Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሕይወትዎን በተሻለ መልኩ ለማራመድ አስፈላጊ አይታአ 25
💡 @wating_for_love👈
💡 @wating_for_love👈
💡 @wating_for_love👈
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

ያንተ የሆነችን ሴት አታስለቅስ፤ ምክንያቱም እምባዋን የሚጠርጉ ሌሎች አሉና

#ሴት፡ ምን ለማለት ፈልገህ ነው?
#ወንድ፡ ግንኙነታችን ማቋረጥ እንዳለብን አስቢያለው
#ሴት፡ ለምን?
#ወንድ፡ አላቅም፤ ብዙም ደስተኛ አይደለውም፤ ይቅርታ ግን ከፈለግሽ ንፁ ጓደኛማቾች መሆን እንችላለን።
#ሴት፡ እየቀለድክ መሆን አለበት።
#ወንድ፡ በጣም አዝናለው፤ ባንቺ ምክንያት አይደለም፤ በእራሴ ምክንያት ነው፤ ነገሮችን ካለምንም ችግርና ፈቃድ ማድረግ እፈልጋለው፤ ለፍቅር ህይወት ዝግጁ አይደለውም።
#ሴት፡ ግን እኮ እንደ ምታፈቅረኝ ነግረከኛል፤ እነዛን ሁሉ ቃልኪዳኖች ገብተህልኛል፤ እንድቀርብህ አድርገኸኛል፤ ሁሉ ነገሬን ሰጥቼካለው፡፡ እንዴት ይሄን ታደርግብኛለክ?
#ሴት፡ ሌላ ሴት አለች አይደል? ግልፁን ንገረኝ!
#ወንድ፡ ማንም የለም፤ በቃ በቻዬን መሆን ፈልጌ ነው፤ አስደሳች ግዜ ነበር ያሳለፍነው፡፡
#ሴት ፡ በጣም መጥፎ ሰው ነክ፤ ሁለተኛ እንዳታናግረኝ።

በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ሴቷ online ስትገባ ወንዱ ከሌላ ሴት ጋር ፎቶ post አድርጎ ተመለከተች፡፡ "ሌላ ሴት እንዳለች ገምቼ ነበር፤ በጣም ውሸታም ነክ" ብላ txt አረገችለት፡፡ ግን ምላሽ አላገኘችም፡፡
ቀኖች መቁጠራቸውን ቀጠሉ እሷም ያለማቋረጥ ስለሱ ታስብ ነበር። በስተመጨረሻ "በጣም ናፍቀኸኛል፤ እባክህ ዳግም እናውራ" በማለት txt አረገችለት፡፡ አሁንም ምላሽ የለም፡፡

አሁንም በህይወቱ ምን አዲስ ነገር እንደተፈጠረ ለማወቅ የልጁን Social media በየቀኑ ትመለከታለች። አሁንም ታፈቅረዋለች ቢሆንም እሱን እረስታ ወደፊት መሄድ እንዳለባት ታቃለች፤ ነገር ግን መቁረጥ አልቻለችም፡፡
#ሴት፡ " ሁሉም ነገር አንተ ጋር ሰላም እንደሆነ ተስፋ አደርጋለው፤ ሲመችህ txt አርግልኝ፤ ንፁ ጓደኞች እንድንሆን እየሞከርኩ ነው፡፡" ነገር ግን አሁንም ከወንዱ ምንም ምላሽ የለም፡፡ በሳምንታት ውስጥ ከአዲሷ ልጅ ጋር ፍቅረኛሞች መሆኑን አረጋገጠች፡፡ በዚህ ግዜ ሁሉም ነገር ቆረጠላት፤ እንደተዋሸች፣ እንደተከዳች፣ እንደተጠላች ተሰማት፡፡ እናም ለመቁረጥ ወሰነች፡፡

ከተወሰኑ ግዚያት በኀላ ሙሉ በሙሉ ለእሱ የነበራትን ስሜት አውጥታ መጣል ቻለች፡፡ ከሌላ ደስ ከሚል ሰው ጋር ፍቅር ጀመረች፡፡ አንድ ቀን ከአዲሱ ፍቅረኛዋ ጋር ፎቶ post አደረገች፡፡

#ወንድ፡ "ሰላም እንዴት ነሽ? አንቺ ጋር ሁሉም ሰላም ነበር ብዬ ተስፋ አደርጋለው፤ ነፃ ስትሆኝ txt አርጊልኝ፤ ናፍቀሽኛል ወጣ ብለን እንጨዋወታለን፡፡ txtuን አየችው፤ ከሌላ ወንድ ጋር ስላያት ብቻ ትኩረት ለመስጠትና እንደሚያስብላት ለመምሰል መሞከሩ አሳቃት፡፡ ይህን ያደረገው በመቅናቱና በእሷ ከተካት ሴት ጋር ደስተኛ ባለመሆኑ ብቻ እንደሆነ አውቃለች፤ ለዛም ነው ዳግም ሊያወራት የሞከረው፡፡

#ጭብጥ
my brother በእጅህ ያለው ነገር ከእጅህ ሳይወጣ መውደድና ማድነቅን እወቅበት፤ ወርቁን በመዳፍህ ይዘህ ሳለ ነሀሱን ፍለጋ አትኳትን፤
Dr. Eyob Mamo
ከአጉል መብተኞች ሰፈር ውጣ!
አንዲት ሴት አንዲት መኝታ ከፍል ያላት ኮንዶሚኒየም ተከራይታ ትኖራለች፡፡ ይህቺ ሴት መጠነኛ ገቢ ያላት ብትሆንም ጠንካራ ሰራተኛና ለሰው አዛኝ ነበረች፡፡ አንድ ቀን ጎረቤቷ እጅግ ድሃና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ እንዳለው ወደማወቅ መጣችና ለመርዳት አሰበች፡፡ ስለዚህም፣ አንድ ቀን ከስራ ስትመለስ ያላትን ጊዜ አጨናንቃ ዳቦ ጋግራ ልትተዋወቀውና ልትጠይቀው ብቅ አለች፡፡ ሰላምታ ከተለዋወጡና ራሷን ካስተዋወቀችው በኋላ ትንሽ አጫውታውና ዳቦውንም ሰጥታው ሄደች፡፡
ይህንን መልካም ስራ በመስራቷ ውስጧ ደስ ብሎት ብታድርም ጠዋት ስትነሳ ግን ዳቦ ይዛ በመሄድ ስለጠየቀችው እንዳላመሰገናት ትዝ አላትና ደነቃት! ዳቦውን ለመጨረስ ሶስት ቀን ይፈጅበታል ብላ ስለገመተች በሶስተኛው ቀን እንደገና ያላትን ጊዜ አጨናንቃ ዳቦ ጋግራ ልትጠይቀው ጎራ አለች፡፡ በድጋሚ ስላያት ደስ ያለው ይህ ሰው፣ እንደገና ዳቦ መያዟን ሲያይ የበለጠ ፈነደቀ፡፡ ከተጨዋወቱ በኋላ ዳቦውን ትታለች ተሰነባብተው ወደ ቤቷ ገባች፡፡ በንቃት ስትከታተለው አሁንም ምስጋና አላቀረበም - ገረማት!
ይህቺ ሴት የሰውየውን መደሰትና በዳቦው መጠቀም ስላየች ባያመሰግናትም እንኳ በየሶስት ቀኑ ዳቦ በመጋገር እርሱን ለማገልግል ወስና እንደገና ሌላ ሶስት ቀን ጠብቃ ያንኑ ነገር ለማድረግ ስትሄድ ሰውየው ትንሽ ቀዝቀዝ ብሏል፡፡ “ምነው፣ ሁሉ ሰላም ነው?” ብላ ስትጠይቀው፣ “ሁሉም ሰላም ነው” ካላት በኋላ በመቀጠል፣ “በነገራችን ላይ ባለፈው ያመጣሽው ዳቦ ትንሽ ጨው ስለበዛበት በሚቀጥለው ጨውን ቀነስ አድረጊው” አላት፡፡ ትንሽ ደንገጥ ብትልም፣ ምናልባት ያለው የግንዛቤ ደረጃ ይሄ ይሆናል በማለት ተጫውታ ተለያዩ፡፡ ሆኖም፣ እንደገና ከሶስት ቀናት በኋላ ስትሄድ ገና በእጇ ላይ ያለውን ዳቦ ተመልክቶ፣ “ዛሬ የዳዬ መጠን ቀነስ ብሏል ልበል?” በማለት ወቀሳት፡፡
ሌላ ሶሰት ቀን ጠብቃ ልትጠይቀው አሰበችና ጊዜ ስላልነበራት ዳቦ ባለመጋገሯ ምክንያት ብታመነታም ባዶ እጇን ልትጠይቀው ሄደች፡፡ ገና በሩን እንደከፈተ ያየው እጅ እጇን ነው፡፡ የያዘችው ዳቦ ባለመኖሩ በጣም ተበሳጨና፣ “ዳቦዬስ የት አለ?” በማለት ተቆጣት፡፡ ዳቦ ያላመጣችበትን ምክንያት ከገረችውና ትንሽ ካጫወተችው ተለያዩ፡፡ ሳታስበው በየሶስት ቀኑ ለሰውዬው ምንም ያልጎደለው ዳቦ የማቅረብ ባለእዳ እንደሆነች ስለተሰማት ደግማ ላለመሄድ ወሰነች፡፡
ለፍተንና ሰርተን አንድን ነገር ከመገንባት ይልቅ የለፉና በትጋት የሰሩ ሰዎች ለእኛ እዳ እንዳለባቸው የማሰብ መብተኝነት አደገኛ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ይህቺ አለም የእነሱ እዳ እንዳለባት ያስባሉ፡፡ በእነሱ አመለካከት ቤተሰቦቻች፣ ጓደኞቻቸው፣ የከተማው ባለጠጎች፣ የተሻለ ኑሮ ያላቸው ሰዎች . . . ለእነሱ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባቸው የማሰብ የመብተኝነት አመለካከት አላቸው፡፡ የዚህ አይነቱ አመለካከት መዘዙ ብዙ ነው፡፡
መብተኝነት ሁሉም ሰው ለራሱ ብቻ እንደሚሮጥና ለአንተ ማንም ግድ እንደሌለው በማሰብ ወቃሽና ነኝናጫ ያደርግሃል፡፡ መብተኝነት ጠንክረህ እንዳትሰራና ቁጭ ብለህ ሰዎች ለአንተ ማድረግ ያለባቸውን እየቆጠርክ በመጠበቅ ዘመንህን እንድታስበላ ያደርግሃል፡፡ መብተኝነት ሌሎች ለፍተው የገነቡት ውብ የሆነ ነገር የአንተ እንደሆነ እንዲሰማህ ይዋሽሃል፡፡
የመብተኝነት ስሜት ሲብስብህ ሽብርተኛና በኃይል ሰዎች የገነቡትን አፍራሽ፣ አልፎም ነጣቂ ወደመሆን ቀጠና ይወስድሃል፡፡ በዙሪያህ ያለው አለም በትጋት ሲገሰግስ አንተ ወደኋላ እንዳትቀር መብተኝነትን ጣልና ሰራተኛነትን አንሳ!@youthkiller
"ልጄ ሆይ፦
የምሥጢር ሙዳይ ሁን እንጂ የእሳት ማንደጃ ወናፍ አትሁን ። ሰዎች ሊሰሙህ በሚችሉበት ችሎታቸውና ፍላጎታቸው መጠን ብቻ ተናገር ፣ ቁጥብ እንጂ ዝርው አትሁን ። ለዕውቀት ትጋ ። በከፊል በተረዳኸው ነገር ራስክን እንደ አዋቂ አትቁጠር ። በከፊል ከማወቅ አለማወቅ ይሻላል ። ሥራ ስትሠራ ደግሞ ነገ ትቼው ለምሞተው ወይም ብሠራ የሚጠቀመው ሌላ ነው በሚል ተስፋ ቢስ ሆነህ ሳይሆን ዘላለም እንደምትኖር ያክል በመትጋት ነው ። ትጋት ጥሩ ነው ። ችኮላህ ግን ውጤት አያመጣም ፣ በችኮላ መሥራትና በፍጥነት መሥራት የተለያዩ ናቸው ። ርኩሰት የዕውቀትና ስልጣና መገለጫ አይደለምና ማንነትንና ሰብዓዊ ክብርን ከሚያጎድፉ ተግባራት መታቀብን ገንዘብ አድርግ ። "
" እናም በየዕለቱ በኑሮህ ጠንቃቃ ሁን ። ያለጸጸት ነገን ለመኖር ዛሬን በቁም ነገር አሳልፍ ፤ ውሳኔዎችህ ትክክለኛ መሆናቸውን መርምር ፤ ልክ እንደገና ሕይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ወይም እንደገና ሕይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ደግመህ የምትኖረውንና ለማከናዎን የምትመርጠውን ዐይነት ሕይወት ለመኖር ሞክር ። ...."
© ዳን ኢትዮፒካ
ምንጭ ዝጎራ ገጽ 315
ደራሲ ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
አጠቃላይ ለጭንቀት መላ የሚሆኑ መፍትሄዎች የሚከተሉት ናቸዉ ።

° በውስጣችን የሚቆጠቁጠውን
የተስፋቢስነት ስሜት ማወቅ

°የቁጣ ስሜቶቻችንን መለየት

°የ አካል እንቅስቃሴ ማድረግ

°ማህበራዊ ሕይወት ውስጥ ንቁ
ተሳትፎ ማድረግ

°የሚወዱትን ስራ መስራት

°ራስን በወቀሳ ውርጅበኝ
አለማሸማቀቅ

°ባለሙያ ማማከር
.
@youthkiller
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች እንዴት ናቹ ሰላማቹ ይብዛ እንደተለመደው አዝናኝና አስተማሪ ፅሁፎችን ይዘነ መቅረባችንን አጠናረን አሁን ደግሞ በ ዩትዩት(youtube) ቻናል ወደ እናንተ መጥተናል እንድትከታተሉን ባክብሮት እንጋብዛለን linkun እናስቀምጥላቹአለን መልካም አዳር
ፍላጎትን ከፍርሃት የማስበለጥ ስኬት
“እንዲሳካልህ ከፈለክ፣ ካለብህ የመውደቅ ፍርሃት ይልቅ ለስኬት ያለህ ፍላጎት ሊልቅ ይገባዋል” – Bill Cosby
ከልባችን ያልተጸየፍነውን ነገር አንሸሸውም፤ በጽኑ ያልፈለግነውንና ያልተከታተልነውን ነገር ደግሞ በፍጹም ልንደርስበት አንችልም፡፡ የአንድ አንድ ሰው ሕልም በትምህርት አንድ ደረጃ መድረስ ነው፡፡ የሌሎች ሕልም ደግሞ ቤተሰባቸው አሁን ካለበት ችግር ማላቀቅ ነው፡፡ ከዚህም ባለፈ ሁኔታ፣ በስራ፣ በግል ጤንነት፣ እና በሌሎች ሁኔታዎች አንጻር ሰዎች ግብን አውጥተው እዚያ ለመድረስ ይጣጣራሉ፡፡ የእነዚህ ሁኔታዎች መሳካት የአጠቃላይ ሕይወት መሳካት ባይሆንም የስእሉ አካል ስለሆኑ አስፈላጊ ጉዳዮች ናቸው፡፡
በዚህ ሰው ሁሉ በሚጋራው አንድ ደረጃ የመድረስ ጉዞ ውስጥ ማንንም የማይምር አንድ ችግር አለ፤ እርሱም የፍርሃት ችግር ነው፡፡ ሁላችንም ቢሆን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የምንፈራቸው ነገሮች አሉን፡ የመውደቅ ፍርሃት፣ ስኬት የማጣት ፍርሃት፣ ተቀባይነት የማጣት ፍርሃት፣ ጀምሮ የማቋረጥ ፍርሃት …፡፡ በአጭሩ፣ ከፍርሃት ነጻ የሆነ ሰው የለም፡፡ ይህንን ሰው ሁሉ የሚጋራውን ፍርሃት የተሰኘውን ተራራ አልፎ ወደ አላማ ለመዝለቅና ወደግባችን ለመድረስ ያለን የውስጥ ፍላጎት ካለብን ስጋትና ፍርሃት በብዙ እጥፍ ሊጠነክር ይገባዋል፡፡
ለመራመድ ያሰብከውን እርምጃ አስበውና ያንን ነገር ለማድረግ ያለህን ፍላጎትና በውስጥ የምትፈራውን ነገር በሚዛን ላይ አስቀምጣቸው፡፡ የትኛው ያመዝናል? ፍርሃቱ ካየለ ወደኋላ ያስቀርሃል፣ ፍላጎቱ ካየለ ግን ፍርሃትህን አሸንፈህ እንድትዘልቅ ብርታት ይሆንሃል፡፡ ፍላጎትህን ከፍርሃትህ ለማስበለጥ ከፈለክ ደግሞ ክምትወስደው እርምጃ የተነሳ የምታገኛቸውን ወሳኝ ለውጦችና ጥቅሞች ማሰብ፣ ማወቅና ማሰላሰል ያስፈልጋል፡፡ @youthkiller
​​🎄እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በአል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
በአሉ የሰላም የፍቅር የብልጽግና የተቸገሩትን የምንረዳበት ከተጣላነው ጋር የምንታረቅበት በአል ይሁንልን
@youthkiller
@youthkiller
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የንባብ ቅምሻ
(የታዋቂው ካህሊል ጂብራን ምርጥ ጥቅሶች)

📖📖📖
ውበት

ውበትን የምታገኙት የማይታየውን ስታዩ ነው፤ በግልፅ ያልሆነውን ስትረዱ ነው፤ ድምፅ የሌለውን ንግግር ስትስሙ ነው፡፡ ውበት፣ በውስጣችሁ ተጀምሮ ከሥጋዊ ፍላጐቶቻችሁ ባሻገር የሚያበቃ ድንቅ የሀዘንና ደስታ ውህድ ነው፡፡ ልቦና ውስጥ የሚገኝ ብርሃን ነው።


📖📖📖
ስልጣን

"ወንድሜ ፣ራስ ወዳድነት በጭፍን የበላይ የመሆን መንስኤ ነው። የበላይነቱም ደግሞ ወገንተኝነትን ይፈጥራል። ወገንተኝነትም ወደ አለመስማማት እና ጠብ የሚወስድ ስልጣን ይፈጥራል።
ነፍስ ደግሞ በድንቁርና ሳይሆን በዕውቀት ሀይል እና በፍትህ ነው የምታምነው።መሃይምነትንና ጭፍን ጭቆናን ለማስፋፋት መሳሪያ (ጎራዴ) የሚያቀርበውን ስልጣን ትቃወማለች


📖📖📖
ዜግነት
ጥሩ ዜጋ መሆን ምን ይመስላችኋል?
የእናንተን መብት ከማስከበራችሁ በፊት የሌላውን ሰው መብት ማክበር ነው፡፡ ነገር ግን ዘወትር መብታችሁን እወቁ፡፡
በእጆቻችሁ ጠቃሚና የተዋቡ ነገሮችን መፍጠር ነው ፤ ሌሎች ከፍቅርና ከእምነት ጋር የፈጠሩትን ፈጠራቸውንም ማድነቅ ነው፡፡
በልፋታችሁና በላባችሁ ብቻ ፍሬ ማፍራት ነው፡፡ እናንተ ስትለዩዋቸው ልጆቻችሁ የሌሎች ጥገኛ እንዳይሆኑ የምታገኙትን በረከት በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም ነው፡፡

📖📖📖
አንድ ኣበባ ህይወቱን እና ጥዑም መዓዛውን ከመሬት እንደሚያገኝ ሁሉ፣ ነፍስም ጥበብና ጥንካሬን ከድክመትና ከስህተት ታገኛለች፡፡

📖📖📖
ታላቅ ሰው ሁለት ልቦች አሉት፡፡ በአንደኛው ሲደማ በሌላኛው ይታገ
ህይወት ወርቅ ስትሰጠኝ ለአንተ ብር ወይ ነሀስ ሰጥቼህ ራሴን እንደቸር (ለጋስ) የቆጠርኩት ምን ያህል ገብጋባ ብሆን ነው?!!

@youthkiller
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት አደራችሁ🙏

ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየዋል። ሮጦ ሄዶ በትህትናና በአድናቆት ሰላም ካለው በኃላ "አስታወስከኝ ወይ?" አለው። አስተማሪውም ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ "ይቅርታ አላስታውስኩህም እንዴት እንደተዋወቅን ልትነግረኝ ትችላለህ?" በማለት መለሰለት፡፡

ወጣቱም ልጅ እንዲህ እያለ ተረከለት "3ኛ ክፍል እያለን ያንተ ተማሪ ነበርኩ። ታዲያ አንድ ቀን የክፍል ጓደኛዬን ቆንጆና ልዩ የሆነውን የእጅ ሰዓቱን ሰርቄበት ነበር። እሱም እያለቀሰ ሄዶ የእጅ ሰዓቱ እንደተሰረቀበት ላንተ ይናገራል፤ አንተም መጥተህ ልትፈትሸን ሁላችንም ክፍል ውስጥ ያለን ልጆች አይናችንን ጨፍነን እጃችንን ከፍ አድርገን ፊታችንን ወደ ግድግዳ አዙረን እንድንቆም አዘዝከን።

በዛን ጊዜ እኔ የፍተሻውን ውጤት እያሰብኩ በጣም ተረበሽኩ፤ የሚገባበትን አጣሁ። አስበው ሰዓቱ በኔ ኪስ ውስጥ ተገኝቶ ሁሉም ተማሪ ሌባ እያለ ስሰድበኝ፤ ግቢ ውስጥ መጠቋቆሚያ ስሆን፤ ከት/ቤት ተባርሬ ወላጅ አምጣ ስባልና ወላጆቼ ይሄን አሳፋሪ ድርጊቴን ሲሰሙ። በዚህ ጭንቅ ውስጥ እያለሁ የፍተሻው ተራ ደርሶ እጅህ ወደ ኪሴ ሲገባና ሰዓቱን ቀስ አድርገህ ከኪሴ ስታወጣ ተሰመኝ፤ በቃ መጥፎ ዜናውን ልነገር ነው አለቀልኝ ብዬ ስጠባበቅ አንተ ግን ምንም ሳትል የመጨረሻው ልጅ ጋር እስክትደርስ ፍተሻውን ቀጠልክ። ፍተሻውም ሲያልቅ አይናችሁን ግለጡና ወደየቦታችሁ ተመለሱ አልከን። እኔ ግን መልሰህ ታስቆመኛለህ ብዬ መቀመጡን ፈራሁ። በጣም የሚገርመው አንተ ሰዓቱን አውጥተህ ለባለቤቱ መለስክለት፤ ግን ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኘህና ማን እንደሰረቀበት ምንም አልተናገርክም ነበር።

በት/ቤት ቆይታዬም ምን እንደተፈጠረ ማንም አላወቀብኝም ነበር፤ አንተም ምንም ብለኸኝ አታውቅም። እኔ ግን ስሜንና ክብሬን እንዳደንክና ስብዕናዬን እንደጠበክልኝ ዛሬም ድረስ አስታውስሃለው። አንተም ይሄን ታሪክ ቶሎ ትረሳለህ ብዬ አልገምትም አሁንስ አስታወስከኝ?" አለው።

አስተማሪውም በመገረም ውስጥ ሆኖ "ትንሽ ትንሽ አስታውሳለው በማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛሁ ግን አላስታውስም፤ ምክንያቱም እኔም ስፈትሻችሁ የነበረው አይኔን ጨፍኜ ነበር!!"አለው።

#NB በህይወታችን ለሚናከናውናቸው ነገሮች ሁሉ ጥበብ ያስፈልገናል። እንደ አስተማሪ እንደ ወላጅ እንደ መሪ...ወዘተ ለአንዳንድ ነገሮች አይናችንን መጨፈን አለብን ምክንያቱም ሁሉም ጥፋቶች በቅጣት ብቻ አይታረሙም!!!

🙌መልካም ቀን
@youthkiller
ጥምቀትከ ይኩነነ ቤዛ ያመነ የተጠመቀ ይድናል እንኳን ያላመነ ግን ይፈረድበታል ለጌታችን ለመዳኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በሰላም አደሳቹ መልካም በዓል @youthkiller
አንድ በምሽት አቅጣጫ የጠፋበት መርከብ ከሩቅ ያየ ሰው ወደ እቤቱ ገብቶ ሻማ ይለኩሳል
ሻማውም ለምን ለኮስከኝ ቢለው ሰውዬው ‹‹አቅጣጫ የጠፋው መርከብ ከሩቅ ያታየኛል
ለሱ በእሳት ልጠቁመው ነው ይለዋል ሻማውም ‹‹ታዲያ እኔ ሻማ ነኝ እንዴት ከሩቅ እታያለሁ›› ቢል ሰውዬውም መለሰ ‹‹ሻማዬ ሆይ አንተ ብቻ የቻልከውን ብራ›› አለውና ይዞት ይወጣና ብዙ ደረቅ እንጨቶችን እንደ ዳመራ ከቆለለ ቦሃላ በሻማው እሳት እንጨቶቹን ለኮሰ ብርሃኑም ብዙ ሆነ
ያኔ መርከቡም ተመልክቶ መጣ
ሰውዬውም ለሻማው እንዲህ አለው ‹‹ሻማዬ ሆይ አየህ አንተ በቻልካት መጠን ስለበራህ ያንተን ብርሀን ተቀብለው የሚያደማምቁ ብዙዎች አሉ›› አለው፡፡
እንግዲህ እንዲህ ነው የኔ ጥረት ትንሽ ናት አትበል፡፡ የቻልከውን ካደረክ ሌሎች ያንተን ብርሃን የሚቀበሉ እልፎች አሉ
‹‹የትም ሁን ማንም ሁን ያቅምህን በጎ ለማድረግ ግን አትስነፍ ደግነት
እንደ ጥሩ ሽቶ ነው ከአንዱ ተነስቶ ወደ አንዱ ይጋባል››
እንግዲህ አንዲህ ነው ለመስጠት የግድ ሃብታም መሆን
አይጠበቅብህም፡፡
ደግሞ ማንም ሰው ልስጥ ካለ የሚሰጠው አያጣም፡፡


@youthkillet
#Solve_IT_2020

' Solve IT ' ባለፉት አመታት የቴክኖሎጂ አቅማቸውን ተጠቅመው ችግር ፈቺ ግኝቶችን ለፈጠሩ ወጣቶች ከ100,000 አስከ 25,000 ብር መነሻ ገንዘብ አበርክቷል፡፡

ዘንድሮም ኃሳብ ላላቸው ወጣቶች ኃሳባቸውን በእውቀትና በገንዘብ ለመደገፍ ወደ 15 የተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በመንቀሳቀስ ግንዛቤ ማስጨበጫና ምዝገባ በማድረግ አወዳድሮ ይሸልማል፡፡

ከየካቲት 2 እስከ የካቲት 6 አምስት ቡድን ወደ ሰባት የሀገራችን ከተሞች ( ጅማ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ጋምቤላ፣ ሀዋሳ፣ ጅጅጋና አክሱም ) የመጀመሪያ ጉዞውን በማድረግ ስለውድድሩ ለወጣቶች በቂ ግንዛቤ ይሰጣል፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫውም በዩኒቨርሲቲና በኮሌጅ፣ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በቴክኒክና ሙያ፣ በወጣት ማዕከሎች፣ በሆቴሎችና በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ይሰጣል፡፡

የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን ኃሳብ አለኝ የሚል በግልም ሆነ በቡድን የሚመጡ ወጣቶች፣ ዕድሜያቸው ከ18 - 28 ከሆነና ከዚህ በፊት በዚህ ውድድር ያልተሳተፈ/ፉ በሙሉ መመዝገብና መወዳደር ይችላል/ሉ፡፡

http://www.icog-solveit.com

@youthkiller
🙏ሰላም ለእናንተ ይሁን

"የተሳሳተ አካሄድ እንጂ የተሳሳተ መንገድ የለም"

ሁለት ወጣቶች ወደ ቤታቸው ለመሄድ የታክሲ ሰልፍ ላይ ቆመዋል፡፡ ታክሲው መጣና ሁለቱም ተሳፈሩ፡፡ ከ30 ደቂቃ ጉዞ በኀላ "መጨረሻ" በማለት ረዳቱ ሲናገር ሁሉም ከታክሲው ወረዱ፡፡ በዚህ ወቅት አንደኛው ወጣት በትክክል ሰፈሩ ሲደርስ ሌላኛው ግን በስተት ካለሰፈሩ ነበር የመጣው፡፡

በስተት ሌላ ሰፈር የሄደው ወጣት "የተሳሳተ መንገድ ነው የመጣውት" ብሎ ማማረር ጀመረ፡፡
ነገር ግን የተሳሳተው መንገዱ ነው ወይስ ወጣቱ?

መንገዱማ ትክክለኛ ስለሆነ ሌላኛውን ወጣት በትክክል ሰፈሩ አድርሶታል፡፡ ነገር ግን መንገዱ ሳይሆን ተሳፋሪው የተሳሳተ በመሆኑ አንዱን ደሞ የማይፈልገው ሰፈር አምጥቶታል፡፡

✍️ የአብዛኞቻችን ህይወትም ተመሳሳይ ነው፡፡ መሆን የምንፈልገው ዶክተር ነው፡፡ ነገር ግን የምንማረው ያሬድ ሙዚቃ ቤት ነው፡፡ መሆን የምንፈልገው ታዋቂ ዘፋኝ ነው ነገር ግን የተሳፈርነው በኢንጅነሮች ታክሲ ነው፡፡ በህይወታችን ደስተኛ መሆን ከፈለግን ወደ ምንፈልገው ቦታ የሚያደርሰንን ትክክለኛ መንገድ ፈልገን መጓዝ ይጠበቅብናል፡፡ ነገር ግን ወደ እኛ ፍላጎት በማይወስድ መንገድ በመገኘታችን ብቻ ያ መንገድ ተሳስቷል ማለት አንችልም፤ ምክንያቱም በዛ መንገድ ተጉዘው ካሰቡበት የሚደርሱ ብዙ አሉና፡፡
@youthkiller
Channel photo updated
2024/09/21 10:58:43
Back to Top
HTML Embed Code: