Telegram Web Link
ጦርነት ውስጥ ራስህን አስበህ ታውቃለህ? ታውቂያለሽ?
.
.
መሳሪያ በታትነህ ጠራርገህ ታውቃለህ? የጥይት ሒሳብ ተከራክረህስ ይኾን? በማለዳ ተነስተህ በጀርባህ ንብረት አዝለህ፣ ከስክስ ጫማ አድርገህ ተራራውን ሮጠህ ታውቃለህ? ምሽግ ቆፍረህስ!?
የጥይት አሩር÷ ጭሱን በአፍህ እና በአፍንጫህ ምገህ ታውቃለህ? ቦንብ ከአውሮፕላን እንደ ዝናብ ሲዘንብ÷ የምድሩን ከርስና ገፁን ሲያርደውስ አይተኸል? ምድርስ በዚህ ምክንያት ስትንቀጠቀጥ እግርህ ያውቃልን?
የሰዎች እግር ሲቆረጥ÷ አካላቸው እዚያና እዚህ ሲበታተንስ አስተውልኸልስ ይኾን? የእናቶች እሪታ÷ የልጆች ለቅሶ በጦርነት መኸል ጆሮህ ሰምቶ ያውቃል? ወንዶች በጩቤ ሲሞሻለቁ÷ ሴቶች በድምፅ አልባ መሳሪያ ሰው ሲጥሉ÷ አናት ሲፈጠርቁስ አስበኸው ይኾን?
ይኽን ኹሉ ሰቆቃ እና ዕውነት ለመሸከም ትከሻም፤ ልብም የለንም፡፡
ቅዱስ መፅሐፍ እንደሚለው ሰላምን እንሻለን፤ እንከተላለን እንጂ!
ጦርነት መሬ ነው፡፡
ለምለም እንጀራ የምትበላበት ሰዐት አይኖርህም፡፡ ጠይም ከንፈር ያላት ወዳጅህን አታገኛትም፡፡ ደጀ ሰላም በለሊት ተነስተህ አትሳለምም፡፡ የአዛን ድምፅ የምትሰማበት ጊዜ እንደ ሰማይ ይርቀኸል፡፡ ዱንቡሼ ፊት ያላቸው እንቦቃቅሎችን አታይም፡፡ የእናትህን የእጅ ደበሳ እንደ ገነት ደጅ ይርቀኸል፡፡ ቋንቋህ እና ኑሮህ እንደ ባቢሎን ይኾንብኸል፡፡
ከጦርነት ማግስት እንኳን ውጥንቅጡ የወጣ ከተማ ትታቀፋለህ፡፡ የሞቱ ሰዎች የሬሳ ክምር፣ ሬሳዎቹን ሊበሉ የሚያንዣብቡ ጥንብ አንሳዎች፣ እግራቸውን የተቆረጡ ሰዎች፣ ደረታቸው የተቦረደሱ÷ አንጀታቸው ከሆድ እቃቸው የወጡ ሰብዖች ከቅርብህ÷ ከርቀትህ ታገኛለህ፡፡
ከተማው÷ ሐገሩ የአይጦች ምሽግ ይኾንብኸል፡፡ ፍርስራሽ ቤቶች፣ መሶብ የሌላቸው ጓዳዎች፣ አባወራ የማይገኝባቸው ደጆች ይሰጥኸል፡፡ የሚስቁ ድምፃች፣ ደምግባት ያላቸው ፊቶች ተቀብረዋልና!
ጦርነት ሐገር ይሰራል የሚለውን የብሉይ ሐቲትን አንቀበልም!
ከዚህ ኹሉ የምድር ሲኦልነት÷
እኛ ውይይትን÷ ሰላም እና ወንድማማችነትን እንመርጣለን፡፡
ከለመለመው መስካችን እንጀራ መብላት እንመኛለን፡፡ ማሳችንን ማረስ÷ ብዕራችንን ስለ ፍቅር እንዲተፋ ማድረግ አምሮታችን ነው፡፡ ከህፃናቱ ጋር አፃለሌን መዝፈን ነው የምንፈልገው፡፡
አምላካችን ፊት አባታችን ሆይ ማለት እንዲጎልብን አንሻም፡፡ አዛናችንን በምሳ ሰዐት ታጥበን ማድረስ የዘወትር ሃያትችን እንዲኾን እንቃትታለን፡፡ በፍቅር ሰላምታ ተሰጣጥተን የሰላም ሐገር መገንባት የዘወትር ፀሎታችን ነው፡፡
ኹሉን በፍቅር አድርጉ ተብላልና÷
እኛ የፍቅር ሰው÷ የሰላም ሰው መኾናችን እስከ ዕለተ ሞታችን ድረስ መለያ ቀለማችን ነው፡፡

@wegoch
@wegoch
ለምሽታችን ምርጥ አዲስ ፕራንክ....ከ ቴዶ 🙊😉
https://m.youtube.com/watch?v=T29d6KO45A4&t=1s
እዚጋ ደሞ ሌላ ትኩሳት
""""""""""""""""""""""""""""
ኧረ ጉድ ነው እናንተዬ......በስንቱ ጭንቅላታችን ስሜታችን ተነክቶ እንቻለው?.....የት እንሂድ?... ወዴት እንድረስ... ወይ አሰልፈው ይረሽኑን እና እንረፈው። ("ምን ሆንክ?" ትላላችሁ መቼም...) ኮሮናን ተዉት......ስራ መቀዝቀዙንም ተዉት.....ትምህርት መዘጋቱንም ተዉት.....የሀገር እረብሻውንም ተዉት.....ሰዉ በየክልሉ መሞቱንም ተዉት....አንበጣዉንም ተዉት!....እንደው ከላይ ከዘረዘርኳቸው አስጨናቂ ወሬዎች ትንሽ ፈታ ብንል ብለን የቲቪ ሪሞታችንን ይዘን ጋቢ ቢጤ ጣል አድርገን በየአልጋችን፣ በየሶፋችንና በየወንበራችን (ሰው ባለው ነው መቼም ) አረፍ ብለን ቲቪያችንን ስንከፍት ህሊናችንን እያገላበጠ የሚገርፍ ማስታወቂያዎች ጋ ገጭ እንላለን።

አሁን የኔ አሙዋሙዋት
አሙዋሙዋት ነው ወይ?
ጉች ጉች ያለ ጡት
አንድ ቀን ሳላይ....

ያለው ያገሬ ሰው እኮ በኛ ደርሶ ቁጭ አለ።(በእውነት)....የሪል ስቴቱ ብዛት ለጉድ ነው "ካሳንቺስ መሀል እንትን ሪል ስቴት ሌግዠሪ ህይወትን ይኑሩ ሺ አመት አይኖር....." ይላል አስተዋዋቂው ድምፁን ጎርነን ቀጠን እያደረገ።....ኧረ ወንድሜ 64ቱንም አመት እንዴት እንደሚያልቅ ጨንቆናል ዘረኛ ይድፋን፣ ኮሮና ይድፋን ገና አላወቅነውም። በቁማችን ግን ሰቀቀኑ እየገደለን ነው። ምን አይነት ቤት ነው የምታሳዩን እንቁልልጭ እያላችሁት ነው ደሀውን......ኧረ ተዉ ግፍ አለው ለኑሮዋችን ተዉን በGood morning ሻይ ቅጠል እና በዘኒት ቅባት ማስታወቂያዎች እኮ ነው የለመድነው ድንገት ምነው ሰቀላችሁን?....ቲቪ የገዛበትን ብር ብድር ሳይከፍል ህዝቤ ተሳቆ ....ለደስታ በገዛት ቲቪ ደሞ የባስ በእናንተ አፓርታማ እና ሪል ስቴት ይሳቀቅ እንዴ ሆኦኦ....

ወይ እዛው የናንተን ቅንጡ ኑሮ የምታሳዩበት ቻናል ለብቻችሁ ከፍታችሁ እዩ(ሀብታሞች)......እኛ ደሀዎቹን አታቁለጭልጩን ኑሮ የሚያቁለጨልጨን ይበቃል።

አሁን በቀደም ጎረቤቴ የሆነ አንድ አባት ከህፃን ልጁ ጋ ሲያወሩ ጆሮዬን ጣል አድርጌ እሰማቸው ጀመር(ለነገሩ ጆሮዬን ጣልኩ አልጣልኩ የተፈሳችው የተገሳችውም ትሰማኛለች ኩታ ገጠም ከመሆኑ የተነሳ)
ልጅ፦ አባቢ አባቢ ቦቦ ግዛልኝ....
አባት፦ አንተ ልጅ እንደገና ቁልቁል ሽንት ቤቱ ምን ሆነና አድገህ የለም እንዴ?(ፖፖ ያለው መስሎት ነበር እኔ እየሰማው በውስጤ በሳቅ ፍርስ)
ልጅ፦ ኧረ አይደለም አባዬ ቦቦ ወተት ነው እነ ቸሬ...ቤቢ...ትርሲትም ተገዝቶላቸዋል አስቀምሰውኛል ይጣፍጣል
አባት፦ ስንት ብር መሆኑ ነው?
ልጅ፦ 15 ብር
አባት ክው .....ስራ ሲሄድ ለትራንስፖርት አድርሳ የምትመልሰውን 15 ብር ልጁ ፉት ሲላት ታይቶት...
አባት፦ በቃ የኔ ልጅ ለደሞዝ እገዛልሀለው
ልጅ ሆዬ እንባው ዱብ ዱብ "ግዛልኝ ዛሬ ነው የምፈልገው..."
አባትም ቆጣ ብሎ "ሂድልኝ አንተ ውሪ ...የምንም ጣፋጭ ለምዶ ሊባልግ ይፈልጋል እንዴ..." ሊመታው አርጩሜ ሲፈልግ ልጅ ፈርቶ ቁጭ ....አባት ውስጡ እያለቀሰ ላዩን ተቆጥቶ ልጁን አሳረፈው....ቢኖረውና ቢገዛለት ምንኛ ደስ ባለው ግን ዛሬ አንድ ወተት ቢያጠጣው ነገ ስራም መሄጃም አይኖረው፤ ስለዚህ የልጁን አምሮት በቁጣ ማብረድ ግድ ሆነበት።
ስሰማቸው ስለነበር አቡሽ አሳዘነኝ ደሞዝ ሰሞኑን ስለተቀበልኩ ልገዛለት አሰብኩና አባቱ ፊት ብገዛለት አባትየው እንዳያፍር እንዳይናደድም ብዬ (መቼም ደሃ ብንሆንም ኩሩ አይደለን) እቅድ አቀድኩ.... አቡሽን ቤተ ክርስትያን ይዤው መሄድ እና ስንመለስ ያማረውን እገዛለታለሁ አልኩ። አባቱንም አስፈቅጄ ቅርባችን ወደአለው ሚካኤል ቤተ ክርስትያን ተያይዘን ሄድን ተሳልመን ገባንና ወደ ግንቡ ጠጋ ብዬ ፀሎቴን አድርሼ ጨረስኩ ወደ አንድ መቀመጫም ሄጄ አረፍ አልኩ። አቡሽ አሁንም ግንቡን ተለጥፎ ፀሎቱን ያደርሳል ካሰብኩት ደቂቃም ሲቆይብኝ ምን ብሎ እየፀለየ ይሆን የሚል ጥያቄ ፈጠረብኝ። ከዛ እሱም ጨረሰና ተያይዘን ወጣን ከዛ ጠየኩት"አቡሽዬ ምን ብለህ ፀለይክ?"
በሚያሳዝን አይኑ ቀና ብሎ እያየኝ በቁምነገር እንዲህ ብሎ መለሰልኝ "እግዚአብሄር ወይ ቦቦ ግዛልኝ ነው ያልኩት" መንገድ ላይ እንደዛ ስቄ አላውቅም አቡሽም ቀና ብሎ እያየኝ ግራ ገብቶት ፈገግ እያለ"ምነው አብርሽ?" አለ።
"ና ና ፈጣሪ ፀሎትህን ሰምቶሀል..." ወደ ሱቁ አመራን

እዚጋ ደሞ ሌላ ትኩሳት
ወገኔ አለቀ በጉጉት እሳት
እሳት
እሳት.....በሉልኝማ

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@wegoch
@wegoch
@paappii
ወይ እንጀራ ወይ ሞት
(በእውቀቱ ስዩም)
.
ታሪክ ፀሀፊዎች “ዘመነ መሳፍንት “ ብለው በሚጠሩት ፤ እኔ ደሞ “ ዘመነ የጁ “ በምለው ዘመን ውስጥ አንዲት አረሆ የሚከተለውን ግጥም አንጎራጉራ ነበር፤
"እሄዳለሁ ሜጫ እሄዳለሁ ዳሞት
ሳላገኝ አልቀርም ወይ እንጀራ ወይ ሞት "
በነገራችን ላይ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ባላገሮችንና ጌቶችን በፈጠራ በማዝናናት የሚተዳደሩ የግጥምና የዜማ ባለፀጋ ሴቶች ና አረሆ ተብለው ይጠሩ ነበር::
ያኔ ካንዱ አውራጃ ወደ አንዱ አውራጃ የሚኬደው በባዶ እግር፤ ግፋ ቢልም በበቅሎ ነው ! ሲመሽ በሸማ ድንኩዋን ስር ወይም ዛፍ ስር ይታደራል ! አባይን መሻገርማ አይጣል ነበር ፤ ካዞ ብታመልጥ ሽፍታ አይምርህም ! አቶ ሀዲስ አለማየሁ እንዳሉት አባይ “ ብዙ ሞቶች ተሰብስበው የሚገኙበት ቦታ” ነበር፤ በዚያ ላይ በየቦታው መሳፍንቱ ጎራ ለይተው በየቦታው ይከሳከሳሉ ፤ በግርግር መሀል በራሪ ጥይት መሞት መደፈርና መጠለፍ ሊያጋጥም ይችላል!
የጠቀስኩት ግጥም ዝምብሎ የድሮ ግጥም አይደለም! ዛሬም የብዙሀኑን የኢትዮጵያዊ ህይወት የሚገልፅ ይመስለኛል ! “ሜጫንና ዳሞትን “ በሌሎች ቦታዎች ተክቶ ማንበብ ብቻ ነው እሚጠበቅብን ! ከጥቂት አመታት በፊት በሰደት ወጥቶ መሞትን ስናስብ መጀመርያ ወደ አእምሮአችን የሚመጣው አረብ አገር ወይም ደቡብ አፍሪካ ነበር ፤ ብዙ ሰው ወቅቱን ያልጠበቀ ሞት ሸሽቶ ነበር ወደ አሜሪካ የሚሰደደው ሞት አሜሪካ ውስጥ ለመጥፋት የተቃረበ ብርቅየ አውሬ ሆኖ ቆይቷል ፤ ዘንድሮ ይሄ ቀርቷል ! ከሁለት ቀናት በፊት ባንድ ቀን ብቻ ዘጠኝ መቶ ሰባ አንድ ሰዎች እንደ ጥቢ ቅጠል ረግፈዋል! አሜሪካ እንጀራ አምሮት ለመጣ ስደተኛ ሞትን በሰፌድ ማቅረብ ጀምራለች::
ይህ ብቻ አይደለም ! አሜሪካኖች ምርጫ ላይ ናቸው! የትራምፕ ደጋፊዎች እንደ ጌታቸው መጋጣነታቸውን -ወይም ባዲስባ አራዳ አማርኛ " ሰገጤነታቸውን " መደበቅ እሚችሉ አይደሉም ! ሰውየውም ሽንፈቴን በፀጋ አልቀበልም ብሏል ! ደጋፊዎች ጎራ ለይተው ሊላመጡ ይችላሉ! እዚህ አገር ድብድቡ ከተጀመረ እንደ ሸገር በድንጊያ ወይም እንደ ፍልስጤም በወንጭፍ አይደለም! ሁሉም " ነጣ ዘለግ ያለ ስናይፐር ታጣቂ" ነው!
አሁን ሳስበው መሞቴ ካልቀረ እዛው ባገር በቀል ዱላ መሞት ይሻለኝ ነበር፤ ደግነቱ በሜክስኮ ድንበር ግንብ ታጥሮ አለማለቁ ጠቀመኝ! የፈራሁት ከደረሰ፤ በቅርቡ “ የበውቄ ኩብለላ-ከማንኩሳ እከጉዋታማላ “ የሚል ማስታወሻ ጠብቁ፤

@wegoch
@wegoch
የመጀመሪያው እምቢታ!
«ዘውድአለም ታደሠ»
(አማን መዝሙር)

«ሰላም ነው ስሜ» አለችኝ!
«ሰላም የሚባሉ ሴቶች ብዙ ግዜ ፀረሰላም ናቸው ይባላል» አልኳት!
«ይሆናል ...» ብላ ሳቀች! ሰላምን ካገኘኋት ገና ሰላሳ ደቂቃ አይሞላኝም። ሰው ሰላም ሊል ወደኋላ የቀረ ጓደኛዬን ቆሜ ስጠብቅ ድንገት በኔ በኩል መጣች። ልከኛ ነች! መሃከለኛ ቁመት፣ መሃከለኛ ፀጉር፣ መሃከለኛ የሰውነት ቅርፅ ... በመሃከለኛ እርምጃ ስትመጣ የማላውቀው ሃይል የሆነ ነገር በል በል አለኝ! አጠገቤ ስትደርስ «እንተዋወቅ» አልኳት! የምር በቃ ይሄን ነው ያልኳት! ማነሽ? ወዴት ነሽ? ገለመሌ የለም፣ አለ አይደል ልክ ፊልም ላይ እንደምናያቸው
አክተሮች መጀመሪያ አስቆ ፣ አባብሎ፣ አሽኮርምሞ “እጅ ፅሁፍሽ እንዴት ነው?”
ምናምን ብሎ መጀንጀን የለ እንዲሁ ድርቅ ብዬ እንተዋወቅ! «ሰላም እባላለሁ» አለችኝ! «ሰላም የሚባሉ ሴቶች ብዙ ግዜ ፀረሰላም ናቸው ይባላል» አልኳት! «ይሆናል ...» ብላ ሳቀች! «ፀሃይ ነው ለምን ትንሽ አረፍ ብለሽ ቡና ምናምን ጠጥተን መንገድሽን
አትቀጥዪም?» አልኳት! «እሺ» አለችኝ!
ጓደኛዬን ጥዬ አንዱ ካፌ ይዣት ገባሁና ሻይ ቡና ብለን ስንወጣ «ለክፉም
ለደጉም ቁጥር ብንለዋወጥ» አልኳት!
«እሺ» አለችኝ። (ልጅቷ እምቢ አታውቅም ጎበዝ) ቁጥሯን ተቀብዬ ደወልኩላትና ጥቂት አውርተን «ነገ ከተመቸሽ እንገናኝ?» አልኳት
«እሺ ....!»
ብዙ ግዜ ተገናኘን! ተቀራረብን ወደድኳት! ፈራ ተባ እያልኩ «ወደድኩሽ»
አልኳት። ትንሽ አስባ «እሺ» አለችኝ።
«ፍቅረኛዬ ብትሆኚ ደስ ይለኛል»
«እሺ ....»
የእሺታዋ ብዛት ግራ ቢገባኝም ወድጄዋለሁ። ምንም ነገር አትቃወም! እምቢ አታውቅ! አትጨቃጨቅ! በቃ ሁሉን እሺ ነው! እንዲህ ቦታ እንሂድ? እሺ! እንዲህ እናርግ? እሺ! ... ሁለት አመት ከአምስት ወር ሆነን አንድም ቀን ፀባይዋ ሳይለወጥ! አንድም ቀን ኮምፕሌን ሳታደርግ! እንዲሁ ግራ እንዳጋባችኝ ሁለት አመት ከአምስት ወር በፍቅር!! የሆነ ቀን ቀለበት ከኪሴ አውጥቼ «አግቢኝ» አልኳት!
«እሺ ....!»
እሺ ጠላሁ! በቃ ደበረኝ! አለ አይደል የሆነ ውድን ነገር በርካሽ ስናገኘው «ይሄ ነገር ፎርጂድ ይሆን እንዴ?» ብለን የምንጠራጠረው አይነት? ቆይ እስከዛሬ በኔ ስሜት፣ በኔ ፍላጎት፣ በኔ እቅድ እሺ ብቻ እያለች ኖረች! የራሷ ስሜትስ? የራሷ ፍላጎትስ? የራሷን ህልም የት አርጋው ነው ሰው ህልም ውስጥ ጭልጥ ብላ
ምትጠልቀው? ተጋባን!
«ልጅ እንውለድ?»
«እሺ!»
ግራ ታጋባኝ ነበር! አሁን ግን የእሺታዋን ጋጋታ እንደድንዛዜ አየሁት። አለ አይደል
ስሜትን ካለማዳመጥ የሚመጣ፣ ፍላጎቷን ሳታውቅ የምትኖር ነፋሱ ወደነዳት የምትንሳፈፈ ፌስታል ያህል ቀለለችኝ! በቀደዱላት ቦይ የምትፈስ ወራጅ ውሃ መሰለችኝ! አዎ ውሃ! ከገደቧት የምትረጋ፣ መንገድ ከሰጧት የምትጓዝ፣ እሳት ላይ ሲጥዷት የምትሞቅ፣ ፍሪጅ ሲጨምሯት የምትበርድ ብርጭቆ ውስጥ ሲያረጓት ብርጭቆውን የምትመስል፣ በስኒ ሲጨልፏት የስኒውን ቅርፅ የምትይዝ
፣ የራሷ ቅርፅና መልክ የሌላት ውሃ መሰለችኝ! ተራ ውሃ! ለምን አመሸህ? ለምን ይሄን አላረግክም? ብሎ ጭቅጭቅ እሷጋ የለም! እንኳን ባመሽ ባድር በነጋታው ምንም እንዳልተፈጠረ በፈገግታ ትቀበለኛለች! ብስጭት ብዬ ስናገራት መልስ አትሰጥም! ይሄን አርጊ ያን አታርጊ ስላት ለምን? ማለት የለም «እሺ» ነው! በቃ እሺ ብቻ! በጓደኞቼ ሚስቶች እቀናለሁ። ሲቆጡ ቁጣቸው ውስጥ የኔነት አለ። ሲቀኑ ቅናታቸው ውስጥ ስስት አለ! ሲከፉ መከፋታቸው ውስጥ ፍቅር አለ! የኔዋ ግን .... በቃ በድን! ታግዬ እንኳ ላስከፋት የማልችል፣ ሁሉን ነገር ከመቀበል ውጪ እምቢ የማታውቅ ግኡዝ ፍጥረት ትመስለኛለች!
አንዳንዴማ ነካ ሚያድጋት ሁሉ ይመስለኛል! እኔው አጥፍቼ እኔኑ ይቅርታ
ስትጠይቀኝ ብግን እላለሁ። አስከፍቻት ውዬ ስመለስ ከበር በፈግታ ስትቀበለኝ
እየተወነች ይመስለኛል! አውቄ የማይሆን ሃሳብ ስነግራት እሺ ስትለኝ ጩህ ጩህ ይለኛል! አንዳንዴ ስጋ የለበሰች አሻንጉሊት ያገባሁ ሁሉ ይመስለኛል! በኔ
ፍላጎትና መጠን ዲዛይን የተደረገች ሮቦት ትመስለኛለች! ሰለቸኝ! በድን አቅፌ የምተኛ መሰለኝ። ለካ ጠብ ብቻ ሳይሆን ቅጥ የለሽ ሰላምም ይረብሻል! ለካ አለመስማማት ብቻ ሳይሆን ዝም ብሎ መስማማትም ይጨንቃል! «እንኳን ሰው ድንጋይና ድንጋይ እንኳ ይጋጫል» ይላሉ አበው። አንዳንድ ሰላም ከድንጋይም ያሳንሳል! በተጋባን ባመቱ «እንፋታ» አልኳት
«እሺ!» አለችኝ!
ለምን? የለ! ድንጋጤ የለ! በቃ «እሺ ብቻ!» ...ፊቷ ላይ ግን የሆነ ሃዘን መሳይ
ነገር አይቻለሁ! ቢሆንም ይሄንንም «እሺ» ብላ መቀበሏ የበለጠ አናደደኝ! ከዚች ጋርማ መኖር አልችልም። አልኩት ራሴን! ጠኋት ተነስቼ ወደምሄድበት እሄዳለሁ ቤቱን እሷ ቤቢን ይዛ ትኑርበት። ልጄ ሲናፍቀኝ እየመጣሁ አየዋለሁ! አልኩ በሆዴ! በጠኋት ሻንጣዬን ይዤ ልወጣ ስነሳ እሷ ቀድማኝ ቤቢን ይዛው ሄዳለች! ቁምሳጥኑ ውስጥ እኔ የገዛሁላት ልብሶች ብቻ ቀርተዋል! ፍሪጁ ላይ አንድ ወረቀት ተለጥፏል። ጠጋ ብዬ አየሁት «ራስህን ጠብቅ» ይላል! ግራ ገባኝ! እንዳሰብኩት ነፃነት አልተሰማኝም። የሆነ ሃዘንና ድብርት የቀላቀለ ነገር ይሰማኛል። ሳምንቱን ሙሉ ሰከርኩ! ከሳምንት በኋላ ደወልኩላት! ስልኳን አታነሳም። በህቷ ስልክ ስደውል ቤተሰብ ጋር እንዳለችና ልታናግረኝ እንደማትፈልግ ነገሩኝ! ይሄን ስሰማ የሆነ ደስ ነገር አለኝ! ማለት አለ አይደል እሷም እንደሰዉ እንደምትከፋ በማወቄ የሆነ ደስ የሚል ስሜት ተሰማኝ! አንድ ወር ቆይቼ ደወልኩላት። አሁንም አታነሳም። ግራ ተጋባሁ! ጨነቀኝ! ምንም ያልበደለችኝን ሚስቴን ምን ሁኚ ብዬ ነው ያባረርኳት? ትዳሬን ምን ይሁን ብዬ ነው ያፈረስኩት? ምን አርጊ ምን ፍጠሪ ነው ያልኳት ቆይ? ፀፀት ሁለመናዬን ወረረኝ! ቢቸግረኝ የቅርብ ጓደኛዬን ይቅርታ ጠይቆ እንዲያመጣት ላኩት። እሷ ማንንም ስለማታስከፋ እሺ እንደምትለው እርግጠኛ ነበርኩ! ለማሰቢያ የሚሆን ግዜ እንዲሰጣት ነግራው አሰናበተችው። ካሁን አሁን መጣች ብዬ ስጠብቅ የፍቺ ወረቀት በሬ ድረስ ላከችልኝ! ምድርና ሰማይ ዞረብኝ! ወረቀቱን በእጄ አንጠልጥዬ ስበር ቤተሰቧ ቤት ሄጄ
በሩን አንኳኳሁ። ራሷ ከፈተች! ፊቷ ላይ ምንም አይነት ለውጥ አላየሁም። አይኖቿ ላይ ግን እንለያይ ስላት ያየሁትን ሃዘን አይቻለሁ። «ምንድነው ይሄ?» አልኳት «እንፋታ ብለኸኝ የለ? የፍርድቤት መጥሪያ ነው» አለችኝ። ድምጿ ውስጥ
የቀድሞ ልስላሴዋ የለም። ሌላ ሴት ነው ምትመስለው። እግሯ ላይ ወድቄ ይቅር እንድትለኝ ለመንኳት! ዝም ብላ ስታየኝ ቆይታ አንድ ቃል
ከአፏ አወጣች
«እምቢ!»
ጆሮዬን አላመንኩም። እምቢ የሚለው ቃል ለካ እንዲህ ያማል? እምቢታዋ ውስጥ ከእሺታዋ የሚበልጥ ጥንካሬ አለ! እምቢታዋ ጨካኝ ነው! ያስፈራል !
ከዚያን ቀን ወዲህ ለመታረቅ ያልፈነቀልኩት ድንጋይ ያልሰደድኩት ሽማግሌ የለም! ነገር ግን ሁሉም እምቢታዋን ለማሸነፍ የሚያበቃ ጥንካሬ
አልነበራቸውም! እምቢታዋ ዘልአለማዊ ነው!

@wegoch
@wegoch
@paappii
አያድርስና .. ወያኔ ብትመለስስ ..!
«ዘውድአለም ታደሠ»
(አማን መዝሙር)
አሁን እንደው አያድርገውና ነገ ልክ ከእንቅልፋችን ስንነሳ ወያኔ በባሌም በቦሌም ብላ ቤተመንግስት ገብታ ራዲዮኑ «ብሶት ዮዎሎዶ ሎዲጂታል ዎያኔ ሶርአዊት ሎኩሉተ አመት ሎአህዳዊው ሎአቢይ ሞንጉስት የያዘውን ቤይተመንግስት ቦሞራራ ትግል ቶቆፃፅሮታል» በሚል ሰበር ዜና ሰርፕራይዝ ብታደርገን ምን ይፈጠር ይሆን ብዬ በምናቤ ለመሳል ሞከርኩ።
መጀመሪያ ከሐገር የሚጠፋው ያ "ጌታቸው አሰፋ በሽጉጥ ፀጉሬን ላጭቶኛል" ያለው ሰውዬ ይመስለኛል
ጋሽ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደተለመደው በቴሌቭዥን መጥተው «አሁን ገና ብርሃን አየን። ባለፉት ሁለት አመታት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ነበርን» ብለው ጌታን ያመሰግናሉ። አብዲ ኢሌ እንደማንዴላ እጁን እያውለበለበ እንደነፃነት ታጋይ ጀነን ብሎ ከእስር
ቤት ይፈታል። በለው! ይብላኝላቸው ለፋና ጋዜጠኞች እያንዳንዳቸው ጌታቸው አሰፋ ጋር ቀርበው እንደአርጋው በዳሶ በጭንቅላታቸው ቆመው ንስሃ እንዲገቡ ይደረጋል። ሃያ ሁለት እንደቀድሞዋ ጎልድ ሌብል እየጠጡ በየመሃሉ ወጣ እያሉ ሽጉጥ በሚተኩሱ የከተማ ዶን ኮርሌዎኔዎች ትሞላለች። ጋዜጠኛ አንሙት አብርሃም ኦዞንን ለመሸንቆር በማሴርና በ treason ሲከሰስ ያየሰው ሺመልስ ደግሞ ባለብእሩ ቼጉቬራ ተብሎ የክብር ዶክትሬት ከመቀሌ
ዩኒቨርስቲ ይሰጠዋል። አብይ የጀመራቸው ሸገር ፓርክና እንጦጦ ፓርክ ከምንከተለው ግራ ዘመም
ርእዮተ አለም ጋር አይሄዱም ሰውንም ስራ ያስፈታሉ ብለው ኮንዶሚኒየም
ይገነቡባቸዋል። ጌታቸው ረዳ አወሉ አብዱን አፈላልጎ ይደበድበዋል ዳንኤል ብርሃኔ «እንዳያልፉት የለም» የሚለውን የትግል መዝሙር እየዘመረ እንደበፊቱ ሸራተን ቁጭ ብሎ በአራት ቺክ ተከቦ አክቲቪዝሙን ያጧቱፋል። ያ "አብይ ሳምባዬ ነው" የሚል መፈክር ይዞ የወጣው ሰውዬ እሱን ሰርዞ "ደብረፂዮን ጣፊያዬ ነው" የሚል ጥቅስ ይፅፍበታል
«ልማቱ ፣ ብሔር ብሔረሰቦች፣ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ የመለስ ሌጋሲ ፣ ኪራይ ሰብሳቢነት» ምናምን የሚሉ ቃላት
ወደቦታቸው ይመለሳሉ። መንግስት ካለፈ በኋላ ማድነቅ የሚወደው የኢትዮጵያ ህዝብ ምፅ ምፅ እያለ
«አዪዪ ጥጋብና ተድላ በአብይ አህመድ ግዜ ቀረ» ይላል አንዳንድ ጥቃቅንና አነስተኛ ብሔሮች ባለፉት ሁለት አመታት ምን ያህል ሲጨቆኑ እንደኖሩ እንባ በአራት መንታ እያወረዱ ይናገራሉ። የፈንቅል መሪዎች በሱዳን በኩል ይነኩታል:) የትግራይ ፕሬዘዳንት ነኝ ያለው ነብዩ ስሁል «አረ ፕራንክ ነው» ብሎ ያስተባብላል ጓድ አባዱላ ገመዳ በዚያ አንጀት በሚበላ እንግሊዝኛው "how many times death came to me” ይልና ፈገግ ብሎ "if love is between us never die" ብሎ ይመሰጣል ጓድ አረጋዊ በርሄ «ምነው ትንሽ እንኳ ስልጣን ላይ ብታቆየኝ» ብለው እንባቸውን ወደሰማይ ይረጫሉ ።
ደህዴኖች ያው ላሸነፈው ናቸው መቼስ። «ኢኛኮ ቢልፂጊና ሚባል ናጋር ዲሮም
አልቴሜቼኒም ናበር» ብለው ለደብረፂዮን ባህላዊ ልብስ በማሰፋት በአስጌ ዘፈን
እየጨፈሩ ይቀበሉታል ለውጡ ከመጣ በኋላ ስማቸውን ከሃጎስ ወደ ደቻሳ የቀየሩ ሰዎች ለሶስተኛ ግዜ ወደሀጎስ ለመቀየር ፍርድቤት ይሰለፋሉ ማእከላዊ በአዲስ መልክ ስራ ይጀምራል። የሃይላንድ ላስቲኮች ከብክነት ይድናሉ። ለሚ ኩራ የሚለው አዲሱ ሰፈር “ደፂ ኩራ" ወደሚል ይለወጣል : የዲሲ ግብረሃይል በዚያች አንድ ለናቷ እንግሊዝኛው "shame on you, you are bloody hand" እያለ ያወግዛል። ታማኝ በየነ ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል።
ኤርሚያስ ለገሰ በእጁ ያለውን ሚስጥር ለማውጣት ደፋ ቀና ይላል ወዳጄ ዮናታን የአብይን ፎቶ ግድግዳው ላይ ሰቅሎ «ምነው ተለየሽኝ መስከረም ሳይጠባ» በሚለው ዘፈን ያነባል እኔ ደግሞ “ብልፅግናዎች አፍዝ አደንዝዝ አድርገውብኝ ነው እንጂ ውስጤኮ
ከጭቁኑ ህዝብ ጋር ነው” ብዬ በራሴ ላይ ግለሂስ አወርዳለሁ

@wegoch
@wegoch
@paappii
ወይ አያቶቻችን…… ?
[ሰሎሞን ሹመቱ]
________________________
ሰፈር ዉስጥ ተቀንጠን ትንሿ የጓደኛችን የሃይሌ እህት መጣችና ቁጭ አለች! ወሬያችን ይገባታል ብለን ስላላሰብን ከሷ ፊት ሊወሩ የማይገቡ ፖለቲካዊ ወሬዎችንም እያወራን ነው፡ በዚህ መሀል ስለ ሀገሪቱ ብጥብጥ አንስተን ስናወራ፥ ቀልጠፍ ብላ "እረ አባየ እኮ ይህችን ሃገር እንደዚህ አይነት ምስቅልቅል ዉስጥ የከተታት የአያቶቻችን ጡር ነው! ብሏል አለችን። ሁላችን ደንግጠንም ተገርመንም። ሁላችንም ወደ ሃይሌ ስንዞር ባክህ እኔ ሰምቸ አላውቅም እንደዚህ አይነት ነገር አለ ወደኔ አፍጥጦ። ወዲያው በዚያው ሰአት የጓደኛችን አባት ከስራ ወደ ቤት እየመጡ ድንጋያችን ላይ ተኮልኩለብ ሲያገኙን ሰላምታ ሰጡን እኛም የጅምላ ሰላምታ ሰጠናቸው።

ታድያ ከመሀላችን አንዱ " ጋሼ ኢትዮጲያን ለዚህ ሁሉ ያበቃት የአያቶቻችን ጡር ነው ብለዋል አለችን፥ እንደት እንደዛ አሉ? አላቸው። እርጅና በተጫነውና በጎረነነው ድምጻቸው ማብራራት ቀጠሉ "አያቶቻችን አገልጋይ ባሪያዎች ነበሯቸው፥ ታድያ በአንድ ወቅት የኛ አያቶች ልጃቸው ስትሞትባቸው " የኔ ልጅማ ብቻዋን መቃብር ጨለማ ዉስጥ አትገባም ብለው ልጃቸውን መቃብሩን እንድታላምድላቸው ብቻዋን እንዳትፈራ ብለው አንዷን ባሪያቸውን ከነ ነፍሷ ቀብረዋታል። አሉ። ታድያ የዚህ ጡር ከዚህ የባሰ ዉጥንቅጥ ዉስጥ ቢያስገባንስ ይገርናል እንደ?" ብለው ሁላችንንም በግልምጫ ቃኙን እውነትነቱን የተጠራጠሩ አይመስሉም ጓደኞቸ። እኔ ግን ሁለት ነገሮች ተምታቱብኝና ማብራሪያ በመጠየቅ አይነት ጠየኳቸው፥

"ጋሸ ግን የሚጣ አያቶች ናቸው ወይስ የእርስዎ አያቶች ናቸው ይሄን ተግባር የፈጸሙት "አልኳቸው። አልገባኝም ምን ለማለት ነው? አሉኝ፥ እኔም ቀጠልኩና "ማለቴ ሚጣም ስትነግረን እኮ አያቶቻችን ነው ያለችን እርስዎም ሲነግሩን አያቶቻችን አሉ! መቸም የእርስዎና የነ ሚጣ አያቶች የተለያዩ ናቸው አይደል? " ስላቸው፥ ግራ እንደመጋባት ብለው ሊያብራሩ ሲጀምሩ፥ ጓደኞቸ ጫጫታ ባለው ሁኔታ "እየው ይሄ ነገረኛ አሁን ይሄ ምን ማብራሪያ አለው፡ በቃ ህግ ተማሪ ስትባሉ" ምናምን እያሉ ሲንጫጩ፥ ቆዩ እንጂ እኔ እኮ እሳቸውን ነው የጠየኩት መልስ ሊሰጡኝ ነው እኮ አልኳቸው ቆጣ ብየ። ሁሉም ዝም አሉና መልሳቸውን ስንጠብቅ "አይ ልጁስ ልክ ብለሀል! አባቴም እኮ አያቶቻችን ብሎ ሲያወራ ነው የሰማሁት" አሉንና፥ ግን ካላደረጉት ለምን ብለው ያወሩታል ይሄን ብለው ጥያቄ መልሰው አቀረቡልኝ። "እኔ እንኳን የድሮ ሰው ራስቸውንና ቤተሰባቸውን ከፍ ያደረጉና ያገነኑ ስለሚመስላቸው ይሆናል ብየ እገምታለሁ!" አልኳቸውና በተቀመጥንበት ትተውን ሄዱ።

በዚህ መሀል አንዱ ጓደኛችን ይሄ ጊዜን የኋሊት የሚመልሱት ሰውየ ጋ ለምን ሄደን አንጠይቅም ግን የምር እንደዛ የሚያደርግ አለ ግን? እውነት ይመስላችኋል? የሚል ሀሳብ አነሳ።
ጊዜ የሚመልሱ ሰውየ በአካባቢያችን አሉ " የጊዜ አለቃ " ይሏቸዋል። የኋሊት ዘመንን ጎትተው በዛ ዘመን የነበሩ ሰዎችን አነዋወር ሁሉ እንድትጠይቅ እና እንድታይ ያደርጉሃል ይባላል። ሄደን ባናውቅም። ሁላችንም በዝምታ የተስማማን መሆኑ ያስታውቃል። ልንሄድ ቀጠሮ ይዘን በዛ ቀን ከዛ ሰው ጋ ሄድን፡

የመጣንበትን ነገርናቸውና ማንን እንደምንፈልግ ሲጠይቁን ሃይሌ ቀደም ብሎ የእኔን ፥ ቅድመ አያቶች፥ ቅመ አያቶችና ቅማቶች የሰሩትን ማየት ነው ምንፈልገው፡፡ ከዛ መጡ መደዳውን ተደረደሩ ቅድመ አያቴን "ልጃችሁ ስትሞት ብቻዋን እንዳትሆን ሰው አብራችሁ ቀብራችሁላታል እንደ" ሲላቸው። አዎና ! አሉ በኩራት። እኔ ግን ወሽመጤ ስብር ብሎ ትንፋሽ መተንፈስም ተሳነኝ፡፡

እንደ መቸ ደሞ ሰው በነፍሱ ይቀበራል እንደ አላቸው። " አይ እኛ ሳንሆን ይሄን ያደረጉት አያቶቻችን ናቸው አሉ እኛ አልደረስንባቸውም አሉ! ይህን ሲናገሩ ትንፋሸ ተመለሰች። ኡፍፍ እንደት ይጨንቃል ሆሆ። ሌላውን ተወው የሳቸውን አያት ፈልጋቸው ስለው ዞር ዞር አለና አኛኛቸው። ከፊታችን አምጥቶም ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡

" እሳቸው ቆፍጠን ብለው፡ ይገርምሃል ዘራችን የባለአባት ዘር ነበር፡ እና ግን ዘራቸውን መተካት አልችል ብለው ፈጣሪያቸውን ቢማጸኑም አልሰማ አላቸው፡፡ ወይ ሰምቶ ዘገየባቸው፡ በእድሜያቸው የማታ የማታ ምን የመሰለች ቆንጅየ ሴት ልጅ በእቅፋቸው ሰጣቸው፡ አይናቸውን በአይናቸው አዩ፥ ወልደው ሳሙ፡፡ በንጉስ ስርዓት ያደገችው ልጃቸው ታድያ ለአቅመ ሄዋን በደረሰች ጊዜ የነገስታት ዘር ለሆነ ኮበሌ ታጭታ ሳለች፥ ይሄ ነው የማይባል ነገር ነፍሷን ከስጋዋ ለየው፥ ይህች ብቸኛ ልጃቸውን ሞት ነጠቃቸው። ከዛማ የናትና አባቷን ነገር አታውራው እናትና እና አባት እንደዛ ሲያዝንም ታይቶ አይታወቅም፡ ፊታቸውን ነጩትልባቸውን በጥቁር ድንጋይ ወገሩት ጸጉራቸውን ተላጩት። ግን ያችን ለአፍታ ጨለማ ዉስጥ ቆይታ የማታውቅ ልጅ ከመሬት በታች አፈር ሊያለብሷት መሆኑ ሲታወሳቸው 9 ወር የተሸከመ የእናት ማህጸን አልችል አለ፥ እንባቸው አባይን ሆነ። በዚህ መሀል አባት ብድግ ብለው ጓዶቻቸውን ጠቀስ አድርገው ጠሩና 'ልጀ ብቻዋን ቀብር አትወርድም 3 ቀን እንኳን የምታላምዳት አንዷን አብራችሁ አስገቡልኝ፥ የኔ ልጅማ ብቻዋን እዛ ጨለማ አትቀመጥም' አሏቸው። ጓዶቻቸውም ተስማምተው ከባሪያዎቻቸው አንዷን መርጠው ለ 3ቀን መቃብር እንደምትቆይ በ3ኛው ቀን ሲመለሱ ካልሞተች እንደምትወጣ ተስማምተው ጨረሱ፥ ለነገሩ መስማማት የለውም ያሏትን ነው ምታደርገው፡፡
®®®®®®®
ይሄን ሁሉ ሲያወሩ ራሴ አየር እንደሚሞላ ኳስ ሲወጠር ይታወቀኛል፥ ግን እውነቱን ልናውቅ ነውና የመጣነው ማዳመጡ ግድ ነው። " ከ. .ዛ ብለው ነገሩን ቀጠሉ፥ ከዛ ልጂቷም ተቀበረች ያች ባሪያም አብራ ትቀበረች በሶስተኛው ቀን ግን ባሪያይቱም ሞታ ተገኘች" ብለው አያቶችችን እንደ ተረት ንግረውናል። እንዲህ ያለው የባላባት ዘር ነበርን። አሉ።
®®®®®®
በጣም ተበሳጭቸ "እንደ ተረት ሳይሆን ይሄ በትክክል ተረት ተረት ነው፡ እንደ ተረት የተነገረ አይደለም፡፡ ሄይ ተነሱ እንሂድ ባክህ በዚህ አያያዝ አያቶቻችን እየተባለ አዳምና ሄዋን ጋ መድረሳችን አይቀርም። ብየ ቀድሜያቸው ወጣሁ። ስንቱ ተረት ይሆን ታሪካችን ሆኖ የተጻፈልን?ወይ ዘመን ብየ " አይ አያቶቻችን አልኩኝ"

@wegoch
@wegoch
@paappii
'የመንፈስ ችግር'
እጓለ ገ/ዮሐንስ
.
.
ነገራችን ሁሉ የእንባይ ካብ ሆነ፡፡ ታጥቦ ጭቃ መሆናችን ያስፈራኝ ከጀመረ ቆየ፡፡ ከተስፋ ይልቅ ፍርሃት ካሸነፈኝም ጊዜ ነጎደ፡፡ የእኛ ነገር ጉም እንደመጨበጥ ነው፡፡ በሀሳባችን፣ በተግባራችን የሽንፈት ሙሽሮች ሁነናል፡፡ ደንቆሮነታችን አብቦ፤ አለማወቅ ገሎናል፡፡ እንደው አለመዳናችን ለምንኖርበት ትውልድ መለያ ምልክቱ ነው፡፡
ሊቁ እጓለ ገ/ዩሐንስ ከአውሮፓ ትምህርታቸው ተመልሰው ሀገር ቤት ተገኙ፡፡ በ1953 ሲመለሱ ተስፋ ካደሩት ነገር በላይ ክፉ ያረገዘው የሀገራቸው ባህሪ እና የሰማይ ምጡ አስፈራቸው፡፡ ይህንን ጉዳይም 'የመንፈስ ችግር' አሉት፡፡
የመንፈስ ችግር ያሉት ነገር ምንድን ነው? ትናንት የመንፈስ ችግር ያሉት ደዌአችን ዛሬስ ላይ ተጣብቆብን የለም ወይ!? የትናንት ህመማችን ዛሬም ድረስ ተሻግሮ የህመምተኞች ሀገር ፈጥረናል? የመንፈስ ችግር ተብለው ከጠቀሳቸው ጉዳዬች ውስጥ አንዱ ይህ ነው፡፡
''አንድ ሰው የማይመስለውን ነገር ለማፍረስ ብቻ ይሰለፋል'' ይላሉ፡፡
ትናንት ይህ ባህሪያችን በየአምዱ ተስተውላል፡፡ ዛሬም ይህ ደዌአችን የመገናኛ መንገድን ቀይሶ እንታመምበታለን፡፡ የኛ ነው ከምንለው ሀሳብ ውጪ ለመስማት ጆሮ የለንም፡፡ መርምረን ክፉና ደጉን አንለይም፡፡ ፊደል ቆጥረናል ያሉትም አይደማመጡም፡፡ ብዙዎች ማፍረስን እንጂ መገንባትን አልተለማመድንም፡፡ የአፍራሽ ግብረ ሀይል ብዙ ነው፡፡ ሀገሪታም በዚህ ምክንያት ምጥ ውስጥ ገብታለች፡፡
ሁለተኛው የሚያነሱት የመንፈስ ችግራችን ስለ ትምህርት ነው፡፡ ''ሰው ከሙሉ የሰውነት ደረጃ የሚደርሰው በትምህርት ነው፡፡ ሰው ትክክለኛውን ትምህርት ካገኘ ለስላሳና (ኖብል) እግዚአብሄርን የሚመስል ፍጥረት ነው፡፡ ትምህርት ያላገኘ እንደሆነ ግን በምድር ካሉት አራዊት ሁሉ የባሰ ነው ብለው አበክረው ይናገራሉ፡፡''
የትውፊታዊው ትምህርት በሀገራችን የረጅም ዘመን ታሪክ አለው፡፡ በምግባር፣ በስራ ተተርጉሞ በአለማዊውም፤ በመንፈሳዊውም አለም ምስጉን ነበርን፡፡ የዘመናዊው ትምህርት መምጣት ግን የራሳችንን ውበት አስጥሎናል የሰው ወርቅ የምንናፍቅና፤ የራሳችንን ችግር በሌሎች እውቀት ለመሸንገል ዋጋ ከፍለናል፡፡ (ዘመናዊው እውቀት አልጠቀምንም እያልኩኝ አይደለም፡፡))
የትምህርት መንገዳችን ስለሌሎች የሚነግር እንጂ ለራስ የተፃፈ አይደለም፡፡ በስነ ህይወት፣ በህዝብ አስተዳደር፣ በህግ፣ በከዋክብት ጥናት፣ በህክምና የነበረንን ፅድቅ ትተን ከሰው ጓዳ ውለናል፡፡ ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ተረቱ በኛ ላይ ደረሰ፡፡ ከፈረንሳውያኑ፣ ከእንግሊዚያውያኑ፣ ከአሜሪካውያኑ የተማርነው ፈቀቅም አላደረገንም፡፡ እንደውም ጥራዝ ነጠቅ አደረገን፡፡ የራሳችን የህይወት መላ ከማበጀት ይልቅ ሌሎችን ለመምሰል በረታን፡፡ ትምህርቱ ሳይሰርፅብን፤ እውቀት ሳይደላደልብን ሌሎችን መሰልን፡፡ የራስን ጥለን የሰው አንጠልጥለን፡፡ የሀገር ቤት ትውፊታዊ እሴትን ረስተን እኔን ብቻ አልን፡፡ እኔን ብቻ ስሙ የሚለው ሀሳብም ከማህበራዊ ህይወት፣ ከፖለቲካው ተዛምቶ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነ ነገራችን፡፡ ነገራችንን አድካሚ፣ አሰልቺ ሆኖ ለስላሳ ፍጥረት ከመሆን ይልቅ ወንድም፤ በወንድሙ ላይ ተነስቶ የአውሬ ባህሪያችን በተደጋጋሚ ጊዜ ታየ፡፡ መሪር እንባን የእለት ውሎአችን ሆነ፡፡ እውቀት ሳይሰርፅብን በአብዬታውያን ወንድሞች ሀገር ጉድ ፈላባት፡፡
በሀገራችን በኢትዮጵያ ከሚያደክሙን የህይወት ህመማችን አንዱ የብሄር ትርክትና እና የዘረኝነት መንፈስ ነው፡፡ ክፉ መንፈስ ነው፡፡ ይህ የዘውጌ ሀሳብ ተመሳሳይ አእምሮ ያላቸው ሰዎች፣ ለተፎካካሪነትን እድል የማይሰጥ የሀሳብ ጭራን ይዘው ይኖራሉ፡፡ ዘረኝነት እና ብሄር ተኮር ሀሳቦች ከሌላው ወገን የሚመጣውን ሀሳብ አይሰሙም፡፡ አሸናፊ ሀሳብ ከሌላው ወገን የሚመጣ እንደሆነ አያምኑም፡፡ በንስር አይን ከማየት ይልቅ እንደ ጋሪው ፈረስ ሁናል ጉዛቸው፡፡ ይህንን በሽታችንን እጓለ ገብረዩሐንስ ''ዮሐንስ ጠምቆ ዮሐንስ ጠጣ ይሉታል፡፡'' ሀሳብ ሀገር የለውም፣ ምክንያታዊነት እና የህሊና ጉዞ ሁሉን በማከለ መንገድ የሚጋዝ አቃፊ ማንነት ነው፡፡ እከሌን የተሻገረ የሰውነት ጉዞ ነው፡፡
የመንፈስ ህመማችን ስላሳመማቻቸው መዘርዘሩን ገፍተውበታል፡፡ ነገር በብርሌ ከሆነልን ብለው ቀጥለዋል፡፡ ህሊናን እንደ አኩፋዳ ይስሉታል፡፡ በአኩፋዳ ውስጥ ጥሬውም፣ ብስሉም ይገኝበታል፡፡ ይህንን መደበላለቅ የሚያስተካክለው ደግሞ ሕግ ስነስርአት ነው፡፡ ስለ ህግና ስነስርአት ትናንትም ዛሬም ድኩማን ነን፡፡ ''ለህሊና ዋና ጠላቱ ድብልቅልቅ ዝብርቅርቅ ነገር ብቻ ነው፡፡''
የህሊናችን ዋና ጠላቶች እኛው ነን፡፡ በህግ፣ በደንብ፣ በስርአት ከመኖር ይልቅ በጉልበት፤ በማን አለብኝነት እንነዳለን፡፡ በዚህ ውስጥ በሚደርሰው ጉዳት ራሳችን እስካልተነካን ድረስ አፋችን አይከፈትም፤ እጃችን አይሰራም፡፡ እኔ ምን አገባኝ እንላለን፡፡ የወንድማችን፣ የእህታችን መነካት ግድ አይሰጠንም፡፡ የለበጣ ኑሮ አሸንፎናል፡፡ ከአንገት በላይ ኑሮን ይዘነዋል፡፡ እኔ ብቻ የሚለው ምርጫችን የዘወትር ጉዛችን እስረኞች አድርጎናል፡፡ የተረጋጋ፣ የተስተካከለ፣ ዜማ ያለው ኑሮ ያስፈራናል፡፡ በሬ ወለደ፣ ታይታ ኑሮ አሸንፎናል፡፡ ስርአትና ህግ ለሁላችን ጌጥ ይሆን ነበር፡፡
አንድ ሰው አሻግሮ ሳያይ ሲቀር፣ እስከ አፍንጫው ሲያስብ ችግር እንዳለ እናውቃለን፡፡ የኔ ትውልድ የዚህ ቀይ መብራት ነዋሪ ነው፡፡ ሀሳባችን፣ አለማችን ከአፍንጫችን አይዘልም፡፡ ድርጊታችን፣ ውሳኔአችን፣ የምንፅፈው ጉዳይ፣ ስድድባችን፣ አፀያፊ ምርጫችን የታሪካችን አንድ ክፍል እንደሆነ ረስተናል፡፡ እንደ ንፋሱ አመጣጥ ነው ጉዛችን፡፡ ህልም ያለን አንመስልም፡፡ የመንገድ፤ የመንገዱን ነው የምናስበው፡፡ ሊቁ እጓለ እንዳሉትም የመንፈስ ችግራችን ''ጎልማሳ ጦርም ሆነ ሽመል አርቆ ይወረውራል፡፡ ዓላማውን ሳይመታ ቢቀር ከክንዱ መድከም ብቻ ሳይሆን ከዓላማው ወላዋይነት ሊሆን ይችላል'' ብለዋል፡፡
እኛ እዚህ ውስጥ አናልምም፣ ለኢላማችን አንተኩስም፣ አቅሙም፣ ክህሎቱም የለንም፡፡ የእኛን የህይወት ጉዞ የሚያውቀው የነገው ንፋስ ነው፡፡ (በእውቀቱ እንዳለው!))
እነዚህ የመንፈስ ችግሮች በህይወት እኛን፤ በታሪክ ውስጥ ደግሞ ሀገር እየጎዱ ነው፡፡ እኛም ዘመናችንን እንድንባርክ፣ የታሪክ ሸክማችንን ለማቃለል ብርቱ የሆነ ጥሪ አለብን፡፡ ሊቁ እጓለ የመንፈስ ችግራችን ብቻ ሳይሆን፤ የመውጫ መንዱን አመላክተዋል፡፡ አንደኛው የመፍትሄ ሀሳባቸው ''በአሮጌ ቤት የሚኖረውን ሰው ተጠግተህ ቤትህ የማይረባ ነው ማለት አይገባም፡፡ ከበረቱ አጠገብ አዲስ ቤት መሥራት ነው ይላሉ፡፡ ይህ ሀሳብ በድርጊት ገላጭነትን ይነግረናል፡፡ ባለጌ ከማለት ይልቅ፣ ጨዋ የሆነውን ነገር አድርጎ ማሳየት፡፡ ዘረኝነት ከማስፋፋት ይልቅ፤ ሰውነትን ማበረታታትን በማሳየት አስተማሪነትን ማስፋፋት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስለ ውይይት ፈዋሽነት፤ የመንፈስ ችግርን አዳኝነት ተናግረዋል፡፡ ''አንድም ሀሳብ የመጨረሻ ነገር ነው ብሎ በተረጋገጠ መልክ አያቀርብም፡፡ በጥያቄ መልክ አቅርቦ ከተነጋጋሪው ጋር በመከራከር አብሮ ወደ እውነት ለመድረስ ይጣጣራል፡፡ እውነት በእንዲህ ያለ ዲያሎጋዊ ማህበራዊ ጥረት ብቻ የምትገኝ ነች ብለዋል፡፡''
ማህበራዊ ጥረታችን ወደ እውነት ጉዞ የሚያደርግ አይመስልም፡፡ እውነት ከተራራው ጫፍ ናት፡፡ እርስ በርሳችን ወደ ገድል ለመገፋፋት የምንጥር እንጂ፡፡ የመንፈስ ችግራችንን ተረድተን፣ በማህበራዊ ውይይት ከእውነት ታዛ ለመኖር የምንጥር ከሆነ
ከደዌአችንን እንፈወሳለን፡፡ የመንፈስ ችግራችንን እንደ እውነት ከተቀበልንና ከደዌአችን ጋር መኖርን ካስቀደምን ሞት ቅርባችን ነው፡፡ መሞት ብቻ ሳይሆን ቀባሪ ያጣንም እንሆናለን፡፡

@wegoch
@wegoch
እሷ ማሪያ ትባላለች።
እናቴ ነች።
በዚያኛው በኩል የምታዩት ምስል ደሞ አባቴ ሴፍ ይባላል።
ከኔ ውጭ አንድ ሴት ልጅ አላቸው።
የልብስ ስራ በመስራት ቤተሰቡን ያስተዳድር ነበር። በአንድ ወቅት ጓደኞቹ ወደ ቤት መጡ።
ጀርመን ጠረፍ አካባቢ ስራ አለና እንሂድ አሉት። ባለው ገንዘብ ቤተሰቡን ማስተዳደር የከበደው ሴፍ ወሰነ። አብሮ ሄደ። እዚያ እንደደረሰ ግን ጥሩ ገንዘብ መላክ ጀመረ። እኛም ዘና አልን። እየቆዬ ግን ገንዘብ መላክ አቆመ። ምነው ሲባል በ1942 የሃገሬው መንግስት በማስገደድ ወደ ውትድርና እንደላከው ሰማን። በተመሳሳይ ጀርመን በከፍተኛ ጦርነት ውስጥ ገባች። የቤተሰቡ ጭንቀት
ከፍተኛ ነበር። ከሁለት አመታት በኋላ እናታችን ማርያ ዊናንዶ በመባል የሚጠራው ታዋቂ ሰውን ለመጠየቅ እድል አገኘች። እሱም "ሴፍ ደህና ነው። በፀደይ ራት ይመጣል" አላት። እናታችን እየበረረች መጣች። ትፍለቀለቃለች።
ቤቱን ማስተካከል ጀመረች። ግቢውን አረንጓዴ ለማድረግ ለፋች። ምክንያቱም
ፀደይ እየገባ ነው። ለአባታችን አምራ ለመታየት ተቆነጃጀች። ሁሉም ተደረገ።
ግን ፀደይ አለፈ፤ በቃ መጥቶ ሄደ፤ ድጋሜ ክረምቱ ሊገባ ነው። አባታችን ሴፍ ግን አልመጣም።
በአመቱ እናታችን አንድ ደብዳቤ ደረሳት። "ውድ ማሪያ፤ ባለቤትሽ ሴፍ በባለፈው
አመት በሬቨንፐርክ አርፏል" ይላል።
ነገር ግን እናታችን ማሪያ ከደብዳቤው ይልቅ የዊናንዶን ተስፋ መረጠች።
አባታችን አንድ ቀን ከጎኗ ሆኖ እንደሚያጫውታት አመነች።
26 አመታትን ይመጣል እያለች ጠበቀች። አባታችን በዛው ቀረ።
በየትኛውም ፀደይ ወራት እንደማይመጣ አወቅን። ከሁሉም ተስፋዎች የሚያመው የማይሆንን ነገር መጠበቅ መሆኑን አወቅን።

@wegoch
@wegoch
@paappii
የተለያዩ ሰዎች ቁጣቸውን (አለመስማማታቸውን) የሚገልፁባቸው መንገዶች። አብረናቸውም ለመኖር የሚረዱ ሙያዊ ምክሮች።
---------------
ሰው ከሰው ጋር ሲኖር ግጭት መከሰቱ የማይቀር ነው። ሁላችንም ከሥራ ባልደረባዎቻችን፣ ከቤተሰብ አባል ወይም ከጓደኛችን ጋር ፍትሃዊ የሆኑ ክርክሮች እና ግጭቶችን እናስተናግዳለን። አንዳንድ ሰዎች ግጭትን ወይም አለመግባባትን በቀላሉ ተረድተው በጥበብ ነገሩን ማብረድ ሲችሉ ሌሎች ደግሞ ጭራሽ ትንሿን አለመግባባት አስፍተው ወደ ትልቅ ፀብ እንዲያመራ የማድረግ ባህሪይ አላቸው።

አለመግባባትን ተረድቶ እንደየሁኔታው ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የሰዎችን ባህርይ መረዳት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የስነ-ልቦና ተመራማሪዎች ይናገራሉ። ለዚህም እንዲረዳ ቁጣን እና አለመስማማትንም በሚገልፁባቸው መንገዶች ረገድ ሰዎችን በ 4 ዋና ዋና ክፍሎች ያስቀምጧቸዋል። እያንዳንዱንም ሰዎች በጭቅጭቅ ጊዜ እንዴት ጭንቅላታቸውን ማንበብ እንደምንችል እና ምላሻችን ምን መሆን እንዳለበት እንደሚከተለው ይነግሩናል።

1. ነጭናጫ ሰዎች (Behavioral Anger)።

እነዚህ ሰዎች ባልተጠበቀ ሁኔታ እና ሰዓት የምቆጡ ሰዎች ናቸው። ቁጣቸውንም በቃል ወይም አካላዊ በሆነ መልኩ ይገልፃሉ። ቁጣቸው በጣም አስፈሪ ብሎም እቃዎችን በመወርወር እና በመሳሰሉት ብስጭታቸውን ሊገለፅ ይችላል።

ከእንደዚህ አይነት ሰዎችን ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል

እነዚህ ሰዎች ብዙ ጊዜ በራሳቸው መተማመን ዙሪያ ክፍተት ያለባቸው፣ ስለነሱ መጥፎ ነገር ሲነገራቸው በቀላሉ የሚከፉ ሰዎች ናቸው። ምንም እንኩዋን ነገሮች ፈታኝ ቢሆኑም እራስዎ ተረጋግተው ነገሩን ለማረጋጋት ይሞክሩ እንጂ እሳትን በእሳት አይዋጉ። ምክንያቱም ቁጣቸውን የበለጠ ስለሚያባብስ። ተረጋግተው የተቆጡበትን ነገር እንዴት መፍትሄ እንደሚሰጡት ይጠይቁ። ጥፋተኛው ማን እንደሆነ፣ ትክክል ወይም ስህተት የሆነ ማን እንደሆነ ለማስረዳት አይሞክሩ ምክንያቱም ጭንቅላታቸው በጊዜው ምክንያታዊ በሆነ ሁኔታ ለመወያየት ዝግጁ ስላልሆኑ። ለወደፊቱም ምቾት የማይሰጣቸውን ነገርም በተቻለዎ መጠን አይነካኩባቸው።

2. ኃይለ-ቃል ወርዋሪ፣ በነገር የሚጎሽሙ (Verbal Anger)።

እነዚህ ሰዎች ቁጣቸውን የሚገልፁት ኃይለ-ቃሎችን በአሽሙር፣ በነቀፋ፣ እና መመሳሰሉት የቃላት ጦሮች በመወርወር ነው። አላማቸውም የሌሎችን ስሜት እና ስነ-ልቦና በመንካት ቁጣቸውን እና ቅሬታቸውን ለመግለፅ ነው ። ከተረጋጉ በኋላ ግን ብዙውን ጊዜ የሀፍረት እና የጸጸት ስሜት ይሰማቸዋል።

ከእንደዚህ አይነት ሰዎችን ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል

የነዚህ ሰዎች አላማ ስሜትዎን እና ስነ-ልቦናዎን መጉዳት መሆኑን ተገንዝበው ለኃይለ-ቃላቸው ብዙም ቦታ እንዳይሰጡ ለራስዎ በደንብ ይንገሩት። ይህንም ሲያደርጉ አላማቸውን ማክሸፍ ይችላሉ።አንዳንዴም እንደሁኔታው እያዩ በወረወሩት ቃል ዙሪያ ቀልድን ፈጥረው ለመመለስ ይሞክሩ። ይህን ማድረግ በቃሉ አለመጎዳትዎን ያስገነዝባቸዋል፣ አንዳንዴም በመካከላችሁ ያለውን ውጥረት ለማርገብ ይረዳል። ቃላታቸው ጠንክሮ ግን መስመር ሲያልፍ፣ ክስ ባልተሞላበት ነገር ግን በሰከነ እና ፈርጠም ባለ መንገድ መስመር እንዳለፉ ይንገሯቸው። ሁሉም ካልሰራ ግን ዝምታን መርጠው በራሷቸው ጊዜ እንዲበርዱ ዕድልን ይስጧቸው።

3. ምክንያታዊ በሆነ መልኩ እና ለውጥ ለማምጣት የሚቆጡ (Assertive anger)።

እነዚህ ግለሰቦች ቁጣቸውን አወንታዊ ለውጦችን ለማምጣት ይጠቀሙበታል። ሁኔታውን በጥሩ ሁኔታ እና በንፅፅር እያደረጉ በረጋ እና በዘመናዊ መልኩ ከሌሎች ጋር ያላቸውን ችግሮች በግልጽ ይነጋገራሉ። ከዚያም ከሌሎች ወገኖች ጋር ችግሮችን እንዴት መፍታት እንደሚችሉ ይወያያሉ።

ከእንደዚህ አይነት ሰዎችን ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል

እነዚህ ሰዎች ቁጣቸውን የሚገልፁት ሆን ብለው እርስዎን መጉዳት ፈልገው ሳይሆን የነገሩን መለወጥ በመሻት ነው። ብዙ ጊዜም የሚፈልጉት ለውጥ አውንታዊ ለውጥ በመሆኑ ለመረዳት ይሞክሩ እና መረዳትዎን ይግለጹላቸው። ከእርስዎም የሚፈልጉትን ነገር ለመስጠት ይሞክሩ፣ ለውጡንም ለማምጣት አብረው ለመተባበር ይሞክሩ።

ለምሳሌ በስራ ላይ ያለ ፕሮጀክትን እርስዎ እያጓተቱ መሆኑን አለቃዎ በምክንያት ቢገልፅልዎ፣ የነገሩን አሳሳቢነት መረዳትዎን እና እንዴት ማሻሻል እንደሚችሉ አብረው ይስሩ፣ ነገሩንም ለማሻሻል ቆራጥነትዎን ይግለፁላቸው።

4. በአፍ መስማማትን እየገለፁ ግን በሚያደርጉት ተግባራቸውን አለመስማማትን የሚያሳዩ (Passive aggressiveness)።

እነዚህ ሰዎች ያልተስማማቸው ነገር ሲኖር ፊት ለፊት መግለፅ (መጋፈጥ) አይወዱም። በቃላት ከመግለፅ ይልቅ መቃወማቸውን ቀስ እያሉ በድርጊታቸው መግለፅን ይመርጣሉ። ይህንም በማድረግ ሳይታወቅባቸው ሊያታልሉዎ ይሞክራሉ። አንድን ነገር በጋራ ለመስራት እቅድ ሲያዝ ባይስማሙበትም እሽታን ይገልፃሉ፣ ነገር ግን በሁዋላ እቅዱን ለማዳከም የሚረዷቸውን መንገዶችን ያፈላልጋሉ።

ከእንደዚህ አይነት ሰዎችን ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል

በነገሮች ላይ ከነዚህ ሰዎች ጋር ሲስማሙ፣ ፍርጥም እና ጠንከር ባለ መልኩ ውሳኔዎችን ለማስቀመጥ ይሞክሩ። ውሳኔዎችን ለማዳከምም የሚያደርጉዋቸውን እንቅስቃሴዎች በንቃት እያዩ ወደዉሳኔው ለማምጣት ይሞክሩ። አለበለዚያ ግን ግልፅ በሆነ መልኩ ድርጊታቸው እንደማይስማማዎት በግልፅ አፍረጥርጦ መንገር ያስፈልጋል።


@wegoch
@wegoch
@paappii

ምንጭ: sewasew
ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ የወደቀውን ጓደኛውን ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል፤አለቃውም መሞቱ ለማያጠራጥር ሰው ብለህ ህይወትህን
አደጋ ላይ እንድትጥል አልፈቅድልህም፤በማለት ፍቃድ
ይነፍገዋል!! ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል፤ከፍለጋ በኋላ እሱም ሞት አፋፍ ላይ ባደረሰው
ሁኔታ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል፤ አለቃውም”ይሞታል ብዬህ አልነበረም? ለሚሞት ሠው
ብለህ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል ነበረብህ፤ በማለት ይወቅሰዋል፤ወታደሩ ግን በስራው ደስተኛ ነበር !! አለቃዬ ይህኮ ምንም ማለት አይደለም፤ ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ ደርሸበት ያለኝን
ብነግርህ ትረዳኝ ነበር፤ አለቃውም ”ምን አለህ? ሲለው ወታደሩም ንግግሩ ቀጠለ....
«#እንደምትመጣ_እርግጠኛ_ነበርኩ »!!
ጓደኝነት ፀጋ ነዉ ለሁሉም ሰዉ አልተሰጠም

@wegoch
@wegoch
@paappii

#ከዙኪ ገፅ የተወሰደ
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (ልዑል መኮንን)
#ይነበብ
ውድ የቴሌግራምና ፌስቡክ ጓዶች እንዴት ናችሁ?

መቼም በዚህ ሰዓት 'ሰላም ነው?' የሚለውን ቃል ከአንደበታችን እንዳናወጣ በሀገራችን እየሆነ ያለው ነገር ያስረናል፡፡

አዎ፡፡ እኛ ከኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያውያን ጎን ነን !!! ኢትዮጵያ ምንጊዜም ድል ታደርጋለች፡፡ አዎ እኛ ከንግግር በዘለለ አንድ ነገር በጋራ ብናደርግስ ፡ ብለን ወሳኝ ጉዳይ ለማከናወን ተነስተናል፡፡

ይህ ጥሪ ለሁላችሁም ነው ህዳር 20 እሁድ እለት #የግጥም_አብዮት እና የ #ግጥም_ብቻ ከተሰኙት ግሩፕ ጋር ለመልካም ነገር ዘምታችሁ #ደሜን_ለሀገሬ እያላችሁ ትለግሱ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

እኔ ከኢትዮጵያ ጎን ነኝ የሚል ሁሉ ደሙን ሰጥቶ አለሁልሽ ይበላት፡፡ መልካምነት ዋጋው ትልቅ ነው ወደ ህይወታችን ይዞ የሚመጣው በረከትም አያልቅም፡፡ ኑ ለመልካም እንዝመት! ሩቅ ያላችሁ በየትኛውም ክፍለ ሀገራት የሚገኙ #ለመልካም_ዘማቾች ቀኑን በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቀይ መስቀል በመሄድ እለቱን ያስቡ፡፡

በዚህም መሰረት ፦

ህዳር 20 (እሁድ )
ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ
ስቴዲየም ወደሚገኘው የቀይ መስቀል ማህበር ግቢ ውስጥ እንገናኝ 🙏🙏🙏

*
Telegram
@Tkida and @gebriel19

#ለመልካም_ዘማቾች
#የግጥም_አብዮት
#ግጥም_ብቻ

📍📍📍 በዚህ ዘመቻ ላይ አብረን እንዘምታለን የምትሉ ሁሉ ድምፃችሁን አሰሙ ፡፡ #Share

📍📍📍 ኢትዮጵያዊ ነን የምንል ሁሉ ቢያንስ ለ10 ሰው ይህንን በማካፈል ዘመቻውን እንቀላቀል/እንደግፍ 🙏

@getem
@getem
Huawei የቴሌኮም ማስፋፊያ ፕሮጀክት ላይ እሰራ በነበረ ጊዜ ቻይኖችን
በጣም የሚያማርራቸው ነገር ቢኖር የዓመት በዓሎቻችን ብዛት ነበር።
አዲስ ዓመት አክብረን ወዲያው መስቀል ይመጣል። እኛም መስቀሉ የተገኘበት
ምናምን ነው ብለን ፈቃድ እንጠይቃለን። አለቃም ይሁን እሺ ይሁን ብሎ ይፈቅዳል። ከዛ ገና ላይ ፈቃድ ፈልገን ምክንያቱን ሲጠይቀን ጂሰስ የተወለደበት እለት መሆኑን ነግረነው መልካም በዓል ብሎ ሸኘን። ወዲያው ጥምቀት መጣና ጂሰስ መጠመቁን ምክንያት በማድረግ ፍቃድ ጠየቅነው። እየመረረው ፈቀደ። ፋሲካ ደረሰ። አለቃን ሰብሰብ ብለን ከአርብ አስከ ሰኞ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ፈቃድ እንዲሰጠን ጠየቅነው። በምሬት: _"ጂሰስ ምን ሆነ ደሞ?" አለን።
"ሞተ" አልነው።
"ግልግል" አለ
ወዲያው አንዱ ከመሃላችን ''ኧረ እሑድ ይነሳል"

@wegoch
@wegoch
@paappii
#Alex mamz
መናደፍ የጊንጡ ባህርይ ነው!

" አንድ ጥበበኛ ወጣት እጅግ በሚያምርና ዕይታን በሚስብ ወንዝ ዳርቻ ተቀምጦ ሳለ በንፋስ ተገፍቶ ወደ ውሃው የወደቀ እጅግ በጣም አስፈሪ ጊንጥ ይመለከታል ።

የጊንጡ ህይወት እንዳያልፍ ብሎ በማሰብም ይታደገው ዘንድ ወስኖ ሊያወጣው እጁን ወደ ወንዙ ሰደደ። ጊንጡ ግን ህይወቱን ሊታደግ ለሚጥረው ሰው ምላሹ መንደፍ ሆነ። በጊንጡ አፀፋ የተደናገጠው ወጣት በቅፅበት የሚነዝረው እጁን አነሳ።

ነገር ግን አንዲትም ደቂቃ ሳይዘገይ ስቃዩን እንደተሸከመ ለሁለተኛ ጊዜ የዚያን ጊንጥ ህይወት ለማዳን እጁን ዳግም ሰደደ። አጅሬ ጊንጥም ለሁለተኛ ጊዜ ተናደፈ። ወጣቱ በሲቃ ውስጥ ሆኖ እየተዝለፈለፈ የተነደፈ ጣቱን በጨርቅ ጠቅልሎ ለሶስተኛ ጊዜ እጁን ወደ ጊንጡ ከመሰንዘር አልቦዘነም።

ይሄን ጊዜ ድራማዊ የሚመስለውን ትዕይንት በቅርብ ርቀት ሆኖ ሲከታተል የነበረ አንድ ሰው በመገረም እንዲህ ሲል ጮኸ

« አንተ ሰው! ምን እስኪያደርግህ ነው የምትጠብቀው ? እየነደፈህ ለምን ልታድነው ትጥራለህ ? ለምን አትገድለውም ?» ይለዋል።

ወጣቱ ግን ለዚያ ግለሰብ የሚሆን ጆሮ ያለው አይመስልም ። ላመል እንኳን አንገቱን ወደ ሰውየው ሳይመልስ ጊንጡን ለማዳን ጥረቱን ቀጠለ ። በመጨረሻም ተሳክቶለት ጊንጡን ከሞት ታደገው።

ከዚያም ቀድሞ ጊንጡን ስለመግደል ምክር ለግሶት ወደ ነበረው ግለሰብ እያማተረ እንዲህ ሲል በጩኸት ተናገረ

« ስማኝ ወዳጄ ... መናደፍ የጊንጡ ባህርይ ነው ፤ የኔ ባህርይ ደግሞ ማዘንና ማሰብ ሆነ ። ታዲያ ስለምንድን ነው የኔ ባህርይ ከርሱ ባህርይ የከፋ እንዲሆን የምትመክረኝ ? » አለው።

//

ምንም እንኳን አንዳንድ ጊዜ እንዲህ እንደ ጊንጡ በመናደፍ እያቆሰሉህና እያደሙህ ፤ እየገዘገዙህና እየሸረከቱህ የሚመሳሰሉ ሰዎች ቢኖሩም እምነትህ ባጎናፀፈህ መልካም ሥነ ምግባር ልትገራቸውና ልታቀርባቸው ግድ ይልሃል። በዙሪያህ ያሉ አካላት ወደ እልህና አላስፈላጊ ስሜት ውስጥ እንድትገባ ቢያደርጉህና ያልሆነ ሥነ ምግባር ውስጥ እንድትዘፈቅ ቢወተውቱህም ጆሮ ልትቸራቸው አይገባም ። “

【እርካብና መንበር 】
ከ ዲ ራ አ ዝ
[ገፅ : 103 - 104 ]

@wegoch
@wegoch
@paappii
አስቾኳይ የእርዳታ ጥሪ ለ እህታችን !!
★ በቅንነት ሼር ሼር ሳያድርጉ እንዳያልፉ

የሕይወት አድን ጥሪ ወገን ለወገን ደራሽ ነውና

#ETHIOPIAN || ሀያት ኢብራሂም ኡመር ትበላለች የ 11class ተማሪ ነች በ ባሌ ጎባ ነዋሪ ስትሆን በደረሰበት ከፍተኛ በሆነ የኩላሊት ህመም ሁለት #ኩላሊቶቹዋ ከጥቅም ውጪ ሆነው ዲያለሲስ እየተደረገላት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ትገኛልች ።

ውድ ወገኖች ለእህታችን በሃኪሞች በተነገረው የቀድሞ ጤንነቱ እንዲመለስ ያለው አማራጭ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ ብቻ እንደሆነ #የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ ወደ ውጭ ሃገር መሄድ ይኖርበታል ለህክምና በጠቅላላ 2,000,000(ሁለት ሚሊዮን ብር)ያስፈልጋታል ውድ ወገኖች ወገን ለወገን ደራሽ ነውና ለህታችን #ህይወት ለመታደግ የእርዳታ እጆቻቹ እድትዘረጉለት ዘንዳ በፈጣሪ ስም እንማፀናለን መርዳት ባትችሉ እንኳን ለሚረዱ ሰው ሼር በማድረግ እድተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን!

የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር
+251925386501

እንዲሁም ቤተሰቡዋ ጋር

0920942369
0912823605

በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ !! በቅንነት ሼር ያድርጉ
ፊት ለፊቴ ቡና እየጠጡ ኬክ የሚበሉት ጥንዶች ሸ ር ሙ ጣ ሊሉኝ ይችላሉ። የማለትም መብት አላቸው. . . ሁሌ ከማንም ጋር ስለሚያዩኝ. . .ሁሌ እነሱ
ስለማይለዋወጡ. . .፤ የልቤን ጓዳ የሚፈትሽ ወንድ በማጣቴ የሚያገኘኝ ሁሉ ቢያውቀኝ እያልኩ ጭኔን እከፍትለታለው. . .በጋለ ስጋው ይ ቦ ረ ቡ ረ ኛ ል! ምን አልባት. . .እዛ ጥግ ትንሽ እህቱን ስፕራይት የሚያጠጣት የሚያምር ነጭ ጫማ ካኪ ሱሪ፣ ነጭ ቲ-ሸርት በቀይ ጃኬት የለበሰው ባለ ሉጫ ፀጉሩ ቀይ ወጣት፣ ወደ'ሷ አትዪ ይላት ይሆናል. . . እህቱን! መቁላላቴን አይታ እንዳትባልግበት. . . ዛሬ ዛሬ የልጅነት ትውስታዎቼ - ጓደኞቼ. . . በመንገድ ሲያዩኝ ፊታቸውን ያዞሩ
ይሆናል፣ መንገድ ይቀይራሉ። ልቅነቴ እንደ ጉንፋን የሚጋባ እየመሰላቸው. . .
ያቺ ከርታታ እናቴን ካየዋት ስንት ጊዜዬ? ለምንድነው ድምጿ እንኳን የማይናፍቀኝ? ተቀይማኝ ይሆን. . .አባቴ ሞቶ ለቅሶ ስላልደረስኩ. . .ለበዓል እንደእኩዮቼ ባሌንና ልጄን ይዤ ሄጄ ቤቷን ስለማላደምቅ? ወጓን ስላላሳየዋት? .
. . ያኔ የህይወቴን መጨለም አልረዳ ስትለኝ. . .ልቤ ለዛ ቀይ ልጅ መሟሟቷ
አልገባ ሲላት. . .እሱን ለመርሳት መጠጥ ስጀምር አምሽቼ ስገባ. . . ማልቀስ ጀመረች፣ መጨረሻዬ ይኼ ነው ወይ አለችኝ. . .ለምን አትረዳኝም? አለመረዳቷ
የእናትነት ውለታዋን ይፍቀው ጀመር. . . . አደበዘዘው? እኔንጃ. . . ሸሸኋት ፍቅሬን
ወዳየኋት ቦታ ሔድኩኝ. . .ከወንድሜ ጋ ' እሱጋ እንድረጋጋ ላኩኝ. . . ፍቅሬ እየጨመረ. . .ፍቅሬ እየደበዘዘ የልቡን ባላቅም አፉና አካሉ ወደ ቀድሞዋ
ፍቅረኛው ተ ሸ ረ ሸ ረ! የኔም ልብ ውልቅልቁ ጠፋ. . . ዛሬ ዛሬ. . . የምወደው ሙዚቃ አስጠላኝ! ብቸኝነቴን ለመሸሽ በየካፌው በረንዳ ከአንዱ ጋር ቡናዬን አጣጥማለሁ ቡናው ልቤን ሲነካው ደስ ይለኛል የምሞት እየመሰለኝ. . .በዝናብ ውሽንፍር በቀኑ መጨለም የሚደበዝዘውን አስፓልት
አያለሁ. . .ማንም ይሄድበታል መንገዱ ፣ ልክ እንደ'ኔ ሰውነት. . .

@wegoch
@wegoch
@wegoch

#mesfin
2024/09/24 05:19:08
Back to Top
HTML Embed Code: