Telegram Web Link
«እቤት ሌላ ሰው የለም?» አልኳት ምን ብዬ መጠየቅ እንዳለብኝ ግራ እየገባኝ

«እ ሀኪሙ ገና መለመላውን ወደምድር እንደመጣ ህጣን ማር ከአር እንደማይለዪ ነገረኝ። አጠያየቅዎ ቤተሰብ እንዳሎት ከሆነ አይድከሙ። ብቻዎትን ነው የሚኖሩት። እኔና የበር ጠባቂው ጎንጥ ብቻ ነን!» አባባሏ ምንም የሰብዓዊነት ርህራሄ ያለው አይደለም። እንዴት ያለ ክፉ አሰሪ ብሆንባት ነው ?

«አብሮኝ የሚኖር ሰው እንኳን ባይኖር ሌላ ቦታ የሚኖር » ብዬ ሳልጨርስ

«እኔ እርሶ ቤት ከገባሁ ገና ሶስት ወሬ ነው። እርሶን ብሎ የመጣ ሰውም አላውቅም። እርሶም ፈልገውት የሄዱት ወዳጅ ይኑሮት የማውቀው የለኝም።»

«መቼም የምሰራበት ቦታ ባልደረቦች ይኖሩኛል። ምንድነው ስራዬ? የምሰራበትን ቦታ ታውቂዋለሽ?» እንደሁኔታዋ ብታውቅም የምትነግረኝ አትመስልም።

«እርፍ ወግ! እኔ አላውቅም እትዬ!! ከቀጠሩኝ ቀን ጀምሮ ሰው ብለው ያናገሩኝ ዛሬ ነው። እንዴት አውቄው? በወጉ እንደሰርቶ አዳሪው በጠዋት ተነስተው ስራ ሲገቡ አይቼዎት አላውቅም። እንደው ያሎት ቀን ውልብ ብለው ከቤት ይጠፋሉ። ለሊት በጭፍራው ሰዓት ወደቤት ይመለሳሉ። ብቻ ቤትዎ ከሳምንት እስከሳምንት ሙሉ ነው።» ቃላቶችዋ ውስጥ ያልተፋቻቸው ሌሎች ቃላት ይሰማሉ። በስመአብ!! ስራዬ ከወንጀል ጋር የተያያዘ ይሆን እንዴ? ብዙ ነገር ልጠይቃት ቅደም ተከተሉን እየሰካካሁ ፤ ምን ዓይነት ሴት ብሆን ነው እንዲህ ሆስፒታል አልጋ ላይ ተኮራምቼ እያየችኝ የማላሳዝናት እያልኩ አስባለሁ።

.............  ይቀጥላል...................

@wegoch
@wegoch
@paappii
የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… ክፍል ሁለት
(ሜሪ ፈለቀ)

በአጭሩ የአዲስ አበባ ነዋሪ በሁለት ይከፈላል። ብዙሃኑ እኔን የማያውቀኝ እና የቀረው ጥቂቱ እኔን የሚጠላኝ።

«ይሄን ሁሉ ጥላቻ ትከሻዬ ላይ ቆልዬ እንዴት ኖርኩ? እንዴት አላጎበጠኝም? » በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ አትክልቱን የሚያጠጣውን ጎንጤን ጠየቅሁት።

« አይ እትዬ ዛሬ ሌላ ሰው ሆነው  በንፁህ ልብ ስለተቀበሉት ነው የሚያጎብጥ ሸክም የሆነብዎት። ቂም ባቄመና በጠለሸ  ልብ ሆነው ሲቀበሉት እንዲህ አልተሰማዎት ይሆናል።» አለኝ ከስራው ሳይስተጓጎል። እሱ 'ምንም የማውቀው የለም' ይበለኝ እንጂ በእያንዳንዱ የቃላት ምልሳችን ውስጥ ከነገረኝ በላይ ስለእኔ እንደሚያውቅ የሚያሳብቅ ንግግር ይሰነቅራል። ለጎንጥ ጥሩ ሰው የነበርኩ ሆኜ ወዶኝ አይደለም እንዲህ ቀና መልስ የሚመልስልኝ። እግሩ ስር ፈራርሼ በሽንፈቴ ነው ልቡን ያገኘሁት።

ሆስፒታል ተኝቼ ተናኜ (የቤት ሰራተኛዬ) እየተመላለሰች ስትጠይቀኝ በእያንዳንዱ ቀን ለምጠይቃት ጥያቄ በምትሰጠኝ መልስ ከአደጋው በፊት የነበረችውን ሜላት አበጃጅቼ ላውቃት ጣርኩ። ተናኜ የምታውቀው ጥቂት ነው። በሳምንት ውስጥ አብዛኛውን ቀን ጂም ሄጄ እሰራ ነበር ፣ አብዛኛውን ቀን አመሻሽ ወጥቼ ለሊት እሷ ስትተኛ ነው የምመለሰው፤ በእሷ አገላለፅ ከፈሴ የተጣላሁ ምንም የማያስደስተኝ መንቻካ ሴት ነበርኩ። ጎንጤ በዘበኝነት 1 ዓመት መስራቱን ስትነግረኝ ከሷ የተሻለ መረጃ ይኖረዋል በሚል ሆስፒታል መጥቶ እንዲያየኝ እንድትነግረው ጠየቅኳት።

«ይቅርታ ያድርጉልኝ እመቤቴ ስራዬ ደጃፎትን መጠበቅ ነው። ስራዬን ጥዬ መምጣት አይሆንልኝም። በተረፈው እግዜር ይማሮት!» ብሎ መልዕክት ሰዷል።» ብላ የእርሱን እንቢታ ስትነግረኝ በእርሱ እንቢታ ደስ ያላት ነው የምትመስለው። የሆነ 'የታባሽ' የሚል ዓይነት እምቅ! የዛን ቀን ማልቀስ አማረኝ። ወደሰማይ እያንጋጠጥኩ አምላክን ለመንኩት። ግንሳ ክፉ ሴት ከነበርኩ አምላክስ ያውቀኝ ይሆን?  ህይወት በረደችኝ .......የሆነ እራቁቴን አጋልጣ አደባባይ ያሰጣችኝ ዓይነት መንዘፍዘፍ ተንዘፈዘፍኩ።

አንዳንድ ገልቱኮ 'ያለፈውን ረስተህ አዲስ ህይወት ጀምር ......' ዓይነት ምክር ይመክር ይሆናል። ሰው ያለትናንቱ ምንድነው? ይኸው እጥብ አድርጌ ትናንትን ረስቼው መች ከአዲስ መጀመር ቻልኩ? ከምን እንደምጀምር ተደናብሮብኝ ተገትሬ የለ? ትናንት የዛሬ መንደርደሪያ ይሆናል እንጂ ትናንትን እርሳው እንዴት ይባላል? ትናንት ከሌለ ዛሬ መች ይመጣል? ሰውማ ትናንቱን ነው። ዛሬውን የሚንደረደረው ከትናንት ተነስቶ ነው። እረስቶ ሳይሆን ትናንቱ ጥፋት ከሆነ ተምሮበት፣ ጥሩ መሰረት ከሆነ ደግሞ አዳብሮት ይቀጥላል።

ከሆስፒታል የምወጣበት ቀን ሲደርስ ሆዴ በፍርሃት ሲላወስ ታወቀኝ። የቱ በትክክል እንዳስፈራኝ አላውቅም። እቤቴ ስሄድ ያቺ ተኛኜ የምትጠላትን ሜላት የማገኛት አይነት ስሜት ይሰማኛል። ከቤቴ ይልቅ ሆስፒታል ውስጥ የተሻለ ሰላም የማገኝ ዓይነት ስሜት ፣ ወደቤቴ ሳይሆን ወደግዞት የምሄድ ስሜት ልቤን ተጫነው። ሊገድለኝ የሞከረው ሰው ድጋሚ መጥቶ ቢጨርሰኝስ? ሆስፒታል ውስጥ አኑሩኝ ይባላል? አብሮኝ የተኛ ታካሚ ወዳጅ በተናኜ መሪነት በመኪናው እቤቴ እየሸኘን እጄ ይንቀጠቀጣል። መንገዱ ሩቅ ቢሆንና ቶሎ ባንደርስ?

«ልብስ ልደርብሎት እንዴ? እየተንቀጠቀጡ ነውኮ! » አለችኝ ተናኜ። መንቀጥቀጤን ለመደበቅ አንዱን እጄን በአንደኛው ጭምቅ አድርጌ ያዝኩት። የሆነ ጥቁርና ነጭ ቀለም የተቀባ የብረት በር ፊት ለፊት እንደቆምን የሰማይ ስባሪ የሚያህል፣ ፊቱ ላይ መጀነኑ የሚንጎማለል፣ አንገቱ ላይ ፎጣ ጣል ያደረገ  ጎልማሳ ሰው በሩን ከፈተልን።

«ጎንጤ እሱ ነው?» አልኳት ወደተናኜ ዘወር ብዬ ሳላስበው። በአዎንታ ራሷን ነቀነቀች። ጎንጤ ይሆናል ብዬ የሳልኩት ሰውዬ የሆነ ኮስማና ሸምገል ያለ ደካማ ነገር ነው። ያደረሰንን ሰው አመስግኜ በሩን እያለፍኩ።

«ደህና ዋልክ?» አልኩት ጎንጤን።

«እግዜሐር ይመስገን። እንኳን ለቤትዎ አበቃዎት!» ብሎኝ በሩን መዘጋጋት ያዘ።

ጊቢውን ዙርያ ገባውን አየሁት። ከቤቱ ፊትለፊት ባለ ሰፋ ያለ ቦታ አበቦች ፈክተውበታል። መለስተኛ ቪላ ቤት ነገር ነው። ከቤቱ በአንደኛው ጎን ባለ ክፍት ቦታ መኪና ቆሟል። እንደእንግዳ ዙሪያ ገባውን በአይኔ ስነቅስባቸው ግራ ተጋብተው ነው መሰለኝ። ሁለቱም ቆመው ያዩኛል። እንደተቆጡት ህፃን ብርግግ ብዬ ፈጥኜ ወደበሩ ሄድኩ። እቤት ገብቼ ምን እንደምፈልግ እርግጠኛ ባልሆንም ቤቱን መበርበር ያዝኩ። የፎቶ አልበም ፣ የትዳር ሰርተፊኬት ፣ ወይ የሆነ ደብዳቤ ብቻ አላውቅም አንድ የሆነ ነገር። ሳጎነብስ ቁስሌ እየተሰማኝ መበርበሬን ቀጠልኩ። ቤቱ ሳሎን ሶስት መኝታ ቤት እና ሰፊ ጓዳ እና መታጠቢያ ቤት ነው ያለው። መኝታ ቤቴ መሆኑን የነገረችኝ ክፍል ስገባ ሙሉውን የቁምሳጥኑን በሮች ከከደነው መስታወት ጋር ተፋጠጥኩ። ራሴን በደንብ አየሁት። ትክት ያለው ገፅታ! ክፉ ከመሆኔ ሌላ መከራ የበዛበት ህይወት ይሆን ያሳለፍኩት? የአልጋው ራስጌ ኮመዲኖ ላይ በፍሬም ያለ ፎቶ አይኔን ጠለፈኝ። አንደኛው የራሴ ምስል ነው። ወይም መሰለኝ። ከሆነ ወንድ ጋር ተቃቅፈን እየሳቅን። ከኛ ምስል ጀርባ ቁመቱ በረዛዘመ አረንጓዴ ሳር የተሸፈነ መስክ ይታያል። ቦታውን የማውቀው ዓይነት ስሜት ይሰማኛል ግን ትዝ የሚለኝ ነገር የለም። አሁን ካለሁበት ድንጋይ ቤት ይልቅ ምስሉ ላይ ያለው ሜዳ የቤት ዓይነት ስሜት ሰጠኝ። የሆነ በሳሮቹ መሃል ስሮጥ እርጥበት ያለው ሳር እግሬን እየሳመኝ ዓይነት። እዛ መስክ ላይ ደስተኛ ሴት የሆንኩ የምቦርቅ ዓይነት ሽውታ ትውስታ ይሁን ቅዠት ሰውነቴን ይወረዋል። እሺ የት ነው? እሱስ ማን ነው? አባቴ አይሆንም። በእድሜ እኩያዬ ቢሆን ነው። ተጨማሪ መረጃ ካገኘሁ ብዬ ቁምሳጥኑን አተራምሰው ጀመር። አንደኛውን መሳቢያ ስቤው በድንጋጤ እሪሪሪ ብዬ ጮህኩ። ጎንጥም ተናኜም  እየተሯሯጡ ሲደርሱ መሳቢያው እንደተከፈተ ራቅ ብዬ ቆሜ ደንዝዣለሁ።

«ሽጉጥ መኝታ ቤቴ ውስጥ ምን ይሰራል?» ስላቸው ግራ በመጋባት ተያዩ።

«የራስዎ ሽጉጥ ነዋ ሆ!» አለ ጎንጥ ለማይረባ ምክንያት ሮጦ በመምጣቱ እየተናደደ።

«እኮ ሽጉጥ ምን ያደርግልኛል?»

«እሱን እኔ በምን አውቃለሁ?» ብሎ አየሩን እየቀዘፈ በትክክል የማልሰማውን ነገር እያጉተመተመ ወጣ። ተናኜ ያሳዘንኳት መሰለች ወይም እኔ መሰለኝ ቆማ በግራ መጋባት ስታየኝ ቆይታ።

«እንግዲህ ጠላት ቢኖሮትም አይደል ሊገድሎት የሞከረው? ራሶትን ሊጠብቁበት ይሆናላ ያስቀመጡት።» አለች የተከፈተውን መሳቢያ መልሳ እየዘጋች።

«ገላዬን ታጥቤ የምለብሰው ንፁህ ልብስ አውጪልኝ በናትሽ።» አልኳት ለጊዜው እዛ ቁምሳጥን ውስጥ ያለ ተጨማሪ አስደንጋጭ ነገር ለመጋፈጥ በቂ አቅም አልነበረኝም።

ገላዬን እየታጠብኩ ጀርባዬን ለማሸት ስንጠራራ በመስታወቱ ውስጥ ጀርባዬን አይቼው

«በስመአብ !» ብዬ ጮህኩ። ሰካራም የሳለው ስዕል ይመስላል ጀርባዬ! ከማጅራቴ ጀምሮ የቂጤን ኳሶች ጭምር በንቅሳት የተዥጎረጎረ ነው። የንቅሳቱ ዓይነት አበዛዝ የሰው ጀርባ ሳይሆን ለህፃን ልጅ በምስል ማስተማሪያ ደብተር ነው የሚመስለው።  የልብ ምስል፣ አንበሳ፣ ፈረስ የሚጋልብ ሰው ወይ መልዓክ ያለየለት ነገር  በትልቁ የተፃፈ «ኪዳን» የሚል ፅሁፍ ፣ በደንብ የማይታዩኝ ብዙ ጥቃቅን ምስሎች  .......
በመስታወቱ ጀርባዬን ሙሉ በሙሉ ላየው ስታገል የሆነ ማስታወስ ይሁን ያልገባኝ የሳሩ መስክ ዓይነት ስሜት ሽው አለብኝ። የሆነ የተቆራረጠ ትርጉም የለሽ ምስል። ጨለምለም ያለ ክፍል ውስጥ የሚነድ ሊያልቅ የደረሰ ሻማ ፣ ስኒከር ጫማ የተጫማ አንድ የሰው እግር እና የመጠጥ ሽታ ከ30 ደቂቃ በላይ መስታወቱ ላይ ባፈጥም የተለየ ትዝ የሚለኝ ነገር የለም። ምን ዓይነት ህይወት የኖርኩ ሰው ብሆን ነው ቂጤን ንቀሱኝ ብዬ ገልቤ የሰጠሁት? ቤተሰብ አልነበረኝ ይሆን? በመሃል ደግሞ ሌላ ሀሳብ ይጠልፈኛል:: ቋንቋ የሚሞሪ አካል አይደለም ? ጭንቅላቴ ገደል ማሚቶ የሚያስተጋባበት ወና ሆኖ እንዴት አማርኛ ማውራት ቻልኩ? አነበብኩኮኣ? እንዴት ማንበብ አልጠፋኝም?

«ፖሊሶቹ መጥተዋል።» አለችኝ ተናኜ እዛው እንዳፈጠጥኩ። የምሰጠው ቃል ባይኖረኝም ቃሌን ሊቀበሉ መሆኑ ነው። ለባብሼ ወደሳሎን መጣሁ። ከእኔ ያገኙት መረጃ ባይኖርም ሲጠይቁኝ ቆይተው ቦርሳ እና ስልኬን ሰጥተውኝ ሄዱ። ስልኩን ከማገላበጥ ውጪ የማደርገው ግራ ገብቶኝ ቀና ስል ተናኜ እያየችኝ ነው። አፈርኩኝ መሰለኝ እሱን ቁጭ አድርጌ ቦርሳውን መበርበር ጀመርኩ። መታወቂያ ፣ መንጃ ፈቃድ እና የብር ኖቶች ያሉበት ትንሽዬ ቦርሳ ውስጡ አለ። ምንም ፍንጭ የለውም። የሆነች ተጨማድዳ የተቀመጠች ትንሽዬ ወረቀት አገኘሁ። አገላብጬ ሳነብ  የሽያጭ ሪሲት መሆኑን ተረዳሁ። ጂም ውሃ የገዛሁበት ነው።  ቁስል እንዳለኝ ሁሉ ዘንግቼ መዥረጥ ብዬ ወጣሁና

«እስፖርት የምሰራበት ጂም የት እንደሆነ ታውቃለህ?» አልኩት ጎንጤን
«እ!» አለ አዎ እንደማለት ነገር። እንዲያሳየኝ ጠይቄው ታክሲ ጠርቶ አብሮኝ ሄደ::

ገብቼ ምን እንደምል እንኳን አላውቅም! 'እስኪ ካወቃችሁኝ ራሴን አፋልጉኝ ማን ነበርኩ ?' ነው የምላቸው? በሩን አልፌ እንደገባሁ ቆምኩ። ከፊትለፊቴ እስፖርት እየሰራ ያለ ሰውነቱ የተነፋፋ ወጣት ነገር በሆነ ነገር ፈላጊ አይን አፍጥጦ እያየኝ ያዝኩት። የሚያውቀኝ ሰው ቢሆን ነው ብዬ የሆነ ነገር እስኪለኝ አትኩሬ ማየት ቀጠልኩ። የለበስኩትን ፒጃማ ቅንድቡን ሰቅሎ ከገረመመ በኋላ

«ምን ታፈጫለሽ?» አባባሉ። ቢያውቀኝም በወዳጅነት የሚያውቀኝ ሰው እንዳልሆነ ያሳብቃል። ምንም ሳላስብ ወዳለበት እየተጠጋሁ።

«ይቅርታ እና ታውቀኛለህ ማለት ነው?» ስለው እየጎፈላ ከማሽኑ ላይ ወርዶ ደረቱን እየነፋፋ
«ኸረ ተይ ሴት ነሽ ብዬ ነው የታገስኩሽ ግን?» ከማለቱ የሆነኛው ከሌላ አቅጣጫ እየሮጠ መጥቶ

«እኔ ብጥብጥ አልፈልግም ሜላት አርፌ ስራዬን ልስራበት!» አለ በልመና ዓይነት። መናገርም መራመድም የጠፋውን ሚሞሪዬን ተከተሉት መሰለኝ እንደተገተርኩ ቀረሁ።

       ..................... ይቀጥላል ..........................

@wegoch
@wegoch
@paappii
#አይኖች_ይሰማሉ_እጆች_ያወራሉ
የሥዕል አውደ ርዕይ
በ ሠዓሊ ኖህ አበበ

ረቡዕ , ጥቅምት 2 2015
ከምሽቱ 12:00 ሰዓት

እስከ ጥቅምት 21,2015 አ.ም ይቆያል።
@seiloch
የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሶስት)
(ሜሪ ፈለቀ)

«ኸረ እኔ ብጥብጥ ፈልጌ አይደለም የመጣሁት ! እባካችሁ? አደጋ ደርሶብኝ ሚሞሪዬ በሙሉ ጠፍቷል። የማስታውሰው ነገር የለም! ካወቃችሁኝ ማን እንደነበርኩ እንድትነግሩኝ ልጠይቃችሁ ነው!» ያልኩት ምን ማለት ነው? አላውቅም! 'ማነኝ?' ብሎ መጠየቅ ምን የሚሉት የነፈዝ ጥያቄ ነው? 'ሜላት ነሽ!' ነዋ ሊሉኝ የሚችሉት አይደል? ስም ግን ማንነትን እንዴት ይገልፃል? እንዴት ነው ሰው 'ማንነህ?' ሲሉት 'እገሌ ነኝ 'የሚለው? ስሜንስ አስታውሼው ነው? ወይስ ዶክተሩ ስለነገረኝ ነው ያወቅኩት?

«ሙድ ትይዣለሽ እንዴ?  ባቡር በገጨሽ! እሱማ ፀሎቴ ነበር! ይህቺ ደግሞ የሰሞኑ ሙድሽ ናት? አደጋ ትላለች እንዴ በናታችሁ?» አለ የመጀመሪያው ሰውነቱ የተነፋፋው ወጣት ስነስርዓትም ርህራሄም በሌለው ሁኔታ። ያልኩትን እንዳላመነኝ ቢገባኝም ስሜቱ ግን ቅድም ከነበረው ፍርሃት ወይ ማክበር ያልገባኝ ማመንታት አሁን ወደ ንቀት ወይ ድፍረት ያልለየሁት ስሜት ተቀየረ:: ሊገላግል የመጣው ልጅ ግን እንደመረጋጋት ብሎ በጥርጣሬ አስተውሎ እያየኝ ነበር።

«በስመአብ! ምነው ይሄን ያህል? እንዲህ አይነት ነገር በራሴ ላይ አሟርታለሁ?» አልኩኝ በልመና! እንዴት እንደማሳምነናቸው ግራ እየገባኝ

«አንቺ የምርሽን ነው እንዴ?» አለ ሊገላግል የመጣው ልጅ! ባለ ንፍፊት ሰውነታሙም ከቅድሙ አሁን ግራ የተጋባ ቢመስልም ፍርጥም ብሎ

«ሰይፊኝ ካመንኩሽ!» አለ አንገቱ ላይ በጣቱ ከቀኝ ወደግራ የመቁረጥ ምልክት ሰርቶ

«ካላመንከኝ ላሳይህ » ብዬ የተመታሁበትን ቁስሌን ላሳያቸው ከላይ የለበስኩትን ልብስ ልገልጥ ስል ጎንጤ ከየት መጣ ሳልለው ዘሎ እጄን ቀጨም አደረገ እና ልገልጥ የጀመርኩትን ልብስ ወደታች እያለበሰ

«አንተ በአግባቡ ተጠየቅክ አይደል እንዴ? በወጉ አትመልስም? የምን ኩፍ ማለት ነው?» አለው ከእግሩ እስከጭንቅላቱ በንቀት እያየው።

«አንተ ደግሞ ማነኝ ነው የምትለው?» አለ ያኛውም እየተጠጋው።

«ሰውዬ ተከበር! ነገር አትፈልገኝ!»

«ምን እንዳታመጣ?»  ሁለቱም ተኮፋፍሰው ሊነካከሱ የተፋጠጡ አውሬዎች መሰሉ። ቅድም ሊገላግል የመጣው ልጅ በመሃከላቸው ገባ!

ጎንጤ እንድንሄድ በእጁ ወደበሩ እያሳየኝ በሚያስፈራ ፊት እንድቀድመው ሲጠብቀኝ ምንም ሳልል ወጣሁ። ተከትሎኝ ወጥቶ እያለፈ የነበረ ታክሲ አስቁሞ አሁንም እንድገባ በእጁ ምልክት ሰጠኝ። ምንም ቃል ሳይናገር ቁጣው ይጋረፋል። እንዲህ የሚያስፈራ ሰውዬ ሊያስተዳድረኝ ነው ላስተዳድረው የቀጠርኩት? እልህ የታጨቀበት አተነፋፈስ ቁና ቁና እየተነፈሰ ፈርቼው ምንም ሳልናገር እቤት ደረስን። ድንገት በመጣልኝ ሃሳብ

«መቼም ጎረቤቶቼ ያውቁኛል አይደል? » ብዬ ወደ ቀኝ ወዳሉ ጎረቤቶቼ በር ላመራ እግሬን ከመዘርጋቴ ወደቤት መሄዱን ሳይገታ እየተራመደ ዞርም ብሎ ሳያየኝ

«እእ (ጭንቅላቱን በተቃውሞ እየናጠ) እኔ እርሶን ብሆን አልሞክረውም!» ሲለኝ ቆምኩ።

«እህእ? ቆይ ሰላም የሆንኩት አንድ ሰው የለም?» አልኩኝ ለራሴ ይሁን ለእርሱ

«እሱን አላውቅም!»

«እሺ እነሱስ?» አልኩት በግራ በኩል ወዳለው በር እየጠቆምኩ።

«ህእ!(ፌዝ ባለበት ሽራፊ ፈገግታ) እሱኛውም ጥሩ ሃሳብ አልመሰለኝም!» እያለ በሩን ከፍቶ ክፍቱን ለእኔ ትቶት ወደጊቢ ገባ። ተከትዬው እየገባሁ።

«ይሄን ያህል ምን ዓይነት ሰው ብሆን ነው ከሰው ሁሉ ጋር የምናከስ የነበረው? መቼም ከዚህ ሁሉ ሰው ጋር ፀብ ከሆንኩ ችግሩ ሰውጋ ሳይሆን እኔጋ ነው የሚሆነው! ይሄን ያህል ክፉ ሰው ነበርኩ?» አልኩት

«እኔ አልወጣኝም!» ብሎ በሩ አጠገብ ያለ የእንጨት ወንበር ላይ ተቀምጦ እኔን ላለማየት በሚመስል አጥር አጥሩን ማየት ጀመረ።

«በአፍህ ባትልም ሁኔታህ ያስታውቃል። እሺ የሌላው ይቅር አንተ ምን አድርጌህ ነው እንዲህ የምትጠላኝ? ምን እንዳደረግኩ እንኳን በማላውቀው ጥፋቴ ስትቀጣኝ ግፍ አይሆንም?»

«ሆ! እኔ ክፉ ደግ አያናግሩኝ! እንዲህ ነው እንዲያ ነው አልወጣኝም! ከፈለጉ ሄደው ማንኳኳት ይችላሉ።»(ወደጎረቤት ጊቢ በእጁ እየጠቆመ)

«ከእነርሱ አንተ አትቀርብም? 1 ዓመት እዚህ ቤት ነበርክ! ንገረኝ ምን አይነት ሴት ነበርኩ? ምንድነው የምሰራው? ከማን ጋር ነው የምውለው? እንዴት አንድስ ወዳጅ የለኝም?»

«የማውቀው ነገር የለም። ምንም ነግረውኝ አያውቁም! ሆ! እኔ የምውለው እዚችሁ ደጅ እርሶ ከቤትዎ! ምን ያገናኘናል?» አለ አሁንም ወንበሩ ላይ እንደተኮፈሰ

«እኔ ባልነግርህም ወይ ያየኸው ወይ የሰማኸው ግን ይኖራል?»

«ወሬ ለቃቅሜ የማቀብል ባለጌ አይደለሁም። ያላየሁትን አላወራም!» አለኝ ድርቅ ብሎ

«እኮ ያየኸውን ንገረኝ! ቢያንስ ላንተ ምን ዓይነት ሰው እንደነበርኩ ንገረኝ?»

«ሆ!» ከማለት ውጪ አልመለሰልኝም! ተስፋ ቆረጥኩ። በተወሰነ መልኩ ድርቅናው አናደደኝም! ቅድም በዛ ንፍፊታም ሰውዬ ፊት ለእኔ እንደሚያስብ ዓይነት ሰው ሲሆን አልነበረ? ስራው ቤቴን መጠበቅ እንጂ እኔን መጠበቅ ነው? እየጠላኝ ግን ደግሞ ሊጠብቀኝ መሞከር አይጋጭም? ወደቤት ገብቼ የህመም ማስታገሻ ከዋጥኩ በኋላ ተኛሁ!!

«እራት አይበሉም?» ብላ ተናኜ ስትቀሰቅሰኝ ብዙ እንደተኛው ያወቅኩት። ማታ አራት ሰዓት ሆኗል። እራቴን ከበላሁ በኋላ ለመተኛት ብሞክርም አቃተኝ። ምሽቱን ፈራሁት። አይኔን መጨፈን ፈራሁ። ጨለማውን ፈራሁት። ፀጥታውን ፈራሁት። የተኛሁበትን መኝታ ቤት ፈራሁት:: የሆነ ሰው ተደብቆ እያየኝ ሁሉ መሰለኝ:: ከአልጋዬ እንኳን ተነስቼ መንቀሳቀስ ፈራሁ። 'አምላኬ ሆይ እባክህ ለሊቱን ቶሎ አንጋው' ብዬ የጅል ፀሎት ፀለይኩ:: መብራቱ እንደበራ እኔም ከአንዱ ጎን ወደሌላው እንደተገላበጥኩ ነጋ። ብርሃኑ ከክፉ ይጠብቀኝ ይመስል ብርሃን ወገግ ሲል ፍርሃቴ እየረገበ አይኔ ተከደነ። ስነቃ የመጣው ይምጣ ብዬ በሩን ከፍቼ የሚቀጥለውን ቤት በር አንኳኳሁ። የሆነ የዋህ የሚመስል ፊት ያለው አጠር ያለ ቀይ ሰው በሩን ከፈተ።

«ደህና አረፈድክ?» ከማለቴ የዋህ ፊቱ ደም መሰለ። በሩ ላይ ስላየኝ የደነገጠም የተናደደም መሰለኝ።

«ደሞ ምን ፈልገሽ ነው? እንዴ? አንቺ ትዳር የለሽም እና የሰው ትዳር ሰላም መሆን አይችልም?» ሲለኝ ህመም ተሰማኝ። ቁስሌንም ልቤንም ራሴንም አንድ ላይ ያመመኝ ነገር መሰለኝ። ዝም ብዬ ቆምኩ። አካሌ ቆመ እንጂ ውስጤ የሆነ ነገር ፈርሷል። የሆነ ራቁትነት ስሜት ተሰማኝ። በትክክል የማልገልፀው ስሜት ግን እርቃኔን በብዙ ሰዎች ፊት ቆሜ ሀፍረቴን ለመሸፈን ስቃዬን እየበላሁ ያለሁ  ዓይነት ስሜት ......... የተዋረድኩ ግን ውርደቴ ለሌሎች ጌጥ የሆነ የተሸነፍኩ ግን በመሸነፌ የሚደሰት እንጂ የሚያዝንልኝ የሌለ.......... እንክትክት ብዬ የወደቅኩ ግን ሊያነሳኝ እጁን የሚዘረጋ ሳይሁን የወደቅኩበት ሁሉም እያየኝ የሚያልፍ .......

«ድንቄም ሰላም ትዳር! (የጎንጤን ድምጽ ከትከሻዬ ላይ ሰማሁት) ከነገሩ የእግዜር ሰላምታ አይቀድምም?»

ሰውየው በሩን በሃይል አጋጭቶ ዘግቶት በጣም እየጮኸ «ኤደን? አንቺ ኤደን? » እየተጣራ ከበሩ ራቀ። ስድብ የቀላቀለው በጩኸት የታጀበ ንግግር ይሰማኛል።
«አልነገረኝም እንዳይሉ ተናግሬያለሁ!» ብሎ ጎንጤ ጥሎኝ እንደትናንቱ በሩን ክፍት ትቶት ወደውስጥ ገባ። የእንፉቅቅ እርምጃ እየተራመድኩ ወደጊቢ ገባሁ። ትኩስ እንባ ጉንጬን እያራሰ ያጥበኝ ጀመር። አምላክ ግን እንዴት ባሳዝነው ነው እንዲህ የሚቀጣኝ? ልብ ይበርደዋል? እንዲህ ያለ ነገር አለ ይሆን? ልቤን በረደኝ። ያለፈውን ራሴን ማወቅ የመፈለጌን ያህል በዛው መጠን ላውቀው የምችለውን ትናንቴን ፈራሁት። እግሩ ስር ፈራርሼ በሽንፈቴ ነው ልቡን ያገኘሁት ያልኩት ይሄን ቅፅበት ነው።

«እሺ በድዬህ የነበረውን ማረኝ? ይቅርታ አድርግልኝ? የማውቀውም፣ እርዳኝ የምለውም፣ የምሄድበትም ማንም የሌለኝ ሆኜ፣ ያጋጠመኝ ሁሉ ሲያላግጥብኝ አላሳዝንህም? እንዲህ ውሉ ጠፍቶኝ ስደናበር ምንስ ክፉ የነበርኩ ቢሆን ትንሽ ልብህ አይራራም? እባክህ እንድታግዘኝ እየለመንኩህ ነው።»  ብዬ በዛለ ጉልበቴ እግሩ ስር ተነጠፍኩ።

«ኸረ በመድሃንያለም!» ብሎ ደንግጦ ዘሎ አነሳኝ። « የምረዳዎት ነገር ካለ ምን ገዶኝ! ሆ! ሀጢያት ሊያስገቡኝ?» አለ ወደ ሰማይ መልከት አድርጎ እስከዛ ሰዓት ባላየሁበት እርግብ ያለ ድምፅ ..... እየተጎተትኩ በረንዳው ላይ ያለ ወንበር ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ። እንባዬ አልቆም አለኝ።

«ኸረ በድሃንያለም ይሁንብዎት ሀጢያት አያስቆጥሩብኝ? » አለ በተጨነቀ ድምፅ ፊቴ እየተንጎራደደ። መቆሟን እስከዛ ሰዓት ድረስ ያላስዋልኳት ተናኜ ሳጓን ወደ ውስጧ ስትስብ በሩ ላይ ቆማ የሹራቧን አንገትጌ ስባ በጥርሷ ነክሳ አብራኝ እያለቀሰች እንደሆነ አየሁ። ስንተያይ እንባዋን እየጠራረገች ወደ ውስጥ ገባች። ጎረቤቴ አሁንም እየጮኸ ነው። ማልቀሴን ገታ አድርጌ ለመስማት ስጥር

«ደንፍቶ ደንፍቶ ይተዋል።» አለኝ ጎንጤ። 'ማን ላይ ነው የሚደነፋው?' ብዬ መጠየቅ አሰብኩ እና ስለደከመኝ ይሁን ባይመልስልኝስ ብዬ ይሁን አላውቅም ዝም አልኩ። ትንሽ ቆይቶ

«በገባ በወጣ ቁጥር ሚስቱን መርገጥ ነበር ስራው። በነጋ በጠባ እየደቆሳት ምን ጥሎባት እንደሁ ፍቅር አለባት መሰለኝ በየቀኑ ጎረቤት እየገባ ያስታርቃቸዋል መልሳ ስሩ ነች። ከሳምንት በኃላ መልሶ ያሻታል። ይጯጯሃሉ፣ ጎረቤት ይገለግላል። በሳምንቱ መልሰው እዛው ናቸው። እንደለመደው አንድ ማታ ሲያሻት በደም ብትነከር ልጃቸው እሪሪ ብላ ትጮሃለች፣ ጎረቤት የአጥሩን በር ይደበድባል፣ ለካንስ አጅሬው የቤቱን በር ዘግቶ ነው የሚደበድባት። እርሶ 'መሰላል አቀብለኝ!' ብለው በዚህ በኩል አድርገው (ከጎረቤት የሚያዋስነንን አጥር እያመለከተ) ዘለው ገቡ። የቤቱን በር በምን እንደሰበሩት ያየ የለም። ብቻ መስታወቱ ረግፎ ነበር።» ብሎ ዝም አለ። ሽራፊ ፈገግታው በአጋጣሚው የመኩራት ዓይነት መሆኑ ግራ አጋባኝ። ወሬውን ያጠናቀቀ ያህል ዝም ሲል

«ከዛስ?» አልኩኝ አንገቴን አስግጌ

«ህም! ከዚያማ እንዴት አድርገው ቢያሹት እንደሆነ እንጃ ለብዙ ቀናት 'እገሌ ነኝ!' ካላለ በቀር ፊቱ አይለይም ነበር! እንደመሰለኝ ከሆነ ከዱላው በላይ ሽጉጥ አውጥተው እንደሚገድሉት አስፈራርተውት ስለነበር መሰለኝ ወደፖሊስም አልሄደ ወደዚህም መልሶ ዝር አላለም። ያቺ ገልቱ ሚስትየው ናት በበነጋው መጥታ እንዴት ባሌ ላይ ሽጉጥ መዘዙ ብላ የደነፋችው! ከዛ ቀን በኋላ እንዳረጀ ውሻ ያላዝናል እንጂ እጁን አንስቶባት አያውቅም!» ብሎኝ አሁንም ሽራፊ ፈገግታውን ፈገግ ብሎ ዝም አለ።

                 .............. ይቀጥላል ...............

@wegoch
@wegoch
@paappii
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል አራት)
(ሜሪ ፈለቀ)

«እትዬ ትናንት ሲያይዎት ሙታንቲው ላይ ቅዘኑን የሚለቅ ሽንታም ሁላ ዛሬ ዝቅ ብለው ይቅርታ ቢጠይቁት ለምህረት እቅፉን ከሚዘረጋልዎ ይልቅ በቀል የሚፈትል ይበዛል። የተዋረደ የመሰለውን ጊዜያት እርሶን በማዋረድ ሊያካክስ ይጥራል። ግድ የሎትም ይቅርታ መጠየቁ ይቆይዎት።» የሚለኝ 'ለምን ጎረቤቶቼን ይቅርታ አልጠይቃቸውም?' ብዬው ነው።

እቤቱ ገብቼ ከደበደብኩት ጎረቤቴ በተቃራኒ ካሉት ጎረቤቶቼ ጋር የፀብ መነሾዬ ምን እንደነበር ጎንጤም አያውቅም። ድንገት በር ላይ ከተገጣጠምን ግን በእርሱ ቃላት ፀያፍ ስድቦች እንለዋወጣለን።
'እስኪ ንገረኝ እንዴት ያለ ስድብ ነው የሰደብኳቸው?' ስለው። እያንገሸገሸው
'እትዬ ሲናገሩስ አፍዎ አለፍ ይላል! እኔ አልደግመውም' ነው ያለኝ። እሱን ምን አድርጌው እንደጠላኝ ስጠይቀው
' በይቅርታ አለፍነውም አይደል? ከይቅርታ በፊት እንጂ ከይቅርታ በኃላ የበደል ዝርዝር አይቀርብም።' ብሎኝ ነው ያለፈው።

«አንተ ይቅርታ አድርገህልኝ አይደል? ተናኜ ይቅርታ አድርጋልኝ አይደል? ወይስ አላደረግክልኝም? ልትበቀለኝ መች አሰብክ? ወይስ ታስባለህ?»

«ኸረ መድሃንያለም ይቅር ይበሎት! እኔ የመሰለኝን ነው የነገርክዎት። አይ አሻፈረኝ ካሉ ይሞክሩት። ኋላ የሚከተለው ምንም ቢሆን የመቋቋም አቅሙ አለኝ ካሉ ....... » ብሎ ትከሻውን በምንቸገረኝ ሰበከ። የሚያወራው ከልምድ ይመስላል፣ ከሚያውቀው ካለፈበት ልምድ፣

«ይቅርታ በመጠየቄ ከእነርሱ ይልቅ ራሴን ነፃ የማወጣው እኔ አይደለሁ? የሚሰማንን መጥፎ ስሜት ለይቅርታ ባጎነበስኩበት አራግፌ የምነሳው ራሴም አይደለሁ?»

«ከተነሱ ነዋ! ለይቅርታ ባጎነበሱበት የሚረግጥዎ ካጋጠሞትስ? በመድሃንያለም ዘንድ ይቅርታ መጠያየቅ ወደ ፍቅር መሸጋገሪያ ድልድይ ነው። ያ ግን የይቅርታ ትርጉም ለሚገባው ሰው ነው። የኛ ሰው ይቅርታ ጠያቂ የተዋረደ፣ ይቅርታ ተጠያቂ ክብር የተጎናፀፈ አድርጎ ነው ይቅርታን የሚፈታው። የኛ ሰው ለብቻው በጓዳ እግሩ ስር ወድቀው ይቅርታ ቢጠይቁት እንደማይረካ አያውቁም? ሰው በተሰበሰበበት ስህተትዎትን ማመንዎ አይደለም ይቅርታዎን ትልቅ የሚያደርግለት። በሰዎች ፊት ለእግሩ ስር መዋልዎ እንጂ ምክንያቱም በሰዎች ፊት የእሱን ልክነት እና ፅድቅ አወጁለታ። በሰዎች ፊት የእርሶን ከእርሱ እግር ስር ዝቅ ማለት አሳዩለታ። እንደዛም ሆኖ የሚረካ እንዳይመስልዎ! ከዛ ለሚቀጥለው ዘመን ሁሉ ፈቅ እንዲሉ አይፈልግም!»

አምርሮ ስለተናገረ ይሆን ስለይቅርታ ሌላ ሀሳብ መሰንዘር አልፈለግሁም። ግንስ ምን እንዳደረግኩ ሙሉውን ጥፋቴን የማላስታውሰውን በደል ይቅርታ አድርጉልኝ ማለት ልክ ነው? ከይቅርታው በፊት ሀጥያቱ ይቀድማል። እኔ ደግሞ እሱን አላስታውሰውም። ብቻ ምንም ይሆንና ብቻዬን አልሁን! ብቻ እግራቸው ስር መውደቄ ያደረግኳቸውን ነገር አስረስቶ ባይወዱኝ እንኳን ጥላቻቸውን እንዲተው ካደረገልኝ ምን አለበት? ልቤን ከሚበርደው የማወራው ሰው አጊንቼ ክብሬ ቢቀል አይሻለኝም? ክብር ያለሰው ምንድነው? ኸረ ከሰው ጋር የማይጋሩት ህይወት ምንስ በድሎት የተንቆጠቆጠ ቢሆን ትርጉም አለው?

ከዚህ በኋላ በሚቀጥሉት ቀናት ራሴን ፍለጋ ቤቴን መበርበሬም ሆነ ተናኜን እና ጎንጤን በጥያቄ ማስጨነቄ ትናንቴን ይበልጡን እንድፈራው እና እንድጠላው አደረገኝ። እያንዳንዱን ፍንጭ ሰካክቼ መረጃ ለማግኘት በቅደም ተከተል ሄድኩ። መክፈቻ ኮዱን የማላስታውሰው ዝግ ካዝና፣ 1.2 ሚሊየን ብር ተቀማጭ ያለበት የባንክ ደብተር፣ አብዛኛዎቹ ቀዳዳ የሚበዛባቸው ሰፋፊ ጅንስ ሱሪዎች ፣ ሰንሰለት እና ብልጭልጭ የሚበዛባቸው ጃኬቶች እና ኮቶች፣ የወንድ የሚመስሉ ጫማዎች፣ አልጋዬ ራስጌ ያለው ፎቶ ላይ ያለው ልጅ ሌሎች ፎቶዎች ፣ ሽጉጥ፣ ስልክ ፣ በንቅሳት የተዥጎረጎረ ጀርባ እና ቂጥ ያለው ሰውነቴ ፣ በአጭሩ የተቆረጠ ጥቁር ፀጉሬ ....
 
1. ኮዱን ያላስታወስኩት ካዝና

የተከረቸመ ነገር መቼም ሚስጥር ነው። ይሄ ዝግ ብረት የእንቆቅልሼ ሁሉ መፍቻ መሰሎኝ ነበር። ጎንጤን ካዝናውን የሚሰብርልኝ ባለሙያ እንዲያመጣልኝ አድርጌ ተሰበረ። ውስጡ ያገኘኋቸው ነገሮች የበለጠ የሚያወዛግቡኝ እንጂ ትክክለኛ መልስ የሚሆኑ አልነበሩም። ጥሬ ገንዘብ፣ የጋብቻ ቀለበቶች ፣ የቤት ካርታ እና ውል፣ የወታደር ልብስ ቀለም ያለው የሲጋራ መለኮሻ ላይተር ናቸው። በመጀመሪያ እጄ ፈጥኖ ያነሳው ላይተሩን ነው።

«አጨስ ነበር እንዴ?» አልኩት ጎንጤን
«እኔ ሲያጨሱ አይቼ አላውቅም! እትዬ አስታወሱ እንዴ?» አለኝ በጣም ተጠግቶ አይኖቹን አቦዝዞ እያየኝ።

«ምኑን?» ካልኩት በኋላ ካላስታወስኩ ሲጋራ መለኮሻ መሆኑን በምን አወቅኩ? ብዬ ግራ ተጋባሁ። አገላብጬ እያየሁት አስባለሁ። የቁሶቹ ምስል ጭንቅላቴ ውስጥ አይከሰትልኝም። ልክ በዓይኔ ሳያቸው ግን ምን እንደሆኑ አውቃለሁ። ለምሳሌ ሆስፒታል ከነቃሁ በኋላ እንጀራ ለመጀመሪያ ጌዜ ሲያቀርቡልኝ ሳልጠይቅ ጠቅልዬ እንደጎረስኩት። ሾርባ ከማንኪያው ጋር ሲያቀርቡልኝ በማንኪያው ተጨልፎ እንደሚበላ ማንም እንዳላስተማረኝ፣! ይሄ እብደት ነው ወይስ ትርጉም ይሰጣል? ስለሆነ ነገር ያለን እውቀት የትውስታ አንዱ አካል አይደለም? በአይኔ ቀለበቶቹ ላይ አፍጥጫለሁ እጄ ግን የሲጋራ መለኮሻውን ማስቀመጥ አቃተው። ግማሽ ትውስታ ብሎ ነገር አለ ይሁን? ላይተሩን የሆነ ሰው እጅ ላይ የማውቀው ይመስለኛል። በደም ተጨማልቆ በከፊል የተዘረጋ እጅ መዳፍ ላይ! አይኔን ከድኜ እከፍታለሁ............. እጅ ብቻ! ላይተሩን አስቀምጬ ቀለበቶቹን አነሳኋቸው። አነስ ያለውን ጣቴ ውስጥ አስገባሁት።

«አግብቼ ነበር?» ያልኩት መልስ ባልጠበቀ አጠያየቅ ነው። ሁለቱም ዝም ሲሉ ግን የሚያውቁት ነገር እንዳለ ተሰማኝ። «አግብቼ ነበር?» ብዬ አስረግጬ ጠየቅኩ። ተናኜ ተንተባተበች።

«እኔ እዚህ ቤት በነበርኩበት ጊዜ ብቻዎትን ነበሩ!» አለ ጎንጤ ፍርጥም ብሎ እና ተናኜን በቁጣ ዓይን እያጉረጠረጠባት።
«ከዛ በፊትስ?»
«እኔ የማውቀው የለኝም!» አለ አሁንም ፍርጥም ብሎ። የሚያውቀው እንዳለ ግን ያሳብቅበታል።

የራሴ ካልሆነ የሰው ቀለበት ካዝና ውስጥ ላስቀምጥ የምችልበት ምን ምክንያት ይኖራል? ከቤቱ ካርታ ጋር ያሉትን ወረቀቶች በሙሉ ለመረዳት ሞከርኩ። ብዙው ግራ አጋባኝ። ካርታውም ውሉም ሁለት የተለያየ ነው። ያ ማለት ከዚህ ቤት በተጨማሪ ሌላ ቤት በስሜ አለ። የንግድ ቤት የሚል። ውሉ ላይ ብዙ ያልገባኝ ጥልቅ ነገር አለ። በግርድፉ ከገባኝ ግን አቶ ሙሉ ሰው መሆን አንድአርጌ ከሚባል ሰው ነው ንብረቱ በእኔ ስም በውርስ የዞረው። ውሉ የተፈረመበት ቀን 08-11-2004 ፣ የሰውየው እድሜ 40 ይላል።

«አቶ ሙሉሰው መሆን የሚባል ስም ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?» አልኳቸው

«በፍፁም!» አለች ተናኜ። የጎንጤ ዝምታ ግን ሰምቶ እንደሚያውቅ ነገረኝ።
«ምኔ ነበር?» አልኩት

«እትዬ እኔ በወሬ ብቻ የሰማሁትን ነገር እንዲህ ነው እንዲያ ነው ብዬ እንድነግርዎት አያስገድዱኝ። ምናልባትም ሀቁ ከዛ የራቀ ሊሆን ይችላል። እንኳን ዓመታት ያለፈው ወሬ ቀርቶ የትናንት ወሬ እንኳን ከአንዱ አፍ ወደሌላው ስታልፍ ተቀባብታ ወፍራ ነው። » አለ በልምምጥ። ምንም ይሁን ምን ወሬው ለመንገር እንደጎረቤቶቼ ፀብ ቀላል ያለመሆኑ ገባኝ።

«ምንም ይሁን የሰማኸውን ንገረኝ እና ማጣራቱን ራሴው ላጣራ! ምንድነው ወሬው»
«እትዬ አምላክ እንደአዲስ በንፁህ ልብ የመኖር እድል ሲሰጥዎ እርሱ አዋቂ አይደል? እንደው ያለፈውን ከመበርበር እንደአዲስ......... »

«ንገረኝ ምንድነው? ንገረኝ አልኩህኮ!» ብዬ ጮህኩ

«ባለቤትዎ እንደነበሩ ሲወራ ሰምቻለሁ።» ብሎ ዝም አለ
«ይሄን ሁሉ የታሸኸው ይሄን ልትነግረኝ አይደለም! ከዛስ? ምን ሆነ?»

«ሞተው ነው (እንደበረዶ የቀዘቀዙ ቃላት ) እንደሚባለው ከሆነ እርሶ በሞታቸው እጅዎ አለበት ተብሎ ታስረው ነበር።»

«ለንብረት ብለው የገደሏቸው ነው የሚባለውማ ከወሬው» አለች ተናኜ ለማውራት ሰበብ ትፈልግ ይመስል። ጎንጤ ሲያፈጥባት «እህእ ንገሩኝ ብለው አይደል?» ብላ አፈጠጠች። ያቺን ሜላት እኔ ራሴ ጠላኋት። እኔ ራሴ ባገኛት አልገላትም ነበር?

«እትዬ እውነታውን የሚያውቀውኮ አንድ ፈጣሪ ብቻ ነው።» አለኝ ሊያፅናናኝ ይሁን ከልቡ አልገባኝም። ፖሊሶቹ እየደጋገሙ ሊገድለኝ የሚችል የምጠረጥረው ጠላት እንዳለኝ የማስታውስ ከሆነ ብለው ሲያደርቁኝ ይሄን ክፍል ለእኔ መንገር አልታያቸውም? የአደጋው መንስኤ ከዚህኛው ጋር የተያያዘ ነገር ይኖረው እንደው ማሰብ ተስኗቸው ነው? ወይስ አያውቁም? ወይስ እውነትም ወሬ ነው? ምኑ ነው ልክ ? ምኑ ነው ቅዠት?

እንደእብድ መዥረጥ ብዬ ተነስቼ ፖሊሶቹ የማስታውሰው ፍንጭ ካገኘሁ እንድመጣ የነገሩኝ ቢሮ ጎንጤን አስከትዬ ሄድኩ። ገና ኮሪደሩን አልፌ እየሄድኩ እኔ የማላውቀው እሱ ግን በትክክል እንደሚያውቀኝ የሚያስታውቅ ፖሊስ

«እሺ አጅሪት?» አለኝ። አጅሪት አባባሉ ስልችት ያለበት፣ ትዝብት ያለበት ፣ ፍርድ ያለበት አይነት ነው።

                         ................  ይቀጥላል .............

@wegoch
@wegoch
@paappii
#የመኖር አጋማሽ ..የመሞት ሲሶ ... መሃል መንገድ ላይ ..... (ክፍል አምስት)
(ሜሪ ፈለቀ)

ማነኝ?
ለመርማሪ ፖሊሱ 'ነፍሰ ገዳይ' ነኝ:: እገሌ ዶክተር ነው: ኢንጅነር ነው... ምናምን እንደሚባለው... 'እ ... ሜላት? እሷኮ ነፍሰ ገዳይ ናት!' የሚል ማዕረግ ያለኝ ነኝ:: .. ድርጊት ወይም ድርጊቶች ናቸው ማንነቶቻችን?? እንደዛስ እንኳን ቢሆን እኔ የትኛዋን ነኝ?? እንደተናኜ አባባል 'አር ከማር የምትለየዋን' የአሁኗን ሜላት ወይስ ነፍሰገዳይዋን ሜላት?

"እትዬ በሰዓቱ የሆነውን ያደረጉበትን ምክኝያት: የነበሩበትን ሁናቴ እና ሌሎች አጃቢ ግብሮች ማወቅ ባልቻሉበት ሁኔታ ድርጊቱ ብቻውን የተሟላ መረጃ አይደምኮ!!" ዝም ስለው አሁንም ይቀጥላል!

ከፖሊስ ጣቢያው ከተመለስኩ ጀምሮ ለሰዓታት የማውቃቸውን ቃላት እዛ መርማሪ ፖሊስ ጠረዼዛ ላይ አስቀምጬው እንደመጣሁ ሁላ ዲዳ ሆንኩ:: ሳሎን ሶፋው ላይ እንደተጋደምኩ  ተናኜ የሚለበስ አምጥታ ደረበችልኝ:: ጎንጤ ለእኔ ይሁን ለራሱ እንጃ ብቻ ነፍሰ ገዳይነቴን ማለዘቢያ ሰበብ ያስረዳኛል::

የሚለው ነገር እኮ እውነት ነው ለምሳሌ 'ሜላት ባሏን ገደለች' ከሚለው በምንም አጃቢ ምክንያት ካልታሸ ዓረፍተ ነገር:: 'ሜላት ባሏ ሊገድላት ሲል ሽጉጡን ቀምታ ገደለችው' ቢባል ራሱ ነፍሰ ገዳይነት ግን ራሷን ለመከላከል የገደለች ትንሽ የሚታዘንላት ነፍሰ ገዳይ ያደርገኛል:: ወይም 'ሜላት እህቷን ሊገድል ሽጉጥ ደግኖ የነበረውን ባሏን እህቷን ለማትረፍ ባደረገችው ትግል የባሏ ህይወት ሊያልፍ ችሏል' ያው ነፍሰ ገዳይነት ትንሽም ጀግንነት ሁሉ ይኖረዋል:: .... የእኔው አጃቢ ሁኔታኮ 'ሜላት ባሏን ገደለች' የሚለው ልዝብ ገላጩ ነው:: ... 'አጅሪት' ያለኝ መርማሪ ፖሊስ የማስታወስ ችሎታዬን ማጣቴን ከግምት አስገብቶ በማባበል ቃል መርጦ እንደነገረኝ.... እስከዛሬ በስራው እንደእኔ ዓይነት ኬዝ ገጥሞት አያውቅም!! እንደእርሱ ገለፃ ..

የሆነ ቀን ቢሮው ተቀምጦ የተለመደ ስርቆት: ድብድብ... ወንጀሎችን ሲመረምር በሩን ከፍቼ ገባሁ:: ሁለት የሰው ቆለጥ ጠረዼዛው ላይ ዱብ ሲል ነው የገባው ሰው ባልደረባው አለመሆኑን ያወቀው... በደም የተለወሰ እጄን ልብሴ ላይ እየጠራገግሁ

" ፍሬውን ማስረጃ እንዲሆንህ ነው ያመጣሁልህ! ዋናውን ከፈለግከው አጉርሼዋለሁ:: " አልኩት:: ሬሳው ያልኳቸው ቦታ እንዳልኩትም ዋናውን ጎርሶ አገኙት:: የወንድነት ንብረቱ ከፊሉ መርማሪው ጠረዼዛ ላይ ... ከፊሉ አፉ ውስጥ ከመዝረክረኩ ውጪ በጥይት ነው የተገደለው.... ምክንያቴን እንዳስረዳ ስጠየቅ 'እንዴት እንደምገድለው ለረዥም ጊዜ ሳስብ ቆይቼ ተሳካልኝ::... ለዝህችው አቅሙ ይሄ የማይረባ.. ስንት እንዳስለፋኝ::" ብቻ ነው ያልኩት... በድርጊቴ ከልኩ በላይ መርካቴ ሲደመር ሟች ለመሬት ለሰማይ የከበደ በህዝብ ዘንድ የተወደደ ባለስልጣን መሆኑ ፍርዱን የእድሜ ልክ እስራት አስፈረደብኝ::

እኔ ይሄ ነፍሰ ገዳይነት በምን ምክንያት ቢቀመም: በምን ነባራዊ ሁኔታ ቢሰነግ ነው የሚለዝበው??

ገዳይነት ብቻ አይደለም እንደሁኔታው ሊገዝፍ እና ሊቀል የሚችለው?? የሟች ነፍስም ሊገዝፍ እና ሊቀል ይችላል... እንትን አውራጃ በነበረ የእርስ በእርስ ግጭት 200 ሰው ሞተ ከሚል ዜና እና እገሌ የሚባለው እውቁ ፖለቲከኛ ተገደለ! ከሚል ዜና ሲነፃፀር ከ200 ነፍስ የአንዱ ታዋቂ ነፍስ ይገዝፋል:: ... ያው ሞት ሚዛን ይሰፈርለታል:: ....

"እኔ ምን አውቃለሁ የሳብሽውን ገመድ!! " ብሎኝ ነበር መርማሪው የእድሜ ልክ ከተፈረደብኝ እንዴት ልወጣ እንደቻልኩ ስጠይቀው::

ሰውዬው ስለነገረኝ ይሆን አስታውሼ አላውቅም:: አይኔን ለመጨፈን ስሞክር የሚታየኝ ጠረዼዛ ላይ የሚንከባለል ቆለጥ ነው::....  የምግብ ጣዕም ሁሉ ደም ደም አለኝ:: .... ከዚህ በኃላ ስላለፈው ለማወቅ መቆፈሬን ማቆም ይኑርብኝ መቀጠል ግራ ገባኝ::... ፍርሃት ብቻ ነው የሚንጠኝ:: ጎንጤ አርጅቶ ሽፋኑ የተልፈሰፈሰ መፅሃፍ ቅዱስ አምጥቶ ከተኛሁበት ራስጌ እያስቀመጠ

"ባታነቢው እንኳን ከራስጌሽ ይኑር :: ከበረታሽ ግን አንብቢው ያበረታሻል:: " ብሎኝ ብሎኝ ሲወጣ መፅሃፍ ቅዱሱን አንስቼ አገላበጥኩት:: በእርግጠኝነት የማልገልፀው የእሩቅነት ... የባይተዋርነት ስሜት ተሰማኝ:: ከመንፈሳዊነት የራቀ ህይወት እንደነበረኝ ለመረዳት ምንም ቀመር የሚያስፈልገው ሆኖ አይደለም:: እንደው ግን ቢያንስ በልጅነቴ... አንዱ የህይወቴ ቀን ላይ እንኳን ከእግዚአብሄር ደጅ ተገኝቼ አውቅ ይሆን??

"ተናኜ? ተናኜ? (በሩ ላይ ተለጥፋ እስክጠራት እየጠበቀች ይሁን ዘላ ገባች) ቤተክርስቲያን የሚለበስ ልብስ አውጪልኝ እስኪ... ይዘሽኝ ትሄጃለሽ" አልኳት... ሄዳ የሆነ የራሷን ሰፊ ጉርድ ይዛ ተመለሰች

"ይሄ ከበቃዎት ይሞክሩት እንጂ እትይ እርሶ ቀሚስ የሚመስል ነገርኮ የሎትም" አለች... ጎንጤ ብድግ ብሎ ሲከተን

"አንተ እዚሁ ሁን ችግር የለውም!" ብዬው ነበር:: አልሰማኝም!

"የማይሆነውን! በመንገድ ምን ሊገጥሞት እንደሚች ምን አውቃለሁ? አንዱ የጠገበ ቢጋጭዎትስ? ደሞ ቤተክስኪኑ ትንሽ ያስኬዳል እንደዚያ እርቀት ለመሄድ የሚያስችል አልጠነከሩም! ታክሲ ይጠራልዎ!" ብሎ ለሶስት በታክሲ ሄድን... ቤተክርስትያን ጊቢ ውስጥ አንዱን ዛፍ ደገፍ ብዬ ተቀመጥኩ... ተናኜ ትታኝ ልትፀልይ መሰለኝ ሄደች:: ጎንጤ ትንሽ ራቅ ብሎ እጁን ደረቱ ላይ መስቀልኛ አጣምሮ ያነበንባል:: .... የመጣሁት ላዋራው ነበር:: ልፀልይ: ልለምን.... ዝም ብቻ ነበር ግን ያልኩት... ምን ብዬ ነው የምለምነው?? ብዙ ደቂቃ ፀጥ ብዬ ተቀመጥኩ...

"ልጅ ሜላት" የሚል ድምፅ ሰምቼ ዞርኩ!! ነጭ ነጠላ ራሳቸው ላይ የጠመጠሙ : በእድሜ ተለቅ ያሉ ሰው ናቸው::

"አንቺ ነሽ? " ብለው የተገረመ እና የመደሰት ቅልቅል ፈገግ እያሉ በትኩረት እያዩኝ.... " ያሰብሽው ሞላልሽ?" አሉ እየተጠጉኝ በጋቢያቸው ስር ደብቀው የያዙትን መስቀል አውጥተው እየተጠጉኝ..... ዝም ብዬ አያቸዋለሁ:: ከመፅሃፍ ቅዱሱ ይልቅ እኚህን ሰው ልቤ ያውቃቸዋል:: ብርድ ያንዘፈዘፈው ልቤ ባልገባኝ ምክንያት ሞቀው...

"ምነው ልጄ ደህናም አይደለሽ? ምነው አፍሽ ሰነፈብኝ?" አሉኝ ቀርበው ግራ በመጋባት እያዩኝ .... ጎንጤ ቀረብ ብሎ የሚሆነውን ይከታተላል:: .... ሳላስበው እንባዬ ይፈነቅለኝ ጀመር.... ለመጀመሪያ ጊዜ ከአደጋው ከነቃሁ ከወር ከአንድ ቀን በኃላ ... በስሜ ጠርቶ በፍቅር ያየኝ ሰው ገጠመኝ.... ድምፅ አውጥቼ እነፋረቅ ጀመር::

"እኔን ልጄ!! ምን ገጠመሽ? " ሲሉኝ ከተቀመጥኩበት ዘልዬ ተጠመጠምኩባቸው... ግራ እንደገባቸው ያስታውቃሉ:: አቀፉኝ..... እቅፋቸው ውስጥ ነፍሰ ገዳይ መሆኔን ረሳሁት.... ያየኝ ሁሉ ዓይን ውስጥ ያየሁትን ፍርድ እና ጥላቻ ረሳሁት... ግራ መጋባቴን ረሳሁት.... ባዶነቴን ረሳሁት .... ለደቂቃዎች ብዙ ነገሬን ረሳሁት... ሲያባብሉኝ ቆይተው .... እኔ ተቀምጬበት የነበረ ዛፍ አጠገብ ያለ ጉቶ ላይ አረፍ አሉ እንድቀመጥ እግራቸው ስር አስዩኝ:: .... ከሁኔታቸው ከዚህ በፊት አድርጌው የማውቀው ነገር እንደሆነ ገባኝ:: እግራቸው ስር ተዘርፍጬ ጉልበታቸውን ደገፍ ብዬ የተፈጠረውን ነገር ሆስፒታል ከነቃሁ ሰዓት ጀምሬ ነገርኳቸው:: ዝም ብለው ሲሰሙኝ ቆይተው ብርዳሙ ልቤን የሚያሞቅ ፈገግታ ፈገግ ብለው::
"ልጄ እኔ በዘመናት እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ፀሎት በአንድም በሌላም መንገድ ሲመልስ አይቻለሁ:: ያንቺ ግን ይለያል! (መገረማቸው ይሰማል) የዛሬ ሁለት ወር ገደማ የገብርኤል እለት ማግስት እዝህችው ቦታ እንደዝህችው ተቀምጠሽ 'ያለፈውን ሁሉ በላዺስ ማጥፋት ቢቻል እና እንደአዲስ ሀ ብዬ መኖር ብችል?' ያልሽኝ! 'በቃሉ: በንሰሃ: በጌታችን ደም እንደአዲስ ስርየትን አጊንተሽ መኖር ትችያለሽኮ!' ብልሽ .... 'አይ አባ መች እንዲህ ቀሎ!' ነበር ያልሽኝ:: ልጄ የተመኘሽውን አዲስ ህይወትኮ ነው እግዚአብሔር የሰጠሽ!! " አሉኝ ትከሻዬን ዳበስ ዳበስ እያደረጉ.... እዚህችው መኖር አይቻልም?? ቤት አልፈልግም... ፀሃይም ዝናብም... ክረምትም በጋም ለምን እዝህችው እግራቸው ስር ሆኜ አያልፍም?

የጠየቅኩትን አዲስ ህይወት እንድፅፍ ጭንቅላቴን ነጭ ወረቀት አድርጎ እንደሰጠኝ ቢነግሩኝም ስለራሴ የነገርኳቸው ነገር ካለ እንዲነግሩኝ ጠየቅኳቸው::

"መጀመሪያ ያገኘሁሽ ቀን ... እርግጠኛ ቀኑን አላስታውሰውም... ሰባት ስምንት ወር ቢሆን ነው... እዝህችው ጋር ቆመሽ በአምላክሽ ተቀይመሽ ጮክ ብለሽ እየተጣላሽው ነበር:: እያለፍኩ ገርመም ሳደርግሽ 'ምን ያፈጣሉ? በእግዚአብሄር የተናደደ ሰው አይተው አያውቁም? ' ብለሽኝ ነው ያስቆምሽኝ.... የዛን እለት ለብዙ ዓመታት ፈልገሽ አስፈልገሽ ያገኘሻት እናትሽ ስታገኛት በማይድን በሽታ ልትሞት ወራት እንደቀራት የሰማሽ ቀን ነበር:: ... ዝርዝሩን አልጠየቅኩሽም... ሲጠይቁሽም አትወጂም.... ከዛን ቀን በኃላ ቢያንስ በሳምንት ካልያም በሁለት ሳምንት አርብ አርብ ትመጫለሽ... ያሳለፍሽው ህይወት በዝርዝር ባትነግሪኝም ከባድ እንደሆነ ግልፅ ነው:: .... መጥተሽ እዚህጋ ትቀመጫለሽ... አንዳንዴ ታዋሪኛለሽ ሌላ ጊዜ በዝምታ ቆይተሽ ትሄጃለሽ.... "

"እናቴ ምን ሆነች ከዛ? የት እንደሆነች ነግሬዎታለሁ?"

"አልነገርሽኝም ልጄ! እናትሽ እኔ እስካገኘሁሽ ድረስ በህይወት ነበሩ:: ወንድም እንዳለሽ ነግረሽኛል:: ስለእናትሽ ለወንድምሽ መንገር ተጨንቀሽ ነበር:: አዝናለሁ ልጄ ከዚህ በላይ የማውቀው የለም!" አሉኝ አሁንም ትከሻዬን ዳበስ ዳበስ እያደረጉኝ.....  እናት? የት ናት? ወንድም?? ታዲያ ለምንድነው ብቻዬን የምኖረው? ለምንድነው ጎንጤም ተናኜም ፖሊሶቹም የማያውቋቸው?? እነርሱስ ቢሆን እንዴት ሊፈልጉኝ አልመጡም? ....

            ...........ይቀጥላል.......

@wegoch
@wegoch
@paappii
#የመኖር አካፋይ ፣ የመሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ስድስት)
(ሜሪ ፈለቀ)
«ልጄ ዘመንሽን ሁሉ ክፉ ያደረጉብሽን ሰዎች ለመበቀል ስትዪ ነው የኖርሽው። እንደገባኝ ከሆነ ከበቀል እና ለወንድምሽ ከመኖር ውጪ ሌላ ልምድም ህልምም ስላልነበረሽ የጎዳሽን ሰው ካጠፋሽ በኋላ አንቺ የምትኖሪለት ነገር አጥተሽ ነበር። ልጄ የበደሉሽን ይቅር በይ፣ ራስሽን ይቅር በይ! ለፍቅር በፍቅር ለመኖር ራስሽን አስለምጂ! እግዚአብሄር አዲስን እድል ሰጥቶሻል።» አሉኝ ከጉልበታቸው ላይ ሳልነሳ ብዙ ደቂቃዎች ወይም ሰዓት ካለፈኝ በኋላ
«አባ ለምንድነው ብዙ የሚያውቁት ነገር ያለ ግን ያልነገሩኝ የሚመስለኝ?»
«የማይበጅሽን ብነግርሽ ምን ሊጠቅምሽ ልጄ? ስላሴ ከጭንቅላትሽ ብን አድርጎ ያጠፋው ባይጠቅምሽ አይደል? ወይም ለጊዜው ባያስፈልግሽ? »
«አባ ያለትናንት ዛሬን መኖር ይቻላል? ትናንት የሌለበትስ ዛሬ አለ? እያንዳንዱ ከሰዎች ጋር የሚያያይዘኝ ገመድ ከትናንት ጋር የተጋመደ አይደለም? ቤተሰቦቼም እኮ ትናንቴ ውስጥ የነበሩ ናቸው። እሺ ካልነገሩኝ እናቴን ወይ ወንድሜን እንዴት አገኛቸዋለሁ?»
«የሚጠቅምሽን መረጃ አልደብቅሽም ልጄ። ስለእናትሽ ብዙም አላወራሽኝ ስለወንድምሽ ግን አውርተሽ አትጠግቢም። ስሙ በየእለቱ የምደግመው ስለለሆነ አልዘነጋሁትም። ኪዳን! አዎ ኪዳን ነው።» ጀርባዬ ላይ በትልቁ የተነቀስኩት የወንድሜን ስም ነው ማለት ነው። «ጥይምናው እና ፈገግታው ያንቺው ነው።» ሲሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጉልበታቸው ቀና አልኩ
«እንዴ አባ ያውቁታል? አብሮኝ መጥቶ ያውቅ ነበር?» አልኩኝ በጉጉት
«እንደዛ አይደለም ልጄ! በስልክሽ ነው ምስሉን ያሳየሽኝ። » ጠይም ሳቂታ .......... የአልጋዬ ኮመዲኖ ላይ ያለው ፎቶ ነው የሚሆነው
ስልኬ! ......... እንዴት እንደምከፍተው ማወቅ አቅቶኝ መሳቢያ ውስጥ ያስቀመጥኩት መስታወቱ የተሰነጣጠቀ ስልኬ! ቀና ብዬ ጎንጤን አየሁት። ከተቀመጥኩበት እየተነሳሁ
«አባ ልሂድ በቃ! ብመጣ አገኝዎታለሁ? »
«አለሁኝ ከቤቱ የት እሄዳለሁ? (ወደ ሰማይ መልከት አደረጉ) በአይንሽ ካጣሽኝ መልከፃድቅን ጥሩልኝ በይ!» የለበስኩትን እያጤኑ «ለምስጋና እንደመጣሽ አምኜ አምላኬን አመሰግናለሁ» አሉኝ። መጨረሻ ላይ የተናገሩት እንዳልገባኝ ገብቷቸው ፈገግ እያሉ። «ሁሌም ስትመጪ  ሌጣሽን ያለክንብንብ ደግሞም የክፉ ነገሮች ምስል ያለበት ልብስ ለብሰሽ ነበር። አንድ እለት ከጀርባው ትልቅ የእባብ ምስል ያለበት ጃኬት አድርገሽ 'ምነው ልጄ  ከጀርባሽ ፈልገሽው ነው?' ብልሽ። ' ከእግዚአብሄር የታረቅኩ ቀን ለምስጋና ስመጣ ቀሚስ ለብሼ ነጠላ ደርቤ እመጣለሁ።' ብለሽኝ ነበር።» አሉኝ።
እቤት የምደርስበት ሰዓት እርቆብኝ ከደረስኩ በኋላ ከስልኬ ጋር ተፋጥጫለሁ። ጭንቅላቴ ውስጥ ምስላቸው የሌሉ ነገሮችን እንኳን ስይዛቸው በደመነፍስ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አውቅ ነበር። ለምንድነው ስልኬን ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ የገባኝ?
«ባትሪ ያለው አልመሰለኝም! እንዱለው ይሆን?» አለኝ ጎንጤ አለማወቄ ቢገባውም እንዳያሳፍረኝ በመጠንቀቅ ዓይነት። አቀበልኩት። ተቀብሎኝ ግድግዳው ላይ ተሰክቶ ገመዱ የተዝረከረከ ገመድ ብድግ ሲያደርግ የሚቀጥለው ሂደት ጫፉን ስልኩ ላይ መሰካት እንደሆነ አውቃለሁ። የሆነ አለ አይደል ሰው መንገድ ጠፍቶበት ልክ ቤቱን ሲያየው ይኸው እንደሚለው ዓይነት ነገር?
አባ 'እግዚአብሄር ጭንቅላትሽን እንደህፃን ልጅ ነጭ ወረቀት አድርጎ ሰጥቶሻል፣ የሚቀጥለውን ዘመንሽን አስተካክለሽ ፃፊበት' ይበሉኝ እንጂ እንደህፃን ነጭ ወረቀት የሆነ ጭንቅላት እንዳልቀረኝ አውቃለሁ። እንደህፃን እንዴት እንደምበላ ከ 'ሀ' አልጀመርኩም ወይም አፌ አልጠፋብኝም፣ መራመድ ለመቻል ከመዳህ አልጀመርኩም ፣ 'ኡፉ ነው' ባልባልም እሳት እንደሚፋጅ ሳየው አውቄያለሁ፣ ሽንቴን ልብሴ ላይ ይሁን ሽንት ቤት የምሸናው ሳላውቅ እላዬ ላይ አልለቀቅኩም፣ ሱሪ ለመልበስ በአንገቴ አላስገባሁም ወይም ጫማ ለማጥለቅ ግራ አልተጋባሁም፣ አልጋ ሳይ ይሄ መተኛሽ ነው ሳልባል ገልጬ ውስጥ ገብቼ ተኝቻለሁ ፣ የጥርስ ብሩሽ ሳይ ምንም ሳልጠይቅ እጂ አንስቶ ጥርሴን ቦርሿል  .........
2. ስልኬ
ስልኬ ለመጀመር የሚያስችለውን ባትሪ ሲያገኝ ራሱ ከፈተ። እስክሪኑ ሲበራ ዘልዬ አጠገቡ ደረስኩ እና አነሳሁት። ያ አልጋዬ አጠገብ ያለው ፎቶ ላይ ያለው ልጅ ዓይኖች ያሉት ፎቶ ይታያል። ራሱ ነው! ኪዳን ነው። ትልቅ ሰው ሆኖ! ይሄን ምስል ሳየው እስከአሁን ምስሎቹን በወረቀት ሳየው ከተሰማኝ የተለየ ስሜት ተሰማኝ። የሆነ የሚያፍን ፈንጠዝያ! ልቤ ሰውነቴ ውስጥ ይነጥር ጀመር። ስልኬን በችኮላ ብነካካውም በኮድ ተዘግቷል። ተስፋ ቆርጬ መሬቱ ላይ እንደተቀመጥኩ
«እትዬ ስልኮትን በፊትዎት ነው ሲከፍቱ ያየሁት!» አለችኝ። እንዳልገባኝ አውቃ ስልኩ እጄ ላይ እንዳለ ወደ ፊቴ ስታቀርበው እውነትም የኮድ ምልክቱ ተነሳ። የሚቀጥለውን ፍለጋዬን ለማድረግ  በረጅሙ ተነፈስኩ። ወዲያው ስልኩ በመደዳ የማያቆም ተደጋጋሚ ድምፅ ያሰማ ጀመር። ለምን እንደሆነ ድምፁ ረበሸኝ። የሆነ ቀጥሎ መጥፎ ክስተት ይከሰት ይመስል ጭንቅላቴን ወጠረኝ። መሬቱ ላይ አስቀመጥኩት። የሆነ ግጭት ጭንቅላቴ ውስጥ የተከሰተ መሰለኝ። የሆነ የተኩስ ድምፅ ነገር።
«ምነው እትይ? አመሞት እንዴ? » ወድያው አስከትላ «ጎንጥ! አንተ ጎንጥ» ጆሮዬ ላይ አምባርቃ ተጣራች። በረንዳው ላይ የነበረ መሰለኝ
«ምንድነው?» ዘሎ አጠገቤ ደረሰ።
«እኔእንጃ የስልኩ ድምፅ ረበሸኝ።» አልኩት ስልኩን ካስቀመጥኩበት አንስቼ እያቀበልኩት።
«ደውሎ ያጣዎትን ስልክ መልእክት እየላከልዎት ነውኮ! ሌላም መልዕክቶች አሉት።»
«የሚጠቅም ነገር ካለው አንብብልኝ» አልኩት ልቤ ለምን እንደፈራ ሳላውቀው እየተርበተብኝ። ዝም ብሎ ስልኩን ሲነካካ ቆይቶ
«ሾካካ የሚባል ሰው 'ዛሬ ፖሊሶች ለድንገተኛ ፍተሻ ስለሚመጡ ቤቱ ይፅዳ' የሚል መልዕክት ልኮልዎት ነበር። ኦው ብዙ መልዕክት ነው የላከው። 'ምነው ዘጋሽኝ? በሰላም ነው ስልክሽ የማይሰራው?'......... 'ኸረ ምንድነው ጉዱ አንቺ ሳይኖሪኮ ቤቱ ስርዓት አጣ! '...... »
«ተስተምረሃል እና?» አለች ተናኜ በጣም በተገረመ አባባል አገጭዋን በእጅዋ ደግፉ ጎንጤን እያየችው። እሷ ማንበብ እንደማይችል እንዴት አሰበች እኔ እንዴት እንደሚያነብ እርግጠኛ ሆንኩ? አላውቅም! እሱ ተናኜን ቁጣና ግልምጫ ደባልቆ ለግሷት ወደንባቡ ሲመለስ የሚያነብበት ስልት እና ፍጥነት ስለእርሱ ብዙ የማላውቀው ነገር እንዳለ እንድጠረጥር አደረገኝ።
« ........ 'ሜሉ መላ ሳይገባልኝኮ ሁለት ሳምንት ተቆጠረ.' ........... እእ 'መታመምሽን በወሬ ሰማሁ መጥቼ እንዳልጠይቅሽ ቤትሽን የሚነግረኝ አጣሁ። ብደውል ስልክሽ አሁንም ዝግ ነው።'»
«ራሱ ሾካካው ነው?» ያልኩት አስቤው አልነበረም። ሁለቱም እኩል ሲስቁ አባባሌ ራሴንም አሳቀኝ! ጎንጤ ሳቁን ሲገታ

«አዎ ራሱ ነው!........ ' አንቺ በቅርቡ የማትመለሺ ከሆነ ለዳዊት መላዬን እንዲቆርስልኝ ንገሪልኝ ዛሬ ሄጄ ስጠይቀው የማውቅልህ ነገር የለም ብሎ አባርሮኛል።' ......... እ ሌላ ያልተመዘገበ ቁጥር........ ' እመቤት ነኝ ሜሉ ያለፈውን ሳምንት ስትቀሪ ባይመችሽ ነው ብዬ አለፍኩ ይሄንን ሳምንት ስትቀሪ ግን አሳሰብሽኝ። በሰላም ነው?' ........ሌላ ደግሞ ዳዊት የሚባል ሰው.........
»ካለ በኋላ ድምፁን ዝግ አድርጎ «እትይ ይሄን ራስዎ ቢያነቡት ሳይሻል አይቀርም ብሎ ስልኩን ዘረጋልኝ። እትዬ ነበር የሚለኝ እሱም እንደ ተናኜ እትይ ብሎ መጥራት መጀመሩ ቁልምጫ መሆኑ ነው?
«አንብበው ችግር የለውም ኸረ!» አልኩት እስከዛሬ ከሚያውቀው የባሰ ምን ሊመጣ ይችላል ብዬ እያሰብኩ። መቼም የገዛ ባሌን ፍሬዎች የቲማቲም ወይ የብርቱካን ፍሬ ከዛፉ እንደመቀንጠስ ቀለል አድርጌ ከሰውነቱ ቆርጬ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ ከመውሰድ የባሰ ጉዳይ ሊኖር አይችልም!
«አይ እትይ ግድ የልዎትም ራስዎ ያንብቡት!» አለ እያመነታ ስልኩን የዘረጋበት እጁን ሳይመልስ
«ግድ የለህም አንብበው» ስለው እያመነታ
«ካሉ እሺ!» ብሎ እስከዛሬ ያላየሁበት አይነት የማፈር ይሁን የመቅለስለስ ያልገባኝን ፊት እያሳየኝ ማንበብ ጀመረ። « የእኔ ፍቅር ስደውልልሽ አታነሺም  ስትመጪ የምንጠጣውን እንዳትረሺ! በጣም ቆየሽኮ ፍቅር በሰላም ነው ስልክ የማታነሺው? ....... »
«እሺ እሱን ተወው እና ሌላ አንብብ ኪዳን የሚል መልእክት የለም?» አልኩት እኔም እንደማፈር እያደረገኝ። ፍቅረኛ ነበረኝ? ቢያንስ የእኔ ፍቅር የሚለኝ ሰው ነበረ።
«እኮ!» ብሎ ጣቱን ወደላይ እና ወደ ታች ኪዳንን ፍለጋ ይፈትለው ጀመር። «አይ እትይ ኪዳን የሚል የለም! ምናልባት በሌላ ስም ይሆናል የመዘገቡት! ስም መዝገቡም ውስጥ ኪዳን የሚል የለም!»
«እሺ እስቲ ሊሎቹን አንብብልኝ እና በሌላ ስምም ከሆነ ከመልእክቱ እንደርስበት ይሆናል።» አልኩኝ።
«ሌላ ያልተመዘገበ ቁጥር አሁንም 'እመቤት ነኝ ሜሉ ያስቀየምኩሽ ነገር አለ እንዴ? በባለፈው ንግግሬ ተቀይመሽኝ ይሆን? ግራ ገባኝኮ!  ምንም ውስጥ ሆነሽ ቢያንስ መልእክት ትልኪብኝ ነበር። እንዲህ ጨክነሽብኝ አታውቂም! ብደውልም ስልክሽ አይሰራም። እባክሽ ቢያንስ ደህና መሆንሽን እንኳን አሳውቂኝ!»
«እናቴ ትሆን እንዴ?»
«መደወል እንችል ነበር ግን በሁለት የተለያየ ቁጥር ነው መልእክቱ የተላከው። በየትኛው እንደውል?» አለ ጎንጤ
«ምናልባት የራሷ ስልክ የላትም ይሆናል። አባ ታማለች ብለውኝ የለ? ባለፈው ሳምንት ሳትጠይቂኝ አይደል የሚለው የመጀመሪያው መልእክት?»
«ይሆን ይሆናል። ግን እትይ ለማንኛውም ለጊዜው ማን ምን እንደሆነ እስኪለይ ላገኙት ሁሉ ሰው ምንም እንደማያስታውሱ አይናገሩ! አጋጣሚውን ተጠቅሞ ሊጎዳዎት የሚያስብ ሰው ሊኖር ይችላል።» አለ ሀሳብ እንደገባው ሰው።
«አንደኛው ስልክ ላይ እንደውል!» አልኩኝ። ስልኩ አድምቆ ሶስታችንም በምንሰማው መጠን ሲጠራ ቆይቶ ከወድያኛው ጫፍ ተነሳ እና የወንድ ድምፅ «ሀሎ» አለ። ቀጥሎ የምለው ግራ ገብቶኝ ሳለ ጎንጤ ስልኩን ወደራሱ አስጠግቶ
«ይቅርታ ያድርጉልኝ እና በዚህ ስልክ እመቤትን ማግኘት እችል ይሆን? ሰው መልዕክት ሰዶኝ ነው!» አለ። የሰውየው ድምፅ ያመነታ መሰለ።
«ማነህ አንተ? እመቤትን ለምንድነው የፈለግካት? ማነው የላከህስ?»
«እኔን አያውቁኝም! እንደው እመቤትን ማግኘትን ብችል ወይ የማገኝበትን ሌላ ስልክ ቢጠቁሙኝ።»
«ተሳስተሃል። እመቤት የምትባል ሴት በዚህ ስልክ የለችም!» ስልኩ ተዘጋ። መልሶ እየደወለ። «ሲወሸክት ነው! » አለኝ ለእኔ
«እመቤት የምትባል ሴት አላውቅም አልኩህ አይደል?» አለ ሰውየው እየተቆጣ
«እየዋሹ ነው እሎታለሁኝኣ! በዚሁ ስልክ ከእመቤት መልዕክት ተልኮ ነበር። እመቤትን ካላወቋቸው እመቤት ነኝ የሚል መልእክት እንዴት እዚህ ደረሰ?» አለ ጎንጤ ቆፍጠን ብሎ ሰውየው ስልኩን ሲነካካ ድምፁ ይሰማል።
«ማነው ላከኝ ያልከው?» አለ በጥርጣሬ እንደማጣራት
«ሜላት»
«ታዲያ ራሷ ሜላት ለምን አልደወለችም አንተጋ ስልኳ ምን ይሰራል?»
«ለጊዜው እትዬ ሜላት ታመዋል። እንደየትም ብለህ መልእክት አድርስልኝ ብለውኝ ነው!» ሲለው ሰውየው የጠበበው ድምጽ አሰማ።
«እ መልእክቱን ብትነግረኝ እኔ እመቤትን ሳገኛት አደርስልሃለሁ። እመቤት የት እንዳለች ሜላት ነግራሃለች?» አለ አሁንም እንደጨነቀው።
«በፍፁም! በዚህ ስልክ ደውል ብቻ ነው ያሉኝ!»
«ዌል ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ናት!» አባባሉ 'እስቲ መልእክትህን እዛ ሄደህ ታደርስ እንደሆነ እናያለን!' አይነት ነው።
«እባክዎትን ካላስቸገርኩ ደውዬ እንደነበር መልእክት ያድርሱልኝ!» ብሎ ዘጋ ስልኩን። እናቴ ልትሆን አትችልም! እናቴ እስር ቤት ምን ታደርጋለች? ታማ የለ? ጎንጤ ስልኩን ሲበረብር ስልኩ እጁ ላይ ጮኸ
«እትይ ዳዊት እየደወለ ነው!» አለኝ ስልኩ ላይ አንዳች ነገር ያየ ይመስል እያፈጠጠ።
«አንሳዋ!» አልኩት መልሼ እያፈጠጥኩ
«ኸረግ! ተዚያ ምን ልለው?» ብሎ ስልኩን ክፍት አድርጎ ጆሮዬ ላይ ለጥፎልኝ ለተናኜ እንድትወጣ በዓይኑ ምልክት ሰጥቷት እሱም ወጣ!
«ኦህ ማይ ጋድ ፋይናሊ! በሀሳብ ከማለቄ በፊት! ስልክሽ መከፈቱን ቴሌ ማሳወቂያ ሲልክልኝ አይኔን ነበር ማመን ያቃተኝ! ሜሉዬ የኔ ፍቅር! ምን ባደርግሽ ነው እንዲህ የጨከንሽብኝ?» ሀሎ እንኳን ሳልለው ያለማቋረጥ ይለፈልፋል።
«ትንሽ አሞኝ ነበር» አልኩኝ ጎንጤ ያለኝን አስታውሼ
«ኦህ ማይ ጋድ! ታዲያ አትደውዪልኝም ነበር? እሺ አሁን የት ነው ያለሽው? የት ልምጣ? ኦህ አምላኬ? እሺ አሁን እንዴት ነሽ?»
የሚጠይቀኝ እንድመልስለት አይመስልም! የሆነ ልክ ያልሆነ ስሜት እንዲሰማኝ አደረገኝ። እቤት እንዲመጣ ስነግረው የቤቴን አቅጣጫ አልጠየቀኝም!
«ጎንጥ ? ዳዊት የሚባል ሰው እዚህ ቤት መጥቶ ያውቃል? ሆስፒታል እያለሁ መጥቶ ጠይቆህ ከሆነ?» አልኩት ወደበረንዳ ብቅ ብዬ። እኔስ ጎንጤን ተናኜ እንደምትጠራው ጎንጥ ማለቴ ማቆላመጤ ይሆን?
«በፍፁም እትይ!»
በር በሩን እያየሁ ቆይቼ መጣ! አራት ጊዜ ባጥፈው ያለምንም መጣበብ ሰፋፊዎቹ ጅንስ ሱሪዎቼ ጎን ኪስ መሰስ ብሎ ጥልቅ የሚል፣ ቀጭን ለመባል ራሱ መወፈር ያለበት ፣ አጭር ቀይ ስጋም ቀልብ የራቀው የሆነ ጥላ ቢስ ነገር ነው። አሁን ከዚህ ጋር ምን ይደረጋል? መቼም ወንድ ነው ብዬ ከስር ሆኜ አልደረግለትም! ከላይ ብሆንበት ከእጥረቱ ከቅጥነቱ ፈሱ ነው የሚያመልጠው።
                            ....................ይቀጥላል.........

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሥዕል ለማሳል በ+251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ!


@seiloch
@seiloch
#የመኖር አካፋይ ፣ የመ-ሞት ሲሶ ፣ መንገድ መሃል ………… (ክፍል ሰባት)
(ሜሪ ፈለቀ)


በር በሩን እያየሁ ቆይቼ መጣ! አራት ጊዜ ባጥፈው ያለምንም መጣበብ ሰፋፊዎቹ ጅንስ ሱሪዎቼ ጎን ኪስ መሰስ ብሎ ጥልቅ የሚል፣ ቀጭን ለመባል ራሱ መወፈር ስጋ መጨመር  ያለበት ፣ አጭር ቀይ……….. ስጋም ቀልብም የራቀው የሆነ ጥላ ቢስ ነገር ነው። አሁን ከዚህ ጋር ምን ይደረጋል? መቼም ወንድ ነው ብዬ ከስር ሆኜ አልተደረግኩለትም አይደል?! ከላይ ብሆንበት ከእጥረቱ ከቅጥነቱ ፈሱ ነው የሚያመልጠው ነውኮ የሚመስለው። ኸረ እንደው በፈጣሪ ምኑ ደስ ብሎኝ ይሆን አብሬው የነበርኩት? ምናልባት ሌላ በፍቅር የሚፈልገኝ ወንድ ጠፋቶ ምርጫ አጥቼ ይሆናል።

ዓይኖቹ የሌባ ዓይኖች ናቸው…….. ቅብዝብዝ የሚሉ ከይሲ ዓይኖች……. ሲያወራ ሁሉም የሰውነቱ አካል ይሳተፋል። በእግሮቹ ጥፍር እንደመቆም፣ ጫማውን መሬቱ ላይ እንደመሳብ፣ ጉልበት እና ጉልበቱን እንደማጋጨት፣ ከወገቡም ሰበርበር እንደማለት፣ የእጁቹን ጣቶች እንደማፍተልተል ነገር ፣ መዳፍ እና መዳፉን እንደማሻሸት፣ ትከሻውን እንደመስበቅ፣ አንገቱን ከወሬው ስልት ጋር እንደመወዝወዝ ፣ ከንፈሩን እንደመንከስ፣ አፍንጫውን እንደመንፋት፣ ዓይኖቹ ከወዲያ ወዲህ እንደመቅበዝበዝ፣ በቄንጥ ያበጠረው ሉጫ ፀጉሩ እንደመንቀጥቀጥ…………. ብቻ ከወሬው ጋር የማይሾር አካል የለውም።

ምንም ከማላስታውሰው ከእኔ በላይ እሱ ግራ ገባው! እንደመነካካካት እንደማቀፍ እንደመሳም ሁሉንም ቅጥ በሌለው ሁኔታ ለኮፍ ለኮፍ አድርጎ ከወነ። አንድ ነገር በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ይፈራኛል! እንዲህ አገጩ እስኪዝረበረብ እየፈራኝ ምን ሆኖ ነው «የእኔ ፍቅር » የሚለኝ? አስገድጄው ወይ በቦክስ አላግቼው ይሆን እንዴ ፍቅረኛዬ ያደረግኩት? ጎንጥ ባያስጠነቅቀኝ ምንም እንደማላስታውስ ነግሬው ምን ሲሆን አብሮኝ እንደሆነ ባወቅኩ! ………

«በቀናችን ስትቀሪ እና ስልክ ሳታነሺ ስትቀሪ መጀመሪያ ያው break ፈልገሽ መስሎኝ ነበር። በኋላ ስታመሪ ግራ ገባኝ! በዛ ላይ ስልክሽ ዝግ ሲሆን በቃ ከአንዱ ተጣልታ አንዱ ሸቤ ናት ብዬ አስቤ ሳጣራ መታመምሽን ሰማሁ! ማለቴ መመታትሽን! ያው መጥቼ እንዳልጠይቅሽ ያው አንቺ ነሽ!» ያሄን ሁሉ የሚያወራው እዛው ደጅ እንደቆመ ነው። ጎንጥ እንዳልወደደው ያስታውቃል። በአይኑ ቂጥ በጥርጣሬ እና ባለመደሰት ሲያየው ቆይቶ እኔ ወደ ቤት እንዲገባ ስጋብዘው እሱ ደጅ ቀረ። ‘ያው አንቺ ነሽ!’ ማለት ምን ማለት ነው? መጠየቅ አትወጂም ነው? አትፈልጊም ነው? ምን ማለት ነው? ምንም ነገር ብናገር ከትውስታ ነፃ መሆኔን ላቃጥር ስለምችል እኔ ብዙ ዝም ማለት መረጥኩ። ያለማቋረጥ ከለፈለፈው ብዙ ነገር ገጣጥሜ የተረዳሁት እኔ እና እሱ የምንጋራው ምን እንደሆነ በግልፅ ያላወቅኩት ንግድ ቤት አለን። ስለመጠጥ፣ ሙዚቃ እና ሴቶች የሆነ የሆነ ነገር አውርቷል። ……ብቻ  በወሬው መሃል ጣል ጣል ካደረገው የሚያያዝ ነገር በመነሳት  ለመገመት ብሞክርም ከስልኬ ካገኘሁት መልእክት ጋር ተደምሮ ብዙ አልገባኝም። ፖሊሶች ለድንገተኛ ፍተሻ የሚመጡት ምን ዓይነት ንግድ ቢሆን ነው?

«….. ብቻ ብዙ ነገር በአንድ ወር ተመሳቅሏል። ያ ሾካካ ደግሞ ገንዘብ አልተሰጠኝም ብሎ ሊያስፈራራኝ አልዳዳው መሰለሽ? ቃልኪዳን በጣም ስለጠገበች አባርሪያታለሁ። በወሬ አላድክምሽ ስትመለሺ ሁሉንም ትደርሺበት የለ! ይልቅ አንቺ እንዴት ነሽ? የመታሽ ሰው ማንነት ታወቀ? …… »

«ዛሬውኑ መመለስ እፈልጋለሁ። ለምን አሁኑኑ አብሬህ ሄጄ ፊቴን አሳይቼ አልመለስም?» አልኩኝ ሄጄ የምገባው ምን ውስጥ እንደሆነ ባላውቅም ማወቅ እያጓጓኝ

«አሁን ይሻላል? የምልሽ አሁን ምን እንሰራለን ወይ አንደኛሽን በኋላ ሁሉም ሲገቡ ብትመጪ አይሻልም?» ፊቱ ላይ ግራ የመጋባት እና ጥርጣሬ ነገር ነገሰ። የሆነ ነገር እንደተሳሳትኩ ገባኝ

«ይሁን ሁሉም ባይኖሩም ቤቱ ያለበትን ሁኔታ ቃኘት አድርጌ እመለሳለሁ።» አልኩኝ እሱ ሲያወራ «ቤቱ» እያለ ሲያወራ ከሰማሁት ኮርጄ

«ካልሽ እሺ! ወስጄ እመልስሻለሁ!» አለኝ የሆነ ያልተዋጠለት ነገር እንዳለ እያስታወቀበት።

መኝታ ቤት ገብቼ ተናኜን ጠራኋት እና በፊት እንደምለብሰው አለባበስ ልብስ መርጣ እንድትሰጠኝ አደረግኩ። ምንድነው ብዬ ነው ይሆን እንደዚህ እለብስ የነበረው? መለወጤን ለማንም በቃልም በተግባርም ማሳየት ስላልነበረብኝ ያወጣችልኝን ልብሶች ለባብሼ ከዳዊት ጋር ለመሄድ ተነሳሁ።

«እትይ አንዴ ለብቻዎ ላናግሮት?» አለኝ ጎንጥ ወደ ውጪ ብቅ ስንል። ወደጓሮ ዘወር ብለን ድምፁን ዝግ አድርጎ በሹክሹክታ
«ይቅርታ ያድርጉልኝ እትይ ከዚህ ሰውዬ ጋር ብቻዎትን መሄድዎን አልወደድኩትም። የት እንደሚሄዱስ ያውቃሉ? ልከተልዎት!» አለ ፍርጥም ብሎ

«ግድ የለህም ጎንጥ ምንም አልሆንም! እስከመቼ እንደህፃን ልጅ ትጠብቀኛለህ? የከፋ ነገር እንኳን ቢመጣ ምንም የበፊቷን ሜላት መሆን ባልችል ይሄን አንድ ጭብጥ ሰውዬ መገንበር ያቅተኛል? » ስለው ፈገግ ነገር ብሎ

«ብቻውን ከሆነስ ቆርጥመው ይበሉታል። የት እንደሚወስድዎ ነው ያሳሰበኝ።»
«ግድ የለህም አጠራጣሪ እና ሰው የሌለበት ቦታ ከሆነ እጠነቀቃለሁ።»
«ግድ የሎትም ልከተልዎት?»
«ግድ የለህም ይሄን ብቻዬን ልወጣው! ይልቅ አንቱ የምትለኝን ነገር ተው!»


እንደጠበቅኩትም መኪናውን እየነዳ ያለማቋረጥ እየለፈለፈ ፣ እንዳልጠበቅኩትም አልፎ አልፎ አንድ እጁን እየሰደደ ወይ ትከሻዬን አልያም ጭኔን እንደመዳበስ እያደረገኝ (በጣም ደስ የማይል ስሜት አለው። በተለይ ጭኔ ላይ እጁን ሲያሳርፍ! መጀመሪያ ሲነካኝ ከመቀመጫዬ እንደመዝለልም አድርጎኝ ነበር። ) መንገዱን ተያያዝነው። የምንሄድበትን መንገድ በጭንቅላቴ ለመመዝገብ ፣ የማያቸውን ፅሁፎች ጭንቅላቴ ውስጥ ለማስቀረት እሞክራለሁ። አንዳንዶቹን በትልልቅ የተፃፉ ጽሁፎች የማውቃቸው የማውቃቸው ይመስለኛል። ይመስለኛል እንጂ ከምስሉ ተያይዞ የማስታውሰው ነገር የለም። ይሄ በጣም የሚያስጨንቅ ስሜት አለው። ትውስታ ይሆን ጭንቅላቴ የሚፈጥረው ስሜት ይሆን አለመለየት ፣ የቱ የነበረ የቱ አዲስ መሆኑን አለመለየት ከመርሳቱ በላይ ጭንቅላት ይወጥራል። ለምሳሌ መንገዱን አላውቀውም ነገር ግን መታጠፊያ ጋር ስንደርስ በዛ መታጠፊያ እንደሚታጠፍ ገምቼ ይሁን አውቄ አላውቅም። ግን ልክ መኪናውን እየነዳሁ ያለሁት እኔ ብሆን ልክ እዛ መታጠፊያ ጋር ስደርስ ማንም ሳይነግረኝ መሪውን የማዞር ይመስለኛል። ከትውስታዬ ማህደር ከሆነ መንገዱን ሳላውቀው እንዴት መታጠፊያዎቹን ብቻ አስታውሳለሁ? የሆነ ቀን ለክትትል ሀኪም ቤት ስሄድ ለሀኪሙ የሚሰማኝን መቀዣበር ስነግረው

«በህይወትሽ ውስጥ በተደጋጋሚ ታደርጊያቸው የነበሩትን ነገሮች በደመነፍስ ሰውነትሽ ሲያደርጋቸው ልታገኚ ትችያለሽ። ሳታውቂው ታዘወትሪበት የነበረ ቦታ መገኘት፣ ቋንቋ ድንገት ሰዎች ሲያወሩ መረዳት ወይ መንገር ፣ በፊት ትወጃቸው ከነበሩ ነገሮች ጋር መቆራኘት፣ ትጠያቸው የነበሩ ነገሮችን መጥላት ……..
የመሳሰሉ ነገሮች የሚከሰቱ ናቸው። ከነገሮች ጋር ተያይዞ ጭንቅላትሽ የሚከስተው ምስል ካለ ግን ያ የትውስታሽ አካል ነው። ምናልባት እቦታው ላይ ብትገኚ ክስተቱን የማስታወስ እድልሽ ሰፊ ሊሆን ይችላል።» ብሎኝ ነበር። በእርግጥ የአዕምሮ ክፍላችንን የሚያሳይ ምስል አስቀምጦ ብዙ የተወሳሰበ ነገር ሊያስረዳኝ ሞክሯል። አልገቡኝም እንጂ! ቤተ ክርስቲያን ሄጄ እቀመጥበት ከነበረበት ቦታ እና ከወንድሜ መልክ የቱ ነበር ለስሜቴ መቅረብ የነበረበት? የጎንጥን ፊት ሳላስታውስ እንዴት ሽጉጥን ማስታወስ አወቅሁበት? ዋናውን መንገድ ወይም መዳረሻዬን ሳላውቅ እንዴት ኩርባዎቹን አወቅሁ?

አንድ የሆነ ትልቅ ህንፃ ጋር ደርሰን መኪናውን ካቆመ በኋላ ሰባተኛው ወለል ላይ እየመራ አደረሰኝ እና የሆነ በር ከፍተን ገባን።  የማያቸውን ነገሮች የማውቃቸው ወይም አዲስ እንዳልሆነብኝ ለማስመሰል የማደርገው ሂደት ምን ያህል ይሳካልኝ አላውቅም! ሁለት ሴቶች ወለሉን እያፀዱ ነው። እዚህም እዚያም ወለሉ መሃል ዘርዘር ብለው የተቀመጡት ጠረጴዛዎች ላይ ወንበሮች ተደፋፍተውባቸዋል። ጥግጥጉን በቀይ ገመድ የታጠሩ ጥቋቁር ሶፋዎች አሉ፣ አንደኛውን ግድግዳ ሙሉ በተለያዩ ጠርሙሶችና ሌሎች ነገሮች የተሞላ መደርደሪያ ሸፍኖታል። ከመደርደሪያው እና ከፊቱ ካለው ከፍ ያለ እግራቸው ረዣዥም ወንበሮች ከተደፋበት መደገፊያ ነገር መሃል ሁለት ወንዶች እየተቀባበሉ ብርጭቆ እያደረቁ ይደረድራሉ። መግባቴን ሲያዩ ሁለቱ ወንዶች ስራቸውን ትተው ቆሙ። አንደኛው ወገቡጋ የሚደርሰውን መደገፊያ ነገር ዘሎ አጠገቤ ደረሰ።

«ውይ ሜሉዬ እንኳን እግዚአብሄር ለዚህ አበቃሽ! » ጭንቅ አድርጎ እያቀፈኝ በጆሮዬ እንደማንሾካሾክ ነገር «ቤቱ በአፍ ጢሙ ተደፍቶ ስራ አጥ ከመሆኔ በፊት ለጥቂት ነው የደረሽልኝ» ብሎ ለቀቀኝ። ፈገግ ብቻ አልኩ። የበፊቷ ሜላት እንዲህ ያለ አስጨናቂ መታቀፍ ሲደርስባት በጥፊ ትለፈው በፈገግታ መገመት ባልችልም……. እየተቀባበሉ እንኳን ደህና መጣሽ ይበሉኝ እንጂ መጀመሪያ ካቀፈኝ ሰው ውጪ የጨበጠኝም ያቀፈኝም የለም። ልክ እንደሚያውቅ ሰው የሽንት ቤት ምልክት ከሚታይበት ተቃራኒ ያለውን  ቀጣዩን በር አልፌ ወደ ውስጥ ገባሁ። ሰፊ ኮሪደር እና የተለያዩ ክፍሎች አሉ። እያንዳንዱ ክፍል ውስጥ ሶፋ እና መሃሉ ላይ የብረት ዘንግ ያለበት ከፍ ያለ በቆዳ የተለበጠ ክብ አልጋ መሳይ ነገር አለ። የመጨረሻውን ክፍል ከፍቼ ስገባ አንዲት ቢነኳት ቆዳዋ ተሰርጉዶ የሚቀር የምትመስል ቆንጅዬ ወጣት በፓንት እና በጡት ማስያዣ እዛው አልጋ መሳዩ ቦታ ላይ ተኝታለች። በሩን ከፍቼ ስገባ ብንን ብላ ነቃች እና እንደመደንገጥ ብላ

«ማታ በጣም ዝዬ ስለነበር እዛ ድረስ ከምሄድ ብዬ እዚሁ ተኝቼ ነውኮ! እ? አሁኑኑ ተጣጥቤ ፏ እላለሁ። ይቅርታ በጣም» እያለች ተለማመጠችኝ። ለምን ይቅርታ እንደጠየቀችኝም፤ ስራዋ ምን እንደሆነም፤ ለምን እርቃኗን እንዳለችም ……. ምኑም በእርግጠኝነት ስላልገባኝ በአጠገቤ አልፋ ልትወጣ ስትል ትከሻዋን በአይዞሽ ዓይነት መታ መታ አደረግኳት። ልምምጧ ያሳዝናል። እንዴት ባሳቅቃት ነው ይህችን የመሰለች ልጅ ስታየኝ እንዲህ የምትርመጠመጠው?

እንደገባኝ ከሆነ እቤቱ ውስጥ የሚከወነውን ለማየት ሲመሽ መምጣት አለብኝ። ስር ስሬ ሲከተለኝ የነበረው ዳዊት ወደ ቤት እየመለሰኝ አስብ የነበረው ……. ስንት ዓይነት ሰው ነኝ? ወይም ነበርኩ የሚለውን ነበር። አንደኛው መጥቶ የሚጠመጠምብኝ፣ ሌላኛዋ ስታየኝ ሽንቷ ሊያመልጣት የሚዳዳ ፣ ለዳዊት የሚፈራን ግን የእኔ ፍቅር የሚለኝ …….. አባ እንደልጃቸው ፀጉሬን የሚደባብሱኝ ፣ ጎረቤቶቼ የሚጠሉኝ ፣ ጎንጥ እና ተናኜም ቢሆኑ እንደክፉ ሴት የሚያዩኝ …….. ትክክለኛዋ ሜላት የትኛዋ ነበርኩ? ወይስ ሁሉንም ነኝ? ለማናቸው ነው ትክክለኛ ማንነቴን የገለፅኩት? ለማናቸውስ ነው ያስመሰልኩት? ዝም ብዬ ሳስበው ለምሳሌ ልጅ ቢኖረኝ ፍቅረኛዬ ወይ ባሌ በሚያውቀኝ መልኩ ሊያውቀኝ አይችልም። ምናልባት ባስታውሰው ወላጆቼም ጓደኞቼ በሚያውቁኝ መንገድ አያውቁኝም። የምወደው ጓደኛ ኖሮኝ ቢያውቅ ለእሷ የምሆነውን መሆን ቅድም ብርጭቆ ሲያፀዳ ለነበረው ልጅ አልሆንም። ምናልባት እያስመሰልኩ አይደል ይሆናል። እኔ እንደልጅ፣ እኔ እንደሚስት፣ እኔ እንደጓደኛ፣ እኔው እንደእናት፣ እኔው እንደአለቃ …… እንደብዙ ነገር እንደብዙ የምኖር የእነዚህ ሁሉ ስብጥሮች እሆን ይሆናል።

በር ላይ አድርሶኝ ስንሰነባበት ከንፈሬን ሊስመኝ ሲጠጋኝ ሳላስበው ገፋሁት። ካደረግኩት በኋላ እሱ ፊት ላይ የነበረው ምላሽ እንድፀፀት አደረገኝ።

«ይቅርታ ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆንኩ ነው!»
«እረዳሻለሁ የኔ ፍቅር!» ብሎ ወደመኪናው ገባ!

እቤት ከገባሁ በኋላ ቅድም አስቀምጬው የነበረውን ስልክ መበርበር ጀመርኩ። ብቻ የሆነ ፍንጭ! የሆነ መረጃ! ያልነካሁት ያልፈተሽኩት ምልክት የለም። ከፎቶዎቹ ውጪ ለኪዳን የተጠጋጋ ስምም ሆነ መልእክት የለም። ሌሎች የማላውቃቸው ሰዎች ብቻቸውንም አንዳንዱ ከእኔ ጋር ፎቶ አይቻለሁ። የሆነ ነገር ካስታወስኩ ብዬ ፎቶዎቹን እየደጋገምኩ ባይም ጠብ የሚል ነገር የለም። እናቴ ልትሆን ትችላለች ብዬ የጠረጠርኳት አንዲት ሴት ጋር ተደጋጋሚ ፎቶ አለን። አልጋ ላይ ተኝታ አጠገቧ ተጋድሜ፣ አልጋ ላይ ተኝታ ጉሉኮስ ተሰክቶላት አልጋዋ አጠገብ ተንበርክኬ፣ የሆነ በረንዳ ላይ የሚመስል ቦታ ምግብ እየበላን ፣ ደግሞ ብቻዋን ፈገግ ብላ ……… አንዳቸውም የት ላገኛት እንደምችል መላ አልሰጡኝም።

«እትይ ይሄ መኪና ለምን ጋራዥ አይገባም? በታክሲ ከሚመላለሱም ሰው ከሚያስቸግሩም ይሻልዎታል!» አለኝ ጎንጥ አመሻሽ ላይ ብቅ ብሎ አንድ ጎኗ የተጋጨ እና የጥይት ብስ ያለባት መኪናዬ ወደቆመችበት አቅጣጫ በአገጩ እየጠቆመ።

«ማን ሊነዳው?»
«እሷ ትሰራና መንዳቱስ አይጠፋዎትም! ካልሆነም …… ብሎ አቅማማ
«መኪና መንዳት ትችላለህ እንዴ?» አልኩት ደገፍ ብዬ ከተቀመጥኩበት እየሰገግኩ
« እንዲያ ነገር! ለአንዱ ዲታ ሹፌር ሆኜ 7 ዓመት ሾፍሬያለሁ።» አለ በማጣጣል አይነት።
«ታዲያ ለምን አልነገርከኝም እስከዛሬ? ደግሞ አንቱ አትበለኝ አላልኩህም?»
«አይ እትይ አፌ አይለምድልኝም አንች ማለቱን! ልምድ እንዲህ መች ቶሎ ይለቃል?»
«ሞክረው! መኪናዋን ነገ ውሰዳት ጋራዥ እኔ በታክሲ ደርሼ እመጣለሁ።» ካልኩት በኋላ ነው ስለቤቱ ያየሁትንም ያሰብኩትንም እንዳልነገርኩት ያስታወስኩት።

«እንዲህ ከመሸ ወዲያ መሄድ ደግ ነው ታዲያ? ወይ ልከተሎት!» ብሎ ይተገትገኝ ጀመር። «እትይ ዘንግተውት እንጂ ብዙ ጠላት ያሎት ሰው ኖት!» አሁንም ትንሽ ይቆይና «ባይሆን ከደጅ እጠብቆታለሁ! መንገዱን ላካሂዶት!»
«አንቱ አትበለኝ አልኩህኮ!»
«ይሁን እሺ እኔ ምኑም አላማረኝ እትይ!»
«እህእ!»
«ኸረግ እትይ እንዳትለኝማ አይበሉኝ!»

ባያሳምነውም ታክሲ ጠርቶ ሸኘኝ። የህንፃውን ስም ስነግረው ባለታክሲው አወቀው። እየሄድን የሆነ ጭር ያለ መንገድ ላይ የሆነ መኪና መጥቶ መንገድ ዘጋብን። ባለታክሲው እየተሳደበ መኪናውን አቆመ። ከቆመው መኪና ውስጥ ሁለት የገዛዘፍ ወንዶች ወርደው ደረታቸውን አሳብጠው እየተራመዱ ወደእኛ ቀረቡ!!

@wegoch
@wegoch
@paappii
[ Behavioral Economics ተፈርሾ]

(#አሃዱ)

የአበሻ ፊልም ላይ ሁሌ ድሃው ሲበደል፣ ሲገፋ፣ ሲከፋ ይከርምና - መጨረሻ ላይ ፈጣሪ ጣልቃ ገብቶ ይታደገዋል። ይረዳዋል። ሃብታምየውን ክፉ ገፀ-ባህሪ ደግሞ አግዜሩ ይቀጣለታል።

ቆንጅዬዋም ልጅ ታፈቅረዋለች።

ድሃውም ልቡ በሐሴት ይሞላል። እንደ ፈንዲሻ ይፍነከነካል።  እሺ ትለውና አልጋ ላይ ፈገግ ብለው ይተቃቀፋሉ። (ያው ሲፋቅ በመላጣው ሲከካት ያድራል)

ከዛም ፊልሙ ሲያልቅ

ለአለም፣
ለአለም፣
እንዳይለያየን ዘለዓለም።

የሚል ማጀቢያ ዘፈን ይለቀቃል። ተመልካቹም በከፍተኛ አድናቆት ያጨበጭባል።

(#ክልኤቱ)

ፊልሙን ጨርሰው ከወጡ በኋላ ወንድየው ሲኒማ የጋበዛትን ቸከስ ወይን ይጋብዛታል። ስለፊልሙ፣ ስለፍቅር ሃያልነት፣ ስለ ቸሩ እግዚአብሔር ፈራጅነት ይቀደድላታል። ይስቃሉ ይጫወታሉ። ከዛም አልጋ እንያዝ ይላታል። እሷም በአንዴ ከሰጠሁትማ ይንቀኛል፣ ትንሽ ልሸው ብላ፣ 'አልችልም። ዛሬ ፔሬድ ላይ ነኝ' ትለዋለች።

ይናደዳል።

'ለምን ቀድመሽ አልነገርሽኝም?!' ብሎ ይቆጣል። ያወጣው ወጪ፣ ገተታው፣ ጉጉቱ፣ ኪሳራው ቱግ ያደርገዋል። ኑሮ ውድነቱ፣የጋበዛት ሸክላ ጥብስ፣ አለቃው፣ አከራዩ፣ ATM ምናምን ትዝ ይለዋል።

ይጣላታል።

ሙልጭጭጭ አድርጎ ይሰድባታል። ደንግጣና በርግጋ ጥላው ትሄዳለች። መልሶ በቴክስት ሊሰድባት ሜሴንጀሩን ሲከፍተው ብሎክ አድርጋዋለች።

(#ሰልስቱ)

ወንዶች ጓደኞቹ ጋራ ተደዋውሎ ይሄዳል። ስለኳስ ስለ ፖለቲክ እያወራ ውሎውንና ብስጭቱን ይረሳዋል።  ማታ አልጋው ላይ ሆኖ አስቴር በዳኔን እና መስከረም አበራን ፌስቡክ ላይ ይዘራጠጣል።  አዲስ ቸከስ በሜሴንጀር መጀናጀን ይጀምራል። ስልኳን ይቀበላል። ተቀጣጥረው፣ በሳምንቱ ተገናኝተው ሲኒማ ይዟት ይገባል።

¤

እዚህኛው ፊልምም ላይ ድሃው ሲበደል፣ ሲገፋ፣ ሲከፋ ይከርምና - መጨረሻ ላይ ፈጣሪ ጣልቃ ገብቶ ይታደገዋል። ይረዳዋል። ሃብታምየውን ገፀ-ባህሪ ይቀጣለታል። ለአለም፣ ለአለም፣ እንዳይለያየን ዘለዓለም የሚል ማጀቢያ ዘፈን ይለቀቃል። ተመልካቹም በከፍተኛ አድናቆት ያጨበጭባል።

. . . . ያወጣው ወጪ፣ ገተታው፣ ጉጉቱ፣ ኪሳራው ቱግ ያደርገዋል። ኑሮ ውድነቱ፣የጋበዛት ሸክላ ጥብስ፣ አለቃው፣ አከራዩ፣ ATM ምናምን ትዝ ይለዋል። ይናደዳል - ይጣላታል።

¤

[ህይወትም ይቀጥላል]

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Eyob mihreteab yohannes
አስበላሽው
።።።።።።።።
ቆሜ ልቀር ነው ብዬ በተቀመጡት (ቅምጥ በሆኑት)መቅናት ስጀምር መላዕክ ይላከው ሰይጣን በውል የማላውቀው ሰው ሽማግሌ ላከብኝ።

  መኩራት!አይታሰብም!ለምን ጥቁረቱ ኮሎኔል መንግስቱን አያስንቅም?ለምን አይኑ የመርፌ ቀዳዳ አታክልም?
ለምን አፍንጫው ግሪደር እንደባረከው የኮረኮንች መንገድ አይደፈጠጥም?
ለምን ከንፈሩን የቄራ በላቾች አይሻሙበትም?
ለምን ጥርሱ የሕወሃትን አውደ ውጊያ አይመስልም?
ኧረ ለምን እንትን ራሱ የሌለው አይሆንም? "የሰው ልጅ በስጋ ምግብ ብቻ አይኖርም፤ በእግዚአብሔር ቃል ጭምር እንጂ" ብለው የለ አባቄሱ?

  እናማ ቆሞ የመቅረት ፍርሀቻ ከ 'ዙስ' (ከእንስሳት ጋር ከሚገናኙ ሰዎች)መሀል አንዷ ሳያረገኝ እግዜር ማንን እያክለፈለፈ እንዳመጣልኝ ለማየት ቋመጥኩ።ሽማግሌዎቹ በተባለው ቀን መጡ።የምኝታ ክፍሌ መግቢያ ላይ ያለውን መጋረጃ በትንሹ ገልጬ የሚነጋገሩትን ለመስማት ጆሮዬን አሾልኩ።አያቴ እናቴን ለአባቴ ስትድር የለበሰችውን ግማሽ ምዕተ አመት ሊያስቆጥር ጥቂት የቀረውን ጉንፍ ቀሚሷን ከተቆለፈበት አውጥታ ከነኩታው ግጥም አርጋ ለብሳዋለች።ይህ ቀሚስና አያቴ የሚገርም ጥምረት አላቸው።ሰው በተሰበሰበበት

"ይሄንን ቀሚስ የሰራልኝ ሸማኔ ነፍሱን ይማርና ዕውነተ ሸማኔ ነበር...ልብስ ብቻም አልነበር አከላት ሲሸምንም ወደር የለው ነበር..."ስትል ስቅቅ ብዬ

"ኧረ አያቴ እባክሽን እየመረጥሽ አውሪ"እላለሁ።

"ምራጭ ይንሳሽ!ለነገሩ ነስቶሻል...ቆሞ ቀር በቅሎ!አሁንማ ምን ሸማኔ አለ?ወንዱን ሁላ አመንምኑ ጨረሰው...ምድረ ላስቲካም!የቀረውም በግዜ ገብቶ ተምሽቱ ወገብ ይልቅ የብርሌ አንገት ማነቅ ይቀናዋል የጀጋው ጅወርጅስ ይነቀውና!"

ደግሞ ሌላ ጊዜ

"አቤት ይኸን ቀሚስ ሳሰራ የነበረው አጀብ!አቤት!እኔ ይደነቁ እንደሁ ነገር  እሚደንቀኝም አልነበርኩ...አረቄ አውጭታይቱም፣ቅጠል ለቃሚይቱም፣የመሳፍንቱም ቅምጥ፣የወዛደሩም ምሽት ዐይኗን ጥላብኝ...በስተመጨራረሻ እሱ መልዐኩ ህብስቷን ያንጥፈውና...ያች ህብስቴ የሚሏት ጋለሞታ በመተቷ ተብትባኝ አደናቅፎኝ ብወድቅ እንዲህ አጉል ቦታ ተቀዶ ቀረ..."ትላለች ከእንትኗ ዝቅ ብላ ያለችዋን ትንሽዬ ቀዳዳ እያሳየች።ምን ዓይነት አወዳደቅ ልብስን እዚያ ቦታ ላይ እንደሚቀድ ለሰሚው ግራ ቢሆንም ከይደነቁ አፍ ከወጣ ምንም ነገር ሳትወድ በግድህ ታምናለህ!ካልሆነ የእርግማን በኮንቴነረሯን ታራግፍብሀለች።

  ከተላኩብኝ ሶስት  ሽማግሌዎች አንዱ ቀትረ ቀላሉ አባ ሙሉነህ ናቸው። ''ስምን ሳጥናኤል ያወጣዋል! ''ያስብለኛል ተፈጥሯቸው!አንድ የሞላ ነገር ሳይኖራቸው ምን የታየው ደንባራ ነቢይ 'ሙሉነህ' እንዳላቸው ሳስበው ይደንቀኛል። ደሞዛቸው ጎደሎ፣ባለቤታቸው ጎደሎ፣ ልጆቻቸዉ ጎደሎ፣ጓዳቸው ጎደሎ ፣ ዘመዶቻቸው እንዳል ጎደሎ!!ትልቁ ልጃቸው በዓመታት ልምምድ ዘርፈ ብዙ ማጅራቶችን መቶ  በገዛላቸው 'ቲቪ'  ከእሁድ እስከ እሁድ ተቀምጠው ያለ ደህና ቀለብ የፓለቲካ ክርክር ሲያዩ መንምነው ሰንደል ካከሉ ቆይተዋል። እሳቸውን የላከብኝም ጎደሎ እንዳይሆንብኝ ሰጋሁ።

ሁለተኛው ሽማግሌ አባ ምህረቴ ናቸው።የመንደሩ እድሜ ጠገብ ሰይጣን(ማለቴ አዛውንት) በመሆናቸው ሁሉም ያውቃቸዋል ።ከአያቴ ጋር ከተኮራረፉ ቢቆዩም ማህበራዊ ገፃችን ይኸው ዛሬ አገናኛቸው።

የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ይመስለኛል የሰፈራችን የኪዳነምህረት ደብር የሰበካ ጉባኤ አባላት ሲመረጡ አንዳንድ አሽለጥላጮች ለአባ ምህረቴ ድምፅ ይሰጡና ያስመርጧቸዋል።ከመራጮቹ አንዱ

"አባ ምህረቴ'ኮ ማለት የታፈሩ ጨዋ አዛውንት ናቸው!ሰው በልቶ የጠገበ የማይመስላቸው፣ትሁት፣ሰው ቀና ብለው የማያዩ..."ሲል አያቴ ከተሰብሳቢው መሀል ተነስታ

"ማነህ...ማነህ አስመራጭ!ያልከው በሞላ አንድ ሀሰት የለውም...ልክ ነው!'ሰው በልቶ የጠገጠ አይመስላቸውም' ላልከው እኔ አለሁ ምስክር!አንዴ ለምሳ የሚበሉት የኔን የዕለት ቀለብ ስለሆነ ሰው በልቶ የጠገበ ባይመስላቸው አይደንቅም!አዎ አይደንቅም!...ደሞ ' ሰው ቀና ብለው አያዩም ' ላልከው ሌላ ተዓምር የለውም ጎባጣ ስለሆኑ ነው ''ካለቻቸው ወዲህ የእግዜር ሰላምታ እንኳን መለዋወጥ ትተው ነበር።

ሶስተኛው ሽማግሌ ቆጥቋጣው አባ ዘለዓለም ናቸው።መብራት አጥፋ አላጠፋም በሚል ግብግብ ከተከራያቸው ተጋጭተው ባተረፏት መጠነኛ የግንባራቸው ጠባሳ ነው መንደርተኛው አፍ ውስጥ የገቡት።እንደሰማሁት ከሆነ ሚስቱ የወለደች ተከራያቸውን

"አንተ ማነህ...መብራቱን በግዜ አታብራው እንጅ ገና ቀን አይደል?"ሲሉት

"ኧረ  ጋሼ መብራቱ ሲጠፋኮ ጨቅላው እያለቀሰ አስቸግሮን ነው"ብሏቸዋል ።

"ኧና  ምሸቱ ጠንከር እስቲል ጨረቃ ላይ አውጥታችሁ አታጫውቱትም?"ብለው ያንን ያልጠነከረ ጨቅላ የበረንዳ ብርድ አስመትተው ሳንባውን ከጥቅም ውጭ አረጉት አሉ።ህፃኑ ትኩሳትና ሳል ሲያዳፋው የጨነቃቸው እናትና አባት ከምሽቱ 05:00 ገደማ መብራት ሲያበሩ፣አባ ዘለዓለም ለሽንት ሲወጡ ይገጣጠማሉ!ሶስተኛው የዐለም ጦርነት ሆነ!...ሚሳኤል ተተኮሰ!

  "አተ! ምንድነው በዚህ ለ
ምሸት መብራቱን የለኮስከው?"

  "ኧረ ጋሼ ልጁ ታሞብን ነው"

  "ምንድነው ያመመው?"

   " እንጃ ትኩሳት አለው"

"ዋእ!እና በትኩሳቱ ላይ አምፖሉን ለኩሳችሁ ልታነዱ ነው?"ብለዋል አሉ ዕውነት ይሁን ግነት ባላውቅም!በመሀል ግብግብ ተነስቶ የበሰጨው ተከራይ በጠርሙስ ግንባራቸውን ከተረከካቸው ወዲህ ነው አደብ የገዙት።

ሽማግሌዎቹ ከአያቴ ፊት ለፊት ተደርድረው እርስበርሳቸው ይተያያሉ።

ወዲያው አባ ሙሉነህ ከቀሪዎቹ ሽማግሌዎች አንድ እርምጃ ወደፊት ወደ አያቴ ጠጋ አሉና

  "እንግዲህ እማ ይደነቁ ያው እንደሚያውቁት ዛሬ የመጣነው መልካም ፈቃድዎ ተሆነ ልጅዎትን ለልጃችን ልንል ነው"ሲሉ አያቴ

"ለመሆኑ ምንምን ጥሪት አለው?"ብላ የሀብት ክፍፍሉን ከአሁኑ ልታሰላ ነው ብዬ ስጠብቅ የግንባሯን ቆዳ ሰብሰብ አድርጋ

  "ለመሆኑ ሰውየው ማነው?"አለች ።

"እሱንማ  በቀደም ዕለት ተነጋገርንም አይደል እማ ይዴ?"(አባ ሙሉነህ)

"የለም!የተነጋገርነውማ የሰውየውን ስም እና የምጫችሁን ቀን ብቻ ነው!አዎ!እሱንም እኔን ሳታማክሩ በግላችሁ ነው የወሰናችሁት።አሁን እሱን ተውትና ስለ ሰውየው  ንገሩኝ ማነው ያላችሁት ስሙን ?ሺመክት ነው?"

"አዎ ሽመክት!እንደው እንዴት ያለ የቤት አስተዳደር የተካነ ቆጣቢ መሰለዎት!"አሉ አባ ዘለዓለም ጣልቃ ገብተው።

"ስራውስ?"

"ስራው ተሰው አልፎ እግዚሀር የወደደው የተመረጠ የበተስኪያን አገልጋይ ነው።እዚሁ እኛው ደብር ችዳነምረት የመጣ አዲስ ዲያቆን ነው"(አባ ምህረቴ)

"ዲያቆን?"

"አዋን ዲያቆን ምነው?"(አባ ምህረቴ)

"ኧረ ምንም...ዲያቆን ሸጋ ነው ወንድሞቸ...ግን እንዲያው..."

"ግን ምን እማ ይዴ?"(አባ ሙሉነህ)

"ምንም ...እንዲያው ዲያቆን ተሆነ ጋብቻው በበተስኪያን ይሁን ማለቱ አይቀርም ብየ ነው እንጅ"

"አሀ!እሱማ ምን ጥያቄ አለው?እግዚሀሩ በወደደው በፈቀደው በቅዱሱ ተክሊል ቢጋቡ ምንድነው ችግሩ?"(አባ ሙሉነህ)

"ትክል ያርጋትና አንዳች ተካይ ቆይ እስቲ ወዳጆቸ አረፍ ብላችሁ ጠብቁኝ መጣሁ "አለችና አያቴ ወደኔ መጣች።

[[[እዚህ ጋር "ትክል ያርጋትና አንዳች ተካይ"የሚለውን እርግማን አያትየው ድምፃቸውን ዝቅ አርገው ነው የሚሉት]]]

ደመነፍሴን ወደሁዋላ ተራምጄ አልጋዬ ላይ ከመቀመጤ መጋረጃዬን ገልጣ በተማፅኖ እያየችኝ
"አንች ጀጤነሽ" አለችኝ።
"አቤት"
"እንደው በጣድቁ ...አደራሽን በጣድቁ እንዳታሳፍሪኝ!"
"ምንድነው አያቴ?"
"ንጡህ ነሽ አይደል?"
"ማለት?"
"የሚል አላት ብያለሁኮ እችን ተንከሲስ!ንጡህ ነሽ ድንግል ነሽ ወይ ነውኮ 'ምልሽ" አቀርቅሬ ዝም አልኩኝ።ለሰከንዶች ምላሼን ስትጠብቅ ቆይታ ተስፋ ስትቆርጥ

"በይ'ንጂ ንገሪኝ ...አየ!አየ!አየ ለፍቶ መና አስበላሽው? ጀጤነሽ አስበላሽው?ያን የመሰለ ዳቦ አስበላሽው?ሀይ!ሀይ!ሀይ!ሀይ!ሀይ!"አለችና ወደሽማግሌዎቹ ሄደች።እኔም ባቀረቀርኩበት ቆየሁ።ከዚያ በላይ የተነጋገሩበትን የምሰማበት ድፍረት አልነበረኝም።

✍️ማዕዶት ያየሕ

@wegoch
@wegoch
@paappii
ባለትዳሮች ደግሞ እስኪ አዳዲስ ጅንጀና ፍጠሩ...

እንዴ ሁሌ አንድ አይነት ያለፈበት ነገር ቸከሶቹም ይደብራቸውል እኮ!

“ይሄ በትዳሬ ደስተኛ አይደለሁም”፣ “አልጋ ከለየን ቆየን”፣ “ሶፋ ላይ ነው ማድረው”፣ “ለልጆቹ ብለን ነው አብረን ያለነው”፣ “በትክክል ካወራን እራሱ ረጅም ግዜ ሆኖናል”፣ “”ምግብ እንኳን አንድ ላይ ከበላን ቆይተናል”... ምናምን ዝብዘባ ኸረ ላሽ እንዲ ብላችሁ እኮ ብትፋቱ አሪፍ ነበር በስንተኛው ወር መንታ ልጅ ትወልዳላችሁ እኮ ደሞ!

እስኪ አዲስ የተጣላችሁበትን ምክንያት ፍጠሩ እስኪ ላይክ...

ወንዶቹ..

ቅልጥም በልታ መጣ ከዛ በዘነዘና ሰብራ ትበላለች

ስስማት እንጥሏ ይዋጋል

ጉልበቷ እያደር መጥቆር አመጣ

ቅቤ ተቀብታ በስስ ፌስታል አስራ ማደር ጀመረች

የብብቷን ፀጉር ማሳደግ ጀመረች

ፓንቷን በሶስት ቀን ነው የምትቀይረው

ሁሌ ሽንት ቤት ገብታ ፍላሽ ሳታደርግ ትረሳዋለች

ሴቶች ደግሞ...

ስኪኒ ሱሪ መልበስ ጀመረ

መጠጥ መጠጣት አቆመ

አፍንጫውን ይጎሮጉራል

ሲቀመጥ የቂጡ ፍንክት ይታያል

ሁለት ካልሲ ብቻ ነው ያለው

አፉ ጥግ ጥግ ላይ ነጭ ነገር ማውጣት ጀመረ

የሆነ ነገር በወደቀ ቁጥር "እሜ ድረሽ!" እያለ ከወንድ ልጅ የማይጠበቅ ቀጭን ድምፅ ያወጥል...

ምናምን የሚሉ የማያስሟሟችሁን ምክንያቶች ደርድሩ እንጂ!

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Habtish doi yilma
#የመኖር አጋማሽ ..የመ: ሞ : ት ሲሶ ... መንገድ መሃል ..... (ክፍል ስምንት)
(ሜሪ ፈለቀ)

'ማናችሁ? ምን ፈለጋችሁ?' ከማለቴ በፊት ከታክሲው ኃላ መቀመጫ ጎትተው አስወጥተው ያበጥሩኝ ጀመር:: .... 'ምን አድርጌያችሁ ነው?' ማለት አፌ ይፈልጋል... በየትኛው ትንፋሽ?... እንኳን የማወራበት... የምተነፍስበት ፋታ ሳይሰጡ ተቀባበሉኝ.... ባለታክሲው ሁለት ቡጢውን ሲያጣጥም መፍጨርጨሩንም ተወው:: ... ሶስተኛ ሲሰልሱት እንዲተውኝ መለመኑንም ተወው! መሬቱ ላይ ወድቄ 'እንካ በእርግጫ' ተባባሉብኝ.... የምቱ ቁጥር ሲጨምር የህመሙ መጠን ቀነሰ... ሰውነቴ የደነዘዘ መሰለኝ.... አንደኛው በጫማው ደሬቴን ሲለኝ... ቁስሌ የተቀደደ አይነት ስሜት ተሰማኝ... ሳያስፈቅደኝ ልቤ ክድት ... ጭልጥ ይልብኝ እና ምቱ ያነቃኛል.... በስልምልምታ ከሩቅ እየቀረበ የመጣ የመኪና ድምፅ እና መብራት የተፈራረቁብኝ ይመስለኛል::..... የሚደልቁኝ ጫማዎች በፍጥነት ጥለውኝ ሲሄዱ ነገር.... ... ልቤ ቅልጥ ብሎ ጥፍት አለብኝ....

የሆነ በርቀት ነገር "እትይ! እትይ!" ... የሚል ጥሪ ይሰማኛል:: ... አይኖቼን ልገልጥ ስሞክር የአይኖቼ ቆቦች ህመማቸው ያሰቃየኛል:: ... ያልታመመ የሰውነት አካል የለኝም:: ... ሀኪም ቤት ተኝቻለሁ::.... ጎንጥ የአልጋዬን ጠርዝ ይዞራል:: ያልተጠቀለለ የሰውነት አካል የለኝም::.... አይኔን መግለጤን ሲያይ

"እትይ ነቁ? ክብር ምስጋና ይግባህ አምላከ ስላሴ!" ብሎ ወደ ሰማይ አየ.... ፊቴ ላይ ሳይቀር በፋሻ ተጠቅልያለሁ!.... እንባዬ ሲወርድ ወደ ጆሮዬ እየሄደ የሚያልፍበት ቆዳ ሁሉ አልኮል እንደተደፋበት ቁስል ያቃጥለኛል::... አንገቴ ቀስሮ በሚይዝ መደገፊያ ተደግፎ ስለታሰረ አይኔን እንጂ አንገቴን ማዞር አልችልም:: አፌን ላንቀሳቅስ ብሞክር የተሰነጠቀ ከንፈሬ ስቃይ ውስጥ ይጥደኛል::...

"እትይ! ግድ የለም እነዚህን ሽንታሞች አገኛቸዋለሁ!!" ይለኛል ጎንጥ እሳት በሚተፋ የንዴት እና የእልህ ትንፋሽ .... በቁጭት አንዱን እጁን በቡጢ ጨብጦ ሌላኛውን ይመታል::

በጥይት ተመትቼ ስነቃ እንዲህ በህመም አልተሰቃየሁም ነበር::.... ተኛኜ እና ጎንጥ እየተፈራረቁ እያስታመሙኝ ሆስፒታል ከረምኩ::.... ከሳምንታት በኃላ የተሰበረ አፍንጫዬ አገገመ.... የተሰነጠቀ ከንፈሬ ቁስል ሻረ... የተሰባበሩት የጎድን አጥንቶቼ ተደጋገፋ... የበለዙ ስጋዎቼ ፈዘዙ..... አንገቴ ያለ ድጋፍ ዞረ.... የዞረ ክንዴ ቦታው ሰገበ... ወደ አንጀቴ የፈሰሰ ደሜ ተቀዳ..... የተቀደደ ቁስሌ ተሰፋ......

"ተሻለሽ?" ሲሉኝ .... "ደህና ነኝ!" እላለሁ! ... የጠየቁኝ የስጋ ቁስሌን እንደሆነ ስለማውቅ...

እኔ ግን አልተሻለኝም!! ደህና አይደለሁም!! ጭራሽ ለደህና የቀረበ ነገር አይደለሁም!! ... ጎንጥ አጠገቤ ሆኖ እጄን ካልያዘኝ እንቅልፍ የማይወስደኝ ፈሪ ሆኛለሁ:: ኮሽ ባለ ቁጥር ከአልጋዬ የማልዘለው እሱ እየጠበቀኝ እንደሆነ ሳውቅ ብቻ ነው:: .... ካለበለዚያ ኮቴ ያስደነግጠኛል:: .... የትንኝ ጥዝታታታ እንኳን ጩሂ ጩሂ ይለኛል:: መጠየቅም መመለስም ተውኩ:: መሞትም መኖርም ፈራሁ!! ... ተናኜ አብራኝ ስትውል.... የቆጥ የባጡን ስትለፈክፍ አልመልስ ስላት!!

"ኸረ እትይ በማርያም እንዲህ አይሁኑ!" ትለኛለች:: ጭንቅ ጥብብ ሲላት ደግሞ
"እትይ? ካልሆነ እብስ ብለው ለምን የሆነ ሀገር አይሄዱም?" ትለኛለች::
"እትይ? እስኪ ትንሽ ነገር ደግሞ ይቅመሱ በማርያም?"

..... አግጯን ደገፍ ታደርግና "ምፅ!" ብላ እንባዋን ትለቀዋለች:: ...

"ምን ልሁን ነው የምትይ?" ይላታል ጎንጥ ማልቀሷን ሲያውቅ:: ....

የዛን ቀን ሹፌሩ የመኪና ታርጋቸውን መዝግቦ ስለነበር ለፖሊስ መረጃ ብንሰጥም ፖሊሶቹ የእኔ ጉዳይ ግድ የሚሰጣቸው አልመሰሉም:: ጎንጥ ብስጭት ብሎ

"በነጋ በጠባ 'ያላሰለሰ ጥረት እያደረግን ነው! ' ይሉኛል:: ጠብ የሚል ነገር የለም! እንዴት ያለ ህግ ነው?" አለኝ የሆነ ቀን.... አልመለስኩለትም!! .... ቀን ቀን ተናኜ ትውልልኛለች:: ማታ ማታ እሱ ያድራል:: ... ዳዊት አንድ ሁለቴ ሊጠይቀኝ መጥቶ ነበር:: እንዳይመጣ ስለነገርኩት ቀረ!! ....

"እትይ ? ዛሬ ጎንጥ ስለማይመጣ ምሽቱንም እኔ ነኝ የማስተዳድሮት.... እቤት ደረስ ብዬ እራት አበሳስዬ ላምጣ?" አለች በጨነቀው ልምምጥ....

"ለምንድነው ጎንጥ የማይመጣው? " አልኩኝ የወላለቀ ሰውነቴን እየጎተትኩ ተቀምጬ

"አላውቅም እትይ!! የምፈጣጥመው ነገር አለኝ ! ነው ያለው!"

"እሺ ትተሽኝ አትሂጂ.... ከካፍቴሪያ የሆነ ነገር ግዢ" ብያት (የሆስፒታሉ ጊቢ ውስጥ ያለ ካፍቴሪያ ነው) እሷ ልታመጣ ስትሄድ ከፋኝ!! እንደህፃን ልጅ አለቀስኩ:: .... ሆስፒታል ማደር ደክሞት ይሆን??? እኔን መጠበቅ ከነአካቴው ደክሞት ይሆን?? ጠልቶኝ ይሆን?? .... ላይመለስ ትቶኝ ቢሄድ ምንድነው የምሆነው?? ከእርሱና ከተናኜ ውጪ ማንንም እንደማላውቅ እያወቀ ትቶኝ ይሄድ ይሆን?? ይቅር ይበለኝ እና ብር አምጣ ብዬ ከካዝናው ውስጥ ያወጣሁት ብር የት እንዳለ ነግሬዋለሁኮ .... ብሩን ይዞ እኔን ትቶኝ ሄዶ ቢሆንስ? እኔ በወር የምከፍለውን ደመወዝ ከ20 ዓመት በላይ የሚከፍለው ብር ነው..... በስመአብ !! ኸረ እንደሱ አያደርግም!!!

ለሊቱ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ነጋ!! ተናኜ ሳለቅስ ካየችኝ ከእኔ ብሳ ታርፈዋለች:: አልጋዬ ስር ፍራሿን ዘርግታ እንቅልፍ እስኪወስዳት ጠብቄ ..... ብዙ አልቅሼ እንባዬ ሁላ ያለቀ መሰለኝ!! ፍርሃት ሆዴን አላወሰው!!! የበር ድምፅ በሰማሁ ቁጥር ልቤ ይርዳል:: ሰውነቴ ይንቀጠቀጣል::....  ነግቶ ብርሃን ሲሆን እንቅልፍ ጣለኝ:: .... ብርሃን ከክፋት የሚጠብቀኝ ይመስል ሲፈካ ልቤ ይረጋጋል:: ከእንቅልፌ ስነቃ አይኔን ሳልገልጥ በፊት እጄን የያዘኝን እጅ ጨበጥኩ.... አይኖቼን ስገልጣቸው ጎንጥ ለሊት ሲያድር እንደሚያደርገው ወንበር ላይ ተቀምጦ እጄን ይዞኝ ... አንገቱን አልጋው ላይ ደፍቶ ተኝቷል::  .... ደስታ ይሁን መከፋት የማላውቀው ስሜት ናጠኝ::: ህቅታዬ እንዳይረብሸው እየታገልኩ ተንሰቀሰቅኩ:: ... ከደቂቃዎች በኃላ ግን ልያዘውም ብል ፈንቅሎኝ የወጣ ህቅታዬ ቀሰቀሰው.... እንደነቃ ሳየው ይብስ ድምፅ አውጥቼ ማልቀስ ጀመርኩ:: ....

"መድሃንያለም! እትይ? ምን ሆነው ነው?? ኸረ በመድሃንያለም ነፍስያዬን አያስጨንቋት?? " የሚያደርገው ግር ብሎት እጄን ባልጨበጠ እጁ እንባዬን ሊጠርግ ይታገላል::

"የሄ.... ድክ ... መስሎኝ..." ብዬ መጨረስ አቃተኝ:: ህቅ ማለት ቀጠልኩ:: ክፉ ነገር እንደነገርኩት ሁሉ ... ዝግንን ብሎት እጄን እንደጨበጠ ከተቀመጠበት እየተነሳ

"መሄድ ሲሉ?? መሄድ ! መሄድ!? ... ይቅር ይበሎት! ምኑን አሰቡት? እንዲህ ያለ ሁኔታ ላይ እንዴት ትቼዎት እሄዳለሁ?? እንዴት ያለ ሰው ነው ብለው ነው የሚያስቡኝ?" አለ ቁጣም በቀላቀለው አነጋገር!!

"ይቅርታ አድርግልኝ!! እኔ አላውቅም!! ምን እንደማስብ... ግራ የገባኝ ሰው ነኝ! ካንተ እና ከተናኜ ውጪ ማን ምን እንደሆነ እንኳን አላውቅም!! አንተ ብትሄድ..." ብዬ መጨረስ ቸገረኝ:: ተመልሶ እየተቀመጠ በሚለማመጥ ድምፅ

"የትም አልሄድም! እርሶ አልፈልግህም ብለው እስካላበረሩኝ ድረስ እኔ የትም አልሄድም!!" አለኝ:: ...
2024/09/22 05:40:55
Back to Top
HTML Embed Code: