Telegram Web Link
ፍቅር በዚያ ወራት

፤፤፤ ሚካኤል.አ ፤፤፤

(ክፍል 1)

ስሜ ንፁህ ይባላል ። የስሜ እዳ አለብኝ። እንኳን ለሰው ልጅ ለመላዕክት እንኳ ያልተገባ መጠሪያ መያዜን ሳስበው እሸማቀቃለሁ።
ከክፍል ጓደኞቼ ጋር እየጨፈርን.. .ሺሻ እያጨስን በምናሳልፋቸው ወቅቶች ስሜን የሚጠራኝ ሰው ባይኖር ስል እመኛለሁ።
ደግሞ ማንም እንደሚያውቀው የትምህርት ቤት ህይወት (ላይፍ ይሉታል ጓደኞቼ በቋንቋቸው) ፈታኝ መሰናክሎች አሉት ።
ጥሩ ፋሽን የማይለብስ ...የማያጨስ ...የማይጨፍር ተማሪ ፋራ ተደርጎ ይቆጠራል። ከማህበራዊ ህይወት ገሸሽ ይደረጋል። ከዚህ ክበብ መውጣት የማይፈልግ ሰው ደግሞ በሰዎች ፍላጎት መሾር ይጀምራል።
ስጨፍር የሰው ነኝ...ከወንዶች ጋር ስላፋ የሰው ነኝ...አጭር ቀሚስ አድርጌ እንደ እሳት የሚጋረፉ ወላፈን ጭኖቼን ሳሳይ የሰው ነኝ።
ስስቅ የሰው ነኝ ። ሁሉ ነገሬ አርቴፊሻል !
ከዚህ ግብግብ ስወጣ ግን ጥያቄ አለብኝ።
የህሊናዬን ጥያቄ ማፈን ስለምፈልግ መጠጥ እጠጣላሁ።
ለምን ትጨፍሪያለሽ?
ለምን ከወንዶች ጋር የውሸት ትስቂያለሽ?
ለምን ትቅሚያለሽ?
ለምን ታጨሻለሽ?
ከዛ መጠጣት.. . መጠጥ ደግሞ ጀንትል ያደርገኛል። ህሊናዬን እናትህን እለዋለሁ ።
እጠጣለሁ.. .እጨፍራለሁ...እቅማለሁ...አምራለሁ ...
እንቅልፍ ይወስደኛል።
ስተኛ ም ዝም አልልም...ተኝቶ ማሰብ ይቻላል ወይ? ለምትሉኝ ሰዎች መልሴ ድብን አድርጎ ማሰብ ይቻላል የሚለው ነው።
የማስበው ዶክተር ዘካርያድን ነው። ምርጥ መምህሬ ... ማኔጅመንት ያስተምረናል...ራሴን ማኔጅ ማድረግ ለተሳነኝ ሴት የድርጅት ማኔጅመንት መማር ግን አያስቅም?
ዛኪ መደበቂያዬ ነው። በሱ ክፍል እኔን ጨምሮ የብዙ ሴት ጓደኞቼ አይን ይስለመለማል ። የሄዋን ዘር ይውደድህ ተብሎ የተመረቀ መምህር ።
አይቅለበለብም...አይቸኩልም...
እርጋታው...እውቀቱ.. .ንፅህናው (ፍንትው ያለ ነጭ ሸሚዝ የሚያደርግ ብቸኛው መምህር እኮ ነው)... ሁሉም ባህሪያቶቹ የሴትን ልጅ ልብ መክፈቺያ ቁልፎች ናቸው።
ቆፍጣና ወንድ !
ከትምህርት በተረፈው ሰዓት ማህበረ ቅዱሳን እንደሚያገለግል ሰምቻለሁ።
እሱ ሰላም ሲለኝ ሀጥያቴ ተሰርዮ የተቀደስኩ ይመስለኛል። ሳቁ.. .ጨዋታ አዋቂነቱ አይምጣብኝ ። በመሀል ጣል የሚያደርጋት ስብከት ለኔ የህይወት ስንቅ መሆኑን ማን በነገረው?
እንደ ሌሎች ቀለብላባ ወንድ መምህራን ለሴት ልጅ ባትና ዳሌ እጅ ስለማይሰጥ የፍቅር ፋኖስ ልቤ ውስጥ ተለኮሰ!
ቡም !
አዲስ ወጋገን...አዲስ ፍኖት ተለኮሰ !
ከእንቅልፌ ስነሳ ትራሴን ጭምድድ አድርጌ አቅፈዋለሁ። ዛኪ ነፍስያዬን ያግላታል። ሰውነቴን ሲተኩሰኝ እሰማዋለሁ። ትንፋሹ ከሱ ጋር ሳይሆን ከኔ ጋር ያድራል።
ከሁለት ሰዓታት በኋላ አይኑን ማየቴን ሳስበው ሀሴትን አደርጋለሁ።
ሆኖም ከደስታዬ ሲለጥቅ አንድ ጥያቄ ገረፍ አድርጎኝ ያልፋል።
ኪሩ ከዚህ ሁሉ አፍቃሪ ሴቶቹ መሀል እኔን እንዴት ሊመርጠኝ ይችላል?
ከኔ በላይ ቆንጆ ሴቶች ደግሞ አሉ። ልቤ ን ግን አያክሉትም...ልቤ ተራራ ነው። ማንንም ማንበርከክ ...ማንም እንዲያሸረግድልኝ የሚያደርግ ቅብዓ ቅዱስ አለኝ።
ሰለዚህ እሱን አማልሎ ወጥመዴ ውስጥ የማስገባበት ብልሀት ወጠንኩኝ...ትምህርት ቤት ስሄድ እሱን እንደምረታው ለራሴ እየነገርኩት ነው።
ንፁህ ታሸንፊያለሽ ! ብሎ የሚፎክር ጀብደኛ ልብ አለኝ።
ዶክተር ኪሩ መጣሁልህ !

(ይቀጥላል...)

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፍቅር በዚያ ወራት 

ክፍል 2

(ሚካኤል .አ)

የክፍላችን በር ጋር እስክደርስ የነበረኝ በራስ መተማመን ስሜት እምን ጉድጓድ እንደገባ አላውቅም። ዶክተር ዛኪን ሳየው ልቤ በአፌ ልትወጣ ታገለችኝ። 

እንደ ልማዱ ፅድት ብሎ መጥቷል። (በጣም የሚገርመኝ ነገር ጫማው ላይ እንኳ ብናኝ አቧራ የለምኮ ) ... ለነገሩ ከቤቱ ወጥቶ በኔ ልብ ላይ ተራምዶ ክፍል እየደረሰ በየት በኩል አቧራ ሊነካው ይችላል?

በማስተማሩ በፊት ሁላችንንም በስስት እያየ ሰላምታ ይሰጠናል...ጨዋታ አዋቂ ነው። 

ቢያንስ ፊት ለፊት ከሚቀመጡ አንድ ሁለት ልጆች ጋር ሳይጨዋወት ወደ ማስተማሩ አይገባም። ሲስቅ ከልቡ ነው ... ነጭ ባይሆንም ፈዛዛ ሽሮ መልክ ያላቸው ስድር ጥርሶች አሉት ። ድዱ በእጅ ሳይወቀር ተፈጥሮ አሽሞንሙና ሰርታዋለች ። 

እሱ ይስቃል.. .ልቤ ታለቅሳለች ። ስድር ጥርሶቹ የኔን ነፍስ የሚያጠፋባቸው ድርድር ጥይቶች መሆናቸውን ማን በነገረው ?

ፈገግታው ደስም ይለኛል.. .ያስቀናኛልም። 

በተለይ ለነጃት ሲስቅላት እነዳለሁ ።

ደግነቱ እንደዚህ አይነት አክራሪ ክርስትያን ሙስሊሟን ነጃት ሊወድ ስለማይችል ለራሴ ቅናት መፅናኛ አላጣም።

ይሁንና ግን ይሄን አስቤ እንኳ ልቤ እርፍ አትልልኝም...ያቺ ጣውንቴ አይኖቿ ያምራሉ ...ሰውነቷ ከኔ ይበልጥ የሚስቡ ይመስለኛል...ብዙ ጊዜ ዛኪ አቀርቅሮ ትምህርት ሲተነትን እነዛ ሎጋ የእግር ጣቶቿን እያየ ስለሚመስለኝ እበሽቃለሁ ።

የሆነ ቀን ላይ የፊት ኒቃቧ ሲወርድ መልኳን አየሁት ...ለክፋቱ ደግሞ ዶክተር ፊትለፊታችን ነው። መልኳን ሲያይ መደንገጡን አይቼበታለሁ ...(ድንገትም ስለማፈቅረው መስሎኝም ሊሆን ይችላል )

ከሁሉም ተማሪ በላይ ዘልዬ ፊቷን የሸፈንኩላት እኔ ነኝ። ሙስሊም ጓደኞቿ አላህ ይባርክሽ ብለው መረቁኝ... (ይሄን ያደረኩት ከነጃት የውበት ፆር ዛኪዬን ለመደበቅ መሆኑን የሚያውቀው አላህ ሲባርከኝ እኮ ታየኝ !)

በቃ ከዛን ቀን በኋላ አይኖቼ ሁለቱንም ይከታተላቸዋል። ለሴት ልጅ ውበት ግድ አልባው ዛኪ ለነጃት ግን የተመየ ስሜት ያሳደረ ይመስለኛል....። ክፍል ውስጥ ፊትለፊት ስለምትቀመጥ ሳያሳስቃት ምንም ነገር አይጀምርም። 

ደግሞ ሌላ የሚያበሽቀኝ ነገር የሷ ሳቅ ነው። ስታየው ገና አይኖቿ ይበራሉ.. .ትንሽ ያወራት ጊዜማ ነፍስያዋ ትዘላለች) 

በዚህ ቅናት ተነሳስቼ እኔም እንደሌሎች ቸካይ ተማሪዎች ፊትለፊት ሄጄ ተቀመጥኩ ።

ብዙ አልምጥ ጓደኞቼ ተሳለቁብኝ። ትምህርት እንደሚደብረኝ ብቻ ሳይሆን እኔም ትምህርትን እንደምደብረው ሁሉም በዙሪያዬ ያሉ ልጆች ያውቃሉ። የኔ ፊት ወንበር ሄዶ መቀመጥ ተማሪውን ብቻ ሳይሆን መምህሬንም ገርሞታል ።

"ዛሬ እንዴት ነው? ... የመማር ሞራልሽ መጥቷል ማለት ነው" ፈገግ አለልኝ ።

ሞትኩለት !

ክለብ ለክለብ የሚቅለበለበው ምላሴ ጉሮሮዬ ላይ ገብቶ ተሰነቀረ ።

የሆነ ቅጥ የሌለው መልስ መለስኩኝ.. .

"አ....አ......መ...ሰ....ለ....እ....ኝ "

ስደናበር ነጃትና ጓደኞቿ ተያይተው ሳቁብኝ። 

በቃ ጠመድኳት ይህችን ሴት !

"ንፁህ ምን ሆነሻል እጅሽ እየተንቀጠቀጠ ነው እኮ!  አመመሽ እንዴ? "

"አዎ ቲቸር !" 

ይኸው የኔ ትሁት ዛኪ ደገፍ አድርጎ ከክፍል እንድወጣ ዕድል ሰጠኝ ።

አለንጋ ጣቶቹ ወገቤን ሲይዙኝ የእውነት ታመምኩለት ...ሰውነቴን እሱ ላይ ጣልኩት ።

የክፍሉን በር ከፍቶ ወጣን ።

"አይዞሽ ንፁህ.. ."

እንዲህ ሲለኝ የነጃት የቅናት ዛር አናቴ ላይ ተፈናጠጠ ።

በድፍረት ከናፍሩን ስሜ ፍቅሬን ልገልፅለት ደፈርኩ ...

አንድ 

ሁለት

ሶስ.....

     (ይቀጥላል)

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፍቅር በዚያ ወራት
(ሚካኤል.አ)
#ክፍል 3
ከንፈሮቹን ልጎርሳቸው ተጠጋሁት.. ወደ ከናፍሩ ስጠጋ የውብ ትንፋሹ መዓዛ አወደኝ ። የተቀባው ሽቶ በአፉ ከሚያላምጠው ሜንት ማስቲካ ጋር ሲዳበል የገነት መግቢያው የሱ መዓዛ ነው ቢሉኝ ውሸት ነው አልልም።
ወድያው "አይዞሽ ውዴ! " የሚል ድምፅ ሰማሁ ።
ሺት !
የፈራኋት ጣውንቴ መጣች ። የነጃት ጥላቻዬ አስራ አንድ በመቶ ሲያድግ ተሰማኝ (ፖለቲካ አይደለም !)... በሷ ቤት አንድ ቀን ኒቃቧ ከፊቷ ሲወርድ ቀድሜ ስለደረስኩላት በችግሬ ጊዜ ቀድማኝ መድረሷ ነው። ችግሬ እሷ እንደሆነች ብታውቅ ስል ተመኘሁ።
"ነጅዬ እባክሽ handle " አድርጊያት ብሎ ዶክተር ወደ ክፍሉ ገባ። ነጅዬ ሲላት ደግሞ ነብር ሆንኩኝ... ከየት መጣ ያልተባለ ቀዝቃዛ ውሀ ፊቴ ላይ ከነበለችብኝ።
የዛክዬን ከናፍር ከመጉረስ ስታግደኝ ነው መቀዝቀዝ የጀመርኩት ።
"ተረጋጊ እንጅ ፀጉሬን ..." ብዬ ጮህኩባት ።
እሷ እንኳን ልትደነግጥ ወገቤ ስር ገብታ አነሳችኝ ። በጥፊ ጉንጯን ባቀላው ስሜቴ ነው ።
እሷና ጓደኞቿ አንከብክበው ጥላ ያላት አፀደ ስር አኖሩኝ ። ንፋሱ ከውሀው ቅዝቃዜ ጋር ተዳብሎ በረደኝ ።
ጥርሶቼ በእልህና ቅዝቃዜ ተንገራገጩ።
"አይዞሽ ንፁህ.. . "
ራስሽ አይዞሽ ብዬ ልመልስላት ይሆን?
አይኖቿ የሚስቁለት.. .ነፍሷ የምትፈነጥዝለት ዛኪን ልቀማት መሆኑን ማን ሹክ ባላት ?
...
ከዛ ክስተት በኋላ ወደ መደበቂያዬ ሮጥኩ !
ክለብ.. .
ጠጣሁ.. . አምሮቴ ንቅል እስኪልልኝ ጠጣሁ ።
ሞቅ እንዳለኝ ያየ አንድ ጎረምሳ የሚያጨሰውን ሺሻ ትቶ ወደኔ አቅጣጫ መጣ።
"ቆንጆ ነሽ" አለኝ።
ዝም!
"ምነው የከፋሽ ነገር አለ ?"
ዝም!
ምናለ ከዛኪ በስተቀር የዓለም ወንዶች ሁሉ ባያናግሩኝ? አባቴና ወንድሜ እንኳ እንዲያናግሩኝ የምፈልግ አይመስለኝም።
አሁን ይሄ የሰማይ ስባሪ የሚያህል ወደል እንዴት ያናግረኛል ?
ጠጪ ...አጫሽ ወንድ ነው ያስጠላኝ።
ያዘነ ለመምሰል ሞከረ !
ውሸት.. . አይኖቹ ውሸት! ...ሳቁ ውሸት...ንግግሩ ውሸት ...
ቆንጆ ነሽ ሲለኝ አመሰግናለሁ ቢለኝ ...አብረን እንፍታታ ብሎ ይቀጥላል ።
እሺ ብለው እኔ ጋር ለማስመሰል ውስኪ ያወርዳል።
ምድር ላይ ያፈቀራት ሴት እኔ ብቻ የሆንኩኝ ያህል አስመስሎ ይንከባከበኛል...ከዛ መተኛት !
አንዴ ጭኔ ስር ገብቶ በለሴን ከቀጠፈ እኮ በነጋታው ስልክ አያነሳልኝም።
ይሄ ህይወት ሰልችቶኛል.. . ነፍሴ ዛኪ ጉያ ገብታ መሸሸግ ትፈልጋለች ።
ሀጥያቴ የሚጠራው በሱ ላቦት ነው።
"ማሬ አመልሽም ?"
"ማርህን ጎዣም ፈልግ !" አንባረቅሁበት ። ከመቅፅበት ከስሬ በሮ ጠፋ ። ፈሪ ወንድ !
አሁን ይሄ ነው የኔን ጀንታላ ዛክ የሚተካልኝ?
ሌላ ብስጭት.. .
መጠጥ.. . ሻት ...
በቃ ራሴን አጣሁት ። የክለቡ ብልጭ ድርግም መብራት ...መጠጡ.. .ሙዚቃው ናላዬን አዞረኝ ።
ምንም ሆንኩ !
እንደምንም ተንገዳግጄ ሰው መሀል ገብቼ ጨፈርኩ።
እንደ ልማዴ የሰው ሆንኩ...ሳቄ ...ደስታዬ ሁሉ የሰው ሊሆኑ ራሳቸውን ከመቃብር ቀስቅሰው ተነሱ።
ከሩቅ ለሚያየኝ ሰው ደስተኛ ነኝ...ነፈዝኩ...ነጎድኩ ...ብንንንንንንንንንን....
አላልኩም ?
ስጠጣ የሰው ነኝ ብዬ አልነበረምን ?
ማልዶ ስነሳ ራሴን ከሰው ጋር አገኘሁት ።
አንሶላዬን ገልጬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ።
አብሮኝ ያደረው ወንድ እንደ ጆንያ ተንደባሎ ፊቱን ወደኔ አዞረ?
እንዴ?
ይሄ የኢኮኖሚክስ መምህሩ እዘዝ ነው እንዴ?
ዛኪ የነፍስና ገላዬን መርከስ አይቶ የጠላኝ መሰለኝ...
"አንተ ማነህ ?"
.
(ይቀጥላል)

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ


@seiloch
@seiloch
ፍቅር በዚያ ወራት !
ክፍል 4
(ሚካኤል አ)
"አንተ ማነህ ?"
የደነገጥኩት ክፉኛ ነው ። ራሴን ለዶክተር ዛክ አሳልፌ ሰጥቻለሁ ብዬ ስለማስብ ብቻ ገላዬን ከሱ ነጥቄ ያረከስኩ ነው የመሰለኝ።
ንፁህ ረከሰች !
ያ ህሊናዬን የሚኮረኩመኝ ፀፀት አገረሸ።
"ማር ነሽ አለኝ " አጠገቤ ተንጋሎ የነበረው ጎረምሳ።
"እንዴ ዶክተር እዘዘ?"
በሳቅ ተንከተከተ ። የዶክተር ዛኪ ጓደኛ ...
"ከተማሪዬ ጋር በዚህ መልኩ ይነጋል ብዬ አላምንም "
እንዲህ ሲለኝ ደግሞ አለቀስኩ ... አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጬ አለቀስኩ ። እንባዬ ይቅርታ ነው ... ዛኪዬ ማረኝ ብሎ የሚግፈለፈል እንባ በልቤ ውስጥ ፈልቶ በጉንጬ ላይ ፈሷል። የፊት ጉንጬን ይለበልበኛል ።
እዘዝ ግንኙነታችን በኮንዶም መሆኑን አስረድቶ ሊያባብለኝ ሞከረ። ያሳሰበኝ የገላዬ ጤና አልነበረም...የልቤ...የህሊናዬን ህመም የአካል ጤንነቴ አያክመውም።
ብዙ እብዶች.. . የአካል ጤነኞች ነን። ህሊናችን ግን ስለሚያነክስ ታማሚዎች ነን።
ሰው ከውስጡ ካልታረቀ በስተቀር በሽተኛ ነው። ንዋይም...ቤተሰብም ... ሀሴትም እኔን ከህመሜ አይታደጉኝም። መንፃት የምፈልገው ለስሜ ክብር ለመስጠት ነው።
ለስሜ ክብር ስሰጥ ህሊናዬን እወለውለዋለሁ ። ህሊናዬ ሲነፃ ለዛኪ እገባዋለሁ የሚል የራስ መተማመን ይኖረኛል። ለዛኪ እስካልተገባሁት ድረስ ደግሞ ስንኩል ነኝ።
የዛሬው አጋጣሚ ደግሞ ሌላ የሽንፈቴ ገፅ ነው። ለእዘዝ ከብሬ ባገኘው እንኳ የቅርብ ጓደኛውን ባየሁት ቁጥር መርከሴ ይታሰበኛል ።
"ንፁህ ተረጋጊ..." እጆቹን አይኖቼ ላይ ሊያሳርፍ ሲሞክር ገፈተርኩት ።
እዘዝ ባለጌ ነህ ትለዋለች ነፍስያዬ ። የጓደኛህን ገላ አታለህ የቀማህ እርኩስ ነህ ይለዋል ውስጤ ።
እያየሁ ጠላሁት ... መርከስ መልክ ቢኖረው እዘዝ ነው ። መርከስ መልክ ቢኖረው ንፁህ ናት ።
ልብሴን ለባብሼ ክፍሉን ለቅቄ ወጣሁ ። ከሲኦል የማመልጥ ይመስለኛል። የሆቴሉ የመጀመርያ ኮሪደር ስደርስ እያመለጥኩ ነው።
ብንንንንንንንን.. ..
።።።።።።።።።።
ከዛች ቀን በኃላ ትምህርት ቤት አልሄድም። እንደ እርጎ የሰከነው ዛኪን ማየት ሌላ ፀፀት ነው ለኔ ።
የነጃትን አይኖች ማየት ለኔ ተጨማሪ አርጩሜ ነው ።
የፍቅር አምላክ የዛኪን ልቦና ወደ ነጃት አዙሮ ለሽልማት ሲያጫት አየሁ።
አፈርኩ ... ለአምስት ቀናት አፍሬ ከክፍል ቀረሁ ።
ከሰመመኔ ለቀናት አልነቃሁም።
የፀፀት በትር ገላዬን አድቅቆት ቆዘምኩ ...
ከዚህ መዛል ንቂ ሲለኝ ግን ሀሙስ የምትባል ቀን ሌላ ተዓምር ይዛ መጣች።
ሀሙስ የቀን ቅዱስ ። ማለዳውን በቅድስና አልያም የፀፀት ቤንዚኗን ለማርከፍከፍ በላዬ ላይ ተሰየመች ።
ጉዱ የስልክ ጥሪዬ ነው ።
እንደ ኤሊ እየተንቀራፈፍኩ በዳበሳ ስልኬን አገኘኋት ። አንድ አይኔን ሳልገልጥ ደዋዩን አየሁት ።
መንቃት ብቻ አይደለም ...
ከአልጋዬ ተስፈንጥሬ ቆምኩኝ። ደዋዩ ነፍሴን ሙሉ የሚያደርጋት ሀኪሜ ነው ።
Teacher zaki.. .
ስልኬ ከእጄ በምን ፍጥነት ወድቆ ወለሉ ላይ እንዳረፈ አልገባኝም።
በምን ተዓምር ዛክ እኔ ጋር ደወለ ?
ላንሳው ይሆን?
(ይቀጥላል.. . )

@wegoch
@wegoch
@paappii
"ሸግዬ ሸጊቱ" መፃፍ በቅርቡ ትመጣለች ይጠብቁን
ኩባያው
(በማዕዶት ያየህ)

አይደለም በጀማ የተሰራ የጊቢ ምግብ በሰራተኛ የተበሰለና በቅመማቅመም ራሱን የሳተ የቤት ምግብ የሚያማርጠው ጨጓራዬ በሆነ ምትሀት ከሳምንት 5 ቀን ክክ መብላት ለመደ።እርሾ እንደበዛው ሊጥ የሚቆመጭር ፍርፍር በዚሁ ምትሀት ጣፈጠኝ።የሰማያዊ ኩባያ ልክፍት ከጊቢው ካፌ የማይጠፋ ረሀብተኛ አደረገኝ።

ያችን ሰማያዊ ኩባያ የነካ ከንፈር የኔን ከንፈር እስኪነካ ደጅ ጠኚ ሆንኩ።የሆነ ቀን(ትዝ ይለኛል አርብ ነበር ቀኑ)በጧት ስነሳ ጤነኛ ያልሆነ ረሀብ ነፍስ ዘርቶ ጨጓራዬ ላይ ስዕል ሲስል ታወቀኝ።የትምህርት ሰዓቴ ስለደረሰ ከጊቢ ወጥቼ ምግብ አዝዤ ለመመገብ የሚሆን ጊዜ እንደሌለኝ ሲገባኝ ከጓደኞቼ ጋር ወደጊቢው ካፌ ሄድኩ።ምግቤን ተቀብዬ ከመቀመጤ የሆነ ምትሀት የሚመስል ድምፅ ሰማሁ።ቀና ስል የመግቢያው በር አካባቢ የተማሪ መመገቢያ ካርድ ላይ ምልክት የሚያደርገው ሰውዬ ከአንዲት ልቅም ያለች ቆንጆ ጋር የጦፈ ክርክር ይዟል።ልብ ብዬ ሳጤነው የክርክሩ መነሾ የልጅቱ አፍሮ ፀጉር ነው።

"ፀጉሬ አጭር ስለሆነ አይያዝም።ሲሰራ እና ሲበጠር ደግሞ ሀይለኛ ራስ ምታት አለብኝ ያመኛል።ምናለ ብታስገባኝ ጋሼ? ክላስ እየረፈደብኝ ነው'ኮ"ትላለች በማስተዛዘን።

"የኔ ጉዳይ አይደለም!ስትፈልጊ ከስር በምላጭ ተሞሽለቂው!ይህ አይነበብም?ምን ይላል?ጠጉር አንጨባሮ መግባት አይቻልም አይልም?"ሲል አንባረቀ ሰውየው።ልጅቱ አስተዛዝኖ መለመኑ እንደማይሆንላት ስታውቅ ጎንበስ አለችና ያንን የህወሀት ተጋዳላይ የመሰለ ፀጉሯን መሀል ለመሀል በእጆቿ ከፍታ መሀል አናቷን ለሰውየው አሳየችው።ደንግጦ አማተበና እንድትገባ ፈቀደላት።ዳቦ ተቀብላ በግራዋ ፣ በሰማያዊ ኩባያ ደግሞ ሻይ በቀኝ እጇ ይዛ ከፊትለፊቴ ያለ ወንበር ስባ ተቀ

ተቀመጠች።ከያዘችው ዳቦ ግማሹን ቆርሳ በሻዪአ እያማገች ተመገበችው ።ኩባያውን ወደአፏ አስጠግታ ከንፈሯን ስታስነካው አላት የሆነ ምትሀት!ያኔ እንደኔ አትኩሮ ያያት ካለ በእርግጠኝነት ትን ብሎታል ።የውበት ትንታ...የማማር ትንታ...የሰማያዊ ኩባያ ትንታ...የአፍሮ ትንታ...እኔንም ትን ብሎኝ የጀመርኩትን ሻይ ሳላጋምስ ዳቦዬን ለጓደኞቼ ትቼ ተከትያት ወጣሁ።ሮጠች...ሳይረፍድ ለመድረስ...ሮጥኩ...ዕድሌን ላለማሳለፍ...ደረስኩባትና እያለከለክሁ ያንን ኩባያ የያዘችበትን ቀኝ እጇን ለቀም አደረኩት።ደንግጣ ዘወር አለችና እጇን ከጄ መንጭቃ አስለቀቀችው።

"ረጋ በይ ሰዓት ገና ነው"አልኳት የእጅ ሰዓቴን ወደሷ ጠጋ አድርጌ ለመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ ገና 20 ደቂቃ እንደሚቀራት እያሳየሁዋት።በስሱ ረጋ አለች።

"ራስሽን ምን ሆነሽ ነው?"ጠየኩ ወደፀጉሯ እያየሁ።ቅድም ለካፌ ተቆጣጣሪው እንዳሳየችው ጎፈሬዋን ለሁለት ከፍላ መሀል አናቷን አሳየችኝ።ከግንባሯ ማብቂያ አንስቶ ወደሁዋላ የሚሄድ በግምት አምስት ሳንቲ ሜትር የሚሆን የትኩስ ቁስል ስፌት!ቅፍፍ አለኝና ፊቴን ከሰከስኩት።

"አየኸው?"
"አዎ. ...ምን ሆነሽ ነው?"
"የብረት ዱላ አርፎብኝ?"
"ምን?😳"(እዚህጋ ሳልጮህ አልቀረሁም)
"ኧረ ቀስ እንዴ!መስኮት መቶኝ ነው የብረት መስኮት...እኔ ራሱኮ ሲመታኝ እንዲህ አልጮህኩም ሆሆሆ "
"ቆይ መቼ ነው የመታሽ?"
"ሳምንት ሆነው"
"የት ነው?"
"ቤቴ...ሲቆላኝ!የሚያደርገኝን ሲያሳጣኝ"
"እንዴት ማለት?"
"ከሆነ ሰው ጋር ተጣልቼ ወደክፍሌ ገባሁና ከተኛሁበት ስነሳ መከፈቱን ያላስተዋልኩት መስኮት ተንፈስ አረገኝ።"
"እንዲህም አርጎ መተንፈስ የለም እቴ!እሺ ከዛስ ወዲያ?"
"ከዚያማ ቁስሉም ተሰፋ እኔም አፍሮ ሆኜ ቀረሁ ይባላል።"
"ይህን ያህል ምናይነት አመታት ቢሆን ነው የመስኮት ጫፍ መቶሽ ለስፌት የደረስሽው?"
"መስኮቱ ለተጣላሁት ሰው ወግኖ አይመስልህም?"
"ሃሃሃሃ...ሃሃሃሃ...ማነው ባክሽ የመስኮት ረዳት ያለው?ታድሎ!"
"ሆሆ ገላዬነህ አንተ ከሰሙህ ብዙ ትጠይቃለህ...አሁን ረፍዶብኛል ቻው!"ብላኝ ስትሮጥ
"እሺ ቢያንስ ስልክሽን ስጭኝ!"አልኩ ሰው ሰምቶ እስኪታዘበኝ ጮክ ብዬ።
በፈገግታ ተሞልታ ዘወር አለችና
"ለሌላ መስኮት እሚበቃ ጭንቅላት የለኝም"አለችኝ።ቅር እያለኝ ተመለስኩ።ከዛች አርብ በሁዋላ ጨጓራዬ ድኖ ያገኘውን እየበላ ሳንቀያየም ማደር ያዘ።እንዳታልፈኝ ብዬ ከማለዳው 12:50 ጀምሬ ካፌ እሰለፋለሁ።ግን አላያትም...ያንን አምፖል የሚያህል ዐይኗን...የተከመከመ አፍሮዋን...ችምችም ያሉ ጥርሶቿን ዳግም ባይ ብዬ ከታሪካዊ ጠላቴ ከክክ ጋር እርቅ ፈፀምኩ።ዳሩ የት ተገኝታ?ሰማያዊ የሻይ ኩባያ በደረሰኝና ባየሁ ቁጥር ጥቁር ከናፍሯን እያስታወስኩ እጃጃላለሁ።ግን እሷ የለችም..ብቻ የሆነ ቀን አያታለሁ...የሆነ ቀን...

#Maedot (Tizur_12)

01/10/2014 ዓ.ም.

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሽቶና ትዝታ
።።።።።።።።

መኖሬን ሳላዳምጠው ለሞት በሬን መክፈት አልፈልግም።የነፃነቴን ወጋገን እስከ ገደሉ ጫፍ ነው የማሳድደው።እና በ29 ዓመቴ የሞዴል የሚመስል ቁመና ይዤ፣የጋብቻ ቀለበት ከጣቴ ሳይገኝ፣ፀጉሬን አፍሮ አድርጌ ፣በመለሎ ቁመቴ ላይ ሂል ጫማ ጨምሬበት፣ጥቁር ቻፕስቲክ በስሱ ተቀብቼ ከቀጭን ወገቤ ጋር የልቤን እያወራሁ መራመድ ያስደስተኛል።የሆነች ንግስት እንደሆንኩ ይሰማኛል።ሳባን የሆንኩ ዓይነት።"ጥንቅቅ ያልሽ ወይዘሪት ነሽኮ መዓዚ!"ይሉኛል የስራ ባልደረቦቼ ሲያሞካሹኝ።

ወደ አዲሱ ተመድቤ ወደማስተምርበት ክፍል ስደርስ የሆነ ሽቶ ይሸተኛል።የመጀመሪያ ባሌ ሽቶ...ልወልድለት ቀን ስቆርጥ ቁርጤን አሳውቆኝ የተወኝ ባሌ ሽቶ።ልክ ወደ ክፍሉ ከመቃረቤ ነው ያ ሽቶ ከነአዳፋ ትዝታው እየተጎተተ በአፍንጫዬ የሚገባው።ከነዱላው፣ከነስድቡ፣ከነኩራቱ፣ከነትዕቢቱ...ልሸሽ ብል የማልሸሸው ዐይነት ኩራቱ ድቅን ይልብኛል።ባስ ሲል በስጋ አምሮት ነድጄ ስገላበጥ ሰክሮ ገብቶ ጥቅልል ብሎ የሚጋደመው ነገር ሽው ይልብኛል።

ለራሴም ለልጄም የሚሆን ጥሩ መሰረት ሳላዘጋጅ መውለድ የማይዋጥልኝ ሴት ነኝ።ለልጄ ተገቢውን ትምህርት እንደማስተምረው፣እንደማላስርበው፣እንደማላስበርደው፣እንደማያዝንብኝና ከኔ በመወለዱ አንድም ቀን እንደማያማርር እርግጠኛ ሳልሆን አላረግዝም ማለቴ ነበር ነገር ያበላሸው።

"ሰው እንዴት ሳይኮሎጂ ተምሮ የባሉን ፍላጎት መረዳት ያቅተዋል?"ይለኝ ነበር ያልሰከረ ጊዜ።እኔም አለት ነበርኩ ሀዘኔታ አይሰማኝም ነበር።

"You are beyond the science Mister"እለዋለሁ።

"ተይ እንጂ!ሃሃሃሃ"ጥቅልል ብሎ ለጥ ሲል እጮሀለሁ።(ተራ ጩኸት እንዳይመስላችሁ ደግሞ...ሆረር ፊልም የሚያይ ህፃን ጩኸት ነው የምጮኸው)
ደንግጦ
"ሴትዮ ምነካሽ አበድሽ?"
"አዎ አብጃለሁ...እና ምን ይጠበስ?"
"ምን ሆንኩ ነው ምትይው ቆይ"
"ለምንድነው ወደኔ ዞረህ እማትተኛው?"ስለው ዝምምምምም ይላል።ስቃጠል አድሬ ጧት ጠግቦ እንዳደረ ሰው ተነስቼ ወደስራዬ አዘግማለሁ።የኔ ጭቅጨቃ ሲደጋገም ዝምታው ድንበሩን ጥሶ ወደማመናጨቅና ወደመሳደብ አደገ...አለፍ ሲል ወደ ዱላ...በሁዋላ ጦመኛ መሆኔ ሳያንስ ዱላውን የምቋቋምበት አቅሜ ሲከዳኝ ፈታሁት።አልክድም ብዙ ሌሊቶችን ነፍርቄአለሁ።ደግነቱ ሆዴ ቶሎ ቆረጠልኝ።ልጅ ከመውለድ ባልን መፍታት የሚል ትልቅ እብደት አዘል ውሳኔ ወሰንኩ።

ስሙና ግብሩ ተጣልተው ፍስሐ ሆኖ ፍስሐ ያልሰጠኝን ፍስሐ ረሳሁት ብዬ እፎይ ስል ይኸው አሁን ደግሞ ሽቶው ወደሁዋላ ሶስት ዐመታትን ጎትቶ እነዚያን የቃጠሎ ሌሊቶች አስታወሰኝ።ከተማውን አካልዬ አለ የሚባለውን ስስ ፒጃማ ገዝቼ ፣በቀይ ቻፒስቲክ ከንፈሬን ኢንጆሪ አስመስዬ ለራት ጠረጴዛው ላይ ስሰየም ከቀረበለት ግማሹን እንኳን ሳይበላ ስልክ እየደወለ ወደ በረንዳ ይወጣል።ሲጨርስ እንደልማዱ ተጠቅልሎ ይተኛል።

የልጅ አምሮቱን ለሁለት ዐመታት ማስታመም ተስኖት አይገፉ አገፋፍን ገፋኝ።"መውለድ የምፈልገው ከሁለት ዐመታት በሁዋላ ነው"ስላልኩ ብቻ ጭኔ ስር ባለው እሳት እኔኑ ቀጣኝ...ከፈታኝ በሁዋላ ወዲያው ነው አግብቶ የወለደው...ፍጥነቱ በጌታ!ልክ ቀለበታችንን ባወለቅን በአስረኛው ወር ከማሞቂያ ያልወጣች የጨቅላ ህፃን ፎቶ ላከልኝ።ከታች

"Am dad now...my beautiful mule😁😁"ከሚል መልዕክት ጋር...
ይኸው ደግሞ ሽቶው መጣ..."ከዚህ በሁዋላ ሽቶ እንዳትጠቀሙ "ብዬ ተማሪዎቼን አልከለክል ነገር...ኤጭ!!

ማዕዶት ያየህ(@Tizur_12)

02/10/2014 ዓ.ም.

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፍቅር በዚያ ወራት !

(ክፍል 5)
ሚካኤል.አ

ለምን እንደሆነ ባላውቅም የዛኪን ስልክ አለማንሳት አልቻልኩም። ድምፁ ናፍቆኛል.. .

"ሄሎ "

"ሄሎ ንፁህ.. ."

ዝም አልኩት ። ረጋ ያለ ድምፅ!  ... 

ንፁህ ብሎ ሲጠራኝ እንባዬ ፈሰሰ ። አፍቃሪው ልቤ በክህደት ሰንሰለት ተተብትቦ በፀፀት አርጩሜ እየተወገረ ነው።

"ሄሎ " .. የድምፄን መጥፋት ሲረዳ ደግሞ ተናገረ ።

"ሄሎ ቲቸር "

"በሰላም ነው የጠፋሽው? ህመሙ አልተሻለሽም እንዴ?"

የተሻለኝ ህመም የለም። ጭራሽ የማይድን ሌላ የውስጥ ቁስል አመርቅዣለሁ ።

እወደዋለሁ.. .

የንሰሀዬ መንገድ የሱ ስክነት ነው። እሱ ቢያቅፈኝ...እሱ ቢያስብልኝ... እሱ መዳፉን አውሶ ቢዳብሰኝ እንደስሜ እነፃ ነበር ።

"ምንድነው ለቅሶ ነው የምሰማው ?" 

"አዎ ዛክ "

"ምን ሆነሻል ?" 

"እወ.. .."

ሰውን እወድሀለሁ ብሎ መናገር ለካ ይከብዳል ።

ቃላቶቼን ከምኔው እንደዋጥኳቸው አላቅም። ለሱ ፍቅሬን መግለፅ ስሜቱን የሚገድልብኝ ይመለኛል። ዛክ ከወንዶች ሁሉ ይለያል ብዬ ባስብም ሁሉም ወንዶች ደግሞ የሚያመሳስላቸው የጋራ ባህሪ እንዳላቸው አምናለሁ ። 

ሴት ልጅ ለወንድ ልጅ የውስጧን ስሜት በግልፅ ከነገረችው ለሷ ያለው አመለካከት ይወርዳል። ወንድ ልጅ ከአፍቃሪው ይልቅ በኩራት ገመድ ወጥራ ለምታሰቃየው ሴት የልቡ በራፍ ይከፈታል ።

ኩራት !

ወንዶች መለመን ይፈልጋሉ.. . እንደ ወርቅ ተደብቃ የማህደሯ ክርታስን ለመቆፈር የምታታግል ሴት የወንዶችን ልብ ቁልፍ በእጇ ይዛ ትዞራለች ።

"ምን አልሽ?"

"አወ...ቅማ ዶክተር እባክህ ትንሽ ህመሜ ስለጠነከረ ተጨማሪ ቀናትን ባልመጣ እንዳትቀየመኝ። "

"ለምን እቀየምሻለሁ?  ትምህርትም...ስራም.. .ከጤና በላይ አይሆኑም። ስትኖሪ ነው ሁሉ ነገር የሚኖረው።

በይ ፈጣሪ ይማርሽ ።"

"አሜን !" አልኩት ።

ይሄን ያልኩት ግን ለበሽታዬ ድህነት አይደለም። ፈጣሪ እኔ ላይ የሰራሽውን ሀጥያት ይቅር ብሎ ይማርሽ እንዳለኝ ነው የተረዳሁት የኔ ካህን ።

ስልኩ ሲቋረጥ ከንፈሬን ወደ ስክሪኑ ሰድጄ ሳምኩት ።

እኔ የሱ መቅደላዊት ማርያም ... 

በደሌ በፍቅሩ የሚነፃ ከሆነ ብዬ በእንባዬ ራስኩኝ።

....

በዛኑ ቀን ዶክተር እዘዝ ደወለ።

በሙት ስሜቴ ስልኩን አነሳሁት ። እድለ ቢሶች ከምንወደው ነገር ይልቅ የማንወደው ነገር ይከተለናል ። ዶክተር እዘዝ ን አልወደውም። በተለይ ከዛ ክስተት በኃላ የርኩሰቴ ቤንዚን ሆኖ ይሰማኛል።

"ጣፋጯ " አለኝ።

መራሩ ልበለው ይሆን?

"ይቅርታ ዶክተር ...እንደዚህ አትበለኝ "

" ምነው አንዴ የቀመሽውን ገላ መድገም አትወጅም መሰለኝ። ይሄ እኮ የሴቶች ሳይሆን የእኛ ባህሪ ነበር ለወትሮው ...

ቂ....ቂ...ቂ ..."

ሳቅ ይሄን ያህል ይቀፋል?

"ሁሉም ነገር ባጋጣሚ ነው የሆነው "

ቲቸር እዘዝ ቀፋፊ ሳቁን ቀጠለው ።

"ቂ....ቂ ...ቂ 

ለማንኛውም ተረጋጊ ...ጥሩ ጊዜ ነበረን። ጥሩም ሆነን ሴሚስተሩን እንጨርሳለን"

ይሄን ሲል እየዛተ ነው። ለኔ ጥሩ ካልሆንሽ ጥሩ ጊዜ አይኖረንም ሊለኝ እንደፈለገ ግልፅ ነው።

"እባክህ..."

አላስጨረሰኝም ። ስልኩ ከወዲያኛው አቅጣጫ የመዘጋት ድምፅ አሰማኝ። 

ካሁን በኃላ ትምህርት ቤቴ ገሀነሜ ነው። 

ዶክተር እዘዝ የሰይጣኑ ቁንጮ ሉሲፈሬ ነው።

ዛክን በድዬ ከሱ ጋር ያሳለፍኩትን የአልጋ ላይ ጨዋታ እንደማልደግመው አውቃለሁ።

ገላዬን ስነሳው ደግሞ ነጥብ እንደሚነሳኝ እሙን ነው ። 

የኔና የሱ ግንኙነትን ደግሞ ዛክዬ ከሰማ ሌላ የህይወት ፍላት ላስተናግድ ነው ።

ሁለት ፍላት በአንድ እስትንፋሴ የምሸከምበት አቅም ያለኝ አይመስለኝም።

አልጋዬ ማህፀን ገብቼ ተሸፋፍኜ ተኛሁ ።

የውሸት እንቅልፍ ነበር ...

ሰኞ ትምህርት ቤት ስሄድ ለሚገጥመኝ ጦርነት ልቦናዬን ማዘጋጀት ጀመርኩ ።

አሸናፊው ማን እንደሚሆን እናያለን! 

@wegoch
@wegoch
@paappii
Forwarded from ❀ርብቂ Ribki Photography (Ribka Sisay)
በጠዋቱ በበሩ ሳልፍ ባንዲራውን ውጪ አስጥቷል....ባዶ እግሩን በራፉ ላይ ዘፍ ብሏል...ለንቦጩ አጀብ ነው...በደስታ የተወረረ ሰው ቢያየው ያኮርፋል...የሚጋባ ለንቦጭ አጣጣል...ወይ ጉድ!!!

ማንን ይሆን ያኮረፈው?
ባንዲራውን??

ነገሩ ትላንት ማታ ሰክሮ ሲዘፍን ሰምቼው ነበር.....

ተደጋግፈን እንዳወጋን ...እኔም ያንቺ አንቺም የኔ ወገን....ተለጣጥፈን እንዳዜምን ...እኔም ያንቺ አንቺም የኔ ዘመን...መኩሪያራዬ መነሻዬ የኔ ዘለበት....መከታሽን ደጀንሽን ምን ባጠፋው ተውሽኝ....ተለየሽኝ

እያለ ሲያላዝን ነበር ...በስተመጨረሻማ በታተንሽኝ እያለ ይጮህ ጀመር...ይሄ ማህበር የሆነ ሰውዬ😏
.............
Photo: Mar,11,22
Addis Ababa,Ethiopia
© Ribka Sisay
@ribkiphoto
................
#ፍቅር በዚያ ወራት

(ክፍል 6)

........ሚካኤል.አ 

ሰኞ ከባድ ነው ። ከቀን ሰኞ ከወር ግንቦት ይከብደኛል። 

በዛ ላይ ሰኞነቱ ብቻ ሳይሆን ትምህርትቤት ስሄድ የሚገጥመኝ ጦርነት አለ ።

ጠላቶቼ ሁለት ናቸው!

ዶክተር እዘዝና ነጃት ...

የትምህርት ቤቱ በራፍ ጋር ስደርስ እግሬን ብርክ ብርክ አለኝ።

"ንፁህ ድፈሪ! "

እንዲህ ነኝ። 

ዮሀንስ አፈወርቅ ከጦርነት ሁሉ ትልቁ ጦርነት ራስን ማሸነፍ ነው ይላል ።

ሰማዕት በወፍጮ ይፈጫል...ስጋው እንደ ዱቄት ይበተናል...ገላው ይሰቀላል።

የዛን ዘመን ፅድቅ መመዘኛ ይሄ ነበር። አሁን ዘመን ተራቆ ከአካል ውጊያ ይልቅ ሰይጣን ጦርነቱን ቀይሮ ራስን በራስ ላይ አስነስቷል።

መቆሸሽን አውቆ ራስን ለንሰሀ የማዘጋጀት ጥፋቱ የቱ ጋር ነው?

ሁላችንም ከጥፋት ጋር ተወልደናል...ሀጥያትን በህይወት ልምዳችን ቀስመናል ... 

ሀጥያት እንደ ውሀ ነው ። እያሳሳቀ ሲውስድ እየሄድኩ ነው ወይ? ብለን ሳንጠይቅ ሄደናል።

መጠጥ...ዝሙት.. .ክፋት ሲወስድም ልክ እንደዚህ ነው። የትኛውም ሱሰኛ ነገ ሱሱን እንደሚያቆም ስለሚያምን ሱሱኛ ነኝ ብሎ አምኖ አይናገርም። 

ግን አንድ ከሰዓትን ጫት አልያም ሲጃራ መዝለል አይችልም።

የእኔን ውልደት የምፈልገው በዚህ መንገድ አይደለም።

ዶክተር ዛኪን ሳገኘው ከሌላ ወንዶች ጋር ተኝቻለው የሚል የመቅለል ስሜት እንዳይሰማኝ መበርታት አለብኝ። እኔ የምሸነፈው ከሱ በፊት የነበረኝን የወንድ ታሪክ በማሰብ አይሆንም። ከዛኪ በኋላ የምትኖረው ንፁህ ሌላ ታሪክ ነች። ቀሚሷ ለየትኛውም ወንድ አይገለብም...ይህች ንፁህ ድንግል ናት። 

ከዛክ ውጭ ማንም የማህደሯን ቁልፍ ከፍቶ አይጎበኛትም። ከዛኪ በኅላ አሸናፊ ነኝ።

ይሄን እያሰብኩ ወደ ክፍል ኮሪደሮች ተጠጋሁ ።

ዶክተር እዘዝን ሳየው ከመቼው እንደዛልኩ አላውቅም !

ሀፍረቴ ጀመረኝ። ያ ሁሉ ጀብዴ እምን ጉድጔድ ገባ ደግሞ ?

ይህ ሰው አውቆኛል...አሁን እሱ ላይ ልኩራ ብል እንኳ ቀምሻታለሁ ብሎ ይመፃደቃል ።

ይሄ ነው የእኔ ብስጭት!

ብዙ ሴቶች ለደረሰብን ወንድ ደካሞች ነን።

ስንቱ አይደል እንዴ ወልዶ ከብዶ አብቅቶ ከድሮው ፍቅረኛው ጋር በስህተት የወደቀው?

ወንዶችም ይሄን ስነ ልቦና ስለሚያውቁት ማገዶ እንደማንፈጅ አስበው ይደፍሩናል።

ቀድሞ ገላችን ላይ የተኛ ወንድ ቀለበት ም ልጅም እያየ የማሸነፍ ሞራል አለው።

እዘዝም በራስ መተማመኑ የመነጨው ከዚህ ይመስለኛል።

"ከክላስ በኋላ ደውይ ። ራት ከኔ ጋር ነሽ!" አለኝ።

ምንም አልመለስኩም። እንቢ የማለት ድፍረቱን አያሳጣኝ ያለው ስህተቴ ና ይሄ ግሬድ የሚሉት የአጋንንት መምህራን ሰንሰለት ነው።

እሱን እንቢ ብለው የትምህርት ህይወቴ እንደ ሸማኔ ቤት ይዝረከረካል ።

ዛክን የማጥመድ ሩጫዬ ቀለበት ውስጥ ይወድቃል ።

እንጃ ብቻ ዝም አልኩት ።  ዝም ማለቴ ለሱ እሺታ ነው። ለምን አልልም? 

ስህተቴ ለሱ የጨመረለትን በራስ መተማመን የኔ ፀፀት ሊቋቋመው አይችልም። በዛ ላይ ብስጭቱም አለብኝ።

ክፍል ገባሁ...

ስጋዬ ወንበር ላይ ተቀመጠ ። መንፈሴ ከጎኔ የለም። ሁሉም ተማሪ "ተሻለሽ ?" ይለኛል።

"አዎን ይመስገን " እላለሁ በባዶ እስትንፋሴ።

ነጃትን አየኋት ደግሞ ...

ከሩቅ እጇን አውለበለበችኝ። የሽንፈቴ ሰንደቅ አላማ የተውለበለበ ነው የመሰለኝ።

አፍታ ቆይቶ መልዓኬ መጣ ።

ክፍሉ ውስጥ ሲገባ ደስ የሚል መዓዛው ያውደናል ። ቀሳውስቱ በቅዳሴያቸው እጣኑን ሁሉ እሱ ላይ ይሆን የሚያጨሱትን?

ፊቱ ላይ ሰላም ያረባል...የሆነ ቅዱስ መንፈስ የሚከተለው ይመስለኛል።

"Welcome ንፁህ " አለኝ የሱን ትቢያ ሴት ።

አንገቴን በአክብሮት ወዘወዝኩለት። ነፍስያዬም እኮ እንዲህ ነው የምትዘልለት።

ከተዘፈዘፈችበት በክሪክ የማትነሳው ነጃት ዳስተሩን ተቀብላ ሰሌዳውን ስታጠፋለት ቀናሁ።

አያት ...

ደግሞ የሚያያት በስስት ነው ። በ አንድ ሰዓት ክፍለ ጊዜ ስድሳ ጊዜ እየሰረቀ ያያታል።

አበድኩ !

ባዶ ነፍሴ ቃተተች። 

እሱ አስተምሮ ... ሌሎች መምህራንም አስተምረው (ያስተምራሉ መሰለኝ)...ክፍለ ጊዜው ተገባደደ።

ነጃት ቀረበችኝ።... ላናግራት ስላልፈለግሁ ፊቴን አጨማድጄ ዝም አልኳት ። ደንግጣለች!

እንኳን መደንገጥ ለምን እንጦረጦስ አትወርድም?

የመጣችብኝ በሰላሜ ጣዖት ዛክ ነው። 

ሰው መጥላት የማልችለው ንፁህ ሰው ጠላሁ ። አምርሬ ጠላኌት ።

ስወጣ ፍጥነቴ ለራሴ ይታወቀኛል ። ከሩጫዬ የገታኝ የዛ ሰላቢ ስልክ ነው ። 

የሞባይል ስልኬ ላይ የደወለው እዘዝ ነው ።

ዝም ልበለው ይሆን?

እሺ ነገስ ?

እሺ ከነገ በስቲያስ?

ትምህርቴን ላቁምን ? ዛኪን አልየውን ?

የእዘዝን ስልክ ሳያነሱ ፊት መንሳት እኔን ከፉክክሩ ገበያ የሚያወጣኝ መሰለኝ።

ስልኩን ካነሳሁት ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ፀፀት ላስተናግድ ነው።

እንጃ ብቻ በደመነፍሴ ስልኩን አነሳሁለት.. .


ይቀጥላል.. .

@wegoch
@wegoch
@paappii
ከበደሉ በጣም እንደው በጣም ያመመኝ እንደሚያዝንልኝ መዘብዘቡ ነው ፤ ያደረገውን
እያወቁ በዳይ ፣ አዛኝ መስሎ ሲጎዘጎዝ ሳይሰቀጥጠው መስማት የሚቻለው ምን አይነት
ጆሮ ነው !? አለማችን ያጎደፉት እየበደሉን ደግመው መጥተው ለበደላቸው ከአራምባ እና ቆቦ ምክንያት እየደረቱ የሚደረድሩ ፤ ተጠቅመው ሳለ እንደተጎዱ ሙሾ የሚያወርዱ ተርመስማሽ ነፍሶች ናቸው ። ደሞ የበደሉት ስለሚያብለሰለስሏት በደላቸውን ማፍዘዣ አሳማኝ የምትመስል ነገር አያጡም። ግሩምም የሚጠቅመውን ፣ የሚያምንበትን ደስታውን ለማግኘት የቻለውን ነገር ሁሉ አድርጎ የክህደቱ ህመም ትኩሳት እየፈጀኝ ሳለ መጣ ሊገስፀኝ ፣ መጣ የካደኝን አሳማኝ ያለውን ምክንያት ሊተነትን። አላማው አንድ ነው የጥፋተኝነት ስሜት ሲያቃጭልበት ማስታገሻው ሊያደርገኝ ነው ። ይሄ እውነት የሚጠፋኝ መስሎታል ፤ የቂል ሰው ድክመት በተወሰነ ነገር ሲበልጠን በሁሉም ነገር የሚበልጠን ይመስለዋል ። በእርግጥ እኔ አፍቃሪ ስለሆንኩ እሱ ላይ ያለኝ ተስፋ ጨርሶኑ ስላልሟሸሸ አዲስ ነገር ከነገረኝ ብዬ ሲቀጥረኝ ቀድሜ ነበር የደረስኩት የቱ አፍቃሪ ነው ያፈቀረውን ሰው አንደበት ችላ ማለት የሚቻለው ?!
አፍቃሪ መቼም የዋህ ፍጥረት ነው ፤ ተስፋው እንደበልግ ዝናብ ጥፍት ብርት የሚል! ሲቀጥረኝ አዲስ ነገር ጠብቄ ፣ አምሬ ለመገኘት መስታወት ላይ ተገትሬ ፤ ሊለኝ የሚችሉትን ነገሮች አውጠንጥኜ ፤ ፀልዬ ከቀጠሯችን እጅግ ፈጥኜ ተገኘሁ ግሩም ያው ነው አለባበሱ ፣ አወራሩ ፣ ብልጣብልጥነቱ ያው ነው። በራሱ መንገድ ለመሄድ ፍቅሬን ተረማምዶት በአዘንኩልሽ ሰበብ የልቡን ፀፀት እየዘበዘበ ይመክረኛል ።
ዝምታ እኮ ወርቅ ነው ፤ ስለምን ዝም አይልም?
ወይ ጭራሹኑ ቢጠፋስ ! በመንገዴ ዳና እየተከተለ ባያደማኝ ፤ መድማቴ ስላልገባው ይሆን ወይስ የራሱን ስሜት ለማጥገብ ይሆን ? ብቻ ሌላ ፀፀት እንዲሰማኝ ዶልቶ ነው የመጣው ። ከጀርባዬ ተሸሽጎ ያደረገውን ሆነ በግልፅ ያደረገውን በደል እኮ አውቃለሁ ምን አለ ይቅርታ
በድያለሁ ብሎ ቢሰናበተኝ ንስሃ ለመግባት ሄዶ ለንስሃ አባቱ ንፁህ ነኝ እያሉ ለማሳመን መዳከር ምን ይረባል? አንዳንድ ሰው ብልጥቱን የትም አስከትሎት ይገባል ፤ ለመንፃትም ሄዶ ቀድሞ ከሰራው በደል የበለጠ ሃጥያት ይከምራል
ግሩምን ሰማሁት ፤ አንድም ለእኔ የሚጠቅም ነገር አልያዘም ፤ ከፀፀት ለማምለጥ ነው
የመጣው ፤ ሊኮንነኝ ነው የመጣው ፤ በእኔ ምክንያት ስላጣው ነገር ሊነግረኝ ቃላት ሰናንዶ
ነው የመጣው። ለተካደች ፣ ለተበደለች እንዲህም ሆና ለምታፈቅረው አንዲት ሴት የሚለው ዝባዝንኬ መስማት ምን ይጠቅማታል ?
ምንም !! ስለምን ገና ለገና ታፈቅረኛለች ብሎ
ገና ለገና አንደበተ-ርትዑ ስለሆነ ገና ለገና ድሮ ስላሳመነኝ ገና ለገና ህሊናው ስለቆረቆረው እና ስለሚቆረቁረው ለምን እኔን በማይጠቅመኝ ላይ እና ባልዋልኩበት እንደ ኦሪት ፍየል ይሰዋኛል ።
ይሄን ሁላ የቃል ጋጋታ ሳይራራልኝ ማንጋጋት ነበረበት?? ሰነፍ ሰው ልብ ውስጥ ለመቅረት በሚያደርገው ጥረት ነው ከልባችን አንቅረን
የምናወጣው። በጥሞና ጣልቃ ሳልገባ ከሰማሁት በኋላ ራስ ወዳድነቱ በቀናት ብዛት እንደማይለወጥ ፤ ከነፍሱ ጋ የተጣበቀ ማንነቱ እንደሆነ ተገለፀልኝ ። እንደዛ ለምኜው ፣ ተስዬ ፣ ፀልዬ አምላክ አንተን እንቢ ያለኝ በአንድ ምክንያት
ነው.

ቢራራልኝ ነው!!!


@wegoch
@wegoch
@paappii

#Adhanom Mitiku
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ


@seiloch
@seiloch
Forwarded from ❀ርብቂ Ribki Photography (Ribka Sisay)
ከፊትሽ ለፍርድ ቆመናል!
ያጠፋም እንዲማር የማረም እንዲካስ ፍቃድሽ ይሁን!!
.......
ከአጭር ታሪክ የተወሰደ...
©Ribka Sisay
Feb, 06, 2022
@ribkiphoto
ሌላ ቀንም የአማን ጥያቄ ይከተለዋል ።

“አይ በዚህ ሰሞንማ የሆነ ነገር ተፈጥሯል ! ሎተሪ ወይ ዲቪማ ወቶልሀል 

መሰለኝ ”

ማርኮን በውስጡ የሚጮኸው መልሱ እንዲህ ይላል ። ሎተሪ ምንድነው ? በዛ 

ቢባል ገንዘብ ... የተሻለ ቤት መኖር የተሻለ መኪና መያዝ ። ይሄ ማለት ግን 

የተሻለ ሰውን የማየት ያህል አያስደስትም ። ዲቪስ ምንድነው? ሀገርን ጥሎ 

መኮብለል ፣ ድህነትን ደህና ሰንብት ለማለት የሚጓዙት ዘመናዊ ባርነት ! ይሄስ 

በበረሀ መሀል የፈለቀችን ምንጭ ከማየት በላይ እንዴት ደስ ሊል ይችላል ?

በረሀው እነ ሳባ ናቸው ። ሁሉ ነገራቸው ግለት ነው ፣ ሁሉ ነገራቸው ወከባ 

ነው ። ይስቃሉ ፣ ሲስቁ ይጮሀሉ …….. ካ ካ ካ ብለው ሲገለፍጡ ሲያይ እንደ ካካ ይጠየፋቸዋል ። ሲያወሩ ለአፋቸው ልጓም የላቸውም ። ለፋሲካ እርድተገዝቶ ገበያ መሀል ውስጥ እንደደነበረ በግ መቆሚያ የላቸውም ። ያንን ያነሳሉ ፣ ይሄን ይጥላሉ ፣ ሰው ያንጓጥጣሉ ፣ ከእነሱ የበለጠች ሴት ስትመጣ ስሟን ያብጠለጥላሉ ።

ሁሉ ነገራቸው ትኩረት መሳብ ነው ። እዚህች ምግብ ቤት ውስጥ የምትመገቡ 

ክቡራን ተማሪዎች ሁሉ እኛን ብቻ እዩን የሚል ስግብግብ የታዋቂነት ስሜታቸው 

በግልፅ አፍ አውጥቶ ይጮሀል ።

እኛ ስልጡን ነን ፣ የተሻለ እንለብሳለን ፣ የተሻለ ሽቶ እንቀባለን ፣ የተሻለ ሜካፕ 

እንለቀለቃለን ፣ ከሁሉ እንበልጣለን ፣ ከሁሉ እንለያለን ፣ ፊታችሁን አመድ 

በወረሳችሁ ተማሪዎች መሀል ለተዓምር የወረድን ንግስቶች ነን ፣ የውበት 

ሹሞች ነን እወቁልን የሚል ጩኸት !

እሱ በጩኸታቸው መሀል በተዓምር የወረደ ፅሞና ይታየዋል ፤ ፀጉሯን ተኩስ 

ሳይነካት ተፈጥሮ ያለሰለሰላት ሴት ትታየዋለች ፣ የእግር ጣቶቿ ቀለምም 

ይሁን የሚለጠፍ ጥፍርን አይሹም ፤ ብቻቸውን ውበት ናቸው ። ተረከዟ እንደ 

በረሀ እንቧይ ይቀላል ። ቆዳዋ እንኳን ተነክቶ ታይቶ ራሱ ትንቡክ ብሎ እንደ 

ቲማቲም የሚፈርስ ይመስላል ።

ዝምታዋን ተሻግረው በስልት ከምትገልጣቸው ከናፍሮቿ መሀል ላይ እንደ ነጭ እርግብ ክንፍ የነጡ ጥርሶች አሉ ። አቀማመጣቸው እንደ ሰሜን ኮሪያ ወታደር 

በእኩልነት ነው ። ስድር ናቸው ። ፈገር ስትል ከጥርሶቿ ፍካት በላይ የተወቀረ 

ድዷ የውበት ፍላፃ ይወረውራል ። እንደ መጥቆር ያለ ድድ በስልት ከተሰደሩ 

ጥርሶች በላይ ሲታይ አጃኢብ ያሰኛል ። ዓይኗ አይቅለበለብም ፣ አይቅበዘበዝም። 

ቅርዝዝ ብሎ ይጮሀል ። ከዓይኗ ቆብ ላይ የሚታዩት የሽፋሽፍት ፀጉሮች 

አርቴፊሻል ከሚተከለው ምናምንቴ በላይ ውበቱ ይጎላል። የእጅ ጣቶቿን በርቀት 

አይቶዋቸዋል ። ትንሿ የግራ እጇ ጣት አናት ላይ ቢንቢ የነከሰቻት ምልክት አለ ። ምናባሽ ነው አለቅጥ እንደዚህ የምትቆነጂው? ብላ ቢንቢዋ ቀድማው ስለነከሰቻት ለመጀመያ ጊዜ ሰውነቱን ትቶ ቢንቢ መሆን ተመኘ። እሷ የነካችውን የእንጀራ ጠርዝ ፣ እሷ የተቀመጠችበት ብርኩማ ፣ እሷ የተራመደችበት መሬትን ባደረገኝ ምናለበት ? አለ። ደግሞስ ምን ያለው የወንበር ነፈዝ ነው ተቀምጣበት ስትነሳ ይዞ የማያስቀራት ? ምን ያለው ገልቱ እንጀራ ነው ገና ስትቆርሰው እኔ ልብላሽ ብሎ የማያሰፈስፈው ?

እሺ ከሷ በላይ ውበት ከየት ይምጣላቸው ? ሌላው ቢቀር እሷን የሚያስተምረው 

ጅማ ዩንቨርስቲ ኪቶ ፉርዲሳ ካምፓስን ለምን ዓለም ተሰብስቦ አይሸልመውም 

? ለምን የምርጦቹ ምርጥ መዝጋቢው ጂንየስ ቡክ የእሷን ስም ከደረቱ ላይ 

አልተነቀሰውም ?

ዓለሙን ምን ነካው ? ሰው ፣ ተማሪው ፣ መምህሩ እና ሀገሬው እሷን አይቶ 

እንደዚህ እንደቀልድ ማለፍን እንዴት ቻለበት ? ወይስ ይህች ሴት ለእኔ ብቻ 

የምትታየኝ መንፈስ ናት ? ራሱን ጠየቀ።

“ እንጃ !” መልሶ ለራሱ ጥያቄ ራሱ መልስ ሰጠበት ።
Forwarded from Sunset Hiking
#Sunsethiking is hosting a day hike to " ENSARO"

💡Hiking Date :- July 10, 2021 (Hamle 03, 2014)

💵 Hiking Cost:- 900 ETB only

🛫Departure: Piasa (Taitu Hotel)
@12:30 LT

🎉🎊Package includes🎋🎊

🚍 Transportation
🌲 Bottled water
🌺 Guide + scout
🍂 photography 📷
💐 Breakfast
🏖 lunch
🧜‍♂️ Swimming
☕️ Coffee

💦Sanitizer & facemask mandatory!
☘️walking hour: 3 hour (up to 5 km of walking)
Hiking Level: Medium !

for more join the
🎸@sunsethiking👣
🏓@sunsetphotography📸
🍿@sunsethikers

🎫 tickets available at
@Paappii ( +251922303747)
አንዳንድ ትዝታ አለ
-ዝምታችን -ከዝምታ ገዝፎ በአርምሞ በተዘጋንበት ጊዜ :በዕዝነ ልቡናችን በኩል <<ኡኡ>> ብሎ የሚጮህ ፡፡ በለሆሳስ ÷በዝግታ ካሳለፍነዉ የእድሜ ዘመን፡ ቅፅበቶቻችንን ከሽርፍራፊ የልጅነት ምስላችን በልጦ ፡በልቦቻችን ጥጋጥግ ካንጠለጠልነዉ ፡ ተናፋቂ ትዝታወች መሀል ፡ ምናለ በደገምነዉ እያልን የምንመኘዉ፡፡
ከትላንት ትዝታወቻችን ጋር ፡ ባንቀላፋን ቁጥር ሳንሰለች ደጋግመን የምንኖረዉ፡፡ አንዳንድ ትዝታ አለ ፡ እንደወይን እያደር ጣዕሙ የሚጨምር ፡ በእምባ በተምሸርንበት ጊዜ እንኳ ÷ በሐዘን ወህኒ ተወርዉረን ፡ መረሳት ክፋ እድል ፊት ለፊታችን ሲጋረጥ፡ የመኖር ጣዕም ሲጎመዝዝ ÷በእቅፋ ሚያስጠልለን፡፡ አንዳንድ ትዝታ አለ በዘመን መጎስቆል ባረመምንበት ጊዜ እንደ አዲስ የሚወልደን ፡ የማያረጅ የእድሜያችን ሞቃት ምዕራፍ ፡፡ አነዳንድ ትዝታ አለ --- አየ ጉድ - ትዝ አለችኝ መሰል፡፡

ያብስራ እዮብ(ደብተራዉ)፡፡

@wegoch
#ዋንጫው
(ሚካኤል.አ)
"ቲቲን ቤቴ ልጋብዛት ነው" አለኝ ላሎ ።
በሀሳቡ ለመስማማት ታከተኝ...
"ዛሬ ብር አንባሩን ልደረምስላት ነው። የሆነ ፍንዳታ ከሰማህ እንዳትሳቀቅ" አለኝ ቀጥሎ ...ላሎ ዘናጭ ነው ። ሱፉን ግጥም አድርጎ ሲንቀሳቀስ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተላከ ባለስልጣን ይመስላል ።
ደግሞ ቲቲን ሲተዋወቃት ደህንነት ነኝ ብሎ ነው። የሆነ ሰማኸኝ በለው ስልክ አለው ።
በዚህ ስማርት ዘመን ያን ስልክ ይዞ ሲንቀሳቀስ ያሳዝነኛል ።
የሆነ ቀን አንድ ግሮሰሪ ስንዝናና አንድ ለፍዳዳ ሰካራም እየደነሰ ላሎን ገፈተረው ።
ላሎ የመጀመርያውን ግፊያ በትዕግስት አለፈ ... ሰካራሙ ሰውዬ ጭራሽ እየተለፋደደ.. ."ወያኔዎችን ያባረርነው እንደዚህ መደነስ አምሮን ነው ... ኢንሶዳቲን " አለን። (አትፍሩ ለማለት የተጠቀማት የኦሮምኛ ቃል ነች። አካም አካም አትበሉ ብለው ጠሚው ፓርላማ ውስጥ የተናገሩትን አልሰማም መሰለኝ :) )
ሰካራሙ ጭራሽ ታስራ እንደተፈታች ጥጃ ፊታችን ቧረቀ...ደግሞ ላሎን ገፋው ... (ይቅርታ ደረመሰው ) ... የላሎ ትዕግስት ሙጣጯ ተፈፀመ ።
ከኪሱ ያን ድንጋይ ስልክ አንስቶ የሰካራሙ ግንባር ላይ አስቀመጠው ። ሰካራሙ ሊታረድ እንደተዘጋጀ በሬ አጓርቶ ወደቀ ።
ጭራሽ ከሰውየው ይልቅ ለስልኩ ተጨንቆ ተሯሩጦ አነሳት ።
ያ ስልክ ምን ይሆናል ብሎ እንደሆነ እንጃ!
ስልኩን ሲያነሳው እንኳን ሊሰበር ጭራሽ ከጥግ በኩል የተፈገፈገው ምልክት ጠፍቶ አዲስ ሆኖ አረፈው :)
በቃ ታድያ ላሎ ይሄን ስልክ ሲይዝ ደህንነት ነኝ የሚለው ጨረሩን ይለቃል።
"ተው ቲቲ ደህንነት ሳትሆን መምህር መሆንህን ያወቀች ቀን ጉድህ ይፈላል" ብለውም አልሰማ አለኝ። አሁን ደግሞ ጭራሽ ቤቴ ልጋብዛት ነው ሲል ከማርስ ላይ እንደመጣ ዩፎ ትኩር ብዬ አየሁት ።
ስጋቴን አልመከርኩትም...ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ ነው ! ብዬ ንቄ መተዌ ነው ።
ከዛ በኋላ ስሰማ አምስት ኪሎ የምትገኘው ደሳሳ የኪራይ ቤቱ ሊወስዳት መንገድ እየሄዱ ሳለ አንዲት ሰይጣን የላካት ፈልፈላ "ቲቸርዬ " ብላ ተንደርድራ አቀፈችው ።
ቲቲ መብረቅ የወደቀባት ይመስል ክው አለች። የሎጥ ሚስትን ይመስል የጨው ሀውልት ሆና ቀረች ። (ምስኪን ቲቲዬ !)
ከዛ እንደምንም አምጣ "አስተማሪ ነህ እንዴ? " ብላ ጠየቀችው ።
እሱ ደረቱን ነፋ አድርጎ ...
"ይሄ ከቨር ነው...ደህንነት ሆነሽ በሽፋን ነው መስራት ያለብሽ " አላት.. . ተንደርድራ የተጠመጠመችበትን ፈላ እንደ ሎሚ አሽቶ እየጨመቃት ። (በውስጡ ልጅቷን እንደ ኳስ ማንጠር ሁሉ ከጅሎ ነበር )
ሀውልቷ ቲቲ የእየሱስ እስትንፋስ እንደደረሰው በሽተኛ ነፍስ ዘራች ና መንገዳቸውን ቀጠሉ።
ልክ የላሎ ቤት ሲደርሱ ማመን አልቻለችም ።
ከቤቷ ጥበት የዝርክርክ ካልሲዎቹ ጥንባት ዊድ ሆኖ አዞራት ። ወደ ኋላ ተወነጨፈች።
እንኳን እግሯን ልትከፍትለት የልቧን በር ከርችማ ጥላው ፈረጠጠች (ያው ያለችውን መናገር ለሞራሉ ይከብዳል እንጅ እጅ ማስታጠቢያ ውስጥ እየኖርክ እኔን ስጀነጅን አይከብድህም ? ብላ ቅስሙን ከሽክሻለታለች)
በቃ !
ፍቅር በህንድ ፊልም ላይ ብቻ ያለ መንፈስ መሆኑ ያልገባው ላሎ ሱሰኛ ሆኖ አረፈው።
ሲጃራ እና ሺሻ ሲያንቦለቡል ትንሽ የገጠር ጎጆ ቤት የተቃጠለ ይመስል ነበር :)
ከዚህ ሙድ እንዲወጣ ብመክረው ብዘክረው እንደልማዱ አሻፈረኝ አለ ።
ዛድያ..ያ የተከበረ አስተማሪ ታድያ አንድ ቀን ሺሻ ቤት ሲያውደለድል በሰፈር ሚኒሻና በፖሊስ ተቀበደደ።
ሺሻ ቤቷ መልካቸው ከመወየቡ የተነሳ ያንድ አባትና እናት ልጆች በሚመስሉ ሱሰኞች ተሞልቶ ነበር ።
ከቤቷ ሲወጡ ...እንደ ዳርፉር ስደተኛ በሰልፍ ተቀጣጥለው ነው።
ለክፋቱ ደግሞ ሁሉንም የሺሻ እቃ አሸክመዋቸው በሰፈራችን በኩል ነበር የሚያልፉት ።
አቤት ሀፍረት !
አቤት ውርደት!
ምድር ደግሞ ለክፋቷ ተከፍታ አልውጥም አለቻቸው። ስንት ዶክተር ስንት ጠበቃ እየተግተለተለ ወጣ።
የላሎ አከራይቶ ሁኔታውን በጥንቃቄ ሲከታተሉ ቆዩና ወደኔ ጠጋ ብለው.. .
"ላሎ የምን ዋንጫ ነው የያዘው ?" ብለው ጠየቁኝ።
"የዓመቱ ምርጥ አስተማሪ ተብሎ ተሸልሞ ነው"
"ፎሊሶቹስ ምንድናቸው?"
"ዋንጫው የወርቅ ስለሆነ እንዳይዘረፉ እየጠበቋቸው ነው "
እልልልልልል አሉ እትዬ...
"ላሎ ድሮውንም የሚያኮራ ልጄ ነው ... ተመስገንልኝ ያኔ መድሀኒተ ዓለም :) "

@wegoch
@wegoch
@paappii
2024/09/22 14:39:12
Back to Top
HTML Embed Code: