Telegram Web Link
Le Eotc ቤተ መጻሕፍት chanal abalat
Enkan legetachin ena amilakachin beale lidet aderesen aderesachu
Audio
የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን
                         
Size 34.9MB
Length 1:40:13

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ልደተ ክርስቶስ እንዲህ አለ፦

ጌታ ሆይ ቅድስት እናትህ ድንግል ሳለች አንተን ፀንሳ በመውለድ እናትነትን ገንዘቧ አደረገች፤ ድንግል ሆና ሳለች ከጡቶቿ ወተት ፈሰሰ፤ ድንግል ከሆነች መሬት ንጹሕ ምንጭ እንዲፈልቅ፤ እንዲሁ ድንግል ከሆነችው እናትህ ጡቶች ወተት ፈለቀ፡፡ እርሱዋ አንተን ብትሸከምህ አንተ ጽንዕ ሰጥተሃት ነው፤ በተራብክ ጊዜ አንተን ከጡቶቹዋ ትመግብህ ዘንድ፣ ነቢዩ ዳንኤል በታላቅ ተራራ የመሰለህ አንተን አንደ ሕፃናት ታቀፈችህ፤ በፈቃድህ የተጠማህ አንተን በእጆቹዋ በፍቅር ትዳብስህ ዘንድ፤ የምህረት እሳት የሆንኽ አንተ ክንዶቿን መለኮታዊው እሳት እንዳይቃጥላቸው ጠበቅኻቸው፡፡

ጌታ ሆይ እናትህ ግሩም የሆኑ ተአምራት የተፈጸሙባት መካን ናት። ወደ እርሱዋ የሁሉ ጌታ የሆነው ገባ፤ የአገልጋዩን አርአያ ነስቶ ተወለደ። የእግዚአብሔር ቃሉ የሆነ እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ ዝምተኛ ሆኖ ተወለደ። ነጎድጓድ የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ ጭምት ሆኖ ተወለደ። እረኛ የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ በግ ሆኖ በመወለድ በአባግዕ ቋንቋ ተናገረ፡፡

ጌታ ሆይ የእናትህ ማኅፀን ከተፈጥሯዊው ሥርዓት በተቃራኒው ፈጸመ፤ ሁሉን ያከናወነ በባለጸግነቱ ወደ እርሷ ገባ፤ ደሃ ሆኖ ተወለደ። ከሁሉ በክብር የሚልቀው እርሱ ወደ እርሷ ገባ፤ ትሑት ሆኖ ተወለደ። በክብሩ ገናና የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ የባሪያውን መልክ ይዞ ተወለደ። ብርቱ የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ ጥበቃ እንደሚያስፈልገው ሕፃን ሆኖ በማኅፀን ተገኘ። ፍጥረትን ሁሉ የሚመግበው መራብንና መጠማትን ገንዘቡ አደረገ፤ (አጣጣመ) ሁሉን በበረከቱ የሚያለብሰውና የሚያስጌጠው እርሱ ራቁቱን ተወለደ።

እኛን ለማዳን ሲል የእኛን ተፈጥሮ ገንዘቡ ላደረገ ለእርሱ ክብር ምስጋና ይሁን።

መልካም በዓለ ልደት...... @EotcLibilery @EotcLibilery @EotcLibilery
+ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ +

ጌታችን በቤተልሔም ለመወለዱ ምክንያት የሆነው ለሕዝብ ቆጠራ ሲሉ ወደ ይሁዳ አውራጃ በመምጣታቸው ነበር:: ለቆጠራ መጥተው ከመቆጠራቸው በፊት ጌታችን ተወለደ:: ወደ ናዝሬት ከመመለሳቸው በፊት ግን ሁለት ሆነው ሊቆጠሩ የመጡበትን የሕዝብ ቆጠራ ሦስት ሆነው አድርገው ተቆጥረዋል::

እባካችሁ ያንን የቆጠራ መዝገብ ያለበትን ቦታ የምታውቁ የሮማውያን ታሪክ መርማሪዎች ካላችሁ ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል:: ደግሞ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ምን ያደርግልሃል? ካላችሁ መዝገቡ ይገኝ እንጂ እኔ ግን የምፈልገው አንድ ስም አለ:: ከብዙ የይሁዳ ተወላጆች ስም መካከል ሰሎሜ ዮሴፍ ማርያም ከሚሉ ስሞች አጠገብ አንድ ዓለም የዳነበት ስም በሕዝብ ቆጠራው መዝገብ ሥር ተጽፎአል::

ጉልበት ሁሉ የሚሰግድለት ስም : ከሰማይ በታች እንድንበት ዘንድ የተሠጠን ስም : ከስም በላይ የሆነ ስም : ቅዱስ ገብርኤል በክብር ይዞት የወረደና ለድንግሊቱ የነገራት ስም : አጋንንት ሲሰሙት የሚንቀጠቀጡለት ስም : ሙታንን የሚያስነሣ ድውያንን የሚፈውስ ስም በዚያ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ላይ እንደዋዛ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል::

ኢየሱስ ✍🏽

አንተ የሕዝብ ቆጠራ ሠራተኛ ሆይ ይህንን ስም እዚያ መዝገብ ላይ ስትጽፈው ብዕርህ አልተሰበረም ወይ? ቀለሙስ አልሸሸም ወይ? እጆችህስ አልተንቀጠቀጡም ወይ?

ጌታችን በዚያ መዝገብ ላይ ተጻፈ:: በዚያ መዝገብ ከጌታ ጋር የተጻፉት ንጽሕት ድንግልና ጻድቁ ዮሴፍ ብቻ አልነበሩም:: በዚያች ግዛት ያሉ ሰዎች ሁሉ አብረው ተጽፈዋል:: ጥሩ ሰዎች ክፉ ሰዎች ወንጀለኞች ነፍሰ ገዳዮች ሰካራሞች አመንዝሮች በዚያ መዝገብ ላይ ስማቸው ተጽፎአል::

ክርስቶስም ገና ከመወለዱ ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: በሕይወት ዘመኑ የኃጢአተኞች ወዳጅ የሚል ቅጽል ስም የወጣለት ጌታ በዕለተ አርብም በግራና ቀኙ ከወንበዴዎች ጋር አብሮ የተሰቀለው ጌታ አሁንም በልደቱ ጊዜ "ከዓመፀኞች ጋር ተቆጠረ" (ኢሳ 53:12)

እኛን ከቅዱሳን ጋር ሊደምረን እሱ ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: እኛን "ስማችሁ በሰማይ ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ" ለማለት እርሱ በምድር መዝገብ ላይ ተጻፈ::

ወዳጄ ክርስቶስ ስለ አንተ ሲል ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: አንተ ስለ እርሱ ከንጹሐን ጋር ተቆጠርለት:: በተወለደበት ጊዜ ከሰካራሞችና ዘራፊዎች ስም ዝርዝር ጋር ለአንተ ሲል አብሮ ተቆጠረ:: እስቲ አንተ ልደቱን አስበህ ከሚሰክሩት ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ውጣ:: ከዘራፊዎችም መካከል ተለይ:: ክርስቶስ ወደ አንድ ነገር የሚገባው የሚገቡትን ሊያወጣ ነው:: ወደ ሞት የገባው ሙታንን ሊያወጣ ነው:: ወደ ሲኦል የወረደው ነፍሳትን ከሲኦል ሊያወጣ ነው:: ወደ ሮማውያን የሕዝብ ቆጠራ የኃጢአተኞች መዝገብ ስሙ የገባውም የሁላችንን በደል ተሸክሞ እኛን ከዚያ መዝገብ ሊያስወጣን ነው::

"ስማችሁ ግን በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ"
ሉቃ 10:20

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 28 2013 ዓ ም
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ነቢዩ ኢሳይያስ ‘ስሙም ድንቅ!’ ብሎ እንደተናገረው የታተመችው ደብዳቤ ድንግል ማርያም የታቀፈችው ማድነቅ እንጂ ማወቅ የማይቻል ሕፃንን ነበር፡፡

እኛ የሰው ልጆች የጠበቅነው ፈራጅና ተበቃይ ፣ በእጆቹ ሰይፍን የያዘ ንጉሥን ነበር፡፡ እርሱ ግን የመጣው ሕፃን ሆኖ ነበር፡፡ እንደ ኃያል ገዢ ስንጠብቀው ‘ከእናቱ ጡት ወተትን እየለመነ እንደ ሕፃናት አለቀሰ’

የሰው ልጆች ራሳችንን ከእግዚአብሔር ጋር በማስተካከል ለሠራነው በደል ቅጣትን ልንሰማ ለተጠያቂነት ዝግጁ ሆነን ጠበቅነው፡፡ እርሱ ግን ፍቅራችንንና እንክብካቤያችንን ፣ ደግነታችንን የሚጠይቅ ፣ መታቀፍን የሚሻ ሕፃን ሆኖ እጆቹን ወደ እኛ ዘረጋ፡፡

እኛ መቼም በእግዚአብሔር ላይ ኖሮን የማያውቀውን እምነት እግዚአብሔር በእኛ ላይ አሳየ፡፡ የእኛ ኩራትና ትዕቢት ሳያግደው ራሱን ዝቅ በማድረግ ወደ እኛ ወረደ፡፡

በዚህ ሕፃን ዓለም ሁሉ ተደነቀ ፤ ሁሉም ከጠበቀው በላይ የሆነ ነገርን አገኘ፡፡

መካኒቱ ኤልሳቤጥ ወለደች ፣

ዲዳው ዘካርያስ ትንቢት ተናገረ ፣

ድንግሊቱ እናት ሆነች ፤

እረኞች ከመላእክት ጋር ቆመው ወግ አወጉ ፤

የከብቶች በረት ቤተ መንግሥት ሆነ ፣

እንስሳት የወለደችን እናት ከብርድ ለመከለል ከበቧት ፣

ከዋክብት መንገድ መሪ ሆኑ ፣

ነገሥታት በድሆች ቤት እጅ መንሻ አቀረቡ ፤

አረጋዊው ስምዖን ሞትን መፍራት አቆመ ፤

ኃያሉ ንጉሥ ሔሮድስ ሁለት ዓመት ያላለፉ ጨቅላ ሕፃናትን እንደ ኃያላን ወታደሮች ፈራቸው፡፡

ይህ ሕፃን ያላመጣው ድንቅ ነገር አልነበረም!

የብርሃን እናት ገጽ 275
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 29 2015 ዓ.ም.
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ይህችን መዝሙር ለእናንተ ጻፉ (ዘዳ 31:19)

የልደት ሰሞን የምንሰማት ዜማዋ ያማረ አንዲት መዝሙር አለች :-

"እንደ ዮሴፍ ወይ እንደ ሰሎሜ በሆንን
ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም  ኢየሩሳሌም
    በሆንን አምላክ ሲወለድ ባየን"

የሚል መዝሙር ነው:: በጣም ደስ የሚያሰኝ ሃሳብ ያለው ቢሆንም ትንሽ የሚከነክን ጂኦግራፊያዊ ችግር አለው::

እንደሚታወቀው ጌታ የተወለደው ከኢየሩሳሌም 10 ኪሎ ሜትር በምትርቀው በቤተልሔም ነው:: ምንም ቅርብ ቢሆንም ምንም እንኩዋን ሁለቱም የይሁዳ ግዛቶች ቢሆኑም ምንም እንኩዋን ኢየሩሳሌም ብሎ ጠቅላላውን መጥራት የተለመደ ቢሆንም ነገር ግን ጌታ በተወለደ ምሽት ኢየሩሳሌም የተገኘ ሰው እንደዮሴፍና ሰሎሜ አምላክ ሲወለድ አያይም:: በዛሬው አስተዳደራዊ ክልል ደግሞ ከሆነ ደግሞ መዝሙሩ የበለጠ ይበላሽና "ጌታ በፍልስጤም ሲወለድ ምነው እኔ እስራኤል ውስጥ በሆንሁ" እንደማለት ይሆናል::

ይህን የመሰለ መዝሙር ታዲያ ምን እናድርገው ካልን ዜማው ሳይሰብር እንዲህ መዘመር ይቻላል :

"እንደ ዮሴፍ ወይ እንደ ሰሎሜ በሆንን
በቤተልሔም በቤተልሔም በቤተልሔም
    በሆንን አምላክ ሲወለድ ባየን"

ከዚያ ውጪ በጌታ ልደት ሌሊት በቤተ ክርስቲያን የሚያሳልፍ ሁሉ በጌታ ልደት እንደተገኘ ነው:: "እመቦ ዘአክበረ ልደተ እግዚእ ይከውን ክብሩ ከመ ሰብአ ሰገል" (የጌታን ልደት የሚያከብር ቢኖር ክብሩ እንደ ሰብአ ሰገል ክብር ይሆናል) ይላል ሊቁ::
የእኛ ቤተ ክርስቲያን የገና ሰሞን የሚሠራና በዓሉ ሲያልፍ የሚፈርስ የቤተልሔም ግርግም ሳይሆን ለሁልጊዜ ቋሚ የሆነ አገልግሎት የሚፈጸምበት ቤተልሔም ያላት ቤተክርስቲያን ናት:: ወደ ቤተክርስቲያን ሒድ : ፊትህን ወደ ምሥራቅ መለስ ካደረግህ ቤተልሔምን ታያታለህ:: "የነቢያት ሀገራቸው ቤተልሔም ሆይ ደስ ይበልሽ" ብለህ ጌታ የተወለደበትን ሥፍራ ተሳለም::

በልደቱ በዓል ቀን ወደ ሌላ ሥፍራ አትሒድ:: የጌታ ልደት በዲያቢሎስ ጭፈራ ቤት አይከበርም:: በእንግዶች ማደሪያ ሔደህ ልደቱን ለማክበር እንዳትሞክር:: እርሱ ያለው ቤተልሔም ነው:: ልደቱን በዝማሬ ካከበርህ ደስ ይለዋል ትልቅ ሽልማትን ይሠጥሃል::

ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል :-

"ሄሮድስ ልደቱን ላከበረችለት ልጅ ደስ ተሰኝቶ ክፋትን የተሞላ ሥጦታን ይኸውም የመጥምቁን አንገት በወጪት ሠጥቶአት ነበር::  ክፉው ሄሮድስ ይህን ካደረገ ርኅሩኁ ክርስቶስ ልደቱን የሚያከብሩ ሰዎችን ምን ያህል በጎ ሽልማትን ይሸልማቸው ይሆን?"

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቁር ውኃ : ኢትዮጵያ
ታኅሣሥ 25 2012 ዓ ም
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም በደረሰ የእሳት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ።

በደብረሊባኖስ ገዳም በጠበልተኞች ማረፊያ ክፍል ውስጥ በተነሳ ድንገተኛ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉም ታውቋል።

በትላንትናው ዕለት ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ በገዳሙ የጠበልተኞች ማረፊያ ክፍል በተነሳው የእሳት አደጋ ከ20 በላይ ክፍሎች የወደሙ ሲሆን እሳቱ ሌሎች አደጋዎችን እንዳያደርስ በገዳሙ መነኮሳት፣ በአካባቢው ምእመናን እና በጸጥታ ኃይል አባላት ከፍተኛ ርብርብ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ልሳነ #ግእዝ #ክፍል #ሦስት
አኀዝ/ቁጥር
ግእዝ ቋንቋ የራሱ የሆኑ ቁጥሮች አሉት። መሥራች ቁጥሮች የሚባሉትም የሚከተሉት ናቸው።
፩=አሐዱ=አንድ
፪=ክልዔቱ=ሁለት
፫=ሠለስቱ=ሦስት
፬=አርባዕቱ=አራት
፭=ኀምስቱ=አምስት
፮=ስድስቱ=ስድስት
፯=ሰብዓቱ=ሰባት
፰=ሰመንቱ=ስምንት
፱=ተስዓቱ=ዘጠኝ
፲=አሠርቱ=አስር
፳=ዕሥራ=ሃያ
፴=ሠላሳ=ሠላሳ
፵=አርብዓ=አርባ
፶=ኀምሳ=አምሳ
፷=ስድሳ/ስሳ=ስልሳ
፸=ሰብዓ=ሰባ
፹=ሰማንያ=ሰማንያ
፺=ተስዓ=ዘጠና
፻=ምእት=መቶ
፼=እልፍ=አስር ሺ
፻፼=አእላፋት=ሚልዮን
፼፼=ትእልፊታት=መቶ ሚልዮን
፻፼፼=ምእልፊታት=አስር ቢልዮን
ናቸው። እነዚህ መስራች ቁጥሮች ናቸው። ለዛሬ እስከ ቁጥር ፲፻ (አንድ ሺ) ያሉትን እንመልከት። አስር ካልን በኋላ አስራ አንድ ለማለት አሠርቱ ወአሐዱ ማለት ነው። ሲጻፍም ፲፩ ይሆናል። 46 ቁጥርን በግእዝ ጻፍ ብትባል ፵፮ ታደርገዋለህ። ሲነበብ ደግሞ አርብዓ ወስድስቱ ይላል።

ከመቶ እስከ አንድ ሺ ያሉ ቁጥሮች ወደ ግእዝ ሲለወጡ ደግሞ እንደሚከተለው ነው። ለምሳሌ 200 ወደ ግእዝ ሲለወጥ ፪፻ ይሆናል። ሲነበብም ክልዔቱ ምእት ይሆናል። 204 ወደ ግእዝ ሲለወጥ ደግሞ ፪፻፬ ይሆናል ሲነበብ ደግሞ ክልዔቱ ምእት ወአርባዕቱ ይሆናል። 253 ወደ ግእዝ ሲለወጥ ፪፻፶፫ ይሆናል ሲነበብም ክልዔቱ ምእት ኀምሳ ወሠለስቱ ይሆናል። በዚህ መልኩ እስከ አንድ ሺ ያሉ ቁጥሮችን መስራት ይቻላል። ለምሳሌ 444ን በግእዝ ለመጻፍ ፬፻፵፬ ይሆናል ሲነበብም አርባዕቱ ምእት አርብዓ ወአርባዕቱ ይላል ማለት ነው። እንዲህ እያለ አንድ ሺ ላይ ሲደርስ አሠርቱ ምእት ይላል። አስር መቶ እንደማለት ያለ ነው። ከአንድ ሺ እስከ አስር ሺ በቀጣይ ክፍል እንመለከታለን።

የዕለቱ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ቁጥሮች ግእዝ ለውጡ። እንዴት እንደሚነበቡም ግለጽ።
፩) 996
፪) 84
፫) 340
፬) 702
፭) 175
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ልሳነ #ግእዝ #ክፍል #አራት
ከ1000 እስከ 10000 ያሉ ቁጥሮች
፲፻_አሠርቱ ምእት1 ሺ
፳፻_ዕሥራ ምእት_2 ሺ
፴፻_ሠላሳ ምእት_3 ሺ
፵፻_አርብዓ ምእት4 ሺ
፶፻_ኀምሳ ምእት_5 ሺ
፷፻_ስሳ ምእት__6
፸፻_ሰብዓ ምእት_7 ሺ
፹፻ሰማንያ ምእት8 ሺ
፺፻_ተስዓ ምእት_9 ሺ
እልፍ__10 ሺ
ነው። በዚህ መካከል ያሉ ቁጥሮችን ለመጻፍ ለምሳሌ 1008ን በግእዝ ለመጻፍ ፲፻፰ ይሆናል ሲነበብም አሠርቱ ምእት ወሰመንቱ ይሆናል። 1018ን በግእዝ ለመጻፍ ፲፻፲፰ ይሆናል ሲነበብም አሠርቱ ምእት አሠርቱ ወሰመንቱ ይሆናል። 1118ን በግእዝ ለመጻፍ ፲፻፩፻፲፰ ወይም ፲፩፻፲፰ ይሆናል። ሲነበብም የመጀመሪያው አሠርቱ ምእት ወአሐዱ ምእት አሠርቱ ወሰመንቱ ይላል። ሁለተኛው ደግሞ አሠርቱ ወሰመንቱ ምእት አሠርቱ ወሰመንቱ ይላል። በብዛት መጻሕፍት ላይ የምናገኘው ሁለተኛውን ነው። 2016 በግእዝ ለመጻፍ ፳፻፲፮ ይላል። ሲነበብም እሥር ምእት አሠርቱ ወስድስቱ ይላል። 7683 በግእዝ ሲጻፍ ፸፻፮፻፹፫ ይሆናል። ሲነበብም ሰብዓ ምእት ወስድስቱ ምእት ሰማንያ ወሠለስቱ ይላል። እንዲህ እያልን አስር ሺ ላይ ስንደርስ እልፍ እንላለን ማለት ነው።

የዕለቱ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ቁጥሮች ወደ ግእዝ ለውጥ። ንባባቸውንም በግእዝ ጻፍ።
፩) 3251
፪) 8888
፫) 7004
፬) 5500
፭) 4690
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ልሳነ #ግእዝ #ክፍል #አምስት
ከ10000 እስከ ሚልዮን ያሉ ቁጥሮች
_እልፍ_10 ሺ
፪፼ክልዔቱ እልፍ20 ሺ
፫፼ሠለስቱ እልፍ30 ሺ
፬፼አርባዕቱ እልፍ40 ሺ
፭፼ኀምስቱ እልፍ50 ሺ
፮፼ስድስቱ እልፍ60 ሺ
፯፼ሰብዓቱ እልፍ70 ሺ
፰፼ሰመንቱ እልፍ80 ሺ
፱፼ተስዓቱ እልፍ_90 ሺ
፲፼አሠርቱ እልፍ_100 ሺ
አንድ መቶ ሺ አሠርቱ እልፍ ነው። በሌላ አገላለጽ አእላፍ እየተባለም ይጠራል። ከዚያ ቀጥሎ ያሉ ቁጥሮች ደግሞ እንደሚከተለው ቀርበዋል።
፳፼_ዕሥራ እልፍ_200 ሺ
፴፼ሠላሳ እልፍ300 ሺ
፵፼አርብዓ እልፍ400 ሺ
፶፼ኀምሳ እልፍ500 ሺ
፷፼ስድሳ እልፍ600 ሺ
፸፼ሰብዓ እልፍ700 ሺ
፹፼ሰማንያ እልፍ800 ሺ
፺፼ተስዓ እልፍ900 ሺ
፻፼አእላፋት_1 ሚልየን
ናቸው። በምሳሌ ለመመልከት ያህል 20004 በግእዝ ሲጻፍ ፪፼፬ ይሆናል ሲነበብ ክልዔቱ እልፍ ወአርባዕቱ ይላል። 20690 በግእዝ ሲጻፍ ፪፼፮፻፺ ይሆናል። ሲነበብ ክልዔቱ እልፍ ስድስቱ ምእት ወተስዓ ይላል። 48749 በግእዝ ስንጽፈው ፬፼፹፻፯፻፵፱ ይላል ሲነበብም አርባዕቱ እልፍ ወሰማንያ ምእት ወሰብዓቱ ምእት አርብዓ ወተስዓቱ ይላል። 144000 በግእዝ ሲጻፍ ፲፼፬፼፵፻ ይላል ሲነበብም አሠርቱ እልፍ ወአርባዕቱ እልፍ ወአርብዓ ምእት ይላል። በመጨረሻም 777777 በግእዝ ሲጻፍ ፸፼፯፼፸፻፯፻፸፯ ይላል ሲነበብም ሰብዓ እልፍ ወሰብዓቱ እልፍ ወሰብዓ ምእት ሰብዓ ወሰብዓቱ ይላል ማለት ነው።

የዕለቱ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ቁጥሮች ወደ ግእዝ ለውጥ ንባባቸውንም አስቀምጥ።
፩) 50045
፪) 238029
፫) 612340
፬) 708257
፭) 983216
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ልሳነ #ግእዝ #ክፍል #ስድስት
ከሚልዮን በላይ ያሉ ቁጥሮች
፻፼አእላፋት1 ሚልዮን
፪፻፼ክልዔቱ አእላፋት2 ሚልዮን
፫፻፼ሠለስቱ አእላፋት3 ሚልዮን
፬፻፼አርባዕቱ አእላፋት4 ሚልዮን
፭፻፼ኀምስቱ አእላፋት5 ሚልዮን
፮፻፼ስድስቱ አእላፋት6 ሚልዮን
፯፻፼ሰብዓቱ አእላፋት7 ሚልዮን
፰፻፼ሰመንቱ አእላፋት8 ሚልዮን
፱፻፼ተስዓቱ አእላፋት9 ሚልዮን
፲፻፼አሠርቱ አእላፋት10 ሚልዮን
ይላል ማለት ነው። አሠርቱ አእላፋት በሌላ አገላለጽ ትእልፊት እየተባለም ይጠራል። ከዚህ በኋላ ዕሥራ አእላፋት (፳፻፼) ሠላሳ አእላፋት (፴፻፼) እያለ እስከ ትእልፊታት (፼፼) ይዘልቃል። ትእልፊታት ደግሞ ክልኤቱ ትእልፊታት (፪፼፼) ሠለስቱ ትእልፊታት እያለ እስከ ምእልፊታት ይዘልቃል (፻፼፼)። በመካከል ፲፼፼ (አሠርቱ ትእልፊታት) በሌላ አገላለጽ ምእልፊት ይባላል።አንድ ቢልዮን የሚባለው በግእዝ ምእልፊት ነው። በግእዝ ቋንቋም እስከ ፈለገን ድረስ መቁጠር እንችላለን። አንድ ምሳሌ እንመልከት ለምሳሌ 2763892623 ውደ ግእዝ ሲለወጥ ፳፼፼፯፻፼፻፷፻፼፫፼፻፹፼፱፼፳፻፮፻፳፫ ይሆናል።ሲነበብም ዕሥራ ትእልፊታት ወሰብዓቱ ትእልፊታት ስድሳ አእላፋት ወሠለስቱ አእላፋት ሰማንያ እልፍ ወተስዓቱ እልፍ ዕሥራ ምእት ወስድስቱ ምእት ዕሥራ ወሠለስቱ ይላል ማለት ነው።

የዕለቱ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ቁጥሮች ወደ ግእዝ ለውጥ ንባባቸውንም ጻፍ
፩) 3456987247
፪) 234789289
መምህር በትረ ማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
እውነተኛ የበጎች በር
                         
Size 27.8MB
Length 1:11:18

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የትዳር ሕይወት ማለት ሩቅ አገር ከአንድ ከመረጡት ሰው ጋር የሚያደርጉት የሕይወት ዘመን ጉዞ ነው።

ጉዞ እንደ መኾኑ ዓቀበት አለው፤ ቁልቁለት አለው።

አስደሳች ሜዳ አለው፤ አሳዛኝ ጉጻጉጽም አለው።

መንገዱ የአስፓልት ሊኾን ይችላል፤ የፒስታም ሊኾን ይችላል።

በጫማ ሊኾን ይችላል፤ እንደ አበበ ቢቂላ በባዶ እግርም ሊኾን ይችላል።

በሰሐራ በረኻ አንድ ወንድና አንዲት ሴት የሚያደርጉት ጉዞ አድርጋችሁ ማሰብ ትችላላችሁ። በዚሁ መካከል አንዱ ከአንዱ መለያየትስ ይቅርና ቢኳረፉ ራሱ ምን ዓይነት ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል አሰባችሁት?

ታዲያ ይህን ጉዞ ለመጓዝ ሳያስብበት የሚገባ ማን ሰነፍ ሰው ነው? ቀድሞ ስለ መንገዱ ከባድነትና ቀላልነት፣ አብሯት ስለምትሔደው ሴት ድካምና ጥንካሬ መረጃ ሳይኖረው (Orient ሳይደረግ) ድንገት ተነሥቶ የሚሔድ ታዲያ ማን ነው?

እናስ? እናማ ከማግባትዎ በፊት ጉዞዎ እንዳይበላሽ አብዝተው ይድከሙ እንጂ ካገቡ በኋላ የተበላሹ ነገሮችን ለማስተካከል አይድከሙ። ስለ መንገዱና ሊገጥምዎት የሚችለውን ዕንቅፋት እንዴት ማስቀረትና ማለፍ እንዳለብዎት አስቀድመው ይወቁ እንጂ ጉዞ ከጀመሩና ዕንቅፋት ሲገጥምዎትና ወድቀው ሲቆስሉ ስለ ማደናቀፊያ ድንጋዩ ለማወቅ አይጣሩ።
(ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የትዳር ዓላማ ከገባን

"የትዳር ዓላማ፥ ሊቁ እንደሚነግረን ጽድቅን ለመፈጸም ነው፡፡ ይህን ዓላማ አድርጎ ወደ ትዳር የሚገባ ክርስቲያን ልጅ ባይወልድ እንኳን አይፋታም፤ .... አንዳቸው ቢሰንፉ እንኳን ከዝሙት ተጠብቀውና ራሳቸውን ገዝተው እግዚአብሔርን በማመስገን ይኖራሉ እንጂ አይፋቱም፡፡ ጋብቻ የተሰጠው ለዚህ ነው፡፡ የጋብቻ ግቡ ይኼ ነው፡፡ የጋብቻ ጥቅሙ ይኼ ነው፡፡"

"በአሁኑ ሰዓት በባልና በሚስት መካከል የሚፈጠሩት ችግሮች አብዛኞቹ ይህን ካለመገንዘብ የሚመጡ ናቸው፡፡ ወጣቶች የትዳር ዓላማ ጽድቅ እንደ ኾነ ከገባቸው ግን በመካከላቸው የሚፈጠሩትን “አለመግባባቶች” በቀላሉ መፍታት ይችላሉ፡፡ መጽደቂያ ኾነው በተሰጡት ነገሮች እንዲሁ አይጨቃጨቁም፡፡ አንዱ ሲቈጣ፥ ሌላኛው የትዳር አጋር የትዳር ዓላማ ጽድቅን መፈጸም እንደ ኾነ ከገባው ይታገሣል፡፡ የአንዱ ጠባይ ክፉ ቢኾን ሌላኛው የትዳር አጋር የትዳር ዓላማ ምን እንደ ኾነ ከተረዳ ይህን የትዳር አጋሩን ክፉ ጠባይ ወደ መልካም ለመቀየር ይጥራል፡፡ ከሰውነታችን አንዱ ክፍል ለምሳሌ እጅ ቢታመም ከሌላው ሰውነታችን ይልቅ ልዩ እንክብካቤ እንደምናደርግለት ኹሉ ይህን የትዳር አጋርም የትዳር ዓላማ ጽድቅን መፈጸም እንደ ኾነ ከተረዳ የተረዳውንም በተግባር ለመኖር የሚጥር ከኾነ ለባለቤቱ ልዩ እንክብካቤ ያደርጋል እንጂ አይማረርም፡፡ ይህ ግን እንደ ተናገርን የትዳር ዓላማ ከገባው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ዓላማ ትተን መመዘኛችን በዚህ ምድር በሚቀሩ ነገሮች ላይ መኾን የለበትም፡፡ የትዳር አጋርን የምንፈልግበት ምክንያት ጽድቅን ለመፈጸም መኾን አለበት፡፡"

(ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው ገጽ 40-41 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ጥር 3 የደብረ_ሊባኖስ_ገዳምን_የመሠረቱና_በስማቸው_የተሠየመላቸው እና የእንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳምን_ጸበል_ያፈለቁ የታላቁ አባት አባ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ በዓለ ዕረፍት ነው ።

#ጥር ፫፤ #የአቡነ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ_በዓለ_ዕረፍት_ክብረ_በዓል_የሚከብርባቸው ፲፩ ገዳማትና አድባራት (ከታች)፡፡

#በአ.አ. #እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት ቀድሞ በቅዳሴና በውዳሴ ታቦተ ሕጋቸው ሲከበር የቆየው የአቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ ታቦተ ሕጋቸው #ረቡዕ_ጥር 3/2015 ዓ.ም.
አራተኛ ጊዜ_ታቦተ_ሕጋቸው_ወጥቶ_ይከብራል፡፡ (ሁላችሁም እንድትገኙ ገዳሟ ጥሪዋን አስተላልፋላች)፡፡
አባ ሊባኖስ #የደብረ_ሊባኖስ_ገዳምን_የመሠረቱና_በስማቸው_የተሠየመላቸው
፠ ቅዱስ ላሊበላ ከ11ዱ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱን በስማቸው ያነፀላቸው፡፡
#ከደረቅ_ዐለት_ላይ_ውሃ_እያፈለቁ_ድውያንን_የሚፈውሱ_ተአምረኛ_አባት
፠ በኤርትራ አካለ ጉዛይ ገዳመ መጣዕ፣ በአኵሱም ከተማ አጠገብ፣ በላስታ ላሊበላ፣ ደብረ ወርቅ አቡነ ሊባኖስ ገዳም፣ እንዲሁም ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ በአ.አ. እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ገዳም ክብረ በዓል የሚከበርላቸው።

፠ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ንግሥት ሊድሯቸው ሲሉ መመነን በመፈለጋቸው መልአክ በሌሊት መጥቶ ወደ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዘንድ አደረሳቸው፡፡
፠ አባ ጳኩሚስም ሥርዐተ ገዳምን፥ አስኬማ መላእክትን፥ ቅናተ ዮሐንስን አስተማሯቸው፤ አመነኮሷቸውና ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር እንዲገናኙ አደረጓቸው፡፡
፠ ቀድሞ የመራቸው መልአክ ከአባ ጳኩሚስ ‹‹ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሂድና ተጋድሎህን በዚያ ፈጽም ዝናህ በስፋት ይነገራል፣ ለብዙዎችም አባት ትሆናቸዋለህ›› አላቸው፡፡ ቀጥሎም ራሱ መልአኩ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸውና በአኵሱም ተቀመጡ፡፡
፠ በዚያም ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ወደ ሸዋ መጡና ወንጌልን ዞረው አስተምረው ብዙ ድውያንን ፈውሰው (ቀድሞ የዋልድባን ገዳም ባስፋፉ አባቶች የተመሠረተችውን #የእንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳምን እስፋፍተው፡፡) ተመልሰው ወደ አኵሱም ሄዱ፡፡
፠ በአኵሱምም 7 የተለያዩ ጸበሎችን ከድንጋይ ላይ በተአምራት አፍልቀው ድውያንን ፈውሰው ፥ ዕውራንን አበሩ፡፡ በዓታቸውንም ከአኵሱም ጽዮን ፊት ለፊት አድርገው ሲኖሩ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባታችን በተአምራት ከጭንጫ ካፈለቁት ጸበል ‹‹ተራ ውሃ ነው›› ብላ አንዲት ሴት ልጇን አዝላ ልትቀዳ መጣች፡፡ ወዲውም ከቦታው ስትደርስ አድጧት ወደቀችና ልጇም አምልጥጧት ልቡን ድንጋይ መቶት ሞተ፡፡ ሴትዮዋም ስትጮህ አባ ሊባኖስ ፈጥነው ወጡና በልጁ ላይ ጸልየው በመስቀል ምልክት አማትበው ከሞት አስነሥተውታል፡፡ ሕፃኑ ልጅ ከሞት እንደተነሣ ‹‹አምላከ አባ ሊባኖስ›› ብሎ አመሰገነ፡፡ (ስዕላቸው የሚገልጸው ይህንን ተአምር ነው፡፡)
፠ ይህንንም ደግ ሥራቸውንና ተአምራታቸውን ያዩ አንዳንድ እኩይ ካህናት በቅናት ተመልተው ‹‹ምትሃት ነው የሚያሳየው›› ብለው በጻድቁ ላይ ሕዝቡን አሳደሙባቸው፡፡ አባታችንም ካህናቱን ለመምከር ቢሞክሩም አላስቀምጥ አሏቸው፡፡ ይልቁንም ጦር ጦራቸውን ይዘው አሳደዷቸው፡፡
፠ አባታችንም በዚህ እጅግ አዝነው ከአኵሱም ተነሥተው ደርቃ ወደምትባል ቦታ ሄዱ፡፡ በዚያም በጾም በጸሎት እየተጋደሉ ሲኖሩ፤ በእነዚያ በጠሏቸውና በክፋት በተነሡባቸው ካህናት አገር ግን ለ3 ዓመት ምንም ዝናብ ሳይዘንብ ቀረ፡፡ አባታችን በተሰደዱባት በደርቃ አገር ግን ብዙ ዝናብ ይዘንብ ነበር፡፡ አባታችን በዚያችም አገር እንደልማዳቸው ከዐለት ላይ ውኃ አፍልቀው በውኃው ብዙ ድውያንን ፈውሰውበታል፡፡ በዚያም ትልቅ በዓት መሥርተው በተጋድሎ ሲኖሩ በክፉ የተነሡባቸው እኩይ የሆኑ ካህናት መጥተው ‹‹አባታችን በከንቱ አምተንሃል በድለንሃልና ይቅር በለን፣ በድርቅ ማለቃችን ነውና ዝናብም እንዲዘንብልን ጸልይን›› ብለው ከእግራቸው ሥር ወደቁ፡፡ አባታችንም ይቅር ብለው ከፈጣሪ አማለዷቸው፡፡ ዝናቡም ወዲያው ዘነበላቸውና በአገሪቱ ጥጋብ ሆነ፡፡

፠ ከዚህም በኋላ አባታችን አስቀድመው ወዳዩአት ወደ ሸዋ ምድር ግራርያ (የአሁኗ ደብረ ሊባኖስ) መጡና በዓታቸውን በአሰቦት ጫካ አደረጉ፡፡ ነገር ግን መልአኩ ተገልጦላቸው ‹‹ሊባኖስ ሆይ! ከዚህ ቦታ የአንተ መኖሪያ አይደለም፣ በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያገናኝ የሚያስታርቅ ታላቅ ጻድቅ (አቡነ ተክለ ሃይማኖት) ይወጣበታልና ይህ ቦታ የእርሱ ርስት ነው፣ የብዙ መነኮሳትም መንደር ይሆናል ነገር ግን የቦታው ስም በአንተ ስም ይጠራልሃል›› አላቸው፡፡ በኋላ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተወልደው በዓታቸውን በዚያ ቦታ ላይ ሲያጸኑ ቦታው ግን ‹‹ደብረ ሊባኖስ›› ተብሎ በመጀመሪያው አባት ስም ተሰየመ፡፡
፠ መልአኩም በሌሊት እየመራ ወደ አኵሱም ወሰዳቸው፡፡ ከዚያም ‹‹ታሪክ ወደምትሠራበት ዕጣ ክፍልህ ወደሆነው ቦታ አደርስሃለሁ›› አላቸውና ወደ ኤርትራ አካለ ጉዛይ አውራጃ ልዩ ስሙ መጣዕ ወደተባለው ቦታ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም አባታችን ድውያንን እየፈወሱ፣ ለምፃሞችን እያዳኑ፣ ሙታንን እያስነሡ ብዙ ተአምራትን እያደረጉ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹ሊባኖስ ዘመጣዕ›› የሚባለውን ትልቁን ገዳማቸውን መሠረቱ፡፡ በወቅቱ የነበረው አፄ ገብረ መስቀልም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን አሠራላቸው፡፡

፠ ቅዱስ ላሊበላ 23 ዓመት ሙሉ ካነጻቸው እጅግ ድንቅ 11 ቤተ መቅደሶች ውስጥ አንደኛውን በአባ ሊባኖስ ስም ሰይሞላቸዋል፡፡ አፄ ገብረ መስቀል ያሠራላቸው ሌላኛው ገዳማቸው ትግራይ ተንቤን ውስጥ ይገኛል፡፡ እጅግ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የሚታወቁት አባታችን እንደ ተስዓቱ ቅዱሳን ከሮም በመምጣት በሀገራችን ላይ ብርሃንን አብርተዋል፡፡
፠+፠ በመጨረሻም ጥቅምት 2 ቀን ተፀንሰው ፤
፠+፠ ሐምሌ 3 ቀን ተወለደው፤
፠+፠ በ140 ዓመታቸው ጥር 3 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡
፠+፠ ቅዳሴ ቤታቸው ደግሞ ሐምሌ 3 ነው፡፡ ይኸውም ለመጀመሪያ ጊዜ በዐፄ ገብረ መስቀል ጊዜ በስማቸው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ የተመረቀበት ዕለት ነው፡፡
* እኛም ለክብረ በዓሉ የሚሆነውን ከዋይዜማው ጀምሮ ሙሉውን ሥርዐተ ማኅሌት እነሆ ብለናል፡፡

#እንጦጦ_ሐመረ_ኖኅ_ኪዳነ_ምሕረት_ገዳም

፠ እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት በ485 ዓ.ም. የሸዋ አባቶች የዐብዩ መድኀኔዓለምንና የበረከት ኪዳነ ምሕረት ታቦትን ይዘው ለ3 ወራት የተሰባሰቡባት ስትሆን፤ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን እንጦጦ ላይ አስቀምጠውና ገዳሟን መሥርተው፤ ታቦተ መድኀኔ ዓለምን ይዘው ወደ ዋልድባ በመሄድ ቀድሞ ጌታችን የገደመውን ገዳም ለ2ኛ ጊዜ አስፋፍተውታል፡፡
፠ ከ16 ዓመታትት በኋላ በ500 ዓ.ም. ደግሞ አቡነ ሊባኖስ ዘመጣዕ ከአኵሱም ወደ ሸዋ ሲመጡ ሐመረ ኖኅን በገዳምነት ገድመው ጠበሏን አፍልቀው ሕሙማንን ፈውሰው ተመልሰዋል፡፡
፠ በ197 ዓ.ም. አንድ ምዕመን ለአቡነ ተክለሃይማኖት አስፈቅደው፤ ገድላቸውን ከአኵሱም አጽፈው በማምጣት ማኅሌቱ እንዲቆም፣ ገድላቸው እንዲነበብ፤ 50 ብር እየከፈሉ የጻድቁን ዝክር እንዲገለገል አስደርገዋል፡፡
፠ የአባቶቻችን አምላክ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ይመስገን፨

#ጥር ፫፤ #የአቡነ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ_በዓለ_ዕረፍት_ክብረ_በዓል_የሚከብርባቸው ፲፩ ገዳማትና አድባራት፡፡

(አባ ሊባኖስ በሃገራችን ላይ 80 ገዳማትን መሥርተዋል)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/25 20:30:31
Back to Top
HTML Embed Code: