Telegram Web Link
ኢሬቻ - «ሆ...ያ...መሬዎ...መሬዎ»
___________________
ዘመድ አዝማዱ ተጠራርቶ የባህል ልብስ በመልበስ እርጥብ ሣርና አደይ አበባ በመያዝ «ፈጣሪን እናምናለን፤ በምድር ላይ በፈጠራቸው ነገሮች በሙሉ እንደነቃለን፤ እናደንቃለን...... ሆ...ያ... መሬዎ .... መሬዎ» የሚሉበት ወቅት ....ኢሬቻ ። ክረምቱ በሠላም ተገባዶ፣ ፀደይ አብቦ፣ ተራራውና ሜዳው አሸብርቆ፣ እንስሳቱ እርጥብ ሳር ግጠው ሲፈነጥዙ፣ በአሮጌው ዘመን የተዘራው በአዲሱ ዓመት ሲያፈራ የሚስተዋልበት ጊዜ .... ኢሬቻ።
ወዳጅ ዘመድ በሰላም በመገናኘታቸው ፈጣሪን እያመሰገኑ ወደ ወንዝ ወርደው ሙላቱ የቀነሰውን ወንዝ በእርጥብ ሳርና በአደይ አበባ እየነከሩ በክረምት ዶፍና ጎርፍ ዝናብ የደፈረሰው ወንዝ ውሃው መጥራቱን፣ የፀደይ መገለጫ መሆኑን ያሳያሉ። ቀጣዩ ወቅትም የሠላም፣ የጤና እና ሁሉ ነገር በፌሽታ የተሞላ ይሆን ዘንድ ፈጣሪን እየተማፀኑ ኢሬቻን ያከብራሉ።
የኢሬቻ በዓል ኢሬቻ ቱሉ እና ኢሬቻ መልካ በሚል ሁለት ዓይነት አከባበር አለው። ኢሬቻ ቱሉ የሚከናወነው የክረምቱ ዝናብ በሚጠበቅበትና ሰማዩ እየጠቆረ፣ ዝናብ እያረገዘ መሬት ከበጋው ፀሃይ እፎይ በምትልበትና ልምላሜ ለመላበስ በጉጉት በምትጠብቅበት ወቅት ነው። ኢሬቻ የክረምቱ ዝናብ በሚጠበቅበት ወቅት ካልጣለ በድርቅ ሳቢያ የተለያዩ ችግሮች እንዳይከሰቱ በየካቲት ወር አጋማሽ ከፍ ባለ ተራራ ላይ በመውጣት ፈጣሪ ክረምቱን ሰናይ እንዲያደርገውና ዝናብ እንዲያዘንብ የሚለመንበት ነው።
ኢሬቻ መልካ ደግሞ ክረምቱ ተጠናቆ ፀደይ ሲገባ መስከረም ወር አጋማሽ አካባቢ የሚከበር ሲሆን፣ በክረምት የውሃ ሙላት ተራርቆ የነበረው ዘመድ አዝማድ ተገናኝቶ ምስጋና እና ደስታ የሚገለፅበት ወቅት ነው። በዚህ ወቅትም አደይ አበቦች ፍክት ብለው ተማሪዎችም ወደ ትምህርት ቤት የሚተሙበት ብሎም የክረምቱ ጭጋግ ተገፎ የደስ ደስ ያለው ነፋሻማ አየር ሰዎች በአፍንጫቸው የሚመገቡበት ወቅት ነው። እሸትም ተቀጥፎ የሚቀመስበት የቀጣይ ኢሬቻ መልካ እና ኢሬቻ ቱሉ በናፍቆት የሚጠበቅበት ወቅት ነው። ኢሬቻም ሲከበር በርካታ ትሩፋቶችን ይዞ ብቅ ይላል። ኢሬቻ ጥቅሙም ዘርፈ ብዙ ነው። በተለይ ደግሞ ከጥንት ጀምሮ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ በስፋት ሲከበር የኖረው የኢሬቻ በዓለ ዛሬም ይከበራል። በዓሉም የያዛቸው ትርፋቶች እነሆ!
እርቅ የሚሰበክበት ማንኛውም የኢሬቻን በዓል ለማክበር ሲንቀሳቀስ መጀመሪያ ማድረግ ያለበት ነገር ቢኖር የበዓሉን ህግጋቶች ጠንቅቆ ማወቅ ነው። ከእነዚህም ውስጥ እርቅ ከሁሉም የቀደመ ሥፍራ ይሰጠዋል። በኢሬቻ በዓል «ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ፀሎት» የሚባለው ባህላዊ ትውፊት ወይንም ኢትዮጵ ያዊው አባባል በትክክል ይተገበራል። የኢሬቻ በዓል ከመጀመሩም በፊት እርቅ ይካሄዳል።
በሆራ አርሰዲ በተካሄደው የኢሬቻ በዓልም አባገዳው ድምፃቸውን ሞርደው እንዲህ አሉ። « አጠገባችሁ ካለው ሰው ጋር እጅ ለእጅ ተያያዙ፤ ሠላምታም ተለዋወጡ። አንዳችሁ ሌላችሁን አስቀይማችሁ ሊሆን ይችላል። ይቅር ተባባሉ። ይህ ቦታ እርቅ፣ ሰላምና አንድነት የሚሰበክበት ነው።»
የበዓሉ ታዳሚዎች በሙሉ እጅ ለእጅም ተያይዘው ይቅር ተባባሉ። እነሆ! ኢሬቻ በዚህ መልኩ እርቅን ይሰብካል። የበዓሉ አንዱ እና ትልቁም ዓላማ ልማት ለማምጣት ሰላም ይቀድማል የሚለው ነው። የኢሬቻ በዓል በአባገዳዎች እየተመራ በእርጥብ ሳርና አደይ አበባ ውሃው ውስጥ እየተነከረ ወደ ሰዎች ውሃው ፍንጥር... ፍንጥር.... ሳይደረግ የሰዎች ልብ በቅድሚያ በይቅርታ ሙላት መሸነፍ አለበት። ከፊትም ከኋላም ስጋት የለም። ይቅርታ ተሰብኳልና። በዚህ ስፍራ ስርቆት ማሰብም ፍፁም ከበዓሉ ጋር የማይሄድና የተወገዘ ነው። በዚህ አካባቢ ስለ በዓሉ ደስታ እንጂ ሰዎችን ማሳዘን እንደ ኢሬቻ ሕግ ፈፅሞ የተከለከለ ነው። በኢሬቻ እለት «የወደቀን አንሳ የሞተን ቅበር» የሚለው አባባል የወደቀውን እንስተህ ለባለቤቱ መልስ በሚለው የተተካ ይመስላል።
በርካቶችም የወደቀ ንብረት እያነሱ ይመልሳሉ። በቃ! እለቱ የማዘን ሳይሆን የደስታ፤ የኩርፊያ ሳይሆን የእርቅ፤ የመራራቅ ሳይሆን ሰው በአካል ብቻም ሳይሆን በመንፈስ ልብ ለልብ የሚናበብበት ልዩ ቀን ስለመሆኑ ከኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
የባሕላዊ እሴቶች ማስተዋወቂያና የቱሪስት መሳቢያ
የሚዘወተሩ አልባሳት ብዙም በኢሬቻ ቀን አይመከሩም። ኢሬቻ ከገዳ ሥርዓት ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያለው ከመሆኑም በተጨማሪ አለባበሱም በገዳ ሥርዓት የተቃኘ ነው። ወጣቶች፣ አረጋውያንና ሌሎችም በዓሉን የሚታደሙ አካላት አለባበሳቸው ባህላዊ ነው።
ከበዓሉ ታዳሚዎች መካከል አቶ ፍሰሃ ገብረ ሚካኤል ኢሬቻ፤ ባህላዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ይናገራል። በተለይ አባገዳዎች የሚጫሙት ባህላዊ ጫማ፣ የሚለብሱት ቡልኮና ቦላሌ እንዲሁም በገዳ ሥርዓት ከእግራቸው እስከ እራሳቸው ድረስ ባህላዊ እሴት ያረፈባቸው ሌሎች ጌጣጌጦች ቀልብ የሚስቡ ናቸው። ከዚህ ባሻገር ግን የቀድሞው ባህል እንደተጠበቀ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ፣ ኦሮሞ የራሱን ባህል እንዲያከብርና እንዲያዳብር ብሎም እነዚህ ባህላዊ እሴቶች አብይ የኩራት ምንጭ አድርጎ እንዲጠብቃቸው ለማስተዋወቅ ነው ኢሬቻ የሚከበረው።
ከዚህም በተጨማሪ በዓሉ የቱሪስት መዳረሻ እየሆነም ነው። ከጀርመን የመጣውና በኢትዮጵያ ባሕላዊ እሴቶች ቀልቡ የተሳበው ሚስተር ቲም ፓስካል ኢሬቻ ውበት ያለው በዓል እንደሆነ ይገልጻል። በርካታ ሰዎች እንዲህ በአንድ ላይ ተሰብስበው የሚያከብሩትና በአንድነት እየጨፈሩ የሚደሰቱባቸው በዓላት በኢትዮጵያ በርካታ ናቸው። የኢትዮጵውያን ባህልዊ እሴቶች የሚያደንቀው ጀርመናዊው ሚስተር ቲም የመስቀል ደመራ በዓልን እንደታደመና እንደተደመመም ያስታውሳል። «ይኸው የመስቀል ደመራ በዓል የፈጠረብኝን አግራሞት አጣጥሜ ሳልጨርስ ነው የኢሬቻን በዓል የታደምኩት። ኢትዮጵያውያን ያልተነካና ያልተበረዘ ባህል አላቸው። በቅኝ ግዛትም አልተያዙም። ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ቱባ ባህላቸው እንዲህ ከነድንግልናው የቆየው» ይላል። ኢሬቻ ኢትዮጵያውያን በአግባቡ ከተንከባከቡት የዓለም ቅርስ ሆኖ የቢሊዮኖችን ቀልብ የሚይዝ ህዝባዊ ትዕይንት እንደሆነ ያበስራል። ከዚህም ባሻገር በርካታ ቱሪስቶችን በመሳብ አገሪቱን የበለጠ ለማስተዋወቅ ትልቅ ሚና እንዳለው ሚስተር ቲም ፓስካል ይጠቁማል።

💚💛❤️
baga Ayyaanna kabajamaa ummata Oromootti issin gahee.
🔴⚫️⚪️
#በረከት_ግርማ

@wegoch
@wegoch
~ራሴው ማበዴ ነው~
(ሜሪ ፈለቀ)

"ተሳፋሪዎቻችን ይህ የበረራ ቁጥር 206 ነው… … ” ጭንቅላቷ እየሸወዳት እንደሆነ የማውቀው እንዲህ ማለት ስትጀምር ነው። በግልቡ እብደቷ እየጀመራት ነው ማለት ነው። እናቴ ናት!!

ይሄን ሀረግ ማለት ከጀመረች ትርጉሙ የዛሬ 20 ዓመት ወደ ኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆስተስ የነበረችበት ዘመን ላይ ናት… … ማርጀቷን አታውቅም፣ እኔንም አታውቀኝም ፣ ባሏ እሷን ትቶ ጓደኛዋን እንዳገባ አታውቅም ፣ ንብረቷን እንደተቀማች አታውቅም ፣ ጡቶቿ እንደተቆረጡ አታስታውስም ………… አንዳንዴ ራሷንም አታውቅም ~ ሰው ካላያት ራሷን ትጎዳለች። እብደቷ ሲነሳባት መከራዬ ናት። ምሬቴ ናት። ስቃዬ ናት። …… ጥለሻት ጥፊ ጥፊ ይለኛል። ጭንቅላቴን በቅውሰቷ ትዋጀዋለች። ብገላገላት የምታስመኘኝ መንቻካ አሮጊት ትሆናለች። መድሃኒቷን አትውጥልኝም፣ እንድነካት አትፈቅድልኝም ፣ አምናኝ እንቅልፏን አትተኛም…… ከየት የምታመጣው እንደሆነ የማይገባኝ ጉልበት አላት…… ታጠፋበታለች። እንደእኔ የምትጠላውና የምትፈራው አይኖራትም።

"የማላውቅሽ መስሎሽ? ቅናታም መርዘኛ! …… መድሃኒቱን በምግብ ለውሰሽ ልታበይኝ? አንድዬን ልትወስጂብኝ? እኔ አይናለም በህይወት ሳለሁ ቤቴ ሊፈርስ?” ትለኛለች ያገኘችውን እቃ እየወረወረችብኝ። አንድዬ የምትለው አባቴን ነው። የድሮ ባሏን።

"ማነሽ ደግሞ አንቺ? ወደ ቤቴ ውሰዱኝ… …… ኡኡኡኡኡ… … መድሃኒት ሊያበሉኝ ነው።……”

ዶክተሯ መጥቶ መርፌዋን እስኪወጋት በሷ እብደት እኔ አብዳለሁ። ስትረጋጋልኝ እብዷ እናቴን ከጠባቂ ጋር እቤት አስቀምጬ እወጣለሁ። …… ያበደች እናት እንደሌላት፣ አንዲት የኑሮ ሰበዝ እንዳልጎደለባት ፣ እንደደላት ሴት ሁኜ…… አዘውትሬ እንደምለብሰው ሙሉ ልብሴን አጊጬ ወደ ስራዬ እሄዳለሁ።

“ ኪዳነ ምህረት ምን በደልኩሽ? ምነው ጌታዬ ስቃዬን ቆለልክብኝ? ምናለ ብትገላግለኝ?” ስትል ደግሞ ትርጉሙ ወደ አሁን ተመልሳለች ማለት ነው። ያሳለፈችውን ስቃይ እያስታወሰች መታመም ጀምራለች ማለት ነው። እብደቷ ሲተዋት ታስለቅሰኛለች። ሆዴ ኩርምትምት ይልላታል። እንዳሰቃየችኝ ታውቀዋለች። ላበደችባቸው ቀናት እንግልቴ ስትከፍለኝ ጡት የለሽ ደረቷ ላይ ለጥፋኝ ታባብለኛለች። ምን መስማት እንደምትፈልግ አውቃለሁ።

"እማ በህይወት እስካለሽ አልተውሽም። ምንም ብታደርጊ እችልሻለሁ።” እላታለሁ። አትመልስልኝም። ብቻ ጨምቃ አቅፋኝ ትንሰቀሰቃለች። የአዕምሮ ህሙማን ሆስፒታል መግባት ሞቷ ነው። ትለምነኛለች። ሁለቴ ገብታ ታውቃለች። ይብስባታል እንጂ አይሻላትም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰውነቷም እየደከመ ህመሟም እያዛላት ነው። ትናንትና የሚሚን የሰርግ መጥሪያ ወረቀት ካየች ጀምሮ የበረራ ቁጥሯን መቁጠር ጀምራለች።

ሚሚ አባቴ ከሌላ ሚስቱ የወለዳት እህቴ ናት። ሰርጉን እኔም እናቴም እንደማንሄድ ያውቃሉ። ለምን እንደማይተውን አላውቅም። ባገኙት ሰበብና አጋጣሚ እኔና እናቴ ሰላም እንዳይሰማን ይታትራሉ። እማዬን ለማረጋጋት እማይኮነውን ሁሉ እየሆንኩ እንፈራገጣለሁ። በሚሚ ሰርግ ጉዳይ ግን ከእማዬ ይልቅ እንዳላብድ መጠበቅ ያለብኝ እኔ ነበርኩ። ምክንያቱም ሚሚ የምታገባው የልጅነት ፍቅረኛዬን ነው። የሰርግ ወረቀቱን ለእኔ አምጥተው የሰጡበት ምክንያትም እንደእናቴ እንዳብድላቸው ነው። ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ……

እኔ በሙያዬ ጠበቃ ነኝ። ……… በአንድ ቅሌታም ከፍተኛ ባለስልጣን ኬዝ ሰበብ ስሜ በሀገሪቷ የናኘ ጠበቃ…… አስታወሳችሁትኣ? አያቱ ከሚያክሉ አሮጊቶች ጋር የሚወሰልተው ሰውዬ…… አዎን ለደፈራቸው የ70 ዓመት ምስኪን አሮጊት የቆምኩት እና ያስፈረድኩበት እኔ ነበርኩ። ያ መርገምት ካርቱሚስት በአንደኛው ሳምንታዊ ጋዜጣ ላይ ጥርስ የሌላት ድዳም እና ምላሷ ከፒያሳ እስከመገናኛ የሚደርስ አሮጊት አድርጎ የሳለኝ… … አዎን እኔ ነኝ። ……… አሁን ማን እንደሆንኩ አወቃችሁኣ?

“ቢሮሽ ሰው እየጠበቀሽ ነው።” አለችኝ ወይኗ ገና ከመግባቴ።

"ደህና አደርሽ ወይኗ።” ብዬ እየተጣደፍኩ ስገባ

"አባትሽ ነው። አባቷ ነኝ ነው ያለው። አባት እንዳለሽ አልጠረጠርኩም ነበር። ……” አለኝ ፍትህ።

"አባትሽ?” ተንደርድሬ ቢሮዬ ገባሁ። ደንግጦ ተነሳ። በዓይኔ ካየሁት እንኳን ሰባት ዓመት ሆኖኛል። ምናባቱ ሊሰራ ነው አሁን የሚፈልገኝ? ጭራሽ ቢሮዬ ድረስ?

★ ★ አልጨረስንም ★ ★

@wegoch
@wegoch
@paappii
ዜማና ሰውነት
ግዕዝ (ተቀዳሚ)
ሰዎች "እንዴት ነው ሰብራህ የሄደችው ?" ብለው ሲጠይቁኝ " ልቤ
እስከሚያነክስ" ብዬ ከመለስኩላቸው ረጂም ጊዜ ቢያልፍም ድንገት ቀና ስል
የጠራ የመስከረም ሰማይ አይቼ ናፈቀችኝ ። ለእንቁጣጣሽ በፈካ ቢጫ አደይ ያቆጠቆጠ አረንጓዴ መስክ ላይ ይሄን ብራ ሰማያዊ ሰማይ ደርበን የተራከብን ነን ። በሚያሳሳ የመስከረም ቀን መኻል አፍላነት ያቀጣጠለው፤ ነፋስ ስሞ ያበረደው ገላችን ላይ ጣል ያደረግነው ፤ የተጋፈፍነው ሰማይን ነው ። ሽቅብ ያየሁበትን አይኔን ቶሎ ሰበርኩ እንጂ ባተኩር ከጭኗ የተላቀቀ የጠይምነቷን ባዘቶ ጉም ሰርቶ አየው ነበር ። ሁሉ እንደዛሬ ስላይደለ ልብ ብዬ ባየው ህመሙ ነፍሴ ላይ ያረብባል እንጂ ። በልጅነት ቀናቷ ድንግል ልቧን እና ነፍሷን የገረሰስኩ ተቀዳሚ ግዕዟ ነኝ። ማለት የመጀመሪያውን መሳም የትኛውም መሳም እንደማይሽረው ፤ የመጀመሪያው ዜማ ድንቅነት በሌሎች እንደማይሸፈነው ፤ በልቧ ቅኝት ላይ ተደላድዬ የተፃፍኩ ማንም የማይሰረዘኝ ዜማዋ ነኝ ። ለመጣ ለሄደው ሳትሰለች የምትነግረኝ ገድሏ ከአንደበቷ የምወጣ ብቸኛ ተረኳ መሆን ትምክተኛ አድርጎኝ ፤ ልታቅፈኝ የዘረጋቻቸው እጆቿ አየር ላይ
እንደተንከረፈፉ ትቻት ስነጉድ ፤ በማንም ያልተሳሙ ለጋ ከንፈሮቿ ሊስሙኝ ሲተጉ
ስገፋ ተስፋ ቆረጠችና ያልቃል ብዬ ያልገመትኩትን ለኔ ያላትን ፍቅር ለሌላ
አጋርታ አገኘኹዋት ። በኔ ግዕዟ ላይ እዝል ደርባ የምታዜም ሆነች ። ፀፀት ልቤን ሲበላኝ እስከዛሬ ትምክህት የሸበበው አንደበቴን ከፍቼ እንደምወዳት
ነገርኳት ። ሁለተኛ ፍቅሯ ከኔ እንደማይበልጥባት አውቃ ይሁን የዘመናት ህልሟ ስለሆንኩ ብቻ ግን መውደዴን ስነግራት ደስ አላት አቅፋኝ አለቀሰች ። "ሁሌም አለሁልህ "አለችኝ ።
ፍቅሬ በእኔ በግዕዟ በሁለተኛዋ እዝሏ ዜማ የምትንገላታ አሳዛኝ አራራይ ሆነች ። በዚህ ዜማ የታመምን ሶስት ሰዎች ነበርን ። ከእርሱ ጋር አሸብሽባ እንደምትመጣ እያወኩ በቅዳሴዋ ልዘምም ደፋ ቀና ስል ከጠይም ገላዋ ላይ የሚነሳ የእዝሏ ጠረን ፣ ከሴትነቷ የሚተን የእርሱ ጢስ ዜማዬን እና አቋቋሜን ቢያዛባውም ። በ"የኔ ነበረች ፤ ሁሌም የኔ ነች። " እምቢተኝነት በቅኝት መኻል ሽብርክ የሚል ልቤን ታቅፌ ወረቧ ላይ ከርሚያለሁ ። አሁን ይሄን እኔ እና እርሷ የተጋፈፍነውን የመስከረም ብራ ሰማይ ቀና ብዬ ባይ በተመሳሳይ ቀን እኔ ጋር ከመምጣቷ በፊት ከእዝሏ ጋር የነበራትን ወረብ በበራሪ ኮከብ እንደ ስዕል አስቀምጦ ያሳየኛል ። ግን አይኔን አቅንቼ ሰማዩን ሳይ ትዝ ባለችኝ ቅፅበት አንገቴን መልሼ እጄን ደረቴ ላይ አጣምሬ የልቤ ድሪቶ ውስጥ ቀበርኳት ። ቢሆንም እኔ ምንም የልቤ ስርቻ ውስጥ እንደመነኛ ልጥላት ብሞክር
በእርሷ ልብ ውስጥ ግን ያለኝን ቦታ አውቃለሁ ፤ ብዙ ሁለተኞች ያልሻሩኝ የሁሉ ነገር አሃዱዋ ተቀዳሚ ግዕዟ ነኝ ።
እዝል (ተደራቢ) ትዝ የምትለኝ በእኩለ ሌሊት ነቅቼ ሲጋራዬን ለኩሼ ያጨስኩ ቀን ነው ። ከሁሉ ከሁሉ የምትወደው ከንፈሬን ነው ። ከንፈሬ ላይ ባለችው ጥቁር ነቁጥ ሁሉ ሳትቀር ትቀና ነበር "ማርያም ለምን ሌላ ቦታ አልሳመችህም?" ብላ ታኮርፈኛለች
። ሌሊት እንዳልቀሰቅሳት ተጠንቅቄ ተነስቼ ወንበር ስቤ ተቀምጬ ሲጋራዬን
ስለኩስ ከእንቅልፏ ትነቃለች ። በቅጡ ያልተከፈቱ አይኖቿን ገርበብ አድርጋ "
ጭሱን ከአፍህ ልውሰድ?" ትለኛለች ። ቀጥላ ከመኝታዋ ተነስታ ጭኔ መሃል
ትንበረከክ እና አጭሼ የምተነፍሰውን ጭስ ከአፌ አንደ ወፍ ትቀበላለች ። የዛኔ
ከንፈሮቻችን ተጋጥመው ቅጡ በማይገባን ወረብ ቆመን መወዛወዝ
እንጀምራለን። ሁሉም እንደሚያውቀው ከኔ ቀድሞ በገጠማት ዜማ ያልተደሰተች ዘማሪ ነች እኔ አፍላነቷ ጎትቶ ከቀሚሷ ስር ከገላዋ ላይ ያዋለኝ እዝሏ ተደራቢ ዜማዋ ነኝ ። አለ አይደል በግዕዝ የጋለ እሳቷን አቀዝቅዤ አረጋጋታለሁ ። ቀልበ ቢስ ቀልቃላ እና ሃይለኛ ቅላፄዋን ዳብሼ ገርቼ እመልስላታለሁ ። የመጀመሪያዋ ነውና ለግዕዟ ያላትን ስሜት በአንዴ አውጥተሽ ጣይ ባልላትም ። በኔ እርጋታ
አገግማለች ። ፍቅር ከጀመርን ከጥቂት ጊዜ በኹዋላ በወረባችን መኻል የቀደመ ትትርናዋን ችላ ብላ ሁሉ ነገሯ ሲቀየርብኝ ግራ ገባኝ ። ቆይቼ አስቸጋሪ ግዕዟን አስጣልኳት ያልኳት እርሷ የቀደመ ቅላፄዋን ሳትተው በእኔ ላይ ደርባ ማዜም መጀመሯን አወኩኝ ። ይህን ሳውቅ እውነቱን በልቤ ደብቄ ሸፋች ልቧን ላረጋጋ ርቃኗን አስተኝቼ ከላይ እስከ ታች በከንፈሬ እየዳበስኩ በእንባዬ አርጥቤ አጠብኳት ። እንዲህ ሳደርግ በሃይለኛ እና እምቢተኛ የሚማረክ እርሷነቷ ለኔ መለማመጥ
ትኩረት መስጠት ተሳነው ። እናም ያኔ የጀመርነው ለስላሳ ቅኝት ዜማችን
ተቆራረጠ ። አሁን ዛሬ ላይ ስለ እርሷ ሳስብ ሃዘን በልቤ ያልፋል ። በህይወቷ ከተጣባት ጠንካራ ግዕዝ ላሳርፋት የጣርኩ ለስላሳ እዝሏ ብሆንም እዚያና እዚህ የሚረግጥ አሳዛኝ አራራይ ነፍሷ ግን ያን እንድታደርግ አልፈቀደም ። ከብዙ ጊዜ በኹዋላም ቢሆን እኔ ላይ ካደረገችው ክህደት ይልቅ ለቅብዝብዝ እርሷነቷ እና በዚህ ምክንያት ለሚበላሹ ዜማዎቿ የማዝን ተደራቢ ዜማዋ እዝሏ ነኝ ። አራራይ ( አሳዛኝ) ሰዎች በሰራኹዋቸው ነገሮች በሙሉ ይበሳጫሉ ። ይበሳጩና ያዝናሉ ።
የበደልኳቸው እንኳን ትንሽ ተበሳጭተውብኝ ቀጥሎ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ለእኔ ማዘን ነው ። እኔነቴ ሰው ጨክኖ ጆሮ እንደ ማይነፍገው አሳዛኝ ዜማ ነው ፤ እንደ አራራይ ።
ስለ ዜማ ሳስብ ስለ ሁለቱ የቀድሞ ፍቅረኞቼ አስባለሁ ። የመጀመሪያው ግዕዜ ነው ...... ልጅነቴን በጥበቃ የጨረሸ ፤ የኮራብኝ ፤ የተጀነነብኝ ፣ ደጅ ያስጠናኝ ፣ ያስለመነኝ ፣ እልህ ያጋባኝ ፣ የፈተነኝ ። ሁለተኛው ደግሞ እዝሌ ነው ......የደረብኩት ፣ ያረጋጋኝ ፣ያበረደኝ ፣የወደደኝ ። ስለምነው የከረምኩት ግን የገፋኝ ። በኋላም ከሚያሳርፈኝ ጋር እፎይ ማለቴን ሲያይ ስመኘው የኖርኩት ፍቅር ካልሰጠሁሽ ብሎ ፊቴ ቆመ ። አመታት እርሱን የኔ በማድረግ ምኞት አልፈው በመጨረሻ ፊቴ ሲቆም አይሆንም ማለት አቅቶኝ ፤ እዝሌንም በቃኸኝ ግዕዜን አግኝቻለሁ ብዬ እንዳልለው የምጠለልበት የምሰክንበት ጥጋቴ ነውና እንዳላጣው ፈርቼ በሁለት ቢላ የምበላ ሆንኩኝ ። ሁለቱንም በተለያዩ ምክንያቶች ሳላስባቸው ውዬ አላውቅም ። ባስታወስኳቸው ቁጥር ግን ሃዘን ይከበኛል ። ሁለቱም በመቅበዝበዝ እና በመንገብገብ ያበላሸኹዋቸው የህይወቴ ዋና ዋና ዜማዎች ናቸው ። በእርግጥ ከነርሱ በኋላም ያማረብኝ ቅላፄ የተዋጣልኝ አቋቋም የለም ግን እንደ ሁለቱ ያበላሸሁት የለም ። አሁን ላይ ከግዕዜና ከእዝሌ የተረፈኝን አራራይ ዜማ ለራሴ ወስጄ ሌት ተቀን እህህ እላለሁ ። ሁሉን የእኔ ይሁን የሚል ልጅነቴን ለተከተለ ደመነፍሴ ፣ በሁለት ዜማ አንድ ቅኝት ለናፈቀ ለጋነቴ ፣ ለባተልኩት ፣ ለባከንኩት ፣ ከሁሉ ከሁሉ በአንድ እለት ግዕዝም እዝልንም ለተቀበለ ሴትነቴ በአራራይ ዜማ እህህ እላለሁ ።
በመጨረሻ የገባኝ ግን ሁሉ በአሳዛኝ ዜማ እንደሚቋጭ ነው ፤ ህይወት የሚባል ውብ ነገርም ቢሆን ........

@wegoch
@wegoch
@paappii
★ ★ ራሴው ማበዴ ነው……#2 ★ ★
(ሜሪ ፈለቀ)

"አቤት?” አልኩት ለሰላምታ የዘረጋውን እጁን ችላ ብዬ ወንበሬ ላይ እየተቀመጥኩ። ፀጉሩ አልፎ አልፎ ከመሸበቱ ውጪ ብዙም አልተለወጠም።

"ደህና ነሽ ሚሚሾ?"

"ምን ፈልገህ ነው የመጣኸው? ደህና መሆኔ አሳስቦህ አይሆንም መቼም!! የልጅህ ሰርግ ጥሪ ወረቀት እንደደረሰኝ ለማረጋገጥ ከሆነ ደርሶኛል። እማም ደርሷታል። ጨርቄን ጥዬ እንደሆን እንድታይ ሚስትህ ከሆነ የላከችህ። ሂድና ንገራት! ረስተናችኋል። እባካችሁ ከህይወታችን ውጡ። እና ከቢሮዬም ውጣ……” መናደድ አልፈልግም። ግን አስቤያቸው አለመናደድ ያቅተኛል። ሁሌም እንዲህ ናቸው። ስተዋቸው አይተውኝም። ዝቅጥ ብለው ያዘቅጡኛል። ስለእውነቱ የሁሉም ክፉ ነገር ሀሳብ ባለቤት ሚስቱ ናት። እሱ መልሱ ዝምታ ነው። ጋግርት። ግን ከእርሷ ቅጥ የለሽ ክፋት በላይ የሱ ዝምታ ይሰብረኝ ነበር።

"ለግሌ ጉዳይ ነው የመጣሁት።” አለኛ አፉን ሞልቶ።

"ሰውየው ከእኔ ጋር የሚያገናኝ የግል ጉዳይ የለህም። እባክህ መጥፎ ነገር አታናግረኝ። ውጣልኝ……”

"የውብዳርን ልፈታት ነው። በመሀከላችን ብዙ ጣጣዎች ስላሉ ጠበቃ ያስፈልገኛል። …” ወደ በሩ እየተራመደ “… ትረጂኛለሽ ብዬ ተስፋ ነበረኝ። ጭራሽ ልትሰሚኝ እንኳን ፈቃድሽ ካልሆነ ምን አደርጋለሁ? ባልደረቦችሽን ላማክራቸዋ?” በሩን ከፍቶት ወጣ። ምን? እኮ የቤተሰቤን ጉድ ባልደረቦቼ ሊሰሙ? በተለይ ደግሞ ፍትህ? ኡኡኡ ልል ትንሽ ነበር የቀረኝ። በሩጫ ተከተልኩት። አጠገቡ ስደርስ እልህም ንዴትም አነቀኝ። ጮኬ ማውራት ግን አልችልም። እኔን የሚያነድበት አንዲት የነገር ሽራፊ ለሚፈልገው ፍትህ ራሴን አላጋልጥም።

“ምንድነው ግን ከኔ የምትፈልገው? ምን አድርጌ ነው እየተከታተላችሁ ልታጠፋኝ የምትተጉት? በምትወዳት ልጅህ ይሁንብህ ተወኝ?” አልኩት ጥርሴን ነክሼ ከእንባዬ እየታገልኩ። ሁሌም እንደዚህ ነው። ቤተሰቤን አስመልክቶ መጨረሻዬ እንባ ነው። ተሸናፊ ነኝ። አሸናፊዎች ናቸው። በፈለጉበት ቀን መጥተው ከዓይኔ እንባዬን ለመቅዳት የመብታቸው ያህል ቀላል ነው። የፈለጉትን ይቀሙኛል። …… እኔ ይህቺ ነኝ! የአደባባይ አንበሳ! የቤቴ አይጥ ነኝ።

"አንድ ጊዜ ብቻ ቁጭ ብለሽ እንድትሰሚኝ እፈልጋለሁ። እውነቱን ላስረዳሽ እፈልጋለሁ። የምፈልገው እሱን ነው።”

"እባክህ ሂድልኝ። እባክህ ተወኝ። አንድ ያልነጠቃችሁኝ ነገር ስራዬ ነው። አንድ የእናንተ የክፋት እጅ ያልደረሰበት ቦታ የስራ ቦታዬ ነው። እባክህ ልለምንህ እሱን ተውልኝ።………” ከየት መጣ ሳልለው ፍትህ አጠገባችን ደርሶ

"እንዴ አባባ ሻይ ቡና ምን ይምጣሎት?…” እየለፈለፈ እያለ አየኝና ደነገጠ። “…… እንዴ ቦስ ችግር አለ እንዴ?ምነው የተፈጠረ ነገር አለ?” አብረን ስራ የጀመርን ሰሞን ሊያናድደኝ ሲፈልግ ‘ቦስ’ እያለ መጥራት ጀመረ። ዛሬም ድረስ እንደዛ ነው የሚጠራኝ። ዝም ካልኩት መጠየቁን እስከማታ አያቆምም።

"ፍትህ ዘወር በልልኝ!” ብዬ ጮህኩበት።

ለምኜም ተቆጥቼም አባቴን ሸኘሁት። ሌላ ቀን እንደሚመለስ ነግሮኝ ሲወጣ ያዘነልኝ ይመስል ነበር። የውላችሁ…… እዚህ ተረክ ውስጥ ማንም ጥሩ ማንም መጥፎ የለም። ሁሉም ጥሩ አይደሉም። ሁሉምም መጥፎ አይደሉም። እናቴን ጨምሮ!! ስለቤተሰቦቼ ሁሉንም ባላውቅም አንዳቸውም ንፁህ አይደሉም። የተዘራሩትን ነው የሚተጫጨዱት። ለነገሩስ የሰው መቶ ፐርሰንት ጥሩ ወይ መጥፎ የታለው? ጥሩ የምንለው ሰው ክፋቱን በጥሩነቱ የሸፈነ። ክፉ የምንለውስ ጥሩነቱን በክፋት የሸፈነ አይደለምን? እንጂማ ሁሉም የክፋትና የመልካምነት ስብጥር አይደል? ጎልቶ ባሳየው ይጠራበታል።

እኔስ? ባልበላሁት ጉሮሮዬን እየቧጠጠ ያስመልሰኛል። ያልዘራሁት እሾህና አሜኬላ እየበቀለ እድሜዬን ሙሉ ሲያንቀኝ አለ። ራሴ ከዘራሁት መልካም ዘር ቀድሞ እነሱ የዘሩት እንክርዳድ ደርሶ እበላዋለሁ። እንደአረቄ አዙሮ ይደፋኛል።

"ቦስ ቡና ላምጣልሽ?” ቢሮዬ መጥቶ ነው።

"እባክህ ፍትህ… … እየደጋገምክ የቢሮዬን በር መክፈት አቁም።”
"Am just worried… … የሆንሽውን እያየሁ ዝም ብዬ ልቀመጥ?”

"አዎን እንደሱ አድርግ። ዝም በለኝ።”

"እሺ እቤት ሄደሽ እረፊ። እዚ ሆነሽ ምንም ነገር በትክክል አትሰሪም።” አለኝ። እማ ትዝ አለችኝ። ኮቴን አንስቼ አልፌው ሄድኩ። እቤት ስደርስ የቀረበላት ምግብ ላይ ትተክዛለች። የማይሰማ ነገር ታጉተመትማለች። ሰራተኛዋ ቆማ እየጠበቀቻት ነበር።

"እማ እባክሽ ዛሬ አይሆንም። ዛሬ ደህና ሁኚልኝ። ዛሬ አልችልም። አልችልም!!”

ቀና ብላ አየችኝ። “አንቺ ደግሞ ማነሽ? የውብዳር ናት የላከችሽ? ” አምላኬ ሆይ አይሆንም! አይሆንም!!

"አይደለም እማ አንዱዓለም ነው የላከኝ።" ከቃላቶቹ ጋር እንባዬ ይወርዳል። እሷ የእሱ ስም ከተነሳ እያለቀስኩ ይሁን እየሳቅኩ ግድ የላትም። ሲጀምራት ሰሞን የእርሱ ስም ያረጋጋታል። እሱ ይሄን ማወቁን እንጃ! እብደቷም መድሃኒቷም እሱ ነው።

"እና ምን አለሽ?”

"የኔ ጨረቃ ናፈቅሽኝ እኮ! ባክሽ ይሄ ስራ ይቅርብሽና ሁሌ ማታ ማታ ልይሽ?………”ባሏ እሷ ስራ ስትሄድ የፃፈላት ደብዳቤዎች ናቸው። እሷም በቃሏ ሁሉንም ታውቃቸዋለች። እኔም እንደዛው። ለዓመታት በቃሌ አነብንቤላታለሁ። አብራኝ ቃሎቹን እያጣጣመች እንቅልፍ ይወስዳታል። ……… ዛሬም ለአንድ ሰዓት ያህል የባሏን መልእክት ነግሪያት እሷ ሶፋው ላይ ፈገግ እንዳለች እንቅልፍ ጣላት።

★ ★ አሁንም አልጨረስንም ★ ★

@wegoch
@wegoch
@paappii
Forwarded from Sunset Hiking
#Hiking #outdoor #photography

Hiking to the majestic Mt. #Eerer with #Sunset Family.

📅Hiking Date :- October 11, 2020 (ጥቅምት 1, 2013)

💵 Hiking Cost #400 ETB only

🛫Departure: Shebelle (Mexico)🍁

Departure Time - 12:00 LT 🍂🌴🍁

🎉🎊Package includes🎋🎊

🚍 Transportation
🌲 Bottled water
🌺 Guide
🍂 photography 📷
💐 snack
🌷 Family Chilling & Talent performance ( if any)🙊🙊

NB.
🏖 Package does not include lunch.
🚫 Sanitizer & facemask mandatory!

Brought to you by
💥#Sunset_Hiking_Team

for more join the
🔸channel @sunsethiking🍁

🔻📷 @sunsetphotography🍁

🎫 tickets available at
@Paappii
@thomaskagnew
@Chere_daregot
~ ራሴው ማበዴ ነው… …#3 ~
(ሜሪ ፈለቀ)

ከሀያ ዓመት በላይ የሆናቸው በወጣትነቷ ውዷ ከፃፈላት ደብዳቤዎች ዛሬም ድረስ አብረዋት ያሉ እያንዳንዱን በቃሏ የምታውቃቸው 23 የፍቅር ደብዳቤዎች አሏት። ሁሉንም ከነተፃፉበት ቀን ሳይቀር እኔም በቃሌ አውቃቸዋለሁ። እንደዚህ ከፍ ያለ ፍቅር መቋጫው እንዴት አስከፊ መለያየት እንደሆነ ሳስብ ይገርመኛል። እሷ ዛሬን ማሰብም መኖርም አትፈልግም። በትናንት ትዝታዋ ውስጥ ተወሽቃ ቀኖቿን መጨረስ ነው የምትፈልገው። እናቴ ያልገባት ነገር የሷን ትዝታ ስተዘትዝ የእኔም ቀኖች ከመድረሻቸው እየተቀነሱ እንደሆነ ነው።

"ቦስ ሰላም ነሽ?” ለሶስተኛ ጊዜ ስልክ ደውሎ ነው።

"ደህና ነኝ አልኩህ እኮ ፍትህ! ነገ እንገናኛለን። በቃ ደህና እደር!”

"እሺ ምግብ በልተሻል? አድራሻሽን ከነገርሽኝ ያለሽበት ላምጣልሽ?”

“ፍትህ ምግብ በልቻለሁ። ራሴን መንከባከብ አያቅተኝም። ባክህ እረፍ!”

ፍትህ ማለት በብዙ የሚያበሽቀኝ በበሽ የሚያበግነኝ ባህሪ ያለው ነው። ቢሯችንን የከፈትነው ከሁለት ምርጥ ጠበቆች ጋር በጋራ ነበር። አንደኛው ከወራት በፊት በግሉ ምክንያት ስራ ሲያቆም ፍትህን የቅርብ ጓደኛውና ጎበዝ ጠበቃ መሆኑን አሳምኖን ነው አብረን መስራት የጀመርነው።ፍትህ ቅንጡና ለብዙ ነገር ግድ የለሽ ነው። ለምን በየዕለቱ ቢሮ እንደሚገባም ሆነ ለምን ጠበቃ መሆን እንደፈለገ አይገባኝም። ምክንያቱም ለስራው ፍቅርም ትጋትም የለውም። ገንዘብ የሚያሳስበው ሰው እንዳልሆነ ለመገመት ደግሞ የሚጠቀማቸውን ቁሶችና አላስፈላጊ ወጪዎቹን ማየት በቂ ነው።

ከነገረስራው ሁላ ሴትን ልጅ ከአልጋ ወርዳ ማሰብ የሚከብደው ብሽቅ መሆኑ ያናድደኛል። ስማቸውን እንኳን በውል ከማያስታውሳቸው እልፍ ሴቶች ጋር ነው።

"ባል ሳታገቢ ነው የምታረጂው ታስታውቂያለሽ።” ይለኝ ነበር ስራ የጀመረ ሰሞን እራት ልጋብዝሽ ብሎኝ እንቢ ስላልኩት ሲያበሽቀኝ።

"አንቺ የሴት ልስላሴ የለሽም። ነገር ላይ እርርርር ትያለሽ። ጠብሰሽ ማወቅሽንም እንጃ።” ይለኛል በሌላ ቀን። ልስማው አልስማው ግድ የለውም ይለፈልፋል። ልቀየመው ልናደድበት ግድ የለውም አፉ እንዳመጣለት ነው የሚመርገው።

"አለቃ አለቃ መጫወት ትወጃለሽ። ሁሉም ቦታ ዋና አክተር መሆን አይደብርሽም?” ይለኛል በምንም ጉዳይ አስተያየት ልሰጠው ከሞከርኩ።

"በራስሽ ትመፃደቂያለሽ። ራስሽን ለዓለም ህዝብ እንደተላከ መሲህ ነው የምትቆጥሪው። ሁሌ ልክ እንደሆንሽ፣ ካንቺ በላይ አዋቂ እንደሌለ ነው የምታስቢው።……” ብሎኛል ጠጥቶ አድሮ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ያመለጠው ቀን ልክ እንዳላደረገ ስነግረው። ለምን እንደሆነ አይገባኝም ብቻ የምሰራው ሁሉ አይዋጥለትም። እንደማንኛዋም ሴት መሆኔን ሳይጠቁመኝ አያልፍም። እኔን የሚናገርበት ስህተት ያገኘብኝ ከመሰለው አለቀልኝ። በነገር ሲተረኩሰኝ ይሰነብታል።

አባቴ ቢሮ መጥቶ ዓይኖቼ በእንባ ተሞልተው ሳወራው ካየኝ ቀን ጀምሮ የማውቀው ፍትህ አልሆነም። ምናልባት ግትርና ደንዳና የምትመስለው ሴትዮ ተሸንፋና ተመሳቅላ ስላያት የቆለላት ሴት ተንዳበት ግራ ገብቶታል ወይም ደካማ ጎኔን አውቆ ሊሳለቅ እየተከታተለኝ ነው አልያም አሳዝኜዋለሁ። ሁሉም እንዲሆኑ የማልፈልጋቸው ናቸው።

"ቦስ ቅድም አባትሽ መጥተው ነበር።” አለኝ ከፊቴ ላይ ስሜቴን እየዘገነ

"እና?” አልኩት ምንም ያልተሰማው ለመምሰል ዘና እያልኩ።

"እኔን ፈልገው ነው የመጡት። አንቺ ፍርድ ቤት መሆንሽን አስቀድመው አረጋግጠው ነው የመጡት።” አነጋገሩ ‘ምን ማድረግ እችል ነበር?’ የሚል አንድምታ አለው። ፀጥ አልኩ። ለሰከንዶች ጭንቅላቴ ረጭ አለ። ማሰብ አቆምኩ።

"ከእናትሽ ጋር መፋታት እንደሚፈልጉ እና አንቺ እንቢ ስላልሻቸው ሊያማክሩኝ ነበር። ጠበቃቸው እንድሆን ይፈልጋሉ።” የውብዳርን እናትሽ ማለቱ ብዙ እንዳላወሩ ገባኝ። …… ጭንቅላቴ ወና ስለሆነ የምጠይቀውም የማወራውም አልነበረኝም።

"የእህትሽን የሰርግ ካርድ ሰጥተውኝ ነው የሄዱት። እንዳልቀርና ብዙ የሚያጫውቱኝ ነገር… …” ቀጠለ…… “የሆነ ነገር በይኛ ቦስ?” ምን ልበለው? አትሂድ? እንደውም አባቴን አታናግረው? ለአባቴ ጠበቃው ከሆንክ ስለእኔ ብዙ ታውቃለህና ይቅርብህ? እናስ? ደከማ ጎኔ እንዳይታወቅ? ፍትህ እንዳያሸንፈኝ? በስራዬ የሚያውቁኝ ሁሉ የሚያውቋትን ጠንካራ እና በራሷ የምትተማመን ሴት ዙፋን ለማስጠበቅ?

ስራዬንም ቢሮዬንም እወደዋለሁ። ምክንያቱ ደግሞ ከቢሮዬ ውጪ ያለውን ፣ ያለፈውንና የሚመጣውን የማላስበው እዚህ ነው። እዚህ ሌላ ሴት ነኝ። አንድ ደራሲ መፅሃፍ ሲፅፍ የሚቀርፃቸውን ገፀ ባህሪያት ኑሮ ሲያበጅ ራሱን በፈጠራቸው ገፀ– ባህርያትና ዓለም ውስጥ የሚደብቅ ይመስለኛል። ለኔ ስራዬ እንደዛ ነው። በማገለግላቸው ደንበኞቼ ውድቀትና መነሳት ውስጥ ራሴን ደብቃለሁ። አንዳንዱ በመጠጥ አንዳንዱ በሌላ ሱስ ያደለው ደግሞ በሚወደው ሰው እና በፍቅር ውስጥ ራሱን እንደሚደብቀው።

ፍትህ የአባቴ ጠበቃ ሆነ ማለት ስለቤተሰቦቼ እኔ የማላውቀውንም ጉዳይ ጭምር አወቀ ማለት ነው። ያ ማለት ደግሞ ቢሮዬ ውስጥ የነበረኝ በራስ መተማመን እና ነፃነት ጠፋ ማለት ነው። ከዛ ቢሮ መግባት እጠላለሁ። ያኔ ራሴን የምሸሽግበት ቦታ አይኖረኝም። አደባባይ ተሰጣሁ ማለት ነው። ያኔ ለመንኮታኮት ተምዘገዘግኩ ማለት ነው።

"እና ትሄዳለህ? ማለቴ ሰርጉን?” አልኩት በመጨረሻ። ሰርጉ የድሮ ፍቅረኛዬና የእህቴ እንዳልሆነ ሁሉ እንደማንኛውም ‘ሰርጉን’ ብዬ

"ለምን እቀራለሁ?”

“ጠበቃው ልትሆን ወስነሃል ማለት ነው?”

“እንዳልቀበል የሚያደርገኝ ምክንያት አለሽ?”

"አይ ምክንያት የለኝም። ግን ባትቀበለው ደስ ይለኛል።”

"እኮ ለምን?” ለምንም ነገር ግድ የሌለው ሰው ይሄ ኬዝ እንዲህ ሀሳቡን የሰረቀው ከእኔ ጋር ስለተያያዘ ብቻ ነው። ለ‘ለምኑ’ መልስ የለኝም።


★ አሁንም በድጋሚ አልጨረስንም ★

@wegoch
@wegoch
@paappii
~ ራሴው ማበዴ ነው… …#4 ~
(ሜሪ ፈለቀ)

"ልትነግሪኝ የምትፈልጊው ነገር አለሽ?”

"ማለት? ስለምን?”

"እኔ እንጃ ቦስ አባትሽ እዚህ ቢሮ እግራቸው ከረገጠ ቀን ጀምሮ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ፍፁም ልክ አይደለሽም። ያዘንሽ ያዘንሽ ፣ የተከፋሽ ፣ የሆነ ነገር ያደከመሽ አይነት ነው የምትመስዪው።” ሲለኝ ለቅፅበት ያደከመኝን ሁሉ ልነግረው ዳድቶኝ ነበር።

ራሴን አውቄ ሀላፊነትን መሸከም ከቻልኩበት ጊዜ ጀምሮ ለሚያውቀኝ ሰው ወይም በምንም አጋጣሚ ቢሆን ድጋሚ ላገኘው ለምችለው ሰው ስለራሴ ተናግሬ አላውቅም። ነገር ውስጤ ተቆልሎ የሆነ ዓይነት እምቅ ሀይል ሆኖ እንደ ኒውክለር ሊፈነዳ የመሰለኝ ወቅት ላይ አንድ ሶስቴ ከዛን ቀን በኋላ ፊታቸውን አይቻቸው ለማላውቃቸው ሰዎች የተሰማኝን ዝርግፍግፍፍፍ አድርጌ ከመፈንዳት ተርፊያለሁ። አንዷ ‘ነገ አረብ ሀገር ልሄድ ነው።’ ያለችኝ ፀጉር ቤት ያገኘኋት ሴት ናት። ፀጉራችንን ተስርተን ስንወጣ ለማኪያቶ ካፌ ተቀምጠን ያወራኋት። ሁለተኛው ናዝሬት ለስራ ሄጄ ያረፍኩበት ሆቴል ብቻዬን ራት ስበላ አይቶኝ ‘እንብላ’ ባለኝ ሰበብ ያወቅኩት ጎልማሳ ነው። (ሊበላኝ(ሊያባላኝ) ባሰበ ምሽቱን የተበላው።) ሶስተኛው ከቂሊንጦ ስመለስ ሊፍት የሰጠኝ ሽማግሌ ነው። አንዳቸውንም ከዛ በፊትም ሆነ ከዛ በኋላ አይቻቸው አላውቅም። ስሜን አያውቁም ፣ ማን መሆኔን ፣ የት መሆኔን አያውቁም……… ሳወራላቸው ነገ ሲያዩኝ ምን ይሰማቸዋል? አልልም…… ሳለቅስ ወይ ስዝረከረክ ይዳኙኛል አያሰጋኝም…… በነሱ ፊት መሸነፌ ወይ ተስፋ መቁረጤ ድክመቴ አይሆንም። …… ለምንም ግድ የለኝም። ልግባቸው ላደናግራቸውም ጉዳዬ አይደለም። የተሰማኝን በሙሉ ዘርግፌ ተንፍሻለሁ።

ለሚያውቀኝ ሰው እንደዛ አላደርግም። ለሚያውቁኝ ሁሉ(ከቤተሰቦቼ ውጪ) ያቺ አልቅሳ የማታውቀው ፣ብርቱዋ ፣ ደካማ ጎኗን ማንም የማያውቅባት፣ መጠቃቷን ማንም የማያውቅላት… … የጉብዝና ምሳሌ የሆነችዋን ራሔል ነኝ።

"ፍትህ አንተ ደግሞ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ስራህን እርግፍ አድርገህ ትተህ እኔን ስራ አድርገኸኛል። am fine!! በቀን አስሬ ቢሮዬን የምትከፍተውን ነገር አቁም። please?” አልኩት። ብዙ ቀን ብዬዋለሁ ሰበብ እየፈለገ በጥያቄ ይወጥረኛል እንጂ።

"እሺ። ከፈለግሽኝ ግን አለሁ።” ብሎኝ ቆይቷል። ከቢሮዬ ግን አልወጣም። ከወንበሩም አልተንቀሳቀሰም። ሁሌም የማስበው የኖህ ታሪክ ትዝ አለኝ። ከውሃ ጥፋቱ በኋላ ኖህም ገበሬ ሆነ። ወይንም ተከለ። ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ። …… በድንኳንም ውስጥ ራቁቱን ሆነ ታናሹ ልጁ ካምም የአባቱን እርቃን ባየ ጊዜ ተሳለቀ። በአባቱ ገመና ሙድ ያዘ። ሁለቱ ልጆቹ ያፌትና ሴም ግን እርቃኑን እንኳን እንዳያዩበት አክብረውት ፎጣ በትከሻቸው አድርገው የኋሊት እየተራመዱ የአባታቸውን እርቃን ሸፈኑ… …… ኖህም ካምን ረገመው… ………… ይመስለኛል። ሲመስለኝ ሲመስለኝ……… የካም ነገድ የአክሱምን ልጅ ወለደ…… የአክሱምም ልጅ ልጆች በወንድምና ወዳጃቸው ገመናና ድክመት ሲደነቋቆሉ… … ሲሸረዳደዱ…… አንዱ የአንዱን ድክመት ሲጋለቡ ኖረው ኖረው። የእንጀራ እናቴ አባት ላይ ደረሱ። እሳቸውም ቀንደኛ ሸርዳጅ የሆነች ትውልድ አፈሩ……… ምናምን ምናምን………

የኖርኩት ዘመን የተረዳሁት አብዛኛው ሰው ከትልቁ ስኬትህ ውስጥ እንኳን ምናምኒት የምታክል ውድቀትህን ወይ እንከንህን ይፈልጋል። ካገኘብህ አለቀልህ። ሰማይ ያከለ ስኬትህን የጎመንዘር በምታክል እንከንህ ያጣፋልሃል።

"ፍትህ?”

"አቤት ቦስ?”

"ነገ ሰርጉን ትሄዳለህ እንዴ?”

"አወና!! እንዴ ቆይ ቆይ…… ትሄዳለህ ነው ትመጣለህ? ያ ማለት የእህትሽ ሰርግ ላይ አንቺ አትኖሪም ማለት ነው? ኦ……ኬ …… I think ይሄ ኬዝ ካሰብኩት በላይ ሊመስጠኝ ነው። ምንድነው እሱ?”

"ምንም big deal አይደለም። መሄድ አለመሄድህን ለማወቅ ነው። አበቃ!! የሆነ ታላቅ ግኝት ያገኘህ አታስመስለው።”

"እሄዳለሁ።” ብሎኝ ዓይኖቹን ዓይኖቼ ውስጥ ዘፍዝፎ ስሜቴን ሊጨምቅ ይታገላል።

"መልካም።” አልኩት ድምፄ ከስሜቴ ጋር አብሮ ሲወርድ እየታወቀኝ።

"በቃ?” ብሎ አፈጠጠብኝ ከተቀመጠበት መንጭቆ እየተነሳ። "በቃ ሌላ የምትዪኝ ነገር የለም?”

"እንዴ? ምን እንድልህ ነው የምትፈልገው?”

"አላውቅም!! ብቻ ከቤተሰብሽ ጋር በተያያዘ አንድ እንዳላውቅ የፈለግሽው ነገር ያለ ይመስለኛል። አላውቅም!! ንገሪኝ ማወቅ ያለብኝ ነገር ካለ ከሌላ ሰው ከምሰማው በፊት ንገሪኝ!”

"Excuse me? ከሌላ ሰው ከመስማትህ በፊት?ራስህን ምን ቦታ ላይ ነው የሰቀልከው ባክህ?” ሆኖ እንደማያውቀው እየጯጯህን ነው።

"Sorry boss! ራስን መስቀል አይደለም። እንደጓደኛ……”

"እኔና አንተ ጓደኛሞች አይደለንም! ደግሞ ቦስ አትበለኝ። አለቃህ አይደለሁም። ስም አለኝ። እኔና አንተ የስራ ባልደረቦች ብቻ ነን። የሚያገናኘንም ስራ ብቻ ነው።” ንግግራችን የማያስፈልገውን ያህል ቁጣ እየተቆጣሁ እንዳለሁ ራሴን ስሰማው አውቃለሁ። ግን ቁጣዬ ምክንያቱ ፍትህ ብቻ አልነበረምና መመጠን አልችልም።

"እሺ ጓደኛሽ አድርጊኝ? I mean not just for sayin… … real ጓደኛሽ ልሁን?።” አለኝ ሹክሹክታ በመሰለ ድምፅ እና ከኔ በተቃረነ እርጋታ። ሁኔታዬ ራሴኑ አሳፈረኝ። እሱ ላይ የምጮህበት ምንም ምክንያት የለኝም። ፀጥ አልኩ። ጠረጴዛዬ ላይ በአንድ መቀመጨው እየተቀመጠ

" I know አንቺ በጣም ጠንካራ ሴት ነሽ። ያ ማለት ግን ሰው አያስፈልግሽም ማለት አይደለም። ያንቺን ጭንቀት ማወቄ ላንቺ ያለኝን ቦታ አይቀንሰውም። በምታልፊበት ነገር ሁሉ ውስጥ አልፈሽ እዚህ መገኘትሽ ምን ያህል ጠንካራ ሴት መሆንሽን ያገዝፍብኛል እንጂ።” አለኝ የፍትህ በማይመስል እርጋታና ብስለት።

"ለምን ብለህ ምክንያቱን አትጠይቀኝ። እባክህ ሰርጉን አትሂድ?” ማለት ብቻ ነበር የመጣልኝ ሀሳብ

"እሺ።” አለ እንደዘበት። ከዛም ያልሰጠሁትን እጄን ፈልቅቆ እየማለ “ ይኸው !ቦስ ይቅርታ ራሔል ሙች! አልሄድም። ከፈለግሽ በቤተሰብሽ ኬዝም አልገባም። ያ የሚያስደስትሽ ከሆነ ምክንያትሽንም ማወቅ አልፈልግም። ራስሽ ፈልገሽ እስካልነገርሽኝ ድጋሚ አልጠይቅሽም። ግን አንድ እንድታደርጊልኝ የምፈልገው ነገር አለ!” እያለኝ ስልኬ ጠራ። ከቤት ነው። አንስቼው ስለእማዬ በሰማሁት ነገር እግሮቼ ዛሉብኝ። የብርትኳን ቢላዋ አንስታ ታፋዋ ላይ ሰክታለች። ሰራተኛዋ እየተርበተበተች ነው የነገረችኝ። ስለእማዬ በሰማሁ ቅፅበት ፍትህን ረስቼዋለሁ።

"ምንድነው እሱ? ምንድነው? እናትሽ ምን ሆነው ነው?” አፌ ቃላት መትፋት አቃተው። ምንም አላስፈቀደኝምም። አልጠየቀኝምም። ስልኬን አንስቶ መልሶ ደወለ። ልሄድ ቆሚያለሁ። ግን መንቀሳቀስ ከበደኝ። ከሰራተኛዋ ጋር እያወራ እንደሆነ አውቃለሁ። ግን አልሰማውም። ኮቴንና ቦርሳዬን ሰብስቦ እጄን መንጭቆ ይዞኝ ሲወጣ እግሬን ለመራመድ ማዘዜን ባላውቅም ተከትዬው መኪናው ጋር ደርሻለሁ። በሩን ከፍቶ መኪናው ውስጥ ሲያስገባኝ፣ ስንሄድ፣ ከሰራተኛዋ ጋር ሲደዋወል፣ እቤት ይዞኝ ሲገባ… …… ጆሮዬ ጭውውውውው ይልብኛል። ጭንቅላቴ የሆነ ከባድ ነገር እንደተጫነብኝ ለአንገቴ ከብዶታል። …………

★ ★ ★ አሁንም በድግምጋሚ አልጨረስንም ★ ★ ★

@wegoch
@wegoch
@paappii
~ራሴው ማበዴ ነው… … #5~
(ሜሪ ፈለቀ)

"ራሔል ከዚህ በላይ እናትሽን እቤት ልታቆያቸው የምትችዪ አይመስለኝም። አደገኛ ነው የሚሆነው።”

"ዶክተር በፍፁም ሆስፒታል እንደማልተዋት ቃል ገብቼላታለሁ። አይሆንም!! ታውቅ የለ ምን ያህል እንደምትጠላ?”

“ራሔል እስቲ ተቀመጪ።” አለኝ ወንበሩን እያሳየኝ። በእማዬ ምክንያት ከማውቀው ልምድ በዶክተሮች አባባል ‘እስኪ አረፍ በይ፣ እስኪ ተቀመጪ፣ ለመረጋጋት ሞክሪ፣ የቅርብ ዘመድ ነሽ ወይ?…… ’ ዓይነት ንግግሮች ‘ ለሚከተለው አሳዛኝ ዜና ተዘጋጂ።’ የሚል አንድምታ ነው ያዘለው። ቅርፍፍፍፍፍ እያልኩ ተቀመጥኩ።

" አየሽ ራሔል በህይወት አንዳንዴ ትክክለኛው ውሳኔ ከባዱ ውሳኔ ይሆናል። አሁን እናትሽ ከፍተኛ የህክምና ክትትል ያስፈልጋቸዋል። እእ… … (እንዲህ እ…እ ሲጀምር የሚነግረኝ ነገር ጨንቆታል።) እ ራሔል ታውቂያለሽ እናትሽ ከአዕምሮ መታወኩ በላይ ካንሰሩ ጎድቷቸዋል። ብዙ ጊዜ የላቸውም።…… ” ምን እያለ እንደሆነ ገብቶኛል። ግን ደግሞ አልገባኝም። ብዙ ምክር አክሎበት እናቴ ከግማሽ ዓመት ያለፈ ጊዜ እንደሌላት ነገረኝ። በህይወት እያለች እንዳትሰቃይ ላደርግላት የምችለው ብቸኛ ነገር አባቴ እንዲያያት ማግባባት መሆኑንም አከለልኝ። …… አልጠየቅኩም። አልመለስኩም። ቢሮውን ለቅቄ ወጣሁ። ፍትህ ውጪ እየጠበቀኝ ነበር። ከትናንት ጀምሮ እዚሁ ነበረ።

"ፍትህ ምንም ነገር እንዳትጠይቀኝ።” ብዬው ነበር።

"ምንም ልጠይቅሽ አላሰብኩም።” ነበር መልሱ። እስከአሁንም ስለምንም አልጠየቀኝም። ወደ ስራው እንዲመለስ ደጋግሜ ወትውቼዋለሁ። አልሰማኝም እንጂ። ከዶክተሩ ቢሮ እንደወጣሁ ፍትህ ወደነበረበት ሄጄ ወንበር ላይ ዘፍ አልኩ። አጠገቤ ያለው ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳይመቻች አቀፈኝ። ጥሩ ዜና እንዳልሰማሁ ገብቶታል።

"እማዬ መሞቻዋ ደርሷል ተዘጋጂ አለኝ።” ስለው ደንግጦ ለቀቀኝ። "ከስድስት ወር ያለፈ ጊዜ የላትም።”

"እሺ። እሺ በቃ! እሺ።” የሚለኝ ከኔ በባሰ ግራ ተጋብቶ የሚለው ጠፍቶት መሆኑ ገብቶኛል። "እሺ በቃ ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን። አንድ መንገድ አናጣም።” ይለኛል።

"አሰቃየሁሽ አይደል?” አለችኝ እማዬ ገና ወደ ክፍሏ ስገባ። ሁሌም ቢሆን መጥፎ ነገር ካደረገች በኋላ ልክ ከቅዥቱ እንደባነነ ሰው ፍፁም ጤነኛ ጭንቅላት ይኖራታል።

"አንቺ ተሰቃየሽብኝ እማ።” እያልኳት ለአፍታ ሞት ለሷ ግልግል መሆኑ በጭንቅላቴ ሽው አለኝ። እንደዛ በማሰቤ ራሴን ተፀየፍኩት። ግን እንዳትሞት የምፈልገው ለሷ ነው ለራሴ? ዘመኗን ከመድሃኒት፣ ከቴራፒዎችና ከቅዥት ጋር በስቃይ እየኖረች ያለች እናቴ እንዳትሞት የምፈልገው ለሷ ስል ነው ለራሴ?

"እማ ፍትህ ይባላል። አንድ ላይ ነው የምንሰራው። ትናንት ሆስፒታል ያደረሰሽ……”

"አስታውሳለሁ። አውቄዋለሁ ልጄ…” አለችኝ ከግርጌዋ ቆሞ ወደነበረው ፍትህ እያየች። "መልካም ልጅ ነህ። በክፉ ሰዓት ባላውቅህ ደስ ይለኝ ነበር።” እያለችው። ወደ ክፍሉ አንድ ሰው ገባ። ድርብብ ያለ ጎልማሳ፤ ልብወለዶች ላይ ያለ ደግ አባት የሚመስል፤ ፀጉሩ እና ፂሙ ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት፤ ቁመቱ ረዥም፤ ቀላ ያለ ፤በለስላሳ ፂም የተሸፈነ ጉንጭ ያለው፤ ደልደል ያለ…… ሰውዬ

"ካስዬ መጣህ?” አለ ፍትህ ከቆመበት ሳይንቀሳቀስ ቀጠለና “ራሔል እሷ ናት። እሳቸው እናቷ ናቸው።” አለው።

"እንዴት ነሽ ልጄ?” ብሎ ሳብ አድርጎ በግዙፍ ሰውነቱ ውስጥ ወሸቀኝ። ፀጉሬን ደጋግሞ እየሳመ ወደ ሰውነቱ አጣብቆ አቀፈኝ።ልል የነበረው ‘ፍትህ የማላውቀውን ሰው እንዴት ይጠራብኛል? ነበር። ደረቱ ላይ በእጆቹ ተከብቤ ላስብ የቻልኩት ግን ‘ይሄን ፍቅር የት ነው የማውቀው?’ የሚለውን ብቻ ነው። ጀርባዬን አይዞሽ እንደማለት፣ አለሁልሽ እንደማለት አሸት አሸት አድርጎ ወደ እማዬ ሄደ። ወንበሩን ሳብ አድርጎ አጠገቧ እየተቀመጠ

"ሽማግሌ ነኝ አንቺን አንቱ አልልሽም። እንዴት ነሽ? እጅሽን ደግሞ እንዲህ አታድርጊው (የጉሉኮሱ መርፌ የተደረገላትን እጇን አንስቶ አስተካክሎ እያስቀመጠላት።) ያብጥብሽና ያምሻል።…………” አኳኋኑ ትናንት አብሯት የነበረ፣ ሲያስታምማት የከረመ ፣ የምታውቀው፣ የቅርብ ወዳጇ ዓይነት እንጂ ዛሬ የሚያውቃት አይመስልም።

"አባቴ ነው።” አለ ፍትህ

ለወትሮው አዲስ ፊት የሚያስደነብራት እማዬ እንኳን እንደምታውቀው ሰው ሁሉ የሚጠይቃትን ጥያቄ ደስ እያላት ትመልስለታለች። እጇን፣ ፀጉሯን የለበሰችውን ጋቢ እያስተካከለ ነው የሚያወራው። "ምግብ መውሰድ ትችያለሽ? ምግብ ከወሰድሽ ስንት ሰዓት ሆነሽ? ምን ባመጣልሽ ደስ ብሎሽ ትቀምሻለሽ? ……… ”

(አንዳንድ ሰው ገጥሟችሁ አያውቅም? ሰውየውን ገና እንዳያችሁት ላትወዱት አትችሉም። አንዳንድ ሰው ደግሞ አለላችሁ ገና እንዳያችሁት አትወዱትም። ጥሩ እያደረገላችሁ እንኳን ይከብዳችኋል።ሰውየውን የከበበው ቫይብ ነው!! ወይ ይስባችኋል አልያም ይገፈትራችኋል።)

ፍትህን ሆስፒታል ከእማዬ ጋር እንዲቆይ እና እኔ አርፌ እንድመለስ የነገረን በማስፈቀድ ዓይነት አይደለም። ትዕዛዝም አይደለም። ብቻ ‘እንቢ’ የሚሉት ዓይነት አጠያየቅ አይደለም። የገረመኝ ግን የእማዬ ከፍትህ ጋር ለመቆየት በደስታ መስማማት ነው።

“ወዴት ነው የምንሄደው?” አልኩኝ በመኪናው እቤት ሊያደርሰኝ ተስማምተን መንገድ ከጀመርን በኋላ

"ወደቤት ነዋ!”

"መንገድ ስተዋል በዚህጋ ነው ቤቴ።”

"ውይይ ………አንቱ ብለሽ አግተለተልሽኝ እኮ።(ዝግንን እያለው) የምንሄደው እኛ ቤት ነው። አሁን እቤትሽ ባደርስሽም አታርፊም። ብትፈልጊም ትናንት የተፈጠረውን ረስተሽ ምንም እንዳልተፈጠረ ልትተኚ አትችዪም።”

"ኸረ እንደውም የማላውቀው አዲስ ቤት እንቅልፍ እሺ አይለኝም። እዛው እቤቴ ይሻለኛል።” ያልኩት ከምሬ ነው። በእርግጥ ቤቴም ብሄድ ሰውነቴን ባሳርፍ እንጂ እንቅልፍ እንደማይወስደኝ አውቃለሁ።

"እስቲ ግድ የለሽም። እንድረስና መተኛት ካቃተሽ ራሴው ቤትሽ አደርስሻለሁ።” ብሎኝ መንዳቱን ቀጠለ።

ክፉ እና ደግ እንዳለየች ህፃን ልጁ እጄን ይዞ እየመራኝ ሳሎን አስገባኝ። ጎኑ ስር ሲያቅፈኝ፣ አንዴ ግንባሬን ሌላ ጊዜ ፀጉሬን ሲስመኝ ፣ እጄን ሲይዘኝ… …… ለእሱ ብዙ ዘመን ሲያደርገው እንደኖረ ሁሉ የተለመደ አይነት ነው። እኔ ያልለመድኩት ነገር ስለመሆኑ ማወቁን እንጃ! ማወቅ መፈለጉንም እንጃ!! እቤቱ እንደገባሁ መብላት መፈለጌን አልጠየቀኝም።ለሰራተኛቸው ምግብ እንድታቀርብ እና ለእንቅልፍ እንደሚረዳኝ ነግሮኝ ወተትም አፍልታ እንድታመጣ አዘዛት። መታጠብ እፈልግ እንደሆነ አይደለም የጠየቀኝ። ውሃው ሙቅ ወይስ ቀዝቃዛ ቢሆን እንደምመርጥ እንጂ። በእያንዳንዱ እንቅስቃሴው ለዘመናት አብረን የኖርን አይነት እንዲሰማኝ ያደርገኛል። ከታጠብኩ በኋላ እንድለብስ የፍትህን ቢጃማ ሱሪና ቲሸርት መታጠቢያ ቤቱ መስቀያ ላይ ሲሰቅል ይደብረኝ እንደሆነ አልጠየቀኝም። ቢሰፋኝም የሱሪውን ወገብ በማሰሪያው አጥብቤ እንድለብሰው ነገረኝ እንጂ። ምግቡን በእጄ አላስነካኝም። እያጎረሰኝ መብላት ጀመርኩ። እየሆነ ያለው ሁሉ ግራ ገባኝ።

"ለምንድነው እንዲህ ጥሩ የሆንክልኝ? ወይስ ለሁሉም ሰው እንዲህ ነህ?” አልኩት

"ለማንም ሰው ቢሆን አዎን ጥሩ ለመሆን ነው የምሞክረው። ላንቺ ግን በተለየ ጥሩ ለመሆን እየሞከርኩ ነው።”

“ለምን? ለምን በተለየ?”
አልኩት የዘረጋልኝን ጉርሻ ከመጉረሴ በፊት.....

አሁንም አልጨረስንም ***

@wegoch
@wegoch
@paappii
ራሴው ማበዴ ነው ~6
(ሜሪ ፈለቀ)


"ምክንያቱም ልጄ ይወድሻል። አንቺ ትወጂዋለሽ ወይስ አትወጂውም ሌላ ነገር ነው። ይህን የማደርገውም push ላደርግሽ አይደለም።”

"ማን? ፍትህ? መውደድ ማለት? በፍቅር እያልከኝ አይደለምኣ?”

"ነው። እንደዛ እያልኩሽ ነው። ወተቱን ማጊበትና ይህቺን ጉረሺ።” ያጎረሰኝን አላምጬ ሳበቃ

"እስከማውቀው ድረስ ፍትህ እንደኔ አይነት ሴት ምርጫው አይደለችም። ደግሞ ይቅርታ አድርግልኝና በሴት ረገድ ልጅህ መረን ነው። በጣም ይቅርታ ግን!”

"አውቃለሁ። ስለልጄ የማላውቀው ነገር የለም። ፍትህ እናቱን ያጣው በ13 ዓመቱ ነው። እኔ ለስራ ሌላ ሀገር በሄድኩ ማታ እቤት ገብተው በዘረፉን ወንበዴዎች በሽጉጥ ነው የተገደለችው። (እስከአሁን ያላየሁበትን መከፋት ፊቱ ላይ አየሁ።) ስትመታና ስትወድቅ ስትሞትም ፍትህ እዛው ነበር። እያያት!! ለብዙ አመታት የእናቱ ሞት ሀዘን የተጫነው ምስኪን ልጅ ነበር። ተንከባክቤ አሳደግኩት ፤ ደስተኛ ያደርገዋል ብዬ ያሰብኩትን ሁሉ አደረግኩ ፤ የእናቱ መጉደል ፍፃሜውን እንዳያበላሽ ስለፈራሁ አቀበጥኩት። ነገር ግን ቆይቶ ሲገባኝ ልጄን ለድርጊቶቹ ሀላፊነት የማይወስድ ግድ የለሽ አደርጌ ነው ያሳደግኩት፤ መጎዳቱን ፍራቻ ሲያጠፋ እንኳን አምርሬ አልቆጣውም ነበር። ምንም ጎድሎበት አያውቅም።ያለው ሁሉ በጥረቱ ያገኘው አልነበረም እናም ዋጋ የሚያስከፍለው ምንም ነገር አይፈልግም። ጥሩ ትምህርት ቤት አስተምሬዋለሁ። አስጠኚ ቀጥሬ እንዲጎብዝ ጥሬያለሁ። ዩንቨርስቲ ገብቶ ተመርቆ ቢወጣም ስራ መስራት አይፈልግም። እኔን ላለማስከፋት ነው ስራ የሚሰራው። ከዛ ይልቅ ከሴትና ከመጠጥ ጋር ውሎ አዳሩ ቢሆን ደስተኛ ነው። ስለእውነት አሁንም ቢሆን ጨክኜ አምርሬ ልቆጣው ያሳሳኛል። ቁጭ አድርጌ እመክረዋለሁ። እናንተጋ መስራት ከጀመረ ቀን ጀምሮ ስለአንቺ ሳያወራልኝ አድሮ አያውቅም። ቆንጆ መሆንሽን፣ ደረቅ መሆንሽን፣ በስራሽ ጉብዝናሽን፣ ስቀሽ እንደማታውቂ…… ። ላለፋት ሁለት ሳምንት ግን ፍትህ ሌላ ሰው ነበር። በጊዜ ወደቤቱ ይገባና ሲጨቀጭቀኝ ያመሻል። ‘ምን ሆና ይሆን? አትወደኝም እኮ ቁምነገር የሌለው ዱርዬ ነው የምመስላት፣ ካስዬ ቆይ እሺ እንድታዋራኝ ከዚህ በላይ ምን ላድርግ?’ ሲለኝ ይመሻል። ትናንት ደውሎ የተፈጠረውን ነገረኝ። ልጄ በህይወቱ ስለምንም እንደዚህ ግድ ሰጥቶት አያውቅም።” የሚያወራልኝን እየሰማሁ የቀረበውን ምግብ በጉርሻ አገባድጄዋለሁ።

"በቃኝ በናትህ ብዙ በላሁ።”

"አንድ የመጨረሻ ይህቺን!”

የፍትህ መኝታ ቤት እንዳርፍ ተሰናዳልኝ። ድምፁ ዝግ ያለ ተመሳጮች ለተመስጦ የሚጠቀሙበትን የሚመስል የኮሪያ ክላሲካል ሙዚቃ ተከፍቶ ክፍሉ የሆነ የሚያባብል ድባብ አለው።
"በቃ ትንሽ አረፍ በይና እናትሽጋ እንሄዳለን። የምትፈልጊው ነገር አለ?”

“የለም። በጣም ነው የማመሰግነው።” አልኩት አልጋው ጫፍ ላይ እየተቀመጥኩ።

"እንደሱ ስትዪኝ ይከፋኛል። እቤቴ እኮ አስገባሁሽ ፤ በእጆቼ አጎረስኩሽ …… ከዚህ በላይ ቅርበት ምንድነው? እንደአባትሽ እይኝ።…… ” ይሄን ሲለኝ ከየት መጣ ያላልኩት የእንባዬ ጥርቅም በሳግ ታጅቦ ተንዠቀዠቀ።… … አጠገቤ መጥቶ በእጆቹ አጀብ ደረቱ ላይ አኖረኝ። አላባበለኝም። እንዳለቅስ ፈቀደልኝ።

"ንገሪኝ!” አለኝ ሲበርድልኝ ጠብቆ

"ምኑን?”

"ይሄ የዛሬ ወይ የትናንት ሀዘን የፈነቀለው ለቅሶ እንዳልሆነ አውቃለሁ። ንገሪኝ ሁሉንም!!”

እናቴ ከመሞቷ በፊት ልውልላት የምችለው አንድ ውለታ አባቴ እንዲያገኛት ማድረግ ነው። ቢያንስ የዘመናት ፍቅሯን እጁን ዳብሳ ደስተኛ ሆና ትሞታለች። እናቴን ማጣት ማሰብ አልፈልግም። የባሰው ደግሞ ስትለየኝ ማን መሆኔን እንኳን ሳታውቅ እብደቷ ተነስቶባት መሆኑን ማሰብ ያሳብደኛል። ያ እንዲሆን አልፈልግም። የቀራትን ጊዜ ጭንቅላቷ ልክ መሆን አለበት!! ውስጤ እንዲቀር የምፈልገው የእናቴ ምስል የምትፈራኝና የምትሸሸኝ ‘አንቺ ደግሞ ማነሽ?’ የምትለኝ እብዷ እናቴ ምስል አይደለም። ያቺ በለስላሳ እጆቿ ደባብሳኝ የማትረካዋ ፣ እሷ ያልኖረችውን የስነ ምግባር ኑሮ እንድኖር የምትመክረኝ፣ በሌላት ጡት ‘በጡቴ ይዤሻለሁ በቀል ከሀሳብሽ አይኑር።’ ብላ የምትለምነኝ፣ ልጄ ስስቴ የምትለኝ፣ አገላብጣ እየሳመች ‘አሳቃየሁሽ ልጄ’ እያለች የምትለማመጠኝ፣ ለእርሷ ስል መኖሬ የሚገባት(የሚያሳስባት) እናቴ… … እሷን እናቴን ነው በልቤ ይዣት መኖር የምፈልገው።

"እንደምንም ብዬ አባቴን ማናገር አለብኝ።” አልኩት ካሳሁንን ሳለቅስ ቆይቼ። ያልኩት ግርር እንደሚለው ያሰብኩት ባይገባውም የገባው ለመምሰል ሲሞክር ሳየው ነው።

"ግን ልታናግሪው አትፈልጊም?” አለኝ።

"ላገኘውም አልፈልግም። የእሱን እርዳታ መጠየቅ ደግሞ ያሳምመኛል። ለእማዬ ስል ግን አደርግላታለሁ። ለሷ ስል አደርግላታለሁ።” አልገባውም። በጥያቄ ሊያስጨንቀኝም አልፈለገም። ከእቅፉ ወጥቼ ጋደም እንዳልኩ ከየትኛው ሃሳቤ በኋላ እንቅልፍ እንደወሰደኝ አላውቅም።… ……

በሚቀጥሉት ቀናት የካሳሁንን እና የፍትህን እማዬ አጠገብ መሆን፣ ራሴን ካሳሁን እቅፍ ውስጥ ወይም የፍትህ አልጋ ላይ አልያም የፍትህ ቢጃማ ውስጥ ማግኘት፣ የፍትህን በቡናና በቁርስ ሰበብ የቢሮዬን በር መክፈት… የተለመድኳቸው ክስተቶች ሆኑ። የሚፈጥሩብኝን ስሜት ግን በደነዘዘ ልቤ መረዳት አልቻልኩም።

ከሳምንት በኋላ አራታችንም(እኔ እና የስራ አጋሮቼ ፀሃፊያችንን ወይኗን ጨምሮ) ቢሮ ተሰበሰብን እና ለተወሰነ ጊዜ ስራ ላቆም መሆኑን ስነግራቸው በድንጋጤ አፈጠጡብኝ።

"ለምን? ቆይ እስከመቼ? ምን ተፈጥሮ ነው?” ጌትነት ነው የሚጠይቀኝ።

"እስከመቼ እንደሆነ አላውቅም ጌትሽ! ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው። መቼ እንደሆነ ባላውቅም ቃል እገባልሃለሁ ወደ ስራዬ እመለሳለሁ። እስከዛ ድረስ እጄ ላይ ያሉትን እንድትሰራልኝ ፈልጋለሁ።”

"ስራ ማቆሙ አስፈላጊ ነው? ራሁ please ፍቀጂልኝ እኔ ልርዳሽ? በምትፈልጊው ሁሉ እኔና ካስዬ ከጎንሽ ነን።” አለኝ ፍትህ ሌሎቹ ሲወጡ ጠብቆ።

"ፍትህ ልትረዳኝ ትፈልጋለህ?” አልኩት (ቁልምጫው ልቤን ቢሰርቀውም ባልሰማ አለፍኩት)

"Whatever it is.”

"መልካም! ብዙ ትግል እና ትእግስት የሚጠይቅ ስራ እጄ ላይ አለ። ሙሉ ሰዓትና አቅም ይፈልጋል።አሁን በሙሉ አቅሜ ልሰራ አልችልም። አስቸጋሪ ቢሆንም ይሄን ኬዝ አንተ እንድትይዝልኝ እፈልጋለሁ።”

" ራሁ እኔ ያንቺን ያህል ጎበዝ አይደለሁም። ……”

“ሁና! ጎበዝ ሁን! ጉብዝና ተፈጥሮ አይደለም። ጎበዝ ለመሆን ትለፋለህ እንጂ ጉብዝና ድንገት ጉብ የሚልብህ መንፈስ አይደለም። እኔን መርዳት ትፈልጋለህ? ይኸው……(መረጃ የያዘ ፍላሽ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጥኩለት)… አሁን እማዬጋ መሄዴ ነው። እየውና ስትወስን ደውልልኝ… ” ብዬው ወጣሁ።

"እሺ ላድርስሽ?”

"Am ok መንዳት እችላለሁ።”

እማዬጋ ስደርስ ካሳሁን ከእማዬ ክፍል አቅራቢያ ውጪ ተቀምጧል።

"አባትሽ ውስጥ ነው። ብቻቸውን ይሁኑ ብዬ ነው።” አለኝ ቀለል አድርጎ። ለመግባት ስፈጥን እጄን ይዞኝ። "ምንም አትሆንም እንደውም ደስተኛ ናት። ተያቸው።” አለኝ።

"ደስ የማይል ነገር ቢናገራትስ? የሆነ ነገር ብትሆን……” እጄን አስለቅቄው ገባሁ። መግባቴን ያየችው እሷ ብቻ ናት። እሱ (አባቴ) ከግርጌዋ ተንበርክኮ ሁለት እግሮቿን አቅፎ ያለቅሳል። እየሆነ ያለው ሁሉ ግርር አለኝ…… ከተቋሰሉት መቋሰል በላይ እንደምትወደው የሷን አውቃለሁ። የእሱ ግን… …

‘ገዳይሽ እኔ ነኝ ማሪኝ ፤ ያንቺን ስቃይ ለኔ
ያድርገው፤ ባንቺ ቦታ ልሰቃይልሽ……’ ይላታል። ያቀፋቸውን እግሮቿን ይስማል። ‘ማሪኝ እማ እኔው ነኝ በሽታሽ። ለምን አልነገርሽኝም? ለምን ሀጢያቴን አበዛሽው?’ እንባው እግሮቿን ያርሳቸዋል። እሷን አየኋት። እንባዋ ወደጆሮዎቿ ሲወርዱ ስትጠርጋቸው አየኋት።

* አሁንም አልጨረስንምኣ?******

@wegoch
@wegoch
@paappii
ራሴው ማበዴ ነው ... #7
(ሜሪ ፈለቀ)

እንባዋ ወደጆሮዎቿ ሲወርዱ ስትጠርጋቸው አየኋት። የእኔ መኖር ምቾት የሰጣት ስላልመሰለኝ ቀስ ብዬ ወጣሁ። እኚህ ሰዎች ሙድ ነው የሚይዙብኝ? ጭንቅላቴ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች እየተርመሰመሱ ቢሆንም ደምቆ የሚያቃጭልብኝ ‘መታመሟን ማን ነገረው?’ የሚለው ነው።

"እኔ ነኝ የነገርኩት።” አለኝ ካሳሁን ያሰብኩትን ያወቀብኝ መሰለኝ። ቀጠል አድርጎ "እነርሱ እስኪጨርሱ አንድ ቦታ ደርሰን እንምጣ?” ብሎኝ ተንቀሳቀሰ። ተከትዬው መኪናው ውስጥ ገባሁ። ብዙ ከተጓዝን በኋላተጀምሮ ያላለቀ ቤት ያለበት ጊቢ ይዞኝ ገባ። እያየሁት መንፈሱ ሲቀየር አስተዋልኩኝ። ሀዘን የተጫነው ሰውዬ ሆነ። ምንም ምንም ሳይለኝ ግድግዳውን ተደግፎ የተቀመጠ መጥረጊያ አንስቶ በጅምር ከቀረ የከራረመ የሚመስለውን ቤት ግድግዳና መሬት በጥንቃቄ ማፅዳት እና ማውራት ጀመረ።

"አበባ ጎበዝ አርክቴክት ነበረች። የፍትህ እናትን ማለቴ ነው። ለወደፊት ኑሯችን ራሷ ዲዛይን ያደረገችውን ቤት መገንባት ነበር የምትፈልገው። ይሄ ነበር የወደፊት ቤቷ ( መጥረጉን ቆም አድርጎ ቤቱን አመላከተኝ) ቤቷ ተሰርቶ ሳያልቅ እሷ ሞተች። ቤቱን አሰርቶ የመጨረስ ብርታቱ አልነበረኝም። በነበረበት ቆመ። ስትናፍቀኝ ላዋራት ፈልጌ መቃብሯ ጋር ስሄድ ሀዘኔ ይበረታል። ሙት መሆኗ በድን ያደርገኛል። እዚህ ስመጣ ግን እንደዛ አይሰማኝም። እዚህ የኔ አበባ ህይወት አላት። እዚህ ህልውናዋ ይሰማኛል። እና መቃብሯጋ መሄዴን ትቼ እዚህ መምጣት አዘወተርኩ። የሆነ ቀን እንደለመድኩት ስመጣ ፍትህ ቤቱን ሲያፀዳ አገኘሁት። ሁሌ ስመጣ ቦታው ፅዱ እንደነበር አስታወስኩ። ምንም አልተባባልንም። እስከትናንት ድረስም በዚህ ጉዳይ ቃላት ተለዋውጠን አናውቅም። ለ19 ዓመታት ይሄ ቦታ ፅዱ ነበር። እንዲህ ቆሽሾ አያውቅም። ሁሌም እሁድ ጠዋት መጥቶ እንደሚያፀዳው አውቃለሁ። አልመጣበትም። ሁሌም እሁድ ከሰአት እንደምመጣ ያውቃል። አይመጣብኝም። ትናንት ከዚህ በኋላ ወደዚህ ተመልሶ እንደማይመጣ ነገረኝ። በእናቱ ትዝታና ሀዘን መደበቅ እንደሚበቃው ነገረኝ። አየሽ ሁሌም የአዲስ ነገር ጅማሬ የአሮጌው መቋጫ ነው። ከአሮጌው ቅጥያ ከሆነ ምኑን አዲስ ሆነ?”

እየሆነ ያለው፣ የሰማሁት እና የማስበው ተፐውዟል። የካሳሁንና የአበባ ታሪክ ከእናትና አባቴ ታሪክ ጋር ይደባለቅብኛል። አባቴ ለእናቴ የፃፈላት ደብዳቤ ካሳሁን ለሚስቱ የፃፈላት ይመስለኛል። ደግሞ ስለፍትህ አስባለሁ። በፍፁም ለቅፅበት እንኳን ከፍቶት የሚያውቅ የማይመስለኝ ሰው ለነዚህ ሁሉ ዓመታት ይሄን ስቃይ እሹሩሩ ሲል ነበር የኖረው? እርስ በርሱ የተከላለሰ ነገር እያሰብኩ የቤቱ ደፍ ላይ ቁጭ አልኩ። መጥረጉን ሲጨርስ አጠገቤ መጥቶ ተቀመጠ።

"ታውቃለህ ከእናቴ በቀር የሚያውቀኝ ሰው ሳለቅስ አይቶኝ አያውቅም።” ካልኩት በኋላ እሱ ካወራው ልብ የሚቦረቡር ታሪክ ወይም እሱ ካለበት ስሜት ጋር በመልክም በቅርፅም የማይገናኝ ነገር ማውራቴ አሳፈረኝ።


"አየሽ አንዳንዴ ምንም ካልሰራንበት ዘመናችን ስህተት የሰራንበት ዘመን ይሻላል። ምክንያቱም ምንም ውስጥ ምንም የለም። ስህተት ውስጥ ቢያንስ የመሳሳቻ አንዱን መንገድ አውቀሽዋል። ደግመሽ በዚያ መንገድ መንደፋደፍ ወይም መንገድ መቀየር ያንቺ ምርጫ ይሆናል።” አለኝ። ለእኔ ያውራ ለራሱ ወይ ለሚስቱ አልገባኝም። ጭራሽ ያለውም አልገባኝም። ምን እየሆንን ነው? ጭራሽ እኔ የማወራው ነጭ እሱ የሚመልስልኝ ጥቁር!! እያበድን ነው እንዴ?… …ፀጥ ተባብለን ከቆየን በኋላ ተነሳ። ተመልሼ ሆስፒታል ስሄድ አባቴን ባላገኘው ደስ ስለሚለኝ መቆየታችንን ወድጄዋለሁ። ተከተልኩት። …… ቃል ሳንተነፍስ ሆስፒታል ደረስን።

"እኔ በቃ ወደቤት ልሂድ! ከቻልኩ በኋላ ብቅ እላለሁ።” አለኝ ከመኪናው ሳይወርድ። ተሰናብቼው ወደ እማዬ ክፍል እየሄድኩ ካሳሁንን ከጭንቅላቴ ማውጣት አልቻልኩም። መከፋት የተጫነውን ፊቱን ከሀሳቤ ማደብዘዝ አቃተኝ። እማዬና ፍትህ ከክፍሉ ውጪ የሚሰማ ሳቅ እየተሳሳቁ ደረስኩ። ሰላም ብያቸው ሳልጨርስ

"እኔ የምለው ጀብዱ ትወጃለሽኣ?” አለኝ ፍትህ የተጋነነ መገረም ባለው ድምፅ። የሰጠሁትን መረጃ አይቶት እንደሆነ ገብቶኛል።

“ማን ይጠላል?” አልኩት።

"እኔ!” አለኝ ኮስተር ብሎና አስረግጦ።

"ሃሃሃሃ ፈሪ ነህ ማለት ነዋ! ሊያውም የምትጠላው ጀብዱን አይደለም። የሚጠይቀውን ድፍረትና risk ነው። ” እያልኩት ፊቱ ላይ ስስት ያለበት ፈገግታ ተንሰራፋ…… እያወራን ካለበት ስሜት የማይገናኝ ዕይታ እያየኝ ነው። "ምንድነው?” አልኩት ግራ ሲያጋባኝ።

"ሳቅሽ!! ራሁ ድምፅ አውጥተሽ ሳቅሽ እኮ! ራስሽን ሰምተሽዋል?” እየፈነደቀ ነገር ነው ልበል? ድምፁ ውስጥ የምሰማው ነገር ምንድነው? ከመደሰት ያለፈ

"እና?”

"በፍፁም ድምፅ አውጥተሽ ስትስቂ ሰምቼሽ አላውቅማ።”
(ስቄ አላውቅም ይሆን? መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ የሳቅኩት? መቼስ ይሆን የሚያስቅ ነገር የሰማሁት? ከሁልጊዜው በላይ እንባን በሚያዘንብ ሁኔታ ተከብቤ ዛሬ ምን አሳቀኝ?)
አሳፈረኝ። ያሳፈረኝ ዕይታው ይሁን አነጋገሩ አልገባኝም። ‘ተሽኮረመመች’ ተባብለው ከእማዬ ጋር ተሳሳቁብኝ። አፍንጫዬ አላበኝ። ጉንጬ የቀላም የነደደም መሰለኝ። ምንድነው እየሆንኩ ያለሁት? መቼ ነው እንዲህ የሆንኩት?
ድሮ ድሮ ድሮ ድሮ ድሮ ድሮ… ……....

"ይሄ ኬዝ እንዲህ ቀልብሽን የሳበው የትኛው ነጥብ ነው? ግልፅ ማስረጃ ነው የተያዘባት። ራሷም ድርጊቱን መፈፀሟን አምናለች።”

"ፍትህ ሰዎቹን ፈራሃቸው እንዴ?”

"በፍፁም ፈርቼ አይደለም። ከእነሱ ጋር ስለመያያዙም ገና መላምት ነው ያለሽ።”

ከፍትህ ጋር ሻይ እየጠጣን እየተነጋገርን ያለነው ስለትዝታ ነው። ትዝታ የ23 ዓመት ልጅ ናት። የአጎቷን ‘ፍቅረኛ’ በአጎቷ ሽጉጥ አራት ጊዜ ተኩሳ መግደሏን አምናለች። ለፖሊስ እጇን የሰጠችው ራሷ ናት። ለመግደል አበቃኝ ያለችው ምክንያት ለጥፊም የሚጋብዝ አይደለም። አጎት በአዲሳባችን ካሉ ባለሀብት አንዱ ነው። በተጨማሪም የሚንስቴር ወንድም ነው። ትዝታ አባቷ በ7 አመቷ ስለሞተ ያሳደጋት አጎቷ ነው። በ16 አመቷ ከጋብቻ ውጪ የወደቻትን ልጇንም እያሳደገላት ነው።

"ሰውየው ምንም ነገር የማድረግ አቅሙ ያለው ሆኖ ሳለ ጠበቃ እንኳን የቀጠሩላት የእናቷ ዘመዶች ናቸው። አስበው ትዝታ ልጁ ማለት ናት። ሌላው የሟች ጉዳይ ነው። ሟች የናጠጠ ሀብታም ሰውዬ ፍቅረኛ ሆና እናትና አባቷ ግን ከልጃቸው እጅ ስባሪ ሳንቲም ያልተለገሳቸው እና ለእለት ምግብ የሚቸግራቸው ሰዎች መሆናቸው ሲደመር ፍቅረኛ እንዳላትም አለማወቃቸው የሚጎረብጥ ነገር አለው። ትዝታ የሆነን ሰው እየተከላከለች እንደሆነ ነው የሚሰማኝ።"

"ማንን?”

"እሱን ማወቅ ያንተ ድርሻ ነው። እ? ገብተህበታል?”

"እሺ። ገብቼበታለሁ።” ይበለኝ እንጂ እንዳላመነበት ያስታውቅበታል።

"ፍትህ በህይወትህ ያልተለመደ ዓይነት ስኬት ላይ መድረስ ከፈለግክ ያልተለመደ ዓይነት ድፍረት ሊኖርህ ይገባል። ከተራ መንገድ ለመውጣት ማፈንገጥ አለብህ። ለእኔ ብለህ ብቻ እንድታደርገው አልፈልግም። አንዲት እርምጃ ከመራመድህ በፊት አንተ እንድታምንበት እፈልጋለሁ።” አልኩት።

"እስቲ መጀመሪያ ከትዝታ ጋር የምገናኝበትን መንገድ አመቻቺልኝ።”

"ሌላው ችግር ይሄ ነው። ጉዳዩን ውስብስብ እና አዳጋች የሚያደርገው ትዝታ ምንም አይነት መረጃ አትሰጥህም። መታሰር ነው የምትፈልገው። ጠበቃ እንዲኖራትም አትፈልግም። አንድ ሺህ ጊዜ ብትጠይቃት አንድ ሺህ ጊዜ የምትመልስልህ አንድ ዓይነት
መልስ ነው። ለማንኛውም ግን ነገ ቀጠሮ አለኝ እናገኛታለን።”

በዚህ ጉዳይ ላይ እርግጠኛ ባልሆንኩበት ምክንያት ፍትህ ጥሩ ሰርቶ ማየት እፈልጋለሁ። እንድኮራበት እፈልጋለሁ። አባቱ እንዲኮራበት እፈልጋለሁ። እሱም ራሱ በራሱ እንዲኮራ እፈልጋለሁ።

"ፍትህ አባትህ ዛሬ ደብሮታል። አንተ ወደ ቤት ሂድ። እኔ እማዬጋ ልመለስ።”

"ህምም እናቴጋ ሄዶ ነበር?”

"አዎን” አልኩት ሂሳብ እንዲቀበሉን አስተናጋጅ ለመጥራት እጄን እያነሳሁ። እጄን ለቀም አድርጎ ያዘኝ። ደንግጬ አየዋለሁ።

"ይቅርታ ራሁ አስደነገጥኩሽ። ትንሽ አብረሽኝ ቆዪ?” አለኝ ያያዘውን እጄን አጥብቆ እየያዘው። በጭንቅላቴ እሺ አልኩት። ዓይኖቹን ሳያርገበግብ ስላፈጠጠብኝ ተጨነቅኩ። ዓይኔን ከዓይኑ ብነቅልም እንዳፈጠጠብኝ ይታወቀኛል። ምራቄን ስውጥ ጉሮሮዬ ያስተጋባል። ያልያዘውን እጄን ጣቶች ከጠረጴዛው ስር አፍተለትላለሁ።

"ዓይኖቼን እንድታያቸው የግድ ስለስራ ነው ማውራት ያለብን?” ድምፁ ወፍራም ግን ለስላሳ ዓይነት ሆነ። የሰውነቴ ቆዳ ላይ እንደሆነ ሞገድ ሽው ሲል ይታወቀኛል።

"እያሳፈርከኝ ነው ፍትህ!” አልኩት። ባላየውም ፈገግ ማለቱን አውቄያለሁ። ባይናገርም አንደኛውን እጁን ዘርግቶ የጠየቀኝ ሌላኛውን እጄን መሆኑን ስላወቅኩ አቀበልኩት። እጆቼን ዘርግቶ ጣቶቼን እያያቸው ቀና ይላል።

"ጣቶችሽ ያምራሉ።” ባለኝ ቅፅበት ተራ በተራ ሁለቱንም እጆቼን ጣቶቼጋ ሳማቸው። ሆነ ብሎ ከንፈሮቹን ጣቶቼ ላይ አቆይቶ የተሰማኝን ለማወቅ ዓይኖቼን ይፈልጋል። በርግጌ ተነስቼ ልቆም ትንሽ ነበር የቀረኝ። ‘አገኘሁሽ’ አይነት ፈገግታ ፈገግ አለ።

"ፍትህ ሰው እያየንኮ ነው?”

"እና እኔ ምንአገባኝ? ዓይኑን የሚያሳርፍበት ቆንጆ ጎኑ ባይኖር ነው።” ብሎኝ የእጆቼን መዳፍ ተራ በተራ ሳማቸው። አይኔን ጨፈንኩ ልበል?

"ስለአንቺ የማላውቀውን አንድ ነገር ንገሪኝ?” አለኝ ወደእኔ እየሰገገ ተጠግቶኝ።

"ምንም አታውቅምኮ። ስለምንድነው ማወቅ የፈለግከው?”

"አሁን እኔ ማወቅ ስለሚገባኝ ነገር” ድምፁ ልክ የሆነ ስሜት አይሰጥም። እንኳን ቃላት ሰካክቼ በስርዓቱ ላወራ የማስበውን እንኳን ይበትንብኛል።

"ማለት?”

"አሁን መስማትም ማወቅም የምፈልገው እነዚህን እጆች የሚጨብጣቸው ሰው አለመኖሩን ነው።(እጆቹ እጆቼ ላይ አስማታዊ መርመስመሳቸውን አያቆሙም።) ፤ ፀጉርሽ ውስጥ ጣቶቹን ሰክቶ የአንገትሽን ጠረን የሚምግ፣ ከንፈሮችሽን ጎርሶ በትንፋሽሽ እድሜውን የሚቀጥል፣ (ዓይኖቹ የሚጠራቸው የሰውነት አካሌ ላይ በስድ እይታ ያርፋሉ። እኔን ግን ምን እየነካኝ ነው? የምሰማው ድርጊት እየሆነ ያለ ያህል ይሞቀኛል።) በአይኖችሽ መስለምለም ቀኖቹን የሚያደምቅ፣ የሸሚዞችሽን ቁልፍ ከፍቶ… ”

"እረፍ ፍትህ! እረፍ በቃህ! ማንም የለም!” አስቤ የተናገርኩት አልነበረም። አሁንም የቅድሙን ፈገግታ ደገመልኝ። እጆቼን ስለለቀቀልኝ ተነፈስኩ። ሆስፒታል ሸኝቶኝ ተመለሰ። ካፌ ተቀምጠን ያደረገውን እንዳላደረገ በቅጡ እንኳን ሳይጨብጠኝ ነው የሄደው። ተናደድኩ ልበል? ምን እየሆንኩ ነው? ምን እንዲያደርግ ነበር የፈለግኩት? ምናልባት የሚያደርገው ሁሉ ለብዙ ሌሎች ሴቶች ያደረገው ለእርሱ ምኑም ያልሆነ ይሆን? ምንዓይነቷ ቀሽም ነኝ?

እማዬ አስር ጊዜ “ምን ሆነሻል?” ስትለኝ ራሴን ገስፃለሁ። እየሆንኩ ያለሁት በግሳፄ ማቆም የምችለው ጉዳይ ግን አልሆነም።

"አባትሽ ስለመጣ ተናደሻል?” እማዬ ስትጠይቀኝ በራሴ በሸቅኩ። ምንም የኑሮ ማገር እንዳላፈነገጠብኝ ስለፍትህ በዚህ ጥልቀት ማሰቤ አናደደኝ።

"ኸረ እማዬ… … ለምን እናደዳለሁ? አንቺ ደስ ካለሽ የኔ ደስታ ያ ነው።”

"እንደምትጠዪው አውቃለሁ። አንቺን ደስ ካላለሽ ድጋሚ እንዳይመጣ እነግረዋለሁ።”

"እማዬ አንደኛ አልጠላውም። አልወደውም ማለት እጠላዋለሁ ማለት አይደለም። ከመጥላትና ከመውደድ ፅንፍ መሃል ምንም ስሜት ማጣት አለ። እንደዛ ነው ለሱ ያለኝ ስሜት። ሁለተኛ የአንቺ ፈቃድ ይሁን እንጂ በተመቸው ሰዓት መጥቶ ሊያይሽ ይችላል።”

የአባቴን ጉዳይ በጤነኛ ጭንቅላቷ ስትሆን ደፍራ አታወራኝም። በዚህ ሁሉ ስቃይዋ እሱን ማፍቀሯ እኔን መበደል የሚመስላት ይመስለኛል። ለእኔ አንዳችም የአባት ርህራሄ ያላሳየኝን ሰው ጭንቅላቷ እስኪዛባ ማፍቀሯ እኔ ለእርሷ ያደረግኩትን መልካምነት መደለዝ ይመስላታል መሰለኝ። ስለእውነቱ ሰውየውን አልወደውም። እሷ ስለምታፈቅረው ግን አልናደድባትም። ያንን ደግሞ ያስተማረችኝ ራሷ ናት። ‘ኩታ በየፈርጁ ይለበሳል።’ ትለኛለች። ለእሱ ያላት ፍቅርና ለእኔ ያላት ቦታ የሚጋጭም ፣አንዱ ሲጨምር ሌላው የሚቀንስም ፣ የሚወዳደርም አይደለም። ስለዚህ እኔንና እሱን ለምርጫ አላቀርብላትም። ሁለታችንንም በልቧ መያዝ ትችላለች።

"እማዬ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ? ካልፈለግሽ አለመመለስ ትችያለሽ። ”

"ጠይቂኝ!”

"የእውነትሽን ያደረገሽን ነገር ረስተሽለት ነው? ይቅር ብለሽው ነው?”

ኸረ ኡኡኡ አሁንም አልጨረስንም

@wegoch
@wegoch
@paappii
~ ራሴው ማበዴ ነው ..... #8 ~
(ሜሪ ፈለቀ)


"በእርግጥ ይቅር ብዬው ነው። ያ ማለት ያደረገኝን ረስቼው ነው ማለት አይደለም። አየሽ ሚሚሾ በደንብ ስሚኝ ከመስከረም እስከ ነሃሴ በፍቅሩ ከልሎ ፣ በርህራሄው ከብቦሽ፣ በሀዘንሽ አልቅሶ፣ በደስታሽ ፈንጥዞ ፣ በጉያው አሙቆ…… ያከረመሽ ሰው ጳጉሜ 5 ላይ ቢበድልሽ የቱን ትቆጥሪበታለሽ? ብዙ ፍቅሩን ወይስ አንዲት በደሉን? ሰዎች ስሪታችን ሆኖ ከፍቅር ይልቅ በደል በደማችን ቶሎ ይሰርፃል። እኔ የመረጥኩት ብዙ ፍቅሩን ነው። ፍቅሩ በደሉን ይከድንብኛል። ለነፍሴም ሰላም የሚሰጠኝ ያ ነው።” አለችኝ በጣም በተረጋጋ መንፈስ። በልቤ ይዣት መኖር የምፈልገው ይህቺን እናቴን ነው። በብዙ ምክሯና ፍቅሯ በማይነቃነቅ የሞራል አለት ላይ የተከለችኝ እናቴን።

"እሺ!” ከማለት ውጪ እሷ ላለችበት የፍቅር ልእልና መልስ አልነበረኝም።

"ደግሞም ልጄ የተበደልነው ህመም ከበደልነው በላይ የሚጠዘጥዝ እንደሆነ ስለሚሰማን የተደረገብን እንጂ ያደረግነው የሚፈጥረው ቁስል አያመንም እንጂ አባትሽን ከበደለኝ በላይ በድዬዋለሁ። ምናልባትም እኔ ካለፍኩት ስቃይ ያለፈ ተሰቃይቷል።” አለችኝ ቀጥላ። ‘አንቺ በየሆስፒታሉ ስትሰቃዪ እሱ ሚስት አግብቶ ወልዷል። የወለዳትን ልጅ ድሯል። እንዴት ተሰቃየ?’ ልላት ነበር ያሰብኩት። እንደ እማዬ ፍቅርና ቅንነት የሞላበት ሀሳብ ባልታደልም ይሄን ማለት ቅን ሀሳቧን በክፋት የመበረዝ ሀጢያት ስለመሰለኝ ዝምታን መረጥኩ።

በሰዎች የእለት ተዕለት ኑሮ ውስጥ የማይቀየር አንድ ህግ አለ። የሰዎች ድርጊት የሀሳባቸው ልጅ ነው። ልምዳቸው ደግሞ የሀሳባቸው የልጅ ልጅ ነው። ታስባለህ– ታደርጋለህ– ልምድህ ይሆናል። ድርጊትህ ወይም የየዕለት ልምድህ በሀሳብህ ያረገዝከውን አንኳር ይመስላል።

በሚቀጥለው ቀን አባቴ እናቴን ሊያያት ሲመጣ እኔና ፍትህ ትዝታን ልናያት ሄድን።

"እኔ የማንም እርዳታ አያስፈልገኝም። አንቺንም እሱንም አልፈልግም።” አለችኝ ትዝታ ከዛሬ በኋላ ጠበቃዋ ፍትህ መሆኑን ስነግራት። ከብዙ ልመና ቀረሽ ንግግር በኋላ ፍትህ ጠበቃ እንዲሆን በ‘ምንቸገረኝ’ ተስማማች። ትቻቸው ልወጣ ስል

"ጠበቃ ልጅ አለሽ?” አለችኝ።

"የለኝም። ምነው ጠየቅሽኝ? ትዝታ በልጅሽ እያስፈራራሽ ያለ ሰው አለ? ንገሪኝ? ማንም ቢሆን ከህግ አያመልጥም። በእኔ ልትተማመኚብኝ ትችያለሽ እባክሽ ንገሪኝ።” ከዚህ በኋላ ምንም ቃል አልተናገረችም። ትቻቸው ወጥቼ እንኳን የኔ ጭንቅላት ግን በሀሳብ እዚህና እዚያ መርገጡን አላቆመም።

ከዚህ ቀን በኋላ አባቴ በየቀኑ እናቴጋ ይመጣል፣ ፍትህ በትዝታ ጉዳይ አዲስ ነገር ለማግኘት ቀን ሲሯሯጥ ይውላል… … አመሻሹን እማዬጋ መጥቶ አይቶን ወደቤቱ ይሄዳል ወይ ያድራል ፣ ካሳሁን በተመቸው ሰዓት ሁሉ ከእኔና ከእማዬ ጎን ይሆናል… ፤ እኔ የፍትህ ክፍል ማደሬን ትቼ ፍትህ ሆስፒታል የሚያድር ቀን እቤቴ አድራለሁ። ሌላውን ቀን ከእማዬጋር። ……
በአንዱ ቀን አባቴ በትንሽዬ ካርቶን ያለ ነገር ሰጥቶኝ ሄደ። እቤቴ ገብቼ አየሁት። ደብዳቤዎች ናቸው። እማዬጋ የሌሉ እሱ የፃፈላት ደብዳቤዎች። አንብቤያቸው ስጨርስ አንድ ነገር ገባኝ። እማዬጋ ያሉት በሙሉ የፍቅር ደብዳቤዎች ናቸው። እሱጋ ያሉት ግን ቅሬታና በደል የተፃፈባቸው ናቸው። እንደ እማዬ አባባል እሱ አንዲትን በደል መርጧል። እሷ ለዘመናት የፍቅር ደብዳቤዎቹን ስታነብ እሱ ለዘመናት በደሉን እያነበበ ቂም ሲደምር ኖሯል። …… እሷ ከመስከረም እስከ ነሃሴ ላይ ናት። እሱ ግን ጳጉሜ 5 ላይ ነው። በሬ ሲንኳኳ ነው የባነንኩት

"ፍትህ? እማዬ ምን ሆነች?”

"ኸረ ምንም አልሆነችም። አባትሽ እሷጋ ሊያድር ነው። ወደቤት ከመግባቴ በፊት ስለትዝታ አንዳንድ ነገር ላውራሽ ብዬ ነው የመጣሁት።”

"ነገ መድረስ የማይችል ጉዳይ ነው?”

"ወሬው ይደርሳል። ……” ብሎኝ እጆቹን በአንገቴ ስር አሳልፎ ፀጉሬ መሀከል ጣቶቹን ሰክቶ ወደራሱ አስጠጋኝ። አንገቴ ስር ስሞኝ በሹክሹክታ "… ይሄ ግን ለነገ ማደር አይችልም ነበር።” አለኝ።

በሰላሳ አንድ ዓመቴ ማንም ወንድ ነክቷት የማታውቅ ድንግል ሴት መሆን የሚያኮራ ነገር ይሁን የሚያሳፍር አላውቅም። (‘ድንግል’ የሚለውን ቃል እጠላዋለሁ። ቃሉን እንጂ ነገርየውን አይደለም። በእርግጥ ነገርየውንም ልውደደው ልጥላው እርግጠኛ አይደለሁም። ቃሉ ግን የሆነ አፍ ላይ ሲባል ራሱ ድንግል፣ ደናግል፣ ድንጉላ……… ድንዝና አለበት።) እውነታው እግሮቼ መሃል ካለ ነገር ድፍንነት ወይ ጠባብነት በላይ ዓይኖቼን የማያስነቅሉ የኔን ትኩረት የሚሹ አሳሳቢ የዕለት ተዕለት ጉዳዮች የከበቡኝ ሴት ሆኜ በመኖሬ ትርጉሙም ጣዕሙም አይገባኝም። ድንገት እንኳን በሀሳቤ ሽው ካለ የማልም የነበረው አቅፎኝ የሚያድር የሆነ የማላውቀው ፈርጣማ ወንድ ሰውነት ነው። ማቀፍ ብቻ!! ሌላውን ‘ፓኬጅ’ አላስበውም። እኔ እና እማዬ ብቻችን መኖር የጀመርን ዓመት እማዬ ሲነሳባት ለሊቶቹ ይረዝሙብኛል። ምን እንደምፈራ አላውቅም ግን ስለምፈራ ዓይኔን አልከድንም። ጨለማው፣ ኮሽታው፣ ፀጥታው…… ሁሉም ያስፈራኛል። እጅግ ጥልቅ ፍርሃት እፈራለሁ። ድፍረት የፍርሃት ተቃራኒ አይደለም። የፍርሃት ሌላ ተቃራኒ ሊኖረው ይገባል። ምክንያቱም ድፍረት አለመፍራት አይደለማ። ይልቁንስ ድፍረት ፍርሃትን መጋፈጥ ነው። ድፍረት ፍርሃት እንዳያስቆምህ እየተንቀጠቀጥክም ሆነ እየዳህክ በፍርሃትህ ጫካ ውስጥ ሰንጥቀህ ማለፍ ነው።

እማዬ እና አባቴ ከተለያዩ በኋላ ከታላቅ እህቷ (ከአክስቴ) ጋር ነበር የምንኖረው። የአስራ ሁለተኛ ክፍል ትምህርቴን ጨርሼ ውጤት እየጠበቅኩ በነበረበት ክረምት አክስቴ ትኖር የነበረበትን ትልቅነቱ እና ፀጥታው የሚያስፈራ ቤቷንና ቢያንስ በዓመት ሶስቴ እብደቷ የሚነሳባት እህቷን (እናቴን) አስተዳድሪ ብላኝ አውስትራሊያ ከሄዱ ከእኔ እድሜ በላይ ያስቆጠሩ ቤተሰቦቻቸውን ተቀላቀለች። ከእርሷ በቀር ሀገር ውስጥ የቀረ የቅርብ ዘመድ ያልነበራት እናቴ ብዙም ሳትቆይ የበረራ ቁጥሯን መቁጠር ጀመረች። እንኳን እሷን ላረጋጋት እኔ ከርሷ ብሼ እጅና እግሬ እየተንቀጠቀጠ አለቅሳለሁ። መድሃኒቷን በስቃይ ወስዳ ስታንቀላፋልኝ። እያንዳንዱ የቆዳዬ ነጠብጣብ ቀዳዳ ፍርሃትን እየማገ ወደሰውነቴ ሲነዛው እየተሰማኝ ተስፋ ላለመቁረጥ እና ላለመውደቅ እታገላለሁ። ለፍርሃት እጅ ላለመስጠት!! ያ ነው ድፍረት ማለት። መታገል!! በነዚህ ጊዜያት ነበር በእቅፉ የሚከልለኝ ሰውነት የምመኘው!! ሰውነቱን እንጂ ሰውየውን አልሜ አላውቅም። ሰፊ ትከሻ፣ ሰፊ ደረት፣ ፈርጣማ ጡንቻ፣ ረዥም ቁመት…… ለውበት ሳይሆን ከፍርሃቴ ለመከለያ፤ ለስሜት ሳይሆን ለመደበቂያ፤ ለመፈንጠዣ ሳይሆን ለመወሸቂያ… …ከአንገቱ በላይ ባይኖረውም አልያም ምንም ቢመስልም አስቤው አላውቅም።

"ራሁ? እየሰማሽኝ እኮ አይደለም። ምን ሆነሻል? ከቅድም ጀምሮ ላጫውትሽ እሞክራለሁ። ከእኔ ጋር አይደለሽም።”

"ይቅርታ ፍትህ ትንሽ ራሴን አሞኛል።”

"ምን ላድርግልሽ? ሀኪም ቤት ልውሰድሽ? (እጁን ግንባሬ ላይ አድርጎ ማተኮሴን ያረጋግጣል። በጭንቅላቴ ንቅናቄ መሄድ ያለመፈለጌን ነገርኩት።) እሺ በቃ ነገ ይደርሳል ነገ አወራሻለሁ።እረፍት አድርጊ!” ብሎኝ ተነሳ። ምን አስቤ እንደሆነ እንኳን ለመረዳት ከራሴ ተማክሬ ያላደረግኩትን ድርጊት ተስፈንጥሬ እጁን ይዤ አሰቆምኩት። ቀጥዬ ለምን እንዳስቆምኩት የምሰጠው ምክንያት አልነበረኝም።

"ወዬ? ምን ላድርግልሽ? እንዲህ አድርግልኝ በይኝ። እ ራሁ? (ተመልሶ ተቀምጦ ይዞ ያስቀረውን እጄን እያሻሸ ፣ዓይን ዓይኔን እያ
የ እና ሁሉም የስሜት ህዋሳቶቼ በሚገባቸው ድምፅ ተንሾካሾከ።) ልታወሪልኝ የምትፈልጊው ነገር አለ? እ? እሺ እንዳድርልሽ ትፈልጊያለሽ?”

"አይይይ አልፈልግም።” አልኩት። አጠገቤ እንዲሆን እኮ እፈልጋለሁ። ሲነካኝ ግን እበረግጋለሁ። እጆቼን ሲያሻሽ ፣ ቅድም እንዳደረገው አንገቴ ስር ሲስመኝ ፣ ዓይኖቼን በሚለማመጡ ዓይኖቹ ሲያያቸው…… መሸሽ እፈልጋለሁ። እንዲህ ሲያደርግ የሚሰማኝን ስሜት ስለምጠላው አይደለም። ስለምወደው እንጂ። ነገር ግን ደስ የሚለኝ አዲስ ስሜት ያስፈራኛል። ሁሌም ቢሆን ያልተለማመድነው አዲስ ነገር፣ አዲስ ሀሳብ፣ አዲስ ስሜት……… ብቻ አዲስ ልምድ መጠኑ ቢለያይም ፍርሃት ያጅበዋል። ምክንያቱ ደግሞ ውጤቱ ከግምት ያለፈ ማረጋገጫ የለውም። ለዚህ ይመስለኛል የብዙ ሰዎች ኑሮ የተለመደ እና የተደጋገመ የሚሆነው። ከአዲስ ነገር ጋር አብሮ ብልጭ የሚለውን ፍርሃት መጋፈጥ የቻሉ ጥቂት ደፋሮች ለአለማችን አዳዲስ ሀሳቦች እና ፈጠራዎች አበርክተዋል።

"እሺ እኛ ቤት እንሂድ? ከካስዬ ጋር ስትጫወቺ ይለቅሻል። እንሂድ?”

"አይ… … ስለትዝታ የደረስኩበት ነገር አለኝ አላልክም ነበር? እሱን እንድትነግረኝ ነው።” የሚል ምክንያት ነበር የመጣልኝ

"ስለትዝታ ልትጠይቂኝ ነው እጅሽ የሚያልብሽ?( ያላበው መዳፌን በእጁ እየጠረገ ያደርቃል። ይሄኔ እኮ ድምፅ ከጆሮ ውጪ በሌላ የስሜት ህዋስ እንዴት ይተረጎማል? ብሎ የሚጠይቅ አላዋቂ አይጠፋም። አሁን ፍትህ እያወራ ያለበት ባለጣዕም ድምፅ ቀላል ይጣፍጣል?) ስለትዝታ ልትጠይቂኝ ነው ዓይንሽ የሚሸሸኝ? (ይሄን ያለበት ድምፅስ ቀላል የሚያውድ መዓዛ አለው?) ስለትዝታ ልትጠይቂኝ ነው ጉንጭሽ የቀላው? (ይሄኛው ቀለማት አሉት። ዓይን የሚይዝ የቀለም ስብጥር) ስለትዝታ ልትጠይቂኝ ነው ቃላት ለማውጣት ያማጥሽው?( ይሄኛው እንደሚያባብል የውሃ ዳር ንፋስ በቆዳዬ ላይ ሽውውውው እያለ ይዳብሰኛል።)" ጭራሽ የማወራው ጠፋብኝ። በዛው ድምፅ ቀጠለ

"ስለስራ ስታወሪ ዓይኖችሽ ዓይኖቼን ያሳድዳሉ ፣ አንገትሽን ቀና አድርገሽ የምትናገሪው ተፅፎ የተሰጠሽ አይነት ‘articulated’ ነው፣ በጥያቄሽ ብዛት እኔን ያልበኛል። …… ንገሪኝ ምን ልትዪኝ ነበር እጄን የያዝሽኝ?” (ይሄንን ድምፅ ጥፍሬ እና ፀጉሮቼ እንኳን ላይሰሙት አይችሉም።)

"ምንም!! ምንም የምልህ ነገር ኖሮኝ አይደለም። …… በቃ እንድትቆይ ብቻ ፈልጌ ነው።”

"እሺ (ያልከለለውን ፀጉሬን ወደኋላ እያደረገ) እሺ እንድቆይልሽ እስከምትፈልጊው ጊዜ ሙሉ የእድሜዬን ቁጥርም ቢሆን እቆይልሻለሁ። ምን እያደረግኩልሽ እንድቆይ ነው የምትፈልጊው?”

"አላውቅም!! ፍትህ የተሰማኝን ስለነገርኩህ እንዳፍር እያደረግከኝ ነው።" ስለው ፈገግ ማለቱን ሳላየው በምን አወቅኩ? ምራቄን እየደጋገምኩ በሚያስተጋባ ጉሮሮዬ የምውጠው ምን ሆኜ ነው? አፍንጫዬ ሳይቀር የሚያልበኝስ?

"እሺ!!” ብሎኝ እጄን ለቀቀኝ። ከሶፋው ላይ ትንሽዬዋን ትራስ አንስቶ እኔ ከተቀመጥኩበት በተቃራኒ ጥግ ተቀመጠ።ትራሷን ጭኑ ላይ ካስቀመጠ በኋላ በእጁ እየመታ ጠቆመኝ። ጀርባዬን ሰጥቼው እግሬን ሰቅዬ እሱን ተንተርሼ ተጋደምኩ።

"ፊትሽን አትከልዪኝ። ወደዚህ ዙሪና ከፈለግሽ ዓይንሽን ጨፍኚ።” አለኝ ቀጠለና። እንዳለኝ አደረግኩ። ዓይኔን ግን አልጨፈንኩም። ፀጉሬን በጣቱ እያበጠረ ለደቂቃዎች ካለምንም የቃላት ልውውጥ ከቆየን በኋላ።

"እንቅልፍሽ ከመጣ መተኛት ትችያለሽ።” አለኝ

"ከዛስ? አንተስ?”

"ያላደለው ጨለማ ላይ አፍጥጦ ያድር የለ? አንቺን የመሰለ ውበት ላይ አፍጥጦ ማደር ተገኝቶ ነው? ውብ’ኮ ነሽ ካስዬ ይሙት! (እጄን የማስቀምጥበት አጥቼ አቅበዘበዝኩት።) እፍረትሽ መጣ?” ብሎኝ ሳቅ ሲል በጨረፍታ አየሁት።

" አንዳንድ ነገር ሳጣራ ነበር። ምን ያህል እንደሚጠቅመኝ ባላውቅም አንዳንድ መረጃዎች ……”

"እስኪ ንገረኝ።"

"የሟች ታሪክ ትዝታ ካለችው የራቀ ነው። ሟች የሰውየው ፍቅረኛ አልነበረችም። ከዚያ ቀን በፊትም ተያይተው አያውቁም። የምትማርበት ትምህርት ቤት ጓደኞቿ የሞተች ዕለት መጥቶ ከትምህርት ቤቷ ወሰዳት ያሉትን ሰው አገኘሁት።”

"እና?” ከተጋደምኩበት ቀና ብዬ ለመልሱ አቆበቆብኩ። ፈገግ አለ። ‘ስለስራ ሲሆንማ እንዲህ ነው የምትሆኚው’ የሚል ትዝብት ያለበት ዓይነት ፈገግታ።

"ወንጀሉን መሸፈኛ ስራው ትዳር ፈላጊ አገናኝ ነው። ዋነኛ ስራው ተማሪ ህፃናትና ወጣት ሴቶችን ለከተማችን ዋልጌ ሀብታም ሽማግሌዎች ማቅረብ ነው። ‘ሀብታም የሆነ ባል ፈልጋለሁ ስላለችኝ ነው ያገናኘኋት።’ ባይ ነው። ትዝታ ለመጀመሪያ ጊዜ እቤታቸው የመጣችን ሴት ‘ልጄን በጥፊ ስለመታቻት’ በሚል ቀሽም ምክንያት ትገድላታለች ብሎ ማመን ይከብዳል። ካልሆነስ ማንን እየተከላከለች ነው? ሰውየውን? እሱስ ቢሆን ከዚያን ቀን በፊት አይቷት የማያውቃትን ሴት ለመግደል ምን በቂ ምክንያት ይኖረዋል?”

"አንድ የሆነ ነገር ግን አለ። ልጅ አለሽ ወይ ብላ የጠየቀችኝ ቀን በደንብ አስተውለሃታል? አነጋገሯ ለልጇ ብላ እየከፈለች ያለችው መስዋዕትነት እንደሆነ ነገር ነው።”

"ሌላው ነገር… …ማንም የሚያውቀው ሰው ክፉ ስለማያወራለት አጎቷ አንድ ትኩረቴን የሳበ መረጃ ሰማሁ። የትዝታ ፍቅረኛ ፣ የልጇ አባት ትዝታ እርጉዝ በነበረችበት ወቅት እቤታቸው ድረስ መጥቶ አጎትየውን ደብድቦት ሄደ። ከዚያ ቀን በኋላ ልጁን አየሁት የሚል ሰው የለም። ትዝታም ምንም ልትነግረኝ ፈቃደኛ አይደለችም። አጎትየው በሁለቱ ግንኙነት ደስተኛ ካልነበረ ጥቃት ሊያደርስ የሚገባው እሱ ሆኖ የተገላቢጦሽ እንዴት ሆነ?”

"እሱን እያሰብኩ ነበር። ጎብዘኻል ግን ደስ ብሎኛል።” አልኩት ለጊዜውም ቢሆን ያ የሚያሽኮረምመኝ ፍትህ ተዘንግቶኝ ዓይን ዓይኑን እያየሁ።

"በልብሽ ደምቄ ለመፃፍ የሚያስከፍለኝ ጉብዝናን ከሆነ እተጋለሁዋ ምን አማራጭ አለኝ?” አለኝ እሽኩርምሚቴን በሚያመጣው ድምፁ። ተመልሼ እንደመጀመሪያው እላዩ ላይ ተጋደምኩ እና ዓይኔን ጨፈንኩ።

★ አልጨረስንም ካላችሁ አልጨረስንም★
★ጨርሰናል ካላችሁም አልጨረስንም.....

@wegoch
@wegoch
@paappii
~ ራሴው ማበዴ ነው .....#9~
(ሜሪ ፈለቀ)

ፀጉሬን በጣቶቹ እያበጠረ መነሻም ማረፊያም የሌለው ወሬ እያወራኝ ለምን ያህል ደቂቃ እንደቆየ አላውቅም። እንቅልፍ ወስዶኝ የነቃሁት ለሊት ዘጠኝ ሰዓት ነው። የሶፋውን መደገፊያ ተደግፎ በተቀመጠበት እንቅልፍ ወስዶታል። ጣቶቹ ከፀጉሬ መሃል አልወጡም። በሁለት የሶፋ ትራስ እግሬን ሸፍኖ ከብርድ ከልሎልኛል። ሆስፒታል ለማደር አስቦ ስለነበር የወጣው ቱታ ሱሪና ጃኬት ነበር የለበሰው። ጃኬቱን አውልቆት እጄን አልብሶኝ በ‘ፓክ አውት’ ነበር። ቀሰቀስኩት።

" ፍትህ ተነስ በስርዓቱ ተኛ አንገትህን ያምሃል። ተነስ እኔ መኝታ ቤት ተኛ። እኔ እማዬ ክፍል እተኛለሁ።” ይሄን የሚለው በምክንያትና በእውቀት ካላመንኩ የሚለው ጭንቅላቴ ነው። ልቤ ግን ከአጠገቡ መራቅን አልፈለገም።

"ከአንቺጋ እንድተኛ ካልፈቀድሽልኝ እዚሁ ሶፋ ላይ የምለብሰው ስጪኝና እተኛለሁ።” አለኝ አይኑን እንኳን አስተካክሎ ሳይገልጥ። ግራ ገባኝ ምን እንደምለው። ያንን እሱም ያወቀ መሰለኝ

"አብረን ተኝተን ነበር እኮ! አልጋ ላይ ሲሆን ምኑ ይለያል? ራሁ ስወድሽ አታወሳስቢው።”

"እሺ!” እያልኩት ወደመኝታዬ ገባሁ። ተከትሎኝ ገብቶ ጫማውን ብቻ አውልቆ ቀድሞኝ አልጋ ልብሶቹ ውስጥ ገብቶ በጀርባው ተኛ። አይኑን ጨፍኖ እጁን ለማቀፍ ዘረጋልኝ። አለማወሳሰብ ይሔ መሆኑን እየገመትኩ እቅፉ ውስጥ ገባሁ። በሁለቱም እጆቹ ደረቱ ላይ አጣብቆ አቅፎኝ ተኛ።… … አፌን እየሞላ እና ጉሮሮዬ ውስጥ የገደል ማሚቶ እየሰራ የሚያልፈውን ምራቄን እየዋጥኩ፤ ድው ድውታው ለእርሱ የሚሰማውን ልቤን ለመቆጣጠር እየታገልኩ የሚቀጥለውን እንቅስቃሴ ጠበቅኩ።… … ጠበቅኩ። …… ጠበቅኩ። …ተኝቷል። …… እንቅልፍ ወስዶታል። ካለፍርሃት ተኛሁ።
.
.
.

"አገኘሁት! ራሁ አገኘሁት!” ይለኛል የሆስፒታሉ ኮሪደር መሃል እየደነሰ

"ምኑን? እስኪ አንዴ ዳንስህን አቁመህ ንገረኝ!”

"የትዝታን ፍቅረኛ አገኘሁት!”

"በጣም ጥሩ! የሚጠቅም መረጃ አገኘህ?”

"ገና ነው። ደቡብ አፍሪካ ነው ያለው። ከሀገር እንዲወጣ ያደረገው ማን እንደሆን ገምቺ? የትዝታ አጎት! አስፈራርተውት ነው ከሀገር እንዲወጣ ያደረጉት።”

"ለምን?”

"ትዝታን ለሌላ ለተከበረ ሰው ሊድሯት እንደሆነና ከሷ ህይወት እንዲወጣ እንዳስፈራሩት ጓደኛው ነው መረጃ የሰጠኝ። የሚደውልለትን ስልክ ሰጥቶኝ ደውዬለት ነበር።”

"እና?”

" በዚህ ርቀት ሆኖ እንኳን ይፈራቸዋል። ገና ስለትዝታ ሳነሳበት ‘ሰውየው አረመኔ ነው። አታውቁትም። ትንፍሽ ብል ይገድለኛል።’ አለኝ። ትዝታ ያለችበትን ሁኔታ አስረዳሁት። ልጁ ያለእናትና አባት መቅረቷ መሆኑን ስነግረው ስራ ቦታ መሆኑን እና መልሶ እንደሚደውልልኝ ነግሮኝ ስልኩን ዘጋው።”

"በቃ?”

"ለጊዜው አዎን በቃ!”

“እና የሚያስደንስህ ይሄ ነው? ገና የመፅሃፉን ሽፋን እየገለጥክ እንደሆነ አልገባህም ልበል? ገና ገፅ አንድን እንኳን አላነበብክም እኮ!”

"ራሁዬ ገፅ አንድ ላይ ነኝ ማለት ታዲያ ቢያንስ ትክክለኛውን ትራክ አጊንቻለሁ ማለት አይደል? የተሳሳተ መፅሃፍ ካልገለጥኩ am good ማለት ነው። ሌላው የውልሽ ትዝታን አናገርኳት። ‘ተወኝ’ ከሚል ቃል ውጪ ትንፍሽ ብላ የማታውቅ ልጅ። የልጇን አባት እንዳገኘሁት ስነግራት ከመቀመጫዋ ዘላ ተነስታ ‘በህይወት አለ?’ ብላ ነበር የጠየቀችኝ። ደስ ያላት ትመስላለች። ሞቷል ብላ አስባ ነበር ማለት ነው። ከዚህ ተጨማሪ ነገር ልትናገር አልፈለገችም። ይልቅ ያሰብሽውን ንገሪኝ።”

"የማስበውማ እንዴትም ብለህ ድጋሚ ልታናግረው ይገባል! ስለሰውየው የሚያውቀው ነገር የሚያስገድለው ወይም ከሀገር የሚያሰድደው ከሆነ ሰውየው እንዴት ያለ ወንጀል ውስጥ የዘቀጠ ቢሆን ነው? ስለሰውየው ተጨማሪ መረጃዎች መሰብሰብ አለብህ። የማስበው ዜሮ ላይ እንዳለን ነው።”

በእርግጥ ለእርሱ ይሄን ልበለው እንጂ በትዝታ ጉዳይ የሚገኙት መረጃዎች ብጥቅጣቂና ለማስረጃነት የማይበቁ ምስክርነቶች መሆናቸው ተስፋ አስቆራጭ ሆኖ እንኳን በየቀኑ መረጃ ለማግኘት የሚያደርገው ጥረት እያስገረመኝ ነው። ካሳሁን በሁኔታው መደሰቱን እያመሰገነኝ ነግሮኛል።

"እሺ እማዬን ተሰናብቻት ልውጣ!” ብሎኝ አልፎኝ ወደ ውስጥ ገባ። እማዬ ዛሬ ጠዋት እንዲህ ብላኝ ነበር።

"ሚሚሾ ወጣትነትሽን ለእኔ ብለሽ ገብረሻል። ለራስሽ መኖር ያለብሽ ጊዜ የደረሰ ይመስለኛል። ፍትህ መልካም ሰው ነው። ይወድሻል። አትግፊው።”

"በምን አወቅሽ?” ስላት ሳቀችብኝ። …… ፍትህን እንደወደደችው አውቃለሁ። ከእርሱም ጋር ሆነ ከካሳሁን ጋር ስትጫወት ያለስስት ነው። እነሱ አጠገቧ ሲኖሩ ደስተኛ ናት።…… ካሳሁን ሲኖር ፍትህን ያበሽቀዋል። እኔና እማዬ እንስቅበታለን። እሱ ሳይኖር እማዬና ፍትህ በእኔ ሙድ እየያዙ ይስቃሉ። …… ሆስፒታል ያለን አይመስልም… …… ወደሞት እየተንደረደረች ያለች እማዬን የከበብን አንመስልም። አዲስ ህፃን ወደቤተሰቡ የቀላቀለች እናት ከበን የምንደሰት ነው የምንመስለው። አባቴም በየቀኑ መምጣቱን አላቆመም። እሱ ሲመጣ እኔ እወጣለሁ። ላናግረው እንደማልፈልግ እርሱም ያውቃል። አይሞክርም። ከእኔ ይልቅ ከፍትህ ጋር ያወራሉ። እንዲህ እየሆነ እማዬ ሆስፒታል ከገባች አንድ ወር አልፏታል።

" ፍቅር ብርሃን ነው ሚሚሾ አይደበቅም። በምንም ልትከልዪው ብትሞክሪ የብርሃን ፍንጣቂዎቹ ቀዳዳ እየፈለጉ ያበራሉ። እንደሚወድሽ ትጠራጠሪያለሽ?” አለችኝ።

"አላውቅም እማ! ገና አጭር ጊዜ ነው ካወቅኩት እንኳን። አላውቀውም!” ከማለት ውጪ ግራ ስለሚያጋባኝ ድርጊቱ ለሷ ማውራት አልችልም። አንዴ በፍቅር አክናፍ አፈናጦኝ አርያም የደረስኩ እንዲሰማኝ ያደርገኝና መልሶ ለቀናት በመሃከላችን ከጓደኝነት የዘለለ ነገር እንደሌለ ያስመስላል። ባለፈው ለት አቅፎኝ አድሮ ጠዋት ስነቃ አጠገቤ ካለመኖሩ በላይ ሳገኘው ማታ እቅፉ ውስጥ እንዳልነበርኩ ያስመስላል። አላውቅም! እንዴትስ ማወቅ እችላለሁ? አዝኖልኝ ይሆን ወዶኝ ራሱ ካልነገረኝ በምን አውቃለሁ?

"ሚሚሾዬ የምትፈልጊውን ነገር ለማግኘት ምቹ ጊዜ እስኪመጣ ወይም ጊዜው የምትፈልጊውን ይዞ እስኪመጣ ቁጭ ብለሽ ለመጠበቅ ህይወት በጣም አጭር ናት። በእጅሽ ያለውን ጊዜ ምቹ አድርጊው።” አለችኝ የተዘጋጀ ምግብ እንደመጉረስ ቀላል ነገር የተናገረች ይመስል ልዝብ ብላ።

በቆምኩበት ሀሳብ ሳመነዥክ ፍትህ ተመልሶ መጣ።
“ባለፈው እማዬ ራሷን የጎዳች ቀን ስናወራ የእህቴን ሰርግ ላለመሄድ እና ለአባቴ ጥብቅና ላለመቆም በምላሹ አንድ ነገር እንዳደርግልህ ጠይቀኸኝ ነበር። ታስታውሳለህ? ምን ነበር?” አልኩት ለመሄድ እየተጣደፈ ስለነበረ ላቆየው ፈልግያለሁ።

"እኔ እንጃ! ብዬሽ ነበር? ትዝ አይለኝም።” አለኝ ጥድፈቱን ሳያቆም ትከሻዬን ጨበጥ አድርጎኝ በቆምኩበት ትቶኝ ሄደ። ከፋኝ። የሚናገረውንና የሚያደርገውን ነገር በፍቅር የምተረጉመው ብቻዬን እንደሆነ ተሰማኝ።ለእርሱ ከቀን ተቀን የተለመደ ድርጊትና ንግግር በላይ ዋጋ ያለው ነገር አልነበረም ማለት ነው። እግሬን እየጎተትኩ እማዬጋ ተመለስኩ። እማዬ እየደጋገመች ምን እንደሆንኩ ትጠይቀኛለች። እየደጋገምኩ የሆንኩት ያለመኖሩን እመልስላታለሁ። ሲመሻሽ ካሳሁን ቢመጣም እንደሌላው ቀን መደሰት አልቻልኩም። አንድ የሰውነቴ አካል የከዳኝ መሰለኝ። በሩ በተከፈተ ቁጥር እሱ እየመሰለኝ አፈጣለሁ። አባቴ ሊያድር ስለመጣ እኔና ካሳሁን ወደየቤታችን ሄድን። ጭራሽ ያለወትሮው ስልክም ሳይደውልልኝ አደረ። በሚቀጥለው ቀን ምሽት ሆስፒታል እማዬጋ ቁጭ ብዬ ደውሎልኝ
ሊያገኘኝ እንደሚፈልግ ነገረኝ።

"ታዲዎስ ተገድሏል!” አለኝ የተቀጣጠርንበት ካፌ ደርሼ ገና ሳልቀመጥ። ያለኝ ገብቶኝ ሳያልቅ ቀጠለ "ያልታወቁ ሰዎች በጩቤ ወግተውት መንገድ ላይ ወድቆ ነው የተገኘው።” ተስፋ የቆረጠ፣ የተናደደ፣ ያዘነ… … ብዙ ዓይነት ስሜት ነው የሚፈራረቅበት። "…… ጓደኛው ነው ደውሎ የነገረኝ። ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ? ‘በሰላም ይኖር የነበረውን ልጅ አስገደልከው። አንተ ነህ ያስገደልከው።’ አለኝ።” የተፈጠረው ነገር በጣም ስሜታዊ ስላደረገው ቅደም ተከተሉን ያልጠበቀ ወሬ ነው የሚያወራኝ።

የትዝታ ፍቅረኛ ታዲዎስ ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ ለቤተሰቡ መርዶ ተረድቷቸው አስክሬን እየጠበቁ ነው። ፍትህ በተደጋጋሚ ደውሎለት ስልኩ እንቢ ብሎት ነበር። የትዝታ አባት ትንፍሽ ቢል እንደሚገድለው ለፍትህ በተናገረ ማግስት ሞቶ መገኘቱ አጋጣሚ ሊሆን አይችልም። ግን ማስረጃ የለም። አጋጣሚ ግጥምጥሞሽም ሊሆን ይችላል። የሟች ጓደኛ ሞቱ ከፍትህ ጋር ከማውራቱ ጋር የተያያዘ መሆኑን በምን እርግጠኛ ሊሆን ቻለ?

"ትዝታ አንቺን ማግኘት ትፈልጋለች።” አለኝ በጎርናና ድምፅ "ምናልባት የምትነግርሽ ነገር ሳይኖር አይቀርም። የታዲዎስን አሟሟት ስነግራት ኩርምት ብላ ነበር የተንሰቀሰቀችው። እሷም ‘አስገደልከው’ አለችኝ። ማን? ለምን? ለሚለው ጥያቄዬ ግን መልሷ ዝምታ ነበር።” ሀዘናቸው ተጋብቶበታል። እሱም አስክሬን የሚጠብቅ ለቀስተኛ መስሏል።

"እሺ! አንተ ተረጋጋ እና ወዴት እንደሚወስደን እናስብ።”

"አይታይሽም? ወዴትም መሄጃ የለም።”

"ገና ከአሁኑ ተስፋ ቆርጫለሁ እንዳትለኝ? ገና ሳትጀምረው ይሄ ጉዳይ የተወሳሰበ ሊሆን እንደሚችል ነግሬህ ነበር። ገና ከመጀመርህ እጅ መስጠትህ ነው?” ስለው በቃል አልመለሰልኝም። ሁኔታው ግን የመሸነፍ ነው። ላፅናናው አልሞከርኩም። ምን እያሰበ እንደሆነ አላውቅም። እኔም በሀሳብ ተጠምጃለሁ። …… ሆስፒታል ማደር የእርሱ ተራ ነበረ።

"ወደቤት ሄደህ እረፍ! እማዬጋ እኔ እሆናለሁ።" አልኩት። ሄደ። እስከ ሶስት ቀን አልተመለሰም። ስልኩም ዝግ ነበር።

"ምን ሆኖ ነው? አስቀየምሽው እንዴ? ንገሪኝ ምን ተፈጥሮ ነው?” እማዬ ሶስት ቀን ስላላያት በጥያቄ ልትደፋኝ ነው። በስራ ምክንያት መሆኑን ብነግራትም አላመነችኝም። ካሳሁን ሲመጣም ተመሳሳይ መልስ ቢሰጣትም አላመነችም። አባቴ እንኳን ‘ምነው ጠፋ?’ ብሎ ጠየቀኝ።

ትዝታን ላገኛት ቀጠሮ አስይዤ አገኘኋት። አልቅሳ የሷን ጉዳይ እንድንተወው ለመነችኝ።

"ነገር መቆፈራችሁን ካልተዋችሁ ሌላ ተጨማሪ ሰው ይጎዳል።” አለችኝ ቃል በቃል።

"ተጨማሪ ማለት ከታዲዎስ ሌላ ማለትሽ ነው? ማነው የሚጎዳው? ልጅሽ? አጎትሽ? ሌላ ማን?” ከዚህ በኋላ ለጠየቅኳት ብዙ ጥያቄ መልስ አልሰጠችኝም።

"የልጅሽ አባት በሰው ነው የተገደለው። በእርግጠኝነት የምታውቂው ነገር አለ። መናገር ግን አትፈልጊም። ማንን ነው እየተከላከልሽ ያለሽው? ለልጅሽ ስታድግ ምን ምላሽ ይኖርሻል? አባቴስ ስትልሽ ምንድነው የምትያት? የአባቷን ገዳይ በነፃነት እንዲኖር የፈቀድሽበትን ምክንያት ታስረጃታለሽ? አባቷን በግፍ ላጣች ልጅ በቂ ምክንያትስ ይመስልሻል? ወይስ የአባቷን አሟሟት ትዋሻታለሽ? እስከመቼ? እውነት ቢረፍድም አንድ ቀን መውጣቷኮ አይቀርም።……… ” ምንም ቢሆን እናት ናትና ደካማ ጎኗ ልጇ ናት። ትዝታ ግን አልተሸነፈችም። ልወጣ ቦርሳዬን ሳነሳ

"የሱ ልጅ አይደለችም። አባቷ አይደለም።” አለችኝ። ከዛ በላይ ግን ልትነግረኝ አልፈለገችም።

★ ኸረ ወየው አያልቅም እንዴ? 😂

@wegoch
@wegoch
@paappii
~ ራሴው ማበዴ ነው…… #10~
(ሜሪ ፈለቀ)

«የሱ ልጅ አይደለችም። አባቷ አይደለም።” አለችኝ። ከዛ በላይ ግን ልትነግረኝ አልፈለገችም። እየወጣሁ ለፍትህ ደወልኩለት እና ተገናኘን። ከትዝታ ጋር ያወራሁትን ነገርኩት። ሞቶ የነበረው መነቃቃቱ አንሰራርቶ መላምቶቹን ይነግረኝ ጀመር።

"የልጇ አባት እሱ ያለመሆኑን የተናገረችው እውነት ከሆነ ትዝታ ከሌላ ሰው ጋር ግንኙነት ነበራት። ምናልባትም አጎቷ ልድራት ነው ካለው ሰውጋ… … አንዱ ባለስልጣን ወይም አንዱ ሀብታም ይሆናል። ምናልባት ሟች በሆነ መንገድ ከዚህ ሰው ጋር ተያያዥነት ሊኖራት ይችላል። …… ምናልባት…… በስመአብ ወ ወልድ… … እኔ ያሰብኩትን አስበሻል?”

"በትክክል!!…… እያሰብኩ ያለሁት እንደሱ ነው!” አልኩት ያሰብኩት እየዘገነንኝ::

የገዛ ሚስትህ በአደባባይ አብረሃት እየሄድክ ጡቶቿን የከለላቸውን ጨርቆች ገፋ ሳምልኝ ብትልህ ብልግና ይሆንብሃል። በሷ ድርጊት አንተ ትሸማቀቃለህ። መኝታ ቤታችሁ ውስጥ ራቁቷን ሆና ያንኑ ነገር ብትልህ ለቦታው የሚገባ ቅድስና አድርገህ ልትቆጥረው ትችላለህ። ምናልባትም ከዛ በላይ ‘ስድ’ ብትሆንልህ ያምርሃል።

በመንፈሳዊው ዓለም የመጀመሪያው ለሰው ልጆች የተሰጠ የተፃፈ ህግ አስርቱ ትዕዛዛት ናቸው። አትግደል የሚል ህግ ፅፎ ሰጥቷቸዋል። ጠላት በተነሳባቸው ጊዜ ግን አሳልፌ ሰጥቻችኋለሁና ዝመቱባቸው ብሎ እልፎች ያስገድላል።

በምድረኛው ህግም መግደል ወንጀል ነው ይልሃል። አንዳንድ ወንጀሎች ግን በዛው ህግ በሞት ያስቀጣሉ። እናም ፍትህ ነው ይልሃል። በተመሳሳይ በቀል ሀጢያት ነው ይሉሃል። የበደለህን ሰው አስጠፍንገህ ወህኒ ማስወርወር ግን በቀል ሳይሆን ፍትህ ነው ትባላለህ። ምናልባት አንተም ከዛ በላይ የምታደርገው ላይኖር ይችል ይሆናል እኮ!

አየህ በዚህኛው አለም ስትኖር ሀጢያት ወይ ፅድቅ፣ ልክ ወይ ስህተት፣ መልካም ወይም ክፉ፣ ብልግና ወይ ጨዋነት… … እነዚህ አንዱ ከሌላኛው ተቃራኒ ዋልታ የሚገኝ መቼም የማይስማሙ ሊመስል ይችላል። አይደለም! እንደውም አንዱ በአንደኛው የሚተካካበት ቦታ አለ። በመሃከላቸው የተሰመረ የሚመስልህን ቀይ መስመር ስታልፍ ከአንደኛው ክልል ወደሌላኛው አልተሻገርክም። ጊዜ፣ ቦታና ሁኔታ…… ምናልባትም ሌላ ተጨማሪ ገቢር ትርጉማቸውን ያፋልሰዋል።

በዚህ ተረክ ውስጥ ማለትም የሆነውን ለመረዳት(ለመዳኘት አላልኩም) ከነዚህ ሁለት ተቃራኒ ፅንፍ ከሚመስሉ ሀሳቦች መሃከል በሀሳባችን በምናሰምረው መሃል መስመር ላይ እንቁም! ወደየትኛውም እቅፍ ተጠግተን አንሙቅ።

እናማ ከአባቴና ከእናቴ ደብዳቤ .. ከተነገሩኝ እና ከነበርኩበት ተነስቼ የሆነው በአጭሩ ሲደበለል እንዲህ ነው…………

አንድ
የውብ ዳር አባቴን እና እናቴን ለያይታ አባቴን ያገባችው ስላፈቀረችው አልነበረም። ለበቀል እንጂ! የውብዳርና እማዬ ከልጅነት ጀምሮ ጓደኛሞች ነበሩ። የውብዳር ወንድም ያፈቀራትን እናቴን ማግባት የነፍስም የስጋም ፍፃሜያዊ ትልሙ ነበር። እና እናቴ ከአባቴ ጋር ፍቅር ስትጀምር ለምናልባቱ ያስቀመጡት የባይሆን ጭላንጭል የሌላቸው ስጋና ነፍሱ አድመው በዚህ ዓለም ዓለመኖርን መረጡ። የውብዳር ለብቸኛ ታላቅ ወንድሟ መርዝ ጠጥቶ መሞት ተጠያቂዋ ጓደኛዋ መሆኗን ብታምንም በራሷ እጅ ፍትህን ካላደረገች በቀር በየትኛውም ህግ እንደማትዳኝ ታውቃለች። (እዚህጋ የእማዬን ሚና በትክክል አላውቅም። ‘ከዳችው’ የሚለውን የየውብዳርን ቃል ወይም ‘ምንም አልነበረንም’ የሚለውን የእማዬን ቃል የትኛውን እንደማምን አላውቅም።) የሆነው ሆነና እናትና አባቴ ሲጋቡ የእናቴ ሚዜዋ የውብዳር ነበረች። በዓል ሆኖ እኛ ቤት ያልመጣችበት ቀን የለም።(እናቴ ስራ የሆነችባቸውን በዓላት የእመቤትነት ስርዓቱን የምትከውነው እሷ ነበረች።) እኔ ወይ አባዬ ታመን እማዬ ከሌለች እያደረች የምታስተዳድረን እሷ ነበረች። ልደቴ ሲከበር የሚያጓጓኝ የእርሷ ስጦታ ነበር። በቤታችን የፎቶ አልበም ውስጥ እሷ የሌለችበት ፎቶ ውስን እንደሆነው ሁሉ በኑሯችን ውስጥም እሷ የሌለችበት ገፅ ውስን ነበር።

ዘጠኝ ዓመት እስኪሆነኝ ድረስ አባትና እናቴ ሲሳሳሙ ወይ ሲላፍ ደርሼባቸው በሀፍረት ጉንጫቸው ቀልቶ አስደንግጫቸው ይሆናል እንጂ ተጣልተው ሲጨቃጨቁ ከእንቅልፌ ነቅቼ ያውም እናቴ አባቴን በጥፊ ስትለው አይቼ በመጮሄ አስደንግጫቸው አላውቅም። በሰዓቱ የፀቡ መንስኤ እማዬ የሴት ፓንት መኝታ ቤት ማግኘቷ መሆኑን ብሰማም አባዬ ከየውብዳር ጋር መማገጡን እሱ ከሰጠኝ ደብዳቤዎች ነው የተረዳሁት። (በደብዳቤው ላይ ጠጥቶ እንደነበር እና ስህተት እንደሆነ ፅፎ ይቅርታ ይለምናታል። የውብዳር ፓንቷን መኝታ ቤት ጥላ መሄዷ ያሰበችበት ተንኮል ነበረ።) ከዚህ በኋላ በብዙ ላብና እድሜ የከመሩትን ጡብ በአንድ ቀን እንደማፍረስ ሁሉ ቤታችን የፈረሰው ተምዘግዝጎ ነበር። እማዬ የበለጠ የጎዳት ከሌላ ሴት ጋር መተኛቱ አይደለም። ከምትወዳት ጓደኛዋ ጋር መተኛቱ እንጂ…… የየውዳር በቀል የገባት ሲቆይ ነው።

እዚህ ተረክ ውስጥ ማናቸውም ጥሩ አይደሉም። ማናቸውም ክፉ አይደሉም። እንደማንኛውም ሰው ባበዙት ድርጊት ይጠሩበታል። ቤታችን በየእለቱ ጭቅጭቅ ሆነ። እማዬ አባቴን ጥላ ከእኔጋ ማደር ጀመረች። በነዚህ ሁሉ ጊዜያት የይቅርታ ደብዳቤ ፅፎላታል። ብዙም ሳይቆይ የውብዳር ማርገዟ ታወቀ። እናቴ ከልጁና ከእሷ እንዲመርጥ ነገረችው። ይሄን ከሰማች በኋላ እማዬ አንድ ቀን ከስራ ውጪ ሌላ ቦታ አደረች። ከሌላ ሰው ጋር… … አባቴ አወቀ። …… የአባቴ በደል ወይስ የራሷ ፀፀት .... ትዳሯ ሊፈርስ መንደርደሩ ... አላውቅም ብቻ ብዙ ሳይቆይ በአዕምሮ መታወክ ስራዋን አጣች። እህቷ ፀበል ይዛት ትኳትን ጀመር። አባቴ መምረጥ ነበረበት። እብድ ሚስቱን ወይም በፍቅርህ ሞትኩ የምትለውን የውብዳርን፤ በደሏን በራሱ በደል አጣፍቶ ይቅር ማለት እና ከእናቴ ጋር መኖር (ይሄ ያልተወለደች ልጁን ችላ ማለትን ያካትታል።) ወይም አዲስ ህይወት መጀመር።

አየህ ክልል ብሎ ፍልስፍና እንደሌለ? ያበደች ሚስቱን ትቶ ገና ተወልዳ ያላያትን ልጁን መምረጥ ልክ አይደለም። ለፍቅሩና ለሚስቱ አድልቶ በእነርሱ በደል ምንም የማታውቀውን ልጁን ቤተሰብ መንሳትም ልክ አይሆንም። ግድ ሲሆን ግን ከሁለት ስህተት አንዱን ስህተት መምረጥ ልክ ይሆናላ!

ትልቅ የሚባል ስኬት ፣ ፍፁም የሚባል ፍቅር ፣ ግዙፍ የሚባል እምነት ፣ የማይረታ የሚባል አንድነት…… ለመውደቅ ‘ትልቅ ምክንያት’ ሊያንገዳግደው ግድ አይደለም። ብዙ ትንሽ ምክንያቶች ከስሩ መንግለው ይደፉታል።

ሁለት
ቤተሰቦቼ በራሳቸው ጡዘት ሲጦዙ ዕጣ ፈንታዬ ምን እንደሚሆን አርቀው ያላሰቡልኝ እኔ እነርሱ በበሉት የተበላሸ ምግብ እኔ ስቀዝን ኖርኩ። እነርሱ በበሉት የተበላሸ ፍሬ የእኔ ጥርስ በለዘ። እናቴ በከፊል ጤነኛ በሆነ ጭንቅላቷ በከፊል በእህቷ ጭንቅላት ከአባቴ ጋር ላለመኖር ወሰነች። አባቴ የውብዳርን አገባ። ከአባቴ እና ከእንጀራ እናቴጋ ሁለት ዓመት ኖርኩ። ያጣሁት እናቴን ብቻ አልነበረም። አባቴም በዝምታና በድባቴ የተከበበ እኔ ከማውቀው ሳቅና ፍቅር ከሞላው አባቴ የተለየ ሌላ ሰው ሆነ። አብዛኛውን ምሽት አምሽቶ ጠጥቶ ስለሚገባ አላገኘውም። የቤቱ አዛዥ ሚስቱ ናት! እሱ ደግሞ ለሚሆነው ሁሉ መልሱ ዝምታ ነው። አክስቴ ስትወስደኝ ሚስቱ ምን ያህል እንደምትከፋብኝ ስለሚያውቅ አባቴ አልተቃወመም።

እዚህጋ ስህተትም ልክም ፅድቅም ሀጢያትም… … መልካምነትም ክፋትም… … ሁሉም ቦታ የላቸውም። ምክንያቱም ለእነዚህ ሁሉ ክስተቶች አንዲት ጥሬ ዘር ያላበረከትኩ
እኔ ጎተራ ሙሉ መራራ ፍሬ ሳጭድ በየትኛው ሚዛን ተዳኝቶ ከአንዳቸው ይመደባል?

"ብትጠይኝ አልፈርድብሽም። በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ የተጎዳሽው አንቺ ነሽ።” አለኝ አባቴ ከዘመናት በኋላ ዛሬ ላይ

"ስለእውነት እንደክህደትህ ብጠላህ ደስ ይለኛል። ከቤትህ አውጥተህ እንደጣልከው ቆሻሻ ስለረሳኸኝ አስከፍልህ ነበር። እድሜ ለእናቴ በል በሷ ልብ ውስጥ ስላነገሰችው ማንነትህ ስል እንደማንኛውም በህይወቴ ትርጉም እንደሌለው ሰው ቆጥሬሃለሁ።”

"ምንም ብልሽ ላንቺ በቂ የሚሆን ምክንያት ልሰጥሽ አልችልም። ግን አልከዳሁሽም። አንድም ቀን ረስቼሽም አላውቅም። አንቺንም ሆነ እናትሽን እንዳላያችሁ አክስትሽ በህግ አስከልክላኛለች። አንቺን ከእናትሽ መንጠቁ ደግሞ
እናትሽን እንደመግደል ነበር።”

አያችሁ…… ትልቅ ምክንያት አያስፈልግም። አባት ልጁን ለመተው እንኳን ቢሆን ትንንሽ ብዙ ምክንያቶች ሀያል ጉልበት አላቸው። እናቴን በማጣቱ መጎዳቱ፣ ሌላኛዋንም ልጁን እንደእኔ የተመሳቀለ ህይወት እንዳይኖራት ለመከላከል፣ የአክስቴ ሀይለኛነት፣ የእኔ እማዬጋ ለመኖር መፈለግ፣ የእንጀራ እናቴ ክፋት……… አንዳቸው ለብቻቸው ምንም የማይሆኑ ሲደማመሩ በኔና በሱ መሀከል ያለውን ትስስር መበጠስ የቻሉ ምክንያቶች ናቸው።

አሁን ደግሞ ሚስቱን ሊፈታት ነው። ምክንያቱ ልጁ ስላገባች ከየውዳር ጋር የሚያኖር ምክንያት እንደሌለው ስለሚያስብ።

"ይቅርታ ልጄ! አሁን ይቅርታዬ ያለፍሽበትን ነገር እንደማይሽር አውቃለሁ። አስቤሽ ሁሌም እንደምታመም ግን እወቂ።”

"አሁን ዋናው ነገር የእማዬ ደስታ ነው። በቀራት ጊዜ ደስተኛ እንድትሆንልኝ እፈልጋለሁ።” አልኩት አንድ ቀን መጥቶ ይጠይቀኛል ብዬ የጠበቅኳቸው ቀናት እንዳልነበሩ፣ ከእኔና ከእናቴ የውዳርንና እህቴን በመምረጡ በእህቴ እንዳልቀናሁ፣ እነርሱን ትቶ ከእኛጋር እንዲኖር ልለምነው አስቤ እንደማላውቅ: …………

ሶስት
ፍትህ ፍርዱ ልክ እንዳልሆነ እያወቀ ትዝታ 25 ዓመት ሲፈረድባት እጅ ሰጥቶ መቀመጥን መረጠ። ምክንያቱ ደግሞ የነበረው ምርጫ ማሸነፍ ወይ መሸነፍ አልነበረም። ይሄ ቀሽም የአንደኛ ደረጃ መምህር ያዘጋጀው ዓይነት ምርጫ ቀላል በሆነለት ነበር። ሁለት የማይመረጡ ምርጫዎች ነበሩት። ትዝታን ማዳን ወይ ቤተሰቡን ማዳን!! ትዝታን መርጦ ከሚወዳቸው አንዳችንን ማጣት ለእርሱ በምንም ስሌት ልክ አይሆንም። የሚወዳቸውን መርጦ ትዝታን መክዳትም በሂሳብም በሳይንስም ልክ አይሆንም። አየህ ድንበር ብሎ ፈሊጥ እንደሌለ? ግድ ሲሆን ከሁለት ስህተት አንዱን ስህተት መምረጥ ልክ የሚሆንበት አጋጣሚ ይፈጠራል። ቆይ ቆይ…… እንዲህ ቀላልና ምክንያታዊ ውሳኔ አልነበረም። ሁላችንንም ዋጋ ያስከፈ እንጂ…… ከስሩ እንጀምር.........

እንደውም ትዝታን ማዳን የሚለው ምርጫ አይደለም። ትዝታ መዳን አትፈልግም። ደፍሯታል ወይም አታሏታል…… ልጅን ያህል ነገር ወልዳለች። ለምን ለዚህ ሰው ትከላከልለታለች? የልጇ አባት አጎቷ መሆኑን ፍትህ ሲጠይቃት ድንጋጤዋ እውነቱን ቢያሳብቅባትም ካደች።

"በቅቶኛል። ራሁ ይህቺ ልጅ ምንም መስዋዕትነት የሚገባት አይደለችም።” አለኝ ፍትህ።

"ፍትህ ለእርሷ ብለህ ነው ወይስ ለሙያህ? ለእውነት? ለፍትህ?”

"የሆነ ሰው አርፌ ካልተቀመጥኩ አንቺን፣ ካስዬን ወይ እማዬን እንደሚያስከፍለኝ አስጠንቅቆኛል። ማስፈራሪያ ብቻ አይደለም።" አለኝ በሰጋ ልብ። እሱ ይሄን ከማለቱ ከአንድ ሰዓት በፊት የማላውቀው ሰው ሆስፒታሉ መግቢያ ጋር አስቁሞኝ ተመሳሳይ ማስጠንቀቂያ ለእኔም ሰጥቶኛል።

★ ለመጨረስ ሳንቃረብ አልቀረንም ★

@wegoch
@wegoch
@paappii
~ ራሴው ማበዴ ነው… #11 ~
(የመጨረሻ ክፍል)
(ሜሪ ፈለቀ)

[አልነገርኩትም። የማላውቀው ሰው የሆስፒታሉ መግቢያ በርጋ ጠብቆኝ የትዝታን ጉዳይ ማነፍነፍ ካላቆምኩ ከምወዳቸው ሰዎች አንዳቸውን እንደማጣ እንዳስጠነቀቀኝ አልነገርኩትም። ብዙ ነገር አልነገርኩትም። እንዲያውም ምንም አልነገርኩትም። እማዬ ከዚህ በኋላ ህክምና የሚፈይድላት ነገር ስለሌለ ወደቤቷ ወስደናት ዓይን ዓይኗን እያየሁ የምትሞትበትን ቀን መጠበቅ ትኩስ ቁስል ላይ ሚጥሚጣ እንደመበተን እየለበለበኝ እንደሆነ አልነገርኩትም። እቅፉ ውስጥ ሆኜ እዬዬ ብዬ ማልቀስ እንደምፈልግም። ከሰሞኑ አባቴን ሆስፒታል በማድረስ ሰበብ አዘውትረው ሲመጡ እህቴና ባሏን ማየት ልቤን በደም ፈንታ ቅናት እንደሚያስረጨው አልነገርኩትም። በእኔና በእርሱ መሃል ምንም ነገር እንደሌለ የሚሆነው መሆን እየከፋኝ አልቅሺ አልቅሺ እንደሚለኝ አልነገርኩትም። በዚህ ሁሉ ማጥ ውስጥ አቅፎኝ ያደረ ቀን የማግኩት ጠረኑን እርሱ አጠገቤ ሳይኖር እንኳን ካለበት ንፋሱ እያንጓለለ ለአፍንጫዬ እንደሚያቀብለው አልነገርኩትም። አጠገቤ ሆኖ ስለስራ እያወራኝ ልነካው እንደምፈልግ፣ ልስመው እንደምጎመዥ፣ እርሱ የኔ ቢሆንና በፈለግኩት ቁልምጫ ልጠራው እንደምመኝ… … አልነገርኩትም።]

"ማንናቸው?" አለኝ ዓይኔን ተከትሎ መኪና ውስጥ ያሉትን እህቴንና ባሏን እያያቸው

"እህምም…… እህቴ ናት! ባሏ ነው። አባቴን ወደቤት ሊያደርሱት እየጠበቁት ነው።” አልኩት አንገቴን ሰብሬ

"ታዲያ ምን?” አለኝ ዓይኔን እየፈለገ

"ምን?”

"ለምንድነው ስታያቸው በነበረው እይታ የምታያቸው? ምንድነው እሱ?"

"ኸረ ምንም አይደለም። በቃ ከእህቴ ጋር ስለማንነጋገር ነው።"

"አይደለም ራሁ። እያየሁሽ እኮ ነው። ቆይ ምንባደርግ ነው የተሰማሽን ልትነግሪኝ የምታምኚኝ? የበለጠ የቀረብኩሽ በመሰለኝ ቁጥር ለአካልሽ እንጂ ለልብሽ አልቀርብሽም። አብሬሽ ውዬ ባድር ቅርበቴ አይሰማሽም።…”

"ፍቅረኛዬ ነበረ። እህቴ ያገባችው ሰው…” ወቀሳውን እንዲያቆምልኝ ይሆን ለልቤ መቅረቡን እንዲያውቅልኝ አላውቅም። ነገርኩት!!

[ ዘጠነኛ ክፍል ስገባ አንድ ወንበር ላይ ከተቀመጥን ጀምሮ ብቸኛ ጓደኛዬ ዓለማየሁ እንደነበረ ግን አልነገርኩትም። የአስረኛ ክፍል ፈተና ተፈትነን ከተማሪዎች ጋር ከከተማ የወጣን ጊዜ ከንፈሬን ሲስመኝ ከርሱ ውጪ ያለውን ዓለም እንደረሳሁ አልነገርኩትም። በመከራ ከተከበበው ኑሮዬ የተረፈኝን ሰዓት ከርሱ ጋር ማሳለፌ በነገ ተስፋ እንዳልቆርጥ መፅናኛዬ ሆኖ በጥሩ ውጤት አብረን ዩንቨርስቲ እንደገባን አልነገርኩትም። ብዙ ጊዜ ‘ድብቅ ነሽ አላውቅሽም’ እያለ ቢነጫነጭም ይተወኛል ብዬ ለአፍታ አስቤ ባለማወቄ ሲተወኝ ከእማዬጋ አብሬ ማበድ ዳድቶኝ እንደነበረም አልነገርኩትም። የባሰው ደግሞ ከዓመታት በኋላ እሱ ዩንቨርስቲ አስተማሪ ሆኖ ተማሪው ከሆነችው እህቴ ጋር በአጋጣሚ ይሁን አስቦበት እስከአሁንም በማይገባኝ ሁናቴ ግንኙነት መጀመራቸውን ሆነ ብሎ ደውሎ የነገረኝ ማታ ራሴን ልስት እንደነበረ አልነገርኩትም። እህቴ ከዩንቨርስቲ በተባረረች በወራት ውስጥ የሰርጋቸው ጥሪ ካርድ ሲደርሰኝ ራሴን ባለመፈለግ ስሜት ውስጥ አዝቅጬው መብሰክሰኬን አልነገርኩትም። ከዓለማየሁ በፊትም በኋላም ሌላ ፍቅር እንደማላውቅም አልነገርኩትም።]

"እና አሁንም ድረስ ትወጂዋለሽ? እየቀናሽ ነው?” አለኝ

"አይይይ ለሱ ምንም ስሜት የለኝም። በሱ አልቀናም።”

"በሷ?" እያለኝ በጣም ተጠጋኝ። ትንፋሹ ጉንጮቼ ላይ እያቃጠለኝ አስቤ የተሰደሩ ቃላት መናገር አልችልም ነበር። በጭንቅላቴ ንቅናቄ ‘አዎን’ አልኩት። አልበቃውም እንድቀጥልለት ይጠብቃል። ምራቄ እያነቀኝ ነው።

"አባቴ ከእኔ እሷን ነበር የመረጠው። ፍቅረኛዬም… …” አላስጨረሰኝም ከንፈሬን በከንፈሩ ከደነው። መሳሙ ቀለምም ነበረው፣ ሽታም ነበረው፣ ጣዕምም ነበረው……

"በሚፈጠሩ ክስተቶች ውስጥ ራስሽን እየከተትሽ አትስፈሪ። ሁኔታዎች ሁሉ አንቺን ሚዛን ላይ አስቀምጠው አይለኩም።” አለኝ ለምን ያህል ደቂቃ እንደሆነ ስሞኝ ሲያበቃ… … ሰምቼዋለሁ? ገብቶኛልስ? መሳሙን እያጣጣምኩ ነበር።

"ተያቸው! እርሻቸው!” አለኝ ወደእነእህቴ እያየ። እያየኋቸው ነበር። የልጅ ስሜት ቢመስልም አዎን ሲስመኝ ማየታቸውን ለማረጋገጥ ነበር የማያቸው። አለ አይደለ እኔም ሰው አለኝ አይነት! አልጎዳችሁኝም አይነት! እንዳዩኝ በማወቄም በከፊል የታባታችሁ አይነት ስሜት……

በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ብዙ ነገር ተቀየረ። እንደውም ሁሉም ነገር!! እማዬ ወደቤት መጣች። ካስዬና አባቴ እቤታችን እየመጡ እናቴን መጠየቅ ጀመሩ። እኔና ፍትህ ቤተሰቦቻችን እስኪያውቁ እንደፍቅረኛሞች ገብተን መውጣት ጀመርን። ፍትህ የትዝታን ጉዳይ ተለዋጭ ቀጠሮ ሊጠይቅ በተዘጋጀበት ወቅት እጅ ያሰጠው ሁናቴ ተፈጠረ። ሁላችንንም ሁሉንም የሚቀይር ነገር ተፈጠረ:: አባቴ ሞቶ ተገኘ።
.
.
.
አዎ አባቴ ....


ቆይ ቆይ ፍትህ በትዝታ ጉዳይ ተስፋ መቁረጡ እና 25 ዓመት ሲፈረድባት መዋጡ ቀላል አልነበረም። ቤተሰቡን በሙሉ ያስከፈለ መስዋዕትነት እንጂ… …… ካልንበት እንቀጥል። አባቴ ተገደለ! ይቅርታ እንዳደርግለት ሲለማመጠኝ የነበረው አባቴ አንድስ እንኳን በጎ ቃል ሳልነግረው ሞተ። አልጠላህም ሳልለው.... አንድ ቀን በወጉ ሰላም ሳልለው...... በሱ ምትክ ከካስዬ ጋር እንደልጅ እና አባት ስንሆን ሲቀና ሰንብቶ ..,,,,በራሴው ጉዳይ እርሱ አንዲት ጠጠር ባላበረከተበት የነገር ካብ ህይወቱን አጣ!! ለፍትህ ይሄ የመጀመሪያው መሆኑ እና ካላረፈ ሌሎቻችንም ተራ ጠባቂዎች መሆናችን እና ቀጣይዋ እኔ መሆኔ ማስጠንቀቂያ ደረሰው። ይሄኔ ነው እጅ የሰጠው! ከእኔ በላይ ሁሉ የተጎዳ መሰለኝ።

"በፍፁም አንቺን ለምርጫ ማቅረብ አልችልም። አንቺን ማጣት አልችልም።” ይለኛል እየደጋገመ። ለማን እንዳለቀሰ ያልገባኝን ለቅሶ በአባቴ ቀብር ላይ ምርር ብሎ አለቀሰ። ግራ የገባው ስሜት ውስጥ ጠለቅኩ። አንዱ አካሌ ሽባ የሆነ ነገር ይመስለኛል። ከሬሳው ጋር የቀበርኩት ነገር ያለ ይመስል የሆነ ስሜቴ ወደአባቴ መቃብር ይጎትተኛል።

የባሰው ነገር ለእናቴ የፍቅሯን ሞት ማርዳት ነበር። በየቀኑ እየመጣ ሲያያት የከረመውን ሰው በምንም ሰበብ ቀረ ልንላት አንችልም። እንደገና እንደተዋት በምንም ምክንያት ሰንገን ብንነግራት ጤነኛ አትሆንም። መሞቱንም ብታውቅ ጤነኛ አትሆንም። ቢያንስ ግን ከመከዳት ስሜት ፍቅረኛዋ እያፈቀራት መሞቱን ማወቋ ይሻላል በሚል ተስማምተን የተሻለ ሁኔታ ላይ ያለው ካስዬ ነገራት። ዝም አለች። ለሁለት ሰዓታት ዝም አለች። እኔን የምታይበትን መንገድ አልወደድኩትም። ያንቺ ጦስ ነው ፍቅሬን ያሳጣኝ አይነት መልዕክት አለው። ድንገት ከየት ባመጣችው ጉልበት እንደሆነ እንጃ ተስፈንጥራ ተነስታ ቀብሩን እሄዳለሁ ብላ አመሰችን። ካስሽ ይዟት ሄደ። ካስሽ ደግፏት ፍቅሯ አፈር ሲገባ አነባች። አለቃቀሷ ግጥምም ቃልም ሳይኖረው ዜማ አለው። እያየኋት ለአባቴ ይሁን ለእርሷ ብቻ አነባሁ! ስለእውነት የውብዳር እንኳን ስታለቅስ አሳዘነችኝ። በየመሃሉ ለሞቱ ተጠያቂ መሆኔን ልትነግረኝ አንዳንድ ሀረግ ትመዛለች። እህቴ አፈሩ ላይ ተልሞሰሞሰች። ትንፋሽ አጥሮኝ ደረቴ ላይ ሲያፍነኝ ነው ቀብሩ ያበቃው እና ወደቤታችን የተመለስነው።

እቤት ከመግባታችን እማዬ "ይሄ የበረራ ቁጥር… …” ማለት ጀመረች። መሬቷ ያንሳፈፈችኝ አይነት ስሜት ተሰማኝ። ግራቪቲ የከዳኝ! ያልበላሁት ምግብ ወደ ላይ ወደላይ አለኝ። እሪሪሪ ብዬ ማልቀስ እፈልጋለሁ። ግን ጉሮሮዬም
2024/09/24 12:24:31
Back to Top
HTML Embed Code: