Telegram Web Link
ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች በአዲስ አቀራረብ በአዲስ የፍቅር ታሪክ
ዛሬ ምሽት 2:00 ላይ ይለቀቃል::
#_Share
Share ማድረግ አይርሱ
ወዳቹሀለው😘
https://www.tg-me.com/yefeker_tiksoche
https://www.tg-me.com/yefeker_tiksoche
https://www.tg-me.com/yefeker_tiksoche
💊🔮​​​ናፍቀሽኛል ሆዴ🌺

                  መንገድሽ መንገዴ
                     ሆኖ የዘለቀው
                   ፍቅርሽ ስለገዛኝ
               ባሪያሽ ስለሆንኩ ነው

                   ሆዴ ናፍቀሽኛል
                  ምፈልገው ቢሟላ
                 የጠየኩትንም ባገኝ
                  አልጠግብም እኔ
                 አይንሽ ነው የራበኝ

                   ፍቅር ናፍቀሽኛል
                   ሆዴ ናፍቀሽኛል
                  አንቺን ለማግኘት
               ልቤ አጥብቆ ይመኛል፡፡
           
     
#ሼር

       
#የፍቅር ጥቅሶች
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche

🔔🥀ከተመቻችሁ
#_Share ማድረግ°°° አይርሱ🥹
​​"የድሀ ፍቅር"

#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ,::

ክፍል 1⃣

      ቢኒያም እባላለው ተወልጄ ያደግሁት ስም የለውም ማለቴ አዲስ አበባ ሆኖ አስፓልት ዳር ትንሽዬ የሸራ ዳስ ውስጥ  ነው አባቴን አላውቀውም እናቴ ነች ያሳደገችኝ ሌላም እንድ ወንድም አለኝ ናቲ ይባላል,ብቻ እናታችን እኛ እንዳንራብ የምትችለውን ሁሉ ታደርግልናለች ከሰው እኩል እንጂ ከሰው በታች ስትሆኑ ማየት አልፈልግም ትላለች ,
   
        እናቴ ያገኝችውን ትሰራለች የፓላስቲክ ቤት ብትኖረንም እናቴ ተመላላሽ ሆቴል አንሶላ ማጠብና አልጋ ማንጠፍ ከዛ  መልስ ደግሞ ተመላላሽ የሰው ቤት እንጅራ መጋገር ልብስ ማጠብ ትሰራለች ብቻ እረፍት የላትም እኔም ትንሽ ጠንከር ሰላልኩ ጫማ መጥረግ ማስቲካ ከረሚላ የሞባይል ካርድ እሽጣለው ብቻ ትንሽም ቢሆን አግዛታለው እናቴ ትምህርቴን በደንብ እንድማር ትፈልጋለች ,
  
         በቃ ከሀብታም ልጅ እኩል አድርጋ ትልቅ ትምህርት ቤት አስገባችኝ እሷ እየለፋች ለኔ ለወር ለትምህርት ቤት ትከፍላለች የ 10ኛ ክፍል ጎበዝ ተማሪ ነኝ ጎበዝ ስለሆንኩ ተማሪዎቹም አሰተማሪዎቹም ይወዱኛል ድህነቴ ትዝ አይላቸውም እኔም የእናቴን ምኞት ለማሳካት በርትቼ አጠናለው እማራለው በትርፍ ጊዜዬ እናቴን አግዛታለው  ከትምህርት ቤት እምደተመለስክ የተቀዳደደ ሱሪዬን ለብሼ ወደ ስራ እሄዳለው እናቴን ማገዝ ግዴታዬ ስለሆነ,.
  
     በትምህርት ቤታችን ውስጥ በጣም የዋህና ምስኪን ሜላት ናት አንዳንዴ ምሳ ስለማልቋጥር የሷን ምሳ አብረን እንበላለን ብቻ ጥሩ ልጅ ነች በጣም ተቀራርበናል የኔ ማንነትና እሷ ግን በፍፀም አይገናኝም ሰማይና ምድር ነበር ነገር ግን በሁለታችን ልብ ውስጥ ፍቅር ተፈጠረ,
   
       እኔና ሜላት የፍቅር ግንኝነት ጀመርን እኔ የድሀ ልጅ ነኝ እሷ ግን የሀብታም ልጅ ነች በፍቅር ግን ሁለታችንም እኩል ነን ሀብታሞች,የሚገርመው ድህነቴን እያወቀች ለደቂቃ ተከፍታብኝ አታውቅም ሁሌም አብራኝ ነች የምንኖርበት የሸራ ቤት እንኳን ደብሯት አያውቅም ብቻ ሁለታችንም በፍቅር  ክንፍ ብለናል,
       
       የትምህርት ክፍላችን አንድ ስለሆነ በትምህርት  በደረጃና በእውቀት ትንሽ በለጥ ስለምላት እረዳታለው እኔም የእናቴን አላማና ፍላጎት ለማሳካት በደንብ እየተማርኩ ነው አስረኛ ክፍልን ማትሪክ ተፈተንን,ሁለት ወር ክረምትን ሜላት ከቤት ብዙም መውጣት ስለማይፈቀድላት በሳምንት አንዴ እየተገናኝን ቀጠልን ተነፋፍቀን ስንገናኝ ደስ ይለኛል ሁለት ወር ክረምትን እኔ የቀን ስራ እየሰራሁ እናቴን ያንኑ ስራዋን እየሰራች ቤት ተከራየን ከዝናብ ብቻ የምታድን ትንሽዬ ቤት በ100 ብር አገኝንና እዛች ውስጥ መኖር ጀመርን አሁን ጎርፍ መጣ አልመጣ ሀሳብ የለም ብቻ ተመስገን ነው .
 
        ሜላት ቤተሰቦቿ ሳያዬ ልብስም እቃም ታመጣለች የማይፈልጉትንም ታመጣልናለች ደስተኛ ባልሆንም እምቢ ማለት ግን አልፈልግም  እምቢ ስል አንዳንዴ ሲከፋት ሰለማይ ነበር  ዝም የምላት መድረስ አይቀር መስከረም ደረሰ የማትሪክ ውጤት መጣ,.......


    ይቀጥላል✍🏻
👉 
https://www.tg-me.com/yefeker_tiksoche
👉 
https://www.tg-me.com/yefeker_tiksoche
👉 
https://www.tg-me.com/yefeker_tiksoche
​​የድሀ ፍቅር
ክፍል 2

#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ,
    ክረምት አልቆ መስከረም ሲጠባ አዲስ ተስፋ አዲስ አመት ተጀመረ የማትሪክም ውጤት መጣ .በሚገርም ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ነበር ያለፍኩት .ደስ የሚል ዜና እናቴ ይሄንን ስትስማ የሚሰማትን ደስታ ሳስብ በጣም ተደሰትኩ .,ሜላትም አልፋለች በከፈተኛ ውጤት ባይሆንም ጥሩ ሰርታለች ሁለታችንም ተደሰትን ኦ አምላኬ ነገን አንተ ታውቃለህ አልኩ በልቤ!!

   ሜላቴ እናቴጋ መሄድ አለብኝ አልኳት አብረን እንሂድ አለችኝ እሽ ብያት እናቴ ጋ ሄድን እናቴ ገና ከውጪ ስታየኝ ፊቴ በደስታ መሞላቱን ስታይ እልልታዋን አቀለጠችው ተንበርክካ ጌታ ሆይ አንተ ታውቃለህ አለች!!የደስታ እንባ በጉንጮቻ ላይ ኮለል ብለው ወረዱ እኔም ተንበርክኬ እናቴን አቀፍኳት በደስታ ተላቀስን ,"እናቴ ገና አኮራሻለው"አልኳት በጆሮዋ የደስታ እንባ እየተናነቀኝ,.

    ሜላት ፍዝዝ ብላ የሚሆነውን ሁሉ ታያለች እሷም ግን በቁሟ እንባዋ ይወርድ ነበር ,እኔና እናቴ ተቃቅፈን ተነሳን እናቴ በቃ ቤተክርስትያን ተሳልሜ ልምጣ ገብርኤል ስለቴን ሰምቷል ብላ ነጠላዋን አንጠልጥላ ከቤት ተመስገን ተመስገን!!እያለች ሄደች ,ናቲ ,"አይገርምህም እኔም እንዳንተ ጅግና ነው የምሆነው"ብሎ መጥቶ ተጠመጠመብኝ .,ጎበዝ እንደዚህ አስብ እሽ ብዬው መጣሁ እዚሁ ሁን ብዬው ሜላትን ልሽኝ ወጣሁ,.

   ሜላት የሆነ ነገር ውስጧን እየከነከነው ነው ግን ምን እንደሆን አላውቅም.ወደ ኪሷ ገብታ 20 ብር አውጥታ እንካ አለችኝ ምን ላድርገው አልኳት ካፌ ገብተን ትንሽ እናውራ አለችኝ እሽ አልኳትና ብሩን ወደ ኪሴ ከተትኩት.,

   ካፌ ገብተን ሻይ አዘዝን ታውቃለህ ፍቅሬ የናንተ ቤተሰብ በጣም ያስቀናል አለችኝ መሬት መሬት እያየች .እኔ አሁን እቤት ስገባ ማለፍና መውደቄን እንኳን አልጠየቅም እንኳን ይሄን ያክል ፍቅር ላይ ይቅርና አሰቀንታችሁኛል አለችኝ እንዳቀረቀረች,.እኛ ቤት ንፁህ ፍቅር እንዳለ አውቃለው የሷን ስትነግረኝ ግን ግራ ገባኝ.,ብቻ በፍረሀት ለምን?አልኳት .እ!አለች,.እኛ ቤት ማንም ስለምይንም አይጨነቅም ትማራለህ ካልተሳካልህ የፈረደበት የአባቴ ካንፖኒ አለ እዛ ትገባለህ በቃ ይሄ ነው አለችኝ በንዴት,.

    አሁን ደግሜ ሌላ ጥያቄ ለመጠየቅ አልደፈርኩም ዝም አልኩ ለማንኛውም እንሂድ አለችኝ እሽ ብያት የሰጠችኝን ብር ከኪሴ አውጥቼ ከፍዬ ከካፌው ወጣ እሷን ታክሲ አስይዜ ቻው ተባብለን ተለያየን,.

     ወደ ቤት እየተመለስኩ ብዙ ነገሮችን አሰብኩ ለምን ቤተስብ ፍቅር የለውም ,ለነገሩ ገንዘብ ስላላቸው ባይማሩስ ሜላትም ዝም ብላ ነው የምትደክመው ምናለ እኔ የነሱ ቤተሰብ በሆንኩ.,!አይ ተመስገን እንኳንም አልሆንኩ የእናቴ ፍቅር ከገንዘብ በላይ ነው ::እያልኩ ወደ ቤቴ ገባሁ .,እቤት ስደርስ እናቴ ብና አቀራርባ ሻማ ገዝታ ጠበቀችኝ ደስ አለኝ ,"እናቴ እወድሻለው"ብዬ ግንባሯን ስሜ ተቀመጥኩኝ.,
 
    እናቴ ደስ ስላላት ደስ ብሎኛል,በቃ እናቴ ከዛም ከዛም ብላ ያጠራቀመቻትን ብር ሰብስባ ዬኒፎርም ልታሰፋልኝ ስታስብ ሜላት ዬኒፎርሙን ቀድማ አሰፍታ አመጣችልኝ በጣም ሰነገጥኩ እኔ ከዚህ በላይ እንድትረጂኝ አልፈልግም አልኳት,ሜላት ግን በቃ እሽ ብላ ዬኒፎርሙን ሰጥታኝ ከቤት ቻው ብላ ሄደች.እናቴ ደነገጠች እኔም ተከትዬ ሳልሸኛት  ፈዝዤ ቀረሁ..........

    ይቀጥላል✍🏻
👉 
https://www.tg-me.com/yefeker_tiksoche
👉
https://www.tg-me.com/yefeker_tiksoche
👉
https://www.tg-me.com/yefeker_tiksoche
​​የድሀ ፍቅር

                   Part 3
#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ.,

እናቴ በክረምት ወራት ሰርታ ያጠራቀመችውን ብር
ሰብስባ
ዩኒፎርም ልታሰፋልኝ ስታስብ
.ሜላት ቀድማ ዩኒፎርም አሰፍታ አመጣችልኝ
ደነገጥሁ ለምን
ገዛሽ ?እኔ እንድትረጂኝ አልፈልግም::አልኳት
ተቆጥቼ .ሜላትም ፊቷን አዙራ ከቤት
ወጣች .ስቆጣ ሰምታኝ
የማታውቀው እናቴ ደነገጠች.እኔም ሜላትን
ከመከተል ይልቅ
ፈዝዤ ቀረሁ,....
ድንገት ታናሽ ወንድሜ ገፍትሮኝ ወደ ውጪ ሲሮጥ
ብንን
እንደማለት አልኩ .እንደዛው
እንደቆምኩ ብዙም ሳልቆይ ታናሼ ምን እንዳላት
ባላውቅም
ሜላትን ይዟት መጣ .እስኪ ዞር
በል እንግባበት,ብሎኝ ይዟት ገብቶ ያለችው
መቀመጫ የኔ
የበሰበሰች ፈራሽ ላይ ተቀመጭ
አላት,.
እኔ አሁንም ፈዝዣለው እማዬ ቡና አፍይ እስኪ
አላት እናቴ እሽ
ብላ ተፍ ተፍ ማለት
ጀመረች.አቦ አትቁምብና ና ተቀመጥ!!አለኝ እሽ
ብዬ ሜላት ስር
ቁጭ አልኩ ለማየት
ፈራኃት .እንዳቀረቀርኩ ይቅርታ አድርጊልኝ ሜላት
አጥፍቻለው
አልኳት ,!አይ ችግር
የለውም !!አለችኝ ካጎነበስኩበት ቀና ብዬ አየኃት
.እውነትሽን
ነው አልኳት አዎ
አልችኝ,.እጆቿን ያዝ አድርጌ ሜላትዬ እውድሻለው
አፈቅርሻለው
ግን በገንዘብ እንድትረጂኝ
ሳይሆን ንፁህ ፍቅርሽን ነው የምፈልገው አልኳት
አይናይኗን
እያየሁ.
እየውልህ የኔ ውብ እኔ እየረዳሁህ አይደለም
ማደርግ
ስለፈለግሁ እንጂ ደግሞ ካንተና
ከእናንተ ቤተሰብ የማገኘው ፍቅር ከሺ ሚልዮን
ብር በላይ
ደስታን ይሰጣል .አትበሳጭብኝ
ይቅርታ እሽ አለችኝ .,ታናሽ ወንድሜ ጣልቃ
በመግባት እድሜ
ለኔ መለስኩልህ ፈዛዛ ይኸኔ
እቤቷ ደርሳ ነበር አለኝ ተሳሳቅን ቡና ተፈላ ቤት
ያፈራውን
ቀማመስን በቃ ደስተኛ ሆነን
አመሽን በጣም ማምሽት ሰለማይፈቀድ ሜላቴንም
ወደ ቤቷ
ሸኘኃት.....
እኔም እሷን ሽኝቼ ቤተክርስቲያን ተሳልሜ ወደ ቤቴ
ተመለስኩ..እናቴም ዩኒፎርም
ስለተገዛላት ያለው ብር ለደብተርና እስክርቢቶ
ይሆናል ተመስገን
አለች.ዞር ብላ አንተ ከዚህ
በኃላ እንደዚህ ጮኸህ ስትቆጣ መስማት
አልፈልግም
አለችኝ.እሽ አልኳት,.
ቀናቶች ሄደው የትምህርት መሳሪያዎቼን አሟልቼ
ትምህርቴን
ጀመርኩ ሜላቴም እኩል
ጅመርን አንድ ክፍል መሆን ፈልገን ነበር ግን
አልተሳካም
መምህሮቹ አልፈቅድ አሉ ይሁን
ብለን በክፍል ተለያየን ግን እርፍት ሲሆን እኔ
ቀድሜ ቀወጣሁ
እነሱ ክፍል በር ላይ
እጠብቃታለው እሷም ከቀደመች እንደዛው .ደስ
የሚለው
ሁላችንም ዩኒፎርም ስለምንለብስ
የድሀ የሀብታም ልጅ ብሎ ነገር የለም .የሚበላ
ስንፈልግ ሜላት
ብር ሰጥታኝ እኔ
እከፍላለው .,
እኔና ሜላት ተለያይተን አናውቅም እኔም ከእሷ
ውጪ እሷም
ከእኔ ውጪ ትምህርት ቤት
ውስጥ ጏደኛ የለንም.ተማሪዎች ሁሉ ይቀኑብናል
.እሷ ቆንጆ
ነገር ስለሆነች ሌሎች
ይመኟታል እሷ ግን ከኔ ውጪ ማንንም
አትፈልግም.,እኔም
እንደዛው.
ከትምህርት ቤት ውጪ እኔ እናቴን ለማገዝ ስራ
ስለምሰራ
ብዙም አንገናኝም ጥናት
ካለብን ግን አብረን እናጠናለን ጥናት ስንጨርስ
ወክ አድርገን
እንለያያለን እናቴም
አብሮነታችን በጣም አስደስቷታል ደስተኛ ነች
እኔም እንደዛው
.አንድ ቀን ፈተና ስለደረሰ
ስናጠና ቆይተን ልሸኛት ወጥቼ ሻይ ቡና እንበል
ብላኝ ካፌ
ውስጥ ተቀምጠን ያላሰብነው
ሰው ድንገት መጣብን..........................
ይቀጥላል ...
.......ሄድሽ በቃ፠
  
ልቤ ሲመፃደቅ እሷ አለች ብሎ
ግን እየተሰማው አንድ አካሉ ጎሎ
አመሻሹን ሲያመው ልቤን እየዋለ
ካንቺ ፍቅር ሌላ አልቀበል አለ
አንድ ቀን ጠየኩት ልቤን በዝግታ
"ምንስ አስነካችህ ምንስ አሳስታ"
እሱ ግን አለፈኝ በአሳዛኝ ዝምታ
"በል አሁን ይብቃ አውጣት ቶሎ ብለህ
የፍቅሯን መቀነት ወደዚያ ጋ ጥለህ"
እርሷን ስለመርሳት ሳማክረው ውዬ
ንግግሬን ጨረስኩ አምስት ነጥብ ብዬ
አፉንም ከፈተ ነገረኝ ያለውን
አይኔ ያያት እለት የላከበት ጣሩን
እንዲህም አለ ጀመረ ወሬውን
"አይንህ እንዳስገባት ምን አለ ባወጣት
እርሳት ትለኛለህ ሳትጠብቅ ለከት
ምንሆንክ አንተማ ምንህስ ተነካ
ምኗን እንደወደድኩ አልገባህም ለካ
የውጪ ገፅታ ሀሰተኛ ውበት
የታዘለ በፊት ጠፊውን ደምግባት
አይደለም ለእሷ እኔ የምመኝላት
አለ እንጂ ከውበት በላይ ውበት
የተፈጠረች እለት የተሰጣት በገነት ፈጣሪዋን መምሰል ነው የሚያስብላት ውብ ናት
እግዚር መልካም ሆኖ መልካም እንዳረጋት
የተረዳችና የሆነችው ውብ ናት
እሷኮ ክብሯን የጠበቀች
እንደ ሌሎች ሴቶች ያልተገላለጠች
እቺን አጥቼማ እንዴት አላለቅስም
በብዙ ልቦች ፊት ቆሜ ማቅ አለብስም"
ልቤን ተረዳሁት ተናግሮ አበቃ በሲቃ
ግን ቆይ አንቺ........ሄድሽ በቃ😔

     
🍂🍃 የድሀ ፍቅር 🍃🍂

                  ክፍል4

#በእውነትኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ.//

እኔና ሜላት ፈተና ስለደረሰ ሰናጠና አምሽተን
ልሸኛት
እንደወጣሁ ካፌ ሻይ ብና እንበል
ብላኝ ገብተን ቁጭ እንዳልን ድንገት የሜላት አባት
ከፊት
ለፊታችን ድቅን አሉብን ... እኔ ሰለማላውቃቸው
ዝም አልኩ
ሜላት ተርበተበተች ማ..ማነዉ አልኳት ? በጣቶቿ
አፏን
ተመተመች ዝም በል ለማለት ነበር...
ሜላት ከመቀመጫዋ ተነስታ አ...አባቢ አለች
እየተርበተበተች
... አባቢ ስትል ቀልቤ ግፍፍ አለ ..
ደግነቱ ዩኒፎርሜን ከላይ ያለውን አላወለቅሁትም
ነበር። የየየክፍሌ ተማሪ ነው ስናጠና ቆይተን ሻይ
ብና
እንበል ብለን ነው አለች እየተርበተበተች...
አባቷም ሰላምታ አይቀድምም ልጄ አሉ ...
ይቅርታ አባቢ ብላ አቅፋ ሳመቻቸው .እኔም
ከመቀመጫዬ ተነስቼ ሰላም አልኳቸው.
የሜላት አባት ሰላም ብለውን በጊዜ ግቢ ቻው
ብለውን ሌላ
ወንበር ወደ አለው ጏደኛቸው
ሄዱ .,እኔና ሜላት ደንግጠናል ያዘዝነው
መጥቶልን ቶሎ ቶሎ
ጠጣን አባቷ ቀድመው ሂሳብ
ከፍለውልን ስለነበር ቻው ብለናቸው ተያይዘን
ወጣን.,.
ሜላት ፊቷ ላይ የፍረሀት ስሜት ይነበባል ሜላቴ
ምን ሆንሽ ምን
እያሰብሽ ነው አልኳት።
አባቢ... አለች አባትሽ ምን? ኡሁን እቤት ስገባ
ጭቅጭቁ
አይጣል ነው አለች በፍረሀት። አይቆጡሽም
አስጠኒዬ ነው
በያቸው ባይሆን ሁለተኛ አብረን
እንዳያዬን እንጠነቀቃለን
አልኳት እሽ አልችኝና ግንባሯን ለመጀመርያ ጊዜ
ስሜ ተለየኃት.,
ሜላትን በታክሲ ሽኝቼ እኔ ወክ እያደርግሁ ወደ
ቤት ተመለስኩ
ግን የሜላትዬ ፍርሀት እኔን
አሳሰበኝ አባቷ ይቆጡ ይሆን ብዙ ነገሮችን
አሰብኩ .ምክንያቱም
የሜላት ቤተሰቦች
ሀብታም ስለሆኑ ልጃቸው ደግሞ ከእንደኔ አይነት
መናጢ ድሀ
ጋር የፍቅር ግንኝነት
እንዳላት ቢያውቁ ከባድ ነው የሚሆነው...
አምላኬ አደራህን
ብዬ እቤቴ ገባሁ መንጋት አይቀር ነጋ...
ጠዋት ትምህርት ቤት ቶሎ ሄድኩ በሩ ላይ
ጠበቅኃት እሷም
እንደምጨነቅ ስለገባት
በጠዋት መጣችልኝ ደስ አለኝ ቶሎ ብዬ ምን
ተፈጠረ አልኳት
.,ሰላም በለኝ እንጂ ቅድሚያ
አለችኝ አቅፌ ሳምኳት .ምንም አልተፈጠረም
አባቢ ምንም
አላልኝም አለችኝ በጣም
ተደሰትኩ ለሚቀጥለው እንጠነቀቃለን አልኳትና
ተያይዘን ወደ
ትምህርት ቤቱ ግቢ ገባን,.
እኔና ሜላቴ ፍቅራችንን በድብቅ አድርገን
መዝናናትም ስንፊልግ
ደበቅ ያለ ቦታ እየሄድን
እንዝናናለን .አብዛኛውን ጊዜ ግን እኛ ቤት ነው
የምናሳልፈው.አመቱ አልቆ ተፈትነን ውጤት
መጣ ሁለታችንም አልፈናል ደስ የሚል ነገር
ተመስገን
አልተነጣጠልንም.,
ሁለት ወር ክረምትን ያው እንደተለመደው እኔ
እናቴን በማገዝ
አሳለፍኩ ከሜላትም ጋ አልፎ
አልፎ እቤት እየመጣች ካልሆነም ማታ ማታ እነሱ
ሰፈር
ቤተክርስቲያን ውስጥ
እንገናኛለን..በቃ ደስ በሚል መዋደድና መፈቃቀር
አብረን
ቀጠልን .,
አዲሱ አመት ገብቶ ትምህርት ጀመርን 12ኛ
ክፍልን በጣም
መጠናት እንዳለበት
ስለማምን ብዙ ጊዜያችንን በጥናት ነው
የምናሳልፈው .ሜላትም
ከኔ ጋር ታጠናለች
በርትተን መማር እንዳለብን ሁለታችንም
እናምናለንና .,ስለዚህ
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል
እናጠናለን.
እኔ ስናጠና ስለ ትምህርት ወክ ስናደርግ ስለ ነገ
ተስፋ ነው
የማስበው ወደፊት ምን
ማድርግ እንዳለብኝና ምን መሆን እንደምችል ብዙ
ነገር ሜላትን
እንደማገባት ነው
የማምነው ,.ሁሌም ስለያት ወይ ግንባሯን ወይ
አንገቷ ስር ስሜ
እለያታለው....
አንድ ቀን ማታ ልሽኛት ታክሲ ተራ ቆመን ሜላት
ፊቷን ሳይ
አኩርፋለች ምነው
ሜላትዬ ምን ሆነሽ ነው አልኳት.,ሳመኝ አለችኝ
አይናይኔን
እያየች ,.እ!! አልኳት ሳመኝኝኝኝ!
አልቸኝ ግንባሯን ሳምኳት ,ኡፍ ብላ ተበሳጨች
,ትዝ ሲለኝ እእ....እ
....... ይቀጥላል....
​የድሀ ፍቅር

ክፍል 5
#በእውነተኛ_ህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ/

ሜላትን ልሽኛት ታክሲ ተራ ቆመን ታክሲ
እየጠበቅን ነው ሜላት
ፊቷን ጥለዋለች ሳመኝ
አለችኝ ግንባሯን በስሱ ሳምኳት ይበልጥ
አኮረፈች ሁሌም
ስሽኛት ግንባሯን ስሜ ነው
የምለያት .ግን ማኩረፏ ስላስደነገጠኝ ጉንጭና
ጉንጫን በእጆቼ ይዜ ከንፈሯን ሳምኳት ደስ
አላት ለመጀመርያ ጊዜ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው
,.
ድንገት አጠገባችን መኪና ሲጥጥ ብሎ ቆመ
ደንግጠን ዞር
ስንል የሜላት አባት መኪና ነበር
ነይ ግቢ የሚል አጭር ቃል ,ሜላትም እሽ ብላ
ቻው ብላኝ ወደ
መኪናው ገባች አባቷ እኔን
ገላምጦኝ መኪናውን አስነስቶ ሄደ.,
ወይኔ አምላኬ ምናለ ባልሳምኳት ብታኮርፍ ይሻል
ነበር ብዬ
አሰብኩ ቀኑ አርብ ስለነበር
ቅዳሜና እሁድ እንዴት ሊያልፍ ነው ስልክ እንኳን
የለኝ ብቻ
ጨነቀኝ እቤት ገብቼ ለእናቴ
የተፈጠረውን ነገርኳት አዘነች ግን በቃ አይዞህ
አምላክ ያለው
ይሆናል አለችኝ ,እሽ አልኳት
በማግስቱ እነ ሜላት ሰፈር ቤተክርስቲያን ሄድኩ
ሜላት የለችም
ጨነቀኝ ምን ተፈጥሮ
ይሆን አላውቅም ሜላት ግን የለችም.,እሁድም
አላገኝኃትም
ይበልጥ ጨነቀኝ.,
ሰኞ ጠዋት በጠዋት ተነስቼ ትምህርት ቤት ሄድኩ
ሜላት ግን
የለችም ተደውሎ ወደ
ውስጥ እየገባሁ እያለ አንድ መኪና መጥቶ በር
እኛ ክፍል በር ላይ ስደርስ ሜላት ከየት
እንደመጣች ሳላውቅ
መጥታ ተጠመጠመችብኝ
ከንፈሬን አንገቴን አይኔን
ሁሉ ነገሬን ሳመችኝ ደህና ነህ ይቅርታ ይቅርታ እሽ
አለችኝ ምን
ተፈጠረ ምን ሆነሽ ነው
አልኳት ለረፍት ሰአት እነግርሀለው አሁን እንግባ
መምህር
ሳይገባ አለችኝ እሽ አልኳትና
እሷም ወደ ክፍሏ እኔም ወደ ክፍሌ ገባን.,
የእረፍት ሰአት ደርሶ ሜላትን አግንቻት
የተፈጠረውን
እስክትነግረኝ ቸኩያለው በጣም
ጨንቆኝም ነበር ,መማር ሳይሆን መፍዘዝ ሆነ
ሰአቱን መግፋት
ብችል ገፍቼ አሳልፈው ነበር
ግን አልቻልኩም ,የእረፍት ሰአት ደረሰ መድረስ
አይቀር ወጥቼ
ልክ ሳገኛት ተጠምጥሜ
ሳምኳት ምንድነው የተፈጠረው ንገሪኝ አልኳት እሽ
አለችኝና
ቁጭ አልን,.
ሜላት ከቤተሰቧ ጋር ትልቅ ብጥብጥ
እንደተፈጠረና ሁለተኛ ከኔ ጋር ከታየች ችግር
እንደሚፈጠር ነግረዋት ሰለነበር አንተንም
እንዲጎዱህ
ስለማልፈልግ ነው የጠፋሁት
ጠዋትም ወንድሜ እንዳያይህ ብዬ ነው ዝም
ብዬህ የገባሁት
ከዚህ በኃላ ከ ትምህርት ቤት
ውጭ መገናኝት የምንችል አይመስለኝም
ምናልባት ማታ ማታ
ቤተክርስቲያን እንገናኛለን
አለችኝ እሽ ብቻ አንቺ ምንም አትሁኚብኝ አልኳት
.,
ሜላትም ከቦርሳዋ ውስጥ አንድ ትንሽዬ ስልክ
አውጥታ በዚህ
ስልክ እንደዋወል አለችኝ
እሽ አልኳት በቃ ከልቤ እንደምወዳትና ብትለየኝ
እንደምጎዳ
በደንብ ገባኝ ከዝይች ቀን
ጀምሮ በስልክ ወይም ትምህርት ቤት ካልሆነ
በስተቀር ሌላ ቦታ መገናኝት አቆምን ሜላት
ማጥናት ትታለች በቃ ከኔጋር ለምዳ ብቻዋን
ማጥናት
አልቻለችም.,
የማትሪክ 12ኛ ፈተና እየደረሰ ነው እኔ በጥናት
ተወጥሪያለው
ሜላት ግን ማጥናት ትታ
እቤት ነው የምትውለው እኔም በምን መልኩ
ላስጠናት
እንደምችል ግራ ገብቶኛል ,ማታ
ነው ስልክ ደወልችልኝ አወራን ምንም
እንዳላጠናች ነገረችኝ
አጥኚ ነገ ከትምህርት መልስ
እንደምትቆይ ተናገሪና እናጠናለን አልኳት እሽ
ብላኝ ቻው
ተባብለን ስልኩ ተዘጋ..በድጋሚ
ስልኬ ጮኸ የማላውቀው ስልክ ነበር,........

ይቀጥላል.......
#የድሀ_ልጅ_ፍቅር
ክፍል 6

#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

እኔና ሜላት በስልክ ስናወራ ቆይተን ነገ ቤተስብን
አስፈቅደሽ እናጠናለን ብያት ስልኩ ተዘጋ። ስልኩን
እንደዘጋሁት ሌላ ስልክ ተደወለልኝ የማላውቀው
ስልክ ነበር ዝም አልኩት። ደግሞ ተደወለልኝ ግራ
ገባኝ ከሜላት ውጪ ይሄንን ስልክ ማንም
አያውቀውም... በሶስተኛው አነሳሁት በር ላይ ነኝ
ውጣ የሚል ጎርናና ድምፅ.. ማን ልበል ስለው
ውጣ! ብሎኝ ስልኩን ዘጋው። ደነገጥሁ! ለእናቴ
ሳልነግር መጣሁ ብዬ ወደ ውጪ ወጣሁ አንድ
ግብዳ ሰውዬ በር ላይ ቆሞ አገኘሁት። አቤት ማን
ልበል? አልኩት.. ና! አለኝ ቆጣ ብሎ ተጠጋሁት
ስልክህን! አለኝ.. አልሰጥም አልኩት ! አምጣ !!
ብሎ ጮኸ ሰጠሁት 'ስማ ከዚህ በኃላ ከሜላት ጋ
እንዳላይህ ካየሁህ ግን ከምድርገፀ ነው
የማጠፋህ' አለኝ። ወዲያው ከፊት ለፊት የመኪና
መብራት በረጅሙ በራ ወደኛ ተጠጋ። የመኪናው
መብራት አይኔን እየወጋኝም ቢሆን የግዴን
አየሁት... የሜላት ወንድም ነበር መኪናው
ውስጥ የነበረው። አጠገቤ የነበረውም ግብዳ
አስፈሪ ሰውዬ ካስጠነቀቀኝ በኃላ መኪናው
ውስጥ ገብተው ሄዱ።
ሜላት የሰጠችኝ ስልክ አዲስ ሴም ነበር ግን
ከስልኳ ውስጥ
ነበር ስልክ ቁጥሩን የወሰዱት በስልክ
እንደምንገናኝና ትምህርት ቤትም አብረን
እንደምንውል፣ ቤተክርስትያን እንደምንገናኝም፣
በደንብ ያውቃሉ። ምክንያቱም በቅርብ እርቀት
ይከታታሉን ስለነበር። በጣም አዘንኩ ትንሽ በር
ላይ ከቆምኩ በኃላ ወደ ቤት ገባሁ ለእናቴ
ሁሉንም ነገር ነገርኳት። በቃ ይቺ አመት
እስክትጠናቀቅ ድረስ አብራችሁ አትሁኑ አለችኝ
ግን እንዴት አድርጌ... አንድ ቀን ጠዋት ተነስቼ
ቤተክርስቲያን ደርሼ ስመጣ የስራ ማስታወቂያ
ለማንበብ ጠጋ ብዬ ቆምኩ ድንገት አይኔ
ተወርውሮ አንድ ስራ ላይ አረፈ እነ ሜላት ሰፈር
ካሴት(cd)ፊልም ማከራየት የወር ደሞዝ 150
ብር ይላል ደስ አለኝ ወዲያው ሄጄ ተነጋገርኩ ስራ
ስላልነበረኝ እዛ ተቀጠርኩ። ስልክ ቤት ሄጄ
ለሜላት ነገርኳት ደስ አላት ፊልም ለመክራየት
እየመጣች እንደምንገናኝ ተነጋገርን።
እቤት ሄጄ ለእናቴ ሁሉንም ነገርኳት ግን ክፍያው
በቂ አይደለም
ጫማ ብጠርግ በቀን ከ150 ብር በላይ አገኛለው
ብቻ ትንሽ
ጊዜ ልየው ብዬ አሰብኩኝ። እናቴ ደስ ያለህን
አድርግ
አለችኝ። ስራ ጀመርኩ.. ከሜላትም ጋ መገናኝት
ጀመርን ስናፍቃት መጥታ አይታኝ በአይን አውርተን
እንለያያለን። እኔም ከቀጠረኝ ሰዉዬጋ ተነጋግሬ
በር ላይ ጫማ መጥረግ ጀመርኩ። ታናሽ ወንድሜ
ፊልም ማከራየት ጀመረ።
እንደምንም ብለን ሁለት ወር ክረምት እየተገፋ
ነው እኔም
የአቅሜን እየሰራሁ ጫማ እየጠረግሁ ጎን ለጎን
የሞባይል ካርድ ማስቲካ ሌሎች ትናንሽ ነገሮችን
እየሸጥሁ ነው። እናቴ የሰው ቤት እንጅራ
መጋገርና ልብስ ማጠብ ትታ ሆቴል አንሶላ
ማጠብና አልጋ ማስተካከል ትሰራለች። ባለቻት
ሰአት ደግሞ ሽንኩርት ቃሪያ ድንች ትቸረችራለች
ተመስገን አሁን ነገሮች እየተስተካከሉ ነው።
ሁለት ወር ክረምት አለፈ የማትሪክ ውጤት
ሊመጣ ነው ውጤቱ ምን እንደሚሆን አይታወቅም
ብቻ አሪፍ ውጤት አምጥቼ እንደማልፍ እርግጠኛ
ነኝ ከፈጣሪ ጋር !. ሜላቴም እንድታልፍ ፀሎቴ
ነው! ብቻ መድረሱ አይቀር የማትሪክ ፈተና መጣ
ሲባል እኔም ሜላትም ተያይዘን ውጤት ለመቀበል
ሄድን።
ውጤትም ተቀበልን ግን ...............

ይቀጥላል...........
🍃🍂የድሀ ፍቅር🍂🍃

ክፍል 7⃣

#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

... የማትሪክ ፈተና መጥቶ እኔና ሜላት ውጤት
ለመቀበል
ትምህርት ቤት ተገናኝን። የማትሪክ ውጤት
ቅድሚያ የኔ ወጣ ደስ የሚል ውጤት አምጥቼ
አለፍኩ በጣም ደስ እለኝ ሜላትም
ደስ አላት። ከቆይታ በሁዋላ የሜላትም ውጤት
መጣ.. በሚያሳዝን ሁኔታ ሜላት ግን አላለፈችም
ነበር... በጣም ያሳዝናል! አዘንኩ!
አብረን እንደምንቀጥል ነበር የማስበው በቃ ግን
አልሆነም፤
ሜላት በውጤቷ ብዙም አልተበሳጨችም ይልቅስ
የኔ ማለፍ
አስደስቷታል። እኔ ግን አዝኛለው። ውዴ አለችኝ
እንደከፋኝ አውቃ ወዬ አልኳት.. አየህ የእኔ
መውደቅ አሪፍ ነው
ምንክያቱም ባልፍ እንኳን አንድ ዮኒቨርሲቲ
ላይደርሰን ይችል
ነበር... እኔ እዚህ ከሆንኩ ግን ቢያንስ አንተጋ
እየመጣሁ እጠይቅሀለው የፈረደበት የአባቴ
ድርጅት አለ እዛ መቀጠር
እችላለው ለእናትህና ለወንድምህም እኔ ቅርብ
ሆኜ
እንከባከባቸዋለው አለችኝ።
ከሜላት ያልጠበኩትን ነገር ስሰማ በጣም
ደነገጥኩ ይከፋታል
ብዬ አስቤ ነበር በተቃራኒው ግን አልከፋትም።
እሽ! ብያት ተያይዘን እኛ ቤት ሄድን ለእናቴ የኔ
ማለፍ አስደሰታት ሜላት እንዳላለፈች ስታውቅ
አዘነች ግን ሁሉም ለበጎ ነው። እናቴ
እንደተለመደው ነጠላዋን አንጠልጥላ ወደ
ቤተክርስቲያን ሄደች። እኔና ሜላትም ያበጠው
ይፈንዳ ብለን ተያይዘን ዘና ለማለት ሄድን። ያን
ጊዜ ግን ብር ስለነበረኝ እኔ ልክፍል አልኩ
ሜላት አልፈቀደችልኝም!
እኔና ሜላት ስንዝናና ውለን መሽቶ ልንለያይ ስንል
የባንክ
አካወንት መክፈት እንዳለብኝና አንዳንድ ነገሮችን
ማስተካከል መጀመር እንዳለብኝ ነገረችኝ።
ብዙም ሳይቆይ በሜላት ሀሳብ አመንጪነት
ተያይዘን ለመዝናናት ከከተማ ወጣን።
በሕይወቴ የማልረሳቸዉ ሁለት ድንቅ ቀናት
ካሳለፍን በኧላ ወደ አዲስ አበባ ተመለስን። ነገ
ማታ እቤት እመጣለው ብላኝ ተለያየን...
በማግስቱ ማታ ሜላት እቤት መጣች በእጆቿ
ፊስታል
አንጠልጥላለች ተቀብያት ገብታ ተቀመጠች ገና
ከመቀመጧ ምንም እንዳትለኝ አለችኝ በፍረሀት
ምንድነው አልኳት።
ፌስታሉን ፈትታ ለቢጃማ የሚሆን ቱታ የውጪ
ቲሽርት ጅንስ ሱሪ ጫማ ቦርሳ ስልክ ሳይቀራት
ገዝታ ነበር የመጣችው ምን ልበል ምንም
እንዳትል ብላ አስጠንቅቃኛለች ዝም አልኩ
አመስግናለው! ከማለት ውጪ...
ሜላት ለኔ ከምንም በላይ ነች! በርትተህ ተማር
እኔም እየመጣሁ እጠይቅሀለው እነ ማዘር
ከናፈቁህ አንተም በእረፍት ጊዜ መጥተህ
ታያቸዋለህ ብቻ ትኩረትህ ትምህርትህ ላይ
ይሁን አለችኝ። እሽ ማሬ አልኳት! እናቴም ተባረኪ
ልጄ አለቻት
በርታ እሽ ልጄ አለችኝ በስስት እያየች የእናት
እንጀት ሆኖባታል። ወንድሜም ስማ ለኛ
እንዳታስብ እሽ እኔ እንዳንተ ጎበዝ
እሆናለው አለኝ። እሽ እልኳቸው ሁላችንም እንባ
ተናንቆናል! ትንሽ አምሽተን ሜላትን ሸኘኃት።
የተለመደውን ግንባሯን አንገቷን ከንፈሯን ስሜ
ተለየኃት።
ዝግጅቴን አጠናቅቄ የዮኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ
ስለነበር ለመሄድ ወሰንኩ። ሜላትም እናቴና
ወንድሜ ሆነው ሸኙኝ። እንደምወዳቸው!
ነገርኳቸው ሜላቴ አፈቅርሻለው! አልኳት በቃ ቻው
ብዬ ተለየኃቸው። የሚያስፈልገኝን ሁሉ ይዤ ጉዞ
ጀመርኩ የብቸኝነት ህይወት አንድ ተብሎ
ተጀመረ።
እኔና ሜላት እንደዋወላለን ሜላቴ እዛው አባቷ
መስሪያ ቤት መስራት ጀምራለች። እኔም
ትምህርቴን የመጀመርያ አመት የኢንጅነሪንግ
ተማሪ ሆኜ ጀምርያለው። ነገር ግን አሁንም አንድ
ነገር አስባለው.......
 
#ይቀጥላል
​የድሀ ፍቅር
ክፍል 8⃣

#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

የአንደኛ እመት የኢንጂነሪንግ ተማሪ ሆኜ
ትምህርቴን ጀመርኩ ,ከቤተሰብ ተለይቻለው
ሜላቴንም በቀን ሰወስት ጊዜ በስልክ ሰለማወራት
እንጂ ናፍቃኛለች ,ለወንድሜ ትንሽዬ ስልክ ገዝታ
ሜላት ሰጥታው በሷ ይደውልልኛ በርታ እሽ እኔ
ለእናታችን አለውላት ይለኛል የእናቴንም ድምፀ
ስስማ ሰላም ይሰማኛል.,
ትምህርቴን በሚገባ እየተከታታተልኩ ነው
ምክንያቱም የእናቴን የወንድሜን የሜላትን ህልም
ማሳካት እንዳለብኝና በተራዬ እነሱን ማስደሰት
እንዳለብኝ አምናለው ለዛም ነበር በርትቼ
የማጠናውና የምማረው.ሜላት አባቷ መስሪያ
ቤት እየሰራች ነው በየ ወሩ ትንሽ ብር በባንክ
ታስገባልኛለች በቃ የምታደርግልኝ ነገር
ከአይምሮዬ በላይ ነው ,እሷ ለኔ የተሰጠች ልዬ
ስጦታ ናት,.
በዮኒቨርሲቲው ውስጥ ብዙም ጋደኛ አላፈራሁም
ምክንያቱም አንዳንዶቹ ልጆች የከተማ ልጅ
መሆኔን ይጠራጠራሉ,በዛ ላይ ለነሱ ስልጣኔ
ማለት መጠጣት መቃም ማጨስ ነው ያንን
ካላደርግሁ ለነሱ ፋራ ነኝ ስለዚህ ማንንም
መቅርብ አልፈልግም .አንዳንዴ ከዶርም ከወጣሁ
እንኳን ቤተክርስቲያን እንጂ ሌላ ቦታ የትም
አልሄድም መሄድም አልፈልግም,.
በዚህ ሁኔታ ግማሽ አመት ሆኖ ለእርፍት ወደ
አዲስ አበባ መጣሁ ሜላት ልምጣና ልጠይቅህ
ስትለኝ እምቢ ያልኳት እንድትንገላታ ስላልፈለግሁ
እንጂ ሳትናፍቀኝ ቀርታ አልነበርም ሁሉም
ተሰብስበው አገኝኃቸው ሜላት መኪና
ተገዝቶላታል ከከተማ ውጪ ግን አይፈቀድላትም
,ሳገኛቸው ደስ አለኝ አብረን ወደ እኛ ቤት ሄድን
ቤት ቀይረዋል ነገሮች ሁሉ ተስተካክለዋል ደስ
አለኝ እናቴም በቋሚነት የጉልት ስራ እየሰራች
ነው,.
የእረፍት ጊዜዬን ከቤትሰቤና ከሜላት ጋ በደንብ
አሳለፍኩ ቀኑ አልቆ ወደ ዮኒቨርስቲ አመራሁ በቃ
ትምህርቴን በደንብ እየተማርኩ ነው በማህል
ሜላት መጣች አብረን ዘና አልን ሁለት ቀን
ተቀምጣ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰች ,እኔም ወደ
ጥናቴ ተመለስኩ የ አንደኛ አመት በደረጃ ደስ
በምይል ውጤት ተጠናቀቀ,እኔም ቤተሰቤም
ተደሰትን,.
ወደ ቤተሰብ ተመለስኩኝ ሁለት ወር ክረምትን
በፍቅር አሳለፍን ሜላቴም አብራኝ ነች ከስራ
መልስ መኪናዋን ታቆምና በታክሲ እኛ ቤት
ትመጣለች አብረን አምሽተን እሸኛታለው ,በእኔና
በሜላት መሀከል ምንም አይነት መጋጨትም ሆነ
መኮራረፍ ተፈጥሮ አያውቅም በድህነቴ
እወዳታለው ከእነ ድህነቴ ትወደኛለች በቃ
ፍቅራችን እዚህ ድረስ ነው,.
የሁለት ወር ከርምት አልፎ ወደ ዮኒቨርሲቲ
ተመለስኩኝ ትምህርቴን በሚገባ መከታተል
ጀመርኩ ,በቃ ሜላት እየመጣች እየጠየቀችኝ
እኔም በእረፍት ጊዜ እየሄድኩ እያየኃቸው አመቱ
ተጠናቀቀ ክረምት ሆኖ ወደ ቤተሰብ ተመለስኩ
ሜላትን ግን አላገኝኃትም ነበር ,.
እቤት ሄጄ ሜላቴጋ ደወልኩ እመጣለው እቤት
ቅድም ስብስባ ሰለነበረ ነው አለችኝ ልቤ ፈራ
ማታ ደርሶ እስከምትመጣ ስጠቃት አመሸሁ
መጣች ተጠምጥማብኝ አለቀሰች ይሄን ያክል
ናፍቄሻለው ብዬ ቀለድኩባት አይ አይደለም
አለችኝ ልትነግርርኝ የፈለገችው ነገር እንዳለ
ከአይኗ እነበብኩ እንባዋ በጉንጮቿ ላይ መውረድ
ጀመሩ ግራ ገባኝ,........

ይቀጥላል ...
​​💕የድሀ ፍቅር❣️

ክፍል 9⃣

#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ👈

ሜላቴ እቤት መጥታ ተጠምጥማ ሰላም አለችን ከድሮዋ ተለውጣብኛለች ፈገግታዋ የለም እንዲያውም እንባዋ ቅርር ብሏል ,ሜላቴ የኔ ፍቅር ምን ሆነሻል አልኳት ,ከመቀመጫዋ ተነስታ ተጠመጠመችብኝ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ግራ ገባኝ ,ሜላቴ ለመጀመርያ ጊዜ ከአይኗ እንባ ሲወርድ አየሁ በሳቅና በደስታዋ ነው እኔ የማውቃት,.
በጣም ግራ ገባች ምን ሆነሽ ነው ይሄን ያክል ናፍቄሻለው እንዴ አልኳት እየቀለድኩ ,ማልቀሷን አላቆመችም ምን ሆንሽብኝ ብዬ እንባዋን ጠራረግሁላት እስኪ ንገሪኝ ምንድነው የተፈጠረው?አስከፋሁሽ?ያስከፋሽ ሰው አለ ምን ሆንሽ የኔ ፍቅር አልኳት እንባዋን ለማስቆም እየሞከርኩ,.
ሜላቴም እንባዋን ለማስቆም እየታገለች በሚያሳዝን ድምፅ እወድሀለው! አፈቅርሀለው! ካንተ ተለይቼ መኖር አልችልም አለችኝ ,እንዴ የኔ ፍቅር ምን ሆነሽ ነው ምን ተፈጠረ አልኳት ,ሜላቴም ከልብ አዝና እንደዚህ ብላ የተፈጠረውን ነገረችኝ.,
በጣም እያዘነች አባቷ ሊድሯት እንደሆነ ነገረችኝ, ከአባቷ ጋር አብሮ የሚሰራ አንድ ሀብታም ልጁ ከአሜሪካ ተመልሶ ሀገሩ ተመልሶ መኖር ስለሚፈልግ እኔን እንዲድርለት ሲጠይቅ አባቴ እሽ አላቸው ግራ ገብቶኛል አይሆንም ካልሽ ልጄ አይደለሽም አላውቅሽም አታውቂኝም ብሎ አስፈራርቶኛል አለችኝ እንባዋ እየወረደ,.
የምላት ስለጠፋብኝ ዝም አልኩ እኔ እሷን የኔ ማድርግ የምችለው በፍቅር ብቻ ነው .በሌላ ነገር በምንም የኔ ማድርግ እንደማልችል አውቃለው... በተለይ አባቷን በምንም ነገር ማሳመን እንደማልችል ሲገባኝ ተሰፋ የመቁረጥ ስሜት ተሰማኝ ግን እሷን ይበልጥ ማሳዘን ስላልፈለግሁ አይዞሽ በቃ አታልቅሺ አልኳት ስሜቴን እየደበቅሁ,.
እኔም አንድ አመት ነው የቀረኝ ለመመረቅ ስለዚህ አብረን እንሆናለን እስከዛ ግን ጠንካራ መሆን ይኖርብናል አልኳት እሽ ግን ያገባሻል የተባልኩት ልጅ አመት ያክል የሚቆይ አይመስለኝም አለችኝ .አይዞሽ ተሰፋ አለን ግን አባትሽን እሽ እንዳትያቸው ቆይ እያልሽ ትንሽ እንዲቆይ አድርጊ,ሜላቴ የኔ ፍቅር አፈቅርሻለው ላጣሽ አልፈልግም አልኳት,.አቀፈችኝ አፈቅርሀለው እኔም ላጣህ አልፈልግም አለችኝ.,
ሜላት ድንገት ስልኳ ጮኸ አባቷ ነበሩ ስልኳን አነሳችው የት ነሽ የሚል ጥያቄ አቀርብላት ሰላምም ሳይሏት አለው እዚሁ ቢሮ አካባቢ ነኝ አለቻቸው የት እንዳለሽ አውቃለው እዛ የድሀ ልጅ ጋ ነሽ አይደል ሲሉ እኔና ሜላት አይን ለአይን ተያየን,........

ይቀጥላል......
የድሀ ልጅ ፍቅር
ክፍል 🔟
#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

እኔና ሜላቴ አብረን እየተነጋገርን ማልቀስ እንደሌለባት እየመከርኳት እያለ ድንገት የሜላት ስልክ ጮኸ አባቷ ነበሩ ስልኩን እንዳነሳችው ሰላም እንኳን ሳይሏት የት ነሽ አልዋት .ሜላትም እረጋ ብላ አባቢ እዚሁ ቢሮ አካባቢ ነኝ መጣሁ አለች በትህትና .አትዋሽ ውሽታም ከዛ ከድሀ ልጅ ጋ ነሽ አይደል ብለው ጮሁ እኔና ሜላት አይን ለአይን ግጥምጥም አልን ደነገጠች .እሽ መጣሁ ብላ ስልኩን ዘጋችው.,
ሜላት አይኔን ለማየት አቅም አጣች እንደአቀረቀረች ይቅርታ ውዴ አለችኝ። የአባቷ አባባል ምንም ቢያበሳጨኝም እሷን ግን ማስከፋት አልፈለግሁም.ተጠግቼ አቀፍኳት ካቀረቀረችበት ቀና አድርጌ ግንባሯን ሳምኳት በቃ ችግር የለውም አትጨነቂ እሽ የኔ ፍቅር አልኳት .አዝናለው የአባቴን ይሄንን መጥፎ ባህሪ መቀየር አልቻልኩም አለች ችግር የለውም አትዘኚ ይበልጥ እንዳይቆጡ ሂጂ አልኳት እሽ ብላኝ ተነስታ ሄደች.,
እኔም ከሄደች በኃላ ብዙ ነገር አሰብኩ .እኔና ሜላት ስንለያይ ቻው ብላኝ ስትሄድ አንገቷን ግንባሯን ከንፈሯን ሳልስማት ሄዳ አታውቅም ዛሬ ግን ቻው ብቻ ብላኝ ነው የወጣችው .ግራ ገብቶኛል በጣምም ጨንቆኛል .እንዳላጣት በጣም ፍርቻለው ሌላው ቢቀር ውለታዋን በፍቅር መመለስ ነበር ምኞቼ ግን ዛሬ ላይ ልቤ በፍረሀት ተውጧል.አምላኬ አንተ እርዳኝ አልኩ በልቤ።
እቤት ውስጥ የነበርኩት እኔ ብቻ ነበርኩ እናቴም ወንድሜም የሉም ስለዚህ ሲመጡ የሚበሉት ምግብ ማዘጋጀት ፈለግሁ ተነስቼ ቤቱን አስተካክዬ ምግብ ሰራሁ ቡና አቀራረብኩ.. ከዛ እናቴን መጠበቅ ጀመርኩ ሜላቴ ግን ከአባቷ ጋር ምን እንደተፈጠረ ምንም አልነገርችኝም አልደወለችልኝም ጨንቆኛል,..
ለሜላቴ ልደውልላት ስልኬን አነሳውና አስቀምጠዋለሁ.. ምናልባት አባቷ አብረዋት ቢሆኑስ ብዬ አስብና እተወዋለው.,ዝም ብዬ በሀሳብ እየተብሰለሰልኩ እናቴና ወንድሜ መጡ እናቴ ቤቱን ስታይ ደስ አላት ዮኒቨርሲቲ ከመሄዴ በፊት ቀድሜ እቤት ከገባሁ ምግብ ሰርቼ ቤት አስተካክዬ ነበር የምጠብቃት., ዛሬም ያንን ስታይ በጣም ደስ አላት ,. የእናቴ ደስታ እኔንም አስደሰተኝ.,
የእናቴን ደስታ እያየው ድንገት ስልኬ ጮኸ ሜላቴ ነበረች ስልኩን አነሳሁት በር ላይ ነኝ ውጣ አለችኝ ደንግጬ ተንደርድሬ ወጣሁ ከመኪናዋ አልወረደችም መኪናውን ከፍታልኝ ገባሁ .እቅፍ አድርጋ ሳመችኝ ትንፋሽ እስኪያጥረን ድረስ ተሳሳምን ቅድም ሳልስምህ የወጣሁት በአባቴ ተበሳጭቼ ነው ይቅርታ አለችኝ.. ሄዳም ምንም እንዳልተፈጠረና ዋሽታ አባቷን እንዳሳመነቻቸው ነገረችኝ.
ሜላቴ ቶሎ መሄድ አለባት ለዛም ነው ከመኪና ሳትወርድ የጠራችኝ በቃ አባቷን ማሳመኗ በጣም ስላስደስተኝ አቅፌ ሳምኳት በቃ መሄድ አለብኝ ብላኝ ከንፈሬን ጉንጫን አይኔን ግንባሬን ስማኝ ሄደች.እኔ ተመልሼ እቤቴ ገባሁ.እራት በልተን ቡናችንን እየጠጣን ለእናቴ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኳት በጣም አዘነች እናቴ አንድ ነገር ማለት ትወዳለች"ሁን ያለው ይሆናል"ሁን ያለው ይሆናል ልጄ አይዞህ ሁሉም ለበጎ ነው አለችኝ እሽ አልኳት.,
ሜላት አባቷን ቆይ ትንሽ ብላቸዋለች የጋብቻውን ነገር አንስተውባት አያውቁም እኔም ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ አመት ተመራቂ ነኝ አባቷ ትንሽ ዝም ካሉ የሚያገባትም ትንሽ ከቆየ አሪፍ ነው ብዬ አሰብኩኝ .,ትምህርቴን ጀምሬ በጥሩ ሁኔታ እየተማርኩ ነው ሙሉ ትኩረቴ ትምህርቴ ላይ ነው ,.ምክንያቱም የእናቴን ደስታ ለማየት ነው ድካሜ.,ከክላስ ውጥቼ ዶርማችን ውስጥ ቁጭ ብዬ እያጠናሁ እያለ ስልኬ ጮኸ ሜላት ነበረች.........

ይቀጥላል✍🏻....
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌   ‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​ክፍል 1⃣1⃣
🌺የድሀ ፍቅር🌺
#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

የመጨረሻ አመት ተመራቂ ስለሆንኩ በጣም ተወጥሬ እያጠናሁ ነው አንደኛው ሲሚስተር አልቆ ሁለተኛው ሲሚስተር ላይ ነን አጋጣሚ ላይብረሪ ከምሄድ ማንም ዶርም ውስጥ ስለሌለ እዚሁ ላጥና ብዬ እያጠናሁ ነበር .ድንገት ስልኬ ጮኸ ሜላት ነበረች.ስልኩን አነሳሁት የኔ ፍቅር እንዴት ነሽልኝ አልኳት ድምፃ ደስ አይልም ነበር.አለውልህ እንዴት ነህልኝ ውዴ አለችኝ.
ሜላቴ የሆነ ነገር ካልሆነች በስተቀር እንደዚህ ፍዝዝ ብላ አታወራኝም.ደግሞ ምን ተፈጠረ ወይ አምላኬ አልኩ በልቤ.ምነው የኔ ፍቅር ምን ሆንሽብኝ ድምፀሽ ትክክል አይደለም አልኳት.ውዴ ግራ ገብቶኛል ብላ ማልቀስ ጀመረች ምንድነው ምን ተፈጠረ ንገሪኝ አልኳት .አባቴ መልስሽ ከዛሬ እንዳያልፍ ወይ እሽ ወይም እንቢ ብለሽ አታስጠብቂኝ መልሱን ማታ እንድትነግርትኝ ብሎኛል አለችኝ እያለቀሰች .ደነገጥኩ በጣም ምን ትበላቸው.,
የኔ ፍቅር ተረጋጊ መፍትሄ አናጣም አልኳት ""እሽ በይ እንዳትለኝ ብቻ ""አለችኝ በጩኸት አላደርገውም የኔ ፍቅር አልኳት .አፈቅርሻለው ላጣሽ አልፈልግም አልኳት .እሷም አፈቅርሀለው.እሽ መቼም አልለይህም ሁሌም አብሬህ ነኝ .ለማንኛውም በቃ በኃላ አወራሀለው ብላኝ ስልኩ ተዘጋ ተረበሽኩ ግን ምን ላድርግ ምንም .ማጥናት እንኳን አልቻልኩም ዝም ብዬ ቁጭ አልኩ ከሜላቴ ጋር ሆኜ ያሳለፍኳቸው እያንዳንዶ ጊዜና ሰአት ድቅን ብለው በትዝታ ወሰዱኝ.,
ሜላት ስልኩን ዘግታ ባንክ ሄዳ ያላትን ብር እንዲሁም ሌላ ብር ጨምራ ወደ እኔ አካወንት ውስጥ ታስገባዋለች እኔ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም.ሜላት ይሄንን ያደረገችው .አባቷ ጨክነው ከቤት ብትባረር እንኳን ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ይሆናል ብላ አስባ ነበረ .ወደ ቤቷ ከመሄዷ በፊት ደወለችልኝ አባቷን በፍፁም ማሳመን ስለማትችል በቃ አልፈልገውም ማግባት አልፈልግም ብላ መልስ ለመስጠት እንደተዘጋጀችና ወደ ቤት መግባቷን ነግራኝ ስልኩ ተዘጋ.,
እኔም ፀሎቴን ቀጠልኩ ምንም እንዳይፈጠር አምላኬ ሆይ አደራህን አልኩት,በቃ ግራ ስለገባኝ ለእናቴ ደወልኩላት , ሰላም ካልኳት በኃላ ድምፄ ስለተቀየረባት ምን ሆንክ ብላ ጠየቀችኝ መቼም የእናት አንጀት ሆኖባት ምነው ልጄ እራበህ ጠማህ ምንድነው ድምፅእህ አለችኝ .እኔም ሁሉንም ነገር ነገርኳት ጨንቆኛል አልኳት አይዞህ አምላክ ያውቃል ልጄ አለችኝ እሽ .,እማ ምን አደርጋለው በፀጋ መቀበል ነው ብዬ አሰብኩ ,ልጄ አላማህን እንዳትረሳ ይቺ ልጅ ያንተ ከሆነች የትም አትሄድም እሽ በትምህርትህ በርትተህ እኔንም እሷንም ማስደሰት ይኖርብሀል አለችኝ ,እናቴ እውነቷን ነው እሽ እማ በቃ ሰላም እደሩ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት ,
እናቴ ያለችኝን ነገር እያሰብኩ ደብተሬን ማገላበጥ ጀመርኩ ግን ጥናት ማጥናት አልቻልኩም.ወዲያው ሜላት ደወለች ምን !ምን!ተፈጠረ አልኳት በፍጥነት.ተረጋጋ ምንም አልተፈጠረም አባቴ ድንገት ስራ ተብሎ ነገ ከከተማ ስለሚወጣ በጊዜ ተኝቷል ከሳምንት በኃላ ፈጣሪ ያውቃል አለችኝ .ተመስገን ጌታዬ አልኩ ደስ አለኝ .ትንሽ ተሳስቀን ደህና እደሪ ደህና እደር ተባብለን ስልኩ ተዘጋ.ከዚህ በኃላ ማጥናት አለብኝ ብዬ ማጥናት ጀመርኩኝ.,
በማግስቱ ጠዋት ስልኬት ትቼ ወደ ትምህርት ገብቼ ስለነበር ስልኬ ሲደወል ማወቅ አልችልም .በደንብ በጥሩ መንፈስ ተማርኩኝ .ላይብረሪም ገብቼ ሳጠና ቆየሁ .ከዛ ሜላቴ ትዝ ስትለኝ ልደውልላት ብዬ ወደ ዶርማችን ሄድኩ ስልኬን ሳነሳው ያየሁት missed call ከሁለት መቶ በላይ ነበር እናቴና ሜላት ነበሩ ደነገጥኩ.,ስልኬን አንስቼ በመጀመርያ እናቴ ጋ ደወልኩ ግን አታነሳም ለሜላትም ስደውል ስልኳ አይሰራም., ምን እንደተፈጠረ ማወቅ አልቻልኩም ግራ ገባኝ .በዛው ደቂቃ ትንሽ ቆይ መልሼ እደውላለው የሚል ሜሴጅ በሜላት ስልክ ተላከልኝ.......

ይቀጥላል✍🏻.....
   ‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
የድሀ ፍቅር
ክፍል 1⃣2⃣
#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

ፈተና ስለደረስብኝ ለማጥናት ላይብረሪ ቆይቼ ስመጣ በጣም ብዙ miss call አገኝው እናቴም ሜላትም ደውለው ነበር በጣም ደነገጥኩ ደግሜ ስደውል ስልካቸውን አያነሱም ግራ ገባኝ .በሜላት ስልክ ትንሽ ታገስኝ እሰውላለው የሚል ሜሴጅ ደረሰኝ... ትንሽ ተረጋጋሁ...
ከትንሽ ቆይታ በኃላ ሜላት ደወለች .በፍጥነት አነሳሁት ምንድነው ምን ተፈጠረ ሜላቴ አልኳት ተረጋጋ ምንም አልተፈጠረም አለችኝ እና ለምን ይሄን ያክል ጊዜ ደጋግማችሁ ደወላችሁ አልኳት የኔ ውድ እንዳትደነግጥ በጥሞና አዳምጠኝ ,አለችኝ እሽ አልኳት ግን ምንድነው አልኳት ልቤ ፍራት ፍራት እያለው .ካልተረጋጋህ ልነግርህ አልችልም አለችኝ እሽ !እሽ ! ንገሪኝ አልኳት ለመረጋጋት እየሞከርኩ..
እየውልህ የኔ ፍቅር ዛሬ ትንሽ ችግር የፈጥሯል አንተ ትምህርት ልትጨርስ አንድ ወር ነው የቀረህ አይደል እኛ ደግሞ ይቺን አንድ ወር በዘዴ ማለፍ ይኖርብናል አለችኝ ምንድነው ግራ ገባኝ እኮ ንገሪኝ አልኳት,.ውስጤ ግን ይበልጥ ፍርሀት ውስጥ ገብቷል.ምን መሰለህ የኔ ውድ ማታ እንደነገርኩህ አባቴ ሌላ ቦታ ለስራ ሊሄድ ነበር, ነገር ግን ጠዋት ትንሽ ችግር ተፈጥሮ እኔ ከቤት ወጥቻለው አለችኝ .,ደነገጥኩ ለምን እንዴት ብዬ ጥያቄየን አፋጠንኩት.ተረጋጋ አባቴ ውሳኔየን ሲጠይቀኝ የማላውቀውን የማልወደውን ሰው ማግባት እንደማልችልና እንደማልፈልግ ስነግረው ከቤት አባረረኝ አሁን እናንተ ቤት ነኝ አለችኝ ..
ብደነግጥም ድንጋጤዬን ዋጥ አድርጌው,.ወይኔ በጌታ እሽ በቃ እሱው ጋ ሁኚ ግን ተጠንቀቁ አልኳት ችግር የለውም እኔ ግን የደወልኩት ዋነኛው ምክንያት ይሄ አይደለም አባቴ ምናልባት የት ዮኒቨርሲቲ እንደደረሰህና ያለህበትን ካወቀ ችግር እንዳያደርስብ እንድትጠነቀቅ ልነግርህ ነው ምክንያቱም በጣም ሲዝት ነበር አለችኝ.አይ ችግር የለም እዚህ ምንም አይፈጠርም አታስቢ አልኳት .
አባቷ እኔን ምንም ማድርግ አይችሉም የፈራሁት ለወንድሜና ለእናቴ ነው ምንም እንዲሆኑብኝ አልፈልግም .ሜላቴንም ማጣት አልፈልግም .,እሷ ሀብታም እኔ ድሀ ሆነኜ ያለን ፍቅር እሷም እንደኔ ድሀ ስትሆን ይዘልቅ ይሆን ?አላውቅም ብቻ ግን አሁን ላይ አፈቅራታለው ሁሉም ምንም አይሁኑብኝ .,የሚገርመው እኔ ሳላውቅ ሜላቴ ብር በእኔ አካወንት ማስገባቷን ስትነግረኝ ደነገጥኩ ብዙ ብር ነው ስፈልግ ስፈልግ ትልክልኛለህ ይቀመጥ ለጊዜው ትንሽ ብር እጄ ላይ አለ አለችኝ እሽ አልኳት.,
ሜላት እኛ ቤት መኖር ከጀመረች ሳምንት ሆኗቷል እኔም ፈተና ስለደረሰብኝ በጥናት ተወጥሪያለው በቃ ብቻ ስለ ወደፊቱም አስባለው .አንዳንዴ የነገን አምላክ ያውቃል ብዬ እተወዋለው ሜላት እኔ ጋ መምጣት ፈልጋ ነበር እኔ ግን የፈተና ሰአት ስለደረስ አትምጪ አልኳት ምክንያቱም እሷን ትቼ ማጥናት አልችልም ግዴታ አብሪያት መዝናናት ይኖርብኛል .እሷም ስለተረዳችኝ ምንም አላለችኝም እሽ ብላ ቀረች.,
ሜላት ስራ አቁማለች ምንም አትሰራም እኛ ድሮ ከምንኖርበት ቤት ለቀው ሌላ ቦታ ተከራይተው ነው የሚኖሩም ምክንያቱም ወንድሟ ቤታችንን ያውቀው ስለነበር እንዳያገኛት በማሰብ ነበር .የሜላት እናት ለሜላት እባቷ ሳያውቅ ብርም አንዳንድ ነገር ያደርጉላታል እባቷ ግን ደውለው አያውቁም .የት እንደምትኖርም ለማጣራት አልፈለጉም ብር ስትጨርስ ተመልሳ ትመጣለች ብለው አስበዋል.እሷ ግን ወደ ቤት አልተመለሰችም ነበር..,
ማታ ሳጠና አምሽቼ ጠዋት ተነስቼ ሻወር ወስጄ ወደ ላይብረሪ ሄድኩኝ ትንሽ አጠናሁና ተመልሼ ወደ ዶርም ገባሁ .ሜላቴ ደወለች በጣም እያለቀሰች ነው እባቷ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ሆስፖታል ገብተዋል ተብሎ ተነግሯት ወደ ሆስፖታል እየሄደች መሆኑን ነገረችኝ ደነገጥኩ ምንም አባቷ ሊለያዬን ቢፈልጉም ምንም እንዲሆኑ ግን አልፈልግም ነበር .በቃ አይዞሽ ተረጋግተሽ ሂጂ አልኳት .በቃ ደረስኩ ብላኝ ስልኩ ተዘጋ እኔም ቆሜ ቀረሁ ......

ይቀጥላል✍🏻....
‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​የድሀ ፍቅር❣️
ክፍል 1⃣3⃣
#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

ሜላቴ ደወለችልኝ በጣም እያለቀሰች ነበር። በጣም ስለደነገጥሁ ምን እንደተፈጠረ ጠየቅኃት እሷም አባቷ የመኪና አደጋ ደርሶበት ሆስፒታል ተጠርታ እየሄደች እንደሆነ ነገረችኝ። በቃ አይዞሽ ሁሉም ለበጎ ነው አባትሽ ምንም አይሆኑም ተረጋጊ አልኳት እሽ በቃ ሆስፒታል ደርሻለው በኃላ እናወራለን ብላኝ ስልኩን ዘጋችው። ደነገጥኩ! አምላኬ ምን ይፈጠር ይሆን አባቷ ምንም እንዲሆኑ አልፈልግም ሜላቴ ትጎዳብኛለች። በቃ ጌታዬ አደራህን ብዬ ወደ ዶርሜ ገባሁ።
ዶርሜ ውስጥ ቁጭ ብዬ ስልኬን መጠባበቅ ጀመርኩ እስካሁን አልደወለችም ግራ ገባኝ ምን እንደተፈጠረ ማወቅ አልቻልኩም ማንም ጋ መደወል አልቻልኩ እናቴ ጋ ለመደወል አስቤ እሷን ማስጨነቅ ስለመሰለኝ ተውኩት። ደብተሬን ማገላበጥ ጀመርኩ ማጥናት ባልችልም ከደብተሬ ጋ ግን ተፋጠጥን።
ሜላቴ አልደወለችም በጣም ሲብስብኝ ምን ተፈጠረ የኔ ፍቅር ብዬ ሜሴጅ ላኩላት። ደህና ነው ትንሽ ቆይቼ እደውልልሀለው እሽ አለችኝ ትንሽ ተረጋጋሁ... ወደ ጥናቴ ተመለስኩ ሰአቱ እየመሸ ስለነበር ከዶርም አልወጣሁም። ወዲያው እናቴ ደወለችልኝ ሰላም አለችኝ ምን እንደ ተፈጠረ ጠየቅኃት ምንም አልተፈጠረም ሜላት ደውላ ደውዬ እንድነግርህ ነግራኝ ነው አባቷ ደህና ናቸው ምንም አልሆኑም ዛሬ ሆስፒታል ስለሚያድሩ እሷም እዛው ነው የምታድረው ለመደወል ስላልተመቸኝ ነው ብላሀለች አለችኝ እሽ አልኳት ...የአባቷ ደህና መሆን አስደስተኝ።
ጠዋት ተነስቼ ወደ ክላስ ከመግባቴ በፊት ለሜላት ሜሴጅ ፃፍኩላት" አባትሽ ተሻላቸው አንቺስ እንዴት ነሽ የኔ ፍቅር?" አላየችውም መልስም አልተላከልኝም ወደ ክላስ ገባሁ ,ከትምህርት መልስ ላይብረሪ ገብቼ አጥንቼ ስወጣ ሜላት ደወለችልኝ ይቅርታ የኔ ውድ ለመደወል ስላልተመቸኝ ነው .ምናልባት ሳወራ ስምተው ስልኬን ፈትሽው ቁጥርህን እንዳይወስዱ በማሰብ ነው ይቅርታ አለችኝ እር ችግር የለውም ,አባትሽ ግን እንዴት ናቸው አልኳት ተሽሎቷል ወደ ቤት ልንወስደው ነው እኔም ወደ ቤት እመለሳለው እስከሚሻለው ድረስ አለችኝ።
የሜላት ወደ ቤት መመለስ ቢያስደስተኝም ,ላግባት ያለው ልጅ መምጫው ስለደረስ ግን አሳስቦኛል ,ብቻ ምንም ማለት ስላልፈለግሁ እሽ በቃ ሂጂ አባትሽኝ እግዚአብሄር ጨርሶ ይማራቸው ብያት ስልኩ ተዘጋ ፈተና ለመፈተን ሳምንት ስለቀረን በጣም በጥናት ተወጥሪያለው ወደ ጥናቴ ተመልሼ ሳጠና አመሸሁ ,
ሜላት አንድ ታላቅ እህት አለቻት አላገባችም ማግባት አትፈልግም የመጀመርያ ፍቅረኛዋ በመኪና አደጋ ስለሞተባት ብዙ ተሰቃይታለች ሌላ ወንድ አልፈልግም እሱም ቀርቷል እንኳን ሌላው የሚል አመለካከት አላት . ሜላት እቤቷ ተመልሳለች አባቷም ደህና ናቸው ከቤት ልጁን አባረረ ላለመባል እንጂ ተመልሳ ወደ ቤት እንድትገባ አይፈልጉም ነበር.,
ሜላት ስልክ ደውለችልኝ እቤት እንደሆነችና ማታ ነገ እንግዳ እቤት ይመጣል ስለተባልኩ ብር ያስፈልገኛል ላክልኝ አለችኝ እሽ ብዬ የራሷን ብር አውጥቼ የምትፈልገውን ያክል ላክሁላት.እንግዳው ማን እንደሆነ አላውቅም ግን ሲያወሩ የሰማሁት የአባቴ የስራ ባልደረቦች እንደሆኑ ነው አለችኝ ችግር የለውም ብቻ እራስሽን ጠብቂ አልኳትና ስልኬን ዘግቼ ወደ ጥናት ተመለስኩኝ.,
እኔ ከተመረቅሁ በኃላ ቶሎ ስራ ይዜ ሜላቴን ማስደሰት እናቴን ማስደስት ነው የምፈልገው .,ለዛም ነው የምችለውን ያክል ጠንክሬ የምማረዉ.ሜላቴ ቀኑን ሙሉ አልደወለችም እንግዳ አለ ስላለች ልረብሻት ስላልፈለግሁ ዝም ብዬ አመሽሁ .ሜላቴ ደወለችልኝ .የሚገርም ነገር ልንገርህ አለችኝ በደስታ እየተፍለቀለቀች ምን ተገኝቶ ነው ንገሪኝ እስኪ የኔ ፍቅር አልኳት ሜላቴ ፍፁም ደስተኛ ነበረች......

ይቀጥላል.....
   ‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​የድሀ ፍቅር❣️
ክፍል 1⃣4⃣
#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

...ሜላት ደወለችልኝ በጣም ደስተኛ ነበረች ,ደስተኛ ስለሆነች በጣም ደስ አለኝ ግን ምን እንዳስደሰታት አላውቅም.የኔ ፍቅር ምን ተገኝ ዛሬ ደስተኛ ሆነሽልኛል አልኳት .የኔ ውድ ዛሬ አዲስ አበባ ብትሆን አለህበት ድረስ እመጣ ነበር አለችኝ ,በደንብ አሳቀችኝ,የኔ ፍቅር እውነት ደስታሽ እኔንም አስደስተኝ,.
የኔ ፍቅር አለችኝ ሜላት በሚያምር ድምፆ ወዬ የኔ ውድ አልኳት ,በምን ደስ እንዳለኝ ታውቃለህ .ንገሪኛ ካልነገርሽኝ በምን አውቃለው አልኳት ,ሊያገባኝ የሚፈልገው ልጅ መጣ .አለችኝ ቆሌዬ ግፍፍ አለ ተርበተበትኩ ሜላቴን ይሄንን ያክል ያስደስታል ብዬ አስቤ አላውቅም ,ግን ደስታዋ አስደነገጠኝ ,ምን ማለት ነው የእሱ መምጣት ነው እንደዚህ ያስደሰተሽ?አልኳት ከትትትትትትት ብላ ሳቀችብኝ .ይበልጥ ተናደድኩ,. እሽ ጠዋት እደውልልሻለው አልኳት ቆይ ቆይ እንዳትዘጋው አለችኝ...
የሜላት በልጁ መምጣት እንደዚህ መደሰት በጣም አበሳጭቶኛል.ለዛም ነበር ደህና እደሪ ብዬ ስልኩን ልዘጋባት የነበረው.መናደዴ ስለገባት ልንገርህ ምን መሰለህ ልጅ ስለመጣ አይደለም የተደሰትኩት እሱ እኔን ሳይሆን ታላቅ እህቴን ማግባት እንደሚፈልግ ስለተናገረ ነው .አለችኝ ቆሌዬ ግፍፍ አለ ምን አልኳት አወ እህቴን እንዳያት እሷን ነው ያጫችሁልኝ ብሎ ሲጠይቅ አባቴም አወ አለ .ከዛ እኔ ከጨዋታው ውጪ ሆንኩልህ ማለት ነው አለችኝ እየተፍለቀለቀች.,
ኦ አምላኬ ብዬ ደስ አለኝ ሜላቴ እኔ ማመን አልችልም አልኳት ,እመን በቃ ከዚህ በኃላ ማንም በመሀከላችን አይገባም አለችኝ .አብረን ደስ አለን .ፈተናዬን ጨረሼ እስከማገኛት ድረስ ጏጉቻለው .ፈተና ለመፈተን ለ3 ቀን ያክል ሲቀረኝ ሙሉ በሙሉ ትኩረቴ ጥናቴ ላይ ሆኖል ,ሜላትን በቀን አንድ ጊዜ ነው የማገኛት,
የሳምንት ፈተናዬን እንደምንም ተወጣሁ በጣም ይከብድ ነበር ግን በቃ ሰራሁት .ውጤት እስከሚመጣ ድረስ ቤተሰብ ጋ ሂድኩኝ ሜላቴ መኪናዋን ይዛ መጥታ ወሰደችኝ ,ፈፁም ሰላም ተሰማኝ እናቴ ያላትን ብር አሰባስባ ለእኔ የምርቃት ዝግጅት ለማዘጋጅት ደፋ ቀና ማለት ጀመረች,እኔ ግን ምንም ድግስ አልፈልግም ብላት ልትሰማኝ ፈቃደኛ አይደለችም ,
ጊዜው ደርሶ የምርቃት ቀን ደርሶ እኔም ሜላቴም እናቴም ታናሽ ወንድሜን ይዘን ወደ ዮኒቨርሲቲ ሄድን የሚገርመው ከዮኒቨርሲቲ ተማሪዎች የበለጠውን ውጤት ያመጣሁት እኔ ነበርኩ የማዕረግ ተመራቂ ሆኜ ተመረቅሁኝ .እናቴን አሰደስትኩ ሜላቴን አስደሰትኩ በቃ እኔም የልፋቴን ውጤት ሳይ ደስ አለኝ.,
ሁሉንም አስደስቼ ድህነቴ ሳያግደኝ የምፈልግበት ደረጃ ላይ ደረስኩኝ,በዮኒቨርሲቲያችን ከተማሩና ከፍተኛ ውጤት ካመጠት ተማሪዎች ውስጥ ተመርጠን የውጪ የትምህርት እድል እንደመጣልን ተነገረኝ,ለሜላት ይሄ ዜና ባያስደስታትም ለኔ ግን ጥሩ እድል ነበር ,እኔና ሜላት ፍቅራችን በጣም ደስ የሚል ነው ለደቂቃ እንኳን ተጣልተን አናውቅም ,.ይህ የትምህርት እድል ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ግን በወጣሁ በገባሁ ቁጥር ,ስልክ ባወራን ቁጥር መጨቃጨቅ ጀምረናል ነገሩ በጣም እያሳሰበኝ ነው

ይቀጥላል........

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌
💕የድሀ ፍቅር❣️
ክፍል1⃣5⃣
#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

አሪፍ ውጤት ስለነበረ ያመጣሁት ከዮኒቨርሲቲያችን ውስጥ እኔና ሌላ ሁለት ልጆች ለትምህርት እድል ወደ ውጪ ለመሄድ ተመረጥን .ነገር ግን ሜላት ደስተኝይ እንደማትሆን ሳስብ ግራ ገባኝ .ከተመረቅሁ በኃላ እኔና ሜላት እንደድሮው አይደለንም በቃ አብዛኛን ጊዜ እኛ ቤት ስለምትውል በቃ ፀባይዋ ተቀያይሯል ,የት ወጣህ የት ገባህ ማለትም ጀምራለች..,
እኔ በፍፁም ሜላቴን ማስከፋት አልፈልግም ምክንያቱም ሜላት ሁሉ ነገሬ ናት ፍቅር ሀ ብዬ የጀመርኩባት ብቻ ሳትሆን ዛሬ ላይ ለመድረስ ትልቅ አስተዋፆ ያበረከተችም ጨምር ናት በቃ የምትለኝን ከማድረግ ውጪ ምንም ነገር አላረግም በፍፁም መከፍቷን ማየት አልፈልግም.,
ሜላት አንዳንዴ በነገር ወጋ ታደርገኛለች እዚህ አድርሼህ ትለኛለች ግን እኔ ምንም መናገር አልፈልግም ብትልም እውነቷን ነው በሷ ሀይል ነው እዚህ የደረስኩት ግን ,አንዳንዴ ይሄንን ሳስብ የትምህርት እድሉን መጠቀም እንዳለብኝ ይሰማኛል ምክንያቱም ነገ አብረን መኖር ስንጀምር ነገሮች ሊበላሹ ይችላሉ የኔ የሆነ ነገር ሳይኖረኝ አብረን መኖር እንደማንችል ይሰማኛል,.
ሜላት አብረን እንድንኖር ትፈልጋለች በተለይ ታላቅ እህቷ በሚያምር ሰርግ ካገባች በኃላ የማግባት ትዳር የመመስረት ፍላጎቷ ጨምሯል እኔ ደግሞ ይሄንን የማድረግ አቅሙ የለኝም .ሜላቴ ሁሌም በስልክም ሆነ በአካል ወሬዋ ትዳር አብሮ መኖር ከዛም ባለፈ ስለ ገንዘብ ሆኗል ,የእሷ ገንዘብ እንደሚያኖረን ትነግረኛለች ግን ይሄ ለእኔ አላስደሰተኝም እስካሁን ያደረገችልኝ ይበቃል .ከዚህ በኃላ እኔ የምትፈልገውን ላደርግላት ነው የምፈልገው .ስለዚህ የሷ ሀሳብ አልተስማማኝም .,.
ሁሌም በህይወቴ የሚፈጠሩትን ነገሮች ውሳኔ ከመወሰኔ በፊት ለእናቴ አሳውቃታለው በቃ እሷ አድርግ ያለችኝን አደርጋለው እሷ አይሆንም ካለች እተዋለው በቃ አሁንም እናቴን ማማከርና ውሳኔዋን ማወቅ እፈልጋለው ,እሷ ያለችው ይሆናል .ማታ ላይ በረንዳ ቁጭ ብለን እያወራን እያለ ለእናቴ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኳት .ምንም አላስቀረሁም ውሳኔሽን እፍልጋለው ምን ልወስን ግራ ገባኝ አልኳት,.
እናቴ በጣም ስለምታስብልኝ ትክክለኛውን ውሳኔ ነው የምትነግረኝ ,ልጄ እዚህ ደረጃ ለመድረስህ የሜላት አስተዋፆ በጣም ትልቅ ነው እሷን በፍፁም እንዳታስከፋት ,የትምህርት እድልህንም እንዳታጣ ይሄ ላንተ በጣም ጥሩ እድል ነው ለወደፊት ህይወትህ ይጠቅምሀል ,እኔ የምልህ ከሜላት ጋ ተነጋግራችሁ ውሳኔ ወስኑ ነው.አስፋላጊ ከሆነ ነገ ማታ ጥራትና እንመካከር ይሄ ይሻላል ነው የምልህ አለችኝ ,እሽ እማ አልኳት
እናቴ ያለችኝ ነገር ትንሽ ቀለል እንዲለኝ አደረገኝ ,በማግስቱ ጠዋት ተነስቼ ሜላቴ ጋ ደውዬ ማታ ላገኛት እንደምፈልግና እቤት እንድትመጣ ነገርኳት እሽ አለችኝ .ሜላት ጥሩ ስሜት የላትም ብቻ ግን እሽ ስላለች ደስ ብሎኛል ,ሜላቴ መጥታ ምን እንደምንባባል እያሰብኩ ዋልኩ .መምሸቱ አይቀር ሜላትም መጣች.እኔም እናቴም ሜላቴም ቁጭ ብለን መነጋገር ጀመርን ,.,
እናቴ ለሜላት ሁሉንም ነገር ነገረቻት በቃ በመነጋገር የድሮ ፍቅራችሁን አድሱ ,እኔ እንደድሮው እንድትሆኑ ነው የምፈልገው አለችኝ .ተነጋግረን አንድ ውሳኔ ላይ ደረስን እኔም የትምህርት እድሌን እንዳያመልጠኝ መሄድና መማር እንዳለብኝ ,እኔና ሜላትም ቀለበት ማድረግ እንዳለብን ተወሰነ .በሀገር ባህላችን እኔና እናቴ ለሜላት ቤተሰቦች ሽማግሌ ላክን ቤተስቦቿ ትንሽ ቢግደረደሩም እሽ አሉ ,እኔና ሜላት ቀለበት አሰርን .እኔም ወደ አወስትራሊያ ለትምህርት ሄድኩ,.ፍቅራችን እንደድሮው ሆነ እኔ ያለ ሜላት ሜላት ያለ እኔ ማንንም አንፈልግም ,.ፍቅራችን ችግር ቢበዛውም ችግሩን ተቆቁመን አለፍን::


ይቀጥላል... ‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
💕የድሀ ፍቅር❣️
ክፍል 1⃣6⃣
#በእውነተኛ_የህይወት_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

ከሀገር ከቤተሰብ ከፍቅረኛ ከጏደኛ እርቆ መሄድ እጅግ በጣም ከባድ ነው ,ነገር ግን የግዴታ ውዴታ ሲሆን ይለመዳል,እኔም ለትንሽ ጊዜ የመከፋትና የመናፈቁ ስሜት ከራሴ ጋ እንድጣላ አድርጎኝ ነበር ,በተለይ ሜላት ስትናፍቀኝ ክንፍ ቢኖረኝ ኖሮ በርሬ እሄድ ነበር ,ድምፃን ስስማ ደግሞ እረጋጋለው ,በቃ ግን ለትንሽ ጊዜ ተቸግሬ ነበር ,ሜላቴ ለኔ ከስጦታም በላይ ነች .የምትረዳኝ! የምታፀናናኝ!ብቻ ባጠቃላይ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነች,
ሁሌም በእሷ ማበርታታትና በእሷ አለሁልህ ባይነት ሁሉን ነገር መቋቋም ችያለው,ፍቅሯ ለኔ ለመኖሬ ዋነኛው ምክንያት ነው,ለደቂቃ ስለሷ ሳላስብ መዋልም ማደርም አልፈልግም !ሳስባት ይበልጥ ሰላም ይሰማኛል! እናቴን ሳወራ ደስታ ይሰማኛል !እናቴም አለውልህ ልጄ በርታልኝ እሽ !ስትለኝ እንዴት ልቤ በሀሴት እንደምትሞላ !ኡፍፍ እንዴት ደስ ይላል!
በእነሱ ብርታት እኔም በርትቼ እየተማርኩ ነው በቃ በዛውም ስራ እሰራለው ,ብቻ ግን ደስተኛ ነኝ ለደቂቃ ከፍቶኝ አያውቅም ሲከፋኝ መድሀኒቴ ሜላቴ ጋ ደውዬ ደስታዬን አስመልሳለው!ሀሀሀ እንዳንዴ ግርም ይለኛል ,ብዙ የስደት ጏደኞች አፍርቻለው ከእነሱጋ ተሰብስበን ስለ አለፈው ህይወታችን ስናወራ እኔ ሁሌም ስለ ሜላት,ስለ እናቴ ስለ ታናሽ ወንድሜ ሳወራ ,ሌሎቹ ግን ታክሲ ወስጥ ተዋውቂያት !ባጃጅ ላይ ስልኳን ተከብያት!ጭፈራ ቤት ስትጨፍር ተመችታኝ,ሳራ .ሊሊ ,ኪያ,ሚሚ,እያሉ ሲደረድሩት እንዴይ የከተማውን ሴት ሁሉ ተቆጣጥራችሁት የለ እንዴ !እላቸውና ግርም ይለኛል,መቼም እንዳንተ ድሀ ካልሆኑ በስተቀር ሴትን ለማማለል ቀላል ነው ይሉና ይስቃሉ!እሱስ ልክ ናቸው !
ብዙውን ጊዜ ከስራም ከትምህርትም መልስ ከጏደኞቼ ጋር ከመሆን ይልቅ እቤቴ ብሆን እመርጣለው እንዳንዴ ወሬያቸው ብዙም አያስደስተኝም!እኔ ከእናቴ ና ከድህነቴ ብዙ ነገር ስለተማርኩኝ የምንም ነገር ችግር የለብኝም !ቢርበኝ እንኳን ስርቼ የመብላት አቅሙ አለኝ!ተመስገን ሞያም አለችኝ.ሀሀሀሀሀ አንዳንድ ሴቶች ሞያ ያለው ወንድ ደስ አይለኝም ኩሽና ገብቶ ሲርመጠመጥ ሳየው የምግብ ፍላጎቴ ይዘጋል! ሲሉ በተቃራኒው ደግሞ'ሞያ ያለው ወንድ ደስ ይለኛል ቢያንስ እንኳን ሲደክመኝ ያግዘኛል! ይላሉ ,የኔዋ ሜላትም ጠዋት ጠዋት የመነሳት ልምድ ስለሌላት ቁርስ ሰርቼ ተነሽ ስላት ደስ ሳይላት አይቀርም ምንም ብላኝ አታውቅም!! እናንተስ ሞያ ያለው ወንድ እንዴት ነው ይመቻችኃል? እስኪ መልሱት,
የስደት ህይወት ብዙ ከባድ ነገሮች ይኖሩታል እነሱን ደግሞ በትዕግስት ማለፍ መልካም ነው,እኔ አብዛኛውን ጊዜ ብቻየን የምሆነው ከችግሮችና ከግርግሮች ለመራቅ ነው !ጏደኛ የቱንም ያክል አስፈላጊ ቢሆን !የእሱ ተመሳሳይ ከልሆንክ ከባድ ነው!የኔ ጏደኞች ጨዋ የሚባሉት እንኳን የሱስ ተጠቂዋች ናቸው ለዛም ነው የምርቃቸው,ሀሀሀሀ አንዳንዴ አንተ ግን ልጃገርድ ይመስል ምን ያሽኮረምምሀል !! ሲሉኝ ግርም ይለኛል! እኔ ለእነሱ ፋራ ነኝ ,ደስ ሲል ፋራነት እንዲህ ከሆነ አወ ፋራ ነኝ,.
አንድ የማስበው ነገር አለ እሱም አላማየን ነው ከሀገር የወጣሁበትን ትልቁን አላማ የእናቴን ጉጉት የሜላቴን ናፍቆት ብቻ ብዙ ነገሮች, ለዛም ነው ከነገሮች የተቆጠብኩት!ከሀገሬ ከወጣሁ ስድስት ወር ሆኖኛል,ብቻ በደንብ ተለማምጄዋለው ናፍቆቱንም ቻል አድርጌዋለው!ሜላቴም ስራ እየሰራች ከቤተሰብ ጋ ነች ናፍቃኛለች,
የማይከፈል በገንዘብ የማይተመን የእምነት እዳን እና ፍቅርን ላሸከመህ ሰው መልስህ የሚሆነው ታማኝ ሆኖ መገኝትና እሱን ማስደስት ነው ይሄንን ደግሞ ለሜላቴ ቃል ገብቻለው ,ፍቅሯ በልቤ ብቻ ሳይሆን !በደም ስሬ ሳይቀር ስለተሰራጨ ከእሷ ውጪ ማሰብም ሆነ ማየት አልፈልግም,!አንድ ቀን ስራ ውዬ ድክም ብሎኝ እቤት ገብቼ እርቦኝ ስለነበር ምግብ ሰርቼ በላሁና ሜላቴን ለማውራት (Skype )ከፈትኩ ሜላቴ መስመር ላይ ሰለነበረች ማውራት ጀመርን !በዛ በሚያምረው ድምፆ የኔ ፍቅር ?አለችኝ አይኗን እያስለመለመች,ሜላቴ በጣም ወፈርሽ አልናፍቅሽም ማለት ነው አልኳት? የኔ ውድ ?አለችኝ ደግማ ? ወዬ እናቴ,ምን ልታዘዝሽ አልኳት,አይንህን ጨፍን አለችኝ ,ለምን የኔ እናት አልኳት,ዝም ብለህ ታዘዝ ስትለኝ እሽ ብዬ አይኔን ጨፈንኩ ,ከደቂቃዋች በኃላ ማየት ትችላለህ አለችኝ .,አይኔን ስገልጥ ግን ማመን አቃተኝ በህልሜም መሰለኝ ተነሳሁ ተቀመጥኩ .የማደርገው ሁሉ ጠፋብኝ.............
እንቀጥላለን

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
💕የድሀ ልጅ ፍቅር❣️
ክፍል 1⃣7⃣
#በእዉነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ

ሜላቴ አይንህን ጨፍን ብላኝ .ጨፍኜ ስገልጥ ያየሁትን ነገር ማመን ነበር ያቃተኝ.በህልሜም መሰለኝ ተነሳሁ ተቀመጥኩ .እውነት ነው እናቴ የማየው?! እውነት ነው!?ብዬ ሜላቴን ደጋግሜ ጠየቅኃት !አወ የኔ ፍቅር በእውንህ ነው .እስከዛሬ ያልነገርኩህ .ትንሽ ልታገስ ብዬ ነው.አለችኝ.ሜላቴ እርጉዝ ነች የስድስት ወር እርጉዝ ናት !!የማይታመን ነገር ሆነብኝ ምን አይነት ስጦታ ነው የምትሰጭኝ ?እሽ ምን ልሁንልሽ ?የኔ እመቤት አፈቅርሻለው!!አልኳት በደስታ ብዛት እንባየ በጉንጮቼ ሲወርድ ይታወቀኛል የምናገረው ጠፍቶብኝ እየተርበተበትኩ ነው!!

ደስታዬ ወደር አልነበረውም የሚገርመው እኔም ከሀገርኡ ከወጣሁ ስድስት ወር አልፎኛል ,እንዴት መታደል ነው የልጅ አባት ልሆን ነው,ሜላቴን ባመሰግናትም ልጠግባት አልቻልኩም ,ምናለ አብሬሽ ብሆን የሚያምርሽን በማቅረብ በመንከባከብ አግዝሽ ነበር የኔ ፍቅር ምን ልሁንልሽ ? አልኳት በፍቅር እያዬኃት!የኔ ውድ ምንም አፍቅረኝ ብቻ አለችኝ ,የናፍቆት አስተያየት እያየችኝ,መታቀፍ የናፈቁ ትከሻዎቿን እያሸች ,የኔ እናት አፈቅርሻለው እስከ ዘላለም አልኳት,

እኔና ሜላቴ በ(Skype)ለረዥም ሰአት አወራን እኔማ ስናወራ ውለን ብናድር አልጠግባትም ፈገግ ስትል ደስታየን አገኝዋለው.!በደንብ አውርተን በቃ ልጃችንን አደራ ብያት ስልኩ ተዘጋ! ኦ አምላኬ ምኒኛ መታደል ነው አትኔን በአይኔ ልታሳየኝ ነው ተመስገን!ተመስገን!! አልኩኝ ደስታዬ ወደር ስላልነበረው ከጏደኞቼ ጋር አብረን ደስታን ለማጣጣም ወስኜ ወጣሁ እውነትም ደስ ብሎኝ አመሽ ሜላቴን ሺ ጊዜ አመሰገንኳት!!

በደስታዬ መሀል ወደ ሀገሬ የምመለስበትን ጊዜ ሳስብ ግን እርቀቱ የሰማይ ያክል እራቀብኝ ,ብቻ ተመውገን ነው,አሁን ትልቅ የሆነ የቤት ስራ እንዳለብኝ ገባኝ ቤተሰብ አስተዳዳሪ የራሴ የሆነ ትዳር እንደሚኖረኝና ብዙ ነገሮችን ማሟላት እንዳለብኝ ማሰብ ጀመርኩ,ምሽቱ በደስታ ተጠናቀቀ.ደስ ብሎኝ መሽ አደረ ነጋ, ጠዋት ከመኝታዬ ስነሳ ደስታው አብሮኝ ነበር ለወደፊት አሰብኩ ልጆቼን አሰብኳቸው ፍቅሬን ሜላቴን አሰብኳት,!!

ህይወት ብዙ ጊዜ የራሳ የሆነ መልክ አላት እራሷ የምታመጣው ,ህይወቴ ሙሉ በሙሉ ተቀየረ የምኖረው ለብዙ ሰዎች ሆነ ደስታዬ ወደር አጣ ,ፈቅር ማለት ይህ ነው ,ሜላቴ እንደምታፈቅረኝ ለደቂቃ ተጠራጥሬ አላውቅም አሁን ግን ይበልጥ እንደምታፈቅረኝ ተረዳሁ,ምክንያቱም እኔ አጠገቧ ሳልሆን ብቻዋን ልጄ ለማሳደግ ማሰቧ ለኔ ያላት ፍቅር ምን ያክል እንደሆነ ለመገመት አይከብድም!

ሜላት ለኔ ከምንም ነገር ከማንም በላይ ነች.አንድ እውነት ልንገራችሁ.ሴት ልጅ ከልቧ ከወደደችና ካፈቀረች እራሷን አሳልፋ እስከመስጠት ትደርሳለች ,ለምሳሌ ሜላቴን ተመልከቱ ስለምታፈቅረኝ ብቻ ለእኔ ደስታ ብላ ልጄን በሆዷ ይዛለች ገና ብዙ ስቅይይ አለባት,ስትወልድ ትሰቃያለች ዘጠኝ ወር ሙሉ በሆዷ ትሸከማለች,ሰወስት አመት ታጠባዋለች,በቃ የፍቅር ትክክለኛ መሰዋአት ይህ ነው ታድያ ለዚች የፍቅር ንግስት ምን አድርጌ ውለታዋን ልከፍላት እችላለው? በታማኝነትና እሷን በመንከባከብ !!

ቀን ቀንን እየተካ ወራቶች እየተተኩ የሜላት መውለጃ ደረሰ,እኔም በትርፍ ጊዜዬ እየሰራሁ እማራለው ,የምችለውን ሁሉ አደርጋለው ሜላቴ እናቷ ጋ ነው ያለችው ,አንዳንዴ አባቷ በነገር እንደሚወጏት ሳስብ እሳቀቃለው ,ያኔ የተናገሩ ይሄ የድሀ ልጅ ያሉትን ነገር አልረሳውም አሁንማ ምን ይሉ ይሆን አምላኬ ሜላቴ እንዳትሳቀቅብኝ እያልኩ ሁሌ አስባለው,ሜላት እናቴ ጋ እንድትሆን እፈልግ ነበር ,ነገሮች ተቀይረዋል እኔም ሰርቼ ለእናቴ ስለምልክ ቢያንስ የምትፈልገውን ነገር ማሟላት አያቅተንም ነበር, ለነገሩ ሜላቴ የብር ችግር የለባትም,,

ነገሩ እኔም ደፍሬ ይሄንን ላድርግልሽ ብዬ አላውቅም ,እኔና ብቻ የምትፈልገውን ታደርግላታለች ,የሜላት መውለጃ ጊዜ ደርሷል ,እኔም ጭንቀቴ ጨምሯል ,በቃ ሁሌም ፀሎት አደርጋለው በሰላም እንድትገላገል ለፈጣሪ ፀሎቴን አሰማለው ,ቀን ላይ ሜላቴ ደውላልጅ አወራን ደህና ነኝ ሰሞኑን ግን መውለዴ አይቀርም አለችኝ አይዞሽ እንዳትፈሪ እሽ ብያት ስልኩ ተዘጋ! እኔም ደብሮኝ መሽ ,ማታ ምንም ምግብ መብላት ስላላስደሰተኝ ውስጤ እየተረበሸብኝ ,ፀሎት አድርጌ ወደ መኝታዬ አመራሁ ! ስንት ተገላብጫ እንቅልፍ ወሰደኝ,እኩለ ለሊት ግን የስልክ ጥሪ ቀሰቀሰኝ...........

ይቀጥላል.......
‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
2024/09/21 07:49:24
Back to Top
HTML Embed Code: