Telegram Web Link
Forwarded from Sunset Hiking (Cherinet K.)
View over #Jema's #Gorge from #Portuguese_bridge.

#Sunset_Hiking 🌇 is hosting another day hike (round trip) to Portuguese bridge (#Debre_Libanos) by Nov 29, 2020 (ህዳር 20, 2013) 🇪🇹- round 2

Activities
🏔#Hiking
🎸 #Live_music_performance (with #Zamir_Acoustic_Band)
🧘‍♀ #Yoga_Intro (with #Meron_Mario)

What to see 👁 👁
#Waterfall
#Jema Gorge
#Cave
🦍 #Gelada_Baboon

#Package_Includes
🥗 #Lunch (Traditional #Agelgil)
🍂 #Photography
🚍 Transportation
💧Bottled water
💐Snack
🟢Entrance fee
🌺 Guide

💵 Hiking #Cost only 500 birr

📍 📍 📍 Location- 110 km North of Addis (around Fiche) with Max. Elev of 2450 m.

🛫Departure: Piasa (Taitu Hotel) at 12:30 LT

Tickets 🎫 🎫 🎫 available 👇
@Cherinet_K (0911759127)

NB. Okay for #beginners.


For more join
Group - https://www.tg-me.com/sunsethike
Channel - https://www.tg-me.com/sunsethiking
Photogrpahy - https://www.tg-me.com/sunsetphotography
ፍቃዱ ወደ ትምህርት ቤት እንሂድ ሊለኝ አያቴ ቤት መጣ። በርግጥ በወቅቱ አያቴ ጋር ሄጄ የነበረው ፍቃዱ መኖሪያቤታችን መጥቶ ትምህርት ቤት እንሂድ ሊለኝ ይችላል በሚል ስጋት ነበር ። ሆኖም አልተሳካልኝም ( ያ የነገር ሜንጦ የሆነ ልጅ አንገቱን እያሰገገ አያቴ በራፍ ድረስ ከተፍ አለልኝ ። ደግሞ እኮ ሚካኤል አለ ይላል ? ቅዱስ ሚካኤል ስዕሉ ላይ እንዳለው ጋንጩር አናቱ ላይ ቆሞ ይርገጠውና 😞!!) አያቴ በረንዳ ላይ ካለች አንዲት ብርኩማ ላይ ተቀምጣ ... ዜና ታዳምጣለች ። (በዛ ሳምሶናይት ቦርሳ በሚመስል ቴፕ ዜና ስትሰማ ታድያ ራሷን በሀዘኔታ ትነቀንቃለች። የዛች ቴፕ ታሪክ እጅግ የቆየ ከመሆኑ የተነሳ ከሆነ ጊዜ በኋላ ቤቴ በሙዚየምነት እንደማስቀምጣት አውቃለሁ )
"ሚኪያሴ ወደ ትምህርት ቤት ስትሄድ ጠንቀቅ እያልህ ልጄ ! ዛሬ ልጆችን ወስደው አዲስ አበባ መለመኛ እያደረጓቸው ነው። አይንህን አውጥተው መለመኛ ያደርጉሀል ። በዛ ላይ ያንተ አይን ቀድሞውንም የወጣ ነው ዋጋም የለህ ! ...ደግሞ እንዳንተ ያለውን ቆንጆ ነው የሚወስዱት አሉ " ... ይሄን ስትለኝ ድንጋጤ በመላ አካሌ ሲሰራጭ ይታወቀኛል። የልጅነት ልቤ በከባድ ፍርሀት ተውጣ ቅዝቅዝ ትላለች ።
"ደግሞ ምንድነው የያዛችሁት?" እንደ ጎረምሳ ደረት የሰፋ መነፅሯን አውልቃ አየችን።
"ቢራቢሮ እየገደልን እንሂድ ብለን እኮ ነው" ፍቄ መለሰ።
"ስሙ! በየመንገዱ ቢራቢሮ እንግደል ብላችሁ ስትሯሯጡ አንዱ ደንባራ ሹፌር መጥቶ እንዳይድጣችሁ ። "
"እሺ"
"እሺ ይላል እንዴ ደግሞ ? ምን ያለው ትንኩሽት ነው ይሄ ልጅ ። አስቀምጡ ልምጩን!" ...አያቴ አንባረቀች።
"ይሄ ልጅ አባቱ እንዲህ እንደሚያደርግ ቢያውቅ የሚለቀው ይመስልሀል? አንተስ እንደው አንደኛውን ለይቶልሀል !"- ...ለምን እንደሆነ ባይገባኝም አያቴ ፍቄን አትወደውም። ሌባ ነው እጁ አይፆምም ትላለች ብዙ ጊዜ። ደግሞ ቤታቸው ቅርብ ስለሆነ አብጠርጥራ ባህሪውን ታውቅበታለች ። ስራው ከልጅ ሳይሆን ከሰላሳ ዓመት ጎረምሳም አይጠበቅም ብላ ብዙ ጊዜ ስታማርረው እሰማታለሁ ። በርግጥ ፍቄ ሌባ ብቻ ሳይሆን ነገረኛም ጭምር ነው። እኔም ከሱ ጋር ጓደኛ የሆንኩት ወድጄው ሳይሆን ከአንድ ክፉ አደጋ ራሴን ለመጠበቅ ነበር።
አንድ ጊዜ ወደ ትምህርት ቤት እየሄድን...ማንም የሌለበት ጠባብ ሸለቆ ውስጥ ስንደርስ ከኪሱ የተጠቀለለ ወረቀት አወጣና ለኮሰው። ለኩሶ አጨሰው። ግራ ገብቶኝ አየሁት... ገና የአራተኛ ክፍል የሆንን ፈልፈሎች ሲጃራ ስናጨስ ከተገኘን ጉድ ነው መቼም ! ...ደግሞ ወረቀቱ በሲጃራ መልክ ተጠቅልሎ ይሰራ እንጅ የሚገዛው ኒያላ ስ አልነበረም።
"ይቅርብን አልኩት!"
"ባክህ አትፍራ ... እንካ.. ." ብሎ እጁን ሰደደልኝ። ተዟዙሬ አካባቢዬን በፍርሀት ቃኘሁትና ተቀበልሁት።
ወረቀቱን ሳብ ...ሳብ ሳደርገው ጭሱ ጉሮሮዬ ላይ ተሰክቶ አልወርድም እያለ አሳለኝ። አንዴ አጭስበት ይለቅሀል አለኝ... እንደገና አንድ ጊዜ ሳብብብ ሳደርገው ታድያ ከየት መጣ ያልተባለ ድምፅ ጆሮዋችን ላይ አቃጨለ።
እናንተ ጉዶች ????
...ዞር አልን...ዞር ስንል የፍቄ እናት አፀዱ ነች።... ፍቄ ከስሬ ብን ብሎ ተሰለበ (ተነነ ብል ይቀለኛል። ሰው ቅዱስ ሲሆን ብቻ ሳይሆን እርኩስም ሆኖ ወደሰማይ ማረግ ይችላል ለካ !) ... እኔም ደንብሬ ስለነበር እሱን ተከትዬው ከነፍኩኝ።
"አይቻችኋለሁ ። ማታ ትመጧታላች.....ሁ ...." የአፀድዬ ድምፅ ከርቀት ተሰማኝ።
ታድያ በዛኑ ቀን ከትምህርት ቤት መልስ እየተሸማቀቅን ቤት ገባን...አፀዱ ቀስ ብላ ፍቄን ያዘችውና በማማሰያ አንቆራጣ ቀጥቅጣው ጥፋቱን እዛው ላይ ረሳችለት ። እኔ ጋር ግን ጉዳዩ ገና ተጀመረ እንጂ አልተፈፀመም ነበር ።
ፍቄ በጠዋቱ ቤት ይመጣና ዳቦ እና ሻይ ስጠኝ አለበለዚያ ለአባትህ ሲጋራ እንዳጨስን ልንገርብህ ይለኛል።
ያቺን ናፒ የምትባለውን ቆንጆ ልጅ ሁለተኛ ካንተ ጋር ሳይሆን ከኔ ጋር ነው መሄድ ያለባት
እንዴ ለምን ? ናፒ እኮ የኔ ጓደኛ ነች
አንተ ሲጃ ……………….
ቃሉን መጨረስ አይጠበቅበትም እሺ ይሁንልህ ብዬው ህመሜን እውጣለሁ ።
ሌላ ጊዜ ደግሞ ...
ፍራንክ ከቤት ይዘህ ና ብሎ ያስጨንቀኛል።
ህይወቴን በሴራው ጠፍንጎ ሳልወድ በግዴ ጓደኛው አድርጎኝ አረፈው።
እናም በሰዓቱ አያቴ ስትቆጣንም በአይኑ መልከት አደረገኝ። አርጩሜውን አንሳ ማለቱ እንደሆነ ገብቶኛል።
አርጩሜውን ባነሳው አያቴ ልትራገም ሆነ ።
እንቢ ብለው ሲጃራ አጨስን ብሎ ለአባቴ ሊያንሿክክ ሆነ ።
በዚህ ሁለት አጣብቂኞች መሀል ቆሜ ጩኸቴን አቀለጥሁት ። ኡ ኡ ኡ ይ እባብ እባብ እባብ
እግሬን እያነሳሁ ክፉኛ ስወራጭ ፍቄ ስሬ አልነበረም ። ያኔ አፀድዬ ስታየን ጊዜ እንደነበረው ተኖ ተሰለበ ። አያቴ ግራ ተጋብታ በረንዳው ላይ ቆማ ታየኛለች ። በዚህ ደስታ መሀል ሆኜ በረዥሙ እፎይ ከማለቴ ለጥቆ አንድ ሲደብረኝ የኖረ ድምፅ ከጀርባዬ ተከተለ ።
“ሚኪያስ አርጩሜውን አንሳው 🙂 ወይም ሲጃራ … !” (ሚካኤል አስጨናቂ )

@wegoch
@wegoch
@paappii
ስንብት
'
'
ብዙ ጊዜዬን ከማሳልፍበት ብዥታ ወጥቼ ራሴን ገዝቼባቸዋለሁ ብዬ ባሰብኩባቸው የህይወቴ ጥቂት ቀናት የማልመው በብሩህ ፀሃያማ ቀን ስለመሞት ነበር ። ቃጠሎ ባልበዛበት ለስስ ባለ ፀሃያማ ቀን ፤ እንደ ጥቅምት ባለ ቀን መሞት ። የሃምሌ ቀናት የጨለማ ኑሮ ላሳለፍኩ ለእኔ በብራ ጥቅምት መሞት የመጨረሻው ብሩህ ምኞቴ እና ታላቅ ደስታዬ ነበር ። ዛሬ ድንገት ከድብታዬ እንደ መባነን ያለ ስሜት ተሰማኝ እና ማዳበሪያ አገልድሜ የጠበኩት በባዶ እየሄድኩ የፈለኩት ያ የጥቅምት ፀሃያማ ቀን መድረሱን አወቅሁ። በርግጥ ከሆነ ጊዜ በፊትም ይህ የጥቅምት ቀን የመጣ መስሎኝ ሞቴን መንገድ ዳር ፈልጌው ነበር ። ግን ቀኑ እና ሞቴ ሳይገጣጠሙ ቀርተው እስከ ዛሬ አለሁ ። ቀኑ ልክ እንደዛሬው ደማቅ ረፋድ ነበር ። የሚፈቀር የፀሃይ ብርሃን አየሩ ላይ ተንሰራፍቶ ነበር ። ጧት ከእንቅልፌ ስነቃ ልክ እንደ ዛሬው ልከኝነት እና እርግጠኝነት ውስጤን ሞልተውት ነበር ። የመሞቻ ቀኔ መሆኑን አምኜ የደስታና ሃሴት አየር እየቀዘፍኩ የመሞቻ ቦታዬን ልመርጥ ከተጋደምኩበት ተነሳሁ ።
በመንገዴ በሞቴና በህይወቴ መካከል ያለውን ልዩነት የማያስተውሉ በማይገባኝ
ምክንያት ወደተለያየ አቅጣጫ የሚራወጡ ሰዎች ቢገጥሙኝም እንደሁልጊዜው ጉዞ ላይ ስለነበሩ ልብ ብሎ ያየኝ አልነበረም ። ወጪ ወራጁ ፤ አላፊ አግዳሚው " እብዱ"ብሎ በወል ስም ይጠራኛል። ባጠገባቸው ሳልፍ የሚደነብሩ ሴቶች ፤ ፈንጠር የሚሉ ወንዶች ሁሉም እብድ በሚል የሚያሸሽ ስም መኖሬን የዘነጉ ሁሉ በዚህ የማዕረግ ስም ስለሚጠሩኝ እኔም ድሮ እናትና አባቴ ያወጡልኝን ስም ዘንግቼዋለሁ። ለእነኝህ በዙሪያየ ለሚርመሰመሱ ፍጡራን የማስደነግጥ እና የማስፈነጥር እድፋም ተንቀሳቃሽ በድን ነኝ ። በርግጥ ከመላመድ ብዛት ዝምተኛ ባህርዬን ያወቁ አንዳንዶች ያገለደምኩትን ማዳበሪያ የተቀባሁትን ከሰል ወይንም የተሸከምኳቸውን ሃይለንዶች አይተው ከአጠገቤ ሲፈረጥጡ " አይናካም ......" ብለው ያረጋጓቸዋል ። ግን የሁሉም ድርጊት ደንታ ሰጥቶኝ አያውቅም ። ብዙ ጊዜም መንቃት የሚቻልበት በማይመስለኝ ህልም መሳይ ረጅም ጥልቀት መኻል እንዳለሁ ስለሚሰማኝ የማያቸው ሰዎች ሁሉ ደቃቃ ይሆኑብኛል ..... የሆኑ ትናንሽ .... ልክ እንደ ጉንዳን ፤ድምፃቸውም ዝግ ያለና የማይሰማ ። እንደዚህ ሆነው ሳያቸው ሁሌ ከምቀመጥበት አስፋልት ጠርዝ ከሚገኝ የስልክ እንጨት ስር ሆኜ እጄን ሰድጃ በሁለት ጣቴ ይዤ ላንጠለጥላቸው እለፋለሁ ። ያኔ ጉንዳንነታቸው ይብስብኛል ። ማነሳቸው ይጎላብኝና በተቀመጥኩበት እጄን እዘረጋለሁ ። ግን
ደርሼ አልደርስባቸውም የሚናገሩ ቢመስለኝም አፋቸው ይንቀሳቀሳል እንጂ
የሚያወጡት የጠራ ድምፅ አይሰማኝም ። ሁሌም በዙሪያዬ የነበሩ ሰዎች እንደዛ
ትንሽ ቢሆኑና ከጥቃቅን ጉዳያቸው ልቄ ከፍ ብዬ ያልተስተዋልኩ ብሆንም እኔ የሚሰማኝ ግን ከግዝፈቴ ብዛት ከእይታቸው መራቄ ነበር ። እና በዚያ የሞቴ ቀን ነው ብዬ በነቃሁበት እለት በመንገደኛው መኻል እየተመላለስኩ ለብዙ መአት ጊዜ የተቅበዘበዝኩበት ሰፈር የታረዝኩ የተጠማሁበት መንገድ ላይ ጥሩ መሞቻዬን አሰስኩ። በመጨረሻ ተሳክቶልኝ መንገድ ዳር የነበረ በጠፍጠፋ አራት ማዕዘን ድንጋይ የተዘጋ የቆሻሻ መውረጃ ጉድጓድ አገኘሁ ። አስፋልት ዳር በሚገኝ የቆሻሻ መተላለፊያ ጉድጓድ ውስጥ መሞት በጣም ጥሩ ሃሳብ እንደሆነ ተሰማኝ ። በህይወት እያለሁ ምንም ያልፈየዱልኝ ሰዎች ለራሳቸው ጉዳይ ብለውም ቢሆን ይሄን ጉድጓድ በመቆፈራቸው ጥሩነታቸውን እንደቸሩኝ አሰብኩ ።
ጉድጓዱ ዳር ተንበርክኬ ክዳኑን መግፋት ጀመርኩ ። እህል ከቀመስኩ ስንት ቀናት እንዳለፉ ረስቼው ነበር የድንጋይ ንጣፉን ማንሸራተት ቋጥኝ የመግፋት ያህል ሲከብደኝ ግን ያላዳመጥኩት ከባድ ረሃብ እንደተጠናወተኝ አወቅኹ። ለትንሽ ቅፅበትም ድንጋይ መግፋቴን ገትቼ በባዶ ሆድ ላለመሞት ፍርፋሪ ላገኝ ወደምችልበት በቅርብ ርቀት ወደማገኝ ምግብ ቤት አይኔን ላኩ ። በምግብ ቤቱ
በረንዳ ላይ ተኮልኩለው የሚመገቡ ሰዎች አይን ከአይኔ ጋር ቢጋጭ በሚል
ተስፋ ትንሽ ደቂቃዎችን በዚያ ያሉ ሰዎችን ስመለከት ቆየሁ ። ከቆይታ በኋላ አይቶኝ ረሃቤና ፍላጎቴ ገብቶት የሚጠራኝ እንደሌለ ስረዳ አይኖቼን መልሼ ያለ የሌለ ጉልበቴን ሰብስቤ የተውኩትን የድንጋይ ንጣፍ መግፋቴን ቀጠልኩ። ከስንት ግፊያ በኋላ ፈቀቅ ብሎ በተከፈተው የጉድጓዱ ክፍተት በኩል የታፈነ እና የሚገፋተር ቆሻሻ ሽታ ተንኖ ወጥቶ ያጎነበሰ ፊቴን አፈነኝ ። መጀመሪያ አካባቢ የቆሻሻውን ሽታ ተጠይፌ ፊቴን ማዞር ፈልጌ ነበር ። ወዲያው ግን የመጣሁበት አላማ ሞት መሆኑ ትውስ ሲለኝ የድንጋይ ንጣፉን ወደ ጎን ገፍቼ የቆሻሻው ጉድጓድ ውስጥ ጭንቅላቴን ቁልቁል ደፈቅሁ። ጉድጓድ ውስጥ ጭንቅላቴን አስቀድሜ ስገባ ሙሉ በሙሉ ለመግባት አስቤ ቢሆንም ያገመደልኩትን ማደበሪያ ከጉድጓዱ ውጪ የሆነ ነገር ጠልፎት እግሮቼ
ተንጨፍረው ውጪ ቀሩ ። በዚህ ሁኔታ ጥቂት ደቂቃዎች አልፈው በቆሻሻው ታፍኜ አፍ አፍንጫዬ እና ጆሮዬ ተደፍነው አይኖቼ ተጋርደው አስቀያሚ ሽታ ያለው
የቆሻሻ ባህር ውስጥ ቆየሁ ። ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ከአላፊ አግዳሚው መኻል ወደ ጉዱጓዱ የሚመጡ ኮቴዎች ድምፅ የተዘፈቅኩበትን ቆሻሻ አልፎ ጆሮዬ ሲደር ታወቀኝ ። ከገባሁበት ጎትቶ ሊያወጣኝ የደፈረ አልነበረም ። ግን ክብ ሰርተው ቁልቁል የሚያዩኝ ብዙ ሰዎች ንግግር ይሰማኛል ። " ራሱ እኮ ነው የገባው .... አሁን አይቼዋለሁ ከፊቴ ነበረ .... መጥቶ ጉዱጓዱን ከፍቶ ገባ" ትላለች አንዷ
" አፈር ልብላ ሰው ደብድቦ ጨምሮት ነው?" ትጠይቃለች ሌላኛዋ " ኧረ ማን ይደበድበዋል ! እብድ እኮ ነው ራሱ ገብቶ ነው " ይመልሳል ሶስተኛው " ውይ እብድ ነው እንዴ ? ደህና ሰው መስሎኝ " የቅድሟ አዛኝ መሳይ ጠያቂ እንዲህ በማንነቴ እየተከራከሩ እብድ መሆኔን ሲያውቁ ሞቴን አቃልለው ቀድመው የሰጡኝን ርህራሄ ከመግፈፋቸው በፊት መታፈኑ ስላንገሸገሸኝ ተረባርበው ከገባሁበት እንዲያወጡኝ ፈልጌ ነበር ። " ውይ እብድ ነው እንዴ ? ደህና ሰው መስሎኝ " ን ስሰማ ግን ከነእርሱ የጭካኔ ክርፋት የምምገው ቆሻሻቸው እንደሚሻል አሰብኩ ። ከእነዚህ ፍጡራን መገላገል አለብኝ ። ግን የተሻለ መሞቻ መምረጥ ነበረብኝ ። በእነርሱ ቆሻሻ ታፍኜ መሞት አልነበረብኝም ። ይሄንን እያሰብኩ በሰመመን ውስጥ ሆኜ ቁልቁል የሚያዩኝን ሰዎች አዲስ የተቀላቀለ የሚመስል ሌላ ሰው
" ለምን አናወጣውም ? ፌስታል አለ? በፌስቴል እናውጣው ፌስታል ፈልጉ" ሲል ሰማሁትና አጎንብሼ በተደፈቅኩበት ፈገግ ለማለት ሞከርኩ ፤ ፈገግ ስል ድድር ቆሻሻ ጥርሴ ላይ ተጋገረ ። ከእኔ ነፍስ የበለጠ በውሃና ሳሙና የሚፀዳ የሚነኩት ቆሻሻ ሲጠነቀቁ ላዬ የተዘፈኩበት ቆሻሻ የእነርሱ አይመስልም ። የነፍሴን ዋጋ ከእጃቸው ንፅህና ጋር ሲያነፃፅሩ በስንት ሃጢያትና ወንጀል የተጨማለቁ አይመስሉም ። ፌስታል የሚፈልገው ሰውዬ ድምፅ እየራቀኝ ሄደ ። ይመስለኛል ፌስታል ሊገዛ ነው ። ወዲያው አንድ ሌላ ሰው " ለምን ቆማችሁ ታዩታላችሁ እናውጣው እንጂ" ሲል ተሰማኝ " ቆሻሻ ነው ፌስታል ሊገዛ ነው " ብሎ መለሰለት ሌላ ሰው " ያማችኹዋል እንዴ ! ሰውዬውኮ እየሞተ ነው ፤ እናውጣው እንጂ " ብሎ ከእግሮቼ ጋር የተንከረፈፈ አንድ እጄን መጎተት ጀመረ ። ወዲያው እግሬን ሌላ ሰው ሲይዘኝ ታወቀኝ ። እግሬን የያዘው ሰው በፌስታል እጁ ላይ ጠቅልሏል ። አራት
አምስት የሚሆኑ ሰዎች ከጉድጓዱ አወጡኝና መሬቱ ላይ ተቀመጥኩ ። ቆመው የሚያዩኝን ሰዎች አንዴ
ገርምኳቸው እና የመሞቴን ሃሳብ እንዳመከኑብኝ ሳስብ ተመልሼ ወደ ጉድጓዱ ለመግባት ፈልጌ ታገልኳቸው ።
"ድጋሚ ሊገባ ነው ... አትልቀቀው" ተባብለው ጥፍንግ አድርገው ያዙኝ። ወዲያው ከየት እንደመጣ ግራ የሚያጋባ ዶፍ መዝነብ ጀመረ ። የከበቡኝ ሰዎች በሙሉ ያንፏቀኩትን የድንጋይ ንጣፍ መልሰው ጉዱጓዱን ከድነው ተበተኑ። ብቻዬን ቀረሁ ፤ ብቻዬን ዶፍ መሃል ቀረሁ በብራ የጥቅምት ቀን የመሞት
እቅዴን ዝናቡ አከሰመብኝ የዛን ጊዜ ከተወለድኩ ጀምሮ አልቅሼ የማላውቀውን ለቅሶ አለቀስኩ ። እንባዬ ከዝናቡ ጋር ተባብሮ እላዬ ላይ የነበረውን ቆሻሻ አጠበልኝ። የዛን እለቱ ሞቴ አጎጉቶኝ ከተመለሰ በኹዋላ ታዲያ እንደ ዛሬዋ አይነት ቀን ስጠብቅ ነፍሴን ከጉድፍ ባቃለሉ ሰዎች መኻል ብዙ ኖርኩ ። በመጨረሻ ግን የናፈቀኝ ደማቅ ፀሃያማ ቀን ደርሶ መሞቻዬን ለመምረጥ ተነሳሁ። ጥሩ መሞቻ የመሰለኝ ቦታ ላይ ደርሼ ከተማውን አንዴ ቁልቁል አየሁት ። ከዚህ ሆኜ ሳያቸው ሰው የሚባሉ ፍጡራን ከጉንዳንም አንሰዋል ። ቀኑ ደስ ይላል ፤ በመጨረሻ ለስ ብላ የወጣች ፀሃይ ፣ ቀዝቀዝ ብሎ የሚነፍስ ነፋስ ፣
ለመውጣት የምትታገለኝ ነፍስ ፣ በቃኸኝ ያልኩት ስጋዬ አንድ ላይ ተገናኝተናል ።
እጆቼን ዘርግቼ አየሩ ላይ ተደፋሁ እግሮቼ ከቆሙበት ተነቀሉ ። የለበስኩት
ማዳበሪያ እንደ ክንፍ በላዬ ላይ ተንሳፈፈ ከሩቅ ለሚያየኝ ወፍ ነው የምመስለው ። ወደ ታች እየተምዘገዘኩ ነው ። ወደታች እየወረድኩ አየር ላይ ነኝ በወፎች እጅግ ቀናሁ ለካ መቅዘፍ እና መብረር ከመኖር ይበልጥ ደስ ይል ነበር ። ምናለ ወፍ ሆኜ ብፈጠር የሚል ምኞቴን ሳልጨርስ በሃይለኛ ግጭት ከመሬት ጋር ተላተምኩ ። ጭንቅላቴ ደንዝዟል ቢሆንም የሚፈሰኝ ትኩስ ደም ይሞቀኛል። መላ ቅጡ የጠፋው ህመም መኻል ነኝ ። ሰዎች ተሯሩጠው ደረሱ ።
" ምን ሆኖ ነው?"
" ከፎቁ ላይ ወድቆ . ... ከላይ ነው የወደቀው ከ 21 ኛው ፎቅ ..0 አይተርፍ "
" ሰው ገፍትሮት ይሆን ?"
" አይመስለኝም .... እብድ ነው"
እብድ ነውን ስሰማ በደም ተሸፍኜ በተንጋለልኩበት ፈገግ አልኩ ። የእብድ ሰው ነፍስ ዋጋ የወረደ መሆኑን ባውቅም ከ'ደህና ሰው' ነፍስ ጋር ያለውን ትክክለኛ ምንዛሬ ሳላውቅ መሞቴ ልክ እንዳልነበር አሰብኩ ። በመጨረሻ ፈገግታዬን እንኳን ሳልሰበስብ ሁሉ ነገር ጨለመ።

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሰው መሆን አይቀርም
(በእውቀቱ ስዩም)

-መስከረም 2፤ 1967-
ከስድስት የማያንሱ አፍላ መኮንንኖች ወደ ቤተመንግስት ዘው ብለው ገቡ! ከጥቂት ደቂቆች በሁዋላ አዛውንቱን ንጉሰነገስት ቀዳማዊ ሃይለስላሴን በቤተመንግስት ቢሮአቸው አፈፍ አስነስተው አንዲት ውራጅ ቮልስ ዋገን ውስጥ ቀረቀሯቸው:: ከኒህ አፈናቃይ ወጣት መኮንኖች አንዱ መቶ አለቃ ፍቅረስላሴ ወግደረስ ይባላል ፤ በጊዜው የነበረውን ስሜቱን ካመታት በሁዋላ አስታውሶ ሲፅፍ “ ለብዙ አመታት ስጠብቀው የቆየሁት ምኞቴ ሲፈፀም በማየቴ ደስ አለኝ “ ይላል ፤
-ከአስራ ስድስት አመታት በሁዋላ -
“ የሰሜኑ ኮከብ “ ብሎ ራሱን የሚያንቆለጳጱሰው የኢሀአዴግ ጦር አዲሳባን ተቆጣጠረ፤ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሬድዮ “ የመንግስት ባለልጣናት በአርባ ስምንት ሰአት ውስጥ እጃችሁን እንድትሰጡ” እሚል አዋጅ አስነገረ፤ በስልጣን ላይ የነበሩ ሁሉ አዋጁን ሰምተው አንድ ዳንግሌ በግ ተሰልፈው በመሄድ ገበሩ፤ ከኒህ መካከል አንዱ በጠቅላይ ምኒስትር መአረግ የቆየው ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ ነበር፤ በቀጥታ ወደ መከላከያ ምኒስተር ነዳ፤ እዛ ሲደርስ የግቢው በር አሜት በጠማው ህዝብ ተከቧል” አንዳንዶች ከንፈራቸውን በአዘኔታ ሲመጡ አንዳንዶች የስድብ ናዳ ያወርዱብኝ ጀመር “ ይላል፤ ከአመታት በፊት፤ አረጋዊው ንጉስ ፤እንደ ጃንጥላ ታጥፈው፤ በቮልስ ተጠርዘው “ ሌባ ! ሌባ! “ የሚል ርግማን ሲይስተናግዱ ታዝቦ የተደሰተው ሰውየ ዛሬ ደግሞ በተራው ከውርደት ጋር ተጋፈጠ !
የጊዜው ሃይለኞች ፤ እንኩዋን ደህና መጣህ ብለው ተቀብለው፤ ለመጭው ለሃያ አመት ወደሚማቅቅበት እስር ቤት ወረወሩት! በተራቸው በመፍለጥ በመቁረጥ በማፈን እና በመዝፈን ላይ ተሰማሩ! ዛሬ እኒያ ሃያላን በተራቸው ክንዳቸው ልሟል:: ጉልበታቸው ደክሟል ፤
" ሰባሁለት ሰአት ሰጠናችሁ፤ሰባሁለት መረቅናችሁ” የሚል ሃያል ተነስቶባቸዋል ! ያኔ ሃይለስላሴን ሲወድቁ ጠብቆ በዘለፋ ያጠናገረ፤ በፍቅረስላሴ ላይ የስድብ ናዳ ያወረደ ሰፊ ህዝብ በተረኛ ወዳቂዎች ውርደት ይጨፍራል፤ የልግጫ ሜም ይሰራል!
በፈረቃ መከባበር እያቃተን በፈረቃ እንዋረዳለን! ስልጣን ላይ የሚወጣ ሁሉ ዳፍንታም ነው፤ ጉልበት አላፊ ጠፊ ፤ ድልም ያንድ ሰሞን መሆኑን ማየት አይችልም!
ጣይቱ ብጡል ከስልጣን ስትወርድ ያንጎራጎረቺው ግጥም የሁሉም የቀድሞ ሃያላን ድምፅ የሚወክል ይመስለኛል፤
“እምቢልታ ማስነፋት ነበር አመላችን
ነጋሪት ማስመታት ነበር አመላችን
ሰው መሆን አይቀርም ደረሰ ተራችን “

@wegoch
@wegoch
የባል ገበያ
(ክፍል አንድ)
ሜሪ ፈለቀ

እንዴት ተጣበሳችሁ?” ብላ ዛሬም አፋጠጠችኝ። ምን ቀን አቅለብልቦኝ ቋንቋውን የምማረው ለቪዛ መሆኑን እንደነገርኳት እንጃ……

“እስቲ መጀመሪያ አንቺ ንገሪኝ።” ጥያቄዋን ሽሽት እንጂ የሷን የጠበሳ ታሪክ የመስማት ጉጉት ኖሮኝ አልነበረም። እንኳን ተጠይቃ እንዲሁም ምላሷ ሞት አያውቅም።

“እኔማ ዴቲንግ ሳይት ላይ ነው የጠበስኩት። …… እኛ ክላስ ከሰላምና ከኤልሳ በስተቀር ሁሉም በ ‘balshemeta.com‘ ዴቲንግ ሳይት ነው የጠበሱት። …” አፀደ ስታወራ መወራጨቷ እና ቅብጥብጥነቷ ልትበር የምታኮበኩብ ያስመስላታል። …… ያንጨፈረረችው ፀጉሯ ሳይቀር እየፈጠነች ከከንፈሯ ከምታግተለትላቸው ቃላት ጋር ብን ትን ይላል። ቢሆንም ወሬዋ ጆሮና ቀልቤን ጠለፈው…… በዴቲንግ ሳይት የውጪ ሀገር ሰው መጥበስና ወደውጪ ሀገር ለመውጣት መታተር የኔ ብቻ ታሪክ ነበር የመሰለኝ።

“እና ሁላችሁም ቋንቋውን የምትማሩት አግብታችሁ ከሃገር ለመውጣት ነው?”

“አወና! አንቺም እንደዛው አይደል?”

“እ…ሱ…ማ ነው! በተመሳሳይ መንገድ ለተመሳሳይ ዓላማ አንድ ክፍል መገኘታችን ገርሞኝ ነው።” አልኳት

አንባቢ እህቴ ሆይ የምፅፍልሽ ዶሮ ፣ ሽንኩርት ፣ ቄጤማ፣ መከለሻ…… ስለሚሸመትበት የበዓል ገበያ አይደለም። በቆዳ ቀለም፣ በእድሜ፣ በዜግነት፣ በኑሮ ደረጃ ፣ በቁመት፣ በውፍረት……… ብቻ ባሻሽ መስፈርት ባል የሚሆን ወንድ ስለሚሸመትበት የገበያ ማዕከል እንጂ…… ለመገበያየት የሚያስፈልግሽ አውድማው ላይ ዘው ብሎ መዝለቅ ብቻ ነው።… …
balshemeta.com dating site ‘ ይሰኛል መደብሩ። (ሄዋኔ ይሄን ፅሁፍ አንብበሽ ስትጨርሺ የጎልጉል ፍለጋ ሳጥን ውስጥ ‘ፈልግ‘ን እንደምትጠነቁዪ በመጠርጠር በዚህ ተረክ ውስጥ የተጠቀሰው የሳይቱ ስም ተቀይሯል። …… ሃሃሃሃ)

የዳሌ ቁጥርሽ ሳይቀር ስለራስሽ የጠለቀ ጥያቄ እና የመልስ ሳጥን ይከታተልልሻል። … … ይሄ ብቻ በቂ አይሆንም። ባልሽ እንዲሆን የምትፈልጊውን ሰው ገላው ላይ ያለ የማሪያም ስሞሽ ጭምር በመጥቀስ መስፈርትሽን ታኖሪያለሽ። …… አክለሽ አምስት ቄንጠኛ ፎቶግራፎችን ትለጥፊያለሽ። (በእርግጥ የፎቶው ቄንጥ ግዴታ አይደለም።) አከተመ። ገበያው ውስጥ መሰስ ብለሽ ገብተሻል። …… በተለያየ የዓለማችን ክፍል ካሉ ወንዶች(አብዛኛዎቹ አዛውንቶች እና ለአዛውንትነት የቀረቡ ናቸው) መልዕክቶች ይደርሱሻል። …… የመረጥሽውን ታናግሪያለሽ።

በተመሳሳይ መንገድ አንድ አሜሪካዊ አግብታ የሄደች ወዳጄ (እንደመታደል ሆኖ እኩያዋን ነው ያገኘችው።) በጠቆመችኝ መሰረት በአንድ ያበደ ቀን ሸመታው መሃል ዘመትኩ። …… ከእብድ እስከ ስድ፣ ከአይንአፋር እስከ አደንቁር፣ ከአዋቂ እስከ ልብ አውላቂ፣ ከአስተዋይ እስከ ደም–አፍይ… …… ሳምንታት ከፈጀ አሰልቺ የንግግር ልውውጦሽ በኋላ ከሁለት ሰወች ጋር በቋሚነት ተግባብቼ ማውራት ስለቻልኩ ከሳይቱ ወጥቼ በቫይበር እና በፌስ ቡክ ማውራት ጀመርኩ። አንደኛው ፎቶግራፍ ካለመለጠፉም በላይ እንዳየውም ሆነ እንዲያየኝ ፍላጎት የለውም። የሚፅፍልኝ ቁምነገር ግን ችላ እንድለው አላደረገኝም።

አንደኛው ፈረንሳዊ ጎልማሳ ነው። ከእርሱ ጋር በስካይፒ አወራን። መወሰን ስለነበረብኝ መረጥኩ።…… ከወራት በኋላ ልቀበለው ቦሌ አየር ማረፊያ ተገኘሁ። ……

በአካል የማያውቁትን ሰው ፍቅረኛዬ ብሎ አስቦ ለመቀበል መሄድ የሆነ የማያውቁት ሰው ቀብር ላይ ተገኝቶ ከሬሳው ቀድሜ ጉድጓድ ውስጥ ካልተነጠፍኩ ብሎ ለያዥ ለገናዥ እንደማስቸገር ያለ የቂልነት ዓይነት ስሜት ነበር የፈጠረብኝ። …… ሳየው ምንድነው የማደርገው? አቅፈዋለሁ? እስመዋለሁ? ኸረ ከነጭራሹ በአካል ሳየው ባላውቀውስ? …… በአካል ስንገናኝ ቢያስጠላኝስ? …… እሱስ ካገኘኝ በኋላ ባስጠላው? እኔን ለማግኘት አህጉር ማቋረጡ ቢፀፅተውስ? ………

ክብ ፊቱንና አፍንጫና አይኑን ያጣበበ ሰፊ ጉንጩን እንዳየሁ አወቅኩት። …… ሳይደናገር ሻንጣውን እየገፋ በፈገግታ ወደኔ አቅጣጫ ቀረበ። ሲስቅ ጉንጩ ይንጠለጠልና ሊወድቅ እየመሰለኝ ልደግፍለት መዳፌን ማቅረብ እየቃጣኝ ከብዙ የመተቃቀፍ ሰላምታ በኋላ ሆቴል ደረስን። …… በእርግጥ ከጠበቅኩት ክብደት በላይ አንድ ጎረምሳ ያህል ጨምሮብኛል።(ወደ 30 ኪሎ የሚሆን)

ከፊት ለፊቱ ሲታይ ጥቅጥቅ ብሎ ሙሉ የሚመስለው ፀጉሩ የመሃል አናቱ አመላለጥ የሚቀመጠው በቂጡ ሳይሆን በአናቱ አስመስሎታል።……

አብረን በነበርንባቸው ሳምንታት ለመላመድ ጊዜ አልፈጀብንም። ቁጥብ፣ ስነስርዓታም እና ፈገግታም ነው። ሳቄ ሊያመልጠኝ እየታገለኝ ልለምደው ያልቻልኩት የአልጋ ላይ ባህሪውን ነበር። … …… ጉዳዩን እየከወነ እንደላንቲካ ተኮሳትሮ ሲያፈጥብኝ ከፀበኛው ጋር መንገድ ላይ ድንገት የተፋጠጠ እንጂ ፍቅር እየሰራን አይመስልም። በየመሃሉ የመሳደብ አይነት ምላሱን ብቅ ጥልቅ የማድረግ ልምዱ ሳቄን ያታግለኛል። …… ወደ ሀገሩ ሊመለስ በረራው ሰዓታት ሲቀሩት እንደተለመደው በምላሱ ‘እየተሳደበ‘ ሲተጋ … የጠጣሁት ወይን ተደምሮ ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ። ……… ይሄኔ ተበሳጨ። …… ብስጭት ግን በእንግሊዘኛ አይመስጥም። …… ‘ኤጭ‘ ሳይባል ብስጭት ምኑን ብስጭት ሆነ? ‘ኤድያ‘ ካልገባበት ምኑን ተበሳጨ?

ትጋቱን አቁሞ ታሪክ ይሉት ትንግርት አወጋኝ። …… ከአመታት በፊት በአደጋ የዘር ፍሬውን ላጣ ጓደኛው የቀኝ ፍሬውን መለገሱን እና ከዚያ ወዲህ ለመርካት እንደሚቸገር የነገረኝን ቀልድ ነው ብዬ እንዳላልፍ እንባ ካዡ አይኖቹ የምሩን መሆኑን ተረድቻለሁ።…… የሰማሁትን እርግጠኛ መሆኔን በመጠራጠሬ ነክቼ ‘ይሄንን ነው የለገስከው?‘ ማለት ሊቃጣኝ ስዳዳ… … ገበያ እንደቀረበ ቲማቲም ፍሬዎቹን ለቀም አድርጎ ሰብስቦ

“አየሽ አንዱ ፍሬ የለም። እንቺ ነክተሽ አረጋግጪ! ” አለኝ። ‘ንኪ‘ ያለኝ የሎሚ ፍሬ ይመስል ቀለል አድርጎ

“አንዳች መዓት ይንካህ!” አልኩኝ በሆዴ እየዘገነነኝ…… ለአራት ሳምንታት አብሬው የነበርኩት ሰው ሳይሆን የሆነ የሚሸክክ ፍጡር ሆነብኝ። …… ምኑ እንደዘገነነኝ አላውቅም። ፍሬ— አልባ መሆኑ? አሁንም አሁንም አፍንጫውን እየሞዠቀ ቆለጡን እየነካካ ማለቃቀሱ? ብቻ የሰውነቴ ቆዳ ሽፍ እስኪል ሸከከኝ…… ጥዬው ብሄድ ደስ ባለኝ።

👉🏽👉🏽👉🏽አልጨረስንም👈🏽👈🏽👈🏽

@wegoch
@wegoch
@paappii
🌟Blend'N Magazine is here as expected with its 5th edition with more special and fresh contents starring international photographer Aida Muluneh and research institute N.E.R.D ... make sure you subscribe to get the latest updates. Read online on www.blendn.ml
Subscribe | Join | Contact
Blend'N Magazine
★★የባል ገበያ ★★
(ክፍል ሁለት)
ሜሪ ፈለቀ

ጥዬው ብሄድ ደስ ባለኝ። …… እንደምንም ለሁለት ሰዓታት ታግሼ አየር ማረፊያ ድረስ ሸኘሁት። …… እቅዳችን የነበረው ከወር በኋላ ተመልሶ መጥቶ ልንጋባ ነበር።…… ፊቴን ሳዞር የመጀመሪያ ስራዬ ሊያገኘኝ የሚችልበትን መንገዶች በሙሉ መዝጋት ነበር። ………
……
……
"አዚቲ እኮ ቪዛዋ ተሰጣት።" አለች አፀደ እንደ ልምዷ እየተቅለበለበች። ክላስ ውስጥ ያለው ሴት በሙሉ በቄንጥ ተንጫጫ

"ምን ያደርጋል ግን……" ቀጠለች ሴቱ ለ ‘ኦ ማይ ጋድ‘ ቄንጥ የሰቀለውን እጁን ከአየር ላይ ሳያወርድ

በአንድ የአውሮፓ ቋንቋ ትምህርት ቤት ውስጥ ቋንቋ ለመማር ነው የተሰበሰብነው። …… በሚገርም ሁኔታ ከአንድ ወንድ በቀር ሁላችንም ሴቶች መሆናችን ሲገርመኝ። ሁላችንም ለቪዛ ከትምህርት ቤቱ የቋንቋ ብቃት ሰርተፊኬት ስለሚያስፈልግ የምንማር ነን። ከዚህ በላይ የደነቀኝ ግን ከሁለት ሴቶች በቀር ሁላችንም በተመሳሳይ የሳይበር ጠበሳ ትዳር መስርተን በጋብቻ አመሃኝተን ከሀገር ለመውጣት የሚጠበቅብንን እያሟላን መሆናችን ነው።

አዚቲ (ቪዛዋ የተፈቀደላት) ከወራት በፊት ነበር ያገባችው። ጓደኞቿ ሲያላግጡባት
‘ባሏ ከመምጣቱ ሳምንት በፊት አስቀድሞ ከዘራውን ነው የላከው። ከዘራውን ይዛ ሄዳ ነው ቦሌ የተቀበለችው‘ ይሏታል። እሷ በራሷ የምትፎግር ፍሪክ ናት። ትስቃለች።
ያገባችው ሰው ከተጋቡ ጀምሮ ቪዛው እስኪፈቀድ ሀገሩን ትቶ ገስትሀውስ ተከራይተው አብሯት እየኖረ ነበረ።

አዚቲ እንኳን በደሞዝ በእቁብ የማትቻል ወመኔ ሱሰኛ ናት። …… ሰውየውን በስተርጅና ቃሚና ቀምቃሚ አደረገችው። …… እንደአፀደ ገለፃ ቪዛው መፈቀዱን በሰማ እለት በከፍተኛ ምርቃና ውስጥ ሆኖ አንድ ነገር ተከሰተለት። …… ኢትዮጲያን ወዷታል። …… አዚቲን የመሄዱን ሀሳብ ትተው እዚሁ እንዲኖሩ ቢያማክራት ‘ነብር አየኝ በል‘ አለች።(በእርግጥ በእንግሊዘኛ እንዴት እንዳለችው እንጃ!) በመጨረሻ ሰውየው ውሳኔውን አስተላለፈ።

"ከፈለግሽ አንቺ መሄድ ትችያለሽ! እኔ ከዝች ሀገር እግሬ ንቅንቅ አይልም!"
አፀደ ወሬውን ከአፏ ቀምቶ ሌላ ሰው የሚያወራባት ይመስል እየተሽቀዳደመች አውርታ ስትጨርስ ፍርፍር ብዬ መሳቅ አምሮኝ ነበር። ከሀብቴ(የክፍላችን ብቸኛ ወንድ) በቀር ሁሉም የለቅሶ ቤት ፍራሽ ላይ የተቀመጡ ያህል ተክዘው ሳይ ሳቄን ዋጥኩት። ……
……
……
ባለአንድ ፍሬውን ተጣማሪዬን ከተለየሁ በኋላ ለቪዛ እየተማርኩ የመገኘቴ ኋሊት እንዲህ ነው። ……
ሸኝቼው ስመለስ የምቀጥለው ኑሮ እንዳልነበረኝ ገባኝ። የሆነ መንገድ ላይ መኖሬን ቀጥ አድርጌዋለሁ…… የሆነ ሩቅ መንገድ ላይ…… መኖር ወደውጪሃገር መሄድ ሆኗል። …… እዛች ቦታ ላይ ኢትዮጲያ ውስጥ መኖር አቁሚያለሁ። …… መኖር ከሃገር ለመውጣት መሰናዳት ሆኗል። …… …… ይሄን አቁሜ እዛጋ የሰበርኩትን ድልድይ ገጥሜ መኖር እንደማልችል የገባኝ…… ፈረንጅ መጥበሴን እናቴ በሰማች ማግስት ስልክ ደውላ

"እልልልል ልጄ ከሰው እኩል ልታደርጊኝ ነው?" ስትለኝ

"ፈረንጅ ካገባሽ ሳይክል ትገዢልኛለሽኣ?" ታናሽ ወንድሜ በለሊት ቀስቅሶኝ ሲጠይቀኝ

"አሰይ ልጄ የአባትሽን መቃብር አሳድሽለት!" ስትለኝ አክስቴ

"መድሃኒያለም ሳልሞት ያንቺን ዓለም ሊያሳየኝ ነው።… …እንደው ልጄ የምትታለብ ላሜ ሞታብኛለች ደህና ላም አይተሽ ግዢልኝ። እመርቅሻለሁ።" ስትል አያቴ
ይሄኔ ለራሴ ወሰንኩ። በየትም መንገድ ከሀገር እወጣለሁ። …… ከውሳኔዬ እኩል መፃፃፍ አቁሜ ከነበረው አንደኛው ሰውጋ መፃፃፌን ቀጠልኩ። ……
መልኩ ምን እንደሚመስል አላውቅም።የውጪ ዜጋ ከመሆኑ ውጪ ስለራሱ የነገረኝ ነገር የለም። ሲያወራኝ (በፅሁፍ) ግን የማውቀው… … የሚያውቀኝ…… ረዥም ጊዜ አብረን የሆንን አይነት ነው የሚሰማኝ። …… ሰው የማያውቀውን ሰው ይለምዳል? ለመድኩት። …… የእውነት ያለ ሰው መሆኑን እንኳን ማረጋገጥ የማልችለውን ሰው አመንኩት። …… ጣቶቼ ከስልኬ ላይ ሳይነሱ ይመሻል። ……… ስለብዙ ነገር በማውራታችን የተዋወቅን መሰለ። …… ሰው ይሁን ማሽን፣ ሴት ይሁን ወንድ፣ እብድ ይሁን ጤነኛ… … የማላውቀው ሰው ትንፋሽ ይሞቀኛል። በህልሜ ሁሉ አየዋለሁ። …… ጠዋት ያየሁትን ፊት ለማስታወስ ብሞክር አይመጣልኝም። …… እበሳጫለሁ። …… ራሴ ያበድኩ ያበድኩ ይመስለኛል። ……
መጥቶ እንደሚያገባኝ ቃል ገባልኝ። …… ላላምነው ብፈልግም አመንኩት። …… ቋንቋውን እንድማር በአካውንቴ ብር አስገባልኝ። …… የማደርገው ሁሉ መጃጃል እንደሆነ እየገባኝ ተመዝግቤ መማር ጀመርኩ።……
እመጣለሁ ያለበት ቀን ስምንት ቀን ብቻ ቀርቶታል። …… መጃጃሌን አላቆምኩም። …… ስቀበለው ምን እንደምለብስ፣ የምሰጠውን አበባ፣ የቀኑን እርዝመት…… አስባለሁ። …… ባይመጣስ? እላለሁ መልሼ። ምን ስለመምሰሉ ቦታ ያለመስጠቴ ይገርመኛል። ላስብም ብሞክር ወዲያው ተወዋለሁ።
አራት ቀን……
ሶስት ቀን……
ሁለት ቀን……
አንድ ቀን……
አንድ ሰዓት ሲቀረው ቦሌ ተገኘሁ።…… ትምህርት ቤት ስለሰማኋቸው የሴቶች ገጠመኝ እያሰብኩ ‘እንዲህ ቢሆንስ?‘ ‘እንዲያ ቢሆንስ?‘ ሀሳብ እገምዳለሁ።
……
👉🏽👉🏽👉🏽አልጨረስንም👈🏽👈🏽👈🏽

@wegoch
@wegoch
@paappii
★★የባል ገበያ ★★
(ክፍል ሶስት)
ሜሪ ፈለቀ

"ሸሚዝ በከረቫት አይነት ሁሌ ሲጠነቀቁ አትመኛቸው። ወይ እጃቸው እስክትገቢ ነው አልያም የሆነ የሚያካክሱት አልባሌ አመል አለባቸው።" ያለችው ሳቢ ትዝ አለችኝ። …… ሳቢን የማውቃት በሀብቴ ነው።

ሳቢ ፈረንጅ የማግባት ፍቅር እንጂ ከሃገር የመውጣት ፍቅር አልነበረም ዴቲንግ ሳይት ላይ የጣዳት። እንኮኮ አድርጌሽ ልዙር የሚል ፈረንሳዊ ጠበሰች። …… ፊልም ላይ እንደምታየው እና እንደምትመኘው ውሃ ካልጠበስኩልሽ የሚላት ዓይነት ሆነ። …… ወደኢትዮጲያ መጥቶ እንዳያት የጋብቻ ጥያቄ አቀረበላት። ተጋቡ። …… እፍ አሉ። …… ከፍቅራቸው ምጥቀት በአንድ ቆርኪ ውሃ ገላችንን እንታጠብ አሉ። …… ሁሉም ፍፁም መሰለ። ……
እየቆየ ሳቢ አንድ ነገር እየከነከናት መጣ። ባሏ ከርሷ ጋር ባለው ወሲብ ደስተኛ አይደለም። … …… ጭራሽ ባያደርግም ደስተኛ ነው። የምታየው እንደዛ ቢሆንም በአፉ ደስተኛ እንደሆነ ይነግራታል። …… ሁሉን ለሚሆንላት ባሏ ደስታ መሆን ያለመቻሏ ህመም እየሆነባት ሳለ እንደተለመደው በሷ ቆስቋሽነት ካላቡ በኋላ እሷ ወደ መታጠቢያ ቤት ስትገባ እሱ ወደ ላይብረሪው ጋውኑን ደርቦ ሄደ።

…… ሳቢ ግራ ተጋባች። ምን ብትሆንለት ደስተኛ እንደሚሆን በማሰብ ናወዘች። …… ልታናግረው ፈልጋ ወደ ላይብረሪው እግሯን አነሳች። …… በሩን ከፍታ ያየችው መዓት ሲኦል ደርሶ መልስ ሆነባት። …… ሰው ብላ ያገባችው ባል ከሀገሩ ይዟት ከመጣ ውሻው ጋር የሚዳራ እንስሳ ሆኖ አገኘችው…… ራሷን ሳተች። …… ፈረንጅም ውሻም ጠላች። …… ሳባ መልሳ ራሷን ለመሆን ብዙ ከፈለች።……
……
……
በስመአብ! አሁን ይሄን ቀፋፊ ታሪክ ለምን አስባለሁ?
አውሮፕላኑ አርፏል። …… ሰወች እየወጡ ነው።……
ከመፍራቴ የተነሳ ባይመጣ ተመኘሁ። ውስጤ የሳልኩትን ስዕል ከሚያፈርስብኝ ቢቀር አለምኩ። …… በቃ ሁሌ እየጠበቅኩት ብኖር…… ለካንስ ተስፋ ከውጤቱ በላይ የሚያስደስተው ጥበቃው ነው። …… ወይም ጉዞው……
ሻንጣ እየገፋ የሚመጣ አስቀያሚ ሰው ባየው ቁጥር ‘እርሱ ባልሆነ‘ እላለሁ።…… ለአይኔ የሞላውን ‘እሱ ይሆን?‘ ብዬ አፈጣለሁ። … ከማርጀቱ የጎበጠ ነጭ ሲመጣ ባልሆነ ብዬ አይኔን ጨፈንኩ። ሳገኘው እንደምጠመጠምበት ነው የማስበው። …… ይሄ ሰውዬ ቢሆንስ? ሆ! ከአዛውንት ጋር እንጥልጥሎሽ ልጫወት? አይሆንም!

"እኔ አውቅሻለሁ። የቆምሽበት ድረስ ራሴ እመጣለሁ።" ነው ያለኝ ምስሉ የሌለኝን ሰው እንዴት እንደምቀበለው ስጠይቀው።
ስለእውነት ጥበቃዬን አቁሜ መሄድ ሁሉ ቃጥቶኝ ነበር። ……

"ሄላ……ኦህ ማይ ዲር ጋድ! እንዴት ነው የተለወጥሽው?" አለኝ የማውቀው የመሰለኝ ድምፅ

"እንዴ? መውደድ?" ተቃቀፍን። ……

"እንዳላግዝህ ሰው እየጠበቅኩ ነው።" አልኩት ሻንጣዎቹን እያየሁ። በሰላምታ ባጠፋሁት ደቂቃ ያለፈኝ ሰው ካለ ዙሪያ ገባዬን እያየሁ።

"ኢትስ ኦኬ!" አለኝ በእጄ የያዝኩትን ፅጌሬዳ እያየ ፈገግ ብሎ ቀጠለ

"ፍቅረኛሽን መሆን አለበት።"

"እ" አልኩኝ ቶሎ ካጠገቤ እንዲሄድ እየፈለግኩ። እኔ ምን እንደሚመስል ያላወቅኩትን ሰው እንዲያይብኝ አልፈለግኩም። ያውም መውደድ… …

"ፍቅርን ድጋሚ በማግኘትሽ ላንቺ ደስተኛ ነኝ።" አለኝ ሳይንቀሳቀስ
‘ጥለኸኝ ስትሄድ የቀበርከኝ ነበር የመሰለህ?‘ ልለው ነበር ያሰብኩት… … እሱን ማቆያ ስለመሰለኝ

"አመሰግናለሁ።“ ብዬው ፈንጠር ብዬ ቆምኩ። አይኖቼን ስራ ሰጠኋቸው።

"Am here" አለኝ መውደድ ፊቴ ቆሞ።

"መውደድ ሰው እየጠበቅኩ ነው አልኩህ አይደል? ምን እየሆንክ ነው?ለምን አትሄድልኝም።" ጮህኩበት

"እመኚኝ እኔን ነው እየጠበቅሽ ያለሽው።…… " ሊያሳምነኝ ያወራናቸውን ሁሉ ነገሮች ሲነግረኝ…… አንድ የሆነ የተዛባ ነገር የተፈጠረ መሰለኝ…… ወይም አይኔ አልያም ጆሮዬ ካልሆነም ህልም ነው…… መውደድ? አይሆንም!! አይሆንም!! ……
……
👉🏽👉🏽አሁንም አልጨረስንም👈🏽👈🏽

@wegoch
@wegoch
@paappii
★★የባል ገበያ ★★
(ክፍል አራት)
ሜሪ ፈለቀ

አይሆንም!! ……

"መውደድ እየቀለድኩ ነው በለኝ?"

"እየቀለድኩ አለመሆኔን ታውቂያለሽ!! ስትፃፃፊው የነበረው ሰው እኔ ነኝ።"

መውደድን ልጠብቀው አልችልም። …… በማትረባ ቅንዝራም አሮጊት የቀየረኝን መውደድ በፅጌሬዳ እንኳን ደህና መጣህልኝ ልለው በፍፁም አልችልም።…

… ለወራት በጠዋት ስነቃ በጉጉት ያነበብኩት "good morning ma sunshine" የሚለው ልቤን እንደጠዋት ፀሃይ የሚያሞቅ መልዕክት የመውደድ መሆኑን ሳስብ ያለፉ ጠዋቶቼ አንገሸገሹኝ። ዘወትር ምሽት ለወራት "darling u r in ma arms, hv a sweet dream" …የሚሉትን ቃላት የመውደድ ጣቶች እንደተየቡት ለማመን ሳሰላስል … አልጋዬ ላይ በምቾት የተገላበጠ ጎኔን ጠላሁት…… መውደድን ብበጫጭቀው እንኳን ንዴቴ የሚበርድ አልመሰለኝም።…… በእጄ የያዝኩትን አበባ መሬት ላይ ወርውሬ በእግሬ ደፈጠጥኩት!! ምንም ብናገረው ሁሉም ቃል ገለባ ነው። …… ዝም ብዬው ልሄድ እግሮቼን አነሳሁና… ብስጭት፣ እልህ፣ እንባ…… መላ አካላቴን ናጠኝ።

"ታውቃለህ? መቀለድህ ከነበር ጅላጅል ቀልድ ነው የቀለድከው። የማትረባ ዥልጥ ነህ!! ምን እንዳደረግክ ታውቃለህ? ለነገሩ ልታውቅ የምትችልበት ማሰቢያ አይኖርህም። አፈር ብላ!! ከንቱ!! ቂላ ቂል ከንቱ ነህ!" …… ምንም ያህል ልሰድበው ብሞክር ከተሰማኝ ብስጭት ጋር ሚዛን ላይ ሲሰፈር ያቆለጳጰስኩት ያህል ምርቃት መስሎ ተሰማኝ። …… ለዛሬ ቀን የሚሆን የክት ስድብ አጣሁ። …… አይኖቹን ከአይኖቼ ሳይሰብር ከቆመበት ሳይንቀሳቀስ ያየኛል። ………

"‘የምታፈቅሪው ሰው ደጋግሞ ግዙፍ በደል ቢበድልሽ ስንቴ ይቅር ትይዋለሽ?‘ ስልሽ የመለስሽልን መልስ ታስታውሻለሽ?" በረጋ ድምፅ ጠየቀኝ።

‘ድርጊቱን ያደረገበት ምክኒያት እንጂ በደሉ ብቻውን ትልቅም ትንሽም አይሆንም።‘ ብዬው እንደነበር አስታወስኩ።

‘በደሉን የሚያገዝፈው የትኛው ምክንያት ነው?‘ ላለኝ ጥያቄ

‘አንደኛ እኔን ለመጉዳት አስቦ ሲሆን ሁለተኛ ራሱን ለመጥቀም አስቦ ሲጎዳኝ። ባጠቃላይ የበደሉ ዘር የክፋት ጭማቂ ሲሆን ጥፋቱ ኢምንትም ቢሆን ይገዝፍብኛል።…… የማፈቅረው ሰው ያለምንም ክፋት፣ ሳያውቅ ወይም ተሳስቶ ለሚበድለኝ በደል ገና ሳይበድለኝ በፊት ሁላ ይቅር ብዬዋለሁ። …… ‘ ብዬ መልሼለት ነበር። …… እንዳስታወስኩት እርግጠኛ በመሆን ከንፈሩን ለመፍገግ እያሸሸ

"በደሌ ከይቅርታ በላይ ትልቅ መሆኑን ለማወቅ እድል ስጪኝና ምክኒያቱን ልንገርሽ።……ካለዚያ ምክኒያታዊነትሽ ከጥሩ አባባሎችሽ መሃል አንዱ ብቻ እንደሆነ ልመን? "

"ክህደት በምንም መልኩ ቢሆን ክህደት ነው። ቅን ምክንያት ልትለጥፍለት አትችልም። …… ምክኒያትህን ልሰማ ቢገባ እንኳን ያን ማድረግ የነበረብህ ከአራት ዓመት በፊት ነበር። ……" ለሱ ቆሜ ማብራሪያ መስጠቴ በራሱ አበሸቀኝ።

አባቴ ታሞ ለቀናት ባንገናኝ ፍጥረት የሚቀናበት ንፁህ ፍቅራችንን እንደምንም ሲተወው መች ምክኒያት ሰጠኝ? ከፊቷ ይልቅ ስትራመድ ወደ ታች ተረከዟን ወደ ላይ ማጅራቷን የሚነካ እስኪመስለኝ የምታስደንሰው የሚያሳቅቅ ትልቅ ቂጧ ትዝ የሚለኝን ሴትዮ ማግባቱን እንኳን መች ከሱ ሰማሁ? ለአንድ ቀን ድምፄን ካልሰማ ‘ሳልሞትብሽ ስልክሽን አንሺው‘ ይለኝ የነበረ ሰው ከሃገር መውጣቱን ከሄደ በኋላ ቤተሰቦቹ ሲነግሩኝ ሳሎናቸው መሃል ራሴን ስቼ መውደቄ ለሱ ምኑ ነበር? ከዛሬ ነገ መጥቶ ይቅርታ ይጠይቀኛል ብዬ ስጠብቀው መች ለአፍታ ትውስ አልኩት?
አባቴ ከሞተ በኋላ በየቀኑ ሳይደክመኝ ስለሱ አስብ ነበር። ……ቢያንስ ለማፅፅናናት ይደውልልኛል ፣ መከፋቴን ሲያይ አያስችለውም፣ እንባዬን ከሚያይ ከየትኛውም ዓለም ክፍል ይመጣልኛል፣ ከቂጣሟ አሮጊት ሚስቱ እንደምበልጥበት ይነግረኛል…… ሳኮርፈው ሁሌ ያደርግ እንደነበረው የታችኛው ከንፈሬን ብቻ እየደጋገመ ይስመኛል። …… ሲጣፍጠኝ በደሉ ይሸረፍብኛል። …… እጆቹ ወገቤን አልፈው ሲወርዱ ምን አድርጎኝ እንደነበር ይጠፋብኛል። …… ሰውነቱ ሰውነቴን ተጭኖ ሲዘልቀኝ እንኳን የአሮጊቷ ቂጥ ትዝ ሊለኝ ሰማይ በቂጡ ከምድር ቢጋጭ ጉዳዬ አይሆንም…… ከዛ የኔ ብቻ አደርገዋለሁ።…… እያልኩ አስብ ነበር።
ተስፋ ቆርጬ እስክደነዝዝ እሱ የት ነበር?

"ውዴ? እባክሽ ሁሉንም ነገር ያደረግኩት ላንቺ ስል ነበር።" ብሎ ‘አፌዘ‘
እንድናርፍበት የተከራየሁትን ሆቴል ቁልፍ ወርውሬለት ሊቀበለው የመጣውን የሆቴሉን መኪና ጠቁሜው በእግሬም በሃሳቤም ወደተውኩት ኑሮ ተራመድኩ። …… እንደማገባ የነገርኳት እናቴ ፣ ‘ልጄ ልታገባ ነው ግን ሚስጥር ነው‘ ብላ እናቴ የነገረቻቸው ቁጥር አልባ የማውቃቸው ሰወች፣ ከሀገር በመውጣት ስንድት ሰበብ የገተርኩት ኑሮዬ፣ ማንነቱን ለማያውቀው ሰው ጦሽ ያለው ገልቱ ልቤ፣ አርቄ ከሰቀልኩበት የተፈጠፈጠው ከሀገር የመውጣት ህልሜ፣ አከታትዬ የምወልዳቸው ድቅል ሁለት ወንድ ልጆቼ፣ ለእናቴ የምሰራላት ቪላ ቤት ………… የቧቸርኩባቸው ቅዠቶቼ ናቸው። ስነቃ የበነኑ። …… ለካንስ በቅዠት መፈንጠዙ አይከብድም። …… ቅዠቱን ማቆምም ብዙ አያታግልም። …… ወደ እውነታው መመለሱ ነው እብደት። …… ……
………
……
መውደድን ከኋላዬ ትቼው ከሚታገለኝ እንባዬ ጋር ግብ ግብ ገጥሜ ወደ ቤቴ መጓዝ ጀመርኩ። ……
👉🏽👉🏽 አልጨረስንም👈🏽👈🏽

@wegoch
@wegoch
@paappii
ከአቡሻ ጣሪያ ስር !
ትዝ ይለኛል ታላቅ እህቴ በጩኸት ግቢውን ስትደባልቀው ! “ኡ ኡ እማዬ ነይ ጉድሽን እይ” ነው ያለቻት ።
የምን ጉድ መጣ ደግሞ ። እኛ ቤት ከወር ቀለብ እኩል የማይጠፋ ጉድ የሚባል ሌላ የሚዘጋጅ አስቤዛ አለን ።
የጉዳችን ምንጮች ብዙ ቢሆኑም ዘጠና በመቶዎቹ ግን ከታናሽ ወንድማችን አቡሻ ክፍል የሚሰሙ ተዓምራት ናቸው።
ታናሽ ወንድሜ አቡሻ በመሀል አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በለሊት ተነስቶ ነብር ሊበላኝ ነው ብሎ ሲቀውጠው የነበረ የጉድ ማህደራችን ነው ። አቤት በሰዓቱ የነበረ የእናቴ ድንጋጤ ! እንዴት ከመኝታዋ እንደተነሳች ፣ ከመቼው ጋቢዋን ከበላይ እንደደረበች ሳናውቅ ከመቅፅበት አቡሻ ክፍል ተገኘች ።
ሌሎቻችን አቡሻ ባመሸበት እዳ እኛ ለምን በነብር እንበላ በሚል ፍርሀት ሁኔታውን በሳሎናችን በር በኩል ነበር ስንከታተል የነበረው ። በዛ ክፉ ሰዓት የእናትነት እና የእህትነት ድንበር ላይ የምትሰመረው ብቸኛ ቀጭን መስመር ለአይን ጎልታ መታየት ጀመረች። በርግጥ በወንድም እና ወንድም መሀከል መስመር መኖሩ አይን ላለው ሰው አይደለም ማየት ለተሳነውም በዳበሰ ለመለየት ያስችላል ። እናትና እህትነት መሀከል ግን መቀራረብ አለ ። እናት ለልጅዋ የምታስበውን አቅራቢያ እህት ለወንድሟ ታስባለች። እናት ልጇን የምትወደው አንድ ኪሎ ቢሆን እህት ሩብ ቀረሽ ለኪሎውን ያህል ወንድሟን ትወዳለች ። ብዙውን ጊዜ በእናትነት እና በመልካም እህትነት መሀከል ያለውን ልዩነትም አጥርቶ ለማየት የሚቸግርበት ወቅቶች አሉ። ስንቱ እህት ነው ለወንድሙ ከእናትነት በላይ ዋጋ ሲከፍል የሚኖረው ?ዛሬ ግን ያቺ ድንበር ተለየች ። አቡሻ ነብር ሊበላኝ ነው ብሎ ግቢውን ሲቀውጠው ሁለት ወዳጆቹ ደንግጠው ተነስተው ነበር። እህታችንም እናታችንም የአቡሻን አሰቃቂ ጩኸት ሰምተው ባንነዋል ። ልዩነቱ የመጣው የሳሎኑን በር ከፍቶ አቡሻን ለማዳን በሚደረገው ተጋድሎ ላይ ነበር ። እህቴ ወንድሟን ለመታደግ ከድርጊት ይልቅ ሳሎን ተቀምጣ ፀሎት ማድረጉን መርጣለች ። እናቴ ግን የሳሎኑን በር በዛ አስፈሪ ለሊት ከፍታ አቡሻ ክፍል በር ላይ ተገኘች ።
አቡሻ አየሁት ብሎ የሚጮኸው ነብር ልጇን ከሚነካው ይልቅ እሷን አጋድሞ እንደ ፍየል ቢቆረጣጥማት ትመርታጣለች ። የእናትነት ተፈጥሮአዊ ፍቅር እና ስስቱ በእንደዚህ ያለ ክፉ ቀናት ወለል ብሎ ይገለፃል ። እኔ አቡሻ ይተርፍ ዘንድ መልካም ምኞቴን ከማሳደር የዘለለ ለፀሎቱም ለድርጊቱም ተሳንፌ ቆሜ ትዕይንቱን እከታተላለሁ። “የታል ነብር ?” “ይኸው እማ ዬ ወይኔ ተበልቼልሽ ነበር “ አቡሽ ፊት ላይ የሚታየው ድንጋጤ ለተመልካች ሁሉ ሳይቀር ስጋትን ያጋባል ። እናቴ ልጄ አበደ መሰለኝ ብላ እንባዎቿ ተንዠቀዠቁ ። እኔ ይሄ ሀሽሻም ወንድሜ ምናምኑን አጫጭሶ መጥቶ አልጋ ልብሱ ላይ የነበረው የነብር ምስል እውነተኛው ነብር መስሎት እንደሚጮህ ግን ቀድሞውኑ ጠርጥሬ ነበር 🙂

@wegoch
@wegoch
@paappii

#mikael aschenaki
🏞 ከእንግዲህ #ስጦታ ምን እሰጣለው ብለው መጨናነቅ የለም። ለሚወዱት ሰው በመረጡት 𝕤𝕚𝕫𝕖 #ቆዳ_ላይ እንዲሁም #ሸራ(𝕔𝕒𝕟𝕧𝕒𝕤) ላይ ሥዕል አስለው ማቅረብ ብቻ ነው።


🟢#ለምርቃት 👨‍🎓

🔵#ለሰርግ 👰🤵

🔴#ለፍቅረኛዎ 👩‍❤️‍👨

እና ለወዳጅ ዘመዶ👨‍👩‍👧‍👦 በተመጣጣኝ 💵ዋጋ አስለው ያበርክቱ ።


🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
ለበለጠ መረጃ
📱Inbox @gebriel_19
📱0984740577

@𝕤𝕖𝕚𝕝𝕠𝕔𝕙
@𝕤𝕖𝕚𝕝𝕠𝕔𝕙
ርዕስ አልባ ( አንዳንድ ድርሰቶች ከህይወታችን ርዕስ አልባነትን ይወርሳሉ)
ለሁሉም ሰው እንደምመስለው የዋህ ፤ አፍቃሪ እና ሚስኪን ብቻ አልነበርኩም ።
እንደማንኛዋም ሰው ትንሽ እብሪት እና ድድብና አላጣሁም ። እርሱ ግን ካለ ምክንያት ብቻ ሳይሆን ከነ እንከኔ ይወደኝ ነበር ፤ ባይወደኝ ቀንድ ያጠረኝ
አጋንንት መሆኔን እያወቀ ክንፍ ማቆጥቆጥ እንደቀራት መልዓክ አያየኝም ነበር ፤ ባይወደኝ የትም እንደምረግጥ የትም እንደምጋደም እያወቀ እንኳን ገላዬን ለማቀፍ አይቸኩልም ነበር ፤ ባይወደኝ ስመረቅን የማወራለትን ያን ሁሉ ዝባዝንኬ አፉን ከፍቶ አይን አይኔን እያዬ አይሰማኝም ነበር ። አሁን ከጊዜያት በኋላ ለምን እንደተራራቅን አስባለሁ ። ከእርሱ ያራቀኝ ሃጢያቴ
ነው። የዋህ አማኝነቱ ፤ በጭንቅላቱ ዙሪያ ቀለበት ሰርቶ አናቱ ላይ የሚውል
ቅዱስነቱ ፊት ለፊት መቆም ያቃተው ስራዬ ከእርሱ እንዳራቀኝ አውቃለሁ ።
ተቃቅፈን ባደርንባቸው ቀናት ጀርባውን ስዳብስ ስለምነካቸው ጤፍ መሰል
ትንንሽ ደቃቅ ሽፍታዎች በጠራራ ሌሊት ከእንቅልፌ ነቅቼ አስባለሁ ፤ ለስላሳ
ጀርባው ላይ የፈሰሱ ደቃቃ ጉጠቶች ይናፍቁኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ፤
ግን ከአመታት በኋላ የጣቴ ጫፎች ሊዳስሱት ሲጓጉ ተሰማኝ። የተለየሁት በየቀኑ " የት ነሽ? " ይለኝ ስለነበር ፤ በየምሽቱ " ሰፈርሽ መጥቻለሁ ናፍቀሽኝ ነው አይቼሽ ልመለስ " ስለሚለኝ ነው ብል የሚያምነኝ እንደሌለ አውቃለሁ ። ግን በሰጠኝ ክብር ልክ ክብር የጠላብኝ ስለነበርኩ ለ "የት ነሽ? " ጥያቄው " ምን አገባህ " ለ " ከቤት ወጥተሽ ልይሽ" ልመናው " እንዴት ብትንቀኝ ነው በዚ ሰአት" መልሴ ሆነ ። አሁን ከረፈደ ታዲያ ምን ገባኝ? የፍቅር አንደኛ ደረጃ ጠላት እብሪት መሆኑ .......ሊገፋኝ ሲገባ ስላቀፈኝ ሊንቀኝ ሲገባ ስላከበረኝ እብሪቴ ቅጥ አጣ ። በሚሰጠኝ ፍቅር ልክ " የግል ንብረቱ አደረገኝ እንዴ?" የሚል እልህ ውስጥ ገብቼ ያከበረው ገላዬን ለገዛ ጓደኛው አሳልፌ ሰጠሁ። በማንአብኝነት 'በኩራት' ያደረኩት ነገር
የኋላ የኋላ በሃፍረት እና በፀፀት የሚያሸማቅቀኝ የሚሆን አልመሰለኝም ነበር ። ባደረኩት አፍሬ ለአመታት ከእርሱ ጠፋሁ ። ከብዙ ጊዜ በኋላ ያገኘሁት ከአንዱ ጋር አድሬ ከቤቱ ወጥቼ ወደ ሰፈሬ ስሄድ የያዝኩት ባጃጅ ውስጥ ነበር ። ሰላም ከተባባልን በኋላ ብዙም ሳይሄድ ደርሻለሁ ብሎ ከባጃጁ ወረደ ። እርሱ ከሄደ በኋላ እኩይ ስራዬን እና ዱርዬነቴን እግዜር ሊያስታውሰኝ ሲጥር በጧት ከእንቅልፉ ቀስቅሶ የማስቆመው ባጃጅ ውስጥ እንዳስቀመጠው አሰበኩ። የሆነ አንድ ቀን ተደዋውለን ተገናኘን። የምር ናፍቆኝ ነበር። ራቁቱን አቅፌው ጀርባው ላይ ያሉ እነዛን ነጠብጣቦችን ስዳስስ ሃዘንና ፀፀት ተባብረው በልቤ ሲያርፉ ተሰማኝ ። እንባ ስራዬን ባያጥብልኝም ማልቀስ ግን አምሮኝ ፤ አልቅሼም ነበር ቢሆንም በእንባዬ መሃል ልጠይቀው የሚገባኝን ይቅርታ አልጠየኩትም ፤ ለምን ይሄን ያህል እንደሚራራልኝ አልጠየኩትም ። ለምን በመልካምነቱ ሊቀጣኝ እንደሚያሰቃየኝ ፤ ለምን ሁሌ በፀጥታ እንደሚያቅፈኝ አልጠየቅኩትም ። በእንዲህ ያለው ጧት ድንገት ትዝ ሲለኝ ተማፅኖው ልብ የሚበላ Brett
Youngን እየሰማሁ የምጠይቀው ይቅርታ ውስጥ ያለ ምህረት ሰላም
እንደሚሰጠኝ አስባለሁ ።
" If you made up your mind, then make it
But make this fast
If you ever loved me
Have mercy "
ግን የቀደመ የአልፍላነት ድፍረቴ ዛሬ ይቅርታ ለመጠየቅ እንኳን የሚያስችል
እንጥፍጣፊ አቅም ስላልተወልኝ፤ በናፈቀኝ ቁጥር በዘፋኙ አሳዛኝ ድምፅ ውስጥ የራሴን ተማፅኖ ንፋስ ሽው የሚልበትን ልቤን ደግፌ አዳምጣለሁ ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#በኤልሳ ሙሉጌታ
#ቀበሮ_ገዳይ
( በእውቀቱ ስዩም)
.
ድሮ ልጅ እያለን ደብረማርቆስ ውስጥ ቀበሮ ገዳይ የሚባል የመቶ ሜትር ሩዋጭ ነበር፤እናቱ ያወጣችለትን ስም የሚያውቅ የለም፤ ከለታት አንድ ቀን ፤ቀበሮ በሩጫ አባርሮ ጅራቱን ይዞ በርግጫ ደቅድቆ ገድሉዋል እየተባለ ይወራለት ነበር፤ ደብረማርቆስ ስቴድየም ውስጥ ውድድር ላይ የሚያደርገው ነገር ትዝ ይለኛል፤ ገና ሩጫው ሊጀመር ሲል ከጎረቤት አውራጃ ከመጡ ተወዳዳሪዎች ተነጥሎ ወደ ደጋፊዎቹ ዞሮ እጁን ያውለበልባል! ረጅም ስለነበረ የምስራቅ ጎጃምን ሰማይ በፎጣ የሚወለውል ነው እሚመስል! ከዚያ ፤በአክሮባት ወደ ሁዋላ ይገለባበጣል ! ያባ ታምሩ ወፍጮ መዘውር ራሱ እንደዛ አይገላበጥም፤ ይቀጥልና ወደ ሌሎች ተወዳዳሪዎች ዞሮ ይገረምማቸዋል፤ “ አሁን ቢቸግር እንጂ እናንተን ከመሰለ ውርጋጦች ጋር መሽቀዳደም ነበረብኝ “ የሚል ይመስላል፤
ልክ ሩጫ ሲጀመር ቀድሞ ይወጣና ይፈተለካል፤ በጣም ከመፍጠኑ የተነሳ ፎቶግራፍ ለማንሳት እንኩዋን አይመችም! ሁለት ካሜራማኖች ከጎ ከጎኑ ተከትለን ፎቶ እናነሳለን ብለው በልብ ድካም ሞተዋል ባጭሩ፤ ልጁ ቀበሮ ገዳይ ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኛ ገዳይም ነበር! ግን ችግሩ ምን መሰላችሁ? ቀበሮ ገዳይ ሩጫውን ለማጠናቀቀ አስር ሜትር ሲቀረው አቁዋርጦ ይወጣና ተመልካቹን ከሩዋጮች እሚለየውን የሽቦው አጥር ተደግፎ ያስመልሳል! እና አሁን ሳየው በህይወታችን ውስጥ ያሉት ብዙ ነገሮች እንደ ቀበሮ ገዳይ እንጂ እንደ ሃይሌ አይደሉም ፤ ነገሮችን ስንጀምርና ያለን ጉልበት እስከመጨረሻው አይቆየንም ፤ ኮረና የጀመረ ሰሞን፤ የዳንቴል ማስክ ሰርቼ በነፍስ ወከፍ ለህዝብ ካላዳረስኩ ብላ ስትገለገል የነበረች ሴትዮ፤ ዛሬ ዶክተር ሊድያ ገፅ ስር “ ይሄ ነገር ዛሬም አለ እንዴ ?’ የሚል ኮመንት ታስቀምጣለች፤ ጦርነትም እንዲሁ ነው፤ ውጊያ የተጀመረ ሰሞን የወኔ ችግር አይኖርም ባንድ ቀን ውጊያ ሁለት የጠላት ወታደር ገድለህ ፤ አምስት ማርከህ ሶስቱን ደግሞ እንዳይለመዳችሁ ብለህ ራሳቸውን ዳብሰህ ታሰናብታለህ፤ ጦርነቱ ካመት በላይ የሚቀጥል ከሆነ ግን ሌላ ጣጣ ይመጣል ፤ ወኔ በወይኔ ይተካል፤ በጥላሁን ገሰሰ ዘፈን ቀርቶ፤ ቂጥህን ራሱ በሳንጃ ብትወጋ ወደፊት መንቀሳቀስ ታቆማለህ፤ በሳንጃ የተወጋ ቂጥህን እንደ ሃብሃብ ፈንክተህ ጥለህ ፤ የተረፈ ቂጥህን አስከትለህ፤ ወደ ቤትህ መመለስ ነው የምትፈልገው!
የፍቅርም ነገር እንደዚያ ይመስለኛል፤ ሲጀምር በነበረው ጉልበት የሚቀጥል ፍቅር ያለን ሰዎች የታደልን ነን ንዋይ ደበበ አፍላ ሳለ፤ ባንድ ብርጌድ ማሲንቆ መቺ ታጅቦ የሚዘፍነው ዘፈን ነበር” ያላንቺ እኖራለሁ እኔ መች ወጣኝ’ ይላል፤ መላው የሰው ዘር ለኦክስጂን ሲጠቀምበት የኖረውን አገላለፅ ነው ንዋይ ለፍቅረኛው የሰጠው፤
ንዋይ በሌላ ዘፈን
“አትጥፊ በብዙ ከልቤ እንዳትወጭ
እንደዛም ስላልኩሽ ቶሎ ቶሎ አትምጭ”
ብሎ አረፈ፤
የመጀመርያው አገላለፅ ፍቅር የተጀመረ ሰሞን የነበረውን ስሜት ሲያንፀባርቅ ፤ ሁለተኛው ግጥም የሰነበተ ፍቅርን ይወክላል
.
.
@wegoch
@wegoch
★★ የባል ገበያ ★★
(ክፍል አምስት)
ሜሪ ፈለቀ

እንደሰፈሬ ልጆች ሲሊፐሬ ሲበጠስ በሚስማር አስይዤ ተጫምቼ ፣ ቄስ ትምህርት ቤት እስክገባ ፓንት ሳልታጠቅ፣ በባለኮፍያው ሚስማር ተበስቶ በሚስማሩ የተከደነ የፀጉር ቅባት ተቀብቼ፣ የተሰጣ የሽሮ ስጥ ሰርቄ ትምህርት ቤት እየቆረጠምኩ፣ የአባዬ ካልሲ አውራ ጣቱጋ ሲቀደድ ሰፍቼለት፣ እታባ ጎመን በጎድን የቀቀለች ቀን አመትበዓል እየመሰለኝ…… ……… ያደግኩኝ ነጭ የድሃ ልጅ ነኝ። ……… ለሰወች የምንሰጠው በፍቅር የታጨቀ ልብ እንጂ በገንዘብ የታጨቀ ኪስ አልነበረንም። ……
አስረኛ ክፍል ከምማርበት ከትምህርት ጉብዝናዬ እኩል በረብሻ ከምታወቅበት የመንግስት ትምህርት ቤቴ ፊት ለፊት …… የመውደድ ቤተሰቦች ለእይታ ርቆ አንጋጠው ወደ ላይ የሚያዩት ቤታቸውን ገዝተው የገቡ ሰሞን ከትምህርት ቤት ስወጣ አንደኛው ፎቅ በረንዳቸው ላይ ወንበር ላይ ተቀምጦ ተማሪ እየተንጫጫ ወደቤቱ ሲሄድ ያያል። አየሁት። በሚቀጥሉት ቀናት …… አየዋለሁ። ለጓደኞቼ አሳያቸዋለሁ።

…… ከሶስት ጓደኞቼ ጋር በሽቅድድም ‘ወጣ‘ ‘ያውና‘ ‘ገባልሽ‘ እያሉኝ እናየዋለን። …… እንደሚያየን እናውቃለን። ስንወጣ ካጣነው እንጠብቀዋለን።…… በአይን ፍቅር የተያዝኩት እኔ መሆኔን አምኜ ስለተናገርኩ እንጂ ሳያውቁት ሁሉም ካላዩት ከኔ የባሰ ይከፋቸዋል። …… ለሁለት ወራት አብረውኝ ጠብቀው እያዩት በአይን ፍቅር ወድቀዋል። …… ተቧድነን እንደወደድነው የማውቀው ቆይቶ በእርሱ ምክኒያት ሲያኮርፉኝ ነበር።

ለአራት ቀናት ድራሹ ጠፋ!! …… ብንጠብቀው ብቅ አልል አለ። …… እየከፋን ወደየቤታችን ገባን። ጠብቄ ላየው ወስኜ ተመልሼ መጣሁ። …… በሩጋ ከሴት ጋር እየሳቀ ሲያወራ ደረስኩኝ። …… እያመነታሁ ላልፋቸው ስቀርብ ጓደኛዬ መሆኗን አየሁ።…… እንደሷ ላስቀው መሞከር የማይረባ ፉክክር መሆኑ ወዲያው ገባኝ።ቅናት በየደምስሬ ሲሯሯጥ ሰውነቴ አብጦ የሚፈነዳ መሰለኝ።…… ምንም ቢፈጠር በዛ ቅፅበት ከሚሰማኝ መንደድና መበሳጨት እንደማይብስ አወቅኩ። ……

…… በመሃከላቸው ባለው ጠባብ ርቀት መሃል ራሴን አገኘሁት።…… ለማሰቢያ የሚሆነው ሽራፊ ሰከንድ ሳላባክን ራሴን እንኳን ባስገረመኝ ድፍረት የማርን ጥፍጥና የሚሽር ከንፈሩን ጎረስኩት። …… የቀኝ እጁ በወገቤ ዙሪያ አልፎ ወደራሱ ሲያጣብቀኝ… የጓደኛዬ ኮቴ እየራቀ ሲሰማኝ… መሳሳማችንን ስንገታ ማፈሬ ሲመጣብኝ…… ስሙንና የዩንቨርስቲ አንደኛ ዓመት አርክቴክቸር ተማሪ መሆኑን ሲነግረኝ……በዛ ሰሞን የጠፋው ፈተና ስለነበር ዶርም እያደረ መሆኑን ሲያስረዳኝ…… እኔን ለማዋራት ቀን ሲጠብቅ እንደገላገልኩት እየነገረኝ ወደ ቤቴ ሲሸኘኝ…… መለያየት አቅቶን እየተሰነባበትን ስንሳሳም ደሞ ስንሰነባበት ደሞ ስንሳሳም…… የፍቅር ታሪኬ ከመውደድ ጋር እንደተገመደ እርግጠኛ ሆንኩ።…………

ለምናልባቱ ለራሴ ያስቀረሁት አንድም ማንነት ሳይቀረኝ በመላ አካሌና በመላ ነፍሴ በፍቅር ወደቅኩለት። …… የየዕለት የአይኔ ሱስ፣ የልቤ ጌታ፣ የደስታ ስካሬ፣ የህልውናዬ ትርጉም…… በእያንዳንዱ የወደፊት እርምጃዬ መውደድ እየገዘፈ መዓት አክሎ ውስጤ ተቆለለ። …… ‘እኔ‘ ያለእርሱ ጠፋሁ። …… ከአመት በኋላ የራሱ የሆነን ነገር እንደሰጠሁት እየተሰማኝ ለማንም ያልተከፈቱ ጭኖቼን ከፍቼ የሰይጣን ይሁን የእግዜር ማረጋገጥ ወደማልችለው ሽቅርቅር ግዛት አብሬው ተሳፈርኩ።………

በብዙ መጎራበጦች ውስጥ እኔ እንደምበልጥበት አሳምኖኛል። …… ቤተሰቦቹ ክብራቸውን የማልመጥን አይነት ሴት መሆኔን ሲነግሩት ክብሩ እኔ መሆኔን ነግሯቸው ተጎራብጧል። …… አባቴ ለብዙ ነገር የሚጠብቃት ልጁን ስላባለገበት ጠብቆ ሲያንቀው ፣ እግሩ ስር ወድቆ በእንባ ህይወቱ እኔ እንደሆንኩ አሳምኖ እስከስኬቴ ጫፍ እንደሚገፋኝ ቃል ገብቶለታል። …… ደሳሳ ቤታችን ቤቱ ሆነ። …… አባዬና እታባ ከእኔ ለይተው የማያዩት ልጃቸው ሆነ።……

መውደድ
ቁም ነገር አጫውቶኝ የእውቀቱ አድማስ እያስደመመኝ አፌን ከፍቼ የምሰማው፣
ነገሮችን ባየ ቅፅበት ቀልድ ፈጥሮ የጉንጮቼ ጡንቻዎች እስኪዝሉ የሚያስቀኝ፣
ሲጠነቀቅልኝና ሲንከባከበኝ መላዕክት እቅፍ ውስጥ ሆኜ የምቀብጥ እንዲመስለኝ የሚያደርገኝ፣
ፍቅር ሲሰጠኝ ነፍሴን የፍቅር እንጉርጉሮ የሚያዜማት፣
ሲስመኝ ነፍሴን ብሰጠው እስካልሳሳ ድረስ የምወደው አባቴን የሚያስረሳኝ፣
እጆቹ ከእንብርቴ በታች ሲያልፉ እግዜርንም ሰይጣንንም ምድርንም ሰማይንም አስረስቶ ትንፋሼን የሚያቆማት፣
የሰው ልጅ በዛ መጠን እንዴት ፍፁም መሆን እንደሚችል በማይታመን ሁኔታ መውደድ እንደዛ ሆኖ እኔም ዩንቨርስቲ ገባሁ እሱም ተመረቀ። …… 5 እንከን አልባ ዓመታት አለፉን።


ተጋብተን ልንኖር እቅድ እያወጣን ሳለ አባዬ ታመመ። …… ከዚህ በኋላ የሆነው ሁሉ ድርሰቱን ጨርሶ ለመገላገል መጨረሻውን በአጫጭር አረፍተነገሮች እንደሚነዳ ብሽቅ ደራሲ በጣም ፈጣን ነበር።…… አባዬ ከሀገር ውጪ ወጥቶ መታከም ነበረበት። …… የሰፈር ሰው፣ ዘመድ አዝማድ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት… … የሚችለውን ያህል ብር አዋጣ። እቁብም እድርም ተባለ። …… የሚያስፈልገው ገንዘብ መጠን ንቅንቅ አልል አለ። ……
መውደድ ቤተሰቦቹም ዘመዶቹንም ቢያንስ እንዲያበድሩት ጠይቋቸው ነበር። …… ከኔ ጋር በነበረው ግንኙነት ቀድሞውኑም ደስተኞች ስላልነበሩ አላገጡበት።…… አባዬ ንጭንጩ እየበዛ መጣ…… እታባም በባሏ ሰቀቀን ታመመች። ገና ድክ ድክ የሚለው ታናሽ ወንድሜ ሰውነቱ ከሳ። ከትምህርት ቤት ይልቅ እቤት ማሳለፍ ጀመርኩ። … … ከስራ መልስ እቤት መጥቶ አባዬን ሳያየው የማይሄድ የነበረው መውደድ ለቀናት ሳይመጣ ቀረ። …… ደውሎ ስለአባዬ ከጠየቀኝ በኋላ ወዲያው ስልኩን ይዘጋዋል። …… ግራ ቢያጋባኝም እቤት ከነበረብኝ ጫና ጋር ምንም ማሰብ አልቻልኩም።

አንድም ናፍቆት ውስጤን ሲቆላው ሁለትም ሸክሜን ላጋራው ስራ ቦታው ሄድኩ። …… እሱ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ለኔ ጠረጴዛው ላይ ተንሰራፍቶ የተዘፈዘፈ ትልቅ ቂጧ ጎልቶ የሚታየኝ ሴት ከፊትለፊቱ በእግሮቹ መሃል ጠረጴዛው ላይ ተቀምጣ የእድሜዋ ያልሆነ ልዘት ትለዛለች።…… ግራ ተጋብቼ ቆሜ ሳያቸው አየኝ። ዘሎ ከወንበሩ ተነሳ። …… ፊቷን ሳየው አስታወስኳት።

ከአመት በፊት ‘አንቺን የሚያክል ቂጥ ያላት የአባቴ ጀለስ ከውጪ መጥታ እቤታችን አርፋለች።‘ ብሎ ያሳየኝ ሴትዮ ናት። ለመውደድ ከሀገር እንዲወጣ በርሷ በኩል ፕሮሰስ ተጀምሮለት ነበር። …… የእሷ የ‘ማነች?‘ አስተያየት ካየሁት የጠለቀ ግንኙነት እንዳላቸው ነገረኝ። …… እጁን ይዛ በቆመበት አስቀረችው። አልታገላትም። …… ጥፋት ሲያጠፋ እንደሚያየኝ ባለበት ቆሞ በልምምጥ ያየኛል። ማመን አልፈለግኩም።

" ጌትዬ ምንድነው? ማናት? ምን እያደረግክ ነው?" አልኩት ምንም ቢለኝ ከአይኔም ከስሜቴም በላይ የእርሱን ቃል አምነዋለሁና እንዲያስተባብልልኝ ጠበቅኩ።…… ዝም አለኝ።

"ጌትዬ ንረገኝ? ያሰብሽው ልክ አይደለም በለኝ?" ከየት መጣ ያላልኩት እንባዬ ከቃላቱ ጋር ፈሰሰ። አይኖቼን ሽሽት ፊቱን አዙሮ ዝም አለኝ።……
……………
…………
👉🏽አሁንም አልጨረስንም👈🏽

@wegoch
@wegoch
@paappii
★★ የባል ገበያ ★★
(ክፍል ስድስት)
ሜሪ ፈለቀ

"ጌትዬ ንረገኝ? ያሰብሽው ልክ አይደለም በለኝ?" ከየት መጣ ያላልኩት እንባዬ ከቃላቱ ጋር ፈሰሰ። አይኖቼን ሽሽት ፊቱን አዙሮ ዝም አለኝ።……

"ኦ…ህ ማ…ይ ዲ…ር ጋ…ድ! አዲሱ(የመውደድ አባት ነው) ያወራልኝ ልጅ እንዳትሆን?" መውደድን ነው የምትጠይቀው ቀጠል አድርጋ "አባቷ ሊሞት ነገር ነው ካልተሳሳትኩ?" እሱን እየጠየቀችው ቆሻሻ እንዳየ ሰው በመፀየፍ ስታየኝ ባንቃት ደስ ባለኝ። …… ክንፏን ያጣች ቢራቢሮ ሆኛለሁ። የኔ መውደድ እንዲህ ስንጓጠጥ ሰምቶ ዝም አይልም። ……

ማንም ቢሆን ዘሎ ይከመርበት ነበር። …… ትቻቸው ስወጣ አልተከተለኝም። የሴትየዋ ዝገት ዝገት የሚል ሳቅ ተከትሎኛል። …… የማውቀው ሁሉ ነገር ጠፋብኝ…… የማምነው ነገር ሁሉ ተንኮታኮተ… የማስበው ነገር አጣሁ…… አላለቀስኩም። ግራ ገብቶኛል። ……

እቤት ስደርስ "እመቤቴ ሁሉንም ነገር በቅርቡ አስረዳሻለሁ። በነፍሴ ልክ አፈቅርሻለሁ።" የሚል መልዕክት ደረሰኝ ምንም ማመዛዘን አልቻልኩም። መናደድም አቃተኝ። …… ጠበቅኩት። …… እራሴን ያለእርሱ ማሰብ በፍፁም አልቻልኩም። …… መጥቶ የሆነ ምክኒያት እንዲነግረኝ ጠበቅኩት። እንዳምነው…… ምንም እንዳልተፈጠረ ረስተን አብሬው ልሆን…… የሴትየዋን ለዛ ያጣ ቅብጠት መርሳት አቃተኝ። ……

ልጆቿ ከሚያካክሉ ወንዶች ጋር የመውጣት ልክፍት እንዳለባት ስለርሷ የነገረኝን አስታወስኩ።
ከኔጋር የሚያብደውን የፍቅር እብደት ከሷ ጋር ሲያብደው ማሰብ ጨርቄን ሊያስጥለኝ ይደርሳል። … መውደድ ትልቅ ቂጥ ይወዳል። … ከኔ ጋር ፍቅር ስንሰራ እንደሚያደርገው ትልቅ ቂጧን ማየት በሚችልበት አቅጣጫ እያደረገ ሲሰራት አስባለሁ። ……

ግዙፍ ሰውነቱ ላይ ስትፈነጭበት እስላታለሁ። እሪሪሪሪሪሪ ማለት ያምረኛል። …… መስታወቱ ፊት እቆማለሁ። ዞሬ ኋላዬን አያለሁ። ከዛች የተረገመች አሮጊት ጋር መቀመጫዬን አወዳድራለሁ::

ቀናት አለፉ። …… አልመጣም። የአባዬን ደህንነት ለማረጋገጥ እንኳን እታባጋ ሆነ የሚደውለው። ……

ብዙም ባልራቀ ቀን ያቺን ሴትዮ ማግባቱን ስሰማ አዞረኝ። …… ከእርሱ ለማረጋገጥ እቤታቸው ስሄድ ጭራሽ ከሴትየዋ ጋር ከሃገር መውጣቱን ነገሩኝ። …… ራሴን ስቼ ወደቅኩ:: ጎመዘዘኝ ..... ቀኑም ማታውም አንድ ሆነብኝ:: ጨለማ !!

የማታ የዞረ ድምሩ እንዳለቀቀው ሰካራም ስደነባበር የአባዬ ነፍስ አባት ለአባዬ መታከሚያ የሚሆን ብር መገኘቱን አበሰሩን። ታክሞ ግን መዳን አልቻለም። ገንዘቡ በጊዜው አልደረሰለትም። …… ከወራት በኋላ እቤቱ ተመልሶ አረፈ። …… እታባ ከአባዬ ሞት በኋላ ባሰባት። …… ቤቷን ማስተዳደር ስላለባት አየታመመች ለመስራት ብትሞክርም ከአቅሟ በላይ ነበር።

ይህቺ አለም የሌላውን ውድቀት መጠቀሚያ የሚያደርጉ ብሽቅ ሰወች የሞሉባት ናት። …… እንደውም አንዳንዱ ሌላው ካልወደቀ ከፍታው ደስ አይለውም። …… ስኬቱን የሚለካው በራሱ ስኬት ሳይሆን በሌላው ውድቀት ነው። …… አባዬን ልጅህን ካልዳርክልኝ እያለ የሚነዘንዘው ታደሰ የሚባል ነጋዴ አጋጣሚውን ተጠቅሞ እቤታችንን ይደግፍ ነበር። …… አብሬሽ ካልተጋደምኩ ብሎ ሲታገለኝ በብርጭቆ እስከፈነከትኩት ቀን ድረስ። … …

ትምህርቴን እንደነገሩ እየተማርኩ።እስከጨርስ ስራ በተጨማሪ መስራት ነበረብኝ። አዲስ ቤት ተከራየን።

የአይኑን ብርሃን በቅርቡ እንዳጣ ሰው በእያንዳንዱ ቀኖቼ ውስጥ አስተካክዬ የማልረግጥ ደንባራ ሆንኩ። …… እየቆየ መውደድን ብቻ ሳይሆን ፍቅርን፣ እምነትን፣ እውነትን አርቄ ቀበርኳቸው። …… የእታባንና የሚያውቁኝን ሰወች ሁሉ "ለአንድ ወንድ ብለሽ ቆመሽ ልትቀሪ ነው" ንዝንዝ በድንዛዜ ባልፈውም ጥሎኝ ለመሄዱ በቂ ምክኒያት ሊሰጠኝ ያላከበረኝን ወንድ በልቤ ዙፋን ላይ እንደሾምኩት ማኖር ከአቅሜ በላይ ከባድ ነበር። ……



በየቀኑ መልስ የሌለው ጥያቄ እጠይቃለሁ። ለምን?
……
……
"የጉድ ሃገር ገንፎ እያደር ይፋጃል!" አሉ… …
ክህደቱ ሳያንሰኝ ‘ላንቺ ስል ነው‘ ይበለኝ? ላንቺ ስል ነው ማለት ምን ማለት ነው? … ለኔ ሲል ነው ፍቅራችንን ገድሎ የቀበረው? ላንቺ ስል ነው የከዳሁሽ፣ ላንቺ ስል ነው የተውኩሽ፣ ላንቺ ስል ነው ልብሽን ያነካከትኩት፣ ላንቺ ስል ነው በሌላ ሴት የቀየርኩሽ… ማለቱ ነው?… …
ጭራሽ ምክንያቱ ለይቅርታ ሚዛን መብቃቱን ለማመዛን እንድሰማው ሲጠይቀኝ ምላሱን እንኳን ድንቅፍ አላለውም። ………
……
…… በሁለቱም ተቃራኒ የስሜት ጠርዝ የሚቸነክረኝ ሰው ነው መውደድ። …… በፍቅርና በጥላቻ፣ በክብርና በውርደት፣ በፈንጠዝያና በመሪሪ ሀዘን፣ በስኬትና በውድቀት፣ በፍሰሃና በህመም…… …… በነዚህ ሁለት ፅንፎች የሚያላጋኝ እሱ ነው። ……
አሁን ላይ ምንምና ስለማንም ባልሰማ፣ ባላይ፣ ባላስብ…… የሆነ ዓለም ጠርዝ ላይ ብቻዬን ብሆን…… ‘እገሌ ምን ይለኛል?‘ ‘እገሌን ምን እለዋለሁ?‘ የማልልበት… … ቦታ ላይ ብገኝ? የሰው ልጅ እንደሰው ሰራሽ ኮምፒውተር ‘undo‘ ጠቋሚ ቢኖረው ምንነበር? …… የምመልሳቸው ብዙ ውድቀቶች ነበሩኝ።…………
ስልኬን አጠፋፍቼ ኡኡታዬን ማዳመጥ ጀመርኩ። ………

ስለ መውደድ ማሰብ በሸሸሁ ልክ ምላሴ ጨው ጨው እስኪለኝ ክህደቱን እንደገና ማሰብ ጀመርኩ።…… አንዳንዴ የምር ግን ምክኒያቱ ምን ነበር? እላለሁ። ……

"ውሻዬ? አባ ይፈልጉሻል።" አለችኝ እታባ ከውጪ እየገባች።

"አባ? አባ? ………ወደውስጥ አይገቡም እንዴ?"
የአባቴ የነፍስ አባት ነበሩ። ወጥቼ እንዲገቡ ብወተውታቸውም አልገባ አሉኝ።

…… እዚህ ቤት ከገባን በኋላ መጥተው አያውቁም። የዛሬ ጉብኝታቸው ገርሞኛል። … ለምን እንደፈለጉኝ ሲነግሩኝ የሆነ ቅዠት እየቃዠሁ መሰለኝ።………

"የዛኔ ለምንድነው ያልነገሩኝ?" ብዬ ጮህኩባቸው

"አትንገራት ብሎኝ ነበር። የሆነውን ሁሉ ያወቅኩት አሁን ነው።" በቆሙበት ትቻቸው ወደውስጥ ገባሁ። ያገኘሁትን ለብሼ ስወጣ ከእታባ ጋር ቆመው እያወሩ ነበር።

"አይደለም። አባዬን ለማዳን ብለህ አይደለም ከዛች ሴትዮ ጋር የሄድከው። እንደዛ ቢሆን ትነግረኝ ነበር።" የሆቴሉን ክፍል በር እንደከፈተልኝ እየደነፋሁ ገባሁ።

"ብነግርሽ እሺ ትዪኝ ነበር? ከአባትሽና ከእኔ ምረጪ ብልሽ ማናችንን ትመርጪ ነበር? አንቺን እዛ አጣብቂኝ ውስጥ መክተት ያመኝ ነበር። አባትሽን ለማዳን እኔን አይሁን እንጂ ምንም ትከፍዪ ነበር።" አለኝ እርግት ብሎ

👉🏽አልጨረስንም ደግሞ👈🏽

@wegoch
@wegoch
@paappii
🏞 ከእንግዲህ #ስጦታ ምን እሰጣለው ብለው መጨናነቅ የለም። ለሚወዱት ሰው በመረጡት 𝕤𝕚𝕫𝕖 #ቆዳ_ላይ እንዲሁም #ሸራ(𝕔𝕒𝕟𝕧𝕒𝕤) ላይ ሥዕል አስለው ማቅረብ ብቻ ነው።


🟢#ለምርቃት 👨‍🎓
🔵#ለሰርግ 👰🤵
🔴#ለፍቅረኛዎ 👩‍❤️‍👨

እና ለወዳጅ ዘመዶ👨‍👩‍👧‍👦 በተመጣጣኝ 💵ዋጋ አስለው ያበርክቱ ።


🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
ለበለጠ መረጃ
📱Inbox @gebriel_19
📱0984740577

@𝕤𝕖𝕚𝕝𝕠𝕔𝕙
@𝕤𝕖𝕚𝕝𝕠𝕔𝕙
★★ የባል ገበያ ★★
(የመጨረሻ ክፍል)
ሜሪ ፈለቀ

"ብነግርሽ እሺ ትዪኝ ነበር? ከአባትሽና ከእኔ ምረጪ ብልሽ ማናችንን ትመርጪ ነበር? አንቺን እዛ አጣብቂኝ ውስጥ መክተት ያመኝ ነበር። አባትሽን ለማዳን እኔን አይሁን እንጂ ምንም ትከፍዪ ነበር።"

"አላምንህም!! ስትዋሸኝ ነው። አራት አመት ሙሉ… …"

"ይሄን የምንነጋገረው አባትሽ መትረፍ ችለው ቢሆን ኖሮ ትርጉሙ ይቀየር ነበር። ፍቅሬን ከፍዬም ላድናቸው አለመቻሌን ስሰማ ሁሉንም ጥዬ መጥቼ ነበር። …… አንቺ የት ነበርሽ? እ? ከታደሰ ጋር…… ረስተሽኝ ነበር።" የሚያወራው ግራ ገባኝ

"እኔ? እኔ ከታደሰ ጋር? በወራት ውስጥ ፍቅሬን እንኳን ብረሳ ክህደትህ የሰጠኝን ቁስል ድኜ ከሌላ ሰው ያውም ከታደሰ… … ከየት ያመጣኸው ወሬ ነው?"

ሸሚዙን ከፍቶ ደረቱ ላይ ያለ ጠባሳውን አሳየኝ። …… ለቅፅበት ደረቱን ሳይ ሙቀት ተሰማኝ።

"አይንሽን ለማየት ጓጉቼ እቤት ስደርስ እታባን አገኘኋት። …… ስታየኝ ፊቷ ላይ የነበረው ጥላቻ እንደዛ ትንሰፈሰፍልኝ የነበረችው እታባ አትመስልም። … አልፈረድኩባትም። … ከታደሰ ጋር ልትጋቢ መሆንሽን እና እንዳልበጠብጥሽ ነገረችኝ። …… ተስፋ ሳልቆርጥ ላገኝሽ ሞከርኩ። … ሁሌም ከታደሰ ጋር ነበርሽ። ከቁርስ እስከ እራት……"

(አየሁሽ ያለኝ ቦታ ሁሉ ነበርኩ። ነገር ግን እሱ እንዳሰበው ከታደሰ ጋር ፍቅር ጀምሬ አልነበረም።)

"ታደሰ መምጣቴን ሰምቶ ነበር ላገኝሽ እንዳልሞክር አስጠነቀቀኝ። … እንደማገኝሽ ነገርኩት። ባገኝሽ ሀሳብሽን አስቀይርሻለሁ ብዬ እርግጠኛ ነበርኩ:: ይሄንን እርሱ የሰጠኝ ጠባሳ ነው:: ( የደረቱን ጠባሳ በእጁ እያሳየኝ) የሆነ እለት ማታ እራት አብረሽው በልተሽ ሸኝቶሽ ሲመለስ እኔ ሰፈር ስጠብቅሽ ተገናኘን:: .... ታውቂያለሽ የማይረባ ነው:: በሰፈር ጎረምሳ ሊያስገድለኝ ነበር:: ከሆስፒታል ስወጣ ቤት ቀይራችኋል። እታባ ማንም የቀየራችሁትን ቤት ለእኔ እንዳያሳይ ሰፈር አስጠንቅቃቸዋለች።እመኚኝ ላገኝሽ ያልሞከርኩበት መንገድ አልነበረም። እኔ አንቺን በመፈለግ ስባዝን ሄለን(ቂጣሟ ሚስቱ) የኔን ልጅ ስትወልድ ህይወቷ አለፈ። … ቢያንስ ለልጄ ስል መመለስ ነበረብኝ። ተመለስኩ።………"

" ምኑም እውነት አይመስልም። …… ሰበብህ ነው። ያገኘሃት ጊዜ ይሄን ሁሉ ለእታባ ልትነግራት ትችል ነበር። ልታገኘኝ የምትችልበት አንድ መንገድ አታጣም ነበር። …" ያለው ሁሉ እውነት ባይሆን ነው ደስ የሚለኝ ……

"ሞክሬ ነበር። …… በሩን ይዛ ቆማ ነው እንድወጣላት የጮኸችብኝ። ……አስጠልቻት ነበር።"

ከዚህ በኋላ ያለውን በትክክል አልሰማሁትም። የሸሚዙን ቁልፍ ከፍቶ ያጋለጠውን ደረቱን ፈዝዤ አየዋለሁ። …… መንካት ያምረኛል። ……

አብሮት የሚሰራ ነጭ ሰውዬ ሳይቱ ላይ ያለውን ፎቶ እያሳየው ቆንጆ መሆኔን እንዲያረጋግጥለት የጠየቀው ጊዜ እንዳገኘኝ የነገረኝን ሰምቼዋለሁ። ……

እጄን ሲይዘኝ በርግጌ መነጨቅኩት። ትቼው ስከንፍ እቤት ሄድኩኝ።ማሰብ ስላቆምኩኝ እንጂ የምጠይቀው ጥያቄ ነበረኝ። …… እታባ ስነግራት በእንባና በፀፀት ልትፈነዳ ደረሰች። …… ምን እንደተሰማኝ አላውቅም።

ማልቀስም መሳቅም አልቻልኩም። ዝም ብቻ… …… እገባለሁ ፣ እወጣለሁ፣ እተኛለሁ ፣ እነሳለሁ፣ እቀመጣለሁ……… የማስበው ምን እንደሆነ አላውቅም እኮ ግን ወጥሬ እያሰብኩ ነው። ያወራውን ሁሉ መርሳት ፈልጋለሁ። …… የታችኛው ቁልፍ ብቻ ቀርቶ የከፈተውን ሸሚዙን አስባለሁ። ……… ባሰብኩት ቅፅበት የቀረውን ቁልፍ በጥሼ ራቁቱን ማየት ያምረኛል።…… ወደ ውጪ ስወጣ መሽቷል። …… ለሊቱ ቶሎ እንዲነጋ ይናፍቀኛል። ነገ አዲስ ነገር ይዞ መምጣቱን አላውቅም። …… ተኛሁ። ማንቀላፋት አቃተኝ። ……

ጀርባዬ እስኪቀላ ተገላበጥኩ።… … አንዱን ስይዝ አንዱን ስለቅ እኩለ ለሊት ሆነ። …… መጨረሻ ላይ ማሰብ የቻልኩት መውደድ እቅፍ ውስጥ መገኘት መፈለጌን ብቻ ሆነ። …… በዛ ለሊት የሆቴሉ በር ላይ መገኘቴን ማመን የቻለ አይመስልም። …… ሸሚዙን ቀይሮታል። የሆቴሉን ጋውን ለብሶ ነው የከፈተልኝ። ……

(አንባቢ ሆይ ከዚህ በኃላ ያለው ይቅርብህ🤣🤣)

_____አሁን ጨረስን_________

@wegoch
@wegoch
@paappii
2024/09/24 11:17:56
Back to Top
HTML Embed Code: