስቴፋን ዴ ቭሪጅ እና መርት ሙልዱር በራሱ መረብ ላይ ሲያስቆጥሩ ለቱርክ አካይዲን ከመረብ አሳርፏል።

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን በግማሽ ፍፃሜው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን እሮብ ምሽት 4:00 የሚገጥሙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
Forwarded from WANAW SPORT
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇹 WANAW 🤝 ESFNA 🇺🇸

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የተካሄደው 41ኛው ዓመታዊ የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ውብ ማሊያዎች!

ዋናው ስፖርት የዚህ ደማቅ ፌስቲቫል ይፋዊ ስፖንሰር እና ትጥቅ አቅራቢ በመሆኑ በድጋሚ የተሰማውን ኩራት ይገልፃል።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
" ለተመዘገበው ውጤት ሀላፊነት እወስዳለሁ "ዶሪቫል ጁኒየር

የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ከዩራጓይ ጋር ያደረገውን የኮፓ አሜሪካ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በመለያ ምት ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።

አርባ አንድ ጥፋቶች በተሰሩበት ጨዋታ ዩራጓይ ከአስራ ሶስት አመታት በኋላ ለኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ መድረስ ችለዋል።

ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዶሪቫል ጁኒየር " የተመዘገበው ውጤት የምንፈልገው አልነበረም።

ውጤቱን በመቀበል ሀላፊነቱን እወስዳለሁ ነገርግን ቡድኑ ሁሉም ሰው ቀድሞ ወደነበረበት ቦታ እንዲመለስ ይፈልጋል።"ሲሉ ተደምጠዋል።

የኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ማክሰኞ ሌሊት - አርጀንቲና ከ ካናዳ

እሮብ ሌሊት - ዩራጓይ ከ ኮሎምቢያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኢትዮጵያ  ቡና ይፋዊ አጋር የሆነው ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡናን  26ኛ የጨዋታ ቀን የዲጂታል መፅሄት ይዞ ቀርቧል።
በመፅሄቱ ላይ የዕለቱ ጨዋታን የተመለከቱና ሌሎች የተለያዩ መረጃዎች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

የጨዋታ መፅሄት ቁጥር 26
ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ ቡና
ዛሬ 09:00
መፅሄቱን ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጫኑ https://www.tg-me.com/betikaethiopia/5385
እንዲሁም QR ኮዱን ስካን ሲያደርጉ ቀጥታ ወደ መፅሔቱ ይወስድዎታል!
ለኢትዮጵያ ቡና ቤተሰቦች ማጋራትዎን እንዳይዘነጉ!
ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡና ይፋዊ አጋር
ጄደን ሳንቾ ወደ ዩናይትድ ልምምድ ሊመለስ ነው !

የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች በነገው እለት ሰኞ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ለማድረግ ካሪንግተን ልምምድ ማዕከል ሪፖርት እንደሚገኙ ተገልጿል።

በውሰት ለዶርትመንድ ሲጫወት የነበረው እና ከአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጋር ያለውን ችግር ያልፈታው ጄደን ሳንቾ ነገ ወደ ክለቡ መመለስ እንደሚጠበቅበት ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድን በቋሚ ዝውውር ለመልቀቅ ከሌሎች ክለቦች ጋር በንግግር ላይ የሚገኘው ሜሰን ግሪንውድ በበኩሉ የእረፍት ጊዜው እንደተራዘመለት ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ከቫን ዴ ቢክ ዝውውር ስንት ያገኛል ?

የማንችስተር ዩናይትዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዶኒ ቫን ዴቢክ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊውን የስፔን ክለብ ጂሮና ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ከተጨዋቹ ዝውውር 500,000 ዩሮ እንደሚቀበሉ ሲገለፅ በውሉ ውስጥ ታይቶ የሚጨምር እስከ አራት ሚልዮን ዩሮ የሚሆን ክፍያ እንደሚካተት ተነግሯል።

ኔዘርላንዳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዶኒ ቫን ዴቢክ ከአራት አመታት በፊት ከአያክስ በ35 ሚልዮን ፓውንድ ማንችስተር ዩናይትድን መቀላቀሉ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ባየር ሙኒክ ኦሊሴን ለማስፈረም ተስማማ ! የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የክሪስታል ፓላሱን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር በግል ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ከክሪስታል ፓላስ የቀረበለትን አዲስ ውል ውድቅ በማድረግ ባየር ሙኒክን ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል። የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ኦሊሴን…
ሚሼል ኦሊሴ ጀርመን ሙኒክ ደርሷል !

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ወደ ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ጀርመን ደርሷል።

የ 22ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ በሚቀጥሉት ሰዓታት የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ክሪስታል ፓላስን በመልቀቅ ለባየር ሙኒክ የአምስት አመት ኮንትራት ይፈርማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቶኒ ክሩስ ፔድሪን ይቅርታ ጠይቋል ! ጀርመናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ ትላንት በስፔን በተሸነፉበት ጨዋታ ፔድሪ ላይ ለሰራው ጥፋት በማህበራዊ ትስስር ገፁ ተጫዋቹን ይቅርታ ጠይቋል። " ፔድሪ ጉዳት እንዲያጋጥመው ሆንብዬ አስቤ አልነበረም ጥፋቱን የሰራሁት " ያለው ቶኒ ክሩስ ይቅርታ ማለት እና ቶሎ እንድትመለስ መመኘት እፈልጋለሁ አንተ ምርጥ ተጨዋች ነህ።"ሲል ተናግሯል። በጨዋታው ፔድሪ…
" የክሩስ ጥፋት በእግርኳስ የሚፈጠር ነገር ነው " ፔድሪ

ስፔናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፔድሪ ጀርመናዊው አማካይ ቶኒ ክሩስ ለሰራበት ከባድ ጥፋት ላቀረበለት የይቅርታ መልዕክት አመስግኗል።

ፔድሪ በንግግሩም " ቶኒ ክሩስ ለመልዕክትህ አመሰግናለሁ ይህ እግርኳስ ነው የሚፈጠር ነገር ነው ፣ የአንተ የእግርኳስ ህይወት እና ስኬት ለዘለዓለም ይኖራል " በማለት ተናግሯል።

ለብሔራዊ ቡድኑ ደጋፊዎች መልዕክት ያስተላለፈው ፔድሪ " ጀርመን የመጣሁት ለአውሮፓ ዋንጫው ነው ፣ አሁንም ባልጫወትም እስከመጨረሻው እዚህ እቆያለሁ ምክንያቱም ህልም አለን።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጆሽዋ ዚርክዜ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ? የጣልያኑ ክለብ ቦሎኛ ሀላፊ ሳርቶሪ ኔዘርላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ በዚህ ክረምት ክለቡን ይለቃል የሚል እምነት እንዳላቸው በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል። በኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን ለማስፈረም ከተወካዮቹ ጋር አሁን ላይ በንግግር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። የሴርያው ክለብ ኤስ ሚላን…
ዩናይትድ ጆሽዋ ዚርክዜን ለማስፈረም ተቃርበዋል !

ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ከቦሎኛ ለማስፈረም የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ ከተጨዋቹ ጋር በግል ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች የ 23ዓመቱን ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ለማስፈረም የውል ማፍረሻ ለመክፈል ወይም በአዳስ የዝውውር ሒሳብ ለመደራደር እየተወያዩ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቲያጎ አልካንትራ ጫማውን ሊሰቅል ነው !

በቅርቡ ከሊቨርፑል ጋር የተለያየው ስፔናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቲያጎ አልካንትራ ራሱን ከእግርኳስ አለም ለማግለል ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል።

ተደጋጋሚ ጉዳቶች ሲያጋጥሙት የነበረው የቀድሞ የባየር ሙኒክ ተጨዋች ቲያጎ አልካንትራ ጫማውን ለመስቀል መገደዱ ተዘግቧል።

ቲያጎ አልካንትራ አብዛኛውን የእግርኳስ ህይወቱን ያሳለፈው በባየር ሙኒክ ቤት ሲሆን በቆየባቸው ሰባት አመታት አስራ ሰባት ዋንጫዎችን አሳክቷል።

ቲያጎ አልካንትራ በተጫወተባቸው ባርሴሎና ፣ ባየር ሙኒክ እና ሊቨርፑል ምን አሳካ ?

7️⃣ ቡንደስሊጋ

4️⃣ ላሊጋ ፣ DFB ፖካል

2️⃣ ሻምፒየንስ ሊግ ፣ የአለም ክለቦች ዋንጫ ፣ DFL ሱፐር ካፕ

1️⃣ ኮፓ ዴ ላሬ ፣ ኤፌ ካፕ ፣ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ፣ ሱፐር ኮፓ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ ቡና ሻምፒዮን ሆኗል !

በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

የቡናማዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ዋሳዋ ጂኦፊሪ 2x በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ለጦና ንቦቹ አበባየሁ ሀጂሶ አስቆጥሯል።

ኢትዮጵያ ቡና ለአመታት ተቋርጦ በዚህ አመት የጀመረውን የኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር ለስድስተኛ ጊዜ ማሳካት ችለዋል።

ኢትዮጵያ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር የሚሳተፍ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በርካታ የኔዘርላንድ ደጋፊዎች ይጠበቃሉ !

የኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቡድን እሮብ ምሽት ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር በሚያደርገው የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በርካታ ደጋፊዎች እንደሚጠበቁ ተገልጿል።

በጨዋታው ከ 80,000 በላይ የኔዘርላንድስ ደጋፊዎች ጨዋታው ወደሚደረግበት ዶርትመንድ ከተማ ያመራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል።

ጨዋታው ከኔዘርላንድ ድንበር በቅርብ ርቀት ( 236 ኪ.ሜ ) ላይ በሚገኘው የጀርመኑ ዶርትመንድ ከተማ የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሚሼል ኦሊሴ ጀርመን ሙኒክ ደርሷል ! ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ወደ ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ጀርመን ደርሷል። የ 22ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ በሚቀጥሉት ሰዓታት የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ ተገልጿል። ተጨዋቹ ክሪስታል ፓላስን በመልቀቅ ለባየር ሙኒክ የአምስት አመት ኮንትራት ይፈርማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።…
ባየር ሙኒክ በይፋ ተጨዋች አስፈርመዋል !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኦሊሴ ከክሪስታል ፓላስ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ባየር ሙኒክ የ 22ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ኦሊሴ በአምስት አመት ኮንትራት 50 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ ሒሳብ ማስፈረማቸውን አስታውቀዋል።

" ለትልቅ ክለብ ልጫወት በመሆኑ ደስተኛ ነኝ ትልቅ ፈተና ነው ነገርግን ስፈልገው የነበረ ነው በዚህ ደረጃ ራሴን ማሳየት እፈልጋለሁ።" ሲል ኦሊሴ ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ከግብ ጠባቂው ጋር ሊለያይ ነው !

ስፔናዊው የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ግብ ጠባቂ አድርያን ከአምስት አመታት በኋላ ክለቡን ሊለቅ መሆኑ ተገልጿል።

የ 37ዓመቱ ግብ ጠባቂ አድሪያን ከሊቨርፑል ውሉን እንዲያራዝም ጥያቄ ቢቀርብለትም ለመልቀቅ ከውሳኔ መድረሱ ተዘግቧል።

ግብ ጠባቂው በቀጣይ የቀድሞ ክለቡን ሪያል ቤቲስ ለመቀላቀል መቃረቡ ተነግሯል።

በአሰልጣኝ አርኔ ስሎት የሚመራው ሊቨርፑል በሚቀጥለው የውድድር አመት ሶስተኛ ግብ ጠባቂ አድርገው ቪቴሽላቭ ጃሮስን ወደ ዋናው ቡድን እንደሚያሳድጉ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ግብ ጠባቂ ለማስፈረም አነጋግሯል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ ዳንኤል ቤንትሌይ ለማስፈረም ክለቡ ዎልቭስን ማነጋገራቸው ተገልጿል።

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት መድፈኞቹ ተጨዋቹ ለአርሰናል ጥሩ አማራጭ ግብ ጠባቂ ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸው ተነግሯል።

ዎልቭስ የ 31ዓመቱን ግብ ጠባቂ ዳንኤል ቤንትሌይ ስለመሸጥ የሚያስበው ጥሩ የሚባል የዝውውር ሒሳብ ከቀረበላቸው መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 20:35:03
Back to Top
HTML Embed Code: