Telegram Web Link
áˆĩለሚሰáˆĢው መáˆĩጊá‹ĩ ቅáˆŦá‰ŗ አለንáĸ (#áŠĨጅግ_በáŒŖም_አáˆĩቸáŠŗይ_áˆĩለሆነ_አሁኑኑ #share #share á‹Ģá‹ĩርጉ፡፡)
ምዕመናኖቹ የተነሡá‰ĩ በልማá‰ĩ ሰበá‰Ĩ áŠĨንጂ ለመáˆĩጊá‹ĩ መáˆĨáˆĒá‹Ģ ተá‰Ĩለው áŠĨንá‹ŗልሆነ ሃገር á‹ĢወቀውáĨ ፀሐይ የሞቀው ጉá‹ŗይ ነው፡፡
ቤተ ክርáˆĩቲá‹Ģኑ በአፍáˆĒáŠĢ ኅá‰Ĩረá‰ĩ ማáˆĩፋፊá‹Ģ ልማá‰ĩ ተነáˆĨá‰ļ አሁን á‰Ŗለበá‰ĩ á‰Ļá‰ŗ ሲቀመáŒĨ ተገá‰ĸው ማáŠĢáŠĢáˆģ á‰Ļá‰ŗ áˆĩላልተሰጠው ከዛáˆŦ ነገ ይሰጠኛል á‰Ĩሎ áŠĨየጠበቀ á‰Ŗለበá‰ĩ ሁኔá‰ŗ፤ በá‰Ļá‰ŗው ላይ ቀá‹ĩሞ á‰Ļá‰ŗ ለሌላው áŠĨምነá‰ĩ መáˆĩጠá‰ĩ በáˆĢሹ ውáˆŗáŒŖዊ á‰Ŋግርና ደá‰Ŗ ለመሆኑ አመላáŠĢá‰Ŋ ነው፡፡
በአáŠĢá‰Ŗá‰ĸው ለሚኖሩ á‰Ĩዙ ሕዝበ ክርáˆĩቲá‹Ģን በቂ መጠለá‹Ģ áŠĨንáŠŗን የሌለው ቅáŒŊረ ቤተ ክርáˆĩቲá‹Ģን áŠĨá‹Ģለና በተደጋጋሚ áŒĨá‹Ģቄ áŠĨየቀረበ ምላáˆŊ áˆŗይሰáŒĨ፤ ከአጠገቡ የ200 ሜá‰ĩር áŠĨንáŠŗን ርቀá‰ĩ በሌለው á‹Ģውም በቊáŒĨር አነáˆĩተኛ ለሆኑ ሙáˆĩሊም ወንá‹ĩሞá‰ģá‰Ŋን መንግáˆĨá‰ĩ 30áˆēህ የሚጠጋ áŠĢáˆŦ ሜá‰ĩር ለመáˆĩጠá‰ĩ መዘጋጀቱ፤ የተፈáˆĢ ዋልዋና የአሊ አá‰Ĩá‹ļ ለáŠĨáˆĩልምና á‹Ģደላ ደá‰Ŗን áŠĨንá‹ĩናáˆĩá‰ŗውáˆĩ á‹Ģደርገናል፡፡
++++++
በአ/ኅ/ደ/ም/ቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል áŠĢቴá‹ĩáˆĢል ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን á‰ĩይዩ በዛáˆŦው ዕለá‰ĩ ለáŠĨáˆĩልምና áŠĨምነá‰ĩ ተከá‰ŗዮá‰Ŋ የአምልኮ á‰Ļá‰ŗ áŠĨንዲሆን 30,000 áŠĢáˆŦ የሚሆን á‰Ļá‰ŗ ተሰáŒĨá‰ļ በነገው ዕለá‰ĩ የመሠረá‰ĩ á‹ĩንጋይ ለመáŒŖል áŠĨየተዘጋጁ ነው ሁላá‰Ŋሁም ፎá‰ļውን áŠĨና መልዕክቱን በማንኛውም ማሕበáˆĢዊ ሚዲá‹Ģ በማጋáˆĢá‰ĩ ሃይማኖá‰ŗዊ ግዴá‰ŗá‰Ŋንን áŠĨንወáŒŖ !!
በልማá‰ĩ ምክንá‹Ģá‰ĩ ሃይማኖá‰ĩን ማá‹ŗከም በግልáŒŊ áŠĨየá‰ŗየ ነው፡፡ በá‰Ĩዛá‰ĩ የáŠĻርá‰ļá‹ļክáˆĩ áŠĨምነá‰ĩ ተከá‰ŗዮá‰Ŋ የሚኖሩበá‰ĩን áˆĩፍáˆĢ በልማá‰ĩ áˆĩም በማሰቃየá‰ĩ በ10 áŠĨና 15 ቀነ ገደá‰Ĩ አፍርሰው ለ5 áŠĨና 6 ዓመá‰ŗá‰ĩ á‹Ģለምንም ልማá‰ĩ áŠĻና ሆኖ ተመልክተነዋል፡፡
ሆኖም አሁን በግልፅ ከላይ áŠĨንደጠቀáˆĩኩá‰ĩ ዓይነá‰ĩ á‹ĩርጊá‰ĩ ከመንግáˆĨá‰ĩ አáŠĢላá‰ĩ የሃይማኖá‰ĩ ማá‹ŗከም áˆĨáˆĢ áŠĨየተáŠĢሄደ ነው፡፡
መáˆĩጊá‹ĩ አይá‰ŗነáŒŊ áˆŗይሆን ከቤተክርáˆĩቲá‹Ģን ይáˆĢቅ አንረá‰ŖበáˆŊ የሚለው ሀáˆŗá‰Ĩ á‰ĸá‹Ģዝ የሰመረ ነውáĸ
በልማá‰ĩ áˆĩም áŠĨምነá‰ĩን የማáˆĩፉፉá‰ĩ ሴáˆĢ ከቀá‹ĩሞውም የሹማምንá‰ĩ ግá‰Ĩር áŠĨንደሆነ ይá‰ŗወቃልáĸ አሁን ደግሞ በቀá‹ĩሞ የሀገáˆĒቱ አáˆĩተá‹ŗደር ለልማá‰ĩ በማለá‰ĩ የፈረሱ አáŠĢá‰Ŗá‰ĸዎá‰Ŋን áŠĨና á‰Ļá‰ŗዎá‰Ŋን ለáŠĨáˆĩልምና አማኞá‰Ŋ መáˆĩጊá‹ĩ áŠĨንዲሰሩá‰Ŗቸው በመáˆĩጠá‰ĩ በáˆĩልáŒŖን ወንበር የተቀመጡ የáŠĨምነቱ ተከá‰ŗዮá‰Ŋ áŒĢና áŠĨá‹Ģደረጉ ይመáˆĩላልáĸ
ከá‰ŗá‰Ŋ በምáˆĩሉ ምá‰ĩመለከቱá‰ĩ á‰Ļá‰ĩ በተለምá‹ļ ቡልጋርá‹Ģ አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ ሀá‹Ģ ቀበሌ ወይም áˆŗይá‰Ŧርá‹Ģ የሚá‰Ŗለው አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ ሲሆን áŠĨዚህ አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ ላይ አá‰Ĩዛኞቹ የክርáˆĩá‰ĩና áŠĨምነá‰ĩ ተከá‰ŗዮá‰Ŋ የነበሩበá‰ĩ ነውáĸ áŠĨንደተለመደው ልማá‰ĩ በሚá‰Ŗለው መንግáˆĩá‰ŗዊ ቋንቋ ከተነሱ ከ4 ዓመá‰ĩ በላይ አáˆĩቆáŒĨረዋልáĸá‰Ļá‰ŗውም áŒĢáŠĢ ሆኖ ዛፎá‰Ŋ በቅለውበá‰ĩ መንግáˆĩá‰ŗዊ áˆŗይሆን ተፈáŒĨሯዊ ልማá‰ĩን ይዟልáĸ á‰ŗá‹ĩá‹Ģማ አሁን á‹Ģለው የአዲáˆĩ አበá‰Ŗ አáˆĩተá‹ŗደር የáŠĨáˆĩልምና ማዕከልና መáˆĩጊá‹ĩ ይሰሩበá‰ĩ ዘንá‹ĩ áŠĨዚá‹Ģው á‰Ļá‰ŗ ላይ 30 áˆē áŠĢáˆŦ ለግሷá‰ŋል የሚል ተá‰ŖáˆĢáˆĒ ወáˆŦ ሰማንáĸ መጠርጠር ደግነቱ አáˆĩቀá‹ĩሞ ለመጮህ የተመቸ ይሆናልáĸ ይደንቃል ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን የይዞá‰ŗ ማረጋገáŒĢ áŠĢርá‰ŗ áˆĩá‰ĩጠይቅ መከáˆĢ áŠĨንá‹ŗላየá‰Ŋ ሁላ áŠĨንደቀልá‹ĩ አንá‹ĩ መንደርን á‰Ĩá‹ĩግ አደርጎ áŠĨንáŠĢቹ ማለá‰ĩ ምን የሚሉá‰ĩ ፈሊáŒĨ ነውáĸ
á‰ŗá‹ĩá‹Ģ ምን á‰Ŋግር አለው የሚል áŒĨá‹Ģቄ መጠየቁ የማይቀር ነው የነዋáˆĒው áŠĨና የአáŠĢá‰Ŗá‰ĸው ቅáˆŦá‰ŗ ይህ መáˆĩጊá‹ĩ áŠĨንዲሰáˆĢበá‰ĩ የተሰጠው á‰Ļá‰ŗ በáŒŖም ቅርá‰Ĩ በሚá‰Ŗል ሁኔá‰ŗ ከ27 ዓመá‰ĩ በላይ የቆየ የቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን አለ በተለመá‹ļም ሙሉ áˆĩሙ የአፍáˆĒáŠĢ ኅá‰Ĩረá‰ĩ ደá‰Ĩረ ምህረá‰ĩ ቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል áŠĢቴá‹ĩáˆĢል ተá‰Ĩሎ ይጠáˆĢልáĸ á‰Ĩዙ የክርáˆĩá‰ĩá‹Ģን ነዋáˆĒ በሚገኝበá‰ĩ á‰Ļá‰ŗ መáˆĨáˆĢቱ áˆŗይከፉ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን አጠገá‰Ĩ የመáˆĩጊá‹ĩ áˆĨáˆĢን አምáŒĨá‰ļ መደቀኑ ይዋáŒŖላቹ ይለይላቹ የሚል መልáŠĨክá‰ĩ á‹Ģለው ይመáˆĩላልáĸ
áŠĢልጠፋ á‰Ļá‰ŗ አá‰Ĩá‹Ģተ ክርáˆĩቲá‹Ģናá‰ĩ በሚገኙበá‰ĩ ቅርá‰Ĩ ርቀá‰ĩ ላይ መáˆĩጊá‹ĩ áˆĩሊ á‰Ĩሉ ይሁንá‰ŗን መáˆĩጠá‰ĩ ምን የሚሉá‰ĩ á‰Ŋሎá‰ŗ ነውáĸ ከዚህ በፊá‰ĩም ለቱርክ á‰Ŗለሃá‰Ĩá‰ļá‰Ŋ የተዘጋጀ á‰Ļá‰ŗ áŠĨየተá‰Ŗለ ለሃይማኖá‰ŗዊ ግልጋሎá‰ĩ ሲውል á‰Ŗናይም ሰምተን ግን አልፈናልáĸ አሁን ደግሞ ይá‰Ŗáˆĩ á‰Ĩሎ አንá‹ĩ ቀበሌ የሚá‹Ģክል á‰Ļá‰ŗ መáˆĩጠá‰ĩ ወንበር ከመልቀቄ በፊá‰ĩ የሚል ሴáˆĢ የá‹Ģዘ áŠĨንዲመáˆĩለን ሆኗልáĸ
ሌላው á‰ĩልቁ á‰Ŋግር በá‰Ĩዙ á‰ĩáŠĨግáˆĩá‰ĩ ተቀመáŒĻ የነበረውን ወáŒŖá‰ĩ ማነáˆŗáˆŗቱ ነውáĸ በአáŠĢá‰Ŗá‰ĸው á‹Ģሉ ይሆን ከሩቅ á‹Ģሉ ወáŒŖá‰ļá‰Ŋ ይህን ሲሰሙ ከነፍáˆĩ á‹Ģለፍ á‰ĩርፍ ምን አለ በሚል ግá‰Ĩግá‰Ĩ ውáˆĩáŒĨ ገá‰Ĩተው አላáˆĩፈላጊ የሆኑ ግጭá‰ļá‰Ŋን አለመግá‰Ŗá‰Ŗá‰ļá‰Ŋን á‹Ģáˆĩከá‰ĩላልáĸ ተá‰ģá‰Ŋለን áŠĨንኑር á‰Ĩሎ የሰከነውን ወáŒŖá‰ĩ á‹Ģደገበá‰ĩ አáŒĨá‰ĸá‹Ģ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን ላይ መáŒĨá‰ļ "አላሁ አክበር" የሚል á‹ĩምáŒŊ ማሰማá‰ĩ ንቀá‰ĩ áˆĩለሚመáˆĩል አሁንም ከቤተክርáˆĩቲá‹Ģን ቅርá‰Ĩ ርቀá‰ĩ ለመáˆĩጊá‹ĩ ተá‰Ĩለው የሚሰጡ á‰Ļá‰ŗዎá‰Ŋ á‰ĸá‰ŗሰሰá‰Ĩá‰Ŗቸው áŒĨሊ ነውáĸ
ከ50 ሚልዮን በላይ ተከá‰ŗይ á‹Ģላá‰ĩን ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን መáŒĨቀም á‰Ŗንá‰Ŋልም መጉá‹ŗቱ ዋጋ የሚá‹Ģáˆĩከፍል áˆĩለሆን ዓመáŒŊ áˆŗይበረá‰ŗ ቡልጋርá‹Ģ አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ አፍáˆĒáŠĢ ህá‰Ĩረá‰ĩን á‰ŗኮ የቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን áŠĢለበá‰ĩ ቅርá‰Ĩ ርቀá‰ĩ ላይ የተሰጠው የመáˆĩጊá‹ĩ መáˆĩርá‹Ģ 30.000áŠĢáˆŦ መáˆŦá‰ĩ በተለዋጭ መáˆŦá‰ĩ á‰Ļá‰ŗ á‰ĸለወáŒĨ መልáŠĢም ነው ይህ áˆĨáˆĢ የሀገር á‰Ŗለውለá‰ŗ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģንን መናቅ ነውና ክቡáˆĢን ሹማምንá‰ĩ በተለይ የመሰጊዱ አሰáˆĒ መáŠŗንንá‰ļá‰Ŋ አáˆĩቡበá‰ĩáĸ
ወáˆŦ ነጋáˆŦ áŠĨንá‹ŗበጀው ነገ በ12 የመሠረá‰ĩ á‹ĩንጋይ በከንቲá‰Ŗው áŠĨና በሚኒáˆĩተር ሞፈáˆĒá‹Ģá‰ĩ የሚáŒŖል ሲሆን የቤተክርáˆĩቲá‹Ģናá‰Ŋን ሰበáŠĢ ጉá‰Ŗኤ áŠĨና አáˆĩተá‹ŗደር መáˆĩጊá‹ĩ ይሰáˆĢበá‰ŗል የተá‰Ŗለበá‰ĩን á‰Ļá‰ŗ አይተዋል በá‰Ļá‰ŗው የáŠĨምነቱ ተከá‰ŗዮá‰Ŋ ለነገው መሠረá‰ĩ á‹ĩንጋይ የሚáŒŖልበá‰ĩን ሲá‹Ģጸዱ ተመልክተዋልáĸ
áŠĨኛ ጉá‹ŗá‹Ģá‰Ŋን ከሙáˆĩሊም ወንá‹ĩሞá‰ģá‰Ŋን ጋር አይደለም áŒĨá‹Ģቄá‹Ģá‰Ŋን áŠĨዚህ á‰Ļá‰ŗ ላይ አጠገá‰Ĩ ለአጠገá‰Ĩ ሕገ መንግáˆĩቱ ላይ የተቀመጠውን áŠĨንáŠŗን á‰Ŗላከበረ መልኩ 200 ሜá‰ĩር áŠĨንáŠŗን በማይሞላ ርቀá‰ĩ áŠĨንዴá‰ĩ ይá‰ŗሰá‰Ŗልáĸ

á‰ĩልቁ á‰Ŋግር መáˆĩጊá‹ĩ መሰáˆĢቱ áˆŗይሆን
1. በá‰Ļá‰ŗው የነበረውን ሕዝበ ክርáˆĩቲá‹Ģን ለልማá‰ĩ በሚል ሰበá‰Ĩ ከቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል ቤተ-ክርáˆĩቲá‹Ģን አርቀው በግፍ መውሰá‹ŗቸው፤
2. ከá‰Ļá‰ŗው በቅርá‰Ĩ ርቀá‰ĩ የቄáˆĢ መáˆĩጊá‹ĩ áŠĨá‹Ģለ ሌላ መጨመር፤
3. ከá‰Ļá‰ŗው በቅርá‰Ĩ ርቀá‰ĩ ከሚገኘው ከቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል ቤተ-ክርáˆĩቲá‹Ģን አጠገá‰Ĩ መሰáˆĢቱ ይህ የሚá‹Ģáˆĩከá‰ĩለው የá‹ĩምፅ መረá‰ŖበáˆŊ ወá‹ŗልተፈለገ ግጭá‰ĩ á‹ĢመáˆĢል፤
4. የቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል ቤተ-ክርáˆĩቲá‹Ģን ለረጅም ዓመá‰ŗá‰ĩ ሲá‹Ģነáˆŗ የነበረው የá‰Ļá‰ŗ áŒĨá‹Ģቄ ምንም ምላáˆŊ áˆŗá‹Ģገኝ ይá‰Ŗáˆĩ á‰Ĩሎ á‰Ļá‰ŗው ጠá‰Ŗá‰Ĩ áˆĩለሆነ ከቅፅረ ቤተ-ክርáˆĩቲá‹Ģኑ ውáŒĒ ሆነው የሚá‹Ģáˆĩቀá‹ĩሹá‰ĩን ምዕመናን በá‹ĩምፅ የሚበክል ሌላ የዕምነá‰ĩ ተቋም ማቋቋም የማንá‰ŗገሰው á‹ĩርጊá‰ĩ ነውáĸ
5. á‰Ļá‰ŗውን መንግáˆĨá‰ĩ የማይሠáˆĢበá‰ĩ ከሆነ ለተፈናቀሉá‰ĩ ምዕመናን ተመልáˆļ á‰ĸሰáŒĨ፡፡ (ምዕመናኖቹ የተነሡá‰ĩ በልማá‰ĩ ሰበá‰Ĩ áŠĨንጂ በመáˆĩጊá‹ĩ ሰበá‰Ĩ áŠĨንá‹ŗልሆነ ሃገር á‹Ģወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉá‹ŗይ ነው፡፡)
6. ከመá‰ŧ ጀምሮ ነው ቤተ ክርáˆĩቲá‹Ģንና ሌሎá‰Ŋ የáŠĨምነá‰ĩ á‹ĩርጅá‰ļá‰Ŋ ማምለáŠĒá‹Ģ á‰Ļá‰ŗቸውን ሲሠሊ መሠረá‰ĩ á‹ĩንጋይ ለማáˆĩቀመáŒĨ ከንቲá‰Ŗውና የሰላም ሚኒáˆĩተር ተገኝተው የሚá‹Ģውቁá‰ĩ፤ ዛáˆŦáˆĩ ምን አዲáˆĩ ነገር አግኝተው ይሆንን!!!
*** áˆĩለዚህ ይህንን ተግá‰Ŗር መንግáˆĨá‰ĩ በአáˆĩቸáŠŗይ áŠĨንዲá‹Ģቆም በáŠĨግዚአá‰Ĩሔር áˆĩም áŠĨንጠይቃለን፤ áŠĢልሆነ ግን ወደ አላáˆĩፈላጊ ግጭá‰ĩ á‹ĢመáˆĢናልáĸ
** መሠረá‰ĩ ለመáŒŖል የሚገኙá‰ĩ ከንቲá‰Ŗውና የሰላም ሚኒáˆĩተር ሞፈáˆĒá‹Ģá‰ĩም ሌላው የáŠĨምነá‰ĩ ተቋም ላይ ለመሠረá‰ĩ á‹ĩንጋይ ተገኝተው የማá‹Ģውቁá‰ĩን áŠĨዚህ ልገኝ á‰Ĩለው á‹Ģሰቡá‰ĩን ልá‰Ĩ á‰Ĩለው á‰ĸá‹Ģáˆĩቡበá‰ĩ መልáŠĢም ነው፡፡
''ይá‰ĩá‰Ŗረክ አምላከ አበዊነ''
(ዘገá‰Ŗው የአፍáˆĒáŠĢ ኅá‰Ĩረá‰ĩ ደá‰Ĩረ ምሕረá‰ĩ ቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል ቤተ ክርáˆĩá‹Ģን ሰ/á‰ĩ/ቤá‰ĩ ነው፡፡)
ቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል 12â™Ĩ
ከሚáŠĢኤል በቀር የሚረá‹ŗኝ ማንም የለምáĸ á‹ŗን ፲áĨáŗፊ
#የቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤልን áˆĩም በጠáˆĢን ቊáŒĨር የምንመሰክረው áˆĩለ áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ነው፤ ምክንá‹Ģቱም የáˆĩሙ á‰ĩርጓሜው áŠĨንደ áŠĨግዚአá‰Ĩሔር á‹Ģለ ማን ነው áˆĩለሚል
በመሆኑም áŠĨግዚአá‰Ĩሔርን በá‰Ŗሕርይ የሚመáˆĩለውáĨ
በáˆĨልáŒŖንም የሚተáŠĢከለውáĨ በምá‹ĩርም በሰማይም áŠĨንደሌለ የሚናገር ልዩáĨ ክቡር áˆĩም ነውáĸ የነá‰ĸá‹Ģá‰ĩ አለቃ ሙሴ á‰Ŗሕረ ኤርá‰ĩáˆĢን ለሁለá‰ĩ ከፍሎ ሕዝቡን á‹Ģáˆģገረለá‰ĩንና ፈርዖንን ከነሠáˆĢዊቱ á‹Ģሰጠመለá‰ĩን አምላክ áŠĨግዚአá‰Ĩሔርን በመዝሙር ሲá‹ĢመሰግንáĨ ÂĢአቤቱ በአማልክá‰ĩ መáŠĢከል (በáˆĩም አማልክá‰ĩ ከሚá‰ŖሉáĨ በáˆĩመ አማልክá‰ĩ ከሚጠሩáĨ አንá‹ĩም አማልክá‰ĩ ዘበጸጋ ከተá‰Ŗሉ ከነá‰ĸá‹Ģá‰ĩ ከáŠĢህናá‰ĩ መáŠĢከል) አንተን የሚመáˆĩል ማነው? በቅዱáˆŗንም ዘንá‹ĩ áŠĨንደ አንተ የከበረ ማነው?Âģ á‰Ĩሏልáĸ ዘጸ ፲፭áĨ፲፩áĸ ቅዱáˆĩ á‹ŗዊá‰ĩምáĻ ÂĢአቤቱáĨ ከአማልክá‰ĩ የሚመáˆĩልህ የለም፤Âģ á‰Ĩሏልáĸ (መዝ ፚ፭áĨ፰)áĸ
ቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል ለፍáŒĨረá‰ŗá‰ĩ ሁሉ የሚáˆĢá‹ŗና የሚá‹Ģዝን የምሕረá‰ĩና የመá‹ŗኛ፤ የሰላም መልአክ ነው፡፡ ‹‹በዚá‹Ģም ዘመን áˆĩለ ሕዝá‰Ĩህ ልጆá‰Ŋ የሚቆመው á‰ŗላቁ አለቃ ሚáŠĢኤል ይነáˆŖልâ€ēâ€ē (á‹ŗን.፲áĢáĨፊ)በማለá‰ĩ በነá‰ĸዩ á‹ŗንኤል የተነገረ ሲሆን በሌላ á‰Ļá‰ŗ ‹‹ከዋነኞቹ አለቆá‰Ŋ አንዱ ሚáŠĢኤል ሊረá‹ŗኝ መáŒŖâ€ēâ€ē (á‹ŗን. ፲áĨ፲áĢ) በማለá‰ĩ á‹Ģáˆĩረá‹ŗል፡፡
ቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል አርምሞ á‰ĩዕግáˆĨá‰ĩን የሚወá‹ĩ መልአክ ነው፡፡ ‹‹የመላáŠĨክá‰ĩ አለቃ ቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል ከዲá‹Ģá‰Ĩሎáˆĩ ጋር በተከáˆĢከረ ጊዜ áˆĩለ ሙሴ áˆĨጋ ሲነጋገር ጌá‰ŗ ይገáˆĨáŒŊህ አለው áŠĨንጂ የáˆĩá‹ĩá‰Ĩን ፍርá‹ĩ ሊናገረው አልደፈረምâ€ēâ€ē (ይሁá‹ŗ ፊáĨ፱)
ቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል ከáŠĨግዚአá‰Ĩሔር በተሰጠው ኃይል ዲá‹Ģá‰Ĩሎáˆĩን á‹ĩል የነáˆŖ መልአክ ነው፡፡ ‹‹በሰማይ áŒĻርነá‰ĩ ተነáˆŖ ሚáŠĢኤልና áŠĨርሹ መላáŠĨክá‰ĩ ከዘንá‹ļው ከመላáŠĨክቱም ጋር ተዋጉâ€ēâ€ē (áˆĢáŠĨ. ፲áĒáĨ፯)ይላልáĸ
በá‹Ģለንበá‰ĩ á‰Ļá‰ŗ ቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል በክንፉ ከልሎ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠá‰Ĩቀን!
† በመላው ዓለም የምá‰ĩገኙ áŠĻርá‰ļá‹ļክáˆŗውá‹Ģን አáŒĨá‰Ĩቃá‰Ŋሁ ተቃወሙ!! †
★ዓá‰Ĩይ አህመá‹ĩና á‰ŗከለ ኡማ የነጃዋር መሐመá‹ĩን የፓለቲáŠĢ አፍ ማዘጊá‹Ģ áŠĨንዲሆን áŠĻርá‰ļá‹ļክáˆĩ ተዋህá‹ļን መáˆĩዋዕá‰ĩ áŠĨá‹Ģደረጉ ነውáĸ★
★ 400ኛ መáˆĩáŠĒá‹ĩ በአዲáˆĩ አá‰Ŗá‰Ŗ ለመá‰ĩከል 30 áˆēህ áŠĢáˆŦ ሜá‰ĩር áŠĨየሰጡ ነውáĸ★
★አክáˆĢáˆĒ ሙáˆĩሊሞá‰Ŋ የተወሰነ ግርግር áŠĨá‹Ģáˆĩነሱ ተለዋጭ á‰Ļá‰ŗ ይሰጠን በማለá‰ĩ በመሰáˆĒ አáŠĢሄá‹ĩ ሕገ ወáŒĨ የመáˆŦá‰ĩ ወáˆĢáˆĢ መፈጸምን ከመንግáˆĨá‰ĩ ጋር ሆነው áŠĨየሰሩ ነውና ልንነቃና ልናáˆĩቆማቸው ይገá‰Ŗልáĸ★
★ አሊ አá‰Ĩá‹ļ የአዲáˆĩ አበá‰Ŗ ከንቲá‰Ŗ áŠĨá‹Ģለ ከ270 በላይ መáˆĩáŠĒá‹ļá‰Ŋ áŠĨንዲሰሩ መáˆŦá‰ĩ በገፍ áŠĨየሰጠ ክርáˆĩቲá‹Ģኖá‰Ŋን ክፋኛ ይበá‹ĩል ነበርáĸለፕሮፓጋንá‹ŗው የሚጠቀመው ቃል áˆĢጉኤልና አኗር መáˆĩáŠĒá‹ĩ ፊá‰ĩለፊá‰ĩ ናቸው ምን ሆኑ áŠĨá‹Ģለ ከቤተክርáˆĩቲá‹Ģን አቅáˆĢá‰ĸá‹Ģ መáˆĩáŠĒá‹ļá‰Ŋ በማáˆĩተከል አክáˆĢáˆĒ áŠĨáˆĩልምናን á‹Ģáˆĩፋፋ ነበር በáŠĨነዚህ መáˆĩáŠĒá‹ļá‰Ŋ á‰Ĩዙ ጊዜ ገጀáˆĢና የáŒĻር መáˆŗáˆĒá‹Ģ ይáˆĢገፍá‰Ŗቸው አá‹ĩማና ክርáˆĩá‰ĩና ጠል áˆĩá‰Ĩከá‰ļá‰Ŋ ይተላለፋá‰Ŗቸው ነበር አሁንም áŠĨየተደረገ á‹Ģለው ተመáˆŗáˆŗይ የáŒĨፋá‰ĩ ሴáˆĢ በመሆኑ ሕዝበ ክርáˆĩቲá‹Ģን በአንá‹ĩነá‰ĩ በመቆም ይህንን መንግáˆĨá‰ŗዊ ጋጠወáŒĨነá‰ĩ በአáˆĩቸáŠŗይ ልናáˆĩቆም ይገá‰Ŗልáĸ★
መናፍቁ ዓá‰Ĩይ አህመá‹ĩና መናፍቁ á‰ŗከለ ኡማ áŠĨጅግ በሚá‹Ģáˆŗፍር ሁኔá‰ŗ ጊዚá‹Ģዊ áˆĩልáŒŖናቸውን ተገን አá‹ĩርገው ፍጹም ኃላፊነá‰ĩና ተጠá‹Ģቂነá‰ĩ በጎደለው አá‹ĩሎአዊ አሰáˆĢር ዓይን á‹ĢወáŒŖ መንግáˆĨá‰ŗዊ ሕገ ወáŒĨነá‰ĩ በአዲáˆĩ አá‰Ŗá‰Ŗ ከተማ ውáˆĩáŒĨ áŠĨየፈጸሙ ነውáĸ
ሕዝበ ክርáˆĩቲá‹Ģን ከንፈር áŠĨየመጠáŒĨን ምን ይደረግ á‰ŗዲá‹Ģ በሚል የáˆĩንፍና ንግግር በቸልá‰ŗ የምናልፈው áˆŗይሆን áŠĨáˆĩáŠĢሁን ለፓለቲáŠĢ á‰ĩርፍና ተቀናቃኞá‰ģቸውን ለማáˆĩደሰá‰ĩ የሰጡá‰ĩን ሕገ ወáŒĨ á‰Ļá‰ŗዎá‰Ŋና አሁንም ለመáˆĩጠá‰ĩ á‹Ģዘጋጁá‰ĩን á‰Ļá‰ŗ ሁሉ በከፍተኛ ተቃውሞ ማáˆĩመለáˆĩ ይኖርá‰Ĩናልáĸ
መሰáˆĒው ዓá‰ĸይ አህመá‹ĩ የአረá‰Ĩ ሃገáˆĢá‰ĩ መáˆĒዎá‰Ŋን ለማáˆĩደሰá‰ĩና ከáŠĨነርሱ የሚለቃቅመውን ገንዘá‰Ĩ ላለማáŒŖá‰ĩ ሕገ ወáŒĨ መáˆĩáŠĒá‹ļá‰Ŋ በከተማው ውáˆĩáŒĨ በከፍተኛ ሁኔá‰ŗ áŠĨንዲáˆĩፋፉ áŠĨá‹Ģደረገ ይገኛልáĸ
ከá‰ŗá‰Ŋ በፎá‰ļ የምá‰ĩመለከቷቸው á‰Ļá‰ŗዎá‰Ŋ በመንግáˆĩá‰ŗዊ ሕገ ወáŒĨ አሰáˆĢር ለመáˆĩáŠĒá‹ĩ መáˆĨáˆĒá‹Ģነá‰ĩ የተሰጡ በመሆናቸው á‰ŖáˆĩቸáŠŗይ ተመልሰው ሀገáˆĢዊ ልማá‰ĩ ሊáŠĢሄá‹ĩá‰Ŗቸው ይገá‰Ŗልáĸ
ሕዝበ ክርáˆĩቲá‹Ģን ሆይ!! ሀገር ውáˆĩáŒĨ የተረጋጋ ሰላም áŠĨንዲመáŒŖ á‰Ĩለን áŠĨáˆĩከ ዛáˆŦ ሁሉን ነገር በዝምá‰ŗ ማለፋá‰Ŋንን áŠĨንደ ፍáˆĢá‰ģና áŠĨንá‹ŗላዊቅነá‰ĩ ቆáŒĨረውá‰ŗልáĸምንም አá‹Ģመጡም á‰Ĩለው ክፋኛ ንቀውናልáŖ የአá‰Ŗá‰ļá‰ģá‰Ŋንንም ርáˆĩá‰ĩ ለፓለቲáŠĢ ፍጆá‰ŗቸው ማሟá‹Ģ áŠĨንዲውል ለአክáˆĢáˆĒ ሙáˆĩሊሞá‰Ŋ አáˆŗልፈው ሰáŒĨተዋል ለዚህም ነው የáŠĻርá‰ļá‹ļክáˆĩ ተዋሕá‹ļ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን በፍርá‹ĩ ቤá‰ĩ ለዓመá‰ŗá‰ĩ áŠĨየተከáˆĢከረá‰Ŋበá‰ĩ á‹Ģለውን የቀá‹ĩሞ የá‰Ļá‰ŗ ይዞá‰ŗዋን ለመáˆĩáŠĒá‹ĩ መáˆĩáˆĒá‹Ģነá‰ĩ አáˆŗልፎ በመáˆĩጠá‰ĩ ሕዝበ ክርáˆĩቲá‹Ģንን በንቀá‰ĩ áŠĨá‹Ģáˆĩቆጡ áˆĩለሆነ ክርáˆĩቲá‹Ģኖá‰Ŋ አáŒĨá‰Ĩቀን ልንá‰ŗገል ይገá‰Ŗልáĸ
በፎá‰ļው ላይ የምá‰ĩመለከቱá‰ĩ በሕገ ወáŒĨ መንግáˆĨá‰ŗዊ ውáˆŗኔ ለመáˆĩáŠĒá‹ĩነá‰ĩ የተሰጡá‰ĩ á‰Ļá‰ŗዎá‰Ŋ
1ኛ.አፍáˆĒáŠĢ ሕá‰Ĩረá‰ĩ áŒŊ/ቤá‰ĩ አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ
2ኛ.ተክለ ሃይማኖá‰ĩ ሰፈር ጠማማ ፎቅ አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ
3ኛ.áŠĢáˆŗንá‰Ŋáˆĩ መንገá‹ĩ á‹ŗር ላይ
4ኛ.ሸáˆĢተን ለልማá‰ĩ ተá‰Ĩሎ የተከለለ á‰Ļá‰ŗ
5ኛ.በአዲáˆĩ አበá‰Ŗ ለቡ መá‰ĨáˆĢá‰ĩ ኃይል ልዩ áˆĩሙ ንዋይ á‰ģሌንጅ የሚá‰Ŗል አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ በሕገ ወáŒĨ የመáˆŦá‰ĩ ወረáˆĢ መáˆĩáŠĒá‹ļá‰Ŋ በአጭር ርቀá‰ĩ ተተክለዋልáĸ
6ኛ.በአዲáˆĩ አበá‰Ŗ አለምá‰Ŗንክ á‰ĩውልá‹ĩ ተáˆĩፋ á‰ĩቤá‰ĩ አጠገá‰Ĩና ሀይሌጋርመንá‰ĩ በወረáˆĢ የተሰሩ መáˆĩጊá‹ļá‰Ŋ በመሰáˆĒው ዓá‰Ĩይ አህመá‹ĩና በá‰ŗከለ ኡማ አáˆĩተá‹ŗደር ነውáĸ
በአፍáˆĒáŠĢ ሕá‰Ĩረá‰ĩ ደá‰Ĩረ ምሕረá‰ĩ ቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል áŠĢቴá‹ĩáˆĢል ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን á‰ĩይዩ በዛáˆŦው ዕለá‰ĩ ለáŠĨáˆĩልምና áŠĨምነá‰ĩ ተከá‰ŗዮá‰Ŋ የአምልኮ á‰Ļá‰ŗ áŠĨንዲሆን 30,000 áŠĢáˆŦ የሚሆን á‰Ļá‰ŗ ተሰáŒĨá‰ļ በነገው ዕለá‰ĩ የመሠረá‰ĩ á‹ĩንጋይ ለመáŒŖል áŠĨየተዘጋጁ ነው ሁላá‰Ŋሁም ፎá‰ļውን áŠĨና መልዕክቱን በማንኛውም ማሕበáˆĢዊ ሚዲá‹Ģ በማጋáˆĢá‰ĩ ሃይማኖá‰ŗዊ ግዴá‰ŗá‰Ŋንን áŠĨንወáŒŖ !!
በልማá‰ĩ ምክንá‹Ģá‰ĩ ሃይማኖá‰ĩን ማá‹ŗከም በግልáŒŊ áŠĨየá‰ŗየ ነው፡፡ በá‰Ĩዛá‰ĩ የáŠĻርá‰ļá‹ļክáˆĩ áŠĨምነá‰ĩ ተከá‰ŗዮá‰Ŋ የሚኖሩበá‰ĩን áˆĩፍáˆĢ በልማá‰ĩ áˆĩም በማሰቃየá‰ĩ በ10 áŠĨና 15 ቀነ ገደá‰Ĩ አፍርሰው ለ5 áŠĨና 6 ዓመá‰ŗá‰ĩ á‹Ģለምንም ልማá‰ĩ á‰Ŗá‹ļ ሆኖ ተመልክተነዋል፡፡
ሆኖም አሁን በግልፅ ከላይ áŠĨንደጠቀáˆĩኩá‰ĩ ዓይነá‰ĩ á‹ĩርጊá‰ĩ ከመንግáˆĨá‰ĩ አáŠĢላá‰ĩ የሃይማኖá‰ĩ ማá‹ŗከም áˆĨáˆĢ በግልáŒŊ áŠĨየተáŠĢሄደ ነው፡፡
በልማá‰ĩ áˆĩም áŠĨምነá‰ĩን የማáˆĩፉፉá‰ĩ ሴáˆĢ ከቀá‹ĩሞውም የሹማምንá‰ĩ ግá‰Ĩር áŠĨንደሆነ ይá‰ŗወቃልáĸ አሁን ደግሞ በቀá‹ĩሞ የሀገáˆĒቱ አáˆĩተá‹ŗደር ለልማá‰ĩ በማለá‰ĩ የፈረሱ አáŠĢá‰Ŗá‰ĸዎá‰Ŋን áŠĨና á‰Ļá‰ŗዎá‰Ŋን ለáŠĨáˆĩልምና አማኞá‰Ŋ መáˆĩጊá‹ĩ áŠĨንዲሰሩá‰Ŗቸው በመáˆĩጠá‰ĩ ኃላፊነá‰ĩ የጎደለው ጨለምተኛ አሰáˆĢር በáˆĩልáŒŖን ወንበር ላይ የተቀመጡ የáŠĨምነቱ ተከá‰ŗዮá‰Ŋ áŒĢና áŠĨá‹Ģደረጉ በመáˆĨáˆĢá‰ĩ ላይ ይገኛልáĸ
ከá‰ŗá‰Ŋ በምáˆĩሉ ምá‰ĩመለከቱá‰ĩ á‰Ļá‰ĩ በተለምá‹ļ ቡልጋርá‹Ģ አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ 20 ቀበሌ ወይም áˆŗይá‰Ŧርá‹Ģ የሚá‰Ŗለው አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ ሲሆን áŠĨዚህ አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ ላይ አá‰Ĩዛኞቹ የክርáˆĩá‰ĩና áŠĨምነá‰ĩ ተከá‰ŗዮá‰Ŋ የነበሩበá‰ĩ ነውáĸ áŠĨንደተለመደው ልማá‰ĩ በሚá‰Ŗለው መንግáˆĩá‰ŗዊ ቋንቋ ከተነሱ ከ4 ዓመá‰ĩ በላይ አáˆĩቆáŒĨረዋልáĸá‰Ļá‰ŗውም áŒĢáŠĢ ሆኖ ዛፎá‰Ŋ በቅለውበá‰ĩ መንግáˆĩá‰ŗዊ áˆŗይሆን ተፈáŒĨሯዊ ልማá‰ĩ ይዞ ቆይá‰ļ ነበርáĸ á‰ŗá‹ĩá‹Ģ አሁን á‹Ģለው የአዲáˆĩ አበá‰Ŗ አáˆĩተá‹ŗደር የáŠĨáˆĩልምና ማዕከልና መáˆĩጊá‹ĩ ይሰሩበá‰ĩ ዘንá‹ĩ áŠĨዚው á‰Ļá‰ŗ ላይ 30 áˆē áŠĢáˆŦ ለግሷቸዋል áĸየáŠĻርá‰ļá‹ļክáˆĩ ተዋሕá‹ļ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን የይዞá‰ŗ ማረጋገáŒĢ áŠĢርá‰ŗ áˆĩá‰ĩጠይቅ መከáˆĢ áŠĨንá‹ŗላየá‰Ŋ ሁላ áŠĨንደቀልá‹ĩ አንá‹ĩ መንደርን á‰Ĩá‹ĩግ አደርጎ áŠĨንáŠĢቹ ማለá‰ĩ ምን የሚሉá‰ĩ ጠá‰Ŗá‰Ĩ ጨለምተኝነá‰ĩ ነው?!
የነዋáˆĒው áŠĨና የአáŠĢá‰Ŗá‰ĸው ቅáˆŦá‰ŗ ይህ መáˆĩጊá‹ĩ áŠĨንዲሰáˆĢበá‰ĩ የተሰጠው á‰Ļá‰ŗ በáŒŖም ቅርá‰Ĩ በሚá‰Ŗል ሁኔá‰ŗ ከ27 ዓመá‰ĩ በላይ የቆየ የቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን አለ በተለመá‹ļም ሙሉ áˆĩሙ የአፍáˆĒáŠĢ ኅá‰Ĩረá‰ĩ ደá‰Ĩረ ምህረá‰ĩ ቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል áŠĢቴá‹ĩáˆĢል ተá‰Ĩሎ ይጠáˆĢልáĸ á‰Ĩዙ የክርáˆĩá‰ĩá‹Ģን ነዋáˆĒ በሚገኝበá‰ĩ á‰Ļá‰ŗ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን አጠገá‰Ĩ የመáˆĩጊá‹ĩ áˆĨáˆĢን አምáŒĨá‰ļ መደቀኑ ይዋáŒŖላቹáŖ ይለይላቹ የሚል መልáŠĨክá‰ĩ á‹Ģለው መንግáˆĨá‰ŗዊ አሸá‰ŖáˆĒነá‰ĩ ነውáĸ
አá‰Ĩá‹Ģተ ክርáˆĩቲá‹Ģናá‰ĩ በሚገኙበá‰ĩ ቅርá‰Ĩ ርቀá‰ĩ ላይ መáˆĩጊá‹ĩ áˆĩሊ á‰Ĩሎ ይሁንá‰ŗን መáˆĩጠá‰ĩ ምን የሚሉá‰ĩ á‰Ŋሎá‰ŗ ነውáĸከዚህ በፊá‰ĩም ለቱርክ á‰Ŗለሃá‰Ĩá‰ļá‰Ŋ የተዘጋጀ á‰Ļá‰ŗ áŠĨየተá‰Ŗለ ለሃይማኖá‰ŗዊ ግልጋሎá‰ĩ ሲውል á‰Ŗናይም ሰምተን ግን አልፈናልáĸ አሁን ደግሞ ይá‰Ŗáˆĩ á‰Ĩሎ አንá‹ĩ ቀበሌ የሚá‹Ģክል á‰Ļá‰ŗ መáˆĩጠá‰ĩ ወንበር ከመልቀቄ በፊá‰ĩ የሚል ሴáˆĢ የá‹Ģዘ የፓለቲáŠĢ ሸፍáŒĨ ነውáĸ
ሌላው á‰ĩልቁ á‰Ŋግር በá‰Ĩዙ á‰ĩዕግáˆĩá‰ĩ ተቀመáŒĻ የነበረውን ወáŒŖá‰ĩ ማነáˆŗáˆŗቱ ነውáĸበአáŠĢá‰Ŗá‰ĸው á‹Ģሉá‰ĩም ይሁን ከሩቅ á‹Ģሉ ወáŒŖá‰ļá‰Ŋ ይህን ሲሰሙ ከነፍáˆĩ á‹Ģለፍ á‰ĩርፍ ምን አለ በሚል ግá‰Ĩግá‰Ĩ ውáˆĩáŒĨ ገá‰Ĩተው አላáˆĩፈላጊ የሆኑ ግጭá‰ļá‰Ŋና አለመግá‰Ŗá‰Ŗá‰ļá‰Ŋን á‹Ģáˆĩከá‰ĩላልáĸተá‰ģá‰Ŋለን áŠĨንኑር á‰Ĩሎ የሰከነውን ወáŒŖá‰ĩ á‹Ģደገበá‰ĩ አáŒĨá‰ĸá‹Ģ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን ላይ መáŒĨá‰ļ "አላሁ አክበር"የሚል á‹ĩምáŒŊ ማሰማá‰ĩ ከፍተኛ ንቀá‰ĩ á‰Ĩá‰ģ áˆŗይሆን ምንá‰ŗመáŒŖለህ የሚል áˆĩá‹ĩá‰Ĩ ነውáĸ አሁንም ከቤተክርáˆĩቲá‹Ģን ቅርá‰Ĩ ርቀá‰ĩ ለመáˆĩጊá‹ĩ ተá‰Ĩለው የሚሰጡ á‰Ļá‰ŗዎá‰Ŋ በአáˆĩቸáŠŗይ መቆም አለá‰Ŗቸውáĸ
ከ60 ሚልየን በላይ ተከá‰ŗይ á‹Ģላá‰ĩን ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን መáŒĨቀም á‰Ŗንá‰Ŋልም መጉá‹ŗቱ ዋጋ የሚá‹Ģáˆĩከፍል áˆĩለሆን ዓመáŒŊ áˆŗይበረá‰ŗ ቡልጋርá‹Ģ አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ አፍáˆĒáŠĢ ህá‰Ĩረá‰ĩን á‰ŗኮ የቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን áŠĢለበá‰ĩ ቅርá‰Ĩ ርቀá‰ĩ ላይ የተሰጠው የመáˆĩጊá‹ĩ መáˆĩርá‹Ģ 30.000áŠĢáˆŦ መáˆŦá‰ĩ በአáˆĩቸáŠŗይ መመለáˆĩ አለበá‰ĩáĸ ይህ ሕገ ወáŒĨ አሰáˆĢር የሀገር á‰Ŗለውለá‰ŗ የሆነá‰Ŋውን ቤተክርáˆĩቲá‹Ģንን መናቅ ነውና መንግáˆĨá‰ĩ አáˆĩá‰Ĩበá‰ĩáĸ
áˆŧር በማá‹ĩረግ ለሁሉም ሰው መረጃውን áŠĨንá‹ĩርá‹Ģáˆĩ

✏ī¸ ከወንá‹ĩማá‰Ŋን ናá‰ĩናኤል áĸ

ይሄን መልዕክá‰ĩ áˆŧር በማá‹ĩረግ ሀላፊነá‰ŗá‰Ŋንን áŠĨንወáŒŖ
አንá‹ĩ አምላክ በሚሆን በአá‰Ĩ በወልá‹ĩ በመንፈáˆĩ ቅዱáˆĩ áˆĩም አሜን
አá‰Ŗ አርáˆŗንዮáˆĩ-የጌá‰ŗá‰Ŋንን መከáˆĢ áŠĨá‹Ģሰበ ሲá‹Ģለቅáˆĩ ከለቅáˆļው á‰Ĩዛá‰ĩ የተነáˆŗ ቅንá‹ĩቡ ተነቆሎ አልቋልáĸ
áŒģá‹ĩቁ የአቴናን ፍልáˆĩፍና ጠንቅቆ የተማረáŖ የፀሐይንና የጨረቃን አáŠĢሄá‹ŗቸውን የተመáˆĢመረና የሮሙን ንጉáˆĨ ልጆá‰Ŋ ቅዱáˆŗን የሆኑ የከበሩ አኖáˆŦዎáˆĩንና አርቃዴዎáˆĩን አáˆĩተምሮ á‹Ģáˆŗደጋቸው በኋላም በዓá‰ĩ አáŒŊንá‰ļ በá‰ŗላቅ ተጋá‹ĩሎ የኖረ ሲሆን ይáŠŊም ቅዱáˆĩ ከሮሜ አገር ሰዎá‰Ŋ ከá‰Ŗለጸጎá‰Ŋና ከá‰ŗላላቆá‰ŋ ወገን ነው፡፡ በዚáŠŊá‰Ŋ ዕለá‰ĩ ግንá‰Ļá‰ĩ 13 በዓመá‰ŗዊ የዕረፍá‰ĩ በዓሉ á‰ŗáˆĩá‰Ļ ይውላልáĸ

የቤተ ክርáˆĩቲá‹Ģን á‰ĩምህርá‰ĩ ተምሮ ዲቁና ከተሾመ በኋላ ወደ አቴና ሄá‹ļ ፍልáˆĩፍናን ጠንቅቆ ተማረ፡፡ የፀሐይንና የጨረቃን አáŠĢሄá‹ŗቸውንና የዘመናá‰ĩንም መለáŠĒá‹Ģ ተማረ፡፡ በá‰ĩምህርቱም ከሁሉም በላይ ከፍ á‹Ģለ ሆነ፡፡ በመንፈáˆŗዊ á‰ĩምህርቱም ፍጹም ሆኖ አምላáŠĢዊ á‰ĩሩፋá‰ĩን የሚሠáˆĢ ሆነ፡፡

በሮሜ አገር á‰ŗላቁ ቴዎá‹ļáˆĩዮáˆĩ በነገሠ ጊዜ ልጆቹን አኖáˆŦዎáˆĩንና አርቃዴዎáˆĩን የሚá‹Ģáˆĩተምርለá‰ĩ áŒĨበበኛ ሰው ፈለገ፡፡ በዚáŠŊም ጊዜ ከአá‰Ŗ አርáˆŗንዮáˆĩ የበለጠ ደገኛ አዋቂ አልተገኘምና áŠĨርሱን ወáˆĩው ከንጉሡ ጋር አገናኙá‰ĩ፡፡ ንጉሡም ልጆቹን áŠĨንዲá‹Ģáˆĩተምርá‰ĩ ለመነው፡፡ አá‰Ŗ አርáˆŗንዮáˆĩም አኖáˆŦዎáˆĩንና አርቃዴዎáˆĩን áŠĨá‹Ģáˆĩተማረ አáˆŗደጋቸው፡፡ በá‰Ĩዙ á‹ĩáŠĢምም áˆĩለሚá‹ĢáˆĩተምáˆĢቸው á‹ĢለርኅáˆĢኄ á‰Ĩዙ áŠĨየቀáŒŖና áŠĨየደበደበ ነበር á‹Ģáˆŗደጋቸው፡፡ ‹‹ተáˆĩፋ ገና áˆŗለá‰Ŋ ልጅህን ገáˆĨáŒŊáŖ መሞቱንም አá‰ĩáˆģâ€ēâ€ē (ምáˆŗ 18፡19)áŖ ‹‹ልጅህን ቅáŒŖ ዕረፍá‰ĩንም ይሠáŒĨሃልâ€ēâ€ē (ምáˆŗ 29፡17) áŠĨንዲል መáŒŊሐፍ፡፡
ንጉሡም በሞá‰ĩ á‰Ŗረፈ ጊዜ ልጆቹ አኖáˆŦዎáˆĩ በሮሜ አገርáŖ አርቃዴዎáˆĩ ደግሞ በቁáˆĩáŒĨንáŒĨንá‹Ģ ነገሡ፡፡ በá‰ŗናáˆŊነá‰ŗቸው ጊዜ áŠĨየገረፈ ሲá‹ĢáˆĩተምáˆĢቸው የነበረው አá‰Ŗ አርáˆŗንዮáˆĩ ግን áŠĨርሹ ሲነግሡ በዚህ ጊዜ ከዓለም ይወáŒŖ ዘንá‹ĩ ወደደ፡፡ ምን áŠĨንደሚá‹Ģደርግም ሲá‹Ģáˆĩá‰Ĩ ከáŠĨግዚአá‰Ĩሔር ዘንá‹ĩ ‹‹አርáˆŗኒ አርáˆŗኒ ከዚህ ዓለም ውáŒŖâ€ēâ€ē የሚል á‹ĩምáŒŊ መáŒŖለá‰ĩ፡፡ áŠĨርሱም ፈáŒĨኖ በመውáŒŖá‰ĩ ልá‰Ĩሱን ለውáŒĻ ወደ áŠĨáˆĩክንá‹ĩርá‹Ģ አገር ሄደ፡፡ ከዚá‹Ģም የከበረ የአá‰Ŗ መቃርáˆĩ ገá‹ŗም ወá‹ŗለበá‰ĩ ወደ አáˆĩቄáŒĨáˆĩ በረሃ ደርáˆļ በጾም በጸሎá‰ĩ በመáˆĩገá‹ĩ በአርምሞና በá‰ĩሩፋá‰ĩ ሁሉ ፍጹም ተጋá‹ĩሎን ተጋደለ፡፡ ምንም ምን የማይናገር ሆነ፡፡ áˆĩለዝምá‰ŗውም በጠየቁá‰ĩ ጊዜ ‹‹áŠĨኔ áˆĩለáˆĢሴ አዝናለሁâ€ēâ€ē ይላቸዋል፡፡ áŠĨርሹ ግን በውáˆĩáŒĨና በአፍአ ፍጹም á‰ĩሑá‰ĩና ቅን የዋህ ነው፡፡ የáŠĨጅ áˆĨáˆĢውንም áŠĨየሠáˆĢ ከዕለá‰ĩ ምግቡ áŠĨá‹Ģáˆĩተረፈ ይመጸውá‰ŗል፡፡ ወደ ቤተ ክርáˆĩቲá‹Ģንም በገá‰Ŗ ጊዜ ሰው áŠĨንá‹ŗá‹Ģየው በምሰáˆļው ኋላ ይሠወáˆĢል፡፡ á‹ĩንቅ á‹ĩንቅ የሆኑ ተአምáˆĢá‰ĩንም á‹Ģደርጋል ነገር ግን ከውá‹ŗሴ ከንቱ ፈáŒĨኖ ይሸáˆģል፡፡ áŠĨግዚአá‰Ĩሔርም የá‰Ĩዙ ቅዱáˆŗንን ገá‹ĩል ገለጸለá‰ĩና ገá‹ĩላቸውን áŒģፈ፡፡

አá‰Ŗ አርáˆŗንዮáˆĩ የነፍáˆŗቸውን á‹ĩኅነá‰ĩ ለሚሹ ሁሉ áŒĨቅም á‹Ģላቸውን á‰Ĩዙ á‹ĩርáˆŗá‰ĩንና ተግáˆŖáŒģá‰ĩን ደረሰ፡፡ መልኩ á‹Ģማረ ፊቱም á‰Ĩሩህ ደáˆĩ የሚá‹Ģሰኝ ነው፡፡ ቁመቱ ረጅም ነው፡፡ ፂሙም ከወገቡ መá‰ŗጠቂá‹Ģ የሚደርáˆĩ ረጅም ነው፡፡ ከልቅáˆļው á‰Ĩዛá‰ĩ የተነáˆŖ ቅንá‹ĩቡ ተነቀለ፡፡ በá‰ŗላቅ ተጋá‹ĩሎም ከኖረ በኋላ ወደ መልáŠĢም áˆŊምግልና ደረሰ፡፡ በሮሜ አገር 40 ዓመá‰ĩáŖ በአáˆĩቄáŒĨáˆĩ ገá‹ŗም 35 ዓመá‰ĩáŖ በምáˆĩር ገá‹ŗም 20 ዓመá‰ĩáŖ በáŠĨáˆĩክንá‹ĩርá‹Ģ áˆĻáˆĩá‰ĩ ዓመá‰ĩ ወደ ገá‹ŗምም ተመልáˆļ 2 ዓመá‰ĩ ኖረ፡፡ በአጠቃላይም ዕá‹ĩሜው መá‰ļ ዓመá‰ĩ ሲሆነው በዚáŠŊá‰Ŋ ዕለá‰ĩ በሰላም ዐረፈ፡፡ የአá‰Ŗ አርáˆŗንዮáˆĩ ረá‹ĩኤá‰ĩ በረከቱ ይደርá‰ĨንáŖ በጸሎቱ ይማረን፡፡
+ + +

የአá‰Ŗ አርáˆŗንዮáˆĩ ገርፈውና ገáˆĨጸው á‹Ģáˆŗደጓቸው ልጆá‰ģቸው የከበሩ ቅዱáˆŗን ነገáˆĨá‰ŗá‰ĩ አኖáˆŦዎáˆĩና አርቃዴዎáˆĩ áŠĨንዴá‰ĩ ላለው áŒŊá‹ĩቅ áŠĨንደበቁ ማየቱ ተገá‰ĸ ነው፡፡ ከቅዱáˆĩ አኖáˆŦዎáˆĩ áŠĨንጀምር፡፡ የአኖáˆŦዎáˆĩን ቅá‹ĩáˆĩና ለማወቅም የአá‰Ŗ á‹ŗንኤልን á‰ŗáˆĒክ ማየቱ ግá‹ĩ ነው፡፡ ዓለሙ ሁሉ የáŠĨግሩን á‰ĩá‰ĸá‹Ģ á‹Ģህል áŠĨንáŠŗን ዋጋ የሌለው áŠĨጅግ የከበረው አá‰Ŗ á‹ŗንኤል ከá‰ŗለቁ áŒģá‹ĩቅ ንጉáˆĨ ከቅዱáˆĩ አኖáˆŦዎáˆĩ ጋር የተገናኘ á‰ŗáˆĒክ አለው፡፡ ይኸውም አá‰Ŗ á‹ŗንኤል 40 ዓመá‰ĩ ሙሉ በአáˆĩቄáŒĨáˆĩ ገá‹ŗም ሲኖር ከቅጠል በቀር ተመግá‰Ļ አá‹Ģውቅም ነበርና ከáŒŊá‹ĩቁና ከá‰Ĩቃቱ የተነáˆŖ ከá‰Ĩዙ ዘመን በኋላ የመመáŠĢá‰ĩ ክፉ ሀáˆŗá‰Ĩ መáŒŖበá‰ĩ፡፡ ‹‹በገá‹ŗም ውáˆĩáŒĨ áŠĨንደáŠĨኔ á‰ĩርሕምá‰ĩን ገንዘá‰Ĩ á‹Ģደረገ ይኖር ይሆን?â€ēâ€ē á‰Ĩሎም አሰበ፡፡ ሰውን ወá‹ŗá‹ĩ የሆነ ጌá‰ŗá‰Ŋንም ይህን ክፉ ሀáˆŗቡን ሊá‹Ģርቅለá‰ĩ áˆŊá‰ļ á‰Ĩርሃናዊ መልአኩን ላከለá‰ĩ፡፡ መልአኩም አá‰Ŗ á‹ŗንኤልን áˆĩለ á‰ĩምክህቱ á‰ĸቆáŒŖውም አá‰Ŗ á‹ŗንኤል መልአኩን መልáˆļ ‹‹ጌá‰ŗá‹Ŧ ከáŠĨኔ የሚáˆģል áŠĢለ ንገረኝáŖ ወደ áŠĨርሹ ሄጄ አየው ዘንá‹ĩ áŠĨወá‹ŗለሁáŖ በመመáŠĢቴም ወደ ፈáŒŖáˆĒá‹Ŧ በልመና áŠĨመለáˆĩ ዘንá‹ĩâ€ēâ€ē አለው፡፡ መልአኩም ‹‹áŠĨግዚአá‰Ĩሔርን የሚፈáˆĢ ሰው የሮሜና የቁáˆĩáŒĨንáŒĨንá‹Ģ ንጉáˆĨ አኖáˆŦዎáˆĩ በመንግáˆĨተ ሰማá‹Ģá‰ĩ á‰ŖልንጀáˆĢህ ነውâ€ēâ€ē አለው፡፡

‹‹ንጉáˆĨ አኖáˆŦዎáˆĩም የመነኮáˆŗá‰ĩን áˆĨáˆĢዎá‰Ŋ ሁሉ áˆĩለሚሠáˆĢ ከልá‰Ĩሰ መንግáˆĨቱ áˆĨር በáˆĨጋው ላይ ማቅ ይለá‰Ĩáˆĩ ነበርâ€ēâ€ē ተá‰Ĩሎ በáˆĩንክáˆŗሊ ላይ የተáŒģፈለá‰ĩ áŒģá‹ĩቅ ንጉáˆĨ ሲሆን ሰማá‹Ģውá‹Ģን የሆኑ ቅዱáˆŗን መላáŠĨክá‰ĩም ቅá‹ĩáˆĩናውን የመሰከሩለá‰ĩ በንግáˆĨና á‹Ģለ á‰ŗላቅ የáŠĨግዚአá‰Ĩሔር አገልጋይ ነው፡፡ አá‰Ŗ á‹ŗንኤልም ይህ በሰማ ጊዜ መáˆŦá‰ĩ ላይ ወá‹ĩቆ በáˆĢሱም ላይ አመá‹ĩ ነáˆĩንáˆļ የዚህን የሮም ንጉáˆĨ አኖáˆŦዎáˆĩን ግá‰Ĩር á‹Ģáˆŗየው ዘንá‹ĩ ጌá‰ŗá‰Ŋንን ለመነ፡፡ ደመናም መáŒĨá‰ŗ ነáŒĨቃ ወሰደá‰Ŋውና ንጉáˆĨ አኖáˆŦዎáˆĩ ደጅ አደረሰቸውና ንጉሡን በዙፋኑ ላይ ሆኖ á‰Ŗየው ጊዜ ከግርማው የተነáˆŖ አይá‰ļá‰ĩ በá‰ŗላቅ ፍርሃá‰ĩ ውáˆĩáŒĨ ሆኖ ከáŠĨግሩም በá‰ŗá‰Ŋ ሰገደለá‰ĩና አኗኗሩንም ይነግረው ዘንá‹ĩ በጌá‰ŗá‰Ŋን áˆĩም አማፀነው፡፡ ንጉáˆĨ አኖáˆŦዎáˆĩም ሰሌን በመá‰ŗá‰ŗá‰ĩ በáŠĨጅ áˆĨáˆĢው ደክሞ ከሚá‹Ģገኘው በቀር ምንም áˆŗይበላና áˆŗይለá‰Ĩáˆĩ 40 ዓመá‰ĩ áŠĨንደሆነውáŖ ሰሌን á‰ŗá‰ļ ሸáŒĻ áŠĢገኘውም ውáˆĩáŒĨ ከዕለá‰ĩ ምግቡ መግá‹Ŗ የሚተርፈውን ለá‹ĩኆá‰Ŋና ለáŒĻም አá‹ŗáˆĒዎá‰Ŋ áŠĨንደሚመጸውá‰ĩáŖ ምግቡም áŠĨንጀáˆĢና ጨውáŖ ቅጠል መáŒģáŒģም áŠĨንደሆነáŖ የማንንም ንá‰Ĩረá‰ĩ ፈáŒŊሞ áŠĨንá‹ŗልንáŠĢáŖ á‹ĩንግልናውንም ጠá‰Ĩቆ áŠĨንደሚኖርáŖ ከንግáˆĨና የወርቅ áŠĢá‰Ŗው ውáˆĩáŒĨ ወገቡን በሰንሰለá‰ĩ አáˆĨሎ áŠĨንደሚኖር ነገረው፡፡ አá‰Ŗ á‹ŗንኤልም á‹ĩጋሚ ከáŠĨግሩ áˆĨር ወá‹ĩቆ ሰግá‹ļለá‰ĩ áˆĩለ á‰ĩምክህቱም ፈáŒŊሞ áŠĨá‹Ģዘኑ ወደ በዓá‰ŗቱ ተመልሷል፡፡ረá‹ĩኤá‰ĩ በረከቱ ይደርá‰ĨንáŖ በጸሎቱ ይማረን፡፡
ላመáˆĩግንህ የáŠĨኔ ጌá‰ŗ
♡የመዝሙር ግáŒĨሞá‰Ŋ♡
✞ላመáˆĩግንህ የáŠĨኔ ጌá‰ŗ✞

ላመáˆĩግንህ የáŠĨኔ ጌá‰ŗ ላመáˆĩግንህ
ልቀኝልህ የáŠĨኔ ጌá‰ŗ ልቀኝልህ
ሕይወቴ ነው ዝማáˆŦá‹Ŧ á‰ĩሩፋቴ
የሰጠኸኝ áŠĨንá‹ŗከá‰Ĩርህ አንተ አá‰Ŗቴ(áĒ)

ከኔ የሆነ የምሰáŒĨህ á‰Ŗይኖረኝም
ከሰጠኸኝ የአንተን መáˆĩጠá‰ĩ አይከá‰Ĩደኝም
áŒĨበቤ ነህ የምáˆĩጋና መሠረቴ
ዝማáˆŦá‹Ŧን á‹Ģፈሰከው በህይወቴ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምáˆĩጋና
ይኸው ውሰá‹ĩ ቅኝá‰ĩህን áŠĨንደገና(áĒ)
አዝ= = = = =
á‰Ŗá‹ļ áŠĨኮ ነኝ የáŠĨኔ ጌá‰ŗ ምን ልቅá‹ŗልህ
በáŠĨጄ ላይ አንá‹ŗá‰Ŋ የለኝ የምሰáŒĨህ
ላንተ ክá‰Ĩር የሚመáŒĨን ህይወá‰ĩ የለኝ
ዝማáˆŦá‹Ŧን በቸርነá‰ĩ ተቀበለኝ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምáˆĩጋና
ይኸው ውሰá‹ĩ ቅኝá‰ĩህን áŠĨንደገና(áĒ)
አዝ= = = = =
ከምá‹ĩር ላይ ከአፈር áˆĩá‰ĩፈáŒĨረኝ
ከምáˆĩጋና የተለየ ምን áˆĨáˆĢ አለኝ
ቀን áŠĨና ሌá‰ĩ በመቅደáˆĩህ áŠĨቆማለሁ
አምላáŠŦ ሆይ áˆŗወá‹ĩáˆĩህ áŠĨኖáˆĢለሁ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምáˆĩጋና
ይኸው ውሰá‹ĩ ቅኝá‰ĩህን áŠĨንደገና(áĒ)
አዝ= = = = =
ዕዝáˆĢ áˆĩጠኝ የከበረ መሰንቆህን
á‹ŗዊá‰ĩ áˆĩጠኝ የሚፈውáˆĩ በገናህን
መዝሙር ቅኔ ተምርá‹Ģለሁ ከአá‰Ŗá‰ļá‰ŧ
ዘምáˆĢለሁ á‰Ŗንተ ፍቅር ተነክá‰ŧ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምáˆĩጋና
ይኸው ውሰá‹ĩ ቅኝá‰ĩህን áŠĨንደገና(áĒ)
መዝሙር
ቀሲáˆĩ ምንá‹ŗá‹Ŧ á‰Ĩርሃኑ

"áŠĨግዚአá‰Ĩሔርን አመáˆĩግኑ"
ፊ ዜና ፲፮áĨ፷
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮

╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ ══
ዛáˆŦ áŠĨኮ ቅዱáˆĩ áŠĨሩፋኤል ነው 13🙏
áŠĨንግዲህ ከá‰ŖህáˆĒው ቅá‹ĩáˆĩና ፍáŒĨረቱን በጸጋ ቅá‹ĩáˆĩና መርáŒĻ የሚለይ áŠĨግዚአá‰Ĩሔር አክá‰Ĩሎ áŠĨንዲህ á‹Ģለ ሰማá‹Ģዊ ፀጋ ከሰáŒŖቸው ቅዱáˆŗን መላáŠĨክá‰ĩ መáŠĢከል በáˆĩልáŒŖኑ ሊቀመናá‰Ĩርá‰ĩ (የመናá‰Ĩርá‰ĩ አለቃ) የሆነ በሹመá‰ĩ ፈá‰ŗሔ ማኅጸን (ማሕጸን የሚፈá‰ŗ) ከáˆŗቴ áŠĨውáˆĢን (የáŠĨውáˆĢንን ዓይን የሚá‹ĢበáˆĢ) ሰá‹ŗዴ አጋንንá‰ĩ (አጋንንá‰ĩን የሚá‹Ģá‰Ŗርር) ፈዋሴ ዱá‹Ģን (á‹ĩውá‹Ģንን የሚፈውáˆĩ)áŖ አቃቤ ኆኅá‰ĩ (የምህረá‰ĩን ደጁ የሚጠá‰Ĩቅ) ተá‰Ĩሎ የተገለጠ ከሊቃነ መላáŠĨክቱ ቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤልና ቅዱáˆĩ ገá‰Ĩርኤል ተከá‰ĩሎ የሚነáˆŗ መልአክ áˆĢሱን áŠĨንዲህ በማለá‰ĩ ገለጠ ÂĢ የቅዱáˆŗንን ጸሎá‰ĩ ከሚá‹Ģáˆŗርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ጌá‰ĩነá‰ĩ ከሚá‹Ģገቡ ከከበሩ ከሰá‰Ŗቱ አለቆá‰Ŋ አንዱ አለቃ áŠĨኔ ሩፋኤል ነኝÂģ (áŒĻá‰ĸ.12Ãˇ15)
ይህ የከበረ á‰ŗላቅ መልአክ ሰሙ የáŠĨá‰ĨáˆĢይáˆĩáŒĨ ሁለá‰ĩ ቃላá‰ĩ áŒĨምረá‰ĩ ውጤá‰ĩ ነው፡፡ ሩፋ ማለá‰ĩ ጤናáŖ ፈውáˆĩáŖ መá‹ĩኃኒá‰ĩ ማለá‰ĩ ሲሆን ኤል ሚለው በሌሎቹም መላáŠĨክá‰ĩ áˆĩም ላይ የሚቀጠል áˆĩመ አምላክ ነው ይህም ÂĢ መልአáŠŦን በፊá‰ĩህ áŠĨሰá‹ŗለሁâ€Ļ.. áˆĩሜ በáŠĨርሹ áˆĩለሆነ . አá‰ŗáˆĩመርሊá‰ĩÂģ (ዘጸ.23Ãˇ20-22) áŠĨá‹ŗለው ነው፡፡
á‰ŗዲá‹Ģ ሩፋኤል የሚለው በáŒĨምረá‰ĩ ከአምላክ ለሰዎá‰Ŋ የተሰጠ ፈውáˆĩ የሚለውን ይተáŠĢል ÂĢበሰው ቁáˆĩል የተሾመ ከከበሩ ከመላáŠĨክá‰ĩ አንዱ ሩፋኤል ነው፡Âģ (ሄኖ.6Ãˇ3)
ይህ መልአክ áŠĨንደሌሎቹ ሊቃነ መላáŠĨክá‰ĩ ሁሉ የሰው ልጆá‰Ŋን ይጠá‰Ĩቃቸዋል(á‹ŗን.4Ãˇ13 ዘጸ. 23Ãˇ20 መዝ. 90Ãˇ11-13 )
á‹Ģማልá‹ŗልáŖ ከፈáŒŖáˆĒ á‹Ģáˆĩá‰ŗርቃቸዋል፡፡(ዘáŠĢ.1Ãˇ12)
በፈáˆĒሀ áŠĨግዚአቤሔር áŠĨና በአክá‰Ĩሮተ መላáŠĨክá‰ĩ á‹Ģሉá‰ĩን á‹ĩናቸዋል (ዘፍ.49Ãˇ15 መዝ.3Ãˇ37)
ÂĢ áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ሃይሉን የሚገልáŒĨበá‰ĩን ቅáŒŖቱን ሊá‹Ģáˆŗይ á‰ĸወá‹ĩ አáˆĩቀá‹ĩሞ መርáŒĻ በወደá‹ŗቸው ለይቅርá‰ŗ የተዘጋጁ የይቅርá‰ŗ መላáŠĨክá‰ĩን á‹ĢመáŒŖልÂģ (ሮሜ.9Ãˇ22)
ቅዱáˆĩ ሩፋኤል ሊቀመናá‰Ĩርá‰ĩን á‹ĩንቅ ገá‰ĸር ተአምáˆĢቱን á‹Ģዩ ምዕመናን
â€Ļâ€Ļየወላá‹ĩ ማኅፀን áŠĨንዲፈá‰ŗ
áˆĩለተሸመ ከጌá‰ŗ
አዋላጅ á‰Ĩá‰ĩኖር á‰Ŗá‰ĩኖርም
ሐáŠĒም ሩፋኤል አይá‰ŗáŒŖም
በምáŒĨ ጊዜ ሲጨነቁ የá‰Ŗላገር ሴá‰ļá‰Ŋ ሁሉ
የመልአኩን መልክ አንግተው ማርá‹Ģም ማርá‹Ģም ይላሉ
ማየጸሎቱን ጠáŒĨተው á‰ļሎ ፈáŒĨነው ይወልá‹ŗሉ â€Ļâ€Ļ
áŠĨá‹Ģሉ ደጅ ጠንተው ይማጸኑá‰ŗል፡፡
ዜና ግá‰Ĩሩን ሊቁ ዮሐንáˆĩ አፈወርቅ ከተናገረለá‰ĩ በመነáˆŗá‰ĩ በቅዱáˆŗን ላይ á‹ĩንቅ የሆነ áŠĨግዚአá‰Ĩሔር በመልአኩ አá‹ĩሎ á‹Ģደረጋቸውን ተግá‰ŖáˆĢá‰ĩ አበው የበረከá‰ĩ ምንጭ በሆነ á‹ĩርáˆŗኑ ላይ አኑረው የበረከቱ ተáŠĢፋይ áŠĨንá‹ĩንሆን ሰáŒĨተውናል፡፡ በጉልህ ሠፍረው ከምናገኛቸው á‰Ĩዙ á‹ĩንቅ áˆĨáˆĢዎá‰Ŋ መሀል áŒĨቂá‰ļቹን áŠĨነሆ
~~~> በáˆĨነ-áˆĩዕሉ የተማጸኑáŖ በምልጃው á‰ŗምነው የጸኑ ቴዎá‹ļáˆĩዮáˆĩንና ዲዮናáˆĩዮáˆĩን በገሃá‹ĩ ተገልጾ ለንግáˆĩናና ለáŒĩáŒĩáˆĩና ክá‰Ĩር አá‰Ĩቅቷቸዋል፡፡
~~~> የንጉáˆĩ ቴዎá‹ļáˆĩዮáˆĩ ልጅም áŒģá‹ĩቁ አኖáˆŦዋáˆĩም በፈáŒŖáˆĒው ህግ áŠĨየተመáˆĢ የሊቀ መናá‰Ĩርቱን መá‰ŗሰá‰ĸá‹Ģ ቤተ መቅደáˆĩ አáˆŗንጾ ሲá‹Ģáˆĩመርቅ ለበለጠ ክá‰Ĩር ልቡን አነቃቅá‰ļ ለá‰ŗናáˆŊ ወንá‹ĩሙ ለአርቃዴዋáˆĩ የነጋáˆĸነá‰ĩ áˆĩልáŒŖኑን á‰ĩá‰ļ መንኖ በáˆĩውርና በáŒŊሙና áŠĨዲኖር ረá‹ĩá‰ļá‰ŗል፡፡
~~~> በሊቀáŒŗáŒŗáˆŗá‰ĩ ቴዎፍሎáˆĩ ዘመን አá‰Ŗá‰ļá‰Ŋ ለሊቀመናá‰Ĩርቱ ክá‰Ĩር በአáˆŖ አንበáˆĒ ጀርá‰Ŗ ላይ á‹Ģáˆŗነጹá‰ĩን መá‰ŗሰá‰ĸá‹Ģ ቤተ መቅደáˆĩ በወደቡ አጠገá‰Ĩ በáŠĨáˆĩክንá‹ĩáˆĒá‹Ģ áˆŗለá‰Ŋ ጠላá‰ĩ ዲá‹Ģá‰ĸሎáˆĩ አነዋውጾ ለምáˆĩጋና የá‰ŗደሙá‰ĩን ምዕመናን ሊá‹Ģጠፉ አáˆŖ አንበáˆĒውን á‰ĸá‹Ģውከው ወደ ሊቀመናá‰Ĩርቱ ተማáŒŊነው áŠĨርá‹ŗን á‰ĸሉ ፈáŒĨኖ ደርáˆļ በበá‰ĩረ መáˆĩቀሉ (ዘንጉ) ገáˆĨጾ ከáŒĨፋá‰ĩ á‰ŗá‹ĩጓቸዋል፡፡
በቅዱáˆĩ መáŒŊሐፍም áŠĨንደተገለጠው
~~~> áˆŖáˆĢ ወለተ áˆĢጉኤልን አáˆĩማንá‹ĩዮáˆĩ ከተá‰Ŗለው የጭን ጋንኤን ሲá‰ŗደጋá‰ĩ የáŒĻá‰ĸá‹Ģን አá‰Ŗá‰ĩ የáŒĻá‰ĸá‰ĩን ዓይን አበáˆĢለá‰ĩ (መáŒŊሐፍ áŒĻá‰ĸá‰ĩ)
ከዚህም አልፎ የይáˆĩሐቅን áŠĨናá‰ĩ áˆŖáˆĢንáŖ የáˆļምáˆļንን áŠĨናá‰ĩ (áŠĨንá‰ĩኩይን) ምክነá‰ŗቸውን የቆረጠ ወልá‹ļ ለመáˆŗም á‹Ģበቃቸው ይኸው ፈá‰ŗሔማኅጸን የልዑል áŠĨግዚአá‰Ĩሔር መልአክተኛ ቅዱáˆĩ ሩፋኤል ነው፡፡ከመልአኩ ከቅዱáˆĩ ሩፋኤል ረá‹ĩኤá‰ĩ á‹Ģáˆŗá‹ĩርá‰Ĩን አሜን !!!
አንá‹ĩ አምላክ በሚሆን በአá‰Ĩ በወልá‹ĩ በመንፈáˆĩ ቅዱáˆĩ áˆĩም አሜን✝✝
ግንá‰Ļá‰ĩ 14-á‹ĩንጋዩን áŠĨንደ ጀልá‰Ŗ ተጠቅመው የáŒŖናን ሐይቅ የተáˆģገሩá‰ĩ የአቡነ á‹Ģáˆŗይ ዓመá‰ŗዊ መá‰ŗሰá‰ĸá‹Ģ በዓላቸው ነው፡፡
+ ሙáˆŊáˆĢው ቅዱáˆĩ ገá‰Ĩረክርáˆĩá‰ļáˆĩ ከáŒĢጉላ ቤቱ ወáŒĨá‰ļ የመነነበá‰ĩ ዕለá‰ĩ ነው፡፡
+ የአንá‹ĩነá‰ĩ ማኅበርን የመሠረተáŖ በአá‰Ŗ መቃርáˆĩ áŠĨጅ ከመነኮሰ በኋላ áŠĨነ አረጋዊን á‹Ģመነኮሰውና ገá‹ŗማዊ ኑሮንና ምንኩáˆĩናን á‹Ģáˆĩፋፋው ወንá‹ĩና ሴá‰ĩ መነኮáˆŗá‰ĩም ፊá‰ĩ ለፊá‰ĩ áŠĨንá‹ŗይተá‹Ģዩ á‰Ĩሎ ሕግ የሠáˆĢ á‰ŗላቁ አá‰Ŗá‰ĩ አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ ዐረፈ፡፡ áŠĨርሱም በአá‹ŗም መቃá‰Ĩር ላይ 60 ዓመá‰ĩ ቆሞ የጸለየ ሲሆን በአንዲá‰ĩ ሴá‰ĩ ላይ አá‹ĩረው የነበሩá‰ĩን 100 አጋንንá‰ĩ በጸሎá‰ĩ ወደ áŠĨርሹ áŠĨንዲገለበጡና በáŠĨርሹ ላይ áŠĨንዲá‹Ģá‹ĩሊ አá‹ĩርጎ በጾም ጸሎá‰ĩ áˆĩግደá‰ĩ á‹Ģቃጠላቸው ነው፡፡
+ ከሀገረ ፈርማ የተገኙá‰ĩ አá‰Ŗ ሲማኮáˆĩ በሰማዕá‰ĩነá‰ĩ ዐረፉ፡፡

አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ፡- አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ ግá‰Ĩፅ ውáˆĩáŒĨ ኤáˆĩና በምá‰ĩá‰Ŗል መንደር ከአረማውá‹Ģን ቤተሰá‰Ļá‰Ŋ በ290 ዓ.ም ተወለደ፡፡ በቆáˆĩጠንáŒĸኖáˆĩ ዘመነ መንግáˆĨá‰ĩ ለውá‰ĩá‹ĩርናም ተመልምሎ አገልግሎá‰ĩ ሰáŒĨቷል፡፡ በውá‰ĩá‹ĩርናው ዘመን የክርáˆĩቲá‹Ģኖá‰Ŋን ቆáˆĢáŒĨነá‰ĩáŖ ደግነá‰ĩና ርኀáˆĢኄ በማየቱ ልቡ áˆĩለተነáŠĢ ግá‹ŗጁን ፈáŒŊሞ ሲመለáˆĩ በ313 ዓ.ም የክርáˆĩá‰ĩናን áŠĨምነá‰ĩ ጠንቅቆ በመማር አምኖ ተጠመቀ፡፡ የአá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ ልቡና የቅዱáˆĩ áŠĨንáŒĻንáˆĩ ደቀ መዝሙር በነበረው በአá‰Ŗ ጴላáŒĻንáˆĩ ኑሮ áˆĩለተማረከ ወደ በረሃ ወርá‹ļ የá‰Ĩሕá‰ĩውናን ኑሮና áˆĨርዓá‰ĩ ሲማር ከቆየ በኋላ በ320 ዓ.ም በዓá‰Ŗይ ወንዝ አጠገá‰Ĩ á‰ŗቤኒáˆĩ ከተá‰Ŗለው á‰Ļá‰ŗ የáˆĢሱን ገá‹ŗም መሠረተ፡፡ ይáŠŊም á‰ŗላቅ አá‰Ŗá‰ĩ ከአá‰Ŗ ጰላሞን ዘንá‹ĩ መንኩáˆļ ሲá‹Ģገለግለው ኖረ፡፡ የምንኩáˆĩናንም áˆĨáˆĢ áŠĨየሠáˆĢ á‰Ĩዙ ዘመናá‰ĩ ኖረ፡፡ ከáŠĨግዚአá‰Ĩሔር የá‰ŗዘዘ መልአክ ተገልáŒĻለá‰ĩ áŠĨንደ አá‰Ŗá‰ļá‰ģá‰Ŋን ሐዋርá‹Ģá‰ĩ የአንá‹ĩነá‰ĩን ማኅበር ለመáˆĨáˆĢá‰ĩ መነኮáˆŗá‰ĩን áŠĨንዲሰበáˆĩá‰Ĩ አዘዘው፡፡ በá‰ŗዘዘውም መሠረá‰ĩ á‰Ĩዙዎá‰Ŋ መነኮáˆŗá‰ĩን ሰá‰Ĩáˆĩá‰Ļ በየá‰Ļá‰ŗው á‰Ĩዙ ገá‹ŗማá‰ĩን ገደመላቸው፡፡
ርዕሰ መነኮáˆŗá‰ĩ የሆኑá‰ĩ አቡነ áŠĨንáŒĻንáˆĩ በáŠĨግዚአá‰Ĩሔር ፈቃá‹ĩና á‰ĩáŠĨዛዝ ምንኩáˆĩናን ከሊቀ መልአኩ ከቅዱáˆĩ ሚáŠĢኤል áŠĨጅ ተቀበሉ፡፡ áŠĨንáŒĻንáˆĩም á‰ŗላቁ መቃርáˆĩን አመነኮሷቸው፤ á‰ŗላቁ መቃርáˆĩም áŒŗኩሚáˆĩን አመነኮሷቸው፤ አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩም አá‰Ŗ ቴዎá‹ĩሎáˆĩ አመነኮሷቸው፤ አá‰Ŗ ቴዎá‹ĩሎáˆĩም አቡነ አረጋዊን አመለኮሷቸው፡፡ አቡነ አረጋዊ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ ቤዛነንáŖ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ ቤዛነ መáˆĩቀል ሞዐንáŖ መáˆĩቀል ሞዐ ዮሐኒንáŖ ዮሐኒ áŠĸየሱáˆĩ ሞዐንና ተክለ ሃይማኖá‰ĩን (በቆá‰Ĩና በአáˆĩáŠŦማ)áŖ áŠĸየሱáˆĩ ሞዐ ተክለ ሃይማኖá‰ĩን (በቅናá‰ĩና በቀሚáˆĩ)áŖ ተክለ ሃይማኖá‰ĩ áŠĸየሱáˆĩ ሞዐን (በቆá‰Ĩና በአáˆĩáŠŦማ) ወልደዋል፡፡ አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ መጀመáˆĒá‹Ģ ወደ ምንኩáˆĩናው ዓለም የመáŒŖው በá‰ŗላቁ አá‰Ŗ ጰላሞን አማáŠĢኝነá‰ĩ ነው፡፡ ለተወሰነ ጊዜም መንፈáˆŗዊ አá‰Ŗቱን áŠĨየረá‹ŗ ሕይወተ መነኮáˆŗá‰ĩን አáŒĨንቷል፡፡ በመንፈáˆŗዊ ሕይወቱና በተጋá‹ĩሎ áŠĨየበረá‰ŗና áŠĨየደረጀ ሲሄá‹ĩ ከአá‰Ŗ ጰላሞን ተለይá‰ļ ማሕበር መáˆĨርá‰ļ ለመኖር አምላኩን ጠይቆ ፈቃá‹ĩ በማግኘቱ በሕግ የሚመáˆĢ የመጀመáˆĒá‹Ģውን ገá‹ŗም መáˆĨርቷል፡፡

ቅዱáˆĩ አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ ጸሎቱ አጋንንá‰ĩን ከአáŠĢá‰Ŗá‰ĸው አá‹Ģáˆĩቀርá‰Ŗቸውም ነበር፡፡ አáŠĢሉ አልቆ በአáŒĨንá‰ļቹ áŠĨáˆĩáŠĒቆም á‹ĩረáˆĩ በጾም በጸሎá‰ĩ ይጋደል ነበር፡፡ ዓርá‰Ĩ ዓርá‰Ĩ የጌá‰ŗá‰Ŋንን ሕማማá‰ĩ áŠĨá‹Ģሰበ ከáŠĨንá‰Ŗ ጋር ይሰግá‹ŗል፡፡ áŠĨንá‰Ŗውና ላበቱ ከፊቱ áŠĨየወረደ አáŠĢá‰Ŗá‰ĸው ጭቃ ይሆን ነበር፡፡ ጌá‰ŗá‰Ŋንም መáˆĩቀል ተሸክሞ ይá‰ŗየው ነበር፡፡ ከዕለá‰ŗá‰ĩም በአንደኛው ቀን አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ áŠĨንደወá‰ĩሮው ሲሰግá‹ĩ ወዙ ወርá‹ļ መáˆŦቱን ጭቃ አደረገውáŖ ወዲá‹Ģው ጌá‰ŗá‰Ŋን ተገለጸለá‰ĩና áŒŗኩሚáˆĩ ‹‹አንተን አገኝ á‰Ĩá‹Ŧ áŠĨንዲህ áŠĨደክማለሁâ€ēâ€ē አለው፡፡ ጌá‰ŗá‰Ŋንም ‹‹áŠĨኔም áŠĨንጂ ላንተ á‰Ĩá‹Ŧ áŠĨንዲህ ሆኜ ተሰቅá‹Ģለሁâ€ēâ€ē á‰Ĩሎ በዕለተ ዓርá‰Ĩ áŠĨንደተሰቀለ ሆኖ ጐኑን áŠĨንደተወጋ ደሙ áŠĨንደፈሰሰ ሆኖ á‰ŗይá‰ļá‰ŗል፡፡

ከዕለá‰ŗá‰ĩ በአንደኛው ቀን አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ በበረሃ áˆŗለ መልአክ መáŒĨá‰ļ በነሐáˆĩ የተáŒģፈ ሕግ ሰጠው፤ áŠĨርሱም በዚህ የመጀመáˆĒá‹Ģውን áˆĨርዓተ መነኮáˆŗá‰ĩን አዘጋጅቷዋል፡፡ ከዚህም á‰Ŗለፈ በርáŠĢá‰ŗ áˆĨáˆĢዎá‰Ŋን ሠርቷል፡፡ ቅዱáˆĩ á‹ģኩሚáˆĩ áŒĢማ áˆŗይáŒĢማ áŠĨሾህን áˆŗይሰቀቅ ይረግáŒĨም ነበር፡፡ አá‰Ŗá‰ŗá‰Ŋን ቅዱáˆĩ áŒŗኩሚáˆĩ ከርሕáˆĢሔው የተነáˆŖ አጋንንá‰ĩ á‹Ģደሩá‰Ŗቸውን ሰዎá‰Ŋ ሲá‹Ģገኝ በቀáŒĨá‰ŗ ከመፈወáˆĩ ይልቅ ደዌውን ርኩáˆŗን መናፍáˆĩቱንም ወደ áŠĨርሹ áŠĨንዲገለበጡ á‹Ģደርግ ነበር፡፡ ከዚá‹Ģም በጾም በጸሎá‰ĩና በáˆĩግደá‰ĩ መá‹ĩረáˆģ á‹ĢáˆŗáŒŖቸዋል፡፡ á‹Ģንጊዜ በግá‹ŗቸው áŠĨየጮሁ ሲወጡ አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ ‹‹ምነው á‰ĩንáˆŊ ቆዩ áŠĨንጂâ€ēâ€ē áŠĨá‹Ģለ ይቀáŒŖጠá‰Ĩá‰Ŗቸዋል፡፡ አንá‹ĩ ዕለá‰ĩ ቅዱáˆĩ አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ አንዲá‰ĩ ሴá‰ĩ á‰Ĩዙ አጋንንá‰ĩ ሰፍረውá‰Ŗá‰ĩ áˆĩá‰ĩሠቃይ አየና ‹‹አቤቱ ጌá‰ŗá‹Ŧ ሆይ! ይህን ሁሉ áŠĨንዴá‰ĩ á‰ĩá‰Ŋለዋለá‰Ŋ?â€ēâ€ē á‰Ĩሎ በáŠĨርሡ ላይ á‹Ģለውን የአጋንንá‰ĩ መንጋ ወደ áŠĨርሹ áŠĨንዲገለበáŒĨ ፈáŒŖáˆĒውን በጸሎá‰ĩ ጠየቀ፡፡ በዚá‹Ģም ጊዜ በአንá‹ĩ ቀፎ ውáˆĩáŒĨ á‹Ģሉ ንá‰Ļá‰Ŋ ወደ ሌላ ቀፎ áŠĨንደሚገለበጡ áŠĨነዚá‹Ģ በሴá‰ĩዮዋ ላይ አá‹ĩረው የነበሩ አጋንንá‰ĩ በሙሉ ከዚá‹Ģá‰Ŋ ሴá‰ĩዮ ወáŒĨተው በአá‰Ŗ áŒŗጉሚáˆĩ ላይ ሰፈሩ፡፡ áŠĨርሱም ማቅ ለá‰Ĩáˆļ አመá‹ĩ ነáˆĩንáˆļ በáˆĨግደá‰ĩ በጾምና በጸሎá‰ĩ አሠቃá‹Ģቸው፡፡ አጋንንቱም የአá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩን á‰ĩሩፋá‰ĩና ተጋá‹ĩሎ መቋቋም áˆĩላልá‰ģሉ አጋንንቱ ‹‹áŠĨንሂá‹ĩ áŠĨንጂ áŠĨንግዲህማ ከዚህ ምን áŠĨናደርጋለንâ€ēâ€ē ሲሉ ሰማቸው፡፡ ቅዱáˆĩ áŒŗኩሚáˆĩም ‹‹ለምን አá‰ĩቆዩም ሰው áŠĨንዲህ áŠĢለ ኃáŒĨáŠĨ ወá‹ŗጁ ቤá‰ĩኮ áŒĨቂá‰ĩ ጊዜ á‹Ģርፋልâ€ēâ€ē á‰ĸላቸው ‹‹áŠĨኛáˆĩ ከገነá‰ĩ áŠĢáˆĩወáŒŖነው ከአá‹ŗም በቀር áŠĨንዲህ á‹Ģለ ሰው አላየንምáŖ á‰ĩሩፋቱ አቃጠለን ሊá‹Ģáˆĩቀምጠን አልá‰ģለምâ€ēâ€ē á‰Ĩለው መáˆĩክረውለá‰ĩ ወáŒĨተው ሄዱ፡፡
አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩን áˆĩለ ክá‰Ĩሊ መልአክ ነáŒĨቆ ወáˆĩá‹ļ ገነá‰ĩንና ሲáŠĻልን አáˆŗይá‰ļ በኋላ ወደ ምá‹ĩር መልáˆļá‰ŗል፡፡ ከዚህም በኋላ áŒģá‹ĩቁ በዙáˆĒá‹Ģው ለተሰበሰቡá‰ĩ መነኰáˆŗá‰ĩ የአንá‹ĩነá‰ĩ ኑሮ ሕግ አወáŒŖላቸው፡፡ ምንኩáˆĩና በáŠĨግዚአá‰Ĩሔር ፈቃá‹ĩ በአá‰Ŗ áŠĨንáŒĻንáˆĩ á‰ĸመሠረá‰ĩም ሕይወቱን በማáˆĩፋፋá‰ĩ ደረጃ የቅዱáˆĩ áŒŗኩሚáˆĩን á‹Ģህል የደከመና የተáˆŗáŠĢለá‰ĩ ግን የለም፡፡ በአá‰Ŗ áŠĨንáŒĻንáˆĩ የተጀመረውን የመነኰáˆŗá‰ĩን የማኅበር ኑሮ አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ በተጠናከረ መልኩ áˆĨርዓá‰ĩ አውáŒĨá‰ļ የበለጠ ከማáˆĩፋፋቱም በተጨማáˆĒ ዘጠኝ የወንá‹ļá‰Ŋና ሁለá‰ĩ የሴá‰ļá‰Ŋ ገá‹ŗማá‰ĩ መáˆĨርቷል፡፡ አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ á‹ĢወáŒŖው የመነኰáˆŗá‰ĩ የአኗኗር ሕግ ዋናው ቅጂ ሲጠፋ ወደ ላቲን የተተረጐመው ግን áŠĨáˆĩከዛáˆŦ á‹ĩረáˆĩ ይገኛል፡፡ ከሕግጋቱ መáŠĢከል፡- መነኮáˆŗá‰ĩ ጠዋá‰ĩና ማá‰ŗ በማኅበር áŠĨንዲጸልዩáŖ በኅá‰Ĩረá‰ĩ በአንá‹ĩነá‰ĩ áŠĨንዲሠሩáŖ ቅዱáˆŗá‰ĩ መáŒģሕፍá‰ĩን አዘውá‰ĩረው áŠĨንዲመለከቱáŖ መነኮáˆŗá‰ĩ ሚመá‰ĩ áŠĨንá‹ŗይሾሙ ከልክሏልáŖ መነኮáˆŗá‰ĩ የቁም áŒŊሕፈá‰ĩ áŠĨንዲማሩáŖ ገá‰ĸና ወáŒĢቸው አንá‹ĩ ላይ áŠĨንዲሆንáŖ በአንá‹ĩነá‰ĩ áŠĨንዲመገቡáŖ አንá‹ĩ ዓይነá‰ĩ ልá‰Ĩáˆĩ áŠĨንዲኖáˆĢቸውáŖ ንáŒŊሕናቸውን ጠá‰Ĩቀው áŠĨንዲኖሩáŖ ከገá‹ŗማቸው በፍጹም áŠĨንá‹ŗይወጡ ከልክሏልáŖ የመጀመáˆĒá‹Ģውን áˆĨርዓተ መነኮáˆŗá‰ĩ አዘጋጅቷልáŖ መነኮáˆŗá‰ĩ ደግነá‰ĩáŖ ፍቅርና á‰ŗዛá‹Ĩነá‰ĩ áŠĨንዲኖáˆĢቸው የሚሉá‰ĩና የመáˆŗሰሉá‰ĩ ናቸው፡፡

ሐዋርá‹Ģው ቅዱáˆĩ አá‰ĩናቴዎáˆĩ ወደ ላዕላይ ግá‰ĨáŒŊ በወáŒŖ ጊዜ ይህን አá‰Ŗá‰ĩ áŒŗኩሚáˆĩን ቅáˆĩና ሊሾመው ወደደ፡፡ ከáŠĨርሱም ሸሸ፡፡ áŠĨጅግ የከበረ አá‰ĩናቴዎáˆĩም ልጆቹን ‹‹‹የማይናወáŒŊ ቤá‰ĩን የሠáˆĢህ ቅዱáˆĩ ሆይ! ከከንቱ ውá‹ŗሴ የáˆĢቅህ አንተ á‰Ĩፁዕ ነህáŖ ልጆá‰Ŋህም á‰Ĩፁዓን ናቸውâ€ē á‰Ĩሎሃል በሉá‰ĩ አá‰Ŗá‰ŗá‰Ŋሁንâ€ēâ€ē አላቸው፡፡
ይáŠŊም ቅዱáˆĩ አá‰Ŗá‰ĩ አንá‹ĩ ጊዜ ሲáŠĻልን á‹Ģዩ ዘንá‹ĩ ወደዱ፡፡ áŠĨነሆም የáŠĨግዚአá‰Ĩሔር መልአክ ነáŒĨቆ ወáˆĩá‹ļ በገነá‰ĩ የáŒģá‹ĩቃንን ማደáˆĒá‹Ģ áŠĨንዲሁም በሲáŠĻል የáˆĨቃይን á‰Ļá‰ŗዎá‰Ŋ ሁሉ አáˆŗá‹Ģቸው፡፡
አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ ከግá‰Ĩፅ ውáŒĒ ምንኩáˆĩናን አáˆĩፋፍቷልáŖ á‰Ĩዙ አá‰Ŗá‰ļá‰Ŋን አáˆĩተምሮ አመንኩሷል፡፡ ለምáˆŗሌ በáŠĸá‰ĩዮá‹Ŋá‹Ģ ምንኩáˆĩናን á‹Ģáˆĩፋፉá‰ĩ
ቡነ አረጋዊ የዚህ ቅዱáˆĩ አá‰Ŗá‰ĩ ደቀ መዝሙር ናቸው፡፡ አንá‹ĩ ሰው ወደ ገá‹ŗማቱ ሲመáŒŖ የáˆĻáˆĩá‰ĩ ዓመá‰ĩ አመክሮ ይሰጠውና ጠá‰Ŗዩና ፍላጐቱ ይገመገማል፡፡ ከዚá‹Ģ በኋላም á‰Ĩርá‰ŗቱና áŒŊናቱ á‰ŗይá‰ļ ወደ ማኅበረ መነኰáˆŗቱ ይቀላቀላል፡፡ አá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ በዚሁ ዓይነá‰ĩ መንገá‹ĩ áˆĨርዓá‰ĩ ሠርተው ሕግ አáŒŊንተው ገá‹ŗማá‰ĩን áŠĢáˆĩፋፉና አበምኔá‰ĩ ሁነው 40 ዓመá‰ĩ áŠĢገለገሉ በኋላ ከጌá‰ŗá‰Ŋን ቃልáŠĒá‹ŗን ተቀá‰Ĩለው ለደቀ መዛሙርá‰ļá‰ģቸው ቅዱáˆĩ ቴዎá‹ĩሎáˆĩ ሹመውላቸው በተወለዱ በ56 ዓመá‰ŗቸው በ346 ዓ.ም በሰላም ዐርፈው ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ ነፍáˆŗቸውን ጌá‰ŗá‰Ŋን በክá‰Ĩር ተቀá‰Ĩሏá‰ŗል፡፡ የአá‰Ŗ áŒŗኩሚáˆĩ ረá‹ĩኤá‰ĩ በረከá‰ŗቸው ይደርá‰ĨንáŖ በጸሎá‰ŗቸው ይማረን፡፡
+ + + + +

አá‰Ŗ ሲማኮáˆĩ፡- ይáŠŊም ቅዱáˆĩ ከሀገረ ፈርማ የተገኘ á‰ŗላቅ ሰማዕá‰ĩ ነው፡፡ ወá‹ŗጆን ሁሉ በሃይማኖá‰ĩ ጸንá‰ļ áˆĩለመኖር á‹ĢáˆĩተምáˆĢቸው ነበር፡፡ ቡላሚáˆĩ የሚá‰Ŗለው ከሃዲ መኮንን ክርáˆĩቲá‹Ģኖá‰Ŋን ሊá‹Ģሠቃይና ሊገá‹ĩል áŠĨንደመáŒŖ በሰማ ጊዜ አá‰Ŗ ሲማኮáˆĩ ሰማዕá‰ĩ ይሆን ዘንá‹ĩ ወደደና ቤተሰá‰Ļቹን ተሰናá‰Ĩá‰ļ ወደ ሰማዕá‰ĩነá‰ĩ አደá‰Ŗá‰Ŗይ ወáŒŖ፡፡ ወደ ሀገረ á‹ĩሜáˆĢ ቅርá‰Ĩ ወደሆነ ወደ ሀገረ በክሩዝ ሄá‹ļ ከሃዲውን መኮንን አገኘው፡፡ áŠĨርሱም አንዲቷን ሰማዕá‰ĩ ይዞ ሲá‹Ģሠቃá‹Ģá‰ĩና ወደ áŠĨáˆŗቱ ምá‹ĩጃ ሲጨምáˆĢá‰ĩ áŠĨáˆŗቱም በተአምáˆĢá‰ĩ ሲቀዘቅáˆĩ ተመለከተ፡፡ ከዚህም በኋላ አá‰Ŗ ሲማኮáˆĩ በፊቱ ቆሞ የጌá‰ŗá‰Ŋንን ክá‰Ĩር መሰከረ፡፡
መኮንኑም አá‰Ŗ ሲማኮáˆĩን ይዞ á‰Ĩዙ አሠቃየው፡፡ በዚህ ጊዜም አá‰Ŗ ሲማኮáˆĩ ዕá‹ĩሜው 20 ዓመá‰ĩ ነበር፡፡ በመጀመáˆĒá‹Ģ ሰቀሉá‰ĩ፤ ቀáŒĨለውም ከመንኮáˆĢኩር ውáˆĩáŒĨ ጨምረው አበáˆĢዩá‰ĩ፡፡ ከáŠĨርሱም á‰Ĩዙ ደም ፈሰሰ፡፡ አንዲá‰ĩም ዐይኗ áˆĨውር የነበረá‰Ŋ ሴá‰ĩ ደሙ ፈáˆļ ዐይኗን በነáŠĢá‰ĩ ጊዜ ዐይኗ á‹ŗነ፡፡
ከዚáŠŊም በኋላ ደግመው በáŠĨንጨá‰ĩ ላይ ሰቅለው አሠቃየው፡፡ በáˆĨቃይም ላይ ሆኖ ወደ ጌá‰ŗá‰Ŋን በለመነ ጊዜ አá‹ŗነው፡፡ መኮንኑም የአá‰Ŗ ሲማኮáˆĩን áˆĢáˆĩ በሰይፍ ይቆርጡá‰ĩ ዘንá‹ĩ አዘዘ፡፡ ሰá‹Ģፊውም ይቆርጠው ዘንá‹ĩ ሰይፉን መዘዘ ነገር ግን ኃይል ተነáˆĨá‰ļá‰ĩ ማነቀáˆŗቀáˆĩ አቃተው፡፡ áŠĨንዲሁም ሁለተኛውáŖ áˆĻáˆĩተኛው â€Ļ áŠĨáˆĩከ ዐáˆĨáˆĢ አáˆĢá‰ĩ ሰይፈኞá‰Ŋ ኃይላቸው ደከመ፡፡ áŠĨነርሱም በምá‹ĩር ላይ ወደቁ፡፡ ከዚህም በኋላ በአንገቱ ገመá‹ĩ አáˆĩገá‰Ĩተው áŠĨáˆĩከ ረጅም ተáˆĢáˆĢ አናá‰ĩ á‹ĩረáˆĩ ጎተቱá‰ĩ፡፡ ነፍሱንም በክá‰Ĩር á‰Ŗለቤá‰ĩ በጌá‰ŗá‰Ŋን áŠĨጅ አáˆŗልፎ ሰáŒĨá‰ļ የምáˆĩክርነá‰ĩ አክሊልን ተቀá‹ŗጀ፡፡ ከወá‰ŗደሮቹም ውáˆĩáŒĨ ዲá‹ŗና ደንቆሮ የነበረ የቅዱሱን áˆĨጋ á‰Ŗየጊዜ ጆሮዎቹ ሰሙáŖ አንደበቱም መናገር ጀመረ፡፡ ከáˆĨጋውም á‰Ĩዙ ተአምáˆĢá‰ĩ ተፈáŒŊመው á‰ŗዩ፡፡ á‰Ĩዙ አረማውá‹Ģንም የቅዱáˆĩ አá‰Ŗ ሲማኮáˆĩን ተአምáˆĢá‰ĩ አይተው በጌá‰ŗá‰Ŋን አምነው ተጠመቁ፡፡ የጌá‰ŗá‰Ŋንንም ክá‰Ĩር መáˆĩከረው በሰማዕá‰ĩ ዐረፉ፡፡ ቁáŒĨáˆĢቸውም አንá‹ĩ áˆēህ ሰá‰Ŗá‰ĩ መá‰ļ ኃምáˆŗ (1750) ሆነ፡፡ የአá‰Ŗ ሲማኮáˆĩና የማኅበርተኞቹ ረá‹ĩኤá‰ĩ በረከá‰ŗቸው ይደርá‰ĨንáŖ በጸሎá‰ŗቸው ይማረን፡፡
+ + + + + +

አቡነ á‹Ģáˆŗይ ዘማንá‹ŗá‰Ŗ፡- አቡነ á‹Ģáˆŗይ ‹‹ሰá‰Ŗቱ ከዋክá‰Ĩá‰ĩâ€ēâ€ē ከሚá‰Ŗሉá‰ĩ የሀገáˆĢá‰Ŋን ቅዱáˆŗን ውáˆĩáŒĨ አንዱ ናቸው፡፡ áŠĨነዚህም ‹‹ሰá‰Ŗቱ ከዋክá‰Ĩá‰ĩâ€ēâ€ē የተá‰Ŗሉá‰ĩ አቡነ áˆŗሙኤል ዘዋልá‹ĩá‰ŖáŖ አቡነ á‹Ģáˆŗይ ዘማንá‹ŗá‰ŖáŖ አቡነ áˆŗሙኤል ዘቆየፃáŖ አቡነ áˆŗሙኤል ዘáŒŖáˆŦáŒŖáŖ አቡነ á‰ŗዴዎáˆĩ ዘá‰Ŗልá‰ŗርዋáŖ አቡነ á‹Ģፍቅረነ áŠĨግዚáŠĨ ዘጉጉቤ áŠĨና አቡነ ዮሐንáˆĩ ዘጉáˆĢንቄ ናቸው፡፡ áŠĨነዚህን የመላáŠĨክá‰ĩን ሕይወá‰ĩ በምá‹ĩር የኖሩ á‰ŗላላቅ የሀገáˆĢá‰Ŋንን ቅዱáˆŗን በአንá‹ĩ ጊዜ አáˆĩተምረውና አመንኩሰው ለáŒŊá‹ĩቅ á‹Ģበቋቸው አቡነ መá‹ĩኃኒነ áŠĨግዚáŠĨ ናቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አáŠĨላፍ ቅዱáˆŗንâ€ēâ€ē የተá‰Ŗሉá‰ĩ አቡነ መá‹ĩኃኒነ áŠĨግዚáŠĨ የáŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ á‰Ĩርሃኗ በሆኑá‰ĩ በአቡነ ተክለ ሃይማኖá‰ĩ áŠĨጅ ከመነኮሱ በኋላ አቡነ መá‹ĩኃኒነ áŠĨግዚáŠĨም በተáˆĢቸው á‹Ģáˆĩተማሯቸውና á‹Ģመነኮሷቸው መነኮáˆŗá‰ĩ ቁáŒĨáˆĢቸው በውል አይá‰ŗወቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖá‰ĩም ለአቡነ መá‹ĩኃኒነ áŠĨግዚáŠĨ ‹‹áˆĩፍር ቁáŒĨር የሌላቸው ከዋክá‰Ĩá‰ĩ ቅዱáˆŗንንâ€ēâ€ē በመንፈáˆĩ ቅዱáˆĩ áŠĨንደሚወልዱ á‰ĩንá‰ĸá‰ĩ ተናግረውላቸው ነበር፡፡ የተንቤኑን አቡነ ዐá‰ĸየ áŠĨግዚáŠĨንáŖ የዞዝ አምá‰Ŗውን አቡነ አá‰Ĩáˆŗዲን ጨምሮ አá‰Ŗá‰ŗá‰Ŋን መá‹ĩኃኒነ áŠĨግዚáŠĨ á‰Ĩርሃን ሆነው በáŒŖም á‰Ĩዙ ቅዱáˆŗንን የለኮሱ á‰ŗላቅ áŒģá‹ĩቅ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንá‹Ģá‰ĩ ነው ‹‹ወላዴ አáŠĨላፍ ቅዱáˆŗንâ€ēâ€ē የተá‰Ŗሉá‰ĩ፡፡

አቡነ መá‹ĩኃኒነ áŠĨነዚህንም ሰá‰Ŗቱን ቅዱáˆŗን በአንá‹ĩ ጊዜ ሲá‹Ģመነኩሷቸው በዚá‹Ģው ቅáŒŊበá‰ĩ መንፈáˆĩ ቅዱáˆĩ ወርá‹ļ ገá‹ŗሙን በá‰Ĩርሃን አáŒĨለቅልቆá‰ĩ á‰ŗይቷል፡፡ ከሰማይም የምáˆĩክርነá‰ĩ á‹ĩምፅ ተሰምቷል፡፡ በዚህም ምክንá‹Ģá‰ĩ አንá‹ĩ ላይ የመነኮሱá‰ĩ áŠĨነዚህ ሰá‰Ŗቱ ቅዱáˆŗን ‹‹ሰá‰Ŗቱ ከዋክá‰Ĩá‰ĩâ€ēâ€ē áŠĨየተá‰Ŗሉ ይጠáˆĢሉ፡፡ áŠĨነዚህም ሰá‰Ŗቱ ከዋክá‰Ĩá‰ĩ የáŒŖናን á‰Ŗሕር በáŠĨግáˆĢቸው ጠቅáŒĨቀው ተáˆģግረው á‰Ĩዙዎቹን ደሴቱ ላይ á‹Ģሉ አáˆĩደናቂ የáŒŖና ገá‹ŗማá‰ĩን የመሠረቱá‰ĩ ናቸው፡፡ ከáŠĨነርሱም ውáˆĩáŒĨ á‰Ŗሕሩን በáŠĨግáˆĢቸውም áŠĨየረገጡ ጠቅáŒĨቀው የተáˆģገሩ አሉ፤ በሌላም á‰Ļá‰ŗ በየá‰Ĩáˆĩ የተሰማሩá‰ĩም á‰ĸሆኑ መáŒģሕፍá‰ļá‰ģቸውን በአንበáˆŗ ጭነው የተጓዙ አሉ፤ á‰ĩልቅ ጠፍáŒŖፋ á‹ĩንጋይን áŠĨንደጀልá‰Ŗ ተጠቅመው በáŠĨርሹ ላይ ሆነው ወደ ደሴá‰ĩ የገቡ አሉ፡፡ አንዱ ዛáˆŦ በዓላá‰ŗቸውን የምናከá‰ĨáˆĢለቸው አቡነ á‹Ģáˆŗይ ናቸው፡፡
ቅዱáˆĩ á‹ŗዊá‰ĩ ‹‹áŠĨግዚአá‰Ĩሔር በቅዱáˆŗኑ ላይ á‹ĩንቅ ነውâ€ēâ€ē (መዝ 67፡35) á‰Ĩሎ áŠĨንደተናገረ áŒģá‹ĩቁ አቡነ á‹Ģáˆŗይ ከáŠĨግዚአá‰Ĩሔር በተሰáŒŖቸውም ጸጋ áŒŖና ሐይቅን የሚá‹Ģቋርጡá‰ĩ በአንá‹ĩ á‰ĩልቅ ጠፍáŒŖፋ á‹ĩንጋይ ላይ ተቀምጠው á‹ĩንጋዩን áŠĨንደ ጀልá‰Ŗ ተጠቅመው ነበር፡፡ á‹Ģ á‹ĩንጋይ ዛáˆŦም á‹ĩረáˆĩ በገá‹ŗማቸው ውáˆĩáŒĨ በክá‰Ĩር ተቀምáŒĻ ይገኛል፡፡ áŒģá‹ĩቁ ከአቡነ áˆŗሙኤል ጋር አá‰Ĩረው ወደዚህ á‰Ļá‰ŗ መጡ፡፡ ከዚá‹Ģም የá‰Ļá‰ŗው አቀማመáŒĨ የá‰Ĩáˆĩ መáˆŦá‰ĩና ደሴá‰ĩ መሆኑን አይተው ‹‹áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ፈቅá‹ļ ይá‰Ŋን ደሴá‰ĩ የጸሎá‰ĩ á‰Ļá‰ŗá‰Ŋን አá‹ĩርጎ á‰ĸሰጠን በጸሎá‰ĩ áŠĨንጠይቀውâ€ēâ€ē ተá‰Ŗá‰Ĩለው ሁሉቱም ቅዱáˆŗን ሹá‰Ŗኤ ገቡ፡፡ ለáˆĩም አጠáˆĢሊ ክá‰Ĩር ምáˆĩጋና ይግá‰Ŗውና ጌá‰ŗá‰Ŋንም ለአቡነ áˆŗሙኤል ዘዋልá‹ĩá‰Ŗ ተገሃá‹ĩ ተልáŒĻላቸው ‹‹ወá‹ŗጄ áˆŗሙኤል ሆይ ይህ á‰Ļá‰ŗ የአንተ አይደለም የወንá‹ĩምህ የá‹Ģáˆŗይ á‰Ļá‰ŗ ነው፡፡ áŠĨኔ ወá‹ŗዘጋጀሁልህ á‰Ļá‰ŗ ወደ ዋሊ ሂá‹ĩâ€ēâ€ē á‰Ĩሎ የዋልá‹ĩá‰Ŗን ምá‹ĩር አáˆŗá‹Ģቸው፡፡ አቡነ áˆŗሙኤልም የጌá‰ŗá‰Ŋንን á‰ĩáŠĨዛዝ ተቀá‰Ĩለው ወንá‹ĩማቸውን አቡነ á‹Ģáˆŗይን ተሰናá‰Ĩተው ወደ ዋልá‹ĩá‰Ŗ ሄደው ገá‹ŗማቸውን አቅንተው ተጋá‹ĩሎቸአውን በዚá‹Ģ ፈጸሙ፡፡

ጌá‰ŗá‰Ŋን á‹ŗግመኛም ለአቡነ á‹Ģáˆŗይ ተገለጠላቸውና ‹‹ወá‹ŗጄ á‹Ģáˆŗይ ሆይ የአá‰Ŗá‰ĩህን መንግáˆĨá‰ĩና የዓለሙን ክá‰Ĩር ከምኞቱ ጋር ለáŠĨኔ á‰Ĩለህ áˆĩለተውክ ይህንኑ á‰Ļá‰ŗ በዚህ ዓለም áˆŗለህ ለአንተáŖ ወደ ዘላለማዊ መንግáˆĨቴ ከወሰá‹ĩኩህ በኋላም ለልጆá‰Ŋህ ምንá‹ŗህ አá‹ĩርጌ ሰáŒĨá‰ŧሃለሁ፤ ምሕረቴንም በá‰Ļá‰ŗህ አዘንá‰Ŗለሁ ቸርነቴም አይለá‹Ģá‰ĩምáŖ á‰Ĩዙ የመንፈáˆĩ ልጆá‰Ŋንም á‰ŗፈáˆĢለህ፤ á‰Ļá‰ŗህም áŠĨኔ ለፍርá‹ĩ áŠĨáˆĩክመáŒŖ á‹ĩረáˆĩ á‰ĩኖáˆĢለá‰Ŋâ€ēâ€ē በማለá‰ĩ ቃልáŠĒá‹ŗኑን አቆመላቸውና ተሰወáˆĢቸው፡፡ ‹‹ምንá‹ŗህâ€ēâ€ē ማለá‰ĩ ደመወዝ ማለá‰ĩ ነውና በዚህም ‹‹ማንá‹ŗá‰Ŗâ€ēâ€ē ማለá‰ĩ ‹‹የአቡነ á‹Ģáˆŗይ ምንá‹ŗ-ደመወዝâ€ēâ€ē ማለá‰ĩ ነው ሲሉ አá‰Ŗá‰ļá‰Ŋ ገá‹ŗሙን ‹‹ማንá‹ŗá‰Ŗ-ምን áŠĨንደ አá‰Ŗâ€ēâ€ē á‰Ĩለው ሰየሙá‰ĩ፡፡
አቡነ á‹Ģáˆŗይ የá‰ĩውልá‹ĩ ሀገáˆĢቸው ሸዋ ተጉለá‰ĩ ነው፡፡ አá‰Ŗá‰ŗቸው ንጉሡ ዓምደ áŒŊዮን ቀá‹ŗማዊ ነው፡፡ ይኸውም ከ1296-1326 ዓ.ም የነበረው ነው፡፡ አቡነ á‹Ģáˆŗይ በልጅነá‰ŗቸው በንጉሡ አá‰Ŗá‰ŗቸው ቤá‰ĩ ሲኖሩ የገá‹ŗማ መነኮáˆŗá‰ĩ ለመንፈáˆŗዊ áˆĨáˆĢ ወደ ንጉሡ ዘንá‹ĩ áŠĨየመጡ ደጅ ሲጠኑ á‹Ģዩአቸዋል፡፡ በዚህም ጊዜ አá‰Ŗá‰ŗá‰Ŋን ገና በልጅነá‰ŗቸው የመነኮáˆŗቱን áŠĨግር á‹ĢáŒĨቡ áˆĩለነበር በዚሁ አጋáŒŖሚ መነኮáˆŗቱን áˆĩለምንኩáˆĩና ሕይወá‰ĩ ይጠይቋቸው ነበር፡፡ መነኮáˆŗቱም ሕይወá‰ŗቸውን á‹Ģáˆĩረዷቸዋል፡፡ አቡነ á‹Ģáˆŗይም á‰Ĩሉá‹Ģá‰ĩንና ሐዲáˆŗá‰ĩን ከልጅነá‰ŗቸው ጀምሮ የተማሩ áˆĩለነበር የአá‰Ŗá‰ļá‰Ŋን á‰ĩምህርá‰ĩና
áˆĩን áŒŊá‹ĩቅ á‰Ĩá‰ĩነግረው ምáˆĨáŒĸሩን ለሀገሩ ሁሉ አá‹ŗረሰበá‰ĩ፡፡ ሙáˆŊáˆĢው ገá‰Ĩረ ክርáˆĩá‰ļáˆĩም ‹‹ግá‰ĨáˆŦ á‰ŗወቀáŖ ከዚህ ውá‹ŗሴ ከንቱ ልáˆŊáˆŊâ€ēâ€ē በማለá‰ĩ ወደሌላ ሀገር በመርከá‰Ĩ ሲጓዝ ፈቃደ áŠĨግዚአá‰Ĩሔር መርከá‰ĸቱን á‹Ģለ አቅáŒŖáŒĢዋ ወáˆĩá‹ļ አá‰Ŗቱ ደጅ አደረሰው፡፡ ማንነቱን áŠĨንደደበቀና ዓለምን ምን á‹Ģህል áŠĨንደናቃá‰ĩ ይረá‹ŗ ዘንá‹ĩ በአá‰Ŗቱና በንጉሡ ደጅ የኔ á‰ĸጤ ለማኝ ሆኖ ለአá‰Ŗቱ ውሾá‰Ŋ የሚሰጠውን ፍርፋáˆĒ áŠĨየተመገበ አሁንም 15 ዓመá‰ĩ ሙሉ በá‰ĩዕግáˆĩá‰ĩ ተቀመጠ፡፡
የአá‰Ŗቱ አáˆŊከሮá‰Ŋ áŠĨንáŠŗን áŠĨáŒŖá‰ĸና ቆáˆģáˆģውን ሁሉ áŠĨየደፉበá‰ĩ ሲá‹Ģሠቃዩá‰ĩ የአá‰Ŗቱ ውሾá‰Ŋ ግን የáŠĨግሩን ቁáˆĩል ይልሱለá‰ĩ ነበር፡፡ በአጠቃላይ ገá‰Ĩረ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ áŠĨጅግ የተከበረ የá‰ŗላቅ ንጉáˆĨ ልጅ ሲሆን ነገር ግን ዓለምን ፍጹም በመናቅ áˆĩለ áŒŊá‹ĩቅ ተሰá‹ļ áŠĨየለመነ á‹Ģገኘውን áŠĨየመጸወተ በጾም በጸሎá‰ĩ áŠĨየተጋደለ 30 ዓመá‰ĩ ሙሉ ተቀመጠ፡፡ በመጨረáˆģም ጌá‰ŗá‰Ŋን áŠĨመቤá‰ŗá‰ŊንንáŖ ቅዱáˆŗን መላáŠĨክá‰ĩን ሁሉáŖ ከገá‰Ĩረ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ በፊá‰ĩ የነበሩ ነá‰ĸá‹Ģá‰ĩን ሁሉáŖ ሐዋርá‹Ģá‰ĩንáŖ áŒģá‹ĩቃንንáŖ ሰማዕá‰ŗá‰ĩን ሁሉ አáˆĩከá‰ĩሎ መáŒĨá‰ļ ቃልáŠĒá‹ŗን ከገá‰Ŗለá‰ĩ በኋላ ከጌá‰ŗá‰Ŋን ጋር አá‰Ĩረውá‰ĩ የመጡá‰ĩ ሁሉ በá‰ŗላቅ ክá‰Ĩርና ምáˆĩጋና áŠĨá‹Ģመሰገኑá‰ĩ ጌá‰ŗá‰Ŋን ክá‰Ĩርá‰ĩ ነፍሱን በáŠĨቅፉ ተቀá‰Ĩሎ አáˆŗርጓá‰ŗል፡፡
የቁáˆĩáŒĨንáŒĨንá‹Ģው ሊቀ áŒŗáŒŗáˆŗá‰ĩ አá‰Ŗ ቴዎፍሎáˆĩ በቅá‹ŗሴ ላይ áˆŗሉ ከንጉሡ ቤá‰ĩ ሄደው የገá‰Ĩረ ክርáˆĩá‰ļáˆĩን áˆĨጋ áŠĨንዲá‹Ģመጡ የáŠĨግዚአá‰Ĩሔር á‹ĩምፅ ከሰማይ በá‰ĩáŠĨዛዝ መáŒŖላቸውና ሄደው á‰ĸá‹Ģዩ የገá‰Ĩረ ክርáˆĩá‰ļáˆĩን áˆĨጋ በንጉáˆĨ አá‰Ŗቱ ደጅ ወá‹ĩቆ አገኙá‰ĩ፡፡ በገá‰Ĩረ ክርáˆĩá‰ļáˆĩም áŠĨጅ ላይ በáŒĨቅል ወረቀá‰ĩ የተáŒģፈ ደá‰Ĩá‹ŗቤ ነበርና ወáˆĩደው ሊá‹Ģነቡá‰ĩ ሲሞክሩ ወረቀቱ አልላቀቅ á‰Ĩሎ ፈáŒŊሞ áŠĨምá‰ĸ አላቸው፡፡ á‰Ĩዙ ምሕላና ጸሎá‰ĩ ከተደረገ በኋላ ወረቀቱ ከáŠĨጁ ላይ ተላቀቀና ሲነበá‰Ĩ ገá‰Ĩረ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ áˆĩለ አምላኩ ፍቅር á‰Ĩሎ ለ30 ዓመá‰ŗá‰ĩ á‹Ģáˆŗለፈውን áŠĨጅግ አሠቃቂ መከáˆĢ በተለይም በአá‰Ŗቱ ደጅ ማንም áˆŗá‹Ģውቀው á‹Ģáˆŗለፈውን áŠĨጅግ አáˆŗዛኝ መከáˆĢና በኀዘን የሚá‹Ģáˆĩለቅሰውን á‰ŗáˆĒኩን በáˆĢሹ áŠĨጅ በዝርዝር áŒŊፎá‰ĩ ተገኝቷል፡፡ ንጉሡ አá‰Ŗቱና ንግáˆĨá‰ĩ áŠĨናቱም ይህንን ልጃቸው የáŒģፈውን መልáŠĨክá‰ĩ á‰Ŗነበቡ ጊዜ የሚሆኑá‰ĩ ጠፋቸው፡፡ በáŒŖም የሚገርመው ደግሞ መጀመáˆĒá‹Ģ ላይ ወላጆቹ ሚáˆĩá‰ĩ አá‹ĩርገው á‹Ģመጡለá‰ĩ የሮሙ ንጉáˆĨ ሴá‰ĩ ልጅ ለá‰Ŗሏ á‰ŗማኝ ሆና 30 ዓመá‰ĩ ሙሉ በáŠĨናá‰ĩ አá‰Ŗቱ ቤá‰ĩ በá‰ĩዕግáˆĩá‰ĩ áˆĩá‰ĩጠá‰Ĩቀው መኖሯ ነው፡፡ áŠĨርሷም á‰ŗáˆĒኩ ሲነበá‰Ĩ á‰Ĩá‰ĩሰማ áŠĨንደ ዕá‰Ĩá‹ĩ ሆነá‰Ŋ፡፡ የቅዱáˆĩ ገá‰Ĩረ ክርáˆĩá‰ļáˆĩን áˆĨጋውን ወደ ቤተ ክርáˆĩቲá‹Ģን ሲወáˆĩዱ áŠĨጅግ አáˆĩገáˆĢሚ ተአምáˆĢá‰ĩ በá‹ĩውá‹Ģን ሕመምተኞá‰Ŋ ላይ ተፈáŒŊሟል፡፡ ከተአምáˆĢቱ የተነáˆŖ መንገዱ በሕዝá‰Ĩ ተጨናንቆ አላáˆŗልፍ á‰ĸላቸው ነገሡ በመንገá‹ĩ á‹ŗር ወርቅ áŠĨየበተነ ሰው ወርቁን ለማንáˆŗá‰ĩ ሲሄá‹ĩ በፍáŒĨነá‰ĩ ወደ ቤተ ክርáˆĩቲá‹Ģን አá‹ĩርሰውá‰ŗል፡፡ የሙáˆŊáˆĢው ቅዱáˆĩ የገá‰Ĩረ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ ረá‹ĩኤá‰ĩ በረከቱ ይደርá‰ĨንáŖ በጸሎቱ ይማረን፡፡
ን ቃል በማገናዘá‰Ĩ የፈáŒŖáˆĒá‹Ģቸው ፍቅር በልቡናቸው áŠĨንደ áŠĨáˆŗá‰ĩ ነደደ፡፡ ይልቁንም ‹‹ሰው ዓለሙን ሁሉ á‰ĸá‹Ģተርፍ ነፍሱን ግን á‰ĸá‹Ģጎá‹ĩል ምን ይጠቅመዋልâ€ēâ€ē የሚለውን የጌá‰ŗá‰Ŋንን ቃል አሰቡ፡፡ ማቴ 16፡26፡፡ ከዚህም በኋላ የንጉሡ አá‰Ŗá‰ŗቸውን የአልጋ ወáˆĢáˆŊነá‰ĩ ማለá‰ĩም የንጉáˆĨነá‰ĩን ክá‰Ĩር ፈáŒŊመው በመናቅ ‹‹áŠĨኔን መከተል የሚወá‹ĩ á‰ĸኖር áŠĨáˆĢሱን ይáŠĢá‹ĩáŖ መáˆĩቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝâ€ēâ€ē (ማቴ 16፡27) á‹Ģለውን የጌá‰ŗá‰Ŋንን ቃል አáˆĩበው ንጉáˆŖውá‹Ģን ቤተሰá‰Ļá‰ģቸውን áŒĨለው ለምነና ወጡ፡፡

ለምነና áŠĨንደወጡም ከሸዋ ተነáˆĨተው ወደ á‰ĩግáˆĢይ ክፍለ ሀገር በአክሱም አቅáˆĢá‰ĸá‹Ģ ከሚገኘው ገá‹ŗም ደá‰Ĩረ በንኮል ከሚá‰Ŗለው ከአቡነ መá‹ĩኃኒነ áŠĨግዚáŠĨ ገá‹ŗም ደረሱ፡፡ አቡነ መá‹ĩኃኒነ áŠĨግዚáŠĨም አቡነ á‹Ģáˆŗይ የáŠĨግዚአá‰Ĩሔር ጸጋ á‹Ģደረá‰Ŗቸው ሰው መሆናቸውንና ወደ áŠĨርáˆŗቸውም áŠĨየመጡ መሆኑን በመንፈáˆĩ ዐውቀውá‰ĩ áˆĩለነበር በደáˆĩá‰ŗ ተቀበሏቸውና በረá‹ĩáŠĨነá‰ĩ ከወንá‹ĩሞá‰ģቸው ጋር áŒ¨áˆ˜áˆ¯á‰¸á‹áĄáĄ አቡነ á‹Ģáˆŗይም የገá‹ŗም መነኮáˆŗá‰ĩን በማገልገል በመንፈáˆŗዊ ተጋá‹ĩሎ á‰Ĩዙ ደከሙ፡፡ በደá‰Ĩረ በንኮል ገá‹ŗምም á‰Ĩዙ áŠĨገáˆĢሚ ተአምáˆĢá‰ĩን አደረጉ፡፡ ከዚህም በኋላ áŠĨግዚአá‰Ĩሔር መልአኩን ልኮ ወደ መáŠĢነ ገá‹ĩላቸው በáŒŖና አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ áŠĨንደሆነ ነገáˆĢቸው፡፡ ‹‹ወላዴ አáŠĨላፍ ቅዱáˆŗንâ€ēâ€ē የተá‰Ŗሉ አቡነ መá‹ĩኃኒነ áŠĨግዚáŠĨም ቀደም á‰Ĩለን የጠáˆĢናቸውን ‹‹ሰá‰Ŗቱን ከዋክá‰Ĩá‰ĩâ€ēâ€ē ምግá‰Ŗር ሃይማኖá‰ŗቸውንáŖ ተጋá‹ĩሎ á‰ĩሩፋá‰ŗቸውንና ገá‰ĸረ ተአምáˆĢá‰ŗቸውን አይተው ፈቃደ áŠĨግዚአá‰Ĩሔርን ጠይቀው በአንá‹ĩ á‰ĸá‹Ģመነኩሷቸው በዚá‹Ģው ቅáŒŊበá‰ĩ መንፈáˆĩ ቅዱáˆĩ ወርá‹ļ ገá‹ŗሙን በá‰Ĩርሃን አáŒĨለቅልቆá‰ĩ á‰ŗይቷል፡፡ ከሰማይም የምáˆĩክርነá‰ĩ á‹ĩምፅ ተሰምቷል፡፡ ከዚህም በኋላ ከሰá‰Ŗቱ ቅዱáˆŗን ውáˆĩáŒĨ áˆĻáˆĩቱ ቅዱáˆŗን አቡነ áˆŗሙኤል ዘዋልá‹ĩá‰ŖáŖ አቡነ á‹Ģáˆŗይ áŠĨና አቡነ á‹Ģፍቅረነ áŠĨግዚáŠĨ ሆነው ከደá‰Ĩረ በንኮል ገá‹ŗም አá‰Ŗá‰ŗቸውን አቡነ መá‹ĩኃኒነ áŠĨግዚáŠĨን ተሰናá‰Ĩተው ወደ áŒŖና ደሴá‰ĩ መáŒĨተዋል፡፡
አቡነ á‹Ģáˆŗይ በ13ኛው መ/ክ/ዘመን በአá‰Ŗá‰ŗቸው የዘመነ ንግáˆĨና መጨረáˆģ ወደ አርá‰Ŗ ምንጭ ሄደው ከዚá‹Ģው ሹá‰Ŗኤ ገá‰Ĩተው ፈáŒŖáˆĒá‹Ģቸውንነ á‰ĸማጸኑ áŠĨግዚአá‰Ĩሔርም ከዚá‹Ģው አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ የሚኖር አንá‹ĩ á‰Ŗሕá‰ŗዊን የመá‹ĩኃነዓለምን áŒŊላá‰ĩ áŠĨንዲወáŒŖቸው አዘዘላቸው፡፡ áŠĨርáˆŗቸውም áŒŊላቱን ተቀá‰Ĩለው በጎጃም በኩል አá‹ĩርገው ወደ áŒŖና ተመልሰው በዘጌ አከá‰Ŗá‰ĸ ሲደረሱ ከáŒŖና á‰Ŗሕር á‹ŗር ቆመው በየá‰Ĩáˆĩ á‹Ģለውን ርቀá‰ĩና በá‰Ŗሕሩ á‹Ģለውን ቅርበá‰ĩ አይተው አሁንም ወደ ፈáŒŖáˆĒá‹Ģቸው በጸሎá‰ĩ ተማጸኑ፡፡ በዚህም ጊዜ ጌá‰ŗá‰Ŋን ተገልáŒĻላቸው ‹‹ወá‹ŗጄ á‹Ģáˆŗይ ሆይ አá‰ĩጨነቅ áŠĨኔ ከአንተ ጋር ነኝáŖ ከጎንህ á‹Ģለውን á‹ĩንጋይ በá‰Ŗሕሩ ላይ áŒĢነው፤ á‹ĩንጋዩም ለልጅ ልጅ áŠĨኔ ዓለምን ለማáˆŗለፍ áŠĨáˆĩከምመáŒŖበá‰ĩ ሰዓá‰ĩ á‹ĩረáˆĩ መá‰ŗሰá‰ĸá‹Ģ á‰ĩሁንህâ€ēâ€ē አላቸውና ተሰወረ፡፡ አቡነ á‹Ģáˆŗይም የመá‹ĩኃኔዓለምን áŒŊላá‰ĩ ይዘው በá‹ĩንጋዩ ላይ áŠĨንደተቀመጡ á‹ĩንጋዩ áŠĨንደá‰ŗንáŠŗ በá‰Ŗሕሩ ላይ ተንáˆŗፈፈ፡፡ á‰Ŗሕሩም ከማዕበሉ á‰Ĩዛá‰ĩ የተነáˆŖ ይá‰ŗወክ ነበር፡፡ አá‰Ŗá‰ŗá‰Ŋንም á‹Ģለ ምንም ቀዘፋ ልá‰Ĩáˆŗቸውም ውኃ áˆŗይነáŠĢው ቁጭ áŠĨንá‹ŗሉ ማን áŠĨንደአá‰Ŗ ወደ ተá‰Ŗለው á‰Ļá‰ŗቸው ደረሱ፡፡

ከዚህም በኋላ አቡነ á‹Ģáˆŗይ ገá‹ŗማቸውን ገá‹ĩመው ወንá‹ĩሞá‰ģቸውን ሰá‰Ĩáˆĩበው በተጋá‹ĩሎ በመኖር á‰Ĩዙ ቅዱáˆŗንን አፍርተዋል፡፡ ከáŠĨነዚህም ውáˆĩáŒĨ የጌá‰ŗá‰Ŋንን áŠĨግር á‹Ģጠቡá‰ĩ አቡነ አá‰ĨáˆŗዲáŖ áŠĨንደ ነá‰ĸዩ ኤልá‹Ģáˆĩ ዝናá‰Ĩንና ነፋáˆĩን የከለከሉá‰ĩ አቡነ á‹Ģዕቆá‰ĨáŖ áŠĨáˆŦá‰ĩን áŠĨንደ ማር á‹ĢáŒŖፈጡá‰ĩ አቡነ ገá‰Ĩረ áŠĸየሱáˆĩáŖ áŠĨንደ ቅዱáˆĩ áŠĨáˆĩáŒĸፋኖáˆĩ ጸጋንና ሞገáˆĩን የተሞሉá‰ĩ አቡነ á‹ŗንኤልáŖ áŠĨንደ ንጉáˆĨ ሰሎሞን áŒĨበá‰Ĩን የተሞሉá‰ĩ አቡነ ፊቅáŒĻርና ሌሎá‰Ŋም á‰Ĩዙዎá‰Ŋ ይጠቀáˆŗሉ፡፡ በወቅቱም á‰Ĩዙ የበቁ ቅዱáˆŗን በአáŠĢá‰Ŗá‰ĸው ነበሩ፡፡ በአáŒŊፋቸውና በáŠĨግáˆĢቸው በá‰Ŗሕሩ ላይ የሚሄዱ ነበሩáŖ በጸጋ ክንፍ ተሰáŒĨቷቸውም የሚበሩ ነበሩ፡፡ የአቡነ á‹Ģáˆŗይ ተአምáˆĢá‰ļá‰ģቸው ተነግረው አá‹Ģልቁም፡፡ በወቅቱ የነበሩá‰ĩ ቅዱáˆŗን ልጆá‰ģቸው ‹‹ከቅዱáˆŗን ማን áŠĨንደ አá‰Ŗ á‹Ģáˆŗይ በከá‰Ŗá‹ĩ á‹ĩንጋይ ላይ ተጭኖ በá‰Ŗሕር ላይ የተጓዘ አለና..â€ēâ€ē á‰Ĩለው ይገረሙá‰Ŗቸው ነበር፡፡ á‰Ļá‰ŗቸውም ከዚá‹Ģን ጊዜ ጀምሮ ‹‹ማን áŠĨንደ አá‰Ŗâ€ēâ€ē ተá‰Ŗለ፡፡ ይህም የአቡነ á‹Ģáˆŗይ ገá‹ŗም በሰሜን ጎንደር ዞን ሀገረ áˆĩá‰Ĩከá‰ĩ በደንá‰ĸá‹Ģ ወረá‹ŗ በጎርጎáˆĢ áŒŖና ሐይቅ አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ ይገኛል፡፡
በáŒŖና ደሴá‰ĩ ላይ ከሚገኙá‰ĩ á‰ŗáˆĒáŠĢዊ á‰Ļá‰ŗዎá‰Ŋ ውáˆĩáŒĨ አንዱ ‹‹አá‰ĩማረኝ ዋáˆģâ€ēâ€ē ነው፡፡ ይህም ዋáˆģ á‰ŗáˆĒኩ ከአቡነ á‹Ģáˆŗይ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ á‰ŗáˆĒኩም áŠĨንዲህ ነው፡- አá‰ĩማረኝ ዋáˆģ በáŒŖና ሐይቅ ደሴá‰ļá‰Ŋ መáŠĢከል ከሚገኙ ገá‹ŗማá‰ĩ መáŠĢከል ከማን áŠĨንደ አቡነ á‹Ģáˆŗይ መá‹ĩኀኔዓለም አንá‹ĩነá‰ĩ ገá‹ŗም በáˆĩተ ምáŠĨáˆĢá‰Ĩ አቅáŒŖáŒĢ የáŒŖና ሐይቅን ጉዞ ከገá‰ŗው አንá‹ĩ ተáˆĢáˆĢ áˆĨር የሚገኝ ዋáˆģ ነው፡፡ ይህ ዋáˆģ ለá‰Ĩዙ ዘመናá‰ĩ አንá‹ĩ á‰ŗላቅ አá‰Ŗá‰ĩ የጸሎá‰ĩ በዓá‰ĩ አá‹ĩርገውá‰ĩ ‹‹አá‰ĩማረኝâ€ēâ€ē áŠĨá‹Ģሉ የጸለዩበá‰ĩ á‰Ļá‰ŗ ነው፡፡ አቡነ á‹Ģáˆŗይ ወደ áŒŖና ደሴá‰ĩ ከአቡነ áˆŗሙኤል ዘዋልá‹ĩá‰Ŗ áŠĨና አቡነ á‹Ģፍቅረነ áŠĨግዚáŠĨ ጋር በመሆን በጸሎá‰ĩ ይተጉ áŠĨንደነበር ገá‹ĩላቸው ይናገáˆĢል፡፡ ከáŠĨግዚአá‰Ĩሔር በተሰáŒŖቸውም ጸጋ በáŒŖና ሐይቅ ላይ áŠĨንደ ጀልá‰Ŗ የሚጓዙበá‰ĩ አንá‹ĩ á‰ĩልቅ ጠፍáŒŖፋ á‹ĩንጋይ በáŒŖና ደሴá‰ĩ ላይ ለአገልግሎá‰ĩ በመፋጠን ላይ áŠĨá‹Ģሉ ዛáˆŦ አá‰ĩማረኝ ዋáˆģ ተá‰Ĩሎ ወደሚጠáˆĢው አáŠĢá‰Ŗá‰ĸ ሲደርሱ አንá‹ĩ አá‰Ŗá‰ĩ ዋáˆģው ውáˆĩáŒĨ “አá‰ĩማረኝáŖ አá‰ĩማረኝáŖ አá‰ĩማረኝ” áŠĨá‹Ģሉ ሲጸልዩ á‹Ģገኟቸዋል፡፡ አቡነ á‹Ģáˆŗይም በሰውá‹Ŧው ጸሎá‰ĩ በመገረም ቀርበዋቸው ‹‹አá‰Ŗቴ ምን ዓይነá‰ĩ ጸሎá‰ĩ ነው የሚጸልዩá‰ĩ?â€ēâ€ē አሏቸው፡፡ á‹Ģም አá‰Ŗá‰ĩ ‹‹አá‰Ŗቴ áŠĨንደ áŠĨርáˆĩዎ á‹Ģሉ አá‰Ŗá‰ĩ መáŒĨተው ‹አá‰ĩማረኝâ€ē áŠĨá‹Ģልክ ጸልይ á‰Ĩሎኝ ነውâ€ēâ€ē በማለá‰ĩ መለሱላቸው፡፡ አቡነ á‹Ģáˆŗይም ‹‹áŠĨንዲህ ዓይነá‰ĩ ምክር የሚመክር ጠላá‰ĩ ዲá‹Ģá‰Ĩሎáˆĩ ነው፡፡ ከዛáˆŦ ጀምረው ‹ማረኝâ€ē áŠĨá‹Ģሉ ይጸልዩ በማለá‰ĩ አቡነ ዘበሰማá‹Ģá‰ĩን አሰተምረዋቸው ይሄá‹ŗሉ፡፡ ‹‹አá‰ĩማረኝâ€ēâ€ē áŠĨá‹Ģሉ ይጸልዩ የነበሩá‰ĩ አá‰Ŗá‰ĩም ‹‹ማረኝâ€ēâ€ē áŠĨá‹Ģሉ መጸለá‹Ģቸውን á‰ĸቀáŒĨሉም á‰Ĩዙ መግፋá‰ĩ áˆŗይá‰Ŋሉ ቀሩና ጸሎቱ ይጠፋá‰Ŗቸዋል፡፡ ወደ ሐይቁ ሲመለከቱም አቡነ á‹Ģáˆŗይ á‹ĩንጋዩን áŠĨንደጀልá‰Ŗ ተጠቅመው áŠĨየሄዱ ነው፡፡ ጸሎቱን á‹Ģáˆĩጠኗቸው አቡነ á‹Ģáˆŗይ ርቀው áˆŗይሄዱá‰Ŗቸው á‹Ģ አá‰Ŗá‰ĩ በውኃ ላይ በáŠĨግáˆĢቸው áŠĨየተáˆĢመዱ በመከተል ይደርሱá‰Ŗቸዋል፡፡ ከኋላቸውም ሆነው ‹‹አá‰Ŗá‰ŗá‰Ŋን á‹Ģáˆĩጠኑኝ ጸሎá‰ĩ ጠፋá‰Ĩኝ፤ áŠĨá‰Ŗክዎን áŠĨንደገና á‹Ģáˆĩተምሩኝâ€ēâ€ē አሏቸው፡፡ አቡነ á‹Ģáˆŗይም ሐይቁን በáŠĨግáˆĢቸው áŠĨረገጡ áŠĨáˆĩáŠĒሄዱ á‹ĩረáˆĩ áŒŊá‹ĩቃቸው የተገለጠውን የáŠĨኚህን አá‰Ŗá‰ĩ መá‰Ĩቃá‰ĩ ተመልከተው ‹‹አá‰Ŗቴ áŠĨግዚአá‰Ĩሔር የልá‰Ĩ ነውና የሚመለከተው áŠĨንá‹ŗáˆĩለመዱá‰ĩ ይጸልዩ የáŠĨርáˆĩዎ ይበልáŒŖልâ€ēâ€ē á‰Ĩለዋቸው ሔዱ፡፡ በዚህም ምክንá‹Ģá‰ĩ á‰Ļá‰ŗው ‹‹አá‰ĩማረኝ ዋáˆģâ€ēâ€ē ተá‰Ĩሎ ተጠርቷል፡፡ የአቡነ á‹Ģáˆŗይ ረá‹ĩኤá‰ĩ በረከá‰ŗቸው ይደርá‰ĨንáŖ በጸሎá‰ŗቸው ይማረን፡፡
+ + + + +

ሙáˆŊáˆĢው ቅዱáˆĩ ገá‰Ĩረ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ፡- ሙáˆŊáˆĢው ገá‰Ĩረ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ ወላጅ አá‰Ŗቱ የቍáˆĩáŒĨንáŒĨንá‹Ģው ንጉáˆĨ ቴዎá‹ļáˆĩዮáˆĩና áŠĨናቱ ንግáˆĨá‰ĩ መርáŠŦዛ በáˆĩለá‰ĩ á‹Ģገኙá‰ĩ á‰Ĩቸኛ ልጃቸው áˆĩለሆነ ሃይማኖá‰ĩን áŠĨá‹Ģáˆĩተማሩá‰ĩ በምግá‰Ŗር በáŠĨጅጉ ተንከá‰Ŗክበው አáˆŗá‹ĩገውá‰ŗል፡፡ የአá‰Ŗቱን ንግáˆĨና በመውረáˆĩ ቍáˆĩáŒĨንáŒĨንá‹Ģን áŠĨንዲገዛላቸው በመፈለግ ወላጆቹ ለአáŠĢለ መጠን ሲደርáˆĩ የሮሙን ንጉáˆĨ ሴá‰ĩ ልጅ አጋቡá‰ĩ፡፡ áŠĨርሹ ግን ዓለምን ፍጹም በመናቅ የክርáˆĩá‰ļáˆĩን መáˆĩቀል ለመሸከም የተዘጋጀ ነበርና የሠርጉ ዕለá‰ĩ ሌሊá‰ĩ የáŠĨርሱንም ሆነ የሙáˆŊይቱን á‹ĩንግልና áŠĨንደጠበቀ ከáŒĢጉላ ቤá‰ĩ ወáŒĨá‰ļ በመርከá‰Ĩ ተáˆŗፍሮ ሩቅ ሀገር በመሄá‹ĩ በቤተክርáˆĩቲá‹Ģን ተቀምáŒĻ ከነá‹ŗá‹Ģን ጋር ተደá‰Ŗልቆ በመለመን ለምኖ á‹Ģገኘውንም ለሌሎá‰Ŋ áŠĨየመጸወተ በጾም በጸሎá‰ĩ ተጠምá‹ļ 15 ዓመá‰ĩ ኖረ፡፡
áŠĨመቤá‰ŗá‰Ŋን ተገልáŒģ ለአንá‹ĩ የቤተክርáˆĩቲá‹Ģኑ አገልጋይ የገá‰Ĩረ
2025/02/25 11:35:05
Back to Top
HTML Embed Code: