Telegram Web Link
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 1⃣2⃣


እኔ ነኝ ሩት!
ፍንድቅድቅ ብያለሁ ከዚህ የበለጠ ምን ሊያስደስተኝ ይችላል በማፈቅረው ሰው መፈቅርን የመሰለ ምን ነገር አለ። ከነገረኝ ነገሮች ሁሉ ዮናታን ያፈቅርሻል የሚለው ሙሉ እኔን ተቆጣጥሮኛል።

"ሩት ደስታሽን ላበላሽ ፈልጌ ሳይሆን እባክሽ ጥያቄዬን መልሽልኝ"  ጮክ ብሎ ተናገረ

"ምን አልከኝ ቢኒ" በራሴ አለም ስዋዥቅ ምን እንዳለኝም አልሰማሁትም ነበር።

"ልጅ አለሽ" ከመደንገጤ የተነሳ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ።

"ሩት እንደጓደኛሽ የምታይኝ ከሆነ እውነቱን ንገሪኝ ልጅ አለሽ" ከተቀመጠበት ተነስቶ እጄን ያዘና አንድቀመጥ አደረገኝ ከዛ በተማፅኖ አይን አይኔን ያይ ጀመር "እባክሽ ሩት ላስጨንቅሽ ፈልጌ አይደለም... ግን ዮናታን ፎቶ ሲያሳየኝ ተጠራጠርኩ" የባሰ ድንጋጤ

"ምን? ዮናታንም ያውቃል"

"አዎ እሱ ነው የነገረኝ ስነግርሽ እኮ አልሰማሽኝም መሰለኝ"

"ልጅ ያላትን ሴት ማን ሊፈልጋት ይችላል እና በዚህ ምክንያት እሱን ላጣው ነው" እንባዬ ከየት መጣ ሳልለው ዱብ ዱብ አለ።

"እና የእውነትም ልጅ አለሽ ማለት ነው"

"አዎ አለችኝ"

"የት?.... እንዴት?... ማለቴ..." አይን አይኔን እያየ ቀበጣጠረ

ከውስጤ አንዳች ነገር ፈንቅሎ የወጣ እስከሚመስለኝ በሀይል ተናገርኩ"ዝርዝሩን አይደለም ላንተ ለራሴም ደግሜ አልነግረውም እና ለዮናታንም ቢሆን ንገረው በጣም የምወዳት ልጅ አለችኝ ግን ስለ ልጄ የት? እንዴት? ከማን ወለድሻት? የሚል ጥያቄ የሚጠይቀኝ ከሆነ አጠገቤ እንዳይደርስ ንገረው.... አንተም ብትሆን እንደዛው" በተቀመጠበት ትቼው እያለቀስኩ ወደ ዶርም ሄድኩ። በር ላይ ስደርስ የዶርም አጋሮቼ እንዳያውቁ እንባዬን ጠራርጌ ገባሁ። የለበስኩትን ቱታ በቀሚስ ቀይሬ ነጠላዬን አንስቼ ወደ ቤተክርስቲያን ሄድኩ። ገና የውጨኛው በር ላይ እንደደረስኩ እንባዬን ዘረገፍኩት

"ለምን አምላኬ...? ያለፈው ህመሜን ለምን እንድረሳው አታደርገኝም? ለምን ዛሬ እንደሆነ ሁሉ እንደፊልም አየዋለሁ? ዛሬም ከእንቅልፌ በርግጌ መነሳት ዛሬም ስለልጄ ሲጠይቁኝ ደስተኛ ሆኜ ስለሷ ከማውራት ይልቅ እሷ የተፈጠረችበትን አጋጣሚ መርገም..... አምላኬ እኔ ከአቅሜ በላይ ሆነብኝ... እንዴት ባደርግ ነው ትላንትናን ረስቼ ዛሬን መኖር የምችለው...." ረጅም ሰዓት በእንባ እና በእልህ ነገርኩት።
፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧

ብዙ አመታቶች ቢቆጠሩም ደስተኛ ቤተሰብ ቢኖረኝም ህልሜ የነበረውን ህክምና እየተማርኩ ቢሆንም የህይወቴ ግማሽ ስኬት ትላንቴን ሊያስረሳኝ አልቻለም። ልክ ዛሬ እንደሆነ ሁሉ ያስፈራኛል.... እንዴት ወንድ የተባለ ፍጡር ላፈቅር እንደቻልኩ ለኔ ጥያቄ ነው። ቢያንስ ግን ውስጤ ያለውን የትዝታ አውሬ እስካልቀሰቀሱብኝ ለሰዎች ሰላማዊና የተረጋጋሁ ሰው ነኝ።

፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧

ክላስ ረፍዶብኝ በፍጥነት እየተራመድኩ
"እንኳን ደስ አለሽ ሩት በዛብህ.... እንኳን ደስ አለሽ" እርምጃዬን ገትቼ ወደኋላ ዞርኩ.... የትናዬት

"እባክሽ ክላስ ረፍዶብኛል" ፊቴን አዙሬ ልሄድ ስል

"ዮናታን ወደ አዲስ አበባ እንደተዘዋወረ ሰማሽ"አለችኝ።  ክው ብዬ ቀረሁ

"ምን እያልሽ ነው" ይሄን ሁሉ ቀን ሊያገኘኝም ሆነ ሊያወራኝ ያልፈለገው ልጅ አላት ስለተባለ እንደሆነ ቢገባኝም እሱ የኔ እንደማይሆን ባስብም ከአይኔ እንዲርቅ ግን አልፈልግም

"ሩት ዮኒ እንደሚወድሽ ከኔ በላይ ማንም ሊያውቅ አይችልም። የኔ ይሆናል ብዬ ባንቺም ላይ በሌሎችም ላይ ብዙ ተንኮል ሰርቻለሁ... " ከአይኗ እንባ ኮለል ብሎ ወረደ

"ይቅርታ አድርጊልኝ ሩት ከልቤ ነው ብዙ ነገር አድርጌሻለሁ። አንቺ እንኳን ለይተሽ ያላወቅሽውን ብዙ ነገር.... መምህር ውጤትሽን እንዲያበላሽ አልጋው ላይ ወድቂያለሁ... የዶርምሽን ልጆች ገንዘብ እየከፈልኩ እዚህ መሆንሽን እንድትጠይ አድርጊያለሁ... ይሄን ይሄን ብልሽ ጊዜ አይበቃኝም። እኔን ይቅር ባትይኝም ችግር የለውም ስለሚገባኝ ነው። እነሱን ግን ይቅር በያቸው ሁሉንም በደካማ ጎናቸው ይዣቸው ነው" ወደ ጎን ስታይ ከሷ እኩል ዞር ብዬ አየሁ ሁሉም ተደርድረው ቆመው ያዩኛል... አንደኛዋ መጥታ እግሬ ላይ ወደቀች ሌሎቹም ተከተሏት እነሱን አንስቼ ዞር ስል የትናዬት የለችም።

ኦ የትናዬት አልኩ ለራሴ አንደኛ አመት ላይ ሰርቻለሁ ያልኩት ኮርስ ውጤት ተበላሽቶብኝ ያየሁት መከራ ትዝ አለኝ።

ዶርሜ ውስጥስ ቢሆን አንዳቸው እንኳን ጓደኛ ሊያደርጉኝ ፈቃደኛ አልነበሩም በማደርገው በእያንዳንዱ ነገር ይሳለቁብኝ ነበር። ትንሽ ህይወት የምትባለው ትሻላለች። ትዝታ፣ ቤዛዊት እና ዝናሽ የነሱ ይለይ ነበር። እንደ ድንገት ተስቶኝ ከሎከር ውጪ እቃ ካስቀመጥኩ ወይም ሳልቆልፍ ከረሳሁ ወይ የሆነ ነገር ይጠፋል ወይም ደግሞ ቅባትና ሎሺኔ ግማሽ ደርሶ ነው የማገኘው... ኧረ ብዙ ብዙ ለመተኛት ካልሆነ ወደ ዶርም አልሄድም ነበር። የነሱ ይህን ያክል እኔን መግፋት ቢኒ ላይ እንድጣበቅ አደረገኝ። ቢኒ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነው ጓደኛዬ ወንድሜ አማካሪዬ አስጠኝዬ... ቃል ከሚገልፀው በላይ እወደዋለሁ። ለሴት ጓደኛ እንኳን ለመንገር የሚከብዱ ነገሮችን ነግረዋለሁ አማክረዋለሁ። ከ1 ነገር በስተቀር ስለኔ ሁሉንም ያውቃል ከ1 ውሸት በስተቀር ምንም ዋሽቼው አላውቅም እሱም የትውልድ ሀገሬ አዲስ አበባ እንደሆነ ነው የነገርኩት ሁሉም ቢሆን የሚያውቁት ይህን ነው።  በአጠቃላይ ቢኒ የማላውቀውን የወንድም ፍቅር ያወኩበት ልጅ ነው። ይሄን ሰሞን እሱም ጥፍት ብሏል ምናልባት ተቀይሞኝ ይሆናል ቢሆንም አልፈርድበትም ካለን ቅርበት አንፃር እንዴት አልነገረችኝም ሊል ይችላል።

፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧

"ይቅርታ ሩቴ ከራሴ ጋር ትንሽ ግጭት ውስጥ ነበርኩ ለዛ ነው ካንቺም ከክላስም የጠፋሁት" የእውነት አናዶኝ ነበር

"አንተ ሰው ያስባል ይጨነቃል እንኳን አትልም ግቢውን ለቀህ የት ሄደህ ነው" ትንሽ ካቅማማ በኋላ

"ቤተሰብ ጋ" አለኝ

"የት ድሬዳዋ.... እዛ ነበርክ"

"አዎ"

"ምነው ቤት ሰላም አይደሉም እንዴ"

"አይ ሰላም ናቸው። አሁን ለጠፋሁበት ራት በመጋበዝ እቀጣለሁ" ፈገግ እያለ እጁን ዘረጋልኝ

"ቅጣቱንማ የምወስነው እኔ ነኝ" ተንደርድሬ እቅፉ ውስጥ ገባሁ "የምር ናፍቀኸኝ ነበር ቢኒ ወንድሜ"

"እኔም ናፍቀሽኝ ነበር...
ተማሪማ ከዚህ የበለጠ ሊቀጣ አይችልም ሀሀሀሀ"

፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ፧፧፧፧፧፧፧

ቶሎ ቶሎ ለባብሼ ከዶርም ልወጣ ስል
"እንዲህ አምሮብሽ ወዴት ነው" አለችኝ ቤዛ። ዝም ብያት ልሄድ አልኩና እንደታረቅን ትዝ ሲለኝ "እራት ቀጠሮ አለብኝ ከተባልኩት ሰዓት አርፍጃለሁ" ፊቴን አዙሬ ልወጣ ስል

"ቆይ ቆይ እና እራት ተጋብዘሽ ነው እንደዚህ የለበሽው ነይ ሂዊ እኛ እናልብሳት" ወደኔ መጣችና ቦርሳዬን ተቀብላ ካስቀመጠችው በኋላ ልብስ እያነሰች ማማረጥ ጀመረች።

"ኧረ ቤዚ ረፍዶብኛል ደግሞኮ ፍቅረኛዬን ላገኝ አልሄድ ቢኒ እኮ ነው" ችኩል ብያለሁ ምክንያቱም ቢኒ ሲያስጠብቁት አይወድም

"ቢሆንም ፏ ዝንጥ ብለሽ ነው መሄድ ያለብሽ" በጥቂት ደቂቃ ውስጥ  ሌላ ሰው አስመሰሉኝ ራሴን በመስታወት ውስጥ ሳየው አምሮብኛል።
┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
ቻናላችንንይቀላቀሉ
ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 1⃣3⃣


"ሩቴ ያለፈ ታሪክሽ ምንም ይሁን ምን አንቺን ከማፍቀር ሊያቆመኝ አይችልም። የኔ ቆንጆ የፍቅር ጓደኛዬ ትሆኛለሽ?"

"ዮኒ.." ተርበተበትኩ... ቢኒን ዞር ብዬ ሳየው ፈገግ ብሎ እያዬን ነው። ፈገግታው ውስጥ ሁሉም ነገር ሰላም ነው የሚል መልዕክት ያነበብኩ መሰለኝ••• አበባውን ተቀበልኩ

።።።።።።። ።።።።።። ።።።።።።። ።።።።።።።

ከዮኒ ጋር ህልም የሚመስሉ ሁለት ሳምንታትን አሳለፍን። ሁሉም ነገር በጣም ደስ የሚል ነበር እያንዳንዷን ቀን ደስ በሚል ሁኔታ አሳለፍናት።

ጎንደርን ለቆ ወደ አዲስ አበባ የሚሄድበት ቀን ደረሰ እኔና ቢን ቀድመን ለመሰናበት አገኘነው።
ካፌ ተገናኝተን ሞቅ ያለ ወሬ እያወራን በመሀል ቢኒ
"ይህን ሁሉ ጊዜ አስለፍተሀት አንድ ወርም ሳይቆይ ልትሄድ ነው?" አለው።

"በልፋት እንኳን ከኔ የበለጠ የለፋች አይመስለኝም ሀሀሀሀ ስቀልድ ነው። ይሄን የመሰለ ፍቅር ትቼ መሄዴ ሳያስከፋኝ ቀርቶ መሰለህ በእርግጥ መጀመሪያ ወድጄና ፈቅጄ እንደውም በጣም ፈልጌው ነበር ዝውውር የጠየኩት" ያልሰማሁት አዲስ ነገር ሆነብኝ

"አንተ ጠይቀህ ነው እንዴ የተዘዋወርከው" ግርም ብሎኝ ጠየኩት

"አዎ ለዚህ ዝውውር እስከ ጥግ ለፍቻለሁ አሁን ግን አልፈልገውም ነበር ግን ምንም ማድረግ አልችልም" እዝን ብሎ አንገቱን ደፋ

"ለምን ነበር ዝውውሩን የጠየከው" ቢኒ ጣልቃ ገባ

"በሷ ምክንያት ነዋ" እጄን በእጁ እያጠላለፈ "ያን ሁሉ ነገር ሰማሁ ምንም ብሰማ እንኳን ላንቺ ያለኝ ፍቅር ሊቀንስ አልቻለም ጭራሽ የማላውቀው ስበት ወዳንቺ ይገፋኛል። መቋቋም አቃተኝ ስራዬ ላይ ሳይቀር ተፅዕኖ ፈጠረብኝ እናም መሸሽን መረጥኩ እና ዝውውር ጠየኩ"


"የዚህ አመት ትምህርት ሲያልቅ እመጣ አይደል ከእናቴ ውጪ የሚቀበለኝ ሰው አለ ማለት ነው" መሄዱ ሀዘን እንዳይለቅብኝ መልካም መልካም ነገሮችን ለማውራትና ለማሰብ ሞከርኩ

"እስከዛው አደራ የምለው ላንተ ነው ቢኒያም.... ናፍቆት ናፍቆት እያለች ትምህርት ላይ እንዳትዘናጋ ደግሞ በስልክም እናወራለን" ቢኒ በአንገት ንቅናቄ እሽታውን ገለፀ።

ፍቅሬን ሞቅ ባለ ስንብት ወደ አዲስ አበባ ሸኘነው።

።።።።። ።።።።። ።።።።።  ።።።።።። ።።።።።

እኔ ልሁን እሱ ይሁን ማን እንደተቀየረ ባይገባኝም ከቢኒ ጋር እንደድሯችን ልንሆን አልቻልንም ሳገኘው ሳወራው  የሆነ ክፍተት እንዳለ ይሰማኛል። መጥፎ ስሜቶች አብረውኝ እንዲቆዩ አልፋግም እሱን ለማውራት ወሰንኩ

"ቢን ግን የተፈጠረ ችግር አለ ማለቴ ምንም እንደድሮው ልንሆን አልቻልንም እኮ ያጠፋሁት ጥፋት አለ እንዴ"

"ኖ ሩት ምንም አላጠፋሽም እኔ ነኝ በራሴ ችግር ምክንያት ነው አንቺም ለይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ አላወኩም.... "

"እና ችግሩን ንገራታ መፍትሄው እኮ በሷ እጅ ነው" የቢኒ ጓደኛ ሀብታሙ ከየት መጣ ሳይባል አጠገባችን ተገኝቷል

"እየውልሽ ሩት ቢኒ ባንቺ ምክንያት ሀገ..." ንግግሩን ሳይጨርስ የቢኒ እጅ አፉ ላይ አረፈ እና እንቅ አድርጎ ያዘው ትንሽ ከታገሉ በኋላ ለቀቀው

"ባለፈው እንደነገርኩህ ነው ወይ ንገራት ካለዛ እኔ እነግራታለሁ"

" ቢኒ ምንድነው ማወቅ ያለብኝ ነገር አለ" ቢኒ ግራ ገብቶት አንዴ እሱን አንዴ እኔን ያያል።

"አቦ ዝም ብለህ እኮ ነው የምታካብደው" ሀብታሙ በንዴት እየተወናጨፈ ትቶን ሄደ

"ቢን ንገረኝ ምንድነው ከኔ የምትደብቀው ነገር አለ እንዴ"

"አይ ሩት ለመደበቅ አይደለም እነግርሻለሁ ምን መሰለሽ ግን.... እ...እ....እ ማለቴ እኔ ካንቺ..... ማለቴ ....አንቺን.... "


ይቀጥላል....
┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
          
ቻናላችንንይቀላቀሉ
ከወደዳችሁት ❤️
ምንሼ Reaction አነሰ ሞቅ ሞቅ አርጉት እንጂ ኣያስከፍል😡😡
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘



ክፍል 1⃣4⃣


ከመጀመሪያ ጀምሮ ምን እንደተፈጠረ ልንገራችሁ። ሩትን አፈቅራታለሁ አጠገቤ እያለች የማንም ሳትሆን በየቀኑ አብሪያት ስሆን ስንተቃቀፍ ስናወራ አብረን ስንበላና ስንጠጣ ጭንቅላቴ የሚያስበው ጓደኛዬ እንደሆነች ቢሆንም ይህ ልቤ ግን ሁሉን ነገር ፍቅር ብሎ ይወስደው ነበር። ሁሉም ነገር የገባኝ ሩትን በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ ሳያት ነው። መቋቋም አቃተኝ

••••••°°°°°°••••••°°°°°°•••••°°°°°••••°°°°

ከዮኒ ጋር ካወራን በኋላ እሷ ያለምንም ጥርጥር የሱ እንደምትሆን አመንኩ በዛው ልክ ደግሞ ሩትን ላጣት እንደሆነ እና መቼም የኔ እንደማትሆን ተረዳሁ....  አለ አይደል በቃ ሳስብ የኖርኩት የዮኒ ብልግና የሆነ ቀን አንገሽግሿት እሱን መፈለጓን ለማቆም የምትወስን..... ከዛ የኔ የምትሆንበት ሰፊ እድል.....
በነዛ ሁሉ ጊዜያቶች ለራሴ ስነግረው የነበረው ሩት መቼም ቢሆን ከዛ ባለጌ ዮኒ ጋር ልትሆን እንደማትችል እና የኔ እና የኔ ብቻ እንደምትሆን ነበር። ሁኔታዎች ግን ባላሰብኩት መንገድ ድብልቅልቃቸው ወጣ ሩትን በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ ላያት ሆነ።

ለዶርም ጓደኞቼ ሩትም ሆነ ማንም ቢጠይቃቸው ቤተሰብ ጋ እንደሄድኩ እንዲነግሩ አስጠንቅቄ ከሀብታሙ ጋር አዲስ አበባ አክስቱ ቤት ሄድን። ሀብታሙ ከስር ከመሰረቱ ለሷ ያለኝን ፍቅር ያውቃል እንድቀርባትም ያደፋፈረኝ እሱ ነበር ለዛም ነው ብቻዬን ልሂድ ስለው አይሆንም ብሎኝ አክስቱ ጋር በነፃነት መሆን እንደምንችል አሳምኖኝ አብሮኝ የመጣው
።።።።።። ።።።።።

ለቀናት ጠጣሁ ሰከርኩ በእብደት አለም ውስጥ ዋዠኩ። መርጋጋት የሚባለው ነገር ከኔ በእጥፍ እራቀ። ሁኔታዬ ያሳሰበው ሀብትሽ ከቀናት በኋላ መጠጥ ከሚባል ቦታ እንዳልደርስ በግድ ከለከለኝ

ወደምጠጣበት ቦታ ለመሄድ ወንበር ላይ ቁጭ ብዬ ጫማዬን እያሰርኩ ፊት ለፊቴ መጥቶ ቆመና "ምን እየሆንክ ነው በዚህ ሁኔታህ ሩትን የምታገኛት ይመስልሀል። ቢኒያም እንደዚህ እየሆነ መሆኑን የምታውቅ መሰለህ.... እሷማ የምታውቀው ቢኒ እንደታላቅ ወንድም የምታየው ጓደኛዋ እንደሆነ ነው። ንገረኝ እስኪ በማን ላይ ነው የተናደድከው በሩት ላይ ነው?"

"አይደለም" አልኩት አንገቴን እንደደፋሁ

"በፍቅር ነው?"

"አይደለም እሷን በማፍቀሬማ ደስተኛ ነኝ"

"በራስህ ነው?"

"አዎ ምክንያቱም እስከዛሬ ያመንኩበት ሁሉ ገደል ገባ"

"ይህ እንዳይሆን ማድረግ የምትችለው ነገር ነበር?"

"አላውቅም ምን ላደርግ እችላለሁ መጀመሪያ ነግሪያት ቢሆን የምትወደው ጓደኛዋ ለመሆን አልችልም ነበር። መሀል ላይ ደግሞ ያመንኩት የሱ ነገር ስልችቷት እኔን እንደምታይ ነበር። አሁን ደግሞ ረፍዷል እና በራሴ የትኛውን ነገር አላደረክም ብዬ ልናደድበት?"

"ጥያቄዬን በጥያቄ ሳይሆን በቀጥታ መልስልኝ በራስህ ነው የተናደድከው?"

"አይደለም" አልኩት

"በዮኒ ነው?"

"አይደለም"?

" እና በማን ነው"?

"አላውቅም" አልኩት እውነት ግን በማን ነው የተናደድኩት

"እሺ ለምንድነው እንደዚ እየሆንክ ያለኸው"

"ትቀልዳለህ እንዴ ሩት የኔ ስለማትሆን ነዋ! በናትህ አሁን መጠጣት ነው የምፈልገው" አልኩት ወሬውን ጨርሶ ዞር እንዲልልኝ በማሰብ

"እንደዚህ መሆንህ ሩትን ያንተ እንድትሆን ያደርጋታል?"

"አያደርጋትም" ከፊት ለፊቴ ዞር አለና ከኮመዲኖ ላይ ቁልፍ እነሳ ከዛ ቀጥታ ወደበሩ አመራ እና ቁልፉን እያሳየኝ

"ስለዚህ በማን እንደተናደድክ አታውቅም ግን ምስኪኑን ጨጓራህን በመጠጥ እያነደድከው ነው ቢያንስ ለጨጓራህ በጠዋት እየተነሳሁ እስከማታ በመጠጥ የማነድህ በዚህ ሰው ተናድጄ ነው ብለህ አንድ ምክንያት ንገረው። ሩት ደግሞ ከእጅህ ወጥታለች ስለዚህ ሁኔታዎችን አምነህ ተቀበል ወይም ያንተ የምትሆን ከሆነ ያንን ጊዜ ጠብቅ.... ወደራስህ ተመልሰህ ጠብቀኝ ምግብ ይዤ እመጣለሁ" በሩን ቆልፎብኝ ሄደ

ያለሁበት አንድ ክፍል ቤት ሌላ መውጫ የለውም ከተቀመጥኩበት ተነሳሁና አልጋ ላይ ወጥቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ።

።።።።።። ።።።።።። ።።።።።  ።።።።   ።።።።። ።።።።
ምን ያክል ሰዓት እንደተኛሁ ባላውቅም የቀናት እንቅልፍ ማጣትና ድካሜ በትንሹ ቀለል ብሎኝ ሆዴን ደግሞ ከባድ ረሀብ እየሞረሞረኝ ነበር። ተነሳሁና የሚበላ ነገር ስፈልግ ጠረጴዛ ላይ ተከድኖ የተቀመጠ ምግብ አገኘሁ። እየበላሁ እያለ ሀብትሽ ገባ

"እሺ አፍቃሪው እኔማ ይሄ ልጅ ሳር እንዳይበቅልበት እያልኩ ነበር" አጠገቤ መጥቶ እየተቀመጠ

"ብዙ ተኛሁ እንዴ"

"ለስድስት ሰዓት ያክል ነው የተኛኸው ያውም ምግቡን ካመጣሁልክ ጀምሮ ያለውን ብቻ ቆጥሬው" አለኝ እየሳቀ "አሁን ማውራት ይኖርብናል እየውልክ እዛ ትተን የመጣነው ትምህርት ነው... ነጋችንን ነው.... ሁሉንም ነገር ለጊዜ ስጠው 'ጊዜ የነገሮች ጌታ ነው' ስትል ሰምቼህ አውቃለሁ። ይህን ጉዳይም ለጊዜ ስጠው ፈጣሪ ያንተ ካላት ከማንም ጋር ብትሆን ተመልሳ ያንተ ትሆናለች ያንተ ካላላት ግን የቱንም ያክል ብትለፋ ያንተ አትሆንም። የሆነች ቢመስልህና በፍቅር አመታቶችን ብታሳልፉ እንኳን ፈጣሪ ወዳለላት ትሄዳለች እንጂ ያንተ አትሆንም ስለዚህ ለፈጣሪ እና ለጊዜ ሁሉንም ተወው። እሷን ማፍቀርህን አቁም አልልህም ብልህም ሊሆን የማይችል እንደሆነ ይገባኛል ግን ለሷ ያለህ ፍቅር ዛሬ ማድረግ ያለብህን ነገሮች እንዳታደርግ አድርጎ ነገህን ሊያጨልምብህ አይገባም" ለኔ ምን ያክል እንደተጨነቀልኝ ገባኝ እኔን ብቻ ሳይሆን እሱንም ከትምህርቱ አስተጓጉየዋለሁ

"ትኬት ቆርጠን ነገ በሌሊት እንሄዳለን" አልኩት። በደስታ አቀፈኝ

።።።።። ።።።።። ።።።። ።።።። ።።።። ።።።።።
ከተመለስን በኋላ ልክ እንደመጀመሪያው ለመቀጠል ሞከርኩ ሩትና ዮኒን ለማገናኘት... አደረኩትም አገናኝኋቸው።

ሩት በሄደችበት እንደሴት ጓደኛዋ እኔን ይዛ መሄድ ነው የለመደችው ዮኒ ጋ በምትወስደኝ ጊዜ ግን
የሚሰማኝን ስሜት መግታት አቃተኝ በቦታው እንደምንም ራሴን ተቆጣጥሬ ዶርም ስገባ ግን ሌላ ሰው ሆንኩ። ማንበብ የሚባለውን ነገር እርግፍ አድርጌ ተውኩ በድጋሚ ጠጥቼ መስከር ጀመርኩ

ነጭናጫ እና ሆደ ባሻ ሆንኩ። ይሄ ሁሉ ሲሆን ሀብትሽ አብሮኝ ተሰቃዬ

"ትነግራታለህ ካለዛ እኔ እነግራታለሁ" አለኝ ክላስ ቀጥቼ በተኛሁበት አጠገቤ መጥቶ እየተቀመጠ። ከተኛሁበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁና

"ያምሃል እንዴ ጭራሽ ጓደኝነታችንንም ልጣው" አልኩት

"ሩት ከማውቃቸው ሁሉ እስተዋይ ልጅ ናት ምን ያክል እንደተሰቃይህ ስታውቅ ታዝንልህ ይሆናል ምናልባት የሚፈጠረውን ማን ያውቃል" አለኝ

"እንድታዝንልኝ ሳይሆን እንድታፈቅረኝ ነው የምፈልገው" አልኩት ጮክ ብዬ

"ፍቅር ከሀዘኔታም ይመነጫል ይህንም ያልከኝ አንተ ነህ የኔ ፈላስፋ" አለኝ እየሳቀ

"ሩት እኮ የሌላ ሰው ሆናለች ማንም አብሯት ባይሆን እሺ እድል ይኖረኛል አሁን ግን..." አላስጨረሰኝም

"ዮናታንን ነው.... አሁን እኮ አጠገቧ አይደለም አዲስ አበባ ሄዷል። ከአይን የራቀ ደግሞ ከልብም ሊርቅ ይችላል። አይኗ ስር ያለኸው አንተ ነህ እድልህን ሞክር። የእውነቴን ነው የምልህ ካለዛ እንደዚ እየሆንኩ እቀጥላለሁ ብትል ሁለም ነገር... ከስር መሰረቱ ጀምሮ የተፈጠረውን እኔ እነግራታለሁ ምርጫው ያንተ ነው ከኔ አፍ ወይስ ካንተ ትስማው" ኮስተር ብሎ ነው የተናገረው ሊያደርገውም ይችላል።
┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
  @yefeker_tiksoche
  @yefeker_tiksoche
  @yefeker_tiksoche
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
የፍቅር ጥቅሶች 💖 pinned «😘 ያበደው ፍቅሬ 😘 ክፍል 1⃣4⃣ ከመጀመሪያ ጀምሮ ምን እንደተፈጠረ ልንገራችሁ። ሩትን አፈቅራታለሁ አጠገቤ እያለች የማንም ሳትሆን በየቀኑ አብሪያት ስሆን ስንተቃቀፍ ስናወራ አብረን ስንበላና ስንጠጣ ጭንቅላቴ የሚያስበው ጓደኛዬ እንደሆነች ቢሆንም ይህ ልቤ ግን ሁሉን ነገር ፍቅር ብሎ ይወስደው ነበር። ሁሉም ነገር የገባኝ ሩትን በሌላ ሰው እቅፍ ውስጥ ሳያት ነው። መቋቋም አቃተኝ ••••••°…»
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 1⃣5⃣


እንደማታሸንፍ እያወክ መታገል ትርፉ መጋጋጥ ነው ብዬ አስባለሁ እኔም እንደዛ እየሆንኩ መሰለኝ እና አንዱን መምረጥ ይኖርብኛል ወይ በትግሌ ቀጥዬ ራሴን ማጣት ወይም እንደተመከርኩት ለጊዜ ሰጥቼ ራሴን ማረጋጋት። መረጋጋትን መርጫለሁ

ሀብትሽ እንዳልነገርኳት ሲያውቅ ዶርሙን ቀውጢ አድርጎት ነበር ግን እንደምንም አረጋግቼው ሀሳቤን ነገርኩት

"አቦ ሀብትሽ ደግሞ አታካብዳ በቃ ከልቤ ነው አልኩህ አይደል እመነኝ"

"እስኪ እናቴን በለኝ እንደዛ ካልክ አምንሀለሁ" እናቴን ብዬ ብዙ ጊዜ አልምልም ከማልኩም በጣም ሳመር እንደሆነ ያውቃሉ።

"እናቴን ሀብትሽ! በቃ ጓደኝነታችንን አጥቼው መሰቃዬት አልፈልግም። ትምህርቴንም እንደድሮዬ እሆናለሁ ባጠቃላይ እንደነገርኩህ ነው የእውነት እስተካከላለሁ"

"እሺ ቢኒ እተማመንብሀለሁ"  ወዳጃዊ በሆነ ፈገግታ እያዬኝ

ሰለ ሀብትሽ ሳስብ ይገርመኛል ባንዴ ብዙ ገፀ ባህሪዎችን የተላበሰ ድንቅ ልጅ.... ተጫዋች... ደስ ሲለው ኮስታራ..... በጣም ሰቃይ ተማሪ.....  ደግና ለሰው አዛኝ ደግሞም ቁጡና ሀይለኛ.... የሚገርም ትዕግስት አለው ብላችሁ ሳትጨርሱ ግልፍተኝነቱን ታዩታላችሁ....bእኔ ከሀብትሽ ጋር ስሆን ከብዙ ሰው ጋር የሆንኩ ነው የሚመስለኝ። ሀብትሽ ለወደደው ሟች ነው ልክ እንደታላቅ ወንድም መንገድ ስስት ካዬኝ ምክር ቁጣ ከዛ ካለፈም ስድብ ይኖራል። በሩት ጉዳይ እንደዚ ስሆን እሱ ካጠገቤ ባይኖርልኝ ኖሮ ምን እንደምሆን ሁሉ መገመት አልችልም....
።።።።።።። ።።።

ቀላል ባይሆንም እንዳልኩት ነገሮች እየቀጠሉ ነው። ከሩት ጋር ሰላማዊ ግንኙነታችንን መልሼ ትምህርቴም ላይ ትኩረቴን አድርጊያለሁ

።።።።።። ።።።።። ።።።።።
#ሩት_ነኝ

ቢኒን ካወራሁት በኋላ ምክንያቱን ነግሮኝ እንደድሯችን ቀጥለናል.... ከዮኒም ጋር በየቀኑ እንደዋወላለን። ከዶርም አጋሮቼም ጋር የሚያስቀና እና ሰላማዊ ግንኙነት ኖሮናል።

የትናዬትን ይቅርታ ከጠየቀችኝ በኋላ አይቻት አላውቅም ጓደኛዋን ስጠይቃት አሜሪካ አጎቷ ጋ እንደሄደች ነገረችኝ። የእውነት ከልቤ አግኝቻት ባወራትና ከልቤ ይቅር እንዳልኳት ብነግራት ደስ ይለኝ ነበር ብቻ ባለችበት ሰላም ትሁን።
።።።።። ።።።።። ።።።።

ፋይናል ፈተና ተፈትነን ወደ ቤት ተመልሻለሁ ወደ ናፍቆቶቼ። በመጣሁ ማግስት ከዮኒ ጋር ተገናኘን በጣም ተነፋፍቀን ነበር ሰው ጉድ እስከሚል ጥምጥም ብዬበት ወገቤን ይዞ አሽከረከረኝ።

"የኔ ናፍቆት እንኳን መጣሽልኝ ደና ነሽ አይደል" ከተቀመጥን በኋላ እጄን ይዞ አይን አይኔን እያየ

"ደና ነኝ ፍቅር አንተስ"

"ካንቺ ናፍቆት በስተቀር እንደምታይኝ በጣም ደህና ነኝ" ከብዙ የናፍቆት ወሬዎች በኋላ

"ቤተሰቦቼን ላስተዋውቅህ እፈልጋለሁ ምን ይመስልሀል" አልኩት

"በጣም ደስ ይለኛል"


ለእናቴ ስነግራት የተደሰተችው ደስታ እኔ እንኳን የሷን ያክል የተደሰትኩ አልመሰለኝም። በተደጋጋሚ "ተመስገን ፈጣሪ ፀሎቴን ሰማህ" ትላለች። ያለፈውን ላናወራ ቃል ስለተገባባን እንጂ በምን ምክንያት እንደዚ እንደምትሆን ገብቶኛል ። በወንድ ምክንያት ያንን ህይወት አሳልፌ ወንድ አጠገቤ የማስደርስ አይመስላትም ነበር ለነገሩ እንኳን እሷ እኔም አይመስለኝም ነበር።

"እና መች ይዤው ልምጣ እማ"

"እሁድ ይዘሽው ነይ" እንዴት ደስ እንዳለኝ

።።።።። ።።።።። ።።።።። ።።።።። ።።።።። ።።።።

"ግባ እንኳን ደህና መጣህ" እናቴን ጎንበስ ብሎ ጉልበቷን ሊስም ሲል ቀና አደረገችውና

"አይገባም ልጄ" ብላ ሰላም ካለችው በኋላ "ወይንሸት እባላለሁ የልጄን ልብ የወሰደ ጀግና ማን ነው?" አለችው በፈገግታ እያየችው

"ዮናታን እባላለሁ" አለ ከአንገቱ ቀርቀር ብሎ

"ይቺ ደግሞ ልጄ ናት ምናሴ ትባላለች እኔ እንኳን እንቁ ነው የምላት የኔ እንቁ ሂጂ ሰላም በይው" አልኳት።

"ዮኒ እሷን ዞር ብሎ ካዬ በኋላ ፍዝዝ ብሎ የነቃው ሄዳ ሰላም ስትለው ነው" ከትውውቁ በኋላ ግብዣና ጨዋታው ቀጠለ።

።።።።።

ከቤት ወጥተን እየሸኘሁት እያለ "ልጅሽ ግን" አለኝ

"ልጄ ሁሉ ነገሬ ነች ዮኒ..... ልጄ ነገዬ.... ማያዬ.... የኔ ተስፋ ናት። በዛ ላይ እኮ እንዴት ጎበዝ ተማሪ እንደሆነች ብታያት" ስለሷ ብዙ ካወራሁለት በኋላ ቀና ብዬ ሳየው ሀሳቡ ከኔ ጋር አይደለም

"እኔ ብቻዬን ስለፈልፍ የት ጠለኸኝ ሄድክ" ድንግጥ አለና

"የትም አለሁ ልጅሽ የማውቃትን አንዲት ልጅ አስታወሰችኝ። ብቻ ተይው የማይገናኝ ነገር ነው" አለኝና ትክዝ አለ

"ምንድነው እሱ"

"አይ ምንም"

ይቀጥላል....
┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋

ቻናላችንንይቀላቀሉ
ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘

ክፍል 1⃣6⃣

"የትም አለሁ ልጅሽ የማውቃትን አንዲት ልጅ አስታወሰችኝ። ብቻ ተይው የማይገናኝ ነገር ነው" አለኝና ትክዝ አለ

"ምንድነው እሱ"

"አይ ምንም" ሸኝቸው ከተመለስኩ በኋላ ለደቂቃዎች ሁኔታውን አሰብኩትና ለምን እንቁን ሲያያት እንደዚህ ፈዘዘ ለሚለው ጥያቄ መልስ ያገኘሁ መሰለኝ ስለሷ ምንም ስላልነገርኩትና ቢጠይቀኝም እንደማልነግረው ስለሚያውቅ ነው።

ከዚህ በኋላ ያሉት ጥቂት አመታቶች ተመሳሳይ ነበሩ። ለእረፍት መምጣት፣ ከዮኒ ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ ጊቢ መሄድ፣ ከቢኒ እና ከሌሎች ጓደኞቼ ጋር የነበረንን ግንኙነት መቀጠል፣ መማር፣ ማንበብ፣ የተለያዩ ሆስፒታሎች አፓረንት መውጣት.... ባጠቃላይ ብዙም አዲስ ነገር የሌለበት ተመሳሳይ ጡዘት ነበር።

የመጨረሻ አመት ላይ ውጥረቱ ከመቸውም ጊዜ የበለጠ ነበር። ዩንቨርስቲያችን ከፍተኛ ውጤት ያመጡ አስር ልጆችን ስኮላርሽፕ እንደሚሰጥ ያወቅንበት ጊዜ ነበር። ጥቂት ቢ እና ኤ ማይነስ ውጤቶች ቢኖሩኝም እድሉን አገኛለሁ ብዬ እየተፍጨረጨርኩ ነበር። ቢኒ እና ሀብትሽ እንኳን በእርግጠኝነት ከአስሮቹ መሀል ይሆናሉ። ሀብታሙ እስካሁን ያለው ውጤቱ ኤ እና ኤ ፕላስ እንደሆነ ነው የምናውቀው። ቢኒ ደግሞ ሁለት ቢ ሌላው ኤ በአጠቃላይ የግቢያችን ሰቃዮች የእስኮላሩም ባለ እድሎች ይሆናሉ ብዬ ከምጠብቃቸው መሀል ናቸው ናቸው።

ውጥረቱ እንዳለ ቀጥሎ ፋይናል ፈተና ተፈተንን እና እፎይ አልን። ምርቃታችን አንድ ሳምንት ሲቀረው ሂዊ እና ቤዛ ወጣ ብለን ፈታ እንበል ብለው ሲጨቀጭቁኝ እሺ አልኳቸው። ሌላ ፕሮግራም ያለብን ይመስል ከግራ ቀኝ እየተቀባበሉ አስዋቡኝ።

"ለቢኒ ልደውልለት እንዴ ከተመቸው አብሮን ቢሆን ደስ ይለኛል" ስላቸው እርስ በርሳቸው ተያዩና ቤዛ

"ትችያለሽ" አለችኝ። እሺ ብዬ ስልኬን አንስቼ ደወልኩለት ሁለቴ እንደጠራ አነሳውና

"ሀሎ ዶክተር ሩት እንደምን አሉ" አለኝ ድምፁን እንደ ሽማግሌ እያደረገ ሳቅሁና በምላሹ

"አለን እግዚአብሔር ይመስገን እርሶስ እንዴት ኖት ዶክተር ቢኒያም" አልኩት።

"አለን ክብሩ ይስፋ ይገርሞታል አሁን ከባድ ቀዶ ጥገና አለብኝ እና ወደዛ ልገባ" አቋረጥኩትና

"እንደዛ ከሆነማ አብረን ቀደን እንጠግነዋለን ሀ ሀ ሀ ሀ የት ነህ ከነ ቤዚ ጋር ልንወጣ ነው ከቻልክ ተቀላቀለን" አልኩት።

"ደስ ይለኛል እንደውም ብቻዬን ደብሮኝ ነበር"

"ሀብትሽስ" አልኩት

"ሀብትሽማ አክስቱ ከአዲስ አበባ መጥታ ረስቶኛል ያው አትፍረጅበት የመዓረግ ተመራቂ ነገር "በል አሁን ወሬውን ተውና ውጣ እኛ ወተናል"  ስልኩን ዘጋሁና ቦርሳዬን አንስቼ ከዶርም ወጣን።

።።።። ።።።። ።።።። ።።።። ።።።  ።።።

በኮንትራት ራቅ ወዳለ ቦታ ሄድንና አንድ ውስጡም ውጪውም ውብ ወደሆነ ሆቴል ገባን።

"እናንተ ፈታ እንበል ብላችሁ ሆቴል ኧረ ፌር አይደለም" አለ ቢኒ ወደነሂዊ እያየ እኔም ሀሳቡን ተጋርቼው በጥያቄ መልክ አይን አይናቸውን እያየሁ እያለ ሂዊ

"ሩት ሰርፕራይዝ አለሽ" አለችና ሳታስፈቅደኝ አይኔን በጨርቅ አሰረችው። እጄን ይዛኝ ትንሽ ከተራመድን በኋላ ወደ ፎቅ ደረጃ ወጣንና በድጋሚ ትንሽ ከተራመድን በኋላ ቆምን

"አይንሽን መግለጥ አይቻልም" አለችኝ ቤዚ

"እኔንም ግራ እያጋባችሁኝ ነው ምንድነው ነገሩ" ቢኒ ተናገረ። የበር መከፈት ድምፅ የሰማሁ መሰለኝ ትንሽ ከተራመድን በኋላ ተዘጋ።

"ሰፕራይዝ" ብለው ባንዴ ጮሁና አይኔ ላይ ያለውን ጨርቅ ሲያነሱት እኔ ደግሞ በተራዬ ጮህሁ። አንዴ ወደግራ አንዴ ወደ ቀኝ አንዴ ደግሞ ፊት ለፊቴ ወደተንበረከከው ዮኒ እያየሁ ነው። ከመደንገጤ የተነሳ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገብቶኛል። ቤዚን ሳያት ጭንቅላቷን በአዎንታ ነቀነቀችልኝ ሂዊም እንደዛው ቢኒን ዞር ብዬ ሳየው ድንዝዝ ብሎ ቆሟል።

"ታገቢኛለሽ የኔ ቆኝጆ" ብሎ ለሁለተኛ ጊዜ ደገመልኝ

"አዎ የኔ ፍቅር አዎ አገባሀለሁ" የደስታ እንባ ከአይኔ ኮለል ብሎ ወረደ። ግራ እጄን ዘረጋሁለትና የቀለበት ጣቴ ላይ የሚያምር ቀለበት አድርጎልኝ ሳም ካረገው በኋላ ጥምጥም ብሎ አቀፈኝ.... እኔም ልጥፍ አልኩበት... ወዲያው በሩ ጓ ብሎ ሲዘጋ ሰማሁ ከእቅፉ ወጥቼ ዞር ስል ቢኒ የለም። ምን ሆኖ ነው ግራ ተጋባሁ


ይቀጥላል....
┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋

ቻናላችንንይቀላቀሉ

ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 1⃣7⃣


ወዲያው በሩ ጓ ብሎ ሲዘጋ ሰማሁ ከእቅፉ ወጥቼ ዞር ስል ቢኒ የለም። ምን ሆኖ ነው ግራ ተጋባሁ...
የቢኒን ነገር በይደር ያዝኩትና ወደ ደስታችን ተመለስኩ። እነ ሂዊ ትንሽ አብረውን ከቆዩ በኋላ ቻው ብለውን ሄዱ እነሱን አስወጥቼ በሩን ዘግቼ ስዞር ዮኒ አጠገቤ መጥቶ ቆሟል። ጊዜ እንኳን ሳይሰጠኝ ከንፈሬ ላይ ተጣበቀ።

ሁሉም ነገር በስሜት ጡዘት ውስጥ እየሆነ ነበር ማንም መመሪያ ሳይሰጥ እያንዳንዱን ምዕራፍ ገለጥነው ከምዕራፎቹ መሀል አንደኛው ላይ ግን ነገር ተበላሸ። ከምትወደው ዮናታን ጋር በስሜት አለም የምትቃትተው ሩት ጠፋችና የአስራ ሶስት አመቷ ሩት ተከሰተች።

"እባክህን ተወኝ.... ሳግ... እንባ... እባክህን አትንካኝ.... ብዙ ትንቅንቅ..... ለእናቴ መድኋኒት ልገዛ ነው.....እናቴን አሟታል..... እባክህን ተወኝ ልሂድ....." ከላዬ ላይ ምንጭቅ ብሎ ተነሳና እየወዘወዘኝ ሩት ሩት ብሎ መጣራት ጀመረ ድምፁ ከሩቅ ቢሰማኝም ካለሁበት የህልም አለም ግን መንቃት አልቻልኩም

"እባክህ ተወኝ" ግራ ሲገባው መሰለኝ በተኛሁበት ውሃ አምጥቶ ፊቴ ላይ አርከፈከፈብኝ የውሃው ቅዝቃዜ ካለሁበት መጥፎ አለም መንጭቆ አወጣኝና ተነስቼ ቁጭ አልኩ። የሆነው ሁሉ ስለገባኝ አይኑን ማየት ፈራሁ እንገቴን ባቀረቀርኩበት ከጀርባዬ መጣና ጥምጥም ብሎ አቀፈኝና

"የኔ ፍቅር" አለኝ ሀዘኔታ በተሞላበት ቅላፄ

"ወዬ ውዴ ይቅርታ እሺ በጣም አዝናለሁ እንደዚ የምሆን አልመሰለኝም ነበር" ምላሴ ተሳሰረ ጫፉን እንኳን ስለማያውቀው እንዲያውቅም ስለማልፈልገው ታሪክ ምን ብዬ አስረዳዋለሁ።

"ተደፍረሽ ነበር አይደል" አለኝ። ረጅም ደቂቃ መልስ ሳልመልስለት ዝምም አልኩት

"ይገባኛል ሩት ማውራት የማትፈልጊው ርዕስና ቁስልሽ እንደሆነ ግን እኔ ባልሽ ልሆን ነው ህመምሽም መካፈል ሀዘንሽን መጋራት እፈልጋለሁ። ሚስቴ ብቻዋን ስትሰቃይ ማየት የበለጠ ነው የሚያሳምመኝ" ንግግሩ አንጄቴን በላው ግን ምን ብዬ ልንገረው ምክንያቱም እኔም እናቴም የነገርነው አዲስ አበባ ተወልጄ እንዳደኩ ነው። ለእናቴ ደግሞ ቃል ገብቼላታለሁ
ማንም ቢጠይቀኝ የአዲስ አበባ ልጅ እንደሆንኩ እንድናገር ነግራኛለች። ምክንያቷ የትውልድ መንደሬን ስም በተናገርኩ ቀጥር ያንን መጥፎ አጋጣሚ በየጊዜ እንዳላስበው ብላ ነው። ይህም የሆነው ሰለዛ ሀገር ከሷ ጋር እንኳን ባወራንበት አጋጣሚ ከሷ ዞር ብዬ ሳለቅስና ሁኔታዎቼ ሲቀያየሩ ስላየች ነበር። እሷም ስለዛ ላታወራ እኔም ማንም ቢጠይቀኝ የተወለድኩት አዲስ አበባ እንደሆነ ልናገር ቃል ያስገባችኝ።

ከጊዜ በኋላ ሁኔታውን ለመድኩትና እውነትም አዲስ አበባ የተወለድኩ እስከሚመስለኝ የምናገረው ውሸት እውነት ሆነልኝ።


"አዎ ልክ ነህ ተደፍሪያለሁ ግን እንዴት? የት? ምናምን ብለህ አትጠይቀኝ ምክንያቱም ድጋሚ በዝርዝር ካሰብኩት እታመምብሀለሁ። ብቻ እመነኝ ከዚህ ሁኔታ ውስጥ እወጣለሁ እንደዚ የምሆን ስላልመሰለኝ ነው እኮ ችላ ብዬው የነበረው"

"ይገባኛል አትጨነቂ የስነ ልቦና አማካሪ ትፈልጊያለሽ"

"አዎ ግን አንተ አትቸገር በራሴ አደርገዋለሁ የማውቃቸው ጎበዝ ሳይካትሪስቶች አሉ" ደረቱ ላይ ልጥፍ ብዬ እቅፍ አድርጎኝ ተኛን ወዲያው ወደ እንቅልፍ አለም ተሸጋገርኩ።

።።።። ።።።።። ።።።።። ።።።።

ቢኒን ለማግኘት እንደሞከርኩ ሳላገኘው የምርቃታችን ቀን ደረሰ። ፕሮግራሙ ደስ በሚል ሁኔታ እየሄደ ተማሪዎች የሚሸለሙበት ሰዓት ደረሰና ልክ እንደገመትነው እንደ ዩንቨርስቲውም እንደ ዲፓርትመንታችንም ሀብታሙ አንደኛ ተብሎ ተሸለመ ሁለተኛ አያንቱ የምትባል የጅማ ልጅ ሶስተኛ ደግሞ የኔ ጀግና ጓደኛ ቢኒ እኔ የተሸለምኩ እስከሚመስለኝ ደስታዬ ወሰን አልነበረውም። ከአዳራሹ ከወጣን በኋላ ቢኒን እንደምንም ፈልጌ አገኘሁትና

"እንኳን ደስ ያለህ" ብዬ አቀፍኩት

"አንቺም እንኳን ደስ ያለሽ ባትሸለሚም በትንሽ ውጤት ነው የበለጥንሽ" አለኝ። ቤተሰቦቹ እየጠበቁት ስለነበር ብዙም ለማውራት አልተመቸንም እኔም ወደ ዮኒና ልታስመርቀኝ ወደመጣችው እናቴ ተመለስኩ።

ዮኒ ወደጆሮዬ ጠጋ ብሎ
"ነይ ከዚህ ግርግር ውስጥ እንውጣ ማዘርም ደክሟቸዋል ትንሽ ይረፉ" አለኝ። እሺ ብዬ ተያይዘን ወጣን።
።።።።። ።።።።። ።።።። ።።።።

ዮኒና እናቴ ቀድመውኝ ወደ አዲስ አበባ ሄደዋል ከጥቂት ቀናት ቆይታ በኋላ እኔም ለመሄድ ዝግጅቴን ጨረስኩ። ከቢኒ ጋርም ምቹ ጊዜ አግኝተን ሳናወራ ልንለያይ ነው።

በትልቅ ሻንጣ ልብሶቼን በሌላ አነስተኛ ሻንጣ ደግሞ መፅሀፍና አንዳንድ ዶክመንቶቼን አድርጌ ዶርሜን ለቅቄ ወጣሁ። ቢኒ ታች እየጠበቀኝ ነበር ሁለት ሻንጣ ሲያይ

" በሻንጣሽ የሆነ ሰው ከተሽ እንዳትሄጂ በደንብ ተፈትሸሻል" ሲል ቀለደብኝ

"ባክህ መፅሀፎቼን አልተውም ብዬ ነው በዚህ ያዝኳቸው" ብዬ አነስተኛውን ሻንጣ አመለከትኩት

"እሱ ነው የሚከብደው በይኛ" ብሎ ትንሹን ሻንጣ ተቀበለኝና ወደ መውጫው መሄድ ጀመርን። ወዲያው ሂዊና ቤዛ እየሮጡ ደረሱብኝና እኔና እነሱ ከፊት ቢኒና ሀብታሙ ደግሞ ከኋላ ሆነን ከግቢ ወጣን።

።።።። ።።።።። ።።።።። ።።።።። ።።።።።

አዲስ አበባ ስደርስ ሌላ ያላሰብኩት ሰርፕራይዝ ጠበቀኝ ዮኒ እኔና እሱ የምንኖርበትን ቤት ተከራይቶ እቃዎቹን አሟልቶ ጠበቀኝ። በዚህ ፍጥነት ይሆናል ብዬ አላሰብኩም....


ይቀጥላል....



ቻናላችንንይቀላቀሉ
┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 1⃣8⃣

አዲስ አበባ ስደርስ ሌላ ያላሰብኩት ሰርፕራይዝ ጠበቀኝ ዮኒ እኔና እሱ የምንኖርበትን ቤት ተከራይቶ እቃዎቹን አሟልቶ ጠበቀኝ። በዚህ ፍጥነት ይሆናል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ደስ የሚለው የእናቴም ሙሉ ፈቃድ ነበረበት

"ዝም ብለሽ መግባት የለም ከዛ በፊት አነስተኛ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ መፈራረም አለባችሁ" አለችኝ። ሰርግ የሚባለውን ግርግር እሱም እኔም አልፈለግነውም ሰርግ ሲባል የሙሽሪት ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ምናምን የሚባል ነገር ይመጣል ለአስራ ምናምን አመት የተለየናቸውን ዘመዶቻችንን ጠርተን በራሳችን ላይ የወሬ ጦስ ማምጣት አልፈለግንም

የጋብቻ ውል ተፈራረምን... እናቴ ደግሞ አነስተኛ ፕሮግራም አዘጋጀች.... ጎረቤት ፣ የሱ እና ጥቂት የኔ ጓደኞች ባሉበት በይፋ ተጋባን እና ወደ ሙሽራዬ ቤት አመራሁ።  ፕሮግራሜ ላይ እንዲገኝ ለቢኒ በተደጋጋሚ ብደውልለትም ስልኩ አይሰራም። ለሀብታሙ ደውዬ ምን እንደሆነ ስጠይቀው

"ሰላም ነው ለትንሽ ጊዜ ማንንም ማውራት ስላልፈለገ ነው። ራሱ ይደውልልሻል አትጨነቂ" አለኝ።

።።።።። ።።።።። ።።።።። ።።።።

በረንዳ ላይ ሳር ጎዝጉዤ እናቴ ከአጠገቤ ተቀምጣ ቡና እያፈላሁ ነው። አቦሉን ቀድቼ ከሰጠኋት በኋላ በተደጋጋሚ ተነጋግረንበት መግባባት ያቃተንን ጉዳይ አነሳሁት።

"እማዬ እሱም የሚፈልገው አብረን እንድንኖር ነው። ቤቱም ቢሆን ሙሉ ግቢ ስለተከራዬን በቂ ነው። በዛ ላይ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ተለይቼ መኖር አልፈልግም። በናትሽ እማ እሺ በይኝ እና አብረን እንኑር"

"የኔ ሚጣ... አሁን ትልቅ ልጅ ሆነሽልኛል፤ ተምረሽ ተመርቀሽ ባለስራ ልትሆኚ ነው ፤ አግብተሽም ወግ ማረግሽን አሳይተሽኛል። ሚጣዬ እኔ የምፈልገው ያንቺን ደስታ ነው። ፀሎቴም ምኞቴም ሳቅሽ ነው። እብሬሽ አንድ ቤት አልኑር እንጂ ሁሌም አጠገብሽ ነኝ። አንቺም ብትሆኚ ሁለት ቤት ይኖርሻል ምናሴም ብትሆን ሁለት ቤት ሲኖራት ደስ ይላታል እንጂ አይከፋትም። ቤቴ ቤትሽ ቤትሽ ደግሞ ቤቴ ነው። እንቁሽን በፈለግሽ ሰዓት መውሰድ ሙሉ መብትሽ ነው እሷም በፈለገች ሰዓት አንቺ ጋር መሆን ትችላለች ያው የአያትነት መብቴ እንደተጠበቀ ሆኖ" አለችና ወደኔ ሳብ ብላ ጉንጬን ሳም አደረግችኝ

"ውይ እማ ደግሞ ዝም ብለሽ እኮ ነው...." ወሬየን ሳልጨርስ ምናሴ እየሮጠች መጣችና

"ማሚ ማሚ ሰንበት ትምህርት ቤት እኮ የእየሉጣ ተውኔት ተሰጠኝ "  ጥምጥም አለችብኝ።

"ጎበዝ የኔ እንቁ በደንብ እንደምትተውኝ እተማመንብሻለሁ ዲያሎግሽን በደንብ አጥኚ እሺ። በይ ነጠላሽን አስቀምጪና ምግብ ብዪ" አስነስቻት ከበረንዳ ወደ ውስጥ ይዣት ገባሁ።

"እና ልጅሽ ማነው?" አልኳት እንጀራውን ሰሀኗ ላይ እያደረኩላት

"ኪ ኪ ኪ ኪ እንዴ ማሚ እኔ ልጅ አለኝ እንዴ ኪ ኪ" ሳቋ እኔንም አሳቀኝ። አብረን ስቀን ከጨረስን በኋላ

"አንቺ እየሉጣን ከሆንሽ ቂርቆስን ሆኖ የሚተውነው እኮ ያንቺ ልጅ ነው የሚባለው"

"እእእእ እሱማ አቤል ነው። እንዴ ግን አቤል የኔ ልጅ ሊሆን...."

"በይ አሁን ምግብሽን ብይ እየተበላ አይወራም ካንቺ ጋር ሳወራ ቡናዬን ረሳሁት" ትቻት ወደ በረንዳ ስወጣ እማዬ የኔ መቀመጫ ላይ ተሰይማ ጀበና የተጣደበትን ማንደጃ ታራግባለች።

"አንቺ እሷን ካገኘሽ አይደለም የጣድሽውን ቡና እኔንም ትረሽኛለሽ.... ነይ ቁጭ በይ ሁለተኛው ፈልቷል" እንፋሎቱ ቦለል የሚለውን ጀበና ከማንደጃው ላይ አነሳችና እንዲሰክን ቁጭ አደረገችው።

።።።። ።።።። ።።።። ።።።።

የቀሩኝን እቃዎች ወደ አዲሱ ቤቴ ወሰድኩ። መፅሀፍ ያደረኩበት ሻንጣ ከግቢ ካመጣሁት በኋላ አልተከፈተም ነበር። መፅሀፎቼን ከሻንጣው አውጥቼ ለመደርደር ስከፍተው በቀይ ፖስታ የታሸገ ደብዳቤ  አየሁ። አነሳሁትና አገላብጨ አየሁት 'የማን ነው' አልኩ ምክንያቱም የኔ አይደለም.... ከግቢ ስወጣ እቃዎቼን አንድ በአንድ ያስተካከልኩት እኔ ነበርኩ ግን ይሄን አላየሁትም። ለማንኛውም አልኩና ከፈትኩት።

"ሰላም ሩት እንዴት ነሽ አልልሽም እስከዛሬ ከአጠገቤ ስለነበርሽ እንዴት እንደሆንሽ አውቃለሁና.... የምልሽ ከዚህ በኋላ እንዴት ትሆኛለሽ ነው። ይከፋሽ ይሆን ወይስ ደስ ይልሽ.... " ገና እንደጀመርኩት የቢኒ ፅሁፍ መሆኑን አወቅሁ። ፈገግ እልኩ ሳላስበው ድምፅ አውጥቼ "ቢኒ ለኔ ደብዳቤ" አልኩና ደብዳቤውን ወደ ማንበብ ተመለስኩ።

"ሩቴ እኔ ላንቺ ምርጥ ጓደኛሽ እንደሆንኩ ከዛም አልፎ ወንድምሽ እንደሆንኩ ነግረሽኝ ታውቂያለሽ። እኔ ደግሞ አንቺ ለኔ ምን እንደሆንሽ ልንገርሽ... አንቺ ማለት ሩቴ ጓደኛዬ አፅናኝዬ መካሪዬ ከመሆንሽ ባሻገር ልቤን በመጀመሪያ እይታ የሰረቅሽ ሌባዬ ነሽ። ሩትዬ ይህን ስልሽ ምን ሊሰማሽ እንደሚችል አላውቅም። ነግሬሽ እስከመጨረሻ አጣሻለሁ በሚል ፍራቻ ለአመታት ፍቅሬን አምቄ ይዤው ቆይቻለሁ። አሁን ግን ልሄድ ነው ካንቺ ከፍቅሬ ከቤተሰቤ እና ከሀገሬ ርቄ ልሄድ ነው። የልቤን ሳልነግርሽ መሄድን አልፈለኩምና በአካል ደፍሬ መግለፅ ያቃተኝን ፍቅር በደብዳቤ ፅፌልሻለሁ።

ሩቴ የኔ ስስት አፈቅርሻለሁ ከሚለው ቃል ውጪ ፍቅርን ሊገልፅ የሚችል ቃል አጣሁ ዝርዝሩን ሁሉ በአካል ሳገኝሽ እነግርሻለሁ ያ የሚሆነው ግን አንቺ እኔን ማግኘት ከፈለግሽ ነው። የድሮ ስልኬን አልጠቀመውም በዚህ ደውይ 0910 35 6... አፈቅርሻለሁ ሩቴ"

ስልክ ቁጥሩ ላይ ረጅም ሰዓት አፈጠጥኩበት

"ምንድነው እንደዚህ የመሰጠሽ እየጠራሁሽ እኮ አትሰሚም"

"ምንም የኔ ፍቅር ለምን ፈልገኸኝ ነው" የያዝኩትን ወረቀት አየተደናበርኩ ለመደበቅ ሞከርኩ

"ምንድነው የያዝሽው የምን ደብዳቤ ነው አምጪው እስኪ ልየው".....

ይቀጥላል....

┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
ቻናላችንንይቀላቀሉ

ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 1⃣9⃣

"ምንም የኔ ፍቅር ለምን ፈልገኸኝ ነው" የያዝኩትን ወረቀት አየተደናበርኩ ለመደበቅ ሞከርኩ

"ምንድነው የያዝሽው የምን ደብዳቤ ነው አምጪው እስኪ ልየው"

"ምንም አይደለም ውዴ ዝም ብሎ ነገር ነው" ድርቅ ብዬ ለማሳመን ሞከርኩ

"እሺ በቃ የቀረውን በኋላ ትጨርሻለሽ ሳሎን ነይ" እሺ ብየው ሲሄድልኝ ደብዳቤውን ዳጎስ ካለው መፅሀፌ ውስጥ ከተትኩትና ተከተልኩት

።።።። ።።።። ።።።   ።።።።። ።።።።።

የዛን እለት ነው የደወልኩለት አዲስ አበባ እንደሆነ ሲነግረኝ ዛሬውኑ እንገናኝ አልኩት ደስ እያለው እሺ አለኝ። ከአንድ ብዙም ሰው ከማይበዛበት መናፈሻ ተቀጣጠርን ቀድሞኝ ነበር የደረሰው እኔን ሲያይ ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆመ ሮጬ ተጠመጠምኩበት

"ናፍቄህ ነበር "

"እኔም ናፍቄሽ ነበር በጣም" ሳሩ ላይ ጎን ለጎን ተቀመጥን

"ብናፍቅህማ እንደዚህ አትጨክንብኝም ነበር የምር ግን ጨካኝ ነህ እሺ" አልኩት ከልቤ እንዳልሆነ ያውቃል

"እሱንማ ብዙ ጊዜ ትነግሪኛለሽ ይልቅ አዲስ ስም ፈልጊልኝ አሁን ከፈለግሽ አፍቃሪ ነህ ማለት ትችያለሽ" ለደቂቃዎች ዝምም አልኩና ነገሮችን በውስጤ ማመላለስ ጀመርኩ ከዛ

"እንዴት ግን ቢኒ እስኪ የማላውቀውን ንገረኝ" ተስተካክሎ ተቀመጠና

"የመጀመሪያ ክላሳችን ቀን ነው ከሀብትሽ ጋር ቀድመን ክላስ ቁጭ ብለናል ብዙም ሳንቆይ ረጅም ቀሚስ የለበሰች ቁመቷ ረጅም ቆንጆ ልጅ ወደ ክፍላችን ገባች። በእያንዳንዱ እርምጃዋ የኔን ልብ የረገጠችው ይመስል ልቤን በእጄ ይዤ የመጀመሪያውን የፍቅር ህመም ታመምኩላት። ልክ ገብታ ወንበር አየት አድርጋ ስትቀመጥ እጄም ከልቤ ላይ ተነሳ። ሀብትሽ እኔንም አንቺንም እያየ በሁኔታዬ ግራ ተጋብቶ

'ቢኒያም ችግር አለ ምን ሆነህ ነው?' አለኝ
ለሱ መልስ ከመመለሴ በፊት ሌሎች ተማሪዎች ግርርር ብለው ገቡ ብዙም ሳይቆይ ዮናታን ገባ። ከክላስ ከወጣን በኋላ የሀብትሽ ምን ሆነህ ነው ጭቅጭቅ አላስቀምጥ ሲለኝ 'ተወኝ ባክህ እኔም ምን እንደሆንኩ አላውቀውም። ልጅቷ ግን...'

'በል ወዳጄ እዚህ ብዙ ቆንጆ የዛኑ ያክል ብዙ መልከ ጥፉ ልታይ ትችላለህ ለቆንጆዎቹ ሁሉ ልብህን ይዘህ እና አይንህን አፍዘህ አትችለውም ትኩረትህን ትምህርትህ ላይ አድርግ' ብሎ የመጀመሪያ ምክሩን መከረኝ።

ከዛማ ሩቴ ምን ልበልሽ ቀናቶች በሄዱ ቁጥር የበለጠ እየወደድኩሽ መጣሁ። ሳይሽ ደግሞ ብቸኛ እና ከማንም ጋር ቅርበት ለመፍጠር የማትሞክሪ ነበርሽ። የትናዬትም አንቺን በእያንዳንዷ ነገር ልታጠቃ ስትሞክር አየሁ። ሀብትሽም ከኔ እኩል ነገሮችን ያይ ነበር። አንድ ቀን ካፌ ቁጭ ብለን ሻይ እየጠጣን በአጠገባችን አልፈሽ ጥግ ካለ ወንበር ላይ ብቻሽን ቁጭ አልሽ። ስትገቢ ጀምሮ እስከምትቀመጪ አይኔ አንቺ ላይ ነበር። ሀብትሽ ወዳንቺ የዞረውን ፊቴን በእጁ ከመለሰ በኋላ 'ይቺን ልጅ አፍቅረሀታል' አለኝ መካድ አልቻልኩም።

'እንደዛ ከሆነ ሳትቀደም ቅረባት'

'እንዴት አድርጌ'

'እሱን ለኔ ተወው የሆነ መንገድ አይጠፋም' ከዛ በኋላ ባሉት እያንዳንዱ ቀን የሱ ግፊት ነበር 'ቅረባት ወይ ከዚህ የበለጠ ትወዳታለህ ወይም ደግሞ መጥፎ ባህሪ ካላት ስታውቃት ትጠላታለህ እንደዚህ በሩቁ ወደሀት ብቻህን አትሰቃይ' በስተመጨረሻ ተሳካልኝና በምታውቂው መንገድ ቀረብኩሽ። እሱ እንዳለው ስቀርብሽ እጥፍ እጥፍ ወደድኩሽ

አንቺ ደግሞ ዮናታንን የዛኑ ያክል እንደምትወጂው አወቅሁ። ከዛ በኋላ ያለውን እንደምታውቂው ነው። ያንቺን ደስታ ብቻ ነበር የምፈልገው" በረጅሙ ተነፈሰና ፊቱን ወደኔ አዙሮ አይን አይኔን ያይ ጀመር አንገቴን ሰበርኩ

"ለምን ግን ቢኒ ለምን ብቻህን ተሰቃየህ? ለምን እስከዛሬ አልነገርከኝም?"

"ፈራሁ ሩቴ የኔ ላትሆኚ እንደማፈቅርሽ ብነግርሽ ጓደኝነታችንን አጣዋለሁ ብዬ ፈራሁ። ለአንድ ቀን እንኳን አኩርፈሽ ብትርቂኝ ብዬ ሳስበው ምድር የምትደፋብኝ መሰለኝ"

እንዴት ይሄን ያክል ጊዜ ሁኔታውን አይቼ መረዳት አቃተኝ እኔን ብሎ ዶክተር አልኩ ለራሴ

"ይሄ ካንተ ሊያርቀኝ አይችልም አንተ ከኔ መራቅ እስካልፈለግህ ድረስ እኔ በፍፁም አርቅህም። ቢኒዬ ወንድሜ ነህ እልሀለሁ ግን አንተ እኔን እህትህ የማድረግ ግዴታ የለብህም። ለምን አፈቀርከኝ አልልህም... አይደለም የኛን ያክል እስከ ጥግ የተቀራረበ ሰው ይቅርና ብዙም ሳይተዋወቁ በፍቅር የሚወድቁ ሰዎች አሉ። እኔ እድለኛ ሰው ነኝ... የእውነቴን ነው የምልህ እድለኛ ሰው ነኝ። ባንተ በመፈቀሬ እድለኛ ነኝ። ቆንጆ፣ ጎበዝ፣ ጠንካራ፣ ሰዎችን የምትረዳ መልካም ልብ ያለህ ሰው ነህ.... እንዳንተ አይነቱን ወንድ ማንም ሴት ቀርባ አይደለም አይታ ትመኘዋለች። የኔን ግን እንደምታውቀው ነው ከመጀመሪያ ጀምሮ በዮኒ ፍቅር ተለክፌ ነበር...... አንተን በፍቅር አስቤህ አላውቅም። እንደምታውቀውም አሁን ባለትዳር ሆኛለሁ ቢሆንም ግን አፍቅረህኛል ብዬ ልርቅህ አልፈልግም ለኔ አሁንም የድሮው ቢኒ ነህ.... ወንድሜ ነህ እዛም ሄደህ ቢሆን ደውልልኝ። አንተ ልራቃት ካላልክ እኔ አርቅህም" ወደኔ ጠጋ ብሎ አቀፈኝ

"ዋው..... ዋው.... ዋው.... የሁለቱ ጓደኛሞች አስገራሚ የፍቅር ጊዜ እንበለው ወይስ በስተመጨረሻ የተጋለጠው የሁለቱ ወጣቶች ፍቅር እንበለው የትኛው ይሻላል" ዮኒ.... ከቢኒ እቅፍ ወጣሁና ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ። ደብዳቤውን በእጁ ይዞ ፊት ለፊቴ ቆሟል....


ይቀጥላል....
┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
ቻናላችንንይቀላቀሉ

ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል ሀያ 2⃣0⃣

የሆነ እንደመልዓክ የቆጠራችሁት ሰው ከሆነ ጊዜ በኋላ ውስጡ ያለውን የሚያስፋራ አውሬ አውጥቶት ሊበላችሁ እየገሰገሰ ሲመጣ ምን ይሰማችኋል። ትሸሻላችሁ ወይስ ቆማችሁ ትበላላችሁ። እኔ ግን ብዙ ነገሬ እስከሚያልቅ ቆሜ ነበር የተበላሁት

የልቤ ንጉስ  ብዬ የፍቅር ማማ ላይ የሰቀልኩት ሰው ልክ የዛን ቀን ትክክለኛ ማንነቱን አየሁት። ማንኛውም ሰው ሲናደድ ብዙ ነገር ሊያደርግ ይችላል የሱ ግን ከዛ የተለየ ነበር። ነገሮችን ለመስማትም ለመረዳትም ፈቃደኛ አልነበረም ያነበበው ደብዳቤ ሳይቀር ቢኒ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅሩን እንደገለፀልኝ እየነገረው እሱ ግን ከመጀመሪያው ጀምሮ ፍቅረኛሞች ነበራችሁ ብሎ ደመደመ።

።።። ።።። ።።።።

"ጯ ጯ" ይህ በማፈቅረው ሰው የተመታሁት የጥፊ ድምፅ ነው። የቦክስን ድምፅ ደግሞ በቃል መግለፅ ይከብዳል እንጂ እኔን እንደመታኝ ቢኒ ዘሎ ተነስቶ ያቀመሰውን ቦክስ ከዛም አንዴ ቢኒ አንዲ ዮኒ ገላጋይ እስኪመጣ የተደባደቡትን በቃል እገልፅላችሁ ነበር።

ከድብድቡ በኋላ ሁለቱንም ሰው ይዟቸው

"አንተ ውሻ አላፈቅራትም ብለህ ያጣበስከኝ ፍቅረኛህን ነበር አይደል?(ደም ያዘለ ምራቅ ከአፉ እየተፋ) አትረባም ወንድ አይደለህም እሺ... ቀሚስ ልበስ"

ቢኒ ደግሞ ሌላ ትዕይንት ነው ከድብድቡ በኋላ እሱንም ሰዎች ቢይዙትም ለመወራጨትም ሆነ ለመሳደብ አልሞከረም የንዴት ትንፋሽ እየተነፈሰ ዝምም ብሎ ዳር ላይ ቆሜ አንዴ እሱን አንዴ ዮኒን እያፈራረቅሁ የማየውን እኔን ያየኛል

"እባካችሁ ልቀቁኝ ምንም አይፈጠርም እሷን ግን ሊጎዳት ይችላል። ሚስቱ ናት ግን እባካችሁ እንዳይጎዳት አድርጉ" አወራሩ ያሳዝን ነበር። ለቀቁትና ወደኔ መጣ

"ይሄ ውሻ ሚስቴ አጠገብ እንዳይደርስ እንዳትነካት አትጠጋት"
ብዙም ሳይቀርበኝ ቆመ

"ከሳምንት በኋላ እበራለሁ እስከዛ ግን ችግር ካለ ደውይልኝ እዛ ስሄድ ደግሞ እኔ እደውልልሻለሁ" አለኝና መልሴን ሳይጠብቅ ፊቱን አዙሮ ከመናፈሻው ወጣ

።።።። ።።።።። ።።።። ።።   ።።። 
ሳሎን ሶፋ ላይ ኩርምት ብዬ ተቀምጫለሁ። ዮኒ ደግሞ ከፊት ለፊቴ ሆኖ ከግራ ወደ ቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ ያለማቋረጥ እየተመላለሰ ይለፈልፋል

"ንገሪኝ እስኪ ስንት ጊዜ ሆናችሁ?" መልሴን ሳይጠብቅ ደግሞ

"የትናዬት ልክ ነበረች አይደል" ለመናገር አፌን እንደከፈትኩ

"ዝምምም በይ ምንም አትናገሪ ባትነግሪኝም አውቄዋለሁ። ግን ከመች ጀምሮ ነው ፍቅረኛ የሆናችሁት አንደኛ አመት እያለሽ"

"ኧረ እኔ ከቢኒ ጋር"
" ዝምም በይ አትንገሪኝ መገመት አይከብደኝም" ለመናገር መሞከሬን አቆምኩና ንዴቱ ሲበርድለት እነግረዋለሁ ብዬ አሰብኩ ግን በፍፁም ያሰብኩት አልሆነም። በውስጡ ያመነበትን የመከዳት፣ የመቀደምና የመሸወድ ስሜት ከውስጡ እንዳስወግድለት እድል ሊሰጠኝ አልቻለም። በራሱ ጭንቃላት ታሪክ ፈጠረና በፈጠረው ታሪክ ደግሞ አመነበት። ሩት ከቢኒያም ጋር የአንደኛ አመት ተማሪ እያሉ ነው ፍቅር የጀመረችው። እኔ ላይ ተመካክረው ነው የተጫወቱብኝ ይህን እና ሌሎች ነገሮችን በጭንቅላቱ ውስጥ ሞላቸው የሚያውቀውን እውነት ሳይቀር ካደ። ከዛ በኋላማ ያሳለፍኩትን እንዴት ልገልፀው እችላለሁ በአጠቃላይ ህይወቴ ሲኦል ሆነ።

ተመስገን ይህን ሰሞን በፍቅር የተሞላ ጊዜ አሳለፍን ብዬ አመስግኜ ሳልጨርስ ሌላ ታሪክ ይፈጠራል። በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ ግን ለሱ ያለኝ ፍቅር እንደድሮው ነበር። ትቼው እንኳን ለመሄድ አቅም አልነበረኝም። በእርግጥ ትቼው ብሄድ ከሱ የተሻለ ደሞዝ ያለኝ ራሴንም ሆነ ልጄን እና እናቴን ቀጥ አድርጌ ማስተዳደር የምችል ሰው ነበርኩ። ግን አፈቅረዋለሁ አንድ ቀን እውነቱን ለመረዳት እንደሚሞክርም አምናለሁ። እምነቴ ከምንም በላይ ለሱ ያለኝ ፍቅር በደልን ችዬ እንድኖር አደረገኝ።

።።።። ።።።።   ።።    ።።።።።።

ይህ ከተፈጠረ ከአመት በኋላ እናቴ በፀና ታማ ሆስፒታል ገባች። እኔ የምሰራበት ሆስፒታል ነበር።  እንደማትተርፍ እያወቅሁ ብዙ ጣርኩ ግን ልመልሳት አልቻልኩም። እናቴ ጥላኝ ሄደች እንደሚሰበር እንቁላል የምትጠነቀቅልኝ እናቴ እንደ አይኗ ብሌን የምትጠብቀኝ እናቴ ለኔ እንደኖረች ተምሬ ደርሸላት ትንሽ እንዳሳረፍኳት ገና ውለታዋን ሳልመልስ በደንብ እፎይይይ ብላ መኖር ሳትጀምር ሞት ነጠቀኝ። አመመኝ.... እጅግ በጣም አመመኝ....


ይቀጥላል....
┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
ቻናላችንንይቀላቀሉ
ከወደዳችሁት ❤️
🚨🔔 ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ 🔔🚨

📌 በዚህ ቻናል ላይ ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ?

😀😀😀😀😀😀😀😀😀

📱🔺➡️የ ቻናል ማስታወቂያ
📱😀➡️ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ
📱🔻➡️ የ ኮንሰርት ማስታወቂያ
📱🔻➡️የ ድርጅት ማስታወቂያ
📱🔹➡️ የ ዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ
📱🔹➡️ትሪትመንቶች እና ሌሎችም የሽያጭ ማስታወቂያዎች 📢

እንዲሁም ማስተዋወቅ ሚፈልጉትን ሁሉበተመጣጣኝ ዋጋ ማስተዋወቅ ይችላሉ !

ምርትና አገልግሎቶን

❤️ከ እኛ ጋ በመስራትዎ ይደሰታሉ።

አሁኑኑ ያናግሩን ➡️👇
@R2ebi
0933620136
የፍቅር ጥቅሶች 💖 pinned «🚨🔔 ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ 🔔🚨 📌 በዚህ ቻናል ላይ ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ? 😀😀😀😀😀😀😀😀😀 📱🔺➡️የ ቻናል ማስታወቂያ 📱😀➡️ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ 📱🔻➡️ የ ኮንሰርት ማስታወቂያ 📱🔻➡️የ ድርጅት ማስታወቂያ 📱🔹➡️ የ ዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ 📱🔹➡️ትሪትመንቶች እና ሌሎችም የሽያጭ ማስታወቂያዎች 📢 እንዲሁም ማስተዋወቅ ሚፈልጉትን ሁሉበተመጣጣኝ ዋጋ ማስተዋወቅ ይችላሉ ! …»
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 2⃣1⃣


እናቴ ጥላኝ ሄደች እንደሚሰበር እንቁላል የምትጠነቀቅልኝ እናቴ እንደ አይኗ ብሌን የምትጠብቀኝ እናቴ ለኔ እንደኖረች ተምሬ ደርሸላት ትንሽ እንዳሳረፍኳት ገና ውለታዋን ሳልመልስ በደንብ እፎይይይ ብላ መኖር ሳትጀምር ሞት ነጠቀኝ። አመመኝ.... እጅግ በጣም አመመኝ። ከኔ የበለጠ እንቁን ማፅናናት ከባድ ነበር። እማዬ ሁሉ ነገሯ ነበረች።

ለአንድ ቀን መዓድ የተጋራሀውን ሰው እንኳን በሞት ማጣት ከባድ ነው። እማ ከዛም በላይ አለሜ ነበረች፤ የራሴን ውብ አለም ፈጥራ ከፍራቻዬ የሸሸገችኝ፣ ጓደኛዬ፣ ስታመም ሀኪሜ፣ ስጨነቅ አማካሪዬ፣ ተቆጪ መካሪዬ፣ ዘጠኝ ወር በሆዷ ተሸክማ ሶስት አመት ጡቷን አጥብታ ያሳደገችኝ እናቴ ለሰው አንድ ለኔ ግን ብዙዬ ነበረች።
ይገርማል አይደል ነው ከመባል ነበር ወደመባል የምንሸጋገርባት የሽርፍራፊ ሰከንዶች ሞት....


አስፈላጊ ያልናቸውን እቃዎች ሰብስበን ወደኔ ቤት ካመጣን በኋላ ቤቱን አፅድተን ለአከራይዋ ቁልፉን አስረከብን።

አከራይዋን ቻው ብለናቸው ልንወጣ ስንል እንቁ
"ማሚ እዚሁ ነው መኖር የምፈልገው እማዬን ትቼ የትም አልሄድም" እየተንሰቀሰቀች የተቆለፈው በር ስር ሄዳ ቁጭ አለች። አጠገቧ ሄጄ ቁጭ አልኩና አቀፍኳት.... ለረጅም ደቂቃ አብረን ተላቀስን።

አከራይዋ ወ/ሮ ትርንጎ ከቤት ሲወጡ ተቃቅፈን ስንላቀስ አዩንና  ወደኛ መጡ

" ምነው ልጆቼ ተነጋግረን አውርተን... ተው እንጂ እኔንም ሆድ አታስብሱኝ እናታችሁንም አትረብሿት ነብሷ በሰላም ትረፍ። በእናንተ እንደዚህ መሆን ደስተኛ የምትሆን ይመስላችኋል በሉ ልጆቼ ኑ ተነሱ" እጇችንን ይዘው ካነሱን በኋላ እንባችንን ጠራረጉልንና መክረውንና አፅናንተውን በር ድረስ ሸኙን።

"በቃ ቻው እማማ ትርንጎ እየመጣን እንጠይቆታለን ብዬ ቃል አልገባልዎትም ግን ቤተ ክርስቲያንም ቢሆን መገናኘታችን አይቀርም። የምሰራበትንም ሆስፒታል ያውቁታል አይደል ለጤናዎትም ብቅ ማለት ይችላሉ። ቤትም ይምጡ አይጥፉ። በሉ ቻው... ከዚህ በላይ አይቸገሩ" ተሳስመን መኪና ውስጥ ገባንና ወደ ቤት ሄድን።

።።።። ።።።።። ።።።።። ።።።።።። ።።።።


እንቁ ሙሉ ለሙሉ እኛ ቤት መኖር ከጀመረች በኋላ የዮኒ ፀባይ ተስተካክሏል። ቶሎ ወደ ቤት ይገባል ትምህርት ቤት ያደርሳታል እልፎ አልፎ አብረው ይዝናናሉ። እኔ ብዙውን ጊዜ በስራ ስለማሳልፍ ባልቀላቀላቸውም የልጄ የአባትነት ክፍተት ሲሞላ በማየቴ ደስተኛ ነበርኩ። ሁልጊዜ አባቴ ማነው የሚለው ጥያቄዋ ሊያሳብደኝ ነበር የሚደርሰው.... ለጊዜውም ቢሆን ጥያቄዋን ትታ ዮኒን እንደ አባት ስታየው ማየቴ እፎይታን ሰጥቶኛል።

ትልቅ ልጅ እየሆነች ነው። አንዳንዴ እማዬ እየሳቀች "መልኳ እኮ አንቺን አስደግፈው የሳሏት ነው የምትመስለው። አንቺም ልጅ ሆነሽ እንደሷ እኮ ነው መልክሽ ካላመንሽ  ያንን አልበም አምጪና ፎቶሽን እና እሷን አስተያይ" ትለኝ ነበር።

ልጅ ሆና ብቻ ሳይሆን እያደገች ስትመጣም የኔኑ መልክ ያዘች።

ከዮኒጋ አልፎ አልፎ ጭቅጭቅ እንደ ቅመም ጣል ጣል ያለበት ራት በልተን እንገባለን። ቢሆንም ግን ከበፊቱ ጋር ሲነፃፀር ተመስገን ያስብላል። ትንሽም ቢሆን ቤቴ ትዳሬ ማለት ጀምሯል ያ ለኔ ትልቅ ነገር ነበር።

።።።።  ።።።።።   ።።።።።።   ።።።።።።

ቢኒ ከሄደ ጀምሮ ሶስቴ ነው የደወለልኝ። አንደኛው ከእናቴ ሞት በኋላ እግዜር ያፅናሽ ለማለት ነበር። ከዛ በፊት ሁለቴ ደውሎ ቢያውቅም ያን ያክል ግን አላወራንም ነበር ሌላው ቢቀር ስለመጫረሻው ቀናችን ደፍሮ የጠየቀ እንኳን አልነበረም።
ቻው ከማለቱ በፊት
" ግን ደስተኛ ነሽ" ይለኛል።

እርግጠኝነት በጎደለውና በቀዘቀዘ መንፈስ "አዎ" አለዋለሁ

ሁለቴም ሳወራው ዮኒ ሰምቶኝ የጥላችን ምክንያት ሆኖ ነበር። ቢኒ የሚባል ስም ቤት ውስጥ በተለይ ከኔ አፍ መስማት አይፈልግም።

።።።። ።።።።  ።።።። ።።።።  ።።።።
ከቀናት በአንዱ አዳር ስራ ገብቼ ደክሞኝ ቤት ስደርስ ከእንቁ መኝታ ቤት የለቅሶ ድምፅ የሰማሁ መሰለኝና ደንግጬ ሄጄ በሯን ስከፍት አልጋ ላይ ኩርምት ብላ ተኝታ ታለቅሳለች።

"እንቁዬ ምንድነው የኔ ልጅ ምን ሆንሽ" ድንግጥ ብላ ተነሳችና እንባዋን እየጠራረገች

"ምንም አልሆንኩም ማሚ"

"ምንድነው ፊትሽ ገርጥቷል እኮ አይንሽም አብጧል አሞሻል እንዴ" እጄን ግንባሯ ላይ አድርጌ ትኩሳቷን ለካሁት ግላለች

"አይ ትንሽ ሆዴን አሞኝ ነው። ማለቴ ፔሬድ ስለመጣብኝ ቁርጠቱን አልቻልኩትም" ፔሬድ ሲመጣ እንደሚያማት ባውቅም እንደዚ በህመም ስታለቅስ አይቻት አላውቅም ነበር። ማስታገሻ ኪኒን እንድትውጥ ካደረኳት በኋላ ተመልሳ ጥቅልል ብላ ተኛች።

መኝታ ቤት ገብቼ ልብሴን ቀይሬ ልተኛ ስል ስልኬ ላይ መልዕክት ገባልኝ።

"ባልሽን አሳርፊው ልንማር እንጂ ልንሸረሙጥ አልመጣንም ቴሌግራም ላይ ሙሉ መረጃውን ታገኛለሽ" ይላል። እየተጠራጠርኩ ቴሌግራም ከፈትኩ ፊት ለፊት የመጣልኝን መልዕክት ስከፍተው
ፎቶ እና አጭር ቪድዮ.....  ዮኒ ከሌላ ሴት ጋር....


ይቀጥላል....
┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋

ቻናላችንንይቀላቀሉ
ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘                               


ክፍል 2⃣2⃣

"ባልሽን አሳርፊው ልንማር እንጂ ልንሸረሙጥ አልመጣንም ቴሌግራም ላይ ሙሉ መረጃውን ታገኛለሽ" ይላል። እየተጠራጠርኩ ቴሌግራም ከፈትኩ ፊት ለፊት የመጣልኝን መልዕክት ስከፍተው
ፎቶ እና አጭር ቪድዮ.....  ዮኒ ከሌላ ሴት ጋር....

እየሰሙ አለማመን ያለም የሚጠበቅም ነው። እያዩ አለማመን ግን ምን ይባላል። በአካል መጥተው ዮኒ ከእከሊት ጋር ማገጠብሽ ቢሉኝ አይደለም እሱን ልጠራጠር ከነገረኝ ሰው ጋር ልጣላ እችላለሁ። አሁን ግን እውነታ ነው ቁጭ ያለልኝ... ከምወደው ባሌ ጋር እርቃን ገላዋን አብራው የምታብድ ሴት እያየሁ ነው። የአንዷ አልበቃ ብሎ ከሌላ ሴት ጋር ደግሞ ከንፈሯ ላይ ተጣብቆ ያለ ፎቶ እያየሁ ነው... ግን አንድ ነገር ብቻ ነው የምለው። "የኔ ዮኒ አያደርገውም" አድርጎታል እኮ ...ግን ይህንን ማመን ያልፈለገ ውስጥ አለኝ... እናም እውነታውን እያየ ግግም ብሎ አላምን አለኝ። አንደኛው ውስጤ ደግሞ ፍቅርን ሳይቀር ወደጎን ብሎ በቀልን ፈለገ። ቢችል አሁን ያለበት ሄዶ ስጋውን ቢዘለዝለው ተመኘ። የማያምነው ውስጤ ገኖ ወጣና
"ዮኒ አያደርገውም" በጩኸት ቤቱን አደበላለኩት። ሰራተኛዬ እልፍነሽ መኝታ ቤቴን ከፈት አደረገችና

"ሰላም ነው ሩት" አለችኝ

"ሰላም ነው እልፌ ወደ ስራሽ ተመለሽ" በሩን ዘግታ ተመለሰች። ረጅም ደቂቃ ዝምምም ብዬ ስልኬ ላይ አፈጠጥኩ

ሀሳቡ አደከመኝ ያየሁት እውነት አራደኝ በዛ ላይ ሰሞኑን የተለየ ኬዝ ስለነበረ ያለ እንቅልፍ ሆስፒታል ነበርኩ። ስልኬን ዘግቼ ያስቀመጥኩት መሰለኝ... ከዛ ወደ አልጋዬ ተራመድኩ.... አንድ.... ሁለት..... ጭልም አለብኝ።

"እናት ኧረ ንቂ የኔ ፍቅር" ይሄን ጥሪ ከሰማሁት ስንት አመት ሆነኝ.... ሁለት.... ሶስት... ብቻ በዛ መሀል... አሁንስ ለምንድነው እየሰማሁት ያለሁት... ሁሉም ነገር ከረፈደ... ካለፈበት በኋላ ለምን?... አይኔን ሳልገልጥ እንቅስቃሴውን እየተከታተልኩ ነው።

"ንገሪኝ እስኪ እናት ማነው ጥፋተኛ እኔ ወይስ አንቺ? በእርግጥ የኔ ጥፋት ሚዛን ይደፋል... ምክንያቱም ካየሽው ውጭ እንኳን ብዙ ጥፋቶችን ሰርቻለሁ ግን ባንቺ ጥፋት ላይ ተመርኩዤ ነው። ታውቂያለሽ ከቢኒ ጋር ድሮም እጠረጥርሽ ነበር እና ጥርጣሬዬን የሚያረጋግጥልኝ ነገር ሳገኝ እውነት አይደለም ብዬ ማመን አቃተኝ። ልታስረጅኝ ስትሞክሪ ውሸቷን ነው ብዬ አልሰማም አልኩሽ እናም ከዛን ጊዜ ጀምሮ ያለማቋረጥ ማገጥኩብሽ... ግን እናት ያሁኑ በደሌ በዛ..... (ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ እና ትንሽ ዝም ካለ በኋላ ቀጠለ) ከስንት ጊዜ በኋላ በአንዲት ልጅ ምክንያት ራሴን አዳመጥኩት። አብረሽኝ ካልተኛሽ ውጤትሽን አበላሸዋለሁ ብዬ አስፈራራኋት.... ብዙ ለመነችኝ... ልመናው አልሰራ ሲላት ግን ያንቺን አድራሻ ፈልጋ ሆስፒታል መጣችና አየችሽ። ስለትዳራችን ሳይቀር ብዙ መረጃ ሰበሰበች ከረፈደ ቢሆንም  ንግግሯ ከእንቅልፌ አነቃችኝ... ትልቁን በደሌን የሰራሁ እለት ከእንቅልፌ ነቃሁ

'ሚስትህ ነፍሷን ሳትሰስት ትሰጥሀለች... አንተ ማመን ባልፈለከው ውሸት ውስጥ ተደብቀህ በሀጢያት ተጨማልቀሀል... ለሷ አትገባትም ምክንያቱም ንፁህ ናት... ግን እግዜር ይቅር የማይለው የለም አምላክህንም ሚስትህንም ይቅርታ ጠይቀህ ወደራስህ ተመለስ። ለውጤቴ ስል አብሬህ ላድር አልፈልግም በተለይ ያቺ ሚስኪ ላይ ይሄን ላደርግ አልችልም። ከፈለግህ ኤፍ አድርገው ህሊናዬን አላቆሽሽም'  ብላኝ ስላንቺ እንዴት እንዳወቀች ሁሉንም ነገር አብራራችልን እና ለአመታት ከተኛሁበት እንቅልፍ ዛሬ ቀስቅሳኝ ሄደች። ያሰብኩት ለሀያ ደቂቃ ብቻ ነው። ወደራሴ ተመለስኩ... እውነታውን ማየት ቻልኩ... በንግግሮቼም ሆነ በተግባር ብዙ እንደገፋሁሽ አወቅሁ... በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን እንዴት እንደምትጠነቀቂልኝ... ምን ያክል እንደምትወጂኝ ተረዳሁ። ወደዚህ ለመምጣት እየተጣደፍኩ ስወጣ ቢሮ በር ላይ ከዚህ በፊት በውጤት አስፈራርቻት አብሪያት የተኛሁትን ልጅ አገኘኋት እናም ቪዲዮና ምስል ላንቺ እንደላከችልሽ ነገረችኝ። ምንም ሳልል ወደዚሁ መጣሁ ወድቀሽ አገኘሁሽ።
ሩቴ እየሰማሽኝ እንደሆነ አውቃለሁ። ይቅር በይኝ አልልሽም በተለይ በአንድ ጉዳይ ያንቺ ይቅርታ አይገባኝም... ብቻ አይንሽን ግለጪና የፈለግሺውን ቅጪኝ" አይኔን ገለጥኩ ከወገቤ ቀና አልኩና ትራስ ተደግፌ ቁጭ አልኩ። ለረጅም ደቂቃ በዝምታ አፈጠጥኩበት

"ደስ ያለሽን አድርጊኝ የፈለግሺውን ቅጪኝ " አንደበቴ ሊናገር ቢፈልግ እንኳን ውስጤ ዝምምምም ብሏል የሚያስፈራ ዝምታ

"ደግሞ አሁን እሰማሻለሁ ከቢኒ ጋር ያደረጋችሁትን ንገሪኝ እኔ እንደተናዘዝኩ ተናዘዢልኝ.... ይቅር ተባብለን  አብረን ባንቀጥልም ጥያቄዎቼን እንድትመልሽልኝ እፈልጋለሁ... የምናሴ አባት ማነው። ሩት አንቺም እኮ ድብቅ ነሽ ከኔ የደበቅሺው ብዙ ሚስጥር አለሽ" ዝምምምም

"እንቁን አሟት ነበር ልያት" ከመኝታ ቤታችን ወጥቼ ወደሷ ስሄድ

"እወቂ ለዚህ ሁሉ ነገር ያንቺም እጅ አለበት....ወይኔ አምላኬ ምንድነው ያደረኩት" ሰማሁት ግን ባልሰማ ወደ ልጄ ክፍል ሄድኩ

በሩን ከፈት አድርጌ ሳያት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ተኝታለች ወደ ውስጥ ገባሁና ቀስ አድርጌ ዘጋሁት። የአልጋዋ ጫፍ ላይ ቁጭ ብዬ የትኛችውን እንቁዬን አየኋት ግንባሯ ላይ ቸፈፍ ያለ ላብ አለ። ፎጣ አንስቼ ስጠርግላት እጄን ለቀም አድርጋ ወረወረችውና

"እባክህ አትንካኝ እባክህ" ከእንቅልፏ ደንግጣ ነቃች

"ምንድነው ልጄ ማንን ነው አትንካኝ የምትይው"

"አይይ እእ....እ


ይቀጥላል....
┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋

ቻናላችንንይቀላቀሉ
ከወደዳችሁት LIKE ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 2⃣3⃣

"የምን እእ ነው ምንድነው ንገሪኝ" ለአመታት ስቃዥ የነበረው ትዝ አለኝ... አይ አይሆንም

"በህልሜ የሚያስፈራ ሰው ገደል ውስጥ ሊከተኝ ሲል አየሁ" ኡፍፍፍፍ.... እኔ ደግሞ ስንቱን አሰብኩት

"አሁን እንዴት ነው ቁርጠቱ ተሻለሽ" ዮኒ በሩን ከፍቶ ገባ

"ምን ሆነሽ ነው ምናሴ ብዙ አመመሽ እንዴ ጠዋት እኮ ረፍዶብኝ ሳላይሽ ሄድኩ" የቅድሙን የተፀፀተ ፊት ሳይሆን ፍም እሳት የሚተፋ አይኑን አየሁት... እንቁ ፊቷን አዙራ ተኛች

"ምንድነው አንቺ ባለጌ ለአባትሽ መልስ ስጪው እንጂ" ፊቷን እንዳዞረች

"ደና ነኝ ተሽሎኛል" አለችው። ተነሳሁና ትቻቸው ወጣሁ። ሳሎን ሶፋ ላይ ቁጭ ብዬ ቲቪው ላይ አፈጠጥኩ..... ሀሳቤ ግን ሩቅ ሄዶ ነበር። መች ነው ይሄን ክፍተት የፈጠርኩት... ለራሴ ደግሜ ልነግረው አልፈልግም የምለውን ያን የመደፈር ታሪኬን ከመደበቅ... አዎ ከዛ ነው የጀመርኩት... ከዛ  የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ አልኩት... ከዛ... ከዛ... ከቢኒ ጋር እንኳን ምንም ግንኙነት የለንም... እሱም እንዳስረዳው እድሉን አልሰጠኝም።

ቢዘገይም ነገሮችን አጥርቼ መሄድ እንዳለብኝ ተሰማኝ እና ታሪኬን ከአንድ ጀምሬ እነግረዋለሁ ብዬ ወሰንኩ... ግን አሁን አይደለም።

።።።።።።  ።።።።።  ።።።።። ።።።።። ።።።።

ሩትን ምን ይጨንቃታል ብትሉ ሰውን ተጣልቶ ማኩረፍ እላችኋለሁ። በህይወቴ እንደመኮራረፍ የምጠላው ነገር የለም አኩርፌ ማደርም አልችልም... በቃ ከሰው ጋ ተጋጨሁ አይደል ወይ እዛው ጋ ችግሩን እነግረዋለሁ ወይም ዝም ብዬ አልፈዋለሁ... ብቻ ያስከፋኝም ላስከፋውም ድጋሚ ሳገኘው ያንን ሰው አዋራዋለሁ። ከዮኒጋ በአንድ ጣራ ስር... አንድ አልጋ ላይ እየተኛን በየቀኑ እያየሁት ለማኩረፍ ሞከርኩ ግን አልተሳካልኝም በደሉን ባልረሳውም ሳላስበው አዋራሁት።

"መነጋገር ያለብን አይመስልሽም" አለኝ። ወደ ስራ ለመሄድ እየተጣደፍኩ እያለ

"አስቤበታለሁ ማውራት አለብን ግን አሁን አይደለም... ሆስፒታላችን የልምድ ልውውጥ ሌላ ከተማ ሊልከኝ ነው። ከአስራ አምስት ቀን በኋላ እመለሳለሁ ያኔ እናወራለን" መኪናዬን አስነስቼ ወጣሁ

።።።።   ።።።።    ።።።።     ።።።።

ሳሎን ቁጭ ብለን ከታሪኬ ሀ ጀመርኩለት
"የአስራ ሶስት አመት ልጅ እያለሁ ነው........." ሁሉንም አንድ በአንድ ዘርዝሬ ነገርኩት ከሱ ግን ያላሰብኩትን ነገር ሰማሁ

"እና ያኔ የደፈርኩት አንቺን ነበር"

"ምን? ምንድነው የምታወራው?"

"ብርቄን ታውቂያታለሽ? ጎረቤታችሁ ናት መሰለኝ"

"አዎ ብርቄን ከነ ነገሯ የማያውቅ አለ እንዴ... ግን አንተ እንዴት?"

"የዩንቨርስቲ ተማሪ እያለሁ እናቴ የማልወዳት አክስቴ ጋ መልዕክት ይዘህ ሂድ ብላ ላከችኝ... እረፍት ስለነበርንም እየተነጫነጭኩ ብርቄ ጋ መጣሁ።
በዛውም ከአክስቴ ጎረቤት ልጅ ዘመናይ ጋር ተዋወቅሁ። በሁለት ቀን ውስጥ ተዋደን ሴክስ አደረግን( አውቃታለሁ አገር ያወቃት ወንድ አሳዳጅ ናት አልገረመኝም ) የዛን እለት ግን እዛ የጭቃ ቤት ውስጥ እያለን ወደኛ የሚመጣ ሰው ድምፅ ሰማን እና እሷ ቶሎ ብላ ወጥታ ሄደች እኔ ግን እዛው ቀረሁ። በወሲብ ስሜት ጦዤ ስወጣ አንቺን ከሩቅ አየሁሽ እና ጠራሁሽ.... ያ ሁሉ ነገር ተፈጠረ" ከነገረኝ ታሪክ ውስጥ አንድ አስደሳች ነገር አገኘሁ... የእንቁን እውነተኛ አባት

"አክስቴ እኔ እንደደፈርኩሽ ስታውቅ... ማንም ሳያየኝ በሌሊት ሀገሩን ለቅቄ እንድሄድ ድጋሚም እንዳልመለስ አስጠንቅቃ ወደ እናቴ ላከችኝ። በሶስት ቀን ቆይታዬ ብዙ ታሪክ ፈጥሬ ተመለስኩ"
' ሳትፈልግ ማን ሊነካት' እያለች ስታወራ የነበረችውን ብርቄን አሰብኳትና ተገረምኩ ወዲያው ደግሞ ደስ የሚለውን ሁኔታ አሰብኩት

"ደስ ሲል" ሳላስበው ቃል ከአፌ ወጣ

"ምኑ ነው ደስ የሚለው የኔ አንቺን መበደል ድሮ እንደጀመረ ማወቅሽ ነው" ግራ ግብት ብሎት ያየኛል

"እንቁ እውነተኛ አባቷን ማግኘቷ"

"ማለት...? ምን እያልሽን ነው? ምናሴ የኔ ልጅ... አይ አይሆንም... ማለት ተደፍረሽ ነው የወለድሻት...? አይ ውሸትሺን ነው።"

መልስ ሳልሰጠው እየሮጥኩ እንቁ መኝታ ቤት ገባሁ ቁጭ ብላ እያነበበች ነው። ስገባ ቀና ብላ አየችኝ

" ምን ተገኘ ማሚ ፊትሽ እኮ በፈገግታ ሊፈነዳ ነው"

"የተገኘውማ አባትሽ ነው"

"የእውነት...(እንባዋ ኮለል ብሎ ወረደ ሰፍ ብላ አፍ አፌን አየችኝ) የት ነው ያለው ማሚ... የኔ አባት የት ነው?( ሳግ አነቃት) ማሚ በተለይ በዚህ ሰዓት አባቴን በጣም እፈልገዋለሁ... እማ ንገሪኛ..."

"ዮኒ እውነተኛ አባትሽ ነው" አንገቷን ወደኔ አስግጋ ሁለመናዋ ጆሮ ሆኖ በአይኗ ሳይቀር ስትማፀነኝ የነበረችው ልጄ ከኣካሏ እኩል ስብር ስትል አየኋት

"እሱ አባቴ አይደለም... ትክክለኛ አባቴን የአብራኩ ክፋይ የሆንኩትን ሰው ነው የምፈልገው" አለችኝ እንዳቀረቀረች

"አዎ የኔ እንቁ አንቺ የዮኒ የአብራኩ ክፋይ ነሽ ታሪኩን እነግርሻለሁ። የአስራ ሶስት አመት ልጅ እያለሁ..." ዝምምም ብላ ሰማችኝ... ምንም አይነት እንቅስቃሴም ሆነ ንግግር አላደረገችም... ዝምምምም.... አውርቼ ስጨርስ

"ደስ አይልም የኔ እንቁ" አልኳት እንባዋ ገደቡን ጥሶ ወረደ 'ምንድነው እንቁ ለምንድነው የምታለቅሺው'

"ደስ ብሎኝ ነው እማ... የደስታ እምባ ነው። ነይ እቀፊኝ" ተቃቀፍንና

"በቃ ይሄን ቀን ፏ አድርገን እናከብረዋለን ነይ ተነሺ" እጇን ይዤ አስነሳኋትና ወደ ሳሎን ሄድን ዮኒ የለም... መኝታ ቤት አየሁት የለም... ቤት ውስጥ የለም... ለአንድ ቀን ብቻ ሳይሆን ለሳምንታት የለም...

።።።። ።።።። ።።።። ።።።

የሆነኛው ቀን ሌሊት ላይ ስልክ ተደውሎልኝ ዮኒ ያለበትን ቦታ ነገሩኝ... ጭፈራ ቤት ነው። ስሄድ ከሁለት ሴቶች ጋ አብሮ እያበደ ነው... ምንም ሳልል ወደቤቴ ተመለስኩ... ለራሴ ግን አንድ ውሳኔ ወስኜ ነበር 'ተመልሶ እዚህ ቤት አይረግጥም'። ብቸኝነት ተሰማኝ... ቅዝቃዜው አንዘፈዘፈኝ.. እናም ብቸኛዋ እንቁዬ ጋ ልሸሸግ ወደሷ መኝታ ቤት ሄድኩ። በሩን ከፍቼ ስገባ ግን የኔ እንቁ መሬት ላይ ተዘርራ አየኋት ጮኩ። እልፍነሽ ስትሮጥ መጣች... ከመሬት አንስተን አልጋ ላይ ካደረግናት በኋላ የልብ ምቷን አየሁት... ቆሟል... አፏን አሸተትኩት ገዳይ መርዝ ጠጥታለች። ሰውነቷን ነካሁት ከበረዶ ቀዝቅዛለች...
የኔ እንቁ የለችም... ትታኝ ሄዳለች...

ይቀጥላል....
┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
ቻናላችንንይቀላቀሉ
ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 2⃣4⃣

#ከጊዜያት_በኋላ

"ንገሪኝ እስኪ ሩቴ ሀኪም እንዲያይሽ ባትፈልጊም ህመምሽን ለኔ ንገሪኝ ዝምምም ብዬ እሰማሻለሁ። ስለ ልጅሽ ስለ ዮኒ ስለተፈጠረው ሁሉንም ንገሪኝ" ሶስት ወራትን በዝምታ ስለዚህ ነገር ሳያነሳብኝ ሳላወራው በየጊዜው የአእምሮ ህመሜ እየተነሳ ከኔው እኩል ሲሰቃይ አሳልፈናል። ትዕግስቱ እንክብካቤው ፍቅሩ ድሮ ከማውቀው የበለጠ ተወዳጅ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ግን ምን ዋጋ አለው ፍቅር አንዳንዴ ፍትሀዊ አይደለም ቢሆንማ ኖሮ የማፈቅረው ዮኒን ሳይሆን ቢኒን ነበር። ወደ መኝታ ቤት ሄድኩ... ተከተለኝ... በሩን ከፍቼ ገባሁና ቤቴ ሄደን ካመጣናቸው እቃዎች መሀል አነስተኛውን ሻንጣዬን አወረድኩት... ከፈትኩት... ውስጡ ያለው ሁሉም የልጄ ማስታወሻ ነው። ለአዲስ አመት የሳለችልኝን አበባ አገኘሁት... እሱን አቅፌ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ

"የኔ ልጅ... የኔ እንቁ... ናፈቅሽኝ እኮ" ቢኒ አጠገቤ ብርክክ ብሎ ትከሻዬን ያዘኝ ከዛም ወደራሱ አስጠግቶ አቀፈኝ።  ህመሜ ሳይነሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሴን አረጋጋሁና ከእቅፉ ወጥቼ ከመፅሀፍ መሀል አጣጥፌ ያስቀመጥኩትን ደብዳቤ አወጣሁት... ከባዱን መርዶ ያረዳኝን... መራራውን እውነታ የጋተኝን ደብዳቤ አወጣሁና ለቢኒ ሰጠሁት። ግራ በተጋባ ፊት ካየኝ በኋላ ከፈተው... ደጋግሜ ከማንበቤ የተነሳ እያንዳንዱን ቃል እንደ ውዳሴ ማርያም የሸመደድኩትን ደብዳቤ እሱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያነበው ከፈተው... እንዲህ ነው የሚለው...


"ማሚ ከበደል ሁሉ የቱ እንደሚከፋ ታውቂያለሽ... አባቴ የምትይው ሰው በስሜት ጦዞ ጭንሽን ሊከፍት ሲታገል ማየቱ...... ማም እውነቱ ይገልሻል አውቃለሁ ...ግን እንደዛ ጠንካራ ስነ ልቦና እንዲኖራት አድርገሽ ያሳደግሻት ልጅሽ ለምን ራሷን አጠፋች? የሚለው ጥያቄም ይገልሻል። ማም እውነቱን እወቂው..... መጀመሪያ የውሸት ቆይቶ ደግሞ የእውነት አባት የሆነኝ ዮኒ የውሸት አባቴ እያለ አንዴ ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ደፍሮኛል። ታስታውሻለሽ ያኔ ፔሬድ አሞኝ ነው ብዬሽ የተኛሁ ጊዜ... ለመጀመሪያ ጊዜ የደፈረኝ ቀን ነበር። አንቺ ውስጥ እያለሽ ሊጠይቀኝ ሲመጣ ፊቴን አዙሬበት ነበር አይደል? ከዛ አንቺ ወጣሽ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ 'በሶስተኛው ቀን መድገም አለብን ካላዛ ተደፍነሽ ትቀሪያለሽ' አለኝ። እናም በሶስተኛው ቀን መኝታ ቤቴ ድረስ መጣ... መከላከል ደከመኝ እና በዝምታ አየሁት ሳይራራልኝ እላዬ ላይ ጨፍሮ ሄደ...  ያንኑ ድርጊቱን የአባትነት እውነታው እስከሚታወቅ ድረስ ደጋገመው። በተለይ ፊልድ መውጣትሽ ለሱ ምቹ ሁኔታ ለኔ ደግሞ ስቃይን ፈጠረ

ካንቺ ፊት ላይ የየሁትን ደስታ እኔ ጋር ፈልጌ አጣሁት። ማም እንዴት ልደሰት... አባቴን አገኘሁ ብዬ እንዴት ደስ ይበለኝ...?  አባትነቱን እኮ ጭኔ መሀል ቆፍሮ ቀብሮታል። እናም አባቴ አይደለም ሊሆንም አይችልም ብዬ በዝምታ ተሸብቤ ቁጭ ብዬ እያለ ሌላ ክስተት ተፈጠረ። በየጊዜው እየመጣ ይቅርታ ብሎኝ 'አደራ ለናትሽ እንዳትነግሪያት' ከሚለኝ ከህሊናቢሱ አባቴ የስምንት ሳምንት ነብሰ ጡር እንደሆንኩ ሆስፒታል አረጋገጥኩ። ያኔ በራሴ ላይ ወሰንኩ... ታሪክ ራሱን አይደግምም... ማም አንቺ አባት እንደሌለኝ እያሰብሽ ወልደሽ እሳደግሺኝ... የኔ ልጅ አባት ግን አባቴ ነው... እናም በራሴ ላይ እና ባልወለድኩት የአባቴ ልጅ ላይ የሞት ፍርድ ወሰንኩ።

ማሚዬ ለኔ ስትይ ጠንክረሽ ኑሪ እወድሻለሁ።
እድለቢሷ ልጅሽ"


ደብዳቤውን አንብቦ ከጨረሰ ቢቆይም እንባ ከአይኖቹ እየወረደ ፍዝዝ ብሎ ተቀምጧል።

"ይህን ደብዳቤ ሳገኘው ቢኒ ጊዜው ረፍዷል... የልጄ ገዳይ አጠገቤ አልነበረም... ትቶኝ ሄዶ ነበር... ፈለኩት በየሆስፒታሉ በየሆቴሉ ግን አጣሁት... ባገኘው በአደባባይ ስጋውም ዘልዝዬ ለአሞራ እሰጠው ነበር"።  እያለቀሰ መጥቶ አቀፈኝ ረጅም ሰአት ተቃቅፈን ተላቀስን...።

"እባክሽ አንድ ነገር እሺ በይኝ የስነልቦና ሀኪም ይይሽ እባክሽ ለኔ ስትይ" ለብዙ ጊዜ ደጋግሞ ቢጨቀጭቀኝም እምቢ ነበር መልሴ

"እሺ ደስ ያለህ ሀኪም ጋ ውሰደኝ"

።።።።። ።።።።። ።።።። ።።።።። ።።።

የስነ ልቦና ህክምናዬን ከጀመርኩ አንድ ሳምንት ቢያልፈኝም ለዶክተሬ ምንም የነገርኩት ነገር አልነበረም። የሆነ ቀን ግን ልክ ከዚህ በፊት ያለውን ታሪክ እንደሚያውቀው ሁሉ

"ዮኒን ብቻ ጥፋተኛ አድርጌ እንዳልፈርድ የሚያደርገኝ እንደዚህ ያሳመመኝ ብዙ ፀፀት ውስጤ አለ። ብዙ ቢሆን ኖሮ.... ብዙ.... ብዙ....

•ከመጀመሪያው ታሪኬን ነግሬው ቢሆን ኖሮ

•ስራ ስራ ማለቴን ትቼ ለልጄ ጊዜ ሰጥቻት ቢሆን ኖሮ

•እንደዛ ሆና እያየኋት ትንሽ እንኳን ለምን አልተጠራጠርኩም... አሁን እኔ ዶክተር እባላለሁ...

ከሁሉም በላይ ፀፀቱ በልቶ ጨረሰኝ... መገጣጠሚያ አጥንቴ እስከሚታይ ከሳሁ... ጠቆርኩ... ታመምኩ... አበድኩ ...ግን ትርጉም አልነበረውም... እኝህ ሁሉ የኔን እንቁ አይመልሱልኝም ባዶ... አንተስ የኔን እንቁ ትመልስልኛለህ? አየህ እዚህ መጥቼ መፋጠጣችንም ትርጉም የለውም ባዶ..." አልኩት። ዝምምም ብሎ ካየኝ በኋላ ከወንበሩ ተነስቶ መጥቶ ፊት ለፊቴ ሶፋ ላይ ተቀመጠ

@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
     

ይቀጥላል....

ቻናላችንንይቀላቀሉ
ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 2⃣5⃣

ከስድስት ወራት ያላሰለሰ የህክምና ክትትል በኋላ ወደራሴ ተመለስኩ ወደ ስራየም ጭምር። ከቢኒ ጋር ደስ የሚል የፍቅር ግንኙነት ጀመርኩ... ህይወት ድጋሚ ቀጠለች። ያለፈው ባይረሳም ህመሙ ቀንሷል... የልቤ በልቤ ተቀብሮ መሳቅ ቻልኩ።

ከቢኒ ጋ ልንጋባ ነው ማለትም ከሁለት ወር በኋላ እንጋባለን። ለፊርማው እንጂ የምንኖረው አንድ ቤት የምንተኛው አንድ አልጋ ላይ ከተጋባን ቆይተናል ለማለት ነው። ልንጋባ መሆኑን ያወቀው ሀብታሙ ካለበት ሀገረ አሜሪካ የሚያምር ቬሎና ሱፍ ልኮልናል። ለቢኒ ሚዜ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ።

የሆነኛው ሌሊት ላይ ተኝቼ ልጄን በህልሜ አየኋት... ብቻዋን አይደለም ዮኒ ሲደፍራት "ድረሽልኝ" እያለች ስትጮህ... ጮኬ ከእንቅልፌ ነቃሁ... አጠገቤ የተኛው ቢኒ ጩኸቴ አስደንግጦት

"ምንድነው ፍቅር አይዞሽ ቅዠት ነው" አለና እቅፉ ውስት ከተተኝ... እኔ ግን የበቀል ጥሜ ድጋሚ አንሰራራ... እፈልገዋለሁ እናም እገለዋለሁ... እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ።

ለቀናት በሀሳብ ተብሰከሰኩ እናም ወሰንኩ ይህን ነገር ከስሩ መንግዬ መጣል ይኖርብኛል። ተቆርጦ ባቆጠቆጠ ቁጥር ህመሙ እየባሰ ነው የሚሄደው ስለዚህ እ ገ ለ ዋ ለ ሁ።

።።።።። ።።።።።። ።።።።።።።

       #አሁን

ትቼው ልሄድ ነው። በቃ ልሄድ ነው የመጨረሻ ውሳኔዬን ወስኛለሁ የምሄደው እንደ ሌላው ጊዜ ጥላቻንና ክህደትን ሽሽት አይደለም...  ፍቅርን እንጂ።
እናም በሀሳብ እየዋዠኩ ደብዳቤ ልፅፍለት ወሰንኩ ቢያንስ ምክንያቴን ማሳወቅ አለብኝ አይደል... ደግሞ ጠፋች ብሎ ሀገር ምድሩን ነው የሚያምሰው...

መፃፍ ጀመርኩ

"አንዳንዴ ልቋቋመው ከምችለው በላይ ይሆንብኛል። ፍቅርህ፣ ስስትህ፣ እንክብካቤህ፣ አንተን ትተህ ለኔ ደስታ መድከምህ፣ ከቃላት ጋጋታ ይልቅ በተግባር የምታሳየኝ መውደድህ በአጠቃላይ ሁሉም ነገርህን መቋቋም ያቅተኛል።

ሰው እንዴት ይህን ያክል ሰውን ሊወድ ይችላል እንዴትስ ሁሉ ነገሩ ፍቅር ብቻ ይሆናል ፍቅር... ፍቅር... አሁንም ፍቅር.... አንተጋ ያለው ፍቅር ብቻ ነው እኔጋ ደግሞ ላንተ ያለኝን ፍቅር ሊፈታተን የሚችል የበቀል ጥም አለ። ያንተ ፍቅር እና የኔ በቀል ጥም ተጣጥመው ሊሄዱ አይችሉም ስለሆነም ጥሜን ልቆርጠው ፍቅርህን መሸሽ መርጫለሁ። ያጣሁት ልጄን... ማያዬን... እንቁዬን... ሁሉ ነገሬን ነው። ገዳይዋን ሳልገድል እረፍት እይሰማኝም። አዝናለሁ ቢኒ...

አፈቅርሀለሁ ግን ልሄድ ነው። ትቼህ ልሄድ ነው... ጠንካራ ነህ ትወጣዋለህ።

ደህና ሁን
ሩት "



ደብዳቤውን ፅፌ ከጨረስኩ በኋላ አጥፌ ፊት ለፊት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጥኩትና ሻወር ልወስድ ገባሁ። ቢኒ ቶሎ እንደማይመጣ ስለማውቅ ዘና ብያለሁ... ታጥቤ ፎጣዬን እንዳሸረጥኩ ስወጣ ቢኒን አልጋ ላይ ቁጭ ብሎ አገኘሁት በእጁ የፃፍኩትን ደብዳቤ ይዟል።

"ምንድነው ፍቅር? ድጋሚ ወደኋላ... ለምን እኔንስ ታደክሚኛለሽ አላሳዝንሽም" አለኝ አጠገቤ መጥቶ አይን አይኔን እያየኝ

"ልጄን በህልሜ አየኋት ቢኒ... አድኚኝ እያለች ስትጮህ አየኋት... ልጄ ከመሬት ስር ተቀብራ...(ሳግ አነቀኝ) አፈር ተጭኖባት እሱ ግን እየተነፈሰ ነው። እፈልገዋለሁ እናም በእጄ እገለዋለሁ" እልሄ ልኩን አለፈ...  ፎጣዬን ጥዬ ልብሴን ለባበስኩና ሻንጣዬን ይዤ ልወጣ ስል።

"ዮኒን አግኝቼዋለሁ" አለኝ። ባለሁበት ቀጥ ብዬ ቆምኩ

"ምን?"

"ይሄን በቀል የተውሽ መስሎኝ ነበር ግን ከፈለግሽ አብሬሽ እሄዳለሁ ያለበትንም አሳይሻለሁ ስትገይውም ቆሜ አይሻለሁ።"

"የት ነው ያለው ቦታውን ብቻ ንገረኝ ብቻዬን እሄዳለሁ"

"እሱን እንዳታስቢው ወይም ራስሽ ፈልገሽ አግኝው... ደግሞ አታገኝውም" አማራጭ የለኝም ሻንጣዬን ይዤ ወደኋላ ተመለስኩ።

"እሺ ውሰደኝ አሁን ውሰደኝ"

"አይ አይሆንም ነገ ነው የምንሄደው"  በእሽታ አንገቴን ነቀነኩለት።

ወደቀኝ ገልመጥ ብዬ ሳይ የሰርግ ቬሎዬ ተሰቅሏል። ለራሴ ወደኋላ የለም  አልኩ...


ይቀጥላል....

ቻናላችንንይቀላቀሉ
┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋
ከወደዳችሁት ❤️
😘 ያበደው ፍቅሬ 😘


ክፍል 2️⃣6️⃣


       💝 #የመጨረሻ_ክፍል

"እሱን እንዳታስቢው ወይም ራስሽ ፈልገሽ አግኝው... ደግሞ አታገኝውም" አማራጭ የለኝም ሻንጣዬን ይዤ ወደኋላ ተመለስኩ።

"እሺ ውሰደኝ አሁን ውሰደኝ"

"አይ አይሆንም ነገ ነው የምንሄደው"  በእሽታ አንገቴን ነቀነኩለት።

ወደቀኝ ገልመጥ ብዬ ሳይ የሰርግ ቬሎዬ ተሰቅሏል። ለራሴ ወደኋላ የለም  አልኩ...

።።።።።። ።።።።። ።።  ።    ።።።።።

"አንደርስም እንዴ ደግሞ እኮ አይኔን በጨርቅ አስረህዋል። የት ነው የምንሄደው ራቀብኝ? ያ ውሻ የት ነው ያለው?"

"አይንሽን ከገለጥሽ ከኔ ጋ ትጣያለሽ ማርያምን የምሬን ነው። ታገሽ ትንሽ ነው የቀረን ደርሰናል" ጥቂት ደቂቃ ከተጓዘ በኋላ መኪናውን አቆመው

"አሁን ጨርቁን ማንሳት ትችያለሽ" ቶሎ ብዬ ፈታሁት... ሰው የሌለበት ቦታ ነው።

"ምንድነው ቢኒ እየቀለድክብኝ ነው" ፊቴን አዙሬ በንዴት አየሁት

"ውረጂ.,. ያውልሽ እዛጋ ይታይሻል...( በወዳደቁ ነገሮች የተሰራች ቤት) እዛ ውስጥ አለልሽ ውረጂና የፈለግሽውን አድርጊው" ሳላቅማማ ወረድኩ። በእልህና ንዴት እየተራመድኩ ወደቤቱ ተጠጋሁ ልገባ ስል

"እባቷ ነኝ ባሏ. ... ሀ ሀ ሀ... ንገሩኝ እስኪ እናቷን አግብቶ ልጁን ያስረገዘ አባት ታውቃላችሁ... አታውቁም? ሙትቻ ለምንድነው የምታፈጡብኝ...  መልሱልኝ... ኧረ ተውኝ ኡ ኡ ኡ..." ጩኸቱ አስደንግጦኝ ወደኋላ ተመለስኩ። ትንሽ ተራምጄ ቆምኩና ልጄን አሰብኳት "እገለዋለሁ" ወደ ቤቷ ተመለስኩና ከፍቼ ጎንበስ ብዬ ገባሁ። የቤቱ ጠረን ይገፈትራል ሰው የመጣም አልመሰለው ዝምም ብሎ ልፍለፋውን ቀጥሏል። የማላውቃቸውን ብዙ የሴት ስሞች ይጠራል... ያለቅሳል፣ ይስቃል፣ ይራገማል፣ ድንገት ደግሞ አስደንጋጭ ጩኸቱን ይለቀዋል። ለደቂቃዎች ዝምምም ብዬ ሰማሁት... በብዙው የቤቱ ቀዳዳ በሚገባ ብርሀን አየሁት ከድምፁ ውጪ ምኑም እሱን አይመስልም። ልብሱ ተቀዳዷል፣ ፊቱ ጠቁሮ ከሰል መስሏል፣ ፀጉሩ ተንጨባሯል፣ እላዩ ላይ ተፀዳድቶ መሬቱ ጭምር በሽንትና ሰገራ ተበክሏል። ዮኒ እኔ ልሰጠው ካሰብኩት ሞት በላይ በቁሙ ሞቷል... ልቤን ሽው የሚል የሀዘኔታ ጦር ወጋኝ። ወዲያው ደግሞ ልጄን የከዳኋት መሰለኝ... እየሮጥኩ ከቤቱ ወጣሁ... ልፍለፋው ከኋላዬ ይሰማኛል... እያለቀስኩ መኪናውን ከፍቼ ስገባ

"አደረግሺው ሩት ገደልሽው" አለኝ

"ሞቷል እኮ ቢኒ የሞተን ሰው ድጋሚ እንዴት እገለዋለሁ" ድፍት ብዬ ተንሰቀሰቅሁ

።።።።። ።።።።። ።።።።። ።።።።።

"ቢኒ እባክህ ምንም ሰላም ሊሰማኝ አልቻለም ዮኒን ሆስፒታል እንውሰደው" ደረቱ ላይ ተኝቼ ለቀናት ከራሴ ጋ ስከራከርበት የነበረውን ሀሳብ ነገርኩት

"እኔ የማውቃትም የምወዳትም ሩት ይቺ ናት ለጠላቷ ሳይቀር የምትራራ። አታስቢ የኔ ቆንጆ ዛሬውኑ እናደርገዋለን" እዛው ቦታ ተመልን ሄድን። ወደዛች ቤት ገባን አጠገቡ ዳቦ ቁጭ ብሏል። ለነፍሱ ያደረ ሰው እንደሚመግበው ገባኝ። መለፍለፉን አላቆመም እንጂ ተዳክሟል... ይዘናቸው የሄድነው ባለሞያዎች በግድ አንስተው ስትሬቸር ላይ አደረጉት... ከኪሱ የተጣጠፈ ወረቀት ወደቀ፤ ቀልጠፍ ብዬ አነሳሁትና ዞር ብዬ ከፈትኩት በትልቁ ርዕስ "ፀፀት" ይላል። ከስሩ ደግሞ "ለማታዩኝ እኔ ግን ብየቀኑ ለማያችሁ ለበደልኳችሁ ሁሉ" ይላል... ትርጉም ያለው ነገር ሊሆን ቢችልም ማንበብ አልፈለኩም... ሌላ ሸክም መሸከም አልፈልግም... እጄ ላይ ያለውን ሶስት ገፅ ወረቀት ቀዳድጄ ዱቄት አደረኩትና ለነፋስ ሰጠሁት ብትትንን... አምቡላንስ ውስጥ አስገብተው ይዘውት ሄዱ። ሰላም ተሰማኝ

።።።።። ።።።   ።።።።። ።።።።

አዳራሹ በእንግዶች ጢም ብሎ ተሞልቷል። ቃል የሚያገባቡን ቄስ ቦታቸውን ይዘው ተቀምጠዋል።

"በሀዘን በደስታዋ በህመም በጤናዋ..." ቢኒ ቃል ገባ እሱ ያለውን መልሰው እኔንም አስባሉኝ።

የጋብቻ ቀለበት ጣቴ ላይ አደረገልኝ እኔም እንደዛው አደረኩለት.....
ገና ወደሰውነት ቅርፅ ያልተቀየረው የአምስት ሳምንት ልጄ ደስ ብሏት/ብሎት ይሆን ሆዴን ዳበስኩት። የልጄ አባት ቢኒ ፈገግ ብሎ አየኝ

"ተመስገን" አልኩ በልቤ የማያልፉ የመሰሉኝ ሁሉ አለፉ... ዛሬ ደስተኛ ነኝ... ነገን አምላክ ያውቃል።


ተ ፈ ፀ መ ።

በፅሁፉ ላይ ያላችሁን ማንኛውንም አስተያየት @R2ebi ላይ አድርሱኝ። ፅሁፉን እያዘገየሁ ላበሳችጨኋችሁ ከጉልበቴ በርከክ ከወገቤ ሸብርክ ብዬ ይቅርታ እጠይቃለሁ 💔 🙏🙏🙏 በሌላ ፅሁፍ እስከምንገናኝ ቻው

ፅሁፉን ከወደዳችሁት ለምትወዱት #share አድርጉ ያልተነበቡ ታሪኮችን ለማንበብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ

@yefeker_tiksoche
ነፍ ደስታ
የበዛ ፍቅር ለእናንተ😘😘😘

ከወደዳችሁት ❤️

✳️በሌላ ተከታታይ ታሪክ በቅርቡ በአሪፉ አቀራረብ እንመለሳለን 🙏
🌹ሰላም ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች አዲስ ታሪክ ይጀመር ❤️ወይስ አጠር ያሉ የፍቅር ግጥሞች እንልቀቅ👍ሃሳባችሁን comment ላይ አስቀምጡኝ
2024/09/21 05:40:49
Back to Top
HTML Embed Code: