Telegram Web Link
"ተኣምር አልፈልግም !"
.
በህይወት መኖር ራሱ ድንቅና ተአምር ነውና እንደ አልዓዛር ሞቶ መነሳት አልፈልግም። ሞትም ሆነ ሕይወት እንደማንም እንደምንም አንዴ ይበቃኛል ።
አይ ድጋሚ በቃኝ ጌታዬ አሁን ኖሬ መጣሁ። ጨጓራዬ ተልጦ ሁለት ወር ማቅቄ መልሶ ፀጉር ሲያቆጠቁጥ" አጀብ አጀብ አጀብ " እያልኩ ማጨብጨብ አልፈልግም፡፡ ቀድሞውኑ የጨጓራዬ ስራ የሚደንቀኝ ነኝ ፡፡ ኩላሊቴስ ፈሳሽ የማጣራቱ ነገር ግርም ድንቅ ይለኛል። ደክሞት እስኪያደክመኝ አልጠብቅም ። እንዲሁ ለታምራቱ አሳቻ ሸለቆ ውስጥ ቀርቅሮ በእጁ የሚያወጣው ነገር አለ።
በትሬ ወደ እባብ እንዲቀየርልኝ በፍፁም አልፈልግም (እራሱ የፈርኦንን ልብ አደንድኖ ሲያበቃ) ። ከሩቅ ተሳልሞ መሞት እንጂ ወደማልገባባት ከተማ ፤ እሺ ብሎ የማይታዘዝ ህዝብ መሪ መሆንም አልፈልግም እንዳውም ። በረቂቅ ውስብስብ ገመዶቹ ሊተነተን የማይቻለው የአንጎላችን አሰራሩ ግሩም ድንቅ መሆኑን … የእጃችን አሻራችን ልዩ ልዩ መሆኑን እንደቀላል አይቼው አላውቅም … ስለዚህ የሰለለች እጅ ፈጥሮልኝ በተአምሩ መተርተር አልሻም ፡፡ ቀድሞውንስ እንደ ሸክላ በእጁ አይደለሁም ? ዓይኔ ብርሃንን ከጨለማ ለይቶ የማየቱ ነገር ብቻ ተአምር ሆኖ ሳለ ከመወለዴ ጀምሮ አይነስውር አድርጎኝ ለክብሩ ሲል ከእለታት አንድ ቀን እንዲያበራልኝ አልፈልግም። ገና ድሮ ተአምር ሳላይ የፀናች እጁን የተዘረጋች ክንዱን አምኛለሁ። እኔ የምፈልገው ዝም እና ዝግ ያለ መደበኛ ህይወት፡፡ ስብራት እና መጠገን የሌለበት ፡፡ እንደማንም እንደምንም … ከእሳት እና ከውሃ ከአንበሳ እና ከድብ … ከፈርኦን እና ከናቡከደነፆር … መሳደድ ፣ ማምለጥ ፣ መትረፍ የሌለበት፡፡ "ምን አለፋው?" እላለሁ ከዚህ ሁሉ በፊት ወድጄ ፈቅጄ አምኜዋለሁ፡፡ በሰላም መድረስ እየተቻለ ፤ ጭራሽ አለመሄድም እያለ 12 ሜትር ተምዘግዝጎ ወደ ገደል ከገባው መኪና ብቸኛ ተራፊ መሆን አልፈልግም ። ማእበሉን አለማስነሳት እየቻለ በውሃ ላይ ለምን ያራምደኛል? አልፈልግም ካልኩ አልፈልግም ወደ ተርሰሴስ ለምን ይሰደኛል? አሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ውሎ ጉበቱን ተንተርሶ ማደር አልፈልግም ... በፈቃደኝነት የሚሄዱ እልፍ ታዛዦች ሞልተውት የለ ? ሁለት አሳ ጠብሰን በአምስት እንጀራ ለአምስት ከበላንኮ አመስጋኝ ነኝ ። አንድ ቀበሌ ህዝብ ካልመገብን አንልም። ቀድሞ እጁን ሰጥቶ የተማረከ ሰው … እጁ ተጠምዝዞ ቂጡ በካልቾ እየተጠለዘ ወደ ተአምር ጎዳና ለምን ይመራል ? ዳሩ ማን ጠይቆት? የህይወትን መንገድ
መቼ ያስመርጥና …የማይመረመረውን ታላቅ ነገር እንዳደረገ አውቃለሁ "የታምራት አምላክ ታምረኛ ፤ ዳንኤል አምላክ ተአምረኛ …" ብዬም ዘምሬአለሁ ፡፡ ያለ ቅጣትና ሽልማት ሰጥ ለጥ ብዬ ስለምኖር የኔ አምላክ ግን ዝም ብሎ ቢተወኝ ደስ ይለኛል ። ሰዎች ሳይጠቋቆሙብኝ ‘’ያቺት ዓይኗ የበራላት … ከማይድን ደዌ የተፈወሰችው … በቀደም ሞታ ተነሳች የተባለችው’’ ሳይባባሉብኝ … በዝምታ በዝግታ በሰላም መኖር አይቻልም ወይ? ያለ ተአምር ማቅ ለብሼ አመድ ነስንሼ ንሰሃ እገባለሁ ኧረ ! በ25 ዓመት ልጅ መውለድ በራሱ ድንቅና ተአምር አይደለም ወይ ? አጥንት ሆዴ ውስጥ እንዴት እንደሚዋደድ ሳላውቅ መውለዴ ተአምር ነውኮ … እንደ ሳራ በ90 አመቴ ወልጄ "እልልል ተአምራቱ አያልቅም" ማለት አልፈልግም ። እንዴ 90 አመት መኖር በራሱ ተአምር ነውኮ። እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ምድር አሸዋ መብዛትስ ምን ያደርግልኛል ? እህህህ ለ38 አመታት በህመም ተቆራምጄ በመጨረሻም አልጋዬን ተሸክሜ
መሄድ አልፈልግም። በቃ አልፈልግም !!! የሠርጌ እለት ውሃ ወደ ወይን ጠጅ እንዲቀየርልኝ በጭራሽ አልፈልግም። ወይን ጠጅ ካለቀባቸው ውሃ ይጠጡ
እንግዶቹ ። በቃ! ውሃ በራሱ ተአምር ነውኮ! ምረጪ ብባል ... ዝም እና ዝግ ያለ መደበኛ ህይወት እንጂ ተአምር
አልፈልግም !

@wegoch
@wegoch
@paappii

#By_Teym_Tsigereda_Gonfa
ችግር ነው የስድስት ዓመት ልጅ መሆን። ሲሚንቶ ላይ ተዘርፍጬ፣ በእርሳስ ቀለም ኒኬል ሰሃን… የሚጣፍጥ ፍርፍር በወተት አወራርዳለሁ። አደይ ባለሙያ ናት። የሰራችው አደለም የነካችው ይጣፍጣል። ችግሩ ምንድነው… አካፋ በሚያክለው ማንኪያ ፍርፍር ዝቄ ሳነሳ፣ የሚበዛው ወደ ሰሃኑ ይወድቃል። የስድስት አመት ልጅ መሆን አንዱ ችግሩ ይሄ ነው። ሌላ ጊዜ እናቴ እያየቺኝ ትስቅና መታ ታጎርሰኝ ነበር፤ እንደሱ አላደረገችም። ሰሞኑን ሳቅ ረስታለች። አባቴ ግን የት ሄደ? መቐለ ነው የኛ ቤት። እንደውም ይሄ የሰማዕታቱ ሃውልት አለ አይደል? ግራና ቀኝ ያሉትን ህንፃዎች እንደ አምና ወደሁዋላ እየተወክ ቁልቁል ስትወርድ፣ የኛ ሰፈር አለ። እና ቤታችን። ከአዲሱ ስታዲየም ብዙ አይርቅም። ባለፈው አባቴ እሽኮኮ አድርጎ ወሰደኝ ወደ ስቴድየሙ። ቁልፍ ከኪሱ አውጥቶ በሩን ከፍተና ገባን…
“በጣም ሰፊ ነው ወንበር ደሞ አለው ብዙ” አልኩ “መስሎህ ነው… ስታድግ ትንሽ ይሆናል… ይበልጥ ትፈልጋለህ…”
አንዳንዴ ትልቅ ሰዎች ምንም ነው ደስ የማይሉት። የሚናገሩት እንዳለ ሚስጥር!
ሰሞኑን የሚያስፈሩና የሚጮሁ ድምፆች አሉ እኛ ሰፈር። ምናቸውም አያስፈራኝ። ብቻ እናቴ ስትፀልይ፣ ስትለማመን ሳይ መፍራት እጀምራለሁ። የሆነ ነገር ልክ
አይደለም ማለት ነው? “ምንድነው የሚጮኸው እማ?”
“አጆኺ… ፈንዲሻ ነው!”
“ስቴድዮሙን በሚያክል ብረምጣድ ነው እንዴ የሚቆሉት?”
“ግሩም ነው… እንዴት አወቅሽ?”
___
አንዳንዴ ደሞ ሰማይ ምድሩን የሚነቀንቅ ጉድ ሰፈራችን ላይ ይወርዳል። ግድግዳ ላይ የተሰቀለው፣ አንድ ቦታ ጥቁር ሽታ ያለበት ትሪያችን እስኪወድቅ ድረስ ቤቱ ይወዛወዛል። በጣም ያስደነግጣል። “እሺ ይሄስ?” እላታለሁ ማማን “ከበሮ ነው… አይዞሽ…” እማ ደሞ ታበዛዋለች… ምነው የፈለገ የስድስት ዓመት ልጅ ብሆን ይሄ ይጠፋኛል? ምነው እነ ትርሓስ አሸንዳ ሲጨፍሩ ከበሮ አላየንም? ምነው
ከጡቶቿና ጥንቅቅ ተደርጎ ከተሰራ ጠጉሯ ሌላ፣ የተናጠና የተናወጠ ነበር?
ቤታችንን ሊያፈርስ የደረሰው ጉድ በጭራሽ ከበሮ አልነበረም። እንዳ ኪዳነምረት በተስክርትያን ያየሁት ዓይነት ትልቅ ከበሮ ከሆነ አላውቅም እንግዲ። ማማና ማማ ትብለፅ ሲያንሾካሽኮ ነበር ትናንት። የሆነ ችግር አለ ማለት። አንሾካሽከው ሁለት ሰዓት እንኳን አልቆየም። ማታ ከምሽቱ ልተኛ ስል አከባቢ፣ አንዳች ድብደባ በራችንን ሊገነጥል ደረሰ። “እንዴት አመሻችሁ” አለ ከውጭ ያለ ድምፅ፣ አንድ ሰው ብቻ አልነበረም…
“መስገኖ… መንኻ?”
“አይዟችሁ… ወታደሮች ነን ክፈቱ!” ባታየኝ ይሻል ነበር። እናቴ ባታየኝ ይሻል ነበር። ችግሩ ዞር አለችና አየችኝ። ዐይኖቿ ካቅም በላይ ከባድ ነበሩ። ተጫኑኝ።
“አጆኺ… እቶም ሰላም አስከባሪ ኢዮም” አለች እናቴ እንደምንም። በሩን እያንገራገረች ስትከፍት፣ በሰደፍ አሏት። እናቴ ወደቀች። ምንም እንዳልተፈጠረ ቤታችንን በርብረው፣ የባባን ፎቶ ፍሬም ሰባብረውና፣ ዕቃውን አተራምሰውና የማማን ወርቆች ይዘው ሄዱ። ይህ ሁሉ ሲሆን ከተጋደምኩበት ስንዝር ፈቅ አላልኩም። ምክንያቱም ከዓለት የሚከብዱ የናቴ ዓይኖች እኔው ላይ ነበሩ

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Yonas Angesom Kidane
"ጫማሽ ሲያምር"
"ከሜክሲኮ አደባባይ በ100 ብር ነውኮ የገዛሁት"
"ሱሪሽ ሲያምር"
"ወይ ስድስት አመቱ ከዛሬ ነገ ለልዋጭ እቀይረዋለሁ እያልኩ"
"ፀጉርሽ ሲያምር"
"ሁለት ሳምንቱ ከተሰራ ተንጨባርሬአለሁ"
"ቀሚስሽ ውብ ነች"
"ከመገናኛ መንገድ ላይ በ150 ብር የተገዛች ነች"
"ምግብሽ ይጣፍጣል ባለሙያ ነሽ"
"አይይ ዘይት አልቆብኝ የይድረስ ይድረስ ነው የሰራሁት ባክሽ"
"ጥዑም ነው ቡናሽ"
"መፍጫዬ ተበላሽቶ ... በትንሽ የቡና ዱቄት ነው ያፈላሁትኮ እንዳውም ቀጥኗል"
"ቲሸርትሽ ውብ ነው"
"ወይኔ ውስጡ ለቄስ እዚጋ ተቀዷልኮ እየተሳቀቅኩ ነው የምለብሰው
አይታይም?"
"ጎበዝ ነሽኮ ስራሽን ጥንቅቅ አድርገሽ የምትሰሪ"
"አርፍጄ እየገባሁ ምን ዋጋ አለኝ ብለሽ ነው"
"ትምህርት ላይ ጥሩ ነሽ የኔ ሰቃይ"
"አላጠናምኮ ብታይ"
"ሸሚዝሽ ያምራል"
"ቁልፉ ተገንጥሎ በመርፌ ቁልፍ ነውኮ ያስያዝኩት"
"የቤትሽ ፅዳት"
"ወይ ተዝረክርኳል እንዳውም"
.
.
.
የኔ ቆንጆ እስቲ ፈገግ ብለሽ "አመሰግናለሁ" ማለትን ብቻ ልመጂ። ዝርዝሩ
አያስፈልግም ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Teym Tsigereda Gonfa
ሴት እና ትዳር (1)
‹‹እርቃን››
ፀሃፊ፡ ቢኮዙሉ ‹‹The Emperor’s Naked”
ትርጉም፡ ሕይወት እምሻው
---------------
የሶስት ወንዶች እና ሁለት ሴት ልጆች እናት ነኝ፡፡ ይህ ማለት፣ ከእንቅልፌ ከምነሳባት ሰከንድ አንስቶ መሽቶ የቤታችን የመጨረሻዋ መብራት እስክትጠፋ ድረስ ቀኑን ሙሉ ስተራመስ ነው የምውለው፡፡ ሌሊቶቼ አጭርና ቶሎ የሚያልቁ ናቸው፡፡ ንጋት ጠላቴ ነው፣ ያልጠገብኩት እንቅልፌን ቀምቶ ለማያባራ የቤት ውስጥ ስራ አሳልፎ ይሰጠኛል፡፡ ቀኖቼ እረፍት አልባ ናቸው፡፡ ቀኖቼ በጩኸት የተሞሉ ናቸው፡፡ ሁሌም አንድ ነገር እንደተሰበረ ነው፡፡ መአት ብርጭቆ እገዛለሁ ግን ሁሉንም አንድ በአንድ ሰብረዋቸው አሁን ሁላችንም በፕላስቲክ ኩባያ ነው የምንጠጣው፡፡
ሁሌም አንዳቸው እንዳለቀሱ ነው፡ ሁሌም አንዳቸው ካንዳቸው እንደተጣሉ ነው፡፡ አንዳቸውም ደብተራቸው የት እንዳለ አያውቁም፡ ወይ ደግሞ ካለሲያቸው ይጠፋባቸዋል፡፡ ወይ ደግሞ ፓንታቸው፡፡ ወይ ሸራ ጫማቸው፡፡ ሁሌም የሆነ ነገር ላይ እንደተንጠለጠሉ ነው፡፡ ‹‹ውረድ…ውረዱ…!›› እያልኩ ከጣራ በላይ ብጮህም እነሱ እቴ! እንደ ሰው በመሬት ላይ ከመሄድ እንደ ጦጣ
ባገኙት ነገር ላይ መንጠላጠልን ይመርጣሉ፡፡ ቲቪው ከተከፈተ- ማለት ቲቪ በሚፈቀድላቸው ሰአት- ድምፁ ከጣራ በላይ ነው፡፡ ግን ማንም በጨዋ ደምብ ቁጭ አያየውም፡፡ ሁሌም ይሄኛውን እንይ…ይሄኛውን አናይም እያሉ ጣቢያ ለመቀየር የኔ ተራ ነው በሚል እንደተናቆሩ ነው፡፡ ጠብ መገላገል፣፡ አንዳቸውን ማባበል፣ አንዳቸውን ማስፈራራት የነጋ ጠባ ስራዬ ነው፡ ሁሌም እህትና ወንድም እኮ ናችሁ…መዋደድ አለባችሁ እያልኩ እመክራለሁ፡፡ ወይ የሆነ ነገር ሸርክቶት የሚደማ እጅ ይዤ ኡፍፍ እያልኩ ፕላስተር አደርጋለሁ፡፡ እስከዛሬ የከፋ ነገር ገጥሞኝ ሃኪም ቤት ሮጬ የሄድኩት ለሁለት ነገር ነው፡፡ አንድ ጊዜ ያንዳቸው እጅ ተሰብሮ፣ አንዴ ደግሞ አንደኛው ሳንቲም ውጦ፡፡ አምስት ልጆች ስላሉኝ የልደት በአል ቶሎ ቶሎ፣ ተከታትሎ ነው የሚመጣው፡፡ እንደገና ሌላ መአት ሻማ፣ እንደገና ሃው ኦልድ አር ዩ ናው እያሉ መዘፈን፣ እንደገና ኬክ መግዛት (የምገዛው ኬክ ሁሌም መጠኑ አንድ አይነት ነው፡፡ አንዱን ካንዱ ያስበለጥኩ እንዳይመስል)፡፡ በዚህ ሁሉ ትርምስ መሃከል አንደኛው ልጄ ሁልጊዜም ጡሩምባውን እንደነፋ ነው፡፡ ትንፋሽ እስኪያጥረው፣ ከመጠን በላይ
ጮህ አድርጎ ነው የሚነፋው፡፡ (ወይ ትኩረት እንድንሰጠው ወይ ደግሞ
ሊያናድደን)፡፡ የሚያወጣው ‹‹ሙዚቃ›› ጭራ እና ቀንድ የሌለው ታምቡር የሚፍቅ ድምፅ ነው፡፡ ያናድደኛል ግን ልጄ ነውና ሳምባው እስኪፈነዳ መንፋት ይችላል፡፡ ምናልባት ከልምምድ ብዛት ችሎታው ሊሻሻል ይችላል፡፡ ለጊዜው ግን የምሰማው ነገር ስሪያ ላይ ያለች ዝሆን የምታወጣው አይነት ነው፡፡
እናት ነኝ፡፡ የእናትነት አለም ይሄ ነው፡፡ ለጤና ጥሩ አይደለም፡፡ ፀጥታ እና የጥሞና ሰአት ካገኘሁ ብዙ ጊዜ ሆኖኛል፡፡ የራሴ ጊዜ እና እረፍት ካገኘሁ አመታት ተቆጥረዋል፡፡ በባዶ እግር የሚሞቅ የባህር ዳርቻ አሸዋ ላይ መቆም የሚሰጠውን ስሜት አላውቀውም፡፡ መዋኛ ገንዳ አጠገብ አለሃሳብ በጀርባ ጋለል ብሎ ‹‹ልጆቼ የት ይሆኑ›› ከሚል ጭንቀት ተላቅቆ ዘና ማለት ምን ምን እንደሚል አላውቀም፡፡
እንደምንም ብዬ ከምሳ ሰአትe በኋላ ለጥቂት ደቂቃ አይኔን የመክደኛ ጊዜ ባገኝ እንኳን ለሳምንት ከእንቅልፌ የምነቃ አይመስለኝም፡፡ አንዳንዴ 17ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ቢሮአችን ማታ አንድ ሰአት ላይ ወጥቼ ለብቻዬ ሊፍት ውስጥ ስገባ ጭንቅላቴን ከቀዝቃዛው የሊፍቱ ግድግዳ ላይ ደገፍ አደርግና፣ ይህቺን አጭር እና ጣፋጭ የፀጥታ ሰአት አጣጥማታለሁ፡፡ መኪናዬ ውስጥ ሬዲዮ ከፍቼ አላውቅም፡፡ ሁሌም የምነዳው በፍፁም ፀጥታ ታጅቤ ነው፡፡ ይሄን ሁሉ ስላችሁ ግን እናት በመሆኔ እንደከፋኝ እና እየተማረርኩ እንደሆነ እንዳታስቡ፡፡
እናት መሆኔን እወደዋለሁ፡፡ ልጆቼን እወዳለሁ፡፡ ቤታችን በፍቅርና በበረከት የተሞላው በእነሱ ምክንያት ነው፡ እናትነት እጣ ፈንታዬ፣ አምላክ የሰጠኝ ፀጋ እና ማእረጌ ነው፡፡ ልጆቼን መንከባከብ እና እድገታቸውን ማየት በምንም የማልቀይረው ደስታዬ ነው፡፡ አንዳንዴ እራት አቀርብላቸውና ዝም ብዬ ቁጭ ብዬ እያየኋቸው በልቤ፣ ‹‹እነዚህ ሁሉ ልጆች የማን ናቸው…ከየትስ መጡ?›› እያልኩ በደስታ እሞላለሁ፡፡
----
ለእናትና አባቴ ብቸኛ ልጅ ነበርኩ፡ቤታችን ትልቅ የድንጋይ ቤት ነበር፡፡ እናት እና አባቴ ቤቱን በፍቅር ሊሞሉት ቢሞክሩም እኔ ግን ብቸኝነት ያጠቃኝ ነበር፡፡ የራሴ ክፍል ነበረኝ፡፡ ገና ከልጅነቴ
ጀምሮ፡፡ በልብስ ወይ ደግሞ በቲቪ ሪሞት ኮንትሮል ከማንም ጋር ተጣልቼ አላውቅም፡፡ የሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ ነበረኝ- ከወንድም ወይ ከእህት በስተቀር፡፡ የወንድም ወይ የእህት ፍላጎት ያንገበግበኝ ነበር፡፡ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ከወንድም እና እህቶቻቸው ጋር ተጠባብቀው ታክሲ ውስጥ ሲገቡ በሃይል እቀና ነበር፡፡ ምሳ እቃ ከፍተው አብረው ሲበሉ፣ እረፍት ላይ አብረው ለመጫወት አንዳቸው አንዳቸውን ሲጠብቁ ሳይ እቀና ነበር፡፡ ምንም
ነገር ቢደርስብኝ ከሁሉም ሰው በፊት ሊያድነኝ እና ሊጠብቀኝ የሚችል፣ በደም
የሚዛመደኝ ሰው ክፉኛ እናፍቅ ነበር፡፡ አስታውሳለሁ፤ አንዴ ትምህርት ቤታችን
በከፊል ሲቃጠል ሁሉም ልጆች ወንድም እና እህታቸውን ፍለጋ ሲሯሯጡ እኔን ብሎ የመጣ ማንም ልጅ አልነበረም፡፡
ለዚህ ነው ብዙ ልጆች እንዲኖሩኝ እመኝ የነበረው፡፡ የዛሬ ባሌን የማግባት እድሌ ሃምሳ በመቶ ነበር፡፡ አሜሪካ ለትምህርት የሄደውን እጮኛዬን የማግባት እድሌ ደግሞ ሃምሳ በመቶ ፡፡ ልቤ ሁለቱንም ይወድ ነበር፡፡ በእርግጥ መጀመሪያ የወደድኩት የመጀመሪያውን፣ አሜሪካ የሄደውን እጮኛዬን ነበር፡፡ ልቤ ለሁለተኛው የተከፈተው አሜሪካ የሄደው እጮኛዬን መጠበቅ ከሰማይ መና የመጠበቅ ያህል ስለሆነብኝ ነው፡፡
እዚህ ሃገር ኢንጂነር መሆን የማይቻል ይመስል አሜሪካ ሄጄ ኢንጂነሪንግ ልማር
ብሎ በጣም ረጅም ጊዜ ቆየ፡፡ የዚያን ጊዜ ኢንተርኔት ጨጓራ የሚልጥና ቀርፋፋ ስለነበር በዚያ ጎታታ ኢንተርኔት
በስካይፕ መገናኘት አቸከኝ፡፡ በቪዲዮ እያወራን አንድ አረፍተ ነገር ሳይጨርስ
ምስሉ ስክሪኑ ላይ ደርቆ ይቀራል፡አንዳንዴ አፉ አጓጉል ተከፍቶ እያለ ነው እንዲህ የሚሆነው፡፡ ታዲያ ይሄን ጊዜ ዝም ብዬ ይሄንን ምስሉን አይና ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነሳ ምን እንደሚመስል ማሰብ እጀምራለሁ፡፡ ጠዋት ሲነሳ ምን እንደሚመስል የማላውቀውን ሰው ለማግባት ማሰቤ ያስፈራኛል፡፡ ሴቶች የሚያገቡት ሰው ጠዋት እንደተነሳ ምን እንደሚመስል ማወቅ አለባቸው ባይ ነኝ፡፡ ከእንቅልፋቸው ሲነሱ ነፍሰ ገዳይ የሚመስሉ ፍቅረኞቸ ነበሩኝ፡፡ በዚያ ምክንያት የተውኳቸው፡፡ ባሌን የተዋወቅኩት ከግብርና ጋር የተያያዘ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ ስለ ማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘር ምናምን የሚያወራ ስልጠና ነገር ነበር፡፡ ወደፊት ገበሬ የመሆን ሃሳብ
ነበረኝ፡፡ ከፕላስቲክ የተሰሩት ወንበሮች ላይ ጎን ለጎን ነበር የተቀመጥነው፡፡ ካሮት የሚመስሉ የእጆቹን ጣቶች ሰረቅ እያደረግኩ ሳይ ትዝ ይለኛል፡፡ ከዚያ
ማውራት ጀመርን- ስለ እንጆሬ፡፡ የእንጆሬ እርሻ ነበር እንዲኖረኝ የምመኘው፡፡ በኋላ ለሻይ ቡና ስንንናኝ አሜሪካ ስላለው እጮኛዬ ነገርኩት፡፡ ‹‹በዱር ካሉ ሁለት ወፎች በእጅ ያለ አንድ ወፍ ይበልጣል›› አይለኝም? ተረት እና ምሳሌያዊ አነጋገር፣ ፈሊጥ ምናምን የሚገባኝ አይነት ሴት አይደለሁም ግን እሱ ነው የሚያዋጣሽ ማለቱ መሰለኝ፡፡ የሚገርመው ግን እንዲህ ማለቱ ልቤ
እንዲፈልገው አደረገ፡፡ አለ አይደል…የሴት እልህ…‹‹ምናባቱ ቆርጦት ነው ለሌላ ወንድ አሳልፎ የሚሰጠኘኝ?›› አይነት ነገር፡፡ ከአመት ተኩል በኋላ በሰርግ ተጋባን፡፡ አሜሪካ ያለው እጮኛዬን ልብ እንደ መስታወት ያደቀቀ እና መቶ ሰዎች ብቻ የተጋበዙበት ቀለል ያለ ሰርግ ነበር፡፡ ባሌ በጥቁር ሱፍ አምሮበት- ሰፊ ትከሻው ኮቱን ወጥሮት- የሚጣፍጥ የአፍተር ሼቩ መአዛ እያወደኝ፡፡ አፍተር ሼቭ የሚጠቀም ወንድ ደስ ይለኛል፡፡ ከሰርጉ ጥቂት ወራት በፊት አርግዤ ነበር፡፡ ግን ሆዴ ስላልገፋ ብዙ አያስታውቅም ነበር፡የእናቴን ውብ ሃብል አድርጌ. አባቴ እጄን ጥብቅ አድርጎ ይዞኝ…..ስለሰርጌ የማስታውሰው ይሄንን ነው፡፡ የአባዬ እጄን አጨማመቅ…. ብዙ ሳልቆይ ልጄን ወለድኩ፡፡ ብዙ ሳልቆይ ስል ሰርጌ ላይ ኬኩ እንደተቆረሰ ማለቴ ሳይሆን ከጥቂት ወራት በኋላ፡፡ ከዚያ በኋላ በተከታታይ መውለድ ቀጠልኩ፡፡ እንደ እኔ ፍላጎት ቢሆን ቤቴን ሆስፒታሉ ውስጥ አድርጌ መመላለሱ ይቀርልኝ ነበር፡፡ ዝም ብዬ መውለድ ቀጠልኩ፡፡
ሶስተኛው ልጃችን እንደተወለደ ባሌ ‹‹አሁን ይበቃናል›› አለ፡፡ ይበቃናል? ይቀልዳል እንዴ? ከቁብ ሳልቆጥረው ሁለት ልጆችን ጨመርኩ፡፡ ልጆች ድንቅ ስጦታዎች ናቸው፡፤ ግን ሰውነትን እንዳልነበር ነው የሚያደርጉት፡የመጀመሪያዎቹ ሁለት ልጆቼ ሰውነቴን ፈጽሞ ቀይረውት ነበር፡፤ ከዚያ በኋላ ግን ለውጡ እምብዛም ነው፡፡ አሁን ሳስበው በሰርጌ እለት ከነበረኝ አቋም አሁን ሳልሻል አልቀርም፡፡ እንደዚያ
ጊዜ ወደ ላይ አይለኝ፡፡ ከዚያ ጊዜ ይልቅ አሁን ሞላ፣ ሰፋ ብያለሁ፡፡ ዳሌዬ ሰፍቷል፡፡ ከበፊት ይልቅ ያሁኑ ሰውነቴ ያኮራኛል፡፡ ያው ወገቤ አከባቤ ትርፍ ስጋ አይጠፋም ግን ለማስተካከል እየታተርኩ ነው፡፡ ደረጃ ስወጣ የሚንቀጠቀጥ ትልቅና የላላ መቀመጫዬ ሊኖረኝ ይችላል፡፡ ግን ያም ሆኖ አማላይ ቢጤ ነኝ፡፡ ….ለምሳሌ መቼ እለት መስሪያ ቤታችን በተለማማጅነት የተቀጠረ የ ሃያ አንድ አመት ጎረምሳ፣( በእድሜ እጥፍ የምበልጠው ጉብል - ወደ ጠረጴዛዬ መጥቶ የባጡንም የቆጡንም ሲቀባጥር ቆይቶ ምን ቢለኝ ጥሩ ነው? ‹‹ነገ…ከቢሮ ወጣ ብለን ሻይ ቡና ብንል ምን ይመስልሻል?›› እውይ፡፡
‹‹በጣም ደስ ይለኝ ነበር …›› አልኩና ግራ እጄን አንስቼ የጋብቻ ቀለበቴን እየጠቆምኩ ‹‹ግን ባለትዳር ነኝ›› አልኩት፡፡ ‹‹ውይ…ይቅርታ…ግን በጣም ቆንጆ ነሽ›› አለኝ፡፡ እውይ፡፡ እድሜው ሰላሳ ሁለት ቢሆንና ከእናቱ ጋር የማይኖር ቢሆን ቡናውን እጋበዝለት ነበር፡፡ አሁን አሁን ከተማው ውስጥ እንደእሱ አይነቶቹ በዝተዋል- ከእናታቸው
ወይ ደግሞ እንደ እናት ከሚሰራቸው ሴቶች ጋር የሚኖሩ ወጣት ወንዶች፡፡
ግብዣውን እቀበል የነበረው ባለትዳር ብሆንም ላጤ ስለሆንኩ ነው፡፡ ትዳሬ ጣእሙን መለወጥ የጀመረው ከአምስት አመታት በኋላ ነበር፡፡ ትዳሬ የተለወጠው ባሌ ስለተለወጠ ነው፡፡ ሁላችንም ተለውጠናል፡፡ ግን ለውጡ ቀ……ስ ያለ ነበር፡፡ …አለ አይደል…ምን የመሰለ የአትክልት ስፍራ ውስጥ እንደሚታይ ትንሽ አረም….መጀመሪያ ስታዩት ያን ያህል ትልቅ ነገር አይመስልም፡፡ ቀስ በቀስ ተስፋፍቶ አትክልትና አበቦቻችሁን ውርር እስኪያደርግ እና አንድ በአንድ ማነቅ እስኪጀምር፡፡
---ይቀጥላል-----

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሴት እና ትዳር- ‹‹እርቃን››- ክፍል ሁለት
------------------------
ትዳራችን ይነፍስበት የጀመረው እዚህ ግባ በማይባሉ ጥቃቅን ነገሮች መነሻነት
ነበር፡፡ አለ አይደል…ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነቃ እንዴት አደርሽ ማለት ሲተው… (ባሎች፣ እባካችሁ..ሁሌም ሚስቶቻችሁን እንዴት አደርሽ ብላችሁ ጠይቁ….በክር ከተሰራች አሻንጉሊት ጋር አይደለም እኮ ተኝታችሁ ያደራችሁት! አንድ ቀን እንዴት አደርሽ ብላችሁ መጠየቅ ስትረሱ ነገም አታስታውሱም…ከዚያ ይለምድባችሁና
ልክ አዳሪ ትምህርት ቤት እንደሚኖር ተማሪ ብድግ ብላችሁ ካልጋ መውጣት
ትጀምራላችሁ፡፡ ) እና እንዳልኳችሁ ጠዋት መነሳትና ሰላም ሳይለኝ ወደ ሽንት ቤት መሄድ ጀመረ፡፡ ሁልጊዜ እንዴት አደርህ የምለው እኔ ሆንኩ፡፡ ከዚያ እኔ ብቻ እንዴት አደርህ ማለቱ ታከተኝ፡፡ እየቆየ ሲሄድ ጠዋት ጠዋት እኔን ማየት እንኳን እንዳቆመ ማስተዋል ጀመርኩ፡፡ ልብስ እየለባበስን ስናወራ እንኳን ጭራሽ አያየኝም፡፡ ለማየት የማስቀይም አይደለሁም፤ ሁሌም ራሴን በመስታወት ስለምመለከት ይሄንን አውቃለሁ፡፡ እና ታዲያ ምን ሆኖ ነው የማያየኝ? እኔ ደግሞ ሰው ካላየኝ ኖርኩ አልኖርኩ ግድ እንደሌለው ነው የሚሰማኝ፡፡ ካላየኸኝ የለሁም ማለት ነው…ድምጽ ብቻ ያላት መንፈስ ሆንኩ ማለት ነው…(.ወንዶች፣ እባካችሁ ሚስቶቻቸሁን እዩ፡፡ ) ጠዋት ጠዋት ሰላም ማደሬን ባይጠይቀኝም፣ ባያየኝም ግን ትዳራችን ጥሩ የሚባል ነበር፡፡ ቤቱን ማስተዳደር ላይ አልሰነፈም፡፡ ለልጆቹ መጫወቻ እና ልብስ ይገዛል፡፡ አንዳንዴም አብሯቸው ይጫወታል፡፡ ከዚያ ሕይወት በማይታሰብ ፍጥነት መክነፍ ጀመረች፡፡ ልጆቻችን ትምህርት ቤት ሲገቡ የትምህርት ቤት ክፍያ ራስ ምታት እና ለነገ ጥሪት የመቋጠር ጭንቀት ይወጥረን ጀመር፡፡ ባለቤቴ ትልልቆቹን ወጪዎች ሲችል እኔ ደግሞ ጥቃቅን የቤት ቀዳዳዎችን እየደፈንሁ ኑሮ ቀጠለ፡፡ ከዚያ ሳይታወቀን ሁለታችንም በየራሳችን ዛቢያ የምንሽከረከር፣ በማይገናኙ መንገዶቻችን አለእረፍት የምንሮጥ እና የምንባዝን ሰዎች ሆንን፡፡ እሱ ቤት ከሚኖርበት ጊዜ ስራ ላይ የሚያሳልፈው ጊዜ እየበዛ፣ ቤት ሲመጣም በድካም ብትንትን ብሎ እና ልጆቹን እንኳን ማናገር እንዳይችል ሆኖ፣ ለመኝታ
ብቻ ሆነ፡፡ እሁድ እሁድ ቤት ይሆናል ግን ከቅዳሜ የዞረ የመጠጥ ድምሩን ስለሚያወራራድ እንዳለ አይቆጠርም፡፡ ሁሌም በስራ ደክሞ ስለሚገባ ልጆቼን ብስክሌት መንዳት እንኳን ያስተማርኳቸው እኔ ነኝ፡፡ ለነገሩ ጭራሽም ለማድረግ አልሞከረ፡፡ እያደር እሱ ሊያከናውናቸው የሚገቡ ስራዎችን ፣ ሊወጣቸው የሚገቡ ሃላፊነቶችን እኔ ማድረግና መወጣት ጀመርኩ፡፡ የቧንቧ ሰራተኛ ፈልጎ ማግኘት…የልጆቹን ትምህርት ቤት መምረጥ፡፡ ልጆቻችን እያደጉ ሲሄዱ አብሯቸው ማሳለፍ ያለበትን ጊዜ ሳያሳልፍ እድሜያቸው
እንዳያልፍና እንዳይቆጨው ብዬ ጊዜ እንዲሰጣቸው የምችለውን ሁሉ ጣርኩ፡፡
እስቲ መናፈሻ ወይ መጫወቻ ቦታ ውሰዳቸው…ብስክሌት አብረሃቸው ጋልብ….አዋራቸው፣ ወንዶቹን ደግሞ እንዴት አይነት ወንድ…እንዴት አይነት አባት መሆን እንዳለባቸው አሳያቸው ስል ወተወትኩት፡፡ እሱ ግን ሁሌም ጊዜውን የሚሻማ ነገር አያጣም፡፡ ሁሌም ከዚህ የሚበልጥበት ነገር አይጠፋም፡፡ ከዚያ የቤተሰቡ ራስ እኔ ሆንኩ፣ ውሳኔ አሳላፊዋ ሆኜ አረፍኩ፡፡ ከጊዜ በኋላ የትምህርት ቤት ክፍያ በጊዜ መክፈል አቆመ፡፡ ጭራሽ ትምህርት ቤቱ ደውሎ
ክፍያ ይጠይቀኝ ጀመር፡፡ ያን ጊዜ የዚያኛውን ሴሚስተር ራሴ እከፍልና
የሚቀጥለውን እንዲከፍል ባየው ባየው እሱ እቴ!
---
አባቴ ለእናቴ ምን አይነት ባል እንደነበር አላውቀም፡- ምናልባት እንደ ባል ያጎደለባት ነገር ይኖር ይሆን አላውቅም፡፡፡ ለእኔ ግን ምን አይነት አባት እንደነበር ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ ሃላፊነቱን የሚያውቅና በአግባቡ የሚወጣ አባት ነበር፡፡ በዚያ ላይ ኩሩ ነበር- የእኔ አባት፡፡
አንዴ አስታውሳለሁ- አስር ወይ አስራ አንድ አመቴ እያለ- ቅዳሜ ቀን ነው…. ጠዋት ቁርስ እየበላን በልጅነት አእምሮዬ ያኔ- ምክንያቱ አልገባኝም ግን የሆኑ የባንክ ሰራተኞች ወደ ቤታችን መጡ፡፡ አባዬ እኔና እማዬን ካለንበት ትቶን
ሊያናግራቸው ይሄዳል፡፡ በሳሎኑ መጋረጃ ውስጥ ውጭ ቆሞ ሲያዋራቸው አያለሁ፡፡ ከአጥራችን ውጪ
የቆመው የጭነት መኪና የቤት እቃችንን በሙሉ ለቃቅሞ ለመሄድ የጓጓ ይመስላል፡፡ እማዬ ከተቀመጠችበት ሳትነሳ፣ አንዴ እንኳን ሳትንቀሳቀስ፣ ተነስታ ወደ አባዬ ሳትሄድ እዛው ቁጭ ብላለች፡፡ የእሷ ተረጋግቶ መቀመጥ እኔንም ሲያረጋጋኝ አስታውሳለሁ፡፡ እሷ እንደዛ ረጋ ብላ ቁጭ ካለች ውጪ እየሆነ ያለው (መጥፎ ነገር ይመስላል) ምንም ነገር ቢሆን አባዬ መላ እንደማያጣለት እና ወደ ቁርሱ እንደሚመለስ ነገረኝ፡፡ እናም ልክ እንዳሰብኩት ሆነ፡፡ አባዬ ያንን ቀን ልክ ሌሎች ቀኖችን እንደሚያሳልፈን በብልሃት አሳለፈን፡፡ ከዚያ በኋላ ስለ ወንድነት ያለኝ ግምት አባቴን ተደግፎ የተሳለ ሆነ፡፡ ወንድ ልጅ፣አባወራ ሲሆን ቤተሰቡ የሚገጥመውን ችግርን ወጥቶ እንደ ወንድ መጋፈጥ እንዳለበት፣ ከዚያም በኩራትና በልበ ሙሉነት መቆም እንዳለበት ከአባዬ ተማርኩ፡፡
.
እናትና ሚስት ሆኜ ቤቴን ማስተዳደር ምኞቴ ነበር፡፡ ባሏን የምትከተል፣ ታታሪና ጨዋ ሚስት መሆን ነበር ፍላጎቴ፡ሚስት፡፡ ቀስ በቀስ ግን የአባወራውን ስራ መረከብ ጀመርኩ፡፡ ባል ሆንኩ፡፡ እሱ መወሰን ያለበትን ነገር መወሰን፡፡ የልጆቹን ትምህርት ቤት ክፍያ መክፈል፡፡
ያን ጊዜ በሌላ አይን እመለከተው ጀመር፡፡ በፊት የምመካበት እና የማደንቀው ወንድ መሆኑን አቆመ፡፡ አቅጣጫው ጠፍቶበት የሚማስን ሰው ሆኖ አገኘሁት፣ አቅጣጫው የጠፋበት ሰውን ደግሞ መከትል አልችልም፡፡ ከጊዜ በኋላ አንዳችን ለአንዳችን ጭራሹን ባእድ ሰዎች ሆነን አረፍነው፡፡ የባል እና ሚስት ወጋችን እንደ በርሃ ዝናብ በጭንቅ የሚመጣ እና በስንት ጊዜ
የሚከሰት ነገር ሆነ፡፡ ከስንት አንዴ ሆኖልን ፍቅር ስንሰራ እንኳን ሃሳቤ ወደማልመው የእንጆሬ እርሻዬ
እየሄደ ያስቸግረኛል፡፡ ስናወራ ከሌላ አለም እንደመጣ ሁሉ፣ ሁሉ ነገሩ እንግዳ ይሆንብኝ ጀመር፡፡ የማላውቀውን ቋንቋ እንደሚናገር እንግዳ ሰው፡፡ ይሄ ሁሉ የሆነው አሪፍ ሚስት መሆኔን ስላቆምኩ ይሆናል፡፡ እንደ በፊቱ አምሽቶ ሲመጣ እና እራት እየበላ የዚያን እለት ቢሮ ስለተፈጠሩ አስደናቂ ነገሮች ሲያወራኝ እያዳመጥኩ፣ ቁጭ ብዬ አላየውም፡፡ ይልቅ ለጥቂት ቀናት ፊልድ ሲሄድ ልቤ ጮቤ ይረግጣል፡፡፡ ያን ጊዜ ቤቱ ይሰፋኛል፣ ክፍሎቹ ወደ ጎን ልጥጥ ይላሉ… ያኔ.መተንፈስ እችላለሁ፡፡ ከፊልድ የሚመለስ ቀን ቀድሜው ገብቼ ደህና የሚበላ ነገር አዘጋጅቼ (ድሮ ቢሆን የምበላው ነገር እኔ ነበርኩ!) ለመጠበቅ አልቸኩልም፡፡ በፊት በፊት በየትኛው አውሮፕላን እንደሚመጣ፣ ትራንዚቱ የት እንደሆነ፣ ስንት ሰአት የት እንደሚደርስ አውቅ ነበር፡፡ አንዳንዴማ ኤርፖርት ሁሉ ሄጄ እቀበለው ነበር- ያውም ምን እንደሚናፍቀው ስለማውቅ ትኩስ ቡና በፔርሙስ ይዤ! አሁንስ? አሁንማ ደስ የሚለኝ ሲሄድልኝ ነው፡፡ ምክንያቱም ቤት ውስጥ ሆኖ ልክ እንደ ወንዶቹ፣ ልክ እንደ ቤተሰብ አስተዳዳሪ፣ እንደ ደህና አባወራ ወዲህ ወዲያ ሲል ላየው ስለማልፈልግ ነው፡፡ በዚያ ላይ…የሚያገኘውን ገንዘብ የት እንደሚያደርገው ሳላውቅ ወይ ሳይነግረኝ… ቤተዘመድ ጋር አብረን ስንሄድ ግን እንደ መልካም ሚስት- እናት እና አባቱ እንደሚፈልጓት አይነት- እሆንና ምግብ አቀርበለታለሁ፡፡ እናቱ ልጃቸው እንዲህች አይነት ድንቅ ሚስት አግብቶና በትዳሩ ተደላድሎ ስለሚኖር ኩራት ኩራት
ይላቸዋል፡፡ የማያደንቀን ሰው የለም፡፡ ‹‹ድንቅ ጥንዶች›› ይሉናል አንዳንዶቹ፡እውነታው ግን የተገላቢጦሽ ነው፡፡
አናወራም፡፡ አንጣላም- ለጠብ የሚሆን ጉልበት እንኳን አልነበረንም፡፡ ውድቅት ላይ ቤት ቢመጣ ግድ አይሰጠኝም፡፡
ውጪ ያስቀመጣት ሴት ብትኖር እንኳን ደንታ የለኝም፡፡ ያስቀመጣት ካለችውም የወንድ ቅርፊት እንጅ ደህና ወንድ እንዳላገኘች ስለማውቅ አይቆረቁረኝም፡፡ የወንድ ልጣጭ ነው ያገኘችው፡፡ የወንድ ጭራ፡፡ የባለቤቷን ጉድለቶች አንድ በአንድ የምትቆጥር፣ ኩንታል ስህተቶቹን ተሸክማ የምትኖር፣ የወንድነት ጥላ የራቀው እርቃን እና ደካማ ባሏን አብጠርጥራ የምታውቅ ሚስት ሆኛለሁ፡፡ እርግጥ ነው- እኔም ደካማ ጎን አለኝ- ምን ጥያቄ አለው? እዚህና እዚያ ምላሴን ያዳልጠኝ ይሆናል፡፡ ነገረኛ ብጤም ሳልሆን አልቀርም፡፡ እሱም ከአንዴም ሁለት ሶስቴ ጨቅጫቃ መሆኔን ነግሮኛል፡፡ እንዲህ ስለመሆኑ እና እንዲህ እንዲሆን ምክንያት ስለሆኑት ነገሮች የማወቅ አንዳችም ፍላጎት ግን የለኝም፡፡ አንዴ የሆነ አውሮፓ ያለ ኤርፖርት ውስጥ ሆኜ በጉዞ የተዳከሙ እና ጥውልግ- ትክት ያሉ ሰዎች- አይኖቻቸውን ባዶ አየር ላይ ተክለው-- ዝም ብሎ በራሱ የሚሄደው ተንቀሳቃሽ ደረጃ ላይ በደመነፍስ ሲሳፈሩና በድንዛዜ ሲሄዱ ሳይ ‹‹ትዳሬ ልክ እንደዚህ ነው››› ስል ትዝ ይለኛል፡በቅርቡ የሆነ ደረሰኝ ኪሱ ውስጥ አግኝቼ ነበር፡፡ ከጓደኞቹ ጋር ሲዝናና አምሽቶ የከፈለበት ነው፡፡ ለአንድ ጠርሙስ ውስኪ እና ለሚበላ ነገር ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር ከፍሏል፡፡ በአንድ ምሽት ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር ያውም በአዘቦት ቀን፡፡ ደረሰኙን ሳይ ልቤ በጩቤ የተወጋ መሰለኝ፡፡ የልጆቹን ትምህርት ቤት ክፍያ አልከፍልም የሚል ግን ለመጠጥ ይሄን ያህል ብር የሚያወጣ ወንድ ሆኗል፡፡ ስለ ልጆቹ ጉብዝና ለወላጆቹ፣ ለዘመድ አዝማድ የሚጎርር ግን ተማሩ አልተማሩ ግን የማይሰጠው ሰው ሆኗል፡፡ ያውም ከእኔ በስንት እጥፍ የሚበልጥ ደሞዝ
እየበላ፡፡ እርግጥ ነው እንዳሻው እንዲሆን ፈቅጄለታለሁ፡፡ የውሸት እንዲኖር ተባብሬዋለሁ፡፡ ጥሩ አባት እና መልካም ባል ነኝ ብሎ የሚያምንበትን የቁጩ አለም ገንብቶ የውሸት እንዲኖር ይሁንታዬን ሰጥቼዋለሁ፡፡ እዋሽለታለሁ፡፡ ከዚህ ሁሉ ነገር የሚስጠላው ነገር ግን የእሱ ውሸታምነት እኔንም የውሸት የምኖር ውሸታም ማድረጉ ነው፡ ሁለመናዬ ውሸት የሆነ ሰው
አድርጎኛል፡፡ ምናልባት ጠርጥራችሁ ከሆነ ከሌላ ሰው ጋር መውጣት አልጀመርኩም፡፡ ሰው ጠፍቶ አይይለም፡፡ መግቢያ መውጫ ያሳጡ ብዙ ወትዋቾች አሉኝ፡፡ ግን በህግ ባለትዳር ነኝ፣ ትዳር ያለኝ ላጤ ብሆንም፡ ከባለቤቴ ጋር ‹‹ትዳር›› የሚባል ለትርፍ የተቋቋመ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የምንመራ ሁለት ሰዎች ብንሆንም፡፡ እንደሚስት በምንም ነገር እንዲያግዘኝ መጠየቅ ካቆምኩ ቆየሁ፡፡ እንደ ቤቱ ራስ፣ እንደ አባዋራ እሱን መከተል ከተውኩ ቆየሁ- መምራት አቁሟላ! ግርማ ሞገሱ ጠፍቶ አይኔ ላይ ከኮሰሰ፣ ለእሱ ያለኝ ክብር ብን ብሎ ከጠፋ ሰነባበተ፡፡ በፊት በፊት ያማልለኝ የነበረ ያ ወንዳወንድነቱ….ለምሳሌ ጠዋት ጠዋት ከወገቡ በላይ ራቁቱን ሆኖ ጥርሱን ሲፍቅ ሳየው የሚሰማኝ ሞቅታ በፀፀት ተተክቷል፡፡ እስከ መቼ ነው እንደዚህ የምኖረው ግን? እኔስ እስኪያንገሸግሸኝ፣ እስኪያቅተኝ ድረስ እዚህ ያጋደለ፣ ጣራው የሚያፈስ ጎጆ
ውስጥ መኖር እችላለሁ፡፡ ከሁሉ የሚያንገበግበኝ ግን ልጆቼ የአባታቸውን ሁኔታ መረዳት መጀመራቸው ነው፡ አባታቸው ለቤተሰቡ ጥላ ከለላ የሚሆን ጠንካራ አባወራ አለመሆኑን ማየት መጀመራቸው ነው፡፡በተለይ ለወንድ ልጆቼ አብዝቼ እጨነቃለሁ፡፡ የአባወራ ምሳሌ አድርገው ለሚስሉት ምስኪን ልጆቼ፡፡ የወንድነት አርአያ አድርገው የሚቆጥሩት - እሱን በሆንኩ የሚሉት ሰው ይሄ በመሆኑ፣ ልጆቼ አውላላ ሜዳ ላይ ስለቀሩብኝ አዝናለሁ፡፡ ስለ ልጆቼ እጣ ፈንታ የምጨነቀው እኔ ብቻ፣ ለቤተሰቤ የምወጋው እኔ ብቻ መሆኔ ልቤን በሃዘን ያደማዋል፡፡ ውስጤን ይሰረስረዋል፡፡ ያበግነኛል፡፡ ከዚህ ግራ የገባው ሁኔታ እንዴት ማምለጥ እንዳለብኝ አላውቀም፡ምክንያቱም….የቤቴን ወጪ መሸፈን እችል ይሆናል፣ ከልጆቼ ጋር ማውራት እና መጫወት እችል ይሆናል፣ የቤት ሥራቸውን አብሬያቸው መስራት፣ ሲጎብዙ ማበረታታት፣ እንደ እናት ስለ እነሱ መፀለይ አያቅተኝ ይሆናል፡፡ ግን እንዴት መልካም አባወራ መሆን እንዳለባቸው ላሳያቸው፣ አርአያ ሆኜ ልመራቸው አልችልም፡፡ ያንን ሊያደርግ የሚችለው አባወራው ብቻ ነው፡፡ የእኔ አባ ወራ ተብዬ ደግሞ ሃላፊነቱን አሽቀንጥሮ ጥሎ፣ ወንድነቱን እንደ አሮጌ ካፖርት አውልቆ ወንበር ላይ ማንጠልጠልን መርጧል፡፡
-----አበቃ------

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Hiwot_Emishaw
- ወንድ ልጅ ሹገር ማሚ ጠብሶ መኪና ሲገዛ ጀብድ ነው ሴት ልጅ መኪና ያለው
ወጣት ወንድ ስትጠብስ ጎልድዲገር ትባላለች ? ከተማው ውስጥ ስንት የአሮጊት ሴቶችን ጭን ሲያሞቁ የሚውሉ የወንድ ጡረተኞች እንዳሉ አናውቅምና ነው ?

- ለወንድ ልጅ ሴት መቀያየር ማዕረጉ ነው ሴት ልጅ ቦይፍሬንድ ስትቀያይር ይች አተራማሽ ቤተሠብ አሠዳቢ ትባላለች !

- ወንድ ልጅ ትዳር እያለው ችት ቢያደርግ ሚስቱን ታገሽውና ለልጆችሽ ስትይ ሁሉን ችለሽ ኑሪ ትባላለች ሚስት ችት ብታደርግ ከቤትህ አባራት ይባላል :: መጥፎ ነገርን ስታወግዙ ለሴት ወንድ ብላችሁ ሣይሆን ድርጊቱን አውግዙ መጥፎ ነገሮች ለሴት ልጅ ብቻ እንደተሠጡ ነው ይሄ Dysfunctional culture በራሡ ለሴት ልጅ ያለው አመለካከት የወረደ ነው ሴት ሁሌም የወንድ ጥገኛ ናት ሴት መኪና ትወዳለች ሴት ብር ትወዳለች :

- ህይዎት ፊልም ላይ እንዳለው አንዲት የሃብታም ልጅ የጋራዥ ሠራተኛ አፍቅራ
ምናምን አይደለም፡፡ ሁሉም ሲያስመስል ነው ማንም ቢሆን የተሻለ ነገር ቢያገኝ አይጠላም !

- youtube ላይ ብር ለመለቃቀም ሲባል ጎልድ ዲገር ምናምን እያሉ የሴት ልጅን ክብር የሚነካ ነገር የሚሠሩ ምድረ ዱቄታም ኮልኮሌ ማነው ፈቶ የለቀቃቸው ? ምንድነው PHD የሠራሁት በስግጥና ነው ማለት ! ችግርህን ለማራገፍ ሴት ልጅን አሸማቆ ገንዘብ ከማግኘት በላይ ድድብና ከየት ተገኝቶ

- በስፖኪዮ የሴት ልጅ ቂጥ ለማየት 360° ዲግሪ አናቱ የሚዞር ወንድ ሁላ ሴት ልጅ ጥቅመኛ ናት የሚል ቪዲዮ ሠርቶ ይለቃል ህዝቡም እንዲህ አይነት ነገር ይመቸዋል ያያል ። ከዛ እሷን አሸማቆ እሡ ገንዘብ ያገኛል ። ይሄ የምርጫ ጉዳይ ነው መኪና ያለው ወንድ ነው የምፈልገው የምትል ሴት ካለች መብቷ ነው ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Bethlehem Habtie
ውብ እግሮች ያሏት ቀይ ሴት ትስበኝ ነበር። ሞላ ያለች፣ ጠጉሯን ቁጥርጥር
የምትሰራ፣ ደስ ሲላት ጂጂ ፍሪዝ የምታንጨባርር፣ መብራት ሲጠፋ የምትበራ፣ ሞቅ ሲለኝ ጠብቃ የምትደውልና “ስሞትልህ ግጥም አንብብልኝ” እያለች የምትስቅ ልጅ ትስበኝ ነበር። “የጥበብ ሰው አስተዋይ ነው” በማለት ራሷን ለጅንጀና ያመቻቸች ሴት ትስበኝ ነበር። “የእንትናን መድበል አነበብክ ዎይ? ሳድስ ያበዛል እንጅ፣ እንዴት ጎበዝ መሰለህ” እያለች፣ ጥቁር ማኪያቶ… ከካፌ ጠረጴዛ ወደ ከንፈሬ የሚያደርገውን ተንሳፋፊ ጉዞ በጨዋታ የምታቋርጥ አይነት ልጅ ትመቸኝ ነበር… ነበር…የኔ ተንከሲስ መጣችና ምርጫዬን ፐወዘችው! ብዙ ከተዜመላቸው ወገን ናት። ጠይም መልከ መልካም፣ ዐይኗ ጎላ ያለ። ካልከፋት አትስቅም። አይከፋትም ደግሞ። ህይወትን እንደ ቼዝ በስሌት ነው
የምትጫወታት። በአንድ ቢጫ ረፋድ፣ ካፌ ዘና ብላ ስፕራይት እየጠጣች ነበር።
በመሃል ስልኳ ጠራ። ቀጥሎ ያደረገችው ፈፅሞ የማይጠበቅ ነው በውነቱ አነሳችዋ ስልኳን! የደወለችላት ጓደኛዋ ምን እንዳለች እንጃ… እንዲህ መለሰች…“ኤዲያ… ግጥም ደግሞ ምን ያደርጋል? ስጠላ!” በያዝኩት መፅሄት አስመስዬ ፈገግ አልኩ… ደስ አለቺኝ… ስልክ አናግራ ስትጨርስ ሄድኩና አጠገቧ ወንበር ሳብኩ…“ሰዓት ይዘሻል የኔ እህት?” “ሃሃ ይቺ ሙድ አልፎባታል… አልሰማህም?” “የመረጥኳት ለምን ሆነና? ይገርምሻል ብዙ ጀንጃኞች ያለፈባቸውን አባባሎች አቅም አሳንሰው ያያሉ… እና አዲስ አቀራረብ ለመፍጠር ይንገላታሉ… ድከሙ ሲላቸው!” “ጋሽ ምኒሊክ ወስናቸውን ታውቃቸዋለህ?”
“አዲስ ጅንጀና ከመፍጠር የተረሱትን መልሶ መጠቀም አይሻልም ብለሽ ነው?”
“‘የእንጆሪ ፍሬ’ የሚል ውብ ዘፈን አላቸው… እንዴት ያምራል መሰለህ… ለምን እንደተዜመ ብነግርህ አታምንም”
ምን ዓይነቷ ቀውስ ላይ ጣለኝ ዛሬ ደግሞ… አልኩና፣ እንደ ስምንተኛው ንጉስ በግራ እጄ አማተብኩ… “ሃይማኖት እባላለሁ… ሰባት ተኩል ሊሆን ነው…” እንዲቹ እየተደናቆርን ሁለት አመት አብረን ቆየን!
____
ሁለት መሃንዲሶች ወዳጅ ቢሆኑ አይሰለችም? ስለምን ሊጨዋወቱ ነው? ስለምን ዝም ሊባባሉ ነው? የተግባቡ ሰሞን ስለ አገራቸው መንገዶች ጥራት
መጓደል ያወሩ ይሆናል። ምናልባት በእርዳታ ብር ተጀምሮ፣ በዘረፋ ሰበብ ስለተጓተተ ‘ደረጃውን የጠበቀ’ መንገድ ያወሩ ይሆናል፣ ያ ሲሰለቻቸው ተማሪ
እያሉ ስለወሰዱት ‘ብሪጅ’ የተባለ ኮርስ ይወያዩ ይሆናል… ከዛስ? “መንገድ ዐይኑ ይጥፋ አይባልም ደርሶ የወሰደውን ሰው ያመጣል መልሶ” ይሉ ይሆናል አንዳቸው
“አቦ ባለፈው አወራንበት እሱን… አዲስ ጨዋታ የለም?”
_
እኔና እሷን ሁለት አመት ያኖረን ልዩነት ነበር። ግጥም ደስ ይለኛል። ግጥም ያስቃታል። ካልከፋት የማትስቀው ጉድ ግጥም ሳነብላት ትስቃለች። ግጥሙ
እያስከፋት ይሆናል እንግዲህ። ተናዳ ከሆነ ደግሞ ግጥም ይበልጥ ያበግናታል። ሁለት አመት ያጣመረን ልዩነትም ሰለቸን መሰል ጭቅጭቅ አመጣን። ጥንዶች ጭቅጭቅን ችለው የሚቀጥሉት አብረው ስለሚተኙ ሳይሆን አይቀርም። እሱም እስኪሰለች። በሆነ ባልሆነው እየጨቀጨቀች አንጎል አደረገችኝ። ለንዝንዟ ምላሽ ባለመስጠት አበሳጨሁዋት። ባንድ ክፉ ማክሰኞ ከንቅልፏ ተነሳች፣ ከአልጋችን ወረደች፣ ፊቷን ታጠበች፣ ጥርሷን ቦረሸችና ጀበና ወርውራ ሳተቺኝ… በስመአብ! ከየት አመጣችው? ሰው ‘የሚፈነከት አይጠፋም’ ብሎ፣ ጀበና ገዝቶ ይደብቃል? ደሞ ሰው በጀበና ለመፈንከት ጥርስ መቦረሽ ያስፈልጋል? እንደ ዲስከስ ወርዋሪ በቅንፍ ቅርፅ ነበር
ጀበናውን የወረወረችው፣ ስቶኝና ግድግዳውን ነርቶ፣ ስብርባሪዎቹ ወደ መሬት ሲወድቁ፣ አንድ ኮሜዲያን ስለ ፍቅርና መዋደድ የተናገረውን እያሰብኩ ነበር… “የምን ፍቅር? መዋደድ ይበቃል! ፍቅር መጨረሻው ጠላትነት ነው! ”በድርጊቷ ተናደድኩ! እንዴት እንደምጎዳት እያሰብኩ፣ ስንደረደር ወደ ጆሮ ግንዷ ተጠጋሁና፣ ሁለት መስመር ግጥም አነበብኩላት… አለቀሰች ተለያየን።
_
ጊዜአት አለፉ… ድንገት የተገናኘነው ከሶስት ዓመት በኋላ ነበር። አምሮባታል። ሲፋቱን የሚያምርባቸው ነገር አለ። የማይታመን… እየሳቀች ነበር! ልቦለድ ፀሃፊ ጠብሳ ይሆናል እንግዲህ። “አ……ንተ…?” አለች እየሳቀች… “እንዴት ነሽ?” “ደህና ነህ? አገባህ? ደህና ነህ? አዲስ ጀበና ገዛህ ዎይ?” “አሃ… ያኛውንም አንቺ ነበርሽ እኮ የገዛሽው… ረሳሽ?” “ያ ይሆናል… ደህና ነህ?” “አለሁ” “በቃ ቻው… ስብሰባ አለብኝ… ልሂድ” እየተራመደች ስትርቀኝ… ከተለያየን ጀምሮ ሲከነክነኝ የኖረ ጥያቄ ታወሰኝ…
“እኔ ምልሽ?”
“ወዬ”
አለችና
ተመለሰች…
“ጋሽ ምኒሊክ ወስናቸው ‘የእንጆሪ ፍሬ’ን ያዜመው ለማን ነበር?”
“ለእውነት”
“የምርሽን?”
“በእውነት!”

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Yonas Angesom Kidane
የሆነ ቦታ ላለኸው ፍቅሬ
_______________________
መሽቷል..... ግን አልገፋበትም..... ነፋሱ ስልት እየቀያየረ ዛፎችን ያሽኮረምማል.... ውቧ ጨረቃ የምድርን እርቃን ገላ ትስማለች..... እዛ ማዶ ጥሻው ስር ሁለት ድመቶች ፍቅር ሊሰሩ ይዘጋጃሉ.....ከፊቴ ሁለት ጥንዶች በነፍስም በስጋም ተሳስረው ጎዳናው ላይ ያብሮነት ዳናቸውን ያሳርፋሉ...... ምሽቱ አንዳች ፍቅር ፍቅር የሚሸት ድባብ ሰፍፎበታል..... በዛ መሀል..... እኔ.....ነጭ ልብስ ላይ ጠብ እንዳለች ጥቁር ቀለም እዚህ ድባብ ላይ ይሆንኩ መሰለኝ.. አለ አይደል ቆንጆ ፊት ላይ እንደወጣች ትንሽ ብጉር! .... ሁሉም ሞልቶ እኔ ብቻ ጎድያለው ... ያንገት ሹራቤ አቻውን ፍለጋ ይመስል ካንገቴ ወደኊላ ይሸሻል..... እጆቼ ሌላ እጆች መሀል መገኘት ሲኖባቸው ኪሴ ውስጥ ተደብቀዋል....... አይኔ የማናቸው ማዕድ ላይ ማረፍ እንዳለበት ግራ እንደገባው በቅናትና ምኞት ተኩሎ የበይ ተመልካች ሆኗል.... እግሬ በጎዳናው ላይ የሚያጋጥመውን እንቀፋት ለብቻው እየተጋፈጠ ያዘግማል................ ብቸኛ ነኝ.... ሰዎች የሚዘረጓቸው የዝምድና ገመዶች የተበጠሱብኝ... ከትልቁ ገመድ 'ቤተሰብ' አንስቶ እስከ ጥቃቅኖቹ ክሮች 'አጭብጫቢ' ድረስ!.... የዛሬው እለት ደግሞ ዙሪያ ገባው ፈራጅ እና ምስክር ሆኖ ብቸኝነቴን ይባስ ያጎላበት እለት ነው ሚመስለው...
ጓደኞች ስቀርብ 'ሙድሽ ደስ አይልም አንዳች የሚከብድ ነገር አለሽ' ይሉኛል.... ስቆ ማሳቁን፣ተጫውቶ መጫወቱን፣ ማማለሉንና መሽኮርመሙን ከየት ተምሬ ልቻልበት?( ቻልኩበት! አለች ኩኩ ሰብስቤ) ከናቴ እንዳልል? ... የት ያሳደገቺኝን? ካባቴ? እሱስ መች ነበረ? እድገቴ የማሳደግያ ድርጅት ውስጥ ሆኖ!
ብዙ ግዜ በብቸኝነት ተወግቻለው... የዛሬው ግን ተለየብኝ... ሆድ አስባሰኝ.... የእንባዬን አገልግል በቀላሉ አስፈታኝ,,,,,,, በመሀል ካንድ ባጃጅ አፈትልኮ የወጣው ድምፅ ይባስ ሁኔታዬን አባባሰው....
.
.
"እስኪያገናኘን እንጅ ግዜና ቦታ
ለኔ የምትሆን የሄዋን ዘር ከቶ መች ጠፍታ
አለች አለች አንድ ቦታ
የኔ ስጦታ"
..
..
የወንድሙ ጅራ ዘፈን! ዘፈኑን ከነፍሴ ሰማውት... ከዚ በፊት ሺ ግዜ ሰምቼዋለው እንደዛሬ ግን አላዳመጥኩትም
....

"ለግዜው እንጅ ብሆን ከርታታ
አገኛታለው የማታ ማታ"
፨፨
፨፨
'ለምን የኔ "ለግዜው" ዘልአለም ሆነ? ለምን የኔ "የማታ ማታ" እንደምፅአት ቀን መምጫው ራቀ?' ይጠይቃል አንጎሌ... መልስ ግን .......
፨፨
፨፨
"አታጣድፉኝ ጥድፊያ አሎድም
ለኔ ያሰባት የትም አቴድም"
...
......
ዘፈኑኮ ርቋል..ግን ውስጤ የቀረው ድምፅ በ10እጥፍ ተባዝቶ ይሰማኛል.

"እኔ ቸኩዬ ነው? ወይስ እሱ ዘግይቶ? ማነው ተጠያቂው?? እኔ?.... ስላልታገስኩ?... እሱ?... ስለዘገየ?? ወይስ ፈጣሪ? እንዲ ስሆን እያየ ዝም ስላለ?....." ይጠይቃል ዳግም አንጎሌ..........
"ተረጋጊ! የእግዜር Timing ፍፁም ልክ ነው.. ያባይሆን ኖሮማ ሁሉም ያለግዜው እየሆነ አስቀያሚ ይሆን ነበር!" ይመልሳል ልቤ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ እውነቱን ይሆን??????

... የት ነህ ግን? ምን እየሰራህ ነው? መቼ ነው ምትመጣው?...... መልስ የሌላቸው የዘወትር ጥያቄዎቼ.... እርግጠኝነት የጎደላቸው የሁሌ ሀሳቦቼ.....
ይሄኔኮ አንዲት እንስት አቅፈህ "ዘላለም አብረን ነን" እያልካት ይሆናል.... ምናልባትም የድመቶቹን ድርጊት እየደገምክ ይሆናል.... ህምም! ....................

.... መቼ ነው ግን ውዴ.... ጨረቃን ምስክር አድርገህ እንደማትለየኝ የምትምልልኝ፣ አርፍደህ መጥተህ ይቅርታ የምትጠይቀኝ፣ ናፍቀኸኝ የምታስለቅሰኝ፣ እጄን ከኪሴ አውጥተህ በጆችህ የምታሞቀኝ፣ በጨረቃና ምድር የቀናውትን መልሰህ እነሱኑ የምታስቀናልኝ? .... መቼ ነው ፍቅሬ ሆይ.............................

ተፃፈ By aggie

@wegoch
@wegoch
@paappii
ነገሮችን አልፌ ሳያቸዉ የምቆጭ አይነት ሰዉ አይደለሁም። ታዉቂ የለ? ትላንት
ያደረኩት ነገር በጊዜዉ ልክ ነበር ከሚሉት መሃል ነኝ። ይሄ አቋሜን ልክነት
የነሳሽዉ አንቺ ነሽ። ከትላንት የሚጎድል ወደዛሬ የማይሻገር ነገር ሁሉ በግዴለሽነት የማይታለፍ ነገር እንዳልሆነ ያስተማርሽኝ አንቺ ነሽ። ሃሃ ቢማሩት
ምን ይሰራል? ማርፈድ እንደሚያቆስል ከቆሰሉ በኋላ መረዳት ምን ያደርጋል?
...
የመጀመሪያ ቀን ሳይሽ አበባ በጆሮ ግንድሽና በለስላሳ ፀጉርሽ መሃል
አስቀምጠሽ ነበር። ደስ አልሽኝ። ለአበባ አበባ ምን ይሰራለታል እያልኩ ንብ ሆኜ
ልቀስምሽ ተጠጋሁ። ስቀርብሽ ደስ አልሽኝ። ታሳሺ ነበር። ባለቀለም ቀሚስሽን ለብሰሽ እንደ እንቦሳ እየዘለልሽ ስትመጪ ሳይሽ መልአክ ትመስይኝ ነበር። ፀጉርሽ መሃል ያለ ጠረንሽን አይኔን ከድኜ ሳጣጥም ሲንደሬላን ያጨዉ ልኡል የሆንኩኝ ይመስለኝ ነበር። የነፍስሽ ንፅህና ከሀጫ በረዶም ያስንቃል። ነገሮቼ ሁሉ በነበር ጫፋቸዉ ተዘምዝሟል። ልክ ቁጫጭ መሸፈኛ ዉስጥ እንዳለ በልቶ እንደጨረሰዉ ከረሜላ አለሁ እያልኩ ነዉ የሄድኩብሽ።
...
አንድ ቀን የፃፍሽልኝን አስታወስሽ? ወረቀቱ አርጅቶም ኪሴ ዉስጥ ተቀምጧል። ላንብብልሽ? እንደ ዱሮዉ "ጌትዬ አንብብልኝ!" ብለሽ እጅሽን ጉንጮችሽ ላይ አድርገሽ አይንሽን ባታንከራትችብኝም ላንብብልሽ።
" ... እጆቼን አጥብቀህ ያዘኝ። ጣቶችህ ህይወቴን ማስቀጠያ ክሮቼ ናቸዉ።
ከልቤ ኩልል እያለ የሚሰማዉ የፍቅር ዜማ ለሌላ ሰዉ ትርጉም አልባ ሹክሹክታ ነዉ። አንተን ካልሳሙ እንዴት ሊገባቸዉ ይችላል? ትንፋሽህ በአንገታቸዉ ዙሪያ ካልዋለ እንዴት ሊሰማቸዉ ይችላል?? ...አይኖችህን ሳይ የሚሰማኝ ምትሃት ልዩ ነዉ። እ አለ አይደል? ፈጣሪ አሰልፎ አይን ሲያድል አንተን ሲያይ ቆይ ላንተ ሌላ አለ። ና ተከተለኝ ብሎ ያዳላልህ ይመስለኛል። ሁሌም እደነግጣለሁ። ሃሃ አያስቅም ሀሳቤ? ፈጣሪ ሲያዳላ ሃሃ... በፀጉሬ መሃል እጅህ ሲርመሰመስ የት እንዳለሁ እዘነጋለሁ። ጣቶችህ ነገር ይፈልጉኛል። መንሳፈፍ ስጀምር ትሄዳለህ። ይ ትሸሸኛለህ። ለምን ሩቅ ትሄዳለህ? ለምን ዝም ብሎ አትስመኝም? ... አንተ የተረት ከተማዬ ልኡል ነህ። የተረት ከተማ ነዋሪዎች ደግሞ እ ልክ እንደ መልአክ አይታዩም ፤ አይዳሰሱም ፤ ...አይሳሙም። ሁሌም እወድሃለሁ።"
እንደዚህ ያልሽን እያነበብኩ ነዉ የምተነፍሰዉ። ፀሃይ ጨረቃም ምንም ናቸዉ ካንቺ ጋር ቀረ ዉበታቸዉ ባንቺ ያልተገራ ምን ተገኘ ፍቅርሽ ሲነካዉ ያልተቃኘ ነገሮች በአሉበት ይቀጥላሉ። ንፅህና ስርአት በሚሉት ኩል ይኳላል እንጂ ነገር ሁሉ መስመሩን ሳይለቅ ይከናወናል። አገባሁ። ወለድኩ። ልጄን በስምሽ ሰይሜ አይኖቿ መሃል ንፅህናሽን የምፈልግ ብኩን ሆኛለሁ እንጂ ደህና ነህ ወይ ካልሽኝ በሰዎች መለኪያ ደህና ነኝ። ትናፍቂኛለሽ። ፀጉርሽ መሃል ያለዉ ፤ አይኔን ከድኜ የማጣጥመዉ ጠረንሽ ሌላ ቦታ ላገኘዉ አሌቻልኩምና ይናፍቀኛል። አፉ አዉጥቼ አልናገር እንጂ የነገሮች ሁሉ ሚዛኔ አንቺ ነሽ። ልክ ነህ እንዲሉኝ የምፈልገዉ ባንቺ ተመዝኜ ነዉ።
ደህና ነኝ...!

@wegoch
@wegoch
@paappii
#Ruth Habte Mariyam
*Israel Ad fernando

Love has no boundaries
............. ደፂ በኢትዮጵያዊያን ብር ሊዝናና ወጀ ቻይና አቀና። ቻይናን ቀኑን
ሙሉ እየዞረ ይቺን ሀገር ከጀሌዎቹ ጋር አስተዳድሮዋት ቢሆን ኖሮ እንዴት
እንደሚግጣት እያሰበ ምራቁን ሲውጥ ዋለ። ሲዞር ውሎ ስለራበውም
ጓንዡ ከምትባል የቻይና ግዛት ከሚገኙ ምግብ ቤቶች ውስጥ ወደ አንዱ
ገባ። ገብቶም ምግብ ከሜኑው ላይ በግምት አዘዘ። የመጣለትም locust
ነበር ያመጣችለት አስተናጋጅ ቻይናዊ በጣም ውብ ነበረች። ደፂም ምንም
ለመብላት ቢፀየፍ አዳማዊ ባህሪው ተነስቶበት ለፍቅሯ ሲል በላ። ከስራ
ስትወጣ ጠብቆ አዋራት። ፍቅረኛው ከሆነች የራሷ ሬስቱራንት
እንደሚከፍትላት እና ለስራዋም ኢትዮጵያ ገበሬውን ያስቸገሩ አምበጦችን
እንደሚያመጣለት ነግሮ በጥቅም አሰራት። እስዋም በማድረግ አቅሙ እና
የትግል ታሪኩን ሰምታ ተማረከችለት።


ደፂ ደስታ በደስታ ሆነ የጥላሁን ገሰሰን "እሩቅ ምስራቅ ሳለሁ ጃፓኗን
ወድጄ..." የሚለውን ዘፈን ለ አብርሀም ገ/መድህን ከፍሎ "...ቻይናዋን
ወድጄ..." የሚል cover አሰርቶ ሌት ከቀን እሱን መስማት ሆነ ስራው።

ከእለታት አንድ ከወደ ቻይና ስልክ ተደውሎ በወቅቱ ከዶሮ በተነሳ ወረርሽኝ
ምክንያት እጮኛው እንዳረፈች ተነገረው። ደፂም ተሰበረ። ካፅናናኝ ብሎ
ለጌታቸው ደውሎ የተፈጠረውን አጫወተው ጌች "ድሮስ የቻይና እቃ
አይበረክትም ብሎ" አላገጠበት... ደፂ ሰው ለማሰር ካዘጋጀው ጨለማ
ክፍል ውስጥ እራሱ ገብቶበት ለብዙ ቀን በዚያ ቆየ።
:
:
ከዚ ሁሉ ጊዜ በኋላ Covid ከወደ ቻይና ተነስቶ ኢትዮጵያ ገባ። ህዝቡም
በበሽታው ተሸብሮ ጥንቃቄ አበዛ ከጊዜያት በኋላ ግን ጥንቃቄ ማድረጉን
አቋመ። ግን ከቻይና የተነሳ ወረርሽኝ ሰው እንደሚገል በሚወዳት ፍቅረኛው
ያየው ደፂ ሳይዘናጋ ማስክ እና ጉዋንቱን በሚገባ እስከ አሁን ያረጋል.....

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ሰው የሚባል የለኝም ሲል "እኔ እያለሁ ብዬ ጓደኛ ሆንኩት። እያለቀሰ.. እየረገመ
...እያማ... እየጮሀ ..ዝም እያለ እየሳቀ ሁሉን አወራኝ። አልታዘብኩትም። ሁሉም
ላይ አንተ ልክ ነህ አላልኩትም። ልክ አይደለህምም አልወጣኝም። ነው ያልኩትን አወራሁ። ረሳ ተፅናና ማማረር ተወ "ነገ መልካም ቀን ነው ይል ጀመረ"
ተመስገን አልኩ። እንደ ጥሪው ደግሞ እንዳመጣጤ መገናኘታችን ሰመረ አልኩ። ደግሞ ለህይወት አንድ ጓደኛ አገኘሁ አልኩ። አሳቀኝ ተረዳኝ አሰበልኝ ደስ አለኝ።
.
ቆየን ቆየን ሀሜቱም ንዴቱም አለቀ ስለራሳችን ማውራት ያዝን እንዲህ
ብታረገው። እንዲ ብታደርግ። ይሔ ልብስ ያምርብሀል። ይሔ ጫማሽ ያምረኛል። ዛሬ ዘንጠሀል። ዘንጠሻል ....ግላዊነት የነገሰባቸው ሙገሳ አድናቆት ከላይ ጀመረ።
.
ማሰብ ጀመርኩ ወዴት እየሔድን ነው ? ያስብ ገባ። ፍቅረኛዬ ባረጋትስ? ከድሮ
ቦታችን ካፌ ተቀየረ ከድሮ በላይ አብረን ረጅም ሰአት እንቆያለን። የረባ ነገር
አይወራም። ድንገት ዝም ዝም ስንባባል ሁለታችንም በልቦናችን "ፍቅረኛዬ ቢሆንስ?" አይን ላይን ስንጋጭ መሽኮርመም የመድሀኒአለም ያለህ !
.
አንድ ቀን ይመችሽ እንደሁ ላውራሽ "ፍቅር ይዞኛል አለ" ክው አልኩ። ማን
ይረዳኛል እንዳንቺ? ማን ሰው አለኝ ? ጓደኛዬም ሚስቴም ሁኚ ሲል .. ቀድሞ
በልቤ ያወራሁትን ያወቀብኝ ይመስል አፈርኩ። ደነገጥኩ። ዝም ዝም እንሒድ
እሺ እንሒድ ወደቤቴ ሸኘኝ የመጨረሻዋ ቻው ላይ እወድሻለሁ ጨመረበት! እንዴት እንደሆነ አላቅም ያን ቀን አንድ ሰው አጣሁ። ያን ቀን አንድ ጓደኛ አጣ !
.
.
እወድሻለሁ ያለያያል ?! እወድሻለሁ አለያየን !

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Betelhem Tachbel
Forwarded from Ribka Sisay
ሊድ እና ሌንስ ፩.pdf
18.4 MB
ሊድ እና ሌንስ ፩ ................. በሚታየኝ እና ባስቀረሁት፤
በሚገባኝ እና ባሰፈርኩት፤
ክስተት እና ምስጠት መጠን... ................ @getem @seiloch @wegoch @ribkiphoto
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል - 1

ሁሉንም ትታቸው ወደ ውጪ ወጣች የገለጠችውን መጽሀፍ ቅዱስ በቀዩ ክር ምልክት ሳታደርግ ጠረቀመችውው ከአጠገቧ ያለውን የውሀ ጉርጓድ ተመለከተች እንደምትፈልጋት ሆናላታለች ክብ አይኖቿ ወደ ሰማዩ ተመለከቱ በጨረቃ ብርሀን አይኖቿም አበሩ ውስጧ የሆነ ነገር ሲብላላ ይሰማታል ደሟ ሲራወጥ ልቧም ፍጥነቷን ጨምራለች
በዚ ምሽት ጨረቃ ይበልጥ እንደምታግዛት አምናለች ሰማዩ ላይ ምንም ሊጋርዳት የሚችል ደመና አይታያትም ብርሀኗን ሊከልላት በአጠገቧ የሚያንዣብብ ነገር ካለ ጠርጋ ለማፅዳት ዝግጁ ነት በውስጧ ጨረቃ ነኝ ብርሀኔን ከመስጠት ያሰብኩትን ከማድረግ የሚያግደኝ ነገር የለም ቀዝቃዛውን አየር ማግ አደረገችው ብዙ ኮኮቦች ከሰማዩ ታዩት ዘወር ብላ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ጠራቻቸው ከኋላዋ ተኮለኮሉ አሁን እንደ ሰማዩ እኛም እናምራለን በውስጧ ምታወራውን ነገር ሰማዩም ሚሰማው ይመስል ምሽቱ ይበልጥ አማረ ሙሉ ጨረቃ ሙሉ ልብ ሙሉ ሰማይ ሙሉ ብርሀን ከፀጥታው የተነሳ የሁሉም ልብ ምት ይሰማል አንድ አይነት ምት አንድ አይነት ፍጥነት ቅዝቃዜው ሚያስቆማቸው አይመስልም አይናቸው ከሰማዩ ፈጧል ኮኮቦች ኮኮብ ያያሉ ጨረቃም ጨረቃን ታያለች አይኗን ነቅላ የዘጋችውን መጽሀፍ ቅዱስ ከፈተች አማተበች አይኗን ጨፍና እጇን ወደ ኪሷ ከታ ከእጇ ማይጠፋውን ሳንቲም አወጣች አይኗን ገልጣ መጽሀፉን ታነብ ጀመረ
ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የላንም የለውም (ዮሐ15-13)
ይህን ሰማይ ካለጨረቃ አስቡት ጨረቃም ኖራ ካለ ኮኮብ አስቡት ይጠባበቃሉ አብረው ይታያሉ ጨረቃ የሆነ ነገር ቢደርስባት ልጆቿ ከዋክብት ዝም አይሉም ኮኮቦችም አንድ ነገር ቢደርስባቸው እናት ጨረቃ ዝም አትልም አለም ላይ ግዑዝ የተባለው ነገር ህይወት ላለው አካል ህይወት አይሰጥም ህይወት ያለውም ለግዑዙ ህይወት ሊሆን አይችልም ግዑዝ ለግዑዝ ህይወትም ከህይወት ያምራል እኛም ከእኛ ሌላ ማንም የለንም ከእናንተ አንድ ከሚጎል የኔ ህይወት ይጉደል የኔ ህይወትም ከሚጎድል የእናንተ ህይወት ይጉደል መጽሀፍ ቅዱሱ ተዘጋ አሜን የሚል ድምፅ አስተጋባ

ህይወትስ ወዴት ናት ሰማይስ ከየት ነው
ደም ከውሀ አለ ጨለማ ብርሀን ነው
ሚያግደን ምድነው ካሰብነው ጥልቅ ህይወት
ወደፊት መጓዝ ነው በጨረቃ ምሽት

ድምፃቸው ከነጎድጓድ ያስደነግጣል ዜማው ያስፈራል አንድ ከመሆኑ የተነሳ አንድ ሰው የሚዘምረው ይመስላል ጥቁር ባርኔጣቸውን አስተካከሉ በተሰበሰቡበት የውሀ ጉርጓድ ውስጥ የጨረቃዋን ነፀብራቅ በውሀው ውስጥ ይመለከታሉ መጽሀፍ ቅዱሳቸውን ከሸጎጡበት ቦርሳ ውስጥ አወጡ ሁሉም በአንድ ድምፅ
ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም (ዮሐ15-13) አሜን
ድምፃቸው ይበልጥ አስተጋባ መጽሀፍ ቅዱሱ ተዘጋ ከተሰበሰቡበት የውሀ ጉርጓድ በመዳፋቸው እጠለቁ ጠጡ በደተርታ ደረጃውን መውረድ ጀመሩ የጊቢው ፀጥታ ያስፈራል ተቃጥሎ ያለቀው እንጨት ጭስ ወደሰማይ ይወጣል የመኪና ሞተር ድምፅ ተሰማ ሁሌ ስህተት እነርሱ ጋር የለም መንገዱን ተያይዘውታል ጥቁሩ መኪና ቀዝቃዛውን አየር መቅደድ ይዟል መኪናው ውስጥ ያለው ፀጥታ ያስደነግጣል የምሽቱ ፀሎት ይበልጥ ግርማ አላብሷቸዋል አነስ ያለች የጃዝ ምት ያላት ዜማ ከመኪናው ትሰማለች
ሹፌሩ ቦታውን አውቋል ቅድም ያበራት የነበረችው መኪና አሁን በዝግታ የንቀሳቅሳት ጀምሯል
መቆሚያውን ይቃኛል
ከመኪናው የነበሩት ሰዎች አሁን የሉም ከህንፃው ውስጥ የአደጋ ጊዜ አላርም ድምፅ መጮህ ጀምሯል
ታላቁ የከተማው ባንክ የሚል ትልቅ ፅሁፍ ከህንፃው ላይ ይነበባል የጃዝ ምት ያለው ዜማ አልቆ ወደ ኦፔራ የተጠጋ ዜማ ከመኪናው መሰማት ጀምሯል
ጨለማው ዜማው የአላርሙ ድምፅ ተጨምሮ ምሽቱ አስፈሪ ሆኑዋል
ከህንፃው የሚጮኸው አላርማን ከመኪናው የሚወጣው ዜማ የገጠመ ይመስላል ብዙ ፍጥነቶች
ንዳው ከሹፌሪ ጎን ድምፅ ተሰማ
በጣቶቿ የዜማውን ድምፅ ከፍ አደረገችው

ህይወትስ ወዴት ናት ሰማዩስ ከየት ነው
ደም ከውሀ አለ ጨለማ ብርሀን ነው

ይቀጥላል.......
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ሚስጥር_ኪስ
~
~
የፈዘዘ ጂንስ ሱሪ አነሳሁ... ለምን ዘንጣለሁ? ለቅሶ ቤት እየሄድኩ መሆኔን
ረሳሁት? መልበስ ግን አማረኝ። 'ቋ' ብዬ ብሄድ... እያሱ ነበር 'ቋ' ብለሽ
ነይ የሚለኝ። አዝኜም የሚያምርብኝ አይነት ብሆን... በስህተት ያማረብኝና
ልረዳው የማልችል ብመስል። ለበስኩት... ያምራል! ኢያሱ ይወደው ነበር
ይሄንን ሱሪ "ያ ነገር ተጨነቀኮ" ይለኛል። መስታወቴ ፊት ዞሬ ነገሬን
አየሁት ተጨንቋል። ኪሱ ጋር የእያሱ ሰፊ እጅ ስንቴ ጠብሶኛል...
የሚያመኝም አይመስለውምኮ ጧ! ያረገውና የጅል ፈገግታ ፈገግ ይላል።
ሲስቅ የታች ከንፈሩ ከላይኞቹ ጥርሶች ስር ስለሚወሸቁ ጅል
ያስመስለዋል። የከንፈር ቀለሜን አነሳሁ... ስቀባው አማረ ግን ደመቀ...
እንዲማ ሆኜ ብሄድ “ምን ልሁን ነው የምትለው?“ ነው የሚሉኝ... በጣቴ
ጠርጌ አደበዘዝኩት። ያልታቀደበት ማማር እስኪመስልልኝ ተጨነኩ...
ቢሆንልኝ ኢያሱ እንደሚወደው አይነት ሆኜ ብቀብረው። ከመቃብር ሳጥኑ
ውስጥ የሞኝ ሳቁን ሲስቅ አስቤው አሳዘነኝ።
~
~
ጫማዬ ያንቀራፍፈኛል... የተረከዜ ሹል ጠጠር መሀል እየተወሸቀ የዝነጣ
መንገዳገድ ያንገዳግደኛል። የተጠየፍኩ አይነት አረማመድ ያራምደኛል።
ቤቱ አልጠፋኝም። ከሩቅ ነው ቤቱን የጠቆመኝ ቆርቆሮዋም ሰፈሩን።
በዚሁ ሰፈር በእግሬ እያለፍኩ ነበር ... ያኔ ከተገናኘን ሁለት ወር ቢሆነን
ነው። ክላክስ ሰምቼ ስዞር ኢያሱ ነው። ሞኝ የሚያስመስለውን ፈገግታ ፊቱ
ላይ ዘርቶ ሲጠራኝ። ከሌሎቹ እሱ ይቀለኛል ቢያንስ የሚያወራው እውነት
ነው። ለእውነቱ አያሳንሰኝም... ከእኔ ጋር መሆኑን ሚስቱ ብትሰማ አንዴም
ሳይከራከራት ያምናል። ሚስትና ልጆች እንዳሉት አልደበቀኝም...
የተሰማውን ይናገራል። ውሸት አያውቅም... የሚደብቀው እውነት ነው
ያለው ኢያሱ።
"ነይ ግቢ"
"አንተ ጉደኛ ምን ታረጋለህ እዚ?"
"ቤቴ እኮ ያውና ጥቁር ብረት በር ይታይሻል?"
"እእእ"
"እሱ ነው። "
"ደፋር ነህ ባክህ። አሁን ለሚስትህ ቤትህ መጥቼ ጉድህን ብነግራትስ?"
"ምን ይጠቅምሻል?"
"አንተ ብር እንድትሰጠኝ ለማስገደድ"
"ስጠኝ ብለሽ አትጠይቂኝም ምን እሷ ጋር ያደርሳል?"
"እምቢ የለኝም ብትልስ"
"ቤቴም መጥተሽ ስትናገሪ 'እምቢ የለኝም' ነዋ የምልሽ"
ጥቁር ብረት በር ያለበት ቤት ውስጥ ድንኳን አለ... ከድንኳኑ የሚወጣ
"ህምምምምምምም" የሚል ድምፅ ይሰማኛል። በሩ ሙሉ ለሙሉ
ተከፍቷል... ኢያሱ ሲወጣ አልቃሽ እንዲገባ ይመስላል። ከሌሎች
ሀዘንተኞች ጋር ተቀላቅዬ ገባሁ... አብሬያቸው ተቀመጥኩ። ቅድም
ያልተሰማኝ ሀዘን አሁን ሆዴ ጋር አለ። "እያሱዬ" ብዬ ልጩህ? ሚስቱና
ልጆቹ ከሩቅ ጋቢ ለብሰው ፈዘዋል... አካባቢያቸው ቀና ያለ ሰው
አይታይም... ንግግር የለም። ሁሉም የሚጨንቅ መወዛወዝ በትንሹ
ይወዛወዛሉ። አውቀውት አይመስልም... የኢያሱ ጉድለት የፈጠረው ሚዛን
መሳት ይሆናል የሚያወዛውዛቸው። ሚስቱ ወፍራም ናት (እንኳን የታባቷ)
አዝናለች (ማዘኗ አናደደኝ)። ሰው ከቧታል... ብቸኛው እንደ ሰው የሚያየኝ
የነበረውን ኢያሱን ስትካፈለኝ የኖረች ዘጠዘጥ ነች። እሷም ጫጩቶቿም
ደበሩኝ... ከእነሱ በኋላ ባውቀውም በማፍቀር ህግ መቅደምና መዘግየት
የለም።
ከአጠገቤ እየቆረጠ የሚያየኝ ወጣት አለ... ወደ እኔ ዞሮ መልኩን ሳይጎዳ
ይነፋረቃል። እያለቀሰ እንኳን አይኑ ታፋዬ ላይ ይንከራተታል።
~
~
"ዝገኝ እንጂ?" ድግስ የሚጋብዝ ነው የሚመስለው። በትሪ የሚታደለው
ንፍሮ የመግባቢያ ርዕስ ስለሆነው ደስ ብሎታል።
"እሺ" ቆነጠርኩ
"ጋሼን ታውቂያቸዋለሽ?" አዎ የዚን ጅንስ ቂጥ በጥፊ ያሳሱት እሳቸው
ነበሩ ብለው ይገባዋል? በሆነ እግዜርኛ መመርመሪያ ቢፈተሽ ጉንጬ ላይ
ድንክ ፂሞቻቸው ቧጭረውኛል ብለው ቀባጣሪ ይለኛል። መስማት
አይደለም ማውራት ነው የፈለገው... ሰማዋለሁ ይሄንን ጩጬ።
"በአይን አዎ"
"እኔን ከልጅነቴ ያውቁኛል... ብዙ ተምሬያለሁ ከእሳቸው" ያላስተማሩህ
ስንት ቆንጆ ነውር አለ መሰለህ...
"ትግባባቸው ነበር?"
"በጣም! እህቴ ናት እሷ" ወደ ኢያሱ ሚስት ጠቆመኝ። የዚች ሴትዮ
ወንዶች እኔ አካባቢ ምን አይተዋል?
"ኦኬ"
"እንዴት ያሉ ሰው መሰሉሽ..." ለምን አይተወኝም? ኢያሱ ሲወራለት
አያምርበትም። የጓዳ ገድሉ አይስብም... ምኑም እሱን አይመስልም። ወይ
ቤተሰቡ ጋር ራሱን አይደለም ወይ የሞተው እያሱ ሌላ ነው። ይፈተሽ
ፈገግታው... ጅልነት ካለበት ራሱ ነው። ምን ይለኛል ይሄ?
~
~
ይሄ ልጅ ያወራልኝን እያሱ አላውቀውም። ሲጀመር ጋሼ ነው 'ሚለው...
ጋሼ ደግሞ እንዳወራልኝ ከሆነ የሰፈር አለጥላጭ ወጥ ነገር ነው። ኢያሱ
በትንፋሽ ቀለም የሰራውን መልኩን ይቦጫጭረዋል ይሄ ነፍስ ያላወቀ
ጩጬ። በእርሱ ቤት ጠበሳ ነው... ሊጎርር ነው... መቃብር ሀውልት ጋር
ሄዶ ደረስኩልህ ጋሼ ብሎ ሊሟዘዝ ነው። ከምንም በላይ የኢያሱን የቆሸሸ
ቁንጅና ሊያበላሽ ሳይታወቀው እየተሯሯጠ ነው። የኢያሱን መልክ ልቤ
ውስጥ ፈልገዋለሁ... ይሄ ፈልፈላ ባወራልኝ ቁጥር ደግሞ እየተጠራጠርኩ
ነው። ብወጣስ? ወጣሁ...
አይከተለኝም አውቃለሁ። ሰው ያፍራል...
~
"ለትንሽ ቀብሬህ ነበርኮ" እምባዬ ተቀምሞ እንደተዘጋጀ ነገር ፍስስስ አለ።
በጣቴ ጠርጌው አየሁት... ጣቴ ላይ ከነበረው ከንፈር ቀለም ጋር ተዋህዶ
ቀጭን ደም ይመስላል።
(በረከት ታደሰ)

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል - 2

ከተሰቀለው ትልቅ ስክሪን ውስጥ የሚታዩት ፎቶዎች ባለፉት ሶስት ወራት ውሰጥ በተመሳሳይ ቀን ከተሰረቁት ትላልቅ ድርጅቶችና ባንኮች ውስጥ ተቀምጠው የተገኙት የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ተመሳሳይ የሆኑት ሳንቲሞች ናቸው መጽሀፍ ቅዱሶቹን ከመመርመሩ የተነሳ ሰባኪ ሊሆን ምንም አልቀረውም ከሳንቲሙ ላይ ያለው ምስል ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ከስሩ የራስ ቅል ያለው ምስል ይዟል ሲገለብጠው ጨረቃ የሚል ፅሁፍ ታትሞበታል
በህይወቱ እንዲህ አይነት ውስብስብ የሆነ ነገር አጋጥሞት አያውቅም ከትላልቅ ባንኮች ውስጥ ገንዘብ እንጂ ማስታወሻና ቁርጥራጭ ወረቀቶች ጠፉ የሚል ዜና የሰማው ካለፈው ሶስት ወር ጀምሮ ነው ይሄን ያህል ገንዘብ ይሄን ያህል ሀብት የሚል መረጃ አልደረሰውም ዛሬም ከተደወለለት ሰአት አንስቶ ስለጠፋው ማስታወሻ ነው እየተነገረው ያለው የባንኩ ሀላፊዎች ሚሊየን ብር ቢጠፋ ከማስታወሻው ጋር ሊወዳድር እንደማይችል አስረግጠው ነግረውታል ከባንኩ ትልቁ ካዝና ውስጥ አንድ ማስታወሻ ጠፍቷል ካዝና ቁጥር 18 በቀን 18 ተሰረቋል የሚል ማስታወሻ ፃፈ እራሱ ሲዞር ይሰማዋል ዛሬም ምንም መረጃ የለም የተገኘው አንድ ሳንቲምና ተገልጦ የተቀመጠ መጽሀፍ ቅዱስ ብቻ ነው
ነፍሴ ሰላምን ከሚጠላው ጋር ብዙ ጊዜ ኖራለች
መዝ120-6
እስከዛሬ ተቀምጠው የተገኙትን ጥቅሶች መዝግቦ ይዟቸዋል የዛሬውንም መዝግቦ ያዘ የተቀመጠውን መጽሀፍ ቅዱስ በያዘው ከረጢት ውስጥ ጨመረው
ከሀሳቡ ብንን አለ ከፊቱ ከሚገኘው ትልቅ ስክሪን ላይ ቅድም ፅፎ የያዘው ጥቅስ ተቀምጧል
ከአቅማችን በላይ ስለሆነ በመጽሀፍ ቅዱስ ጥናትና በተለያዩ ምስጢራዊ ምልክቶች ላይ ጥናት ካደረገች ሴት ጋር ላስተዋውቃችሁ በጣም ትረዳናለች በሩ እስኪከፈት ድረስ አይኑን ከእስክሪኑ ላይ አልነቀለም ጥቁር ባርኔጣ ያደረገች ሴት ከበሩ ወደ ውስጥ ግርማ ባለው እርምጃ መግባት ጀመረች እጇ ላይ አንድ መጽሀፍ ቅዱስ ይታያል ከመጽሀፉ ላይ የተንጠለጠለው ቀይ ክር ወደ ታች ወርዷል በክፍሉ የተሰበሰበው ሰው አይኑን ከአዲሷ ሴት ተክሏል ውብ ናት እድሜዋ ወደ 50ዎቹ ይጠጋል ድምጿን ሞረድ አደረጋ እራሷን አስተዋወቀች እጇን ልካ ባርኔጣዋን አወለቀች ከጀርባዋ የሚያበራው ስክሪን ፀጉሯን ይበልጥ አሳመረው #ሶልያና እባላለሁ ከዚህ በሁዋላ ከምርመራው ቡድን ጋር አብረን እንሰራለን ድምጿ ይመስጣል አፉን የከፈተም አለ ባርኔጣዋን መልሳ አድርጋ ከክፍሉ ወጣች ሁሉም እየተነሳ ተከተላት
ክሩን ከዳዊት መዝሙር ምዕ120 ብታደርጊው ሳይሻል አይቀርም ከኋላ የሚያስቆም ድምፅ ሰማች ቁጥር ስድስትን እረስተሀል አለችው ፍጥነቷ ገርሞታል አብረሽን ስለምሰሪ ደስ ብሎኛል በጣም ታስፈልጊናለሽ እጁን ዘረጋላት ወንጌል አስተማሪ አይደለሁም እንጂ አነስ ያለች ፈገግታ አሳይታ ጨበጠችው ጴጥሮስ እባላለሁ ቆንጆ ስም አለህ ባክህ ልትለየው ፈልጋለች ቡና ወይስ ያለመስማማቷን ገለፀችለት ሊያስገድዳት አየልፈለገም ጠጋ ብሎ ደሞ የሳንቲም መርማሪ እንዳያመጡብኝ የምፀት ሳቅ ስቆ ጥሏት ሄደ ተረጋግታ ተራመደች

ሁሉም ከአስፈሪው ክፍል ተሰብስበው በመስታወት ውስጥ ከተቀመጠው ማስታወሻ ላይ አፍጥጠዋል የእናታቸው መዘግየት አሳስቧቸዋል ከክፍሉ የሚወጣው ዜማ አስፈሪ ነው
ህይወትስ ወዴት ናት ሰማይስ ከየት ነው
ደም ከውሀ አለ ጨለማ ብርሀን ነው
ሚያግደን ምድነው ካሰብነው ጥልቅ ህይወት
ወደፊት መጓዝ ነው በጨረቃ ምሽት
የሚያዩት ማስታወሻ የበገና መዝሙር ደብተር ይላል ጠርዙ ያበራል ማንም ሊነካው አልፈቀደም ካዠከቸነገራቸው ትዕዛዝ ሊወጡ አይቹልም ቆመው መጠበቅ ይዘዋል ሌሊቱ ለመንጋት እያዘገመ ነው ጨረቃ አሁንም አለች

ይቀጥላል......
ብላቴናው በጨረቃ ምሸት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ዳዊት በበገ
_____________

የሥራ ቀጠሮዬ ጋ ለመድረስ እየተጣደፍኩ ነው። ከጠዋቱ 2:30 ከመሆኑ በፊት መድረስ አለብኝ። አንድ "እብድ" (ድርጊቱ ለዚህ መገለጫ ይመጥናል ብዬ ነው) ከፊቴ ይታየኛል። አላፊ አግዳሚውን በድንጋይ እያስፈራራና በስድብ እያከናነበ ነው። ማንም የሚናገረው የለም። ጥቂቶች ከሩቁ መንገድ እየቀየሩ ያፉታል። ጥቃት ያደርስብኛል የሚል ስጋት አልነበረኝም። ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን ምንም አይነት ስሜት ሳላሳይና መንገዴን ሳልለቅ አልፌያለሁ።
ዛሬም ላደርግ የሞከርኩት ይህንኑ ነበር።
አጠገቡ ልደርስ አምስት እርምጃዎች ያክል ሲቀረኝ የዚህ ሰው መላ አትኩሮት
እኔ ላይ እንዳረፈ ታወቀኝ። እንደዚህ አይነት አትኩሮት በቦታው ላይ ሆኖ
ለሚረዳው ይረዝማል። ስድስተኛው የስሜት ህዋሴ ችግር እንዳለ ቢጠቁመኝም የመፍራትም ሆነ የማወላወል ስሜቴን ግን ዋጥ አድርጌው ነበርኩ። አጠገቡ ለመድረስ አንድ ርምጃ ሲቀረኝ መንገዱን በክብር ለቆ አሳለፈኝ። ይሆናል ብዬ ያልጠበኩት እና ከዚህ ቀደምም ሆኖ የማያውቅ ክስተት ነበር። አልፌው ሁለት ሶስት ርምጃ እንዳለፍኩ ደግሞ ስሜ ተጠራ። የጠራኝ ራሱ ነበር። ከስሜ በፊት ግን አንድ ተጨማሪ ቃል ነበረው። ደግሞ እስኪጠራኝ ድረስ ነው መሰል ርምጃዬን ልገታ አልፈለኩም። ደግሞ ጠራኝ፦
"ቲቸር ኄኖክ!" አሁን ግን ቆምኩ። ዞርኩ። በእጁ ይዞት የነበረው ድንጋይ አሁን እጁ ላይ የለም። ያ የእብደት ገጽታም እንዲሁ። እየቀረበኝ ሲመጣ ፊቱ ላይ የሚነበበው መራራ እውነት በላይ ታላቅ ትህትና ተስሎበት አየሁ። ይህን መልክ አውቀዋለሁ። ባስተማሪነት ዘመኔ ተማሪዬ ነበር። በተማረበት የሚሰራ ማነው?! …እኛው! ባስተማረበት የማይሰራም እኛው…"ቲቸር አወከኝ?"
እንዳወኩት ጭንቅላቴን ከፍና ዝቅ በማድረግ ገለፅኩለት።
✸✲✵
አውቄዋለሁ። የማወቅ መስመር ያገናኘን በመደበኛው የትምህርት መድረክ ላይ ነበር። እንዲህ አይነቱ እውቀት በህይወት መንገድ ይገኛል።
ሰው ታውቃለህ?
ሰው ታውቂያለሽ?
ሰው አውቃችሁ ታውቃላችሁ ያወቃችሁትስ ያውቃችኋል?!
ያወቃችሁት ሰው ከሆነ ልታደርጉለት የምትሹትን ነው የምታደርጉት? ወይስ እሱ እንድታደርጉለት የሚሻውን?! እኮ ምንድነው የምታደርጉት?!

ለሠላምታ የዘረጋሁለትን እጄን በሁለት እጁ እንደጨበጠ ነበር እንዲህ ያለኝ፦
"ይገርምሃል ቲቸር፣ 'ንቡር ጠቃሽ' ዘይቤ ያስተማርከኝ ዛሬም ድረስ ይገርመኝል።
በተለይ ያቺ ግጥም!! 'የዳዊት ወንጭፍ' ምናምን የምትለዋ! … እንዳልገባኝ ግን
ታውቃለህ?!"

አላውቅም! እኔ የማውቀው ያስተማሩኝን መሸምደዴና የሸመደድኩትን ማስተማሬን ነበር።
አላውቅም!
ግጥሟ "የቴዎድሮስ ስንብት ከመቅደላ" በተሰኘው የብላቴን ጌታ ጸጋዬ ገብረ
መድህን ግጥም ላይ ለዘይቤው መገለጫ ይሆን ዘንድ ተመዞ የወጣ አፄ
ቴዎድሮስን ከቀደምቱ ዳዊት ታሪክ ያጣቀሰበት ክፍል እንደሆነ ግን ርግጠኛ
ነበርኩ።
"ዳዊት በበገና እንዲያ
ማልቀስ ማላዘን መያዙ
ይህ የጎሊያድ ውላጅ
ቢበዛበት ነው መዘዙ
ምንጩ እንደ አሸን
እየፈላ አገር ምድሩን ማንቀዙ
ቸግሮት ነው መጋፈጡ
ከስንቱ መወናጨፉ
በባላንጣው ሳቢያ ምክንያት
የራሱን ወገን ማርገፉ…"

የበቀቀን ዘይቤ።
ዛሬ እሱ ነው ንቡር ተጠቃሹ። እንደዳዊት የራስን ወገን አርግፎ በፀፀት እያነቡ በገና መደርደር…

@wegoch
@wegoch
@paappii

#ኄኖክ ሥጦታው ናሁሰናይ
ዕውነቱንም ፡ አውቄያለሁ ፡ ሀቁን ፡ ሳይሆን!

°°°Elfarus°°°

አይዞኝ ፡ ጀግና ፡ ቢወድቅ ፡ ጀግና ፡ ካላገዘው ፡ ምኑ ፡ ጀግና ፡ ነው?
ከስሜትሽ ፡ ስትነቂ ፣ እውቀትን ፡ ስታረግፊ ፣ ማንነትሽን ፡ ስትይዢ ፣
እውነትን ፡ ትገዛታለህ ፡ አትሸጣትም ፡ ላይ ፡ ስትደርሺ ፡ የዛኔ ፡ ሞቼም ፡
ቢሆን ፡ ሁሌም ፡ አጠገብሽ ፡ ነኝ ፡ አሁንም ፡ ቢሆን ፡ በቅርበት ፡ አይሻለው
፡ የኔን ፡ ጥበቃ ፡ በቸርነቱ ፡ ለአንቺ ፡ እንዲደርስ ፡ ሁሌም ፡ እማፀነዋለሁ።
"አፈቅርሃለው ፡ ይህም ፡ እስከዛሬ ፡ ከነገርኩ ፡ ሁሉ ፡ ይበልጣል።"
ስለወደቅሽም ፡ አይክፋሽ ፡ ሁሉንም ፡ ነገር ፡ አልደበኩሽምና። ብርታቴን ፡
እንደ ፡ ትምህርት ፡ ቤት ፡ ውድቀቴን ፡ እንደ ፡ ትምህርት ፡ እንድትማሪበት
፡ ነበር ፡ ሁሉን ፡ በየፈርጁ ፡ መንገሬ ፡ ለስጋሽ ፡ ሳይሆን ፡ ለአንድ ፡
ለነፍስሽ ፡ ነበር።
በጊዜ ፡ ሂደት ፡ የማይደረስበት ፤ የማይሰለችም ፡ ነገር ፡ የለም!
የሆነው ፡ ሁሉ ፡ የሚሆን ፡ ነው ፤ የተደረገው ፡ ሁሉ ፡ የሚደረግ ፡ ነው!
ዐዲስ ፡ ነገር ፡ የለም!
ትላንትናን ፡ ያየ ፡ ስለነገ ፡ ያውቃል ፡ ታሪክን ፡ ያስተዋለ ፡ ከጠቢብ ፡
ይልቃል ፡ ነውና ፡ አስተውዪ።
አይዞሽ ፡ የሰማይ ፡ ስርዓት ፡ በምድሩ ፡ ሳንኖረው ፡ አናመጣውም ፡
እንደፊቱ ፡ ዝቅታን ፡ ብንይዝ ፡ ስጋችን ፡ እናሸንፋለን ፤ በነጻነት ፡ እማ ፡
ሁሉም ፡ ጠቢበኛ ፡ ነው ፡ የሰው ፡ ትዳርም ፡ ያፋታል ፡ ያዳራል ፡ ሁሉም ፡
ማርከሻ ፡ አለው ፡ በማለት ፡ ስብዕና ፡ ያስረክሳል። እውነትን ፡ መኖር ፡
አይደለም ፡ መናገርን ፡ ይፈራ ፡ እና ፡ ሀቅን ፡ ይይዛል ፡ ፈጣሪ ፡ ግን ፡ ሀቅ
፡ ሳይሆን ፡ እውነት ፡ ነውና ፤ ማን ፡ ግን ፡ በፈጣሪ ፡ ፊት ፡ የተሰጠች ፡
ነፍስ ፡ ሊያፋታ ፡ ይችላልን ፡ ፩+፩=፪ ፡ የሆነውን ፡ የእግዚአብሔር ፡
እውነት ፡ እንዴት ፡ ተደርጎ? አይዞኝ ፡ አንድ ፡ ሚስጥር ፡ ላስታውስሽ ፡
ለሁሉም ፡ ነገር ፡ እባክህ ፣ ይቅርታ ፣ አመሰግናለሁ ፡ ሚሉትን ፡ ያዢ ፡ እና
፡ ማሸነፍ ፡ ትችያለሽ ፡ ይቅርታንም ፡ ብነፍግሽ። በእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡
ግን ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል ፤ ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ።
ይህ ፡ ለንፁህ ፡ ፍቅርሽ ፡ ሁሌም ፡ መሰክራለሁ ፡ ለሚፈርሰው ፡ ለዚህ ፡
በስባሽ ፡ ጡትና ፡ ቂጥሽ ፡ ከቶ ፡ አልተገዛውም። የገዛኝ ፡ የተገዛልኝ ፡
ማንነትሽ ፡ ነውና ፡ ልብሽ ፡ ቢቆሽሽ ፡ በጊዜ ፡ ሁናቴ ፡ ማንነት ፡ ቢፍቅ ፡
ስሜትሽ ፡ በዓለም ፡ ዕውቀት ፡ አይሎ ፡ ከቶን ፡ እምነትና ፡ እውነትን ፡
አይቀድምምና ፡ አይዞሽ ፡ ለነፍስሽ ፡ መኖር ፡ ስጀምሪ ፡ እግዚአብሔር ፡
ይረዳሻል። ነፍስሽ ፡ በመግዛቷ ፡ ነፍሴን ፡ ተገዝቷልና።

@wegoch
@wegoch
@Mahletzerihun
#የጨረቃ ልጆች

ክፍል -3

ሌሊቱ አድካሚ ሆኖበታል ብቻውን ነው ሲጋራውን አውጥቶ ለኮሰ መንገዱ ይበልጥ ረዘመበት አረፍ ለማለት አስቧል ምሽቱን አላረፈም እንቅልፍ በአይኑ አልዞረም አይኖቹ ደም ለብሰዋል ሲጋራውን ማግ አደረገው የደረቀውን ጥቁር ከንፈሩን በምላሱ አራሰው ጭንቅላቱ ውስጥ ምን እንደሚመላለስ ግራ ገባው ቀና ብሎ ጨረቃዋን ተመለከታት ጨረቃን ይወዳታል ለምን እንደሆነ ባይገባውም ሶልያና የሚል ድምፅ ከጆሮው ያቃጭል ጀምሯል ሀሳቡን አሎደደውም ከጆሮው ሚሰማውን ነገር ለማጥፋት ከሲጋራው በደንብ ሳበለት ከደረት ኪሱ አነስ ያለችውን የማስታወሻ ደብተሩን አወጣ አሁንም ሶልያና የሚለው ድምፅ ይሰማዋል ወረቀቱን ገለጥ አድርጎ ሶልያና ብሎ ከማስታወሻ ደብተሩ ላይ ፃፈ 54 አመቱን ከደፈነ ድፍን 5 ወር ሆኖታል በዚህ ሶስት ወር እንዳየው መከራ ከተወለደ ጀምሮ አይቶ እንደማያውቅ ለልቡ ነግሮታል ወረቀቶቹን ገለጠ እስከዛሬ ያገኛቸውን ጥቅሶች ይመለከት ጀመረ አብዛኞቹን ደጋግም ከማንበቡ የተነሳ በቃሉ ይዟቸዋል
ለመጀመሪያ ጊዜ በማስታወሻ ደብተሩ የያዘውን ጥቅስ አነበበ
ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል
የሐዋርያት ስራ 20:35
እንደዚ አይነት ጨዋታ በመርማሪነት ዘመኑ አይቶ አያውቅም ባያቸው የወንጀል ፊልሞች ውስጥ እንዳልተመለከተ አውቋል ጥቅሱን ደግሞ አነበበው ለሱ የሰጡትን ጭንቀት አስታወሰው ሲጋራውን ከአፉ አውጥቶ ተመለከተው እንዳለቀው ሲጋራ ሲያገኛቸው እንደሚጨርሳቸው አሰበ
አሁንም ምንም ባለማግኘቱ ተበሳጭቷል ሌላ የስልክ ጥሪ ሳይሰማ አይኑን እስኪጨፍን ጓጉቷል

ጠዋቱን አትወደውም የሷ አለም ያለው ከምሽቱ ነው ከፊቷ የተቀመጠውን መስታወት ለልጆቿ ከፍታ ለማሳየት ወስናለች ውስጡ ያለውን ነገር እሷ ማወቋ ብቻ በቂ አይደለም መስታወቱን ከፈተች የበገና መዝሙር ማስታወሻ ደብተር የሚለውን ማስታወሻ አወጣች ማስታወሻውን ቀስ አድርጋ በእጇ ዳበሰችው ዛሬ ማታ ወደ ትልቁ የበገና ማዕከል የምንሄድ ይሆናል ለእያንዳንዳቸው እያቀበለች ማስታወሻውን አሳየቻቸው ከአንድ ገፅ በስተቀር ሙሉ ማስታወሻው ምንም ያልተፃፈበት መሆኑ ሁሉንም አስገርሟቸዋል
በአንደኛው ገፅ ላይ ያለው ስዕል የሳባቸው ይመስላል በገና እየበገነ ያለ አንድ ሰው ተስሎበታል በገናው ላይ እንዲ የሚል ፅሁፍ አለ
አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግንሀለሁ
መዝ42/43-4
ከስዕሉ ላይ ያለው ሰው ዘማሪው ዳዊት መሆኑን ሁሉም አውቀዋል ዛሬ ማታ ከበገና ማዕከሉ ውስጥ የሚወጣው በገና አቤቱ አምላኬ በበገና አመሰግንሀለሁ የሚል ፅሁፍ እንዲኖረው ግድ ይላል።
ስልኳ ላይ ተደጋጋሚ መልዕክቶችና ጥሪዎችን አስተናግዳለች አንድ መልእክት ብቻ ተናግራ ወጣች በዛሬው ምሽት ላይ አሷ አትገኝም ተቃውሞ የለም ግን ትንሽ ግራ መጋባት ከፊታቸው ይታያል

ከእንቅልፉ ሲነቃ ሚወደውን ቡና ስለጠጣ ተነቃቅቷል ሌቱን ፈጠው ያደሩት አይኖቹ ትንሽ እረፍት እንዳገኙ ያስታውቃል ዛሬ ምን እንደሚፈጠር ባያውቅም ያለፉትን ሶስት ወራት በዚ ቀን ብዙ ነገሮች እንደተፈጠሩ ያውቃል አይኖቹ ትናንት የተዋወቃትን ሴት ይፈልጋሉ የሷ እርዳታ በጣም እንደሚያስፈልገው ያውቃል
ከምርመራ ክፍሉ ሲገባ ሲፈልጋት የነበረችው ሴት ከእስክሪኑ ፊት ቆማ እያወራች አገኛት ቀስ ብሎ ገባ ከትልቁ ስክሪን ላይ የተደረደሩ ቁጥሮች አሉ ቁጥሮቹ ብዙ አልጠፉትም አስሩ የመጽሀፍ ቅዱስ የሚስጥር ቁጥሮች የሚባሉት ናቸው። 1 22 40 4 12 10 6 3 7 21 ከዛሬ ሶስት ወር በፊት ከጠፋው ትልቁ ቤተ መፃህፍት ውስጥ ከተሰረቀው ሚስጥራዊ ብራና ጋር አብረው የጠፉት ቁጥሮች ናቸው
ማብራሪያውን ቀጥላለች እነኚህን ቁጥሮች የመጽሀፍ ቅዱስ ሚስጥራዊ ቁጥሮች ከመሆናቸው በተጨማሪ ከተሰረቁት ነገሮች ጋር የታታዥነት አላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ከቤተ መፅሀፍቱ እንነሳ ይህ ቤተ መፅሀፍት በከተማው ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመሰረተ መሆኑን እናውቃለን ስለዚህ 1 የሚለውን ቁጥር ቤተመጽሀፍቱ ይወስዳል። ለሁለተኛ ጊዜ የተሰረቀው የንጉሱ ማስታወሻ ሁለተኛው የንጉሱ ማስታወሻ እንደሆነ ይታወቃል ተቀምጦበት የነበረውን ሳጥን ስናይ በሳጥኑ ላይ ሁለት የሚል ቁጥር እናገኛለን 2-2 ስናገናኛቸው 22 ይሆናል ስለዚህ የንጉሱ ማስታወሻ 22 ቁጥርን ይወስዳል። የዛሬ ሁለት ወሮ አካባቢ የተሰረቀውን የወርቅ ብዕር ደሞ እናገኛለን ብዕሩ 4 ቀለሞችን የያዘ ነው ስለዚህ 4 ቁጥሩን ብዕሩ ይወስዳል ማለት ነው። ሁሉም አፉን ከፍቶ እያዳመጣት ነው ብዕሩ በጠፋ በነጋታው የጠፋው መጽሀፍ 12ቱ መአድናት የሚል መጽሀፍ ነው ይህ ማለት 12ቁጥር መጽሀፉ ወሰደ ማለት ነው። ልክ የዛሬ ወር የጠፋው የወርቅ ሜዳሊያ በላዩ ላይ በግዕዙ 10 የሚል ቁጥር በሜዳሊያው ላይ ታትሞ እናገኛለን ስለዚህ የወርቁ ሜዳሊያ 10 ቁጥርን ይወስዳል። እነዚህ ሚስጥራዊ የመጽሀፍ ቅዱስ ቁጥሮች ተብለው የተቀመጡት ቁጥሮች ካርታም ጭምር ናቸው በቀላሉ ለዘራፊዎቹ ምልክት ይሰጣሉ
ትናንት የጠፋው ማስታወሻ በሶስት ሰዎች የተሳለ ስዕል ውስጡ ይገኝበታል በስዕሉ ላይ ላይ ያለው ሰው መዝሙረኛው ዳዊት ነው ማስታወሻው ደሞ 3 ቁጥርን ይወስዳል ማለት ነው። በስዕሉ ላይ ያለው ምስል በገና ይዞ እየደረደረ ያለ ምስል ነው። የቀሩን ሁለት ቁጥሮች ደሞ 7 እና 21 ናቸው። ልብ ብሎ እያዳመጣት ስለሆነ 40 ቁጥርን ለምን እንደዘለለቻት አልገባውም ማስታወሻውን አውጥቶ ሁሉንም ነገር መዝግቧል 40 ቁጥርን ግን ሊያገኛት አልቻለም ቀና ብሎ ከደገና መስማት ጀመረ
7 ቁጥርን ልውሰድ ከስዕሉ ላይ የሚታየው በገና ይዞ የሚደረድር ሰው ነው ቀጥታ በሀሳባችን ሊመጣቸው የሚገባው ነገር ትልቁ የበገና ማዕከል ነው ከትልቁ ስክሪን ላይ የበገና ማዕከሉ መግቢያ ምስል ተደቀነ እንደምታዩት መግቢያው ላይ ትላልቅ ሰባት የበገና ቅርፆች ይታያሉ ስለዚህ የበገና ማዕከሉ 7 ቁጥርን ይወስዳል ማለት ነው። በብርሀን ፍጥነት ሁሉም ከተቀመጠበት ተነሳ ቀጣዩ አላማ ትልቁ የበገና ማዕከል እንደሆነ አውቀዋል

ይቀጥላል......
ብላቴናው በጨረቃ ምሽት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/09/24 09:14:05
Back to Top
HTML Embed Code: