Telegram Web Link
«ለደስተኛ ሕይወት»
ሼር ማድረግ ደስ ይላል፡፡ የዛሬ ደስታዎን ሼር በማድረግ ይጀምሩ፡፡
1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው።
2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።
3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡
4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።
5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡
6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦ ሰዎችን አትና፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡
7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው።
8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤ የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት ተንከባከበው፡፡
9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።
10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡ share @youthkiller
ከደም አይነትዎ አኳያ አመጋገብዎን እንዴት ማስተካከል እንደሚገባዎ ያስረዳል፡፡ ታዲያ ሼር ማድረግዎን አይርሱ ምክንያቱም ልክ እንደኛ ይሄ መረጃ የሚስፈልጋቸው ሰዎች ይኖራሉና፡፡
የደም ዓይነትዎ “ኦ” (Blood Group O) ከሆነ የምግብ ፕሮፋይል ባለ ከፍተኛ ፕሮቲን እና ሥጋ ተመጋቢ ናቸው። ተስማሚ ምግቦች
• ስጋ
• አሳ
• አትክልት
• ፍራፍሬ
ክብደትን ለመጨመር የሚረድ ምግቦች
• ስንዴ
• በቆሎ
• ኩላሊት
• ምስር
• ጥቅል ጐመን
ክብደትን ለመቀነስ የሚረድ ምግቦች
• ጉበት
• ቀይ ስጋ
• ስፒናች
• ብሮክሊ
• የባህር ውስጥ ምግቦች
የደም ዓይነት “ኤ”(Blood Group A) የምግብ ፕሮፋይል
• አትክልት እና ፍራፍሬ፤ ቅጠላ ቅጠል ተመጋቢ ናቸው።
ተስማሚ ምግብ
• አትክልት
• የባህር ውስጥ ምግቦች
• ጥራጥሬዎች
• ፍራፍሬዎች
ክብደትን ለመጨመር የሚረዱ ምግቦች
• ስጋ
• ወተት
• ኩላሊት
• ስንዴ
ክብደትን ለመቀነስ የሚረድ ምግቦች
• የአትክልት ዘይት
• የአኩሪ አተር ምግቦች
• አትክልቶች
• አናናስ
የደም ዓይነት ‘’ቢ”(Blood Group)
የምግብ ፕሮፋይል
• ከአትክልትና ስጋ የተመጣጠነ ተመጋቢ ናቸው።
ተስማሚ ምግብ
• ስጋ (ዶሮን አይጨምርም)
• ወተት
• ጥራጥሬ
• ቦሎቄ
• አትክልትና ፍራፍሬ
ክብደትን ለመጨመር የሚረድ ምግቦች
• በቆሎ
• ምስር
• ለውዝ
• አጃ
• ስንዴ
ክብደትን ለመቀነስ የሚረድ ምግቦች
• አረንጓዴ አትክልቶች
• እንቁላል
• ጉበት
• ሻይ
የደም ዓይነት ‘’ኤቢ” (Blood Group AB)
የምግብ ፕሮፋይል
• የሁሉም ምግቦች ድብልቅ ተመጋቢ ናቸው።
ተስማሚ ምግብ
• ስጋ
• የባህር ውስጥ ምግቦች
• ወተት
• አደንጓሬ
• አትክልት
• ፍራፍሬ
ክብደትን ለመጨመር የሚረድ ምግቦች
• ቀይ ስጋ
• ኩላሊት
• በቆሎ
• ቦለቄ
ክብደትን ለመቀነስ የሚረድ ምግቦች
• የባህር ውስጥ ምግቦች
• ወተት
• አረንጓዴ አትክልቶች
• አናናስ
መልካም ጤና!! Share @youthkiller
በአንድ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት ውስጥ መምህሯ ተማሪዎቿን በምታስተምርበት ወቅት አንድ Assignment መስጠት ፈለገች።

ተማሪዎቿን ድንች ይዘዉ እንዲመጡ አዘዘች፡፡ ድንቾቹ ላይም የሚጠሏቸዉን ሰዎች ስም እንዲፅፉ አዘዘቻቸዉ። የሚያመጡት የድንች ብዛትም በሚጠሏቸዉ ሰዎች ብዛት ልክ እንዲሆን አለች፡፡

በሁለተኛዉ ቀን አንዳንዶቹ 3 ሌሎች 5 ቀሪዎቹ ደግሞ 8 ድንቾቹን የሚጠሏቸዉን ሰዎች ስም ፅፈዉ አመጡ። መምህሯ ደግሞ <<ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት እኒህን ድንቾች በሻንጣችሁ ይዛችሁ ትዞራላችሁ...ሽንት ቤት ስትሄዱ እንኳ መተዉ አትችሉም!>> ብላ አዘዘች፡፡

ቀኑ እየጨመረ ሲሄድ ድንቹ በመበላሸቱ ሽታዉ ይረብሻቸዉ ስለጀመረ ተማሪዎቹ ቅሬታ ማቅረብ ጀመሩ። በተለይም 8 የያዙት ከሽታው በተጨማሪ ክብደቱ እንደበዛባቸው መናገር ጀመሩ፡፡

ከሳምንት በኋላ የ"አሳይመንቱ" ገደብ ስላበቃ ተማሪዎች ድንቹን አዉጥተዉ እንዲጥሉ ተፈቀደላቸዉ::

ከዛም መምህሯ<<እህ እንዴት ነበር?>> ብላ ጠየቀቻቸው። ሁሉም ማጉረምረም ጀመሩ ..."ኧረረረ ከክብደቱ ሽታዉ...ኧረ በጣም ነዉ የሚያስጠላዉ"...አሉ
መምህሯም <<አያችሁ በልባችሁ የምትሸከሙት ጥላቻም እንዲሁ ነዉ...ጥላቻ ልብን ይመርዛል በምትሄዱበት ሁሉም እየተከተለ ይረብሻችኋል...ለአንድ ሳምንት የተበላሸ ድንችን ሽታ መቋቋም አልቻላችሁም። አስቡት ደግሞ በጥላቻ የተመረዘን ልብ እድሜ ልካችሁን ይዛችሁ ስትኖሩ!!>> አለቻቸዉ። ጥላቻን ከዉስጣችሁ አዉጡትና ከእዳ የፀዳችሁ ሁኑ!!

እዉነተኛ ፍቅር እንከን አልባን ሰዉ ማፍቀር ሳይሆን ንፁህ ያልሆነን ሰዉ በንፁህነት መዉደድ ነዉና!!!

@Youthkiller
"ብቻህን ለመቆም ተዘጋጅ !

የራስህ አስተሳሰብና አቋም እከሌለህ ድረስ ሌሎችን እየመሰልክና እየተመሳሰልክ መኖር ግድ ይለሀል። ጥዋት ስትነሳ እቅድህ ዛሬ ደሞ ማንን ልምሰል ይሆናል እንደማለት ነው።

“ብቻህን ለመቆም ተዘጋጅ፣ ልጅ፣ ወንድም፣ እህት፡ ዘመድ የሚባሉ ነገሮች የምቾት ጊዜ አጫፋሪዎች ናቸው፡፡” እንዲሉ ብርሀኑ ድንቄ

ከመሞትህ በፊት ኑር፦ስለዚህ ከሠው አትጠብቀ እንደምንም በራስህ ቁም አስተውል ለሊቱ ቢረዝምም መንጋቱ ግን አይቀርም ያኔ እማያልቅ ደስታ ታገኛለህ:: ለዚህ ሀሳብ ጥሩ መርህ ዴዝዴራታ ይመስለኛል ዴዚዴራታ ማለት መሠረታዊ የኑሮ መመሪያ ማለት ነው በአንድ ወቅትቦልቲሞር ከሚገኘው የጥንቱ የቅዱስ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተገኘ ነው። ለትውስታ ያህል እንመልከተው

#ዴዚዴራታ

በዚህ ዓለም ጥድፊያና ሁካታ ሳትበገር በእርጋታ ኑር፡፡ ከጸጥታ ሠላም ሊገኝ የሚችል መሆኑንም አትዘንጋ፡፡
ያለአግባብም ሳትበለጥ የተቻለህን ያህል ከሰዎች ሁሉ ጋር ስምምነት ይኑርህ፡፡ እውነት ነው ብለህ የያዝከውን ነገር በጥሞናና በግልፅ ከመናገር ወደኋላ አትበል፡፡ ሌሎች የሚናገሩትን ከመስማትም አትቦዝን፡፡
ሆነ ብሎ ለሚያዳምጣቸው ከዳተኞችም ሆነ ከደደቦች ቁም ነገር አይታጣም፡፡ እራስህን ከሌሎች ሰዎች ማመዛዘን ከያዝክ እብሪተኛና መንፈሰ መራራ ልትሆን ትችላለህ፡፡ ምክንያቱም ከሰዎች መካከል ካንተ የሚበልጡም የሚያንሱም አይታጡም፡፡ በምትሰራው ስራ መሳካትም ሆነ በወደፊት ውጥንህ ተደሰት፡፡ የምትሰራው ስራ ዝቅተኛም ቢሆን የኔ ነው ብለህ ያዘው፡፡ በዚህ ወረቱ ተለዋዋጭ በሆነ ዘመን የሚያዋጣው የአንድ ሙያ ባለቤት ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡

አለም በሸፍጥ የተሞላ በመሆኑ ገንዘብን በሚመለከት ነገር ጥንቃቄ አይጉደልህ፡፡ ይህም ሲባል ሰው ሁሉ ክፉ ነው ብለህ በደፈናው አትገምት፡፡ ከፍተኛ ቁም ነገር ያለው ተግባር ለመፈፀም የሚጣጣሩ ብዙ ሰዎች መኖራቸውንና ህይወትም ብዙ ጀብዱ የሞላበት መሆኑን አትሳት፡፡ በራስህ ተማመን፡፡ በተለይም ፍቅር ማስመሰልን የሚጠላ መሆኑን እወቅ፡፡ እንዲያውም ፍቅር በዘፈቀደ የሚታፍ ነገር አይደለም፡፡ በዚህ የመንፈስ ድርቀትና መሰልቸት የሚያጠቃው አለም እንደሜዳ ሳር ጠውልጎ የሚለመልም ፍቅር ብቻ ነው፡፡ የወጣትነት ወራት ፍላጎትህ ብዙ ዘመን ለተጠራቀመ የሽምግልና ምክር በለዘብታ ይገዛ፡፡ ሳታስበው ለሚያጋጥምህ መከራና ችግር ድጋፍ እንዲሆንህ የመንፈስ ፅናት ይኑርህ፡፡ ሆኖም እንዲህ ያለ ነገር ሳይደርስብኝ አይቀርም እያክ በከንቱ ልብህ አይታወክ፡፡ ብዙውን ጊዜ ፍርሃት የሚመነጨው ከመዳከምና ከብቸኝነት ነው፡፡
ወግ ባለው ሁኔታ ኑሮህን መቆጣጠር አስፈላጊ ቢሆንም እንኳን እራስህን ከመንከባከብ ቸል አትበል፡፡ ከዕፅዋትና ከከዋክብት የማታንስ የዚህ ታላቅ ፍጥረተ ዓለም ዝርያ ስለሆንክ፡ በዚህች ዓለም ላይ የመኖር መብት አለህ፡፡ ሁኔታው ላንተ ግልፅ ሆኖ ባይታይም፡ ይህ ታላቅ ፍጥረተ ዓለም ያለጥርጥር ሚስጥሩ እያደር እየተገለጠ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ህሊናህ አውጥቶ አውርዶ ከተቀበለው አምላክ ጋር ግንኙነትህ የሰመረ ይሁን፡፡

ከትግልህና ከወደፊት ምኞትህ ጋር በዚህ ትርምስ በበዛበት አለም ስለምትኖር ለነፍስህ ሠላም አትንፈጋት፡፡ ከክፋቱ፣ ከልፋቱም ሆነ ከውጣ ውረዱ ጋር ይህ አለም ግሩም ስፍራ ነው፡፡ እንግዲህ ለኑሮህ እወቅበት፡፡ ደስተኛ ለመሆንም ተጣጣር፡፡ የሚል ነው ዲዝዴራታ ከዚህ በላይ ምን ይገልፀዋል

share @youthkiller
ብዙዎቻችን_ባጣነው_ነገር_እንበሳጫለን
# በጣም_አስተማሪ_መልክት_ነው_አንብቡት
# በአንድ_ወቅት አንድ መንፈሳዊ አባት ከነበሩበት ቦታ ወደ በረሃ መሰደድ ግድ ሆነባቸው። ከቅዱስ መጽሐፋቸው ሌላ ሦስት ነገሮች ነበሯቸው።
እነሱም፦ ቅዱስ መጽሐፉን በጨለማ ወቅት ለማንበብ የሚጠቅማቸው ኩራዝ ፣ጎህ ከመቅደዱ በፊት ከእንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸው አንድ አውራ ዶሮ እና ለመጓጓዣነት የሚገለገሉበት አንድ አህያ ነበሩ።
አንድ ቀን ምሽት ከጉዞ የተነሣ በጣም ስለ ደከሙ እኚህ መንፈሳዊ አባት ወደ አንድ መንደር ቀርበው ማደሪያ ቢጠይቁም መንደርተኛው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማንም አላሳደራቸውም። ስለዚህም ከመንደሩ አቅራቢያ አንድ ጉድጓድ ያገኙና በዚያ ውስጥ ገብቶ ለማደር በመወሰን ገብተው አደሩ። እንደ ወትሮው ቅዱስ መጽሐፋቸውን ለማንበብ ኩራዛቸውን ቢለኩሱትም የነበረው ብርቱ ነፋስ አጠፋባቸው።
ስለዚህም ለመተኛት ጋደም እንዳሉ ተኩላ መጥቶ አውራ ዶሮዋቸውን፣ አንበሳም አህያቸውን በሉባቸው። የተደራረበ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሽማግሌው እርዳታን በመሻት ወደዚያ መንደር ቢመለሱ ዘራፊ ሽፍታዎች የመንደሩን ነዋሪዎች በሙሉ ገድለው ንብረት ዘርፈው ዖና መንደር ሆኖ አገኙት።
ሽማግሌው ይህን ሁሉ ባጤኑ ጊዜ እግዚአብሔር ምን ያህል መልካም ነገርን እንዳደረገላቸው አስተዋሉ። በዚያች ምሽት በመንደርተኞቹ በአንዱ ቤት ቢያድሩ ኖሮ የዘራፊዎች ሰለባ ሆነው ሊገደሉ በቻሉ ነበር። ቀንዲላቸውንም ነፋስ ባያጠፋው የብርሃኑ ወጋገን እዚህ ጋር ሰው አለ በማለት ለሽፍታዎቹ ያሳብቅ ነበር። አውራ ዶሮአቸውና አህያቸውም ባይበሉ ኖሮ ከሽፍታዎቹ ተደብቀው ማደር ባልቻሉ ነበር።” እግዚአብሔር ከክፉ ነገሮች ውስጥ መልካም ነገር ማውጣት የሚችል አምላክ ነው።"
እኛም የምንፈልገውን ነገር ፈጣሪ በከለከለን ግዜ ልናመሰግነው እና የተሻለ እንዳሰበልን ልናስብ ይገባል
ስለዚህ እንዲህ በሉ፦ "የሚደርስብኝ ፤ የሚገጥመኝ ፈተናና መከራ ሁሉ አምላኬ ሆይ ለበጎ ታደርግልኛለህና አመሰግንሐለሁ" አሜን. Share @youthkiller
ከዕለታት አንድ ቀን ህጻን ቶማስ ኤዲሴን ከትምህርት ቤት ወደ ቤቱ ተመለሰ። ለእናቱ «እማየ ፣ ይህን መልዕክት ላንቺ እንዳደርስ ከመምህራችን የተሰጠኝ ነው» በማለት በእጁ የያዘውን ወረቀት ሰጣት። ወረቀቱ ላይ የሰፈረውን ፅሁፍ ስታነብ አይኖቿ እንባ አቀረሩ። ለህጻኑ ቶማስ ኤዲሰንም መልዕክቱ «ልጅሽ የምጡቅ አይምሮ ባለቤት ነው፤ ስለሆነም የኛ ትምህርት ቤት ከርሱ አቅምና ብቃት አንጻር የሚመጥነው ባለመሆኑ በቤት ውስጥ አስተምሪው» ይላል በማለት አነበበችለት። እናት ልጇን በራሷ ስልት በቤት ውስጥ ማስተማር ጀመረች። ራሱም በራሱ እንዲማር አተጋችው፡፡ ጊዜዋን ሰውታ ከርሱ ጋር ሌት ከቀን በማሳለፍ አበረታችው፡፡

ዓመታት አለፉ። የቶማስ ኤዲሰን እናት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች። ህጻኑ ቶማስ ኤዲሴን የህይወት ፈተናዎችን ተጋፍጦ የወጣነት የዕድሜ እርከን ላይ ደረሰ። ለአገሩ አሜሪካና ብሎም ለዓለም ብዙ የፈጠራ ትሩፋቶችን አበረከተ። በሰው ልጅ ታሪክ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ አምፑል «ፈጣሪ» ሆነ። ዓለምን ከ«ጨለማ» ወደ «ብርሃን» አሸጋገረ። የሰው ልጅ ከኩራዝ ብርሃን ወደ ኤሌክትሪክ ብርሃን እንዲተዋወቅ መሸጋገሪያ ድልድይ ፈጠረ።

አንድ ቀን ቶማስ ኤዲሰን የእናቱን ሳጥን እየፈተሸ ሳለ አይኖቹ ከአንዲት ወረቀት ላይ ተተክለው ቀሩ። ወረቀቱን አንስቶ በውስጡ የያዘውን መልዕክት ሲያነብ ክው አለ። ወረቀቱ ላይ የሰፈረው ጽሁፍ «ልጅሽ ቂልና የማይገባው ዘገምተኛ ነው፤ ከነገ ጠዋት ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ፈጽሞ አናስገባውም» የሚል ነበር። ቶማስ ኤዲሰን ለብዙ ሰዓታት በእንባ ጎርፍ ታጠበ። ይህች ወረቀት ቶማስ ኤዲሰን ህጻን እያለ ከመምህሩ ለእናቱ እንዲያደርስ የተሰጠው ወረቀት ናት። እናት የልጇን ስሜት ላለመስበር ጽሁፉን ያነበበችው በተቃራኒው ነበር ።.

ቶማስ ኤዲሰን ወረቀቷን ካነበበ በኋላ በማስታወሻው ላይ «ኤዲሰን ሞኝ እና የማይረባ ህጻን ነበር ፤ ግና ውድ በሆነች እናቱ እገዛ የምጡቅ አይምሮ ባለቤት ሊሆን ቻለ» በማለት አሰፈረ ።
የለውጥ ሁሉ መነሻው ፣ የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን አትዘንጋ ፣
ከየትኛውም ውሳኔ በፊት እውቀትን አስቀድም ፣ እውቀትህን ለማዳበር ፣
ሁሉንም ዓይነት፣ የእውቀት መንገድ ተጠቀም ። ከንግግርም ሆነ ከተግባር በፊት ዕውቀት ቀዳሚ ነው"! @youthkiller @youthkiller @youthkiller
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Haraa seenaa biliget isinittin himma!!!
Biliget Lammi biyyaa amerika sooressa biyyaa lafa kanati INA namichi kun waan hunduman guutudha garuu gammachu hin qabu ture. kanaf, guyyaa tokko ka'e waan isaa gammachisu barbacha jalqabe kanafis guyyaa tokko gammachu barbacha gara planeti biiraa deeme qofa jiraachu jalqabe garuu kunis gammachu hin tanef. guyyaa adda biiraa Uffaata adda addaa nyaata gosa adda addaa nyaacha uffaacha jiraachu yaade garuu kunis gammachu hin taanef. kanaf, guyyaa tokko namicha gargara isaa mari'achuf akkas jedhe "ani waan hundumayuu qaba waanin barbadee nyachuu , uffaachuu, Bakkan barbade jiraachu nan danda'a garuu kun hundiyyuu gammachu naaf hin laane kanaaf maal yoon godhe naa gammachisa" jedhe gafaate namichi gargaran isaa kunis gara africatti isaa fide namoota bishaa qulqulu hin tane lafa gadi jedhani dhugan itti agarsise yommuu kana biliget baayee gadee ofirraa gadii ta'e boo'e kanarra kan ka'es namoota naannoo sanaaf guyyaa muraasa gidduutti bishaan Qulqulluun akka argatan tasise kananis jireenya isaatti baayee gammada ta'e . haraa talali Africa keessa hundaa isaayu isatu gargarsan africaf laata kanaf gammachu essaatu hin argatin nama gargaaru irraa argate.
waan dubbistanif galatooma!!!


🇪🇹 @youthkiller 🇪🇹
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ (Gizachew Nega)
# የማትናደፍ_ንብ_ከፈለክ_ከዝንብ_ጋር_ተጋባ "
(በዲ/ን ዳንኤል ክብረት)
ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው ። ለማሩ ስንል ንድፊያውን መታገሥ ፡፡ ቆይተህ
ደግሞ ንድፊያውን መልመድ ፡፡ ገበሬ ቀፎ ሰቅሎ ንብ ሲያንብ ፣ ንብ
እንደምትናደፍ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም ፡፡ የማትናደፍ ንብ ከፈለገ በየደጁ ቆሻሻ
ፍለጋ የምትጓዘው ዝንብ ነበረችለት ፡፡ ዝንብ ምን ጠባይዋ ሸጋ ቢሆን ፤ ጠብ
የሚላት ግን ሌላ ነገር ነው ፡፡
ይህን ያውቃል ገበሬው ፡፡ እያወቀም ንብ ያንባል ፡፡ ማነብ ብቻ ሳይሆን ከንብ ጋር
እንዴት መኖር እንደሚቻልም ያውቃል ፡፡ ንብ ትናደፋለች ፤ ግን እንዳትናደፍ
ማድረግም ይችላል ፡፡ የምትወደውና የማትወደው ሽታ አለ ፡፡ ስትቀርብህ ምን
ማድረግና ምን አለማድረግ እንዳለብህ ገበሬው ያውቃል ፡፡
በሀገራችን ንብ አትገደልም ፡፡ ነውር ነው ፡፡ ብትነድፍም አትገደልም ፡፡ የንቧን
ማር ለመውሰድም ንቧን ገድሎ ፣ አጥፍቶ ፣ ጎድቶ ወይም አሰቃይቶ ሳይሆን
በጭስ ራሱን እየተከላከለ ፣ ፊቱን በጨርቅ ሸፍኖ ፣ ወደ ንቧ ቀፎ ገብቶ ነው
ማሩን የሚቆርጠው ፡፡ ንቧም ሳትጎዳ ፣ ማሩም ሳይጠፋ ፣ እርሷም ሳትናደፍ ፡፡
ትዳርም እንዲህ ነው ፡፡ አኗኗሩን ነው ማወቅ ፤ የንቧን ንድፊያ የመቀነሻውን
መንገድ ነው ማወቅ ፣ የማሩን አቆራረጥ መንገድ ነው ማወቅ ፡፡ ደግሞም‘ኮ
አስገራሚው ገበሬው የሚከባከበው ይህቺኑ የምትናደፈውን ንብ መሆኑ ነው ፡፡
የምትቀስመው አበባ ትፈልጋለች ፣ ንጹሕ አካባቢ ትፈልጋለች ፣ ከጉንዳንና
ከአውሬ ነጻ የሆነ ቀፎ ትፈልጋለች ፡፡ ግን ትናደፋለች ፡፡ ደግሞም ማር ትሰጣለች
፡፡
ትዳር አስደሳች ነገር ብቻ ሳይሆን አስመራሪ ፣ አስጠሊታ ፣ ጨጓራ አንዳጅ ፣ ልብ
አቃጣይም ክፍል አለው ፡፡ ይናደፋል ፡፡ ግን ደግሞ ክብካቤም ይፈልጋል ፡፡ ንጹሕ
ልብ ፣ ታማኝ ኅሊና ፣ ቻይ አንጀት ፣ ታጋሽ ሆድ ፣ ጠቢብ አእምሮ ፣ አሳላፊ ልቡና
ይፈልጋል ። ለምን ቢሉ ? ማር ይሰጣልና ታገሱ ።
ሰናይ ቀን. @youthkiller
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ (Gizachew Nega)
አእምሮህን እንደ አንድ የአትክልት ስፍራ ተመልከተው፡፡ አንድ የአትክልት ስፍራ የተለያዩ አትክልቶችን የሚያበቅለው ስለዘራህበት ብቻ አይደለም፡፡ ብትዘራበትም ባትዘራበትም አረምም ሆነ “ወፍ-ዘራሽ” ነገሮችን ማብቀሉ አይቀርም፡፡ ጥሩ ዘርን ከዘራህበት የዘራህበትን ጥሩ ዘር ያበቅላል፡፡ መጥፎ ዘር ከዘራህበትም እንዲሁ፡፡ ምንም ዘር ካልዘራህበት ደግሞ ይህንና ያንን ማብቀሉ አይቀርም፡፡ አእምሮህም እንዲሁ ነው፡፡ በገጠመኞችና በተለያዩ ሁኔታዎች የሚገቡ “ወፍ-ዘራሽ” ሃሳቦችን ማብቀሉ ካልቀረ፣ መልካም ነገርን እየዘራህበትና ጥሩ ጥሩውን እያሰብክ ጣፋጭ ሁኔታዎች መፍጠር ትችላለህ፡፡
በተፈጥሮአችን ወደ እኛ የምንስበውም ሆነ ራሳችንን ተስበን የምንገኝለት ሁኔታ ከአመለካከታችን ጋር ዝምድና አለው፡፡ ስለዚህም፣ ሰዎች ወደ እነሱ የሚስቡት የሚመኙትን ነገር አይደለም፤ የሆኑትን ነገር ነው እንጂ፡፡ ይህ ልንክደው የማንችል ሕግ ነው፡፡ ከጥቂት ገጠመኞች በስተቀር በጥቅሉ ስናየው ሰው አሁን ያለበት ቦታ የተገኘው በአጋጣሚ አይደለም፡፡ ባሰላሰላቸው ሃሳቦች፣ ባዳበረው እይታና በዚያ ተጽእኖ ምክንያት በወሰናቸው ውሳኔዎች ምክንያት ነው፡፡
ሰው በአመለካከቱ ወደመሆን ያመጣውን ሁኔታ ለማጥፋት ሲታገል የሚኖር ፍጡር ነው፡፡ “ሁኔታዬ መለወጥ አለበት” የሚል የማያቋርጥ ትግል ሲታገል ይታያል፡፡ ያንን ሁኔታ ወደመሆን ያመጣውን አመለካከቱንና እይታውን ግን መለወጥ አይፈልግም፡፡ ይህ ሁኔታውን ወደመኖር ያመጣው አመለካከቱ በውስጡ እንዳለ ላያስተውለው እንኳን ይችላል፡፡ አለማወቅ ግን ከውጤቱ እንዲያመልጥ ሊያደርገው አይችልም፡፡ አመለካከቱን ሳይለውጥ ሁኔታውን ለመለወጥ የሚያደርገው ጥረት ከንቱ ስለሆነ በሁኔታው እንደታሰረ ይኖራል፡፡ @youthkiller
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ (Gizachew Nega)
ምርጥ__የአፍሪካዊያን__አባባሎች "
……" ያለ ሰዓቱ የሚጮኽ ዶሮ መንጋቱን ሳይሆን
መታረዱን ያውጃል!!" (ኢትዮጵያዊያን)
1 "በችግር ጊዜ ብልህ ሰው ድልድይ ሲገነባ፤ ሞኝ
ደግሞ ግድብ ይገድባል!" (ናይጄሪያዊያን)
2 "ሀብት ሲጠቀሙበት እያለቀ ይሄዳል፤ ትምህርት ግን
እየተጠቀሙበት በሄዱ ቁጥር እየጨመረ
ይሄዳል!" (ታንዛኒያውያን)
3 "እውነቱን ላለማየት ዓይናችንን የምንጨፍን ከሆነ
ልንማር የምንችለው ከአደጋ ይሆናል!" (ኬንያዊያን)
4 "ከማሸነፍ ይልቅ በመሸነፍ ወቅት ብዙ ትምህርት
ይገኛል!" (ጋቦናዊያን)
5 "ሞኝ ጨዋታውን በሚለምድበት ጊዜ ተጨዋቹ
ይበተናል!" (አሻንቲዎች/ጋና)
6 "ምክር ልክ እንደ-እንግዳ ነው። የሚቀበለው ካገኘ
ያድራል፤ የሚቀበለው ካጣ ግን የዚያኑ ቀን ተመልሶ
ይሄዳል!" (ኮንጎዎች)
7 " አዋቂዎች በበዙበት ቦታ የአዳማጭ ዕጥረት
አለ!!" (የስህዋሊ አባባል)
8፦ ……" በአንበጣዎች መካከል የሚደረግ ፀብ ለከብቶች
መዝናኛ ነው!!" (ቦትስዋናዊያን)
9፦ ……" ትልቅ ወንበር ብቻውን ንጉሥ ሊያደርግ
አይችልም!!" (ሱዳናዊያን)
10፦ ……" በረሮ ዶሮዎችን የመምራት ሃሣብ ካለው፤
ቀበሮን ጠባቂው አድርጎ መቅጠር
ይኖርበታል!!" (ሴራሊዮናዊያን)
11፦ ……" ቤተሰብ ልክ እንደ-ደን ነው። ከሩቅ ሲያዩት
ጥቅጥቅ ያለ ሲሆን፤ ሲገቡበት ግን እያንዳንዱ የየራሱ
ቦታ አለው!!" (ዛየራዊያን)
12፦ ……" የገንዘብ ስልት ከጦር ስልት
ይበልጣል!!" (ካሜሮናዊያን)
13፦ ……" ገንዘብ ማውራት ባይችልም፤ ውሸትን እውነት
የማድረግ አቅም ግን አለው!!" (ደ/አፍሪካዊያን)
14፦……" ከገንዘብ ውስጥ ስንወጣ አዋቂ እየሆንን
እንሄዳለን!!" (አይቮሪኮስታዊያን)
15፦ ……" እስኪያወራ ድረስ እያንዳንዱ ሰው ውብ እና
ቆንጆ ነው!!" (ዙምባቤዎች)

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ፔጁን ሼር፣……@youthkiller
መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች የማያደርጓቸው 12 ነገሮችን እንከተል!
መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ሃሳባቸውንና ባህሪያቸውን በመግራት እና ስሜታቸውን በመቆጣጠር ይታወቃሉ፡፡
በአዕምሯዊ ብስለት እና በአስተሳሰብ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ የደረሱ ሰዎች የሚከተሉትን ነገሮች አያደርጉም፡፡
1. ፍርሃት የለባቸውም:
መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ምክንያታዊ አስተሳሰብን ስለሚያጎለብቱ ሰዎች ብዙ ጊዜ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚያዊ ህይወታቸው ወደፊት ሊገጥማቸው ስለሚችሉ ችግሮች አስቀድመው ስጋት ውስጥ ለሚጥል ጭንቀት አይዳረጉም፡፡
2. በሌሎች ስዎች ስኬታማነት አይቀኑም:
አዕምሯቸው ሚዛናዊነትን ያጉለበተ ሰዎች ስኬትን ከተቀዳጁ ሌሎች ሰዎች ትምህርትን ለመውሰድ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ እንደሆኑ ይነገራል፡፡
የስነ ልቦና ባለሙያዎች በሌሎች ሰዎች ድክመት እና ስኬትማነት ላይ ማተኮር የራስን እቅድ ያሳጣል ይላሉ፡፡
3 . ባለፈ ነገር አይፀፀቱም:
ስላለፈው ጉዳይ መጨነቅ እና በፀፀት ጊዜን ማሳለፍ ለወደፊቱም እቅድን እንዳይነድፉ መሰናክል ይሆናል፤ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ካለፈው ችግራቸው ወይም ውድቀታቸው ትምህርት በመውሰድ አሁን ያለውን የተሻለ በማድረግ ለነገ ስኬታማነታቸው በጥረት ይሰራሉ፡፡
4. ራሳቸውን አሳልፈው አይሰጡም፤ አይሸነፉም:
ብዙ ጊዜ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች አካላቸው እንኳ ቢደክም በአስተሳሰብ እና በአመለካከታቸው ብርቱ አቋም ይዘው ለስኬት ይበቃሉ፡፡ ራሳቸውንም ለጠላቶቻቸው አንበርክከው አይሰጡም፡፡
5. ለውጥን አይፈሩም:
እነዚህ ሰዎች ነገሮችን አመዛዝነው የሚተነብዩ በመሆናቸው በሚያደርጉት ማንኛውም ነገር ለሚመጣው ውጤት ዝግጁ ናቸው፡፡
6. ከአቅማቸው በላይ በሆነ ጉዳይ ጊዜያቸውን አያባክኑም:
በአዕምሯዊ ብስለታቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ሁሉም ነገር እነሱ ባቀዱት ልክ እንደማይሆን እና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ነገር እንደሚኖር ስለሚያስቡ አይጨነቁም፡፡
ከአቅማቸው በላይ ሆነው ለጭንቀት የሚዳርጉ ነገሮችን በአግባቡ በማስተናገድም ካልተገባ ውጥረት ራሳቸውን ያድናሉ፡፡
በዚህም ሰኬታማነታቸውን ያጎለብታሉ፡፡
7. ሌሎችን ሰዎች አይለማመጡም:
መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች አንድን ነገር ለማድረግ ሌሎችን ሰዎች በመለማማጥ ጊዜያቸውን አያባክኑም፤ አይጨነቁም፡፡
ሰዎችን መለማመጥ፣ ጊዜ እንደሚያባክን፣ ሰዎችን ጥገኛ እንደሚያደርግ እና ለግጭት እንደሚዳርግ ስለሚያውቁ ከዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ራሳቸውን ነጻ አድርገው በራስ መተማመን ይሰራሉ፡፡
በሌሎች ሰዎች ትከሻ ላይ አለመንጠልጠልም በራስ መተማመን እና ጥንካሬን ያዳብራል ብለው ያስባሉ፡፡
8. ራስን ጥፋተኛ ማድረግ:
መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች ለራሳቸው የጥፋተኛነት ስሜትን በማስተናገድ አሉታዊ ነገሮች ላይ ረዥም ጊዜ አያባክኑም፡፡
ከዚያ ይልቅ በአወንታዊ አስተሳብ እና ተግባራት ላይ ያተኩራሉ፡፡ ለመጪው ጊዜ መልካምነትም አበክረው ያቅዳሉ፡፡
9. ተመሳሳይ ስህተት አይሰሩም:
ብዙ ጊዜ ስህተት በድጋሚ ሊከሰት የሚችለው ያለፈውን ካለማገናዘብ እና እንዳይደገም ካለመዘጋጀት እንደሆነ የስነ ልቦና ምሁራን ናገራሉ፡፡
ጥሩ የአዕምሮ ብስለት ያላቸው ሰዎች ደግሞ ለሚሰሩት ስህተት ኃላፊነትን በመውሰድ በቀጣይ እንዳይደገም መፍትሔ አስቀምጠው ይሰራሉ፡፡
10. በመጀመሪያው ውድቀታቸው አይሸነፉም:
አዕምሯዊ ጥንካሬ ያላቸው ሰዎች በመጀመሪያው ውድቀታቸው መሸነፍን አያውጁም፤ ከውድቀታቸው ትምህርትን በመውሰድ የተሻለ ውጤትን ለማምጣትም በትጋት ይሰራሉ፡፡
11. ቅፅበታዊ ውጤትን አይጠብቁም:
አስተሳሰባቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ብዙ ጊዜ የሚሰሩት ስራ ወዲያውኑ ውጤት እንደሚያስገኝላቸው በማሰብ አይጓጉም፡፡
ከዚህ ይልቅ ሁሉ ስራ የራሱ ጊዜእንዳለው እና የስኬቱም ምንጭ የተቀመጠለት ጊዜ፣ የሚደረግለት ተግባራዊ እንቅስቃሴ መሆኑን በእቅዳቸው አስቀምጠው ጉዞ ወደ ፊት ይላሉ፡፡
ይህ ደግሞ ምክንያታዊ ወይም እውናዊ የስኬት ምንጭ በአንድ ሌሊት እንደማይመጣ መረዳትን ያሳያል ነው ያሉት ባለሙያዎቹ፡፡
12. ዓለም ሁሉንም ነገር እንድታበረክትላቸው አይፈልጉም:
ዓለማችን ብዙ ተቃርኖዎች ስኬት እና ውድቀት፣ ሀብትና ድህነት፣ ሀዘን እና ደስታ ወዘተ የተጣመሩባት እንደመሆኗ መንፈሰ ጠንካራ ሰዎች የሚፈልጉትን ሁሉከዓለም እንዲያገኙ አይፈልጉም፡፡
ከዚህ ይልቅ በዓለም ላይ ደስታም ሆነ ሀዘን፣ ስኬትም ሆነ ውድቀት የሚያጋጥመው በራስ ጥረት እና ጥንቃቄ ልክ ነው ብለው ያምናሉ። @youthkiller
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ (Some Body)
በጊዜያዊ ስሜቶች (“ሙዶችህ”) አትታለል

ሰው በተፈጥሮው መልካም ገጠመኝ ሲደርስለትና በጣም በጋለና ግሩም በሆነ ስሜት (“ሙድ”) ውስጥ ሲሆን ከዚያ ቀን ጀምሮ ልብህን የሚያሳዝን ምንም ነገር እንማይገጥመው የማሰብ ዝንባሌ አለው፡፡ በተቃራኒውም በአንዳንድ ክፉ ገጠመኞች ምክንያት በጣም በወደቀ “ሙድ” ስሜት ውስጥ ራሳችንን ስናገኘው ከዚያ ሁኔታ የመውጫ ጭላንጭሉ አይታየንም፡፡ ይህ ከጊዜው “ሙድ” የተነሳ የሚመጣ “የቋሚነት” ስሜት በውሳኔአችን ላይ ጣልቃ ይገባና የኋላ ኋላ የምንጸጸትባቸውን ውሳኔዎች እንድንወስን ይገፋፉናል፡፡

ለምሳሌ፣ ይከፈለትልኛል ብለህ የጠበከው የእድል በር ባልጠበከው መንገድ ቢዘጋና የወደቀ “ሙድ” ውስጥ ብትሆን፣ ኑሮ ሊያስጠላህና የተለያዩ ውሳኔዎችን እንድትወስን ሊገፋፋህ ይችላል፡፡ “ሙዱን” ግን ማሳለፍ የግድ ነው፡፡ አየህ፣ በክፉም ሆነ በጥሩ የጠለቀ ስሜት ውስጥ ስትሆን አእምሮህ ለሕይወትህ የሚጠቅምህንና የማይጠቅምህን ነገር የማመዛዘኑ ሁኔታ ይወርዳል፡፡ እነዚህ የ“ሙድ” ውጣውረዶች ግን እየመጡ የሚሄዱ እንደሆኑና፣ እውነታ ብቻ ዘላቂ እንደሆነ በማሰብ አይኖችህን እውነታው ላይ ጣል - የማያልፍ ነገር የለምና፡፡

“የስሜት ብልህነት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ (Gizachew Nega)
#አጭር_ታሪክ በ #



አንድ በጣሙን ደሃ የሆነ ሰው ከሚስቱ ጋር ይኖር ነበር፡፡ አንድ ቀን ሚስቱ ጸጉሯን የምታበጥርበት ማበጠሪያ እንዲገዛላት ጠየቀችው፡፡ ባል በጣም አዘነ፡፡ በኪሱ አንዳችም ገንዘብ ስለሌለው እያዘነ እንደማይችል ገለጸላት፡፡ ሌላው ይቅርና በቅርቡ ማሰሪያው ለተበጠሰበት የእጅ ሰዓቱ እንኳ ማሰሪያ መግዛት ስላልቻለ በኪሱ ይዞት እንደሚዞር ማሰሪያው የተበጠሰውን ሰዓት እያሳየ እንደማይችል ገለጸላት፡፡ ሚስትም ነገሩን ተወችው፡፡ ባል ወደ ሥራ ሲሄድ በአንድ የሰዓት መሸጫ በኩል ሲያልፍ ወደ መሸጫው ገብቶ ማሰሪያው የተበጠሰውን ሰዓት ሸጠ፡፡ ሌላ ሱቅ ገባ፡፡ ለሚስቱ በጣም የሚያምር ማበጠሪያ ገዛ፡፡
ምሽት ላይ ከስራ ወደ ቤት ሲመለስ ዋንኛ ዕቅዱ ለሚስቱ እንዴት ያንን የሚያምር ማበጠሪያ እንደሚሰጣት ነበር፡፡ ሚስቱን ሲያያት ግን ደነገጠ፡፡ ያ የሚያምረው ዘንፋላ ጸጉሯ በአጭሩ ተቆርጧል፡፡ ባለማመን እንደተዋጠ የገዛላትን ማበጠሪያ ከቦርሳው አውጥቶ ወደ እሷ ቀረብ ሲል አይኗ በእንባ እንደረጠበ በእጆቿ መሃል የያዘችውን ነገር ተመለከተ የሰዓት ማሰሪያ፡፡ ሰዓቱን ሸጦ ማበጠሪያ እንደገዛላት ሁሉ፣ ለካንስ እሷም ያን ዘንፋላ ጸጉሯን አስቆርጣ ሸጣ የሰዓት ማሰሪያ ገዝታለት ነበር፡፡
አንዳቸው ለሌላኛቸው የከፈሉት የፍቅር መስዋእትነት ሁለቱንም ከልብ አስለቀሳቸው 🇪🇹
#ፍቅር_ያሸንፋል

@youthkiller
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Dr. Eyob Mamo

የሚሳካልኝና የማይሳካልኝ

የሚሳካልኝንና የማይሳካልኝን መለየት ማለት ብርቱ ጎኔን በሚገባ ለይቶ ማወቅ ማለት ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ወደዚህች አለም ሲመጣ ቢያንስ ከአንድ ዝንባሌንና ስጦታን ጋር ነው የሚመጣው፡፡ ይህንን ዝንባሌ ወይም ስጦታ በመለየት እነሱ ላይ ማተኮር አስፈላጊ የስኬት ቁልፍ ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች በብዙውን ጊዜአቸውን የሚያሳልፉት ፈጽሞ ዝንባሌአቸው ያልሆነውን ነገር ለማዳበር በመታገል ነው፡፡ አስተዋዮችን ዝንባሌአቸውና ስጦታቸው የቀደደላቸውን ፈር በመከተል ከስኬት ወደ ስኬት ይሸጋገራሉ፡፡

በሚሳካልኝና በማይሳካልኝ መካከል ለመለየት መውሰድ የምችላቸው እርምጃዎች፡-

1. ሁሉን ነገር እንደማትችል አምነህ ተቀበል

ምንም ብንታገል የማንችላቸው ነገሮች እንዳሉ በማመን መቀበልና ራስን ማረጋጋት የብስለት ምልክት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች የማይችሉትን አምኖ መቀበልን እንደ ሽንፈት ስለሚቆጥሩት ካልተሰጣቸው ነገር ጋር ሲታገሉ ራሳቸውን ያደክማሉ፡፡

2. የሚያታግልህን ነገር ልቀቀው

ሳደርገው የሚያታግለኝንና ውስጤን የማያጓጓውን ነገር በመለየት ቀስ በቀስ መልቀቅ የአስተዋይነት ምልክት ነው፡፡ የማይሳካልህ ነገር ላይ ብዙ ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ ስትሰዋ የሚሳካልህን ነገር እየጣልከው እንደሆነ ማስተዋል አለብህ፡፡

3. የሚሳካልህን ነገር አሳድገው

ስታደርገው የሚሳካልህንና ውስጥህን የሚያነሳሳውን ነገር በመለየት የበለጠ ጊዜን በመስጠት ማሳደግ ታላቅ የስኬት ቁልፍ ነው፡፡ ምንም አደረግህ ምንም፣ በብርታትህ ላይ እንጂ በድካምህ ላይ በፍጹም አትገንባ::
@youthkiller
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
2024/09/21 19:51:27
Back to Top
HTML Embed Code: