Telegram Web Link
ወጣቱ ና ሙዱ
ኮሮና

እንዴት አደራቹ ቤተሰቦቼ ዛሬ ይሄን ጠቃሚ መረጃ ላቀብላችሁ ወደድኩ ታድያ እናንተም ተቀባበሉት🙏🙏🙏

🔻||ለጥንቃቄ? ይነበብ ሼር ይደረግ ላልሰሙት እናሰማ ይህንን ጹፍ ሼር ማድረግ የብዙ ሠዎችን ህይወት ከማዳን አይተናነስም።

አንብባችሁ ለሌሎችም አስተላልፉ
ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል!
በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ!< ከሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡

< ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ ...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡
< በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/ Snow አትመገቡ! < የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡

1. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም። ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡
< በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው፡፡

< አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ ተጠቂ አትሆኑም፡፡

2. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡

3. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጡዓቸው ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡ በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች #ምን ምንድን ናቸው?

1. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጎሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል::

2. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ ትራኪያ ከወረደ በኋሊ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡

ሳምባን በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት የሚታይባችሁ ሁሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!! በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል?

1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላበተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡

< ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ ወይም [እንደ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡

< ስለዚህ ለራሳችሁና ለባልንጀራችሁ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡

2. አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም ሊቀንሰው ይችላል፡፡

3. የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ።

እባካችሁ ይህን ክፉ በሽታ ወደ አገራችን እንዳይገባ ቅድሚያ መከላከል ከገባም ምን ማድረግ እንዳለብን ለሌሎች እንዲደርስ መረውን ሼር በማድረግ ሀላፊነትዎን ይወጡ

🙏መልካም ቀን🙏
"SHARE"

@youthkiller
ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገብቷል!

"ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፤ በተደረገው ምርመራ አንድ ጃፓናዊ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። ሁላችንም ከእጅ ንክኪዎች እና አላስፈላጊ ስብሰባዎች እንቆጠብ ለማለት እፈልጋለሁ።" - ኢ/ር ታከለ ኡማ
@youthkiller
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ (face mask) አጠቃቀምና እነማን መጠቀም እንዳለባቸው ልብ ይበሉ!

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (face mask) አጠቃቀሙና እነማን መጠቀም እንዳለባቸው በቅጡ ባለመረዳት ሰዎች ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ሲዳረጉ ይስተዋላል፡፡ ስለሆም ማስክ የሚከተሉት ሰዎች እንዲጠቀሙት ይመከራል፡፡

1. የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ መጠቀም የሚያስፈልገን በበሽታው የተያዘ ወይም የተጠረጠረ ሰው አጠገብ ወይም እየተንከባከብን ከሆነ ብቻ፣

2. ሳልና ትኩሳት ካለብን ለሌላው ጥንቃቄ በማድረግ ስያስለን ወይም ስያስነጠሰን፣ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ያስፈልጋል ለምሳሌ ሰው የሚበዛበት ቦታ ከመሄድ ራስን መቆጠብ ፣ እጅ በደንብ መታጠብ ፣ መጨባበጥ ማቆም እና ማስኩን በስርዓት ማስወገድ እና ለባለሙያ ማሳወቅ ያስፈልጋል::

3. የማስክ አጠቃቀምም ውጤታማ የሚሆነው እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትሮ መታጠብ ሲቻል እና አወገገዱም ጥንቃቄ የተሞላበት ስሆን ብቻ ነው፡፡ ህብረተሰባችን መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና ፍርሀት እርሶም ይከላከሉ።

የበለጠ መረጃ ሲያስፈልግ ነጻ በሆነው 8335 የስልክ መስመር ላይ መደወል ይቻላል።

Via FBC
@youthkiller
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

🔵ብታተርፉበት እንጂ አትከስሩምና በትዕግስት እስከመጨረሻው አንብቡት🔵

አሁን ያገባሁትን ባለቤቴን ያገኘሁት በፌስቡክ ነበር፡፡ ገና ስንተዋወቅ አካባቢ ስለተለያዩ ነገሮች ቻት ማድረግ ጀመርን፡፡ ያላወራነዉ ነገር አልነበረንም ማለት እችላለሁ፡፡

የሚያመጣቸዉ ሃሳቦች ፣ አስተሳሰቡ ፣ በቃ ነገሮችን የሚገልፅበት መንገድ በእጅጉ ማረከኝ፡፡ ፌስቡክ ላይ ብዙ ጓደኞችና ተከታዬች ስለነበሩት የሰዉየዉን ተፅእኖ ፈጣሪነት ያለምንም ማመንታት በመልካም ጎኑ ብቻ እያየሁ ግንኙነታችን እየጠነከረ መጣ፡፡

የፌስቡክ ፎቶዎቹ በተለያዩ ቦታዎች ያደረገዉን ጉዞ የሚያሳዩ ስለነበሩ ይገርመኝ ነበር፡፡ በተለይ ሀገራትን መጎብኘትና አዳዲስ ስፍራዎችን ማየት ስለምፈልግ ፍላጎቴ ከፍላጎቱ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ አስብ ነበር፡፡

የሚለቃቸዉ ፅሁፎች በሙሉ ማለት ይቻላል የሚያተኩሩት ስለሴቶች እኩልነት ፣ ስለሴቶች ጤና ፣ ልዩ ድጋፍና የምክር አገልግሎት ስለነበር ይህ ሰዉ በእዉነቱ ከሆነ ለሴቶች ያለዉ አስተሳሰብ ከሌላዉ ወንድ አንድ ደረጃ ከፍ ያለ እንደሆነ ማሰብ ጀመርኩ፡፡

ከኔ ጋር መልእክት ስንፃፃፍ በጣም በሚማርክና ፍፁም ስርአት በተሞላበት መልኩ ረጋ ብሎ ያወራ ነበር፡፡ ሲጋራ እንደማያጨስና የምንም ሱስ ጥገኛ እንዳልሆነ ይነግረኛል፤ እኔም ያለማመንታት አመንኩት፡፡

የምንኖርበት ከተማ ዉስጥ ሻይ ቡና ለመባባል 'እንገናኝ' ብዬዉ ተቀጣጠርን፡፡ በቀጠሮዉ ሰአት አገኘሁት፡፡ በጣም የሚማርክና የደስ ደስ ያለዉ ሰዉ ነበር፡፡ ስንቱን ነገር ስናወራ ሰአቱ እንዴት እንደበረረ እንኳን ምንም ሳናዉቀዉ ብዙ ሰአት አብረን አሳለፍን፡፡

በተከታታይ ቀናት ለአንድ ወር ያህል እየተገናኘን ግንኙነታችንን የበለጠ አጧጧፍነዉ፡፡ ሳወጣ ሳወርድ ከቆየሁ በኋላ ከቀድሞ ፍቅረኛዬም ጋር ለመለያየት ወሰንኩ፡፡ የቀድሞ የፍቅር ጓደኛዬ ደግሞ ለምን እራሴን ቢዚ እንዳደረኩና እሱን ማግኘት እንደማልፈልግ ደጋግሞ መጠየቅ ጀመረ፡፡

አብሬዉ ብዙ ነገር ካሳለፍኩት ጓደኛዬ ጋር ተለያየን፡፡ ከልቡ የሚወደኝና ስለኔ ሁሉንም ነገር ማለት ይቻላል የሚያዉቅ የሚገርም ፍቅረኛ ነበር፡፡ እኔን የቱ ጋር እንደሚያናድድና እንደሚያስቅ እንኳን ሳይቀር አንድ በአንድ ያዉቃል፡፡ ብዙ ተመሳሳይ ፍላጎቶች ስለነበሩን 'የሚማርክ የፍቅር ጊዜያት' እንዳሳለፍን ትዝ ይለኛል፡፡

አሁን አዲስ ሰዉ በማግኘቴ ደስ አለኝ፡፡ ከዛስ? ከዛማ ልቤ ከዚህ ‘በሳል’ ሰዉ ጋር ፍቅር ብጀምር የተሻለ እንደሆነ ማመን ጀመረ፡፡ ቀጥዬ “ዉብ እኮ ነኝ! ስንት ወንዶች እናግባሽ እያሉ እግሬ ስር ወድቀዉ ሲለማመጡኝ አልነበር? ቆንጆ ሆኜማ ይህንን ሰዉ ማጥመድ ነዉ!” ብሎ ሞኝ ማንነቴ ሲዘላብድ ከመቀበል በቀር ለሰከንድ ሌላኛዉን ጎን ለማየት አልፈለኩም፡፡

አዲሱን የማረከኝን ሰዉ ከተገናኘሁት ጊዜ ጀምሮ ‘ነባሩ ውድ ፍቅረኛዬ’ አስጠላኝ፡፡ እራስ ወዳድና ደንታ ቢስ ሰዉ ስለነበርኩ ቢለማመጠኝም ከዛን ቀን ጀምሬ "አንተን ማግኘት አልፈልግም በቃ፡፡ ህይወቴን አትበጥብጥ!" ብዬ ሁለተኛ እንደማላገኘዉ ነገርኩት፤ እንዳልኩትም አደረኩት።

አዲሱን የፌስቡክ ጓደኛዬን ከጊዜ ወደጊዜ እየወደድኩት መጣሁ፡፡ ሁሌ ተገናኝተን በሃሳብ አለም መሮጥ ፣ ስለሰማይ ፣ ስለምድር በቃ ስለሁሉም ነገር መቀባጠር ስራችን አድርገን ተያያዝነዉ፡፡ ጣፋጭ ቃሎቹ እኔን በሚማርኩ አንደበቱ የሚያወጣቸዉ የፍቅር እንክብሎች እጄን ቶሎ እንድሰጥ አደረገኝ፡፡

ከሁለት ወር ግንኙነት በኋላ እንዳገባዉ ጥያቄ አቀረበልኝ፡፡ እኔም እሺ ብዬ ተጠመጠምኩበት፡፡ ቤተሰቦቼ ግን አልወደዱትም፤ ለምን እንደሆነ አላዉቅም ገና ሲያዩት 'ሁለመናዉ አላማራቸዉም'፡፡

በሚቀጥለዉ ወር ዉስጥ ከቤተሰቦቼ ጋር ጦርነት መሳይ እልህ አስጨራሽ ንትርክ ዉስጥ ገብቼ በኔ አሸናፊነት ከአዲሱ ፍቅረኛዬ ጋር ተጋባን። በሚያሳዝን መልኩ የቀን ቅዠቴ የጀመረዉ የጋብቻችን አለት ማታ ነበር፡፡

አብረን ልንተኛ ስንል እንደሌላዉ ሰላማዊ የጋብቻ ስርአት አሪፍ ጊዜ እናሳልፋለን ብዬ ባስብም እሱ ሆዬ ልብሴን እንዳበደ አንበሳ ቦጫጫቆ ዘሎ ወጣብኝ፡፡ የኔን ስሜት ምንም ሳያዳምጥ በራሱ ስሜት ጋለበብኝ።

ልክ እንደዛ ሲያደርገኝ ‘ኡኡ’ ብዬ መጮህም ፈልጌ ነበር። ግን ነገሮች ይለወጣሉ ብዬ ዝም አልኩ፡፡ ነገር ግን ነገሮች እየባሱ መጡ፡፡ የሃይል እርምጃ በኔ ላይ መፈፀሙን አጠናክሮ ቀጠለበት፡፡ ሴክስ ማድረግ ፈልጎ እንኳን አልፈልግም ብዬ ልተኛ ትንሽ ፊቴን ኮስተር ካደረኩ ይደበድበኝ ነበር፡፡

ጓደኞቼን እንዳላገኝ አገደኝ፡፡ በየቀኑ እየሰከረ እየመጣ እኔን መደብደቡን ስራዬ ብሎ ተያያዘዉ፤ ፌስቡክ ላይ ስለሴቶች እኩልነት ገለመሌ ያወራዉ ሁሉ የት ዉስጥ እንደከተተዉ እኔ አላዉቅም።

ከሁሉም ነገር በላይ በየቀኑ የሚያንገበግበኝ ከሚያፈቅረኝና ከምወደዉ ጓደኛዬ ተለይቼ ‘ዉብ ስለሆንኩ ከሱ የሚበልጥ ሰዉ ላይ እንጂ የሚያንስ ሰዉ ላይማ መቼም አልወድቅም’ በሚል ተራ ባዶ ፉከራ ተሸዉጄ ህይወቴን የማልወጣበት መቀመቅ ዉስጥ መወርወሬ ነዉ፡፡

ለቀድሞዉ ፍቅረኛዬ ጊዜ አለመስጠቴና በእዉርነት መነዳቴ የእጄን እንዳገኝ አደረገኝ። ወይኔ! አሁን የፍቺ ወረቀት ላስገባ ስለሆነ ከዚህ ሰዉዬ መለያየቴ አይቀርም፡፡ ጓደኞች እንደኔ አይነት ህይወት እንዳትመሩ ጠንቀቅ በሉ፡፡ ካየሁት ፍዳ አንዳንድ ምክር ልጠቁማችሁ፡፡

•የፌስቡክ የወሬ ቋት መቼም እንዳይሸውዳችሁ፡፡ እኛ ሴቶች አሪፍ ፣ የሚጣፍጥ ወሬን መስማት ስለምንፈልግ በእንደኔ ባል አይነቱ አዉሬ ወጥመድ ዉስጥ በአንዴ መዉደቅ አለና መቸኮል አያስፈልግም፡፡

•ማንንም ሰዉ ቸኩላችሁ ደካማና ጠንካራ ጎኑን ሳታዩ ‘ሰዉን እኮ አጥንቶ መጨረስ አይቻልም’ በሚል ሸዋጅ መርፌ ተወግታችሁ እንዳታገቡ ተጠንቀቁ፡፡

•ከፍቅረኛችሁ ጋር ከተጣላችሁ 'ለብቻዬማ መኖር አልችልም' በሚል ሞኝነት ከጎናችሁ ያለዉን ሰዉ ማግባት ትልቅ ኪሳራ ነዉ፡፡

•ወንድ ልጅ የሚፈልጋትን ሴት እጁ እስኪያስገባ ድረስ በጣም አሪፍ መሆን ያውቅበታል፡፡ ይህን ስል ሁሉም ወንዶች አስመሳይ ናቸዉ ለማለት አይደለም፡፡ በጣም በሳል፣ የሚያስቡና መልካም ባሎች እንዳሉ ሁሉ እሾህና አሜከላ የሞላዉ አልጋ ሰርተዉ ከላይ በሚያምር አልጋ ልብስ የሚያነጥፉ አንጣፌዎች ሞልተዋል፡፡ ስለዚህ እነዚህን ከሩቁ መሰናበት፡፡

•በእጃችሁ ካለዉ የፍቅር ግንኙነት ጋር የጠበቀ ህይወት ይኑራችሁ፡፡ የማታዉቁትን የፍቅር ህይወት በየዋህነት መጀመሩ አደጋዉ ልክ እንደኔ የከፋ ነዉ፡፡

እህቴ ሁሉም ነገር ከእግዚአብሔር ሲሆን ነውና አስደሳች የሚሆነው፡፡ በአንቺ ብልጠትና እውቀት ተመስርተሽ ህይወትሽን ለመምራት አትሞክሪ፡፡

አንተ ደሞ ወንድሜ እሾኩ ማንነትክን ደብቀህ የመልካምነትን ጭምብል አጥልቀህ የምትጎዳቸው ሴቶች ያንተ እህቶች ቢሆኑስ? አየህ በእህትህ ፣ በልጅህ ላይ ሊሆን የማትፈልገውን ፀያፍ ተግባር በሌሎች ላይ አታድርገው፡፡

🙏ፈጣሪ ከእንደዚህ አይነቱ መከራ ይሰውረን🙏


ይህን ፅሁፍ አንብባችሁ ስትጨርሱ ከእንደዚህ አይነቱ ወጥመድ እንዲያመልጡ ለምትፈልጓቸው በሙሉ Share አርጉት፡፡

🙌መልካም ቀን ቸር ያውለን🙌

#via hulentenawi siket

@youthkiller
Channel photo updated
በኮቪድ-19 ህይወቱ ያለፈው የ30 ዓመቱ ጋዜጠኛ!

ዚምባቡዌ ውስጥ ሕይወቱን ያጣው የሰላሳ (30) ዓመቱ የብሮድካስት ጋዜጠኛ ዞሮሮ ማካምባ ይባላል። በኮሮና ቫይረስ ወጣት ሊሞት አይችልም ተብሎ የሚነገረውን ሐሰት ያደረገው ይኸው ሞት ዚምባቡዌያውያንን አስደንግጧል።

ጋዜጠኛው በአገሩ የታወቀ እንደነበር እና የሀብታም ቤተሰብ ልጅም እንደሆነ ተዘግቧል። ቅዳሜ በቫይረሱ እንደተጠቃ በምርመራ የተረጋገጠው ዞሮሮ የጤናው ሁኔታ በፍጥነት ስላሽቆለቆለ በአገሪቱ መዲና ሀራሬ በጽኑ ሕሙማን ማቆያ ገብቶ ነበር።

#BBC #ETV
@youthkiller
በኮቪድ-19 ምክንያት የሞተችው የ21 ዓመት ወጣት!

ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የጤና እክል ያልነበረባት የ21 ዓመቷ ወጣት በኮሮናቫይረስ ከተያዘች በኋላ መሞቷን ወላጆቿ ተናገሩ።

"ቫይረሱ ልጃችንን ነጠቀን" ያሉት ወላጆች፤ ሁሉም እራሱን ከቫይረሱ ለመጠበቅ የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ክሎይ ሚድልተን የተባለችው ወጣት ምንም አይነት የጤና እክል ሳይኖርባት በዩናይትድ ኪንግደም በቫይረሱ ከሞቱት መካከል አንዷ ነች ተብሏል።

የወጣቷ እናት ዲዓን በፌስቡክ ላይ "ይህን ቫይረስ እንደ ቀላል የምትገምቱት፤ እባካችሁ ዳግም አስቡበት። ከእራሴ ልምድ እንደተረዳሁት ይህ ቫይረስ የ21 ዓመት ሴት ልጄን ነጥቆኛል" ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@youthkiller
#ATTENTION

ዛሬ ሪፖርት ከተደረጉት ኬዞች ውስጥ ታማሚ 3 እና ታማሚ 4 የ28 ዓመት እንዲሁም የ24 ዓመት ወጣቶች ናቸው። ቫይረሱ ወጣቶችን አይዝም በሚል የተሳሳተ አመለካከት የራሳችሁን እንዲሁም የምትወዷቸውን ሰዎች ህይወት አደጋ ላይ እንዳትጥሉ፤ እራሳችሁን ጠብቁ!

እባካችሁ እንቅስቃሴ ቀንሱ፤ ተለመኑን!
@youthkiller
#BREAKING

ስፔን በ24 ሰዓት ውስጥ 769 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸውን ሪፖርት አድርጋለች። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 4,858 ደርሷል።

@youthkiller
ወጣቶች የጤና ባለሞያዎችን ምክር አዳምጡ!

በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ ሪፖርት ካደረገቻቸው ተጨማሪ 3 ኬዞች ውስጥ የ26 ዓመት ወጣት እና የ14 ዓመት ታዳጊ ይገኙበታል። አሁን ሩቅ ሀገር መሄድ አይጠበቅብንም ይህ ቫይረሱ እድሜ፣ ፆታ፣ቀለም፣ የኑሮ ደረጃ እንደማይለይ ማሳያ ነው።

ወጣቶች የጤና ባለሞያዎች የሚሉትን ምክር አዳምጡ ፣ አስፈላጊ ካልሆነ ከቤታችሁ አትውጡ ፤ የግድ ለመጠንቀቅ የሰው ህይወት ማለፍ አለበት ? ወይስ ብዙ ሺ ሰው መታመም አለበት ? እባካችሁ ለእራሳችሁና ለቤተሰባችሁ ጤና የምትባሉትን አድምጡ።

@youthkiller
👍 እስኪ በመጀመርያ 📺Contagion የተባለ ፊልም አስጭናቹሁ እዩት

❗️ከዛሬ 9 ዓመታት በፊት እ.አ.አ 2011 በእኛ አቆጣጠር 2003 ዓ/ም Contagion የተባለ ፊልም ይፋ ሆነ፡፡
ፊልሙ ሙሉ በሙሉ የሚያጠነጥነው አንድ ከየት እንደመጣ ባልታወቀ ቫይረስ ላይ ነው፡፡ የፊልሙ መቼት በቻይና፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ… ሲሆን የቫይረሱ መነሻ መቼት ደግሞ
ቻይና ነበር፡፡

📌ይህ ፊልም፣ አንዲት የምታስል እንስት ሴት በአውሮፕላን ወደ ቤቷ ታመራና ቤት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀጠቀጠች አረፋም እየደፈቀች ስትሞት ይጀምራል፡፡ በኋላ እንደምጠቅሰው፣ እንስቷ ከአንድ የአሳማ በላች ሼፍ ቫይረሱ ለመጀመርያ ጊዜ እንደያዛት እንመለከታለን፡፡ ቫይረሱም ከዛች የመጀመርያ ቀን ጀምሮ ሲነሣ እናያለን፡፡ ዋናው ዓላማዬ በዚህ ፊልም ስለ ቫይረሱ እንዴት እንደነገሩን ማሳየት ነውና ወደሱ እናምራ !

1. በፊልሙ ላይ ቫይረሱ ከቻይና እንደተነሳ ይታያል፡፡
የኮሮና ቫይረስ መነሻም ቻይና እንደሆነ ልብ በሉ፡፡

2. በፊልሙ ላይ ቫይረሱ የማሳል፣ የማስነጠስና የትኩሳት ባሕርይ እንዳለው ይታያል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ምልክትን ልብ በሉ፡፡

3. በፊልሙ ላይ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው የሚነካውን ማንኛውም ዕቃ ሌላ ሰው ቢነካ በቫይረሱ እንደሚጠቃ ያሳያል፡፡ የኮሮና ቫይረስ መተላለፊያን ልብ በሉ፡፡

4. በፊልሙ ላይ ቫይረሱ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ቫይረስ እንደሆነ ይታያል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ዋና ታርጌቱን ልብ በሉ፡፡

5. በፊልሙ ላይ ቫይረሱ በመተንፈሻ አካላት ላይ ካሉት Receptor ሴሎች ላይ ልክ እንደ ቁልፍ እንደሚሰካ ይታያል፡፡ የኮሮና ቫይረስን ተመሳሳይ ባሕርይ ልብ በሉ፡፡

6. በፊልሙ ላይ ቻይናዊያንን ወክሎ የምናየው አንድ ቻይናዊ ካራክተር ቫይረሱ በአሜሪካኖች ሆን ተብሎ እንደተለቀቀና የዓለም የጤና ድርጅትም ዐውቆ እንደደበቀው ሲናገር ይታያል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የቻይናና
የአሜሪካ ሰጣ ገባ ልብ በሉ፡፡

7. በፊልሙ ላይ በቫይረሱ ምክንያት ት/ቤቶች፣ የንግድ ሱቆች ሲዘጉ ይታያል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ያለውን ሁኔታ ልብ በሉ፡፡

8. በፊልሙ ላይ ቫይረሱ በተከሰተበት ጊዜ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጥቁር እንደነበረ ይታያል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የኮሮና ቫይረስ ሲከሰት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር
ጥቁር ያውም አፍሪካዊ ያውም ኢትዮጵያዊ መሆኑ አጋጣሚ ይመስልሃል?

9. በፊልሙ ላይ ቫይረሱ የተነሣው በአንድ ሌሊት አንድ ዛፍ በግሬንደር ሲቆረጥ የተበጠበጡት የሌሊት ወፎች መንቀሳቀስ ይጀምሩና አንድ ሙዝ መሰል ምግብን
በአፋቸው ቆርጠው ሲጥሉና ያንን ምግብም አንድ አሳማ ሲመገብ፣ ይህን አሳማ ደግሞ ቻይናዊው ሼፍ ቆራርጦ ለምግብ በማዘጋጀት ላይ እንዳለ የቫይረሱ መጀመሪያ ተጠቂ የሆነችው ካራክተር ሼፉን ሰላም ስትለው ቫይረሱ እንደተነሣ ይታያል፡፡ የኮሮና ቫይረስ አመጣጥም በሌሊት ወፍ ምክንያት ነው የሚለውን ተረት ተረት ልብ በል፡፡

10. በፊልሙ ላይ ቫይረሱን ለመከላከል ብቸኛ መፍትሔ ተደርጎ የቀረበው እጅን መታጠብ፣ አለመጨባበጥ፣ ፊትን አለመነካካትና ተነጥሎ መቆየት ነው፡፡ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ተደርጎ የተነገሩንን መንገዶች ልብ በሉ፡፡
ፊልሙ ወደፊት የሚመጣውን አስቀምጧል..!?

📌ሚስጥራ ብድኖቹ ብልህ ናቸው፡፡ ሊያደርጉ ያሰቡትን እያንዳንዱን ሴራ ቁልጭ አድርገው አስቀድመው በማሳየት አስተዋይ ሰዎችን በፍርሃት ብቻ የማሽመድመድ ሴራን ተክነውበታል፡፡

⚠️ ወደፊት ይምጣ አይምጣ የማይታወቁ
ጥቂት ነገሮችን ደግሞ እንዲህ አሳይተውናል....

1. በፊልሙ ላይ ከ26 ሚልየን በላይ ሕዝብ እንደሚያልቅ ይታያል፡፡

2. በፊልሙ ላይ ብዙ ሚልየን ሕዝብ ካለቀ በኋላ በአፍንጫ የሚወሰድ መድኃኒት እንደሚያገኙ ይታያል፡፡

3. በፊልሙ ላይ የተገኘው መድኃኒት ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ስለማይበቃ የሰዎችን የልደት ቀን በዕጣ በማውጣት ዕጣው የወጣላቸውን ብቻ መድኃኒቱን ሲያስወስዱ ይታያል፡፡

4. በፊልሙ ላይ ተገኘ የተባለው መድኃኒት ሕዝቡን ለተጨማሪ በሽታዎች የሚዳርግ እንደሆነ ጋዜጠኛ ሆኖ ከተወነው ካራክተር አፍ ሲወራ ይታያል፡፡
እነዚህ ገና ሊመጣ ያለውን ሊያሳዩ የሚችሉ ከሴራዊ ፊልማቸው የተወሰዱ ዐሳቦች ናቸው፡፡ ዕድሜ ከሰጠን ወደፊት እያስተያየን የምንታዘባቸው ይሆናል፡፡

⚠️በአጠቃላይ.. ሚስጢራዊ ቡድኖቹ Order Out of Chaos በሚባል መርሐቸው አንድን ሴራ መፈፀም ሲፈልጉ ያን ሴራ ከመፈፀማቸው በፊት በፊልማቸው ይነግሩናል፡፡ በዚህ ፊልም ያየነውም እሱን ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ያለውን ሁኔታ ቁልጭ አድርገው አሳይተውናል፡፡

⚠️ኮሮና ቫይረስ አንዳንዴ ከፈጣሪ የተላከ ቁጣ አንዳንዴም ከእንሳስት የመጣ በሽታ እንደሆነ ብዙዎቻችን እያመነታን እንከራከራለን፡፡ እውነታው ግን እርሱ አይደለም፡፡ ብዙ የዓለም ሕዝቦች ለሚገዙለት ለሰይጣናዊ መንፈስ ቃል የገቡት ሚስጢራዊ ቡድኖቹ ... እንዲህ አይነት ገዳይ በሽታዎችን ለመፈብረክ ከምድር በታች በተገነቡት ምሥጢራዊ የበሽታ መፈብረኪያ ፋብሪካዎቻቸው የዓለምን ሕዝብ የሚቀንሱ በሽታዎችን እያመረቱ ይገኛሉ፡፡

በአሁን ሰዓት የዓለም ሕዝብ ካያቸው በየትኛውም ዘመን ከተነሡ ችግሮች እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ቫይረስን ነው ያመረቱት፡፡
<<በችግር-እርምጃ-መፍትሔ በተባለ ዕቅዳቸው መሠረት አንድን ችግር ከፈጠሩ በኋላ፤ መፍትሔ ብለው ሕዝቡን በሚያሳምኑት ግን መፍትሔ ባልሆነ መንገድ
# ሌላ_ተያያዥ_ሴራ_ያክላሉ ፡፡>> በአሁኑ ሰዓት የሚታየውም ይህ ነው፡፡ ለኮሮና ቫይረስ መፍትሔ ብለው ያቀረቡዋቸው መንገዶች ከማኅበራዊነት ይልቅ በግላዊነት እንድናምን የሚያደርጉ፣ ብቸኝነትን እንድንለማመድና ከሀገራዊ ፍቅር የወጣን ራስ ወዳድ እንድንሆን የሚያደርጉ፣ ባሕሎችን በመሸርሸር ባሕል የለሽ እንድንሆን
የሚያደርጉ መንገዶች ናቸው፡፡ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ!!!

በክርስትና፣ ቤተክርስትያን የሚደረጉ ሥርዓቶችን፣ መስቀል መሳለም፣ ቅጥር መሳም… ወ.ዘ.ተ እንዲቀሩ በእስልምናም ተሰብስቦ መስገድ እንዲቀሩ የሚያደርግ
የመፍትሔ ዐሳቦችን ዘወትር በየሚድያው እየተነገሩ ነው፡፡

ይህ ብቻ አይደለም፡፡ መንፈሳዊ ሥርዓቶችን ቤት ቁጭ ብለን በቲቪ እንድንፈፅምም ሲነገር ተመልክተናል፡፡
እነዚህ ለጊዜው አሪፍ መፍትሔ የሚመስሉ፣ በረጅም ጊዜ ዕቅድ ግን እጅግ ተንኮል ያለባቸውን መፍትሔዎችን ዘወትር በሚድያዎቻቸው ሊያሳምኑን ይሞክራሉ፡፡
እውነታው ግን ይህ ነው፤ # እምነትና_ባሕል_የለሽ_ት
ውልድን_ መፍጠር፡፡ እውነታው ግን ይህ ነው፤ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን መሸርሸር፡፡ ከዚህ ሌላ እውነት የለም፡፡

ለማንኛውም መፍትሔዎቹን አትጠቀሙ አልልም፡፡ መጠንቀቅም መልካም ነው። ግን ሴራውን ተረዱ፣ ተገንዘቡ፡፡ ሴራውን መረዳት ብቻ ሳይሆን ተጠቀሙበት፡፡ ውጤቱ አሁን አይታይም፡፡ ምናልባት ከደረስን በልጆቻችን
እናየው ይሆናል እንጂ፡፡

"is that Corona virus biological weapon or Not
" ?
ለማንኛውም ይህን ፊልም ተመልከቱት


ስለ ኮሮና ቀድሞ የነገሩን ፊልሞች

1. My Secret Terrius 2008 Korean series TV Drama

2. Contagion 2011

3. Flu 2013 - Chaos ensues after a lethal, airborne virus infects the population of a South Korean city less than 20 kilometres from Seoul
. @youthkiller
🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ 🙏
የጣሊያኑ ዶክተር የጻፈውን ልብ የሚነካ ደብዳቤ እነሆ ላስነብባችሁ:-
ይህንን መልዕክት ለሁሉም አዳርሱ!

በሀገራችን ጣሊያን እጅግ አሳዛኝ ነገር እየኾነ ነው።በእድሜያቸው የገፉ ሕሙማን ከመሞታቸው በፊት በጉንጮቻቸውላይ እንባቸው ሲወርድ ይታያል። ከቀረባቸው አደጋ ሊያመልጡ የሚችሉበት ምንም ዕድል የላቸውም። ሆኖም እንዲሁ ዝም ብለው መሞት አልፈለጉም። በካሜራ ፊት "ደህና ሁኑ" በማለት ነው የሚሰናበቱት።

ሁሉም ጭንቀታቸውን እንደተሸከሙ ነው በጥበብ እያንቀላፉ ያሉት።አብዛኛውን ጊዜ ባልና ሚስት በአንድ ቀን ይሞታሉ። ቅድመ አያቶችና አያቶች ፤ በመጨረሻዋ ሰአት የልጅ ልጆቻቸውን መሰናበት አልቻሉም።

ይሕ በሽታ ከጉንፋን እጅግ የከፋ ነው። እመኑኝ። ይሕ ከጉንፋን እጅግ በጣም የተለየ ነው።እባካችሁ ኮሮና ቫይረስን-"ጉንፋን" እያላችሁ አትጥሩ።

ትኩሳቱ የሚቻል አይደለም። ህሙማኑ ጨርሶ መተንፈስ አይችሉም።ብዙዎቹ ኦክሲጅን እንዲያገኙ ቢደረግም፤ በቀላሉ መተንፈስ የሚታሰብ አይደለም።

በሽታውን ለማከም በጣም ጥቂት የመድሀኒት አይነቶችን ለመጠቀም እየሞከርን ቢሆንም፤ እሱም በህሙማኑ አቅምና ጥንካሬ የሚወሰን ነው።በተለይ በእድሜ የገፉ ህሙማን በሽታውን መቋቋም አልቻሉም።

አሁን እኛ ዶክተሮቹ እያለቀስን ነው።ነርሶቻችንም እያነቡ ነው። የሀዘናችን ምክንያት የብዙ ሰዎችን ህይወት መታደግ አለመቻላችን ነው።

የሰው ልጆች የህይወት ዑደት አይናችን ፊት ለፊት ሲያከትም እያዬን ነው።አሁን ይህን እየነገርኳችሁ እንኳ እጅግ በርካታ ህሙማን ወደ ሆስፒታላችን እየጎረፉ ነው።በአስቸኳይ አስተኝቶ ማከም የሚያስችሉ በርካታ ክፍሎች ያስፈልጉናል።አሁን የሁሉም ህመም አንድ ዓይነት ነው። የሳምባ ምች እና በጣም ጠንካራ የሳምባ ምች !( ጄነራል ኒሞኒያ እና ቬሪ ስትሮንግ ኒሞኒያ!)

የትኛው ጉንፋን እንዲህ እንደሚያደርግ ንገሩኛ!?

ይህ ወረርሽን በጣም ተላላፊ ነው። ይህ ቫይረስ ጠቅላላ የተለየ ነው።

በተለይ ለአንዳንድ ሰዎች እጅግ በጣም አደገኛ ነው። በኛ ሀገር 65 እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው አብዛኞቹ ሰዎች የስኳር ህሙማን ናቸው።የደም ግፊት አለባቸው። ለእነዚህና ለአንዳንድ ወጣቶች ህመሙ ከባድ ነው።

አንዳንድ ወጣት ህሙማንን ብታዩ- ማናችሁም ወጣቶች ስለዚህ ህመም ልትዘናጉ አትችሉም።

በአሁኑ ሰአት በሆስፒታላችን የቀዶ ጥገና አገልግሎት የለም፤ የማዋለጃ ክፍሎች ተዘግተዋል፤ የአይንና የቆዳ ህክምናም ቆሟል። የቀዶ ጥገና ክፍሎች በሙሉ፤ ወደ ድንገተኛ ህክምና መስጫ ክፍል ተቀይረዋል።

አሁን ሁሉም ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ውጊያ ላይ ነው። በእያንዳንዷ ሰዓት የህሙማን ቁጥር እያሻቀበ ነው።የህሙማኑ ወጤትም ያለማቋረጥ እየቀረበልን ነው።፡ሁሉም ፖዘቲቭ! ፖዘቲቭ!!ፖዘቲቭ!!!

አንድ ዓይነት ህሙማን።

የማይቻል ትኩሳት፣

የስቃይ ትንፋሽ

ሳል!

ድካም!

ሁሉም ሊባል በሚችል መልኩ በድንገተኛ ክፍል ህክምና እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ ነው። አንዳንዶቹ በኦክሲጅን እንኳ ታግዘው መተንፈስ አይችሉም።አሁን ኦክሲጅን ማሽን ከወርቅ በላይ ውድ ነው።

ይህ ሁሉ በምን ያህል ፍጥነት እየሆነ እንዳለ ማመን አልቻልኩም።

ቢሆንም ማናችንም ለመቆም አልፈለግንም። ሁሉም እስከ እኩለ ሌሊት እየሰራ ነው።ዶክተሮችም ልክ እንደ ነርሶች ሥራቸውን ቀጥለዋል።እኔም ለሁለት ሳምንታት ወደ ቤቴ አልሄድኩም።ምክንያቱም በእድሜ ለገፉ የቤተሰብ አባሎቼ እፈራለሁ።ልጆቼን እየደወልኩ በካሜራ ነው የማዋራቸው።አንዳንዴ የሚስቴን ምስል ሳይ አለቅሳለሁ።እኛኮ ምንም ጥፋት አልፈጸምንም።

ይህ ህመም አደገኛ እንዳልሆነ ያስወሩት ሁሉ ጥፋተኞች ናቸው። ምክንያቱም "ይህ ህመም ልክ እንደ ጉንፋን ነው" ብለው ነገሩን። እኛም ምንም የጥንቃቄ እርምጃ ሳንወስድ ቆዬን።አሁን በጣም ረፈደብን።

እባካችሁ ከቤት አትውጡ! የምንላችሁን ስሙን!ድንገተኛና አስቸጋሪ ህመም ካላጋጠማችሁ በስተቀር ከቤት አትውጡ! የፊት ጭምብል አድርጉ። የባለሙያዎችን ምክር ስሙ።

የኛ የጤና ሁኔታ ራሱ በጭምብል እጥረት ለአደጋ ተጋልጧል።አንዳንድ ሐኪሞች በቫይረሱ ተይዘዋል።የአብዛኞቹ የቤተሰቦቻቸው አባላት በሞት እና በህይወት መካከል ናቸው።ስለዚህ ራሳችሁን ለማዳን ከወዲሁ ጥረት አድርጉ።በእድሜ የገፉ ቤተሰቦቻችሁም ወደ ውጭ አይውጡ።

እኛ ግን በሙያችን ምክንያት በቤታችን መቆየት አንችልም።እስከ መጨረሻዋ ሰዓት ድረስ የታማሚዎቻችንን ሕይወት ለማዳን እንታገላለን።

እንዳ'ለመታደል ሆኖ ከብዙ ድካም በኋላ ወደ ቤታችን እንሂድ ብንልም በሽታውን ይዘን ነው በተሰበረ ልብ የምንሄደው።

አውቃለሁ። ነገ ጧት ሁሉም ነገር መልካም ሲሆን- ሁሉም ይረሳናል። ምክንያቱም ይህ የሕክምና ሙያ ባህርይ ነው። ለዚህ ነው ራሳችንን ሰጥተን የሰዎችን ህይወት ለማዳን የምንታገለው።

እናም እስካሁን በበሽታው ያልተያዛችሁ ብትሆኑም ፤ ህዝብ ከሚበዛበት ቦታ ራሳችሁን አርቁ።ወደ ፊልም ቤቶች፣ወደ ሙዚየሞችና ወደ መጫዎቻ ሜዳዎች አትሂዱ።ቢያንስ በእድሜ ለገፉ ቤተሰቦቻችሁ አስቡላቸው።አሁን የነሱ ህይወት በእናንተ እጅ ላይ ነው።እናንተ ከተጠነቀቃችሁ፤ እኛ ከምንታደጋቸው ነፍሳት በላይ ብዙዎችን ታድናላችሁ። አሁን እነሱን ልትታደጉ የምትችሉት እናንተ ብቻ ናችሁ።

ይህንን መልዕክት ለሁሉም አዳርሱ፦

(ዶክተር ዳኒየሌ ማቺኒ ከጋቫትሴኒ ሆስፒታል)

 ጌታ ሆይ ለምድሪቷ ምህረትነ አውርድ
ይቅር በለን.....
አሜን .....አሜን......... አሜን ..

''ቸረ ያሰማን''

እባካችሁን ሼር አድርጉት ሰዎች ሁሉ ይስሙ
@youthkiller
​​ልብ ብለው ያንብቡት

«ራሳችንን የምናይበት አስገራሚ ታሪክ»
አንዲት ወጣት ሴት ለጉዞ ኤርፖርት ውስጥ ተቀምጣለች። አውሮፕላኑ እንደሚዘገይ
ባወቀች ጊዜ ኤርፓርት ውስጥ ካሉት ሱቆች ኩኪስና መጽሐፍ ገዛች።

ወደ VIP (የተመረጡ ሰዎች ብቻ ወደ የሚስተናገዱበት) ክፍል ገብታ ለንባብ ምቹ ወደጠሆነው መደገፊያ ወንበር አመራች።
ተደላድላ ተቀምጣ ማንበብ ጀመረች።

አጠገቧ እንድ ሰው መጽሐፍ ያነባል። በሁለት መደገፊያ ወንበሮች መሐል ኩኪስ
ተቀምጧል።

በንባቧ መካከል መተከዢያ ሆኗታል። ታዲያ ከኩኪሷ አንድ ስታነሳ ሰውየውም አንድ አነሳ
ገረማት። ሳያስፈቅዳት መውሰዱ አስደነቃት። ግን ዝም አለች። ቀጥላ እርሷ አንድ ስትወስድ እርሱም ሌላ ወሰደ አሁን ተበሳጨች። ድፍረቱ አናደዳት።

በዚህ አላበቃም እስከ መጨረሻው ቀጠለ። ቅጥል አለች! ግን ንቃ ተወችው። በአካባቢው ያሉ ሰዎችን አትኩሮት መሳብ አልፈለገችም።
ለዚህ ብቻ አይደለም በኩኪስ ምክንያት
ጸብ ረብሻ መፍጠር አልፈለገችም።እንዲህ
እንዲህ እያለ የመጨረሻ አንድ ኩኪስ ቀረች። " ይሄ የተረገመሰው ምን ያደርግ ይሆን? "
ስትል አሰበችና በቀስታ ማየት ጀመረች።

ከዚያም ሰውየው ኩኪሷን ሁለት ቦታ ከፈላትና ግማሹን ወሰደ። ለድፍረቱ ጥግ አጣችለት። ከልክ ያለፈ ስርዓት የለሽ እንደሆነ
ደመደመች።ሰዓቱ ደርሶ አውሮፕላን ላይ እንደተሳፈረች መነጽር ለማውጣት ቦርሳዋን
ስትከፍት አይኗን ማመን አልቻለችም። ያልተከፈተው የታሸገው ኩኪሷ ቦርሳዋ ውስጥአለ።

በጣም አፈረች ተሸማቀቀች። ለካስ የራስዋን ኩኪስ ቦርሳዋ ውስጥ ረስታ
የሰውየውን ነበር ስትበላ የቆየችው። ከሁሉም በላይ በጣም ያጸጸታት ሰውየው እስከ መጨረሻው አንዲት ኩኪስ እስክትቀር ድረስ ያካፍላት የነበረው ምንም ሳይቆጣና
ሳይመረር በደስታ መሆኑ ነበር።

የራሱን ኩኪስ እየበላች በሰውየው ላይ ስትበሳጭበት በመቆየቷ እጅግ አፈረች። አሁን ይቅርታ ለመጠየቅ እንኳን ጊዜው አልፏል። እርሱም በሌላ አውሮፕላን ወደ ሐገሩ አቅንቷል። እርሱን የማግኘት አንድ ተጨማሪ እድል እንኳን የላትም። ብዙ ተመኘች ማመስገን፣ ይቅርታ መጠየቅ፣ ጉዳዩን ማብራራት፣ .....
ግን ሁሉም እሷው ጋ ቀሩ አልፏል።

አራት የማይጠገኑ ነገሮችን አሰበች፦
1. ድንጋይ ከተወረወረ በኋላ
2. ቃላት ከተናገርናቸው በኋላ
3. ድርጊቶች ካመለጡን በኋላ
4. ጊዜ ካለፈ በኋላዋጋ እንደሌለውእኛም

ምንም ነገር ከመናገራችን ከመፈፀማችን በፊት መጀመሪያ ራሳችንን እንይ
ዛሬ ልናመሰግናቸው ዋጋ ልንሰጣቸው ልናከብራቸው የሚገባን ወዳጆቻችን የትዳር
አጋሮቻችንን ጀግኖቻችን ጊዜው ሳያልፍ እናመስግናቸው። ጊዜ ካለፈ በኋላ እድሉ አይገኝምና ዋጋ የለውም።

የውጭ ምንዛሪ ዋጋ የሚመነዘረው በወቅቱ በቀኑ በተሰጠው የምንዛሬ ዋጋ ብቻ ነው።
በትናንት የምንዛሪ ዋጋ ዛሬ መመንዘር አይቻልም።

ስለዚህ ዋጋ reward መስጠት
ያለብን መስጠት ያለብን ቀን ሲሆን ደስ ይላል ካለፈ በኋላ ግን ሁሉም ነገር በነበረበት
አይቀጥልምና ደስ አይልም። ለዚህ አይደል በሕጉ ዓለም " የዘገየ ፍርድ እንደተነፈገ
ይቆጠራል።

የሚባለው«አስተዋይ ልብ መልካምነትን ይመራል»
@youthkiller
በአዋጅ የተከለከሉ

1. ለሀይማኖታዊ ወይም ማህበራዊ አላማ፣ ለመንግስታዊ ወይም ፖለቲካዊ ስራ ወይም ሌላ መሰል አላማ አምልኮ በሚደረግባቸው ቦታዎች፣ በመንግስት ተቋማት፣ በሆቴሎች፣ በማናቸውም የመሰብሰቢያ አዳራሾችና በማናቸውም ቦታ አራትና ከዚያ በላይ ሆኖ በአንድ ቦታ ላይ መገኘት የተከለከለ ነው፤  

2. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አስገዳጅ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ወይም በኮሚቴው የሚቋቋሙና ውክልና የሚሰጣቸው በክልሎች፣ በከተማና በወረዳ ደረጃ ባሉ ንዑሳን ኮሚቴዎች ስብሰባ እንዲደረግ ሊፈቅድ ይችላል፡፡ 

3.  ማንኛውም ሰው ለሰላምታና ሌላ ማንኛውም አላማ በእጅ መጨባበጥ ክልክል ነው፣

4. ማንኛውም ሀገር-አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው በማንኛውም ጊዜ ከተሸከርካሪው ወንበር ብዛት 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤  

5. ማናቸውም የከተማ ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ታክሲ፣ አውቶቡስ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ ከተሸከርካሪው የወንበር ቁጥር 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤ 

6. ማንኛውም የግል ተሸከርካሪ ሾፌሩን ሳይጨምር ከተሸከርካሪው የወንበር ቁጥር 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤

7.  የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከዚህ በፊት ሲጭን ከነበረው አቅሙ 25% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤ 

8.  የኢትዮ-ጂቡቲ የምድር ባቡር ከወንበር ቁጥሩ 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ ተከለከለ ነው፤ 

9.  ማንኛውንም ታራሚን ወይም ተጠርጣሪን በአካል በመገኘት በማረሚያ ቤት ወይም ፖሊስ ጣቢያ መጠየቅ ክልክል ነው፤ ሆኖም ይህ ድንጋጌ በፖሊስ ጣቢያ ለሚገኝ ተጠርጣሪ፣ ከተጠርጣሪው ጋር በአካል ሳይገናኙ ስንቅ ማድረስን አይከለክልም፤ 

10. በጭፈራ ቤቶችና በመጠጥ ቤቶች ማናቸውንም የመጠጥና መዝናኛ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው፤

11. በማናቸውም ቦታ የሺሻ ማስጨስና ጫት ማስቃም አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው፤ 

12. የሲኒማ፣ ቲያትርና በአንድ ቦታ ብዙ ሰዎችን የሚያሰባስቡ መሰል የመዝናኛ አገልግሎቶችን መስጠት ክልክል ነው፣

13. ሆቴሎች፣ ካፌዎች ወይም ምግብ ቤቶች አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜ በአንድ ጠረጴዛ ላይ ከሶስት ሰው በላይ እንዲቀመጥ ማድረግ የተከለከለ ሲሆን ተገልጋዮች በሚቀመጡባቸው ጠረጴዛዎቹ መካከል ያለው ርቀትም ሁለት የአዋቂ እርምጃ መሆን አለበት፤ ሆኖም ተገልጋዮች የሚገለገሉት በጠረጴዛ ላይ ካልሆነ በመካከላቸው የሚኖረው ርቀት ሁለት የአዋቂ እርምጃ መሆን አለበት፤በድንበር አካባቢዎች በሚገኙ ኬላዎች በኩል ወደ ሀገር ውስጥ መግባትም ሆነ ወደ ውጪ መውጣት የተከለከለ ነው፣

14. .በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 11 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ በውጪ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በኬላዎች በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል፤ 

15. ለዚሁ አላማ ከተቋቋመው ኮሚቴ ወይም በተመሳሳይ መልኩ በክልሎች ደረጃ በሚቋቋሙ ንዑስ ኮሚቴዎች ወይም ተመሳሳይ አደረጃጀቶች አማካኝነት ፈቃድ ከተሰጠው ሰው ውጪ በማንኛውም የክልልም ሆነ የፌዴራል መንግስት ባለስልጣን ወይም ባለሙያ ኮቪድ-19ኝን በተመለከተ የፌዴራል ወይም የክልል መንግስትን ወክሎ መግለጫ መስጠት የተከለከለ ነው፣

16. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 11 የተመለከተው ክልከላ ቫይረሱን አስመልክቶ የወጡ ህጎችን በተመለከተ የሚደረግ የሙያ ትንተናን ወይም በህክምና ባለሙያዎች የሚደረጉ ማብራሪያዎችን ወይም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በየእለቱ የሚሰጡ መረጃዎችን አይመለከትም፤ 

17. ማንኛውም የመኖሪያም ሆነ የንግድ ድርጅት ቤት አከራዮች በተከራዩ ስምምነት ካልሆነ በስተቀር ቤቱን እንዲለቅ ማድረግ ወይም የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ ነው፤ 

18. ማናቸውም በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚተዳደሩ ሰራተኞችን የሚያስተዳደሩ የግል ድርጅቶች በስራቸው ያሉ ሰራተኞችን የስራ ውል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚያስቀምጠው ስርአት ውጪ ማቋረጥ የተከለከለ ነው፣ 

19. ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ተቋም በትምህርት ቤት ወይም በሌላ ማናቸውም ቦታ አስተማሪና ተማሪዎች በአካል ተገናኝተው መማር ማስተማር ስራ እንዲሰራ ማድረግ ወይም ማስተማር የተከለከለ ነው፤ 

20. ማንኛውም ሁለትና ከዚያ በላይ ሰው በመሆን የሚጫወቱባቸውን ጨዋታዎች፣ ማጫወትም ሆነ መጫወት የተከለከለ ነው፤ 

21. ማናቸውንም የስፖርት ውድድሮች ወይም የቡድን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የተከለከለ ነው፤

22. የህፃናት ማጫዎቻ ቦታዎች አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው፣ 

23. ማንኛውም ሰው የባንክ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች፣ በገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ በሱቆች፣ በመድሀኒት መሸጫ አካባቢዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች ከሁለት የአዋቂ እርምጃዎ በታች በሆነ ርቀት መቆምም ሆነ መቀመጥ የተከለከለ ነው፡፡ 

24. መሰረታዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት እንደ መብራት ሀይል፣ ከውሃ አቅርቦት ጋር ግንኙነት ያለው ስራ የሚሰሩ ተቋማት ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የህክምና ተቋማት፣ ባንኮች፣ ከምግብ አቅርቦት ጋር ግንኙት ያለው ስራ የሚሰሩ ተቋማት፣ የጽዳት ስራዋችን የሚሰሩ ተቋማትና ባለሙያዎች፣ ከድንገተኛ ና የእሳት አደጋ መከላከል ጋር የተያያዙ ስራዎችን የሚሰሩ ተቋማት፣ ከጥበቃና ደህንነት ጋር የተያያዙ ድርጅቶች እና ተቋማት በማንኛውም መልኩ ስራን አለመስራተ ማቋረጥ ማስተጓጎል እና መሰል ተግባራትን መፈጸም የተከለከለ ነው፤ 

25. የደረቅና የፈሳሽ ጭነት አገልግሎትን፣ የምርት ስራን፣ የእርሻ ስራን ወይም የግንባታ ስራን ማቋረጥ፣ ማሰተጓጎል ወይም አለመስራት የተከለከለ ነው፣ 

26. ኮቪድ-19ኝና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ማህበረሰቡ እንዳይረጋጋ የሚያደርግና በማህበረሰቡ ላይ ስነ-ልቦናዊ ጫና የሚፈጥር ማናቸውንም መረጃ ማሰራጨት የተከለከለ ነው፡፡

@youthkiller
​የተቀማ አዕምሮ የጠፋ አዕምሮ ነው!
(እ.ብ.ይ.)

ብዙዎቻችን አዕምሮዋችንን ተቀምተናል፡፡ የተቀማነው በምንወዳቸው ሰዎች፣ በምንደግፋቸው ቡድኖች፣ አዋቂ ናቸው ብለን በተማመንባቸው ምሁሮች፣ ወዘተ አዕምሯችንን አሳልፈን ሠጥተናል፡፡ አዕምሯችንን የቀሙት ሰዎችን ወይም ነገሮችን ለመክሰስ ሞራሉም ሆነ መብቱ የለንም፡፡ አሳልፈን የሠጠነው ራሳችን እስከሆንን ድረስ ተጠያቂዎቹም ራሳችን ነን፡፡ አዕምሯችን የጠፋው ተቀምተን ነው፤ ስነምግባራችን ያሽቆለቆለው ልቦናችን ተሠልቦ ነው፡፡ የጠፋ አዕምሮ የተቀማ አዕምሮ ነው፡፡ የተቀማ አዕምሮ ደግሞ የተቀማ ሕይወት ነው፡፡

ለምንወደው ሰው ሙሉ በሙሉ አዕምሯችንን ሳይሆን ትኩረታችንን ነው መስጠት ያለብን፡፡ አዕምሯችን ለራሳችን በራሳችን መቆም እንዲችልና በማንም በምንም ወጀብ እንዳይጠለፍና እንዳይቀማ የማድረጉን አቅም ካልገነባን የመጣው ሲያመጣው፣ የቆመው ሲያቆመው፣ የሄደው ሲወስደው እንዲሁ በሌላ ሰው ጭንቅላት የሚንቀሳቀስ የሌላ ሰው ሪሞት ይሆናል፡፡ በራሱ ግንዛቤ፣ አቅምና ማስተዋል ሳይኖረው የሌሎች አጨብጫቢና አጋፋሪ ሆኖ ይቀራል፡፡ ለሰራ ማጨብጨብ ደግ ነገር ነው፤ ላልገባን ሁሉ ሌላው ስላጨበጨበለት ብቻ ማጨብጨብ ግን አዕምሮ አልባነት፣ ሕሊና ቢስነት ነው፡፡

አንዳንዶች አእምሯቸውን የሌሎች መጫሚያ አድርገውታል፡፡ ሁሉም እየረገጠው በሄዱበት የሚሄድ፣ በከነፉበት የሚከንፍ ይሆናል፡፡ አዕምሮው የተቀማ ሰው ወይ አራጋቢ ወይ ደግሞ የአንዱ ፅንፍ አጥቂ ወይም ተከላካይ ተጫዋጭ እንጂ እንደመሃል ዳኞ ሆኖ ነገሮችን በራሱ ሃሳብና ማስተዋል አይበይንም፡፡ በሕይወቱ ሜዳ ላይ ፊሽካው የሚነፋው በሌሎች ዓይንና ጆሮ እንጂ በራሱ ዓይን፣ ጆሮና አዕምሮ ተመርምሮ አይደለም፡፡ መንጋው ስለተንጋጋበት አብሮ ይንጋጋል፤ የሚደግፈው ቡድን ስለጮኸ አብሮ ይጮሃል፡፡ በራሱ ፍርድና ብያኔ አንዲት እርምጃ አይጓዝም፡፡ አዕምሮውን የሌሎች ተከታይ እንዲሆን እንጂ ራሱን እንዲከተል አድርጎ አልሠራውም፡፡ በእርግጥ በጎ የሠሩትን በምግባር መከተል መልካም ነው፤ ከሌሎች ጥበብና እውቀት መቅሰም ታላቅ ልምድ ነው፡፡ ነገር ግን ሌሎችን ሁሌ ተከታይ ሆኖ መኖር ለምንከተላቸው ሰዎችም ሆነ ቡድኖች አዕምሮን አሳልፎ መስጠት ነው፡፡

አብዛኞቻችን በምናውቀው ትንሽዋ ነገር እንኳን ጥልቀት የለንም፡፡ ብዙዎቻችን በጅምላ ድምዳሜ ጠፍተናል፤ አስተዋይነት ይጎድለናል፡፡ መካከለኝነት ይከብደናል፡፡ ሌሎች በሃሳብ ስለተለዩን ብቻ ጠላት እናደርጋቸዋለን፡፡ ሃሳቡንና ሰውየውን መለየት አልለመድንም፡፡ የተለየ ሃሳብ የሚያነሱ ሰዎች አዲስ አተያይና ግንዛቤ እየሰጡን እንደሆነ አንረዳም፡፡ የተራራቁ ጽንፎችን ለማስታረቅ የሚችል አቅምን አልገነባንም፡፡ ለመጣላትና ለመጥላት እንጂ ለመታረቅና መልሶ ለመውደድ ልምድ አላጎለበትንም፡፡ ለግጭት ትንሽ ይበቃናል፤ ለድምዳሜ ቅንጣት ማስረጃ አያሻንም፡፡ ለመክሰስ አንደኞች ነን፡፡ ሌላው ላይ ለመጠቆም ሠከንድ አናባክንም፡፡ የሚገርመው ግን ለምን፣ እንዴት፣ ምን ብሎ ለመጠየቅ ግን ኋለኞችና አርፋጆች ነን፡፡ በዚህ ጉዳይ የተጠቃነው ያውቃሉ ከምንላቸው ሰዎች አንስቶ እስከተራው ማሕበረሰብ ድረስ ጠፍተንበታል፡፡ ይሄ የጽንፈኝነትና የጅምላ ደምዳሚነት ወረርሺኝ በእኛ ላይ የተራባው አዕምሯችንን በሌሎች ብናስቀማ አይደለምን? አስተዋይነታችን የጠፋው አዕምሯችን ቢጠፋ አይደለምን??????

ጂሚ ዲን የተባለ ፀሐፊ እንዲህ ይለናል፡-

‹‹የነፋሱን አቅጣጫ መለወጥ አልችልም፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜም የምፈልገው ቦታ ለመድረስ እንደንፋሱ ሁኔታ የጀልባ ጉዞዬን አስተካክላለሁ፡፡›› ("I can't change the direction of the wind, but I can adjust my sails to always reach my destination.")

አዎ! የመጣው ወጀብ እንዳይወስደኝ ወጀቡን በብርቱ አዕምሮዬ እቆጣጠረዋለሁ፡፡ አዕምሮዬ ውስጥ የሚገባውን ወጀብ ሃሳብ መግባቱን ማቆም ባልችልም ሃሳብ ፈጥሬና አብስልስዬ እገራዋለሁ፡፡ እንዳያጠፋኝ ስርዓት አሲይዘዋለሁ፡፡ ጎርፍን መከላከል የሚቻለው ዝናብ እንዳይዘንብ በማድረግ ሳይሆን መሄጃ መንገዱን በመቀየስ ብቻ ነው፡፡ አዕምሮውን የተቀማ ሰው ልክ የጎርፉን መንገድ ማስቀየስ የማይችልን ገበሬ ይመስላል፡፡ አዕምሮውን ያልተቀማ ሰው ግን ደራሹን ሃሳብ መንገድ ይሠጠዋል እንጂ በጎርፉ አይወሰድም፡፡ በጎርፉ አይጎርፍም፤ በወጀቡ አይወጀብም፡፡ ለእንግዳ ሃሳብ አይደነግጥም፡፡ ሃሳቡን ይመዝናል እንጂ አይጠለፍበትም፡፡

ወዳጄ ሆይ.. አዕምሮህ እንዳይጠፋ የምትወደውን በልኩ ውደድ! ሕሊናህ እንዳይሠረቅ የምትደግፋቸው ሠዎችንም ሆነ ቡድኖችን በምክንያት አድርገው፡፡ አዕምሮህን አሳልፈህ አትስጥ፡፡ አዕምሮውን የሠጠ ሕይወቱ በሌላ ሠው እጅ ነው፡፡ ያንተን ሕይወት አንተ እንጂ ሌሎች እንዲኖሩብህ አትፍቀድ፡፡ አዕምሮህን ጠብቅ! ሕሊናህን ግዛ የዛሬው መልዕክት ነው!

የተቀማ አዕምሮ የጠፋ አዕምሮ ነው!!
የጠፋ አዕምሮ የባከነ ሕይወት ነው!!

ሼር በማድረግ ሌላውን እናስተምር

Join👇
@youthkiller........ via nuenanibib
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን......... በአብይ ሀይልወስልጣን.........አሰሮ ለሰይጣን...............ወአግአዞ ለአዳም.......ሰላም..... እምዜሰ.... ኮነ ፍስሀ ወሰላም ......... ............... እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታች ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በአል በሰላም በጤና አደረሳችሁ በአሉን እቤት በመሆን በመጠን በመመገብ ርቀታችንን በመጠበቅ በደስታ አካባቢያችን ላሉ አቅመ ደካሞች በማካፈል እናክብር..........#stay home please ... @youthkiller
አንድ ሀብታም ሰው በመስኮቱን ተመለከተና አንድ ድሃ ሰው አንድ ነገር ከቆሻሻ መጣያው ውስጥ ሲመርጥ አየ ...እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ ድሀ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ድሃው ሰው ዘወር ብሎ ተመለከተና ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ ሰው አየ ... እርሱም እንዲህ አለ "ተመስገን አምላኬ እንኳን እንደዚህ ሰዉዬ አልሆንኩ አለ"።
:
ራቁቱን በጎዳና የሚራመድ ሰውየ ወደ ፊት ተመለከተ እና አንድ አምቡላንስ አየ አምቡላሱን ላይ በሕመም ምክንያት የሚሰቃይና የሚያለቅስ በሽተኛ አየ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ በሽተኛ እንኳ አልሆንኩ አለ"።
:
ከዚያም የታመመው ሰውየ ሆስፒታል ሲደርስ የሞተን ሰው ተመለከተ ... እርሱም እንዲህ አለ " ተመስገን አምላኬ እንኳ አልሞትኩኝ ምክንያቱም የሞተ ሰው ፈጣሪን አያመሰግንምና አለ"።
:
ዛሬ ስለ ሁሉም የፈጣሪን በረከቶች እና ምሕረት ለምን አናመሰግንም? ከሌለን ነገር እኮ ያለን በእጅጉ ይበልጣል ፡፡
:
* # ሕይወት * # ምንድን_ነው ?
ህይወት በተሻለ መንገድ ለመረዳት ወደ 3 ቦታዎች መሄድ አለብህ:
* 1. መቃበር *
* 2. ሆስፒታል *
* 3. እስር ቤት *
:
በመቃብር ቦታ ሕይወት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ትገነዘባለህ።
:
በሆስፒታሉ ውስጥ ከጤና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ ትገነዘባለህ።
:
በእስር ቤት ነፃነት በጣም ውድ ነገር እንደሆነ ትገነዘባለህ።
:
የዛሬ የምንሄደው መንገድ የነገ የሕይወታችን መሰረት ነው።

ስለዚህ ትሁት እና አመስጋኝ እንሁን። ስንት ቤተሰቦቻችን ፣ ጓደኞቻችን ዛሬ በሕይወት የሉም እኛ ግን በፈጣሪ ፈቃድ ጊዜያችንን እየጠበቅን በሕይወት መቆየት ችለናል ፡፡ ከሞትን በኀላ ደግሞ በዚህች አለም በሰወች ዘንድ የሚቀርልን ትዉስታ ስራችን ከተጨመረ ደግሞ ፎቶአችን ነዉ ፡፡ ስለዚህ ለሰዋች ደግሞ ሁል ጊዜ መልካም ነገር ሰሪ እንሁን ፡፡ በተጨማሪ ሁሌ አመስጋኝ እንሁን ሌላዉ ቢቀር ይህን ፅሁፍ በማንበባችን አምላክን እናመስግን ምክንያቱም ብዙ ሰዋች
1.ማንበብ ስለማይችሉ አያነቡትም
2.ይህን መልዕክት ስላልደረሳቸዉ አያነቡትም
ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪያችን የተመሰገነ ይሁን።

#Share if you really like it
Via psychoet...... @youthkiller
ያወቅነው ግን ያላወቅነው!
(Samuel Geda)
- አንድ ሰው ከብዙ ዓመታት በኋላ ከቀድሞ የትምህርት ቤት ጓደኛው ጋር በመንገድ ይገጣጠማል፣ ለማመን እስኪያዳግተው ድረስ ጓደኛው አዲስና የቅርብ ሞዴል የሆነች መኪና እንደያዘ ይመለከታል። ታዲያ ወደቤት ሲመለስ ፊቱ በሃዘን ተሞልቶ ይተክዝና ያዝን ጀመር። እርሱ ወደ ኋላ እንደቀረ/እንደከሰረ አስቧልና። ይሁንና ያላወቀው ነገር ቢኖር፥ ጓደኛው የመኪና ሾፌር ሲሆን፣ ለመስክ ሥራ በአለቃው መኪና መላኩን ነው።
*
- ሮዛ ሁልጊዜም ፍቅር አትሰጠኝም/አታቀማጥለኝም/ በሚል ሰበብ ከባለቤቷ ጋር ትጋጫለች። ይኸውም፤ በመኪና ካደረሳት በኋላ እንደጓደኛዋ ሄለን ባል ከመኪና ወርዶ፡ ዞሮ፡ በር ከፍቶ እርሷን አለማውረዱን እንደምክንያት ታነሳለች። ሮዝ ያላወቀችው ነገር፡ የነሄለን መኪና፡ የፊት በሩ ላይ ብልሽት ስላለው ከውጪ ካልሆነ በስተቀር ከውስጥ መከፈት አለመቻሉን ነው።
*
- አንዲት ሴት ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ፣ የብዙ አመት ጓደኛዋን ልትጎበኝ በሄደችበት፡ ሶስት የሚያማምሩና ለዓይን የሚያሳሱ ልጆች ሲቦርቁ ዐይታ ስሜቷ ይረበሻል። የመጀመሪያ ልጇን ከወለደች በኋላ ለረጅም አመታት ሌላ ልጅ ለማርገዝ ብትጥርም ሳይሳካ /እየጨነገፈ/ ቀርቷልና። ይሁን እንጂ ያላወቀችው ነገር፡ የጓደኛዋ ልጅ በካንሰር በመያዙ መኖር የሚችለው ለአንድ አመት ብቻ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁለቱ ልጆች ደግሞ የማደጎ ልጆች ናቸው።
* * *
ህይወት ሁሉንም አንድ ዓይነት በሆነ መንገድ የምታስተናግድ መድረክ አይደለችም። ካወቅነው ይልቅ የማናውቀው ብዙ ነው። ዐይነቱና መጠኑ ይለያይ እንጂ ሁሉም ሰው የራሱ ጉድለት አለው። ይሁንና ደስታ የምርጫ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ሰው ግን በህይወቱ ደስተኛ አይደለም።
ይኸውልህ፤ ኤሊ ምን ዓይነት ሸክም እንደተሸከመች ካወቅክ ለምን በጥንቃቄ እንደምትራመድ አትጠይቅም። ከሚታየው ምቾት ባሻገር የማይታዩ ብዙ ሸክሞች፣ ከሚማርኩ ፈገግታዎች ጀርባ ብዙ የልብ ቁስልና ህመሞች እንዳሉ እወቅ። ከሩቅ ያማረ ኑሮ ሁሉ የስኬት ምልክት፣ ከውጭ የሚታይ አንጸባራቂ ነገር ሁሉ ወርቅ አይደለምና። ስለዚህ ያወቅነው 'ደስታውን' ሲሆን ያላወቅነው ደግሞ 'ጉድለቱን/ችግሩንና ድካሙን/' ነው።
"ለምን እኔ ብቻ?" እያልክ ትጠይቅ ይሆን?
እኩዮቼ አግብተዋል።
እኩዮቼ ልጆች አፍርተዋል።
እኩዮቼ ጥሩ ሥራ ይዘዋል።
እኩዮቼ ስኬት ተጎናጽፈዋል።
እኩዮቼ ውድ ቤትና መኪና አሏቸው።
እኩዮቼ በማኅበረሰቡ የተከበሩ ናቸው።
እኩዮቼ እንዲህ ናቸው፤ እንዲያ ናቸው...!!!
ትክክል ብለሃል። ይሁንና ይህንን ጨርሰህ መርሳትህ ያሳፍራል...
እኩዮችህ ሆነው በህይወት የሌሉትን።
እኩዮችህ ሆነው በህመም የሚሰቃዩትን።
እኩዮችህ ሆነው በአእምሮ መታወክ በማህበረሰቡ እንደ እብድ የተቆጠሩትን።
እኩዮችህ ሆነው መንገድ ዳር የሚያድሩትን።
እኩዮችህ ሆነው ወላጅ አልባ የሆኑትን።
እኩዮችህ ሆነው የለት ጉርስ ያጡትን።
እኩዮችህ ሆነው አንተ የምትኖረውን ኑሮ የሚናፍቁና ባንተ ህይወት የሚቀኑ መሰል የሰው ዘርን...ረስተሃል።
ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይንም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል፡ ይሁን እንጂ ከብዙዎች በላይ ደስተኛ ነህ። ስለዚህም ፈጣሪህን ባለህ ነገር አመስግን።
አንተ ለብቻህ የሆነብህ ነገር የለም። አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' መስሎህ ነው። ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፣ የራስህንም አታቃል። ያወቅክ የመሰለህ ያላወቅኸው ብዙ አለና። ስለዚህ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን ደስታን ምርጫህ አድርግ። ሰላምንም ውደዳት። ሁልጊዜም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!
ሰናይ ጊዜ
❗️‼️🤢ለጥንቃቄ 🚸

❗️በቴሌግራም Bitcoin የሚባል ነገር አትሞክሩ | ሰዓታችሁን አታባክኑ
❗️Telegram እና Facebook አካውንት በቀላሉ Hack አይደረግም
❗️Final Corrupt ያደረገ ሚሞሪ አይስተካከልም
❗️Wifi Password በስልክ App ሀክ ይደረጋል ብላችሁ አታስቡ
❗️የሚሞሪ ካርድን የመያዝ አቅም መጨመር አይቻልም | 2GB ወደ 4GB never
❗️ኢትዮጵያ ውስጥ ለጊዜው ነፃ ኢንተርኔት መጠቀም አይቻልም | ቴሌ አንዳንድ ኮንፊገሬሽኖችን Block አርጓቸዋል | ሲሰራ እናሳውቃለን
❗️ቴሌግራም ላይ ያሉ ያለምንም Description የሚለቀቁ አፖችን install አታድርጉ
❗️Online ብር መስራት የምትፈልጉ በመጀመሪያ Verified የሆነ Paypal Account ያስፈልጋችኋል | በWestern Union ምናምን የሚባለው Totally Scam🚸
❗️ብር እንከፍላለን የሚሉ ዌብሳይቶችን ሳታረጋግጡ ጊዜአችሁን አታባክኑ
❗️በቴሌ Package ሲስተም አትጠቀሙ | ከባድ የዘረፋ ሲስተም ነው
❗️በአሁን ሰዓት Bitcoin በቀላሉ ማግኘት አይቻልም | ቢትኮይን ከ Diamond በልጧል
❗️ያገኛችሁትን አፕ ሁሉ ስልካችሁ ላይ install አታድርጉ | Auto Rooter የሆኑ Malicious Applicationኖች እየተበራከቱ ነው!..... @youthkiper
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በቴክኖሎጂ በመታገዝ የከፍተኛ ትምህርትን ለማስቀጠል ያዘጋጃቸውን ድረ ገጾች ይፋ አደረገ።
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ የሁለተኛ መንፈቅ ዓመት የሁሉም ትምህርት አይነቶች ሞጁሎች፣ አጋዥ ንባቦች እና ሌሎችም በየትምህርት አይነቱ ተሰንደው የሚገኙባቸው ድረ ገጾች የማሟላት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገለጿል።
በዚህም የተነሳ http://ndl.ethernet.edu.et/በተሰኘው ድረገጽ የተዘጋጁ የኮርስ ማቴሪያሎችና አጋዥ የትምህርት መጽሃፍት ተደራሽ የሚሆኑበት የዲጂታል ላይብረሪ ዝግጁ መደረጉን በመግለጫው ላይ አመልክቷል።
አክሎም ይህ ድረገጽ (http://ndl.ethernet.edu.et/) አስፈላጊ በሆኑ የትምህርት ይዘቶች እየበለፀገ ይገኛል ብሏል።
እንዲሁም ሚኒስቴሩ በርካታ ይዘቶችን የያዘ የTechIn ላይብረሪዝግጁ (http://library.techin.et/) መሆኑን አስታውቋል።
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የኦንላይን ትምህርት መስጠት የሚያስችላቸው የLearning Management System/MOOCS (https://courses.ethernet.edu.et/) ዝግጁ መደረጉንም በመግለጫው ላይ አመልክቷል።እንዲሁም ተማሪዎች ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላቸው በመሆኑ በስልክም ይሁን በላፕቶፕ እንዲሁም በታብሌት ወደ ተዘጋጁት ድረገጾች ገብተው በሚያነቡበት ጊዜ ከክፍያ ነፃ እንዲሆን ለማድረግ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመነጋገር ላይ መሆኑን ገልጿል።
ለተማሪዎቹ ቢያንስ 10 ተማሪዎች ይህንን መልእክት ያጋሩ ፡፡

@youthkiper
@youthkiper
@youthkiper
2024/09/21 14:03:48
Back to Top
HTML Embed Code: