Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያውያን እንኻን ደስ አለን ጠቅላይ ሚኒስትራችን የአለም የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆኖአል
👉👉🏾 ይህን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት የማንበብ ያህል ነው ፡፡
ምክር ለወዳጅ
:
👉👉🏾 በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።
:
👉🏾👉🏾 ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።
:
👉🏾👉🏾 የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ።
:
👉🏾👉🏾 ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ።
:
👉🏾👉🏾 የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።
:
👉🏾👉🏾 ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ።
:
👉🏾👉🏾 ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።
:
👉🏾👉🏾 ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ።
:
👉🏾👉🏾 እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።
:
👉🏾👉🏾 ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ።
:
👉🏾👉🏾 በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።
:
👉🏾👉🏾 የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።
:
👉🏾👉🏾 ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!
:
👉🏾👉🏾 መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ።
:
👉🏾👉🏾 ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።
:
👉🏾👉🏾 ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ።
:
👉🏾👉🏾 ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ።
:
👉🏾👉🏾 ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።
:
👉🏾👉🏾 የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።
:
👉🏾👉🏾 ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።
:
👉🏾👉🏾 ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።
:
👉🏾👉🏾 ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።
:
👉🏾👉🏾 እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።
:
👉🏾👉🏾 የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድር @youthkiller
ስኬትን ፍለጋ
“ስኬትን ከፈለክ ስኬትን ዓላማህ አድርገህ አትያዝ፡፡ የምታምንበትንና የምትወደውን ነገር ከልብህ ስታደርግ ስኬት ራሱ ይመጣል” - David Frost
ለትክክለኛ አላማ መቆም ስኬትን ይቀድማል እንጂ ስኬት አላማን አይቀድምም፡፡ አንዳንድ ሰዎች፣ “ቢሳካልኝ ኖሮ ይህንና ያንን አደርግ ነበር” በማለት በገንዘብና በተለያዩ አቅጣጫዎች “ቢሳካላቸው” ሊያደርጉ ስለሚፈልጉት የወደፊት አላማ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ አንድ ማስታወስ ያለባቸው እውነታ ግን አንድን አላማ ይዘው መስራታቸው ወደ ስኬት እንደሚወስዳቸው ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ ተሳካላቸው በመባል የሚታወቁ ሰዎች ለስኬት የኖሩ ሰዎች ሳይሆኑ ለአንድ አላማ በጽንአት የኖሩ ናቸው፤ ያንን ሲያደርጉ ስኬት ተከተላቸው፡፡
ለስኬት የሚኖር ሰው ስኬት ያጣ ሲመስለው ያቆማል፡፡ ለአላማ የሚኖር ሰው ግን ስኬት ያላገኘ ቢመስለውም እንኳ ጉዞውን ይቀጥላል፣ ምክንያቱም አላማ የተሰኘውን የስኬቶችን ሁሉ ስኬት በእጁ ጨብጧልና ነው፡፡ “የምትወደውንና መልካም የሆነውን ነገር አድርግ፣ ያንን የምታደርገውን ነገር ደግሞ ውደደው” የሚለው አባባል እውነት ነው፡፡ ስኬትን ፍለጋ ከአላማህ ውጪ የሆነን “ታላቅ” ነገር ከማድረግ፣ አላማን በመከተል አስቸጋሪ ጎዳና መጓዝ ይመረጣል፡፡ @youthkiller
Dr. Eyob Mamo
ሰው መሆን በቂ ነው!
አንድ ቀን አንድ ሰው በድንገት በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ወደቀና መውጣትም አልቻለም፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ ደክሞት በጉድጓዱ መካከል ቁጭ እንዳለ …
• ከንፈር መጣጭ ሰው አየውና - “ሁኔታህን ሳስበው በጣም በሃዘን እሞላለሁ” ብሎት ሄደ፡፡
• ተመራማሪ ሰው አየውና - “ይህ ጉድጓድ ከተማ መሃል ሆኖ ሰው መውደቁ አያስደንቅም” ብሎት ሄደ፡፡
• ፈራጅ ሰው አየውና- “ክፉ ሰዎች ብቻ ናቸው እንደዚህ ሊወድቁ የሚችሉት” ብሎት ሄደ፡፡
• ሂሳብ አዋቂ ሰው አየውና- የጉድጓዱን ስፋና ርዝመት ደምሮና ቀንሶ ሄደ፡፡
• ጋዜጠኛ ሰው አየውና - ሰበር ዜና አቀናብሮ ሄደ፡፡
• የአገር ውስጥ ገቢ ሰራተኛ አየውና- “እዚህ ስትታገል የግብር መክፈያ ጊዜ እንዳያልፍብህና እንዳትቀጣ” በማለት አስጠንቅቆት ሄደ፡፡
• ነጭናጫ ሰው አየውና- “እኔ ወድቄ የነበረበትን ጉድጓድ አላየህ” ብሎት ሄደ፡፡
• ሳይኮሎጂስት አየውና- “ላለህበት ሁኔታ ተወቃሾች አባትና እናትህ ናቸው” ብሎት ሄደ፡፡
• የስኬት አስተማሪው አየውና- “በራስህ ብታምን ከዚህ ትወጣለህ” ብሎት ሄደ፡፡
• ዘረኛ ሰው አየውና - “የምን ሃገር ሰው ነህ?” በማለት ከጠየቀው በኋላ የእርሱን ቋንቋ ስላልተናገረ ጥሎት ሄደ፡፡
• በመጨረሻ ይህንን ሁሉ ድራማ ሲመለከት የነበረ አንድ ጨዋ ጎልማሳ ከብዙ ጥረት በኋላ እየሳበ አወጣው፡፡
ማብራሪያውን ለአንባቢዬ እተወዋለሁ፡፡ @youthkiller
የተቀማውን ኃይልህን አስመልስ!

“ቁጣና ቂመኝነት እያደረገብህ ያለውን ክፉ ነገር ለማየት አይኖችህን ክፈት፡፡ የጎዱህ ሰዎች የወሰዱብህን ጉልበት መልሰህ የራስህ አድርግ”

ሰዎች በአንተ ላይ ከአንተው የቀሙት ኃይል እንዲኖራቸው ስትፈቅድ እየደከምክ ትሄዳለህ፡፡ ይህ የሚሆነው ደግሞ በበደሉህና በጎዱህ ሰዎች ላይ ጥላቻና ቂምን አምቀህ በመያዝ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ለመኖርና ለመሻሻል የሚያስችልህን የግልህን ጉልበት ለእነዚያው ሰዎቸ አሳልፈህ ትሰጣለህ፡፡ የመተኛትና የማረፍ፣ የመመገብ ፍላጎትና የመዝናናት ስሜትህ ከመቀማቱም ባሻገር የስሜት ቀውስ ውጤት ለሆኑ ህመሞችም ራስህን ታጋልጣለህ፡፡ በተጨማሪም የጎዱህን ሰዎች ልክ እስክታስገባና ኃይልህ እንደተመለሰ እስኪሰማህ ድረስ የሕይወትህ ጉዞ ታቆማለህ፤ ትኩረትህ የተወሰደው ኃይልህ ላይ ስለሚሆን ማለት ነው፡፡

የየእለት ኑሮህ ከሰዎች ጋር ያገናኝሃል፡፡ በዚህ ግንኙነት ውስጥ ደግሞ ሰዎችን የመጉዳትና በሰዎች የመጎዳት ሁኔታ የማይቀር ነው፡፡ ስለሆነም፣ የጎዱህ በመሰለህ ሰዎች ላይ ለመልቀቅ የማትፈልገውን ጠንካራ አሉታዊ ስሜት ስትይዝ አቅም እያጣህ ትሄዳለህ፡፡ ይህንን አትርሳ፣ ቂምና ጥላቻ የያዝክበት ሰው በአንተ ላይ ጉልበት ያለው ሰው ነው፡፡ እርሱ የአንተን ሁኔታ ይቆጣጠራል እንጂ አንተ የራስህን ሁኔታ የመቆጣጠር ጉልበት አይኖርህም፡፡ ሰውየው በተገኘበት ቦታ የማትገኘውና ስሙ በተጠራበት ጊዜ ሁሉ ስሜትህ የሚቃወስበት ምክንያቱ ኃይልህን ስለተቀማህ ነው፡፡

ምናልባት እስካሁን ድረስ ስታገኛቸውና አብረሃቸው ስታሳልፍ የመረጋጋትና የመደገፍ ስሜት የሚሰጡህን ሰዎች ለይተሃቸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ባገኘሃቸው ጊዜም ሆነ ስለ እነርሱ ስታስብ ውስጥህን የሚጎትቱትንና የሚያደክሙትን ሰዎችም እንደዚያው አውቀሃቸዋል ብዬ እጠረጥራለሁ፡፡ እነዚህን ኃይልህን የሚያደክሙትን ሰዎች ለይተህ በማወቅ፣ ከእነርሱ ደካማ አመለካከት ተሽለህ በመገኘት በሁኔታቸው አለመነካት፣ አለዚያም ከእነርሱ ጋር የሚኖርህን ግንኙነቶች የምትገድብበትን መንገድ ማመቻቸት፣ ካልቻልክ ደግሞ ስለ እነርሱ ማሰላሰልን ማቆም አስፈላጊ ነው፡፡ ከእይታህ የወጣ ሰው ከትውስታም የወጣ
እንደሚሆን አትርሳ፡፡


Dr_MehretDebebe
Forwarded from ET Airdrop 🇪🇹 (Mak)
com.highcore.hoopstars_13.apk
37.5 MB
Forwarded from ET Airdrop 🇪🇹 (Mak)
@oyinlar_play_market_dasturlar.Crazy.apk
60.9 MB
ከጭንቀት ነፃ የሆነ «ደስተኛ ሕይወት» ለመኖር ወሳኝ የሆኑ አሥር የሕይወት መርሆች አውቅ ከሆኑ የሳይኮሎጂ መፅሀፍቶች የተወሰደ እና ከሳይኮሎጂ ባለሞያዎች/አማካሪዎች የተገኘ መረጃ!
#ሼር ማድረግ ደስ ይላል፡፡ የዛሬ ደስታዎን #ሼር በማድረግ ይጀምሩ፡፡
1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው።
2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።
3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡
4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።
5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡
6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦ ሰዎችን አትና፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡
7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው።
8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤ የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት ተንከባከበው፡፡
9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።
10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡፡ share @youthkiller
ራስህን አክብር
በአንድ በዝቅተኝነት ስሜት የተመቱ ሰዎች ለምክር በሚመጡበት ማእከል ብዙ ሰዎች ተሰብስበዋል፡፡ ችግራቸው አንድ ነው፣ የኑሮአቸው ሁኔታ በራሳቸው ላይ ያላቸውን አመለካከት ደብድቦ ጥሎታል፡፡ በራሳቸው ላይ የወደቀ አመለካከት አላቸው፡፡ ይህ ሰው በምን መልኩ ከዚህ አመለካከት ሊያወጣቸው እንደሚችል ካሰበ በኋላ አንድን ምሳሌ ነገራቸው፡፡
በእጁ አንድ ድፍን መቶ ብር ይዟል፡፡ ወደ ሰዎቹ ዘወር አለና፣ “የዚህ ብር ዋጋ ስንት ነው?” አላቸው፡፡ የሁሉም መልስ እንደተጠበቀው፣ “መቶ ብር” የሚል ነበር፡፡ የሚቀጥለው ጥያቄ፣ “ይህ ብር ምን ሊገዛ ይቻላል” የሚል ነበር፡፡ ሁሉም በመሽቀዳደም ምን ሊገዛ እንደሚችል መናገር ጀመሩ፡፡ በመቀጠልም፣ ይህንን መቶ ብር በመዳፉ አጅግ ጨመደደው፣ ከዚያም ወደ መሬት ጣለውና ረገጠው፡፡ በእጁ አንስቶ ከጨመደደው በኋላ ያንኑ ጥያቄ ጠየቃቸው፣ “የዚህ ብር ዋጋ ስንት ነው?”፡፡ የሁሉም መልስ እንደቀድሞው፣ “መቶ ብር” የሚል ነበር፡፡ ሁለተኛውንም ጥያቄ ደገመው፣ “ይህ ብር ምን ሊገዛ ይቻላል?” የሚል ነበር፡፡ መልሳቸው እንደቀድሞው ነበር፡፡
ከዚያም መልእክቱን አስተላለፈላቸው - “ይህ ብር ተጨማደደ፣ ወደቀ፣ ተረገጠ፣ … ዋጋው ግን ያው ነው፡፡ የእናንተም ዋጋ እንዲሁ ነው፡፡ ምንም አይነት ነገር በሕይወታችሁ ቢያልፍ፣ ዋጋችሁ ግን ያው ነው - የውጪ ገጠመኛችሁና ሁኔታችሁ የማንነታችሁን ዋጋ መቀነስም ሆነ መጨመር አይችልም”፡፡
ራስህን ካላከበርክ ማንም ሰው እንደማያከብርህ እወቅ፡፡ ራስህን ማክበርህን ለማወቅ ስለ ራስህም ሆነ ስለ ሃገርህ ሰዎች፣ ስለ ወገኖችህ የምትናገረውን ንግግር አጢነው፡፡ ራስህን ሳታከብር ወገንህን ልታከብር አትችልም፡፡ ወገኑን የናቀ ሰው በቅድሚያ የናቀው ራሱን ነው፡፡ በሌላ ጎኑ፣ አለባበስህ፣ ለራስህ የምትሰጠው ትኩረት፣ የምትገኝባቸው ስፍራዎች፣ የምትመርጣቸው የጓደኛ አይነቶች ለራስህ የሰጠኸው ዋጋ ምልክቶች ናቸው፡፡
ንጹህ ነኝ ብለህ እያሰብክ ቆሻሻ ቦታ ራስህን ልታገኘው አትችልም፡፡ ጨዋ ነኝ ብለህ እያሰብክ ራሳቸውን ከተራ ነገር ለማውጣት ከማይፈልጉ ሰዎች ጋር ማሳለፍ አትችልም፡፡ የምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ለራስህ የሰጠኸው ዋጋ ነጸብራቆች ናቸው፡፡
“ለራሳችን ያለንን ክብር አሳልፈን ካልሰጠናቸው በስተቀር ሰዎች ሊወስዱብን አይችሉም” - Mahatma Gandhi
ይህንን አትዘንጋ፡- ሰዎች ከሰጠሃቸው መብት የበለጠ ምንም አይነት መብት በአንተ ላይ ሊኖራቸው አይችልም፡፡ እንዳይንቁህ ማድረግ አትችልም፣ ራስህን በማክበር ግን ንቀታቸውን ቦታ ልታሳጣው ትችላለህ፡፡ ስለአንተ ክፉ እንዳያወሩ ማድረግ አትችልም፣ ያወሩትን ክፉ ነገር ተቃራኒ በመኖር ግን ወሬአቸው ውሸት እንደሆነ የማሳየትን መብትህን ግን ሊወስዱብህ አይችሉም፡፡ አብረሃቸው ለማሳለፍና በማንነትህ ላይ ተጽእኖ እንዲያመጡ የፈቀድክላቸው ሰዎች ብቻ በማንነትህ ላይ ያለህን አመለካከት ይወስናሉ፣ ይህንን ደግሞ መቆጣጠር ትችላለህ፡፡ @youthkiller
Dr. Eyob Mamo
“መጫወት ስታቆሙ ታረጃላችሁ”
ሰው መጫወት የሚያቆመው በእድሜ ሲያረጅ አይደለም፣ መጫወት ሲያቆም ግን ወዲያው ማርጀት ይጀምራል፡፡
ደስተኞችና ስኬታማዎች መሆን ከፈለጋችሁ፣ ምስጢሩ ግልጽ ነው፡- በየቀኑ የሚያስቅ ነገር ፈልጋችሁ መሳቅና መጫወት አለባችሁ፡፡ በዙሪያችን ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ሰዎች ይህንና ያንን ሳያደርጉ እድሜያቸው በማለፉ ምክንያት ሲጸጸቱ ይታያሉ፡፡ መለወጥ የማይችሉትን ነገር እያወጡና እያወረዱ ቢጸጸቱ ምንም ለውጥ እንደማያመጡ እያወቁት እንኳን ወደ ፊት መራመድ እስከሚያቅታቸው ድረስ የስሜት ቀውስ ውስጥ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ አመለካከትን በመለወጥ ግን ባሉበት ሁኔታ ማድረግ የሚችሉትን ወደማድረግና በዚያም ወደመደሰት መዝለቅ ይችላሉ፡፡
“ማለም ስታቆሙ ትሞታላችሁ”
ሰው ማለም የሚያቆመው ሲሞት አይደለም፣ ማለም ሲያቆም ግን ወዲያው መሞት ይጀምራል፡፡
የነቃና የሞቀ ኑሮ መኖር ከፈለጋችሁ መንገዱ አንድ ነው፡- ሕልም ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ ምክንያቱም ሕልማችሁን ስታጡ ትሞታላችሁ፡፡ በዙሪያችን በርካታ ሰዎች ሞተው እንኳን እንደሞቱ አልገባቸውም፡፡ መኖር ማለት መተንፈስ፣ መብላት፣ መጠጣት፣ መተኛትና መነሳት ብቻ አይደለም፡፡ መኖር መለወጥና ማደግን ይጨምራል፡፡ መለወጥ ገጽታ ብቻ አይደለም፣ አመለካከትንና ባህሪይንም ይጠቀልላል፡፡ የዚህ አይነቱን ሁለንተናዊ እድገት ለማስተናገድ ደግሞ ሕልምንና ራእይን አለመልቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡
“ማደግ ስታቆሙ ወደኋላ ትቀራላችሁ”
ሰው ማደግ የሚያቆመው ወደኋላ ሲቀር አይደለም፣ ማደግ ሲያቆም ግን ወዲያው ወደኋላ መቅረት ይጀምራል፡፡
በእድሜ በመግፋትና በማደግ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ በእድሜ መግፋት የግድ ነው፣ ማደግና መብሰል ግን የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን እውነት ስንገነዘብ በእድሜ በመግፋትና በመብሰል መካከል ያለውን ልዩነት ስለምንገነዘብ በዚያ ምክንያት ከሚመጡ ባሉበት የመርገጥ፣ አልፎም ወደ ኋላ የመንሸራተት ጠንቆች እንድናለን፡፡
አድሜ መግፋት ለሁሉም የተሰጠ እውነታ ነው፡፡ እድሜን መቁጠር ምንም አይነት ልዩ ስጦታና ችሎታ አይጠይቅም፡፡ የእድሜህ ቁጥር በጨመረ መጠን ለማደግና ለመብሰል ራስህን ካላዘጋጀህ ትሄዳለህ ግን አትደርስም፣ ትባክናለህ ግን አታከናውንም፣ ታስቀምጣለህ ግን አታጠራቅምም፡፡ @youthkiller
አንባቢ ለመባል ብቻ አታንብብ! ለመለወጥ አንብብ!‼️

አንዳንድ መፅሐፍት ደጋግመህ ስታነባቸው ቀልብህን ይገዙታል፤ እንደአዲስ ህሊናህን መልሠው መላልሠው ያነቁታል፡፡ ልቦናህን ገዝተው ስሜትህን ያበርዱታል፡፡ ምግባርህን ይቀርፁታል፤ መንፈስህን ያድሱታል፤ ውስጥህን ዘና ፈታ ያደርጉታል፡፡፡፡

እንደዚህ ዓይነቶቹን መፅሐፍት ስታነብ ሠውነትህን ያስታውሱሃል፡፡ ለምን ዓላማ እንደተፈጠርክ ተፈጥሮህን እንዳትዘነጋ ያስረዱሃል፡፡ ሕሊናህን አንቅተው፣ ስሜትህን ገርተው፣ ምግባርህን ቀርፀው ልዩ ሠውነትን ትጎናፀፍ ዘንድ መረጃ ያቀርቡልሃል፡፡ የቀረበውን መረጃ ዕውቀት የማድረግና ነፍስ እንዲኖረው ትንፋሽ የምታበጅለት ግን አንተ ነህ፡፡

ጥሩዎቹ መፅሐፍት ሕይወትህን በእንዴት ያለ አመራር መምራት እንዳለብህ ፍንጭ ይሠጡሃል፡፡ ማንነትህን እንደአዲስ እየገነቡ የተሻለ ማንነት ትይዝ ዘንድ የሃሳብ ሃይል ይሆኑሃል፡፡

ለዚህም ነው አንደርሠን ኩፐር፡- ‹‹የአንድ ጥሩ መፅሐፍ ምልክቱ ባነበብከው ቁጥር የሚለውጥህ ሲሆን ነው፡፡›› የሚለን፡፡

አንድ ሌላም ሠው፡- ‹‹ከመፅሐፍት ጥሩዎቹ የሚደገሙት ናቸው›› ይለናል፡፡ ጥሩ መፅሀፍት ራሳችንን የምናይባቸው መስታወቶቻችን ናቸው፡፡ እነዚህ መፅሐፍት በውስጣችን ያለውን እንቁ ፈልፍለን እናገኝ ዘንድ መቆፈሪያውንና መፈለጊያውን ሃሳብ ያቀብሉናል፡፡ ዘወትር እየደጋገምን ባጣጣምናቸው ቁጥር ይለውጡናል፡፡

ደጋግመን ማንበባችን ጥሩ ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ቁምነገራቸውን በውስጣችን ለመትከልም ጭምር ስለሚያገለግሉን ነው መፅሀፍቶቹ ለዋጭነታቸውን የምንመሰክረው! በዕውቀት የተተከለ ማንነት በቀላሉ አይነቀልምና!

ጥሩ መፅሐፍት ሠውነትህን ይቀሰቅሱታል፤ ሕሊናህን ያነቁታል! ልማድህን ለበጎ ታደርገው ዘንድ ያግዙሃል! መልካም ሱስህን ለሚጠቅም እንዲውል ድጋፍ ይሆኑሃል፡፡

አንዳንድ አንባቢዎች የመፅሐፍ ቀበኛ ቢሆኑም በስራና በበጎ ምግባር ስላልተለወጡበት አነብናቢና መፅሀፍ ተሸካሚ እንጂ በሚያነቡት መጽሀፉ ተጠቃሚና ኗሪ አልሆኑበትም፡፡

ወዳጄ ሆይ… አንባቢ ለመባል ብቻ አታንብብ! ለመለወጥ አንብብ! በማንበብና በማወቅ፣ በማወቅና በማድረግ መካከል ያለውን ልዩነት አጢነው፡፡ አጢነህም ድልድይ ስራ! ራስህን ለመቅረፅ ለማያስችልህና መንፈሳዊ ብልፅግናን ለማያጎናፅፍህ አጉል ልማድ እጅ አትስጥ! ስለዚህም በጥሩ መፅሃፍትና በመልካም ምግባር ራስህን ሱስ አሲይዝ የዕለቱ መልዕክት ነው!

ደጋግመን ስናነብ የማይሠለቹን መፃሕፍቶች ምርጦቹ ናቸው! ጥሩ መፅሐፍትን ማንበብ ብቻውን ሕይወትን አይለውጥም! ባነበቡት ሃሳብ ሃሳባቸውን የሚያበስሉና በተግባር ለመለወጥ የሚሞክሩ እነሱ እውነተኛ አንባቢዎች ናቸው!

share
ከራስህ ጀምር

የሚከተሉት ቃላት በአንድ ሰው መቃብር ላይ የተፃፋ ናቸው።

ወጣትና ነፃ ሳለሁ ና ምናቤ ገደብ በሌለው ወቅት አለምን ስለመለወጥ አልም ነበር። እያደግኩና እየበሰልኩ ስመጣ ግን እንደማትለወጥ አወቅኩ፣ ስለዚህ ምኞቴን አጠር አደረኩና ሀገሬን ለመለወጥ ወሰንኩ። ነገር ግን እሱም የሚሳካ አልመሰለኝም።ወደ መጨረሻ እድሜዬ እየደረስኩ ስመጣ በአንድ የመጨረሻ ተስፋ የመቁሩጥ ሙከራ ፣ የራሴን ቤተሰቤን ብቻ ፣ ለእኔ ቅርብ የሆኑትን ለመለወጥ ወሰንኩ ፤ እሱም አልሆም።

እና አሁን በምሞትበት አልጋ ላይ ተጋድሜ ድንገት ይህንን አስተዋልኩ፤ ራሴን ለውጬ ቢሆን ኖሮ ፣ ምሳሌ በመሆን ቤተሰቤን መለወጥ እችል ነበር። ከእነርሱ ምሳሌነት ማበረታቻ የተነሳ ፣ ሀገሬን የተሻለ ማድረግና ማን ያውቃል አለምንም መቀየር እችል ይሆን ነበር።
@Youthkiller
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ET Airdrop 🇪🇹 (B$ VENOM [̲̅ə̲̅٨̲̅٥̲̅٦̲̅])
@wating_for_love
@wating_for_love
365Scores: Sports Scores Live v 5.1.0 365Scores
በዚ App full-time ድረስ live ማየት ወይም መከታተል ይችላሉ።
አስተላለፍ ለማየት ከ ጨዋታው 30 ደቂቃ ቀደም ተብሎ ይለቀቃል።
ጨዋታው እየተካሄደ የገባውን ጎል ማየት ።
የዝውውር ዜናዋቸች ወዲያውኑ ማግኘ።
የሁሉንም ሊግ ለየብቻው የ ደረጀ ሰንጠረዥ ማየት።
ቀጣይ ጨዋታቸውን ወይም ከዚ በፊት ያደረጉትን ጨዋታ ማየት።
ወዘተ ብቻ ቀውጢ app ነው
@wating_for_love
@wating_for_love
Forwarded from ET Airdrop 🇪🇹 (B$ VENOM [̲̅ə̲̅٨̲̅٥̲̅٦̲̅])
365scores.apk
16.2 MB
@wating_for_love
@wating_for_love
365Scores: Sports Scores Live v 5.1.0 365Scores
በዚ App full-time ድረስ live ማየት ወይም መከታተል ይችላሉ።
አስተላለፍ ለማየት ከ ጨዋታው 30 ደቂቃ ቀደም ተብሎ ይለቀቃል።
ጨዋታው እየተካሄደ የገባውን ጎል ማየት ።
የዝውውር ዜናዋቸች ወዲያውኑ ማግኘ።
የሁሉንም ሊግ ለየብቻው የ ደረጀ ሰንጠረዥ ማየት።
ቀጣይ ጨዋታቸውን ወይም ከዚ በፊት ያደረጉትን ጨዋታ ማየት።
ወዘተ ብቻ ቀውጢ app ነው
@wating_for_love
@wating_for_love
2024/09/21 19:36:43
Back to Top
HTML Embed Code: