Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ (Gizachew Nega)
🌻🌼🌻🌼🌻 እንቁጣጣሽ 🌼🌻🌼🌻🌼

🌻መስከረም 1/2012ዓ.ም🌻

"ተሰብስበን እንዳማረብን
በአውዳመቱ ፍቅር ያዝንብብን"

የ 2012 ዓ.ም የመጀመሪያዋ ፀሀይ በአገሬ ሰማይ ስር ወጣች፡፡
የዛሬዋ ፀሀይ ሙሉ ዘመናችንን ታበራልን ዘንድ በፍቅር ፣በሰላም ፣በአንድነት ሀገራችን ቤታችን ብለን በአንድነት እጅ ለእጅ ተያይዘን መጓዝ አለብን፡፡
ኢትዮጲያ የቃልኪዳን አገር በልጆቿ ተከብራ ከአለም በላይ ደምቃ ትታይ

🌼 እንኳን አደረሳችሁ 🌼

🌼🇪🇹🌼🇪🇹🌼🇪🇹🌼🇪🇹🌼🇪🇹🌼🇪🇹🌼

🌻🌻🌻 መልካም በዓል 🌻🌻🌻
🇪🇹 ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! @youthkiller
Now, if you're COMMITTED here's what i would like you to do:

:> Take a sheet of paper and write down ONE GOAL for every area of your life health, wealth, relationships, career, business, charitable.
Write down one goal and WHEN you want to achieve it by and then, what I want to do is write down THREE ACTION STEPS that you can take towards achieving those goals.

What is THREE ACTION STEPS? @youthkiller
Hdjddh
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ (Gizachew Nega)
🏃🏃🏃‍♀🏃‍♀
ወጣትነት

🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣

ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም! ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማን ነው መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም!

ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም! ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም!

ወጣትነት ይሄንንም ያንንም ይቺንም ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትን ለመርገጥ እየተጸየፉ መራመድ ማለት አይደለም! ወጣትነት በግዴለሽነት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድነት መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም! ወጣትነት በማይረባው በቀበሌኛው አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል እውቀት በመያዝ ይቺ እውቀት ብቻ ትበቃኛለች እያሉ አጉል መመጻደቅ ማለት አይደለም...

ወጣትነት ባህር ነው ። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው ። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት ነው ። ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው ። ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው ። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው ። ወጣትነት በዘረኝነት ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም አለም አቀፋዊ እይታን ማስፋት ነው ።

ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው ። ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው ። ወጣትነት ብርሃን ነው ። ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው ። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከመጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው ። ወጣትነት ማንበብ ነው ። ወጣትነት መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው ። ወጣትነት ለሌሎች መኖር ነው ። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው ። ወጣትነት እሳት ነው ። ወጣትነት ቤንዚል ነው ። ወጣትነት ቅጠል ነው ። ወጣትነት ጤዛ ነው ። ወጣትነት ታክሲ ነው ። ወጣትነት ምርጫ ነው ። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው ። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው ። ወጣትነት ውስጥን ፈተናን ለማለፍ ማጀገን ነው ። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው ። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው ... ።


ምንጭ ፦ " ኤጭ...! " መጽሐፍ ከገጽ 170-172 የተቀነጨበ
ደራሲ ፦ አዘርግ

👇👇👇👇
Join us @youthkiller

ለአስተያየትዎ
👇👇👇👇
@gzeman
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ (Gizachew Nega)
«ለደስተኛ ሕይወት»
ሼር ማድረግ ደስ ይላል፡፡ የዛሬ ደስታዎን ሼር በማድረግ ይጀምሩ፡፡
1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው።
2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።
3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡
4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።
5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡
6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦ ሰዎችን አትና፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡
7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው።
8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤ የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት ተንከባከበው፡፡
9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።
10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡ share @youthkiller
ጃክ ማ (Jack Ma) ይባላል።
☞ለሶስት ጊዜ ያክል ኮሌጅ ውስጥ ውጤት አልመጣለትም ።
☞30 ግዜ ለስራ አመልክቶ አልተሳካልለትም ።
☞KFC ቻይና ለመጀመሪያ ግዜ ሲከፍት ከእሱ ጋር 24 ሰዎች ለስራ ተወዳድረው እሱ ብቻ እድሉን አጣ::
☞ለፖሊስነት አመልክቶ እሱ ብቻ ተቀባይነት አጣ።
☞አሜሪካ ለሚገኘው ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን
ለመቀጠል ጠይቆ he was rejected በሕይወቱ ውስጥ በጣም ብዙ ውድቀቶችን አስተናግዶዋል:: ግን ተስፋ ቆርጦ እጁን አጣጥፎ አልተቀመጠም።

በ1994 ስለ ኢንተርኔት ሰማ። በ1995 ከትውልድ አገሩ ቻይና ወደ አሜሪካ ባጋጣሚ ያቀናል:: በዚህም ጊዜ በጓደኛው እርዳታ ስለ ኢንተርኔ ምንነት ማወቅ ቻለ። ኢንተርኔትን እንዳወቀ መጀመርያ የፈለገው ቃል "beer" የሚል ነበር። በዚህም ስለ ቢራ የተለያዩ መረጃዎችን ከተለያዩ አገሮች ያገኝ ቢሆንም ከአገሩ ቻይና ግን ምንም አይነት መረጃ ማግኝት አልቻለም።

በዚህም ተበሳጨና ስለ ቻይና አጠቃላይ መረጃ መፈለግ ተያያዘ አሁንም ውጤቱ 0 ነበር። በዚህም ቁጭት ከጓደኛው ጋር ሆኖ ሰለ ቻይና መረጃ የሚሰጥ ድህረ ገጽ ፈጠሩ፡፡ ድህረ ገጽ በተከፈተ በአምስት ሰዓት ውስጥ ከተለያዩ ቻይናዊያን የአብረን እንስራና እንተዋወቅ ጥያቄዎች ቀረቡለት። በዚህም ኢንተርኔት አዋጭ ስራ እንደ ሆነ ተገነዘበ፡፡ እንደዚህ እያለ የአለማችንን
ግዙፍ የe-commerce ተቋም የሆነውን ALIBABA GROUP ለማቋቋም በቃ፡፡
አሁን የ 38.8 billion USD ቢሊየን ዶላር የተጣራ ተቀማጭ እረብጣ owner የሆነው ማክ የአለማችን 33ተኛ ቱጃር ነው።
በማንኛውም ሁኔታ በምንም ምክንያት ተስፋ አትቁረጥ ዛሬ ባይሳካ ነገ ሌላ ብሩህ እና መልካም ቀን ነው። ወዳጄ አንድ ነገር ላይ ችክ አትበል አማራጮችን ተጠቀም አመራጮችን ተመልከት አማራጮችን ፍጠር፡፡
@youthkiller
ሁሉንም ሰው የማስደሰት ሱስ
ከሰዎች ጋር ባለህ ግንኙነት ልትሰራቸው ከምትችላቸው ስህተቶች መካከል ሁሉንም ሰው ለማስደሰት የመሞከር ስህተት አንዱ ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ ስህተት ነው ከምንልበት ምክንያት ዋነኛው፣ ምንም ያህል ሰዎችን ሁሉ ለማስደሰት ብንጣጣር እንኳ ሁኔታው የማይቻል በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰዎችን ሁሉ ለማስደሰት መሞከርና በማንኛውም ጊዜ በሁሉም ሰው ተቀባይነትን ለማግኘት መሯሯጥ እጅግ አድካሚና ለጉዳት የሚዳርግ በመሆኑ ነው፡፡
በአካባቢው የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ ለማስደሰት የሚታገል ሰው የመነሻ ሃሳቡ የተቀባይነትና በሁሉ የመወደድ ፍላጎት ነው፡፡ ከዚህ ነጥብ በመነሳት ከሚያደርጋቸውና ከሚናገራቸው ነገሮች የተነሳ ለጊዜው ሰዎች ሊደሰቱበት ቢችሉም፣ ብዙም ሳይቆይ የመገፋትና የባዶነት ስሜት ይጫጫነዋል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ሰው እርሱን በመቀበልና በሁኔታው በመደሰት እንደማይዘልቅ ቀስ በቀስ ስለሚደርስበት ነው፡፡
ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ትታገላለህ? ራስህን መዝነው …
1. ሌሎች ሰዎች ስለተሰማቸው ስሜት አንተ ሃላፊነት ይሰማሃል?
2. አንድ ሰው በአንተ ላይ እንደተበሳጨ ወይም እንዳዘነ ስታውቅ ከልክ ባለፈ ሁኔታ በስሜትህ ላይ ጫና ያስከትልብሃል?
3. ሰዎች እንደፈለጉ ወዲህና ወዲያ የሚያደርጉህ አይነት ሰው እንደሆንክ ይሰማሃል?
4. በአንድ ጉዳይ ላይ ከሌሎች ሰዎች ተቃራኒ ሃሳብ እያለህ እንኳን ተቀባይነት አጣለሁ በሚል ሰበብ ያንን ሃሳብህን ከመናገር ይልቅ መተባበር ይቀልሃል?
5. ብዙ ጊዜ ግልጽ የሆነ ጥፋት እንዳልሰራህ እያወከው እንኳን ይቅርታ የመጠየቅ ዝንባሌ አለህ?
6. አለመግባባት እንዳይፈጠር ለማድረግ ከአቅምህ በላይ ስትታገል ራስህን ታገኘዋለህ?
7. ሰዎች ስሜትህን ሲጎዱት ስለሁኔታው ለሰዎቹ በግልጽ ማውራት ይከብድሃል?
8. ሰዎች አንድን ነገር እንድታደርግላቸው ሲጠይቁህ ማድረግ ባትፈልግም እንኳን ካለብህ የመገደድ ስሜት የተነሳ እሺ የማለት ዝንባሌ አለህ?
9. ሌሎች ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር ስታይ ከዚያ በመነሳት እነሱን ለማስደሰት ስትል ሁኔታህን፣ ተግባርህንና ባህሪህን ትለዋውጣለህ?
10. ሰዎች በአንተ ላይ ያላቸው አመለካከት ጥሩ እንዲሆን ብዙ ስትሯሯጥ ራስህን ታገኘዋለህ?
ከላይ ለተጠየቁት አስር ጥያቄዎች ከግማሽ በላይ ለሆኑት “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ ምናልባት ከመስመር ያለፈ ሌሎች ሰዎች ለማስደሰት የመታገል ዝንባሌ ሊኖርህ ስለሚችል በሚገባ አስብበት፡፡
በነገራች ላይ፣ በእርግጥም ሰዎች ደስ እንዲላቸው ከራሳችን ምቾት ወጥተን ረጅም ርቀት ልንሄድ የሚገባን ጊዜ ሊኖር ይችላል፣ ሆኖም፣ ሰዎችን ለማስደሰት የማደርገው ጥረት የራሴን ሕልውና ወደሚነካ ክልል ውስጥ የሚያስገባኝ ከሆነ ሁኔታውን በሚገባ ላስብበት ይገባኛል፡፡ @youthkiller
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ
የአዕምሮ ምግቦች

ማንበብ የሰውን ልጅ የአዕምሮ ጡንቻ በማዳበር ለነገሮች ሁሉ ያለንን መረዳት በየጊዜው እንደሚያሳድገው የተረዳ ሰው ከማንበብ ሊቆጠብ አይችልም፡፡ የሰው ልጅ አካለ ሥጋ (Physical Body) ጡንቻዎች በስፖርታዊ እንቅስቃሴና በተመጣጣኝ ምግብ ሊዳብሩና ማራኪ ቅርጽ ሊይዙ ይችሉ ይሆናል፡፡ ጤንነታቸውም በነዚህና በሌሎች የህክምና መንገዶች ሊጠበቁ ይችላሉ፡፡ የአዕምሮ ጡንቻ የሚዳብረውና ጤናው የሚጠበቀው ግን በንባብና በመሳሰሉት የአዕምሮ ምግቦች ነው፡፡ እና የአዕምሮው ጡንቻ እንዳይዳብርና የመረዳት አቅሙ እንዳያድግ የሚፈልግ ማነው? በእውነት ሰው ይሄንን ከተረዳ ለማንበብ ይሰንፋል ብዬ አላምንም፡፡
የሰው ልጅ አንባቢ ሲሆን ሀሳቡ ይሰበሰባል፡፡ አስተውሎቱ ይጨምራል፡፡
@youthkiller👍👍👍
በወንድ ልጅ ህይወት ዉስጥ አራት ወሳኝ ሴቶች አሉ…

፩፦ እምትወልደው እናቱ👩‍👦

፪፦ አብራው እምትወለደው እህቱ👦👧

፫፦ ዘዉድ የምትሆነው ሚስቱ🤵❤️👰

፬፦ ከሱ እምትወለደው ልጁ👨‍👧
🙏❤️❤️❤️❤️❤️❤️🙏

👱‍♀👉ሴቶች አሻንጉሊት አይደሉም ልትጫዋትባቸው…

👱‍♀👉ነፃ ምግብ አይደሉም ቀምሰህ ልተዋቸው

👱‍♀👉ደግሞ ማስቲካም አይደሉም ማአዛዉ ሲያልቅ አዉተህ እንደምትተፋው!!!



ሴት ስለሆነች ሳይሆን ወንድ ስለሆንክ አክብራት። የትኛዉንም አይነት ሴት ትሁን ያላከበርካት ቀን ያኔ ወንድነትህን ጥለኀል።
@youthkiller
ሆሆ
(በእውቀቱ ስዩም)
"ወንድ ሆኖ የማያመነዝር ፤ ወታደር ሆኖ እማይሰነዝር ፤ ነጋዴ ሆኖ እማይዘረዝር የለም ! “ይላል ምኡዝ ::
እውነቱን ነው፤ከጥቂቶቻችን በቀር ብዙ ወንድ በህይወቱ ቢያንስ አንዴ በትዳሩ ላይ ያድጠዋል:: ድርያ በአርቲስት ላይ ይጋነናል እንጂ ፊትና ጭን ከተሰጠው፤ ገበሬ ነጋዴ ፓስተር ሼህ የንስሃ አባት ሳይቀር እንደሚወሰልት እናውቃለን:: መቸም የሴት ገላ ማቀፍ እንዴት እንደሚጥም የቀመሰ ያውቀዋል፤ ግን የሚያስከፍለው ዋጋ ከደስታው ጋር አይመጣጠንም፤ አንድ ጣሳ ደስታ ይሰጥህና አንድ በርሚል ጣጣ ያሸክምሃል!!
1
የሆነ ጊዜ ላይ አሜሪካ ውስጥ ባንድ ከተማ የተከሰተውን ዜና በራሴ መንገድ ስተርተው ይሄን ይመስላል፤
ሰውየው ሚስቱ ማታ ለስራ በሄደችበት ውሽማውን አምጥቶ በተቀደሰው አልጋ ላይ ይፈትጋታል፤ በፍትጊያ መሀል ኮቴ ሰምቶ ቀና ሲል ሚስቱን አያት፤ ውሽምየዋ እንደስፓይደር ውመን በመስኮት ዘልላ ነካችው፤ ባልየው ብቻውን ከሚስቱ ጋር ተፋጠጠ፤ ሚስትዮዋ ለሰይፍ ሩብ ጉዳይ የቀረው ቢላዋ ይዛለች፤ ባሉካ ለመሮጥ ተመኜ ፤ግን እግሩ ቀጤማ ሆነበት፤ በወዛደር አማርኛ እንግለፀው ከተባለ እድሩ የቡልዶዘር ጎማ ሆነበት፤ ሚስትየው ምንም አላለችም፤ አልጋው ላይ እመርር ብላ ወጣችና አገር አማን ነው ብሎ ቆሞ የሚጠብቀውን ብልቱን ጨብጣ ከስሩ መተረችው፤ ከዛ እንደ ቀይ ስር በቁንጮው አንጠልጥላው ወጣችና በቤቱ ጉዋሮ በሚገኘው ዱር ውስጥ ወርውራው ተሰወረች፤
ብዙ ሳይቆይ አምቡላንስ ስልቡን ሰውየ ይዞ ወድ ሆስፒታ መረሸ፤ ያሜሪካ ፖሊስ በቦታው ደርሶ ፤ ከሲአኤ ጋር በመተባበር አካባቢውን በብረት ለበስ መኪና አጥሮ ተቆርጦ የተጣለውን ወሸላ ፍለጋ ተሰማራ፤፤ ከላይ በሂሊኮፍተር ከታች በአነፍናፊ ውሻ የታገዘ ሰአታትን የፈጀ አሰሳ በሁዋላ የተቆረጠው ብልት የጉንዳን መንጋ ወርሶት ተገኘ፤፤ በመጨረሻ ዶክተሮች ወደ ስልቡ ባል ቀርበው፤ “የጠፋብህ ብልት ይሄ ነውን?” ብለው’ በመስቀልኛ ጥያቄ መርምረው አረጋግጠው፤ በቀዶ ጥገና ተከሉለት፤ትንሽ ከመንሻፈፉ በቀር በድሮው ቦታ ተተከለ ፤እረ እንዴውም ከዱሮው ሳይሻል አይቀርም፤ ሚስት ተብየዋን ደስ አይበላትና ሀኪሞች ፤ እንደ ክንዱ በፈለገ ጊዜ የሚዘረጋውና የሚያጥፈው አድርገው ተከሉለት፤
2
ይሄ ደሞ ባልንጀራየ የነገረኝ ነው፤
ዲሲ ውስጥ የሚኖሩ ባልና ሚስት ኢትዮጵያውን የተጋቡበትን አስረኛ አመት በማክበር እየተዝናኑ አመሹ፤ከዚያ ሚስትዮዋ” ቤብ፤ በፍቅራችን ላይ ቅመም የሚጨምር ነገር ላሳይህ " አለችና ከራቫቱን ፈታችለት፤ አያ ‘ቤብ ‘ ክራቫቱን እያስፈታ ፤ ከታች ስራ እንዳይፈታ፤ ቀበቶውን ፈታ፤
ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ አንድ የትራፊክ ፖሊስ መንገድ ዳር ቆሞ ቫይብሬት የሚያደርግ መኪና ስለተመለከተ ጠጋ ብሎ መስኮቱን አንኩዋኩዋ!
“is there any problem ? officer? “ አለ ባልየው ትንፋሹ እየተቆራረጠ::
“መኪና መሳረር ህገወጥ ስለሆነ ልቀጣችሁ ነው” አለና ፖሊሲ ባልየውን መቶ ዶላር ቀጣው፤ ሚስቲቱን ግን ሁለት መቶ ብር ቅጣት ጣለባት፤
ባልየው ትንሽ ቆይቶ ስለከነከነው ፖሊሱን ተከትሎ ደረሰበትና፤
“ቅጣቱስ ይሁን! ይበለኝ፤ የግሬን ነው ያገኘሁት፤ ግን በምን ምክንያት ነው እኔን መቶ ብር ቀጥተህ ሚስቴን ሁለት መቶ ቀጣሃት?’
ፖሊሱ እንዲህ መለሰ፤
“እ ሷ መኪና ውስጥ እንዲህ አይነት ነገር ስታደርግ ያገኘሁዋት ለሁለተኛ ጊዜ ነው፤ ለዝያ ነው እጥፍ ያስከፈልኩዋት”
ባልየው በድንጋጤ ታሞ ይሄው በጎፈንድድሚ እያስታመምነው እንገኛለን፤ @youthkiller
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌻 መስቀል ኃይልነ



🌼 እንኳን ለ መስቀል በዓል በሰላም በፍቅር እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን።


🌸🌸 መልካም በዓል 🌸🌸


🌼🌼🌼 @youthkiller 🌼🌼🌼


🌼 @youthkiller
a Tube - የኛ ቲዩብ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ የመስቀል በዓልን በማስመልከት ያስተላለፉት መልእክት።
ማን ያውቃል? የመስቀል ወፍ እና የአደይ አበባ ቀጠሮ እንዳላቸው መስከረም ሲጠባ፡፡
ማን ያውቃል?
እንዲል ኢትዮጵያዊው ባለቅኔ - እኛ እና መስከረም፤ እኛ እና መስቀልም ዓመት ጠብቀን የምንገናኝ ተነፋፋቂ ባለ ቀጠሮ ነን፡፡
እናም ናፍቆታችንን እንወጣጣ- ፍቅራችንንም እንቀባበል ዘንድ ዓመት ጠብቀን አደባባይ እንወጣለን - ያኔ ደመራ ነው፡፡
የመስቀል በዓል በዐደባባይ ከሚከበሩ የኢትዮጵያውያን በዓላት መካከል አንዱ ነው፡፡
ቀደምት አባቶቻችንና እናቶቻችን ይህንን ታላቅ በዓል በዐደባባይ እንድናከብረው ሥርዓት ሲሠሩ ያለ ምክንያት አልነበረም፡፡
ከበዓሉ ጋር የተያያዙ ሦስት ታላላቅ ሐሳቦችን ሁላችንም እንድንመራባቸው ፈልገው ሳይሆን አይቀርም፡፡
እውነትን ቀብሮ መኖር እንደማይቻል፤ ታሪክ የሚለወጠው በቆራጥነትና በአንድነት መሆኑን፣ አንድ ታላቅ ሐሳብ ኢትዮጵያውያንን እንዲጠቅም ከፈለግን ሐሳቡን ኢትዮጵያዊ ማድረግ እንዳለብን በዓሉ በደመራው ብርሃን ወገግ አድርጎ ያሳየናል፡፡
የክርስቶስን መስቀል የቀበሩት ሰዎች እውነትን ለዘለዓለም ቀብረው ማስቀረት የሚችሉ መስሏቸው ነበር፡፡
ለጊዜው መስቀሉ ከአፈር ሥር ሲቀበር ዓላማቸው የተሳካላቸው መስሏቸው ነበር፡፡
በመስቀሉ ላይ የቆሻሻ ክምር እንዲከመር ሲያደርጉ መስቀሉን ከታሪክ ገጽ ያጠፉት መስሏቸው ነበር፡፡
ይህ ግን የመሰላቸውን መስሎ መቆየት የቻለው እና የዋሆችም መስቀሉ ተቀብሮ፣ ተረስቶ፣ ትቢያ ሆኖ ጠፍቷል ብለው እንዲረሱት ያስቻላቸው ዕሌኒ የምትባል ብርቱ እንስት ከተለየ ብርታት፣ ጽናት እና የይቻላል መንፈስ ጋር እስክትከሠት ድረስ ብቻ ነበር፡፡
በየዘመናቱ እውነትን ለመቅበር የሞከሩ ነበሩ፡፡ በተንኮል፣ በሤራ፣ በግጭት፣ በክፍፍል፣ በጦርነት፣ በጉልበትና በኃይል እውነትን ለመቅበር ብዙዎች ሞክረዋል፡፡
እውነተኞችን በማጥፋትና በመግደል፣ በማሠርና በማስፈራራት እውነት የምትጠፋ መስሏቸው ብዙ ደክመዋል፡፡
መጻሕፍትን አቃጥለዋል፤ የዕውቀት ቦታዎችን አውድመዋል፡፡
እውነት ግን ብትቀጥንም አትበጠስም፡፡ እውነተኞችን በመግደል እና በመቅበር በፍጹም እውነትን ማጥፋት አይቻልም፡፡ እውነትና ተስፋ አብረው የሚሄዱ ናቸው፡፡
እውነተኞች ተስፈኞች ናቸው፡፡
ውሸተኞች ጨለምተኞች ናቸው፡፡
ከእውነት ጋር ያልቆመ ሰው ተስፋ ሊኖረው አይችልም፡፡
ተስፋ እውነተኛ ሰው ብቻ የሚያደርገው መነጽር ነውና፡፡
ተስፋ ባለበት ሁሉ እውነት ትኖራለች - እውነት ባለችበትም እንዲሁ ተስፋ አለ፡፡
መስቀሉን የቀበሩት ሰዎች ሐሰተኞች ስለነበሩ ወደፊት የሚወጣ አልመሰላቸውም፡፡
የመስቀሉ ወዳጆች ግን እውነተኞች ስለነበሩ አንድ ቀን እንደሚገለጥ ያምኑ ነበር፡፡
ለዚህ ነው መስቀሉ የት እንደተቀበረ ከልጅ ልጅ በሚተላለፍ የቃል ትውፊት መረጃውን ለዘመናት አቆይተው ለመስቀሉ አስተርእዮት ዘላለማዊ ገድል የፈጸሙት፡፡
ኢትዮጵያን ታላቅ፣ የበለጸገችና ለሁላችንም እንድትሆን ለማስቻል የያዝነው ዓላማ መሳካቱ የማይቀር እውነት ነው፡፡
ይህን እውነት የሚገዳደሩ ኃያላን ይኖራሉ፡፡
ለጊዜው ዝናራቸውን እስኪጨርሱ፣ ጉልበታቸውንም እስኪያፈሱ ድረስ ያሸነፉ ይመስላሉ፡፡ ድምፃቸው እንደ ነጎድጓድ፣ ጩኸታቸውም እንደ ብዙ ፏፏቴዎች የወል ጩኸት ጎልቶ ይሰማ ይሆናል፡፡ እውነታችንን የቀበሩት መስሏቸው ለጊዜው ይደሰታሉ፡፡
በዙሪያችን ያሉትም እውነታችን የተቀበረ መስሏቸው ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡
ይህ ግን የእውነትን ባሕሪይ ካለመረዳት የሚመጣ ነው፡ ፡
እውነትን መገዳደር እንጂ ማሸነፍ፣ መቃወም እንጂ ማጥፋት ፈጽሞ አይቻልም፡፡
የብዙዎች ጩኸት- የሰነፎች ተረት እና የአላዋቂዎች ትምክህት እውነትን ሊያጠፋት እንደማይችል በጽኑ እናምናለን፡፡
እውነት የተቀበረችበትን ዐመድ እንደ ፍግ እሳት አሙቃ እንደ ገሞራ ትፈነዳለች፤ የተሸፈነችበትን አቧራ እና የክፋት ቁልል ቅርፊቱን እንደሚሰብር ጫጩት ፈንቅላ ትነሣለች፡፡ ነገ ከእውነተኞች ጋር ናት፡፡
እውነተኞች ዛሬ ጥቂቶች ቢመስሉም ነገ እየበዙ ይሄዳሉ፤ ሐሳውያን ዛሬ ብዙዎች ቢመስሉም ነገ እንደ ስንቅ እያነሡ ይሄዳሉ፡ ፡
ለዚህ ነው ከኢትዮጵያ እውነት ጋር እንቆም ዘንድ እስከ የትኛውም ጥግ ተጉዘን፤ የትኛውንም እንቅፋት በጀግንነት እንሻገር ዘንድ የምንታገሰው፡፡
ማንም በማያስብበት፣ ነገሩ ሁሉ የተረሳ በሚመስልበት፣ ኃያላን ሁሉ ዝም ባሉበት በዚያ ጊዜ ዕሌኒ የምትባል ቆራጥ እናት ተነሣች፤ ማንም የማይደፍረውን ደፈረች፣ ከእውነት ጋር ለመቆምም ቆረጠች፤ ያልተሞከረውን ለመሞከር፣ የማይታሰበውን ለማሰብ ወሰነች፡፡
ታሪክ በሥራ እንጂ በወሬ አይለወጥም፤ የሚያወሩ ሰዎች በታሪክ ውስጥ ያልፋሉ፤ ታሪክ ግን አይሠሩም፡፡
ማኅበረሰቡ የሚያውቀውን፣ የለመደውን፣ ደጋግሞ የሞከረውን ነገር በማድረግ ታሪክ አይለወጥም፡፡
ሌሎች ባዘገሙበት መንገድ ብቻ ደጋግሞ በመጓዝ ካሰቡት ለመድረስ አይቻልም፡፡
አዲስ ታሪክ ለመጻፍ አዲስ መንገድ መከተል፣ አዲስ ልማድም መትከል - አዲስ ሥራም መሥራት ይጠይቃል፡፡
ጫካ የሚያቃጥል እሳት ከአንዲት ክብሪት ይነሳል፤ ሀገር የምትለውጥ ውብ ሐሣብም ከአንዲት ቦታ ትመነጫለች፡፡
ተገዳድለን፣ ተጨፋጭፈን፣ ተናቁረን ሞክረነዋል፤ ማሳደድና ማሠር የታሪካችን አካላት ሆነዋል፤ ሤራና ሸር፣ ይውደምና ይመታ መዛግብተ ቃላትን ሞልተውታል፡፡ ለዚህ ነው በአዲስ መንገድ እንሂድ ብለን የተነሣነው፡፡
ዕሌኒ እንደብዙዎቹ የዓለማችን ባለ ቅን ልብ ቅን ሰዎች ዓይነተኛ የመደመር ተምሳሌት ናት፡፡ የእርሷ ቆራጥነት፣ የሕዝቡ ጸሎት፣ የወታደሮቹ ብርታት፣ በኢየሩሳሌም የነበሩት ሰዎች ትጋት፣ መረጃውን የሰጧት ሰዎች ቀናነት፡፡
እነዚህን ሁሉ አስተባብራ ሐሳቧን ተግባር - ተግባሯን ታሪክ ለማድረግ ቻለች፡፡
‹ተቀበረ› የሚለውን ታሪክ ‹ወጣ› በሚለው ቀየረችው፡፡
‹ጠፋ›ን በ‹ተገኘ›- ‹ተሰወረ›ን በ‹ተገለጠ› አጸደለችው፡፡
እውነት እና ተስፋ ነበሯትና የሚቻል የማይመስለውን ቻለች፤ ተራራውን ናደች፡፡
የውሸትን ክምር አፍርሳ የእውነትን ሐውልት አቆመች፡፡
አይሆንም የተባለው ሆነ፤ አይቻልም የተባለው ተቻለ፤ ቀባሪዎቹ አልፈው የተቀበረው ህያው ሆነ፡፡ የቀባሪዎቹ ታሪክ ተዘግቶ የተቀበረው ታሪክ ተከፈተ፡፡
ለዚህ ነው ቀደምት አባቶቻችንና እናቶቻችን የመስቀልን በዓል ከየቦታው በሚሰበሰብ እንጨት፣ ከእንጨቶችም በሚሠራ ደመራ እንድናከብረው ያደረጉን፡፡
እውነትን ለማጽናት ከመደመር የተሻለ ነገር የለም ሲሉን ነው፡፡
መሟላት እንጂ መባላት እንደማይበጀን፤ ትግግዝ እንጂ ውግግዝ እንደማይረባን፤ ትቅቅፍ እንጂ ንቅቅፍ ዋጋ እንደሌለው፤ ዕሌኒ አሳይታናለች፡፡
በዚያ የመስቀል ፍለጋ ጉዞዋ፣ ክርስቲያኖችንም፣ አይሁድንም፣ ሌላ እምነት ያምኑ የነበሩትንም አስተባብራለች፡፡
መንገዷ የጥበብ እንጂ የመጥበብ አልነበረም፡፡
ጉዞዋ ሁሉንም ለእውነት ለማንበርከክ እንጂ አንዱን ለሌላው ለማንበርከክ አልነበረም፡፡
ዛሬ ሁሉም የታሪኩ ባለቤት ሆነዋል፡፡ ከዕሌኒ የምንማረው መንገዳችን ጠላት የመቀነስ፣ ወዳጅ የማብዛት መሆን እንዳለበት ነው፡፡
መስቀሉ የለም፤ ተቀብሮ ጠፍቷል፤ ከእንግዲህ አይገኝም፤ አለቀለት አበቃለት - ሲሉ ለነበሩ ሰዎች ከልኬቷ ወርዳ በመነታረክ፤ ሥራ ፈትታ በመወራወር ዕሌኒ ጊዜ አላጠፋችም፡፡
ታሪክ ልኬት ከወረዱ ጋር በመውረድ፣ ካነሱ ጋር በማነስ ታሪክ እንደማይቀየር ዐውቃለች፡፡
በጮኹት ውሾች ላይ መልሳ በመጮህ ጉልበት አላባከነችም፡፡
እነርሱ ወደ ዝቅታ ሲሄዱ እርሷ ወደ ከፍታ በማምራት ላይ ነበረች፡፡
በየመንገዱ የነበሩ ተስፋ አስቆራጭ ጩኸ
ቶችንና ልብ አፍሳሽ ዕንቅፋቶችን አልፋ፣ የማይሞከረውን ሞክራ፣ አይቻልም የተባለውን ችላ፣ ታሪክን በሠገነት ላይ አስቀመጠችው፡፡ አፈኞች ከማያወርዱበት፣ ወሬኞች ከማይደርሱበት፣ ተንኮለኞች ከማያገኙት ከፍታ ላይ ሰቀለችው፡፡
የእኛም ጉዞ እንደዚያ ይሁን፤ ለሥራ ካልደረሱ፣ ለመብል ካላነሱ ሰዎች ጋር ጊዜያችንን አናጥፋው፡፡
ጉልበታችንን አናባክነው፡፡ ጠላቶቻችን በዘረጉልን የአሽክላ መንገድ ሳይሆን ወደ ልዕልና በሚያደርሰን የራሳችን ጎዳና ላይ እንጓዝ፡፡
ወገባችን አሥረን፣ ዐቅማችንን ቋጥረን፣ ድምፃችንን አጥፍተን ታሪክ የቀየርን ለታ - የውሸት ክምር ይናዳል፤ የወሬ ኩይሳ ይፈርሳል፡፡
መስቀሉ የተገኘው፣ የመጀመሪያው ደመራም የተደመረው፣ የመጀመሪያው በዓልም የተከበረው ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም፡፡
አባቶቻችንና እናቶቻችን ግን ይህን ታላቅ ነገር ወደ ሀገራችን አምጥተው ኢትዮጵያዊ አድርገውታል፡፡
ከእኛው መልክአ ምድር፣ ከእኛው የዘመን አቆጣጠር፣ ከእኛው ባህል ጋር አስማምተው ኢትዮጵያዊ መልክ ሰጥተውታል፡፡
በብዙ ማኅበረሰቦች ዘንድ፣ በየአንዳንዱ ገጠር፣ ዘመናትን እየተሻገረ እንዲሄድ አስችለውታል፡፡
የእኛው የመስቀል አከባበር ዓይነተኛ ቅርሳችን ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበውም ለዚህ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ስለሆነ፡፡
ሁሉን ነገር መቅዳት፣ ቀድተን እንዳለ በሀገራችን ምድር ላይ መድፋት፤ ውጤት አላመጣም፡፡
ሐሳቦችን፣ ልምዶችን፣ መርሖችን፣ ዕውቀቶችን ከሚገኙበት ወስደን ኢትዮጵያዊ መልክ ልንሰጣቸው ይገባል፡፡
ከኛው ባህል፣ እምነት፣ ልማድ፣ አስተሳሰብ፣ አኗኗርና ፍላጎት ጋር ማጣጣም አለብን፡፡ መደመር እንዲህ ነው፡፡
ከምዕራብም ከምሥራቅም አየን፤ በጎ በጎው ወሰድን፤ የራሳችንን ሐሳብ አዋለድን፤ ከኢትዮጵያ ባህልና ታሪክ፣ ፍላጎትና ዐቅም ጋር አዋሐድን - ኢትዮጵያዊ የሆነ የመደመር መንገድንም ጀመርን፡፡
ቀደምቶቻችን የመስቀል በዓል በየመንደሩ እስኪደርስ ድረስ እንደደከሙት ሁሉ መደመርም በየኪሳችን እስኪገባ ድረስ መድከም አለብን፡ ፡
አንዴ ከምዕራብ፣ ሌላ ጊዜ ከምሥራቅ አምጥተን፣ ምሥራቁንና ምዕራቡን ለመሆን ጥረን ነበር፡፡ እየቀዳን የምናመጣው ዘር ግን በኢትዮጵያ ምድር ሊያፈራ አልቻለም፡፡
ለዚህ ነው ግራ ቀኙን አይተን የኛኑ ችግር በኛው መፍትሔ ለመሞከር የተነሣነው፡፡ በመደመር፡፡
መደመር እንደ ደመራው ሁሉ በየመንደሩ - በየጥጋቱ ሁሉ ማብራት አለበት፡፡
ዛሬ የደመራ በዓላችንን ለማየት ዓለም ሁሉ ወደ እኛ እንደሚመጣው ሁሉ፣ ነገ መደመር ያስገኘልንን ለውጥና ብልጽግና - የተለምነውንም የፍቅር ጎዳና ለማየት፣ አይተውም ለመደመር ብዙዎች ይመጣሉ፡፡
እውነተኞች ተስፋ አላቸው፡፡
ደመራን በየዓመቱ የሚያይ ሕዝብ መደመር የሚኖረውን ኃይል ይገነዘባል፡፡ መደመርም እንደ ደመራው ሁሉ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡
ለኢትዮጵያ የሚበጅ ኢትዮጵያዊ - የኢትዮጵያ መንገድ፡፡
እንደ ዕሌኒ ታሪክ ለመለወጥ ቆርጠን፣ በዙሪያችን ያሉትን ሁሉ በእውነትና በፍቅር አስተባብረን፤ እንደ ደመራው ተደምረን - ኢትዮጵያን ማንም ከማያወርድበት ሠገነት ላይ ለማውጣት እንነሣ፡፡
መልካም የመስቀል በዓል ይሁን፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ፣ ተከብራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር! ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም @youthkiller
r. Eyob Mamo
የማንነትህ መለኪያ ስኬት አይደለም
“በቅርጫ ኳስ ጨዋታ ዘመኔ 9 ሺህ ኳሶችን ሞክሬ ስቼአለሁ፡፡ 300 ውድድሮችን ተሸንፌአለሁ፡፡ ባስቆጥረው ቡድኔን ለዋንጫ የሚያበቃውን ኳስ እንድወረውር አምነው ሰጥተውኝ ስቼ አውቃለሁ፡፡ በሕይወቴ ደግሜና ደጋግሜ ወድቄአለሁ፡፡ ለዚህ ነው ስኬታማ የሆንኩት” - Michael Jordan
አብዛኛው ሰው ውስጡን የሚነዳው አንድ ጥማት አለው፡፡ ይህ ጥማት የተመሰከረለትና ጥንቅቅ ያለ ስኬታማ ሆኖ ለመታየት ያለው ጥማት ነው፡፡ “እንደዚህ ባደርግ፣ ይህኛውና ያኛው ነገር ቢኖረኝ፣ እዚያኛው ደረጃ ብደርስ ኖሮ … እረካና ሙሉ ስኬት ውስጥ እገባ ነበር” የሚል የውስጥ ጩኸት በብዙ ሰዎች ውስጥ ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ስለዚህም፣ አንዳንድ ሰዎች ይህንን ጥማት ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግና የትኛውንም ድንጋይ ከመፈንቀል አይመለሱም፡፡
የዚህ አመለካት ምንጩ፣ “ሙሉ ማንነት እንዲኖረኝ በኑሮዬ ስኬታማ መሆን አለብኝ” የሚለው አመለካከት ነው፡፡ የዚህ አመለካከትና የሕይወት ዘይቤ ውጤቱ ደግሞ “ስውር” ፍርሃት ነው፡፡ ሙሉ ማንነት እንዲኖረው ስኬታማ መሆን እንዳለበት ያመነ ሰው አለመሳካትን፣ ስህተትንና መውደቅን እጅግ የሚፈራ ሰው ነው፡፡ የሚሰራው ማንኛውም ስራ ስኬታማ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ከማንነቱ ዋጋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ባለማወቁ ምክንያት ለብዙ ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ራሱን ያጋልጣል፡፡
የአንድ ሰው ማንነት የሚለካው በተሳካለትና ባልተሳካለት ነገር ከሆነ፣ ለዚያ ሰው ሩጫ ማቆሚያ፣ ለውድድሩም መጨረሻ የለውም፡፡ ይህ አይነቱ የሕይወት ዘይቤና አመለካከት የሚያስከትለው ዋነኛ መዘዝ የመውደቅ ወይም ስኬት የማጣት ፍርሃት ነው፡፡ ከዚህ የተዛባ የማንነት መመዘኛ ቀውስ ለመውጣት በስኬት ላይ ያለንን አመለካከት መቃኘት አስፈላጊ ነው፡፡
1. ስኬት ዘርፈ-ብዙ ነው
ለምሳሌ፣ አንድ ሰው በስራው ወይም በንግዱ አለም የተዋጣለት ሆኖና ያሰበው ደረጃ ደርሶ፣ በማሕበራዊውም ሆነ በቤተሰባዊው ኑሮው የተበላሸ ሁኔታ ውስጥ ራሱን ሊያገኘው ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ጤንነቱን ችላ ብሎ እውቀትን ወይም ንብረት ሲሰበስብ የሚኖር ሰው በቀኑ መጨረሻ “ስኬታማ ነኝ” ብሎ እንዲናገር የሚያደርገው ነገር ምንድን ነው? ስለዚህም፣ ስኬት የብዙ መሰረታዊና አስፈላጊ እውነታዎች ጥርቅም ነች እንጂ አንድ ገጽታ ብቻ የላትም፡፡
2. ስኬት የሂደት ጉዳይ ነው
ስኬት የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን የሂደት ጉዳይ ነው፡፡ ስኬት፣ “አንድ ደረጃ ካልደረስኩ አልረጋጋም” ማለት ሳይሆን ጉዞውን በመጀመራችንና በሂደት ላይ በመሆናችን መርካትና መረጋጋት ማለት ነው፡፡ ዘርፈ-ብዙ የሆነው የስኬት ምስጢር ዘርፈ-ብዙ የሆነ ጥረትና ትጋት ይጠይቃል፡፡ ስኬታማ ሰው በሁሉም አቅጣጫ በአንድ ጊዜ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ነው ብሎ ማሰብ ከእውነት እንድንርቅ ያደርገናል፡፡
3. ስኬት ተለዋዋጭ ነው
ትናንት ቀለል ያለው ሁኔታ ዛሬ ከበድ ሲል፣ ዛሬ የጨመረው ሁኔታ ነገ ሊቀንስ፣ ዛሬ የተነሳሳውና የጋለው ፍላጎት ነገ ቀዝቀዝ ሊል ይችላል፡፡ እንደ ሁኔታውና እንደ እለቱ ስሜት ጥረቱን የሚቀያይር ሰው እንደዚያው አይነት ውጤትን ያተርፋል፡፡ እንደ እለቱ ሁኔታና ስሜት ሳይሆን ከዓላማው አንጻር የሚሰራ ሰው ደግሞ ከዚያው አንጻር ስኬታማ ይሆናል፡፡ ይህ በፍጹም የማይለወጥ ሕግ ነው፡፡ @youthkiller
Baga ayaanaa ireechaatin isin gahe ayaanaa gaari እንኻን ለኢሬቻ በአል አደረሳችሁ መልካም በአል
Dr. Eyob Mamo
ሶስት አይነት “ሌዜ-ፌሮች”
“ልቅ (Laissez-faire) የአመራር ስልትን የሚከተል መሪ የጓሮ አትክልት ስፍራው ውስጥ የሚገኙ የጽጌሬዳ አበባዎች ከተለያዩ አረሞች ጋር እንደልብ እንዲያድጉ የሚተውና አሸናፊ ሆኖ የሚወጣው እንዲበቅል የሚፈቅድ መሪ ነው” - John Ruskin
በየዘመናቱ የተለያዩ መሪዎች ልዩ ልዩ የሆኑ የአመራር ዘይቤዎችን ተጠቅመዋል፣ አሁንም በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡ አንድ መሪ አንድን የአመራር ስልት ለመከተል የሚወስንበት ዋነኛ ምክንያት ስኬት ለማግኘት መሆኑን አያጠራጥርም፡፡ ሁኔታውን ጠለቅ ብለን ስንመለከተው ግን መሪው ሊያገኝ የሚፈልገውን ውጤት ወይም በግልጽም ሆነ በስውር የያዘውን አጀንዳ በቀላሉ የሚያመጣለትን ስልት ለመጠቀም ክፍት እንደሚሆን ማሰብ እንችላለን፡፡ የመሪው መነሻ ሃሳብ ያም ሆነ ይህ፣ መሪው ሊያከናውን ያቀደውን ጉዳይ እውን ለማድረግ አንድን የአመራር ስልት ይጠቀማል፡፡
ስለ አመራር ስልቶች ለመነጋገር ከሁሉ በፊት ጥንታዊ በመባል የታወቁትን ሶስቱን የአመራር አይነቶች መጥቀሱ አስፈላጊ ነው፡፡ አነሱም፡- አውቶክራቲክ (Autocratic)፣ ዴሞክራቲክ (Democratic)፣ እና ሌሴፌር (Laissez-faire) ናቸው፡፡
አውቶክራቲክ (Autocratic) አመራር ገደብ የለሽ ስልጣን ያለው የአመራር ስልት ነው፡፡ አውቶክራቲክ መሪ ኃይሉንና ስልጣኑን በመጠቀም ተከታዮችን በመጫን የሚታወቅ መሪ ነው፡፡ ዴሞክራቲክ (Democratic) አመራር ደግሞ መብት ሰጪ የአመራር ስልት ነው፡፡ የእነዚህን የሶስቱን ጥንታዊ ስልቶች ሁኔታ በበለጠ ለመገንዘብ “አመራር A to Z” የተሰኘውን መጽሐፌን ያንብቡ፡፡ ለዛሬው ሌዜ-ፌር (Laissez-faire) ስለተሰኘው “አመራር የለሽ” የአመራር ስልት በጥቂቱ እንቃኝ፡፡
ሌዜ-ፌር (Laissez-faire) አመራር - ልቅ የአመራር “ስልት”
ሌዜ-ፌር የሚለው ቃል በፈረንሳይኛ “ነገሮች በራሳቸው እንዲንከባለሉና እንዲሆኑ መልቀቅ” የሚለውን ሃሳብ የያዘ ነው፡፡ ይህ አይቱን የአመራር ስልት የሚከተል መሪ ተከታዮች ካለምንም ቁጥጥር በራሳቸው የፈለጉትን እንዲያደርጉ የሚለቅቅ መሪ ነው፡፡ የሌዜ-ፌር አመራር፣ “አመራር-አልባ” የአመራር ስልት በመባልም ይታወቃል፡፡ ይህ አይነቱ አመራር ዘይቤ በባህሪያቸው፣ በዲሲፕሊናቸውና በብቃታቸው የተመሰከረላቸው ዜጎችን ለመምራት የሚጠቅም ሊሆን ይችላል፡፡ ከስሙ ትርጓሜ እንደምንረዳው ግን የአመራር ስልቱ ልቅነትን፣ እንደፈለጉ መሆንንና ከቁጥጥር ውጪ የሆነን ማሕበራዊ ሂደትን ስለሚፈጥር ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡
ሶስት አይነት “ሌዜ-ፌሮች”
ቅን “ሌዜ-ፌሮች”
አንዳንድ “ሌዜ-ፌር” መሪዎች፣ ተከታዮች በነጻነት ቢለቀቁና እንደፈለጉ ቢሆኑ ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ብለው በቅንነት ስለሚያስቡ ሕዝቡ እንደፈለገ እንዲሆን ይለቁታል፡፡ ሆኖም፣ ይህ ከቅንነት የሚነሳው “ሌዜ-ፌርነት” ስኬታማ የሚሆነው በእውቀት የበለጸገና በባህሪይ የበሰለ ሕብረተሰብ ባለበት ሁኔታ መሆኑን ሊያስታውሱ ይገባቸዋል፡፡
አቋም-የለሽ “ሌዜ-ፌሮች”
አንዳንድ “ሌዜ-ፌር” መሪዎች፣ ተከታዮች እንደፈለጉ እንዲሆኑ የሚለቁት አቋም ስለሌላቸው ነው፡፡ ከዚህ ጋር የተያያዘው ስሜት ምናልባት አቋም ከያዙና መመሪያ መስጠት ከጀመሩ ተቀባይነት እንደሚያጡ ሊመስላቸውም ይችላል፡፡ ሆኖም፣ ይህ አቋም-የለሽነት የተከታዮችን ልቦና የሚያዝል፣ ቅን ተከታዮችን የሚያርቅና ሁኔታውን ለግላቸው ተጠቃሚነት ለማዋል የሚፈልጉ ሰዎችን ጉልበት የሚሰጥ ሁኔታ ነው፡
ባለ ስውር አጀንዳ “ሌዜ-ፌሮች”
አንዳንድ “ሌዜ-ፌር” መሪዎች፣ ሁሉም እንፈለገ ሲሆን ዝም የሚሉት የተደበቀ አጀንዳ ስላላቸው ነው፡፡ ሁሉም ነገር ዝም ተብሎ እንደፈለገ ሲለቀቅና ሰው እንደፈለገው መሆን ሲጀምር አቅም ኖሮት የሚያሸንፈው አካል የመሪውን የውስጥ ስውር አጀንዳ እንደሚያስፈጽምለት በሚያምንበት ጊዜ መሪው ይህንን “ስልት” ሊጠቀም ይችላል፡፡ ስለዚህም፣ ሰው ምንም ነገር የማድረግ መብቱ ነው” በሚል “የሌዜ-ፌር” ገጽታ ያለው ስልት ሁኔታዎችን በመልቀቅ በሂደቱ ውስጥ አይሎ እነደሚወጣ የሚያውቁትን ሁኔታ ይጠባበቃሉ፡፡
በማይቆጣጠሩትና እንዲሁ በተተወ የጓሮ አትክልት ስፍራ ውስጥ በቀላሉ የሚበቅለው ምን እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡
LIKE & SHARE @youthkiller
2024/09/21 17:07:48
Back to Top
HTML Embed Code: