Telegram Web Link
:¨·.·¨:
                ያሜናዳብ
         ┈┈••◉❖◉●••┈🌺

               💢ክፍል 9

💢እውነትኛ የፍቅር ታሪክ💢
ልቤ የሆነ ስሜት ሲሰማኝ ይታወቀኛል ሁሉም ዝም አለ አይንሽን ግለጪ ስትለኝ ቀስ ብዬ አይኔን ስገልጠው ባለፈው ያስተዋወቁኝ ልጅ ፊቴ ላይ ተደቅኗል ነገሩ ግራ ገባኝ ትዙ ወድጄሻለሁ እባክሽን አብረን እንሁን አለኝ አንቺም በብቸኝነት ነው ያለሽው እኔም እንዳንቺው አለኝ በጥፊ ብለው ደስ ባለኝ ነበር እንደ ምንም ራሴን አረጋግቼ እኔ እኮ የራሴ የምወደው እና የማፈቅረው ሰው አለ በዛ ላይ እኔ እና አንተ የተዋወቅ ነው ትናት ነው አልኩት ምንም አለለኝም እንደዛም እያወራሁት
አፍንጫዬን ያወደኝ ጠረን አሁንም አፍንጫዬ ላይ ነው በዚ መሀል የሙዚቃውን ድምፅ ከፍ አደረጉት ሁሉም በየ ራሱ ጥሩ ሙድ ላይ ነው ኤልሲ ከውጭ ስልክ ስታወራ ቆይታ ወደ
ውጭ እንድወጣ በእጇ ምልክት ጠራችኝ
ስሄድ አናግሪው ይፈልግሻል አለችኝ ማነው ልላት ስል ስልኩን ሰጣኝ ዘላ ገባች ደጋግሜ ሄሎ ስል ዝም ነው መልስ የለም ተናድጄ ስልኩን ልዘጋ ስል ትዙ አለኝ ጆን ነው እጄ ስልኩን ለመያዝ ከበደው ማውራው ጠፋኝ ደህና ነሽ ግን አለኝ ምን አድርጌ ነው ግን አልኩት
ጫጫት ነገር አለ እስቲ ትንሽ ተንቀሳቀሺ አለኝ ሩጬ ክላሴ ገባሁ እንኳን ተወለድሽልን አለ በቃ የእውነት ለመናገር ከምንም በላይ ደስ አለኝ እንባዬ ይፈሳል የተወሰነ አወራሁትና ማታ እደውልልሻለሁ ወደ ፕሮግራምሽ ተመለሺ አለኝ ደስታው እጥፍ ሆነልኝ በቃ ጆንን ካገኘሁ በኋላ ያዩኝ ራሱ ምን አገኘሽ እስኪሉኝ ደስ አለኝ
ቀኑን ደስ በሚል ሁኔታ አሳለፍን ግን ሚገርመ ው ቀን ላይ አፍንጫዬን ያወደው መአዛ አስካሁን አልተረሳኝም ማታ ለይ ጆን ደውሎልኝ ብዙ አወራን በቃ የልደቴን ቀን ተከፋሁ ብዬ ነበር ግን ጭራሽ ተስምቶኝ የማያውቅ አይነት ስሜት ተሰማኝ ልደቴን በዚም በዚያም ብዬ አሳለፍኩ ለጆን ግን ከዛን ቀን በኋላ በተደጋጋሚ ብደውልለት ስልኩ አይሰራም በቃ ከአይኔ ከተለየ አርባ አምስት ቀን ሞላው እኔ ግን ለሰከንድ ከውስጤ አላወጣሁትም ብቻ ቀናት ተቆጠሩ እኔም በመሀል ሁሉም ነገር
አስጠላኝ በቃ አምላኬን አማረርኩ ምን ብበድል ነው ብዬ አለቀስኩ ሁሉም ነገር ግራ ገባኝ ሰው የወደዱት ከአይን በራቀ ቁጥር ይረሳል ይባላል ታድያ ምነው የኔ በረታብኝ ተቃራኒ ሆነብኝ እቤት ማንንም ማውራት አስጠላኝ ልክ ጆን ጋር በተለያየን ሁለተኛ ወሩ በቃ ቀኑ ትዝ ሲለኝ እንደ ማበድ አደረገኝ ጥዋት ላይ ክለሴን ዘግቼ ማንም እንዳይጠይቀኝ ብዬ ተኛሁ ቢቆፍ ቁፍ ቢለምኑኝ አልሰማ አልኩ እንባዬ እስኪ ደርቅ አለቀስኩ ቀኑን ሙሉ ክላሴን ዘግቼ ወደ ማታ ላይ አክስቴ በቃ አለቀሰችብኝ አትልፊ ሂጂ አልኳት ልክ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ላይ ከቀኑ በተለየ በሩ ተንኳኳ ዝም አልኩ አሁንም ተንኳኳ ዝም አልኩ እረ ትዙ ምንሼ ነው አለኝ የጆን ድምፅ ነው በመብረቅ የተመታሁ
መሰለኝ በቃ ለመናገርም ከበደኝ እንደዛ ተኝቼ የዋልኩትን ከአልጋዬ ላይ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ቀስ ብዬ በሩን ስከፍተው ጆን ከፊቴ ላይ ቁሟል ዘልዬ ተጠመጠምኩበት በቃ በጣም ደስ አለኝ ደረቱ ላይ ማስቲሽ ሆንኩበት በይ ልብስ ቀይሪና እራት ልጋብዝሽ አለኝ ብቻ ደነግጫለሁ እሺ ብዬ እስክ ቀይር በጓሮ እናቴ ዘንድ ሂዶ እግሯ ስር ቁጭ ብሎ
ያወራል በቃ እሱ ካለ ግቢው ሰላም አለው ተያይዘን ወጣን በጣም ነበር ደስ ያለኝ እራት ጋብዞኝ ትንሽ መጠጥ ነገር ጠጥቼ ለው ብያለሁ በተላይ ስጠጣ ሁሌም ይስቅብኛል ምናለ የሱን ሳቅ
ለማየት ስል ሁሌም በሰከርኩ እላለሁ በውስጤ ልክ ወደ አራት ሰአት አከባቢ ተመለስን ጆን ሰላም እደሪ ብሎ ወደ ክፍሉ ገባ እኔ ግን ንፋስ እንዲ ልቀበል ብዬ በረንዳ ላይ ቁጭ አልኩ ሰአቱ እየሄደ ነው ልክ ሳስነጥስ ጆን ወጣ ምነው ምን ሆንሽ ብሎ ወደ እኔ መጣ አጠገቤ ቁጭ አለ እረ ተነሽና ግቢ አለኝ መልስ አልሰጠሁትም ብቻ በስስት አይኑን ነው የማየው አንቺን እኮ ነው ምልሽ አለኝ ፈገግ ብዬ ሳመኝና ልግባ አልኩት እረ ድፍረት ሚስቴ እንዳሰማሽ አለኝ ቆሌዬን ሳይሆን ቆዳዬን ነው ግፍፍ ያለ ምን ማለት ፈልጎ ነው እንዴ እኔስ አልኩ
በልቤ ማወራው ጠፋኝ ምነው ደነገጥሽ አለኝ.....


✎ ክፍል አስር(10) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
:¨·.·¨:
                ያሜናዳብ
         ┈┈••◉❖◉●••┈🌺

               💢ክፍል 10

💢እውነትኛ የፍቅር ታሪክ💢

ምን ማለት ፈልጎ ነው እንዴ እኔስ አልኩ
በልቤ ማወራው ጠፋኝ ምነው ደነገጥሽ አለኝ ልክ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ላይ ከቀኑ በተለየ በሩ ተንኳኳ ዝም አልኩ አሁንም ተንኳኳ ዝም አልኩ እረ ትዙ ምንሼ ነው አለኝ የጆን ድምፅ ነው በመብረቅ የተመታሁ መሰለኝ በቃ ለመናገርም ከበደኝ
በልቤ ማወራው ጠፋኝ ምነው ደነገጥሽ አለኝ ራሴን አለመሳቴም እኔ ሁኜ ስለው ስቆ ስቀልድሽ ነው ብሎ ግንባሬን ሳመኝና ከተቀመጥኩበት አስነሳኝና ወደ ቤት
አስገባኝ እኔም ልቤ ቅር እያለኝ ገባሁ ግን በቃ ማታውን አልተኛሁም ሚስቴ ያለው ነገር ሲከነክነኝ አደረ ወደ ጥዋት አከባቢ እንቅልፍ ጣለኝ ወደ አምስት ሰአት ላይ ተነሳሁ ልክ እንደ ነቃው ወደ ጆን ክላስ ነበር የሄድኩ ግን ዝግ ነው ቅር አለኝ አክስቴ ካኋላ እያየችኝ ነበር ሳቀችብኝ ፎንቃ ይሉሻል ይሄን ነው አለች እየሳቀችብኝ እኔም ሳቄ አመለጠኝ ቀን ላይ ደውዬለት ትንሽ ስራ ይዤ ነው እንደ ጨረስኩ እመጣለሁ አለኝ እኔም ቀኑን ሙሉ ስጠብቀው ዋልኩ ማታ ላይ እቤት እራት አብረን በላን ልክ በዚህ መሀል ከሳምንት በኋላ ነገ አንድ ማስተዋውቅሽ ሰው አለ አለኝ ደስ ይለኛል አልኩ ነገውን ልክ ወደ ማታ አከባቢ ደውሎ ግራንድ ሚባል ሆቴል ጠራኝ እኔም ለባብሼ ሄድኩ ሆቴሉ እንደ ደረስኩ እንግዳ ማረፍያ ክፍል ውስጥ ሁኜ ደወልኩለት እንደ መጣ ይዞኝ ወደ ላይ ወጣ ቦታው በጣም የሚያምር ግራፊክስ አለው የሆነች ልጅ ጀርባዋን ሰጣ ተቀምጣለች ልዩ አላት ወዬ ብላ ዞር አለች እረ በፈጣሪ አልኩ በልቤ ደነገጥኩ በጣም ቆንጆ ልጅ ናት ይሄ ነገር እንዴት ነው አልኩ በልቤ
የዘር ነው ወይስ ተፈላልገው ነው የተገናኙ አልኩ ትዙ ያልኩሸ እሷ ነው ሲላት የምርህን ነው ብላ ተነስታ ሳመችኝ እኔም ውስጤ ትንሽ ደስ አለኝ ሁሌም የማያውቁን ሰዋች ስለ እኛ በተነገራቸው መጠን ነው በህሊናቸው ሊስሉን የሚችሉት ጫዋታዋ ደስ ይላል ልክ እንደ
ስሟ ልጅቱም ልዩ ናት ከሰአታት በኋላ እራት በልተን ጆን ወደ መታጠብያ ክፍል ሲሄድ እንድ ጓደኛዋ መጣች አንቺ እንቅልፋም ተነሳሽ አለቻት ሰላም ብላኝ ቁጭ አለች ከእንቅልፏ እንደ ተነሳች ያስታውቅባታል ፍቅር የት ሄደ አለች አለ ይመጣል አለቻት ግራ ገባኝ ማንን ነው
ፍቅር ብላ የጠራችው እልኩ በውስጤ ጆን እንደ መጣ ፍቅር አለችው ቲቲ ተነሳሽ አላት እናቴ ድረሽ አልኩ እንዴት እንደዛ ብላ ትጠራዋለች ፍቅረኛዋ ቢሆን እንጂ ብዬ በቃ ተረበሽኩ ስልኬ ሚሴጅ
ሲገባልኝ አይቼ ከወንበሩ ላይ አነሳሁት እረ አትናደጂ ትዙሻ ይላል ጆን ነው ቀና ብዬ ሳያው ጠቀሰኝ በቅፅበት ያሁሉ ንዴቴ ጠፋ ሰዓቱ እየመሸ ስሄድ ጆን እኛ እንሂድ ሲል.....

✎ ክፍል አስራ አንድ(11) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
:¨·.·¨:
                ያሜናዳብ
         ┈┈••◉❖◉●••┈🌺

               💢ክፍል 11

💢እውነትኛ የፍቅር ታሪክ💢

     ሊያልቅ 4⃣ ክፍሎች ብቻ ቀርተዋል #ሼር በማድረግ ለሌሎችም አጋሩ 💗


ስልኬ ሚሴጅ ሲገባልኝ አይቼ ከወንበሩ ላይ አነሳሁት እረ አትናደጂ ትዙሻ ይላል ጆን ነው ቀና ብዬ ሳያው ጠቀሰኝ በቅፅበት ያሁሉ ንዴቴ ጠፋ ሰአቱ እየመሸ ስሄድ ጆን እኛ እንሂድ ሲል እንዴ ፍቅር ጥለክን ልትሄድ አለች ቅብጠቷ ቅጥ
የለውም ምን ትመስላለች ሞልቃቃ አልኩ በልቤ ልዩ በቃ ሂዱ ስትል ልንሄድ ስንነሳ ቆንጂዬ አደራ ፍቅርን አለችኝ አታስቢ አልኩ ጥርሴ ነክሼ ግን ለጆን ጓደኞቹ ይሁኑ ምኑ ይሁኑ ማውቀው ነገር የለኝም እሱም አልነገረኝም ግን በቃ ጆንን ከሆቴሉ ይዤው ስወጣ በቃ ከነጣቂዋች እጅ አውጥቼው ጉያዬ ውስጥ ያስገባሁ
መሰለኝ ጆን መንገድ ላይ ትንሽ ለው ላድርገሽ ብሎኝ ወደ ባህል ምሽት ቤት ጎራ አልን የተወሰነ ተጫወትን እየመሸ ስለ ሆነ ብዙም አልቆየንም ልክ እቤት እንደ ደረስን አክስቴ እና እናቴ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሏል እናቴ ስታየን ፈገግ አለች በቃ እኔ ጆን ጋር ስላለኝ ቀረቤታ ደስተኛ ናት አክስቴ ጠቀሰችኝ ፈገግ አልኩ
የእውነት ለመናገር በረንዳ ላይ ባይቀመጡ ደስተኛ ነበርኩ እንደ ሚስመኝ እርግጠኛ ነበርኩ ብቻ አመለጠኝ አልኩ በልቤ ግን ያቺ የልዩ ጓደኛ ፍቅር ብላ ስለጠራችው ውስጤን ከነከነኝ በዚህ እንዳለ ሰፈር ላይ በጆን ታማሁኝ መቼም ቢሆን በሚወዱት ሰው መታማትን የመሰለ ነገር የለም እሁድ ቀን ላይ ወደ ጢስ አባይ ጆን ጋር ልንዝናና ሄድነ ብዙ አዋራን በቃ ሰላሳለፋቸው ፈተናዋች ሲነግረኝ እንባዬን እንዴት ልቻለው እሱ ያሳለፈውን ህይወት እኔ
ለመስማት ከበደኝ ወንድሙ ጋር እንደ ታረቀ ሲነግረኝ ግን ከምንም በላይ ደስ አለኝ ወደ ኢትዮጲያ የመጣበትን ጉዳይ እንደጨረሰ ሲነግረኝ ልቤ ተረበሸ ፍረሀት ፍረሀት አለኝ ባይነግረኝ አልኩ ግን ትዙ ባለፎው ልዩ ጋር ሳስተዋውቅሽ ጥሩ ስሜት እንዳልተሰማሽ አውቂያለሁ ይቅርታ ግን አንድ ያልነገርኩሽ ነገር አለ ሲለኝ ተቀምጬ እንኳ ጉልበት አጣሁ
በቃ ደንዝዣለሁ ምን መሰለሽ ትዙ ልዩ እኮ ለእኔ እህቴ እኮናት ሲለኝ በቃ ደስታዬ ወደር አጣ እሺ ቲቲ ያልካትስ ስለው እሷም እህቴ ናት ልዩ ጋር የእንድ አባት የአንድ እናት ነን ቲቲ ጋር በአባት ብቻ ነው ምንገናኘው ሲለኝ ተመስገን አልኩ በልቤ በቃ የዛን ቀን ደስታዬ ወደር የለውም ከሳምንት በኋላ ፌቨን ከሀዋሳ መጣ አየኋት በጣም ነበር ደስ ያለኝ በቃ እቤት አብረን ሂደን ብዙ አዋራን ጆን ሚኪ ጋር እንዳስታረቃቸው ነገረችኝ ከምንም በላይ ደስ አለኝ እስቲ ንገሪኝ ጆን ፍቅረኛሽ ነው አለችኝ ደነገጥኩ ምን እንደ ነካኝ ባላውቅም እረ አይደለም ኖርማል ጓደኛዬ ነው አልኳት ነው እንዴ ፍቅረኛሽ መስሎኝ ነው አለች በራሴ በጣም ተናደድኩ በጆን አፍሬ ወይስ በራሴ አፍሬ ነው አይደለም
ብዬ የተናገርኩት እያልኩ ራሴን ወቀስኩ እሁድ ቀን ከኤልሲ ጋር ከጓደኞቻችን ጋር ውለን ወደ ቤት እየተመለስን እያለ ጆን ደወለልኝ ሳነሳው ወደ ጎን ተመልከቺ አለኝ ዞር ስል ወንድሙ ጋር ካፌ ላይ ቁጭ
ብሏል ሻይ ቡና ብሎ ጠራን ቅድሙንም ናፍቆኝ ነበር ሄድን የእውነት ለመናገር የእናት ሆድ ዝንጉርጉር ሚባለው በጆንና በወንድሙ ላይ በሚገባ ሰርቷል እንኳን ወንድማማች ሊመስሉ ሆድና ጀርባ እንኳ አይሆኑም በፊትም የጆንን ወንድም ፌቨን ጋር እያሉ ድንገት ሳየው ማነው ግን ውቃቤውን የገፈፈው እላለሁ ቢነኩት እጅ ላይ ሰበብ ሚሆን ነው ሚመስለው ጀን
ትክሻዬን ነካ ሲያደርገኝ ከሀሳቤ አነቃኝ በሁለተኛው ቀን ጥዋት ላይ ጆን አ/አ ደረሰን እንምጣ አለኝ ትንሽ ልቤ ደነገጠ እሺ እመዬ ትምጣ እና ልንገራት አልኩት ሳቅ አለና እሺ አለ እናቴ ከደጀ ሰላም እንደመጣች ስነግራት......

✎ ክፍል አስራ ሁለት(12) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
   ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
    
:¨·.·¨:
                ያሜናዳብ
         ┈┈••◉❖◉●••┈🌺

               💢ክፍል 12

💢እውነትኛ የፍቅር ታሪክ💢


እሺ እመዬ ትምጣ እና ልንገራት አልኩት ሳቅ አለና እሺ አለ እናቴ ከደጀ ሰላም እንደመጣች ስነግራት አዋ ነግሮኛል ሂዱ አለች ምን ግዜ ነገረሽ አልኳት ማታ ላይ ነግሮኝ ነበር ልነግርሽ ነበር ተኝተሻል አለችኝ እናቴ ጆን ላይ የጣለችው እምነት
ይሄ ነው ለማለት ይቸግረኛል ከምንም በላይ ታምነዋለች ስድስት ሰዓት እንደ ሆነ ባህር ዳር ኤርፖርት ደረሰን ሰላሳ ደቂቃ አላቹ ሲባል ቁጭ አልን አንድ ያልተመለሰልኝ ነገር ቢኖር በቃ የሆነ ነገር ለማድረግ ደቂቃ አይፈጅ በትም ምንም ነገር ሲያደርግ ለማንም አይናገርም
አድርጎት ወይም ፍፅሞት ነው ማገኘው ማያደርገውን ይቅርና የሚያደርገውን እንኳ መናገር አይፈልግም ከደቂቃዋች በኋላ በረራ አደረግን ልክ ከአርባ ዲቂቃ በኋላ አ/አ ደረስን ምሳ በልተን ወደ ዘጠኝ ሰአት አከባቢ ላይ ወደ አሜርካ ኢንባሲ ሄድነ በቃ ኢንባሲውን ሳየው ትዝ አለኝ ለአመታት አሜርካ ለመሄድ ስል ከጣልያን እስከ ሱዳን ድረስ የሄድኩት ስንት ብሬን
የጨፈጨፍኩበት ፊቴ ላይ ድቅን አለ ግን ጆን ለምን መጣን አልኩት ሳቀብኝ ምትፈርሚው ነገር አለ አለኝ ምን አልኩ በቃ ውስጤ ይሄ ነው ከሚባለው በላይ ደንግጫለሁ ልክ እንደ ገባን ፎቶ አነሱኝ በተላያየ ቦታ አስፈረሙኝ ሜድካል ተብሎ ወደ ምርመራ ክፍል ሄድኩ ብቻ ምን ያላረጉኝ ነገር አለ ለምን እንደ ሆነ አላውቅም ብቻ ጆን ከአጠገቤ ስላል ተለየ ምንም ፍረሀት አልተሰማኝም ውስጤ ከመደንገጥ በስተቀር ልክ እንደ ጨረስን ቁጭ ብለን እያለ አንዱ መጣና ጆን በቃ ሂዱ ያለውን ነገር አሳውቅሀለው ሲለው እሺ ብሎ ወጣን አ/አ ውስጥ እየዞርን አመሸን ጆን ጋር አንድ ክፍል ውስጥ እንደ ምናድር ሳስበው ደስ አለኝ

ሀርሞኒ ሆቴል ሩም ይዘናል አለኝ እህ መቼ ስለው ኦንላይን ኢንተርኔት ላይ ነዋ አለ እየሳቀ አንቺ ከዚህ ነገር ነፃ ነሻ አለ እያፌዘብኝ እንኳን ሆንኩ አልኩት ሰአቱ እየመሸ ሲሄድ ወደ ሆቴሉ ሄድነ ደብል አልጋ ነበር የያዘው እራት ሰዓት እስኪ ደርስ ሻወር ወስደኩ ምናምን ልክ ራታችንን በልተን እንደ ጨርሰን ሩም ገባን
ትንሽ ሚጠጣ ነገር ቀምሼ ስለ ነበረ ወሰወሰኝ ጆንን የቅድሙ መጠጥ አማረኛ አልኩት አረ አንቺ ልጅ እያለ ሩም ድረስ አስመጣ በቃ ማታ ምን እንደ ተፈጠረ አላውቅም ጥዋት ስነሳ ከጆን ደረት ላይ ተለጥፌ ተኝቻለሁ በቃ በድንጋጤ ውሀ ሆንኩ በቃ ምን እንደ ተከሰተ ማወቅ አልቻልኩም ራሴን በጣም አሞኛል የሞት ሞቴን ከደረቱ ላይ እንደምንም ብዬ ተነሳሁ በጣም ራሴን ይዞኛል እንደ ምንም ብዬ ቀና ለማለት ሞከርኩ ልብሴ አልወለቀም የጆን ልብስም አልወለቀም ታድያ እንዴት እሱ ጋር ልተኛ ቻልኩ ብዬ በጣም ነበር ግራ የገባኝ ነገሩ ግርምት ፈጥሮብኛል ማታ በጣም የጠጣሁ መሰለኝ ራሴን በጣም አሞኛል ስንቀሳቀስ ጆን ነቃ አንቺ ሰከራም አለኝ ምንድ ነው የሆንኩት አልኩኝ ለካስ እንደዚህ ሰከራም ነሽ አለኝ አፈርኩኝ እየሳቀብኝ ተነስቶ ሻወር ገባ በጣም ስላመመኝ ሻወር መግባት አልፈለኩም እስኪ መጣ ልብሴን ቀያየርኩ ልክ ሲመጣ አይኔ ደረቱ ላይ አረፈ ይሄ ደረት ላይ ተኝቼ ነዋ የሆንኩትን ሁሉ የረሳው አልኩ በልቤ እረ አይንሽን ንቀይ አለኝ ባክህ ዝምበል የግልህ አደረከውሳ አልኩት ሳቄን አያፈንኩት በለው ማነው የልብ ልብ የሰጠሽ አለኝ እእ አንድ ጢባራም አለ አንድቀን አስተዋውቅሀለው አልኩት እየሳቀብኝ ከሆቴሉ አቅፎኝ ወጣ ልክ ባ/ዳር ገብተን ወደ ሰፈር እየሄድን እያለ የጀን
ወንድም ክላክስ አደረገ ጆን ወንድሙን ሲያየው ፈገግ አለ ከመኪና ወጦ መጣና ጆን እግር ስር ተደፋ...........

✎ ክፍል አስራ ሶስት(13) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
​​ :¨·.·¨:
                ያሜናዳብ
         ┈┈••◉❖◉●••┈🌺

          💢ክፍል 1⃣3⃣

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ


ወደ ሰፈር እየሄድን እያለ የጀን ወንድም ክላክስ አደረገ ጆን ወንድሙን ሲያየው ፈገግ አለ ከመኪና ወጦ መጣና ጆን እግር ስር ተደፋ እኔ ደነገጥኩ ጆን ምንም አልመሰለውም ከፈ አደረገውና ተቃቀፉ ወንድሙ እንባውን እንዴት ይቻለው ግራ ብጋባም ምንም አላልኩም እቤት ድረስ አደረሰን ጆን በኋላ እደውልልሀለው ሲለው እኔ ራሴ እመጣለው ብሎት ተለያየን በጣም አሞኝ ስለነበር ተኛሁ ልክ ከዛን ቀን በኋላ ለሁለት ሳምንት ያህል እንደ ቱሪስት ጆን ጋር ዞርን ያልሄድንበት ሀገር የለም እናቴ የማትመክረኝ ምክር የለም ነገሩ ግራ ገብቶኛል በቃ ህይወቴን ከአሁን በኋላ እንዴት መምራት እንዳለብኝ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ከአሁን በኋላ ህፃንነት እንደሌለ ህይወትን ራሴ መኖር እንደምችል አስቀምጣ ነገረችኝ ምን እንደ ሆነ ባላውቅም ውስጤ ፍረሀት ፍረሀት
ብሎኛል እናቴ በህይወቷ አቋም የሌለው አንዱን ሚጥል እንዱን ሚያነሳ ሰው አትወድም እኔ ደግሞ የእሳት ልጅ አመድ እንደሚባለው ሁሉም ነገር አይናዋጅ ይሆንብኛል ቢሆንም ግን እስከዛሬ ከኖርኩት በላይ ጆንን ካገኘው በኋላ ውስጤ ላይ ያለው ደስታ ልዩ ነው በዚህ
መሀል ጆን ወደ አ/አ ልሄድ ነው አለኝ ደነገጥኩ አሁንም ሊጠፋብኝ ነው አልኩ እንባዬ መጣ ይሄውልሽ ትዙ በአንድ ሳምንት ውስጥ ጓደኞችሽን ተሰናበቺ ሲለኝ በጣም ደነገጥኩ ምይዘውን አጣሁ ወዴት ለመሄድ አልኩት እሱን ስትደርሺ ታውቂዋለሽ አለኝ በቃ ደስታዬን አልቻልኩም ሁሉም ነገር ከአቅሜ በላይ ሆነ እሱም ወደ አ/አ ሊሄድ ብሎ ቦርሳውን ሲያወጣው እንደ ማይመለስ አወኩ አንዳለ ቤት ውስጥ ያለውን ዕቃ እናቴን እንደ ነገርኩሽ አድርጊው አላት እሷም እሺ አለችው ልክ ሊወጣ ሲል አክስቴ ቡና ደርሷል ጆን ግባ አላችው ቦርሳውን በረንዳ ላይ አድርጎ ገባ እኔ እስካሁን ምንም አልተናገርኩትም ግራ
ተገብቻለሁ ወደ ቤት ሲገባ ተከትዬው ገባሁ ከምንም በላይ ሀሳብ የሆነኝ አይኑን ሳላየው እንዴት አድርጌ ሳምንት እቆያለሁ የሚለው ነገር ነው የያዘኝ ጆን ልክ አንድ ቡና እንደ ጠጣ ሹፌሩ ደርሻለሁ አፍጥነው ሰዓት እያለፈ ነው አለው ቶሎ ወጣ እኔም ልሸኝህ ብዬ
አብሬው ወጣሁ በቃ እንባዬ እየተናነቀኝ ነው ትዙ አለቃስላው ብትይ የእውነት
አቀይምሻለሁ አለኝ እኔም እኮ ትናፍቂኛለሽ አንቺ ብቻ አደለሽም ለእኔ ምታስቢው እኔም እኔም እነዳንቺው ለስሜትሽ እጨነቃለሁ አለኝ በቃ ይሄን ከእሱ በመስማቴ ብቻ ደስ አለኝ
በዚህ መሀል ጆን ከሄደ በኋላ ማስተካከል ያለብኝን ሁሉ አስተካከልኩ ጆን በየደቂቃው ይናፍቀኛል ሚገርመው እንደዛ በቀን ስንቴ እየደወልኩ አስለቸውት ይሆን እላለሁ ግን ከእኔ ብሶ አረፈ እኔ ጋር ያለ እስኪመስለኝ ድረስ ሙሉ ጓደኛቼን ተሰናበትኳቸው ብዙም ወከባ ስለ ማልወድ ባሉበት ሂጄ አዲስ አበባ ለተወሰነ ግዜ እቆያለሁ አልኳቸው ለኤልሲ ብቻ ነው እውነቱን የነገርኳት የእውነት ለመናገር ወዴት እንደ ምሄድ አላውቅም ልክ በሳምንቱ ጆን ወደ አ/አ ነይ አለኝ እናቴን ለመጀርመርያ ግዜ ስለያት ልቤ ተረበሸ ግን..........

✎ ክፍል አስራ አራት(14) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
​​​​           
             :¨·.·¨:
              ያሜናዳብ ♥️
         ┈┈••◉❖◉●••┈🌺

               💢ክፍል 14

እውነትኛ የፍቅር ታሪክ🌹


ልክ በሳምንቱ ጆን ወደ አ/አ ነይ አለኝ እናቴን ለመጀርመርያ ግዜ ስለያት ልቤ ተረበሸ ግን ህይወት መቼስ እንደ ፈለጉት አይኖር አ/አ ስገባ ጆን ተቀበለኝ ሳየው በቃ ነፍሴን ያገኘውት ያህል ነበር ደስ ያለኝ ውበቱ ለጉድ ነው በጣም አምሮበታል አቅፎ ሰላም አለኝና ሻንጣዬን መኪና ውስጥ ከተተልኝ መኪና ውስጥ እንደ ገባን ሹፌሩ ሰላም አለኝ ሳየው ከዚህ በፊት ከሀዋሳ ስንመጣ የተቀበለን ሹፌር ነው ሰላም አልኩት ካፒታል ሆቴል ነበር ክላስ የያዘው እኔ የገረመኝ እና ጥያቄ የፈጠረብኝ ነገር ጆንን እስካየሁት ድረስ ትላልቅ ሆቴል ነው ለማረፍም ለመመገብም የሚይዘው ታድያ እንዴት እኛ ቤት ዶርም ሊይዝ ቻለ ብዬ በተደጋጋሚ ራሴን እጠይቃለሁ በዚህ መሀል ከሁለት ቀን በኋላ ዛሬ በረራ ታደርጊያለሽ አንቺ ሲለኝ ደነዘዝኩ በጣም ግራ ተጋባሁ ወዴት ነው ብቻዬን የምሄድ አልኩት ወደ ምትፈልጊበት ነዋ አለኝ ጀን አትቀልድ አልኩኝ እየሳቀ ባክሽ አብረን ነው ምን ሄድ እንዴት ብቻሽን እለቅሻለሁ አለኝ ተመስገን አምላኬ አልኩኝ ሁሉም ነገር ከአቅሜ ባለይ ሁኖብኛል ጆን ያደርገልኝን ሳስብ ለመናገር አቅም ያንሰኛል በቃ ጆን ማለት ለእኔ ሁሉ ነገሬ ነው ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ቦሌ ዓለምአቀፍ ኤርፖርት ሄድን ውስጤ ምን እንደ ሆነ ባላውቅ በፍረሀት ተንዘፍዝፏል ልክ ወደ ፍተሻ እስክን ደርስ ምንም የማውቀው ነገር የለም ፖስፖርቴን እና ቪዛዬን የያዘው ጆን ነው ልክ Backgroundu ላይ ሳየው ወደ አሜርካ መሆኑን አወኩ በድንጋጤ ውሀ ሆንኩ
ፍተሻው ላይ ፖስፖርቴን ሰጠኝ ጆን አልኩኝ ደንግጬ ትዙ አለኝ መልሶ እዛው ላይ ተጠመጠምኩበት ያቀን ለእኔ ከምንም በላይ ነበረ በልቤ ደስታዬን እንደበዛከው ፈጣሪ ደስታህን ያብዛልህ ጆን አልኩኝ ብቻ ሁሌም በሱ ደስተኛ ነኝ በዚህ መሀል ስንት ነገር አልፌ texas ገባሁ እድሜ ልኬን አልሜ ያልተሳካልኝን ጆን ህልሜን አሳካልኝ በቃ ሁሉም ነገር ብርቅ ሁኖብኛል ከምንም በላይ የገረመኝ ግን ጆን የሚኖርበት ቤት ነው አሜርካ ላይ እንደዚህ አይነት ቤት ውስጥ የሚኖር ልጅ ሳይቸግረው እንዴት እኛ ዘንድ ዶርም ሊይዝ ቻለ ብዬ በጣም ጥያቄ ፈጠረብኝ አሁን በዚህ ሰዓት ከእኔ በላይ ደስተኛ የለም በርግጥ አይደለም የሚፈልጉት ሰው ጋር በአንድ ቦታ መኖር ይቅርና ቀጣይ ህይወታችን የምንወደው ሰው ጋር እንደ ምናሳልፍ ስናውቅ ራሱ በተሰፋ
እንሞላለን በዚህ መሀል ጆን አዲስ ሲምካርድ ና ሞባይል ሰጠኝ አመስግኜ ተቀበልኩ ቶሎ የደወልኩ ለእናቴ ነበረ ድመጿን ስሰማ በጣም ደስ አለኝ ዛሬ ብሞት አይቆጨኝም አለችኝ ሁሌም ምኞቴ አንቺ የምትፈልጊውን ነገር ላደርግልሽ ነው ልጄ ዛሬ ይሄው የፈጣሪ ፍቃድ ሆነና ተሰካልሽ አለችኝ እናቴ ምንም ከሀገር እንድወጣ ከአይኗ እንዳልርቅ ብትፈልግም ፍላጎቴ ስለ ሆነ ብቻ መቃወም አልፈለገችኝም እናቴን አውርቼ እንደ ጨረስኩ አክስቴ ስልኩን ተቀብላ እንዳትዘጊው አለችኝ ቆይኝ እዳሪ ልውጣ ብላ እንደ ልማዷ እዳሪ ወጣች ማንም ይሁን ሰው ጋር ተቀምጣ ስልክ ማውራት አትወድም አክስቴ ጋረም ብዙ አዋራን በደቂቃዋች ውስጥ የሰጠችኝ ምክር ለነገሮች ቦታ እንድሰጥ አድርጎኛል በዚህ መሀል የጆን አህት ልዩ ስታየኝ ጨወች በጣም ነበረ ደስ ያላት አቅፋ አለቀኝ አለች ወይኔ አምላኬ አውቀህ መስሎኝ ነበር እኮ አለችው ጆንን በዚህ መሀል ግን ያልጠበኩትን ነገር…


✎ ክፍል አስራ አምስት (15) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
:¨·.·¨:
                ያሜናዳብ
         ┈┈••◉❖◉●••┈🌺

               💢ክፍል 15

💢እውነትኛ የፍቅር ታሪክ💢

🔚የመጨረሻው ክፍል 🔚

በዚህ መሀል ግን ያልጠበኩትን ነገር አየሁ ፌቨን ከጓደኛዋ ጋር ፊቴ ላይ ቁማለች
ደነገጥኩ እንዴት ሊሆን ቻለ አልኩ በቃ ደስታዬ ወደር አጣ የምወዳት ጓደኛዬ ፊቴ ላይ
ሳገኛት ሁሉም ነገር የተሳካልኝ መሰለኝ ዘልዬ ተጠመጠምኩባት በዚህ መሀል ጆን ት/ት
እንድማር አደረገኝ ሁሌም ጆንን ከአይኔ ተለይቶ እስካየው እጓጓለሁ አንድ ቀን በዚህ እንዳለ
ፌቨን ጋር ቁጭ ብለን እያወራን ሁሉንም ነገር ትነግረኝ ጀመር እኔ አፌን ከፍቼ ቀረሁ ጆን
ከወንድም ጋ የተጣላበት ምክንያት አባታቸው ሲሞት ሙሉ ውሩሱን ለጆን ብቻ ነበረ
ያወረሰው የጆን አባት በጣም ብዙ ግዜ ታሟል ተሰቃይቷል ሁሉም ሰለቸው ጆን ግን
ህይወቱ እስኪያልፍ ድረስ ከአጠገቡ አልተለየውም ነበር በዚህ ምክንያት ጆንን አስበልጦ
ሰለ ሚወደው ሁሉንም ሀብቱ በእሱስም አዞረለት ከዛን ቀን ጅምሮ የጆን ወንድም
ቂመኛ ሆነ ጆንን በሚፈልገው ነገር ሁሉ ጎዳሁ ስንት አመት የተማርበት የደከመበትን ፋይል
ሳይቀር አቃጠለበት ጆን ይሄንም ችሎ ዝም አለ ይሄ አልበቃ ብሎት ጆንን ለማስገደል
ለቅጥረኛ ነፈስ ገዳይ ብር ሰጣቸው የጆን አባት ሁሉንም ነገር ሲሰማ አስጠራው ያሜናዳብ
እና አንተ ለእኔ ልጆቼ ናቹ ግን ምግባራቹ ባህሪያቹ ለየቅል ነው አይኔን በመርፌ እየነካህብኝ
ነው እጆችህን ሰብስብ አለ በለዚያ መቼም ይቅር አልልህም አለው በዚህም የተነሳ ደነገጠ
አባቱ ጆንን ያሜናዳብ ብሎ ነው ሚጠራወ በእምነቱ በጣም ጠንካራ ነው ሁሌም ስለ ጆን
ሲጠየቅ #የእሴይ_ሥር_ያሜናዳብ_ሰረገላ_የዳዊት #መሰንቆ_የሰለሞን_አክሊ
የታጠረችተክልየተዘጋች #የውኃ\ገድጓድ_አንቺ_ነሽ_አመቤቴ ይላል እና የእኔ
የምድር #ያሜናዳቤ እሱ ነው ይላል ልክ አባቱ እንደዚህ ባለው
ማታውን ነፍሰ ገደዮች ጆንን ደብድቦ ሊገሉት ሲሉ ደውሎ ካልነካቹት ተውት አላቸው እንደ
ደበደቡት ሲነግሩት ከአከባቢው ጥፉ አላቸው እነሱም እንደ ተባሉ አደረጉ መጨረሻ ለይ
ጆን በወደቀበት ሰው አይቶት ሆስፒታል አስገባው በጣም ስለ ተጎዳ ወደ ውጭ ሀገር ሂዶ
እንዲታከም ተነገራቸው በዚህ ግዜ ልዩ ደውላ አሜርካ ላለው ሀያታቸው ነገረችው ለረጅም
አመት አሜርካ ነበር ሚኖረው እንደዛ እንደ ሆነ ሲሰማ በጣም ነበር ያዘነው ወዲያው ወደ
አሜርካ እንዲልኩት አደረገ ጆን ከዛን ቀን በኋላ አባቱ ሲሞት ብቻ ነው ወደ ኢተዮጲያ
የመጣ እሱንም አልቆየም አባቱ ለእሱ ያወረሰውን ሙል ሀብት በወንድሙ ስም አዞረለት
በሰአቱ የጆን ወንድም ማመን ነበር ያቃተው ያን ካደረገ በኋላ ሁለት እህቶቹን ወደ አሜርካ
ይዞ ወጣ በሰአቱ የወንድሙ ሁኔታ ምንም ስላል ተመቸው ያን ሁሉ አመት አሳልፎ ከአመታት
በኋላ ወንድሙ ጋር
ሊታረቅ ወደ ባ/ዳር መጣ ወንድሙም ለብዙ አመት ጆን ለይ የፈፀመውን ነገር እያሰበ
ብቻውን ነበር ሲያለቅስ የኖረው ጆንን ለመጀመርያ ግዜ ሲያየው በጣም ደንግጧል ይቅር
በለኝ ብዬ መሄድ ያለብኝ እኔ እንጂ እሱ አደለም ብሎ በጣም አዝኖ ነበር በራሱ እናንተ
ቤት ዶርም ሊይዝበት የቻለው ደግሞ ከእናተ ቤት ዶርም ተከራይቶ የነበረው የጆን ጓደኛ
ነው ጀን ወደ ኢትዮጲያ ከመምጣቱ በፊት ስለ ወንድሙ እንዲያጣራለት ነግሮት ነበር
በሰአቱ እኔ አንቺ ኤልሲ እና ኪያ ወይም የጆን ወንድም አብረን ነበረ ምንጓዝ ያሰለሆነ
ወንድሙን ለማግኘት ባንቺ መጣ አለችኝ እኔ ደርቄ ቀረሁ ጆን ይሄን ሁሉ ነገር ማሳለፉ
በጣም ገረመኝ ምን አይነት ትዕግስት ነው አልኩኝ በጣም ደነቀኝ እኔም ሁሉ ነገሬን ለጆን
አሳልፌ ሰጠሁት ፍቅርን ከምገልፀው ባለይ አስተማረኝ
ዛሬ ያሁሉ አልፎ ጆን ጋር ልንጋባ ወራት ነው የቀረን ከእኔ በላይ ደስተኛ የለም
ህይወት እንደ ፈለጓት ሳይሆን የህይወታችን ደራሲ
የሆነ ፈጣሪ ያሰበልንን ሲሰጠን ብቻ ነው ልባችን የሚያርፈው ማንም ሰው የሚመኘው ነገር
ይኖራል
በዛ ነገር ላይ ተስፋ መቁረጥ የለባቹም እኔ አሜርካ መሄድ የምፈልገውን ያክል ማንም
ፈልጎ አያውቅም
ነገሮች እንደ ማይሆኑ ባውቅም ተስፋ ግን አልቆረጥኩም ይሄው ፈጣሪ መሻቴን አይቶ
አልከለከለኝም ሁሌም ተስፋ አትቁረጡ አመሰግናለሁ


        🙏ተፈፀመ🙏
በሌላ ታሪክ እስከ ምን ገናኝ ሰላም ሁኑልኝ። ሌላ የፍቅር ታሪክ በቅርብ ስለሚለቀቅ ቶሎ እንዲደርሳቹ ላይክ እና ሼር አትርሱ ።


አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
💛
@yefeker_tiksoche 💜
💛
@yefeker_tiksoche 💜
  ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉

   ሀሳባችሁን እታች ባለው ሀሳብ ማስቀመጫ    ላይ መግለፅ ትችላላችሁ 💗
🌹ያችን ሴት ሁኚ🌹....
🍃

ማንም ስለፈለገ የማያገኛት🍃
በብልጭልጭ የማትታለለው
በቃ ለራሷ ክብር ያላትን🥀

@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
​​​​
😘አንዴ ብትሰጠኝ🤣

ቀምሼው አላውቅም
እያልኳት አትስጭኝ
ልብሱን ገለጥ አርጋ
መልኩን ብታሳየኝ
እኔው ሰፍ ብዬ
አልኳት ስጭኝ ስጭኝ
እርሷም ሳትሳሳ
አንድ ጊዜ ብትሰጠኝ
ሁሌም ስጭኝ አልኳት
በጣም ነው የጣመኝ
ስሙንም ስትነግረኝ
እንዳይጠፋኝ ብላ
ለካስ የማውቀው ነው
ደስታ ከረሚላ!!!
      😁😁😁        
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
​​​​​​​​​​.                  💚 የፍቅር ንቅሳት 💚

          🤍●▬ተከታታይ ታሪክ▬●🤍

   💞
#እውነተኛ ልብ አንጠልጣይ  የፍቅር ታሪክ●💞

♨️ለመጀመር የእናንተ ፍላጎት ያስፈልገናል VOTE አርጉ ለማንበብ የሚፈልግ የ♥️ ምልክቱን በመንካት VOTE ያድርጉ
              ,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,
                       ተ🀄️🀄️ሉን👇
                 በቴሌግራም  ይከታተሉን
                
..............♥️💍••●🍃🌹🍃●•..............        
        💛
@yefeker_tiksoche 💛

#ሼር
የፍቅር ጥቅሶች 💖 pinned «‍ ​​​​​​​​​​.                  💚 የፍቅር ንቅሳት 💚           🤍●▬ተከታታይ ታሪክ▬●🤍    💞●#እውነተኛ ልብ አንጠልጣይ  የፍቅር ታሪክ●💞 ♨️ለመጀመር የእናንተ ፍላጎት ያስፈልገናል VOTE አርጉ ለማንበብ የሚፈልግ የ♥️ ምልክቱን በመንካት VOTE ያድርጉ               ,,,,,🌹🌹🌹🌹,,,,,                        ተ🀄️🀄️ሉን👇                 …»
​​ተከታታይ ልቦለድ

             🌹የፍቅር ንቅሣት

                                     ክፍል 1⃣


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ

       ▶️  የካቲት 5/2010አ.ም ለኔ ልዩ ቀን ነበረች።ለኔ ብቻ ሣይሆን ለሮቢዬም እንደዛው ርብቃ እባላለው።የካቲት 5 ከሮቢዬ ጋ የፍቅር ጊዜያችንን ሀ ብለን የጀመርንባት የቀኖች እና የፍቅራችን የመጀመሪያ ቀን ሠኞ ነበረች።ከሮቢዬ ጋ የተዋወቅንበት አጋጣሚ እነሆ እናት አና አባቴ ስለተለያዩ እኔ የምኖረው ከአባቴ ጋ ነው ይሁንና የሣምንቱን መጨረሻ የእረፍት ቀነሠቶች እናቴ ገረ ነበር ማሣልፈው እኔ እና ሮቢ በተገናኘንበት ጊዜ እናቴ ከአባቴ በኀላ ካገባችው ባሏ ከአንድ ልጃቸው(ከእህቴ) እና ከእናቷ(ከአያቴ) ጋ እነ ሮቢ ግቢ ተከራይተው ነበር ሚኖሩት።እለተ ቅዳሜ ነበር ህዳር 23/2010አ.ም እናቴ እነ ሮቢ ቤት በቅርቡ ስለሆነ የተከራየችው እኔ ስለማላውቀው ልትወስደኝ ነበር ከአባቴ ጋ ምኖርበት ቤት የመጣችው ከእናቴ ጋ ተያይዘን ወደ አዲሡ ቤታቸው ሄድን።ስንደርስ በሩን የከፈተችልን ሮቢ ልክ እንደ እህቱ የሚያያት ፍቅር ነበረች።ማም ከፍቅር ጋ ካስተዋወቀችን በኀላ ወደ ውስጥ ገባን።ወደ ውስጥ ስንገባ የት/ቤት ልብስ ታጥቦ ተሠጥቶ ነበረ።የዩኒፎርሙ አሠፋፍ የወንድ ይመስል ነበር ደሞ አልተሣሣትኩም የሮቢ ነው።እቤት ገብቼ ትንሽ አረፍ እንኳን ሣልል ፍቅር ብዙ ደብተሮች ይዛ መጥታ አስጠኚኝ አለችኝ።ይሄ የማም ስራ ነው።ሁሌ በሄደችበት ሁሉ ከአባቴ ስለወረስኩት ት/ት ላይ ስላለኝ ጉብዝና ታወራለች።ለነገሩ ፍቅር የ3ተኛ ክፍል ተማሪ ነበረች።እናም ፍቅርን እያስጠናሇት እቤት ውስጥ፡ስለሞቀን ወደ ውጪ ወጣን።ውጪ ሮቢ ልብስ እያጠበ እናቱ ደግሞ ቡና እየወቀጠች ነበር።ከዛ እናቱን ሄጄ ሠላም አልኳት ተዋወቅን አስቴር እባላለው ስትለኝ ርብቃ አልኳትኝ።<ሮቢ ና ተዋወቃት የሚሚ ልጅ ናት እኮ>አለችው።ከዛ ከሮቢ ጋ ተዋወቅን።የኔና የሮቢ የመጀመሪያ ትውውቃችን እንዲ ነበር።እኔም ፍቅርን ማስጠናት ጀመርኩኝ።ሮቢ ልብሡን አጥቦ ሲጨርስ አጠገቤ መጥቶ ቁጭ አለና አንድ አንድ እያልን በደንብ መተዋወቅ ጀመርን።ሮቢ ልክ እንደኔ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ነበር።ወደ አመሻሹ ላይ ሁሉም ውጪ ተቀምጦ እኔ ቡና አፈላው።ስጨርስ ሮቢ እና የማም ባል ዛፍ መቁረጥ ጀመሩ።ሮቢ ሲቆርጡ ስልኩ እንዳይወድቅበት ብሎ ዘፈኑን እንደከፈተው lock አድርጎት ለፍቅር ሠጣት።ከዛ ፍቅር አጠገቤ መጥታ ተቀመጠች ድንገት ዞር ስል emergency call ሚለው ላይ ስልክ እየፃፈች ነበር የማነው ፍቅር ስላት የሮቢ ነዋ አለችኝ ታድያ እኔም ሰልኩን ሽምድድ አድርጌ እቤት ገብቼ ስልኬ ላይ save አደረኩት።

ይቀጥላል...

    ✎ ክፍል ሁለት (2) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
   
​​❦ ══ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦

             🌹የፍቅር ንቅሣት

                                     ክፍል 2⃣


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ


    ▶️  ታድያ እኔም ስልኩን ሽምድድ አድርጌ እቤት ገብቼ ስልኬ ላይ save አደረኩት።ከዛ እነ ሮቢ ዛፉን ቆርጠው ጨርሠው አጠገቤ መጥቶ ተቀመጠ።<ሮቢ fb ላይ እኮ friend request ልኬልሀለው accept አታረገኝም እንዴ>አልኩት ፈገግ እያልኩ እሡም <እንዴት accounten አገኘሽው>አለኝ እየተገረመ።<እንዴ ስልክህን አስገብቼ ነዋ search ያረኩት>ስለው አለማመን በሚመስል አነጋገር <እስቲ ስልኬን ንገሪኝ>አለኝ።እኔም ነገርኩት በጣም እደተገረመ ገና ከተዋወቅን 24ሰአት እንኳን ሣይሆነን ከየት እንዳመጣሁት ጠየቀኝ እኔም እያሾፍኩበት ወፏ ነግራኝ አልኩት።ሁለታችንም ከተሣሣቅን በኀላ accountun እንዳላገኘሁትና እሡ friend request እንዲልክልኝ ጠየኩት።እሡም ወዲያው ላከልኝና እኔም ተቀበልኩት።አጠገብ ለአጠገብ ተቀምጠን chat ማረግ ጀመርን። ሁላችንም ወደ ቤት ስንገባ ሮቢ እና የእናቴ ባል ስፖርት መስራት ጀመሩ።የእናቴ ባል ወደ ቤት ሲመጣ ስፖርቱን እንደጨረሡ ስለገባኝ ለሮቢ normal text ላኩለት።ሮቢም ወድያው መለሠልኝና ብዙ አወራን።እኔ እና ሮቢ የተዋወቅንበት ቀን እንዲህ አምሮበት አልቆ ቀጣዪ ቀን እሁድ መጣ።እሁድ በጠዋት ፍቅር እቤታችን መጥታ አስቱ እየጠራችሽ ነው ብላኝ ቤታቸው ይዛኝ ሄደች።ከዛ አስቱ ስገባ በሚያምር ፈገግታ ተቀብላኝ ከፊት ለፊቷ ያለውን የምግብ ጠረጴዛው ጋ ያለውን ወንበር በእጇ እያሣየችኝ ቁጭ እንድል ጋበዘችኝ።እኔም በ1 ቀን ውስጥ ከሁሉም ጋ በጣም ስለተግባባው እንደ ቤቴ አየሁት።አብረን ቁርስ ከበላን በኀላ እኔ ወደ ቤት ሄድኩኝ።እቤት መቀመጥ ስለደበረኝ ውጪ ወጥቼ ስቀመጥ ሮቢም ትንሽ ቆይቶ ወጣ ብቻችንን ስለነበርን የራሣችንን ወሬ ማውራት ጀመርን።ሮቢ ደስ የሚል ልጅ ሆኖ ነው ያገኘሁት።ከሮቢ ጋ ብዙ ከተጨዋወትን በኀላ ጠዋት አብረን ት/ቤት እንደምንሄድ ተነጋግረን ወደየ ቤታችን ገባን።ማታ በfb ብዙ አወራን።አይነጋ የለ ነግቶ እነ ማም ስራ ከሄዱ በኀላ እኔ ደሞ እነ ሮቢ ቤት ሄድኩኝ።እነ ሮቢ ቁርስ እየበሉ ነበር ደና አደራቹ ብያቸው እኔም አብሬያቸው ተቀመጥኩ።አስት ቁርስ ብዪ ስትለኝ አሁን ነው የበላሁት ብዬ ሻይ ብቻ ቀድቼ መጠጣትጀመርኩኝ።ለሚያየን ለብዙ አመት በፍቅር የኖርን ቤተሠቦች እንጂ በፍፁም የ1ቀን ትውውቅ ያለን አከራይ እና ተከራይ አንመስልም።እኔ እና ሮቢም ቦርሣችንን ይዘን ለመውጣት እየተነሣን አርብ ከት/ቤት መልስ እመጣለው ብያቸው አስቱን አቅፌያት ቻው ስላቸው ፍቅር መጥታ አቅፋ ሣመችኝና ቻው አለችኝ።እኔም ወደ ቤት ተመልሼ አያቴንና ትንሿን እህቴን ስሜያቸው ወጣው::

   ከሮቢ ጋ መንገድ ጀመርን ...........


✎ ክፍል ሶስት (3) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@yefeker_tiksoche💜
💛
@yefeker_tiksoche 💜
​​​​❦ ══ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦

             🌹የፍቅር ንቅሣት


                                     ክፍል 3⃣


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ


..... ▶️    እኔም ወደ ቤት ተመልሼ አያቴንና ትንሿን እህቴን ስሜያቸው ወጣው።ከሮቢ ጋ እየሄድን ሁሌም እንደምናወራ እና እንደምንደዋወል እየተነጋገርን ለኔ ት/ቤት በሚቀርበኝ መንገድ ከሸኘኝ በኀላ ተቃቅፈን ቻው ተባባልን።ለኔ ት/ቤት በሚቀርበው መንገድ ስለሄድን ቶሎ ነበር የደረስኩት።ቀኑን ሙሉ እሡን እያሠብኩ ምሣ ሠአት ደርሶ ከጓደኞቼ ጋ ከበላን በኀላ ከጓደኛዬ ጋ ላይብረሪ ገባን ግን ምንም ማጥናት አልቻልኩም።እሧም ጨንቋት ምን እንደሆንኩኝ ስትጠይቀኝ እኔም ፈገግታ ሣይለየኝ ሁለት ቀኑን እንዴት እንዳሣለፍኩኝ ነገርኳት።በጣም በግርምት እያየችኝ<አንቺ ለወንድ ከመች ጀምሮ ነው እንዲ ምትሆኚው ገና በትውውቅ ት/ትሽን እየነካብሽ ነው ስለዚህ ተጠንቀቂ ርብቂ>አለችኝ ፍርሀት በሞላው ድምፅ!ላይብረሪ ገብተን ምንም ሣናጠና ተደውሎ ወጣን።ቀሪውን ሁለት ክፍለ ጊዜ ምንም ሣልሠማ የወደ ቤት ሠአት ደውል ተደወለ።ቶሎ ከአባቴ ጋ ምኖርበት ቤት ሄጄ ቦርሣዬን ብቻ አውልቄ fb ላይ ተጣድኩኝ የአባቴ እናት መጥታ መክሰስ ብዪ እንጂ ብላ እስክትቆጣኝ ስልኬ ላይ ተደፍቼ ነበር።ከዛ ዩኒፎርሜን አወላልቄ እና ተጣጥቤ መክሰስ ከበላው በኀላ ለቀጣዩ ቀን የሚሆነኝን ፕሮግራም ካዘጋጀው በኀላ ትንሽ አጥንቼ መልሼ የፈረደበት ስልኬ ላይ ተደፋው።ከሮቢ ጋ ካወራን በኀላ አባቴ ሲመጣ ሁላችንም እራት በልተን ተኛን።ከሮቢ ጋ በዚ መልኩ በጣም እየተግባባን መጣን።ቀናቶች በቀናቶች እየተተኩ የገና በአል ደረሠ።ሮቢ ትንሽ አሞት ስላልጠየኩት ቅጣት ነበረብኝ።እና የገና ስጦታ ሠጠሁት እሡም ሠጠኝ።ይሄ እንግዲ ፍቅር ከመጀመራችን በፊት የተሠጣጠነው የመጀመሪያ ስጦታ ነው።
የካቲት 4/2010አ.ም እሁድ ቀን እኔ እነ ሮቢ ቤት ቁጭ ብዬ.........

✎ ክፍል አራት(4) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@yefeker_tiksoche 💜
💛
@yefeker_tiksoche 💜
​​​​​​❦ ══ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦

             🌹የፍቅር ንቅሣት

                                     ክፍል 4⃣ እና 5⃣


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ



      የካቲት 4/2010አ.ም እሁድ ቀን እነ ሮቢ ቤት ቁጭ ብዬ ስልኬን ወሠደብኝ።እኔም የሡን ስልክ ወስጄ ፎቶ እያየው ድንገት የኔ ስልክ ላየሸ text ገባ።ማነው ስለው በአንዴ ፊቱ ተቀያይሮ ስልኬን ወርውሮልኝ ወደ ውጪ ወጣ።እኔ በጣም ደንግጬ ስልኬን ሣየው እኛ ት/ቤት የሚማር የጓደኛዬ ፍቅረኛ ነበር text የላከልኝ<እምወድሽ>ነበር ሚለው።እሡ ሁሉንም ሠዉ እንዲ እያለ ነው ሚጠራው የሡ text ምንም አልገረመኝም።ይልቅስ የገረመኝና ጥያቄ የሆነብኝ የሮቢ እንዲህ መሆን ነው ለምን እንዲህ ተናደደ።እንደውም ስልኬን ወርውሮብኝ ጥሎኝ ስለወጣ ተናድጄ እኔም ወደ ቤቴ ሄድኩኝ።ማታ ላይ ፍቅር መጥታ አስት እየጠራችሽ ነው ብላኝ እነሡ ቤት ሄድኩኝ።ከዛ እቤት ስገባ ሮቢ ሶፋ ላይ ተኝቶ በearphone ሙዚቃ እያዳመጠ ስልኩን እየነካካ ነበር ድምፁን በጣም ከፍ ስላደረገው ሚሠማው ዘፈን ይሠማ ነበር<ያለ ተቀናቃኝ ያለ ፉክክር
         ቦታ አለሽ በልቤ በፍቅሬ መንደር>
የሚለው ነበር።እቤት ገብቼ እሡ ከተኛበት ሶፋ አጠገብ ከተቀመጥኩ ብዙ ቆየው ግን እሡ እስካሁን አላዋራኝም ከአስት ጋ ብቻ ነበር ሣወራ የነበረው።አስት ተነስታ ወደ kitchen ስትገባ<ምን ሆነህ ነው ሮቢ>ብዬ text አረኩለት።አይቶት ዝም ሲለኝ በጣም ከፍቶኝ እንደ ሌላው ጊዜ አብሬያቸው እራት ሣልበላ ደና ደሩ ብዬ ወጣው።ልክ እቤት ስገባ text ገባልኝ፤ሮቢ ነበር<የውሸት ነበር ለካ>ይላል።<ምኑ>ብዬ ወዲያው መለስኩለት።<በቃ ተይው>አለኝ።እኔም ነገሩን ከሡ መስማት ፈልጌ እንጂ መጀመሪያም ገብቶኝ ስለነበር ልጁ ምኔም እንዳልሀቀነ እንዲያውም የጓደኛዬ ፍቅረኛ እንደሆነ ላስረዳው ሞከርኩኝ።እሡ ግን ወይ ፍንክች እኔ እኮ የምር ወድጄሽ ነበር አንቺም እንደዛ ይመስለኝ ነበር ሲለኝ አልተሣሣትክም እኮ ታድያ ብዬ ስልክለት balance ጨርሼ ነበር።

ክፍል 5

     እሡ ግን ወይ ፍንክች እኔ እኮ የምር ወድጄሽ ነበር አንቺም እንደዛው ይመስለኝ ነበር ሲለኝ አልተሣሣትክም እኮ ታድያ ብዬ ስልክለት balance ጨርሼ ነበር።ደግሞ ሌላ text ላከልኝ<እሺ ቅድም ላስረዳህ ስትዪ አልነበር አሁን እሠማሻለዉ ስለ ልጁ በደንብ ንገሪኝ>አለኝ።balance እንደጨረስኩኝ አውቆ ነው እንዴ አልኩኝ ለራሴ ከ5 ደቂቃ በኀላ<አየሽ ልታስረጂኝ አትችይም ምንም ማለት አትችይም>አለኝ።ጠዋት ደርሶ ምን ብዬ እንደማስረዳው ሣስብ ለሊቱ ሲጋመስ ነበር እንቅልፍ የወሠደኝ።አይደርስ የለ ያቺ ጠዋት ደረሣ ተገናኘን።እንደ ሌላዉ ቀን እንኳን አቅፎ ሠላም ሊለኝ ይቅርና ለአይኑ ራሡ ያስጠላሁት መሠለኝ ዛሬም አብሬያቸዉ ሣልበላ ስትጨርስ ጥራኝ ብዬው ወጣው።ብዙም ሣይቆይ ፍቅር መጥታ ውጪ እየጠበቀሽ ነው አለችኝ።እኔም ወድያው ወጣውና መሄድ ጀመርን።ማታ እንቅልፍ አሣጥቶኝ ያደረውን ስብሰለሰልበት የነበረውን ልነግረው <ይኸውልህ ሮቢ ልጁ እኮ...>አላስጨረሠኝም።<እኔ እኮ አያገባኝም ለኔ መናገር አይጠበቅብሽም>ሲለኝ ሊፈስ የደረሠውን እንባዬን ዋጥ አድርጌው በዝምታ መጓዝ ጀመርን።ለሁለታችንም እኩል በሚሆነወሸ መንገድ ስንሄድ ይበልጥ ዝምታ ነፈሠ እያንዳንዷ ምንራመዳት እርምጃ የ10 ሠዎችን ያህል ጩኸት ገዘፈብኝ።ጩሂ ጩሂ ሁላ አለኝ።ምንም ትንፍሽ ሣንል መለያያችን ጋ ስንደርስ ተቃቀፍንና ሁለታችንም ጀርባችንን ተሠጣጥተን በየ መንገዳችን ሄድን።ክፍል ውስጥ ያለመደብኝን ጥግ ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ።እረፍት ሠአት ላይ ጓደኞቼ በግድ ይዘውኝ ወጡ።ግን ድንገተኛ ረብሻ በአከባቢው ላይ ስለተነሣ ሁሉም ወላጅ እየመጣ ልጆቹን መውሠድ ጀመረ።ሁሉም ጓደኞቼ ከሄዱ በኀላ አባቴ በድንጋጤ እየበረረ መጣ።ልክ ሣየው ሄጄ ተጠመጠምኩበት።በጣም ፈርቼ ነበር።አባቴም አቅፎኝ ድንጋጤው ሲለቀው ወደ ቤታችን ሄድን።አይገርምም ሮቢ ነበር ለእናቴ ደውሎ ብጥብጥ እንደተነሣ ነግሯት ለአባቴ ደውላ የነገረችው።ሮቢ ለኔ እንደዚ ማሠቡ አስደስቶኝ ወደ ቤት እንደገባው በሠላም ገባህ የሚል text ላኩለት።እሡም ወድያው በሠላም እንደገባ ነግሮኝ የኔን ደህንነት ጠየቀኝ።እናም በዚ ተነስቶ እኔ በጣም እንደምወደው ነገርኩት እሡም ለኔ ተመሣሣይ ስሜት እንዳለው ነግሮኝ የፍቅራችንን የመጀመሪያ ቀን ሀ ብለን ጀመርን።በተነሣው ረብሻ ምክንያት ለ3ቀን ት/ት ተዘግቶ ነበር።በቃ ቀኑንም ለሊቱንም ነበር ምናወራው።

    ገና ትምሀርት ከመከፈቱ .......


✎ ክፍል ስድስት(6) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@yefeker_tiksoche 💜
💛
@yefeker_tiksoche 💜
​​═ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦

             🌹የፍቅር ንቅሣት

                                     ክፍል 6⃣


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ



     📝 በቃ ቀኑንም ለሊቱንም ነበር ምናወራው።ት/ት ሲከፈት እሡም እኛ ት/ቤት ለወደ ቤት ሠአት እየመጣ መገናኘት ጀመርን።ከሠኞ እስከ ሀሙስ እሡ ት/ቤት እየመጣ እንገናኛለን አርብ ደሞ እኔ እናቴ ጋ ከት/ቤት ስወጣ ስለምሄድ ቅዳሜ እና እሁድ አብረን እየዋልን ሠኞ ደሞ አብረን ወደ ት/ቤት እንሄዳለን።የፍቅር ምሣሌዎች እስክንባል ፍቅራችን ገዘፈ።አንዳንዴ ወደ ውጪ ወጣ ስንል ከአባቴ ጋ ምኖርበት ሠፈር እየመጣም እንገናኝ ነበር።ፍቅራችን እንኳን ለሚያቀን መንገድ ላይ ላየን እንኳን የሚያስቀና ነበር።እንዲህ እየተባለ አንድ ወራችን ደረሠ ግን አልተገናኘንም ነበር ምክንያቱም በማግስቱ በጣም የሚወደው አባቱ ሙት አመት ነበር።ስለዚህ ት/ቤት አልሄደም።እኔም ቀኑ ረቡዕ ስለነበር እናቴ ጋ አልሄድኩም አርብ ቀንን ምመርጠው ሁለቷን የእረፍት ቀኔን እሧ ጋ ለማሣለፍ እንጂ ሌላ ምክንያት ኖሮኝ አይደለም።ረቡዕ ወደ ቤት ስገባ አስት ደወለችልኝና ነገ እንዳትቀሪ ብላ በአደራ እና በማስጠንቀቂያ ነገረችኝ።እኔም እንቢ ማለት ስለከበደኝና ለሮቢ እንደማስፈልገው ስለማውቅ እሺ አልኳት።የሧን ስልክ እንደዘጋሁት ወዲያው እናቴ ደወለችና እሧም እንዳትቀሪ ነይ አለችኝ።ለአባቴ ሀሙስ እንደምሄድና ሠኞ እንደምመጣ ነገርኩት።መጋቢት 6/2010አ.ም ሀሙስ ቀን ከት/ቤት ስወጣ እነ ሮቢ ቤት መሄድ ጀመርኩኝ።ድንገት ሄጄ ደስ ላሠኘው ፈልጌ ለሮቢ እንደምመጣ አልነገርኩትም ነበር።ልክ የውጪው በር ጋ ስደርስ ሮቢ እየወጣ ነበር ልክ ሲያየኝ በጣም ደስ አለው።አልመጣም ብዬው ስለነበር ሲያየኝ አላመነም መጥቶ አቀፈኝና ሠላም አለኝ።አብረን ወደ ውስጥ ገባን ግቢ ውስጥ ብዙ ሠው ነበር ሠላም አልኳቸውና አስት እና እናቴን ስሜያቸው ወደ ውስጥ ገባው።ልብሴን ቀያይሬ የሠው ብዛት እስኪቀንስ ትንሽ ጋደም አልኩኝ።ማታ ላይ አስት ጠራችኝና እነሡ ቤት ሄድኩኝ።እናቴ ነበረች ሌሎች ማላውቃቸው ሠዎች ነበሩ።ሮቢ ከሁሉም ጋ አስተዋወቀኝ ዘመዶቹ ነበሩ።ከዛ እራት እየበላን ድንገት ሮቢ ተነስቶ መናገር ጀመረ።

✎ ክፍል ሰባት (7) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
               
​​​​═ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦

             🌹የፍቅር ንቅሣት

                                     ክፍል 7⃣


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ


    ሮቢ ከሁሉም ጋ አስተዋወቀኝ ዘመዶቹ ነበሩ።ከዛ እራት እየበላን ድንገት ሮቢ ተነስቶ መናገር ጀመረ።<ሁላችሁም እንዳከበራችሁን እግዚአብሔር ያክብራችሁ፤ይሄንን ዝግጅት እንዲህ የተሟላ እንዲሆን በሀሣብም ሆነ በስራ ስለረዳችሁን በጣም አመሠግናለሁ በተለይ ሚም ለሊቱን ሙሉ ሳትተኚ ሁሉንም ስራ ሸፍነሽ ስትሠሪ ነበር በእኔና በእናቴ ስም ምስጋናዬን አቀርባለው። አባቴም ነብሱን በአፀደ ገነት ያኑርልኝ።>ብሎ ተቀመጠ።ማስተዋል በተሞላበት ንግግሩ ኮራሁበት።እናቴ ቡና አፍዪ ብላኝ ቡና እያፈላው ብዙ ስነወራ ካመሸን በኀላ ሁሉም ወደ ቤት መሄድና የቀሩት መተኛት ሲጀምሩ እኔና ሮቢ ቁጭ ብለን እያወራን እጄን የሡ እጅ ላይአድርጎ ጣቴን መለካት ጀመረ፤ሮቢ ምን እየሠራህ ነው ስለው ደሞ ሠፊ ቀለበት ገዝቼልሽ የሠው መሣቂያ እንዳልሆን ነዋ አለኝ።ሁለታችንም እየተሣሣቅን እናቴ ድንገት መጥታ እናንተ ከተገናኛቹ በቃ ወሬ አያልቅባችሁም አይደል ነገ እኮ ት/ት አለ ነይ በይ ተኚ አለችኝ እየሣቀች አንተም ደክሞሀል ሮቢ ከትላንት ጀምሮ አልተኛህም በል ተኛ አለችው።አቅፌው ቻው አልኩትና ወደ ቤት ሄድኩኝ።መጋቢት ሰባት ማታ ላይ የኔ ቤተሠቦች አስት የሮቢ ጓደኞች ሌሎች ተከራዮችና እኔና ሮቢ ግቢ ውስጥ ቁጭ ብለን እራት እየበላን እየተጨዋወትን ነበር።ሁሉም እራት በልቶ ጨርሶ የየራሡን ወሬ ማውራት ሲጀምር እኔና ሮቢም ከጓደኞቹ ጋ ማውራት ጀመርን።ሁሉም ቀስ በቀስ ወደ ቤት ሲገባ የሮቢ ሁለቱ ጓደኞቹ ደሞ በ pc film ማየት ጀመሩ እኔና ሮቢ ፊልሙ ስላልተመቸን የራሣችንን ወሬ ማውራት ጀመርን።ከሮቢ ጋ ቁጭ ብለን የባጥ የቆጡን ስነሠወራ ለካ ሠአቱ ሄዶ ነበር፤ከሡ ጋ ስሆን በጣም ነው ደስ የሚለኝ ልክ እንደ ሁል ጊዜው እጄን ይዞኝ እያወራን   ጓደኞቹ ተነስተው በቃ እንሂድ ሲሉ አስትም ወጣችና አው መሸባቹ ሂዱ እናንተም ግቡና ተኙ መቼም እናንተን መለያየት ችግር ነው አለችን።ቅር እያለንም ቢሆን ተነስተን ገባን።ፍቅር ለኔም ሆነ ለሮቢ የመጀመሪያችን ነው። ለኔ በጣም ለብዙ ነገር መጀመሪያዬ ሮቢ ነው።ብዙ ነገሮችን በሡ አይቻለው፤ተምሬያለው።ደስ የሚል እና ሁሌም ቢያስቡት የሚያስቀና የማይሠለች የፍቅር ጊዜ አብረን አሣልፈናል።ቅዳሜ ቀን እኔ ግቢ ውስጥ ለማፍላት እቃ አቀራርቤ ቡናውን እየቆላው አጠገቤ መጥቶ ቁጭ አለና earphone አድርጎልኝ ላንቺ ነው ውዴ ስሚው አለኝ።የናቲ ማን የመጀመሪያዬ ሚለው ዘፈን ነበር።ዘፈኑ ገና መውጣቱ ነው ተነሣሁና ጉንጩን ስሜው ቁጭ አልኩኝ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር።እንዴ ቆይ ሌላም አለ ድጋሜ ትስሚኛለሽ ብሎኝ አሁንም የናቲ ማን track 01 <ተነፋፍቆ ለተገናኘ ሠው
ለጨዋታ ቀን ሌቱም አይበቃው>ሚለውን ዘፈን ከፈተልኝ።ሀሣባችንን በደንብ ሚገልፅ ግጥም ስለነበረው በጣም ነው የወደድኩት ቅዳሜን በጣም ደስ ብሎን አሣለፍን።ማታ ላይ እናቴ የኔና የሮቢ ቅርበት በጣም በዝቶባት ስላጠራጠራት ያለንን ግንኙነት እንድነግራት ጠየቀችኝ።እኔም ምንም ሣልደብቅ ሁሉንም ነገር ነገርኳት፤ሁሉንም ስለነገርኳት ደስ ብሏት ሮቢንም ስለምታውቀው ምንም አላለችኝም።ሁሉም ነገር ሲመቻች እንዴት ደስ ይላል ከሮቢ ጋ ያለን ፍቅር በጣም እየጨመረ መጣ በቃ ሁሉም እስኪቀናብን ነበር ምንፋቀረው፨ሮቢ ከጋበዘኝ ዘፈኖች ውስጥ የናቲ ማን(የመጀመሪያዬ እና ተነፋፍቆ)፤የያሬድ(ዘለላዬ)፤የታሜ(ሀኪሜ ነሽ)፤የሳንቾ(አታሣዩኝ) ሁሌ ስሰማቸው እስካሁን እሡን ነው የሚያስታውሱኝ ግን ከምንም በላይ የብስራት ሱራፌል(ቃል በቃል)ብሎ ያዜመውን ሙዚቃ ስሰማው ሮቢ አብሮኝ ያለ አጠገቤ የተቀመጠ ነው ሚመስለኝ ሁሌ ከሮቢ ጋ አብረን ስንሆን ስለምንሠማው ነበር።አንድ ቀን እንኳን ሣንኮራረፍ ሁለተኛ ወራችን እየቀረበ መጣ።መጋቢት 21/2010አ.ም ነበር ሠማይ የተደፋብኝ እስኪመስለኝ የጨለመብኝ በጣም ከባድ ቀን  ነበር

✎ ክፍል ስምንት (8) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
​​​​​​═ •⊰❂ ተከታታይ ልቦለድ ❂⊱• ══ ❦


             🌹የፍቅር ንቅሣት🧡

                                     ክፍል 8⃣


በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ እና አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ


      🔹  መጋቢት 21/2010አ.ም ነበር ሠማይ የተደፋብኝ እስኪመስለኝ የጨለመብኝ በጣም ከባድ ቀን ነበር።እናቴ ከሮቢ ጋ ያለኝን ግንኙነት እንዳቆም አንዴ እየተቆጣች አንዴ ደሞ እያለቀሠች ነገረችኝ።መጀመሪያ ላይ የቀልዷን ቢመስለኝም እያለቀሠች ስትለምነኝ እና ስትቆጣኝ ነው የእውነቷን መሆኑ የገባኝ።ከሡ ተለይቼ እንደማልኖር እምባዬን እንደ ዝናብ እያወረድኩ ብነግራትም ልመናዋን ወደ ትዕዛዝ ለወጠችው።ከሡ ጋ እንድለያይ የፈለገችው ብዙ ጊዜ ከሠዎች ጋ ስለሚደባደብና ስለሚጣላ እሡን እንጎዳለን ብለው እኔን የሆነ ነገር እንዳያረጉኝ በመፍራት ቢሆንም ከሡ ተለያዪ ከምባል ሞት ሺ ጊዜ ይሻለኝ ነበር።ስለዚህ ግንኙነታችንን በድብቅ ለማድረግ አሠብኩ።በጣም ከባድ ነበር ለሮቢ 3ቀን ብደብቀውም ጭንቀቴ በግልፅ ያስታውቅ ስለነበረ በጣም እንድነግረው ሲያስጨንቀኝ ነገርኩት።በኔ ጥፋት ምክንያት እንዲህ ስላሰቃየሁሽ ይቅርታ ርብቂ ሁሉንም አስተካክለዋለው ብሎኝ ደግመኛ እንደማይጣላ ቃል ገብቶልኝ ሚምንም ይቅርታ እንደሚጠይቃት ነገረኝ።የስንት ቀን ጭንቀቴን እሡ በአንድ አ.ነገር አጠፋልኝ በጣም ደስ አለኝ።የአክስቴ ልጅም ጭንቀቴ በጣም ስላስጨነቃት እናቴን ደዉላ አናገረቻት።እናቴ ባይዋጥላትም ደስተኛ እንድሆን ፈቀደች።በጣም ነበር ደስተኛ የሆንኩት ያፈቀሩትን ሠው በነፃነት ማግኘትን የመሠለ ምን አለ።መጋቢት 30/2010አ.ም እሁድ ቀን የፋሲካ በአል ነበር።ሮቢዬ ከአባቴ ጋ ምኖርበት ሠፈር መጥቶ ተገናኘን።በጣም ናፍቆኝ ነበር ትንሽ ብቻ አብረን ከቆየን በኀላ የገዛሁለትን ሠአት እንደተጠቀለለ ሠጥቼው ቶሎ ወደ ቤት መሄድ ስለነበረበት ሄደ።እኔና ሮቢ በፍቅራችን እንኳን ሌሎች እኛ ራሡ እንቀና ነበር ከሮቢዬ ጋ 3ወር ሞልቶናል ኧረ እንደውም ለልደቴ የሆነ መናፈሻ ሄደን የአንገት ሀብል አደረገልኝ።ከዛ ወደ እናቴ ቤት ስለነበር ምሄደው አብረን ወደ ቤት እየተመለስን cupcake ገዝተን እየበላንና ክሬሙን እየቀባኝ ነበር የሄድነው።እቤት ልንደርስ ስንል አብረን እንደነበርን እንዳያውቁ እኔ መጀመሪያ ገባሁና እሡ ትንሽ ቆይቶ መጣ።

       እቤት ልንደርስ ስንል አብረን እንደነበርን እንዳያውቁ እኔ መጀመሪያ ገባሁና እሡ ትንሽ ቆይቶ መጣ።ልደቴን ደስ ብሎኝ አሣለፍኩ።ሮቢ ለእናቱ የፍቅር ግንኙነት እንደጀመርን እንደነገራት ነግሮኝ ነበር ቢሆንም አስት አሁንም እንደ በፊቷ ነች ምንምአልተለወጠችም😊። ግንቦት 12/2010አ.ም ሁላችንም ተሠብስበን ቤተ ክርስቲያን ሄድን ንግስ ነበር።ከዛ ሮቢ እዛው ቁጭ ብለን<አንቺ የአባቴ ምትክ ነሽ አባቴን ባጣሁት በአመቱ አንቺን ሠጠኝ>አለኝ።ሮቢ ለአባቱ ያለውን ፍቅር ጠንቅቄ ስለማውቅ ደስታዬ ወደር አጣ።ወደፊት ተጋብተን ለሚኖረን ህይወት ማረጋገጫ ፊርማ የሠጠኝ ስለመሠለኝ ምን አይነት ህይወት እንደሚኖረን እያሠብኩ በደስታ ክንፍ አውጥቼ ልበር ምንም አልቀረኝም ነበር።ሮቢ የአባቱን ያህል እንደሚወደኝ ሣስብ መቼም እንደማይተወኝ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ እርግጠኛ ሆንኩኝ።ቀናት ቀናቶችን እየተኩ final exam ከወሠድን በኀላ ከአክስቴ ልጅ ጋ ትንሽ ተጋጭተን እናቴ ጋ መኖር ጀመርኩ።(ርብቃ ምክንያቱን በሙሉ ልትነግረኝ ባትፈልግም በሮቢ ምክንያት እንደሆነ አጫውታኛለች)አሁን ክረምት ነው ስለዚህ ት/ት የለም በዛ ላይ ከሮቢ ጋ አንድ ግቢ ነው ምንኖረው።ጠዋት ነግቶ የመኝታ ሠአት እስኪደርስ እኔና እሡ አንድ ላይ ነን።ቀናቹብኝ አይደል ከሚያፈቅሩት ሠው ጋ አንድ ላይ እየኖሩ አብሮ መዋል አቤት ለዚህ ደስታ ሚሆን ቃል የለኝም።ጠዋት ከነጋ እኔ የለሁት አሸነ ሮቢ ቤት ነኝ፤ይሄ ልምድ እንኳን እኔና ሮቢ አስቱም ለምዳዋለች።አንዳንዴ ባልሄድ እንኳን አስት ፍቅርን እየላከቻት ትጠራኝ ነበር።
      ሀምሌ 5/2010 አ.ም የእኔና የሮቢ ልዩ ቀን ነበር ..........

✎ ክፍል ዘጠኝ (9) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
ፈተናውን ለምታልፉ የቻናላችን ተከታታዮች እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን።

ፈተናውን ማለፍ ሳትችሉ የሬሜዲያል እድል ማግኘት ለቻላችሁ ተከታታዮቻችን ደግሞ በርትታችሁ በመስራት ጉዟችሁን እንድትቀጥሉ የምናሳስብ ሲሆን፡

ፈተናውን የወደቃችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን ግን ህይወት በትምህርት ዘርፍ ብቻ የምትቀጥል አይደለችምና ያላችሁን አማራጮች እንድትመለከቱ፣ የቴክኒክ እና ሞያ ትምህርቶችን እንድትወስዱ ብሎም ከመበሳጨት ይልቅ በቁጭት ሊሳካላችሁ ወደሚችልበት የህይወት መንገዳችሁ እንድትጓዙ ልባዊ ምክር እናስተላልፋለን!።

ህይወት ይቀጥላል never give up💪
#ኢትዮጵያ2017

እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን !

ፈጣሪ አዲሱን ዓመት ፦
- የሰላም
- የፍቅር
- የአንድነት
- ከተፈጥሮ ውጭ የሰው ልጅ ሞት የማንሰማበት
- ሰው ታገተ፣ ተገደለ፣ ታፈነ የሚል ቅስምን ሰባሪ ዜና የምንሰማበት
- ፍጹም እርጋታ ያለበት
- እናት የማታለቅስበት
- ሰው ወጥቶ ቀረ የማይባልበት
- ፍትሕ ለተነፈጉ ሁሉ ፍትህ የሚሰፍንበት
- ፍትሕ አጥተው የሚያነቡ ፍትሕ አግኝተው እንባቸው የሚታበስበት
- እየፈተነን ያለው የኑሮ ጫና መፍትሄ የሚያገኝበት
- በሰላም በነጻነት ያሻን ቦታ ወጥተን የምንገባበት
- በሁላችንም ዘንድ የማያስማሙን ጉዳዮች መፍትሄ የሚያገኙበት
- እርስ በእርስ ልክ እንደጠላት የምንተያይበት ፣ የማንሰዳደብበት
- እሮሮ፣ ስቃይ በደል የማንሰማበት
- ያዘንን ተስፋ የቆረጥን ፤ የምንጽናናበት ተስፋ የምናደርግበት
- ሰራተኞች ፣ ተማሪዎች ፍጹም የተሳካ ዓመት የሚያሳልፉበት
- ከምንም በላይ በሀገራችን የትኛውም ቦታ ሰላም ተረጋግጦ ፣ ስምምነት መጥቶ በሀገራችን ፍጹም ደስታ የምናገኝበት
- ሁሉም በአንድ መንፈስ ለእናት ሀገሩ " አለሁልሽ " ብሎ የሚቆምበት ያደርግል ዘንድ ይመኛል።

ፈጣሪ ምኞታችንን ያሳካልን !

መልካም አዲስ ዓመት !
ከዓመት ዓመት ያደረሰን ፈጣሪ ቀጣዩን እንድናይ ይርዳን !
ለሁላችሁም ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኛለን !

@yefeker_tiksoche @yefeker_tiksoche
2024/09/21 00:32:50
Back to Top
HTML Embed Code: