Telegram Web Link
📌 ለረሃብተኞች ደራሽ ስለማይኖር ሚሊዮኖችን መውስድ ስራቸው ይሆናል። ምልክት አልባው ሁሉ የጥፋቶቱ ሁሉ ኢላማ ይሆናል።''
◆► ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 5 ገፅ-17
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ኢትዮጵያዊ የተክለሃይማኖት ወዳጅ🇨🇬🇨🇬🇨🇬)
📍
በስተመጨረሻም፥
#ለኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_ቤተሰቦች

[📍] የተሸከማችሁት ኃላፊነት ትልቅ ነው። በማስተዋል ተጓዙ ለሌላው ብርሃን ሆናችሁ ተመላለሱ። የሚዘምቱባችሁን፣ የሚያስከፏችሁን፣ የሚያሰድዷችሁን ሁሉ ግድየለም ታገሷቸው። በፍቅር በትዕግሥት ልታስረዷቸው ሞክሩ። እምቢ ካሉ ከጸኑባችሁ ደግሞ ልቀቁላቸው አካባቢያቸውን። ትቢያውንም እያረገፋችሁ ከእግራችሁ ላይ መሔድ ነው። ያ ቀዬ ግን በኋላ ላይ ከባድ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። እነዛም ሕዝቦች ይጎዳሉ። ግን ያ እንዳይሆን ምከሯቸው።

[⚜️] እናንተ ደግሞ እርስ በራሳችሁ እግዚአብሔር በሚወደው መንገድ ላይ ቆማችሁ በፍቅር መተሳሰብ በእምነት መጽናት ይገባችኋል። እግዚአብሔር አሁን ሥራውን ጀምሮ በፊት ለፊት እያያችሁ፣ እየሰማችሁ ነው፤ እያስተዋላችሁ ነው።

[⚜️] ጉድለታችሁን አርሙ ታላላቆቻችሁን አክብሩ ወንድሞቻችሁን አክብሩ ውደዱ ተዋደዱ።

[⚜️] ጽዋችሁን አክብራችሁ ያዙ።

[⚜️] በወንድምህ ላይ የምትነቅፈው ነገር እንኳን ቢኖርህ በትሕትና ነው መነጋገር ያለብህ። በመከባበር ነው መነጋገር ያለብህ! እግዚአብሔር ፍቅርን ነው እንጂ የሚወደው ጸብን አይወድም። ትሕትና ነው እንጂ የሚወደው ትዕቢትን አይወድም። እውነትን እንጂ የሚወደው ሐሰትን አይወድም። ስለዚህ ወደ ስህተት አሠራር ወደ ተሳሳተ አካሄድ አትሒዱ። እምነታችሁን የሚፈትን፣ እምነታችሁን የሚያውክ የስህተት አሠራር ውስጥ እንዳትገቡ ተጠንቀቁ።

[⚜️] ንስሐ ሁልጊዜ ግቡ! በእግዚአብሔር ፍቅር ተመላለሱ። ፍቅርን አጽኑ። በወንድማማች መዋደድ በፍቅር ተሰባሰቡ፤ ተነጋገሩ፤ ተመካከሩ፤ ተዋደዱ። በጽዋችሁም ፍቅር ይንገሥበት። ጠብ ጭቅጭቅ አያስፈልግም።

[⚜️] መማክርቶችን አክብሩ! በዚህ ሰዓት እናንተ እየመሩ ያሉ፥ ይነስም ይብዛም መንፈሳዊ ምሪትን የሚሰጡ ከእግዚአብሔር የተሰጧችሁ ወንድሞቻችሁ ናቸው። አክብሯቸው! አትናቁ! ይሄ ንቀት ማንጓጠጥ እኔ አውቃለሁ ባይነት እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚሠራው ባሕርይ አይደለም፤ ምክራችን ይሄ ነው።

[⚜️] በአሁኑ ጊዜ መንፈሳዊ መነቃቃት ሊኖረን ይገባል! በጾም በጸሎት ልንተጋ ይገባል። ቃሉን ደግሞ ያልሰማችሁ በደንብ ያላነበባችሁ ደግሞ አንብቡ ትምህርቶቹን ተከታተሏቸው። ስሟቸው። የእግዚአብሔርን ቃል በተከታታይ ትምህርት እየሰጠን ነው። እነሱን አድምጡ።

[⚜️] ዝግጅትም ይኑራችሁ! ከዚህ በላይ ምን ምልክት ትፈልጋላችሁ? ቀድሞ ስንት ጊዜ ጀምሮ እኛ ለዝግጅት መክረናል። አሁንም ዝግጅት ይኑራችሁ! ደካማ አትሁኑ! በመንፈስ ጠንካራ ሁኑ!

[️⚜️] ግዴታችሁን፥ አሥራት በኩራታችሁን፣ ቸርነት ማድረጋችሁን፣ ጸሎታችሁን እነዚህን ሁሉ እንደጀመራችሁት መጨረስ፣ መሔድ፣ መጓዝ! ሁሉንም ነገር በካሳ ታገኙታላችሁ። ሁሉንም ነገር በበረከት መልሱን ታገኙታላችሁ። እርስ በርሳችሁ ስለጤና፣ ስለ ሰላም፣ ስለ ፍቅር ስለ ውስጣችሁ አንድነት ስለዚህ ሁሉ ጸልዩ።

[📍] እግዚአብሔር እንዲያጸናችሁ፣ እንዲተክላችሁ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር ደጋግማችሁ አቤት በሉ ምክራችን ይሄ ነው።

➻ የኢ.ዓ.ብ መግለጫ፥ ጥቅምት 21፥ 2016 ዓ.ም መግለጫ (ክፍል 2)
⌚️️ ከ1፡04፡28 - 1፡09፡00
Audio
መልክአ ቅዱስ አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ
🟢🟡🔴
ጥቅምት 28 | ከ9ኙ ቅዱሳን አንዱ #አቡነ_ይምዓታ ዐረፉ።

ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮጵያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት።

አባ ይምዓታ ከዘጠኙ (ተስዓቱ) ቅዱሳን አንዱ ናቸው። ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው።

ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው።

አባ ይምዓታን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግሥት ነው። እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል።

አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች፣ ከዚያ ወደ ኢትዮጵያ ወርደዋል።

በምናኔ ቅድሚያውን አባ ጰንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ።

የአቡነ ይምዓታ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደስ ትግራይ ገርዓልታ ልዩ ስሙ ‹‹ጎሕ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ይገኛል፡፡ ቤተ መቅደሱ ሰማይን እንደ ምሰሶ ደግፈው የያዙ የሚመስሉ በጣም ረጃጅም ተራሮች መካከል በአንደኛው ጭፍ ላይ ይገኛል፡፡

ቤተ መቅደሱ ከባሕር ወለል በላይ በ2300 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ቤተ መቅደሱ ያለበት የተራራው ርዝመት ብቻውን 300 ሜትር ነው፡፡

ቤተ መቅደሱ በር ላይ ለመድረስ በጭንቅና በፍርሃት ሆኖ ተራራውን እንደዝንጀሮ በእጅ እየቧጠጡ መውጣት ይጠይቃል፡፡ እርሱም ቢሆን በገዳሙ አባቶች እገዛና ድጋፍ ካልሆነ መውጣት የማይቻል ነው፡፡

ቤተ መቅደሱ በውስጡ ያሉት የግድግዳ ላይ ሥዕሎችም እጅግ ድንቅና ጥንታዊ ናቸው፡፡

በዚሁ የአቡነ ይምዓታ እጅግ አስደናቂ ቤተ መቅደስ ገድለ አቡነ አረጋዊ ሲናገር፦ በሞት በዐረፉ ጊዜ የሥጋቸው ሥርዓተ ግንዘት የተከናወነው በመላእክት እጅ ነው።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
❗️ዋኖቻችንን እንወቅ❗️(የጥያቄና መልስ መርሐ ግብር) ውድ ቤተሰቦች፥ ዋኖቻችንን እንወቅ በሚል መርህ የቅዱሳንን ዜና ሕይወትና ገድል በጥቂቱ ማሳወቅ መጀመራችን ይታወቃል። ዋና ዓላማው ቅዱሳኑን ጠንቅቆ ማወቅ ብቻ ሳይሆን በሕይወትም እነሱን መምሰል እንድንለምድ ነው። ለዚህም እንዲያግዘን በየዙሩ ከሚለቀቁት የቅዱሳንን ዜና ታሪኮች የተውጣጡ ጥያቄዎችን አዘጋጅተናል። ጥያቄዎቹ የተዘጋጁበት ዓላማ ያነበብነውን…
ዋኖቻችንን እንወቅ❗️[ጥያቄ 5]

ከሕፃንነታቸው ጀምሮ እንደ እመቤታችን በቤተ መቅደስ ቅዱሳን መላእክት ሰማያዊ ኅብስት እየመገቡ ያሳደጓቸው፣ ዳግመኛም በጸሎታቸው ኃይል ተራራን ያፈለሱት (ያንቀሳቀሱት) ታላቁ ጻድቅ #አቡነ_እንድርያስ ከእመቤታችን ጋር አንድ ቀን የዋለ በዓል አላቸው። ይህ በዓላቸው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
17%
የፍልሰት በዓላቸው (ነሐሴ 16)
23%
የዕረፍት በዓላቸው (ጥር 21)
32%
የልደት በዓላቸው (ግንቦት 1)
28%
ቤተ መቅደስ የገቡበት (ታኅሣሥ 3)
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
❗️ዋኖቻችንን እንወቅ❗️(የጥያቄና መልስ መርሐ ግብር) ውድ ቤተሰቦች፥ ዋኖቻችንን እንወቅ በሚል መርህ የቅዱሳንን ዜና ሕይወትና ገድል በጥቂቱ ማሳወቅ መጀመራችን ይታወቃል። ዋና ዓላማው ቅዱሳኑን ጠንቅቆ ማወቅ ብቻ ሳይሆን በሕይወትም እነሱን መምሰል እንድንለምድ ነው። ለዚህም እንዲያግዘን በየዙሩ ከሚለቀቁት የቅዱሳንን ዜና ታሪኮች የተውጣጡ ጥያቄዎችን አዘጋጅተናል። ጥያቄዎቹ የተዘጋጁበት ዓላማ ያነበብነውን…
ዋኖቻችንን እንወቅ❗️[ጥያቄ 7]

የቅዱስ ላሊበላ ሚስት በመስቀል ጦርነት ምክንያት ወደ ሀገራችን መጥተው የነበሩ ሙስሊሞችን የእግዚአብሔር ወንጌል እያስተማረች በግድ ሳይሆን በውዴታቸው እንዲጠመቁ ያደረች ሐዋርያዊት ናት፡፡ ርኅርኅትና አስተዋይ የሆነች የቅዱስ ላሊበላ ሚስት ማን ትባላለች? ቅድስት ክርስቶስ ክብራ ቅድስት መስቀል ክብራ ቅድስት መስቀል ሞገሳ ቅድስት ክርስቶስ ሞገሳ
Anonymous Quiz
18%
ቅድስት ክርስቶስ ክብራ
68%
ቅድስት መስቀል ክብራ
10%
ቅድስት መስቀል ሞገሳ
4%
ቅድስት ክርስቶስ ሞገሳ
🟢🟡🔴
ጥቅምት 30 | ከከበሩ አባቶቻችን መካከል፦

🍀 ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነ ወንጌላዊ፣ ሐዋርያ፣ ሰማዕት፣ ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተባለ #ቅዱስ_ማርቆስ ልደቱ ነው።

ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም፣ አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ። በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል። የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ120ው ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ (20 ዓመት) እርሱ ነበር።

ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል። በተለይ የግብፅና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው። ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና።

ቅዱስ ማርቆስ 16 ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ፣ ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር። ቅዱሱ ከቅዱስ ጳውሎስ፣ ከበርናባስና ጴጥሮስ ጋር ተጉዟል። ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ አረማውያን ገድለውታል።

ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል። ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ) የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ፣ ቅድስት ማርያም (እናቱ) ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ጌታችንን ያገለገለች ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት።
🍀

ዳግመኛም በዚህች ቀን #የመጥምቁ_ዮሐንስ ቅድስት ነፍሱ ከተቆረጠች ራሱ ጋራ በአየር ውስጥ እየበረረች 15 ዓመት ስታስተምር ከኖረች በኋላ በዐረቢያ ምድር በግልጽ ታይታለች፡፡

ርጉም ሄሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የወንድምህን የፊሊጶስን ሚስት ማግባት አይገባህም" እያለች መጀመሪያ ትዘልፈው እንደነበረው ሁሉ አሁንም ዘለፈችው፡፡ መዓዛዋም እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነበር፣ ዐይኖቹም እንደፀሐይ ያበሩ ነበር፡፡
🌿

T.me/Ewnet1Nat
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
📌 ዋኖቻችንን እንወቅ ❗️(የቅዱሳን ታሪክ)

#ክፍል_4 (ነገ ይለቀቃል!)

🟩🟨🟥 "የእግዚአብሔርን፡ ቃል፡ የተናገሯችኹን፡ ዋኖቻችኹን፡ ዐስቡ፥ የኑሯቸውንም፡ ፍሬ፡ እየተመለከታችኹ፡ በእምነታቸው፡ ምሰሏቸው።" ወደ ዕብራውያን 13፥7
ዛሬ ጥቅምት 30/2/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:15 ልዩ ስሙ  ቋሪት ብር አዳማ ዙሪያ ትንሽ የገጠር ከተማ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልወቁ ንፁሃን በድሮን ተጨፍጭፈዋል።

ከግዮን አማራ ገፅ
🇲🇿🪧 በተባባሰው የሞዛምቢክ የምርጫ ውጤት ተቃውሞ ከ20 ያላነሱ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ

የገዥው ፍሬሊሞ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ቻፖ፤ መስከረም 29 በተካሄደው የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 70.67% ድምጽ በማግኘት እንዳሸነፉ መገለጹን ተከትሎ፤ በሀገሪቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነስቷል።
2024/11/15 14:30:01
Back to Top
HTML Embed Code: