Telegram Web Link
የመጽሐፍ ውይይት
በ ብሄራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ

መንደሪን መንደሪን
ደራሲ: ምግባር ሲራጅ

@getem
"ድምቀት ወ ፅልመት"



አርብ 'ለት ነበር ፣ 12:00 ሰአት አካባቢ፣ ቀኑ ቀን አልመስል እያለኝ ወደቤቴ ለመሄድ መንገድ ላይ ሳለው አብዶ ይሁን ፣ እያበደ ይሁን ግራ የሚያጋባ ሰው ድንገት በመንገድ ላይ ያገኘኝና ልክ የዘመናት ጓደኛው እንደሆንኩ ያክል ያወራኝ ጀመር።

" አየሀት ያቺን ጀንበር? ....... ፣ ገና እያጎጠጎጠች ያለች ቆንጆ ሴት ትመስላለች ፣ ልክ እንደ አንዲት ሴተኛ አዳሪ ፣ ልክ እንደ አዲስ ፍቅረኛሞች....፣ ግን ፈጣሪ ለምንድነው ይሄን ያክል የምታሳሳ ልጅ ያስመሰላት?............. ግን አንተ ምን ይታይሀል?....... " አለኝ ። እየተከተለኝ ይሁን መንገዳችን ተገጣጥሞ በምታጠፍበት እየታጠፈ ፣ ጀንበሯን አዘቅዝቆ እያየ ይጠይቀኛል።

" እኔ እንኳን ስራ ፈትቼ እሷን የማይበት ጊዜ የለኝም " አልኩት ። እንዲተወኝ ፈልጌ እንጂ ሳላያት ቀርቼ አልነበረም።

" ተፈጥሮ ለማን የተፈጠረ ይመስልሀል ?"

" ያው ለራሱ መሰለኝ " አልኩት ጥያቄው ስላልገባኝ ።
" ተፈጥሮ ሁሉ ለሌላ ጠፈጥሮ ነው የተፈጠረው ፤ ሰው እንኳን ለሌላ ሰው ነው የተፈጠረው " አለኝ አይኑን ከጀንበሯ ሳይነቅል።

"እና ምን ነበር ይታየኛል ያልከኝ" አለኝ ምንም እንዳላልኩት እያወቀ።

" እኔ እንኳን ቆንጆና ደማቅ ጀንበር ናት ምትታየኝ" አልኩት ፣አስተውዬ ለማየትም አልሞከርኩም ምክንያቱም ሰውየው እብድ ይሁን ጤነኛ እርግጠኛ አልነበርኩም።

"አንድጊዜ ቆንጅዬ ልጅ መንገድ ላይ አየሁና መከተል ጀመርኩ" አለኝ ያቺ ቆንጆዋ ልጅ ጀንበሯ አንደሆነች ያክል ወደ ጀንበሯ እያፈጠጠ።

"እሺ......." አልኩት

"ተከተልኳት ተከተልኳት ተከተልኳት....."

"እሺ ከዛስ.." ደገምኩት

"ተከተልኳት ተከተልኳት ተከተልኳት...."
ሳቄ እንደ ትንታ አመለጠኝና ወዲያው ዝም አልኩኝ።

"ተከተልኳት ፣ እንደዚ ቆንጆ ሆና ግን ማንነቷን የሽማግሌ ኪስ ወስጥ አገኘዋለው ብዬ አላሰብኩም ነበር" አለኝ እንደማዘን ብሎ።

"ሌባ ነበረች?"

" ሌባ ህሊናውን ይሸጥ ይሆናል እንጂ አካሉን አይሸጥም ፣ ይቺ ቆንጆ ሰው....ነቷን ሁሉ ነው የሸጠችው ፣ እኔ እሷን መከተሌ ድካም ነው ያተረፈልኝ ፣ አንተም የጀንበሯን ውበት ብቻ ማየትህ የት እንደሚያደርስህ አላውቅም " አለኝና ለትንሽ ጊዜ ዝም አልን። ግን ምን ማለት እንደፈለገ ማወቅ እንዳለብኝ ተሰማኝ።

"አንተ ምንድን ነው ሚታይህ?" አልኩት።

" ታሳዝነኛለች" አለና እንባው እንደቀልድ መውረድ ጀመረ "በጣም ታሳዝነኛለች ፣ ስልጣኑ ቢኖረኝ እንደዚ እንዳማረባት ዘላለም ባቆያት ደስ ይለኛል ፣ ልብ ብለህ እያት ፣ መንገዷን ተመልከት ፣ ቅድም ስንገናኝ የነበረው ውበቷ አሁን የለም ፣ አሁን ያለው ውበቷ ከደቂቃዎች ቡኋላ አታገኘውም ፣ መንገዷም መጨረሻዋም የከፋ ነው " አለና ጣቱን ወደጀንበሯ እየጠቆመ ፣
" አንቺ ጀንበር ተጠንቀቂ ፣ ቀን ወደነበርሽበት ተመለሺ !!" አለና ሳይሰናበተኝ በመጣንበት መንገድ ተመለሰ።

ምን ሊነግረኝ ፈልጎ ነው? ፣ ማንስ ነው የላከው ?፣ ጀንበሯ ማነች? ፣ ቀንስ ምን ነበረች ?፣ አሁንስ ምን ልትሆን ነው? እያልኩኝ እራሴን ስጠይቅ ያቺ ገና እያጎጠጎጠች ያለች ቆንጆ ሴት የምትመስለዋ ፣ ልክ እንደ አንዲት ሴተኛ አዳሪ የምትመስለዋ ፣ ልክ እንደ አዲስ ፍቅረኛሞች የምታስቀና የነበረች ጀንበር አሁን የለችም ፣ ምድሪቱን ጨለማ ወርሶታል ፣ እኔም ከነጥያቄዎቼ ወደ ቤቴ ገባሁ ።

(ቤካ)

@wegoch
@wegoch
@paappii
-ፅልመት-

ክፍል ሁለት

ከቤተልሄም ጋ በጋራ ወደ ቀለስኩት ጎጆ ሄድኩ ።
ሳሉ አምላክ እንዳየቺኝ ሰላም ሰሌ? አለቺኝ ፤ በስሱ ሰላም ሳሉ ብዬ አጉተመተምኩ። ሳሉ እቤት የምታግዘን አጋዣችን ናት። ቤቴ ያ ቅድም የወጣሁበት ቤት አልመስልህ አለኝ ። አስጠላኝ። ሳሉ "ምነው አመመህ እንዴ" አለቺኝ ምነው? ስላት ፊትህ ጥሩ አይደለም አለቺኝ "አዎ አሞኛል" አልኳት ቀና ስል የሰርጋችን ፎቶ ግድግዳ ላይ ተለጥፎ አየሁት ። ትክ ብዬ ስመለከተው ከግድግዳው ላይ አውረደህ ሰባብረው አለኝ 'ማደጋችን የሚለካው የምንፈልገውን ሁሉ ባለማድረግ ነው' ቀጥታ መኝታ ክፍል ሄጄ ተኛው ። እኔ ገብቼ ጋደም ካልኩ አንድ ሰዓት ቆይታ
የድሮ ሚስቴ ገባች መቼም የድሮ ሚስቴ ነች ። የተፋታነው ቅድም ሆቴል ውስጥ ያን ክንውን ካየሁ በኋላ ነው። አልመጣም እንዴ ሰሌ ስትል ሰማኋት ፤ ድምጿ ለካ ያስጠላል ። ነገሩ ከሃዲ ደሞ ምኑ ያምራል ? ትንሽ አሞታል አለቻት ። ምነው ጠዋት ደና አልነበር እያለች ወደ መኝታ ክፍላችን ስትመጣ ኮቴዋ ይሰማል ። እንደ ተኛው መሰልኩ። ህመማችን የሚባባሰው የበሽታዎቻችን ምክንያት እናክምህ ሲሉ ነው።
ወዳጃችን ሲያቆስለን ህመማችን የሚበረታው እንደሚያስብልን ማስመሰሉ ስለማይቀር
ነው። ብርድ ልብስ ውስጥ ተጠቅልዬ ማሰብ ማቆም ያልቻልኩት ነገር ቢኖር ክህደቷን ነው ።
ሰው ከካደው ጋ እንዴት ኑሮን ይገፋዋል ። አለማወቅን የመሰለ ነፃነት የት አለ ?! ዛሬ እዛ
ሰዋራ ሆቴል ባልገኝ መቼ ህይወት ይገለበጥብኝ ነበር??? እስከዛሬ አልፎ አልፎ በኔ ጉትጎታ ብቻ የምንዋሰበው ለካ ውጪ ከማንም ጋ ስለምትጋደም ነው። ለካ እስከዛሬ ለቅሶ ገለመሌ እያለች አምሽታ የምትመጣው የትም ስትሸረሙጥ ነው ! ጭንቅላት አንዴ አይመረዝ አዕምሮ ውስጥ የሚመጣ አንድ መልካም ጥንጥዬ ነገር እንኳን
አይኖርም ። በጣም ሲመሽ ሰሌ ሰሌ እያለች ቀሰቀሰቺኝ ፤ ቀና አልኩ ፊቴን ስታየው ደነገጠች ፤ ድምጿን ጮክ አድርጋ እንዴ ምነው በጣም አመመክ እንዴ ምን ነው?? ዝም ብዬ ትክ ብዬ አየኋት ። ፊትህ ጠቁሯል ፤ አይንህ ብር ብሏል፤ በጣም አልቦሃል ፤ ምን ሆንክ? ሃኪም ቤት እንሂድ
እያለች ብዙ ቀላበደች ። ፊቴ እንደተጨማተረ ፤ በአስለቀሰችው አይኔ ትኩር ብዬ እያየኋት ደህና ነኝ! አልኳት ሁኔታዬን አይታ ይመስለኛል ቃል አልተነፈሰችም !! ፒጃማ ቀይሬ ተመልሼ ተኛው ፤ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ፤ በጣም በጠዋት ወደ ስራ ሄድኩኝ ። በዛ ሰሞን አመመህ? ምን ሆነሃል ? ከሳህ የማይለኝ አንድም ወዳጅ ጠፋ ።
የውስጥ ሰላም ሲናጋ ፤ የማይናጋ የሰውነት ክፍል መቼ ይኖራል ። ዘውትር ማታ እቤቴ ስመጣ የማንጠለጥለው አትክልት ፣ ኬክ ፣ ዳቦ እርግፍ አድርጌ ተውኩት ። እንደበፊቱ ልጄን ማጫወት እያንዳንዷን እንቅስቄሴ መጠየቅ አቆምኩ ።
ለካ ሰነፍ ሴት የሞቀ ቤት ታቀዘቅዛለች። ቤተልሄምን አላኮረፍኳትም ፤ ሰው የሚኳረፈው ጭላንጭል ፍቅር ሲኖር ነው። ስታወራኝ
እመልስላታለሁ። ቤተልሄም ምክንያታዊ እንደሆንኩ ስለምታውቅ ዝምታዬን አትንቀውም ።ኮስተር ብዬ ያኮረፍኩበትን ጉዳይ ስናገር ፤ የምዘረዝረው አሳማኝ ምክንያት እንደሚኖር ትላንታችን ምስክር ነው። ምክንያታዊነትህን እወድልሃልሁ ትለኝ ነበር ። እንደምትወደኝ ተጠራጥሬ አላውቅም ነበር አንድ ቀንም !ነፍሴ ተጠይፏታል ። ጎጆ እንደ እምነት አይደለም በአንድ ለሊት አይደረመስም ። ቤቴ ላይ
የማፈሰውን ትኩረት እርግፍ አድርጌ ተውኩት ። ስለወጪ ከሳሉ ጋ ብቻ አወራለሁ። ቤቴ በቶሎ ላለመግባት የድሮ ጓደኞቼን ማሰባሰብ እና መጠጣት ጀመርኩ። አንድ ቀን የያሁት ነገር ኑሮዬን ቀለበሰው ። የነበረኝን ፍቅር ደረመሰው ። ፍቅር እንደዚህ ማያያዣው ስስ ነው??
ስለ አለም የነበረኝ ምልከታ ተዛባ ።
እንዲ እየኖርኩ ሳለ አንድ ቀን ወደ ስራ እየሄድኩ የተሳፈርኩበት ታክሲ አቅጣጫ ስቶ ሲበር ይመጣ ከነበረ ዘመናዊ የቤት መኪና ጋ ተላተመ። ከውስጣዊ ስብራት ሳልጠገን ሌላ ውጫዊ አደጋ
ይቀጥላል...

@getem
@getem
@paappii

#Adhanom Mitiku
የጁመዓን ሲሳይ አያውቁም። ዱዐ በማረግ ፈንታ በየጎዳናው ይቅበዘበዛሉ። ከዛ ቅዳሜ ሲሆን አላህ እኔን አይሰማኝም እያሉ ያማርራሉ።

ያ ረቢ ሳይጠይቁ የሚጠብቁህን ምንድነው ምታደርጋቸው? ከእኛ እኩል ነው የምታያቸው?

......
ጁመዓ ሙባረክ💛
...
©Ribka Sisay
....
@ribkiphoto
@wegoch
Forwarded from ❀ርብቂ Ribki Photography (Ribka Sisay)
ካራማራ ጫፉን አያይዤ ልስፋው?
ካራማራ አናቱን ሻሽ ልደርብለት?
ካራማራ ልቡን በምን ላርስለት?
....
©Ribka Sisay
....
@ribkiphoto
Forwarded from ❀ርብቂ Ribki Photography (Ribka Sisay)
ለመጨረሻ ጊዜ ያቀፍኩት እዚህ በር ጋር ነበር:(
ያቺ ሴትዮ ስለማትወደኝ ወደ ቤታቸው ገብቼ አላውቅም።
ሰላሳ ሶስት ሳምንት ከሶስት ቀን ሙሉ አልደወለልኝም:(
ስለዚህ ንጋት እዚህ እየመጣው እጠብቀዋለው! እዚህ ስውል ያቀፈኝ ያቀፈኝ ይመስለኛል!
የሳቅነው ያስለቅሰኛል! የተደሰትንበት ያናድደኛል!

ቆይ ተስገብግበን ናፍቆት ብንለማመድስ ኖሮ?
ቆይ የማላውቅበትን ጠብቅሃለው ምን አስባለኝ?
ቆይ ምንአባቱ የማይመጣልኝ?
ቆይ ምን አባቱ የማያቅፈኝ?
ቆይ ምናአባቷ ይቺ ሴትዮ ስታየኝ የምታዝነው?
..........
©Ribka Sisay
..........
@ribkiphoto
-ፅልመት-

ክፍል ሶስት

ከአራት ቀን ራስን መሳት በኋላ አንድ ትልቅ ሆስፒታል ውስጥ ራሴን አገኘሁት። ጭንቅላቴ የእኔ እንዳልሆነ እስኪሰማኝ ድረስ ህመሙ ከብዶኛል ፤ አንገቴን ላዞር ስሞክር ህመም ተሰማኝ ለካ የአንገት ድጋፍ አጥልቄያለሁ ፤ እግሬ በጀሶ ተጀቡኗል ፤ እንደ ቄስ ጥምጣም የዞረው ፋሻዬ ጭንቅላቴን አልብሶታል። ምን በድዬ ነው አካሌም መንፈሴም አንድ ላይ እስኪጨረምቱ የቆሳሰልኩት። እጅግ ተሰቃየሁ ። ምኔን ላስታም ። ቀና ስል ወንበር ላይ ኩርምት ብላ የተቀመጠች የድሮ ሚስቴን ብቻዋን አያታለሁ። ከስሬ አጠፋም ፤ እዛው ነው የምታድረው ፤ የግሏን ስራ ብትሰራም እኔን ለማስታመም የተወችው ይመስለኛል። አይኔን ስገልጥ አጥቻት አላውቅም ሊጠይቁኝ የሚመጡት ወዳጆቼ እንቀየርልሽ ቢሏት ፤ ዶክተሮቹ ቢመክሯት ፤ የድሮ ሚስቴ
አንገቴን በካራ አለች ፤ ከእዚህ ሆስፒታል እሱ ካልወጣ አልወጣም አለች። ፊት አልሰጣትም ፤ አላዋራትም ። እገላምጣታለሁ እቆጣለሁ ፤ ታለቅሳለች። እነጫነጫለሁ፤ አጉተመትማለሁ ፤ አሽሟጣታለሁ ። በጥቂት ወራት ውስጥ ከሰውነት ተራ ወጣች ማንም ሰው ጥሩ ገቢ ያላት ፤ ፋሽን የምታሳድ ፤ ዛሬ የለበሰችውን ነገ የማትደግም ነበረች ቢባል ግነት ይመስላል። ያለን ነገር ጠቅላላ በነበር ተከበበ ። እኔን ሊጠይቁኝ የሚመጡ ሁሉ ከሰውነት ተራ መውጣቷን እያዩ ዞር ብለው እሷን ገስፀው ፤ አፅናንተው ይሄዳሉ ተቆርቆሪነት በወለደው የወዳጅነት መንፈስ ።
አንድ ቀንም ምግብ ብይ ተጎሳቆልሽ ፤ቤት ሂጂና እደሪ ብያት አላውቅም ፤ በወጉ ስትበላም
ስተኛም አይቻት አላውቅም። የሆነ ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ የድሮ ሚስቴን ሳያት ማድያት ጀማምሯታል ። ፀጉሯ ተሰባብሯል ፤ ሽበት ጀማምሯታል ፤ የለበሰችው ቱታ ራሱ ተነጫጭቶል ። ስቆጣት አይኗ እምባ ሲቋጥር ፤ ስታጎርሰኝ በክፉ አይኔ ሳያት ፤ የስሜቴን መቆጣት ስታይ እያለቀሰች ነበር
የምታጎርሰኝ ። ከቀናት መንጎድ በኋላ ኩርምት ካለችበት ቦታ ላይ ሸለብ አርጓት ሳያት ያለፉት የሆስፒታል ቆይታችን ትውስ አለኝ ፤ አሞኝ ሳቃስት እሷ ስትርበተበት ፤ በስሜቴ መኮማተር የወረደው
እንባዋ ፤ ለመንካት እንኳ በራቀ መልኩ ገላዬን በፎጣ ስታብሰው አንድ ባንድ መጣልኝ ። በእዚህ ሁሉ ፊት መነሳት ውስጥ ፤ በእዚህ ሁሉ መነጫነጭ ውስጥ ልጃችን ኤዶም ጋ
እንኳን ልሂድ ብላ ከሆስፒታል ጥላኝ ወጥታ አታውቅም ። የሁለታችንም ቤተሰቦች
ባይኖሩም የቅርብ ጓደኞቼ እንኳን እንደር ሂጂ ቢሏት እሱን ትቼ ነው የምትለው ኤጭ
ፍርጃ ነው ለዛች እምነቴን ለበላችብኝ ። ለዛች አይኔን ላስለቀሰችው፤ ለዛች ልቤን ለሰበረችው ፤ለዛች አንገቴን ላስደፋችው ፤ለዛች ሳቄን ለቀማችው ፤ለዛች ቀልቤን ለነጠቀችው፤ ለዛች ቤቴን ላቀዘቀዘችው የድሮ ሚስቴ። አሳዘነችኝ !! ከስንት ወር በኋላ ቤተልሄም አልኳት ደንግጣ አየችኝ

ይቀጥላል ....

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Adhanom mitiku
-ፅልመት-

ክፍል አራት

ቤተልሄም አልኳት ደንግጣ ትኩር ብላ አየችኝ ፤ከስንት ወር በኋላ ነው የጠራኋት ድሮ ድሮ ለቀልድ ነበር ሙሉ ስሟን የምጠራት ፤ ድሮ ድሮ ቤተልሄም ስላት ጌታዬዋ ነበር የምትለኝ። ዛሬ ቤተልሄም ብዬ ስጠራት ደንግጣ አፍጥጣ ብቻ አይታኝ አጎነበሰች ፤ ጌታዬዋ ማለት የፈለገች ይመስለኛል ግን ደግሞ ከንፈሯ አልላቀቅ ስላላት ነው ወዬ ማለትም ፈልጋለች ፤ ጆሮዋን ጠርቻት ይሆን አይሆን ማመን ስላልቻለች ነው። ቀስ ብላ በለሆሳስ እየተራመደች ጠጋ አለችኝ እረጋ ብዬ ለስለስ ባለ ቃላት ምነው አልኳት? ትኩር ብላ ከወገቤ ብቻ ቀና ያልኩበት የሆስፒታሉ አልጋ ላይ ቁልቁል በስስት ተመለከተችኝ። ቤት ለምን አትሄጂም ኤዶሜ አትናፍቅሽም አልኳት? አልጋ ላይ እርፍ ብለሽ ፤ ጠንከር ብለሽ ብትመጪ አይሻልም አልኳት ቀስ ብላ በእርጋታ አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ አለች። በስስት በመኪናው አደጋ ሳቢያ የተጎዳውን ሰውነቴን እያየች ። "ትንሽ ቀን ነው የቀረን አብረን እንሄዳለን አለችኝ "። አንች እኮ በጣም እየተጎዳሽ ነው አልኳት። አይኗ በፍጥነት ትኩስ እንባ አረገዘ ጭኔ ላይ ያረፈውን እጄን ሳመችው ። እጄን እንደያዘች ፤ "አንተን ለማን ጥዬ" ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። እጄ በእንባዋ ራሰ ዘማዊቷ መቅደላዊት የጌታዋን እግር በእንባ ስታጥበው የነበረው የንስሃ እንባ ከቤተልሄም እንባ ጋ ተመሳሰለብኝ ። እጄን ከእጇ በቀስታ ነጥቄ የተሰባበረ ፀጉሯ ላይ አደረኩት ። ፀጉሯን ሳሻሻት ፤ ሆዷ ባባ መሰለኝ ፤ የበለጠ አለቀሰች ፤ ሲቃ እየተናነቃት ተንሰቀሰቀች ። ከሲቃዋ ጋ እየታገለች ፤ ቃላቷ እየተደናቀፈባት "ለእኔ ባረገው !" አለቺኝ ። እንዲህ ያለቀሰችው አባቷ የሞቱባት እለት ብቻ ነው ። አለቃቀሷ ፤ ጉስቁልናዋ ፤ ኩርምት ማለቷ አንጀቴን በላው መሰለኝ አይኔ በእንባ ሞላ ። አቅም አነሰኝ እንጂ እንዲህ እየወደድሺኝ ለምን ካድሺኝ ማለት ፈልጌ ነበር። ነገር ግን ማለት የቻልኩት እንደዚህ ራስሽን የሚያስጥልሽን ፤ በዓይንሽ ሙሉ እንዳታይኝ የሚያደርግሽን ስህተት ውስጥ እንዴት ገባሽ አልኳት ?? ቤተልሄም የአይኗ ሽፋሽፍት በእንባ እንደተጨማለቀ በሃሳብ ሄደች ግሩም ጋ ግሩም እቃ የሚያስረክባት ደንበኛዋ ነው። በቴሌግራም ፤ በሜሴንጀር እቃ ያሳያታል ፤ ይጨዋወታሉ ፤ ይከባበራሉ ። ግሩም ነፃ አይነት ሰው ነው ፤ የፈለገውን የሚቀልድ አይነት ፤ በቤተልሄም ግዙፍ መቀመጫ ላይ ያሾፋል ፤ ብቻውን ይስቃል ፤ ወፍራም መቀመጫ ላለው ምን አይነት ወሲብ
ምቹ እንደሆነ ይቀላብዳል ። ትሰማው ትሰማው እና አንተ ጨምላቃ ትለዋለች። ሌላ የስራ ወሬ ይቀጥላል። ክችች አይልም ። እንደዚህ አይነት ቀልድ እና ጨዋታ ከእሷ ጋ ብቻ እንደሚጫወት ሹክ ይላታል ። ቁንጅናዋን ያስታውሳታል ፤ ያከብራታል ወይ እንደሚያከብራት ያስመስላል።
ከሌሎች አቅራቢዎች የተሻለ በጥሩ ዋጋ ስለሚያቀርብላት ፤የገዛቸውን እቃ ገንዘብ በቶሎ
አምጪ ስለማይላት ሙጥኝ ብላበታለች
ግሩም ምቹ ጊዜ ሲያገኝ ፤እንዴት አጣፍጦ እንደሚዋሰብ ይተርክላታል። ጡቷን እንደሚያምር ጠቆም ያደርግላታል ፤ ከወሲብ ወጣ ያለ ቁምነገርም ጨዋታም ያወራታል። ቁም ነገር ሲያወራት ፤ ሸፋዳነቱን ያስረሳታል ፤ ወሲብ ነክ ጉዳይ አይቀላቅልም በሌላ ቀን ይመጣ እና
ስለወሰባት ልጅ መቁነጥነጥ ፤ ማቃሰት ፤ መሻፈድ እርካታ እያዋዛ አፏን አስከፍቶ
ይተርክላታል። አወሳሰቤ ስቧት ድገመኝ ያላለችኝ የለም እያለ አለስልሶ ይጎርራል ከዛ ወሲባዊ ወሬውን አያስረዝመውም ፤ እሷ ከራሷ ጋ ታግላ ከማስቆሟ በፊት ራሱ ያቆማል ። እንድታወራለት በትንሹ መንገድ ስትከፍትለት ሆን ብሎ እንዳልገባው ይሆናል። እጥረት ደሞ ለፍላጎት መናር አስተዎፅዖ ያበረክትም የለ ከባሎ ሰለሙን ጋ የምትወስበው ወሲብ ባህላዊ ሆነባት ። ከሰለሙን ጋ አልፎ አልፎ ትዋሰባለች ፤ ሰለሙን ከእሷ በፊት ልምድ የለውም ፤ ቅደመ ወሲብ የለ ፤ መላላስ ፤ መማጠጥ ፤ መፋተግ ፤ መጋፈፍ ፤ ኖሮት አያውቅም ። እሱ ሲጨርስ የእሷን ስሜት
አይለካም ። ብዙ ቀን ምልክት ብትሰጠው አልገባው ብሏል። የግሩም ወሲባዊ ትረካ የሰለሙንን ድክመት አጎላባት ። በወሲባዊ ህይወቷ ደስተኛ እንዳልሆነች አስተያየችው።
ከራሷ ጋ ተሟግታ እንደዚህ አይነት ወሬ አታውራኝ ባለትዳር ነኝ እኮ እለዋለሁ ብላ ቃላት
አሰናድታ ሱቋ ሲመጣ ሲያገኛት በጠበቀችው እለት አያወራትም። ተገማች አለመሆን አላማን ለማሳካት ምቹ ነው ። አዕምሯችን የምንመግበው ውጤት ነው። እንዴት ሰው የሚያቀውን ከሰማው ጋ ያወዳድራል ። ለነገሩ ሴጣንስ ቢሆን ሄዋንን የረታት ያላየችውን በማስጎምጀት አይደለምን?
ግሩም እንደሚላት አይነት ወሲብ ከባሏ ጋ ለመዋሰብ አስባ ወደ ቤት ብዙ ቀን አቅዳ ቤቷ
ሄዳ ታውቃለች ። በዚህ መጠን ግልፅ መሆን የመጣችበት ቤተሰብ እና ማህበረሰብ አልፈቀደላትም። ከመሬት ተነስታ አወሳሰባችን እንቀይረው ማለት ከበዳት። አንድ ምሽት ልብስ ሲቀይር ሲራቆት ጠብቃ ፤ ጌታዬዋ አለችው ፤ ሲዞር ስሷን ፒጃማ በዳንስ መልኩ አሸቀንጥራ ፤ ጥላ ተጠመጠመችበት ሳመችው ፤ ፈገግ ብሎ ምን ሆነች ዛሬ አስተያየት ሲያያት ትዝብቱ አስፈራት ፤ በአቀደችው መንገድ አልሆነም ፤ የአዘቦታቸውን አወሳሰብ ተዋሰቡ ግሩም ባለትዳር ሆኖ ሌላ ጋ መሄድ የተለመደ ነው እያለ በጋራ የሚያውቋቸውን ሰዎች እንዴት በትዳራቸው ላይ እንደሚሄዱ በማስረጃ ነገራት። ስትገረም ተራ ነገር መሆኑን እያቀለለ ያሳያት ጀመር። ሴጣንስ ኢየሱስን ሊያስተው ጥቅስ እየጠቀሰ አልነበር ።ታማኝ ብላ የምታከብራቸውን ሰዎች እንደጥቅስ እየጠቀሰ ለብልግናቸው አመቻቻት። አንድ ቀን ሱቋ አመሻሽ ላይ የመውጫዋ ሰዓትን ጠብቆ ፤ ሱቅ እየዘጋጋች ሳለች መጣ ፤ ስለ ስራ ሌሎች ጉዳዮች እያወራት ፤ ወሬውን ጠምዝዞ ወሲብ ቀስቃሽ ወሬ ፤ የሚያሻፍድ ስዕላዊ ትረካ በተካተተበት ሁኔታ እየተረከ አፏን ከፍታ ስትመሰጥ በዝግታ የሱቋን በር ተነስቶ ዘጋው ። አንድ አንዴ የሰውነት ሁኔታ ከቃል በላይ ያግባባል ፤ በደመ-ነፍስ እንደሚታረድ በግ ምንም ሳትናገር ጠበቀችው

ይቀጥላል ......

@wegoch
@wegoch
@paappii

#adhanom mitiku
ፅልመት -

ክፍል - አምስት
(የመጨረሻ ክፍል)

በቃል ሳይነጋገሩ ተመካክረው እንደተቃጠሩ ነገር በሽፍደት ገላቸው ላይ የጠለቁ ጨርቆችን የተወላለቁት አስጎምብሶ ፀጉሯን እየነጨ ፤ እየሳመ ፤ ቂጧን እየመታ ፤ እንደምታምር እየነገራት ፤ እየሰደባት ፤እያንሿካሿከ ፤ አንገቷን እያነቀ ፤ አስለምኗት ለረጅም ደቂቃ እየገለባበጠ ወሰባት ። እውነቱ ባሏ እንዲ አዋርዶ ሊወስባት አይችልም። በባሏ ላይ መሄዷ የጥፋተኝነት ስሜት ቢሰማትም አልጠላችውም ። ከዛ ግሩም ለሁለት ሳምንት ጠፋ ። አግኝታው ትክክል እንዳልነበሩ መንገር ብታስብም ግሩም ጠፋ። ከሁለት ሳምንት በኋላ ድሮ እንደሚልክላት የመጡ እቃዎችን በቴክስት ላከላት ። ሱቋ ሄዶ ምንም እንዳልተፈጠረ የስራ ወሬ አዋርቷት ተመለሰ። Slave Sex እያሰሰች መመልከት ጀመረች ።ያየችውን የሚያሳያት ፤ እንዳየችው
የሚያደርጋት ግሩም ብቻ ነው ! ሰሌን መቀመጫዬን እየመታኸኝ ፤ ፀጉሬን እየነጨህ ፤ እየሰደብክ እንዋሰብ እንዴት ትለዋለች ? ግሩምን እሷ ፈለገችው። ግሩም ምንም መወስወስ ሳያስፈልገው ፈለገችው። ተገናኙ እንደፈለገችው ፤ እንዳየችው ለሁለተኛ ጊዜ እሱ በመረጠው ስፍራ ተዋሰቡ ። ከሰለሞን ጋ የምትዋሰበው ለሰለሙን ስሜት ብቻ ብላ ሆነ። ሰሌን እንደምትሳሳለት ፤
እንደምታፈቅረው ፤ እንደምታከብረው የሚያቃት ሁሉ ያውቃል። እች አለም መቼም ግርንቢጥ ነች ምክንያቱ እና ውጤቱ መች ይገናኛል ? ምንአልባት ግርንቢጥ የሆነችው እንደ ቤተልሄም ያሉ ሰውች አቆሽሸዋት ይሆን?? እንደግሩም ያሉ ሰዎች በክለዋት ይሆን ? ወይስ እንደ ሰሌ ያሉ ምልክት የማይገባቸው አልያ ግትር ሰዎች አስተዋፅዖ እያበረከቱ ይሆን ? ለአምስተኛ ጊዜ በእሷ የበለጠ ፍላጎት ፤ በግሩም የቦታ ምርጫ የተገናኙ ቀን ነው ባሏ ሰለሙን ያያቸው።
ቤተልሄም ባሏን ታውቀዋለች ፤ ውስልትናዋን እንደደረሰበት ስድስተኛ የስሜት ህዋሷ
ነግሯታል። ሰሌ በመኳረፍ አያምንም ።የበዛ ኩርፊያ የሚፈታው ችግር የለም የሚያባብሰው እንጂ ይላል። ሰለሞን ቤተልሄምን እንደ ልጁ ኤዶም ነው የሚሳሳላት ፤ መሳሳቱን ተርኮላት አያውቅም ፍቅሩን በምግባር የሚገልጥ ሰው ነው ። ካለ'ኔ ማን አለሽ ሚስቴም ልጄም ነሽ ይላታል። ሰለሞን በሰው ወሬ ባልተረጋገጠ ነገር ፤
ከባድ ባልሆነ ነገር እንዲህ ሊጠየፋት እንደማይችል ታውቃለች። ፊቱን ካጠቆረባት በኋላ ፤ ሰሌ ከጠላት በኋላ ሰውነቷ ቀንሷል፤ ድብርት በልቷታል ። እሷ ራሷ ራሷን ጠልታዋለች። ከተበደለ የበለጠ ፤ መበደሉን የገባው በዳይ ኑሮው ሲኦል ነው። በክፉ ትዝታ ጥልቅ እንዳለች አልጋው ጫፍ ላይ ኩርምት ብላ ጤነኛ ጭኑ ላይ ላመል ያህል እንደተደፋች ዶክተሩ ገባ እንዴት ናችሁ ብሎ ሲገባ የቤተልሄምን ፊት ያጨመላለቀውን የእንባ አሻራ አይቶ በሰለሞን
አደጋ መሰለው። "ምን ሆንሽ ልጅ ቤተልሄም ፤ ተይ እንጂ አሁን ድኖ የለ እንዴ" እያለ በገመተው ጉዳይ ላይ ገሰፃት። በማናውቀው ጉዳይ ላይ ገምተን ማፅናናት ከትዝብት እና ከአስብልሃለሁ ውጪ የሚያመጣው ትርፍ የለም። ከሆስፒታል ከወጡ ከወር በኋላ ፤ከጥፋተኝነት ስሜት ስላልተላቀቀች ነፃ መሆን ሲታገላት ሰለሙን ቤቲሻዬ እናውራ አላት ያቺ የፈራችው እለት ደረሰች ፤ አስባበት አብሰልስላው ፤ አውጥታ እና አውርዳ ከልቧ ብትማከርም ፤ እናውራ ሲላት ሆዷ ባባ ። ፊቷ በሃዘኔታ እያየ ይቅርታ አድርጌልሻለሁ አላት ። ፍቅር የሚለካው ለምናፈቅረው ሰው ይቅር ለማለት እና ለመረዳት በምንሄድበት ርቀት እና ብዛት ነው። ወድቀሽ እምነቴን በላሽብኝ ። ትሆኛለሽ ያላልኩት ቦታ ተገኘሽ። ራስሽን ትበድያለሽ ፤ በዚህ መጠን ትጎሳቆያለሽ ባላልኩበት ደረጃ ፤ ማቅ ከመልበስ የማይተናነስ ፀፀት ውስጥ ራስሽን አድርገሽ ራስሽን ይቅር ማለት አቅቶሽ አየሁሽ ። ሳትነገሪኝ አሳየሺኝ ፤ ስለማውቅሽ ገባሽኝ። ይሄ በእኔ እና በአንቺ መሃል ያለ በእኔ እና በአንቺ መሃል የሚቀር ገመና ነው ። ከፈፀምሽብኝ በደል ያሳየሺኝ ፍቅር ይበልጥብኛል ። ባየሁት ውስጣዊ እና ውጫዊ መቆሳሰል ሳቢያ ብሰቃይም ፈጣሪ እችለው ፤ እማርበት ዘንድ መንገድ ከፍቶልኛል። ደሞም በሌላ ምክንያት ብንጣላ ፤ ብንቆስል ይሻላል እንጂ ፤ ለአንቺስ ዘሙታብኝ ተውኳት ብዬ ስሄድ ፤ አንቺስ ምን አይነት ስሜት ይሰማሻል? ያ ሁሉ ጊዜ ያፈቀርሽኝ ፤ የዋልሺልኝ ለመኖር አንድ ምክንያት እንዳልሆንሽኝ ሁሉ ፤ በአንድ ትልቅ ስህተት በዜሮ ለምን እደረምሰዋለሁ ። ኤዶም ነገ በምን ተጣላቹ ስትለኝ በምንስ እላታለሁ?? ብሎ አይን አይኖን አየ ቤቴልሄም ከብዙ ዝምታ በኋላ "ጌታዬዋ እኔ ካንተ ብለያይ በመለያየቴ ብቻ አይደለም የምጎዳው መተካት ባለመቻሌ ነው። አንተ የምትተካ ሰው አይደለህም ። የእንደዚህ አይነት ክስተት መጨረሻ ወህኒ ቤት ነበር። እወድቃለሁ ባላልኩት መንገድ ወደኩኝ ራሴን እስክጠላው ። መደበቂያ ፤ መኮብለያ እስካጣ ፤ ነፍሴ እስክትጨነቅ ነው መሽቶ በነጋ ቁጥር መፅናኛ ያጣሁት። ይቅርታ መቼ ጠየኩህ ስብራቴን አይተህ ማርከኝ እንጂ። አጥፍቻለሁ ፤ ይቅርታ ስላረክልኝ አመሰግንሃለሁ ። ራሴን በመፀየፍ እንዳልኖር ፤ ትከሻህን ሰጠኸኝ ብላ እግሩ ላይ ወደቀች። አነሳት እና አቀፋት አንገቱ ስር ውሽቅ አለች። አንድ አንድ ውድቀት ትሁት እንድንሆን ያድቦለቡለናል ፤ እንዳንፈርድ ያንፀናል ። አፈቅርሃለሁ ሳይሆን ሳፈቅርህ እኖራለሁ ፤ ነገር ግን ካንተ ጋር መኖር አልችልም። ነገ ሲውል ሲያድር ፤ የሚያስመሽ ጉዳይ ሲገጥመኝ ፤ ስልኬ ቢዘጋ ምን ትላለህ ፤ ምንስ ያስብ ይሆን እያልኩ መሳቀቁ ይገለኛል። ይቅርታ አረክልኝ ማለት እኔ ላይ እምነት ይኖርሃል ማለት አይደለም ፤ እምነት ሲደረመስ እንጂ ሲገነባ ዘመናት ይፈልግል። የቤታችን ምስሶ መተማመናችን ነበር ናድኩት ፤ አይኗ እንባ ግጥም አለ ፤ እንባዋን ለመቆጣጠር ታገለች ፤ አልሆነም አሸንፏት ወረደ ይሄውልህ ጌታዬዋ ፍጡር እንደፈጣሪ አይደለም ይቅር ብሎ አይረሳም ። ፍጡር እንደ ፈጣሪ አይደለም
ለበደልነው በደል ከንስሃ በኋላም ይጠይቀናል ፤ አምላክ ነው ከቀጣን በኋላ ቁስላችንን የማይነካብን ፤ የሚረሳልን ። ነገ ሳስከፋህ በደሌ ውስጥህ ያቃጭልብሃል ። ሰትበድለኝ ጮኬ ስናገር የበደልኩህ ይጮህብኛል ወይ አንተ ታስታውሰኛለህ። ነገ ድንገት ከማንም ጋ በመጋደም ብትጠረጥረኝ እንዴት ትጠረጥረኛለህ ማለት አልችልም፤ አንተም እንዴት በዚህ ተልካሻ ነገር ልጠረጥርሽ እችላለሁ ማለት አትችልም ፤
የትዳራችንን መዓዘን ደርምሼዋለሁ ። ጌታዬዋ ላፍቶ ሄጄ ተከራዮቹን ልቀቁ ብያቸዋለሁ ኤዶሜ ከኔ ጋ ብትሆን ደስ ይለኛል ግን አንተ ደስ እንዳለህ አለችው" እንርግት ፤ ዝም እንዳለ ፊቱ ላይ ምንም ሳይነበብ ቃል ሳያወጣ ቆይቷ አለም እንዲም ነች አለ ።ሌላ ምንም ሳይናገር አንገቱን በእሽታ ነቀነቀ።

-ህይወት ቢቀጥልም ይሄ ፅሁፍ አልቋል -
---- ---- ---- ---- ----

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Adhanom Mitiku
የፍቅር ቀን ወይም የአደይ ቀን

'እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ የፍቅር ጀግና ለማድረግ በአገራችን ቫለንታይንስ ደይ እየተባለ የሚከበረውን የፈረንጆች በዓል ተውሰን እንደ አገራችን ፀባይ ለማክበር እቅድ አውጥተን ነበር፡፡

የጦር ጀግኖች ብቻ ሳይሆን የፍቅር ጀግኖች ያስፈልጉናል፡፡

ቫለንታይን ጥሩ ሃሳብ ነው፡፡ ክፋት የለበትም፡፡ ተቃቅፈው የሚሄዱ ፍቅረኞች ማየት ደስ ይላል፡፡ እጅ ለእጅ ተያይዘው በመንገድ የሚሄዱ ወጣቶች ትዕይንት የሚናፍቅ ነው፡፡ እኔ ወጣት በነበርኩበት ዘመን እንዲህ ማድረግ ያሳፍረን ነበር፡፡ ልጆቻችን በፍቅር እንዲያፍሩ አልፈልግም፡፡

ፍቅርን ከብልግና አምታተናል፡፡

ይሄን ቫለንታይን ቀን በዓል ኢትዮጵያዊ ለማድረግ ሦስት ነገሮች ማሟላት አስበን ነበር፡፡

አንደኛ፤ ከየትኛውም የአገራችን ክፍል አስገራሚ የፍቅር ታሪኮችን መሰብሰብና ለብሔራዊ በዓል የሚያገለግለንን ነቅሰን ማውጣት፤

ሁለተኛ፤ ምሳሌ የሚሆኑንን የአበባ አይነትና የአበባ ቀለም መምረጥ፤

ሦስተኛ፤ በታዋቂ ገጣሚ፤ ሙዚቀኛና ኮርዮግራፈር በአሉን የሚዘክር በቀላሉ አድማጭ ሊያንጎራጉረው የሚችል ዜማ መስራት ነበሩ፡፡

ከነዚህ ውስጥ ኮሚቴው ለብቻው የሚወስናቸው የበዓሉን ቀን፣ የአበባው ዓይነትና የአበባ ቀለም ሲሆኑ፣ የተቀሩት ዐላማዎች ግን በጥናትና በህብረት ውሳኔ ይፀድቃሉ፡፡

አገራችንን ከአደይ የበለጠ ምን አይነት አበባ ሊወክላት ይችላል? ከመስከረም ወር የበለጠ ምን የሚያምር ወር አለ? ቢጫ ቀለምስ ውብ አይደለም?

የአገራችን ስም ከተሰራባቸው ቀለማት አንዱ ዮጵ ትርጓሜው ቢጫ ወርቅ ማለት ነው፡፡ ቢጫ የፀሐይ ብርሃን ነው፡፡ ፀሐይ ከሌለ ሕይወት የለም፡፡ እንደ ፍቅረኞች ፊት የምታበራው ፀሐይ አይደለችም? የተፋቀሩ ሁሉ እየተንቦገቦጉ አይደለ የሚውሉትና የሚያድሩት?

#የስንብት_ቀለማት
አዳም ረታ

@wegoch
@wegoch
@paappii
አንድ ወፈፌ ወንደላጤ ጎረቤት አለኝ። ቀን ቀን ፍፁም ሰላማዊ ሰው ነው። አንገቱን ሰብሮ ሰላምታ ሲሰጥ በከንፈሩ አፈር ቅሞ ለመመለስ ትንሽ ነው የሚቀረው :)
እንደውም አከራያችን እትዬ ዘነብ አንዳንዴ "ልጄ ተው እንዲህ አለቅጥ አታጎንብስ ዲስክህ ይንሸራተታል " ይሉታል።
እሱ ፈገግ ብሎ በሀፍረት ያቀረቅራል ። ጭራሽ የሆነ ጊዜ ላይ ቤቱ ቡና አፍልቶ ጠራን !
በጠባብ ክፍሉ ውስጥ እንደ በግ ኮኮር ተራርቀው የሚገኙ የቤት እቃዎቹን እየገረመመን ተሰየምን።
እትዬ ዘነብ ደግሞ እንደ ሀረር ሰው ቀጥታ ነው ንግግራቸው...ያ ሁሉ የግቢው ሰው በተሰበሰበበት
"አንተ ምነው እቃህን በወግ ብትሰድረው?... " አሉት ... ትንሽ ቆየት ብለው ደግሞ...
"እግዚኦ ያ ምንድነው ሀይላንድ ውስጥ ያለው?" ብለው ጮኹ!
ናደው በድንጋጤ "የቱ ?" ብሎ መለሰ። ሀይላንዱን እኮ አፍጦ እያየው ነው !
"ሀይላንድ ላይ ነው እንዴ የምትሸናው?"
ደነገጥን!
እትዬ ደግሞ አንዳንዴ የሆነ ነገር አይተው ላሽ ቢሉ ምናለበት?
" ኸረ ቢራ ነው እትዬ! ኸረ እንደውም ልቅዳሎት " ብሎ ተነሳ...
እትዬ ሀይላንዱን ሰገራ እንደነካው እንጨት ተጠይፈው ...
"አንተ ሂድ ! ምን ያለው ሰላቶ ነው ባካችሁ?
ላስቲኩን እየው እስቲ? ጎዳና ተዳዳሪ መስሏል እኮ! "
እኛ ለሱ ተሸማቀቅን።
ናደው ወሬውን ለማስቀየስ መሰል... ጀበናውን በእጁ እንደያዘ.. ."አህ ...ህ " ብሎ አቃሰተ ።
"ምነው?" አልኩት እሱ በቀደደው አዲስ ወሬ ለማፈትለክ ...
"ብርድ መቶኛል መሰለኝ..አንዳንዴ ትከሻዬን ይወጋኛል "
"በዚህች ስስ አንሶላ ተሸፍነህ እየተኛክ እንኳን ብርድ መጋኛም ስላልመታህ ፈጣሪን አመስግን " ብለው ቀጠሉ እትዬ.. .
"ስማ ምነው እኔ ቧንቧ ቆጠረብኝ አልኩህ እንዴ? ኣንሶላህን ለቅለቅ አድርግ እንጅ!
አሁን ይሄ አንሶላ ነው ወይስ መሀረብ? ኤድያ!
ከዛች ቀን በኃላ ናደው በማለዳ ተነስቶ አዲስ አልጋ ልብስ ገዝቶ መጣ ... ከሾላ ገበያ ገዝቷት የመጣውን አልጋ ልብስ ለግቢው ተከራይ ሁሉ እያዟዟረ አሳየን።
ሽንጉርጉር አንሶላውን ለሞራሉ ስንል አደነቅንለት ...
እኔ በተለይ ከሱሳ ሱስ አስተርፎ ባዘጋጃት ገንዘብ ይሄን በማድረጉ አሳዘነኝ።
ናደው ቀን ቀን ሰላማዊ ይሁን እንጅ ምሽት ላይ ፍፁም ሌላ ሰው ነው ። ጫቱን ቅሞ.. .አረቄውን መጦ.. .ሀሽሹን በልዞ ሲመጣ ያስፈራል።
ቀን ለሰላምታ መሬት ካላስኩኝ የሚለው ልጅ ምሽት ላይ ደረቱን ገልብጦ የሰማይ ከዋክብትን ልግመጥ ይላል ።
ብቻውን እያወራ ይንገዳገዳል.. .ትንሽ ራመድ...ራመድ ይልና የቤቱን ደረጃ በእንፉቅቁ ይወጣል ።
ለዛን ቀንም ... ለገዛት አንሶላ የፍንጥር ራሱን ሊጋብዝ ፀሀይ ከማዘቅዘቋ በፊት ሹልክ ብሎ ወጣ ።
ከሰዓታት በኋላ እንደልማዱ ደረቱን ገልብጦ መጣ...ደረጃውን በዳዴ ወጥቶ የጠባብ ክፍሉን ቁልፍ ከፈተ ።
ከበሩ በስተግራ ያለችውን ማብሪያ ማጥፊያ በመከራ ተጭኖ አንፖሉን ለኮሰ....
ቤቱ በብርሀን ተሞላች ።
በቅፅበት እሪታውን አቀለጠው ....
"ነብር ...ነብር ....ነብር አልጋዬ ላይ ኡ....ኡ....ኡ..... "
የግቢው ተከራይ ንቅል ብሎ ወጣ ። ይሁንና ከእትዬ በስተቀር የሱን ክፍል የተጠጋ ሰው የለም።
ናደው በተዓምር ይሁን በአስማት የግቢውን አጥር ዘሎ ወጣ ...
እኔ ክፍሌ ውስጥ ሆኜ ድምፄን አጠፋሁ ። ድካም ተጫጭኖኝ ስለነበር.. .ግርግሩን እየሰማሁ እንቅልፍ ይዞኝ እብስ አለ ። ማልዶ
"አሁኑኑ ቤቴን ለቀህ ውጣልኝ!" የሚለው የእትዬ ጩኸት እስኪያባንነኝ ድረስ የት እንዳለሁ አላውቅም።
"ሰውኮ ይሳሳታል እትዬ "
የቤቴን መስኮት ከፍቼ የሁለቱን ግብግብ አያለሁ ... እነ አስኩቲ ጥግ ላይ ሆነው አፋቸውን በመዳፋቸው ሸፍነው ይስቃሉ ።
ሰው ሊባረር ሲል እንዴት ደስ ይላቸዋል? የሚል ንዴት ውስጤን እያንገበገበኝ ነበር ።
እነሱም እኮ ተከራይ ናቸው!
ይሄ በእትዬ የተመዘዘ ሰይፍ ነገ እነርሱ ላይ እንደማያርፍ ምን ዋስትና አላቸው? እያልኩ ተብሰከሰኩ.. .
"ስማ ሚኪያስ !" አሉኝ እትዬ ወደ መስኮቴ ተጠግተው.. .
"ሰላም አይደለም እንዴ እትዬ?"
"ምን ሰላም አለ ? ይሄ ቀውስ ማታ የሰራውን አልሰማህም?"
"ኸረ እንደውም! " ... ካድኩኝ...
"ኸረ እንኳን ያልሰማህ። ይሄ ምናምኑን አጭሶ መጣና ቀን የገዛውን አልጋ ልብስ ዘንግቶት ..."
"አልጋ ልብሱን ረስቶ ምን?"
"አልጋ ልብሱ ላይ ያለውን የነብር ምስል አይቶ አልደነበረ መሰለህ?
አልጋዬ ላይ ነብር ብሎ አንባረቀ እኮ!
ደግሞ እንደ ጤነኛ ሰው አንገት ይሰብራል...አንገቱን ነበር መስበር።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Mikael aschenaki
እንጃ
-----------------------------

ከአመታት በፊት የተለየሁት ባህር ማዶ ይኖር የነበር አንድ ወዳጄ ዘንድሮ አይጠገቡ መንግስት ባደረገለት ጥሪ መሰረት ወደ ሀገር ቤት እንደመጣ ስልኬን አፈላልጎ ደወለልኝ እና ከአመታት በፊት በጀማ ብዙ የሳቅ ድግሶችን ካ'ሳለፍንበት ሰሜን ሆቴል ተቀጣጥረን ተገናኘን።

በጣም ተራርቀን ነበር ምንም አይነት ሶሻል ሚዲያ ላይም አውርተን አናውቅም። ምሳችንን ካዘዝን በኋላ እንዴት ትዝ አልኩህ ግን? ስል ጨዋታ ማስጀመሪያ የሚመስል ጥያቄ ሰነዘርኩ እርሱም ከአፌ ቀበል አድርጎ "አይ ፀጊ አንቺ በቀላሉ የምትረሺ ሰው ነሽ? አልመች ብሎኝ እንጂ ብዙ ግዜ ነው ስልክሽን አፈላልጌ ላገኝሽ እፈልግ የነበረው" አለኝ።

እኔ በቀላሉ የማልረሳው ለምንድነው? ከአይን የራቀ እኮ ከልብ ይርቃል፤ እኔ አሁን በመራራቃችን ምክንያት እረስቼህ ነበር። የግዜ እና የቦታ መራራቅ አይደለም ጓደኝነትን ትዳርን ያረሳሳ የለ አልኩት። ጠፍቶ በመክረሙ ምንም ጥፋተኝነት እንዳይሰማው ለማድረግ በማሰብ። "የአንቺ ግን ሌላው ቢቀር ይሄ ግልፅነትሽ እና ተጫዋችነትሽ የሚረሳ አይደለም።" አለና ደመና ያጠላበት ፈገግታ አስፈገገኝ።

እንዲህ ስንጨዋወት ምሳችን መጣ ባርከን መብላት እንደጀመርን ትክ ብሎ አያየኝ "እኔ የምልሽ ፀጊ ቅዝቅዝ ብለሻል ተጫዋች ነበርሽ እኮ ወይስ የተራራቅን አይነት ስሜት ተሰማሽ?....ነው ወይስ ማደግ ቀልድ እና ሳቅሽን ቀማሽ?...."ሲል ፈገግ ብሎ ጠየቀኝ።
ባክህ እኔ ቀልድ አቁሜአለሁ፤ በዚህ የኑሮ ውድነት ብቀልድስ ማን ይስቅልኛል¿¡ አለኩት የተውኩትን ቀልድ ለማምጣት እየሞከርኩ። ሳቅ ቅርቡ የሆነው ወዳጄም ከትከት ብሎ ከሳቀ በኋላ ኮስተር ለማለት እየሞከረ "የምሬን ነው ፀጊ ምን ሆነሻል?..." አለኝ።

ምን መሰለህ ቀልድ (ቧልት) ከብዙ ሰው ጋር አቀያየመኝ። ቀልድ ለመፍጠር በማደርጋቸው ሙከራዎች ውስጥ ብዙ ቀን እንቅልፍ አልባ ሌሊት አሳለፍኩ፤
ለምን መሰለህ ብዙ ሀበሻ ተጫዋች ሰው ይወዳል ግን ተጫዋች ሰው አያከብርም።
ተጨዋቾች ከሆንክ ስሜት አልባ ያደርግሃል ኩፍስ ለሚለው ወይም ዝም ከሚለው ጓደኛህ ያነሰ ቦታ ይሰጥሃል።
በቤተሰብህ በብሄርህ በገዛ ፊትህ እና በኑሮህ ስታላግጥ አላማህ እሱን ማሳቅ ማጫወት እንደሆነ አይገባውም፤ ይደፍርሃል። በቀልዶችህ መሃል ማስተዋል፣ ማክበር፤ መውደድ የምትቀላቅል አይመስለውም።

በቀልዴ ምክንያት ቁምነገረኛነቴ፣ አንባቢነቴ እና ሰው አክባሪነቴ ሲፌዝበት ያስተዋልኩበት ግዜ ጥቂት የሚባል አይደለም። ማህበረሰባችን ብዙውን ግዜ ከሚጫወት አዋቂ ሰው ይልቅ ዝም ለሚል አላዋቂ ሰው የበለጠ ቦታ ይሰጣል።

ታዲያ ቧልተኝነቴ ካደፋፈረኝ፣ ካስተቸኝ፣ ካስገመገመኝ እና ካስናቀኝ ስራ አይደል አይከፈለኝ ፤ አያሾመኝ ብዬ በሂደት እርግፍ አርጌ ተውኩት! አልኩና የምፀት ሳቄን ፈገግሁ። በትኩረት ሲያዳምጠኝ ቆይቶ እንዲህ አለ "ባለማስተዋላችን ስንት ድምቀቶቻችንን ይሆን ያጣናቸው?!"

ለዚህ ጥያቄው መልሴ እንጃ ብቻ ነው።

እንጃ🤷‍♀
#በፀገነት

@wegoch
@wegoch
@mehalu_aynegerm
አስቱካ አስወጣችልኝ☺️

ይህ ማለዳ ፈገግታዬን ነጥቆኛል ቀኑ የእኔ እስካይመስለኝ ድረስ ገና በጠዋቱ ድብርት ተጫጭኖኝ ነበር ስታሽ አርፍጄ ቢሮ የገባሁት፤ እንደገባሁ ዲስክቶፔን አብርቼ ዩቲዩብ ዘንዳ ጎራ አልኩኝ እጄ ኪይቦርዱ ላይ አስቴር አወቀ "ናፍቆት" ብሎ ፃፈ አይምሮዬ እንዳላዘዘው ስለማውቅ ትንሽ ግርምት ብጤ ጫረብኝ ግን ያው መከረኛ ልቤ በል እንዳለው አላጣሁትም።

አስቱካም ያን መረዋ ድምጿን ታንቆረቁረው ገባች.......ግዜው ይርዘም እንጂ
መች እረሳሃለሁ?
በሆነው ባልሆነው
እናፍቅሃለሁ😔
አሃ..... አልሁ አሁን ቢያንስ ለምን እንደደበረኝ እየገባኝ ነው። በውሃ ቀጠነ፤ አየር ወፈረ የሚናፍቀኝ ያው እሱው ነው፤ ሌላ ማን አለ?😒
አሱ መሆኑን ሳውቅ ደሞ የእሱን ነገር ማሰቤ አይቀር አይደል፤ የእሱን ነገር በአሰብኩ ቁጥር እንደሆነ ልክ እንደ በውቄ ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ። ግን የአሁኑን ፈገግታዬን ድብርቴ ደመናማ ፈገግታ አደረገብኝ። ኤጭ!
"በሰጠሽኝ ፀጋ መጠን የሰራሽኝ ጉድ አያልቅም፤
እኔ ባንቺ ትዝታ እንጂ በተራቢ ቀልድ አልስቅም።"
የሚለውን ስንኝ በውቄ ባይፅፈው ኖሮ እኔ እፅፈው እንደነበር ምንም ጥርጥር የለውም። ከስንኙ በላይ ደሞ ይህች ትህምክቴ ይበልጥ አስፈገገችኝ መሰል☺️

አይ እሱ..... አሁን ምን ልሁን ብሎ ነው የሚናፍቀኝ?🤔..... ቆይ ለምን አርፎ አይቀመጥም? ለምን አይተወኝም?😶
አሁን በስጨትጨት ማለትም ጀምሬአለሁ።

አስቴር ይህን የፍቅር ትንታግ ልታቀጣጥለው ታጥቃ የተነሳች ይመስል ቀጥላለች
"በል ይግረምህና
ዛሬም እወድሃለሁ
እንጀቴን አስሬ
ይሄው እኖራለሁ"...
አሁን የምር አናደደችኝ ሆሆ.. ይቺ ሴትዬ ደሞ ልታሳብደኝ ነው እንዴ?!😳 ለምንድነው እሱን የሚገርመው ? እራስሽ ይግረምሽ ዛሬማ አልወደውም እሺ! አልሁ ጮኽ ብዬ ሆሆ... ብቻዬን ማውራት ጀመርሁ።😞

ቀዝቀዝ ብላ ቀጠለች ደሞ አለሳልሳ ወደ ልቤ ልትሰርግ☹️
"ርቄ ሄጃለሁ ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን ያንተ ፍቅር....
እውነት ነው😩 አልሁ አሁን ደሞ ለራሴ ብቻ በሚሰማ ድምፅ። 'ርቄያለሁ፣ ሁሉን ርግፍ አድርጌ ትቻለሁ፤ በትዝታ ብቻ እንገበገባለሁ። ግን ለምን? ለምን እንደዚህ ልቀጣ? ምን አጠፋሁ? ምን በደልሁ?😟......ከነዛ ሁሉ የመለያየት ግዚያቶች በኋላም እንዲህ የሚያደርገኝ ፍቅርህ ምን ቢሆን ነው ይህን ያህል?😟....... አሁን ልክ እንደ ሀምሌ ሰማይ አይኔ እንባ ቋጥሯል።😟

"ተማምነው ተዋደው
አብረው የኖሩት
ሲለዩት ይከብዳል
እንደ'ግር እሳት
እንደ'ግር እሳት"....
አረ ተይ ግን አስቱካ ተይ አታቀጣጥዪኝ ተይ...☹️ መከረኛው አይኔ የቋጠረውን እንባ ማዝነብን ያዘው።😭 "አይኔ አበሳ አየ" አለች ያች ሙሾ አውራጅ..... እውነትም እነደ'ግር እሳት አልሁ ሲቃ በተናነቀው ድምፀት......

አስቱ ምን ተዳዋ ሳይወጣልኝ እንደው አትተወኝ....
"በልቤ ወድጄ
በአፌ የሚቀብጥህ
ትቼ የማልተውህ
እኔው ነኝ ወዳጅህ".........
አሁን ዋሸሽ አስቱ ምንም እንኳን እስካሁን በልቤ ብወደውም፤ ትቼዋለሁ! በአፌም ብረግመው ነው እንጂ አላቀብጠውም፤ ችዬ ባልረግመውም ብቻ አላቀብጠውም። በቃ!😶 ደሞ አሁን እኔ ወዳጁ አይደለሁም፤ ወዳጅነት እንዴት ነው እንዴ?!!! እልህ የተቀላቀለበት ልቅሶና ማጉረምረም.....

"አይቻልም እና
ያንድ አንድ ሰው
ናፍቆት
መውደድን በወጉ
ፍቅር ያስማሩት".....
ታሪኬንማ እንደዚህ አትገልብጪው እንጂ?☹️
እሱ እኮ ነው የፍቅር መምህሬ፤ ማለቴ የነበርው..... አሉሁና ስቅስቅ ማለት ጀመርሁ።.......

ታዲያ እሷ ምን ገዷት እኔ ብነፋረቅ ይባስ ብላ ደገመችዋ...
"ርቄ ሄጃለሁ ሁሉን ትቼ
ትዝታን በልቤ አስቀርቼ
ምነው የምቀጣ የምቸገር
ከቶ ምን ይሆን ያንተ ሚስጥር"......
የልቅሶ ሲቃ በተናነቀው ድምፄ አብሬአት ማንጎራጎር ገባሁ። በጉንጮቼ የሚወርደው የእንባ ጎርፍ ፤ ፊቴ ላይ ያሉ አካላቶቼን ይዟቸው እንዳይሄድ ሰጋሁ እና እንባዬን ለመገደብ ሞከርሁ።

"የልቤ ምሰሶ ዘንጉ ተሰበረ
የማይመነጠር ምሽግ የነበረ
ምሽግ የነበረ"......
ልቤ ፍስስ አለብኝ ምሰሶ ተሰብሮም የለ... አሁን ለመንሰቅሰቅ የሚሆን አቅምም ከዳኝ ትክዝ ቅዝዝ ብዬ የእባዬ ቋት ያጠራቀመውን የጨረሰ ይመስል አልፎ አልፎ የምትንጠባጠብ እንባዬን ማበስ ያዝሁ .......

"በፅኑ ትዝታ በራቀው መንገዴ
እስቲ ላሰላስልህ ደሞ እንደልማዴ"......
ልቤ ወዲየው ተነስቶ የኋሊት ጋለበና ወደ አብሮነታችን ግዜ ደረሰ። አሁን ትዝታዬ ፈገግታዬን ሊመልስልኝ ነው☺️.....

"ይኸው ልቤ ጥሎኝ ተነስቶ ሲሄድ
'ባንተ መወስወሱን አድርጎ ልማድ
አድርጎ ልማድ"......
የዘወትር ልማድ አደረገው እንጂ ስል ልቤ ከደረሰበት ትዝታ ፈገግ ሲሰኝ ተሰማኝና ወደ በውቄ ግጥም ተመለስሁ................
"የአሳሳምሽ ለዛ ቀርቶ እንደ እንጎቻ የሚጥመኝ፥
የቧጨርሽኝ የነከሽኝ አገርሽቶ ቁስሉ ሲያመኝ፤
ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ።"
ወደ ፈገግታዬ ተመለስሁ፤ ብርሃናማ ፈገግታ ፈግጌ😁 ቀኔን ከዚህ ጀመርሁ።

@wegoch
@wegoch
@mehalu_aynegerm
ታሪክሽን አይቀይረውም ትላላችሁ?!

ናይና በምትባል አንዲት ከተማ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋችንን ተዋህዶ በሚያስተምርበት ግዜ ከሰራቸው ብዙ የማዳን ተአምራቶች የመግደላዊት ማርያም በእኔ ልብ ውስጥ ትልቁን ስፍራ ይይዝብኛል። "እንዴት?"
እንዴት ማለት ጥሩ እርግጥ ነው በአብ ልጅ ክርስቶስ የማዳን ምስጢር እውሮች አይተዋል፣ አንካሶች ሄደዋል፣ ለምፃሞች ነፅተዋል፣ ደንቆሮዎች ሰምተዋል፣ ድውያኖች ተፈውሰዋል፣ ሙታኖችም ተነስተዋል።

ታዲያ የሀጢያተኝቷ መግደላዊት ማርያም ነፍሳዊ ፈውስ ለምን የበለጠብኝ ይመስላችኋል? መልሱ አጭር እና ግልፅ ነው። እውር ስላልሆንሁ የማየቴ ጉዳይ አያሳስበኝም፣ አንካሳ ስላልሆንኩም የመሄዴ ግዜ አይናፍቀኝም፣ ለምፃም ስላልሆንሁ መንፃቴ አይደገኝም፣ መስማቴም እንዳያስጨንቀኝ ደንቆሮ አይደለሁ፣ ድውይም አይደለሁ ፤ አልሞትሁ። ግን ሀጢያተኛ ነኝና ለመግደላዊት ማርያም የተደረገ ፈውስ እኔንም ይናፍቀኛል። ለመግደላዊት ማርያም የተደረገ ተአምር መዳን ብቻ አልነበረም ለትልቅ ክብር መጨትም(መመረጥም) እንጂ .... ወይ ጉድ ዘመኗን ሙሉ ሰባት አይነት ሀጢያት በመስራት ረክሳ የኖረች ሴት የትንሳኤው አብሳሪ ትሆናለች ብሎ ማን ይገምታል?! ማንም ! "ሰዎች ፈረዱብኝ አንተ ግን አዳንኸኝ" እንዲሉ ......

ዛሬ ዛሬ የሰዎችን ሀጢያት መበርበር እና ለሰዎች ሀጢያተኝነታቸውን ለማሳየት መፍጨርጨር መፅደቂያ መንገድ እስኪመስል ድረስ የአኗኗር ባህላችን ሆኗል። የክርስቶስ ቃልም ተዘንግቷል "የቱ?" ነው ያላችሁት? "እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።
በወንድምህም ዓይን ያለውን ጉድፍ ስለምን ታያለህ፥ በዓይንህ ግን ያለውን ምሰሶ ስለ ምን አትመለከትም?
ወይም ወንድምህን፦ ከዓይንህ ጉድፍ ላውጣ ፍቀድልኝ እንዴትስ ትለዋለህ? እነሆም፥ በዓይንህ ምሰሶ አለ።
አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ።" ማቴዎስ 7፥1-5 የሚለውን ነዋ። እውነት ግን እኛ ፃድቅ ሆነን ነው?! ሌባው፣ ሱሰኛው፣ አመንዝራው ና ግፈኛው ላይ ለመፍረድ አፋችንን አሹለን የተነሳነው?!....

ይገርማችኋል መግደላዊት ማርያም ይህ ቀረሽ የማትባል ልቅም ያለች ቆንጆ ስለነበረች ሰዎች ያደንቋት፤ ወንዶችም ይከተሏት ነበር። እዩልኝ እንግዲህ ከይሲ ዲያቢሎስ የተጠናወታት ለምን እንደሆን... በሰዎች ጦስ... በከንቱ መወድስ.. በአጉል ትዕቢት እንድትሞላ አደረጓት ከዚያ ሰባት አጋንንት ሰፈሩባትና ሰባት አይነት ሀጢያቶችን በመስራት ዘመኗን ፀንታ እንድትኖር ሆነች። ግን ማርያም መግደላዊት ሁልግዜም መዳንን ትሻ ነበር፣ ውስጧ ሁሌም ያለቅስ ነበር፣ በኢየሱስ እግሮች ላይ ያዘነበችው እንባ ዝም ብላ የዛን ቀን ያማጠችው አይደለም፤ በዘመናት የፈውስ ጥማቷ የተጠራቀመ እንጂ።

ስንቶቻችን ነን አውደምህረት ስር እየተወሸቅን ሀጢያታችንን በነጠላችን ልንሸፍን የምንሞክር?
ስንቶቻችንስ እንሆን በተጠና የአኗኗር ስልታችን በሰወች ፊት ፃድቅ ለመሆን "እኔ እኮ እንዲህ ነኝ" በሚል ዲስኩራችን ስንደነቋቆር የምንኖረው?
አይ ሞኝነት ፅድቅ እንደሆን በእግዚአብሔር የምትፈተሽ ረቂቅ ምስጢር ነች እንጂ እኛ በምንፈልመው ፊልም መች ሆነ ብለን ነው☹️☹️
እግዚአብሔር ደሞ ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነው።

ስንቶችስ ይሆኑ ለኛ ሀጢያታቸውን ብቻ እያሳዩ ልባቸው የእግዚአብሔር ማዳን በመሻት ታማ በመአልት እና በሌት ምህረትን በመሻት አይናቸው እዥ እስኪያነባ የሚያለቅሱት?!

በዛን ዕለት ኢየሱስ ክርሰቶስ ወደ ፈሪሳዊው ቤት የገባው በፈሪሳዊው ግብዣ ነበር። ያን ፈሪሳዊ ልብ ብላችሁ ካያችሁት እኛል ይመስላል። እሱ የፈለገው ምህረትን አልነበረም፤ ምህረትን መፈለግማ ሀጢያተኛ ነኝ ብሎ ማሰብን ይጠይቃላ። የፈሪሳዊው ፍላጎት ከክርስቶስ እኩል በአንድ ማዕድ መብላት ብቻ ነበር። መግደላዊት ማርያም ግን ክርስቶስ በዛ እንዳለ ባወቀች ግዜ የመዳን ፍላጎቷ ንሮ ወጣ ለጌትነቱ እጅ መንሻ ይሆናት ዘንድ የአልባስጥሮስ ሽቱ አመጣችለት። ክብሩን ለመግለፅም እግሮቹን በእባዋ አርሳ አጥባ በጠጉሯ ጠረገቻቸው፤ የአድነኝ ተማፅኖዋንም ቃል ሳታወጣ እግሮቹን በመሳም አቀረበች። ፈሪሳዊውም ይህን ሲያይ የክርስቶስን የማዳን ሀይል ባላመነ ልቦናው "ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥ ኃጢአተኛ ናትና ብሎ አሰበ።”
የልብን የሚያውቅ ኢየሱስም የስምዖንን ሀሳብ ስላወለቀት "እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል።”
ብሎ በቸርነቱ ከእራስ ጠጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሞሉትን ሰባት የአጋንንት ነገድ አስወጣላት።
እንዲህ ነበር ያላት "ሀጢያትሽ ተሰርዮልሻል፤ እምነትሽ አድኖሻልና በሰላም ሂጂ!" ኡህህህ እንዴት የሚያረካ ቃል ነው። አያችሁ ግን ሰው ከግብሩ ይልቅ በእምነቱ ሲድን.....። እኛ ምናምኒት እምነት የሌለንስ ምን ይውጠን ይሆን?!🤔 ማመን ያቃተን ግን የዋሃዎች ስላልሆንን እኮ ነው። እምነት ማደሪያዋ የዋህ ልብም አይደል....።

ታዲያ የመግደላዊት ማርያም ታሪክ መች እዚህ አበቃና፤ እንደውም ከዚህ ጀመረ እንጂ። ጌታ ፈውሶ ብቻ አልተዋትም። እንደምን ይተዋት? እምነቷ ፅኑ ነው! ከሀጢያት ሸክሟ ነፃ ካወጣት በኋላ ከ36ቱ ቅዱሳት እንስት አንዷ ትሆን ዘንድ መርጦ ተከታዩ አደረጋት። ማርያም መግደላዊትም ከዚያን ዕለት ጀምሮ ፍፁም ተቀየረች። ጌታን እስከ እለተ ህማሙ ድረስ በሌሊትም በመአልትም በቅንነት አገለገለችው። ጌታችን ስለኛ መከራን በተቀበለባት በዚያች ዕለተ ዐርብም ከጠዋት ጀምራ እስከ ማታ ከጎኑ ነበረች፤ ከግርፋቱ እስከ ስቅላቱ እያለቀሰች ተከትላዋለች። በእግረ መስቀሉ ስር ተደፍተው ሲያለቅሱ ከነበሩ እንስቶችም አንዷ እሷ ነበረች። አቤቱ ምህረትህ የጎበኘውን ምንኛ ባረከው...!

የማርያም መግደላዊት ሐዋርያዊትነት መች በዚህ ያበቃና...... እሁድ ሌሊት ገናም ሳይነጋ መቃብሩን ታይ ዘንድ፤ ሽቱም ልትቀባ ወደ ጎለጎታ ገሰገሰች። ፍፁም የአምላክ ፍቅር በልቧ ሰርጿልና የሌሊቱ ግርማም ሆነ የአይሁድ ጭፍሮች አላስፈሯትም። ጌታችንም ከፍጥረት ወገን የመጀመሪያ ትንሳኤውን ያየች ትሆን ዘንድ አደላት። አቤት መባረክ!
የዛን እለትም በመቃብሩ ራስጌ እና ግርጌ ገብርኤል እና ሚካኤልን ቆመው አየቻቸው፤ ዘወር ስትል ደሞ የክብር ባለቤት የሆነው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አየችው። አላወቀችውምና በእናቱ ስም "ማርያም" አላት "ረብኒ(መምህር ሆይ)" ብላ ሰገደችለት። ጌታም "ሄደሽ ለደቀመዛሙርቴ ንገሪያቸው" ብሎ የትንሳኤው ሰባኪ አደረጋት። አቤት የፀጋዋ ብዛቱ...... ሰው የተጠየፈውን እግዚአብሔር ምንኛ ወደደው!......

እናንት በሀጢያቴ የምትጠቋቆሙ፣ ገዝፈው በሚታዩአችሁ የእኔ ሀጢያቶች ውስጥ አንሰው የሚታዩአችሁን የራሳችሁን ሀጢያቶች እያተናነሳችሁ የምትኖሩ እናንተ፣ እናንት እግዚአብሔር ቤት መሄዴ የማይዋጥላችሁ አጉል ዶጋ አዋቂ ነን ባዮች፣ የልቤን ሳታውቁ በግብሬ የምትፈርዱብኝ እናንተ ፤ እናንት ሁሌም ከአይኔ ጉድፍ ልታወጡ የምትጥሩ አጥርታችሁ ማየት ያልቻላችሁ በሙሉ..... የማርያም መግደላዊትን ታሪክ የቀየረ ጌታ የሰናፍጭ ታክል እምነት በልቤ ያቆጠቆጠች ቀን የማይምረኝ ነው የሚመስላችሁ?።

በሏ..! ..ታሪክሽን አይቀይረውም ትላላችሁ?!
ድሮ አምስተኛ ክፍል ሳለን እርስ በርሳቸው የሚፎካከሩ ሁለት ዲያቆናት ነበሩ። ከአብነት ትምህርት የጀመረ ፉክክራቸው ወደ ዘመናዊ ትምህርቱም አምጥተውት ነበር። በተለይ የሽምደዳ ትምህርቶችን የሚችላቸው አልነበረም። ልጅ እያሱ የት ተወልዶ.. .የት እንደሞተ ከነቦታው ከነ ዓመተ ምህረቱ ዱቅ ያደርጉታል። (በነገራችን ላይ አንድ ቀን ልጅ እያሱ ሀይቅ ዳር ተቀምጠው ሲፍታቱ መኮንኖች ከሩቅ ሾፏቸው ። ያን ጊዜ ልጅ እያሱ በርጫ እያደቀቁ ብን ብለው በምርቃና ፏ ብለው ነበር። ከዛ በኋላ ቤተ መንግስት አካባቢ ልጅ እያሱ የእስላም ቅጠል ያላምጣሉ ተብሎ እንደተወራባቸው ታሪክ ይናገራል 😂 ልጅ እያሱ አንቱ ለመባል የማያበቃ ልጅነት ነበራቸው። ሀገራችን በዘመኗ ካጋጠሟት የህፃን ባህሪ ካላቸው ንጉሶች ቀዳሚውን ቦታ ይወስዳሉ። በተለይ ጢዝ ያላት እንስት ካዩ ቅቤ እንደላሰ እባብ ይቅበዘበዛሉ ይባላል ። ብዙው የንግስና ዘመናቸው ላይ ሲወሸክቱ ራስ ተፈሪ በርቀት ይጠባበቋቸው ነበር። ራስ ተፈሪ ቤተስኪያን ተመሳም አንስቶ በቤተ መንግስት ዘንድ እጅግ የተወደደ ምግባር ነበራቸው። በንግስና ዘመናቸውም ትንሽ እንኳ ሳት ብሏቸው ከማጀት ሴቶች አንዷን ቢመቻቹ ለፀፀት ቅርብ ናቸው። ከአልጋ ወርደው ደበሎ አንጥፈው ጌታ ሆይ አፉ በለኝ ይላሉ በፍጥነት። ልጅ እያሱ ግን አንዷን ቆንጆ እየቀመሱ የሌላዋ እንስት ገላ ያሻፍዳቸው ነበር )

ወደ ዲያቆናቱ ልመለስ.. .

እንዳለ ተብየው አንዲት ሸጋ ወዶ ጠየቀ። መጀመሪያ ይሄ የማርተሬዛ ሽልንግ የሚደብቅ ተረከዝህን አለስልስ ብላ ኩም አደረገችው ቆንጆዋ!

እንዳለ ከዚህ የሞራል ስብራት በኋላ ሰይጣን በጆሮው አንድ በቀል ሹክ አለው።

ጱጵ የሚል ድምፅ ከጎናችን ሰማን ። ደግሞ ለክፋቱ እኔ ከቆንጆዋ ልጅ ጎን ነው የተቀመጥኩት። ቆንጆ ይፈሳል ተብሎ ስለማይገመት ተሜው ሁላ አይኑን አጉረጠረጠብኝ። አፍንጫዬን በሹራቤ ስሸፍን ደግሞ ከሱ ብሶ ፈስ እንደሸተተው ሰው አፍንጫውን በጨርቅ ይሸፍናል እንዴ? ተባልኩ...ከ አምስት ደቂቃ ለጥቆ ቆንጆዋ ልጅ ሌላ ጋዝ ለቀቀች። ከመቅፅበት ደንግጣ ክፍሉን ለቃ ሮጠች። ዞር ስል ደብተራው እንዳለ ሆዱን እስኪቆርጠው ድረስ ይስቃል።

የፈስ ድግምት ለቆባት መሆኑ ያኔ ገባኝ :)

በዚህ እውቀቱ የቀናው ደብተራው ሸዋ ሌላ ጉድ ይዞ ከተፍ አለ ። 

የበቀል በትሩ አንዲት ምስኪን መምህራችን ላይ አረፈ ። ቲቸር አስካል መክራን ዘክራን አልሰማ ስላልናት ብዙ ጊዜ በአርጩሜ መከራችንን ታበላናለች። ተማሪው ግርፊያዋን ስለሚጠላ እሷንም አብሮ አይወዳትም ነበር። በተለይ ሸዋ ... የክፍል መልመጃ 3/10 ስላመጣ ክፉኛ ጥርስ ነክሶባት ነበር ። የታሪክ ትምህርትን እንደ ውሀ የሚጠጣው ጎበዝ ተማሪ የሂሳብ ትምህርት ግን አናቱን እንደ ሀበሻ አረቄ ይነካዋል። 

በተለይ ማካፈል የሚባል ስሌት በቀን ሶስት ጊዜ አስረድተውት በቀን አስራ ሶስት ጊዜ ይስታል 😑

አሁን በምን ተዓምር ነው 19 /12.... 21 የሚመጣው ። መምህራችን በአዕምሮህ ነው ወይስ በእግርህ አውራ ጣት አስበህ ነው ይሄንን ውጤት ያመጣኸው ብላ ስትጣይቀው.. ." በ 16 ኪዳነምህረት ነች ። በ12 ሚካኤል ነው። እመቤቴንስ እንዴት ረሳታለሁ?" አለ አሉ 😑
በዚህ ጥርስ የነከሰው ሸዋ ዛዲያ አንድ ከሰዓት ላይ አደናግር ድግምቱን አነብንቦ ክፍል ውስጥ እንትፍ እንትፍ አለ።

ቲቸር አስካልዬ እጇ ቄጠማ ሆነባት። እግሯ እንደ ህልም ሩጫ አልታዘዝ አላት።  ጠመኔው ተሰሌዳው እንዴት ታዋህደው?

አይነ አፋር ነች አይነ አፋርነቷ ጎልቶ አንገቷን ደፋች ።

ደግሞ ለዛን ቀን ያለወትሮዋ እንኳን ሂሳብ ዓ ነገር መፃፍ አትችሉም ብላ አማርኛም እያስተማረችን ነበር።

አማርኛ ብላ ለመፃፍ አገርኛ ብላ ስትፅፍ ሳቅንባት ። የግንባሯ ላቦት ተንዠቀዠቀ ። መልሳ መልመጃ ን ለመፃፍ መግለጫ ብላው አረፈች። ከተማሪው ሁሉ የሸዋ ሳቅ ጎልቶ ተሰማ ።

መጨረሻ ላይ የሰራችው ስህተት ሲታከል ደግሞ ክፍሉ በሙሉ እንደ አደዋ ማስጀመርያ መድፍ አጓራ!

አንብቡ አለችን ዓ ነገር ጥፋ.. .

ምድረ ውሪ ተሰሌዳው የጣፈችውን ጥሁፍ እኩል አነበበው።

"አበበ በሶ በዳ !"😆

ድንጋጤ ጨው አደረጋት ። የፃፈችውን ዞራ አነበችው ።

ቂ....ቂ...ቂ ...ቂ...ቋቂ

ሸዋንም ሳቁንም እኩል ጠላኋቸው :)

ሚካኤል .አ 

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ


@seiloch
@seiloch
Forwarded from ❀ርብቂ Ribki Photography (Ribka Sisay)
#ጦቢያ

#ዝክረ_አድዋ ልዩ ፌስቲቫል አድዋን በጦቢያ መድረክ ያድምቁ

በነፃ ሀሳብና በሰከነ መንፈስ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን እናድምቅ!

የመግቢያ ትኬት በሁሉም የቡና ባንክ ቅርንጫፎች ይገኛል።

የመግቢያ ዋጋ 200ብር
ለበለጠ መረጃ 0919787878

በነገራችን ላይ እኔም ስራዎቼን ይዤ እኖራለው🥰
አያቴ ረጅም ናት : ድሮ ያኔ ትንሽ ልጅ ( ትንሽ ልጅ ሆኘ አውቅ ነበር ?)
እና ያኔ እንግዲህ አጠገብዋ ቆሜ: ቀና ካልኩ : ሽንሽን ቀሚስዋን ገፋ ያደረገ ሆድዋ:
ከወገብዋ በላይ እንዳላይ እየጋረደኝ አንገቴን ወደ ላይ ሰቅየ : አገጨን ወደ ሰማይ አሹየ :
ሳይት : ሳያት አታልቅም ።
ጥቂት እራቅ እልና : እዚያ እ- ላ--ይ የደረሰ አንገትዋን አሻግሬ ፊትዋን እመለከታለሁ ።
ደርባባ ወይዘሮ ናት ። ቀሚስዋ እስከቁጭምጭሚትዋ ይደርሳል ።
አያቴ ?!
አቤት
ቀሚስሽ ለምን መሬት ይደርሳል ?
ረዝሞ ነዋ የኔ ልጅ ።
ታዲያ ለምን ረዘመ : እም ለምን እንኳን አታሳጥሪውም?
ካጠረ ነፋስ እንዳይገልጠኝ ብየ ነዋ ልጄ ።
ነፋስ ቢገልጠው ምን ይሆናል?
እህ! እንዲህ ናትና የዳውዶ መሃመድ ልጅ !
ሴት ልጅ: ንፋስ ቀሚሷን ገልጦባት :
ጭኗን ለመንገደኛ: ከሚያስጎበኝባት
ካፍንጫዋ ሥር : ንፍጧ ቢታይ ይሻላታል ።
አያቴ ምን ነው ያልሽው ?
ወዲህ ነው ልጄ
ወዲህ ? ወዴት ? ምኑ ?
ተይው ልጄ
ምኑን ነው ምተወው አያቴ ?
እርቦሻል እንዴ የኔ ልጅ ? ትላለች በሃዘኔታ
እምምም--- እርቦኛል እንዳልል አልራበኝም : አልራበኝም እንዳልል ደግሞ : ጓዳ ውስጥ
ያለ ወይ ቋንጣ ፣ ካልያም አይብ ፣ ወይ ቃተኛ ፣ ጭኮ ብቻ የሆነ ጎትታ የምታመጣቸው
ድብቅ ጣፋቅ ስንቆች አንዱ: እንዲያመልጠኝ አልፉልግም ።
"አልራበኝም ግን እበላለሁ ።" እላታለሁ ።
አዎ ልጄ: ልጅ ሆዴን አመመኝ እንጂ' ጠገብኩ ' አይልም ።--- እያለች ጓዳ ውስጥ ገብታ :
ከሆነ ቦታ የሆነ ነገር አንጎዳጉዳ: በትላልቅ መዳፎችዋ እና በእረጃጅም ጣቶችዋ የታፈሰ:
አንድ ሠሃን የሚሆን ቆሎ ይዛ :
'ዘርጊ እጅሽን ":- ትለኛለች ።
ዝርግት -
ውውውይ --- ትላለች አጫጭር ጣቶቼን ትንሽየ መዳፌን አይታ
"በቃ በቀሚስሽ ያዥው ። "
ቀሚሴን ከፊት በኩል እስከ ላይ ድርስ ስጎትት ---
"" አይ አይ ምነው--- " ብላ ሳጥኑን ታያለች ።
ከሳጥኑ ውስጥ ሰሃን አውጪ ልትል ፈልጋ ግን አንደበትዋ ተያዘ ።አላመነችኝም ። ሠሃን
ሲሰበር አትወድም የብረት ሰሃንዎችዋን መስጠት አትወድም ።
በይ በቀሚሽ ያዥዋ እንግዲህ። ትለኛለች።
እንደገና ቀሚሴን ከፊት በኩል ይዤ ወደ ላይ በሁለት እጄ አጥፍና : በቀሚሴ ጨርቅ :
ዘምቢል መሳይ የጨርቅ ጉድጓድ እሰራለሁ።
የተገለጡት ጉልበቶቼ እየታዩ : ቆሎውን እቀበላታለሁ ።
በማር የታሸ ሠነፍ ቆሎ ነው ቁርጥም አርጊያት እስኪ --- ትላለች።
አያቴ ቆሎው ግን ለምን ሰነፈ ?
ምንማለትሽ ነው ልጄ ?
ቆሎው ለምን ጎበዝ አይሆንም ነበር?
እርቦሻል እንዴ ልጄ ?
ሌላ ምን ልትሰጠኝ ይሆን እያልኩ
"አልራበኝም ግን እበላለሁ" አልኩ ።
እርቦሻል የኔ ልጅ : ሰው ሲርበው ነው ጥያቄ የሚያበዛው ።
ትለኛለች ።
የተገለጡ ጭኖቼ ሳያሳስቡኝ ቆሎየን ከነጨርቄ በአንድ እጄ ጨብጨ በሌላኛው እጄ:
ለጊዜው ኪስ ሆኖ በሚያገለግለው : ቆሎ ባዘለው የፊት ለፊት ቀሚሴ ጨርቅ ውስጥ
ያለውን ቆሎ እየዝገንኩ ፣ እየቆረጠምኩ ሌላ የጓዳ ሲሳይ እጠብቃለሁ ።
ግን በምን እይዘዋለሁ ? አያቴ ግን ለምን ሰሃን እትሰጠኝም ?
አያቴ
አቤት
ጭኔ እኮ ግን እየታየ ነው ። አልኩ በማስተዛዘን
አያቴ ጓዳ ውስጥ ሆና --- በረጅሙ ትመልሳለች
እህም- ይታያ :- የታየ እንደሆን ምን እንዳይሆን ? !

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Abeba Birhanu
ስለተለየኝ ራሴን የጣልኩ ይመስላቸዋል። ስልኩን ስለማያነሳልኝ ዱካክ እየበላ የሚያሰቃየኝ ነው የሚመስላቸው። አልፈልግሽም ማለቱ ብቻ የመቆም ድፍረቴን የናጠው ነው የሚመስላቸው።
ግን አይደለም !ሁሉን ነገር ተራ ማድረጉ አስደንግጦኝ ነው! አብረን ሳለን ያልወጣንበት የሃሳብ መስመር ፤ያልተንሸራሸርንበት ስፍራ ፤ያላሰስነው ቤርጎ ፤ ያልነገሩኩት ገመና አልነበረም ። ያልሆነው አለመሆን ብቻ ነበር !! በየደቂቃው ከጭንቅላቴ የሚፈልቀውን ዝባዝንኬ ሳላስቀር፤ ባጠገቤ ውል ያለውን ሳይቀር
ነበር የምተነፍሰው። እንዳልቆም አድርጎ ያፍረከረከኝ ፤ ያሳለፍነውን ያገዘፍኩትን ነገር አንድ ሳይቀር ነው አሳንሷት የሄደው። ትረካ የሌለው መለያየት ፤ ውጣ ውረድ የሌለው ፍቺ ፤ የማይተነፈስ ህመም ለማይታይ ጠባሳ ይዳርጋል! እንዴት በዚህ መጠን ተራ ይሆናል ፤ እንዴት እየተፍለቀለቅኩ የምተርከውን ትዝታዬን
እንደዚህ ያባክነዋል። እንዴት ጥሩ ምክንያት አይፈበርክም? አንዴት አካሄዱን ወዝ አያላብሰውም? በዚህ መጠን ተራ አድርጎኝ እንዴት ይሄዳል? እችን ብቻ ነበር የምናክለው ?
አብረን ስንሆን የኔ ነው ብዬ አይደል እርቃኔን የተንጎማለልኩት ? የነበረን ነገር ገብዶብኝ
አይደለ ድክመት እና ስጋቴን መግለጤ?ያሳለፍነውን ውብ ጊዜያት ካለጥንቃቄ በአካሄዱ ተረማምዶበት ነው ያናወዘኝ። እንጂማ መለያየት ተፈጥሮም አይደል ነፍስ ከስጋስ ይለይ የለ ?
መሄዱ አይደለም አካሄዱ ነው መላቅጡ የጠፋ ዱካክ ውስጥ የዶለኝ። አወዳደቃችን ውስጥ የጣያችን ግዝፈት እና ተራነት አሻራ በጉልህ አለ ። ምን አለ አለሳልሶ ቢጥለኝ ፤ ምን አለ ሲተወኝ ይሉኝታ ቢስ ባይሆን ። አብረን በነበረን ጊዜ እንደምወደው እያንዳንዱ ዳናዬ ምስክር ነበር ።
ሰው ለሚወደው አይደለም ላሸነፈው ጠላቱ እንኳ ይራራ የለ? ምን አልባት እኮ የእኔ ብቻዬን የመሆን ፍርሃት ሲያርደኝ መለማመጤን አይቶ ነው ለእኔ
ያለው ስሜቱ የተከለለበት። ምን አልባት ከእኔ የተሻለ ሰው አግኝቶ በእጁ እስኪያረጋት ወረት አውሮት ነው። ምን አልባት እንዲ መሙለጭለጭ ማንነቱ ይሆን ይሆናል። መሄዱ አይደለም ያጎሳቆለኝ ይሄ ማለቂያ የሌለው የምንአልባት ጉዞ ነው ከሰውነት ተራ ያወጣኝ፤ ምንአልባት ቃል ገድፌ የማይወደውን ብዬ ፤ ወይ ምን አልባት ያልዋልኩበትን ነግረውት ይሆን? ወይ የሆንኩትን አገዛዝፈው አሻክረውት ይሆን? ይሄ እና ሌሎች የምን አልባት መላምቴ ነው ጭንቅላቴን ያጣበበው። እንዲህ እንደባተልኩ አልቀርም እረሳሃለሁ ፤ ያኔ እዚህ የዘራሃውን እዛ ስታጭድ መሰስ እያልክ ትመጣለህ ፤ ያኔ የእኔን የምንአልባት የመላምት ችንካርን ትቀምሰዋለህ ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Adhanom Mitiku
2024/09/22 21:16:48
Back to Top
HTML Embed Code: