Telegram Web Link
Forwarded from የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ("የአምር አቡክሙ ሰማያዊ ዘትፈቅዱ ዘእንበለ ትስአልዎ።" ማቴ. ፮፡፰)
#የግሥ #ጥናት #ክፍል #አንድ
ግእዝ=አማርኛ
፩) ሃልሀ=ወደረ (የከብት)
፪) ለሕሐ=ቀዳ (የውሃ የመጽሐፍ)
፫) ላሕልሐ=ራሰ
፬) ለስሐ=አልጫ ሆነ (የወጥ)
፭) ለቅሐ=አበደረ
፮) ለብሐ=ሠራ (የሸክላ ብቻ)
፯) ለትሐ=ተጎነጨ (የመጠጥ)
፰) ሎሐ=ጻፈ
፱) ለጥሐ=ገበረ
፲) ማሕምሐ=አፈረሰ
፲፩) መልኀ=መዘዘ
፲፪) መልሐ=አጣፈጠ
፲፫) መስሐ=ምሳ አደረገ
፲፬) መርሐ=መራ
፲፭) ሞርቅሐ=ላጠ
፲፮) ሞቅሐ=አሰረ (የሰው ብቻ)
፲፯) መትሀ=ሣሣ፣ቀጠነ (የመርቀቅ)
፲፰) መንዝሐ=ተደላደለ
፲፱) መድሐ=ፈጨ
፳) ሞጥሐ=ለበሰ
፳፩) ሰርሐ=ሠራ
፳፪) ሠርሐ=አቅናና፣አከናወነ
፳፫) ሣርኀ=አበራ
፳፬) ሰብሐ=አመሰገነ
፳፭) ሠብሐ=ስብ ሆነ (የከብት)
፳፮) ሰንሐ=በራ ሆነ
፳፯) ሰይሐ=ታመመ
፳፰) ሴሐ=ወገጠ
፳፱) ሰጥሐ=አሰጣ፣ ዘረጋ
፴) ሰፍሐ=ሰፋ (ሰፊ ሆነ)
፴፩) ረምሐ=ወጋ (የጦር)
፴፪) ረስሐ=ጎሰቆለ
፴፫) ረቅሐ=ጋረጠ (የጋሬጣ)
፴፬) ረብሐ=ረባ
፴፭) ረውሐ=ቀደደ
፴፮) ሮሐ=ወለወለ፣አራገበ፣አናፈሰ
፴፯) ቀሕቅሐ=ተንቆራቆሰ፣አሰምቶ ተናገረ
፴፰) ቈልሐ=ፍሬ ያዘ
፴፱) ቀምሐ=አፈራ
፵) ቀርሐ=ጨለጠ
፵፩) ቃርሐ=ተኰሰ
፵፪) ቄሐ=ቀላ (የመቅላት)
፵፫) ቀድሐ=ቀዳ (የመጽሐፍ የውሃ)
፵፬) በኅብኀ=ከረፋ፣ቀረና
፵፭) በኍበኈ=ሸተተ፣ በሰበሰ
፵፮) በልኀ=ተሳለ፣ስለት ሆነ
፵፯) ባልሐ=አዳነ
፵፰) በርሀ=ብርሃን ሆነ
፵፱) በርሐ=በራ ሆነ
፶) በዝኀ=በዛ
፶፩) በጥሐ=በጣ
፶፪) በጽሐ=ደረሰ
፶፫) ታሕትሐ=ፈላ
፶፬) ተመክሐ=ተመካ
፶፭) ቶስሐ=ጨመረ
፶፮) ተራኅርኀ=ቸር ሆነ፣ራራ
፶፯) ተቃድሐ=ተደነባበረ (የድንበር)
፶፰) ተበውሐ=ሠለጠነ፣ፈቃድ ተቀበለ
፶፱) ተንሀ=አገመ
፷) ተወፅሐ=ተፈጨ፣ተቆላ (የመከራ)
፷፩) ተዋህውሀ=ተመላለሰ
፷፪) ተየውሃ=የዋህ ሆነ፣ ተሞኘ፣ ገራም ሆነ
፷፫) ቴሀ=ቀላወጠ
፷፬) ተጋህግሀ=ክፍት ክፍት አለ
፷፭) ተጋውሐ=ጎረቤት ሆነ
፷፮) ተግሀ=ተጋ
፷፯) ተጻብሐ=እንዴት አድርህ ተባባለ
፷፰) ተፈሥሐ=ደስ ተሰኘ
፷፱) ናሕንሐ=ትርፍርፍ አለ
፸) ነስሐ=ተጸጸተ
፸፩) ነስኀ=ሸተተ፣ከረፋ
፸፪) ነቅሀ=ነቃ
፸፫) ነብሐ=ጮኽ (የውሻ፣የሰው፣የንብ)
፸፬) ኖኀ=ረዘመ
፸፭) ነዝሀ=ረጨ
፸፮) ነድሐ=ነዳ
፸፯) ነግሀ=ነጋ
፸፰) ነጽሐ=ንጹሕ ሆነ፣ነጻ
፸፱) ነፍኀ=ነፋ፣ቀበተተ
፹) አምኀ=እጅ ነሣ
፹፩) አመልትሐ=አመሳቀለ
፹፪) አመርግሐ=አንከባለለ
፹፫) አመድቅሐ=ሠራ (የቤት)
፹፬) አመብኵሐ=አናፋ (የእሳት የትንፋሽ)
፹፭) አስተማዝሐ=አቀበጠ አቀማጠለ
፹፮) አርሳሕስሐ=አረሳሳ፣አስነወረ
፹፯) አቅያሕይሐ=አቅላላ
፹፰) አብሐ=አሰናበተ
፹፱) አንሳሕስሐ=አነሳሳ ተነሳሳ
፺) አንቆቅሐ=ቋቋ (የእንቁላል)
፺፩) አንባሕብሐ=ዱብ ዱብ አደረገ
፺፪) አንካሕክሐ=ፈተፈተ
፺፫) አንግሀ=ማለደ
፺፬) አውጽሐ=አቀረበ ቀዳ
፺፭) ኤኀ=ጠፋ
፺፮) አጸንሕሐ=አሻተተ
፺፯) አጽናሕንሐ=ወዘወዘ (የጽና)
፺፰) ከልሐ=ጮኽ (የሰው የከብት)
፺፱) ከልትሐ=አሰረ (የነዶ)
፻) ኰስሐ=ተናጻ
፻፩) ኰርሀ=ግድ አለ
፻፪) ወክሐ=ደነፋ፣ ፎከረ
፻፫) ወጥሐ=ከመረ፣ ደረደረ
፻፬) ዛሕዝሐ=ትርፍርፍ አለ
፻፭) ዘልሐ=ጠመቀ (የጠላ)
፻፮) ዘብሐ=አረደ
፻፯) ዘግሐ=ዘጋ
፻፰) የውሀ=አታለለ
፻፱) ደኅኀ=ጸና
፻፲) ደምሐ=ጠለቀ
፻፲፩) ደርግሐ=ደረተ፣ሰፋ
፻፲፪) ደቅሐ=ደቃ፣ቀጠቀጠ
፻፲፫) ገህሀ=አበራ
፻፲፬) ጋህግሀ=ክፍት ክፍት አደረገ (የመስኮት)
፻፲፭) ገምሀ=ነጨ፣አለፋ፣መለጠ (የቆርበት)
፻፲፮) ገርሀ=ገራ፣ግር ሆነ (የጠባይ የእርሻ)
፻፲፯) ጎርሐ=ተተነኳኮለ
፻፲፰) ገንሐ=ተቆጣ
፻፲፱) ጎሐ=ጠባ፣ነጋ
፻፳) ጠብሐ=አረደ
፻፳፩) ጠፋልሐ=መዘነ
፻፳፪) ጠፍሐ=አጨበጨበ
፻፳፫) ጻሕጽሐ=አጎረፈ
፻፳፬) ጸርሐ=ጮኸ
፻፳፭) ጸብሐ=ጠባ
፻፳፮) ጸብሐ=ገበረ
፻፳፯) ጸንሐ=ቆየ
፻፳፰) ጼሐ=ጠረገ
፻፳፱) ጸፍሐ=ገለበጠ፣ለመጠ
፻፴) ፈልሐ=ፈላ
፻፴፩) ፈርሀ=ፈራ
፻፴፪) ፈትሐ=ፈታ፣ፈረደ
፻፴፫) ፎሐ=ገመሰ
፻፴፬) ፈጽሐ=ገመሰ፣ሰነጠቀ፣ፈነቀለ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#የግሥ #ጥናት #ክፍል #ሁለት
ግእዝ=አማርኛ
፩) ሐለለ=አረረ፣በራ፣ተቃጠለ
፪) ሐመለ=ለቀመ፣ቀነጠሰ
፫) ሐሰለ=ለበበ (የልጓም)
፬) ሐቀለ=ቀማ
፭) ኀበለ=ተደፋፈረ
፮) ሐበለ=ታታ
፯) ሐብለ=ዋሸ
፰) ሐንበለ=ጫነ (የኰረቻ)
፱) ሖለ=ቀላቀለ፣አደባለቀ
፲) ሐዘለ=አዘለ
፲፩) ኀየለ=በረታ
፲፪) ኄለ=መነጨ
፲፫) ሀጕለ=ጠፋ
፲፬) ሐፈለ=ቁንጥር ቁንጥር አለ (የስካር)
፲፭) መሐለ=ማለ
፲፮) መለለ=ላገ፣ጠረበ፣አለሰለሰ (የእንጨት)
፲፯) መምዔለ=ወነጀለ
፲፰) መሰለ=መሰለ
፲፱) መሰለ=ጣዖት ሠራ
፳) መበለ=ብልጭ አለ
፳፩) መዐለ=ወነጀለ
፳፪) መከለ=ቆረጠ
፳፫) ሞጽበለ=ሞረደ
፳፬) ሰሐለ=ሳለ (የብረት)
፳፭) ሳሕለለ=ደረቀ
፳፮) ሰመለ=አለዘበ (የጠባይ የእንጨት)
፳፯) ሰሰለ=ወገደ
፳፰) ሰቀለ=ሰቀለ
፳፱) ሰብለ=ዘረዘረ
፴) ሰንሰለ=አያያዘ፣አቆራኘ
፴፩) ሰአለ=ለመነ
፴፪) ሰከለ=አፈራ
፴፫) ሶለ=ሸተ፣ጮረቃ
፴፬) ሰደለ=መዘነ
፴፭) ሰገለ=ጠነቆለ
፴፮) ሰፈለ=መታ፣ቀጠቀጠ (የዱቄት የብረት)
፴፯) ረመለ=ጠነቆለ
፴፰) ሮለ=በሳ፣ቀደደ
፴፱) ረገለ=ቀዘፈ
፵) ቀለ=ቀለለ
፵፩) ቈልቈለ=ዘቀዘቀ
፵፪) ቈስለ=ቆሰለ
፵፫) ቀበለ=ሸኘ
፵፬) ቀብለ=ጎደለ፣አነሰ
፵፭) ቀተለ=ገደለ
፵፮) ቀፈለ=ለበጠ፣ሸለመ
፵፯) ብህለ=አለ
፵፰) በልበለ=አረጀ፣አለቀ (የልብስ)
፵፱) በሰለ=በሰለ
፶) በቈለ=በቀለ
፶፩) ብዕለ=ባዕለጸጋ ሆነ
፶፪) ቤዐለ=ወደደ
፶፫) በአለ=እንቢ አለ
፶፬) ቤወለ=ወደደ
፶፭) በጠለ=ጠፋ
፶፮) በጸለ=ቦጨቀ
፶፯) ትሕለ=ቀላወጠ
፶፰) ተልዕለ=ከፍ ከፍ አለ
፶፱) ተማሕለለ=ምሕላ ያዘ
፷) ተመዝጎለ=ተከራከረ
፷፩) ተሠሀለ=ይቅር አለ
፷፪) ተሰአለ=ተጠያየቀ፣ጠየቀ
፷፫) ተሰነአለ=ተስማማ
፷፬) ተቀበለ=ተቀበለ
፷፭) ተቀጸለ=ተቀዳጀ
፷፮) ተበቀለ=ቂም ያዘ፣ተበቀለ
፷፯) ተንበለ=ለመነ
፷፰) ተአንተለ=ቸል ቸል አለ
፷፱) ተዐገለ=ቀማ
፸) ተከለ=ተከለ
፸፩) ተኬወለ=ወደኋላ አላ
፸፪) ተወከለ=ታመነ
፸፫) ተድሕለ=ኮበለለ
፸፬) ተደንገለ=ተጠበቀ፣ድንግል ሆነ
፸፭) ተዳወለ=ተዳካ፣ተዋሰነ
፸፮) ተጋደለ=ተጋደለ
፸፯) ተፋወለ=አሟረተ
፸፰) ንኅለ=ፈረሰ
፸፱) ነቀለ=ነቀለ
፹) ነዐለ=ተጫማ
፹፩) ነደለ=በሳ
፹፪) ነጸለ=ለየ፣ነጠለ
፹፫) አሕመልመለ=ለመለመ፣አለመለመ
፹፬) ዐለለ=ጎለተ፣ርስት ጉልት አደረገ
፹፭) አመስቀለ=አመሳቀለ
፹፮) አማዕቀለ=ጥልቅ አደረገ
፹፯) አማዕበለ=ማዕበል አደረገ
፹፰) አማእከለ=መካከል አደረገ
፹፱) አመድበለ=አከማቸ
፺) አስተሰነአለ=አስማማ፣ተስማማ፣ ተሰነባበተ
፺፩) አቍጸለ=ለመለመ፣አለመለመ
፺፪) አብዐለ=አከበረ
፺፫) ዐበለ=አሰኘ
፺፬) አንሳሕለለ/አንዛሕለለ=አለ ዘለል አለ (ሥራ የመፍታት)
፺፭) አንቀልቀለ=ተነዋወጠ፣አነዋወጠ
፺፮) አንበልበለ=ነበልባል አደረገ
፺፯) አንኮለለ=ዱብ ዱብ አደረገ
፺፰) አንጦለለ=ለየ
፺፱) አከለ=በቃ፣ልክ ሆነ
፻) ዐዘለ=በረታ
፻፩) ዔለ=ዞረ፣ተንከረተተ
፻፪) ዐገለ=አቆመ፣በገረ፣አስበገረ፣ ደረደረ
፻፫) አገንጰለ=ጻፈ፣ገለበጠ
፻፬) አጰንገለ=ተረጎመ፣ጻፈ
፻፭) አጽለለ=አረፈ፣አሳረፈ
፻፮) አጽደልደለ=አበራ
፻፯) ክህለ=ቻለ
፻፰) ኵሕለ=ኳለ
፻፱) ከለለ=ጋረደ
፻፲) ከፈለ=ከፈለ
፻፲፩) ወዐለ=ዋለ
፻፲፪) ዝሕለ=ዛገ፣አደፈ፣ሻገተ (የወርቅ የብረት)
፻፲፫) ዘለለ=ጠመቀ፣ዘለለ (የጠላ)
፻፲፬) ዘበለ=ተናጻ
፻፲፭) ዘወለ=አቀለመ፣አጠቆረ
፻፲፮) ደለለ=ከፈከፈ፣ደለለ (የቤት የሰው)
፻፲፯) ደበለ=ሰበሰበ፣አከማቸ
፻፲፰) ገልገለ=ገላገለ
፻፲፱) ገንጰለ=ገለበጠ
፻፳) ገደለ=ጣለ (የጥንብ)
፻፳፩) ጥሕለ=አተለ (የሚያትል ሁሉ)
፻፳፪) ጠለ=ለመለመ
፻፳፫) ጠቀለ=በነገር ነካ
፻፳፬) ጤቀለ=ጻፈ
፻፳፭) ጠብለለ=ጠቀለለ
፻፳፮) ጸሐለ=ሠራ (የብረት)
፻፳፯) ጸለለ=ጋረደ
፻፳፰) ጸለለ=ተንኳፈፈ
፻፳፱) ጸበለ=ትቢያ ሆነ
፻፴) ጸንጸለ=መታ
፻፴፩) ጸዐለ=ሰደበ
፻፴፪) ጽእለ=ቆሰለ
፻፴፫) ጸደለ=በራ
፻፴፬) ፈሐለ=ቁንጥር ቁንጥር አለ
፻፴፭) ፈልፈለ=መነጨ
፻፴፮) ፈተለ=ፈተለ
፻፴፯) ፈደለ=ጻፈ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#የግሥ #ጥናት #ክፍል #ሦስት
ግእዝ=አማርኛ
፩) ሐለመ=አለመ (የሕልም)
፪) ሐመ=ታመመ
፫) ሐመመ=ተመቀኘ
፬) ሐሠመ=ከፋ
፭) ሐረመ=ተወ
፮) ሐርተመ=ጎሰቆለ
፯) ኀተመ=አተመ
፰) ሐከመ=አከመ
፱) ሀደመ=አንቀላፋ
፲) ሐደመ=አወጋ፣ተረተ
፲፩) ልሕመ=ላመ
፲፪) ለምለመ=ለመለመ
፲፫) ለተመ=አሸ፣ፈተገ፣ወገጠ፣ ልጦ ጉርድ አወጣ
፲፬) ለጎመ=ለጎመ፣ገታ
፲፭) ሰለመ=ፈታ
፲፮) ሠረመ=አጠለቀ፣አሰጠመ
፲፯) ሶርየመ/ሶርዔመ=ለምድ አወጣ
፲፰) ሰቀመ=ማረከ
፲፱) ሰተመ=ደረሰ
፳) ሰዐመ=ሳመ
፳፩) ሰከመ=ተሸከመ
፳፪) ሤመ=ሾመ
፳፫) ሰገመ=አሰረ
፳፬) ረመ=ራመመ (የብራና)
፳፭) ረመመ=ጻፈ
፳፮) ረቀመ=ረጨ (የቀለም)
፳፯) ረዐመ=ጮኽ
፳፰) ሬመ=ከፍ ከፍ አለ፣ወጣ (የሰማይ የደርብ)
፳፱) ረገመ=ረገመ
፴) ቀለመ=ጻፈ
፴፩) ቀሠመ=ለቀመ
፴፪) ቀሰመ=አጣፈጠ
፴፫) ቀረመ=ለቀመ
፴፬) ቆመ=ቆመ
፴፭) ቀደመ=ቀደመ
፴፮) ብህመ=ዲዳ ሆነ
፴፯) በለመ=ጻፈ
፴፰) ተለመ=ተለመ (የእርሻ)
፴፱) ተሳለመ=ተፈቃቀረ
፵) ተሰዐመ=ተስማማ
፵፩) ተሰጥመ=ተሰጠመ
፵፪) ተርጎመ=ተረጎመ
፵፫) ተቃወመ=ተከራከረ
፵፬) ተቀየመ=ቂም ያዘ
፵፭) ተነወመ=አለመ
፵፮) ተደመ=ተደነቀ
፵፯) ተጽመመ=ቸል ቸል አለ
፵፰) ተፍእመ=ጎረሰ
፵፱) ንእመ=አክ አለ
፶) ኖመ=ተኛ
፶፩) ዐለመ=ፈጠረ
፶፪) አስተሐመመ=አስተጋ፣ተጋ
፶፫) አስተቃሰመ=አሟረተ
፶፬) አርመመ=ዝም አለ
፶፭) አልኰመ=አስነካ (የነገር፣የመንካ፣የከንፈር)
፶፮) ዐቀመ=ለካ
፶፯) ዐቀመ=ቆረጠ (የነገር)
፶፰) ዐተመ=ተቆጣ
፶፱) አነመ=ሠራ (የልብስ)
፷) ዔመ=መሰገ፣ሰበሰበ
፷፩) አደመ=አማረ
፷፪) አግደምደመ=አግደመደመ (የእግር)
፷፫) ከመመ=ቆረጠ፣አስተካከለ
፷፬) ከረመ=የወይን ጠጅ አደረገ
፷፭) ከርመ=ከረመ
፷፮) ከተመ=ጫፍ ሆነ
፷፯) ወስከመ=ሰነገ፣አሰረ፣ጠለፈ (የማነቂያ)
፷፰) ዝሕመ=ሞቀ
፷፱) ዘመመ=አሰረ፣ ለጎመ፣ አፈነ፣ ዘመመ፣ ለበበ
፸) ዘንመ=ዘነበ
፸፩) ዳሕመመ=አፈረሰ፣ናደ
፸፪) ደምደመ=አጎተነ፣አጎፈረ (የጸጉር)
፸፫) ደክተመ=ድኻ አደግ ሆነ
፸፬) ደክመ=ደከመ
፸፭) ደገመ=ደገመ
፸፮) ገረመ=ተፈራ፣አስፈራ
፸፯) ጎርየመ/ጎርዔመ=አገመ
፸፰) ገዘመ=ቆረጠ
፸፱) ገደመ=አገደመ፣ገደመ (የነገር የመንገድ የገዳም)
፹) ጠለመ=ከዳ፣ሸፈተ
፹፩) ጠመ=ጠመመ
፹፪) ጠቀመ=ሠራ፣አደሰ (የግንብ)
፹፫) ጥዕመ=ቀመሰ
፹፬) ጦመ=ጠቀለለ፣ጠመጠመ፣አጠፈ
፹፭) ጽሕመ=በቀለ
፹፮) ጸልመ=ጠቆረ
፹፯) ጸመ=ደነቆረ
፹፰) ፀመ=ደረቀ
፹፱) ጸምጸመ=ሠራ፣ጨመጨመ (የቤት)
፺) ጸተመ=ደረሰ
፺፩) ጾትኤመ/ጾትየመ/ጾተመ=የወይን ጠጅ አደረገ
፺፪) ጾመ=ጾመ
፺፫) ፀገመ=ጠመመ
፺፬) ፍሕመ=ፋመ፣ሞገደ
፺፭) ፈለመ=ጀመረ
፺፮) ፈፀመ=ነጨ (የፊት)
፺፯) ፈጸመ=ጨረሰ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የግሥ ጥናት ክፍል አራት
ግእዝ=አማርኛ
፩) ኀመሰ=አምስት አደረገ
፪) ኀሠሠ=ፈለገ
፫) ኈሠሠ=ጠረገ
፬) ሐረሰ=አረሰ
፭) ኀበሰ=ጋገረ
፮) ሐንከሰ=አነከሰ
፯) ሖሰ=ቀላቀለ
፰) ሖሰ=ነቀነቀ፣አንቀሳቀሰ
፱) ኄሰ=ተሻለ
፲) ሔሰ=ነቀፈ፣ሰደበ
፲፩) ሐደሰ=አዲስ አደረገ
፲፪) ሐፈሠ=ዘገነ
፲፫) ላቀሰ=አለቀሰ
፲፬) ለብሰ=ለበሰ
፲፭) ለንጰሰ=ሠራ (የልብስ)፣ ተንቦገቦገ (የብርሃን)
፲፮) ሎሰ=ለወሰ
፲፯) መሐሰ=ቆፈረ
፲፰) መለሰ=መለሰ
፲፱) መረሰ=ነከረ፣ዘፈቀ
፳) መርሰሰ=ዳሰሰ፣ነካ
፳፩) መቈሰ=አጠፋ
፳፪) መንኰሰ=መነኮሰ
፳፫) ሜሰ=አደለ፣አሳለፈ
፳፬) ሠለሰ=ሦስት አደረገ
፳፭) ሰንኰረሰ=አስተማረ
፳፮) ሰኰሰ=ጠረገ
፳፯) ሰደሰ=ስድስት አደረገ
፳፰) ርሕሰ=ራሰ፣ረጠበ
፳፱) ረምሰ=ጋለ
፴) ረመሰ=ዘፈቀ፣ነከረ፣ዘፈዘፈ
፴፩) ርእሰ=አለቃ ሆነ
፴፪) ረኵሰ=ረከሰ
፴፫) ሮሰ=ወለደ
፴፬) ቆመሰ=ቆሞስ ሆነ
፴፭) ቀሰ=አገለገለ
፴፮) ቀደሰ=አመሰገነ
፴፯) በስበሰ=አረጀ፣በሰበሰ
፴፰) ብእሰ=ባሰ፣ከፋ
፴፱) ተሞገሰ=ባለሟል ሆነ፣ተወደደ
፵) ተቃለሰ=ታገለ
፵፩) ተበአሰ=ተጣላ
፵፪) ተተረአሰ=ተንተራሰ
፵፫) ተአንሰሰ=እንስሳ ሆነ፣ተሞኘ
፵፬) ተዐገሠ=ቻለ፣ታገሠ
፵፭) ተከነሰ=አንድ ሆነ፣ተቀላቀለ
፵፮) ተከውሰ=ተነቃነቀ
፵፯) ተኬሰ=መታ፣ጠመጠመ፣ መነጨ
፵፰) ተውሕሰ=ዋስ ሆነ፣ተዋሰ
፵፱) ተግሕሠ=ወገደ፣ሸሸ
፶) ተጰጰሰ=ጳጳስ ሆነ
፶፩) ተጸነሰ=ተቸገረ
፶፪) ተፈርነሰ=ተደሰተ፣ተፈረነሰ
፶፫) ተፋሰሰ=እጣ ተጣጣለ
፶፬) ነሐሰ=ሠራ (የቤት፣የመዳብ)
፶፭) ነስነሰ=ጎዘጎዘ፣ነሰነሰ
፶፮) ንእሰ=አነሰ
፶፯) ነግሠ=ነገሠ
፶፰) ነፍሰ=ነፈሰ
፶፱) አልኈሰሰ=ሹክ ሹክ አለ
፷) አመርሰሰ=ጸጥ አደረገ
፷፩) አስተንፈሰ=አሻተተ
፷፪) አርመስመሰ=አጥመሰመሰ፣ አንኮሻኮሸ፣ አርመሰመሰ
፷፫) አበሰ=በደለ
፷፬) አነሰ=አነሰ፣ሰው ሆነ
፷፭) አንበስበሰ=ተገለባበጠ፣ አገለባበጠ
፷፮) አክሞሰሰ=ፍግግ ፍግግ አለ
፷፯) አኮሰ=አቅባባ፣አዋሐደ፣ አገናኘ፣ አማሰለ
፷፰) ዔሰ=ዞረ፣ዛበረ
፷፱) ዐጠሰ=አነጠሰ
፸) አጽሐሰ=አሸበሸበ
፸፩) አፅበሰ=ልምሾ አደረገ
፸፪) ኵሕሰ=ተናጻ
፸፫) ከልሰሰ= አሰረ (የነዶ)
፸፬) ኰስኰሰ=ተዝጎረጎረ
፸፭) ከበሰ=ጠመጠመ
፸፮) ወረሰ=ወረሰ
፸፯) ወቀሠ=ወቀሠ
፸፰) ወደሰ=አመሰገነ
፸፱) ወጠሰ=አቃጠለ፣ተቃጠለ
፹) ዘልገሰ=ታመመ፣ቆሰለ፣አበጠ
፹፩) የብሰ=ደረቀ
፹፪) ደሐሰ=ሠራ (የዳስ)
፹፫) ደመሰ=ጨለመ
፹፬) ደምሰሰ=አጠፋ፣ደመሰሰ
፹፭) ደረሰ=ደረሰ (የድርሰት)
፹፮) ደቀሰ=ተኛ፣አንቀላፋ
፹፯) ደነሰ=ኃጢአት ሠራ
፹፰) ደጎሰ=ደጎሰ
፹፱) ግሕሰ=ወገደ
፺) ገመሰ=ገመሰ
፺፩) ገሰሰ=ዳሰሰ
፺፪) ገረሠ=ሠራ (የወርቅ)
፺፫) ገብሰሰ=አረጀ
፺፬) ጌሠ=ገሠገሠ
፺፭) ጠረሰ=አፋጨ
፺፮) ጠበሰ=ጠበሰ
፺፯) ጤሰ=ጤሰ
፺፰) ፀረሰ=በለዘ
፺፱) ፀበሰ=ልምሾ ሆነ
፻) ፀንሰ=ፀነሰ
፻፩) ፀወሰ=ሰለለ (የሕማም)
፻፪) ፈሐሰ=ፈተለ (የፈትል)፣ አበበ (የአበባ)
፻፫) ፈለሰ=ተሰደደ
፻፬) ፈወሰ=አዳነ
፻፭) ፈደሰ=ቆራ (የሳዱላ)

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የግሥ ጥናት ክፍል አምስት
ግእዝ=አማርኛ
፩) ኀስረ=ጎሰቆለ
፪) ሐረረ=አረረ፣ተኮሰ፣ሞቀ
፫) ሐብረ=አንድ ሆነ፣ተባበረ
፬) ኆበረ=ሸለመ
፭) ሐንገረ=እሽኮኮ አለ
፮) ሖረ=ሔደ
፯) ኀደረ=አደረ
፰) ሐጸረ=አጠረ
፱) ኀጽረ=አጭር ሆነ፣አጠረ (የቁመት፣ የጊዜ)
፲) ኀፈረ=ወደደ
፲፩) ኀፍረ=አፈረ
፲፪) ሎረ=በሳ
፲፫) ለጠረ=መዘነ
፲፬) መሀረ=አስተማረ
፲፭) መረ=መረረ
፲፮) መተረ=ቆረጠ
፲፯) መከረ=መከረ
፲፰) መከረ=ጠበሰ
፲፱) መዘረ=ጠመቀ፣ዘለለ (የጠላ)
፳) መዝበረ=ፈረሰ፣ተናደ፣ተበተነ
፳፩) መደረ=ጸና
፳፪) መጸረ=አመሰኳ
፳፫) መቈረ=አጣፈጠ
፳፬) ሠምረ=ወደደ
፳፭) ሰረረ=ወጣ
፳፮) ሣረረ=ሠራ (የቤት)
፳፯) ሰቈረ=በሳ
፳፰) ሰበረ=ሰበረ
፳፱) ሰተረ=ቀደደ
፴) ሰዐረ=ሻረ
፴፩) ሥዕረ=ለመለመ
፴፪) ሰክረ=ሰከረ
፴፫) ሰወረ=ሸሸገ
፴፬) ሰዘረ=ሰነዘረ
፴፭) ሠገረ=ተራመደ
፴፮) ሠጸረ=ሰነጠቀ፣ፈለጠ
፴፯) ሰፈረ=ለካ፣ሰፈረ
፴፰) ቀሐረ=ተኰሰ (የሕማም)
፴፱) ቀመረ=ቆጠረ
፵) ቈረ=ቀዘቀዘ
፵፩) ቀበረ=ቀበረ
፵፪) ቆበረ=ጭጋግ ሆነ
፵፫) ቀተረ=ሳበ
፵፬) ቀትረ=ቀትር ሆነ
፵፭) ቈጰረ=ቆረጠመ
፵፮) ቀጸረ=ከበበ፣ቀጠረ፣አጠረ (የአጥር)
፵፯) ቈጸረ=ቋጠረ
፵፰) ቀፈረ=ለካ፣ሳበ፣ገተረ (የጦር የደጋን)
፵፱) ባሕረረ=ብርር ብርር አለ፣ባከነ፣ ደነገጠ፣ሰፋ (የመብረር)
፶) በረ=በረረ፣ሮጠ
፶፩) በርበረ=በረበረ፣ዘረፈ፣በዘበዘ
፶፪) በኰረ=ታጎለ
፶፫) በደረ=ቀደመ
፶፬) ተበኵረ=አለቃ ሆነ፣በኵር ሆነ
፶፭) ተዐወረ=ቸል ቸል አለ
፶፮) ተዐዝረ=ጭልጥ ብሎ ሄደ
፶፯) ተዐየረ=ተመጻደቀ፣ተሳደበ
፶፰) ተከወረ=ነዳ፣ቀዘፈ
፶፱) ተወዐረ=አደነቀ
፷) ተዘከረ=አሰበ
፷፩) ተዝኅረ=ኰራ፣ታጀረ፣ተጀነነ (የአካሄድ የአለባበስ)
፷፪) ተድኅረ=ወደኋላ ሆነ
፷፫) ተደረ=በላ፣ተመገበ (የራት)
፷፬) ተደብተረ=ሰፋ (የድንኳን)
፷፭) ተገበረ=አረሰ
፷፮) ተገረ=ተክለ (የካስማ የድንኳን)
፷፯) ተጋወረ=ጎረቤት ሆነ፣ተጎራበተ
፷፰) ተገየረ=መጻተኛ ሆነ
፷፱) ተጠየረ=አሟረተ፣ጠነቆለ
፸) ተፃመረ=አንድ ሆነ
፸፩) ተፃረረ=ተጣላ
፸፪) ተጽዕረ=ተጨነቀ
፸፫) ንኅረ=አኮረፈ (የሰው የውሃ)
፸፬) ነሰረ=በረረ፣ዱብ ዱብ አለ (የደም የአሞራ)
፸፭) ነቈረ=አንድ ዓይና ሆነ
፸፮) ነበረ=ተቀመጠ
፸፯) ነከረ=ለየ
፸፰) ነዘረ=ወጋ፣ነከሰ (የአውሬ)
፸፱) ነገረ=ነገረ
፹) ነጠረ=ብልጭ አለ (የብልጭታ)
፹፩) ነጸረ=አየ
፹፪) ነፀረ=ለየ፣ሰነጠቀ፣ከፈለ
፹፫) ነጽረረ=ከበደ
፹፬) አኀረ=አንድ አደረገ
፹፭) አኅሰርሰረ=አቅባባ፣ቀባ (የውርደት ስም)
፹፮) አመረ=አመለከተ፣ተመለከተ
፹፯) አማኅበረ=ማኅበር አደረገ፣ ሰበሰበ፣ ሸነጓ
፹፰) አመስጠረ=አራቀቀ፣ አመሰጠረ
፹፱) አምረረ=አሳዘነ
፺) አመንዘረ=አመነዘረ
፺፩) አመዐርዐረ=አጣፈጠ
፺፪) አመዝበረ=አፈረሰ፣ናደ
፺፫) አማዕረረ=ማረረ
፺፬) አማዕዘረ=አበራ፣አፍለቀለቀ፣ አንጽባረቀ
፺፭) አምዘረ=ጠመቀ (የጠላ ብቻ)
፺፮) አምደረ=አጸና
፺፯) አሥመረ=አገለገለ
፺፰) አሰረ=አሰረ
፺፱) ዐሠረ=ዐሥር አደረገ
፻) አስቈረረ=ተጸየፈ፣አጸየፈ
፻፩) አስተሐቀረ=አቃለለ
፻፪) አስተመሐረ=አማለደ፣ማለደ
፻፫) አስተናበረ=አዘጋጀ
፻፬) አስተደኀረ=ወደኋላ አለ፣ አከታተለ
፻፭) አስተፃመረ=አንድ አደረገ
፻፮) አስተፃረረ=አጣላ
፻፯) አሥገረ=አጠመደ
፻፰) አረረ=ለቀመ (የአዝመራ)
፻፱) ዐቈረ=ቋጠረ
፻፲) ዐበረ=ድርቅ ሆነ፣ደረቀ
፻፲፩) አብሠረ=ነገረ (የምሥራች)
፻፲፪) አብደረ=መረጠ
፻፲፫) አንከረ=አደነቀ
፻፲፬) አንኰርኰረ=ተገለባበጠ፣ አገለባበጠ
፻፲፭) አንወረ=አነወረ፣ነቀፈ፣ሰደበ
፻፲፮) አንዘረ=መታ (የዘፈን የአዝማሪ)
፻፲፯) አንዶረረ(አንጾረረ)=ጩርቅ ጩርቅ አለ፣ተጨነቀ
፻፲፰) አንገርገረ=ጣለ፣አፍገመገመ፣ ተፍገመገመ (የጋኔን)
፻፲፱) አንጎርጎረ=አጉረመረመ፣ አንጎራጎረ፣ ተጉረመረመ (የመክፋት)
፻፳) አንጸረ=ተመላከተ፣ አመለከተ፣ አሳየ
፻፳፩) አእመረ=አወቀ
፻፳፪) ዖረ=ታወረ
፻፳፫) አውተረ=አዘወተረ
፻፳፬) ዐየረ=አሳልፎ ሰጠ
፻፳፭) አገረ=ወታደር ሆነ፣ተራመደ
፻፳፮) አግመረ=ቻለ
፻፳፯) አግረረ=ገዛ፣አስገዛ
፻፳፰) አገበረ=ግድ አለ
፻፳፱) አጥሀረ=ጠመቀ፣አጠመቀ፣ አጠራ፣ አነጻ (የጠላ፣ የሰው)
፻፴) ዐጸረ=ጠመቀ (የጠላ)
፻፴፩) አፅረረ=ሸፈተ
፻፴፪) አጽበረ=ጭቃ አደረገ
፻፴፫) አፍቀረ=ወደደ
፻፴፬) ኰስተረ=ጠረገ
፻፴፭) ከብረ=ከበረ
፻፴፮) ከተረ=ከበበ፣ጋረደ
፻፴፯) ከፈረ=ለካ (የስፍር)
፻፴፰) ወሠረ=ገዘገዘ፣ሰነጠቀ
፻፴፱) ወቀረ=ወቀረ፣አለዘበ
፻፵) ወተረ=ሳበ፣ገተረ፣ዘረጋ (የደጋን)
፻፵፩) ወዘረ=ሸለመ፣ለበጠ፣አስጌጠ (የሕንጻ)
፻፵፪) ወገረ=ወገረ፣መታ፣ደበደበ
፻፵፫) ወፈረ=ተሰማራ
፻፵፬) ዘመረ=አመሰገነ
፻፵፭) ዘርዘረ=በተነ
፻፵፮) ዘከረ=ስም ጠራ
፻፵፯) ዞረ=ዞረ፣ከበበ
፻፵፰) ዘፈረ=ጫፍ ሆነ (የልብስ)
፻፵፱) ደኀረ=አጨ
፻፶) ደመረ=ጨመረ
፻፶፩) ደበረ=ደበረ፣ገዳም አደረገ
፻፶፪) ደጎረ=በሳ፣ቀደደ
፻፶፫) ደፈረ=ደፈረ
፻፶፬) ገብረ=አደረገ
፻፶፭) ገረረ=ተገዛ
፻፶፮) ገዐረ=ጮኽ፣ተጨነቀ
፻፶፯) ገዘረ=ገረዘ
፻፶፰) ገየረ=ቀባ፣ለሰነ፣ለቀለቀ
፻፶፱) ጎጽፈረ=አከከ
፻፷) ጥህረ=ጮኽ
፻፸) ጦመረ=ጻፈ
፻፸፩) ጠፈረ=ታታ
፻፸፪) ፀመረ=አንድ አደረገ
፻፸፫) ጸበረ=ጭቃ አደረገ
፻፸፬) ጽዕረ=ተጨነቀ
፻፸፭) ጾረ=ተሸከመ
፻፸፮) ጸጎረ=ጨጎራም ሆነ
፻፸፯) ፀፈረ=ታታ፣ጠለፈ (የባጥ)
፻፸፰) ፈኀረ=አጨ
፻፸፱) ፈርፈረ=ቆረሰ (የመቆራረስ)
፻፹) ፈከረ=ተረጎመ
፻፹፩) ፈጠረ=ፈጠረ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የግሥ ጥናት ክፍል ስድስት
ግእዝ=አማርኛ
፩) ኀልቀ=አለቀ
፪) ኈለቈ=ቆጠረ
፫) ሐመቀ=ብላሽ ሆነ
፬) ሐብቀቀ=አረከሰ፣አበላሸ
፭) ሐብቈቈ=ሣሣ
፮) ሐነቀ=አነቀ
፯) ሐንቀቀ=ተድላ ደስታ አደረገ
፰) ልህቀ=አደገ
፱) ሌቀ=አለቃ ሆነ
፲) ለጸቀ=አንድ ሆነ፣ ተጣበቀ
፲፩) ለፈቀ=አጥብቆ ያዘ
፲፪) መቀቀ=አንጣጣ
፲፫) መተቀ=ጣፈጠ፣ማር ማር አለ
፲፬) ሞቀ=ሞቀ
፲፭) መጠቀ=ረዘመ
፲፮) ሠሀቀ=ሳቀ
፲፯) ሰረቀ=ሰረቀ
፲፰) ሠቅሠቀ=ከፈለ፣ለየ
፲፱) ሰበቀ=ሰበቀ፣መታ (የማርስ)
፳) ሠነቀ=ስንቅ ያዘ
፳፩) ሶቀ=ደገፈ (የሚያዝ ነገር ሁሉ)
፳፪) ሰደቀ=ዘረጋ (የሰዴቃ)
፳፫) ሠጠቀ=ሰነጠቀ፣ፈለጠ፣ተረተረ
፳፬) ርሕቀ=ራቀ
፳፭) ረቀ=ረቀቀ
፳፮) ረቀቀ=ጻፈ
፳፯) ረፈቀ=ተቀመጠ
፳፰) በረቀ=ብልጭ አለ
፳፱) ቤደቀ=ሠራ (የቤት)
፴) ተላጸቀ=አንድ ሆነ
፴፩) ተስቈቈ=ሣሣ፣ነፈገ
፴፪) ተሣለቀ=ተዘባበተ፣ተሣለቀ
፴፫) ተዐረቀ=ተራረቀ፣ታረቀ
፴፬) ተዐርቀ=ተራቆተ
፴፭) ተዳደቀ=ተጣላ
፴፮) ተጠውቀ=ተከፋ፣አስከፋ
፴፯) ተጽዕቀ=ተጨነቀ
፴፰) ተጸደቀ=ተመጻደቀ
፴፱) ነሰቀ=ሰደረ፣ደረደረ (የደንጊያ)
፵) ነደቀ=ሠራ (የቤት)
፵፩) ነፈቀ=ከፈለ
፵፪) ናፈቀ=ተጠራጠረ
፵፫) አልጸቀ=ደረሰ
፵፬) ዐመቀ=ጥልቅ ሆነ፣ጎደጎደ
፵፭) ዐሰቀ=አሸበ ሠራ (በልብስ ላይ ወርቅ የማፍሰስ)
፵፮) ዐረቀ=አስታረቀ
፵፯) ዐርቀ=ተራቆተ
፵፰) አበቀ=ታመመ
፵፱) ዐነቀ=አሰረ (የአንገት)
፶) አንጸብረቀ=አንጸባረቀ፣አብረቀረቀ
፶፩) ዖቀ=አወቀ
፶፪) አድለቅለቀ=ተነዋወጠ፣ አነዋወጠ
፶፫) ዐጠቀ=ታጠቀ
፶፬) አጥመቀ=አጠመቀ
፶፭) አጥዐቀ=አጣበቀ
፶፮) ወሰቀ=ሳበ፣ገተረ (የቀስት)
፶፯) ወረቀ=ተፋ
፶፰) ወድቀ=ወደቀ
፶፱) ዘሐቀ=ገፈፈ (የቆዳ)
፷) ዘረቀ=አቧለተ (የዋዛ)
፷፩) ዜርዜቀ=ነፋ (የወንፊት)
፷፪) ደመቀ=ወጋ
፷፫) ደቀ=ልጅ ሆነ
፷፬) ደደቀ=ተጣላ
፷፭) ጕሕቈ=ጎበጠ፣አጎበጠ፣ አጎነበሰ
፷፮) ጠለቀ=አደፈ፣ረከሰ
፷፯) ጠበቀ=ያዘ
፷፰) ጠነቀቀ=ጻፈ
፷፱) ጠንቀቀ=ጠነቀቀ
፸) ጠየቀ=ተረዳ
፸፩) ጽሕቀ=ተጋ
፸፪) ጸረቀ=ጋገረ
፸፫) ጸንቀቀ=ነከረ፣ዘፈቀ፣ለወሰ
፸፬) ጸድቀ=እውነተኛ ሆነ
፸፭) ጸፈቀ=ጀጎለ (የአጥር)
፸፮) ፈሐቀ=ፋቀ
፸፯) ፈረቀ=ከፈለ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#የግሥ #ጥናት #ክፍል #ሰባት
ግእዝ=አማርኛ
፩) ሐለበ=አለበ
፪) ሐሰበ=አሰበ
፫) ሐበበ=ሀብ ሀብ አለ፣ ከዚያም ከዚያም ረገጠ፣ ወዳጅ ሆነ
፬) ሐብሐበ=ማለ
፭) ሐንበበ=አፈራ
፮) ሐንከበ=አሰፈረ
፯) ሐዘበ=ጠረጠረ
፰) ሔበ=ቀዳ፣ጠለቀ (የውሃ)
፱) ሐጠበ=ለቀመ (የእንጨት)
፲) ኀፀበ=አጠበ፣አጠራ፣አነጻ
፲፩) ልህበ=ወዛ፣ላበ፣ሞቀ፣ተኮሰ
፲፪) ለበበ=ሸበበ
፲፫) ለገበ=ሰፋ (የአቅማዳ)
፲፬) መረበ=ጣለ (የዓሣ)
፲፭) ማዕሰበ=ገለሞተ
፲፮) መገበ=ሾመ (የሹመት)
፲፯) ሰሐበ=ጎተተ፣ሳበ
፲፰) ሣህበበ=ሻገተ፣ተበላሸ
፲፱) ሰለበ=ሰለበ
፳) ሠረበ=ማገ፣መጠጠ፣ጠጣ
፳፩) ሰበ=ዞረ፣ከበበ፣ገጠመ (የሠራዊት)
፳፪) ሠብሠበ=ሕግ ሠራ
፳፫) ሠአበ=ተከተለ
፳፬) ሥእበ=ተዳደፈ፣ረከሰ
፳፭) ሰከበ=ተኛ
፳፮) ሤበ=ሸበተ (የሰው ብቻ)
፳፯) ርኅበ=ተራበ
፳፰) ረበ=ረበበ (የመልአክ የደመና ክንፍ ያለው ነገር ሁሉ)
፳፱) ረበበ=ዘረጋ
፴) ረከበ=አገኘ
፴፩) ረጥበ=ረጠበ
፴፪) ቀለበ=ዋጠ
፴፫) ቀረበ=ቆረበ
፴፬) ቄረበ=ቆረበ
፴፭) ቈረበ=ቆረበ
፴፮) ቀርበ=ቀረበ
፴፯) ቀቀበ=ሰፋ (የሰይፍ ማኅደር)
፴፰) ቀጸበ=ጠቀሰ (የጥቅሻ)
፴፱) ተሐዘበ=ታዘበ
፵) ተመንደበ=ተቸገረ፣ተጨነቀ፣ ተጠበበ
፵፩) ተማዕሰበ=ገለሞተ
፵፪) ተመገበ=በላ
፵፫) ተዐፅበ=ተጨነቀ፣ተደነቀ
፵፬) ተጥበበ=ብልሃተኛ ሆነ
፵፭) ነሀበ=ሠራ፣አነበ (የብረታ ብረት የንብ)
፵፮) ነቀበ=ለየ
፵፯) ነበበ=ተናገረ፣ነገረ
፵፰) ነጥበ=ነጠበ
፵፱) አመክዐበ=እጥፍ ድርብ አደረገ
፶) አማዕሰበ=ቤተ ፈት ሆነ (የሚስት)
፶፩) አማዕቀበ=አደራ አለ
፶፪) አማዕተበ=አመሳቀለ፣ አማተበ
፶፫) አስተርከበ=አስተዋለ
፶፬) አስተአዘበ=ሸና፣አፈሰሰ
፶፭) አስተዐፀበ=አደነቀ፣አስጨነቀ
፶፮) ዐሰበ=ሰጠ (የደመዎዝ)
፶፯) ዓሰበ=ፈታ፣ለቀቀ፣ተወ (የሚስት)
፶፰) ዐርበ=ገባ (የፀሐይ)
፶፱) ዐቀበ=ጠበቀ
፷) ዐተበ=ባረከ
፷፩) ዐንሰበ=አሟረተ
፷፪) አንበበ=አነበበ
፷፫) አንጠብጠበ=አንጠበጠበ፣ ተንጠበጠበ
፷፬) አውሰበ=አገባ
፷፭) አውገበ=አኮረፈ (የእንቅልፍ)
፷፮) አውጸበ=ሠራ (የቀለበት)
፷፯) ዐዘበ=ቆነነ፣ሠራ (የጭራ)
፷፰) አጠበ=ለቀመ (የእንጨት)
፷፱) ዐጸበ=አስጨነቀ
፸) አጽሐበ=ዘበዘበ፣ነዘነዘ፣ ጨቀጨቀ፣ ነገር አበዛ፣ አደከመ
፸፩) ከሰበ=ገረዘ፣ቆረጠ
፸፪) ከረበ=ለቀመ፣ሰበሰበ (የወይን)
፸፫) ኬረበ= አራት ዓይነት አድርጎ ጠረበ
፸፬) ኰረበ=ሰቀለ (የባጥ እንደ ዳስ ያለ ሁሉ)
፸፭) ከበበ=ከበበ (የማጀብ)
፸፮) ከብከበ=ሰርግ አደረገ
፸፯) ከተበ=ጻፈ
፸፰) ከዐበ=ሰደረ፣ካበ፣ደረደረ
፸፱) ወሀበ=ሰጠ
፹) ወከበ=ቸኰለ
፹፩) ወጸበ=ሠራ (የቀለበት)
፹፪) ዘረበ=መታ፣ቀጠቀጠ (የመዶሻ)
፹፫) ዘገበ=ሰበሰበ፣አከማቸ (የገንዘብ)
፹፬) የበበ=እልል እልል አለ፣ አመሰገነ፣ ዘመረ፣ ዘፈነ
፹፭) ደበበ=ዘረጋ (የጥላ የዝንቦ)
፹፮) ደብደበ=ነፋ (የሆድ)
፹፯) ደየበ=ወጣ፣አረገ
፹፰) ገለበ=ሸሸ፣ጋለበ፣ነዳ፣ አጠመደ
፹፱) ገልበበ=ሸፈነ፣ከደነ፣አለበሰ፣ አከናነበ
፺) ጠቀበ=ሰፋ፣ጠቀመ (የልብስ)
፺፩) ጠበ= ብልሃተኛ ሆነ
፺፪) ጠበጠበ=ጻፈ
፺፫) ጠብጠበ=ገረፈ
፺፬) ጤበ=ኮላ ኳለ፣ቀባ
፺፭) ጸለበ=ሰቀለ
፺፮) ጸረበ=ጠረበ
፺፯) ጸበ=ጠበበ
፺፰) ጾበ=ጨለጠ፣ጠጣ
፺፱) ጸግበ=ጠገበ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
_ #የግእዝ #ጥያቄዎች_
ምርጫ
፩) ስለ ግእዝ ቋንቋ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ) የራሱ የሆነ ቁጥር አለው
ለ) የራሱ የሆነ ሥርዓተ ንባብ አለው
ሐ) የራሱ የሆነ ፊደል አለው
መ) ሁሉም
፪) 7777 በግእዝ ቁጥር ሲጻፍ___ይሆናል?
ሀ) ፸፻፯፻፸፯
ለ) ፯፯፯፯
ሐ) ፸፯፸፯
መ) ፸፼፯፻፸
፫) "ውእቱኬ፣ ውእቱ፣ ዕንባቆም፣ ሕይወት" የሚሉት ቃላት ሥርዓተ ንባባቸው በቅደም ተከተል ምንድን ነው?
ሀ) ተነሽ፣ ወዳቂ፣ ሰያፍ፣ ተጣይ
ለ) ተነሽ፣ ወዳቂ፣ ተጣይ፣ ሰያፍ
ሐ) ወዳቂ፣ ተነሽ፣ ሰያፍ፣ ተጣይ
መ) ወዳቂ፣ ተነሽ፣ ተጣይ፣ ሰያፍ
፬) መካከለኛ ፊደሉ ጠብቆ የሚነበበው ቃል የቱ ነው?
ሀ) ሰብሐ-ሰባ
ለ) ፈጸመ-ጨረሰ
ሐ) ጸብሐ-ነጋ
መ) መሐረ-ይቅር አለ
፭) ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ) ሠረቀ-ወጣ
ለ) ሠዐለ-ለመነ
ሐ) መሀረ-አስተማረ
መ) ጸለየ-ለመነ

#እውነቱን "ጽድቅ" ውሸቱን "ሐሰት" በማለት መልሱ

፮) "መ" በወዳቂ ቃል ላይ ሲወድቅ ተነስቶ እንዲነበብ ያደርገዋል።
-
፯) "ዝ" የሚለው ቃል ሥርዓተ ንባቡ ወዳቂ ነው።
-
፰) አንድ ሺ ቁጥር በግእዝ ቋንቋ እልፍ ነው።
-
፱) ስምንት ቁጥር በግእዝ ስምንቱ ይባላል።
-
፲) "ሂ፣ ኒ፣ ሰ" በተጣይ፣ በሰያፍና በተነሽ ቃል ላይ ሲወድቁ ብዙ ጊዜ በወዳቂ ንባብ እንዲነበቡ ያደርጋቸዋል።
#አዛምድ
ሀ. ለ.
፲፩) ሠምረ ሀ) ፈለገ
፲፪) ኀሠሠ ለ) ተናገረ
፲፫) ኖመ ሐ) ተኛ
፲፬) አጽደልደለ መ) ወደደ
፲፭) ነበበ ሠ) አበራ

#የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ
፲፮) የ"ወ"ን ካእብ፣ የ"የ"ን ሣልስ እንዲሁም የ "ሐ" እና የ "አ" ን ራብዕ ጻፍ።
-
፲፯) በአማርኛ የምንጠቀምባቸው በግእዝ ቋንቋ የሌሉ ስምንት ፊደላትን ጥቀስ።
-
፲፰) 379124 በግእዝ ሲጻፍ እንዴት ይሆናል?
-
፲፱) ተነሽ ንባብ የማይጨርስባቸው ሆሄያት ማን እና ማን ናቸው?
-
፳) የስቅለት ቀን ግፍዖሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍዑኒ የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ክፍል የሚነበበው በምን የንባብ ዓይነት ነው?

ሠናይ መክፈልት
(መልካም እድል)
አዘጋጅ:-መ/ር በትረማርያም
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
አመ ፭ ለጥር በዓለ ልደቱ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
👉🏻  ሰላም ለአብ ገባሬ ኵሉ ዓለም፤
        ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤
        ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤
        ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤
        ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።

ዚቅ
ዮም አሐደ መርዔተ ኮኑ መላእክት ወሰብእ፤ ከመ ይሰብሕዎ ለክርስቶስ በቃለ አሚን፤ ዮም ይገብሩ በዓለ በበነገዶሙ፤ ልደቶ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ።


     👉🏻 ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤
            ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
           መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ ዘእምቀዲሙ፤
           ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
           እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። 
ዚቅ
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፤ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ።

ወረብ ( በአንኮበር ይትበሃል)
መሠረታቲሃ  መሠረታቲሃ  መሠረታቲሃ  ውስተ አድባር፤
ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ።

           
                      ነግሥ
👉🏻 ስምዖን ወአቅሌስያ እለ ነበሩ በንሂሳ፤
       በኃጢአ ውሉድ በከዩ መጠነ ዓመታት ሠላሳ፤
       ሥሉስ ቅዱስ ሶበ ነፍሑ በውስተ ከርሣ፤
       ተወልደ እምኔሆሙ ቀናየ አናብስት ስሳ፤
       በኃይለ አምላኩ ዘይሰሪ አበሳ። 

                 ዚቅ
መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፤ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ።

ወረብ ( በአንኮበር ይትበሃል)
መሠረታቲሃ  መሠረታቲሃ  መሠረታቲሃ  ውስተ አድባር፤
ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ።

           
                 ነግሥ
👉🏻 ስምዖን ወአቅሌስያ እለ ነበሩ በንሂሳ፤
       በኃጢአ ውሉድ በከዩ መጠነ ዓመታት ሠላሳ፤
       ሥሉስ ቅዱስ ሶበ ነፍሑ በውስተ ከርሣ፤
       ተወልደ እምኔሆሙቀናየ አናብስት ስሳ፤
       በኃይለ አምላኩ ዘይሰሪ አበሳ።

              ዚቅ
ተፈሢሓ በነፍሳ ፆረቶ በከርሣ፤ ተወልደ አንበሳ ዕጓለ አንበሳ፤ ወልድ ዘይሠሪ አበሳ።

           ወረብ
ተፈሢሓ በነፍሳ ተፈሢሓ በነፍሳ በከርሣ ፆረቶ፤
ዕጓለ አንበሳ ተወልደ  አበሳ ዘይሠሪ።

                መልክዐ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

👉🏻ሰላም ለጽንሰትከ በብሥራተ መልአክ ሐዲስ፤
      ወለልደትከ ሰላም በወርኃ ታኅሣሥ፤
ገብረ መንፈስ ቅዱስ አበውዕ ወርቀ አምኃ ልብ ወከርሥ፤
     በእንተ ልደቱ ከመ አብዐ ተርሴስ ፤
    ለቤዛ ኵሉ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ።

       ወረብ
ወርቀ አምኃ ልብ ወከርሥ አበውዕ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፤
ለቤዛ ኵሉ ዓለም በእንተ ልደቱ  ለቤዛ ኵሉ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ።

ዚቅ
በእንተ ልደቱ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ አድባር ኮኑ ኅብስተ ሕይወት፤ ወዕፀወ ገዳምኒ ፈረዩ አስካለ በረከት፤ ማየ ባሕርኒ ኮነት ሀሊበ ወመዓረ፤ ወመላእክት ተጋቢዖሙ፤ ሰፍሑ ክነፊሆሙ፤ ወጸለሉ ላዕለ አቅሌስያ ፤ ወበህየ ገብሩ በዓለ።

           ወረብ
ወመላእክት ተጋቢዖሙ ሰፍሑ ክነፊሆሙ ወጸለሉ ላዕለ አቅሌስያ፤
ወበህየ  በዓለ  ገብሩ ወበህየ ገብሩ በዓለ።

👉🏻 ምልጣን
ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ።

👉🏻እስመ ለዓለም
እንዘ ሀሎነ     በል አመ ፭ ለጥር     ዓዲ
ጸርሑ ጻድቃን     በል  አመ ፫ ለጥር

👉🏻ሰላም
ተወልደ መድኅን   በል አመ ፴ ለታኅሣሥ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የግሥ ጥናት ክፍል ስምንት
    ግእዝ=አማርኛ
፩) ሐለተ=መለመለ
፪) ሐመተ=አከሰለ (የከሰል)
፫) ሐርበተ=ተንበደበደ (የፍርሀት)
፬) ሐብረተ=መከተ
፭) ኀቤተ=አገለገለ
፮) ሐተተ=መረመረ
፯) ሐውከተ=ግር ግር አለ
፰) ሐዘተ=መደበ (የመደብ)
፱) ለተ=ዲዳ ሆነ
፲) ለተተ=ጻፈ
፲፩) ለግነተ=አገነፋ
፲፪) መመተ=አፈገፈገ፣ፈርቶ ሸሸ
፲፫) መሥረተ=ጀመረ
፲፬) ሞተ=ሞተ
፲፭) መጽወተ=መጸወተ፣ሰጠ
፲፮) ስሕተ=ሳተ
፲፯) ሰለተ=ዘበተ
፲፰) ሴረተ=ሸመተ
፲፱) ሰንኈተ=በጣ (የሰውነት)
፳) ሰንበተ=አከበረ (የሰንበት)
፳፩) ሰንከተ=ጋገረ
፳፪) ሠከተ=ወጋ
፳፫) ሰኮተ=ወለወለ፣ሰራ (የመንገድ)
፳፬) ሰክተተ=ጣደ
፳፭) ረአተ=ጋገረ (የራት)
፳፮) ሮተ=ወለወለ፣አሸ
፳፯) ቀብተተ=ነፋ
፳፰) ቀተ=ቅትት ቅትት አለ (የመቃሰት)
፳፱) ቀተተ=ተወራረደ፣ተማማለ
፴) ቀነተ=ታጠቀ
፴፩) ቀፈተ=ደነደነ
፴፪) ብሕተ=ሰለጠነ
፴፫) በነተ=ገበረ
፴፬) በዐተ=ገባ
፴፭) በዘተ=አባዘተ
፴፮) ቤተ=አደረ
፴፯) ተሠይመተ=ሥልጣን ተቀበለ፣ ተሾመ
፴፰) ተትሕተ=ተዋረደ፣ትሑት ሆነ
፴፱) ተአተተ=ወገደ፣ራቀ
፵) ተከተ=ደም ሆነ (የመርገም ብቻ)
፵፩) ተዋከተ=ተፍጃጀ፣ተንጫጫ
፵፪) ተጋህረተ=ተጨናነቀ (የቦታ ጥበት)
፵፫) ነሠተ=አፈረሰ፣ፈነቀለ፣ነቀለ
፵፬) ነቈተ=ሠራ (የቤት)
፵፭) ነአተ=ጋገረ
፵፮) ዐመተ=ከነዳ
፵፯) አመርቆተ=አጎተነ (የጎፈሬ)
፵፰) አምአተ=መቶ አደረገ
፵፱) አስተተ=አቃለለ፣ናቀ
፶) አእተተ=አስወገደ
፶፩) አእኰተ=አመሰገነ
፶፪) አክሞተተ=አሳጠረ
፶፫) አካዕበተ=እጽፍ ድርብ አደረገ
፶፬) አውከተ=ግር ግር አለ
፶፭) ዐገተ=ከበበ (የክፉ፣ የበጎ)
፶፮) አጻመተ=ጨረሰ፣አጠፋ፣ፈጀ
፶፯) ከሠተ=ገለጠ
፶፰) ከበተ=ሸሸገ
፶፱) ከንተተ=አሳጠረ
፷) ኰዐተ=ቆፈረ
፷፩) ወተ=ውትት ውትት አለ
፷፪) ዝህተ=ፈላ (የሚፈላ ሁሉ)
፷፫) ዘርቤተ=ጎዘጎዘ፣አነጠፈ
፷፬) ዘፈተ=ደፈደፈ
፷፭) ደበተ=አጎንብሶ ሄደ
፷፮) ገብተተ=አረጀ
፷፯) ገብነተ=አሞቀ (የዓይብ)
፷፰) ገዐተ=አገነፋ (የገንፎ)
፷፱) ጸለተ=ጋገረ
፸) ጸልመተ=ጨለመ
፸፩) ጸበተ=ዋኘ
፸፪) ፈተተ=ቆረሰ፣ፈተተ
፸፫) ፈየተ=ቀማ
                          
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የግሥ ጥናት ክፍል ዘጠኝ
   ግእዝ=አማርኛ
፩) ሐልየነ=መማለጃ ሰጠ
፪) ኀበነ=ጠመጠመ
፫) ሐዘነ=አዘነ
፬) ሀይመነ=አመነ፣አሳመነ፣ታመነ
፭) ሐይደነ=አበደ
፮) ሐፀነ=አሳደገ
፯) ሐፈነ=ዘገነ፣አፈሰ
፰) ለሰነ=ተናገረ (የልሳን)
፱) ለጠነ=አመሰገነ (የጌታ)
፲) መሐነ=እጅ ነሳ
፲፩) ማሰነ=ጠፋ
፲፪) መቀነ=ጠመመ፣ክፉ ሆነ
፲፫) መነነ=ናቀ
፲፬) መከነ=ቦታ አደረገ
፲፭) መክነ=መካን ሆነ
፲፮) መዝገነ=አመሰገነ
፲፯) መጠነ=ለካ፣ሰፈረ
፲፰) ስኅነ=ሞቀ
፲፱) ሰመነ=ስምንት አደረገ
፳) ሰሰነ=ትርፍርፍ አለ፣ሴሰኛ ሆነ
፳፩) ሰበነ=ጠመጠመ
፳፪) ስእነ=ደከመ
፳፫) ሦነ=አለገገ
፳፬) ሤነ=ሸና
፳፭) ሰይጠነ=አጣላ፣አካሰሰ፣አሳጣ
፳፮) ሰፈነ=ገዛ
፳፯) ረሐነ=ጫነ
፳፰) ረስነ=ጋለ
፳፱) ረበነ=አስተማረ
፴) ረገነ=ቀዘፈ
፴፩) ረጠነ=መድኃኒት አደረገ
፴፪) ቀነነ=ቀኖና ያዘ፣ ሕግ ሠራ፣ ቀኖና ሠጠ
፴፫) ቈንቈነ=ነቀዘ
፴፬) ቀዐነ=ጠመመ፣ጠበበ፣ጨነቀ
፴፭) ቀጥነ=ቀጠነ፣ረቀቀ
፴፮) ባህነነ=ብንን ብንን አለ
፴፯) በነ=በነነ
፴፰) በየነ=ፈረደ
፴፱) በደነ=ወደቀ፣በድን ሆነ (የሥጋ)
፵) ተመስከነ=ተቸገረ
፵፩) ተመየነ/ተመንገነ=ተንኮለኛ ሆነ፣ ተተነኳኮለ
፵፪) ተሳነነ/ተቃረነ=ተጣላ፣ተናከሰ፣ ተዘባተረ፣ ተዋጋ (የሰው የእንስሳ)
፵፫) ተስእነ/ተሠአነ=ተጫማ
፵፬) ተነ=ወጣ፣ተነነ፣ተበተነ፣በነነ (የጉም የጢስ አጓራ)
፵፭) ተንተነ=ፍግምግም አለ (የመውደቅ)
፵፮) ተዐየነ=ተከታተመ
፵፯) ተክህነ=አገለገለ (የቤተ ክርስቲያን)
፵፰) ተኳነነ=ተፈራረደ፣ተዋቀሰ
፵፱) ቶነ=ዘመነ በልግ ሆነ
፶) ተደየነ=ሞተ (የነፍስ ሞት)
፶፩) ቴገነ=ጎለተ (የጉልቻ)
፶፪) ተጽዕነ=ተጫነ
፶፫) ተጸወነ=ተጠጋ፣አስጠጋ
፶፬) ቴፈነ=ገረፈ (የወይፈን)
፶፭) አማሕፀነ=አደራ አለ፣አማጠነ
፶፮) አምነ=አመነ
፶፯) አመስፈነ=ገዛ፣አስገዛ፣ሾመ
፶፰) አማእዘነ=ከበበ (ክብ ሆኖ ለሚሰራ ሁሉ)
፶፱) አስተንተነ=አሰበ፣አሳሰበ፣አተጋ፣ አገለገለ
፷) አስተፍከነ=ደስ አሰኘ
፷፩) ዐቈነ=ገፋ (የወተት)
፷፪) አዕበነ=ደንጊያ አደረገ
፷፫) አውየነ=የወይን ጠጅ አደረገ
፷፬) ዔነ=ገመገመ
፷፭) አድነነ/አጽነነ=አዘነበለ፣ ተደፋ፣ ደፋ፣ ተዘነበለ
፷፮) ዐጠነ=አጠነ
፷፯) ከረስተነ=ክርስቲያን ሆነ
፷፰) ኰርጎነ=አከማቸ፣ሰበሰበ
፷፱) ኰነነ=ገዛ (የሀገር የሰው)
፸) ኮነ=ሆነ
፸፩) ከደነ=ገጠመ
፸፪) ከፈነ=ከፈነ፣ሸፈነ (የመግነዝ)
፸፫) ወሰነ=ደነገገ፣ወሰነ
፸፬) ወጠነ=ጀመረ
፸፭) ዝኅነ=ጸጥ አለ (የማዕበል ብቻ)
፸፮) ዘመነ=ወረተኛ ሆነ፣ ከዚያም ከዚያም ወዳጅ ሆነ
፸፯) ዘገነ=አፈሰ፣ዘገነ
፸፰) ዘፈነ=ዘፈነ
፸፱) የመነ=ቀና
፹) ድኅነ=ዳነ
፹፩) ደመነ=ጋረደ (የደመና)
፹፪) ደነነ=አዘነበለ፣ተዘነበለ
፹፫) ደየነ=ፈረደ፣ዳኘ፣ቀጣ
፹፬) ዴገነ=ተከተለ
፹፭) ደፈነ=ደፈነ፣ዘጋ
፹፮) ጕህነ=ጎረና፣ ጮኽ፣ አዜመ (የድምፅ)
፹፯) ገመነ=ኃጢአት ሠራ፣ በደለ
፹፰) ጠሐነ=ፈጨ
፹፱) ጤገነ=ጣደ፣አበሰለ፣ጋገረ፣ቆላ
፺) ጠነ=በረታ
፺፩) ጸቈነ=ጀጎለ፣አጠረ (የአጥር)
፺፪) ጸነ=ጸነነ፣አዘነበለ (የክፋት)
፺፫) ጸንጸነ=ነቀዘ፣ተበላሸ፣ጠነጠነ፣ አረጀ
፺፬) ጸዐነ=ጫነ
፺፭) ጸወነ=አስጠጋ
፺፮) ጸፈነ=ገፈፈ (የቆርበት)
፺፯) ፈተነ=ፈተነ
፺፰) ፈጠነ=ፈጠነ
፺፱) ፈፀነ=ወደ ታች አለ (የተቅማጥ)
                          
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የግሥ ጥናት ክፍል አስር
   ግእዝ=አማርኛ
፩) ኀሥዐ=በረደ፣ቀዘቀዘ፣ጸጥ አለ (የቁጣ የጠብ)
፪) ኀብአ=ሸሸገ
፫) ሐዝአ=ከለከለ (የክልክል ብቻ)
፬) ሀድአ=ጸጥ አለ
፭) ኀጥአ=አጣ
፮) ለምአ=ለማ፣ቦግ አለ፣በራ
፯) ላዕልዐ=ለንባዳ ሆነ (የልሳን)
፰) ለክአ=ጻፈ
፱) መልአ=መላ
፲) መልዐ=እግር መንገድ ሄደ
፲፩) መምዐ=አፈገፈገ
፲፪) መርዐ=ተዳራ (የዝሙት)
፲፫) ሞአ=አሸነፈ፣ ድል ነሣ
፲፬) መጽአ=መጣ
፲፭) ሰምዐ=ሰማ
፲፮) ሠሥዐ=ሣሣ (የንፍገት የሥሥት)
፲፯) ሠርዐ=ሠራ፣አዘጋጀ (የማዕድ የሕግ)
፲፰) ሰብዐ=ሰባት አደረገ
፲፱) ሰንአ=ተስማማ
፳) ሣዕሥዐ=ቅልጥፍጥፍ አለ (ለመናገር)
፳፩) ሰክአ=ደረደረ
፳፪) ሰኵዐ=አጓዘ (የጉንዳን)
፳፫) ሦዐ=ሠዋ፣አረደ
፳፬) ሰጕዐ=ነደለ፣በሳ
፳፭) ረሥአ=ረሳ፣ዘነጋ
፳፮) ረብዐ=አራት አደረገ
፳፯) ረትዐ=ቀና
፳፰) ረድአ=ረዳ
፳፱) ረግዐ=ረጋ
፴) ረፍአ=ደረተ
፴፩) ቀልዐ=ገለጠ
፴፪) ቀርዐ=መታ፣ደበደበ (የዱላ)
፴፫) ቈቍዐ=አጎበጎበ፣አጎረበ፣ተላጠ
፴፬) ቀብዐ=ቀባ
፴፭) ቀንአ=ቀና (የቅናት)
፴፮) ቆዐ=ጨረቋ፣በለገ
፴፯) ቄዐ=መለሰ፣ተፋ (የሁከት)
፴፰) ቀጽዐ=ቀጣ
፴፱) በልዐ=በላ
፵) በቍዐ=ጠቀመ
፵፩) ቦአ=ገባ
፵፪) ተማልዐ=እግር መንገድ ሄደ፣ አናዳ፣ ወሰደ
፵፫) ተምዐ=ተቆጣ
፵፬) ተምዕዐ=ተበሳጨ
፵፭) ተስዐ=ዘጠኝ አደረገ
፵፮) ተሰብአ=ሰው ሆነ
፵፯) ተሥዕዐ=ተገፈፈ፣ገፈፈ፣በነነ፣ ተበተነ (የዓይን ብሌን)
፵፰) ተቈጥዐ=ተቆጣ
፵፱) ተብዐ=ጨከነ፣በረታ
፶) ተታብዐ=ወንዳ ወንድ ሆነ፣በረታ፣ ጀገነ
፶፩) ተንሥአ=ተነሳ
፶፪) ተወጽአ=ድል ተነሳ፣ተሸነፈ
፶፫) ተዛውዐ=ተጫወተ
፶፬) ተጋብዐ=ተሰበሰበ
፶፭) ተጻብአ=ተጣላ
፶፮) ተፈግዐ=ደስ ተሰኘ
፶፯) ነሥአ=ያዘ
፶፰) ነቅዐ=መነጨ
፶፱) ነትዐ=ሸሸ፣ሮጠ፣ኮበለለ
፷) ነዝዐ=ነቀለ
፷፩) ነድአ=ነዳ
፷፪) አመልዐ=ጭልጥ ብሎ ሄደ
፷፫) አመስብዐ=ሰባት አደረገ
፷፬) አመስኵዐ=አመሰኳ፣አመነዛ
፷፭) አመግዝአ=ገዛ፣ፍሪዳ አደረገ
፷፮) አመፅጕዐ=ታመመ፣አሳመመ
፷፯) አስምዐ=አዳኘ፣አሰማ
፷፰) አስተብቍዐ=ማለደ፣አማለደ
፷፱) አስተብፅዐ=አደነቀ፣አስደነቀ
፸) አስተጋብአ=ሰበሰበ
፸፩) አስትዐ=ገበረ፣እጅ መንሻ ሰጠ
፸፪) አቅያዕይዐ=ተፋ፣ተፋፋ
፸፫) አብሕአ=አቦካ፣አሖመጠጠ
፸፬) አንሳዕስዐ=አፈላ፣አፍለቀለቀ፣ ፈላ፣ገነፈለ፣ተፍለቀለቀ (ለሚፈላ ሁሉ)
፸፭) አንብዐ=አለቀሰ
፸፮) አንጕዐ=ቀለጠመ፣ሰበረ (የአጥንት ብቻ)
፸፯) አንጦልዐ=ጋረደ፣ሸፈነ፣ዘረጋ፣ ተጋረደ፣ተሸፈነ
፸፰) አውሥአ=መለሰ (የመልስ የነገር)
፸፱) አውክዐ=አስቸገረ፣አደከመ፣ አታከተ፣ አሰለቸ
፹) አይኅዐ=ወረደ
፹፩) አይድዐ=ነገረ
፹፪) አድምዐ=አገኘ (የክብር የተስፋ)
፹፫) አጣእጥአ=አከናወነ፣ አበጀ፣ አሳመረ፣ አስጌጠ
፹፬) አጥብዐ=ወደደ
፹፭) አፀንግዐ=በረት ሠራ
፹፮) አጽምዐ=አደመጠ
፹፯) ከልአ=ከለከለ
፹፰) ከልአ=ሁለት አደረገ
፹፱) ኰርዐ=መታ (የዱላ)
፺) ከፍአ=ከፋ
፺፩) ወርአ=ጠወረ
፺፪) ወርአ=ጋረደ፣ሸፈነ (የልብስ)
፺፫) ወቅዐ=ወቃ፣ደበደበ
፺፬) ወውዐ=ደነፋ፣ጮኽ
፺፭) ወድአ=ጨረሰ፣ፈጀ
፺፮) ወግአ=ወጋ
፺፯) ወፅአ=ወጣ
፺፰) ወጽአ=ድል ነሣ፣አሸነፈ
፺፱) ዘርዐ=ዘራ (የእህል የሰው)
፻) ዘንግዐ=ዘነጋ፣ረሳ
፻፩) ዘግዐ=ዘጋ
፻፪) ደርዐ=ቻለ፣ታገሠ፣ጨከነ
፻፫) ደርፍዐ=ደረተ፣ሰፋ
፻፬) ደፍዐ=ደፋ
፻፭) ገምዐ=ላጨ፣መለጠ፣ነጨ፣ ሸለተ፣ቆረጠ (የጸጉር) ሠራ፣አለዘበ (የማሰሮ)
፻፮) ጎሥዐ=ገሣ (የትኩሳት የሰው የከብት)
፻፯) ገብአ=ገባ
፻፰) ገዝአ=ገዛ
፻፱) ጎድዐ=መታ (የደረት ብቻ)
፻፲) ጎጕዐ=ቸኮለ
፻፲፩) ገፍትዐ=ገለበጠ
፻፲፪) ገፍዐ=ገፋ
፻፲፫) ጠልዐ=ወጣ፣በቀለ፣አደገ፣ ረዘመ
፻፲፬) ጠምዐ=ነከረ፣ዘፈቀ
፻፲፭) ጠርዐ=ጮኽ፣ተማጠነ፣አቤቱ አለ፣ይግባኝ አለ
፻፲፮) ጠቅዐ=መታ (የመጥቅዕ)
፻፲፯) ጠብዐ=ጨከነ፣ደፈረ
፻፲፰) ጦዐ=ሸሸ
፻፲፱) ጤዐ=አነሰ
፻፳) ጠግዐ=ተጠጋ፣ተገደፈ፣ ተጣበቀ
፻፳፩) ጠፍአ=ጠፋ
፻፳፪) ጸልአ=ጠላ
፻፳፫) ጸምአ=ተጠማ
፻፳፬) ፀርዐ=ታጎለ፣ቦዘነ
፻፳፭) ጸብአ=አሸነፈ፣ተጣላ
፻፳፮) ጸብዐ=ታጎለ፣ጠፋ
፻፳፯) ጸንዐ=ጸና፣በረታ
፻፳፰) ጸንዐ=አረጋጋ፣አይዞህ አይዞህ አለ
፻፳፱) ፃእፅአ=ጭንጋፍ ሆነ
፻፴) ጸውዐ=ጠራ
፻፴፩) ጼአ=ተላ፣ዛገ
፻፴፪) ፀግዐ=ተጠጋ
፻፴፫) ጸፍዐ=መታ (የጥፊ ብቻ)
፻፴፬) ፈቅዐ=ገመሰ፣ሰነጠቀ
፻፴፭) ፈግዐ=ተደሰተ
                     
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የግሥ ጥናት ክፍል አስራ አንድ
   ግእዝ=አማርኛ
፩) ሐነከ=ሰጠ፣አደቀቀ፣ፈጨ
፪) ሐከከ=ተከራከረ
፫) ሆከ=አወከ
፬) ሔከ=አላመጠ
፭) ለሐኰ=ሠራ
፮) ለአከ=ላከ፣ሰደደ
፯) ለከከ=ጻፈ፣ለከከ፣ቀባ
፰) መሐከ=ራራ
፱) ማሕረከ=ማረከ
፲) መለከ=ገዛ
፲፩) መሰከ=አቀጠነ
፲፪) ምዕከ=ከፋ
፲፫) ስሕከ=ሻከረ
፲፬) ሠረከ=መሸ
፲፭) ሤረከ=ብልሃተኛ ሆነ
፲፮) ሰበከ=አስተማረ
፲፯) ሰበከ=ጣዖት ሠራ
፲፰) ሮከ=ሾመ (የሰው)
፲፱) ረጕነኰ=ጎዘጎዘ (የምንጣፍ)
፳) በረከ=ተንበረከከ
፳፩) ባረከ=ባረከ
፳፪) በተከ=ቆረጠ (የገመድ)
፳፫) በከ=ብላሽ ሆነ
፳፬) ተመልአከ=አለቃ ሆነ
፳፭) ተዐረከ=ወዳጅ ሆነ
፳፮) ንህከ=አዘነ፣ተወዘወዘ፣ተከዘ፣ አሰበ
፳፯) ነሰከ=ነከሰ
፳፰) ንእከ=ቀላቀለ
፳፱) ነክነከ=ወዘወዘ፣ነቀነቀ
፴) አምለከ=አመለከ
፴፩) አስመከ=ተጠጋ
፴፪) አስተብረከ=ሰገደ፣አሰገደ
፴፫) አውከከ=አጎደለ
፴፬) ወሐከ=አነሳሳ
፴፭) ወሰከ=ጨመረ
፴፮) ዘረከ=ሰደበ
፴፯) ደሐከ=ተንቧቸ
፴፰) ደረከ=ጸና
፴፱) ጎነኰ=ከመረ
፵) ጽሕከ=ጨኽኘ
፵፩) ጸኰ=ሹልዳ አወጣ (የሥጋ)
፵፪) ፈለከ=ፈጠረ፣ከፈለ
                          
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/25 20:23:04
Back to Top
HTML Embed Code: