Telegram Web Link
ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ፤ አሳብህን ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ኹሉ በእርሱ ላይ ጣለው፡፡ አንተ እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም፥ አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት ያከብርሃል፡፡ ስለዚህ በምታደርገው ነገር ኹሉ ሽማግሌህ እርሱ እግዚአብሔር እንዲኾን ዘወትር ጠይቀው፡፡

አስቀድመህ እንደዚህ ካደረግህም፥ ወደ ትዳር ከገባህ በኋላ ፍቺ አይገጥምህም፡፡ ሚስትህ ሌላ ሰውን አትመኝም፡፡ በሌላ ሴት እንድትቀናም አታደርግህም፡፡ በመካከላችሁ [ለክፉ የሚሰጥ] ጠብና ክርክር አይኖርም፡፡ ከዚህ ይልቅ ታላቅ የኾነ ሰላምና ፍቅር በመካከላችሁ ይሰፍናል፡፡ እነዚህ ካሉ ደግሞ ሌሎች በጎ ምግባራትን፣ ትሩፋትን ለመፈጸም አትቸገሩም፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ @EotcLibilery @EotcLibilery @EotcLibilery
ግእዝ ክፍል ሰባት
የኢትዮጵያ ሊቃውንት ለእያንዳንዱ ፊደል ነገረ ሃይማኖትን የሚገልጥ ትርጉም ሰጥተዋል።

ሀ ብሂል ሀልወቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም የአብ መኖር ከዓለም በፊት ነው ማለት ነው።
.
ሁ ብሂል ኪያሁ ተወከሉ።በእርሱ (በእግዚአብሔር) ታመኑ።
.
ሂ ብሂል አስተይዎ ብሂዐ አይሁድ ጌታን ሖምጣጤ አጠጡት ማለት ነው።
.
ሃ ብሂል ሃሌ ሉያ።ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ማለት ነው።
.
ሄ ብሂል በኲለሄ ሀሎ። እግዚአብሔር በሁሉ ቦታ እና ጊዜ አለ ማለት ነው።
.
ህ ብሂል ህልው እግዚአብሔር። እግዚአብሔር አለ ማለት ነው።
.
ሆ ብሂል ኦሆ ይቤ ወመጽአ። እሺ ብሎ መጣ ማለት ነው።አዳምን ለማዳን እግዚአብሔር በፈቃዱ ሥጋን መዋሐዱን ያመለክታል።
.
ለ ብሂል ለብሰ ሥጋ ዚኣነ።እግዚአብሔር የእኛን ሥጋ ተዋሐደ ማለት ነው።
.
ሉ ብሂል ሣህሉ ለእግዚአብሔር። የእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ማለት ነው።
.
ሊ ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው ማለት ነው።
.
ላ ብሂል ላሜድ ልዑል እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ልዑል ነው ማለት ነው።
.
ሌ ብሂል መቅለሌ ዕጹብ። ጭንቀትን (ጭንቅን) የሚያቀል እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ል ብሂል መስቀል ዘወልደ አብ። የአብ ልጅ መስቀል ማለት ነው።
.
ሎ ብሂል ዘሀሎ እምቅድም። ቅድመ ዓለም የነበረ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ሐ ብሂል ሐመ ወሞተ በእንቲአነ። ክርስቶስ ስለእኛ መከራን ተቀበለ ሞተ ማለት ነው።
.
ሑ ብሂል ሰብሑ ለስመ እግዚአብሔር። የእግዚአብሔርን ሥም አመስግኑ ማለት ነው።
.
ሒ ብሂል መንጽሒ። ከበደል የሚያነጻ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ሓ ብሂል መፍቀሬ ንሥሓ። ንሥሓን የሚወድ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ሔ ብሂል ሔት ሕያው እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ሕያው ነው ማለት ነው።
.
ሕ ብሂል ሕያው እግዚአብሔር
.
ሖ ብሂል ንሴብሖ ለእግዚአብሔር። እግዚአብሔርን እናመስግነው ማለት ነው።
.
መ ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር። የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው ማለት ነው።
.
ሙ ብሂል ሙጻአ ሕግ
.
ሚ ብሂል ዓለመ ኀታሚ።ዓለምን የፈጠረ፣ ዓለምን የሚያኖር ዓለምን የሚያጠፋ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።
.
ማ ብሂል ፌማ መንፈስ ቅዱስ። መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው።

ሜ ብሂል ሜም ምዑዝ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ምዑዝ ነው ማለት ነው።
.
ም ብሂል አምላከ ሰላም። የሰላም አምላክ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ሞ ብሂል ሞተ በሥጋ። በሥጋ ሞተ ማለት ነው።
.
ሠ ብሂል ሠረቀ በሥጋ እምድንግል። ቃል ከድንግል ማርያም በሥጋ ተወለደ ማለት ነው።
.
ሡ ብሂል መንበረ ንግሡ።
.
ሢ ብሂል ሢመተ መላእክት። የመላእክት ሹመት ማለት ነው።
.
ሣ ብሂል ሣህል ወርትዕ። ይቅርታና ቅንነት ማለት ነው።
.
ሤ ብሂል ሤሞሙ ለካህናት። እግዚአብሔር ካህናትን ሾመ ማለት ነው።
.
ሥ ብሂል ንጉሥ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ንጉሥ ነው ማለት ነው።
.
ሦ ብሂል አንገሦ ለአዳም። እግዚአብሔር አዳምን አነገሠው ማለት ነው።
.
ረ ብሂል ረግዐ ሰማይ ወምድር በጥበቡ። በእግዚአብሔር ጥበብ ሰማይና ምድር ረጋ ማለት ነው።
.
ሩ ብሂል በኲሩ ለአብ። ወልድ የአብ አንድያ ልጁ ማለት ነው።
.
ሪ ብሂል ዘይሰሪ አበሳ። በደልን ይቅር የሚል እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ራ ብሂል ጌራ መድኃኒት።
.
ሬ ብሂል ሬስ ርኡስ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር አለቃ ነው ማለት ነው።
.
ር ብሂል ርግብ መንፈስ ቅዱስ። መንፈስ ቅዱስ ርግብ ማለት ነው።
.
ሮ ብሂል ፈጠሮ ለዓለም። እግዚአብሔር ዓለምን ፈጠረው ማለት ነው።
.
ሰ ብሂል ሰብአ ኮነ ከማነ። እግዚአብሔር ወልድ እንደኛ ሰው ሆነ ማለት ነው።
.
ሱ ብሂል ፋሲልያሱ።

ሲ ብሂል ዘይሤሲ ለኩሉ ዘሥጋ። ደማዊ ፍጥረታትን ሁሉ የሚመግብ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።
.
ሳ ብሂል ሳምኬት ስቡሕ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ምስጉን ነው ማለት ነው።
.
ሴ ብሂል ለባሴ ሥጋ። ሥጋን የተዋሐደ እግዚአብሔር ቃል ማለት ነው።
.
ስ ብሂል ለብስ ለዕሩቃን። ለታረዙት ልብስ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።
.
ሶ ብሂል መርሶ ለአሕማር።
.
ቀ ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ በመጀመሪያ ቃል ነበር ማለት ነው።
.
ቁ ብሂል ጽድቁ ለኃጥእ።
.
ቂ ብሂል ፈራቂሁ ለዓለም።ዓለምን የፈጠረ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ቃ ብሂል ቃልየ አጽምዕ። አቤቱ ቃሌን ስማ ማለት ነው።
.
ቄ ብሂል ሰዋቄ ኃጥኣን።
.
ቅ ብሂል ጻድቅ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር እውነተኛ ነው።

ቆ ብሂል ቆፍ ቅሩብ እግዚአብሔ። እግዚአብሔር ቅርብ ነው ማለት ነው

ምንጭ የሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው መጽሐፈ ግሥ ወሰዋስው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ግእዝ ክፍል ስምንት

በ ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኲሉ ዓለም። ዓለምን ሁሉ ለማዳን በትሕትናው ሰው ሆነ።
.
ቡ ብሂል ጥበቡ ለአብ። የአብ ጥበቡ ማለት ነው።
.
ቢ ብሂል ረቢ ነአምን ብከ። መምህር ክርስቶስ ሆይ እናምንሀለን ማለት ነው።
.
ባ ብሂል ባዕድ እም አማልክተ ሐሰት። ከሐሰት አማልክት የተለየ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ቤ ብሂል ቤት ባዕል እግዚአብሔር እግዚአብሔር ባዕለጸጋ ነው ማለት ነው።
.
ብ ብሂል ብርሃነ ቅዱሳን። የቅዱሳን ብርሃን ማለት ነው።
.
ቦ ብሂል አልቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌሁ። ከእግዚአብሔር በስተቀር ሌላ አምላክ የለም ማለት ነው።
.
ተ ብሂል ተሰብአ ወተሠገወ እማርያም እምቅድስት ድንግል። ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ ማለት ነው።
.
ቱ ብሂል መዝራእቱ ለአብ።የአብ ክንዱ ማለት ነው።
.
ቲ ብሂል ተአኳቲ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ተመስጋኝ ነው ማለት ነው።
.
ታ ብሂል ታው ትጉህ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ትጉህ ነው ማለት ነው።
.
ቴ ብሂል ከሣቴ ብርሃን። ብርሃንን የሚገልጥ ማለት ነው።
.
ት ብሂል ትፍሥሕት ወሐሴት። ፍጹም ደስታ ማለት ነው።

ቶ ብሂል ነአምን ልደቶ ለክርስቶስ። የክርስቶስን መወለድ እናምናለን ማለት ነው።
.
ነ ብሂል ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ። ክርስቶስ ደዌያችንን ነሣ መከራችንንም ተሸከመ ማለት ነው።
.
ኑ ብሂል ዛኅኑ ለባሕር።
.
ኒ ብሂል ኮናኒ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ገዢ ነው ማለት ነው።
.
ና ብሂል መና እስራኤል።
.
ኔ ብሂል መድኃኔ ዓለም። የዓለም መድኃኒት ክርስቶስ ማለት ነው።
.
ን ብሂል መኮንን እግዚአብሔር። እግዚአብሔር መኮንን ነው ማለት ነው።
.
ኖ ብሂል ኖላዊ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ጠባቂ ነው ማለት ነው።
.
ኀ ብሂል ኀብአ ርእሶ።
.
ኁ ብሂል እኁዝ አቅርንቲሁ።
.
ኂ ብሂል ዘልማዱ ኂሩት። በጎነት ልማዱ የሆነ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ኃ ብሂል ኃያል በኃይሉ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ኃያል ነው ማለት ነው።
.
ኄ ብሂል ኄር እግዚአብሔር ቸር ነው ማለት ነው።
.
ኅ ብሂል ኅብስት ለርኁባን። ለተራቡት ኅብስት እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።
.
ኆ ብሂል ኆኅተ ገነት ወልድ። የገነት ቁልፍ ወልድ ነው ማለት ነው።
.
አ ብሂል አአኲቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር። እግዚአብሔርን ፈጽሞ አመሰግነዋለሁ።
.
ኡ ብሂል ሙጻኡ ለቃል።
.
ኢ ብሂል ለሊሁ ተንሣኢ ወለሊሁ አንሣኢ።ክርስቶስ ራሱ ተነሺ ራሱ አንሺ ማለት ነው።
.
ኣ ብሂል ኣሌፍ ፈጣሬ ኩሉ ዓለም ቀዳማይ ወደኃራዊ።
.
ኤ ብሂል አምጻኤ ዓለማት እግዚአብሔር። ዓለማትን ከአለመኖር ያመጣ የፈጠረ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
እ ብሂል እግዚአብሔር እግዚእ። እግዚአብሔር ጌታ ነው ማለት ነው።
.
ኦ ብሂል እግዚኦ። አቤቱ ጌታ ሆይ ማለት ነው።
.
ከ ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው ማለት ነው።
.
ኩ ብሂል ዐርኩ ለመርዓዊ። የሙሽራው ሚዜ ማለት ነው።
.
ኪ ብሂል ኪያሁ ንሰብል። እርሱን ጌታን እናስተምራለን። አንድም ስለእርሱ እንሰብካለን።
.
ካ ብሂል ካፍ ከሃሊ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው ማለት ነው።
.
ኬ ብሂል ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማእከለ አኃው።
.
ክ ብሂል ክብሮሙ ለመላእክት። የመላእክት ክብራቸው ማለት ነው።
.
ኮ ብሂል ዘረዳእኮ ለአብርሃም። አብርሃምን የረዳሀው እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ወ ብሂል ወረደ እምሰማያት። ከሰማያት ወረደ ማለት ነው።
.
ዉ ብሂል ጼው ለምድር። የምድር ጨው ማለት ነው።
.
ዊ ብሂል ናዝራዊ። ኢየሱስ ናዝራዊ ነው ማለት ነው።
.
ዋ ብሂል ዋው ዋሕድ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር።አንድ ነው ማለት ነው።
.
ዌ ብሂል ዜናዌ ትፍሥሕት። ደስታን የሚናገር ማለት ነው።
.
ው ብሂል ሥግው ቃል። ሰው የሆነ አምላክ ማለት ነው።
.
ዎ ብሂል ቤዘዎ ለዓለም። ዓለምን አዳነው።

ምንጭ የሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው መጽሐፈ ግሥ ወሰዋስው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ግእዝ ክፍል ዘጠኝ

ዐ ብሂል ዐቢይ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው።
.
ዑ ብሂል በግዑ ለእግዚአብሔር። የእግዚአብሔር በግ ማለት ነው።
.
ዒ ብሂል ለሊሁ ሠዋኢ ወለሊሁ ተሠዋኢ።ኢየሱስ ራሱ መሥዋእት አቅራቢ ራሱ መሥዋእት ነው ማለት ነው።
.
ዓ ብሂል ዓይነ ኲሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ። ጌታ ሆይ የሰው ሁሉ ሰውነት አንተን ተስፋ ያደርጋል ማለት ነው።
.
ዔ ብሂል ዔ ዐቢይ እግዚአብሔር።
.
ዕ ብሂል ብፁዕ እግዚአብሔር።እግዚአብሔር ብፁዕ ነው ማለት ነው።

ዖ ብሂል ሞዖ ለሞት ወተንሥአ። ክርስቶስ ሞትን አሸንፎ ተነሳ ማለት ነው።
.
ዘ ብሂል ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር። ሁሉን የያዘ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ዙ ብሂል ምርጒዙ ለሐንካስ
.
ዚ ብሂል ናዛዚ። የሚያረጋጋ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ዛ ብሂል ዛይ ዝኲር እግዚአብሔር።
.
ዜ ብሂል አኃዜ ዓለም በእራኁ። ዓለምን በመሐል እጁ የያዘ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ዝ ብሂል ሐዋዝ ሕገ እግዚአብሔር። የእግዚአብሔር ሕግ መልካም ነው ማለት ነው።
.
ዞ ብሂል አግአዞ ለአዳም። አዳምን ነጻ አወጣው ማለት ነው።
.
የ ብሂል የማነ እግዚአብሔር። የእግዚአብሔር ቀኝ ማለት ነው።
.
ዩ ብሂል ዕበዩ ለእግዚአብሔር። የእግዚአብሔር ታላቅነት ማለት ነው።
.
ዪ ብሂል መስተስርዪ። ኃጢኣትን የሚያስተሰርይ ማለት ነው።
.
ያ ብሂል አንተ ኬንያሁ።
.
ዬ ብሂል ዐሣዬ ሕይወት። ሕይወትን የሚያድል ማለት ነው።
.
ይ ብሂል ሲሳይ ለርኁባን።
.
ዮ ብሂል ዮድ የማነ እግዚአብሔር።
.
ደ ብሂል ደመረ መለኮቶ ምስለ ሥጋነ ወሥጋነ ምስለ መለኮቱ። እግዚአብሔር ወልድ ቃሉን ከሥጋችን ሥጋችንን ከቃሉ አዋሐደ ማለት ነው።
.
ዱ ብሂል ፈዋሴ ዱያን። ሕመምተኛን የሚፈውስ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ዲ ብሂል ቃለ ዓዋዲ።
.
ዳ ብሂል ዳሌጥ ድልው እግዚአብሔር።
.
ዴ ብሂል ዐማዴ ሰማይ ወምድር።
.
ድ ብሂል ወልድ ዋሕድ።
.
ዶ ፈነወ ዋሕዶ ወተሰብአ።
.
ገ ብሂል ገባሬ ሰማያት ወምድር። ሰማይና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ጉ ብሂል ለአስካለ ሕይወት ሐረጉ።
.
ጊ ብሂል ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር።
.
ጋ ብሂል ጋሜል ግሩም እግዚአብሔር።
.
ጌ ብሂል ጽጌ ቅዱሳን።
.
ግ ብሂል ሐጋጌ ሕግ።
.
ጎ ብሂል ሰርጎሙ ለሐዋርያት።
.
ጠ ብሂል ጠቢብ እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ጠቢብ ነው ማለት ነው።
.
ጡ ብሂል ውስጡ ለሰብእ እግዚአብሔር።
.
ጢ ብሂል መያጢሆሙ ለኃጥኣን።
.
ጣ ብሂል የውጣ እንተ አሐቲ ሕርመታ።
.
ጤ ብሂል ጤት ጠቢብ እግዚአብሔር።
.
ጥ ብሂል ስሉጥ ወርኡስ እግዚአብሔር።
.
ጦ ብሂል ሦጦ ለመንፈስ ቅዱስ ላእሌነ።
.
ጰ ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ።
.
ጱ ብሂል ኮጱ መዓዛ ሰብእ።

ጲ ብሂል ሠራጲሁ ለዓለም። ዓለምን የሚቀድስ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ጳ ብሂል ጳጳሰ ወንጌል።
.
ጴ ብሂል አክራጴ ኃጢኣት። ከኃጢኣት የሚያነጻ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ጵ ብሂል ጵርስፎራ። ሥጋ ወደሙ ማለት ነው።
.
ጶ ብሂል ጶሊስ።
.
ጸ ብሂል ጸጋ ወጽድቅ እግዚአብሔር።
.
ጹ ብሂል ገጹ ለአብ።
.
ጺ ብሂል ሐዋጺ ነፍሰ ትሑታን። የትሑታንን ሰውነት የሚጎበኝ እግዚአብሔር ማለት ነው።
.
ጻ ብሂል ጻዴ ጻድቅ እግዚአብሔር።
.
ጼ ብሂል አእቃጼ ሰኮና።
.
ጽ ብሂል ጽንሑ ተስፋሁ ለአብ።
.
ጾ ጾም ትፌውስ ቁስለ ነፍስ። ጾም የነፍስን ቁስል ታድናለች።
.
ፀ ብሂል ፀሐየ ጽድቅ እግዚአብሔር። የእውነት ፀሐይ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።
.
ፁ ብሂል ዮም ሠረፁ ጽጌ በረከት።
.
ፂ ብሂል መላፂ ዘክልኤ አፉሁ።
.
ፃ ብሂል ፋፃ መንፈስ ቅዱስ።
ፄ ብሂል ሕፄሁ ለዳዊት
.
ፅ ብሂል ዕፅ አብርሃም ዘሠፀረ ለምሥዋዕ።
.
ፆ ብሂል ማዕፆ አፉሆሙ ለጻድቃን።
.
ፈ ብሂል ፈጠረ ዓለመ በጥበቡ። ዓለምን በጥበቡ ፈጠረ ማለት ነው።
.
ፉ ብሂል ምዕራፉ ለዓለም፣
.
ፊ ብሂል ፊደለ ወንጌል።
.
ፋ ብሂል አልፋ ወኦ
.
ፌ ብሂል ኀዳፌ ነፍሳት።
.
ፍ ብሂል ፍኖት ለኀበ አቡሁ።
.
ፎ ብሂል ፎራ ኅብስተ ቁርባን።
.
ፐ ብሂል ፓፓኤል ሥሙ ለእግዚአብሔር።
.
ፑ ብሂል ኖፑ አስካለ ወንጌል።
.
ፒ ብሂል ፒላሳሁ።

ፓ ብሂል ፓንዋማንጦን።

ፔ ብሂል እግዚአብሔር።

ፕ ብሂል ሮፕ ጽኑዕ እግዚአብሔር።
.
ፖ ብሂል በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ። በመጀመርያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ ማለት ነው።


ምንጭ የሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው መጽሐፈ ግሥ ወሰዋስው።

@EotcLibilery
@EotcLibiler
@EotcLibilery
ግእዝ ክፍል አስር

ኈ ብሂል ኈለቈ አዕፅምትየ። አጥንቶቼን ቆጠረ ማለት ነው።
-
ኊ ብሂል በኍባኊ ሥጋ አዳም። የአዳም ሥጋ የተፈጠረ ነው ማለት ነው።
-
ኋ ብሂል ሰንኋቲ ሥጋ ሰብእ። የሰው ሥጋ የሚበጣ ነው ማለት ነው።
-
ኌ ብሂል ይኌልቍ አሥዕርተ። ሣሮችን ይቆጥራል ማለት ነው።
-
ኍ ብሂል ዑጽፍት ወኅብርት። የለበሰች የተሸለመች ማለት ነው።
-
ቈ ብሂል ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን። ከበደለኞች ጋር ተቆጠረ ማለት ነው።
-
ቊ ብሂል ቍየጺሁ አዕማደ ባላቅ። ጭኖቹ እንደ ምሰሶዎች ናቸው ማለት ነው።
-
ቋ ብሂል እንቋዕ እንቋዕ። እሰይ እሰይ ማለት ነው።
-
ቌ ብሂል ቀነተ ሐቌሁ ለኀጺበ እግረ አርዳኢሁ። የደቀመዛሙርቱን እግር ለማጠብ ወገቡን ታጠቀ ማለት ነው።
-
ቍ ብሂል ቍርባነ ወንጌል። የወንጌል ቁርባን ማለት ነው።
-
ጎ(ጐ) ብሂል ጎሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ። ልቤ መልካም ነገርን አወጣ ማለት ነው።
-
ጒ ብሂል ሰንጓጒ እምኃጢአት። ከኃጢአት የሚያጠራ ማለት ነው።
-
ጓ ብሂል ዕጓለ እመሕያው። ሰው ማለት ነው።
-
ጔ ብሂል ዝንጓጔ መስቀል።
-
ጕ ብሂል ጕንደ ሐረገ ወይን። የወይን ሐረግ ግንድ ማለት ነው።
-
ኰ ብሂል ኰናኔ ዓለም። ዓለምን የሚገዛ ማለት ነው።
-
ኲ ብሂል ኲናተ ጌዴዎን ዘቈልቈለ ላዕለ ስድሳ ምእት ሐራ በምዕር። በአንድ ጊዜ በስድስት ሺ ወታደሮች ላይ የተሰበቀ የጌዴዎን ጦር ማለት ነው።
-
ኳ ብሂል ኳሄላ አይሁድ ወልድ። የአይሁድ ጥንግ ወልድ ማለት ነው። እንደ ጥንግ ያገኘው ሁሉ መትቶታልና።
-
ኴ ብሂል ወይኴንን እም ባሕር እስከ ባሕር። ከጫፍ እስከ ጫፍ ይገዛል ማለት ነው።
-
ኵ ብሂል ኵርጓኔ ቅዱሳን። የቅዱሳን ስብስብ ማለት ነው።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የሐመሮች ቃል ለሊቀጳጳሱ =የእኛ አምላክ ቦርጆ ነው። የአንተ አምላክ ከቦርጆ ከበለጠ ነገ ዝናብ እንዲያዘንብ ንገረው።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~

በአንድ ወቅት የሰሜን ኦሞ ሀገረሰብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አባት ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወደ ሐመሮች መንደር ይሄዳሉ።

ክላሽ ታጥቀው፤መፋቂያ ጥርሳቸው ላይ ሰክተው ለአፍረተ ስጋቸው ብቻ ብጣሽ ጨርቅ ገላቸው ላይ ጥለው በእዛ ሐሩር በሆነው በረሐ እራቁታቸውን የሚሄዱ የሐመር አርብቶ አደር ወጣቶቸው ጥቁር ቀሚስ ከጥቁር አስኬማ ጋር ያጠለቁትን ሊቀ ጳጳስ እንደ ልዩ ፍጥረት በአግራሞት ያያሉ።

በሐመሮች መንደር ለሐዋርያዊ አገልግሎት መጥቻለው ተብሎ ዝም ብሎ መስበክ አይቻልም። ምንአልባትም በድፍረት አደርጋለው ከተባለም ህይወትን የሚያስገብር ታላቅ ድፍረት ይሆናል። ለምንም ዓይነት መንግስታዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ተግባር ቅድሚያ የሐመር መሪ የሆኑት በዕድሜ የጎለመሱት አባትን ፍቃድና ይሁንታ ማግኘት ግዴታ ነው።

ሊቀ ጳጳሱም የሐመሮችን ባለአባት ለማግኘት ወደ ሐመሮች መሪ እልፍኝ ውስጥ ከአስተርጓሚያቸው ጋር ገቡ። የሐመር ባለአባትም ጥቁር በጥቁር ሆነው የመጡትን ሊቀ ጳጳስ ተመለከቱ። ቁርበት እንዲነጠፍላቸው ሎሌያቸውን አዘዙ። ለሊቀ ጳጳሱ ተነጠፈላቸው። በተነጠፈውም ቁርበት ላይ ሊቀ ጳጳሱ እንዲቀመጥ አዘዙ።

ሊቀ ጳጳሱ የመጡበትን ለሐመሩ ባለአባት አስረዱ፤"የሐመር አባላትን ጥምቀት አስጠምቀው ኦርቶዶክስ ለማድረግ እንደሚፈልጉ" ተናገሩ።

የሐመር ባላባትም ለረጅም ሰዓት በዝምታ ሆነው ሰሙ። በስተመጨረሻም አንድ ቃል ከሐመር ከአንደበታቸው አወጡ። ......"ዝናብ ከዘነበ ሣር ይበቅላል። ሣር ካለ ከብት ሣሩን ይመገባል። ከብት ካለ ወተት እና ሥጋ አለ። ወተት እና ሥጋ ካለ ደግሞ ሰው ይኖራል።ስለዚህ የእኛ አምላክ ቦርጆ ነው። ዝናብ እያዘነበ ከብቶቻችንን የሚያኖረው እሱ ነው።በእዚህ ወር ውስጥ ግን ለብዙ ቀናት ዝናብ ጠፍቷል።ቦርጆ ተጣልቶናል መሠለኝ። ነገር ግን የአንተ አምላክ የእኛ አምላክ ከሆነው ቦርጆ የሚበልጥ ከሆነ ነገ ዝንብ እንዲያዘንብ ንገረው።" ሲል ሊቀ ጳጳሱን አጣብቂኝ ውስጥ ከተቱቻቸው።

የወንጌል አንቀጽ ተጠቅሶ፤መጸሐፍት ተዘርግቶ ማስተማር የማይቻልበት ማህበረሰብ ውስጥ በምንም ነገር ወንጌልን ማስረዳት እንደማይቻል ያወቁት ሊቀ ጳጳሱ እግዚአብሔር ይህን ህዝብ ከወደደ ዝናብ አዝንቦ ለቤቱ እንዲጠራቸው ለመኑ።

የእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሆኖ በነጋታው ምድርን የሚያረሰርስ ዶፍ ዝናብ ዘነብ ። የሐመሩም ባላባት ተደነቁ። በንጋታው ሊቀጳጳሱን ጠርተው ተደንቀው አመሰገኑ። የሊቀ ጳጳሱንም እጅ ይዘው ሰፊ ባዶ ቦታ በጦቃሚ ጣታቸው እያመላከቱ "እኔ አርጅቻለውኝ ፤መሄጃዬም ደርሷል። አንተ ቤት ሠርተህ ህዝቤን ጠብቅ" ሲሉ ትንቢት የሚመስል ቃል ለሊቀ ጳጳሱ አሳሳቡ። ቤተክርስቲያንም በስፍራው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሠራ።ሐመሮችም መጥተው እንዲጠመቁ በሀመር ባላባት በኩል አዋጅ ታወጀ። የባለአባታቸውን ድምጽ የሰሙ ሐመሮች ከብታቸውን ትተው ወደ መቅደስ መጥተው የካህናት መዳፍ እስኪዝል ድረስ ተጠመቁ።

እልፍ ነፍሳት ዳኑ። የሐመሩም ባላባት ህዝቤን ጠብቅ ብሎ በነገሩት ትንቢት በሚመስም ቃላቸው ስርዓተ ጥምቀት ከተፈፅሞላቸው በኃላ ይህችን ዓለም ተሰናበቱ፣ ከካራን ወጥተው ከነዓንን ወረሱ።

ትላንት በእዚህ መልኩ ሐመር ላይ የተጀመረው ሐዋርያ አገልግሎት ዛሬ ከ90% በላይ ሐመሮችን ኦርቶዶክስ ማድረግ ተችሏል። የሐመር ልጅ የሆኑ ዲያቆናት እና ካህናትን ፈርተዋል።

እንደ ሙሴ ጸሊም የመሳሳሉ ታላላቅ ገዳማት በሐመሮች መንደር ተገድሟል። ይህ የወንጌል እሳት

ኦሞ ዛሬም ተቀጣጥሎ በዓመት እስከ 50ሺህ አርብቶአደሮች ሐብተ ወልድ ስመ ክርስትና ማግኘት ችለዋል።ዛሬ ወደ ሐመር የሚሄድ ቱሪስት ኢቫንጋዲን ብቻ ተመልክቶ ሳይሆን የሚመለሰው ታላላቅ ገዳማትንም ተሳልሞ በረከት ያፍሳል።።ቅድስ ቤተክርስቲያን ሐመር ላይ ተቃዋሚዎቿን ዘርራ፣የሚፃረሯትን ጥላ በአሸናፊነት ተሰይማለች።

#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

በደቡብ ኢትዮጵያ ካለች ቤተክርስቲያን የታየ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ጥር_4_ተዝካረ_ፍልሰቱ (በዓለ ስዋሬው ) #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ሐዋርያ ፤ ዮሐንስ ወንጌላዊ ፤ ፍቁረ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ

ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ
በተለያዩ ቅጽል ስሞች የሚጠራ፤ ጌታቸችንን ሥነ ስቅለት የሳለ፡፡
ከ81ዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች 5ቱንና ሌሎች መጻሕፍትን (ነገረ ማርያምን ..) የደረሰ፤
#ብዙ ደቀ መዛሙርትን ያስተማረ፤

ጌታ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው፡፡
✤ዮሐንስ ንጹሕ በአምሳለ ትጉሃን፤ (#ዮሐንስ_እንደ_መላእክት_ንጹሕ_ነው፤)
✤ዮሐንስ ድንግል ምክሐ ቅዱሳን፤ (#ዮሐንስ_ድንግል_የቅዱሳን_መመኪያ_ነው፤)
✤ዮሐንስ ስርግው በቀጸላ ሥን በሜላተ ብርሃን፤ (#ዮሐንስ_በብርሃን_መጐናጸፊያና_ሻሽ_የተጌጠ_ነው፤)
✤ዮሐንስ አርጋኖነ ዘቤተ ክርስቲያን፤ (#ዮሐንስ_የቤተ_ክርስቲያን_በገና_ነው፤)
✤ወበቃለ ቀርን ዘይኬልህ በኤፌሶን፥ ይስአል ለነ ስርየተ ለኀጥኣን፡፡ (#በኤፌሶን_ዐዋጅ_የሚናገር_ዮሐንስ_ኀጥኣን_ለምንሆን_ለኛ_ይቅርታን_ይለምንልን፡፡ /መጽሐፈ ሰዐታት/


#100_አካባቢ_ከሚጠጉ_ስሞቹ_ጥቂቶቹን_21ዱን_ስሞች_እነኾ

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ
ዮሐንስ #ፍቁረ እግዚእ፥ (የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ጴጥሮስ ፣ ናያዕቆብ ) ዮሐንስ ቀዳሚዉ ነዉ፡፡
ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት ፣ ምሥጢረ መንግስትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደዉ የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ዮሐ 13፡ 23 ፡፡
ወልደ #ዘብድዮስ
ዮሐንስ #ነባቤ መለኮት ፥
ዮሐንስ #ቦኦርኔጌስ
ዮሐንስ #አብቀለምሲስ ፥ (ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል፡፡ትጉሙም የራዕይ አባት ማለት ነዉ፡፡)
ዮሐንስ #ወንጌላዊ
ዮሐንስ #ድንግል
ዮሐንስ #ታዎሎጎስ ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን አስፍቶ በመጻፉ (ታዎሎጎስ) ተብሏል፡፡ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር)ማለት ነዉ፡፡

1. #ዮሐንስ_ብፁዕ (ብፁዕ ዮሐንስ) ፣ 2. ዮሐንስ ድንግል ፣3. #ዮሐንስ_ፍንው፣4. #ዮሐንስ_ካህን ፣ 5. #ዮሐንስ_ኅሩይ
6. ዮሐንስ ሥርግው፣7. #ዮሐንስ_ምዑዝ8. ዮሐንስ ቅኑይ ፣ 9. #ዮሐንስ_ማኅቶት ፣ 10. ዮሐንስ ቤዛ ሰማይ ፣ 11. #ዮሐንስ_ክቡር12. ዮሐንስ ጻድቅ ፣ 13. #ዮሐንስ_ረድእ፣ 14. ዮሐንስ ማኅቶት፣ 15. #ዮሐንስ_ድንግል፣ 16. ዮሐንስ ንጹሕ ፣ 17. #ዮሐንስ_ለባዊ ፣18. ዮሐንስ መረግድ፣ 19. #ዮሐንስ_ዕንቈ ፣ 20. ዮሐንስ መልአክ ፣21. #ዮሐንስ_ኪሩብ ፣22. #ቁጽረ ገጽ

#ስዋሬው
ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል፡

ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ተጋድሎን አርገጐ ዓለምን ሁሉ ዞሮ ካስተማረ ቦኃላ በመጨረሻም ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መርጦ መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ ፡፡ ጕድጓድም እንዲቆፍሩ አዘዘ ከዚያም ወረዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ የበፍታ ቀሚስ በቀር ሌላ አላረገም ነበር ፡፡ እየጸለየ ወደ ከተማም አሰናበታቸው፡፡

በክርስቶስ ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝብ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዘ ሁሉም እንደየ ስራቸው ጌታ እንደሚከፍላቸው ነገራቸው ፡፡ካዛም እንዲህ አለ እኔ ከሁላችሁም ደም ንፁሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራቹ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩም አላቸው ፡፡ እነርሱም እጅና እግሮቹን ስመውት ትተውት ሄዱ ሲመለሱም ልብስና ጫማ እንጂ ምንም አላገኙም እግዚአብሔርንም አመሰገኑት፡፡

ወልደ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ዘጠና ዓመትም ኖረ፤ እንደባላሟሎቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አለቀመሰም፡፡ ‹‹ያ ደቀ መዝሙር አይሞትን እንዲል ›› ዮሐ 21 ስለ ድንግልናውና ስለንጽሕናው ይህ ሁሉ ሆነ፡፡
በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን አሜን

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/25 18:18:35
Back to Top
HTML Embed Code: