Telegram Web Link
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ


@seiloch
@seiloch
"አሹ ሁለት ብር ይዘሀል?" አለኝ የመንደራችን ቀፋይ፣ ከሁለት ቀናት በፊት
'ምን ይሠራልሀል?' አልኩት የሁል ጊዜ ሠበቦቹ ስለሚያዝናኑኝ
"እራሴን ላጠፋ ፈልጌ አሪፍ ገመድ መግዛት ፈልጌ ነው" አለ ሳቅ እያለ
ከኪሴ ድፍን አሥር ብር አውጥቼ እየሰጠሁት
'ካሚል ሱቅ አሪፍ ሲባጎ ታገኛለህ፤ ሁለት ሜትሩን በሁለት ብር ይሸጥልሀል' አልኩት
"ታድያ አስር ብር ለምን ትሰጠኛለህ?" አለኝ ግራ ተጋብቶ
'በሥድሥት ብሩ ሶስት ሲጋራ አጭስ፤ በአንድ ብሩ መናዘዣ ወረቀት ግዛ' ብዬው ላልፍ ሥል
"የቀረችውን አንድ ብርስ ምን ላርጋት?" አለኝ በጭንቀት
'ወንድ ልጅ ባዶ ኪሱን አይሞትም!' አልኩት ኮሥተር ብዬ

ከሰዓት በሁዋላ ቀፋዬ ራሡን መሥቀሉን ሠማሁ።

ዛሬ፥ በሠልሥቱ ድንኩዋን ውሥጥ ካርታ እየተጫውትኩ ሳስበው የገረመኝ ነገር በኑዛዜው ማብቂያ አካባቢ ሞቱን ሥፖንሠር ሥላደረኩለት ማመሥገኑ ነበር!
.
.
.
.
'ማነህ ... ዳኛው፣ .... እስቲ ቦነስ ጻፍልኝ!'

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Ashenafi melese
" እሷ ምን ታርግ ፍቅርዋ ነው የገደለኝ ። በሳቁ ፣በለዛው ፣ በጭምትነቱ ጣሬን ሳያበዛ ጭጭ ያረገኝ ። ሰው ለምን ሳቅክ ተብሎ ይከሰሳል ? "

"የቱጋዬን ገድላ ሄደች? "

" ማን ?"

መልስ ፦ ተከሳሽና ተፈቃሪ


ካሊድ አቅሉ


ዳኛው ፦ " ተከሳሽ የክስ ማቅለያ አለሽ ?"

ተፈቃሪ ፦ " አዎ በጣም ያፈቅረኝ ነበር በህይወት ኖሮ ይሄን ቢያይ እንኳን ሞትኩ ነው ሚለው። "

ጠበቃ ፦ " እድሜ ልክ ነው መፈረድ ያለበት ሟችን ከሞት በላይ ገላዋለች "

እሷ የሞት ፍርዱን ትፈልጋለች ።
ለምን ቢባል አፍዋን ሞልታ ምትመልሰው መልስ አላት ።

"ለምን ? "

ከኔ ጋር ሰማይ ቤት ለመገናኘት ቀጠሮ አለን ያውም በግዜ ከሞትኩ ልትከተለኝ ከሄደች ቀድማ ልከተላት ።
" ያፈቀሩትን ሲያጡ ያገኙትን ይለማመጡ " በፍቅር አይሰራም በፍቅር ሚሰራው " የሚያፈቅሩትን ሲያጡ እራስን ማጣት ወይም እውነተኛ አፍቃሪ መፈለግ ነው ። "

አብዝቼ ወዳታለው አልፎም ገነት ላይ እየጠበኳት ነው ። የእሱ ገዳይ ተብላ እጇ ላይ ካቴና ታስሮ ፍርድ ቤት ገትረዋታል ።

እሷ ምን ታርግ ፍቅርዋ ነው የገደለኝ በሳቁ ፣ በለዛው ፣ በጭምትነቱ ጣሪን ሳያበዛ ጭጭ አረገኝ ። ሳቅ አብዝታ ባጠገቤ እኔም ስርዋን ስምግ ሄድኩ እንደ ቀልድ ምድርን ትቼ . . .

ሰው ለምን ሳቅክ ተብሎ ይከሰሳል ?

" ለመሞት ቀድሞ የወጣውም ጥፋተኛ ነው። "

ሊፈርዱባት ዳር ዳር ሲላቸው በድኑ አካሌ በር ከፍቶ ገባ ። " ነፍሴን ሰውታ አካሌን ለማን ነው ያስቀረችው ?"

"እንጃ "

አያለው ግን አላስተውልም ሰማለው ግን አላዳምጥም አለ አካሌ እኔው ጋር እኔው ነኝ እኔው ጋር የሌለውት ።
( ነፍሴ ተነጥቃለች )

አካሌ የሷ ጠበቃ መሆን ዳዳው መቼስ ነፍሴን ሰርቃለች ተብሎ አካልዋ አይቀጣም ።

ዳኛው ጎሮሮዋቸውን ጠርገው " ግራና ቀኙን አይተናል ፍርዱን ለከሰአት ።
አሉ የመዶሻውን ድምፅ በማስከተል ።


ይቀጥላል ክፍል 2 . . . . .

@wegoch
@wegoch
@paappii
ክፍል (2)
የመጨረሻው ክፍል

በተባለው ሰአት ፍርድ ቤት ቀረብን የሷን ፀጋ እነሱ ዘነጉት እንጂ የከሰመን ነፍስ ማፍፍት ድቅድቅን የምትሰልብ ፍፁም ስራ መሆንዋን እረስተዋል ወይንም አያውቁም አካሌ በድን የነበረውን የሷን ፍቅር ነስንሳበት ነፍሴን ፍክት አድርጋ ሙሉ አርጋ መልሳለች ። በነፃ ቢለቅዋት እንኳን ፍርድ ቤቱን ከሳ ካሳ መቀበል ያስፈልጋታል ።

" ለምን? " ቢባል

አማርሽ ብሎ መክሰስ ሳቅሽ ብሎ መውቀስ ምን ሚሉት ፈሊጥ ነው ?

ሰው በፀዳልዋ መቆም አቅቶት ከወደቀ እሷ ምን ታርግ አትራመድ አትናገር አትሳቅ አይባል . . .

በዚህ መሀል ከባድ የአላርም ድምፅ ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ አሻግሬ ሰአቱን ሳይ ሁለት ሰአት ከሀያ ደቂቃ ይላል ድንግጥ አልኩ ከህልም ችሎት ወደ መኝታዬ ምድር ስመጣ ።

አምስት ሚስኮልና አንድ መልዕክት አለህ ይላል ስልኬን ድጋሚ ሳበራው "ሶስት ሰአት ላይ የተለመደው ካፌ ጠብቅሀለው"
ይላል የተላከው መልዕክት ። የህልሜን አለም ለመንገር ወደምንገናኝበት ካፌ ነፍሴን ጥዬ እሮጥኩ . . . . .
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
@kalidakelu

@wegoch
@wegoch
@paappii
በመፅሀፍ የሚገኝ ደስታ
ብሄራዊ ትያትር.. . Tommorow afternoon local 7.00
ለሰው መድሀኒቱ ሰው ነው ። መነሻችን የሰው ማህፀን መድረሻችን የሰውነት ስሪት ቀመር ነው።
ከሰው ማህፀን ተፈጥረን በሰውነት አፈር ውስጥ እንደበቃለን።
መድሀኒቴ እናንተ ናችሁ ... ስፅፍ የምናቤ ግብዓት ናችሁ ።
የፅሁፌ ትርፍ ገንዘብ አይደለም...አንድ መፅሀፍ ፅፈህ.. .ሀገር ምድሩ እስኪታዘብህ ፕሮሞት አድርገህ.. . ለሳምንት ምሽቶች መዝናኛ የሚሆን ትርፍ እንኳ አታገኝበትም።
ብዙ ደራሲዎች ለምን ትፅፋላችሁ ብትሏቸው መልሳቸው ምንም ነው። ስነ ፅሁፍ ልክፍት ነው... እያንዳንዱን ስራህን ቅርፅ አስይዘህ መሬት ስታወርደው አዲስ ፍጥረት ፕላኔቷ ላይ ያመጣህ ያህል ይሰማሀል።
ትርፍህ የሰው ሀሴት ነው። ለምሳሌ ሸግዬ ሸጊቱን ያነበቡ ሰዎች ሲደውሉ አንተ በፈጠርካቸው ታሪኮች ላይ በስሜትና ደስታ ሲያጫውቱህ የሚሰማህን እርካታ ብዬ ልገልፅልህ እችላለሁ?
...
ሸግዬዋን ነገ እንመርቃታለን። ሁላችሁንም ጋብዣችኋለሁ...ለብዙዎች በስልክም በቴክስትም እንዳትቀሩ ብያለሁ። ሌሎቻችሁም በስጋ ስራ ተወጥሬ ዘንግቻችሁ ቢሆን ይሄን ተረድታችሁ ነገ ተገኙልኝ።
ስትገኙ ከእናንተ የሚጠበቀው ፅሞናችሁን ይዛችሁ መምጣት ብቻ ነው።
ትኬትም ገንዘብም አልሻም...እናንተ መጥታችሁ በታላላቅ ገጣምያን እና ደራሲያን ስራዎች ተደስታችሁ መሄዳችሁ ብቻ ለኔ ክብር ነው ።
አክብሬ ጋብዣችኋለሁ።
አደራ !!
#ሚካኤል አስጨናቂ
የቤቱን ባለቤት እየናቁ እንዴት ቤቱን መውደድ ይቻላል ?

(ካሊድ አቅሉ )

ዊንታ ድምፅዋን ደመቅ አድርጋ አለምን በእስዋ ልክ ፈታች

" በአንድ ሳንቲም ሰውና አንበስ መሆን አንበሳው ካልቀና ወደ ሰው . . . "

ስንቴ ምንኖር መሰላት ? የምር አሁን ካልኖርን መች እውነተኛ ኑሮን እናጣጥማለን ህይወት ትርጉምዋ ማይገባን ደስታን ከገንዘብ ጋር በማስተሳሰራችን ይመስለኛል ያለመርካት እሳቤን ስናሳድድ በሞት እንቅፋት ተደፍተን መቅረት ። የውሸት ኖሮ የእውነት ሞት ።

መለስ አልኩና " እኔ ምልሽ ዊንታ መች ለማግባት ታስቢያለሽ ? "

" እእ ሀብታም ባል ብቻ ይምጣ መልኩ ውስጣዊ ውበቱ አልልም ጥልቅ ነው ምለው " ፈጣሪ እራሱ ሲጣንን ወደ ገሀነም ሲወረውር እንዲ አልፈጠነም ።

መዋደድን ፍቅርን ስብዕናን ህሊናን በሲኖትራክ ስትወጣባቸው ዳር ሆኚ አይኔን ይዤ የምታዘብ ይመስል ቀፈፈኝ ። ፍቅር እኮ ይቀድማል ትዳርን ያሳደገው መዋደድ አይደል ? የቤቱን ባለቤት እየናቁ ቤቱም መናቅ ይቻላል ?

" ያርግልሽ ባይባልም ለሀብት ያለሽ ቦታ ትዳርን ሳይሆን ሀብትን ምታገቢው ያስመስልብሻል ሀብታም ባል ቤት ያለው ድርጅት ያለው ዱባይ ሚያዝናና. . . "

" ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም ያሉት ሁለት ለተራራቁ ዛፎች ነው ጥንድ የቆሙ ዛፎች ከሆኑ እግርን አንድ ላይ ገላን አንደኛው ላይ ማሳረፍ ይቻላል ። "

ልቆቆማት እንዳልቻልኩ ተሰማኝ ግን የተሸናፊ ወግ መሀል ላይ አሸናፊ መምሰል ነው ። ለዘብ ብዬ ቀጠልኩ " አትሸወጂ ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት አንድ ሰውነት ሁለት ቦታ መክፈል ከባድ ነው ። ለአንዱ ላይ የሚወጣን ሀይል ሁለት ቦታ ከፍሎ ተንገላቶ ማለፍ ነው ። " መድፍ የሆነ መልስ ልካብኝ እሮኬት መልስ ላኩላት አፍዋን ጥያቄዋን መልስዋን ድማሚት እንዳገኘው ከተማ ብን አለ ። ፍርስራሾችዋ ብቻ ሰው ፊት ያንዣብባሉ አስተሳሰብዋ ብን ብሎ ጠፍቶ መልስ ሳይሰጠኝ አካልዋ በድን ሆኑ ጥላኝ መንገዱን ቁልቁል ተያያዛችው ወደ ታች የሚወርደው ገላዋ የስብዕናዋ ማሳያ ሆኖ ታየኝ የሚወርድ እግር የሚወርድ አይምሮ . . . .

@KALIDakelu

ሼር!!

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ፍቅር ና ጦርነት

ክፍል 1

ጳጉሜ 3 2013 ዓ.ም

ከቀን ወደቀን ቢሻለኝም የክረምቱ ብርድ ህመሜን ጨምሮታል ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለሠው ድጋፍ መንቀሳቀስ ችያለሁ ሠፈር ውስጥ ዞር ዞር ማለት ጀምሬያለሁ ። እንዲያውም ከሞት ያተረፈኝን ለቤቴ ያበቃኝ አምላክን ለማመስገን ወደ ቤተ-ክርስቲያን እየሄድኩ ነው ። ለዚህ እበቃለሁ እግሮቼ እንዲህ መንቀሳቀስ ይችላሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር ከ 2 ወር በላይ ከተቀመጥኩበት ዊልቸር እነሳለሁ እንዳሁኑ እንቀሳቀሳለሁ እንደ ሰው ቆሜ እሄዳለሁ ሚል ምንም ግምት አልነበረኝም ታዲያ እኔ አምላኬን ያላመሰገንኩ ማን ሊያመሰግን ከሞት መንጋጋ ያተረፈኝ ያላመሰገንኩ ማን ሊያመሰግን ማንም ለዛነው ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ ለማመስገን ማሰቤ።

ዝናቡ ሚያቆም ባይሆንም ለብርዱ ልብስ ደራርቤ ከቤት ወጣሁ ፧ ከቤታችን በቅርብ የሚገኘው መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን ነው ። ከልጅነቴ ጀምሮ ያደኩት ቤተክርስቲያን ስለሆነ ስምልም ረሱ መድዬን ብዬ ነው ለቤታችን ቅርብ ነው 20ደቂቃ ቢፈጅ ነው አሁን ግን ለኔ ከ 45_60 ደቂቃ ሳይፈጅብኝ አይቀርም እራሴን ጠንክር በል ብዬ ጉዞዬን ጀመርኩ ።

መንገድ ላይ ብዙ ሰው ጋር አልተገናኘሁም በዝናቡ ና ገና ጥዋት በመሆኑ ምክንያት ግን ያገኘሁት ሰው ሁሉ ከንፈራቸውን እየመጠጡ ነው ሚያልፉት ሀዘኔታ ይሁን መገረም ባይገባኝም ምንም ምቾት አልሰጠኝም ። ወደ ቤተክርስቲያን እየደረስኩ ስመጣ ሠውነቴ በጣም ዛለ ድካም ተሰማኝ እንደምንም ብዬ የ ቤተክርስቲያኑን መግቢያ ተሳልሜ ለምእመናን ወደ ተሰራው መጠለያ ገብቼ አረፍኩኝ ። የተጎዳችው እግሬ ህመም መቋቋም አቃተኝ ስልኬን አውጥቼ ስመለከት ከቤት ከተነሳው 50 ደቂቃ ሆኖኛል በጣም አዘንኩ 50 ኪ/ሜ በምጓዝበት እግሬ 50 ደቂቃ ተጓዝኩ ብሎ እንዲህ መሆኑ አናደደኝ አይሰው መሆን ከንቱ በተፈጥሮ ተገረምኩኝ ግን ምንም ቢሆን መጠንከር እንዳለብኝ ለራሴ ነገርኩት ። በመጠለያው ትንሽ እንደቆየው ያላስተዋልኩትን ነገር አስተዋልኩ ያለሁበት በሴቶች ቦታ ነበር ድካሜ ሲጠፋልኝ ቦታ ለመቀየር ከተቀመጥኩበት ስነሳ እግሬ አቅም አቶ ወደድኩኝ ። ከየት መጣች ያልተባለች ልጅ "እኔን " ብላ እጇን ዘረጋችልኝ እኔ ማየው አፍዞኛል መላክ ያየው መሰለኝ ክንፉን የዘረጋ ግን ሴት መላክ ከየት መቶ ፤ ደሞ ማነው መላክን ወንድ ያረገው ብቻ ግራ ገባኝ አምላክ ለኔ የላካት መሰለኝ ባይኔ አካሏን ስቃኘው እንደኔው ፍጡር ናት ፈራሽ ገላ ነው የያዘችው በዛችው ደቂቃ አዘንኩላት ከገነት ተባራ ምድር ላይ ምደክም እንጂ እንደ ሰው የሁለት ሠዎች ውጤት አትመስልም ግን ምን መድረግ ይቻላል እንደኔው ፍጡር ናት ........

ክፍል 2 ይቀጥላል

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፍቅርና ጦርነት

ክፍል 2

"ወንድም ተጎዳህ እንዴ.. ወንድም " ብላ እጄን ስትይዘው ከሀሳቤ ነቃው እንደምንም በሷ እገዛ አመቺ ቦታ ተቀመጥኩኝ እግሬን እንደ ፈለኩኝ ማንቀሳቀስ እንደማልችል ስትረዳ " እግርህን ሚያምህ ከሆነ ለምን መደገፊያ ክራንች ወይም ሚደግፍህ ሰው ሳትይዝ መጣህ " እንዳ ቀረቀረች ጠየቀችኝ "አይ ተሽሎኝ ነበር እኮ ትንሽ ስንቀሳቀስ ነው ያመመኝ " የእግሬ ህመሙ ሲብስብኝ በእጄ ጠበቅ አርጌ ያዝኩት "አይዞህ አምላክ ይርዳህ" ብላ ለመሄድ ስትዘጋጅ መንቀሳቀስ እንደማልችል ና ከሷውጭ ሊረዳኝ ሚችል ሰው እንደ ሌለ የቤተክርስቲያኑ መውጫ ደረጃውን ለመውጣት እንድትረዳኝ ስጠይቃት እሺታዋን ገልጻልኝ አስከምረጋጋ አብራኝ ቁጭ አለች ።

ለደቂቃዎች ሳናወራ ብንቆይም አለባበሷን አይቼ በዚህ በብርድ እንዲህ መልበሷን ና ቤተክርስቲያን ውስጥ መሆኑ ገርሞኝ "ይህ አለባበስ ለቤተክርስቲያን ይፈቀዳል" ብዬጠየኳት እንዳቀረቀረች ፀጉሯን እያስተካከለች "ሰው ነው እንጂ አምላክ ልብስን አያይም የልቤን ችግር ደሞ እሱ ያቃል " ብላ ለይስሙላ ፈገግ አለች ፈገግታዋ ውስጥ ሀዘን አለው ፈገግታዋ ውስጥ መጎዳት አለው ፈገግታዋ ውስጥ ብቸኝነት አለው ።

የለበሰችው ልብስ ስስ የሌሊት ልብስ ሲሆን ሰውነቷን በከፊል ያሳያል ፀጉሯ ፊቷን ካልሸፈንኩ ካልሸፈንኩ ሚል ይመስላል እርዝመቱ መጋረጃ እንጂ ፀጉር አይመስልም እግሮቿ በጭቃ ተበላሽተዋል ውበቷን ግን አልቀነሱትም ትኩር ብዬ ከተመለከትኳት በኋላ እንደበረዳት ገባኝና የለበስኩትን ሹራብ አውልቄ ሰጠኋት ፧ ትንሽ ብትግደረደርም ተቀብላኝ ለበሰችው ሰውነቷ ተፍታታ እንደንጋት ጮራ ፊቷ አበራ "ስምሽ ግን ማነው " ድንገት ጠየኳት ፈገግ ብላ " ፀጋማርያም እባላለሁ " አለችኝ እውነትም የማሪያም ፀጋ በግርምት ላይ ግርምት ጨመረችብኝ አድናቆቴን በሆዴ ደብቄ መሄድ እንደምንችል ነግሬያት ብድግ ስል እሷ ቀድማ ተነስታ ደግፋ አነሳችኝ እጄን ትከሻዋ ላይ አድርጌ መንገዳችን ጀመርን ።

የቤተክርስቲያኑን መውጫ አልፈን ዋና መንገዱ ላይ ስንደርስ ካልቸኳለች ቤቴ ቅርብ ስለሆነ እንድታደርሰኝ ጠየኳት ችግር እንደሌለው ነግራኝ መንገዳችንን ቀጠልን ፤ ቤት እስክንደርስ ስለብዙ ነገር አወራን ። በብዛት ስለራሷ ባትነግረኝም ችግር ውስጥ እንደሆነች ነገረችኝ እኔም ምን ሆኜ እንደተጎዳው ብጠይቀኝም በጦርነት ተጎድቼ እንደሆነ ብነግራት ትፈራለች ብዬ በቀልድ አድርጌ አለፍኩት የተለያዩ ነገሮችን እያነሳን እየተጨዋወትን ቤት ደረስን።

የጊቢውን በር ከፍቼ ወደውስጥ ገባን ቤቱን ከቤተሰብ የወረስኩት እንደሆነና ሁሉንም ክፍሎች ዋናውን ቤት ጨምሮ አከራይቼ እኔ ጥግ ላይ ያለችው ቤት ውስጥ እንደምኖጋ እያስረዳኋት እያለ ስልኬ ጠራ ቤቱ ክፍት እንደሆነና አውርቼ እስክጨርስ ገብታ እንድትጠብቀኝ ነግሬያት ስልክ ማውራት ጀመርኩኝ ። በጣም አስፈላጊ ስልክ ስለነበር ሳላስበው ብዙ ደቂቃ አወራው ስልኩን ጨርሼ ወደቤት ስገባ እንደ ህፃን ልጅ ጥቅልል ብላ ተኝታለች መላክ ይተኛል እንዴ ? ደሞ ማማሯ ውበት ማለት አንቺ ብሎ የተዘፈነው ለሷ ይሁን እንዴ ........

ክፍል 3 ይቀጥላል ......

@wegoch
@wegoch
@paappii
@wegoch
@wegoch
@paappii

#Narrated by Rediet

Written bye Ashenafi melesse
Audio
===ቀልዶች በጃንሆይ ዙሪያ===
አፈንዲ ሙተቂ
--------
እስቲ ዛሬ ደግሞ ልዑል ተፈሪ መኮንን “ግርማዊ ጃንሆይ” ከሆኑ በኋላ የተቀለደባቸውን ቀልዶች እናካፍላችሁ፡፡
------------
ሁለት ሰዎች እየተጨዋወቱ ነው፡፡ አንዱ ጃንሆይን ይወዳል፡፡ አንዱ ጃንሆይን ይጠላል፡፡ ጃንሆይን የሚወደው ሰውዬ “ግርማዊ ጃንሆይ ሺ ዓመት ይንገሡ” አለ፡፡ ጃንሆይን የሚጠላው ሰውዬ በጥፊ ከመታው በኋላ እንዲህ አለው፡፡
“አንተን ብሎ እድሜ ቆራጭ! ግርማዊ ጃንሆይ ለዘላለም ይንገሡ አትልም ነበር?”
------------
ግርማዊ ጃንሆይ የአማኑኤል ሆስፒታልን ሊጎበኙ ሄዱ፡፡ አንዱ ሻል ያለው እብድ እንዳያቸው ተጠጋቸውና “ማን ትባላለህ?” አላቸው፡፡
“ሞአ አንበሳ ዘእም ነገደ ይሁዳ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ነን” አሉት ጃንሆይ፡፡
ይህንን የሰማው እብድ ሳቅ እያለ “ጉድ ነው! እኔንም እብደት ሲጀምረኝ እንዲህ ነበር ያደረገኝ” አላቸው፡፡
(በርሱ ቤት ጃንሆይ ሊታከም የመጣ እብድ መስሎታል)
------------
እነ ኒል አርምስትሮንግ ጨረቃን ረገጡና ዓለም ጉድ አለ፡፡ የዓለም መሪዎች ወደ ፕሬዚዳንት ሊንደን ቢ ጆንሰን የደስታ መልዕክት ማጉረፍ ጀመሩ፡፡ እንደ አጋጣሚ አሜሪካ የነበሩት ቀዳማዊ ኃይሥላሴም እንዲህ አሉ፡፡
“ጨረቃ ላይ በመውጣት የሰራችሁት ስራ ለናንተ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ህዝብም ኩራት ነው፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ ደግሞ ተመራምራችሁ ጸሐይ ላይ እንደምትወጡ መልካሙን ሁሉ እንመኝላችኋን”፡፡
ከጃንሆይ አጠገብ የነበሩት ልጅ ይልማ ዴሬሳ ደነገጡ እና “ጃንሆይ ጸሐይ ላይ መውጣት አይቻልም እኮ” አሏቸው፡፡ ጃንሆይም በስጨት ብለው “አንተ ደግሞ አቃቂር ታበዛለህ! እኛ መናገር እንጂ ስለሌላው ምን አገባን? ቢፈልጉ ጸሐይቱ እንዳታቃጥላቸው ማታ ማታ ይጓዙና ይውጡ!”
------------
የዩጎዝላቪያው ማርሻል ቲቶ ኢትዮጵያን ጎብኝተው ካበቁ በኋላ ለጃንሆይ “ሀገራችሁ ጥሩ ናት። ግን ሰዎቻችሁ በየጎዳናው ይሸናሉ” አሏቸው። በሌላ ጊዜ ጃንሆይ ዩጎዝላቪያን እየገበኙ ሳለ በጎዳና ላይ የሚሸና ሰው አዩ። በዚህን ጊዜም ወደ ሰውዬው እያመለከቱ ለማርሻል ቲቶ “ተመልከት! ያንተም ሰዎች በመንገድ ላይ ይሸናሉ” አሏቸው። ቲቶ በጣም ተናደዱ። ወታደሮችን ጠርተው “እዚያ ወዲያ የሚሸናውን ሰውዬ ይዛችሁ ወደኔ አምጡት” በማለት አዘዟቸው። ወታደሮቹ ሰውዬው አጠገብ ከደረሱ በኋላ ባዶ እጃቸውን ተመለሱ።ቲቶም “ለምን አልያዛችሁትም?” አሉ።
“ይቅርታ ማርሻል የዲፕሎማቲክ መብቱን መድፈር አልቻልንም”
“የምን የዲፕሎማቲክ መብት?”
“ሰውዬው አምባሳደር ነው”
“የየት ሀገር አምባሳደር?”
“የኢትዮጵያ”
---------
ጃንሆይ እና ጸሓፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ከተማ ወርደው መዝናናት አማራቸውና ተያይዘው ወጡ። የተቻለውን ያህል ጥንቃቄ እያደረጉ ሲዝናኑ ከቆዩ በኋላ መሸ። በፒያሳ በኩል ወደ ቤተ መንግሥት በመመለስ ላይ ሳሉ ሲኒማ ኢትዮጵያ ደረሱ። “እስቲ እዚህም ገብተን ትንሽ እንይ” አሉና ወደ ሲኒማው ገብተው ከተመልካቾች ተርታ ተቀመጡ።
በዚያ ዘመን ቴሌቭዥን በየቤቱ ስለሌለ ህዝቡ ወደ ሲኒማ ሄዶ ነው ዜና የሚከታተለው። በዜና ላይ ጃንሆይ የታዩ እንደሆነ ደግሞ ማጨብጨብ የዘመኑ ደንብ ነው። ታዲያ ዜና አንባቢው “ግርማዊ ጃንሆይ ዛሬ የጃፓን አምባሳደርን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ” አለና ዜናውን በምስል አቀረበው። ይሄኔ በአዳራሹ የነበረው ጠቅላላ ህዝብ አጨበጨበ። አሁንም ሌላ የጃንሆይ ዜና ቀረበ። ህዝቡም አጨበጨበ። ሌላ የጃንሆይ ዜና ተከተለ። ህዝቡ አፍታ በአፍታ ማጨብጨቡን ቀጠለ። ጃንሆይና ጸሓፌ ትዕዛዝ ግን አላጨበጨቡም። ይህንን ያየ አንድ ጎልማሳ ተመልካች ወደ ጃንሆይ ተጠግቶ “ሽሜ! ጉድ ሳይፈላብሽ ብታጨበጭቢ ይሻልሻል” አላቸው።
---------

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፍቅርና ጦርነት

ክፍል 3

እናት ልጇ ተኝቶ በስስት እንደምትመለከተው እኔም ፀጋን በስስት አይን አይኗን እያየኋት በአምላክ አፈጣጠር እየተገረምኩ ቀኑም ሳላስበው መሸ .... ደመናማ ቀን ስለነበር መምሸቱን ያወኩት ሁሌም እራት ምታመጣልኝ ለምለም ስትመጣ ነው ። ለምለም እናቴ ከመሞቷ በፊት የቅርብ ጓደኛዎ ነበረች እናቴ በእድሜ ብትበልጣትም ለምለም በሂወት ብዙ ያየች ሴት ናት በኢትዮ_ኤርትራ ጦርነት ምክንያት ኤርትራውያን ወደሀገራቸው ሲባረሩ እናቴ ናት ጓደኛዬ የትም አትሄድም ብላ መታወቂያ አውጥታ ያስቀረቻት ፤ አንዳንዴ እናቴ ትዝ ስትላት ....
"ጦርነት መጥፎ አባረረኝ ፍቅር ደጉ አስቀረኝ " ትላለች

ከህክምና ከመጣሁ ጀምሮ ከለምለም ውጪ ሴት ቤቴ ገብቶ ስለማያውቅ እንደ ሌላ ቀን ሳትቀልድ ሳትጫወት
"በል እኔ ልሂድ ስለዚህ ነገር ግን ነገ እናወራለን " ብላ ድምጽ ሳታሰማ ሄደች ።

በለምለም ድርጊት እየተገረምኩ ፀጋን ከእንቅልፏ ልቀሰቅሳ አስቤ እንዴት እደምቀሰቅሳት ግራ ገባኝ ስቀሰቅሳት ልደነግጥ ስለምችል በራሷ ጊዜ እንድትነቃ የTV ድምጽ ጨመርኩት ፤ ትንሽ ደቂቃ ቆይታ ነቃች ፊቷን የሸፈኑትን ፀጉሯን እያስተካከለች ደንግጣ ተነሳች ...
"መሸ እንዴ"
በመስኳት ውጪ ውጪ እያየች
" አይዞሽ መኪና ጠርቼ እስከ ምትሄጅበት እሸኝሻለው "
ስላት ፊቷ ተቀያየረ ቀስ ብላ ተቀመጠች ምን እንደሆነች ብጠይቃትም መልስ አልሰጠችኝም ። ለደቂቃዎች ዝምታ ሰፈነ እዚህ እንድታድር ብፈልግም እንዴት ልጠይቃት ፈራው በኋላ ሌላ ነገር ያሰብኩኝ ቢመስላትስ አይ ይቅርብኝ ብዬ ዝም አልኩ ። በዛች ቅፅበት አምላኬ ፀሎቴን የሰማ መሰለኝ ክረምትን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደድኩ በስራዬ ምክንያት ክረምት ደስ አይለኝም ወታደር መጠለያ ስለሌለን ዝናብ አንወድም እንደውም አንድ የውጪ ዜጋ የኢትዮጵያን ወታደር ካየ በኋላ .."የኢትዮጵያ ወታደር ዝናብ ሲዘንብ ወደቤት ጥይት ሲዘንብ ወደ ሜዳ " ያለው እስካሁን አረሳውም ።

አሁን ግን አስፈላጊ ስዓት የሰማይ ቀዳዳዋች ተከፍተው ሀይለኛ ዝናብ ዘነበ በዚ ዝናብ እሄዳለሁ እንደማትል ገመትኩ ።

ጉሮሮዬን እየጠረኩኝ " ፀጋ ለምን እዚህ አታድሪም " ልቤ እየመታ ጠየኳት ካቀረቀረችበት ቀስብላ ቀና ብላ " አይ ላስቸግርህ አልፈልግም ባይሆን ዣንጥላ አለህ " አለች በሚያምር ድምጿ እንኳን ሰውን እንስሳትን በሚያራራ ቃና እኔን ግን ልቤን አደነደነው ...." የለኝም ያለሽ አማራጭ እዚህ ማደር ነው ደሞዝናብ ነው በዛላይ መሽቷል አንቺ የዛን ያህል ረድተሽኝ አንቺን በዚህ ጨለማ ለጅብ አልሰጥሽም ባይሆን ነይ እራት እንብላ " ሳላስበው ስሜታዊ ሆንኩኝ የበፊቱ መቶ አለቃ አብርሃ ወኔ መጣብኝ

ሳላስበው የተቆጣኋት መሰለኝ ግን በዚህ ጊዜ ያለኝ አማራጭ እሷን እዚህ ማቆየት ብቻ ነው ፤ በማላቀው መንገድ ልቤ እንዳትለቃት እንዳትለቃት ይለኛል ልብን መስማት አደጋ ቢኖረውም ምንም አማራጭ የለኝም ፤ በረጅሙ ተንፍሳ ምንም አማራጭ እንደሌላት እና ባረኩላት ነገር አመስግና እራታችንን መብላት ጀመርን እርቧት እንደነበር ለመረዳት አልተቸገርኩም ከኔ ጋር እራሱ ከተገናኘን 11 ስዓታት ተቆጥረዋል ከዛ በፊት ምግብ ሳትበላ ምንያህል እንደቆየች አምላክ ብቻ ነው ሚያቀው ፍሪጅ ላይ ከነበረ ምግብ ጨምሬ ተመስገን እስክትል ተመገበች ።

የበላንበትን አነሳስታ ስልክ እንዳስደውላት ጠየቀችኝ ስልኬን ሰጥቻት በረንዳ ላይ ሆና ማዋራት ጀመረች ባላሰብኩት መንገድ ንግግሯ ሳበኝ የደወለችው ለሴት ጓደኛዎ ነበር እንዳልሰማት በትግርኛ ነበር ያዋራቻት ።

እድሜ ለእናቴ ጓደኛ ለምለም ና አብዛኛውን የውትድርና ጊዜዬን ያሳለፍኩት ትግራይ ስለነበር ትግርኛ እችላለሁ ። አውርታ ስትጨርስ መኝታዋን አዘጋጅታ ተኛች እኔ ግን እንቅልፍ እንቢ አለኝ እንዴት ይህን ነገር ሰምቼ እንቅልፌ ይምጣ የአንድ ሰው ሂወት እየተበላሸ እያየው እናት ና አባት ልጅ እየሸጡ ፣ በቤተሰብ ችግር ልጅ ሲበደል እያየው እንዴት ብዬ እቺን ነብስ እንዴት እንደማተርፍ እያሰብኩ እንቅለፍ ወሰደኝ ......


ክፍል 4 ይቀጥላል

@wegoch
@wegoch
@paappii

@takitafu79
( የከሰመ - ፍቅር )
.
.
.
ካሊድ አቅሉ

ሳቅዋ ለዝብዋል ለወጉ ጥርሶችዋን ታሳያለች እንጂ እንዳረጀ አንበሳ ሞገሱ እንጂ መጉላት አይታይበትም ። " አንቺ ግን እንዴት ነሽ ሰው አይናፍቅሽማ ?" አልኳት ሀይል ባነሰው መነጠቁን ባወቀ ደካማ ድምፀት ። " አለው አረ ትንሽ እኮ busy ሆኜ . . . ." አልጨረሰችውም ተውጠው የቀሩ በጉጉት ምጠብቃቸው ቃላት ነበሩ ናፍቃኛለች ማያት በ ስስት ነው ግን ነፍስ አልባ እይታ ። የሚወዱት አካል አለ ብለው ላይሰረዝ የተፃፈ ቀስ በቀስ አሸዋ ላይ እንደተፃፈ ቃል ንፋስ እብስ ሲያረገው ታየኝ ማዘን ምንድነው ተስፋ መቁረጥስ . . . . በልብ መሰበር ከኔ ውጪ መልስ ይኖረዋል ብዬ ለማሰብ ይከብደኛል ። ዘመን ያከለብኝ ግን ገለልተኛ ሰው ሲያየው ከ ሶስት ደቂቃ ማይዘል ዝምታ " ቤት እንዴት ናቸው ?" በሚል ቃል ተሰበረ የሩቅ ዘመድ ማወራ እየመሰለኝ " ቤት ደህና ናቸው " ብዬ ነገር ማሳጠር ፈለኩ ፍቅሬን ለመራቅ በጓደኝነት ስም ዳር ዳር ስትሄድ አየዋት ። ወደ ውሃነት የተቀየረ ሻይ አጠገቤ ሞልቶ ይታያል ሁለት ቀን ሳላገኛት ካለፈ የሚቀየር መልኳ እንገናኝ ስላት መቀየሩ ደንቆኛል ። የሚያፈቅሩትን ሰው እንዴት የቅርብ እሩቅ ማረግ ይቻል ይሆን ? ህመሜን የቀነሰች መስልዋት ከ አስረኛ ፎቅ ከምወረውረው እየጎተትኩ ባወርደው ይሻላል ብላ ስቃዬን አበዛችው ። አልታወቃትም " የተፈቃሪ ትልቁ ስህተት ከእሱ አድማስ ባሻገር ጨለማ ነው ብሎ መደምደሙ ነው " " እና እያነበብሽ ነው ?" ለወንድምነት በቀረበ ቅላፄ ሀሳቤን አሻገርኩ . . . " እእ አዎ አንተን እራሱ ለማግኘት ከመምጣቴ በፊት ላይብረሪ ነበርኩ እነ ሳምሪ እራሱ እዛው እየጠበቁኝ ነው " መች ልሂድ የሚል ቃል አለመፈለግ ሚመራው ሚንቀሳቀስ ግኡዝ አካል ከፊቴ ታየኝ ።

" ግን እኮ ወዳታለው ከዘመን አግዝፌ
እሷን እንዳይጠባት ምሽት እየጠበኩ
ጨረቃን አርግፌ " ( አሁንም )

(ምልሰት) ሽምጥ ወሰደኝ ከአካሌ ቀድሞ አፌ ፍቅራችንን እያስታወሰ ጣረሞት ላይ ያለው ፍቅራችን ታየኝ ። ለመግደል ስትፍጨረጨር ለማትረፍ ሚደክመው ገላዬ ድንጋይ ላይ ውሃ እንደሚያፈስ ታወቀኝ ። " በቃ ሂጂያ እንደዛ ከሆነ አልያዝሽ ይቅርታ ከንባብ አቆርጬ ስለጠራሁሽ " የኑዛዝዬ ማሳረጊያ ነበር . . . . . . . . " ችግር የለውም " ፍቅራችን ከመሞቱ በፊት ገዳይዋ ያወጣችው የመጨረሻ ቃል . . . . .






ከፍቅራችን ሙት አመት ብሀላ ድንገት በሰፈራቸው ሳልፍ ግቢው ተከፍቶ ይጨፈራል እርምጃዬን ገታ አድርጌ ለሰከንዳች ለተከፈተው ሙዚቃ ጆሮዬን ለገስኩ . . . . " አትሸኘዋትም ወይ አትሸኘዋትም ወይ መሄድዋ አይደለም ወይ የዛሬ አመት የዛሬ አመት የማሙሽ እናት. . . . . " ሙዚቃው ቀጠለ እኔም ጉዞዬን ቀጠልኩ . . . . . . .

* * *
@wegoch
@wegoch
@paappii
የፈሪሳዊው መንፈስ
°°°°°°°°
አንዲት ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተኮርምቼ፣ የቀኝና ግራ እጄን መዳፍ አላትሜ፣ በአውራ ጣቶቼ ድጋፍ አገጬን አሳርፌ፣ ሽቅብ ወደ ላይ አንጋጥጬ ተቀምጫለሁ፡፡ ዓይኖቼ በጨለማው መሀል የሰማዩን ሰማያት ሰነጣጥቀው ከእግዜር ዙፋን ፊት ዱለውኛል፡፡ አዕምሮዬ ህመሜንና ጉዳቴን በውስጥ ምላሱ ለአምላኬ ያንበለብላል፡፡ ብዙ የለምን ጥያቄዎች ያዘንባል፡፡

"ለምን ይህ በኔ ሆነ? ምን በድዬህ ነው? ለየትኛው ጥፋቴ ነው ይህ ቅጣት? ለምን ነው ምወደውን ማጣው? ምፈልገውን ማላገኘው? ለምን ፍቅሬን ባጭር ቀጨህ? ለምን የዘለዓለም ፍቅሬን ነጠቅከኝ? ፍቅርን በመሀላችን ማስፈንና ማርጋት እንዴት አቃተህ? ለምን ለእኔ ለልጅህ ማሰብ ተሳነህ? ከሀሊ እጆችህ እኔ የምሻውን ለማድረግ ለምን ታቀቡ? ለምን…?"

ጓደኛዬ እሌኒ ‹‹ምነው ብቻህን?›› በሚል ጥያቄ፣ ከማማረር ጥያቄዬ ገትታ፤ ከሰማይ መንበር ወዳለሁበት የድንጋይ ወንበር በቅጽበት መለሰችኝ፡፡
‹‹ብቻዬን አይደለሁም አምላክ ጋር እያወራሁ ነበር፡፡››
‹‹እያወራህ እንኳ አይደለም፤ ያው እንደለመደብህ እያማረርከው እንጂ! … እውነቱን ልንገርህ! ብቻህን ስትሆን እፈራለሁ፡፡ ፈጣሪን እንደጓደኛ እየገላመጥክ ምትወቅሰው ነው ሚመስለኝ…››
‹‹እንደ አባት እወደዋለሁ! እንደ አባት እለምነዋለሁ! እንደ አባት እጠይቀዋለሁ! እርግጥ ነው ጥያቄዬ ምሬትን ስለተሸከመ ወደ ወቀሳነቱ ያጋድላል… ››
‹‹እኮ! እሱ ነው ሚያስፈራኝ፡፡ ወቀሳና ምሬት ታበዛለህ፡፡ ካለህ ነገር ይልቅ የሌለህን፣ ካገኘኸው ይልቅ ያጣኸውን ነው ምታስበው፡፡ ያለህን ነገሮች አይተህ ለማመስገን ሞክረህ ምታውቅ አይመስለኝም፡፡ ሁሌም…!›› ልትናገር ያሰበችውን ከምላሷ እንዳይፈናጠር አቀበችው፡፡ ‹‹ነገ ምወስድህ ቦታዎች አሉ፤ ከዛ ለምስጋና አንደበትህን ታቀናለህ፡፡ አሁን ግባ ወደ ቤት! መሽቷል!!››

በጧት ቀስቅሳ ነጠላ አስለብሳ ቤተ ክርስቲያን ወሰደችኝ፡፡ ፀበል መጠመቂያ ስፍራው ጋር አጋንንት የሚጫወትባቸውና የሚጨፍርባቸው ምስኪን ፍጥረቶች በፀበል እና በፀሎት ኃይል ይለፈልፋሉ፡፡ ሆስፒታል ሂደን ጤና የናፈቃቸው ህሙማንን ጎበኘን፡፡ ወደ ሞት መንገድ እያዘገሙ ከኑረት ጋር በቀጭን ቱቦ የተሳሰሩ ሰዎችን አየን፡፡ በገዛ ወገናቸው ተፈናቅለው፤ ቤትና ሀብታቸውን ትተው በኬንዳ መጠለያ ስር የታጎሩ በርካታ ሰዎችን ቃኘን፡፡ ዘመድና ዞር ብሎ የሚያቸው ያጡ ጎዳና ላይ የተሰጡትንም እየተዘዋወርን ኮመኮምን፡፡

ልክ እንደጨረስን፤ ‹‹ይህን ሁሉ ያሳየሽኝ "ተመስገን" እንድል ነው›› አልኳት፡፡
‹‹አዎ›› ራሷን ላይና ታች ወዘወዘች፡፡
‹‹ይገርማል!››
‹‹ምኑ?›› በግርምት አየችኝ፡፡
‹‹አንድም የፈሪሳዊያን መንፈስ ተጣብቶን መኖሩ!! አንድም በራስ ወዳድነት አጉል መተብተባችን!!››
‹‹እንዴት?››
‹‹እኒህን ሁሉ ስታሳይኝ የዋልሽው የኔን ህመም በእነሱ ስቃይ ፍቄ… እንደፈሪሳዊው፤ "እንደነሱ ስላላደረግከኝ ተመስገን!" እንድል ነው፡፡ ራስ ወዳድ መሆን አልፈልግም፡፡ እንደውም እንኳን ተመስገን ልል… ስለነሱም አንስቼ የባሰ ልወቅሰውና ልጠይቀው ነው ምፈልገው፡፡›› ጥያት ሄድኩ፡፡ ወደ መቀመጫዬ!! ሽቅብ አንጋጥጬ፣ ሰማያትን ሰንጥቄ፣ ብዙ የለምን ጥያቄዎችን አዝዬ፣ ፈጣሪ ዘንድ ልቀርብ!!

#ኤልዳን

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ፍቅርና ጦርነት

ክፍል 4

የማይነጋ ቀን የማያልፍ መከራየለም እንደሚሉት አበው ጨለማ ጊዜውን ለብርሃን ለቀቀ ፀሀይ የክረምቱን ደመና ሰነጣጥቃ ጨረሯን ወደምድር በትናለች ተስፋ ያለው ቀን ይመስላል ፤ ንጋት ላይ የመተኛት ልምድ የለኝም ዛሬም እንደልማዴ በጥዋት ተነስቻለሁ ።

ህመሙ እንዳገረሸበት ሰው ኩርምት ብዬ ቁጭ አልኩኝ ፀጋ ከእንቅልፏ ስትነሳ ያመመኝ እንዲመስላት ገና ካሁኑ እየተዘጋጀው ነው የዛሬውን ቀን አብራኝ እንድታሳልፍ ፈልጊለው ። ስዓት ስመለከት ገና 12:30 ነው ጊዜው አልሄድ አለኝ እንዴት ቀናችንን እንደምናሳልፍ ሳስብ ፀጋም ከእንቅልፏ ነቃች የእግዜር ሰላምታ ሰታኝ ሰውነቷን እያፍታታች መፀዳጃ የት እንደሆነ ጠይቃኝ ሄደች ።

ብዙም አልቆየችም ተመለሳ መታ የተኛችበትን እያነሳሳች እኔ በስስት እያየኋት ውስጤ ማዘን ጀመረ ማጣት ማጣት መሰለኝ ጭራሽ ማንተያይ ቻው ብላ ተለይታኝ በዛው ቀልጣ ምትቀር መሰለኝ ቢቸግረኝ ምነው አምላክ እህቴ ባደረጋት ብዬ ተመኘው አይ የጨነቀው ግራገባኝ እንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ገብቼ አላቅም እንደዚህም ተሰምቶኝ አያውቅም ቤቴን ወደድኩት ፀሀይ እኔ ቤት ብቻ ያለች መሰለኝ አለም ሁሉ ጨለማ የኔ ቤት ብቻ ብርሀን ያለ መሰለኝ እድሜ ለፀጋማርያም የሷ ህይወት ጨልሞ የኔን አበራችው ፤

ድንገት ስራዋን ጨርሳ ወደኔ ስትዞር ግራገባኝ ተደናበርኩኝ ሳስበው የነበረው ያወቀችብኝ መሰለኝ ታማሚዋን እግሬን በእጄ ይዤው ማቃሰት ጀመርኩኝ ያካበድኩት መሰለኝ የዛኔ ስመታ ራሱ እንዲህ ያቃሰትኩ አይመስለኝም ። ፀጋ በፍጥነት መታ " ምነው አመመህ" ብላ ጠየቀችኝ ማቃሰቴን ሳላቆም ምወጋው መርፌ እንዳለኝና ሚወስደኝ ሰው እንደ ሌለ ነገርኳት ፤ አብረን መሄድ እንደምንችል ነግራኝ እሺ ተባብለን መኪና ያለውን አብሮ አደጌን ያሬድን ጠርቼው በሱ መኪና ሄድን ከቤት ጀምሮ ያሬድን እያየሁት ነበር በጣም ተገርሞል ሰረቅ ሰረቅ አርጎ ፀጋን ይመለከታታል እየተገረምኩኝ መኪናውን እንዲያቆም ነግሬው ፀጋን ተከተይኝ ብዬ ወረድኩኝ ፀጋ ምታየው ነገር ግራ አጋብቷታል ከሴቶች ልብስ ቤት ውጪ ህክምና አይታይም እጇን ይዤው ወደአንዱ ሱቅ ገባን ለሻጯ እንድታስወርጣት ነግሪያት እኔ ቁጭ አልኩኝ ። ልብሶች እየለካች ስታሳየኝ ለብቻዬ የውበት ውድድር ( ሞዴሊንግ ) ማይ መሰለኝ የለካችውን የተወሰኑትን ገዝተን ወደመኪናው ተመለስን ።ያሬድ ፀጋን ሲያያት አፉን ከፍቶ ቀረ ፤ መኪና መንዳት እስኪያቅተው ፈዞ ቀረ ፤

አሪፍ ቁርስ ወዳለበት ቤት ወስዶን እሱን ሸኘሁት ፤ ፀጋ ያሬድ ከሄደ በኋላ " ህክምናውስ መርፌ ምትወጋውስ " ብላ ጠየቀችኝ " ታከምኩ እኮ " ብያት ቦታ ይዘን ቁጭ አለን ።

የሰዓታት ፍጥነት ገረሙኝ ምግቡ ከመቼው ማለቁ ፀጋም እኔን ለሁሉ ነገር አመስግናኝ ቻው ብላኝ ለመሄድ መነሳቷ ሁሉም ነገር ፈጠነብኝ ጀርባዋን ሰታኝ ጉዞዋን ጀመረች የተሸናፊነት ስሜት ተሰማኝ አግኝቶ የማጣት ይዞ የመልቀቅ እያንዳንዱ የፀጋ እርምጃ ጆሮዬ ላይ አስተጋባ እራሴን አንድ ጥያቄ ጠየኩት " አግኝቶ ማጣት ያለ ቢሆንም ያጡትን ማግኘት አይቻልም ?" እራሴው ጠያቂ እራሴው መላሽ ሆኜ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ " ፀጋማርያም አስመሳይ ነሽ " አልኳት ድምፄን ከፍ አድርጌ ድምፄን ስትሰማ መንገዷን አቁማ ወደኔ ዞራ አይን አይኔን እያየች "እንዴት " አለች ሲቃ ባለው ድምጽ ዞር ዞር ብዬ ያለንበትን ስመለከት ጥዋት ስለሆነ ከኛ ውጪ ማንም አልነበረም ጉሮሮዬን ጠራርጌ

" ችግር ውስጥ እንደሆንሽ አቃለው ምትሄጅበት አንድም ቦታ የለም ጓደኛሽም ጋር እንዳትሄጂ ባለቤቷ ደስ እንደማይለው ነግራሻለች ቤተሰብ ጋር እንዳትሄጂ አደጋውስጥ መመለስ ነው ታዲያ ይህን እያወቅሽ ምንም ችግር እንደሌለብሽ ቻው ብሎ መሄድ ምን ይሉታል እውነት እውነት እልሻለሁ ስተት ነው የሰራሽው ውፍፍፍፍፍፍ "

በደንብ ተነፈስኩኝ ሆዴ ውስጥ የቀረ ምንም ነገር ያለ አይመስለኝም አሁን ምጠብቀው የሷን ምላሽ ነው አይኔን አይኗ ላይ ተክዬ እሺ የትም አልሄድም እንድትለኝ መጠበቅ ጀመርኩ እሷ ግን
"ይህን ሁሉ እንዴት አወክ " አለችኝ
አይኗ እንባን አዝለዋል ቀስ ብዬ አጠገቧ ሄጄ
" ውሸት ነው " አልኳት ድምፄን ዝቅ አድርጌ ስሜቷን መቆጣጠር አቃታት እንኳን እናቴ ሞታብኝ እንዲያው አልቅስ አልቅስ ይለኛል አለ የመረረው እንባዋን እንዳላየው ፊቷን አዞረች፤

ማልቀሷን አላቆመችም እጇ ሳብ አድርጌ እቅፊ ውስጥ አስገባኋት እንድትፅናና መቀባጠር ጀመርኩ ግን ህመሟን ሚሽሩ አልነበሩም እንዳቀፍኳት ድምፄን ከፍ አድርጌ እግሬን ብዬ አቃሰትኩ ሀዘኗን ረስታ እንባዋን እየጠራረገች " ምነው አመመህ " አለች በእናትነት ርህራሄ ምንም ብትጎዳም የራሷን ረስታ ሰውን ምትረዳ ምናይነት ፍጡር ናት ። " አውቀህ ነው " አለችኝ ዝምታዬን አይታ ፀጥ ስላት ገባትና ህይወት ያለው ፈገግታን ለግሳኝ ና እንቀመጥ አለችኝ ።

በድርጊቴ እየተገረመች

" ምን አይነት ሰውነህ " አለችኝ

"ጠቆር ያልኩ" አልኳት

ጥርሷቿን ለመጀመሪያ ጊዜ አየኋቸው ከምር ሳቀች

" አይ ለሰው ትጨነቃለህ " ብላ ሁሉን እንድነግርህ ትፈልጋለህ አለች ልሰማት እንደምፈልግ ና ልረዳት እንደምፈልግ ነገርዃ
እሺ ብላ በረጅሙ ተንፍሳ

" እንደምታውቀው በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነኝ ችግር ውስጥ የገባሁት ደሞ በኔ ስተት አይደለም በቤተሰቤ እንጂ ሙሉ ስሜ ፀጋማሪያም ኪዳኔ ነው አባቴ በቀድሞ መንግስት ብዙ መጥፎ ስራዎችን ሰርቷ ለመዘርዘር ሚያስጠላ ነው በዚህ ስራው ባገኘው ሀብት ቦሌ ላይ ህንፃዎች አሉት ይህ መጥፎ ስራው ጊዜ ሲያጋልጠው እኔን ልጁን ለባለ ስልጣን ሊድረኝ አስማማኝ ግን ከዚህ ሁሉ ሚያስጠላው ሚያገባኝ ሰውዬ virus በደሙ ያለበት መሆኑ ነው ይህን ሁሉ ቤተሰቦቼ እያወቁ ምንም አልመሰላቸውም ከቤት ከወጣሁ 4 ቀን ሆኖኛል ጓደኛዬ ጋር ለማረፍ ብሞክር ባለቤቷን አስደበደቡት ብቻ በጣም ችግር ውስጥ ነው ያለሁት "

አለችኝ ከቅድሙ አሁን የቀለላት ትመስላለች

" ጥያቄ ልጠይቅ"አልኳት እሺታዋን ገልፃልኝ

" መኖሪያ ቤት ካገኘሽ ስራ ካገኘሽ ሚጠብቅሺ ካገኘሽ ምን ታረጊያለሽ " አልኳት
እየሳቀች " ትቀልዳለህ በዚህ ሁኔታ ውስጥ አምላክ እራሱ እንዲህ አያደርግልኝም " አለች
"ቢገኝስ " አልኳት ቀጠል አድርጊ
" ደስ ይለኛል" አለች አቀርቅራ

"ተነሽ በቃ ካሁን በኋላ አንቺን ማንም ምንም አያደርግሽም እኔ እያለሁ ካሁን በኋላ ማዘን የለም እሺ ፀጋ" አልኳት እጇን ይዜ

"ተው ቃል አትግባ ሰዋቹን አታቃቸውም ምንም ከማረግ አይመለሱም እንድትጎዳ አልፈልግም ይቅርብህ "አለችኝ

ፈገግ ብዬ" እሱን ለኔተይው "ብዬ እጇን ይዤ ተነስተን ወደ ቤት መንገድ ጀመርን ለሀገሬ በውትድርና ጊዜ ቃል ከገባሁት በላይ ለፀጋ ቃል የገባሁት ከበደኝ ምክንያቱም ለሀገሬ የገባሁት ቃል ባፈርስ ከኔ ውጪ ሀገሬን ሚጠብቃት ሞልተዋል ለፀጋ ግን ከኔ ውጭ ማንም የላትም ማንም እኔ ብቻ .....

ክፍል 5..ይቀጥላል

@wegoch
@wegoch
@wegoch

#sem
አንድ ጆሮ
°°°°°°°°°

ከወደ ጥግ አንድ በካፖርት ላይ ካፖርት የጀቦኑ አዛውንት አረቂያቸውን እየተጎነጩ ቀና ብለው ለፈጣሪ ብሶታቸውን ይዘረግፋሉ፡፡ እኔ ካለሁበት ሁኜ ብሶት ካረቄ ጋር እጋታለሁ፡፡
‹‹ምን ነበር ፈጣሪ፣ የሰውን ጆሮ አንድ አርገህ ፈጥረህ ቢሆን ኖሮ፡፡ ያውም መልካሙን ብቻ የሚሰማ፤ መጥፎውን አግዶ የሚያስቀር፡፡ የዚህ ዘመን ትውልድ ጆሮኮ ሁለት የተለያዩና የተራቀቁ ነገሮችን እየሰማ፤ ከመስማቱም አልፎ እያጋጨ ነው፤ ተበጥብጦ ያበጣበጠነ፡፡ በአንዱ ጆሮ ፍቅር፣ በአንዱ ጥላቻ፣ በአንዱ መዝሙር፣ በሌላው ሙዚቃ፣ በአንዱ ዜና፣ በሌላው የመንደር ወሬ እየለቃቀመ፤ እውነቱን ከሀሰት፣ ጭካኔን ከደግነት፣ ጥሩን ከመጥፎ መለየት ሳይሳነው የቀረ አይመስለኝም፡፡…››
‹‹…ለነገሩ የሰው ልጅ ጆሮ በአንዱ እየሰማ በአንዱ ማፍሰስ የጀመረው አሁን አይመስለኝም፡፡ ሄዋን እራሱ ያንተን መራር የትዕዛዝ ቃልና የሰይጣንን አጓጊ ጣፋጭ ቃል ቱ! በጨለማ የጠላታችንን ስም አስጠራኸኝ፡፡››
የጠጡትን የተፉት መስሎኝ መሬቱን ባይ፤ ጠብታ ምራቃቸው ወለሉ ላይ ተለድፋ አየኋት፡፡ አረቂያቸውን ፉት አድርገው፤ ወጋቸውን ለአምላክ ማጫወት ቀጠሉ፡፡
‹‹ይኸውልህ የሁለታችሁ ቃል ውስጧ ጋር ተጋጭቶ በፈጠረው ስህተት፣ ራሷ ተሳስታ አዳምን አሳሳተችው፡፡ የራሳቸው መሳሳት አንሶ ሰዎችን ወደ ስህተት የሚዘፍቁ መናጢዎች የፈለቁት ዛሬ አይደለም፡፡ ያው የዛሬዎቹ በስልጣኔ ዘምነው፣ ስህተታቸውን እያወቁ ትክክል መሆናቸውን አምነው ለማሳመን መጣራቸው ለየት ያደርጋቸው ይሆናል እንጂ…››
‹‹የዋሁ አዳምም ያንተና የእሷን ቃል በሁለት ጆሮው ሰምቶ፤ ተምታቶበትና ተለያይቶበት ትክክለኛውን መምረጥ እስኪሳነው የቀባዘረ ይመስለኛል፡፡ ለነገሩ እኛንም፣ አምነን ያነገስናቸውና ወዳጅ መስለው የቀረቡን ናቸው የስህተት ኮምጣጤያቸውን በሀሰት ሰፍነግ ጨምቀው ያጠጡን፡፡›› ኮምጣጤውን የተጋቱ ይመስል፤ አረቂያቸውን ፊታቸውን አጨፍግገው በጉሮሯቸው ላኩት፡፡
‹‹ይኸው በዚህ ምክንያት አዳም ተሳሳተ፡፡ በመሳሳቱም ከመንግስትህ አባረርከው፡፡ እኛም ይኼው የምንሰማው ወሬ እየተዘበራረቀብን እድሜ ልካችን ከመንግስት ጋር እንደተጣላን ነው፡፡ ይቅርታ! እንደተቀያየምን፡፡ በምን አቅማችን ነው ምንጣላ? እኛ እንደሆን ከትቢያ ያነስን ነን፡፡…››
‹‹ይገርምኃል… ይህ ከሁለት አጽናፍ የሚመጣ ተቃራኒ ሀሳብና ወሬ ሁለት ጆሮ ላለው ፍጡር ጠንቅ እንደሆነ እንግዲህ እዚህ ዘመን ላይ ደርሷል፡፡…›› ካረቂያቸው ተጎነጩ፡፡ እኔም ተጎንጭቼ ጆሮዬን ወደሳቸው ቀሰርኩ፡፡
‹‹ይኼ ትውልድ እኮ አምላኬ… ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም ጀምሮ በጦርነት ለመዝጋት የሚዳዳው፤ ወንድሙን ፊት ለፊት በፍቅር ቃል አሽቆጥቁጦ ዞር ሲልለት በሀሜት ጥርስ የሚቦጫጭቅ፤ ስለፍቅር ሰብኮ ጥላቻን ተግባራዊ ለማድረግ የሚሯሯጥ፤ ተደምሪያለሁ፣ አንድ ሁኛለሁ ሲል ውሎ ዘር እየዘረዘረ ሲያፈናቅል የሚያድር፤ በደምህና በመስቀልህ እንደተዋጀ አምኖ፣ ጧት ፀሎት አድርሶ ማታ ልክ እንደኔ የመጠጥ ዛር ላይ ሰፍሮ አንተን የሚያማርር ነው፡፡…››
አረቂያቸውን ከተጎነጩ በኋላ ጥርሳቸውን ብልጭ አድርገው የፌዝ ፈገግታ ለአምላክ እያሳዩ፤ ‹‹ያው እኔ ምጎነጨው ለበጎ ነው፡፡ የዚህ ትውልድ የህሊና ቁርጥማት ወደኔ እንዳይተላለፍ አስታግስበትና እረሳበት ዘንድ፡፡›› ሲሉ ማስተባበያ ሰጡ፡፡ ለካ እንዲህም ራስን ማሸሽ ይቻላል ብዬ፤ ፈገግ አልኩ፡፡
‹‹ይኼውልህ ይኼ ትውልድ… ሀገር ኖሮት ሀገሩን ሚያሳድግበትና ሚያስጠራበት አቅም ያጣ፤ ወንድም ኖሮት ወንድሙን የሚያከብርበትና ሚያፈቅርበት ልብ የተነፈገው፤ ቤት ኖሮት ቤት ገብቶ እንዳያርፍ የሰላም ሁኔታ ያሰጋው፤ እውቀት ኖሮት በተማረበት እንዳይሰራ የዘመድ ሰንሰለት ያማረረው፤ በቃ ምን ልበልህ እምነት ኖሮት እምነቱን የሚያምንበት እምነት ያልታደለው ነው፡፡ ግራ ገባኃ!? እኔም ግራ እንደገባኝ ነው፡፡›› እጃቸው መወዛገባቸውን እንዲያሳይ አወናጨፉት፡፡
‹‹አምላኬ ይኼ ትውልድ እኮ የመስማት ችግር የለበትም፤ የመለየት እንጂ፡፡ የሚሰማው የተለያየና ብዙ ሆኖበት መምረጥ ነው የተሳነው፡፡ የሀሰት ፍርድና የእውነት ሰነድን አግባብቶ ሰላማችንን የሚያደፈርስ፤ በጥቂት ሰዎች ልቦና ያደረ የሰይጣን ቁራጭ የሆነ ብትንታኝ ሀሳብ አለ፡፡ ያው አንተ በጥበብህ በረቀቀ መንገድ ብትንትኑን ካላወጣኸው እጇን ወዳንተ ስትዘረጋ የኖረች ሀገራችን፤ እጇን ወደ ኋላ ተጠርንፋ አይንህ እያየ በሀሳዊያን ፍርድ ከፍርድ ቀንህ በፊት የምትጠፋ እየመሰለኝ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ስልህ!… አሃሃ! በስሜ አትማሉ ብለህ ነበር ለካ፡፡ ይቅርታ አምላኬ! በእኔም አትፈርድ! እንዲህ የምቀባጥረው እኮ እንደዚህ ዘመን ትውልድ እምነቴን የማሳርፍበትና የማምንበት እምነት ከውስጤ ተኖ ሄዶብኝ ነው፡፡ እስቲ በረቀቀ ጥበብህ መልስልኝ›› እጃቸውን አንከርፍፈው ወጉን ወደ ልመና ቀየሩት፡፡
‹‹ለትውልዱም ቀናውን ብቻ የሚሰማ አንድ ጆሮ ስጠው፡፡ ወይም…›› መጠጣቸውን ሊጎነጩ ብርጭቋቸውን ብድግ ሲያደርጉ፤ ይህ ፀሎታቸው ፀድቆ እዚሁ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት አፈትልኬ ወጣሁ፡፡
‹‹ወይም እውነቱን ከሀሰት፣ ጥሩውን ከመጥፎ መለየት የሚያስችል አዕምሮ አድለው፡፡›› ንግግራቸው በሁለቱም ጆሮዬ ጥልቅ ሲል ታወቀኝ፡፡ ተመስገን!! ሁለቱም ጆሮዎቼ ይሰማሉ፡፡


#ኤልዳን

@wegoch
@wegoch
@paappii
" መንገድ አስጀምረህ አልፈልግም ብሎ መመለስ ቃል አባይ አያደርግህም ሞት ነው ሚለየን ብለህ መኖር ሊለየን ?"

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
ካሊድ አቅሉ

አንዳንዶች ለምን አልገደልከኝም ብለው ይቀየሙሀል እንለያይ አልኳት " ለምን? " ብትሉኝ ስለማልበጃት የእኔ ህይወት መንገድ መፍሰሻ ጅማሮ ከእሷ መንገድ ጋር ሆድና ጀርባ ነው ። ለሚያፈቅሩት ደግ ደጉን አይደል ሚመኙት እኔ አጥታ ዛሬን ብታለቅስም ነገና ከነገ ወድያ ማያቆርጥ ሳቅ ከፊትዋ እንዳለ ተረድቻለው ።

"ታድያ እንዴት ተገናኛቹ በዚህ ሁሉ ልዩነት? " ብላቹ መጠየቃቹ አይቀርም ስንገናኝማ ያየነውን ቅዠት በህልም እየፈታን ቁሙ ሚለን አካል አተን በለጋ ጉልበት ዳገቱን ጀመርን በሳቅ ተጀምሮ ዳገቱ መሀል ስንደርስ መጀመሪያ ያልሰበሰብነው ሀይል ከየት ይምጣ ድካም ሲመጣ ጣት መጠቋቆም ተጀመረ . . .


ፍቅር ግን ይህን እንድናስተውል ፋታ አይሰጥም ቅርብ ቅርብን ብቻ ይገልጥልናል ። ማስታገሻ መድሀኒት ሳይሆን ነቃይ መድሃኒት እንደሰጠዋት አምናለው ። ሚያሽል መድሃኒት ደግሞ ብዙ ባህሪ ያሳያል ፊት ያሳብጣል ከቀናት ብሀላ ጤነኛ ሰው ያረጋል ። እንባዋ መንታ መንታ ይወርዳል ለሚያየን አልቃሽና አስለቃሽ እንመስላለን እኔን ልብ እንባ ግን ማን አየው ? አፌ መልስ ከሚሰጣት ግዜ በተግባር ሚያሳያትን ለመረዳት ይቀላል ።

" መንገድ አስጀምረህ አልፈልግም ብሎ መመለስ ቃል አባይ አያረግህም ሞት ነው ሚለየን ብለህ መኖር ሊለየን ? "

ላስረዳት ብዙ አልጣርኩም " ጠጣር እውነት መልኩን እስኪገልጥ ብዙ ጭጋግ ያልፋል "

ከፍቅር በላይ ብዙ ነገር ለየን " እኮ ምን?" አትሉኝም

" ሀይማኖት " ለየን . . .

አንድ ቤት ሁለት መንግስት አይነግስም እኔና እሷም ሁለት እውነታ ይዘን አንድ ትልቅ ተ ቋም ውስጥ አንገባም እንደዛ ካረግንማ ከሚያስማማን ሚለየን ገዘፈ ማለት ነው ። የሚታይ ሀዘን እኔን ባይ አያጣም በአፅናኝ ብዛት ይበረታል ።የእኔስ ሀዘን የስውር ስፌቱ ግድ የለም ይሁን እሷ ተፅናንታ ስትስቅ ካየው እሷን መታደጌ ነው የኔ የዘላለም ደስታ ።

ሶፍት አቀበልኳት ተቀብላኝ እንባዋን ስትጠርግ መውደድዋም አብሮ እየወጣ እንደሆነ ሲቃዋ ነገረኝ የቀላ አይን መንጣቱ አልነጋ ያለጭጋግ በብርሃን መተካቱ አይቀር . . . .

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
@wegoch
@wegoch
@paappii
ብዙ የሀበሻ ወንድ በባህሪው ጦረኛ ነው። ተናካሽ ነው ። ሌላው ቢቀርና ጦር ሜዳ ባይዘምት እንኳ የራሱን ጦርነት ይፈጠራል።
ግሮሰሪ ኳስ እያየ ጠርሙስ ይወራወራል...የሞተር ውድድር ይገጥማል.. .ክንዱን እንደሱ ካለ ወንድ ጋር አጨባብጦ ጠረጴዛ ላይ ይታገላል.. . ።
በተለይ ገጠር ያሉ አባቶች ወንድ ልጅ ሲወልዱ ከልጅነቱ ባሻገር ጋሻ እና መከታ የመሆን ግዴታ ስላለበት በጀብድ ታሪኮች እና ተረቶች ልጃቸውን ሞልተውት ያሳድጉታል ።
ለምሳሌ የኔ አባት ልጅ ሆኜ ደፋር እንድሆን ስለሚፈልግ በምሽት ሽንቴ መጣ ስለው አቅራቢያ ፖፖ እያለ እንኳ ወደ አስፈሪው ጓሮ ያደርሰኝና ጥሎኝ ይመለስ ነበር ። ብዙ ጊዜ ለማለት ይቻላል ከጓሮዋችን የበቀለው ቀን በኮባነቱ የማውቀው ግንድ ሁሉ ሳይቀር ክንፍ ያበቀለ አውሬ መስሎኝ ብርርርር ብዬ ቤት እገባለሁ ። ተንደርድሬ እንደመጣሁ በራችን ስር ስደርስ ግን ያልፈራሁ የመምሰል ግዴታ ነበረብኝ ።
አንድ ቀን እንዲሁ አባዬ ጓሮ ጣለኝና ተደብቆ እኔን መከታተል ጀመረ ።
ብዙ ጊዜ ቡሪ የሚባል አጭር ጎረቤታችንን እንደምፈራው ከሁኔታዬ ይረዳ ነበር ።
ቡሪ ሽማግሌ ነው...በዛ ላይ አጭር ነው...ፂሙና ከአናቱ ላይ ጣል የሚያደርጋት ኮፍያ ጎደሎ ሰይጣን የሚመስል ገፅታ አላብሶታል ። እሱም እንደምፈራው ስለሚያውቅ አይወደኝም ። መንገድ ላይ ስሄድ እሱን ካየሁት ቀነኒሳ ነኝ። ዱካዬ አይገኝም ።
አንዳንዴ ባላሰብኩበት ቅፅበት ከኋላዬ ጎሸም ያደርገኛም። ዘወትር ካፉ የጫት ቅጠል አይጠፋም ። ዞር ስል ይገለፍጣል...አፉን ሳየው የገሀነም በር ተከፍቶ ሊሰለቅጠኝ ያሰፈሰፈ ስለሚመስለኝ እጄ ላይ የያዝኩትን ጥዬ እሸመጥጣለሁ። እሱን በማየት ብቻ ከጄ የወደቁ የአቡወለድ ብስኩቶችን ብዛት ሳስበው ዛሬም ድረስ ትልቅ ሆኜ እንኳ ይቆጩኛል።
ሽንቴን ጩርርርርርር እያደረኩ ወደ ነ ቡሪ ግቢ አሻግሬ አየሁ ።
አባዬ ተደብቆ ሁኔታዬን ይቃኛል ። ደግሞ ለክፋቱ ለዛን ቀን ቡሪ ሰክሮ ሲለፋደድ ድምፁን ሰማሁት።
መሽኛ ብዕሬን ወደ ሱሪዬ ሰገባ ዶልኩኝና እንደ እብድ እየጮህኩ ቤት ገባሁ ። በር ጋር መረጋጋት የለ ... ደፋር መምሰል የለ ... እናቴ ቡና የምታፈላበት ረከቦት ስር ከምኔው እንደደረስኩ ዛሬም ድረስ ፍጥነቱን ሳይንቲስቶች ለመገመት የሚችሉ አይመስለኝም።
ምን ልበላችሁ?
ባጭሩ ጋሽዬ አበደ ። ከእናቴ እግር ስር መንጭቆ አውጥቶ በቀበቶ ለጠለጠኝ። "የአስጨናቂ ልጅ ሆነህ የምን እንደ ሴት ሰፈርን በጩኸት መቀወጥ ነው ?" ብሎ ደህና አድርጎ አንቆራጠጠኝ ።
የልጅነት ጊዜያቶቼ በብዙ ፍቅርና ትራጄዲ የተሞሉ ናቸው ። ከአባዬ ጋር ልዝናና ስወጣ ሚሪንዳና ብስኩቴን ከላፍኩኝ በኋላ ወደ ሜዳ ይወስደኝና ከእኩያዎቼ ጋር ትግል ወይ ኳስ ያጋጥመኛል።
ብዙ ጊዜ ትግል የምጋጠመው ከቤቢ ጋር ነው...እሱ ደግሞ ደርሶ ወተት እየጠጣ ያደገ ልጅ ይሄንን ይመስላል ተብሎ ማስታወቂያ የሚሰራለት ድንቡጭ ያለ ወፍራም ነው።
እንደ ወረቀት አጣጥፎ ያነጥፈኛል...አፍንጫዬን ደም ደም የሚሸት ስሜት ሲሰማኝ ማልቀስ እፈልጋለሁ ።
ጋሽ አስጨንቅ ግን ድጋሚ እንድንታገል ቀጭን ትዕዛዝ ያስተላልፋል ...በሶስተኛው አልያም በአራተኛው ሙከራ ተሳክቶልኝ ታግዬ ካላሸነፍኩ አለቀልኝ!
አንዳንዴ ቤቢን ቀስ ብዬ በጆሮው አናግረዋለሁ ።
"አውቀህ ከወደክልኝ ነገ አስር ሳንቲም እሰጥሀለሁ" ስለው ቀስ ብሎ ከብለል ይልልኛል። ያኔ ታድያ ጋሽዬ ዓለም ዋንጫ እንደበላ አሰልጣኝ እሽኮኮ አድርጎኝ እየጨፈረ ቤት ይገባል።
ዛሬም ድረስ ያ የጀግንነት ስሜት ልቤ ውስጥ ስላለ ፍርሀት አያውቀኝም።
ወንዳወንድ ያደርጋሉ የሚባሉ ነገሮችን እከውናለሁ.. . ካፌ ውስጥ ቁጭ ብሎ በስትሮው ጁስ የሚጠጣ ወንድ ስመለከት ራሱ "ግሮሰሪ ሄደህ ድራፍትህን እየላስክ የማትዝናናው ምናባህ ነው ?" ብለህ ነርተው ነርተው ይለኛል ።
ይሄ ጥጋቤ ታድያ በቅርቡ ነበር የበረደው ። ወንድ ልጅ እንደ አውራ ዶሮ በጊዜ ገብቶ አልጋው ላይ መሰቀል የለበትም ብዬ ስለማስብ ግዳይ ጥሎ የነብር ቆዳ እንደለበሰ ዠግና ደረቴን ነፍቼ ስንጎማለል በእኩለ ለሊት ሿሿ ለመስራት ከተሰማሩ ዲቻዎች ጋር አይን ላይን ተጋጨው.. . በጆሮ ግንዴ በኩል ኮብልስቶን ሽው ብሎ አለፈ ...(የፑቲን ተዋጊ ጀቶች ይሄን ያህል ፍጥነት ያላቸው አይመስለኝም )
"ሂናቲን ሀንቴ ውሻ "ብሎ አንድ ወጠምሻ ወደኔ አቅጣጫ ተምዘገዘገ.. .አስማት ሆንኩበት ባገኘሁት መታጠፊያ ሾልኬ ተመምኩ ።
ቤቴ ስገባ እያለከለኩ ነበር ...
በጓሮ በር ገብቼ ...
"ሀኒዬ ዛሬ ለትንሽ ተቀልቤ ነበር ። ወንበዴዎች አሯሯጡኝ እኮ!" አልኳት ለሚስቴ ። ሚስቴ ሳሎን ስለነበረች
"አይዞህ ናማህን ጌታዬ" ...የሚል ምላሽ ሰጠችኝ ። ባለቤቴ ቀጠለች...
"ሆ ዛሬ እርማቸውን ቤተሰቦችህ ለእንግድነት ቢመጡ እንደዚህ ተሯሩጠህ እያለከለክ ትመጣ? "
ሳሎን ስደርስ አባቴ ቀበቶ ፈቶ አይገርፈኝ ነገር የልጅ አባት መሆኔ ታውሶት እያጉረመረመ ተመለከትኩት ።
"ወይኔ አስጨንቅ እንደዛሬም አልተዋረድሁ "
ጋሽዬ አንገቱን በሀዘኔታ እየወዘወዘ ነበር !
"ዎዜ" የሚለው ሙዚቃ ጆሮዬ ላይ አቃጨለብኝ :)

@getem
@getem
@paappii

#Mikael aschenaki
1,ስንቴ: 🎭
•••
ግንባሯ ላይ ግብዳ የመስቀል ንቅሳት አለ።ንቅሳቱ የቀይ ፊቷን ሲሶ የሚያክል ሸፍኖ መልኳን ክፉኛ ስላበላሸው ብዙ ጊዜ በሻሽ እና በነጠላ ትሸፍነዋለች።

ሁል ጊዜ ዘርፈፍ የሚል ቀሚስ አድርጋ ነበር ሰፈር የምትመጣው፤ፓንት ስለማታደርግ ቀሚሷ የቂጧ መካፈያ ውስጥ እየተሰገሰገ አስሬ ምዘዢኝ ይላታል።

*ይሄ የሰፈር ውሪ የእለት መዝናኛ ነበር*

ሁሌ አንድ አይነት ጫማ ነው የምታደርገው። ጥቁር፣በሁለት የእግር ጣቶች መሐል ማጥለቂያ ያለው...የግራ እግሩ ጫማ ማጥለቂያው የተገነጠለ ሲሊፐር... ጣ ጣ ጣ የሚል ድምጽ ከተሰማ ስንቴ ሰፈር መጥታለች ማለት ነው።

ስንቴ ሰፈር ከመጣች ለሶስት ነገር ነው ፡ አንድ ከኑሩ ሱቅ ስኳር ቡና እና ሰንደል ልትገዛ ፣ ሁለት ከቦኖ ውሃ ልትቀዳ ፣ ሶስት ደግሞ እኔን ለማየት።

ትወደኛለች።

•••

2,እኔ 🪢

ሶስት ጊዜ ራሴን ለማጥፋት ሞክሬ አልተሳካልኝም(እጄ ከሽርክት ብዛት ብሪጅስቶን ጎማ መስሏል)። እናቱ ከሞተች በኋላ ነው ወፈፍ ያደረገው ይሉኛል። ውሸታቸውን ነው! እናቴን አልወዳትም ነበር...የሞተች ቀን አሴ ፑልቤት ቦነስ ስጫወት ነው ያደርኩት። ዘጠነኛ ክፍል እያለሁ ሔለን የላኩላትን ቴክስቶች ስክሪንሻት አድርጋ ዋትሳፕ ግሩፕ ላይ ለቅቃ ለተማሪው ሁሉ ያሳየች ቀን ያለቀስኩትን ለቅሶ እንኳን አላለቀስኩላትም።

ሱስ የለብኝም ፤ ከጥንቃቄ ሳይሆን ከስንፍና ። አላጨስም፣አልቅምም፣አልጠጣም- ከቡና በስተቀር። ቡናውን እንኳን ያስለመደቺኝ መሲ ናት።

•••

3,መሲ 🌄

መሲ ከኳታር መጥታ እኛ ግቢ ተከራይታ የምትኖር ልጅ ናት ፤ ቆንጆ አይደለቺም- እንደውም ደቦልቦል ያለች ነገር ነች። ብዙ ነገር ያስለመደቺኝ እሷ ናት። በእኔ ሰው የመልመድ ችግር ጋግርታምነቴን እና ኮሶ ፊቴን ተቋቁማ በትግል ቀረበቺኝ። ቀስ እያልኩ ለመድኳት። የራሴ ክፍል ውስጥ አማትቤ የምገባ ልጅ የመሲ ቤት መዋል እና ማደር ጀመርኩ።

"...ጥርስህን ማነው የሸረፈህ??" ፈገግ እያለች...

"ኤሌትሪክ ልቀጥል ወጥቼ ከጣራ ላይ ወድቄ ነው" አንገቴን እንደደፋሁ።

ትስቅብኛለች 😂😂😂

ሌላ ቀን ደግሞ...

"...ቡቡ ግን ሳትዋሽ ንገረኝ ቺክ በ*ተህ ታውቃለህ??"

አይኔ ብልጥጥ ይልና ከአጠገቧ ብድግ ብዬ ወደቤት መራመድ እጀምራለሁ...ፍንጥር ብላ ትነሳና ይዛ ታስቀረኛለች...

"አባቴ ይሙት ስቀልድህ ነው...አታምርራ...ና ቁጭ በል በጌታ...ቡና እያፈላሁ አይደል? ብቻዬን ልታስጠጣኝ ነው??"

ቁጭ እላለሁ

የሆነ ቀን ደግሞ...

ስለባሏ ትነግረኛለች - "ባሌ አረብ ነበር። የናጠጠ ሀብታም!" የድሮ ባሏን ሃብት ልታሳየኝ አገጯን በአውራጣቷ ፍትግ ታደርገዋለች።(ቱጃር ነው ለማለት)... "... ይሄ የእናንተ ሼኩ... ከስድስት ወር አንዴ እኛ ቤት ይመጣ ነበር... አቤት የኔን ሽሮ ሲወዳት!... በየሄደበት ሁሉ የመሲ ሽሮ ካላለ ያወራም አይመስለው ነበር..."

"ከባልሽ ጋር በምን ተለያያችሁ?" ከሶስት ሰአት በፊት ካገኘኋት ጀምሮ ያወጣሁት የመጀመሪያ ዓ.ነገር ነው።

"እንዳንተ ያለ የሃገሬ ሸበላ ይሻለኛል ብዬ ፈታሁት!"... እንተያይና እንስቃለን...👀<>👀...😂😂

እውነተኛ ምክንያቷ ግን የአመሉ መብዛት ነው...አድርጊ የሚላትን ሁሉ ብትሞክርም ማድረግ ዳገት ሆነባት። ከአቅሟ በላይ ሲሆን ስትሄድ የያዘቻትን ሻንጣ ብድግ አድርጋ ጥላው መጣች።

ሐሙስ ለታ ደግሞ...

"አንተ ቡቡ"

"አቤት"

"ወዬ በለኝ ውሻ"

"ወዬ"

"ጎልደን ሻወር ታውቃለህ??"

👀

•••

4, ኑሩ 🕊️💸

ኑሩ ከወልቂጤ የመጣ የመንደራችን ባለሱቅ ነው። እናቴ በህይወት እያለች የዱቤ ደንበኛዋ ነበር። ምስጢረኛዋም ነበር...ከሃገሩ መጥቶ ታላቅ ወንድሙ ጋር እንዳረፈ መጀመሪያ ያወቃት የሰፈር ሰው እሷ ናት። ወንድሙ ትምህርት አላስተምረውም ስላለ ኑሩን ፊደል የማስቆጠር እዳ በእናቴ አዛዥነት እኔ ላይ አረፈ። ከጨዋታ ሰአቴ ላይ ቀንሼ ከማስጠናቴ በበለጠ ሁሌ ሲመጣ አብሮ ይዞት የሚመጣው የገነተረ ስጋ አይነት ሽታ ስላለ ኑሩን ማስጠናት ለእኔ 'ስቃይ' ነበር። አሁን ከዚህ ጋር ነው 'ሀሁ ፣ አቡጊዳ ፣ ኤቢሲዲ እያልኩ ስዳረቅ 'ምኖረው?' እያልኩ እበሳጭ ነበር። የኑሩ ተአምርነት የተገለጸልኝ ግን ገና በመጀመሪያው ቀን ነበር። ከፍጥነቱ ለማወቅ ያለው ጉጉት ፣ በዛ ላይ ታታሪነቱ ተጨምሮበት ከሳምንት በኋላ ደንደን ያለ መፅሐፍ የሚያነብ ደንበኛ አንባቢ ወጣው።

ያ ኑሩ ነው እንግዲህ ዛሬ ሃምሳ ብር ልፈልጠው ሱቁ ሄጄ አንዴ ታሪክ አንዴ ፍልስፍና እያወራ ቁም ስቅሌን የሚያሳየኝ።

"ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አሁንም ድረስ ጥቁሮች እግራቸው ዝር የማይልበት ከተማ እንዳለ ታውቃለህ??"

"ኑሩ ደግሞ አሁን ይሄ እኔ ከጠየኩህ ሃምሳ ብር ጋር ምን ያገናኘዋል??"

"ላገናኝልህማ ነው ታግሰህ ስማኝ። ከተማዋ ስሟ ኦሬኒያ ይባላል... እናልህ..."

"ኑሩ በእትዬ ሞት ብሩን ስጠኝ...ስለቸኮልኩ እኮ ነው"

የእናቴን ስም ሲሰማ እባብ እንደወጋው ምላሱ ድርቅ ብሎ... ምንም ሳይናገር መሳቢያውን ከፈተና መቶ ብር አውጥቶ አቀበለኝ።

"ሹክረን ኑርሻ እንዳገኘሁ እመልሳለሁ" 🙌🏿

"አፍዋን" አለኝ ፍዝዝ እንዳለ...

ሄድኩ...

•••

5, አባቴ 🚫

ሳልወለድ ሞቷል!

•••

6,እንጀራ አባቴ 🪢

አልወደውም። አልጠላውም። በስሜ ነው የሚጠራኝ... ቃለአብ ይለኛል። አስራ ስድስት አመት አንድ ቤት ኖረን አሁንም 'እንግዳማቾች' ነን። እናቴ ከሞተች በኋላ ደግሞ ጭራሽ ተራርቀናል። ሳምንት ሳንተያይ የምንከርምባቸው ጊዜያት ጥቂት አይደሉም። እናቴ የፀሎት መፅሐፏን እና የቅዱሳንን ስዕል የምታስቀምጥበት ሙዳይ ውስጥ ለቀን የሚሆነኝን ብር አስቀምጦልኝ ወደስራው ይሄዳል። ያላስቀመጠልኝ ቀን ከኑሩ እበደራለሁ።

ያሳዝነኛል። እናትና አባቱን በተስቦ እንዳጣ እናቴ ነግራኛለች። ብቸኛ ወንድሙ ደግሞ በደርግ ጊዜ ለውትድርና ታፍሶ ተወስዶ የደረሰበት አይታወቅም።

እንጀራአባቴን ጮክ ብሎ ሲያወራ ሰምቼው አላውቅም። ድምፁን አጥፍቶ አንድ ቤት ለሰአታት መቀመጥ ይችልበታል... ማታ ከስራ ሲመጣ ሰራተኛዋ ለሶስታችንም ራት ታቀርብና በዝምታ እንበላለን... ስንጨርስ እኔ ብድግ ብዬ መሲ ጋር እሄዳለሁ... ሰራተኛዋ ደሞዟን አጠራቅማ የገዛቻትን ሚጢጢዬ ሳምሰንግ ስልኳን ይዛ ክፍሏ ትገባና ዱባይ ላለ ፍቅረኛዋ በኢሞ ትደውላለች... እንጀራ አባቴ ደግሞ ቴፑን ይዞ በረንዳ ላይ ይወጣና ቁጭ ይላል... በዚህ አሮጌ ቴፕ ከካሳ ተሰማ ውጪ ማንም ተከፍቶ ሰምቼ አላውቅም።

🎶...ያንቺማ ትዝታ ተቀርፆ በላዬ
ሳስብሽ ይረግፋል ሌት ተቀን እንባዬ...🎶

🎵...ውብዬ ውብዬ...🎵

•••

7. የእነ ታምራት ሱቅ

"ታሜ" ተጣራሁ

"ታሜ የለም" እህቱ ነች

"ቃል...ያንን ጁስ እና ሶስት የእንጀራ ላስቲክ ስጪኝ"... ሃምሳ ብር ሰጠኋት

"እሺ"

•••

8, እኔ እና መሲ 😵😵

"እሺ ላስቲኩ ምን ያደርጋል አልጋው ላይ!?"...

"ጎልደን ሻወር የሚባለውን ላሳይህ እኮ ነው ቡቡዬ።"

"ባለፈው እንዳደረግነው አልጋ ውስጥ ገብተን ብናደርግ አይሻልም?... እሱ እኮ አሪፍ ነው።"

"ይሄኛው ደግሞ ከዛ ይበልጣል።"

"እሺ እንዴት ነው የሚደረገው??"

"በመጀመሪያ ቅድም ያመጣኸውን ዋተርሜለን ጁስ ጠጥተሃል??"

"አዎ... ቁዝር አድርጎኛል ብታይ... ሸንቼ ብመጣ ራሱ ሙዴ ነው።"

"የትም አትሂድ... እዚሁ ሽናው"

"ኧ??"
2024/09/22 12:34:51
Back to Top
HTML Embed Code: