Telegram Web Link
ጥሩ ነው ወጣት መሆን
አንዳንድ ነጥቦች ስለ ወጣትነት

የስብሃት ገ/እግዚያብሔር የላቀ ስራ(Masterpiece) የሆነውን ትኩሳትን ያጣጣመ ሁሉ የማይዘነጋት አንዲት አንቀፅ አለች፡፡ “ጥሩ ነው ወጣት መሆን… ትላለች፡፡ …
ጥሩ ነው ወጣት መሆን፡፡ እንትን ባይኖርህ እንትን ይኖርሃል ትለናለች፡፡ “መልክ ባይኖርህ አንጎል ይኖርሃል፣ ዕውቀት ባይኖርህ ጉራ ይኖርሃል፣ ደስታ ባይኖርህም ንዴት ይኖርሃል፣ ፍቅር ባይኖርህ ተስፋ ይኖርሃል፡፡…መጨቆን ቢበዛብህ ሪቮሊሽን ታነሳለህ…መኖር ቢያስጠላህ ወይም ቢያቅትህ ራስህን ትገላለህ…ሰው ባያውቀውም ቅሉ ታሪክ ይኖርሃል፣ ወጣት ነህና…”፡፡ እንዴት የምትጥም በስድ ንባብ የተቀመመች
ቅኔ ነች በሉ! …በእርግጥም…ጥሩ ነው ወጣት መሆን……ግን የቱ ወጣት ነው ይህን ልብ የሚል፡፡ የቱ ወጣት ነው ለመሆኑ እኒህን የተዘረዘሩ የወጣትነት በረከቶች…እንደዘመኑ መልካም ትሩፋቶች የሚገነዘብ፣ የሚረዳ ? አይመስለኝም፡፡ ባህር ውስጥ ተወልዶ አድጎ የሚሞተው አሣ ውሃ ውስጥ መኖሩን ሊገነዘብ እንደማይችለው ሁሉ የትኛውም የምር ወጣት (የሚባል ነገር ካለ?...ግን አሁን ለኔ ለዚህች ፅሁፌ ያስፈልገኛል፡፡) ቢሆን ያ የወጣትነት ዘመኑ እስኪያልፍ ድረስ የእሣት ዘመኑን በረከቶች ፈፅሞ አይገነዘባቸውም፡፡ ሆሆ…እሱ ለራሱ ልጄ…
በስንቱ አናት የሚያዞር የህይወት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ እየዳከረ…በየቅፅበቱ የሃምሌትን ‘‘መሆን፤ አለመሆን’’ በልቡ እያብሰለሰለ…፡፡ መች ደላው እሱ…በማንም ባለቅኔ የማይጨበጥ ህልም የሚፈታ…፡፡ የራሱንም ጉዳጉድ የሚያውቀው ራሱ
ነው፡፡

ወጣትነት የምኞት፣ የመሻት፣ የመፈለግ…ማለቂያ የሌለው ህይወታዊ ኃይል አብራክ ነው፡፡ ችግሩ ግን ይህ ኃይል ወደ ውጭ እንጂ ወደ ውስጥ የማየትን መላ አለመታደሉ ላይ ነው፡፡ የሌለውን የጎደለውን እንጂ ያለውን ታላቅ በረከት ልብ አይልም፤
ወጣት፡፡ ስለዚህ… “እንትን ባይኖረኝ እንትን እኮ አለኝ… እንዴት የታደልኩ ወጣት ነኝ በሉ…” ባይ ወጣት ያለ አይመስለኝም ፡፡ ካሉም…እጅግ በጣም በጣም ጥቂት የታደሉ! አቦ ይመቻቸው፡፡ ለዚህም ነው የወጣትነትን በረከት - ጎልማሳ ዜጎች በየመድረኩ፣ ጎምቱ ባለቅኔዎች በየአድባሩ ሲቀኙት እንጂ በወጣት ባለቅኔዎች ስንኞች ውስጥ የማናገኘው፡፡ የወጣቶቹማ ስንኞች ዜማ “ወዬው” ነው፣ “ስጠብቅሽ
ውዬ” ነው…፣ ‘‘በተናቀች ፍቅር ቁርጠት…’’ ተይዞ እህህ ነው፣ ህልም ነው፣
ፍቅር ነው…ለነገሩ ወጣትነት የፍቅር አዝመራውስ አይደል፡፡ ፍቅር ደግሞ ስስ
ነው፣ በናኝ ከሕልም የላመ፡፡ ባሻው ጊዜ ጎብኝቶህ፣ ሲለው ደግሞ ተነስቶ እብስ
ይልና በእንባ ያጥብሃል፡፡ የስብሃት የትኩሳት ማኒፌስቶ፣ …ፍቅር ባይኖርህ ተስፋ ይኖርሃል ይልሃል፡፡ ግን ሁሌ አይሰራም፡፡ ለመሆኑ በዓለም ዙሪያ ወጣቶች ራሳቸውን ከሚያጠፉባቸው ምክንያቶች ግንባር ቀደሙ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ -“መሰመሩን የሳተ የፍቅር ግንኙነት” ይሉታል፡፡ ያው ነው ፍቅር በሉት…እዚያ ግድም ነው ሰፈሩ፡፡
የትኛውም የተፈጥሮ ኃይል ሲከማች ፍንዳታው ወደ ውጪ እንደመሆኑ የወጣትነት የጋለ ነበልባልም ወደ ውጭ አይቶ ያጣውን የሌለውን ሽቶ መተከዝ ቢያበዛ አይገርምም፡፡ እናም ወጣትነት ተንሸራትታ መሄድ ስትጀምር ብዙዎች ድንገት እንባንንና…ነገሩ ሲገባን… “ጥሩ ነው ወጣት መሆን” እንላለን፡፡ …እንትን ባይኖርህ እንትን ይኖርሃልን እናቀነቅናለን፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ፓብሎ ፒካሶ ወጣት ለመሆን ጊዜ ያስፈልጋል የሚለን፡፡ እንዴት አይቶታል በሉ… It takes time to be young.

ይቀጥላል.....

@youthkiper
ጥሩ ነው ወጣት መሆን
አንዳንድ ነጥቦች ስለ ወጣትነት

የቀጠለ

ጉዳዩ እንዲህም ይመስለኛል፤ መጀመሪያ ላይ ተፈጥሮ በጉርምስና መባቻ የወጣትነትን ዘውድ ስትደፋልን አካላችን ሙሉ የወጣትነት ኃይልና ጉልበት ይጎናፀፋል፡፡ የዋሁ ገላ አይዋሽማ - Hips don’t lie አይደል ያለችው አቀንቃኟ፡፡ ሰውነታችን በርግጥም
ሙሉ ለሙሉ ወጣት ይሆናል፡፡ ችግሩ ግን የነፍሳችንን የወጣትነት መነሣሣት
በባህሉም፣ በምኑም በምኑም ተፅዕኖ አፍነን እናሽመደምደዋለን፡፡ ፍቅር ልባችንን ሲጠራው…አፍረንም ፈርተንም ወይ ባንዱ ተልካሻ ምክንያት ተጠፍንገን…ለዛ ከወዲያ ለተላከ መለኮታዊ ጥሪ የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ እንላለን…ሌላም ሌላም…፡፡

ብዙ ነው ዝርዝሩ፡፡ ብቻ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን እሣት ወይ አበባ በተሰኘው ታላቅ ቅኔው እንደሚለን…
“ልጅነት የሰጠንን…በመለኮት የቀባንን”
“…አባከንኩት አባከንሽው…”
ይሆንና ያልፈዋል፡፡ ወይ ነዶ!
ግን…ወጣትነት ተንሽራትታ መሄድ ስትጀምር…የአፍላነት ጀምበር ወደ ምዕራብ ስታዘግም…ትልቁን በረከት ለተራ ይሉኝታና እርባና ቢስ ለሆነ ምክንያት
እንደሸጥነው ሲገባን…ድንገት ብልጭ ይልብንና… ነፍሳችንን ከታሰረችበት ፈትተን እንለቃታለን፡፡ አስቂኝም ነው ነገሩ፡፡ ለጥቂት ውድ አፍላ ዓመታት የታሰረውን የወጣትነት መንፈስ ባለቀ ሰዓት ፈትተን ለቅቀን…የባከነውን ለማካካስ ባንዴ ወጣት ሆነን ጉብ ነዋ ! በእርግጥም ፒካሶ ብሎታል፣ ወጣት ለመሆን ? ጊዜ ይፈጃል…!!
አንድ ወዳጄ አንዷን ዕውቅ የሀገራችንን ድምፃዊት አንስቶ አይተህልኛል አለኝ “…
ከዛሬ ሃያ ምናምን ዓመታት በፊት በወጣትነቷ ከነበረችው ይልቅ ዛሬኮ ታምራለች፣ ትስባለች” አለኝ፡፡ እንዴት ሊሆን ቻለ ? ነው ነገሩ፡፡ ጉዳዩማ ወዲህ ነው ወዳጄ አልኩት…you know…it takes time to be young…(አየህ…አለ አይደል…አንዳንዴኮ…ወጣት ለመሆን ጊዜ ይፈጃል፡፡)

ስለወጣትነት ሲነሳ እንዲዚህች ጥቅስ ስሜቴን የሚነዝር የለም፡፡ ማን እንዳላት
አላስታውስም፡፡ ጥቅሷ ግን መቼም ባስታወስኳት ቁጥር ልቤ ውስጥ ትነዝራለች፤
“አንድ ወጣት አንድ ወጣት ነው፣ ሁለት ወጣቶች ግማሽ ወጣት ናቸው፣ ሶስት
ወጣቶች ጭራሽ ወጣት አይደሉም፡፡”

ይህቺ ጥቅስ ያዘለችውን ጥልቅ ሀሳብ
ለመተንተን ጥራዞች አይበቁም፡፡ የትኩሳቱ ተራኪ…ብቻዬን በምሽት በከተማው ጎዳናዎች ስዛዋወር ጀብደኝነት ይሰማኛል ይላል፡፡ ወጣቶች በህብረት በስሜት ተሞልተው የሚያደርጉትን ሲያደርጉ አይታችሁ ይሆናል፡፡ ግን የአንድ ወጣት የብቻ
አርምሞን ያህል ጥልቀት አታገኙበትም፡፡ ማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ብቻነቱ ሲተጋ ግላዊ ማንነቱ (individuality) እንደሚደምቅ ግልፅ ነው፡፡ የህይወት ሙላት በሚገማሸርበት ወጣትነት ላይ ይህ ሲከሰት ደግሞ የሚሆነውን ገምቱታ…፡፡

ወጣትነትና ፈጠራ
የሰው ልጅ ፈጠራ ቁንጮ ተብለው የሚጠቀሱ ታላላቅ የኪነት፣ የሳይንስና ሒሳባዊ ፈጠራዎች ባብዛኛው (ሁሉም ላለማለት ያህል) በወጣት ፈጣሪዎች የተበረከቱ ናቸው፡፡ በተለይ የሳይንስና ሂሳብ ዓበይት ፈጠራዎችና ግኝቶች…ሁሉም ማለት ይቻላል የለጋ ወጣቶች ትኩስ የፈጠራ መንፈስ ውጤቶች ናቸው፡፡ አይዛክ ኒውተን በሰው ልጅ የምርምርና የዕውቀት አምባ ወደር የለሽ የሚባለውን የመላውን ክላሲካል ፊዚክስ፣ ካልኩለስንና የብርሃን የምርምር ውጤቶቹን ሰርቶ የጨረሰው ገና በለጋ
የወጣትነት ዕድሜው በ24 ዓመቱ ነበር፡፡ አልበርት አይንሰታይን የዘመናዊው
ዓለም የአስተሳሰብ መሰረት የሆኑ ታላላቅ የምርምር ስራዎቹን ያበረከተው ገና
በ26 ዓመቱ ነው፡፡ ታላቁ ካንቶር የዕድሜው ማብቂያ ድረስ የታተረበትን ሂሳባዊ ዕንቆቅልሽ ሲፈታ ፖል ኮኾን ዕድሜው ገና 22 ነበር፡፡ ዝርዝሩ ማለቂያ የለውም፡፡ ለዚህም ይመስላል ታላላቅ የአሜሪካና የአውሮፓ ስመጥር ዩኒቨርሲቲዎች በተፈጥሮ ሳይንስና በሂሳብ ዘርፎች ለPh.D(ዶክትሬት ዲግሪ)የሚቀበሏቸውን ተማሪዎች ዕድሜ በተቻለ መጠን ከ30 ዓመት ያነሰ እንዲሆን የሚያስገድዱት፡፡

የ1987 ዓ.ም የህዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት እንደሚያስረዳን 57% የሚሆነው የሀገራችን ህዝብ ከ18 ዓመት በታች ነው፡፡ የቅርብ ጊዜው የቆጠራ ውጤትም ከዚሁ የሚርቅ እንደማይሆን ግልፅ ነው፡፡ ይህ ዓይነት የወጣት ዜጋ ስነ-ህዝባዊ ክስተት ያለበት ሌላ ሀገር ለመኖሩ እጠራጠራለሁ፡፡ ጉዳይ አንዳች እጓ ለማውታ (Orphanage) ቢያስመስለንም - ያም ሆነ ይህ ሀገራችን የወጣት ሀገር ነች፡፡ የወጣት
ሀገር ደግሞ ተስፋዋን ሰንቃ ከጠነከረች ነገዋ ብሩህ ለመሆኑ ማን ይጠራጠራል፡፡

ምንጭ -የአለማችን ምርጥ ታሪኮች
ደራሲ- ግሩም ተበጀ

@youthkiper
@youthkiper
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከታች የተዘረዘሩትን website በመጠቀም የራሳቸውን pdf መውረድ ይችላሉ ተብሏል።

በተለይ National Digital Library በማለት Search አድርው በማግኘት pdf አውርደው ያንብቡ ተብሏል።

በ ነፃ ነው እያሉ ይቀልዳሉ እንጂ free data አይሰራም 😭😭 ቢሆንም pdf ለማግኘት እራሱ አስቸጋሪ ነው። ሞክሩት ለማንኛውም።

የሚፈልጉትን መፅሃፍ በነፃ አውርደው ለማንበብ የሚጠቅሙ ምርጥ 5 ዌብሳይቶች - 5 free eBook sites

ሁሉም ሰው ይወቀው! ሼር አድርጉት፤

1. National digital library of Ethiopia -

library.stic.et

2. Project Gutenberg -

www.gutenberg.org

3. Book Boon -

www.bookboon.com

4. Free Ebooks -

www.free-ebooks.net

5. ለአማርኛ መፅሀፍት ይህንን ይጫኑ

http://www.good-amharic-books.com/library

6. ሁሉም ሰው ይወቀው! ሼር አድርጉት፤

---------------
ለምርጥ የሳይንስ መረጃዎች Scitechethiopia ይመረጣል



            Share share🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
@youthkiper
ወጣትነት ለአንተ ወይም ለአንቺ ምን ማለት ነው?
# ወጣትነት_ማለት !!
ወጣትነት ራ ስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን
በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም!


ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ
እና መነታረክ ማለት አይደለም! ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ
የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም!
ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ
አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣
በቧልት መሞላት ማለት አይደለም!

ወጣትነት በግዴለሽነት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት
አይደለም!


ወጣትነት ባህር ነው ። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው ። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት
ነው ። ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው ። ወጣትነት
በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው ። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር
ፈቺነት ነው ። ወጣትነት በዘረኝነት ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣
ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ
መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ሃገራችን ከተቻለም አለም አቀፋዊ እይታን

ማስፋት ነው ።
ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው ። ወጣትነት ልቦናዊ ትዕግዝት
ነው።ወጣትነት የልውጥ ትንቢት ነው።ወጣትነት ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው ። ወጣትነት ብርሃን ነው
። ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው ። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው!
ወጣትነት እስከመጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው ።
ወጣትነት ማንበብ ነው ። ወጣትነት መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ
ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው ። ወጣትነት
ለሌሎች መኖር ነው ። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ
ነው ። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው ። ወጣትነት እሳት
ነው ። ወጣትነት ቤንዚል ነው ። ወጣትነት ቅጠል ነው ። ወጣትነት ጤዛ ነው ።
ወጣትነት ታክሲ ነው ። ወጣትነት ምርጫ ነው ። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች
ጀልባ መሆን ነው ። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው ። ወጣትነት
ውስጥን ፈተናን ለማለፍ ማጀገን ነው ። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና
አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው ። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት
በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው .... ለናንተስ ወጣትነት ማለት ምን ማለት ነው?.....share @youthkiper
❤️ለወንዶች❤️
ወንድሜ ሆይ ወንድነት ወይም አራድነት ማለት ቆንጆ የተባለች ሴትን ሁሉ እያሳደዱ የውሸት ተረት እየነገሩ በማሳመን ለጊዜያዊ ስሜት ተጠቅሞ እንደ ርካሽ እቃ መጣል አይደለም። ሲጀምር ሴት ልጅ እራሷን አሳልፋ የምትሰጥህ አምናህ ነው መታመን ደግሞ ትልቅ ሀላፊነት ነው መወጣት የማትችለውን ሀላፊነት ደግሞ አትውሰድ። ላንተ ቀላል ሊመስልህ ይችላል ለእሷ ግን በጣም ከባድ ነው የአእምሮ የስነልቦና ቀውስ ተስፋ መቁረጥ ያልሆነ ማንነት ውስጥ መግባት የበታችነት ስሜት ብዙ ብዙ ነገር ይካተታል አንተስ ከዛ ምን ተጠቀምክ?? አንተ ያደረከውን ሌላው እህትህ ላይ ቢያደርገውስ?? እህት ባይኖርህ ነገ ሴት ልጅህ ላይ እንደማይደርስ በምን እርግጠኛ ነህ?? ሁሉም የዘራውን ማጨዱ አይቀርም ይልቅ ጊዜህን አታጥፋ ካሉት ከዋክብቶች መሃል አስተውለህ ጨረቃህን ምረጥ። በእጅህ ያለችውን አርክሰህ ከምትተዋት አነግሰህ ተንከባከባት። አባት ስትሆን ደግሞ ለወንድ ልጅህ አርአያ ለሴት ልኽህ ደግሞ የምንግዜም ንጉስ ወደ ፊት ለሚያጋጥሟት ወንዶች መለኪያ ትሆናታለህ።


Share&Join
👇
@youthkiper
ወጣት ወንዶች ከሴቶች በበለጠ የእንቅስቃሴ ገደብ ሕጎችን ይጥሳሉ ተባለ

ወጣት ወንዶች ከሴቶች በበለጠ የእንቅስቃሴ ገደብ ሕጎች እንደሚተላለፉ ተገልጿል። በተለይ እድሜያቸው ከ19 እስከ 24 ከሆኑ ወጣቶች መካከል ግማሾቹ ጓደኞቻቸውን ወይም የቤተሰብ አባሎቻቸውን ለማየት ከቤታቸው ይወጣሉ ተብሏል።

በዚሁ ተመሳሳይ እድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ወጣት ሴቶች መካከል ደግሞ አንድ አራተኛ የሚሆኑት ያለመንቀሳቀስ ሕጉን ይጥሳሉ ብለዋል በዚሁ ዙሪያ ጥናት የሰሩ ተመራማሪዎች።

ተመራማሪዎቹ አክለውም መንግስታት ወጣቶች ላይ ያተኮሩ መልእክቶችን እንዲያስተላልፉ አሳስበዋል።
በዚሁ ጥናት ላይ የተሳተፉ ወጣቶች እንደገለጹት በቤት ውስጥ ረጅም ጊዜ ማሳለፍ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ይከታቸዋል።

በተለይ ደግሞ ቤተሰቦቻቸው ለወሳኝ ስራ ከቤት የሚወጡ ከሆነ ሕጎቹን የመተላለፍ እድላቸው ከፍተኛ ነው share&join us @youthkiper
https://t.co/Nze0yab25X አማካኝነት መልካም የፈጠራ ሀሳቦች እየደረሱን ነው። አቅማችን እና ትኩረታችንን ውጤታማ በሆኑ ተግባራት ላይ በማድረግ፣ የበለጸገች እና ያደገች ሀገርን እንገንባ። በፈጠራ ሥራ ተጠምደው ለሚገኙት ሁሉ አድናቆቴ ይድረስ።

#Pm_Dr_Abey_ahmed
@youthkiper
Opportunity

Good News! 600 Free Online Courses Just Launched by 190 Universities

Subjects: Computer Science, Mathematics, Programming, Data Science, Humanities, Social Sciences, Education & Teaching, Health & Medicine, Business, Personal Development, Engineering, Art & Design, and finally Science.

Details: https://bit.ly/600-online-courses

#600OnlineCourses #MOOCS @youthkiper
የፍቅር ግንኙነትዎን ሊገድሉ የሚችሉ ጉዳዮች

አስተማሪ ጽሑፍ ለሁሉም ወጣት #Share_it
የፍቅር ህይወት በተሞክሮ ውስጥ የምናልፍበትና በሂደት የምናዳብረው ክህሎት ነው፡፡ እንደ ሰው በፍቅር ግንኙነት ውስጥ መፈጸም የማይገባንና የፍቅር አጋራችንን ስሜት ሊጎዱ የሚችሉ ስህተቶችን ልንፈጽም እንችላለን፡፡ ለምሳሌ፡ የጓደኛችንን የልደት ቀን መርሳት፡ በቀጠሮ ሰዓት መዘግየት፡ የፍቅር ጓደኛችንን የስጦታ ምርጫ አለማወቅና የመሳሰሉት ለጊዜው ቅሬታ ቢፈጥሩም፤ ተወቃቅሰንና ተነጋግረን በይቅርታ ልናልፋቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የፍቅር ግኑኝነታችን ጤናማ ሆኖ እንዳይቀጥል የሚያደርጉና ቀጣይነቱን እንድንጠይቅ የሚያስገድዱን ስህተቶችም ይኖራሉ፡፡ የሚከተሉት አምስት ስህተቶች በፍቅር ግንኙነት ላይ አዳጋ ሊያስከትሉ ከሚችሉ ጉዳዮች ውስጥ ይካተታሉ፡፡

1.ምልዑነትን መጠበቅ (Expecting Perfection):- ብዙዎቻችን ወደ ፍቅር ግንኙነት የምንገባው ፍቅረኛችን ውብ እንደሆነ/ች እና በሁሉም ነገር ደግሞ ብቁ እንደሆኑ አድርገን አስበን ነው፡፡ በጊዜ ሂደት ውስጥ የፍቅር አጋራችን ጉደለቶች መታየት ሲጀምሩ ያንን ሰው አስበነው ወደ ነበረው ምልዑነት ለመቀየር ግርግር መፍጠር እንጀምራለን፡፡ ሰዎች ደግሞ በባህሪያቸው በማንነታቸው እንዳሉ ተቀባይነት እንዲያገኙ እንጂ “የመቀየር አለብህ/አለብሽ ” ግፊት ብዙም ምቾት አይሰጣቸውም፡፡ ለዚህ መፍትሄው የፍቅር አጋርዎን አሁን ባለበት ሁኔታ ሳያቅማሙ መቀበል፤ ሁሉም ሰው (እራስዎን ጨምሮ) ጉድለቶች እንዳሉበት መረዳትና የፍቅረኛችንን ክፍተቶች እኛ መሙላት የምንችልበት መንገድ ካለ መሞከር የተሻለ ነው፡፡

2.መወስለት (Cheating)፡- ፍቅር በመርህ ደረጃ የሁለት ተቀራኒ ፆታዎች የአካልና የመንፈስ ውህደትን ይጠይቃል፡፡ ከፍቅረኛችን አሻግረን ሌላ ይምናይ ከሆነ፤ ይባስ ብሎም ከሌላ ተቃራኒ ፆታ ጋር የስሜት ትስስር መፍጠር ወይም ወሲብ መፈጸም የፍቅር ግንኙነትን በፍጥነት ከሚገድሉ ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ስህተት ውስጥ የገቡ ከሆነ ማድረግ የሚገባዎት የፈጸሙትን ስህተት ለፍቅረኛዎ ነግሮ፤ በቀጣይ መደረግ ስለሚገባው ጉዳይ መወያየት ነው፡፡ ውስልትናን ከፍቅር ጓደኛ ደብቆ ማቆየት ቢቻልም በግንኙነታችን ላይ ተጽዕኖውን በተለያየ መንገድ ስለሚያሳርፍ ፍቅራችንን ይገድለዋል፡፡

3.ማኩረፍ (Silent treatment):- በፍቅር ግንኙነት ውስጥ አለመግባባቶችና ጸቦች ይከሰታሉ፡፡ ይሁን እንጂ ችግሮችን ለመፍታት የምንመርጠው መንገድ ማኩረፍ፤ ስልክ መዝጋትና መሸሽ ከሆነ የፍቅር ግንኙነታችን እየገደልነው ነው፡፡ ፍቅርን ጠብቀው ከሚያቆዩ ምሰሶዎች አንዱ ግልጽ ውይይት ነው፡፡ ንዴታችን እስኪበርድልን ጠብቀን በአልተግባባንበት ጉዳይ ላይ መነጋገር ወደተሻለ መንገድ ይመራናል፡፡ በተቃራኒው ያልተወያየንባቸው አለመግባባቶች በውስጣችን በተጠራቀሙ ቁጥር፤ ግንኙነታችን በየጊዜው ይረበሻል፡፡

4.ውሸት (Lying):-የፍቅር ግንኙነትን ጤናማነት ጠብቀው ከሚያቆዩ ነገሮች አንዱ ሀቀኝነት ነው፡፡ ማንኛውንም ጉዳይ ለፍቅረኛችን/ የትዳር አጋራችን በግልጽ የመናገር ልምድ ሲኖረን ግንኙነታችን ይጠነክራል፡፡ ነገር ግን ጓደኛችን በሆነ ጉዳይ ላይ ስንዋሽ ከያዘን/ከያዘችን በቀጣይ ለመታመን ዋስትና የለንም፡፡ ለምሳሌ፡- ስራ ቦታ አምሽቼ ወደ ቤት እየገባሁ ነው ያሉት አፍቃሪዎ ከሌሎች ጓደኞችዎ ጋር ካፌ ውስጥ ሲዝናኑ እንደነበር ቢያውቅ በሌላ ቀን ስራ ቦታ ቢያመሹ እንኳን የፍቅረኛዎን እምነት ማግኘት ይከብዳል፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን እውነቱን ብቻ የመነጋገር ልምድን ማካበት ይኖርብናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር የመወያየት ባህል ቢኖረን ግንኙነታችን ይጠነክራል፡፡ ከፍቅር አጋራችን ደብቀን የምንይዛቸው ጉዳዮች ካሉ በጊዜ ሂደት ግንኙነታችንን ሊያሻክሩ ይችላሉ፡፡

5.ቂም መቋጠር (Holding a grudge):- ማንም ሰው ከስህተት የጸዳ አይደለም፡፡ ከዚህ በፊት የተሰሩ ስህተቶችንና ይቅርታ የተጠየቀባቸውን ጉዳዮች ሁልጊዜ እንደ አዲስ እያነሱ ፍቅረኛን መውቀስ፤ አንቺኮ ከዚህ በፊትም እንዲህ አድርገሽኛል፤ አንተኮ ባለፈውም እንዲህ በድለኸኛል እየተባባልን የምንነታረክ ከሆነ ፍቅራችንን ውሃ እያስበላነው ነው፡፡ ከቂምና በቀል ያልጸዳ ግንኙነት መሰረቱ ጽኑ አይሆንም፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ያለፉ ስህተቶቸን በይቅርታ መርሳት፤ ወደፊት ደግመው እንዳይከሰቱ ደግሞ መፍትሄ መቀየስ ያሻል፡፡

መልካም የፍቅር ጊዜ!!!
@youthkiper
ዉድ ቤተሰቦቻችን እንዴት አደራቹ እንግዲህ እንደ ሁል ጊዜው ለናንተ ይመጥናል ያልነው እና ከናንተም አስተያየት እየተቀበልን እዚ ደርሰናል በጥያቄያቹ መሰረት በቅርቡ የጀመርነውን የትምርት እድል በውጭ ሀገር /scholarship ማስታወቂያዎችን እየለጠፍን እንገኛለን አሁንም እንደ ሁልጊዜ አስተያየቶቻቹ አይለየን @gzeman ላይ አስተያየታችሁን አድርሱን
ይህ መረጃ ላልደረሳችሁ የሀገራችን የጤና ባለሙያዎች!

የኳታር አየር መንገድ 100,000 ነፃ ትኬቶችን ለጤና ባለሙያዎች (Frontline Healthcare Professionals) አዘጋጅቷል። አንድ ባለእድል ሁለት ትኬት የሚደርሰው ሲሆን በአለም ዙርያ ላሉ የጤና ባለሙያዎች በእጣ የሚሰጥ ይሆናል፣ ትኬቱ ወደፈለጉት የአየር መንገዱ መዳረሻ መሄድ ያስችላል።

ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረጉ ያሉ የሀገራችን የጤና ባለሙያዎችም የዚህ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለሚያውቁት ሁሉ ይህን መረጃ ያስተላልፉ። እድሉን መሞከርያው ዛሬ የመጨረሻ ቀን ነው።

መመዝገቢያው ሊንክ:
bit.ly/2WHnwGs

@youthkiper
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ
ዉድ ቤተሰቦቻችን እንዴት አደራቹ እንግዲህ እንደ ሁል ጊዜው ለናንተ ይመጥናል ያልነው እና ከናንተም አስተያየት እየተቀበልን እዚ ደርሰናል በጥያቄያቹ መሰረት በቅርቡ የጀመርነውን የትምርት እድል በውጭ ሀገር /scholarship ማስታወቂያዎችን እየለጠፍን እንገኛለን አሁንም እንደ ሁልጊዜ አስተያየቶቻቹ አይለየን @gzeman ላይ አስተያየታችሁን አድርሱን
🌙 ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን 1441ኛው ለዒድ አል ፈጥር በሰላም አደረሳችሁ በአሉ የሰላም የፍቅር ይሁንላችሁ መልካም በአል 🌙
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ
ዉድ ቤተሰቦቻችን እንዴት አደራቹ እንግዲህ እንደ ሁል ጊዜው ለናንተ ይመጥናል ያልነው እና ከናንተም አስተያየት እየተቀበልን እዚ ደርሰናል በጥያቄያቹ መሰረት በቅርቡ የጀመርነውን የትምርት እድል በውጭ ሀገር /scholarship ማስታወቂያዎችን እየለጠፍን እንገኛለን አሁንም እንደ ሁልጊዜ አስተያየቶቻቹ አይለየን @gzeman ላይ አስተያየታችሁን አድርሱን
Forwarded from ወጣቱ ና ሙዱ
የዛሬው መልክት:
1. ከሰዎች ጋር ሮጠህ ያልደረስክበት ነገር ካለ ወደ ተነሳህበት
ተመልሰህ ከፈጣሪህ ጋር መሮጥ ጀምር፣ ያኔ ካሰብክበት
ሳይሆን ካሰበልህ ቦታ ትደርሳለህ፡፡
2. በአብዛኛው ጊዜ ሴቶች የፍቅርን ትርጉም የሚጠፋባቸው
በውበታቸው ማምለክ ሲጀምሩ ሲሆን ወንዶች ደግሞ
በገንዘባቸው ማምለክ ሲጀምሩ ነው፡፡
3. መጀመሪያ ለራስህ ራስህ መሆን ስትጀምር ለማን ምን
መሆን እንዳለብህ ትገነዘባለህ፡፡
4. የሰው ልጅ የማሰብ ችሎታው ሲጨምር የጓደኞቹን ብዛት
ይቀንሳል፡፡
5. ዝቅተኛ እውቀት ባለህ ቁጥር የምትተኛው እንቅልፍ ከፍተኛ
ይሆናል፡፡
6. ጓደኛን አለማመን ከመካድ የከፋ ነው፡፡
7. የራስህን ትኩስ እንጀራ ለመጋገር ስትል የሌላውን ቂጣ
አትርገጥ፡፡
8. አንዳንድ ሰዎች የሚወድቁት ሌሎችን በሁለት እግሮቻቸው
ለመርገጥ ሲጣጣሩ ነው፡፡
9. ሰው ከጊዜ እና ከማጣት ብዙ ይማራል፡፡
10. አንዳንዴ ሽንፈትም ከድል የበለጠ ዋጋ አለው/ ከማሸነፍ
ይልቅ በመሸነፍ ውስጥ ብዙ እውቀት አለ፡፡
11. ሠው የበለጠ እያገኘ በሄደ ቁጥር የበለጠ ስግብግብ
እየሆነ ይሄዳል፡፡
12. ሠዎች ትርጉም ያለው ሥራ መስራት ካልቻሉ የመኖር
ትርጉምም ይጠፋባቸዋል፡፡
13. የሰው ልጅ ከደስታው ይልቅ የሀዘኑን ጊዜያት መቁጠር
ይወዳል፡፡
14. ባንኮች ዝናብ ሳይኖር ዣንጥላ ያበድሩህና መዝነብ
ሲጀምር ግን ዣንጥላውን ይነጥቁሃል፡፡
15. አዋቂ ሆኖ ለመታየት የምናደርገው ጥረትና ከንቱ ድካም
አላዋቂ አድርጎ ያስቀረናል፡፡ join us @youthkiller
#Ethiotelecom የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እና መምህራን ትምህርታዊ መረጃዎችን ከ http://ndl.ethernet.edu.et/ በነፃ ማግኘት እንዲችሉ አደረገ::

Higher education institution students and teacher now can get educational information on http://ndl.ethernet.edu.et/ with free of charge.

@youthkipper
2024/09/21 11:08:46
Back to Top
HTML Embed Code: