Telegram Web Link
Audio
መልክአ ቅዱስ መርቆሬዎስ
Audio
ገድለ ቅዱስ አቡነ አቢብ
ጥቅምት 25 የአቡነ አቢብ ዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ነው።በዚች ቀን አምላከ አቡነ አቢብ ማረኝ (፫ ጊዜ) ብሎ በሠላም ለኪና በአቡነ በዘሰማያት ያሰውን የጸለየውን ኃጢአቱ ሁሉ ይሰረይለታል።በተሰጣቸው ቃል ኪዳን ልዑል እግዚአብሔር ይማረን። በረከታቸው ይደርብን።
🟢 🟡 🔴
ጥቅምት 25 | #አቡነ_አቢብ (አባ ቡላ) የዕረፍቱ በዓል ነው፨

ይህም ቅዱስ አባት፦

✦ ከቅዱሳን ቤተሰብ በጸሎት የተገኘ፥

✦ በተፀነሰ ዕለት ማንም ያልተከለው ዛፍ አደገና በዛፉ ላይ "ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ" የሚል ጽሑፍ የተገኘለት፥

✦ 1 ዓመት ከሆነው በኋላ የተጠመቀ፣ ተጠምቆ ሲጨርስ ከሰማይ ኅብስት ወርዶ የቆረበ፥

✦ ሕፃን ሳለ በ10 ዓመቱ ሰማዕትነትን የተቀበለ፣ ገነት ከገባ በኋላ ግን በቅ/ጊዮርጊስ እጅግ ተደንቆ "ደግሞ ወደ ምድር ለተጋድሎ ልመለስ ብሎ" የለመነ፥

✦ ስለጌታ ፍቅር ብሎ በተጋድሎ ሕይወቱ 10 ጊዜ በአሰቃቂ ሁኔታ ሞቶ የተነሣ ሰማዕት ነው።

ዕድሜውንም ፈጽሞ ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ጊዜ ሲደርስ ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስ በእጁ ልዩ የሆኑ አክሊሎችን የሚያበሩ ልብሶችንም ይዞ ተገለጠለት።

«ወዳጄ አቢብ ሆይ በማያልቅ ተድላ ደስታ ደስ አሰኝህ ዘንድ ወደእኔ ና።

ስምህን ለሚጠራ፣ መታሰቢያህን ለሚያደርግ እኔ ኃጢአቱን አስተሠርይለት ዘንድ በራሴ ማልኩልህ፤ ወይም ለተራቆተ የሚያለብሰውን ለተራበም የሚያጠግበውን ለተጠማ የሚያጠጣውን የገድልህን መጽሐፍም የሚጽፈውን ወይም የሚያነበውንና የሚሰማውን በጸሎትህም የሚታመኑትን ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እምራቸዋለሁ።


๏ አቅም ቢያጣ 'አምላከ አቢብ ማረኝ' ብሎ 3 ጊዜ በዕለተ ዕረፍትህ የሚለምነኝን፣

๏ በስምህ እንኳ ቁራሽ የሚበላውን ሁሉ እምርልሃለሁ (ከመዓድ በኋላ "በእንተ አቡነ አቢብ መሐረነ ክርስቶስ" ብለን 3 ጊዜ የምንቀምሰው ለዚህ ነው)»

ይህንም ብሎ አፉን ሳመው። በደረቱም ላይ አድርጎ ወደአየር አወጣው። የመላእክትንም ምስጋና በሰማች ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ገባች።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🇨🇬🇨🇬
#_ተግሣጽ_፲፫ { ለኢ.ዓ.ብ ቤተሰብ ብቻ }
#_የተጠራችሁት_በጽድቃችሁ_አይደለም

🇨🇬 የሐዋርያት ሥራ ትምህርት ክፍል ፯-ለ 🇨🇬
| 🕛 | ከ ፶፭ ፡ ፶፩ ጀምሮ

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች፥ ያላችሁበትን እወቁ። እግዚአብሔር እንዴት እንደወደዳችሁ እወቁ፤ አስተውሉ

በታመናችሁበት ልክ እናንተም ታመኑ። በተወደዳችሁበት ልክ፤ ከናንተ ጋር ከነ ነውራችሁ፣ ከነ ጥፋታችሁ፣ ከነ ጉድለታችሁ እግዚአብሔር ተሸከሟችሁ እያጓጓዛችሁ ነው ያለው።

በቃ እግዚአብሔር ሲመርጥ፥ ሲወድድ፥ ሲያጸድቅ፥ ሲተክል "አላጠፋንም፤ ስህተት የለብንም፤ ጉድለት የለብንም፤ ፍጹማን ነን" አ ይ ደ ለ ም። አ ለ ብ ን። ባለ ጉድለቶች ነን። ጥፋትም ይኖርብናል። ግን ዘወትር በንስሐ በፊቱ የምንወድቅ ሕዝቦች ነን።

በተሰበረ ልብ በእንባ በፊቱ ቀርበን እግዚአብሔርን በፍቅሩ ፊት ስንወድቅለት ፍቅሩን የምናገኝ የምናሸንፍ ሕዝቦች ነን።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat 🇨🇬
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930 🇨🇬
...ዛሬ ቤተክርስቲያንን መንግሥት ነው የሚያሽከረክራት ፥ መንግሥት ነው የሚመራት ። ሲኖዶስ ወይም ጳጳሳት ሣይሆኑ ፥ ልብ አድርግ ! ጳጳሳት ብራቸውን ከመብላት ፣ በመኪናቸው ከመሽከርከር ፣ ኧ! የወር ደሞዛቸውን ከመጠበቅ ፣ በስልጣናቸው በኢትዮጵያ መኃይም ህዝብ ከመከበር በቀር ምንም ሥልጣን፣ ሥራ የላቸውም የእኔ ጌታ ።

ለዚህ ደግሞ ተምረናል ብለዋል ተምረው ከሆነ ፣ አውቀናል እናውቃለን ይላሉ አውቀው ከሆነ ፣ ዳዊቱን ጠዋት ማታ ይደግሙታል እየደገሙት ከሆነ አስቀድሞ ነብዩ ዳዊት ትንቢት ተናግሮባቸዋል ወንድማለም ! ትንቢት ተናግሮባቸዋል ። ይኸውም በመዝሙር 49 ነው ከቁጥር 1 ጀምሮ ቢያነቡ ያገኙታል፤ ዳዊቱን ከነሱ የበለጠ የተማረው የለም የሚደግሙት ከሆነ ወ ይ ም ቢደግሙትም ምስጢሩን የሚያውቁት ከሆነ ። ኧ! በመዝሙር 49 ከቁጥር 1 ጀምሮ እስኪ ይመልከቱት ስለማን ነው የተፃፈ ? ስለነሱ ነው። ይኸውም ምንድነው ባጭሩ አንድ ቃል ልንገርህ ☞ አስተጋብኡ : ሎቱ : ፃድቃኑ ፥ እለ : ይገብሩ : መሥዋዕት : ዘበሕጉ የሚል ኃይለቃል አለ አስተጋብኡ : ሎቱ : ፃድቃኑ : እለ : ይገብሩ : መሥዋዕት : ዘበሕጉ ። ይህ ምንድነው ነብዩ ዳዊት አስቀድሞ በዚህ ዘመን ስለሚመጡት የሃይማኖት አባቶች ፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሃይማኖት ባለሟሎት፣ የሃይማኖት ባላደራዎች ስለሚባሉት ከዲያቆን እስከ ጳጳሳት ስላሉት ስለ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች የተናገረባቸው ትንቢት ነው። ይኸውም ምንድነው?፦ እነሆ በዚያን ሰዓት ለእርሱ ማለትም ለእግዚአብሔር ለፈጣሪ ንፁሀንን፣ ደጋጎችን፣ ቅዱሳንን፣ ካህናቱን ሰብስቡለት ! ሰብስቡለት ። ማለትም መሥዋዕቱን፣ ቅዳሴውን ፣ ሠዓታቱን፣ ማህሌቱን .. ሁሉ ሰዓትን ጠብቀው ፣ ዕለትን ጠብቀው ፣ ቀንን ጠብቀው መርጠው የሚሰውለትን፣ የሚቀድሱለትን፣ የሚያመሰግኑትን፣ የሚያገለግሉትን እውነተኛ ቅዱሳን ካህናትን ሰብስቡለት ነው ያለ። ሥለዚህ እኒህ ትንቢት የተነገረላቸው ቅዱሳን ካህናት፣ ቅዱሳን ዲያቆናት፣ ቅዱሳን ጳጳሳት በትንቢቱ መሠረት ጊዜው ደርሶ እስኪመጡና እውነተኛ ቤተክርስቲያንን ተረክበው እውነተኛ መሥዋዕት እስኪሰው፤ እውነተኛ ጻድቃን ህዝበ ክርስቲያንን የሚያገለግሉት እስኪመጡ ድረሥ አሁን ያለው በሙሉ በቤተክርስቲያን ውስጥ የተጎደጎደው የዲያቢሎስ አሻንጉሊት ነው ። እንዴ ! የዲያቢሎስ መሣሪያ ነው ። የዲያብሎስ አገልጋይ ነው ።...


📌 አባ አምኃኢየሱስ ገብረዮሐንስ ከዛሬ 9 አመት በፊት በኢሳት ድምፅ ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቆይታ ላይ ተቀንጭቦ የተወሰደ !
🟢🟡🔴
ጥቅምት 27 | ቤተ ክርስቲያን
#የመድኃኔዓለምን የስቅለት በዓል ታከብራለች። ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ሥጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው። ነገር ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሐዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርታልናለች፡፡
 
🍀 #አባ_መብዓ_ጽዮን
የጻድቁ መታሰቢያ በዓል በየዓመቱ ጥቅምት ፳፯ ቀን ከመድኃኔዓለም የስቅለት በዓል ጋር ይከበራል። ጥቅምት ፳፯ ቀን ለወዳጆቹ እውነተኛውን ዋጋ የሚከፍል መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለጻድቁ አባ መብዓ ጽዮን ብዙ ቃል ኪዳን የገባበት ቀን ነው።


አቡነ መብዓ ጽዮን በይበልጥ የሚታወቁት ሁልጊዜ ወር በገባ በሃያ ሰባት መድኃኔዓለምን አብልጠው በመዘከራቸው ነው፡፡

በዚህም ቀን ‹‹እንደ አንተም በየወሩ በሃያ ሰባት የሞቴ መታሰቢያ ለሚያደርግ ነፍሳትን ከሲኦል አወጣለታለሁ›› የሚል ድንቅ ቃልኪዳን ከጌታችን ተቀብለውበታል፡፡ ይኸውም የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ሲነግራቸው ነው፡፡

በኋላ አባታችን እንዲህ መከሩን፦ ‹‹ክርስቲያኖች ሁሉ የፈጣሪያችንን የመድኃኔዓለም ክርስቶስን የመታሰቢያ በዓሉን እናድርግ፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ ያደረገ ግን የተኮነኑ ነፍሳትን ከደይን ያወጣል፣ በሞቱም ጊዜ ሥቃይን አያያትም፡፡

🍀 #አባ_ጽጌ_ድንግል ዕረፍታቸው ነው።
በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረ ሊቅ ሲኾን፤ አባ ጽጌ ድንግል (ጽጌ ብርሃን) ሀገሩ ይፋት ሃይማኖቱ ኦሪት (ያላመነና ያልተጠመቀ) ነበር።

በኋላ ግን አቡነ ዜና ማርቆስ አሳምነውት ማኅሌተ ጽጌን የደረሰ ቅዱስ ኢትዮጵያዊ አባት ነው።

🍀 ግብፃዊው ጻድቅ #አቡነ_ሐራ_ድንግል ዕረፍታቸው ነው።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
ጥቅምት 26፣2017

ዛሬ  በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ ከተማ በመስሪያና መሸጫ ሼድ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ፤ እናት ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወቷ ማለፉ ተሰማ።

በእሳት አደጋዉ በሼድ ዉስጥ ካሉ  ሱቆች መካከል ስድስት የንግድ ሱቆች ተቃጥለዋል ተብሏል። 
˙ ✥ ••---• ✞ •---•• ✥

#ዘበእንቲአሃ_ለቤተክርስቲያን_ተጸፋእከ በውስተ ዐውድ ከመ ትቀድሳ በደምከ ክቡር። ዘበእንቲአሃ ዝግሐታተ መዋቅሕት ፆረ ወተዐገሰ ምራቀ ርኩሰ እንዘ አልቦ ዘአበሰ #አምላክ_ዲበ_ዕፀ_መስቀል_ተሰቅለ

❮ትርጉም❯
#ለቤተክርስቲያን_ብለህ
ልትቀድሳት በደምህ
በአደባባይ በጥፊ ተመታህ።

ንጹሕ ክርስቶስ በአዳም ጥፋት ልትወቀስ
በከንቱ ልትከሰስ አመላለሱህ ከጲላጦስ
ወደ ሄሮድስ
ሁሉን ቻይ ሳለህ ምንም ማድረግ ሳይሳንህ
በአይሁድ እጅ ተገረፍህ!

ወዮ! ወሰን ለሌላት ትዕግስት ስለኛ ብለህ
መከራ ተቀበልህ
ምንም በደል ሳይኖርብህ አምላክ በእንጨት መስቀል ላይ ሰቀሉህ።

#ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ
Audio
ድርሳነ መድኃኔዓለም ዘረቡዕ
Audio
ገድለ መባ ጽዮን ዘረቡዕ
Audio
ገድለ አባ በግዑ
ዕረቡ ጥቅምት 27 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በሀዲያ ዞን ሸሾጎ ወረዳ ሰሞኑን በጣለው ከባድ ዝናብ ከዘጠኝ መቶ 87 በላይ ሄክታር ማሳ መሬት ላይ የደረሱ ሰብሎችን ከጥቅም ውጪ ማድረጉ ተገለጸ።

በሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ አደጋ ስጋትና ምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ጎርፉ ያደረሰው ጉዳት በወረዳው በሚገኙ 13 ቀበሌዎች ላይ ሲሆን በደረሰው አደጋ 15 ሺ 850 አርሶ አደሮች ተጎጂ ሆነዋል ብሏል፡፡

በመሆኑም ተዘርቶ ለመሰብሰብ የደረሰ የጤፍ፣ የስንዴ የበቆሎ፣ የማሽላና ሌሎችም ሰብሎች ከጥቅም ውጭ ማድረጉን እና 9 መቶ 87 ሄክታር ማሳ በላይ በጎርፍ መጥለቅለቁ ተጠቁሟል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት በነበረው ዝናብ እና ከተራራማ አካባቢ የሚወርደው ጎርፍ ጉደር፣ መቴቾሴ እና ወራ ወንዞች ሞልተው በመፍሰሳቸው የጎርፍ አደጋው መከሰቱ ተገልጻል፡፡

በወረዳው የተከሰተው አደጋ ጉዳት ከወረዳው አቅም በላይ በመሆኑ የሚመለከታቸው የክልሉ እና የፌዴራል ተቋማት ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡም ጥያቄ መቅረቡ ተመላክቷል፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች እየጣለ የሚገኘው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በተለያዩ ክልሎች በደረሱ እና እየደረሱ በሚገኙ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
2024/12/24 18:36:17
Back to Top
HTML Embed Code: