Telegram Web Link
#አሠላሙ_ዓለይኩም #ወራህመቱሏሂ
#ወበረካቱሁ
🍬🌹👭 🍬💕🌹 👭 🍬🌹 🍬🌹👭
#ከሴቶች_ለሴቶች_ክፍል 51
ዳዉንሎድ ያድርጉ ይስሙ ለሌችም ያስተላልፉ
#1::21 : 37 ሴኮንድ
🔍 #LINK
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
ከታች ባሉት ሊንኮች ዳውንሎድ ያድርጉ ያድምጡ ለሌሎችም ያስተላልፉ
👇👇👇👇👇👇👇
ለማውረድ 🎧
ጥራት ያለው ድምፅ
Wifi
https://youtu.be/Fqk-ew2NnNw
https://youtu.be/Fqk-ew2NnNw
Or
https://youtu.be/Fqk-ew2NnNw
https://youtu.be/Fqk-ew2NnNw
🎧 #በዛሬዉ_ልዩ_ከሴቶች_ለሴቶች የሬድዮ ፕሮግራማችን ያካተትናቸዉ፦
📚 #ከእዉቀት_ማእድ_የደርስ_መሰናዷችን
☞አሏሁ ተዓላ ፍጡራኖችን የማይመስል ጌታ እንደሆነ የሚያስታዉስ ደርስ 📚
🕌 #ኢስላምን_በጥበብ
☞የተለያዩ ስነ ፁሁፎች
☞ግጥሞች
💍❣️ #የጥንዶች_ሚዛን⚖️💍
☞የሀብላ የሂወት ታሪክ ክፍል 5
👩‍👩‍👦 #የኢስላም_እንስቶች
☞ስለ ፋጢማህ ቢንት አል_ኽጧብ ረዲየሏሁ ዐንሃ ክፍል 1ትረካ የመጨረሻዉ
🌎ሌሎች ምርጥ ምርጥ አባባሎች #ከጣፋጭ_መንዙማዎች_ጋር ተካተዉበታል ይከታተሉን...
#ስለፕሮግራሙ_ያላችሁን_አስተያየቶች
https://www.tg-me.com/maidaAhmed
ወይም 0936994553 ብላችሁ አድርሱን

🥇shar...share....Share.,
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ለተጨማሪ ትምህርቶች
┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
#በቴሌግራም_አድራሻችን👇👇
ኒሳኡል መሻሪዕ👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
በYou tube አድራሻችን👇👇
https://youtu.be/S-IWg10wa6k
ኡሙ አካዳሚ👇
https://www.tg-me.com/umuakadami

┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
#መልካም_ለይለቱል ጁሙዓህ❤️😍 የኢስላም ከዋክብቶች ክፍል 9 || ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ ክፍል 1|| 👇👇 ገብተዉ ይከታተሉ....share.... አይርሱ
https://youtu.be/WHk4QFg6gN4
https://youtu.be/WHk4QFg6gN4
#የጥበብ_ሁሉ_ቁንጮ_አሏህን_መፍራት_ነው
قَالَ اللهُ تَعَالَى: {يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللهَ حَقَّ تُقَاتِهِ} [آل عمران: 102]
እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ!አሏህን ፍሩ!አሏህን ተገቢዉን መጠንቀቅን ተጠንቀቁ፡፡(አል_ዒምራን 102)
وَقالَ تَعَالَى: {يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللهَ وَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا * يُصْلِحْ لَكُمْ أَعْمَالَكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ} [الأحزاب: 70]
እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ አሏህን ፍሩ! ትክክለኛ ንግግርንም ተናገሩ! (አል_አሕዛብ 70)

የሰዉ ልጅ በተቅዋ አማካኝነት ከአሏህ ዘንድ የላቀ ደረጃን ይጎናፀፋል፡፡ ተቅዋ ያለዉ ሰዉ በዱኒያ መልካም ነገሮች ይገጥሙታል፡፡በአኺራም ትልቅ የክብር ደረጃን ከጌታችን ከአሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ይቸራል፡፡
عن أبي أُمَامَةَ صُدَيّ بنِ عجلانَ الباهِلِيِّ رضي الله عنه قَالَ: سَمِعتُ رسولَ الله صلى الله عليه وسلم يَخْطُبُ في حجةِ الوداعِ، فَقَالَ: ((اتَّقُوا الله وَصلُّوا خَمْسَكُمْ، وَصُومُوا شَهْرَكُمْ، وَأَدُّوا زَكاةَ أَمْوَالِكُمْ، وَأَطِيعُوا أُمَرَاءكُمْ تَدْخُلُوا جَنَّةَ رَبِّكُمْ)). رواه الترمذي، في آخر كتابِ الصلاةِ، وَقالَ: (حديث حسن صحيح).
አቡ ኡማመህ ሱደይ ኢብኑ ዐጅላን አል-ባሂሊይ መልካም ስራቸዉን አሏህ ይዉደድላቸዉና የአሏህ መልእክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የመሰናበቻ ሐጅ እለት ተከታዩን ንግግር ሲያሰሙ ሰምቻለለሁ በማለት እንድህ ሲሉ አስተላልፈዋል "አሏህን ፍሩ! አምስት ወቅት ሶላቶችን ስገዱ፣የረመዷንን ወር ፁሙ፣ከገንዘባችሁ ዘካህ ስጡ! መሪዎቻችሁን ታዘዙ ጌታችሁ(አሏህ)ያዘጋጀላችሁን ጀነት ትገባላችሁ፡፡ (ቲርሚዚይ ዘግበዉታል፣ ሐሰኑን ሶሒሕ ነዉም ብለዉታል)፡፡ ተቅዋ ጀነትን ለመጎናፀፍ ትልቁ መሳሪያ ነዉ፡፡በዚች ዐለም ዉስጥ አሏህን ፈርቶ የእርሱን ትዕዛዝ ፈፅሞ ከሐራም ነገሮች ርቆ መኖር በመጭዉ ዓለም ለስኬት ያበቃል፡፡ ከሐዲሱም ይህንን እንረዳለን፡፡ከዚህ በተጨማሪም አሚሮቻችንን(የበላዮቻችንን) በወንጀል እስካላዘዙን ድረስ መታዝዝ እንዳለብንም ያስገነዝበናል፡፡

ከስንቆች ሁሉ በላጩ አሏህን መፍራት ነዉ፡፡ዑለማዎች ሲናገሩ ስንቅን የፈለገ ሰዉ አሏህን መፍራት ይበቃዋል ይላሉ፡፡
قالَ تَعَالَى: {وَمَنْ يَتَّقِ اللهَ يَجْعَلْ لَهُ مَخْرَجًا * وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لا يَحْتَسِبُ} [الطلاق: 2، 3]
አሏህንም የሚፈራ ሰዉ ለእርሱ መዉጫን ያበጅለታል፡ከ፡ከማያስበዉም በኩል ሲሳይን(ሪዝቅን)ይሰጠዋል፡፡(ጦላቅ 2-3)

https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
ጥር 22/2012 ለሞጣ ሙስሊም ወንድሞቻችን ማቋቋሚያና ለመስጂድ መገንቢያ እጃችንን እንዘርጋ!
January 31/01/2020
---------------------------------
አስ - ሱናህ TV ''ሚዛናዊ መርህ || قناة السنة نهج الاعتدال ||
As-Sunnah TV ''The Way Of Moderation'' ||
__
በሚከተሉት አድራሻዎቻችን ይከታተሉን
የፌስቡክ ገፅ
|| https://www.facebook.com/AssunnahTVOfficial
የቴሌግራም ቻናል
|| https://www.tg-me.com/AssunnahTVOfficial
የWhatsApp ቁጥራችን
||+251 90 300 0102
😍መታደም ለቻለ በሙሉ❤️
#መልካም_ስነ_ምግባር_ያለዉ_ሰዉ_አምሳያዉ_ልክ_እንደ_ከረሜላ_ነዉ፡፡ከረሜላ ቢቀጠቀጥ፣ቢቆረጠምና ቢሸራረፍ ጣፋጭነቱን እንደማያሳጣ ሁሉ መልካም ስነ ምግባርን ከጀሊሉ የታደለ ሙእሚንም #ሰዎች_መጥፎ_ቢያደርጉበት፣ቢሰድቡት፣ቢያሙት፣ሒስድ ቢያደርጉበትና ልኩን ሳያዉቅ ቢያስተናንሱት እርሱ #ለነርሱ_መልካምን_ከማሰብና_እነርሱ በመልካም ከመዋዋል ዉጭ ፀባዩ አይቀየርም፡፡ ብዙ ጊዜ ትንሽ የሆኑ ሰዎችና ስለ ኢስላም አስተምህሮ ጠንቅቀዉ የማያዉቁ አወቅን አወቅን ባዮች መልካም ሰዎችን(ዉስጣቸዉ ንፁህ የሆኑ የዋሆችን) መጥፎ ለማድረግ ቢጥሩም #መልካሞች_ግን_መልካሞች_ናቸዉ፡፡ #የሚከተሉት_ሸሪዓቸዉ_ያመጣላቸዉን_ትዕዛዝ_እንጅ_ነፍስያቸዉን አይደለም፡፡ ይህ ነዉ የመልካም ስነ ምግባር ጥግ፡፡አንድ ሰዉ መጥፎም ሆነ መልካም ዋለልን እኛ አቋማችን ተቀይሮ መጥፎዎች መሆን የለብንም፡፡ ለዚያም ነዉ ታላቁ #ሙሐዲስ_አሸይኽ_ዐብዱሏህ_እንድህ_የሚሉት
حُسْنُ الْخُلُقِ عِبَارَةٌ عَنْ تَحَمُّلِ أَذَى الغَيْرِ وكَفِّ الأَذَى عَنِ المَسْلِمِينَ وَبَذْلِ المَعْرُوفِ أي يُحْسِنَ المُؤمِنَ إلى الذِي يُحْسِنُ إلَيهِ والذِي لا يُحْسِنُ إليهِ
ሸይኻችንአሏህ ይዘንላቸዉና እንድህ አሉ፦ #የመልካም_ስነ_ምግባር_ምልክቶች_ሶስት_ናቸዉ
➊፦ #የሌሎችን_አዛ_መሸከም_መቻል
➋፦ #ሌሎች ሙስሊሞችን አዛ አለማድረግ እና
➌፦ #መልካምም_ሆነ_መጥፎ_ለዋሉልን_ሰዎች_እኛ_ሁሌም መልካም መሆን፡፡
#አዎ_ትልቅ_ሰዉ_ማለት እነዚህን ነገሮች ተሸክሞ ማለፍ የቻለና በነዚህ ስነ ምግባሮች የታነፀ ጀግና ነዉ፡፡ አሏህ መልካሞች ያድርገን፡፡ኣሚን

┏━ 💗 ━━━━ 💗 ━┓
በቴሌግራም አድራሻችን ለመቀላቀል......
https://www.tg-me.com/yeabderiyderesoch👇

┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
#ጓደኛችሁ_ማነው
#ጥሩ_ዛፍ_መልካም_ጥላን ብቻ ሳይሆን መልካም ፍሬንም ይሰጣል። መልካም ጓደኛም እንዲሁ ከጠበቅነውና ካሰብነው በላይ ይሆንልናል።በተደሰትንበት ሀብት በሀብት በሆንበትና ድል በድል በሆንበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከጎናችን የሚሆነው፤ በተከፋንበት፣ ባጣንበት ፣የኔ ያልነው ነገር ሁሉ በራቀን ጊዜ ከጎናችን የማይለይ እሱ #ትክክለኛ_ጓደኛ_ነው#እሱ_ትልቁ_ዛፍ_ነው
ታዲያ እንዲህ አይነት ጓደኛ ለማግኘት መጀመሪያ እራስም እንዲሁ ሆኖ መገኘት ግድ ነዉ። እራሳችንን የዚህ አይነት ሰው ነን ወይ ብሎ መጠየቅም ተገቢ ነው። እራሳችን, ያልሆንነውንና የማናደርገውን ነገር ሌሎች እንዲያደርጉልንና እንዲሆኑልን መመኘት ተስፋ ቢስና ራስ ወዳድ ነው ባይ ነኝ። #እኛ_ራሳችን_ትልቁን_ዛፍ_ለመሆን_እንሞክር!! በኛ ጥላ ሌሎች ሲጠለሉ ከዝናብና ከፀሀይ ሲድኑ እያየን እንደሰት። #ከተትረፈረፉን_ፍሬዎቻችን_ሲቋደሱ_እያየን_እንርካ። ያኔ እኛ እንዲሆኑልን የምንፈልገው ባህሪ እንዲኖራቸው እናስተምራቸዋለን።
ሌሎችም ለኛ እንዲሁ ይሆናሉ። የኛ የመልካምነት ነፀብራቅ በሌሎች ላይ ሆኖ እናየዋለን፡፡ ጥሩ ጓደኛ ስትፈልጉ እናንተ መጀመሪያ ጥሩ ዛፍ ሆናችኋል ወይ? የሚለውን ጥያቄ መመለለስ ተገቢ ነው። እናንተ መልካም ዛፍ ሆናችሁ ጥሩ ፍሬንና የሚመች ጥላን ስትሰጡ ያኔ እንዲሆኑላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ ይሆንላችኋል።
ረሱሉ ሙሐመድ ሶለሏሁ ወለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል፦"ሰውየው በጓደኛ ዲን (እምነት) ላይ ነው ያለው። አንዳችሁ ማንን ጓደኛ አድርጎ እንደሚይዝ ይመለከት "። ታዳ ይሄን መልካም ጓደኛ መርጠን (መርጠናት)ምን እንጠቀማለን ለሚለው እስኪ አብረን እናንበው፦መልካም ጓደኛ መያዝ ጥቅሞቹ ከብዙዉ በትንሹ እንይ፦
➊፦ የውመል ቂያማህ ከጥሩ ጓደኛ ጋር አብረን እንቀሰቀሳለን
➋፦ ከቂያማህ ቀን ጭቀት ያድናል
➌፦ በእነሱ ዱዓ መጠቀም ይቻላል
➍፦አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ዘንድ ለጥሩ ሰዎች ያለውን ዉደታ ያገኛል
➎፦ ሁሌም ከወንጀል ርቆ አሏህን ይገዛል......
ስለዚህ ጓደኛ ስንመርጥ መልካሙን መምረጥ አለብን። #አሏህ_መልካሞች_አድርጎ_መልለካሞቹን_ይወፍቀነ_ያረብ!!

https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
#አል_አቅሷ_የነቢያት_መገናኛ__ኢስራእ_ወል_ሚዕራጅ_ክፍል 1⃣
#الأقصى ملتقى الأنبياء🍂 الإسراء والمعراج
ኢስራእ እና ሚእዕጅ አሏህ ለነቢያችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ከስጣቸው ሙዕጂዛዎች(ተዐምራቶች)መካከል አንዱ ነው:: ይህም አስደናቂ ተዓምር የተከሰተው በወርሃ ረጀብ በ27ኛው ለሊት ነበር፡፡አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ስለዚህ አስገራሚ ክስተት በተከበረዉ ቁርኣኑ ሲነግረን እንዲህ ይለናል፦
قال تعالى {ﺳُﺒْﺤَﺎﻥَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺃَﺳْﺮَﻯٰ ﺑِﻌَﺒْﺪِﻩِ ﻟَﻴْﻠًﺎ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻤَﺴْﺠِﺪِ ﺍﻟْﺤَﺮَﺍﻡِ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟْﻤَﺴْﺠِﺪِ ﺍﻟْﺄَﻗْﺼَﻰ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺑَﺎﺭَﻛْﻨَﺎ ﺣَﻮْﻟَﻪُ ﻟِﻨُﺮِﻳَﻪُ ﻣِﻦْ ﺁﻳَﺎﺗِﻨَﺎ ۚ ﺇِﻧَّﻪُ ﻫُﻮَ ﺍﻟﺴَّﻤِﻴﻊُ ﺍﻟْﺒَﺼِﻴﺮُ}
#ትርጉም ፦ «ጥራት(ለአሏህ) ይገባው ባሪያውን የለሊት ጉዞ ከመስጂደል―ሐራም እስከ መስጂደል―አቅሷ እንዲጓዝ ላደረገው፤ይህ(መስጂደል―አቅሷ) ዙሪያው በበረካ የተሞላ እንዲሆን አደረግነው ይህንን፤ ጉዞ እንዲያደርግ የተደረገው ተዐምራት ልናሳየው ዘንድ ነው፤ እሱ አሏህ ሰሚና ተመልካች የሆነ ጌታ ነው።
#ኢስራእ#ኢስራእ_ማለት የሌሊት ጉዞ ሲሆን ይህም ሰይዳችን ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ከመስጂደል ሐራም ወደ መስጂደል አቅሷ ያደረጉት የሌሊት ጉዞ ነው::
معجزة الإسراء ثابتةٌ بنص القرءان والحديث الصحيح.فيجب الإيمان بأن الله أسرى بالنبي صلى الله عليه وسلم ليلا من مكة المكرمة إلى المسجد الأقصى.وقد أجمع أهل الحق من سلف وخلف المحدثين ومتكلمين ومفسرين وفقهاء على أن الإسراء كان بالجسد والروح وفي اليقظة ،وهذا هو الحق وما هو على الله بعزيز وهو قول ابن عباس وجابر وأنس وعمر وحذيفة وغيرهم من الصحابة وقول الإمام أحمد والطبري وغيرهما من الأئمة فلا خلاف في وقوع الإسراء صلى الله عليه وسلم إذ فيه نص القرءاني صريح فمن أنكره فقد كذب القرءان ومن كذب القرءان فقد كفر.
ረሱሉ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ኢስራእ ማድረጋቸዉ ግልፅ በሆነ ቁርአንና ሶሒህ በሆነ ሐዲስ ተገልፇል፡፡አሏሁ ሱብሓነሁ ወተአዓ ነብያችንን ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም በለሊት ከመከቱል ሙከረማህ ወደ በይተል መቅድስ ኢስራእ እንዳስደረጋቸዉ ማመን ግደታ ነዉ፡፡በዚህ ጉዳይ አህሉል ሐቆች፤ሰለፎች፤ኸለፎች፤ፉቀሀዎችና ሙሐዲሶች ረሱላችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ኢስራእ ያደረጉት በጀሰዳቸዉ በሩሐሙስቸዉና በእንቅልፍ ሳይሆን ነቅተዉ እንደሆነ ምንም ኺላፍ ሳይኖር በኢጅማዕ ተስማምተዉበታል፡፡ይህ ደግሞ ሐቅ ነዉ ለአሏሁ ሱብሐነሁ ወተዓላ ደግሞ ቀላል ነዉ (ከባድ ነገር አይደለም)፡፡ ይህም የኢብኑ ዐባስ፣የጃቢር፣የአነስ፣የዑመር፣የሑዘይፋህና የሌሎችም ሶሐበቶች ንግግር ነዉ፡፡ኢማሙ አሕመድ፤ጦበሪና ሌሎችም አኢማዎች ረሱሉ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ኢስራእ እንዳደረጉ ምንም መቃረን ሳይኖር ተስማምተዋል፡፡ ምክንያቱም ረሱላችን ኢስራእ እንዳደረጉ ግልጽ የሆነ የቁርአን አንቀፅ ስለተገለፀ፡፡ ይህን (ኢስራእ)የለም የሚል በእርግጥ ቁርአንን ያስዋሸ ይሆናል፡፡ ቁርኣንን የሚያስዋሽ ወይም የሚክድ ደግሞ ሙስሊም ሊሆን አይችልም፡፡
አሏሁ ተዓላም ከላይ እንዳየነዉ ረሱሉ ሙሐመድ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ኢስራእ ማድረጋቸዉን
ﺳُﺒْﺤَﺎﻥَ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺃَﺳْﺮَﻯٰ ﺑِﻌَﺒْﺪِﻩِ ﻟَﻴْﻠًﺎ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻤَﺴْﺠِﺪِ ﺍﻟْﺤَﺮَﺍﻡِ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟْﻤَﺴْﺠِﺪِ ﺍﻟْﺄَﻗْﺼَﻰ ﺍﻟَّﺬِﻱ ﺑَﺎﺭَﻛْﻨَﺎ ﺣَﻮْﻟَﻪُ ﻟِﻨُﺮِﻳَﻪُ ﻣِﻦْ ﺁﻳَﺎﺗِﻨَﺎ ۚ ﺇِﻧَّﻪُ ﻫُﻮَ ﺍﻟﺴَّﻤِﻴﻊُ ﺍﻟْﺒَﺼِﻴﺮُ
ሲል ገልፆልናል፡፡#እዚህ_ቁርአን_ላይ ” ﻟﻴﻼ ”የሚለው ቃል መጠቀሱ ከሌሊት የተወሰነችን እና አጭር ጊዜ መሆኑን ለማመላከት ነው ይላሉ የዒልም ባለቤቶች፡፡ምክንያቱም ኢስራእ የሚለው ብቻውን የሌሊት ጉዞ መሆኑን ይገልጽ ነበር ግና ”ﻟﻴﻼ” የምትለዋ ቃል በመጨመሯ ከሌሊቱ የተወሰነች ጊዜ ያህል መሆኑን ተረዳን ሲሉ ይናገራሉ ዑለሞቻችን፡፡
#መስጂደል_ሐራም በዚህ ስያሜ የተሰየመው የተከበረና ልዩ የሆኑ ህግጋቶች ስላሉት ነው ለምሳሌ፦ በእሱ ውስጥ #የሚሰገድ_ሶላት_አጅሩ_ በብዙ_እጥፍ_መባዛቱ_ከመሬት_ሁሉ_በላጭ_በሆነችው_በመካ_መገኘቱ እና የመሳሰሉት ናቸው::
#መስጂደል_አቅሷ_ደግሞ_በዚህ ስያሜ መጠራቱ ከመስጂደል ሐራም ላለው እርቀት ነው፡፡ ሁለቱንም ለመጀመሪያ ጊዜ የገነቡት #ነቢዩሏህ_አደም ዐለይሂ ሰላም ሲሆኑ ካዕባን ከገነቡ ከአርባ_አመት በኋላ ነበር መስጂደል አቅሷን የገነቡት፡፡
”ﺑَﺎﺭَﻛْﻨَﺎ ﺣَﻮْﻟَﻪُ ”
[ ዙርያውን ወደ ባረክነው ] አሏህ በዚህ ቁርአን አያህ #ዙርያውን_ወደ_ባረክነው ሲል የተፈለገበት የሻም ምድር የተባረከች ናት ለማለት ነው::መስጂደል አቅሷ የሚገኘው በፊሊስጢን ሲሆን ፊሊስጢን ደግሞ ከሻም ሃገሮች ውስጥ ናት ።በሐዲስ እንደመጣል #ነብዩ_ሙሐመድ_ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለው ነበር፦
اللهم بارك لنا في شامنا ويمننا،قالوا وفي نجدنا يا رسول الله ؟!قال هناك يطلع قرن الشيطان
« #አሏህ_ሆይ_ሻምን_እና_የመንን_በረካ¿አድርግልን”ብለው ዱዐእ ሲያደርጉ ሶሐበቶች ለነጅድም ያ ረሱለሏህ!አሉ ረሱሉም “ከእዚያማ የሸይጧን ቀንድ ይወጣል» አሉ፡፡ እንዳሉትም #ሙሐመድ_ኢብኑ_ዐብዲል_ወሃብ ወጥቶ ሙስሊሙን አተራመሰው፡፡ ስንቶቹን የጧኢፍ ሙስሊሞች ጨፈጨፈ፡፡እነዚህ አሁን ወሃቢያ ተብለው የሚጠሩት እራሳቸውን ሰለፊያ ብለው የሚሰይሙ በሙሉ የዛ የሸይጧን ቀንድ ተብሎ የተወገዘው #የሙሐመድ_ኢብኑ_ዐብዱል_ወሀብ ተከታዮች ናቸው) የሸይጧን ቀንድ ብለዉ ረሱሉ የመሰከሩባቸዉን ልንርቃቸዉና ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡አሏህ ይጠብቀን::
═════━
#ኢንሻ_አሏህ ,,,#ክፍል 2⃣ ይቀጥላል....
🎖SHARE🎖 እናድርገዉ
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ለተጨማሪ ትምህርቶች

┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
#በቴሌግራም_አድራሻችን👇👇
ኒሳኡል መሻሪዕ👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
You tube👇👇
https://youtu.be/dvuxxKQllK4
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
#አቅሷ_የነቢያት_መገናኛ__ኢስራእ_ዐል_ሚዕራጅ_ክፍል
#الأقصى ملتقى الأنبياء🍂الإسراء والمعراج

 بسم الله الرحمٰن الرحيم الحمد لله رب العالمين والصلاة والسلام على رسول الله
#ነብዩ_ሙሐመድ_ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ኢስራእ ያደረጉት በሌሊት ሲሆን ከመካ #ከኡሙ_ሐኒአ_ቤት_ተነስተው_ወደ_መስጅደል_ሓራም_በመድረስ_ልባቸው_ተቀዶ ታጥቦ በኢማን እና በጥበብ ተሞላ ይህም የአሏህን አስገራሚ እና ድንቃድንቅ ፍጥረታት በጠንካራ ልብ ለመመልከት ያስችላቸው ዘንድ የተደረገ ነበር፡፡
#وروى البيهقي عن شداد بن أوس قال{قلنا يا رسول الله كيف أُسري بك؟؟قال #صليت لأصحابي صلاة العتمة بمكة معتما،وأتاني جبريل عليه السلام بدابة بيضاء فوق الحمار ودون البغل} والبراق دابة من دواب الجنة أبيض طويل يضع حافره عند منتهى طرفه أي أن كل خطوة له منتهى وأقصى بصره قد ركبها الأنبياء مثل سيدنا إبراهيم عليه الصلاة والسلام .فقال اركب #فستصعبت_علي وليس ذلك إباء وتمنعا إنما البراق من شدة فرحه أن النبي سيركبه أصابته هزة فقال جبريل أبمحمد تفعل هذ؟فما ركب أحد أكرم على الله من محمد وأرفض أي جرى وسال البراق عرقا.}
ኢማሙ በይሀቅይ ረዲየሏሁ ዐንሁ ከሸዳድ ኢብኑ አዉስ ባወሩት ሐዲስ አንቱ የአሏህ መልእክተኛ ሆይ እንደት ነበር ኢስራእ ያደረጉት አልናቸዉ??አሉ፣እሳቸዉም የምሽት ሶላትን ኢማም ሆኜ ሰገድኩኝ(እንደምናዉቀዉ ሶላት ግደታ የሆነዉ በኛ ላይ ከኢስራእና ከሚዕራጅ ጉዟቸዉ በኃላ ነዉ ያዕኔ በኢስራእ ጉዟቸዉ የሚሰግዱት ሶላት ሶላተ ለይል ነዉ እንጅ ግደታ ሶላትን አልነበረም)፡፡ከዚያም አሉ ሰይዱና ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም የጀነት የሆነን ቡራቅ የተባለን እንስሳ ይዘዉ መጡ(ቡራቅ ማለት የጀነት እንስሳ ነዉ)፡፡ከሌሎች እንስሶች የሚለይበት ምክንያት ዐይኑ ካረፈበት ቦታ መረገጥ ስለሚችል ነዉ፡፡ያ ቡራቅ በጣም ነጭ ነበር እንደዚሁም ቁመቱ ረዘም ያለ ነዉ ከአህያ በላይና ከበቅሎ ዝቅ ያለ ነበር፡፡እግሩን የሚያሳርፈዉ መጨረሻ ዐይኑ ያየዉ ቦታ ላይ ነበር ማለትም እያንዳንዱ እርምጃዉ የእይታዉ መጨረሻ ነዉ፡፡ከረሱል ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም በፊት የነበሩ ለምሳሌ ሰይዱና ኢብራሂም ዐለይሂ ሰላም ቡራቅን ጋልበዉታል፡፡ከዚያም ምን ይላሉ ቡራቅን ጋለብኩት በጣም ከበደኝ አሉ(ምክንያቱም በጣም እየተፈራገጠ ነበር ቡራቁ) ፣ መፈራገጡም እሳቸዉ እንዳይጋልቡት ሳይሆን ወደፊት እንደሚጋልቡት አዉቆ ከደስታዉ ብዛት ነበር የተፈራገጠዉ በማለት ዑለሞቻችን ይናገራሉ፡፡ ሰይዱና ጂብሪል ዐለይሂ ሰላምም እንድህ አሉት #በሙሐመድ_ላይ_ነዉ_የምትኮራዉ?? ከሙሐመድ የበለጠ አንድም የሚጋልብህ የለም!! አሉ፡፡ከዚያም ተረጋጋና ላብ ያልበዉ ጀመር፡፡ ሰይዱና ጂብሪል ዐለይሂ ሰላምም ያዝ አደረጉና እንድሰቀል አደረጉኝ አሉ፡፡
فدارها بأذنها ثم حملني عليها فانطلقت تهوي بنا يقع حافرها حيث أدرك طرفها حتى بلغنا أرضا ذات نخل فأنزلني فقال صل فصليت ثم ركبنا فقال أتدري أين صليت؟قلت الله أعلم ,قال صليت بيثرب بطيبة ،فنطلقت تهوى بنا يقع حفرها حيث أدرك طرفها.ثم بلغنا أرضا فقال أنزل فنزلت ثم قال صل فصليت ثم ركبنا فقال أتدري أين صليت؟صليت بطور سيناء حيث كلم الله عز وجل موسى عليه السلام،ثم بلغنا أرضا بدت لنا قصور،فقال أنزل فنزلت فقال صل فصليت ثم ركبنا قال أتدري أين صليت؟؟قلت الله أعلم،قال صليت ببيت الحم حيث ولد عيسى عليه السلام المسيح ابن مريم،ثم إنطلق بي حتى المدينة من بابها اليماني قبيلة المسجد فربط به دابته ودخلنا المسجد من باب فيه تميل الشمس والقمر فصليت من المسجد حيث شاء الله
አስከትለዉም እንዲህ አሉ ረሱሉ፦ ብዙ ርቀትን ከተጓዝን በኃላ ቡራቋ ዐይኗ መጨረሻ ከሚያይበት ቦታ እየተረገጠች ከሆነ ቦታ ደረስን ዉረድና ስገድ አሉኝ ወረድኩና ሰገድኩኝ የት እንደሰገድክ ታዉቃለህ አሉኝ??አሏህ ያዉቃል አልኩኝ፡፡ ሰይዱና ጂብሪልም አሁን የሰገድከዉ የሲሪብ(መዲናህ)ነዉ አሉኝ፡፡(የስሪብ ማለት በአሁኑ ሰዓት #መዲነቱል_ሙነወራህ እያልን የምንጠራት ታላቅ ከተማ ናት፡፡ ረሱሉ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ከተረገጧት በኃላ ነዉ መዲነቱል ሙነወራህ ተብላ የተሰየመችዉ)የስሪብ ረሱል ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ሳይገቡባት በፊት በጣም ህመም የሚበዛባት፤ድርቅና ችግሮች የሚበዙባት ሀገር ነበረች፡፡የኛ ነብይ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ሁለ ነገራቸዉ በረካ ነዉና እሳቸዉ ሲገቡባት የተወለለወለችዉ #የምታበራዉ_ከተማ(መዲነቱል ሙነወራህ)ተብላ ተሰየመች፡፡)ከዚያም አሉ ረሱሉ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ቡራቋ ዐይኗ ከሚያርፍበት ቦታ እየተረገጠች ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ ከዚያም ዉረድና ስገድ አሉኝ እኔም ወረጄ ሰገድኩኝ ሰይዱና ጂብሪልም የት እንደሰገድክ ታዉቃለህን??ብለዉ ጠየቁኝ አሉ እኔም አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ያዉቃል ብየ ተናገርኩ አሉ፣ ከዚያም ይህ ቦታ ሰይዱና ሙሳ ዐለይሂ ሰላም አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ጅማሬም ሆነ መጨረሻም የሌለዉን ፣ ሐርፍም ሆነ ቋንቋም ያልሆነዉን ንግግሩን ያሰማባቸዉ ቦታ #ጡሩሲናእ ነዉ በማለት መለሱልኝ፡፡አሁንም እንስሳዋ እይታዋ መጨረሻ ከሚያርፍበት ቦታ እየተረገጠች ህንፃዎች ካሉበት ቦታ ደረስን ጂብሪልም ዉረድና ስገድ አሉኝ ወርጀ ሰገድኩኝ ከዚያም ጋለብን ጠየቁኝ የት እንደሰገድክ ታውቃለህ ብለዉ ጠየቁኝ??አሏህ ያዉቃል ብየ መለስኩኝ አሉ አሁን የሰገድክበት #ነብዩሏህ_ዒሳ ዐለይሂ ሰላም (መሲሕ ኢብኑ መርየም)የተወለዱበት ቦታ በይተልሔም ነዉ አሉኝ አሉ፡፡ከዚያም ጉዟችንን ቀጠልንና ከከተማዋ በይተል መቅዲስ ደረስን ከከተማዋ መግቢያ በቀኝ በኩል ገባንና አሏሁ ተዓላ የሻዉን ያክል ሶላት ሰገድኩኝ አሉ፡፡
#ከነዚህ_ሁሉ_ከረሱሉ_ድርጊቶች_የምንረዳዉ_በየደረሱበት ሲሰግዱ የነበሩት ለተበሩክ መሆኑ ግልፅ ነዉ፡፡ረሱሉ የሌሎችን ነብያቶች በረካ ከፈለጉ አፍዶሉ ኸልቂላህ እኛ ደካሞቹ ታድያ እንደት ተበሩክ አንፈልግም?? #ዛሬ_የመጡ_መጤ_ሰዎች_አይቻልም_እያሉ_ለምን_ይጮሀሉ??የዲነል ኢስላም ጠላት ስለሆኑ ብቻ እንጅ ሌላ ምንም ምክንያት የላቸዉም፡፡
🎖SHARE🎖
┏━ 🌹 ━━━━ 🌹━┓
#ኢንሻ_አሏህ_ክፍል_ሶስት_ይቀጥላል....
┗━ 🌹 ━━━━ 🌹━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ለተጨማሪ ትምህርቶች

┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
#በቴሌግራም_አድራሻችን👇👇
ኒሳኡል መሻሪዕ👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
You tube👇👇
https://youtu.be/dvuxxKQllK4
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
#አቅሷ_የነቢያት_መገናኛ__ኢስራእ_ዐል_ሚዕራጅ_ክፍል
#الأقصى ملتقى الأنبياء🍂الإسراء والمعراج
 بسم الله الرحمٰن الرحيم الحمد لله رب العالمين والصلاة والسلام على رسول الله
#ከክፍል_2_የቀጠለ.....
وكان قد شق صدر النبي صلى الله عليه وسلم قبل أن يسرى به ليلا من بيت أم هنئ من مكة المكرمة من المسجد الحرام.
#ረሱሉ_ዐለይሂ_ሶላቱ_ወሰላምኢስራእ ከማድረጋቸዉ በፊት መካ በመስጅደል ሐራም ከኡሙ ሃኒእ ቤት ዉስጥ እንዳሉ ደረታቸዉ ተቀዶ ነበር፡፡( #ረሱሉ_በሂወት_ሲኖሩ_ደረታቸዉ_ሶስት_ጊዜ_ተከፍቷል፡፡ #መጀመሪያ የሁለት አመት ልጅ ሳሉ፤ #ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ የነብይነት ማዕረግ ሊሰጣቸዉ አርባ አመት ሲሞላቸዉና #ሶስተኛዉ ከኡሙ ሀኒእ ቤት)፡፡
قال أنس بن مالك كان أبو ذر يحدث أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال فرج سقف بيتي وأنا بمكة فنزل جبريل ففرج صدري ثم غسله من ماء زمزم ثم جاء بطست من ذهب ممتلئ حكمة وإيمانا فأفرغها في صدري ثم أطلقه.رواه مسلم
አነስ ኢብኑ ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ አቡ ዘር ረዲየሏሁ ዐንሁ እ ከነብዩ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ይዘዉ እንድህ ብለዋል ይላሉ ፦#የነበርኩበት_ቤት_ጣራዉ_ተከፈተ_ሰይዱና_ጂብሪል_ልቤን ከፈተዉ በዘምዘም ዉሀም አጠበዉ ከዚያም ከወርቅ የሆነ እጥስት ላይ ሒክማና ኢማን ከተሞላ በኃላ በልቤ ዉስጥ ተደረገና እንደነበረበት ተመለሰ አሉ፡፡ሱብሓን አሏህ!
وقد جمع الله عز وجل لسيدنا محمد صلى الله عليه وسلم جميع أنبياء صلوات الله وسلامه عليهم في بيت المقدس من ءادم فمن بعده فصلى بهم إماما.وهذا دليل على أن الأنبياء لهم تصرف بإذن الله بعد موتهم وينفع من شاء الله أن ينفع منهم فهم ليسوا كالناس العاديين فقد روى البزار البيهقي وغيرهما أن الرسول صلى الله عليه وسلم قال《الأنبياء أحياء في قبورهم يصلون》
አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ከሰይዳችን አደም ዐለይሂ ሰላምና ከሳቸዉ በኃላ ያሉትን ሁሉንም ነብያቶች ለሰይዳችን ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም በበይተል መቅድስ ዉስጥ ሰበሰበላቸዉና ኢማም ሆነዉ እንድያሰግዷቸዉ አደረገ፡፡ #ይህም_የሚያስረዳን_ነብያቶች_ከሞቱ_በኃላ_በአሏሁ_ሱብሓነሁ_ወተዓላ_ፈቃድ_ከቀብራቸዉ_እንደሚወጡና_አሏሁ_ተዓላ_ከነሱ_እንድጠቀም የፈለገ ሰዉ ሊጠቅሙት እንደሚችሉ ነዉ፡፡ ምክንያቱም እነሱ ከሰዎች የሚለያቸዉ ነገር ስላለ፡፡ኢማሙ በዛር በይሀቂይና ሌሎችም እንደዘገቡት ረሱሉ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም #በሐዲሳቸዉ_ነብያቶች_በቀብራቸዉ_ዉስጥ_ሕያዉ_ናቸዉ_ይሰግዳሉ _ብለዋል፡፡
وقال رسول الله صلى الله عليه وسلم في الحديث الإسراء والمعراج《ثم دخلت بيت المقدس فجمع لي الأنبياء عليهم السلام فقدمني جبريل حتى أممتهم ثم صعد بي إلى السماء》رواه النسائي
ረሱሉ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ስለ ኢስራእና ሚዕራጅ ጉዟቸዉ ሲናገሩ በይተል መቅድስ ገባሁ ሁሉም ነብያቶች ተሰበሰቡልኝ ሰይዱና ጂብሪል ተቀደም አሉኝ ኢማም ሆኜ አሰገድኳቸዉ ከዚያ ወደ ሰማይ ወጣሁ አሉ፡፡
من عجائب ما رأى الرسول عليه الصلاة والسلام في الإسراء
#ረሱላችን_ዐለይሂ_ሶላቱ_ወሰላም #በኢስራእ_ጉዟቸዉ_ካዯቸዉ ተወምራቶች ዉስጥ፦
*١*،الدنيا؛ وهو في طريقه إلى بيت المقدس رأى الدنيا بصورة عجوز،
➊፦ዱኒያን አይተዋታል፦ረሱሉ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም ወደ በይተል መቅድስ መንገዳቸዉ ላይ ዱኒያ በአረጉት ሴት ተመስላ አይተዋታል፡፡ከዚህ የምንረዳዉ ዱኒያ ጊዜዋ እንዳለቀ ነዉ፡፡ረሱላችንም ዱኒያን ሲገልፇት አንድ ሰዉ እጁን ባህር ዉስጥ ከቶ በጣቱ ይዞት የሚወጣዉ ርጥበት ምንም ያክል አይደለም ልክ እንደዚሁ ዱኒያ ላይ ያለዉ ፀጋ አኺራ ላይ ካለዉ ጸጋ ሲነፃፃር ልክ ባህር ዉስጥ ገብቶ እንደወጣዉ እጁ ነዉ ብለዋል፡ሱብሓን አሏህ!! ለዱኒያ ምን ያክል ልባችንን ከፍተን እንደሰጠናት ሁላችንም እናዉቀዋለን፡፡
*٢*،وإبليس؛رأى شيئا متنحيا عن الطريق يدعوه وهو إبليس وكان من الجن المؤمنين في أول أمره،ثم كفر لاعتراضه على الله .قال تعالى {وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلائِكَةِ اسْجُدُوا لآدَمَ فَسَجَدُوا إلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ ففَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ}.
➋፦ኢብሊስን አይተዉታል፦ኢብሊስ ከመንገዱ ዘንበል ብሎ አዩት፡፡ዑለማዎች ኢብሊስ ከመንገዱ ማዘንበሉ የረሱላችንን መንገድ አለመከተሉ ምልክት ነዉ ይላሉ፡፡ኢብሊስ ከመክፈሩ በፊት ሙእሚን ጂን ነበር፡፡ከዚያም የጌታዉን ትዕዛዝ በመቃወም ከፈረ፡፡አሏሁ ተዓላም በቁርአን እንድህ
ይላል፦
قال الله تعالى{وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدَوا إِلّا إبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ}
ትርጉም፦መላኢካዎችን ለአደም ሱጁድ አድርጉ ባልናቸዉ ሰአት ሱጁድ አደረጉ፤ኢብሊስ ግን አሻፈረኝ አለ እሱም ከጂኖች ነበር በጌታዉ ትእዛዝ ፍስቅናን ፈፀመ፡፡
ولا يجوز أن يقال إن إبليس كان طاووس الملائكة فهو لم يكن ملكا.الدليل على ذلك أن الله تعالى قال(إلَّا إبْلِيسَ كَانَ مِنَ الجِنّ)والرسولِ الله صلى الله عليه وسلم قال: "خُلِقَتِ الملائكةُ من نورٍ، وخُلِقَ الجانُّ من مارِجٍ من نار،
ኢብሊስ የመላኢካዎች ረኢስ ነበር ብሎ ማመን አይቻልም፡፡ኢብሊስ ከመላኢካዎች አልነበረም ለዚህም ነዉ አሏሁ ተዓላ በቁርኣኑ ኢብሊስ ሲቀር ሁሉም መላኢካዎች ሱጁድ ማድረጋቸዉን ገልፆ እሱ ግን ከጂኖች እንደነበረና የጌታዉንም ትእዛዝ ጥሶ ሱጁድ አላደርግም አለ ብሎ የጠቀሰዉ ፡፡ረሱላችንም መላኢካዎች ከብርሀን ነዉ የተፈጠሩት ፤ጂኖች ደግሞ ከእሳት ነዉ የተፈጠሩት ብለዋል፡፡
🎖SHARE🎖
┏━ 🌹 ━━━━ 🌹━┓
#ኢንሻ_አሏህ_ክፍል_4⃣_ይቀጥላል....
┗━ 🌹 ━━━━ 🌹━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ለተጨማሪ ትምህርቶች

┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
#በቴሌግራም_አድራሻችን👇👇
ኒሳኡል መሻሪዕ👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
You tube👇👇
https://youtu.be/dvuxxKQllK4
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
#አቅሷ_የነቢያት_መገናኛ__ኢስራእ_ወል_ሚዕራጅ_ክፍል
#الأقصى ملتقى الأنبياء🍂الإسراء والمعراج
من عجائب ما رأى الرسول عليه الصلاة والسلام في الإسراء
#ረሱላችን_ዐለይሂ_ሶላቱ_ወሰላም በኢስራእ_ጉዟቸዉ_ካዯቸዉ ተዐምራቶች ዉስጥ፦ ከክፍል 3 የቀጠለ....
٣؛ ماشطة بنت فرعون؛ شم رائحة طيبة من قبر ما شطة بنت فرعون وكانت مؤمنة صالحة وجاء في قصتها أنها بينما كانة تمشط رأس بنت فرعون سقط المشط من يدها فقالت بسم الله فسألتها بنت فرعون أو لك رب إله غير أبي؟؟فقالت الماشطة نعم ربي ورب أبيك هو الله،فأخبرت أباها فطلب منها الرجوع عن دينها فأبت فحمى لها ماء فألقى فيه أولادها ثم كلمها طفل لها رضيع قبل أن يرميه 《يا أماه اصبري فإن عذاب الأخرة أشد من عذاب الدنيا فلا تتقاعسي فإنك على حق》فقالت لفرعون "لي عندك طلب،أن تجمع العظام وتدفنها"فقال لك ذالك"فألقاها فيه.وقد ماتت شهيدة هي وأولادها.
➌ ፦ማሺጦቱ ቢንት ፊርዐዉን፦ #ነብያችን_በሆነ_ቀብር_ሲያልፉ_በጣም_ደስ_የሚል_ሽታ_ሸተታቸዉ ሰይዱና ጂብሪልን ሲጠይቋቸዉ ስለዛ ነገር ነገሯቸዉ፤ ያ አስገራሚ ሽታ የሸተታቸዉ የፊርዐዉንን ልጅ ፀጉር ስታበጥር የነበረችን ሷሊሓ ቀብር ነበር፡፡ #ይች_ሷሊሓ_ሴት_የፊርዐዉንን ልጅ ፀጉር ስታበጥር ማበጠሪያዉ ከእጇ በወደቀ ጊዜ በአሏህ ስም አለች የፊርዑዉን ልጅም በሷ አባባል ከእኔ አባት ዉጭ ጌታ አለሽ እንዴ??አለች ያቺ ተቅያህ ሴትም #አዎ_የኔም_ሆነ_የአባትሽ
_ጌታ_አሏህ_ነዉ_ስትል_መለሰች፡፡ያች ልጅ ይህን ነገር ለፊርዐዉን ነገረችዉ፡፡ ፊርዐዉንም በሱ አባባል ጌታ ነኝ እያለ ይጣራ ስለነበር ይህን ነገር ሲሰማ በጣም ተናደደ #ወደ_ነበርሽበት_ዲን_ተመለሽ_ሲል_ማስፈራራት_ጀመረ፡፡ያቺ ተቅያህ ሴት ግን በፍጹፁም የማምነዉ በአሏህ ነዉ አልመለስም በማለት በአቋሟ ፀናች፡፡ጀባሩ ፊርዐዉንም ዉሀ በበርሜል አፈላና ሁሉንም ልጆቿን ከዛ ከፈላ ዘይትና ዉሀ ዉስጥ አስገበባቸዉ😭፡፡ሁሉንም ሲያስገባቸዉ ስጋና አጥንታቸዉ ሲለያይ እያየች ሶበረች፡፡ ከነበረችበት ሀይማኖት ከዲነል ኢስላም ነቅነቅ አላለችም ነበር፡፡አንድ በእቅፏ ያለ ጡት የሚጠባ ልጅ ነበራት፡፡ እሱን ሊያስገባዉ ሲል ሆዷ አልችል አለ😭😭እናት አይደለችም!! #አሏሁ_ሱብሓነሁ_ወተዓላም_ተቅይነቷን_ሲያረጋግጥላት_ያንን_በእቅፏ_ያለን_ልጅ_በችሎታዉ እንድናገር አደረገዉ፡፡ ልጁም #እማየ_አብሽሪ_ሶብሪ_የአኼራ_ቅጣት_ከዱኒያ_ቅጣት_ይበልጣል_ምንም_ወደኃላ_አትበይ_አብሽሪ_ሐቅ_ላይ_ነሽ በማለት አበሸራት፡፡ #አሏሁ_አክበር_ሱብሓን_አሏህ_ እሷም ለጀባሩ ፊርዐዉን አንድ ነገር ብቻ ቃል ግባልኝ!!አጥንቱን ሰብስበህ በአንድ ላይ ከልጆቼ ጋር እንድትቀብረኝ ስትል ተማፀነችዉ፡፡ጀባሩ ፊርዐዉንም ይህን አደርግልሻለሁ ሲል ቃሏን ተቀበለ፡፡ከዚያም ከፈላዉ ዉሀ ዉስጥ ከልጆቿ ጋር አብሮ አስገባት እሷም ልጆቿም ሸሂድ ሆነዉ ሞቱ😭፡፡
#ለዲነል_ኢስላም_መስዋትን_መክፈል_ማለት_ይህ_ነዉ ፡፡የዚች የሷሊሓ የተቅያህ ሴት ቀብር ነበር ረሱሉን በሚያምር ሽታ ያወዳቸዉ፡፡
٤،والمجاهدون في سبيل الله؛رأى قوما يزرعون ويحصودون في يومين فقال له جبريل هؤلاء المجاهدون في سبيل الله،والمجهاد في سبيل الله نوعان؛جهاد بالسنان أي بالسلاح ،وجهاد في سبيل الله بالبيان،وثواب هذا كثواب من جاهد بالسلاح ،فاليوم من أمر بالمعروف ونهى عن المنكر بجد فهو مجاهد في سبيل الله.والمجاهدون لهم دراجة عالية في الأخرة.قال رسول الله صلى الله عليه وسلم" #من_أحيا_سنتي_عند_فساد_أمتي_فله_أجر_شهيد"والمقصود بالسنة هنا الشريعة التي جاء بها رسول الله صلى الله عليه وسلم
➍፦ረሱሉ በኢስራእ ጉዟቸዉ በአሏህ መንገድ ላይ የሚታገሉ ሰዎችን አይተዋል፦ረሱሉ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም #በኢስራእ_ጉዟቸዉ_ሰዎች_በሁለት_ቀን_ዘር_ዘርተዉ_ሲያጭዱ_ተመለከቱ፡፡ ሰይዱና ጂብሪል ዐለይሂ ሰላምም ለረሱላችን እነዚህ ሰዎች በአሏህ መንገድ ላይ ይታገሉ የነበሩ ሰዎች ናቸዉ ሲሉ ነገሯቸዉ፡፡ጂሀድ ሲባል በሁለት ይከፈላል አንደኛዉ ጂሀድ #የመሳሪያ_ጂሀድ_ማለትም በጦር ሜዳ በሰይፍ የሚደረገዉ ጂሀድ ሲሆን ሁለተኛዉ የጂሀድ አይነት ደግሞ #በአንደበት_ግልፅ_በማድረግ_ነዉ፡፡በምላስ ግል ማድረግ በሰይፍ(በመሳሪያ ከሚደረገዉ)ጂሀድ ጋር አጅሩ እኩል ነዉ፡፡በዚህን ጊዜ በጥሩ ማዘዝና በመጥፎ ነገር መከልከል ለአሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ተብሎ ጂሀድ እንደማድረግ ነዉ፡፡በአሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓ መንገድ ላይ የሚታገሉ ሰዎች በአኺራ ትልቅ የሆነ ደረጃ አላቸዉ፡፡ #ረሱሉ_ዐለይሂ_ሶላቱ_ወሰላም በሐዲሳቸዉ" #የኔን_ሱና_ፈሳድ_በበዛበት_ጊዜ_ሐይ_ያደረገ_አንድ_ሸሂድ_የሚያገኘዉን_አጅር_ያገኛል_ብለዋል፡፡ሱና ሲባል የተፈለገበት ረሱላችን ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም የመጡበትን ሸሪዓ ፈሳድ በበዛበት ዘመን ሐይ ያደረገ ነዉ፡፡

🎖SHARE🎖
┏━ 🌹 ━━━━ 🌹━┓
#ኢንሻ_አሏህ_ክፍል_5⃣_ይቀጥላል....
┗━ 🌹 ━━━━ 🌹━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ለተጨማሪ ትምህርቶች

┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
#በቴሌግራም_አድራሻችን👇👇
ኒሳኡል መሻሪዕ👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
You tube👇👇
https://youtu.be/dvuxxKQllK4
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
2024/11/16 09:55:36
Back to Top
HTML Embed Code: