Telegram Web Link
أحبابي في الله تعالى
تذكَّروا وذكّروا غيركم أنَّ #ذكرى معجزة الإسراء والمعراج تصادف يوم الأحد المقبل ٢٧ رجب الموافق في ٢٢-٣-٢٠٢٠، وعليه فإن ليلة الإسراء والمعراج بعد مغيب شمس يوم غد السبت.

تقبل الله طاعاتكم، وكل عام وأنتم بخير

የፊታችን እሁድ የረጀብ ወር 27ኛው ቀን ነው፡፡
ነገ ቅዳሜ ማታ ደግሞ የረጀብ ወር 27ኛው ለይል ነው፡፡በዚች ለይል አምሳያ ነበር ሰይዳችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ኢስራእ እና ሚዕራጅ ያደረጉት!

ለሀገራችን ስላም አማን ዱዓ እንድናደረግ አስታውሳቹሃለሁ፡፡
Share👇

https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
#አቅሷ_የነቢያት_መገናኛ__ኢስራእ_ወል_ሚዕራጅ_ክፍል
#الأقصى ملتقى الأنبياء🍂الإسراء والمعراج
من عجائب ما رأى الرسول عليه الصلاة والسلام في الإسراء
#ረሱላችን_ዐለይሂ_ሶላቱ_ወሰላም #በኢስራእ_ጉዟቸዉ_ካዯቸዉ ተዐምራቶች ዉስጥ፦ ከክፍል 4 የቀጠለ....
٥،خطباء الفتنة؛رأى أناسا تقرض ألسنتهم وشفاههم بمقاريض من نار،قال له جبريل؛هؤلاء خطباء الفتنة،يعني الذين يخطبون للشر والفتنة،أي يدعون الناس إلى الضلال والغش والخيانة.
➎፦ #ረሱሉ_ሶለሏሁ_ዐለይሂ_ወሰለም በኢስራእ ጉዟቸዉ በፊትና የሚናገሩ ሰዎች ምላሳቸዉ በጋለ መቀስ ሲቆረጥ አይተዋል፦ #ሰይዱና_ጂብሪልም ስለነዚህ ሰዎች ሲናገሩ እነዚህ ሰዎች ፊትናን የሚናገሩ ሰዎች እንድሁም ሰዎችን በሸር፤በፊትና ሲያናግሩ የነበሩ ናቸዉ ማለትም ሰዎችን ወደ ጥሜትና ፊትና ሲጣሩ ሲያጭበረብሩ የነበሩ ሰዎች ናቸዉ አሉ፡፡
٦؛والذي يتكلم بالكلمة الفاسدة؛ورأى ثورا يخرج من منفذ ضيقة ثم يريد أن يعود فلا يستطيع أن يعود إلى هذا المنفذ ،فقال جبريل هذا الذي يتكلم بالكلمة الفاسدة التي فيها ضرر على الناس وفتنة ، ثم يريد أن يريدها فلا يستطيع.
➏፦ #ፈሳድ_የሆኑ_ንግግሮችን_የሚናገሩ_ሰዎችን_አይተዋል፦ እነዚህን ሰዎች ሲመለኩት ያዩት አንድ በሬ ትንሽ በሆነች ቀዳዳ ይወጣል ከዚያም ተመልሶ ልግባ ሲል መመለስ አይችልም ነበር፡፡ ሰይዱና ጂብሪልም ስለነዚህ ሰዎች ለረሱሉ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም እነዚህ ሰዎችን ለመጉዳትና ፊትና ለማሳደር ሲናገሩ የነበሩ ናቸዉ ከዚያም የተናገሩትን ንግግር እንመልሰዉ ቢሉ መመለስ አይችሉም አሏቸዉ፡፡
٧،والذي لا يؤدون الزكاة؛ورأ أناسا يسرحون كالأنعام على عورتهم رقاع(ستر صغيرة)قال له جبريل هؤلاء الذين لا يؤدون الزكاة.
➐፦ #ዘካትን_የማያወጡ_ሰዎችን_አይተዋል፡፡ #ሰዎች_ራቁታቸዉን_ሆነዉ_ትንሽ(ቁራጭ ልብስ)ብቻ አድርገዉ ልክ እንደ እንስሳት ሲገፋፉ አይተዋል ሰይዱና ጂብሪልም እነዚህ ሰዎች ዘካትን የማያወጡ ናቸዉ ሲሉ ነገሯቸዉ፡፡
٨،وتاركو الصلاة؛ورأى قوما ترضع روءسهم ثم تعود كما كانت فقال جبريل هؤلاء الذين تتثاقل رءوسهم عن تادية الصلاة
➑፦ #ሶላትን_የማይሰግዱ_ሰዎች_ራሳቸዉ_እየተፈጨ_እንደገና_ወደ ነበረበት_ሲመለስ_አዩ ጂብሪልም እነዚህ ሰዎች ሶላት የማይሰግዱ ሰዎች ናቸዉ አሉ፡፡ያ!አሏህ!!
٩،وازناة؛ورأى قوما يتنافسون على اللحم المتنتن ويتركون اللحم الجيد المشرح فقال جبريل هؤلاء أناس من أمتك يتركون الحلال فلا يطعمونه ويأتون الحرام الخبيث فيأكلونه وهم الزناة.
➒፦ #ዚና_የሚሰሩ_ሰዎችንም_አይተዋል፦ሰዎች ንፁህ ስጋ እያለ የተበላሸ ስጋን ለመብላት ሲሽቀዳደሙ አይተዋል፡፡ ሰይዱና ጂብሪልም እነዚህ ሰዎች ከአንተ ኡመት ዉስጥ ሐላልን ትተዉ ለሐራም የሚሽቀዳደሙ ዛኒዎች ናቸዉ በማለት ነገሯቸዉ፡፡
١٠،وشاربون الخمر؛رأى أناسا يشربون من الصديد الخارج من الزناة،قال له جبريل هؤلاء شاربو الخمر في الدنيا.
➓፦ #ኸምር_የሚጠጡ_ሰዎች_ከዛኒዎች_የሚወጣዉን_የሚያስጠላዉን_ቆሻሻ_ሲጠጡ_አይተዋልሰይዱና ጂብሪልም ስለነዚህ ሰዎች ሲናገሩ እነዚህ ሰዎች በዱኒያ ሲኖሩ ኸምርን ሲጠጡ የነበሩ ናቸዉ አሉ.
١١،والذين يمشون بالغيبة ؛رأى قوما يخميشون وجوههم وصدورهم بأطفار نحاسية ، قال جبريل ؛هؤلاءالذين كانوا يغتابون الناس.واغيبة من أشد أسباب عذاب القبر هي والنميمة وترك الاستنزاه من البول،وغيبة الأتقياء من الكبائر،ثم الغيبة لا تفسد الصوم.قال الإمام أحمد"لو كانت الغيبة تفسد الصوم لما صح لنا صوم
#ነገርን_ሲያመላልሱ_የነበሩ_ሀሜተኞች_ከነሀስ_በሆነ_ጥፍራቸዉ_ፊታቸዉን_ሲቧጭሩ_አይተዋል ሰይዱና ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ስለነዚህ ሰዎች ሲናገሩ ሰዎችን ሲያሙ የነበሩ ናቸዉ አሉ፡፡እንደምናዉቀዉ ሀሜት ለቀብር ቅጣት ሰበብ ነዉ እንድሁም ነገር ማመላለስና ሽንትን ከሸኑ በኃላ የማያዳርቁ ሰዎችም ለቀብር ቅጣት ሰበብ ነዉ፡፡ታላላቅ ተቅይ የአሏህ ባሪያዎችን ማማት ከታላላቅ ወንጀሎች ነዉ፡፡ሀሜት ትልቅ ወንጀል ነዉ እንጂ አንድ አንድ ሰዎች እንደሚሉት ግን ሀሜት ፆምን አያበላሽም፡፡ #ኢማሙ_አሕመድ_ረዲየሏሁ ዓንሁ እንድህ ይላሉ፦ #ሀሜት_ፆምን_የሚያበላሽ_ቢሆን_ኖሮ_አንድም_ፆሙ_ትክክል የሚሆን አልነበረም ይላሉ፡፡ቢሆንም ሀሜት ትልቅ ወንጀል ነዉና ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡
🎖SHARE🎖
┏━ 🌹 ━━━━ 🌹━┓
#ኢንሻ_አሏህ_ክፍል_6⃣_ይቀጥላል....
┗━ 🌹 ━━━━ 🌹━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ለተጨማሪ ትምህርቶች

┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
#በቴሌግራም_አድራሻችን👇👇
ኒሳኡል መሻሪዕ👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
You tube👇👇
https://youtu.be/dvuxxKQllK4
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
#አሠላሙ_ዓለይኩም #ወራህመቱሏሂ
#ወበረካቱሁ
#እንኳን_ለ1441ኛዉ_ዓመተ_ሂጅሪያ_የአሽረፈል_ኸልቅ_ኢስራእ_ወል_ሚዕራጅ_ትልቅ_ተዐምር_የተከሰተበት_ለይል_አደረሳችሁ
🍬🌹👭 🍬💕🌹 👭 🍬🌹 🍬🌹👭
#ከሴቶች_ለሴቶች_ክፍል 56
ዳዉሎድ ያድርጉ ይስሙ ለሌችም ያስተላልፉ
#1:44:77 ሴኮንድ
🔍 #LINK

ከታች ባሉት ሊንኮች ዳውንሎድ ያድርጉ ያድምጡ ለሌሎችም ያስተላልፉ
👇👇👇👇👇👇👇
ለማውረድ 🎧
ጥራት ያለው ድምፅ
👇👇👇
ይጠብቁን
👆👆👆👆👆
━════ 💓💓💓 ═════━
🎧 #በዛሬዉ_ልዩ_ከሴቶች_ለሴቶች የሬድዮ ፕሮግራማችን ያካተትናቸዉ፦
📚 #ከእዉቀት_ማእድ_የደርስ_መሰናዷችን
☞ መልእክተኛዉ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ኢስራእና ሚዕራጅ እንድያደርጉ የተፈለገበትን አላማ የሚያስታዉስ ደርስ📚
☞ግጥም
☞ረሱሉ በኢስራእና ሚዕራጅ ጉዟቸዉ ያያቸዉ ተዐምራቶችን......አካተናል

☞ረሱሉ ከኢራእና ሚዕራጅ መልሳቸዉ በኃላ እዉነት ብለዉ ምንም ሳያገራግሩ ስለተቀበሉ #አቡበክር ሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ እና ስለ መካዎች
👩‍👩‍👦 #የኢስላም_እንስቶች
☞ስለ ጀግናዋ እና ሸሂዷ የኢስላም ሱመያ ስለሆነችዉ #ማሺጦቱ_ቢንት_ፊርዐዉን_ረዲየሏሁ_ዓንሃ ትረካ

🌎ሌሎች ምርጥ ምርጥ አባባሎች ከተጋባዥ #_የኢስራእና_የሚዕራጅ_ትዉስታ_መንዙማዎች_ጋር ተካተዉበታል ይከታተሉን...

#ስለፕሮግራሙ_ያላችሁን_አስተያየቶች
https://www.tg-me.com/MaidaAhmed ወይም 0936994553 ብላችሁ አድርሱን

🥇shar...share....Share.,
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ለተጨማሪ ትምህርቶች
┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
#በቴሌግራም_አድራሻችን👇👇
ኒሳኡል መሻሪዕ👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
ኡሙ አካዳሚ👇
https://www.tg-me.com/umuakadami

┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
#ዛሬ_ናት_ቀናችን_ዛሬያችንን_እንጠቀምበት!
#ዛሬ_በነፃ_የተመከርነዉን ምክር የማንቀበል ከሆ ነገ ቁጭትን በዉድ ዋጋ እንገዛለን!

#ዛሬ_ተዉባህ_ከማድረግ ተዘናግተንና በወንጀል ተጨማልቀን ማደርን ከመረጥን ነገ መለከል መዉት መጥቶ ከወሰደን በኃላ ማምለጫ አናገኝም! ከሳሪዎቹ እኛዉ ነን!
#ዛሬ ተዋርደንና ተቸግረን የዲን ዕዉቀትን ፍለጋ የማንቀሳቀስ ከሆነ ነገ ሳንወድ በግድ የመሃይምነትን ቀንበር እንሸከማለን!

#ዛሬ በርትተን ካልሰራን በምናገኘዉም ብኩን የምንሆን ከሆነ ነገ እኛ ሚስኪኖች ነን!

#ዛሬ ከሞተዉ አማኝ ይልቅ ነገ የሚሞተዉ ይሻላል፡፡ምክንያቱም በመልካም ስራዉ ላይ የአንድ ቀን ስራ ጨምሯል፡፡

#ትናንህ አለፈ ከሙታኖችም ምድብ ተመደበ፡፡ነገ ገና ነዉ አልደረሰም ብርሃኑንም ለእኛ አልፈነጠቀም #ዛሬ_ግን_በእጃችን ገብቷሎ ተላሎች አንሁን ዛሬን እንጠቀምበት፡፡

#ቀናችን እንግዳችን ነዉ፡፡ያረፈብንን እንግዳችንን በጥሩ ሁኔታ እናስተናግደዉ፡፡ በጥሩ ሁኔታ ካስተናገድነዉ በምስጋና ይለየናል በመጥፎ ካስተናገድነዉ ደግሞ በትችትና በወቀሳ ይለየናል፡፡ ጊዜያችንም ዛሬ በመልካም ነገር ካላሳለፍነዉ ነገ የዉመል ቂያማህ ሲወቅሰንና ሲያፀፅተን እናገኘዋለን፡፡

#አሏሁ_ተዓላ_ዛሬያችንን_አሳምሮ ለአኺራችን የምንዘጋጅበትን መልካም ስራ የምንሰራበት ያድርግልን፡፡

https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
#Corona_ virus(COVID-19)
ኮሮና ቫይረስን መጨነቅ እና መፍራት ሳይሆን በእውቀት መራመድ ያቆመዋል!
በውሃ ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽን ለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ፦
☞ ከሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡

☜ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ ...ወዘተ ያሉትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/ Snow አትመገቡ!
☞ የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡

1. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖ ሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም። ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡
በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው፡፡

☞አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ ተጠቂ አትሆኑም፡፡

2. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡

3. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጧቸው ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡
#በቫይረሱ_የመጠቃት_ምልክቶች #ምን ምንድን ናቸው?

1. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጎሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል::

2. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ ትራኪያ ከወረደ በኋላ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡

ሳምባን በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ምችን ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት የሚታይባችሁ ሁሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!!

#በቫይረሱ_ላለመያዝ_ምን ማድረግ ይገባል?

1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላ በተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡

< ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ ወይም [እንደ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡

< ስለዚህ ለራሳችሁና ለጓደኞቻችሁ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡

2. አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም ሊቀንሰው ይችላል፡፡

3. የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ።

Share እናድርገዉ

https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
#አዎ_እሷ_እንድህ_ነች!!! እሷ ማናት?? አንብባችሁ ድረሱበት......
በደኑ ውበት ተማርኮ ዛፍ ቅጠሉን እያየ ሳለ ነበር ከኃላው አንዳች የሚንኮሻኮሽ ድምፅ የሰማው …ምንነቱን ለማረጋገጥ ዞረ…ከኃላው የነበረው #አንበሳ ነበር፡፡ አይኑን ማመን አቃተው ደነገጠ፣ እግሬ አውጭኝ ብሎም መሮጥ ጀመረ፡፡ አንበሳውም ተከተለው፡፡ ጥቂት ከሮጠ በኃላ የውሀ ጉድጎድ አየ ሌላ ምንም አማራጭ ስላልነበረው ዘሎ የውሀ ማውጫው ገመድ ላይ ተንጠለጠለ .....

#አንበሳውም እያጎራ ይጠብቀው ጀመር፡፡ ድንገት ወደ ታች ሲመለከት የውሀ ጉድጎዱ የቆየ ነበርና የእባቦች መጠራቀሚያ ሆኗዋል… የሰውዬው የልብ ምት ጨመረ ከለይም ከታችም ሁለት አስፈሪ ነገሮች ተጋርጠውበታል …
የውስጡን ፍርሀት እያስታመመ ወደ ላይ ቀጥ ሲል ሁለት ነጭ እና ጥቁር አይጦች ገመዱ የታሰረበት እንጨት ላይ ሆነው ገመዱን ሲቆረጥሙት አስተዋለ!



#ኦ_ጌታዬ_ዛሬ
የመጣብኝ መከራ " ብሎ አይጦቹን ለማባረር ገመዱን በመወዛወዝ ማንቀሳቀስ ጀመረ …ወደ ቀኝ ወደ ግራ ራሱን ሲያንቀሳቅስ ከአንዱ የጉድጎዱ ጎን የሆነ ወፈር ያለ ፈሳሽ
ነገር ነካው፡፡ በደንብ ቀረብ ብሎ ሲመለከት በጉድጎዱ ግድግዳ ድንጋይ ክፍተት ውስጥ ንቦች ማር ጥለው ነበር፡፡ ሰውዬው የነበረበትን መከራ ከላይና ከታች የሚጠብቁትን ነገሮች ረስቶ ማሩን መላስ ተያያዘው፡፡ ማሩ በጣም ጣፋጭ ነበርና ያለበትን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ረሳዉ ዓጂብብብብ


በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ድንገት ከእንቅልፉ ባቶ ነቃ… አስፈሪና የሚረብሽ ሕልም ነበር ሲያይ የነበረው …

#ከዚያም ህልሙን ወደ ሚፈታለት ሰው ለመሄድ ወሰነና ወደ አንድ ህልም ፈች አዋቂ ሰው በመሄድ ህልሙን አንድ በአንድ ዘርዝሮ ነገራቸዉ ።

#ሸይኹም ሳቁና የሕልሙ ፍች አልገባህም ሲሉ በመገረም ጠየቁት፡፡ ሰውዬውም አሉታዊ መልሱን መለሰለት…

#ከኃላህ ሲያባርህ የነበረው " #መሊከል_መዉት" ነው፣
#እባቦች ያሉበት ጉድጎድ ደግሞ #ቀብርህ ነው፣
#የተንጠለጠልክበት ገመድ ደግሞ #እድሜህ ነው፣
#ነጭና_ጥቁሮቹ_አይጦች ደግሞ ቀንና ማታ እድሜህን #እየበሉብህ ነው ብለዉ ሸይኹ ነገሩት…

#እሱም ተገረመና ሸይኺ!! ማሩስ ምንድ ነው ?! ሲል ጠየቀ
ሸይኹም … #ማሩማ_ዱናያ_ነች_ጥፍጥናዋ_ሞትና ሒሳብ እንዳለብህ አስረሳችህ …በማለት ደመደሙለት። ሱብሓን አሏህ፡፡ የሰዉ ልጅ የፈለገ ችግርና መከራ ቢገጥመዉ ዱኒያ ግን ከዚያ በላይ ታሸንፈዋለች፡፡ ሁሌም ለዱኒያ ይሮጣል...አኺራን ግን ይዘነጋል፡፡ #ሱብሓን_አሏህ!!

▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ለተጨማሪ ትምህርቶች
┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
#በቴሌግራም_አድራሻችን👇👇
ኒሳኡል መሻሪዕ👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
ኡሙ አካዳሚ👇
https://www.tg-me.com/umuakadami

┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
You tube wedding program
"#ከሴቶች_ለሴቶች_ክፍል 55 {የሰርግ ፕሮግራም) part 55 wedding program" on YouTube👇👇👇
https://youtu.be/l5q4Bt_Y5nE
https://youtu.be/l5q4Bt_Y5nE
"ስለ Corona virus (COVID-19) ማወቅ ያለብን ጠቃሚ መረጃዎች @ኒሳኡል መሻሪዕ 2020" on YouTube
https://youtu.be/9zbxWbXso8c
https://youtu.be/9zbxWbXso8c
#ባሕርን_መሆን_የቻለ_ሰዉ_ብዙ ነገሮችን ማለፍ ይችላል፦
በአንድ ወቅት በሕይወቱ ደስታን ያጣ አንድ ታዳጊ ወጣት አንድ የዕድሜ ባለፀጋ ሽማግሌን ሕይወት እንዳማረረችው ገልፆ መፍትሄ እንዲጠቁሙት ጠየቃቸው፡፡ ሽማግሌው የወጣቱን ሀሳብ በጥሞና ካደመጡ በኋላ በእፍኙ ሙሉ ጥሬ ጨው በብርጭቆ ውሃ ጨምሮ በጥብጦ እንዲጠጣው አዘዙትና “ጣዕው እንዴት ነው?” በማለት ጠየቁት፡፡ ወጣቱም ፊቱን አኮሳትሮ “ #በጣም_አስቀያሚ_ነው!” ሲል መለሰላቸው፡፡ ሽማግሌው ፈገግታ እያሳዩት ወጣቱን ወደ ባሕር ዳርቻ ወስደው ሌላ ጭብጥ ሙሉ ጨው ባሕሩ ውስጥ እንዲጨምርበት አመላከቱት፡፡ በመቀጠልም ከባሕሩ ጨልፎ እንዲጠጣ ካደረጉ በኋላ “ #ጣዕሙ_እንዴት_ነው?” ሲሉ በድጋሜ ጥያቄ አቀረቡለት፡፡ “ #ጥሩ_ነው” በማለት መለሰ ታዳጊው፡፡ አስከትለውም “የጨው ኮምጣጣነትና ያ አስቀያሚው ስሜት ተለይቶሃል?” በማለት ጠየቁት፡፡ “በፍጹም” ሲል መለሰ ወጣቱ፡፡
ከዚህ ሁሉ የተግባር ትምህርት ቀጥለዉ ሽማግሌው የወጣቱን እጅ ይዘው ከጎኑ ተቀመጡና እንዲህ ሲሉ መከሩት፦
#በሕይወት_ጎዳና_የምታደርጋቸው_ትግሎች_እንደ ንፁህ ጥሬ ጨው ናቸው፡፡ ነገር ግን የስቃዩ መጠን ተመሳሳይ ቢሆንም የምንሸከመው ስቃይ የሚወሰነው በምንይዝበት ዕቃ መጠን ነዉ፤ ችግሩን የምናስተናግድበት አግባብም የሚፈጥረውን ጫና በዛው ልክ ይለያየዋል፡፡ ችግሩ ሲጠናብህ ልታደርገው የሚገባው ዋናው ነገር ምልከታህን ማስፋት ነዉ፡፡ ብርጭቆውን ሳይሆን ባሕሩን መሆን ነው ትልቁ የአኗኗር መላው፡፡ እናም ብርጭቆ መሆንህን አቁመህ ባሕሩን ሁን በማለት አሰናበቱት፡፡ ሱብሓን አሏህ!!
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ለተጨማሪ ትምህርቶች
┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
#በቴሌግራም_አድራሻችን👇👇
ኒሳኡል መሻሪዕ👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
You tube 👇
https://youtu.be/VvYk1gc4goI
https://youtu.be/VvYk1gc4goI
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
Watch ""በእውነታ ላይ መፅናት'' [الثبات على الحق] ዶ/ር ሸይኽ አቡበክር ሱለይማን (doctor sheikh abubekir suleyman)" on YouTube
https://youtu.be/5PqqpLGqSJ8
#እዉነት_የትክክለኛ_አማኞች_መለያ_ነች፡፡ #ኢማኑ_ሙሉዕ_የሆነ_ሙእሚን_አይዋሽም! APRIL FOOLS DAY🚫 እኔ ሙስሊም ነኝ!!
እዉነተኞች በሆኑ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ በሆነ ነበር፡፡(ሱረቱ ሙሐመድ፥21)
እዉነትና ሐሰት ቀልብ ዉስጥ አንዱ ሌላዉን አሸንፎ እስኪወጣ ድረስ ይፋለማሉ፡፡ ልቦናዉ ዉስጥ እዉነት በሐሰት ላይ ድል የተቀዳጀለት ሰዉ እዉነትን ይላመዳል፡፡በንግግሩ ሁሉ እዉነትን መምረጥ ይቀናዋል፡፡በመጨረሻም ከአሏህ ዘንድ እዉነተኛ መሆኑ ይረጋገጥለታል፡፡ ሙእሚን ሌሎች ትላልቅ ወንጀሎችን ሊፈፅም ይችላል ዉሸት ግን ፈፅሞ አይናገርም፡፡
#ዉሸት_አደገኛ_ጥፋት_ነዉ፡፡እዉነት ነዉ ብሎ፣አንደበታችንን አምኖ ለሚያደምጠን ሰዉ ዉሸት ከመናገር በላይ ክህደት የለም!
عن ابن مسعود رضي الله عنه عن النَّبيّ صلى الله عليه وسلم، قَالَ: ((إنَّ الصِّدقَ يَهْدِي إِلَى البرِّ، وإنَّ البِرَّ يَهدِي إِلَى الجَنَّةِ، وإنَّ الرَّجُلَ لَيَصدُقُ حَتَّى يُكْتَبَ عِنْدَ اللهِ صِدِّيقًا. وَإِنَّ الكَذِبَ يَهْدِي إِلَى الفُجُورِ، وَإِنَّ الفُجُورَ يَهدِي إِلَى النَّارِ، وَإِنَّ الرَّجُلَ لَيَكْذِبُ حَتَّى يُكتَبَ عِنْدَ الله كَذَّابًا)). مُتَّفَقٌ عَلَيهِ.
ኢብኑ መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ ባስተላለፉት ሐዲስ የአሏህ መልእክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ እዉነት ወደ መልካም ነገር ይመራል፡፡መልካም ተግባር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል፡፡አንድ ሰዉ እዉነትን ይናገራል አሏህ ዘንድ እዉነተኛ ተብሎ እስከሚፃፍ(እስከሚታወቅ)ድረስ፡፡ሐሰት(ዉሸት) ደግሞ ወደ መጥፎ ተግባር ይመራል፤መጥፎ ተግባር ደግሞ ወደ ጀሀነም ይመራል፡፡አንድ ሰዉ ዉሸትን(ሐሰትን) አይናገርም ከአሏህ ዘንድ ዉሸታም ተብሎ እስከሚፃፍ(እስከሚታወቅ) ድረስ፡፡(ቡኻሪይና ሙስሊም ዘግበዉታል)
የሰዉ ልጅ ቃልና ተግባሩ አንድ የሚያደርገዉ፤ፍትሐዊነትን የሚሰጠዉና የሚቀበለዉ እዉነተኛ ሰዉ ሲሆን ብቻ ነዉ፡፡

#እዉነተኝነት_ማለት_የህሊና_ሚዛናዊ_ምስክርነትን_መከተልና_የቁርኣን_ዳኝነትን_መቀበል_ነዉ፡፡በእርግጥ ሁሉም ሰዎች እዉነተኞች በሆኑ ኖሮ ምን ያክል ሰላምና መረጋጋትን ባገኙ ነበር፡፡ዉሸት የሚያስከትላቸዉ ወንጀሎች በሐሰት ዛፍ ላይ የበቀሉ ሰዎችን የሚወጉ እሾኮች ናቸዉ፡፡በአንፃሩ ደግሞ እዉነተኝነት በሐቅ ዛፍ ላይ አፍርቶ ሰዎች እየቀጠፉ በሕይወታቸዉና በመጪዉ ዓለም የሚደሰቱበትና የሚጠቀሙበተሸ መልካም ፍሬ ነዉ፡፡
قَالَ الله تَعَالَى: {يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللهَ وَكُونُوا مَعَ الصَّادِقِينَ} [التوبة: 119]
#እናንተ_ያመናችሁ_ሆይ! አሏህን ፍሩ ከእዉነተኞች ጋርም ሁኑ፡፡(ሱረቱ ተዉባህ፥119
እዉነት መልካም ለተባሉ ነገሮች ሁሉ በር ከፋች ነዉ፡፡ወደ ታላቅ ደረጃ ለመዝለቅም ወሳኝ ነዉ፡፡
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
ለተጨማሪ ትምህርቶች
┏━ 💗 ━━━━ 💗━┓
#በቴሌግራም_አድራሻችን👇👇
ኒሳኡል መሻሪዕ👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
You tube 👇
https://youtu.be/VvYk1gc4goI
https://youtu.be/VvYk1gc4goI
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
#ኒስፉ_ሸዕባን🌙
ዛሬ ዕለተ ማክሰኞ ነው ሌሊቱ የሸዕባን አጋማሽ ሌሊት ነው(በዱዓና በዒባዳ መጠንከር አለብን) ነገ ሮቡዕ ደግሞ የሸዕባን አጋማሽ ወይም አስራ አምስተኛው ቀን ነው መጾሙ ይወደዳል::
የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ አሁን የምንገኘው በሸዕባን ወር ሲሆን ከሸዕባን ደግሞ ልዩ የሆነ #ራሕመት ከሚወርድባት የሸዕባን አጋማሽ(አስራ አራተኛው ቀን) ላይ እንገኛለን::ዛሬ ዕለተ ማክሰኞ ጸሀይ ከገባችበት ሰዐት አንስተን እውነተኛው ጎህ እስከሚወጣ ድረስ የሸዕባን አጋማሽ (አስራ አምስተኛው ቀን)ሌሊት ይባላል::በዚህ ሌሊት ዱዓእ ማድረጉ ይወደዳል ነገ ቀኑን(ሮቡዕን) ደግሞ መጾሙ ይወደዳል::በሐዲስ እንደመጣው ሰይዳችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል
" #إذا_كانت_ليلة_النصف_من_شعبان_فقوموا_ليلها_وصوموا_نهارها"
ትርጉሙ:“የሸዕባን አጋማሽ (አስራ አምስተኛው ቀን)ሌሊት በሆነ ጊዜ ለሊቱን በሶላት(በሌሎች ዒባዶች) እንዲሁም ቀኑን በጾም አሳልፉት”ብለዋል::በሌላ ሐዲስ ደግሞ እንዲህ ብለዋል:-
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم
"يَطَّلِعُ الله إلى خلقه في ليلةِ النصفِ من شعبانَ فيغفرُ لجميع خَلْقِهِ إلا لمشركٍ أو مشاحنٍ" رواه ابن حبان في صحيحه.
ትርጉሙ“የሸዕባን ግማሽ ሌሊት ላይ አሏህ ባሮቹን ልዩ በሆነች ራሕመት ያጎናጽፋቸዋል ሙሽሪክ እና ለዱኒያ ብለው በመካከላቸው ጥላቻ ቂምና ኩርፊያ ያላቸው ሲቀሩም የተቀሩትን አሏህ ይምራቸዋል”::እናም በዚሁ የማስታውሳችሁ ነገር የተኳረፍነው በውስጣችን ጥላቻን ያሳደርንበት ሙስሊም ወንድማችን ወይም እህታችን ካለ ይቅር እንባባል ይህ ራሕመት እንዳያልፈን::እዚህ ጋር ወሀቢያዎችን አይደለም የሚፈለግበት!!!እነሱ በኩፍር እምነታቸው ከሙሽሪኮች ናቸው::ሌላው ጉዳይ በዚች ሌሊት ዱዓእ ስናደርግ ቁርኣንን ሐዲስን በማይጋጭ መልኩ መሆን አለበት::ዱዓም እውቀት ያስፈልገዋልና::በዚች ሌሊት ቁርኣን መቅራቱ ይወደዳል::ሱና ሶላቶችን መስገድ ማብዛት ፣ ዚክር ማብዛት ዲናዊ እውቀት መማማር እና መልካም ስራዎችን በመስራት ማሳለፉ በጥብቅ የተወደደ ነው::ይሁንና “ያሲንን ለይቶ መቅራት ከነብዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም መጥቷል”የሚባለው ስህተት ነው!
#_ጥንቃቄ_1 በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚባሉና የተለመዱ ዱዓዎች አሉ ለምሳሌ እንዲህ የሚል ዱዓ:
"اللَّهُمَّ إِنْ كُنْتَ كَتَبْتَنِي عِنْدَكَ فِي أُمِّ الْكِتَابِ شَقِيًّا أَوْ مَحْرُومًا أَوْ مَطْرُودًا أَوْ مُقَتَّرًا عَلَيَّ فِي الرِّزْقِ، فَامْحُ اللَّهُمَّ بِفَضْلِكَ شَقَاوَتِي وَحِرْمَانِي وَطَرْدِي وَإِقْتَارَ رِزْقِي، وَأَثْبِتْنِي عِنْدَكَ فِي أُمِّ الْكِتَابِ سَعِيدًا مَرْزُوقًا مُوَفَّقًا لِلْخَيْرَاتِ،"
ይህ ዱዓ ከነቢዩም ሆነ ከሶሐበቶች የተገኘ አይደለም::ከሰዪዱና ዑመርም ረዲየሏሁ ዐንሁ አልተገኘም::ኢማሙል በይሀቂይም በኪታባቸው የጠቀሱት ዶዒፍ እንደሆነ በሚገልጽ ቃል እንጂ ትክክል ነው ብለው አይደለም::ይህ ዱዓ ላይ “فَامْحُ اللَّهُمَّ” የሚለው መጀመሪያ ላይ ካለው “اللَّهُمَّ إِنْ كُنْتَ كَتَبْتَنِي عِنْدَكَ فِي أُمِّ الْكِتَابِ شَقِيًّا أَوْ مَحْرُومًا” ከሚለው ጋር እውቀት ከሌላቸው ሰዎች ዘንድ “አሏህ አዘልይ(ጅማሬ የሌለውን) ውሳኔውን ይቀያይራል”የሚልን ሊያሲስመስል እና ሊያሲዝ የሚችል የተሳሳተ ቃል በመሆኑ መተው የተሻለ ነው::ምክንያቱም የውሳኔ መቀያየር በአሏህ ላይ እንደማያመች የሙስሊሞች እምነት ነውና::
አንድ ሰው የአሏህ ውሳኔ ይቀየራል ብሎ ሊያምን አይገባም::የአሏህ ውሳኔ ዱዓ በሚያደርግ ሰው ዱዓም ሆነ ሶደቃ በሚሶድቅም ሶደቃ ይሁን በሚሳልም ሰው ስለትም ይሁን በጭራሽ አይቀየርም::አሏህ በአዘል የሻው ነገር ከመከሰት ቅሮት የለውም::አሏህ በአዘል የወሰነውን ነገር በዱዓ ይቀይራል አይባልም::ለዚህም የሚከተለው ሐዲስ መረጃችን ነው::
فَقَالَ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : " سَأَلْتُ رَبِّي ثَلَاثًا ، فَأَعْطَانِي ثِنْتَيْنِ وَمَنَعَنِي وَاحِدَةً ،
በዚህ ሐዲስ ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል“ጌታዬን ሶስት ነገር ጠይቄው ሁለቱን ሰጠኝ አንዷን ግን አልሰጠኝም” በሌላ ዘገባ ደግሞ “አሏህ እንዲህ አለኝ አሉ“ሙሐመድ ሆይ እኔ ውሳኔን ከወሰንኩ ውሳኔዬ አይቀየርም”::እንግዲህ ለፍጥረታቱ ምርጥ ለኛ አይነታ ነብዩ ሙሐመድ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የአሏህ ውሳኔ የማይቀየር ከሆነ እንዴት ነው በአንድ ተራ ሰው ዱዓ (የሸዕባን አጋማሽም ላይ ሆነ በሌላው ጊዜ) የአሏህ ውሳኔው ይቀየራል የሚባለው?በጭራሽ አሏህ አይቀያየርም ባህሪያቶቹም አይቀያየሩም::
እኛ ሙስሊሞች ዱዓ ስናደርግ ኒያችን “አሏህ የዱዓችንን ተቀባይነት በአዘል ሽቶት ከሆነ ያ ዱዓችን ተቀባይነት ያገኛል አሏህ የሻው ደግሞ ተቀባይነት እንዳያገኝ ከሆነ በአሏህ ፍቃድ ሰዋብ አለን የሚለውን በማሰብ ይሆናል”ማለት ነው::
#ጥንቃቄ_2 አሏህ በቁርኣን“” በማለት የነገረን የሚፈለግበት የሸዕባን አጋማሽ ሌሊት እንዳልሆነ ልናምን ግድ ይላል::ከፊል ሰዎች ዘንድ ይህ ነገር ተስፋፍቶ ቢገኝም ግና እውነታው ይህ አይደለም፡፡ ይልቁንስ በዚህ የቁርኣን አንቀጽ የሚፈለግበት ‘ለይለቱል ቀድርን’ነው::
ታዲያ የዚች አንቀጽ ትርጉም " فِيهَا يُفْرَقُ كُلُّ أَمْرٍ حَكِيمٍ" ምንድን ነው ከተባለ...
ትርጉሟ:“ከዚች አመት አንስቶ እስከ ቀጣዩ አመት ድረስ ከሞትና ህይወት፣ከውልደትንና ሲሳይ እንዲሁም ከመሳሰሉት የሚከሰተውን በዝርዝር አሏህ ለከፊል መላኢኮቹ ያሳውቃቸዋል”ማለት ነው::
አሏህ ዱኒያ አኼራችንን ያሳምርልን #ሑስነል ኺታም ይረዝቀን
#ለዲኑ_የቆምን ኸዳሚዎች ያድርገን
#ተራራ_የሆነ_እውቀት_ከተግባሩ ጋር ይስጠን
የሰይዳችንንም ቀብር ዚያራ ይረዝቀን
በህልማችንም የምናያቸው ያድርገን
የተጨነቁ ወንድምና እህቶችንም ከጭንቀት አሏህ ያውጣቸው
ጀምዒያችንንም በዓለም ላይ የምትስፋፋ ያድርጋት
#መሻይኾቻችንንም_አሏህ_ይጠብቅልን
የታመሙትም ወንድም እህቶቻችንን አሏህ ያሽራቸው
#አሏህ ባወቅነው የምንሰራ ያርገን አሏህ ይዘንልን ይማረንም::ኣሚን ያረበል ዓለሚን
በመጨረሻም ኢማሙ ሻፊዒይ ዱዓእ ተቀባይነት ከሚያገኝበት ወቅቶች መካከል በሸዕባን ወር አጋማሽ ሌሊት የሚደረግ ዱዓ ነው ብለዋል::

💧 #ካስቀየምኳችሁ_ዐዉፍ_በሉኝ_በዱዓችሁም_አትርሱኝ_እኔ_ሐቄን_ነክቶ_ያስቀየመኝ_ካለ_ዐዉፍ_ብያለሁ::

┏━ 💗 ━━━━ 💗 ━┓
በቴሌግራም አድራሻችን ለመቀላቀል......👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
Youtube
https://youtu.be/Cz7tk898CXk
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
”መጃሊሱል - ሁዳ” ክፍል 3 | ልዩ የረመዷን ፕሮግራም ”part 3 of the Ramadan Program ''Mejalisul-Huda|| مجالس الهدى|" on YouTube👇👇share

https://youtu.be/DEncrnlw5z8
https://youtu.be/DEncrnlw5z8
#ምርጫችንን_እናስተካክል!!
ዱኒያ ላይ ስንኖር ወደ አኺራ የሚያደርሱ ሁለት መንገዶች አሉ። አንደኛው ቀጥ ያለና መጨረሻውም ፍፁም ሰላምና ደህንነት የሰፈነበት ነው ።ዱኒያ ላይ ሳሊሖች ሆነን ካለፍን በሰዉ ልጅ ልቦና ዉስጥ ዉል ብሎ የማያዉቅ፣ዐይን አይታዉ የማታዉቀዉና ጆሮም ሰምቶት የማያዉቀዉ የሆነ ዘላለማዊ ትልቅ ፀጋ አለበት፡፡እዚያ ዉስጥ ፍፁም ድካም፣ረሀብ ፣ጥማት ፣ችግርም ሆነ ሐዘን የለበትም፡፡
#ሁለተኛው_ደግሞ_ገደላገደል_የሞላበትና አደገኛ የሆነ መንገድ ነው፡፡ጊዜያዉይ ማረፊያ ጥላና ለዓይን የሚስብ ነገር ቢኖረውም መጨረሻው ከንቱ ነዉ፡፡የቱንም ያክል ደስተኛ ሆኖ ቢኖር መጨረሻ ግን መለየቱ አይቀሬ ነዉ፡፡
አብዛኞቹ ሰዎችም ከአንደኛው ይልቅ ሁለተኛውን መንገድ ይመርጣሉ ዉሸታሟን ተድላ፣ደስታ፣ጥላና ውሃ ፍለጋ ሲሉ ከቀጥተኛ መንገድ ይወጣሉ ፣ ከመጨረሻው ይልቅም መጀመሪያቸው ማለትም አሁን ያሉበትን እንጅ ነገ የሚኖሩበትን አያስተዉሉም፡፡
ከነብያት መካከል አንዱ የሆኑት ሰይዱና ኑሕ ዐለይሂ ሰላም በደዕዋ ሥራ /ወደ አሏህ መንገድ በመጣራት /ብቻ በህዝቦቻቸው ውስጥ ከ950 አመታት በላይ ቆይተዋል ።ይህን ያህል እድሜ ከመኖራቸው ጋር ዱኒያን እንዴት እንዳገኟት ተጠየቁ። እሳቸው እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ #ዱኒያ_ይህች ዓለም_ማለት በአንዱ በር ገብተው በሌላኛው እንደሚወጡ ነው ።ሱብሓን አሏህ!ያን ያክል እንድሜ ኖረዉ እንኳን ዱኒያን በዚች ትንሽ ነገር ከገለፇት እኛስ መቶ አመት የሞላ ኑሮ እንኳን ሳንኖር ግለፇት ብንባል እንዴት እንገልፃታለን?? አሏህ አዕለም!

የትክክለኛ አዕምሮ ባለቤት የሆነ ሰው ከትናንት ውሎው ለዛሬ ዉሎዉ ይማራል። ከእጁ ከመውጣቱ በፊትም በዛሬ ቀኑ ውሰጥ ይበረታል ። ለነገው ደግሞ ያለ ምንም መዘናጋት ይዘጋጃል ። #የዚህችን_ዓለም_መጨረሻ_ያወቀና በጥልቅ የተረዳ ሰው ማድረግ ያለበትን ሁሉ አሁኑኑ ያደርጋል፡፡ጥንቃቄን ይመርጣል ። የመንገዱ ርዝመት ያስፈራው ሰው በቂ ሰንቅ ይሰንቃል።

#አሏሁ_ተዓላ ለአኺራቸዉ ከሚሰነቁት ደጋግ ባሮቹ ያድርገን! ኣሚን መልካም ዕለተ #ጁሙዓ😍❤️

┏━ 💗 ━━━━ 💗 ━┓
በቴሌግራም አድራሻችን ለመቀላቀል......👇
https://www.tg-me.com/nisaulmesharie
Youtube👇👇 https://youtu.be/y4B_GG6axxA
https://youtu.be/y4B_GG6axxA
┗━ 💗 ━━━━ 💓━┛
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
"መጃሊሱል - ሁዳ” ክፍል 5| ልዩ የረመዷን ፕሮግራም ”part 5 of the Ramadan Program ''Mejalisul-Huda|| مجالس الهدى|" on YouTube
https://youtu.be/y-UsbRxMukQ
https://youtu.be/y-UsbRxMukQ
Forwarded from የፍትህ መንገድ (عز الدين)
#ረመዷን_ቀናቶችህ_ዉብ_ናቸዉ🌹 መልዕክት➊
️የረመዷን ወር ወደ አሏህ ለመቃረብ ምርጡ ወቅት ነው። በረመዷን ወር የጀነት በሮች ይከፈታሉ የጀሃነም በሮች ይዘጋሉ።ረሱሉ አሚን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሐበቶቻቸውን እንዲህ በማለት ያበስሯቸው ነበር፦
قدْ جاءَكمْ شهرُ رمضانَ ، شهرٌ مباركٌ افترضَ اللهُ عليكُمْ صيامَهُ ، يفتحُ فيهِ أبوابُ الجنةِ ، ويغلقُ فيهِ أبوابُ الجحيمِ.
«የተባረከው የረመዷን ወር መጥቶላችኋል እሱን መፆም አሏሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ በናንተ ላይ ደንግጓል፤ በረመዷን ወር የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የጀሀነም በሮች ደግሞ ይዘጋሉ»
(ኢማሙ አሕመድ ዘግበውታል)።

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFTc4P9JYsO1QUwzGA

┈┈┈••●💎የፍትህ መንገድ 💎●••┈┈┈
"ረመዷን የእዝነት ወር|| ረመዷንን እንዴት እናሳልፈው?||Ramadan The Month Of Mercy|| How Do We Spend Ramadan||" on YouTube
https://youtu.be/BTpOPjBTzLk
https://youtu.be/BTpOPjBTzLk
"መጃሊሱል - ሁዳ” ክፍል 13 | ልዩ የረመዷን ፕሮግራም ”part 13 of the Ramadan Program ''Mejalisul-Huda|| مجالس الهدى|" on YouTube
https://youtu.be/irQQD01WxZQ
https://youtu.be/irQQD01WxZQ
2024/11/16 10:51:49
Back to Top
HTML Embed Code: