Telegram Web Link
ሰሜን ጠለምት ደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት ገዳም እና በ1985 ዓ.ም ተሰርቆ ከሀገር ከወጣ ከ18 ዓመት በኃላ በ15 ሚሊዮን ዶላር ተሸጦ በ2003 ወደ አገራችን ተመልሶ የመጣው የቅዱስ ያሬድ የእጅ መስቀል!
✞ ቅዱስ ያሬድ የዜማ ሊቅ ብቻ አይደለም። አቡነ ያሬድ የቅድስት ቤተክርስቲያን ጌጧና መሠረቷ ሕይወቷና እስትንፋሷ ነው።
✞ አቡነ ያሬድ የመጽሐፍ መምህር (ብሉያትንና ሐዲሳትን የሊቃውንትንም መጻሕፍት አስማምቶ የተረጐመ) ነው።
✞ አቡነ ያሬድ ባለቅኔ (የቅኔ ጀማሪ) ነው።
✞ አቡነ ያሬድ ልዑለ ስብከት ነው።
✞ አቡነ ያሬድ ሰማዕት ነው።
✞ አቡነ ያሬድ ባሕታዊ ነው።
✞ አቡነ ያሬድ መናኝ ነው።
✞ አቡነ ያሬድ የሱራፌል አምሳያ ነው።
✞ አቡነ ያሬድ ጥዑመ ልሳን ነው።
✞ ቅዱስ ያሬድ የቤተ ክርስቲያን እንዚራ ነው።
✞ ቅዱስ ያሬድ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን ነው።
✞ ቅዱስ ያሬድ መዓርዒረ ዜማ ነው።
✞ አቡነ ያሬድ ካህን (ካህነ ስብሐት) ነው።
✞ ቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ ነው።
✞ ቅዱስ ያሬድ መዘምር ዘበድርሳን
✞ ቅዱስ ያሬድ ሊቅ (ርእሰ ሊቃውንት)
✞ ቅዱስ ያሬድ ዓርከ ሊቃውንት
✞ አቡነ ያሬድ መንፈሳዊ ደራሲ ነው።
✞ ቅዱስ ያሬድ የኢትዮጵያ ብርሃን ነው።
✞ አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም) የኾነ
✞ እግሮቹ በመልካም መንገድ የሚጓዙና ወደ መልካም መንገድ የሚያስጕዙ
✞ ልቡናው የቅድስና ማኅደር የኾነ
✞ ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ የኾነ
✞ አእምሮው የመጠቀ
✞ ድርሰቱ የተራቀቀ
✞ እስከ አርያም ተነጥቆ ዕፁብ ድንቅ ምሥጢራትን የተመገበ የሱራፌል አምሳያቸው ነው። ለዚህም ነው ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዱስ ያሬድን እንዲህ ሲል ያመሰገነው:-
"የመንፈስ ቅዱስ ምግብን የጠገበ፤ ከመጻሕፍት ኹሉ ትርጓሜያተ ድርሰትን ያሰባሰበ፤ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ሀገርን በጥዑም ማሕሌትና በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ፤ የመለኮት ቃልን በላይዋ ላይ እንደ ንጹሕ የወርቅ ሻሻቴ ያፈሰሰ ለኾነ ለካህኑ ያሬድ ሰላምታ ይገባል"
"ሰላም ለያሬድ ቀሲስ ዘጽጉብ እክለ መንፈስ ቅዱስ፤
ዘአስተጋብአ ምድራሳተ እምኲሎሙ መጻሕፍት
ወአሰርገዋ በሐዋዝ ስብሐት ወበጥዑም ማሕሌት
ለብሔረ ኢትዮጵያ በስብሐት ሃሌ ሉያ
ዘከዐወ ቃለ መለኮት ዲቤሃ
ከመ አስራበ ወርቅ ንጹሐ።"

ቅዱስ ያሬድ አክሱም ጽዮንን እየተሳለማት ሣለ ክብርት እመቤታችን ለቅዱስ ያሬድ ተገልጣለት ቅዱስ ኤፍሬምንና ቅዱስ አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ አምጥታ ድርሰታቸውንና ቅዳሴያቸውን እንዲያሰሙት በማድረግ ቅዱስ ያሬድንም ዜማውን እንዲደርስ እረድታዋለች፡፡ ኹለቱንም ታላላቅ ቅዱሳን ነጥቃ ወደ ቅዱስ ያሬድ ካመጣቻቸው በኃላ ‹‹አንተ ውዳሴዬን፣ አንተ ቅዳሴዬን ነግራችሁት በዜማ ያድርስ›› ብላቸው እነርሱም ለቅዱስ ያሬድ ነግረውት በዜማ አድርሶታል፡፡ ቅዱስ ያሬድም በመልክ በመልኩ እያደረገ ዜማውን ደረሰው፡፡ ዜማውንም ሲጨርስ የብርሃን እናቱ እመ አምላክ በያዘችው የብርሃን ባርካው ተስፋውን ነግራው ዐርጋለች፡፡
ይኽም የቅዱስ ያሬድ ድርሰቱ መነሻውም ሆነ መድረሻው ፍጹም መንፈሳዊ እንደሆነ ያሳያል። አባቶቻችንም ይኽን መንፈሳዊ መገለጥ በሥዕልም ጭምር ገልጠውታል። (ሽሬ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ይኽ ዓይነት ሥዕል ከሚገኙበት ገዳማት ውስጥ የሚገኘው አንዱ ነው።)

አቡነ ያሬድ ይባርክበት የነበረው የእጅ መስቀሉ በ1985 ዓ.ም በሆድ አደር ሌቦች አማካኝነት ተሰርቆ ከሀገር ወጥቶ ነበር። በፈረንሳይ ሀገር ለጨረታ ቀርቦ በ15 ሚሊዮን ዶላር ተሸጦ ነበር። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ተሰርቆ ከወጣ ከ18 ዓመት በኃላ በ2003 ወደ አገራችን ተመልሶ መጥቷል። ሊመለስ የቻለውም "ሚስተር ዣክ" የተባሉ በጎ አሳቢ ሰው "...ይህን መስቀል ኢትዮጵያ ውስጥ ጎብኝቼዋለሁ፣ የኢትዮጵያ ንብረት ነው" በማለት ወደ ሀገራችን እንዲመለስ ከሌሎች አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ልጆች ጋር በተደረገ ርብርብ ጨረታውን በ15 ሚሊዮን ዶላር አሸንፈው የአቡነ ያሬድን የእጅ መስቀል ወደ አገራችን መልሰውታል። አምላከ ቅዱስ ያሬድ
ክብር ያድልልን በእውነት!

አቡነ ያሬድ በምናኔ በኖረበት ቅዱስ ቦታ ላይ በስሙ ገዳም ተገድሞ መናንያን አሰረ ፍኖቱን ተከትለው ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው፣ በረዶውንና ውርጩን ታግሠው በስሙ እየተማጸኑ ይኖራሉ፡፡ በቦታው እሁድ እሁድ ከመሬት ውስጥ የከበሮ ድምጽ ይሰማል፣ ቅዱስ ያሬድ መቋሚያውን ወርውሮ ያፈለቀው ፀበል ዛሬም አለ፡፡ ጻድቁ በተሰወረበት በደብረ ሐዊ ተራራ ላይ ብርድ በእጅጉ በጸናበትና በረዶ በሚፈላበት በዚያ አስቸጋሪ ቦታ ላይ እጅግ አስቸጋሪውን የአየር ጠባይ ተቋቁሞ በቦታው ላይ ቢያንስ 7 ቀን ሱባዔ የሚይዝ ካለ ራሱ ቅዱስ ያሬድ እንደሚገለጥለት በቦታው ላይ የሚገኙ አባቶች ይናገራሉ።

አክሱም አቅራቢያ ቁጭ ብሎ ከትሏ ምሳሌ ወስዶ በተማረበት ቦታ ላይ አንዲት እናት ብቻዋን ለቅዱስ ያሬድ አስደናቂ ቤ/ክ በ2010 ዓ.ም አሠርታለታለች። ይኽም ለጻድቁ ለአቡነ ያሬድ ተስላ ስለቷ ደርሶላት እንደሆነ በቦታው ላይ ተነግሮናል። ይኽም ድንቅ ምስክርነት አቡነ ያሬድ ከዜማ ደራሲም በላይ መሆኑን አንድ ማሳያ ነው። በጸሎቱ ሀገርን የሚጠብቅ ባሕታዊ፣ በስሙ ለሚማጸኑት ሁሉ ከአምላኩ ዘንድ ምሕረትን የሚለምን ደገኛ ጻድቅ መሆኑን አንድ ማሳያ ነው።

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሙሉ አካሏና ብርሃኗ የኾነው አቡነ ያሬድ እንደነ ሄኖክና ኤልያስ ሞትን ሳያይ የተሰወረው በዛሬዋ ዕለት ነው። የከበረች በረከቱ ትደርብን! በጸሎቱ ይማረን!!!
ሰላም ለአጽፋረ እግርከ ከዋክብተ ጽባሕ ጽዱላት
እስከ ምዕራብ እግር አብርሃ መልዕልተ አጻብዕ ሰማያት
ከመ ተሰወርከ ያሬድ እምቅድመ ዐይኑ ለሞት
አድኃነነ በጸሎትከ እምዕለት እኪት
ወባልሓነ እምኩሉ መንሱት

ግንቦት ፲፩ ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት ዕለት እንኳን አደረሰን
ዜና ሕይወቱ፡-
ለቅዱስ ዮሐንስ
'አፈወርቅ'
ግንቦት 12 በዓለ እረፍቱ ነው፡፡ እንኳን አደረሳችሁ!
፠ ፠
+++###የቅዱሳን_አጽም####+++

=========--=============

ብዙ ጊዜ በሌላ ቤተ እምነት ያሉ ሰዎችን የሚቸግራቸው ለቅዱሳን የሚሰጠውን ክብር በተመለከተ ነው። በእርግጥ እኛ እናምነዋለን የሚሉትን መጽሐፍ በእርጋታ ቢመረምሩት የቅድስት ቤተክርስቲያንን አስተምህሮ ለመረዳት አይከብዳቸውም ነበር። እግዚአብሔርን ቅዱስ ብለን ስናመሰግን የቅድስና ምንጭና እርሱ መኾኑን በማመን ላይ ተመሥረተን ነው። የቅዱሳን ቅድስናን ስንናገር ግን ከእርሱ ያገኙት መኾኑን በመገንዘብ ነው። ያለ እግዚአብሔር ቅድስናን ያገኘ ማንም የለም ሊኖርም አይችልም። ቅዱሳን ቅዱስ የሚለውን ክብር የሚያገኙት ከእግዚአብሔር ነው፤ በመኾኑም ቅዱሳንን ቅዱስ ብለን ስናከብር አክባሪያቸው የኾነውን አምላክም እያከበርን እንደኾነ ፈጽሞ የማንዘነጋው ነገር ነው።

=========== =============

መጽሐፍ ቅዱስ እንኳንስ ቅዱሳንን የቅዱሳንን ልብስ እንኳን ሲያከብር እናገኛለን። ሁላችን የምናውቀው ቅዱስ ጳውሎስ የዚህ ትልቅ ማሳያ ነውና። ቅዱስ ጳውሎስ ልብስ ለብሶ ወጥቶ በልብሱ ላይ ባለ ኃይል ብዙ ሕሙማን ይፈወሱ እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ በሐዋ 19 ላይ በግልጽ አስቀምጦልናል። የቅዱስ ጳውሎስ ልብስ ቅዱስ ጳውሎስ ነው አንልም፤ ነገር ግን በቅዱሱ አካል በመነካቱ ምክንያት ተቀድሶ የታመመን ፈወሰ እንላለን! እንግዲያውስ እንኳንስ ቅዱሳንን አለማክበር ቀርቶ ምናለ ልብሳቸውን ባደረግን አያሰኝምን? ከዚህ በላይ ደግሞ የቅዱስ ጴጥሮስ ጥላው ይፈውስ እንደነበረ የሐዋ 5 ላይ ይገልጽልናል። እንግዲህ የቅዱሳን ልብሳቸው ብቻ ሳይኾን ልብሳቸው ያረፈበት ጥላ በራሱ ይፈውሳል የሚለውን ከመስማት የበለጠ ምን ድንቅ! ምንስ ብርቅ አለ?!

========== ==============

ቀደምት የቤተክርስቲያን አባቶች የቅዱሳንን አጽም "መንፈሳዊ ጸጋን የተሞሉ" ናቸው በማለት በእጅጉ ይገረማሉ። ይህን በተመለከተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቅዱስ ባስልዮስ፣ ቅዱስ ጎርጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም ሌሎችም ሊቃውንት አስተምረዋል። እነዚህ ቅዱሳን አባቶች የቅዱሳንን አጽም ብቻ ሳይኾን መቃብራቸውን "የመንፈሳዊ ቡራኬ" ምንጭ ያደርጉታል። መንፈሳዊ ኃይል ከቅዱሳን አጽም እንደ ፀሐይ ብርሃን ያበራል። ልብሳቸውና ከልብሳቸው ውጭ ያለው ጥላቸው እንደሚፈውስ ከተጻፈልን ስለ አካላቸውማ እንዴት ይበልጥ እንደኾነ ማሰብ አይከብድም። በእርግጥ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት አጽምን በሦስት ክፍል ይከፍሉታል አንደኛው ክፍል የቅዱስን አካል ነው፤ ሁለተኛው የቅዱሳን ልብሳቸው ነው፤ ሦስተኛ እነዚህን ሁለቱን ክፍሎችን የነኩ ሌሎች ልብሶችም ኾኑ ዕቃዎች ናቸው በማለት ይገልጻሉ።

=========== =============

መጽሐፍ እንዲህ ይላል "ኤልሳም ሞተ ቀበሩትም። ከሞዓብም አደጋ ጣዮች በየዓመቱ መጀመርያ ወደ ሀገሩ ይገቡ ነበር። ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ፤ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ላይ ጣሉት፤ የኤልሳም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውየው ድኖ በእግሩ ቆመ።" 2ነገ 13፡21። ይህ ጥቅስ አንደኛ የቅዱሳን ክብር ከምት በኋላም የጸና መኾኑን ያመለክታል። ተወዳጆች ሆይ! በመቃብር ያለው የኤልሳዕ አጽም የሞተን ማሥነሣት ከቻለ ሕያዊት የኾነች ነፍሱማ እንዴት በበለጠ ትረዳን ይሆን? ሁለተኛ ከጌታችን ትንሣኤ በፊት የትንሣኤን መኖር ያመላከተ ነው። ብዙ ቅዱሳን ሊቃውንት እንዳሉት የኤልሳዕ አጽም የሞተ ከስነሣ ክርስቶስ እንዴት ከሞት አልተነሣም ብለን ልንጠራጠር እንችላለን? ሦስተኛ እግዚአብሔር በቅዱሳን የሚሠራውን ድንቅና ከመነገር በላይ የኾነውን ሥራ እንመለከታለን፤ በሞተው (በዐረፈው) የሞተውን አስነሣ!! ከዚህ በተጨማሪ ምናልባትም በሕሊናችን የሞትን እኛ የሕሊና ሕይወትን ለማግኘት የቅዱሳን አጽም ሊረዱን እንደማችሉስ ማወቅ ከባድ ይሆንባችኋልን?

=========== =============

ሊቁ አባ ጀሮምም "የሰማዕታትን አጽሞች የተገለገሉባቸውን ዕቃዎች እናከብራለን እንጂ አናመልካቸውም። የምናመልከውና የምንሰግድለት ከእነርሱ ጋር ላለው ለእርሱ ለጌታችን ነው። እነርሱን ማክበር አምልኮ ጣዖት አይደለም፤ ምክንያቱም ክርስቲያን ሰማዕታትን እንደ አማልክት በመቁጠር አይሰግዱላቸውም ነበር፤ በሌላ በኩል ሰማዕታት ለእኛ ይጸልዩልናል እንጂ ሐዋርያትና ሰማዕታት በምድር ሳሉ ለሌሎች ሰዎች መጸለይ ከቻሉ ትግላቸውን በአሸናፊነት ካጠናቀቁ በኋላ በምድር ላይ ካቀረቡት ምልጃ እንዴት የበለጠ አያደርጉም?!" በመደነቅ ያብራራል። እንግዲህ የቅዱሳንን አጽም እናከብራለን እነርሱን ማክበር ማለት አክባሪያቸውን እግዚአብሔርን ማክበር ነው። የእነርሱን በረከት ለማግኘት መሻት፥ በእጅጉም መመኘት ጭምር ነው!!! እግዚአብሔር የቅዱሳንን አጽም በረከት ያድለን አሜን።

Deacon yohannis getachew
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

❖ ግንቦት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ °+

=>ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ
ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ?
ምንስ
እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ
ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ
አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: ግን
እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር::

<< ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው? >>

+ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ
ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ::
እነርሱ
ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው::
ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ
አደገ:: ገና
በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና)
ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::

+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም
አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ
ትምሕርት ይህ
ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2
ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኳን በሕይወተ ሥጋ እያለ
ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው::

+ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና
እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ
መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ
ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ
ሲኖር
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ
ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ::
ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን
ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት::

+ከዚህች እለት በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ
ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ
ራዕየ
ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ
ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው
ሳይታክት:
ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና
ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ
አንክሮ
ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና
ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር::

+ከዚህ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ
በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው
ወደውታልና
የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ
ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኳን የሚያወራ ኮሽ የሚል
የለም::
ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር::

+ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት
ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ
መካከል "
አፈ-ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ-ወርቅ
የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ
10 ዓመት
አቁሞታል::

+ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ
ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም
ይሔው
ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት
ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ
አወገዛት::
እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ
አጋዘችው::

+በተሰደደበት ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/
ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት
እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና
ለቅሶ ተደረገ::

+አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ
(ግብዣ አዘጋጀ):: በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ
ታጥቆ ሲጸልይ
ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ 12ቱ
ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) በግርማ ሲወርዱ
ተመለከተ::

+ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ:
ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን
እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ
እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ"
አላቸው::
ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ::

+በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ:
መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ
በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ
ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም::
ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ"
ብሎ በጉባኤ
መካከል ጠየቀው::

+"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ
ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ
አላወቃትም'
ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ
ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር::

+"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ
የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ
ይቀያየራል::
እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ
መልኳ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::

+'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው' እያለ
ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በኋላ ግን አንድ ሕብረ
መልክ
ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም::

+አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ
ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም
ሰምተው ሁሉም
ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ
ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::

+ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ
አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ!
እሰግድ
ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም
የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን
ምስጋናም
ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ
ወጥተዋል::

+ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ: በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን:
ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት
የተነሳ ታላቅ
ዝማሬና እንባ ተደርጓል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን
ባርኳል::

ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:-
*ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
*አፈ በረከት
*አፈ መዐር (ማር)
*አፈ ሶከር (ስኳር)
*አፈ አፈው (ሽቱ)
*ልሳነ ወርቅ
*የዓለም ሁሉ መምሕር
*ርዕሰ ሊቃውንት
*ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)
*ሐዲስ ዳንኤል
*ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)
*መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
*ጥዑመ ቃል - - -

+እግዚአብሔር ከቅዱሱ በረከት አብዝቶ: አብዝቶ: አብዝቶ
ይክፈለን::

+ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
ሥጋቸው ፈልሷል:: ይሕ የተደረገው ጻድቁ ከረፉ ከ56
ዓመታት
በኋላ ነው:: በዕለቱም ድንቅ ድንቅ ተአምራት
ተፈጽመዋል::

+እናታችን ርሕርሕቷ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ደግሞ
በዚሕ ቀን ስሟን ለጠራና መታሠቢያዋን ላደረገ የምሕረት
ቃል ኪዳን
ተቀብላለች::

❖ቸር አምላካቸው ከሁለቱም ብሩሃን ቅዱሳኑ ክብር
ያድለን::

❖ግንቦት 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ (የዓለም ሁሉ መምሕር)
2አቡነ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ (ፍልሠታቸው)
3.ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ (ቃል ኪዳን
የተቀበለችበት)
4.አባ አብርሃም ዘደብረ ሊባኖስ
5.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ
6.እስክንድር ንጉሠ ኢትዮዽያ
7.ቅዱስ መስቀል (የተአምር በዓሉ)
8.አባታችን ያሬድ (የማቱሳላ አባት)
9.ቅዱስ ሚናስ ዲያቆን

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2፡ ቅዱስ ድሜጥሮስ
3፡ ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4፡ ቅዱስ ቴዎድሮስ በናድሌዎስ
5፡ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
6፡ ቅዱስ ላሊበላ
7፡ ቅድስት መስቀል ክብራ

++"+ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም
ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር
አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች
አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት
ሁሉም ያበራል::
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን
አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት
ይብራ:: +"+ (ማቴ.
5:13-16)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
ረድኤት በረከቷ ይደርብንና በዚኽች ዕለት ግንቦት 12 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓሏ ታስባ የምትውለው እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ያደረገችው ተአምር ይህ ነው፡- ‹‹ከዕለታትም በአንደኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ዕለተ ሞቷን እያሰበች በጣና ባሕር ውስጥ ቆማ ስታለቅስና ስትጸልይ ሣለች ዲያብሎስ በሊቀ ጳጳሳት ተመስሎ እጅግ አስደናቂና ግሩም በሆነ አርአያ ወደ እርሷ መጣ፡፡ እርሷም ልትሰግድለት ወደደች፣ ከኃዘኗ ያረጋጋት ዘንድ ከቅዱሳን አንዱ የመጣ መስሏት ነበርና፡፡ ነገር ግን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ፈጥኖ ደረሰና ‹ይህ ሰይጣን እንጂ ጳጳስ ወይም ከቅዱሳን አንዱ አይደለምና አትስገጂለት› ብሎ ወደኋላዋ መለሳት፡፡

ዳግመኛም ‹አሁንም እንደልማድሽ ሂጂና ጠይቂው ማን እንደሆነ ይነግርሻል› አላት፡፡ በዚህን ጊዜ ወደ እርሱ ሂደችና ‹እሰግድልህ ዘንድ አንተ ማን ነህ?፣ ስምህስ ማን ይባላል?› ስትል ጠየቀችው፡፡ እርሱም ‹የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ› አላት፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከእርሷ ጋር እንዳለ አላወቀም ነበርና፡፡ እርሱ በእርሷ ላይ ተንኮል ለመሥራት እንደተራቀቀ ሁሉ እርሷም ነቃችበት ተራቀቀችበት፡፡ ቀጥሎም ‹እንግዲያውስ አንተ ሚካኤል ከሆንክ እስቲ ስለ ጽድቅ ነገር አስተምረኝ› አለችው፡፡ በዚህም ጊዜ ፈጽሞ ተደሰተ ከዓላማዋ አሳስቶ በእጁ የገባችለት መስሎታልና፡፡ እንዲህም አላት፡- ‹ለምን ሰውነትሽን ታደክሚዋለሽ? ከዛሬ ጀምሮ ከዚህ ኃላፊ ዓለም ድካም ማረፍ ያስፈልግሻል፣ መጾምና መጸለይስ ለምን ይጠቅምሻል? በባሕርስ ውስጥ ቆሞ መጸለይና ሰውነትን ማድከም ማን አስተማረሽ?› አላት፡፡ በዚያን ጊዜ ‹አንተ የምትለውና መጻሕፍት የሚናገሩት የተለያየ ሆነሳ!?› አለችው፡፡ እርሱም ‹ማነው የለያየን?› አላት፡፡ እርሷም ‹ከአነጋገርህ የተነሣ እኔ ለየኋችሁ› አለችው፡፡ እርሱም ‹እስኪ ልዩነታችንን ንገሪኝ?› አላት፡፡ እርሷም ‹መጻሕፍት የጾመ፣ የጸለየ፣ የለመነም ሁሉ ፍጹም ዋጋውን ያገኛል ይላሉ፡፡ አንተ ግን አትጹሙ፣ አትጸልዩ ትላለህ› አለችው፡፡ ይህንንም ባለችው ጊዜ በእርሷ ላይ ፈጽሞ ተቆጣ፣ እጅግም አድርጎ አስደነገጣት፡፡

ዳግመኛም መለሰችና ‹በምን ትሸነፋለህ?› አለችው፡፡ አሁንም ቁጣውን አወረደባት፡፡ በሦስተኛው ጊዜ ከተቆጣ በኋላ ‹በእነዚህ በሦስቱ ነገሮች እሸነፋለሁ› ሲል መለሰላት፡፡ ‹አንደኛ ማንኛውም ሰው በዚህ ዓለም በሚኖርበት ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት እንግዳ ተቀብሎ የሚያስተናግድ፤ ሁለተኛው በራሱ ላይ ችግርና መከራ በመጣበት ጊዜ መከራውን ታግሦ የሚኖር፤ ሦስተኛው ቀድሞም ከመሬት የተገኘሁ ነኝ፣ ኋላም ተመልሼ ወደ መሬት እገባለሁ እሞታለሁ እፈርሳለሁ ብሎ በማሰብ ትሕትና የሚሠራና የመሳሰሉትን ሁሉ የሚያደርግ እርሱ ፈጽሞ ያሸንፈኛል› አላት፡፡ ይህንንም ከተናገረ በኋላ ክንፉን እያማታ ወደ አየር በረረ፡፡ እርሷም ከግርማው የተነሣ ፈጽማ ደነገጠች፣ በመሬትም ላይ ወደቀች፡፡ በዚያን ጊዜ ለጌትነቱ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ ቅዱሳት በሚሆኑ እጆቹ ከወደቀችበት አነሣት፡፡ ከዚያም ‹ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራ ሆይ! አይዞሽ አትፍሪው ነገር ግን ወደ ላይ ወደ ሰማይ አቅንተሽ ተመለከቺ› አላት፡፡

ወደ ሰማይ አቅንታ በተመለከተች ጊዜ የዲያብሎስ ክንፉ በሰማይ ላይ ከጽንፍ እስከ አጽናፍ ተዘርግቶ (መላው ዓለምን ሞልቶ) አየች፡፡ ቀጥሎም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹በእኔ በባሕርይ አባቴ በአብ በባሕርይ ሕይወቴ በመንፈስ ቅዱስ ያላመነ ሊያሸንፈው አይችልም› አላት፡፡ ዳግመኛም ‹ማንም ሰው ኃጢአት ቢኖርበት ወደቀደመ ኃጢአቱ ባለመመለስ ንስሐ ቢገባ ከወጥመዱ ያመልጣል› አላት፡፡››

እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዲያቢሎስን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ብላ እርሱን ልትጠራው ብትሄድ እጁዋን ይዞ ሲኦል ቢከታት ቅዱስ ሚካኤል አድኗታል፡፡ ከእነርሱም ጋር በክንፋቸው ተንጠልጥለው ከሲኦል የወጡትን 10 ሺህ የሚሆኑን ነፍሳት ጌታችን አሥራት አድርጎ ሰጣት፡፡
የቅድስት እናታችን ረድኤት በረከቷ ይደርብን፣ በጸሎቷ ይማረን፡፡
✟፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧✟አርማጌዶን✟፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧✟

@wedefkr

ሰላም ለሁላችሁም ይሁን ! ውድ የአርማጌዶን አባላት ለዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት ስለ ኮሮና ቫይረስ እንዲሁም የሚዲያው ማቀላለጥ በተጨማሪም በዙሪያው ስለተሸረቡ ሴራዎች ይሆናል መልካም ቆይታ !

ሁላችንም እንደምናውቀው ሰሞኑን ሚዲያዎች ላይ ሁሉም ዜና ስለ ኮሮና እና ተያያዥ ጉዳዮች እየሆነ ከሆነ ሰነባብቷል እኛ ልናወራ የወደድነው ለምን ከዚህ የባሱ ገዳይ እና አስጨናቂ ቫይረሶች የተሰጣቸው ትኩረት ለምን ከኮሮና ቫይረስ ጋር የማይወዳደር ሆነ ? ለምን ለሌሎቹ የተነፈጋቸው ትኩረት ለኮሮና በሰፊው ተሰጠው ? የሚለው ነው የኛ ጥያቄ መልሱን በግርድፉም ቢሆን ለማቅረብ የሞከርንበትን ጽሁፍ እነሆ ።

መጀመሪያ ስለ የሚዲያዎች ገደብ ያለፈ ማሽቃበጥ ትንሽ ብናወራ ሳይሻል አይቀርም። ሚዲያ እንደምታውቁት የዘመኑ መረጃ ማስተላለፊያ መንገድ ነው ሲፈልጉ ማህበረሰቡን ያሸብሩበታል ፣ ሲፈልጉ ያዝናኑበታል ፣ ይከሱበታል ፣ ይፈርዱበታል ፣ ይመሰክሩበታል ፣ ያሴስኑበታል ፣ ያስጨንቁበታል ፣ ያባሉበታል ብቻ ምን አለፋችሁ የሰዎች አዕምሮ የማዘዣ ጣቢያ ሚዲያዎች ላይ ያለ ይመስል ሁሉም የሚዲያው ጥገኛ ሆኖአል ታዲያ ይሄ ከኮሮና እና ከኛ ጋር ምን አገናኘው ? 🤷🏽‍♂ የምትሉ ትኖራላችሁ ልመጣበት ነው ታገሱኝ !
የሆነ አባባል አለ " ችግርን አግዝፈህ ባየኸው ቁጥር መፍተሔው ይርቅሃል "
ይህ አባባል አሁን ካለው የኮሮና ቫይረስ ጋር ምን እንደሚያገናኘው እንመልከት የኮሮና ቫይረስ በጣም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ያለበት ነገር ነው እንዲሁም ህቡዕ ማህበረሰብ አባላት ሁሌ በሚከተሉዋት #Problem #Reaction #Solution መርሃቸው መሰረት አንድን ነገር ሲፈጥሩ ዝም ብለው አይፈጥሩም ምንም አይነት ነገር ያለበቂ ጥናትና እቅድ ምንም አያደርጉም ። በኮሮናም የምንመለከተው ይህን ነው ። እስቲ ኮሮናን ከዚህ ፍልስፍና ጋር አያይዘን እንመልከተው
#Problem
problem ማለት ችግር ነው ። የተፈጠረው ችግር ደግሞ ኮሮና ነው ኮሮና ብዙ ቀጥተኛ ጥቅሞች ለነሱ ይሰጣል የህዝብ ቁጥር መቀነስ ዋነኛው ነው ። ነገር ግን ችግሩ በራሱ የከፋ አይደለም ከችግሩ በኋላ የሚፈጠሩት ናቸው ዋነኛዎቹ ።

#Reaction
Reaction ማለት መስተጋብር ማለት ነው ስንተነትነው ለአንድ ድርጊት የሚሰጥ አፀፋዊ ምላሽ ማለት ነው ። በኮሮና ለተሰጠው ችግር የሚሰጠውን ምላሽ እንመልከት እዚህ ጋር ነው የዛሬ ነጥቤ አሁን ሚዲያዎች የሚያራግቡት ማህበረሰቡን ለማሸበር ነው ይህም #Solution ለተባለው የህቡዕ ማህበራቱ አደገኛ እቅድ በር ከፋች እንደመሆን ያገለግላል እንደምታውቁት ዘመኑ የመረጃ ነው ሚዲያ ያለው ሰው የፈለገውን ማድረግ ይችላል ለዚህም ነው በተቆጣጠሯቸው ሚዲያዎች ሁሉ ከኮሮና ውጪ ሌላ ትኩሳት የሌለብን ለማስመሰል ሽር ጉድ ሲውሉ የሚውሉት ከነዚህ ዘገባዎች መካከል
1
#WHO 250 ሚሊዮን የሚልቁ አፍሪቃውያን በኮሮና ቫይረስ ይጠቃሉ
2
በየሀገራቱ የስራ አጦች ቁጥር ይበዛል
3
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሀብ ይጋለጣሉ እና ብዙ ብዙ ተብሎለታል ይህ የሆነበት ምክንያት እኛ ላይ ሽብር ለመንዛት እና #Solution ብለው የሚያመጧቸውን ማንኛውም መፍትሔዎች ያለምንም ማንገራገር እንድንቀበል ለማድረግ ነው። ህዝቡ የሞት ጥላ እንዳጠላበት አድርገው የሚዘግቡት። እንዲሁም የዓለም ህዝብ ከነርሱ መንገድ ሌላ መውጫ እንደሌለን እንድናምን ነው ይሄ ሁሉ ላይ ታች የሚባለው የሀገራችን ሚዲያዎችም እኩይ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ያሉ ይመስላሉ በተለይ አንድ አንድ ሚዲያዎች ( ስማቸውን መጥቀስ ስለማልፈልግ ነው ) የ #Microchip ውጤት የሆኑ የክትባት ውጤቶችን በማስተዋወቅ እናም የ #Microchip ውጤት የሆኑ የወሊድ መቆጣጠሪያዎችን ስም በበጎ እያስተዋወቀ ይገኛሉ ይህ #Solution ለተባለው የተውኔቱ ክፍል መንገድ መጥረግ ነው ።
ለዛም ነው በየቀኑ ይህን ያህል ሰው ተያዘ ፣ ይህን ያህል አገገመ ፣ ይህን ያህል ሰው ሊሞት እና ሊያዝ እንደሚችል ተተነበየ ፣ ይህን ያህል ሰው በስራ አጥነት እና በረሀብ ሊሞት ይችላል እያሉ የሚነዘንዙን ።
ይሄን ስል ግን በእውኑ ዓለም ይህ እየሆነ አይደለም ወይም ሊሆን አይችልም ማለት አይደለም ነገር ግን ይሄ ሁሉ ዲስኩር የ #Solution አካል ለሆኑት ተያያዥ መፍትሔዎች መንገድ ጠረጋ ነው እስቲ በመቀጠል #Solution ወደተባለው የተውኔቱ ክፍል እናምራ ።

#Solution

፩ የክትባት ጉዳይ

ስለክትባት ብዙ የሴራ ተመራማሪዎች ብዙ ነገር ብለዋል ። እንዲሁም በአንዳንድ ሀገራት እስከ ህገመንግስታዊ ግዴታ የማድረግ እንቅስቃሴ ድረስ ብዙ አይተናል ነገር ግን የኮሮና ለየት ያለ ነው

ይቀጥላል ...

Share 👉 @wedefkr

join 👉 @wedefkr

comment 📥

@philipo123
(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ ምዕ. 6)
----------
40፤ አሁንም፥ አምላኬ ሆይ፥ በዚህ ስፍራ ወደሚሆነው ጸሎት ዓይኖችህ የተገለጡ፥ ጆሮችህም የሚያደምጡ እንዲሆኑ እለምንሃለሁ።

41፤ አሁንም፥ አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ከኃይልህ ታቦት ጋር ወደ ዕረፍትህ ተነሣ፤ አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በደስታ ደስ ይበላቸው።

42፤ አቤቱ አምላክ ሆይ፥ የቀባኸውን ሰው ፊት አትመልስ ለባሪያም ለዳዊት ያደረግህለትን ምሕረት አስብ።


(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 132)
----------
6፤ እነሆ፥ በኤፍራታ ሰማነው፥ በዱር ውስጥም አገኘነው።

7፤ ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን፤ እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን።

8፤ አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።

9፤ ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ፥ ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው።

10፤ ስለ ዳዊት ስለ ባሪያህ የቀባኸውን ሰው ፊት አትመልስ።
2025/02/25 08:29:48
Back to Top
HTML Embed Code: