Telegram Web Link
ስህተቱ በግዴለሽነት መቅረቡ ነው!

በዘመነ ሐዋርያት በጣም አስቸጋሪና ፈታኝ ከነበሩት ነገሮች መካከል በቋንቋ፤ በባህል፣ በአመጋገብና በአኗኗር እንዲሁም በሥርዓት የማይገናኙ ቤተ አይሁድንና ቤተ አሕዛብን አንድ አድርጎና አጣጥሞ ለመኖር መቸገር ነበር ይህም በሌላው አማኝ ብቻ ሳይሆን በአገልጋዮች ሐዋርያት መካከል ሳይቀር ውዝግብና መለያየት እስከመፍጠር ደርሶ እንደነበረ ታሪክ ያስረዳል ከዚህም አልፎ አንድ ሲኖዶሳዊ ስብሰባ አስፈልጎት በስብሰባ ውሳኔ አግኚቷል
ዛሬም የይሁዲነት ጽንፍ የያዙ የሚመስሉ ሁሉን ካልተጸየፍንና ካላወገዝን የሚሉና ሁሉን ካላደረግን የሚሉ ለአሕዛብነት ጽንፍ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ብቅ ብቅ እያሉ ነው

የሐዋ 10:11,ላይ እንደተጻፈው ለቅዱስ ጴጥሮስ ባየው ራእይ ልዩ ልዩ እንስሳትና አራዊት በተዘረጋ ሸማ ወርደው ታዩትና አርደህ ብላ ሲባል የሚያረክስ ነገር ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም በማለት መልስ ሲሰጥ እግዚአብሔር የቀደሰውን አታርክስ የሚል መልስ ተሰጥቶታል ምሥጢሩ አራዊታዊ ና እንስሳዊ ግብር ሳይቀር የበረታባቸውን አሕዛብን ሁሉ ወደ ክርስትና ለመጥራት የሚገልጽ ቢሆንም ፍጥረታቱ የረከሱ አለመሆናቸውንና እንዳልተከለከሉ ግን ያስረዳል
ነገር ግን ደግሞ ጴጥሮስ አለመብላቱ አእምሯችን ያልፈቀደነውን ነገር የግድ መብላትም እንደሌለብን ያሳያል
ከዚህም አልፈው እንኳን እንደ አሕዛብ መብላት ይቅርና ከአሕዛብ ጋር አብሮ መመገብ ሳይቀር እንደ መርከስ የሚቆጥሩ ስለነበሩ ቅዱስ ጴጥሮስ አይሁድ አዩኝ አላዩኝ ብሎ አብሯቸው ለመብላት ይቸገር ነበርና ቅዱስ ጳውሎስ በአደባባይ እንደወቀሰው በመልእክቱ ሳይቀር ገልጾታል ገላ 2:11 ይህንንም በአመጋገባቸው አሕዛብን መንቀፍ ግብዝነት ተብሎ ተጠርቷል

በኋላ ግን በኢየሩሳሌም በመጀመሪያው የሲኖዶስ ውሳኔ መፍትሔ ስለተሰጠበት አልፎ አልፎ ቢታይም የማኅበር ፈተና መሆኑ ግን ቀንሷል
በመጀመሪያው የሲኖዶስ ጉባኤ ከተወሰኑት ነገሮች መካከል በአመጋገብ ዙሪያ ከአሕዛብነት ወደ ክርስትና የመጡ ክርስቲያኖች ከጣዖት ከተሠዋ ምግብ እንዲርቁ የሞተና ደም አንቆት የሞተን እንስሳ እንዳይበሉ እንጂ ስለ ሌላ የምግብ ክልከላ መመሪያ አልተጻፈም ከቤተ አይሁድ የመጡት ግን በአመጋገብ ዙሪያ በኖሩበት እንዲቀጥሉ ተወስኗል እንጂ እንደ አህዛብ እንዲበሉ አልተገደዱም የሐዋ 15:28
ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊት እናት እንደመሆንዋ መጠን የምንመገበውን መንፈሳዊ ምግብ ትመርጥልናለች እንጂ ሥጋዊ ምግቡንማ ለጸሎትና ለጾም ከምንተጋበት ሰዓት ውጪ ደስ ያለንንና አእምሯችን የተቀበለውን የሚጠቅመንንና ጉዳትም የማያስከትለውን ሁሉ እንድንበላ ፈቅዳልናለች

ብዙ ቤተ አሕዛብና ቤተ አይሁድ ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው ከተሞች መካከል እንደ ሮሜና እንደ ቆሮንቶስ ላሉ ከተሞች ቅዱስ ጳውሎስ በአመጋገብ ጉዳይ ሁለቱን ለማስማማት እጅግ በጥንቃቄ ጽፎላቸዋል ሮሜ 14:17-23፣ 1ቆሮ 6:12፣ 10:23፣ ቲቶ 1:15 ገላ 2:11 ስለ አመጋገብ ሁሉ እንደተፈቀደልን ይገልጽና ነገር ግን ስለ ሁለት ነገር ደግሞ መከልከል እንዳለብን ያስረዳል
የመጀመሪያው ከአእምሮ የተነሣ ለአእምሯችን የሚመች መስሎ ካልታየን መተው እንደሚገባንና አለመብላት እንደሚሻል
ሁለተኛው በእኛ ምክንያት ሰዎች የሚሰናከሉ ከሆነ ደግሞ መተው እንዳለብን ይጠቅሳል

🤔,በሚበሉ እንስሳት መካከልም ሰሞኑን በእግረኛው ሚዲያ የቀረበው ጉዳይ ንግግሩ ምንም ስህተት ሳይኖርበት የአቀራረብ ስህተትና ግዴለሽነት ግን አለበት
ሁላችንም እንደምናውቀው የመጀመሪያ የጉባኤ ቤትም ሆነ የኮሌጅ ክርክሮቻችን ከሚባሉት ነገሮች አንዱ ይህ የምግብ ጉዳይ ሲሆን ታላላቅ መምህራን ግን ጥንቃቄና ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ መልስ ይሰጡበት ነበር
ዛሬ ይሄንን እረስተው ሊቀ ጳጳሱን ጀግና እያሉ የሚያሞጋግሱ ኃላፊነት የሌለበት መልስ መሆኑን የዘነጉና ሌሎች ደግሞ እንደ ትልቅ ክህደት ቆጥረው ሊቀ ጳጳሱ ላይ የትችት ውርጅብኝ የሚያቀርቡ አሉ
ቤተ ክርስቲያን አኃቲ ናት ማለት ሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናት ናቸው ማለት አመጋገባቸው ሁሉ እንደ እኛ ሆኖ ይመስለናል እንዴ?
ቻይናዊው ጃፓናዊው አሜሪካዊው አውሮፓዊው አረቡ አፍሪካዊው ወደ ኦርቶዶክስ ገባ ሲባል አመጋገቡን ሁሉ ቀይሮ ይመስለናል እንዴ? አይደለም እኮ
ነገር ግን እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳውያን ልክ እንደ አይሁድ ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ቀጥታ ስለተሸጋገርን ልክ እንደ አይሁድ የአመጋገብ ሥርዓታችንም ከተፈጥሮ ሕግ ጋር የተስማማ ነውና ከባህል ከማንነት ከትላንት ታሪክ አንጻር ብዙዎችን አንመገብም የማንመገበው የረከሱ ናቸው ብለን ሳይሆን በባህልም በሥርዓትም ሳንመገባቸው ስለኖርን አእምሯችን ስለማይቀበላቸውም ነው

እንደ እኔ እንደ እኔ እዚህ ሚዲያ ላይም ጠያቂውም ሆነ መላሹ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ ለምዕመኑ እንዴት ይረዳዋል የሚል ኃላፊነትን ያልተላበሰ ጥያቄና መልስ ነው የተካሄደው
ጥያቄው የሕዝብ ነው ወይ?
ምን ምን እንብላ ብሎ የጠየቀ አለ ወይ?
ተፈቅዷል መባልስ ለምን ጉዳይ ነው? የሚሉትን ሳያካትት ቀጥታ ደረቅ ጥያቄና መልስ ስለሆነ እንጂ ፕሮግራሙ ጥፋት የለበትም
እኛ ኢትዮጵያውያን በባህላችን በሥርዓታችን ያልተለመደ ነገር መብላት የሌለብን እርኩስ ስለሆነና ኃጢያትም ስለሆነ ሳይሆን በሥርዓት እጅግ ያሸበረቅን ልክ እንደ አይሁድ የኦሪት መሠረት ያለን ባህላችንም የማይፈቅደው አእምሯችንም የማይቀበለው ስለሆነ ያልተለመዱትን ብንበላ
አንደኛ ለሌሎች እንቅፋት እንሆናለን
ሁለተኛ ለሌላ የግዴለሽነት ኃጢያት እንገፋፋለን
ሦስተኛ አእምሯችን የማይቀበለው ነገር ስለሆነ አእምሯችን የማይቀበለውን ነገር በማድረጋችን የመበደልና የመርከስ ስሜት ስለሚፈጠር ከዚህም የተነሣ እንዳንበላ ይመከራል እንጂ ብዙ በሀገራችን የማንበላቸው ነገሮች የማይበሉት ሕገ ወንጌል ከልክሎና ቤተ ክርስቲያንም አትብሉ ብላን አይደለም ይህም ሊታወቅ ከኦርቶዶክሳውያን ውጪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሳይቀሩ አልፎ አልፎ የተወሰኑትን ካልሆነ በስተቀር ይህንን ሲያደርጉት አይታይምና
ሊቀ ጳጳሱም ሆነ ጠያቂው እንደ እውቀት ትክክል ቢሆኑም እንደ ኃላፊነት ግን አጀንዳ እየፈጠሩ ለሌሎች ነገሮች በር ከመክፈት ይልቅ በቁዔት ያለውና ኃላፊነት የሚሰማው ንግግር አላደረጉምና ቢያስወቅስ እንጂ የሚያስመሰግን ሥራ አይመስለኝም
በመሠረቱ የልጁ ጥያቄ መንገድ የሚያስት ቢሆንም ሊቀ ጳጳሱ በተረጋጋ ስሜትና በአባታዊ ጥበብ መልስ እየሰጡ ነበር የእንስሳትን ዝርዝር እየጠራ ሲናገር እርሳቸውም በቁጥብነት እንዴት እንደመለሱ በጣም ገርሞኛል ከዚያ በተረፈ ሊቀ ጳጳሱ ላይ ሌላ ቅሬታ ካለን በሌላ ነገር መውቀስ እንጂ እዚህ ላይ ግን ከክርስትናው አስተምህሮ የተንሸራተቱበትም ሆነ ያጠፉት ጥፋት አይታየኝም ጥያቄውን በተጻፈው የመጽሐፍ ቃል ልክ መልሰውታል እንደ ሚዲያ ግን ለሕዝብ መገለጽና መተንተን ባለበት ልክ የተተነተነና የቀረበ አይመስለኝም ይህ ደግሞ አጠቃላይ የኦርቶዶክሳውያን ባለ ሚዲያዎች ሁሉ የሚመስል ችግር ነው አጀንዳ መምዘዝና ብዙ ሰው ፕሮግራሙን እንዲያደምጠው ለማድረግ ከማሰብ የዘለለ ብዙ ሰው ይማርበታል ወይ የሚል የኃላፊነት ስሜት ብዙም አይታይባቸውም።
ወቀሳውም ቢሆን ያን ያህል አጀንዳ ለመሆንም አያበቃምና ነገሩን ከልኩ በላይ አናስጩኸው እላለሁ።

መ/ር ዘላለም

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
የወይን ባለቤት 
                                                  
Size:- 72MB
Length:-1:18:41
       
     በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
ታላላቅ ሥራን አድርጎልኛልና 
                                                  
Size:- 102MB
Length:-1:33:17
       
     በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
፪. #ገዳመ_አባ_ጽጌ_ድንግል_ገዳም_
አድራሻው፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ → ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፤
ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎጃም (በመርጡለ ማርያም) → መካነ ሰላም ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፤
ወይም፤ ከአ.አ. ቦሌ መርካቶ አውቶቡስ ተራ → መርሐ ቤቴ ወግዲ → ገዳመ ጽጌ፡፡

፫. #አምባ_ጽጌ_ድንግል_ገዳም
አድራሻው፤ ዋግኽምራ ሀገረ ስብከት፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ላሊበላ → ሰቆጣ (ዋግኽምራ)፡፡

፬. #ጎንደር_ደብረ_ፀሐይ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፥ ቸቸላ (ሆስፒታል አጠገብ)፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር ከተማ → ሆስፒታል → ቊስቋም፤

፭. #ደሴ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት፥ ደሴ ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደሴ ከተማ፡፡

#ከኢትዮጵያ_ውጭ_የሚከብርባቸው_ #፩ #ጥንታውያን_ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. #ግብፅ_ቊስቋም _ማርያም_ገዳም_፤
(#እስከ_ቅርብ_ዘመናት_በግብፅ_የኢትዮጵያ_ርስት_የነበረ_)
አድራሻው፤ ግብፅ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ → ግብፅ → ገዳመ ቊስቋም፤

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
2024/11/15 01:05:40
Back to Top
HTML Embed Code: