Telegram Web Link
ደረቴም የታፈነ ይመስለኛል።


"እኔ አለሁ አንቺ እረፊ!” አለኝ ካስዬ። እንዳለውም ከዚያን ቀን በኋላ ኖረ። ምክንያቱም በሚቀጥሉት ቀናት እናቴ ማነሽ? ማለት ጀመረች። ፍትህንም ስታይ መበርገግ ጀመረች። የሚገርመው ካስዬን በባሏ ስም አንድዬ እያለች መጥራት ጀመረች። ከእርሱ ውጪ ማንንም አታስጠጋም። (ሀኪሟ እሷ እንኳን ሳታውቀው ለካስዬ የሆነ የተለየ ስሜት እንደነበራት እና ሲያማት ከፍቅሯ ጋር እንደተማታባት ሳይኮሎጂ ጠቅሶ መላ ምት መታ።) ፍትህ በኔ ልመናና ጭቅጨቃ ይግባኝ በመጠየቁ ስጋቱ ሊያሳብደው ደርሶ ራቅ ያለ ቦታ አዲስ ቤት ተከራይተን አብረን መኖር ጀመርን።

" 20 ዓመት ሙሉ ያላየሁት አባቴ ለወራት ካጠገቤ ነበረ። ይቅር በይኝ እያለኝ ፣ እንደምጠላው እያሰበ… አልጠላህም ሳልለው፣ ስናፍቅህ ነው የኖርኩት ሳልለው፣ ይቅር ብዬሃለሁ ሳልለው ነው የገደሉት……” እንባዬን ማስቆም ተስኖኝ በመሃከላችን ባለው ርቀት እንዲሰማት ጮክ እያልኩ ለትዝታ ነው የምነግራት። አትመልስልኝም። የአባቴ መሞትም የእኔ እንባም ስሜት የሰጣት አትመስልም።

"እናቴ ልትሞትብኝ ነው። በሰዎችሽ ጦስ አዕምሮዋ ተቃውሶ እኔን ልጇን እንኳን አታውቀኝም። ያ ምን ማለት እንደሆነ ታውቂያለሽ? ማን እንደሆንኩ ሳታውቅ ሳትሰናበተኝ እማዬ ትሞትብኛለች ማለት ነው።” ብዙ የሀሳብ ድሮች ያደሩበት በሚመስል ጠባብ እይታ ታየኛለች እንጂ አትመልስልኝም።

"ፍቅረኛሽን አስገድለውታል። አንቺንም ለማይሆን ህይወት ዳርገውሻል። ሀያ አምስት ዓመት ወህኒ እንድትበሰብሺ አጨብጭበው ሸኝተውሻል።ልጅሽም ነገ እጣዋ ምን እንደሆነ አይታወቅም። እና አሁንም ለእነርሱ ትከራከሪያለሽ! ምንድነው ችግርሽ? አሁን ካለሽበት የባሰ ምን እንዳይመጣ ነው?…… ” ለፍልፌ ሳበቃ

"እወደዋለሁ።” አለችኝ

"ማንን?” የማስበው እውነት ባይሆንና ብንንን ብሎ ቢጠፋ እየተመኘሁ

"ሰለሞንን!”(አጎቷ ነው) ደነዘዝኩ። ከሁለት አንዳችን ጤነኛ ባንሆን ነው። ለተከታዮቹ ደቂቃዎች እሷ ተናጋሪ እኔ በድን ሰሚ ሆንን። ትቻት ስወጣም በድኔን እየጎተትኩ ነበር። ጭንቅላቴ ውስጥ የሀሳብ መዘውር ያለ ይመስለኛል። አንዱ ሀሳብ ሌላውን እያስከተለ በመዘውሩ የሚፈጭ…… ርርርርር የሚል የሞተር ድምፅ ያለው መዘውር።

ሰውየው አስገድዷት አይደለም። ገና ከ12 አመቷ ጀምሮ እያባበለ ያስለመዳት የስድ ጨዋታ ነው። ለምዳዋለች። ልምዱን አልጠላችውም። እንደውም ስታወራኝ እንኳን ከሚወዱት ፍቅረኛ ጋር እንዳሳለፉት ጣፋጭ ጊዜ የፊቷ ፀዳል እየበራ ነው። በመጀመሪያ ፊልሞች ያሳያታል። እያንገላቱ፣ እያሰቃዩና እየገረፉ የሚረኩ ወንዶች ፊልም… … በስቃዩ ውስጥ የተሳመች ያህል በማቃሰት የምታብድ… … እንዲያሰቃያት የምትለምን ሴት ያለችበት ፊልም… … ቀስ በቀስ አለማመዳት። ጤነኛ ሰው ሊወደው የማይችለውን sex torture እንደ ሱስ ለመደችው። ደስ ብሏትና ፈልጋ የምታደርገው ቅውሰት ሆነ። አጎትየውን ከሴት ጋር ስላገኘችው በእልህ ታዲዎስን ፍቅረኛዋ አደረገችው። ሰላማዊው ታዲዎስ አጎቷ የሚነዳትን የእብደት ቁልቁለት ሊያንቆለቁላት አይችልምና ሱስ እንዳባዘተው ወመኔ በሱስ ጥም አዛጋች። ከሁለቱም ጋር ሆነች። በዚህ መሃል የአጎቷን ልጅ አረገዘች። ታዲዎስ የእኔ ልጅ ነው ብሎ ቁምስቅሏን ሲያሳያት ነው እውነቱን የነገረችውና የዘመኑ ቁጥር በአጎቷ በጎ ፈቃደኝነት እንዲወሰን የፈረደችበት። ከዛ የቫንፓየር ወይ የማርስ ፍጡሮች ተረት እንጂ ሰውነት የማይመስል አኗኗር ሰውየው ከወንድሙ ልጅጋር እንደባልና ሚስት ኖሩ።… … የዛን ዕለት ምሽት ሴት ይዞ እቤት መጣ! በቅናት የነደደ አካሏ ያዘዛትን አደረገች። ምንም የማታውቅ ንፁህ ነፍስ ጠፋች።

"ልጄ ከአጎቴ እንደወለድኳት እንድታውቅ አልፈልግም። ሶልም ይሄ ነገሩ ቢታወቅ ስሙ ይጠፋል፣ ይታሰራል። የወንድሙም ስም አብሮ ይነሳል(ባለስልጣን ወንድሙን ማለቷ ነው።) ሶልን እወደዋለሁ። መጥፎ ነገር እንዲደርስበት አልፈልግም።” አለችኝ የሆነ ልክ የሆነ ነገር እንደነገረችኝ ሁሉ ሀፍረት ሳይሰማት። ዘገነነችኝ። በእርግጥ አሳዘነችኝም። የሆነ አይነት በሽታ እንደሚሆን አሰብኩ። የገዛ ሰውነቴ እየሸከከኝ ወጣሁ። ጭንቅላቴ ውስጥ ያለው መዘውር አልቆመም።

የኑሯችን መዘውር የሚዞረው በሚገጥሙን ክስተቶች ግብዓትነት አይደለም እያልኩ አስባለሁ። ይልቅስ በገጠሙን ክስተቶች ላይ በወሰንነው ውሳኔና በዘረጋነው እርምጃ እንጂ…… ኑሯችን የውሳኔያችን ውጤት እንጂ ያጋጠሙን መከራና ፍሰሃ ውጤት አይደለም። ……

“ literally she is sick, serious ህክምና ያስፈልጋታል።” አለኝ ፍትህ ነገሩን ስነግረው እየሰቀጠጠው።

"ከአሁን በኋላ የትዝታ ኬዝ አይደለም። አባቷን በስድ ግፈኞች የተቀማች ልጅ ኬዝ ነው። የራሴ ጉዳይ ነው።" አልኩኝ ከመናገሬ በፊት ያሰብኩት ያልመሰለኝን ንግግር! …………

አሁን አልጨረስንም ብትሉም ጨርሰናል::

@wegoch
@wegoch
@paappiii
{{{ ቡና እና እሷ }}}
*****
(ተፃፈ ለቡና ደጋፊዎች ማለቴ ተጠቃሚዎች😜)

ቡና አልወድም . . .!!
ጥቁረቱን ሳይ ከሰይጣን ደም የተቀዳ ይመስለኝ ነበር - ቡና!!
ጥቁር ደም!! ጥቁረቱ ከጨለማ የገዘፈ፡፡ እራሱ ሰይጣንን የመሰለ፡፡ እንደውም ቡና መቆላት ሲጀምር ሰይጣን በጠረኑ ተስቦ የሚመጣ ይመስለኛል፡፡ ልክ ሲወገጥ፣ ስራውን በማን ልቦና ላይ ሰፍሮ፣ በማን ልሳን አንበልብሎ፣ ማንን መውገጥ እንዳለበት የሚያስብ ይመስለኛል፡፡ እሳት ላይ ተጥዶ እስኪፈላ የስራውን እቅድ የሚነድፍ፤ ፈልቶ እስኪሰክን ሲዘቀዘቅ ደግሞ በየሰው ምላስ ለመወንጨፍ በተጠንቀቅ የተንበረከከ አትሌት ይመስለኛል፡፡
የመሰለኝ ሁሉ መስሎኝ አልቀረም፡፡ እናቴ ቡናዋን ቀድታ ለአጣጪዎቿ ካከፋፈለችና እነሱም ከተጎነጩ በኋላ፤ ሰይጣን ደሙን በደማቸው አስርጾ ማሳማት ይጀምራል፡፡
‹ውይ የእንትና ልጅ እኮ ሳታረግዝ አልቀረችም፡፡ ደግሞ ምናለ ከደህና ሰው ቢሆን…›
‹ኤዲያ! እሱ ሰው መስሎሻል፤ ሚስትና ልጁን ቤት ቁጭ አድርጎ ሲልከሰከስ አይደል እንዴ የሚያመሽ፡፡›
‹‹እኔኮ ግርም የሚለኝ…›
‹እሷን ሰው ብለሻት…›
‹ድንቄም አዋቂ!! በፎርጅድ ነው አሉኮ ባለ ድግሪ የሆነው…›
‹ማን እሷ!...›

ቡና አልወድም!...... ነበር፤ ማርታን እስካገኝ፡፡
ማርታን ባወቅኩ ቅፅበት እውነቴና እውቀቴ ተገለባበጠብኝ፡፡ ቡና የሰይጣን ሳይሆን የፈጣሪ መሆኑ ተገለጠልኝ፡፡ እንደውም ለአዳም፣ ጥረህ ግረህ ብላ ተብሎ የተነገረው ቃል፤ በደንብ ተግባራዊ ሚሆነው በቡና ላይ ነው፡፡ ቡና ተቆርጦ፣ ተፈልፍሎ፣ ተለቅሞ፣ ታጥቦ፣ ተቆልቶ፣ ተወግጦ፣ ተፈልቶ፣ ተቀድቶ . . . ይህን ሁሉ የስራ ሂደት አልፎ ነው ለመጠጥነት የሚበቃው፡፡
‹‹ምነው ሞቅ ሞቅ ሳላደርገው፣ በቅጡ እንኳ ሳልጀምር መጣህሳ?›› ትላለች ማርታ፤ የቡና ሲኒዎቿን እየደረደረች፣ ከሰሏን እያያዘች፣ ያን ድንቅ ፈገግታዋን በፊቷ እያፈገገች፡፡ ፊቷን ሳይ የከሰሉ መፍገግና የሲነዎች ንጻት ከጥርሷና ከፈገግታዋ እጅግ በጣም ያንስብኛል፡፡
የቡና ሱስ እያንከለከለ በጠዋት የሚያመጣኝ ይመስላታል፡፡ ከቡናዋ በላይ ከፊቷ የሚፈሰውን ፈገግታ ጠጥቼ ነበር ቀኔን ብሩህ የማደርገው፡፡ ቡናዋን፣ ገበያዋን ለመክፈትና እሷን ለማግኘት ስል ነበር መጠቀም የጀመርኩ፡፡ እየቆየሁ ስሄድ ግን የቡና ሱስ አናቴን ተቆጣጠረው፡፡ በማርታ ፈገግታ ብቻ ቀኔ አልፈካ ሲለኝ፤ ‹‹ማርቲዬ እስቲ የተለመደችውን ጣፋጭ ቡናሽን ቅጅልኝ!›› ማለት ጀመርኩ፤ ገና ወንበር ላይ ቂጤን ሳላሳርፍ፡፡

አንድ ቀን ጠዋት እንደተለመደው የማርታን ፈገግታ በቡና የማጣጣም ሱሴን ለማስታገስ ብቅ አልኩ፡፡ ማርታ ግን አልነበረችም፡፡ ቡናዋም የቡና እቃዎቿም አልነበሩም፡፡ ማርታን ጥበቃ ቆሜ ባለሁበት፣ ፀሀይ በምስራቅ በኩል ብቅ ብላ ቀኑን ሙሉ እያረፈች ተጉዛ በምዕራብ በኩል ሰመጠች፡፡ እኔ አይኔን በተለያየ አቅጣጫ እየወረወርኩ፣ አፌን ሱሱ ባዛጋኝ ቁጥር ከፍቼ እየደረገምኩ ጠበቅኳት፡፡ ብቅ ግን አላለችም፡፡ በማግስቱም በጠዋት መጣሁ፤ የለችም፡፡ በማግስቱ ማግስትም መጣሁ፣ በማግስቱ ማግስት ማግስትም መጣሁ፣ ከዛ በኋላም ለተከታታይ ሶስት ቀን መጣሁ፤ ማርታ ግን የውኃ ሽታ ሁናለች፡፡ እኔን የቡናና የፈገግታ ሱሰኛ አድርጋኝ ጠፍታለች፡፡
ማርታንና ቡናዋን ፍለጋ ተንከራተትኩ፡፡ ማርታን ሳጣ ቡና ለመጠጣት አንዲት ቡና አፍይ ዘንድ ቀርቤ አዘዝኩ፡፡ ቡናው ከጉሮሮዬ አልወርድ አለኝ፡፡ ጣዕሙ ለጉሮሮዬ ሰቀጠጠኝ፡፡ ትቼው ወጣሁ፡፡ "ለካ እስከዛሬ ቡናን ለጉሮሮዬ ያጣፈጠው የማርታ ፈገግታ ነው" ስል አሰብኩ፡፡ እውነቴም፣ እውቀቴም አፈነገጠ፡፡
‹‹ቡና የሰይጣንም የፈጣሪም ሳይሆን የማርታ ነው፡፡ የማርታ!!›› እያልኩ፤ ለቡና ተጠቃሚዎች እየሰበኩ፤ ማርታንና ቡናዋን ፍለጋ ዛሬም እንከራተታለሁ፡፡

እውነቴን ነው!! የማርታን ቡና በፈገግታዋ አጣጥመው ሳይጠጡ፤ ቡና ጠጣሁ ብለው አያውሩ፡፡

ዳንኤል ከበደ (#ኤልዳን_ለእኔ)

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ዛሬ ስንሻውን አገኘሁት !🙂
_________________________

መጀመርያ ላይ የመኪናውን ክላክስ ሰምቼ ስዞር የማላውቀው ሰው ሊጠራኝ አይችልም በሚል እምነት ብቻ ጉዞዬን ልቀጥል ነበር ! ሚኪ ብሎ ጠራኝ ! ጌታ ሆይ ይሄን መሳይ የኮራ የደራ መኪና እያሽከረከረ ያለው እኔ በልጅነቴ የማውቀው ፣ ያ ትምህርት እሱን ከሚገባው ሶስት ግመሎች ተቃቅፈው በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልኩ ይቀላል የሚባልበት ስንሻው እንዳይሆን ብቻ !
ዞር አልሁኝ !
ራሱ ስንሻው ነው ። ፊቱ እንደ ዓለም ካርታ ሉል መስሎ ተድቦልቡሏል ፣ ከላይ ያደረገው ነጭ ሸሚዙን የሚያምር ቅርፅ ያለው ሰውነቱ ይበልጥ ውበት እና ፍካት ሰቶታል ። በግራ እጁ ላይ ያደረገው ሰዓት ለግሉ ብቻ የሚገለገልበት ሳይሆን ለዓለም ህዝቦች ሁሉ ጊዜ የሚያውጅበት ይመስላል ።
አይኔን ብጠራጠርም ቀረብሁት ። ፈገግ ሲል በፍንጭቱ ይበልጥ እርግጠኛነቴ ጨመረ ። ልጅ ሆኖ ተደባዳቢ ነበር ።
እሱ የመቀጣቀጥ ሙዱ ከመጣ ለምን መሬቱን በሀይል እየረገጥህ ትሄዳለህ በሚል ተልካሻ ምክንያት ሁሉ ሳይቀር ለፀብ ይጋበዛል ።
እሱን የማይፈራ የክፍላችን ተማሪ አልነበረም ። ከእሱ የባሰ ረባሽ ተማሪም ክፍላችን ውስጥ አልነበረም ፣ ከእሱ የሚብስ ፎርፌ የሚቀጣ ተማሪ ጮርናቄ ለመብላት በክፍል መስኮቶች የሚዘል አንዳችስ እንኳ አልነበረም ።
እንደውም ትዝ የሚለኝ ቲቸር ንጉስ የሚባሉ መምህራችን አንተ በዚህ ከቀጠልህ” እነ ሚኪ ተምረው ዶክተር አልያም ኢንጅነር ሲሆኑ አንተ ሻንጣ ተቀባይ ወዛደር ትሆናለህ“ ብለው አሟርተውበት ነበር ።
እሱ ግን ይኸው በማላውቀው ምክንያት ዛሬ ከኔ የተሻለ ወዝና ንብረት ይዞ ክላክስ አደረገልኝ !
ይኸው የቲቸር ንጉስ ሟርት አቅጣጫውን ስቶ እኔ ላይ አረፈ !እሱን ወዛደር ብለውት ወዛም ሆኖ አረፈው ! እኔ ተምሬ እሳቸው እንዳሉት ኢንጅነር ሆንኩ ኝ (ስም ብቻ ተረፈኝ ) ስንሻው ሳይማር (ተምሮም ሊሆን ይችላል ) እሳቸው እንዳላሉት ከበርቴ ሆነ ።
'ስንሻው ?"
"ሚኩ ቸካይ ? አንተ እንዴት ነህ ? ምነው ደግሞ ሾለክህ ?" አለኝ
ለምን ከሳህ ማለቱ ነው ! ለምን ሆድህና ጀርባህ ተጣበቀ ምነው የቂጥህ ዋንጫ ወለቀ ምነው ምን ላርግልህ የሚለውን ነጠላ ዜማ እኔ ነኝ ሂዩማን ሄር አድርጌ የለቀቅሁት አልህ ? ማለቱ ነው ።
ይበለኝ !የ አርባ ቀን እድሌ ነው ።
“ደግሞ ደክሞሀል ! ላብህ ” ወደ ብብቴ አመላከተኝ ። ብብቴ አካባቢ ክረምት ገብቷል ። መንገድ እና ድንጋጤ ተባብረው ባህራቸውን ብብቴ መሀል አንጣለውት ነበር ።
ስንሻው መኪናውን ከፍቶልኝ ገባሁ ። እሱ የተቀባው ሽቶ መዓዛ ከመቅደስ እጣን ይልቃል ብል ፈጣሪ ይቀየመኛል ብዬ እንጂ እውነቱስ እንደዛ ነበር ።
መኪና ውስጥ የሽታ ማኪያቶ ተፈጠረ ! ድሮ ማኪያቶ ሲባል ለመጠጥነት ለሚውለው የቡናና ወተት ድብልቅ ይመስለኝ ነበር ።
ለካ የግም እና የጥኡም መዓዛም ማኪያቶ አለ ።
”አይ ሚኩ ትንሽ ከመጥቆርህ እና ከመክሳትህ ውጪ የድሮ መልክህ ቅልብጭ እንዳለ ነው“ አለኝ ለጥቆ !
አንተ አክሱም ተገትረህ የምትቀር ድንጋይ ሊለኝ እንደሆነ ገብቶኛል ! ባጭሩ ይሄ ሰው አንተ ኢትዮጲያ ቢለኝ እኮ ቅኔው ይገባኝ ነበር ። ከዚህ በኋላ የታሪክህን ያህል ሶስት ሺህ ዘመን ያህል ቢጨመርልህም የምትለወጥ አይመስለኝም ሊለኝ እንደሆነ እኮ ማንም ያውቀዋል ።
በኢንጅነሪንግ ነው አይደል የተመረቅኸው ? ጠየቀኝ
ምኑን ተመረቅሁት ? ተረገምኩኝ በለው ልለው ነበር ። ባይሆን በእውቀቴ ልኩራራ ብዬ እንዴታ አልኩት ወሬዬን ላሳምር ።
የት ነው የምትሰራው ?
የምሰራበትን ድርጅት ነገርሁት ።
በለበጣ ፈገግ ብሎ ኡኡይ ተቀጣሪ ነሀ ? አይዞህ በርታ ብሎ መለሰልኝ ።
አንተስ እንዴት ነህ ? ምን እየሰራህ ነው ?
ስንሻው መኪናውን እያሽከረከረ “ እኔማ እድሜ ለቲቸር ንጉስ አንድ ጊዜ የማይረሳ የንግግር ማስጠንቀቂያ ሰቶኝ ነበር ። አንተ ረስተኸው ይሆናል (አይ ጅሉ እኔማ ይሄን ጉድ እያየሁ እንዴት ረሳዋለሁ ?)
....እኔም ታድያ ያቺን ነገር በልቤ ይዤ ከዛ ትምህርት ቤት ስለቅ ወጣሪ ተማሪ ሆንኩኝ ። የውጭ እድልም አጊንቼ እዛ ው ተምሬ ትልቅ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩኝ ። አሁን በጎን ሀገሬ ላይምኢንቨስት ማድረግ ጀምሬያለሁ ። ባይሆን በሙያህ እኔ ጋር ቀጥሬህ ታግዘኛለህ“ አለኝ ።
የልቤ ምት ፍጥነት እሱ ከሚነዳው መኪና እኩል ፈጥኖ ሲረባበሽ ይታወቀኛል !
እሺም እንቢም አላልኩትም ። በልቤ የቲቸር ንጉስን ትንቢት አስቤ እየተሸማቀቅሁ ነበር ።🙂

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Michael Aschenaki
ባያፍራ የኢቡዎች ህልም
______________________
(አይሰምርም አይጨነግፍም?
በሚልየን የሚቆጠሩ ኢቡዎች ደም ፈሷል። ሽንፈትና ውርደትን ተከናንበዋል።
ዛሬም እንደተሸናፊ ጎሳዎች ዝቅ ተደርገው ይታያሉ። ሀገር አልባዎቹ ኢቡዎች በናይጄሪያ ዘላለማዊ ግዞት ተጠፍንገው ዛሬም ሳይወዱ በግዳቸው ይኖራሉ። ነገሩ እንዲህ ነው። ሀገረ ናይጄርያ የተመሰረተችው በእንግሊዝ ፍላጎት ነው። ሰሜናዊ ናይጄሪያ የሀውሳ ጎሳ፣ ደቡብ ምዕራብ ዩርቡን፣ ደቡብ ምስራቅ ደግሞ ዛሬ ከንፈር የምንመጥላቸው ኢግቡዎች በስፋት ይኖሩበታል። እነዚህ በምንም የማይቀራረቡ ጎሳዎችን ለማእድንና ነዳጅ ፍላጎቷና ለቅኝ አገዛዟ እንዲመቻት
እንግሊዝ ናይጄሪያ የሚል ሀገር መሰረተች። ሲፈርድባቸው ኢግቡዎች አዕምሯቸው ብሩህ ነው። ሲጥልባቸው ስራ ፈጣሪነትን ተክነዋል። የተፈጥሮ ነገር የነፃነት ታጋይነት በደማቸው አለና እንግሊዝ ከሀገራቸው እንድትወጣ የነፃነት ትግልን መርተዋል። ቀናነት ተፈጥሯቸው ነው በመላው ናይጄሪያ ተበትነው ሀብት ንብረት አፍርተው መኖሩ ጀመሩ። ናይጄሪያ ፀሀይ ወጣላት። ነፃነቷን ተቀዳጀች። ቅኝ ገዢዋ እንግሊዝ ናይጄሪያን ለቅቄ ወጣሁ አለች። ነገር ግን ወጥታ አልወጣችም። አዲስ በሚመሰረተው ነፃ ሀገር ላይ አሻራዋን ለማኖር እንቅስቃሴ ጀመረች። በአዲሱ ሀገረ ምስረታ ላይ ኢግቡዎች እንዳይሳተፉ ተደረጉ። የመጀመርያው የናይጄሪያ ጠቅላይሚኒስተርም
ከሰሜን ናይጄሪያ የመጣ የሀውሳ ጎሳ አባል ሆነ። ሌሎች ትልልቅ ስልጣኖችም
በሀውሳዎች ተያዘ። በዚህ ቅሬታ ያላቸው ኢግቡዎች ሁሉን ነገር ዳር ሆነው
ይታዘቡ ነበር። ዓመታት ተቆጠሩ። አዲሷ ናይጄሪያ ገና ዳዴ ከማለቷ ባለስልጣኖቿ በሙስና፣ አድሎ፣ ዝርፊያና ህገወጥ ስራዎች ላይ ተዘፈቁ። መጀመርያውንም በመንግስት ምስረታ ላይ ቅሬታ ያላቸው ኢቦዎች መፈንቅለ መንግስት አደረጉ። ወታደራዊውን መፈንቅለ መንግስት ቹኩማ ኒዙጉ እየመራ በሰሜናዊይኑ ቁጥጥር ስር የነበረውን ስልጣን ተረከበ። በሙስና የተዘፈቁ ባለስልጣኖችም የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ተገደሉ። እዚህ ጋ ቹኩማ የሰራው ስህተት አለ። ከባለስልጣኖቹ መሀከል የኢቡ
ጎሳዎችን አልነካቸውም ነበር። ይሄም መሪዎቹ የተገደሉበት የሀውሳ ጎሳ
በአከባቢው ያሉትን ኢቡዎችን ከመኖሪያ በማፈናቀልና ቀመግደል ቁጣውን
ገለፀ። ነገሮች ተባባሱ። ርእሰ ብሔሩ የኢቡ ጎሳ አባል ቢሆንም አንድ ኢቡ የሆነ ወጣት በሰላም ተኝቶ ማደር የሚናፍቀው ህልሙ ሆነ። ስጋት ከበባቸው። ሞት የእለት ተእለት ዜናቸው ሆነ። ይባስ ብሎ መሪው ቹኩማ መፈንቅለ መንግስት ተደረገበት። በሰፈረው ቁና ተሰፈረ። የኢቡዎች ሰቆቃ ተባባሰ። በመላው ሀገሪቱ ተበትነው ያሉት ኢቡዎች ወደመነሻቸው ደቡብ ምስራቅ አከባቢ ተሰበሰቡ። ቤታችን ገባን ብለው እፎይ አሉ። እንደውም እኛ ናይጄሪያ አደለንም የራሳችን ግዛት መመስረት አለብን በሚል መርህ የዛሬ ህልማቸውን ቢያፍራን መሰረቱ። የተቀረው የናይጅሪያ ክፍል የተበተነው ኢቡ ሁሉ የቢያፍራ ግዛትውስጥ ተሰበሰበ። ተይ ባይ የሌላት እንግሊዝ የቢያፍራን ነገር አልወደደችውም። ሰሜናዊያኑን ሀውሳዎች በማስተባበር ወደቢያፍራ ዘመቱ። እልቂት በኢቡዎች ላይ ሆነ። ሚልየኖች ረገፉ። ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤትና የንግድ ማእከሎች በአውሮፕላን በሚጣሉ ቦንቦች ጋዩ። ህፃናትና እናቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ። የአልም ትኩረት ተነፈጋቸው። ኢቡዎች ተሸነፉ። ነፃ ምድር ቢያፍራ ቅዠት ሆና አከተመች። ጦርነቱ አበቃ። አንድ ናይጄሪያ በድጋሚ ቀጠለች። በኢቦች ደም ናይጄሪያ ቀጠለች። የተረፉት ኢቡዎች ግን አሁንም ጥያቄ አላቸው። "እቺ ሀገር የኛ አይደለችም። ጦርነቱን ተሸንፈናል። የዘር ጭፍጨፋ ነው የተረደገብን። ሀገሪቱ የኛ አይደለችም። ዛሬ እኔ እድሜዬ ገፍቷል፣ ባያፍራ እውን ሆና ላልመለከታት እችላለሁ። የልጅ ልጆቼ ግን ህልሜን እውን ያደርጉታል። ነፃ ምድር ባያፍራ ትመሰረታለች። እኛ ናይጄሪያዊያን አይደለንም!" ይላሉ የኢቡ ጎሳ ተወካይ። ዛሬም ይሄ እንቅስቃሴ አለ። ቢያፍራን የመመስረት ትግል ህልም ወይስ ቅዠት?

@wegoch
@wegoch
@paappii

#muaz jemal
#Hike with your #talent.

Sunset Hiking Team is proudly hosting another epic hiking #Dinbaro (Menlik's Window)

(#Free #Outdoor_Photography, #Lunch, #Water, #Snack and much more).

Join us:
@sunsethiking or @sunsetphotography

Register
@chere_daregot(0919296071) by writing your name and talent!
#ገበታ ወ ባሻ !
(ሚካኤል አስጨናቂ)
አከራዬ ባሻ ሰሞኑን እጅግ የበዛ ወከባ ላይ ናቸው ። የግቢውን ብልፅግና ማረጋገጥ አለብኝ ብለው ደፋ ቀናውን ተያይዘውታል ።
እነሆ.. .የዛሬ ሳምንት ታድያ ወደ ቢሮ ለመሄድ ስጣደፍ ከየት መጡ ሳይባል ፊትለፊቴ ተገጨሩ :)
"ሚኪያሴ" አሉኝ! (እውነቱን ለመናገር ቤት አከራዮች ሲያቆላምጡኝ የቆነጠጡኝ ያህል ያመኛል )... ዝናዬ አከራይህ ዛሬ እከል ዬ ብሎ ከጠራህ ነገ የሆነ ጨላ ልትበጥስ ወይም ቤትኪራይ ሊጨመርብህ መሆኑን ልብ በል !
"አቤት ባሻ "
"ገበታ ለግቢያችን የሚል መርሀግብር በዚህ ሰሞን ተዘጋጅቷልና.. . (ንግግራቸውን ሳይጨርሱ የምድረ አዳም ሀጥያት የተከተበበት የመልዓክ መዝገብ የመሰለ የወረቀት መዓት ከጃኬታቸው ኪስ ውስጥ አውጥተው አቀበሉኝ) ...
ከዛ ሁሉ ዝብዝብ የፅሁፍ ብዛት መዋጮ የሚለውን የብሩን መጠን ሾፌ ቆሽቴ ጨሰ።.በየወሩ የምከፍለው የቤት ኪራይ ሳያንስ ገበታ ለግቢ የሚል የ 250 ብር መዋጮ ቀኔን ሰርቆኝ ዋለ ።
እነሆ ከባሻ ጋር በተገናኘን ማግስት ደግሞ ባለቤታቸው እመት ውድነሽ (ኑሮ ውድ ሆኖ ቦክስ እንጋጠም ብሎዋቸዋል መሰል ) ... እንዳኮረፈ ዝንጀሮ ለምቦጫቸውን ጥለውት አየሁ ። (እናቴ እኔን ! ማዘር ጁሱ ተመጦ የተጣለ ላስቲክ ይመስል ተኮራምተው የለ እንዴ?) ...ደግሞ እውነቱን ለመናገር ማዘር እንኲን አኩርፈው ፈገግ ብለው እንኳ አምሮባቸው አያውቅም። ፊታቸው የኬጂ ተማሪ የሚለማመድበት የስዕል ደብተር ይመስል እዚህም እዛም ተዥጎርጉሮ የኬንያ ባንዲራን ይመስላል።
"ማዘር ሰላም ነው?"
ምን ሰላም አለ ልጄ?
ምነው ... ምን ገጠሞት?
"ይሄ የሽማግሌ ህጣን ሰላሜን ነሳኝ :) ሰው እንዴት ቤቱ ውስጥ ያለውን የእህል ዘር አይጥ እየበላበት የግቢ ብረት በር ገዝቶ ያስመርቃል ? ተገቢ ነው መኮንን? ...ማነው ሚካኤል :)
..."እ ህ ህ.. ." የምመልሰው ጠፍቶኝ ተንተባተብሁ ።
" ልክ አይደለም !" ራሳቸው መልሰው ቀጠሉ ...ሶስቱ ልጆቻችን ርስበርሳቸው ጠብ ላይ ሆነው... "
"እዚህ ቤት የተጣላ ሰው አለ እንዴ?"
"እንዴታ ሚካኤል !...ያ ጥቁር ልጄ ሹሼ ከበደን እንዳይሆን አድርጎ ቀጥቅጦት የለ እንዴ? ይሄን ጠብ መፍታት ነው ወይስ ግቢው ውስጥ ችግኝ መትከል ነው የሚቀድመው ?...ቤቴ ውስጥ አይጥ እንደ አብርሀም ዘሮች በዝቶ ተባዝቶ የውጭ በር ሰራ አልሰራ ምን ይጠቅመኛል? እኔ የማወራው ስለ BBC እሱ የሚያወራው ስለ EBC! ...አልተገናኝቶም ልጄ! " የእመት ውድነሽ እንባ ኮለል ብሎ ሲወርድ አንጀቴ ተላወሰ ። በዚህን ጊዜ ባሻ ከየት መጡ ሳይባል ጀርባዬን መታ መታ አድርገው ...
"አየህ ልጄ ባለቤቴ ግቢው ሲያምርበት እኮ ደስ ብሏት ነው የምታነባው " :)
ቀና ብዬ ውድነሽን አየኋቸው።
የሽሙጥ ፈገግታ ፈገግ ብለው ራሳቸውን ከታች ወደ ላይ ሰበቁ ።
"ገና ምን አይተሽ ቤታችን እንደ አማዞን ጫካ ነብርና አንበሳ እንዲሁም ዝሆንና ጎሽ ይመላለሱበታል። "
ባሻ ይሄን የሚሉት በኩራት አካፋና ዶማቸውን ይዘው ሌላ ችግኝ ለመትከል ከስራችን እየተንቀሳቀሱ ነበር :)

@wegoch
@wegoch
@paappii
ቅቤ አምራች ገበሬና ዳቦ አምራች ነጋዴ እንደ አጋጣሚ ድግስ ላይ ተገናኝተው ያወራሉ፡፡ በጨዋታቸው በጣም ስለተግባቡ ከዚህ በኋላ አጋጣሚ ፈጥረው ለመገናኘት ይስማማሉ፡፡ ነጋዴው ጠዋት ጠዋት 300 ግራም ዳቦ ሲልክለት ገበሬው ደግሞ ማታ ማታ 300 ግራም ቅቤ ሊልክለት ተስማሙ፡፡ በዚህ መልኩ ብዙ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ነጋዴ የቅቤ መጠን እየቀነሰ መሄዱን አየ። በመጨረሻም ሚዛን ላይ ሲያስቀምጠው 150 ግራም ሆኖ አገኘው፡፡ በዚህም በጣም አዘነ፤ ተበሳጨም፡፡ ገበሬውንም አስጠራው፡፡ ሌሎች ሰዎች እንዲያዳምጡት አድርጎ ‹ከተስማማነው ውጭ የቅቤውን መጠን ለምን ቀነስከው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ገበሬውም ‹እኔ ፈጽሞ አልቀነስኩትም› ሲል በአግራሞት መለሰ፡፡ ነጋዴውም ቅቤውን በሚዛን ለክቶ አሳየው፡፡ 150 ግራም ነው፡፡ ገበሬውም አዘነ፡፡ ‹እኔ ቤት ውስጥ የ300 ግራም መለኪያ የለኝም፡፡ አንተ ጠዋት ዳቦውን ስትልክልኝ በእጅ ሚዛኑ አንደኛው ሰሐን ላይ አደርገዋለሁ፤ ከዚያም ቅቤውን በሌላኛው ሚዛን አስቀምጠዋለሁ፡፡ ልክ ከዳቦው ጋር እኩል ሲመዝኑ በዕቃ አዘጋጅቼ እልክልሃለሁ› አለው፡፡ ወዲያውም ጠዋት የላከለትን ዳቦ አውጥቶ ሚዛኑ ላይ አስቀመጠው፡፡ ዳቦው 150 ግራም ነበር የሚመዝነው፡፡ ነጋዴው አፈረ፡፡
‹የምታገኘው ለሌላው ባደረግከው ልክ ነው፡፡ 150 ሰጥተህ 300 ልታገኝ
አትችልም፤ እባብ ሰጥተህ ርግብ፣ ድንጋይ ሰጥተህ ዳቦ፣ እሬት ሰጥተህ ማር ልታገኝ አትችልም፤ አንተ ብቻ ብልጥ ልትሆን አትችልም፤ ማሾውን አጥፍተህ
ብርሃን ልታገኝ አትችልም፤ ሌላው ገድለህ አንተ በሰላም ልትኖር አትችልም›
አለው ገበሬው፡፡ ማንኛውም ድርጊት ተመሳሳይና ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ አለው፡፡ አንተ እዚህ ለብቻህ ቤትህ ውስጥ ሆነህ ክፉ ስታደርግ ሌላውም በቤቱ ብቻውን ሆኖ ክፉውን ይመልስሃል፡፡ ‹እዛም ቤት እሳት አለ› እንዳሉት ነው አለቃ ገብረ ሐና፡፡ አንተ ጎመድ ይዘህ ከወጣህ ሌላውም አያቅተውም፤ አንተ ገጀራህን ከሳልክ ሌላውም ይስላል፤ አንተ የሌላውን ወገን ስታፈናቅል፣ ያኛውም ያንተን ወገን
ያፈናቅላል፡፡ ዛፍ ቆርጠህ ዝናብ፣ በካይ ጋዝ እየለቀቅክ የተስተካከለ የአየር ንብረት አትጠብቅ፡፡ ተፈጥሮም በሰጠሃት መጠን ነው የምትመልስህ፡፡ በዓለም
ላይ ሚዛኑ አንድ ነው፤ ተመዛኞቹ ግን ይለያያሉ፡፡ እዚህ ካጎደልክ፣ እዚያም
ያጎድሉብሃል፡፡ እዚህኛው ዩኒቨርሲቲ የዚያኛው ልጅ አለ፤ እዚያኛው ዩኒቨርሲቲም የአንተ ልጅ ይገኛል፡፡ እዚህ የአንተ ወገን ብዙኃኑን ይዟል፣ እዚያ ግን አናሳ ነው፡፡ እዚህ አናሳ የሆነው ደግሞ እዚያ ብዙ ይሆናል፡፡ የብዙኃን ወገን በሆንክበት ቦታ አናሳው ካሰቃየህ፣ አናሳ በሆንክበት ቦታ ደግሞ ብዙኃን ያሰቃዩሃል፡፡ እዚህ ባለ ሥልጣን እንደሆንከው እዚያ ተራ ትሆናልህ፡፡ የሚያዋጣው በሚዛኑ ልክ ትክክለኛውን ማድረግ ብቻ ነው፡፡

@wegoch
@wegoch
@paappii

#eled aymen(elediye)
This is huletegna events and promotion. we are a team of people who love to sing. Also you can showoff your talents by performing on our upcoming acoustic night. 2thegna is the place to be.

Venue: velvet lounge, bole Tk building rooftop

Telegram: @huletgna
Instagram: @hulegna
Join and share.

Call 0900651327 if you want to perform or save a seat.
for more
@MsChanandlerBond
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1495ኛው የነብዩ መሐመድ የልደት በዓል አደረሳችሁ!

Mawlid Al Nabil Al Sharif
@seiloch
@getem
@wegoch
#ቆዳ እና #ሸራ ላይ የወደዱትን ፎቶ ለማሳል
በ +251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ ማዘዝ ይችላሉ ።

🎨ለ ልደት
🎨ለፍቅረኛ
🎨ለ ሰርግ እና
🎨የቤተሰብ ፎቶግራፍ ማሳል ለምትፈልጉ ሁሉ

Join @seiloch
ጦርነት ውስጥ ራስህን አስበህ ታውቃለህ? ታውቂያለሽ?
.
.
መሳሪያ በታትነህ ጠራርገህ ታውቃለህ? የጥይት ሒሳብ ተከራክረህስ ይኾን? በማለዳ ተነስተህ በጀርባህ ንብረት አዝለህ፣ ከስክስ ጫማ አድርገህ ተራራውን ሮጠህ ታውቃለህ? ምሽግ ቆፍረህስ!?
የጥይት አሩር÷ ጭሱን በአፍህ እና በአፍንጫህ ምገህ ታውቃለህ? ቦንብ ከአውሮፕላን እንደ ዝናብ ሲዘንብ÷ የምድሩን ከርስና ገፁን ሲያርደውስ አይተኸል? ምድርስ በዚህ ምክንያት ስትንቀጠቀጥ እግርህ ያውቃልን?
የሰዎች እግር ሲቆረጥ÷ አካላቸው እዚያና እዚህ ሲበታተንስ አስተውልኸልስ ይኾን? የእናቶች እሪታ÷ የልጆች ለቅሶ በጦርነት መኸል ጆሮህ ሰምቶ ያውቃል? ወንዶች በጩቤ ሲሞሻለቁ÷ ሴቶች በድምፅ አልባ መሳሪያ ሰው ሲጥሉ÷ አናት ሲፈጠርቁስ አስበኸው ይኾን?
ይኽን ኹሉ ሰቆቃ እና ዕውነት ለመሸከም ትከሻም፤ ልብም የለንም፡፡
ቅዱስ መፅሐፍ እንደሚለው ሰላምን እንሻለን፤ እንከተላለን እንጂ!
ጦርነት መሬ ነው፡፡
ለምለም እንጀራ የምትበላበት ሰዐት አይኖርህም፡፡ ጠይም ከንፈር ያላት ወዳጅህን አታገኛትም፡፡ ደጀ ሰላም በለሊት ተነስተህ አትሳለምም፡፡ የአዛን ድምፅ የምትሰማበት ጊዜ እንደ ሰማይ ይርቀኸል፡፡ ዱንቡሼ ፊት ያላቸው እንቦቃቅሎችን አታይም፡፡ የእናትህን የእጅ ደበሳ እንደ ገነት ደጅ ይርቀኸል፡፡ ቋንቋህ እና ኑሮህ እንደ ባቢሎን ይኾንብኸል፡፡
ከጦርነት ማግስት እንኳን ውጥንቅጡ የወጣ ከተማ ትታቀፋለህ፡፡ የሞቱ ሰዎች የሬሳ ክምር፣ ሬሳዎቹን ሊበሉ የሚያንዣብቡ ጥንብ አንሳዎች፣ እግራቸውን የተቆረጡ ሰዎች፣ ደረታቸው የተቦረደሱ÷ አንጀታቸው ከሆድ እቃቸው የወጡ ሰብዖች ከቅርብህ÷ ከርቀትህ ታገኛለህ፡፡
ከተማው÷ ሐገሩ የአይጦች ምሽግ ይኾንብኸል፡፡ ፍርስራሽ ቤቶች፣ መሶብ የሌላቸው ጓዳዎች፣ አባወራ የማይገኝባቸው ደጆች ይሰጥኸል፡፡ የሚስቁ ድምፃች፣ ደምግባት ያላቸው ፊቶች ተቀብረዋልና!
ጦርነት ሐገር ይሰራል የሚለውን የብሉይ ሐቲትን አንቀበልም!
ከዚህ ኹሉ የምድር ሲኦልነት÷
እኛ ውይይትን÷ ሰላም እና ወንድማማችነትን እንመርጣለን፡፡
ከለመለመው መስካችን እንጀራ መብላት እንመኛለን፡፡ ማሳችንን ማረስ÷ ብዕራችንን ስለ ፍቅር እንዲተፋ ማድረግ አምሮታችን ነው፡፡ ከህፃናቱ ጋር አፃለሌን መዝፈን ነው የምንፈልገው፡፡
አምላካችን ፊት አባታችን ሆይ ማለት እንዲጎልብን አንሻም፡፡ አዛናችንን በምሳ ሰዐት ታጥበን ማድረስ የዘወትር ሃያትችን እንዲኾን እንቃትታለን፡፡ በፍቅር ሰላምታ ተሰጣጥተን የሰላም ሐገር መገንባት የዘወትር ፀሎታችን ነው፡፡
ኹሉን በፍቅር አድርጉ ተብላልና÷
እኛ የፍቅር ሰው÷ የሰላም ሰው መኾናችን እስከ ዕለተ ሞታችን ድረስ መለያ ቀለማችን ነው፡፡

@wegoch
@wegoch
ለምሽታችን ምርጥ አዲስ ፕራንክ....ከ ቴዶ 🙊😉
https://m.youtube.com/watch?v=T29d6KO45A4&t=1s
እዚጋ ደሞ ሌላ ትኩሳት
""""""""""""""""""""""""""""
ኧረ ጉድ ነው እናንተዬ......በስንቱ ጭንቅላታችን ስሜታችን ተነክቶ እንቻለው?.....የት እንሂድ?... ወዴት እንድረስ... ወይ አሰልፈው ይረሽኑን እና እንረፈው። ("ምን ሆንክ?" ትላላችሁ መቼም...) ኮሮናን ተዉት......ስራ መቀዝቀዙንም ተዉት.....ትምህርት መዘጋቱንም ተዉት.....የሀገር እረብሻውንም ተዉት.....ሰዉ በየክልሉ መሞቱንም ተዉት....አንበጣዉንም ተዉት!....እንደው ከላይ ከዘረዘርኳቸው አስጨናቂ ወሬዎች ትንሽ ፈታ ብንል ብለን የቲቪ ሪሞታችንን ይዘን ጋቢ ቢጤ ጣል አድርገን በየአልጋችን፣ በየሶፋችንና በየወንበራችን (ሰው ባለው ነው መቼም ) አረፍ ብለን ቲቪያችንን ስንከፍት ህሊናችንን እያገላበጠ የሚገርፍ ማስታወቂያዎች ጋ ገጭ እንላለን።

አሁን የኔ አሙዋሙዋት
አሙዋሙዋት ነው ወይ?
ጉች ጉች ያለ ጡት
አንድ ቀን ሳላይ....

ያለው ያገሬ ሰው እኮ በኛ ደርሶ ቁጭ አለ።(በእውነት)....የሪል ስቴቱ ብዛት ለጉድ ነው "ካሳንቺስ መሀል እንትን ሪል ስቴት ሌግዠሪ ህይወትን ይኑሩ ሺ አመት አይኖር....." ይላል አስተዋዋቂው ድምፁን ጎርነን ቀጠን እያደረገ።....ኧረ ወንድሜ 64ቱንም አመት እንዴት እንደሚያልቅ ጨንቆናል ዘረኛ ይድፋን፣ ኮሮና ይድፋን ገና አላወቅነውም። በቁማችን ግን ሰቀቀኑ እየገደለን ነው። ምን አይነት ቤት ነው የምታሳዩን እንቁልልጭ እያላችሁት ነው ደሀውን......ኧረ ተዉ ግፍ አለው ለኑሮዋችን ተዉን በGood morning ሻይ ቅጠል እና በዘኒት ቅባት ማስታወቂያዎች እኮ ነው የለመድነው ድንገት ምነው ሰቀላችሁን?....ቲቪ የገዛበትን ብር ብድር ሳይከፍል ህዝቤ ተሳቆ ....ለደስታ በገዛት ቲቪ ደሞ የባስ በእናንተ አፓርታማ እና ሪል ስቴት ይሳቀቅ እንዴ ሆኦኦ....

ወይ እዛው የናንተን ቅንጡ ኑሮ የምታሳዩበት ቻናል ለብቻችሁ ከፍታችሁ እዩ(ሀብታሞች)......እኛ ደሀዎቹን አታቁለጭልጩን ኑሮ የሚያቁለጨልጨን ይበቃል።

አሁን በቀደም ጎረቤቴ የሆነ አንድ አባት ከህፃን ልጁ ጋ ሲያወሩ ጆሮዬን ጣል አድርጌ እሰማቸው ጀመር(ለነገሩ ጆሮዬን ጣልኩ አልጣልኩ የተፈሳችው የተገሳችውም ትሰማኛለች ኩታ ገጠም ከመሆኑ የተነሳ)
ልጅ፦ አባቢ አባቢ ቦቦ ግዛልኝ....
አባት፦ አንተ ልጅ እንደገና ቁልቁል ሽንት ቤቱ ምን ሆነና አድገህ የለም እንዴ?(ፖፖ ያለው መስሎት ነበር እኔ እየሰማው በውስጤ በሳቅ ፍርስ)
ልጅ፦ ኧረ አይደለም አባዬ ቦቦ ወተት ነው እነ ቸሬ...ቤቢ...ትርሲትም ተገዝቶላቸዋል አስቀምሰውኛል ይጣፍጣል
አባት፦ ስንት ብር መሆኑ ነው?
ልጅ፦ 15 ብር
አባት ክው .....ስራ ሲሄድ ለትራንስፖርት አድርሳ የምትመልሰውን 15 ብር ልጁ ፉት ሲላት ታይቶት...
አባት፦ በቃ የኔ ልጅ ለደሞዝ እገዛልሀለው
ልጅ ሆዬ እንባው ዱብ ዱብ "ግዛልኝ ዛሬ ነው የምፈልገው..."
አባትም ቆጣ ብሎ "ሂድልኝ አንተ ውሪ ...የምንም ጣፋጭ ለምዶ ሊባልግ ይፈልጋል እንዴ..." ሊመታው አርጩሜ ሲፈልግ ልጅ ፈርቶ ቁጭ ....አባት ውስጡ እያለቀሰ ላዩን ተቆጥቶ ልጁን አሳረፈው....ቢኖረውና ቢገዛለት ምንኛ ደስ ባለው ግን ዛሬ አንድ ወተት ቢያጠጣው ነገ ስራም መሄጃም አይኖረው፤ ስለዚህ የልጁን አምሮት በቁጣ ማብረድ ግድ ሆነበት።
ስሰማቸው ስለነበር አቡሽ አሳዘነኝ ደሞዝ ሰሞኑን ስለተቀበልኩ ልገዛለት አሰብኩና አባቱ ፊት ብገዛለት አባትየው እንዳያፍር እንዳይናደድም ብዬ (መቼም ደሃ ብንሆንም ኩሩ አይደለን) እቅድ አቀድኩ.... አቡሽን ቤተ ክርስትያን ይዤው መሄድ እና ስንመለስ ያማረውን እገዛለታለሁ አልኩ። አባቱንም አስፈቅጄ ቅርባችን ወደአለው ሚካኤል ቤተ ክርስትያን ተያይዘን ሄድን ተሳልመን ገባንና ወደ ግንቡ ጠጋ ብዬ ፀሎቴን አድርሼ ጨረስኩ ወደ አንድ መቀመጫም ሄጄ አረፍ አልኩ። አቡሽ አሁንም ግንቡን ተለጥፎ ፀሎቱን ያደርሳል ካሰብኩት ደቂቃም ሲቆይብኝ ምን ብሎ እየፀለየ ይሆን የሚል ጥያቄ ፈጠረብኝ። ከዛ እሱም ጨረሰና ተያይዘን ወጣን ከዛ ጠየኩት"አቡሽዬ ምን ብለህ ፀለይክ?"
በሚያሳዝን አይኑ ቀና ብሎ እያየኝ በቁምነገር እንዲህ ብሎ መለሰልኝ "እግዚአብሄር ወይ ቦቦ ግዛልኝ ነው ያልኩት" መንገድ ላይ እንደዛ ስቄ አላውቅም አቡሽም ቀና ብሎ እያየኝ ግራ ገብቶት ፈገግ እያለ"ምነው አብርሽ?" አለ።
"ና ና ፈጣሪ ፀሎትህን ሰምቶሀል..." ወደ ሱቁ አመራን

እዚጋ ደሞ ሌላ ትኩሳት
ወገኔ አለቀ በጉጉት እሳት
እሳት
እሳት.....በሉልኝማ

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@wegoch
@wegoch
@paappii
ወይ እንጀራ ወይ ሞት
(በእውቀቱ ስዩም)
.
ታሪክ ፀሀፊዎች “ዘመነ መሳፍንት “ ብለው በሚጠሩት ፤ እኔ ደሞ “ ዘመነ የጁ “ በምለው ዘመን ውስጥ አንዲት አረሆ የሚከተለውን ግጥም አንጎራጉራ ነበር፤
"እሄዳለሁ ሜጫ እሄዳለሁ ዳሞት
ሳላገኝ አልቀርም ወይ እንጀራ ወይ ሞት "
በነገራችን ላይ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ባላገሮችንና ጌቶችን በፈጠራ በማዝናናት የሚተዳደሩ የግጥምና የዜማ ባለፀጋ ሴቶች ና አረሆ ተብለው ይጠሩ ነበር::
ያኔ ካንዱ አውራጃ ወደ አንዱ አውራጃ የሚኬደው በባዶ እግር፤ ግፋ ቢልም በበቅሎ ነው ! ሲመሽ በሸማ ድንኩዋን ስር ወይም ዛፍ ስር ይታደራል ! አባይን መሻገርማ አይጣል ነበር ፤ ካዞ ብታመልጥ ሽፍታ አይምርህም ! አቶ ሀዲስ አለማየሁ እንዳሉት አባይ “ ብዙ ሞቶች ተሰብስበው የሚገኙበት ቦታ” ነበር፤ በዚያ ላይ በየቦታው መሳፍንቱ ጎራ ለይተው በየቦታው ይከሳከሳሉ ፤ በግርግር መሀል በራሪ ጥይት መሞት መደፈርና መጠለፍ ሊያጋጥም ይችላል!
የጠቀስኩት ግጥም ዝምብሎ የድሮ ግጥም አይደለም! ዛሬም የብዙሀኑን የኢትዮጵያዊ ህይወት የሚገልፅ ይመስለኛል ! “ሜጫንና ዳሞትን “ በሌሎች ቦታዎች ተክቶ ማንበብ ብቻ ነው እሚጠበቅብን ! ከጥቂት አመታት በፊት በሰደት ወጥቶ መሞትን ስናስብ መጀመርያ ወደ አእምሮአችን የሚመጣው አረብ አገር ወይም ደቡብ አፍሪካ ነበር ፤ ብዙ ሰው ወቅቱን ያልጠበቀ ሞት ሸሽቶ ነበር ወደ አሜሪካ የሚሰደደው ሞት አሜሪካ ውስጥ ለመጥፋት የተቃረበ ብርቅየ አውሬ ሆኖ ቆይቷል ፤ ዘንድሮ ይሄ ቀርቷል ! ከሁለት ቀናት በፊት ባንድ ቀን ብቻ ዘጠኝ መቶ ሰባ አንድ ሰዎች እንደ ጥቢ ቅጠል ረግፈዋል! አሜሪካ እንጀራ አምሮት ለመጣ ስደተኛ ሞትን በሰፌድ ማቅረብ ጀምራለች::
ይህ ብቻ አይደለም ! አሜሪካኖች ምርጫ ላይ ናቸው! የትራምፕ ደጋፊዎች እንደ ጌታቸው መጋጣነታቸውን -ወይም ባዲስባ አራዳ አማርኛ " ሰገጤነታቸውን " መደበቅ እሚችሉ አይደሉም ! ሰውየውም ሽንፈቴን በፀጋ አልቀበልም ብሏል ! ደጋፊዎች ጎራ ለይተው ሊላመጡ ይችላሉ! እዚህ አገር ድብድቡ ከተጀመረ እንደ ሸገር በድንጊያ ወይም እንደ ፍልስጤም በወንጭፍ አይደለም! ሁሉም " ነጣ ዘለግ ያለ ስናይፐር ታጣቂ" ነው!
አሁን ሳስበው መሞቴ ካልቀረ እዛው ባገር በቀል ዱላ መሞት ይሻለኝ ነበር፤ ደግነቱ በሜክስኮ ድንበር ግንብ ታጥሮ አለማለቁ ጠቀመኝ! የፈራሁት ከደረሰ፤ በቅርቡ “ የበውቄ ኩብለላ-ከማንኩሳ እከጉዋታማላ “ የሚል ማስታወሻ ጠብቁ፤

@wegoch
@wegoch
የመጀመሪያው እምቢታ!
«ዘውድአለም ታደሠ»
(አማን መዝሙር)

«ሰላም ነው ስሜ» አለችኝ!
«ሰላም የሚባሉ ሴቶች ብዙ ግዜ ፀረሰላም ናቸው ይባላል» አልኳት!
«ይሆናል ...» ብላ ሳቀች! ሰላምን ካገኘኋት ገና ሰላሳ ደቂቃ አይሞላኝም። ሰው ሰላም ሊል ወደኋላ የቀረ ጓደኛዬን ቆሜ ስጠብቅ ድንገት በኔ በኩል መጣች። ልከኛ ነች! መሃከለኛ ቁመት፣ መሃከለኛ ፀጉር፣ መሃከለኛ የሰውነት ቅርፅ ... በመሃከለኛ እርምጃ ስትመጣ የማላውቀው ሃይል የሆነ ነገር በል በል አለኝ! አጠገቤ ስትደርስ «እንተዋወቅ» አልኳት! የምር በቃ ይሄን ነው ያልኳት! ማነሽ? ወዴት ነሽ? ገለመሌ የለም፣ አለ አይደል ልክ ፊልም ላይ እንደምናያቸው
አክተሮች መጀመሪያ አስቆ ፣ አባብሎ፣ አሽኮርምሞ “እጅ ፅሁፍሽ እንዴት ነው?”
ምናምን ብሎ መጀንጀን የለ እንዲሁ ድርቅ ብዬ እንተዋወቅ! «ሰላም እባላለሁ» አለችኝ! «ሰላም የሚባሉ ሴቶች ብዙ ግዜ ፀረሰላም ናቸው ይባላል» አልኳት! «ይሆናል ...» ብላ ሳቀች! «ፀሃይ ነው ለምን ትንሽ አረፍ ብለሽ ቡና ምናምን ጠጥተን መንገድሽን
አትቀጥዪም?» አልኳት! «እሺ» አለችኝ!
ጓደኛዬን ጥዬ አንዱ ካፌ ይዣት ገባሁና ሻይ ቡና ብለን ስንወጣ «ለክፉም
ለደጉም ቁጥር ብንለዋወጥ» አልኳት!
«እሺ» አለችኝ። (ልጅቷ እምቢ አታውቅም ጎበዝ) ቁጥሯን ተቀብዬ ደወልኩላትና ጥቂት አውርተን «ነገ ከተመቸሽ እንገናኝ?» አልኳት
«እሺ ....!»
ብዙ ግዜ ተገናኘን! ተቀራረብን ወደድኳት! ፈራ ተባ እያልኩ «ወደድኩሽ»
አልኳት። ትንሽ አስባ «እሺ» አለችኝ።
«ፍቅረኛዬ ብትሆኚ ደስ ይለኛል»
«እሺ ....»
የእሺታዋ ብዛት ግራ ቢገባኝም ወድጄዋለሁ። ምንም ነገር አትቃወም! እምቢ አታውቅ! አትጨቃጨቅ! በቃ ሁሉን እሺ ነው! እንዲህ ቦታ እንሂድ? እሺ! እንዲህ እናርግ? እሺ! ... ሁለት አመት ከአምስት ወር ሆነን አንድም ቀን ፀባይዋ ሳይለወጥ! አንድም ቀን ኮምፕሌን ሳታደርግ! እንዲሁ ግራ እንዳጋባችኝ ሁለት አመት ከአምስት ወር በፍቅር!! የሆነ ቀን ቀለበት ከኪሴ አውጥቼ «አግቢኝ» አልኳት!
«እሺ ....!»
እሺ ጠላሁ! በቃ ደበረኝ! አለ አይደል የሆነ ውድን ነገር በርካሽ ስናገኘው «ይሄ ነገር ፎርጂድ ይሆን እንዴ?» ብለን የምንጠራጠረው አይነት? ቆይ እስከዛሬ በኔ ስሜት፣ በኔ ፍላጎት፣ በኔ እቅድ እሺ ብቻ እያለች ኖረች! የራሷ ስሜትስ? የራሷ ፍላጎትስ? የራሷን ህልም የት አርጋው ነው ሰው ህልም ውስጥ ጭልጥ ብላ
ምትጠልቀው? ተጋባን!
«ልጅ እንውለድ?»
«እሺ!»
ግራ ታጋባኝ ነበር! አሁን ግን የእሺታዋን ጋጋታ እንደድንዛዜ አየሁት። አለ አይደል
ስሜትን ካለማዳመጥ የሚመጣ፣ ፍላጎቷን ሳታውቅ የምትኖር ነፋሱ ወደነዳት የምትንሳፈፈ ፌስታል ያህል ቀለለችኝ! በቀደዱላት ቦይ የምትፈስ ወራጅ ውሃ መሰለችኝ! አዎ ውሃ! ከገደቧት የምትረጋ፣ መንገድ ከሰጧት የምትጓዝ፣ እሳት ላይ ሲጥዷት የምትሞቅ፣ ፍሪጅ ሲጨምሯት የምትበርድ ብርጭቆ ውስጥ ሲያረጓት ብርጭቆውን የምትመስል፣ በስኒ ሲጨልፏት የስኒውን ቅርፅ የምትይዝ
፣ የራሷ ቅርፅና መልክ የሌላት ውሃ መሰለችኝ! ተራ ውሃ! ለምን አመሸህ? ለምን ይሄን አላረግክም? ብሎ ጭቅጭቅ እሷጋ የለም! እንኳን ባመሽ ባድር በነጋታው ምንም እንዳልተፈጠረ በፈገግታ ትቀበለኛለች! ብስጭት ብዬ ስናገራት መልስ አትሰጥም! ይሄን አርጊ ያን አታርጊ ስላት ለምን? ማለት የለም «እሺ» ነው! በቃ እሺ ብቻ! በጓደኞቼ ሚስቶች እቀናለሁ። ሲቆጡ ቁጣቸው ውስጥ የኔነት አለ። ሲቀኑ ቅናታቸው ውስጥ ስስት አለ! ሲከፉ መከፋታቸው ውስጥ ፍቅር አለ! የኔዋ ግን .... በቃ በድን! ታግዬ እንኳ ላስከፋት የማልችል፣ ሁሉን ነገር ከመቀበል ውጪ እምቢ የማታውቅ ግኡዝ ፍጥረት ትመስለኛለች!
አንዳንዴማ ነካ ሚያድጋት ሁሉ ይመስለኛል! እኔው አጥፍቼ እኔኑ ይቅርታ
ስትጠይቀኝ ብግን እላለሁ። አስከፍቻት ውዬ ስመለስ ከበር በፈግታ ስትቀበለኝ
እየተወነች ይመስለኛል! አውቄ የማይሆን ሃሳብ ስነግራት እሺ ስትለኝ ጩህ ጩህ ይለኛል! አንዳንዴ ስጋ የለበሰች አሻንጉሊት ያገባሁ ሁሉ ይመስለኛል! በኔ
ፍላጎትና መጠን ዲዛይን የተደረገች ሮቦት ትመስለኛለች! ሰለቸኝ! በድን አቅፌ የምተኛ መሰለኝ። ለካ ጠብ ብቻ ሳይሆን ቅጥ የለሽ ሰላምም ይረብሻል! ለካ አለመስማማት ብቻ ሳይሆን ዝም ብሎ መስማማትም ይጨንቃል! «እንኳን ሰው ድንጋይና ድንጋይ እንኳ ይጋጫል» ይላሉ አበው። አንዳንድ ሰላም ከድንጋይም ያሳንሳል! በተጋባን ባመቱ «እንፋታ» አልኳት
«እሺ!» አለችኝ!
ለምን? የለ! ድንጋጤ የለ! በቃ «እሺ ብቻ!» ...ፊቷ ላይ ግን የሆነ ሃዘን መሳይ
ነገር አይቻለሁ! ቢሆንም ይሄንንም «እሺ» ብላ መቀበሏ የበለጠ አናደደኝ! ከዚች ጋርማ መኖር አልችልም። አልኩት ራሴን! ጠኋት ተነስቼ ወደምሄድበት እሄዳለሁ ቤቱን እሷ ቤቢን ይዛ ትኑርበት። ልጄ ሲናፍቀኝ እየመጣሁ አየዋለሁ! አልኩ በሆዴ! በጠኋት ሻንጣዬን ይዤ ልወጣ ስነሳ እሷ ቀድማኝ ቤቢን ይዛው ሄዳለች! ቁምሳጥኑ ውስጥ እኔ የገዛሁላት ልብሶች ብቻ ቀርተዋል! ፍሪጁ ላይ አንድ ወረቀት ተለጥፏል። ጠጋ ብዬ አየሁት «ራስህን ጠብቅ» ይላል! ግራ ገባኝ! እንዳሰብኩት ነፃነት አልተሰማኝም። የሆነ ሃዘንና ድብርት የቀላቀለ ነገር ይሰማኛል። ሳምንቱን ሙሉ ሰከርኩ! ከሳምንት በኋላ ደወልኩላት! ስልኳን አታነሳም። በህቷ ስልክ ስደውል ቤተሰብ ጋር እንዳለችና ልታናግረኝ እንደማትፈልግ ነገሩኝ! ይሄን ስሰማ የሆነ ደስ ነገር አለኝ! ማለት አለ አይደል እሷም እንደሰዉ እንደምትከፋ በማወቄ የሆነ ደስ የሚል ስሜት ተሰማኝ! አንድ ወር ቆይቼ ደወልኩላት። አሁንም አታነሳም። ግራ ተጋባሁ! ጨነቀኝ! ምንም ያልበደለችኝን ሚስቴን ምን ሁኚ ብዬ ነው ያባረርኳት? ትዳሬን ምን ይሁን ብዬ ነው ያፈረስኩት? ምን አርጊ ምን ፍጠሪ ነው ያልኳት ቆይ? ፀፀት ሁለመናዬን ወረረኝ! ቢቸግረኝ የቅርብ ጓደኛዬን ይቅርታ ጠይቆ እንዲያመጣት ላኩት። እሷ ማንንም ስለማታስከፋ እሺ እንደምትለው እርግጠኛ ነበርኩ! ለማሰቢያ የሚሆን ግዜ እንዲሰጣት ነግራው አሰናበተችው። ካሁን አሁን መጣች ብዬ ስጠብቅ የፍቺ ወረቀት በሬ ድረስ ላከችልኝ! ምድርና ሰማይ ዞረብኝ! ወረቀቱን በእጄ አንጠልጥዬ ስበር ቤተሰቧ ቤት ሄጄ
በሩን አንኳኳሁ። ራሷ ከፈተች! ፊቷ ላይ ምንም አይነት ለውጥ አላየሁም። አይኖቿ ላይ ግን እንለያይ ስላት ያየሁትን ሃዘን አይቻለሁ። «ምንድነው ይሄ?» አልኳት «እንፋታ ብለኸኝ የለ? የፍርድቤት መጥሪያ ነው» አለችኝ። ድምጿ ውስጥ
የቀድሞ ልስላሴዋ የለም። ሌላ ሴት ነው ምትመስለው። እግሯ ላይ ወድቄ ይቅር እንድትለኝ ለመንኳት! ዝም ብላ ስታየኝ ቆይታ አንድ ቃል
ከአፏ አወጣች
«እምቢ!»
ጆሮዬን አላመንኩም። እምቢ የሚለው ቃል ለካ እንዲህ ያማል? እምቢታዋ ውስጥ ከእሺታዋ የሚበልጥ ጥንካሬ አለ! እምቢታዋ ጨካኝ ነው! ያስፈራል !
ከዚያን ቀን ወዲህ ለመታረቅ ያልፈነቀልኩት ድንጋይ ያልሰደድኩት ሽማግሌ የለም! ነገር ግን ሁሉም እምቢታዋን ለማሸነፍ የሚያበቃ ጥንካሬ
አልነበራቸውም! እምቢታዋ ዘልአለማዊ ነው!

@wegoch
@wegoch
@paappii
አያድርስና .. ወያኔ ብትመለስስ ..!
«ዘውድአለም ታደሠ»
(አማን መዝሙር)
አሁን እንደው አያድርገውና ነገ ልክ ከእንቅልፋችን ስንነሳ ወያኔ በባሌም በቦሌም ብላ ቤተመንግስት ገብታ ራዲዮኑ «ብሶት ዮዎሎዶ ሎዲጂታል ዎያኔ ሶርአዊት ሎኩሉተ አመት ሎአህዳዊው ሎአቢይ ሞንጉስት የያዘውን ቤይተመንግስት ቦሞራራ ትግል ቶቆፃፅሮታል» በሚል ሰበር ዜና ሰርፕራይዝ ብታደርገን ምን ይፈጠር ይሆን ብዬ በምናቤ ለመሳል ሞከርኩ።
መጀመሪያ ከሐገር የሚጠፋው ያ "ጌታቸው አሰፋ በሽጉጥ ፀጉሬን ላጭቶኛል" ያለው ሰውዬ ይመስለኛል
ጋሽ ሃይለማርያም ደሳለኝ እንደተለመደው በቴሌቭዥን መጥተው «አሁን ገና ብርሃን አየን። ባለፉት ሁለት አመታት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ነበርን» ብለው ጌታን ያመሰግናሉ። አብዲ ኢሌ እንደማንዴላ እጁን እያውለበለበ እንደነፃነት ታጋይ ጀነን ብሎ ከእስር
ቤት ይፈታል። በለው! ይብላኝላቸው ለፋና ጋዜጠኞች እያንዳንዳቸው ጌታቸው አሰፋ ጋር ቀርበው እንደአርጋው በዳሶ በጭንቅላታቸው ቆመው ንስሃ እንዲገቡ ይደረጋል። ሃያ ሁለት እንደቀድሞዋ ጎልድ ሌብል እየጠጡ በየመሃሉ ወጣ እያሉ ሽጉጥ በሚተኩሱ የከተማ ዶን ኮርሌዎኔዎች ትሞላለች። ጋዜጠኛ አንሙት አብርሃም ኦዞንን ለመሸንቆር በማሴርና በ treason ሲከሰስ ያየሰው ሺመልስ ደግሞ ባለብእሩ ቼጉቬራ ተብሎ የክብር ዶክትሬት ከመቀሌ
ዩኒቨርስቲ ይሰጠዋል። አብይ የጀመራቸው ሸገር ፓርክና እንጦጦ ፓርክ ከምንከተለው ግራ ዘመም
ርእዮተ አለም ጋር አይሄዱም ሰውንም ስራ ያስፈታሉ ብለው ኮንዶሚኒየም
ይገነቡባቸዋል። ጌታቸው ረዳ አወሉ አብዱን አፈላልጎ ይደበድበዋል ዳንኤል ብርሃኔ «እንዳያልፉት የለም» የሚለውን የትግል መዝሙር እየዘመረ እንደበፊቱ ሸራተን ቁጭ ብሎ በአራት ቺክ ተከቦ አክቲቪዝሙን ያጧቱፋል። ያ "አብይ ሳምባዬ ነው" የሚል መፈክር ይዞ የወጣው ሰውዬ እሱን ሰርዞ "ደብረፂዮን ጣፊያዬ ነው" የሚል ጥቅስ ይፅፍበታል
«ልማቱ ፣ ብሔር ብሔረሰቦች፣ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ የመለስ ሌጋሲ ፣ ኪራይ ሰብሳቢነት» ምናምን የሚሉ ቃላት
ወደቦታቸው ይመለሳሉ። መንግስት ካለፈ በኋላ ማድነቅ የሚወደው የኢትዮጵያ ህዝብ ምፅ ምፅ እያለ
«አዪዪ ጥጋብና ተድላ በአብይ አህመድ ግዜ ቀረ» ይላል አንዳንድ ጥቃቅንና አነስተኛ ብሔሮች ባለፉት ሁለት አመታት ምን ያህል ሲጨቆኑ እንደኖሩ እንባ በአራት መንታ እያወረዱ ይናገራሉ። የፈንቅል መሪዎች በሱዳን በኩል ይነኩታል:) የትግራይ ፕሬዘዳንት ነኝ ያለው ነብዩ ስሁል «አረ ፕራንክ ነው» ብሎ ያስተባብላል ጓድ አባዱላ ገመዳ በዚያ አንጀት በሚበላ እንግሊዝኛው "how many times death came to me” ይልና ፈገግ ብሎ "if love is between us never die" ብሎ ይመሰጣል ጓድ አረጋዊ በርሄ «ምነው ትንሽ እንኳ ስልጣን ላይ ብታቆየኝ» ብለው እንባቸውን ወደሰማይ ይረጫሉ ።
ደህዴኖች ያው ላሸነፈው ናቸው መቼስ። «ኢኛኮ ቢልፂጊና ሚባል ናጋር ዲሮም
አልቴሜቼኒም ናበር» ብለው ለደብረፂዮን ባህላዊ ልብስ በማሰፋት በአስጌ ዘፈን
እየጨፈሩ ይቀበሉታል ለውጡ ከመጣ በኋላ ስማቸውን ከሃጎስ ወደ ደቻሳ የቀየሩ ሰዎች ለሶስተኛ ግዜ ወደሀጎስ ለመቀየር ፍርድቤት ይሰለፋሉ ማእከላዊ በአዲስ መልክ ስራ ይጀምራል። የሃይላንድ ላስቲኮች ከብክነት ይድናሉ። ለሚ ኩራ የሚለው አዲሱ ሰፈር “ደፂ ኩራ" ወደሚል ይለወጣል : የዲሲ ግብረሃይል በዚያች አንድ ለናቷ እንግሊዝኛው "shame on you, you are bloody hand" እያለ ያወግዛል። ታማኝ በየነ ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል።
ኤርሚያስ ለገሰ በእጁ ያለውን ሚስጥር ለማውጣት ደፋ ቀና ይላል ወዳጄ ዮናታን የአብይን ፎቶ ግድግዳው ላይ ሰቅሎ «ምነው ተለየሽኝ መስከረም ሳይጠባ» በሚለው ዘፈን ያነባል እኔ ደግሞ “ብልፅግናዎች አፍዝ አደንዝዝ አድርገውብኝ ነው እንጂ ውስጤኮ
ከጭቁኑ ህዝብ ጋር ነው” ብዬ በራሴ ላይ ግለሂስ አወርዳለሁ

@wegoch
@wegoch
@paappii
ወይ አያቶቻችን…… ?
[ሰሎሞን ሹመቱ]
________________________
ሰፈር ዉስጥ ተቀንጠን ትንሿ የጓደኛችን የሃይሌ እህት መጣችና ቁጭ አለች! ወሬያችን ይገባታል ብለን ስላላሰብን ከሷ ፊት ሊወሩ የማይገቡ ፖለቲካዊ ወሬዎችንም እያወራን ነው፡ በዚህ መሀል ስለ ሀገሪቱ ብጥብጥ አንስተን ስናወራ፥ ቀልጠፍ ብላ "እረ አባየ እኮ ይህችን ሃገር እንደዚህ አይነት ምስቅልቅል ዉስጥ የከተታት የአያቶቻችን ጡር ነው! ብሏል አለችን። ሁላችን ደንግጠንም ተገርመንም። ሁላችንም ወደ ሃይሌ ስንዞር ባክህ እኔ ሰምቸ አላውቅም እንደዚህ አይነት ነገር አለ ወደኔ አፍጥጦ። ወዲያው በዚያው ሰአት የጓደኛችን አባት ከስራ ወደ ቤት እየመጡ ድንጋያችን ላይ ተኮልኩለብ ሲያገኙን ሰላምታ ሰጡን እኛም የጅምላ ሰላምታ ሰጠናቸው።

ታድያ ከመሀላችን አንዱ " ጋሼ ኢትዮጲያን ለዚህ ሁሉ ያበቃት የአያቶቻችን ጡር ነው ብለዋል አለችን፥ እንደት እንደዛ አሉ? አላቸው። እርጅና በተጫነውና በጎረነነው ድምጻቸው ማብራራት ቀጠሉ "አያቶቻችን አገልጋይ ባሪያዎች ነበሯቸው፥ ታድያ በአንድ ወቅት የኛ አያቶች ልጃቸው ስትሞትባቸው " የኔ ልጅማ ብቻዋን መቃብር ጨለማ ዉስጥ አትገባም ብለው ልጃቸውን መቃብሩን እንድታላምድላቸው ብቻዋን እንዳትፈራ ብለው አንዷን ባሪያቸውን ከነ ነፍሷ ቀብረዋታል። አሉ። ታድያ የዚህ ጡር ከዚህ የባሰ ዉጥንቅጥ ዉስጥ ቢያስገባንስ ይገርናል እንደ?" ብለው ሁላችንንም በግልምጫ ቃኙን እውነትነቱን የተጠራጠሩ አይመስሉም ጓደኞቸ። እኔ ግን ሁለት ነገሮች ተምታቱብኝና ማብራሪያ በመጠየቅ አይነት ጠየኳቸው፥

"ጋሸ ግን የሚጣ አያቶች ናቸው ወይስ የእርስዎ አያቶች ናቸው ይሄን ተግባር የፈጸሙት "አልኳቸው። አልገባኝም ምን ለማለት ነው? አሉኝ፥ እኔም ቀጠልኩና "ማለቴ ሚጣም ስትነግረን እኮ አያቶቻችን ነው ያለችን እርስዎም ሲነግሩን አያቶቻችን አሉ! መቸም የእርስዎና የነ ሚጣ አያቶች የተለያዩ ናቸው አይደል? " ስላቸው፥ ግራ እንደመጋባት ብለው ሊያብራሩ ሲጀምሩ፥ ጓደኞቸ ጫጫታ ባለው ሁኔታ "እየው ይሄ ነገረኛ አሁን ይሄ ምን ማብራሪያ አለው፡ በቃ ህግ ተማሪ ስትባሉ" ምናምን እያሉ ሲንጫጩ፥ ቆዩ እንጂ እኔ እኮ እሳቸውን ነው የጠየኩት መልስ ሊሰጡኝ ነው እኮ አልኳቸው ቆጣ ብየ። ሁሉም ዝም አሉና መልሳቸውን ስንጠብቅ "አይ ልጁስ ልክ ብለሀል! አባቴም እኮ አያቶቻችን ብሎ ሲያወራ ነው የሰማሁት" አሉንና፥ ግን ካላደረጉት ለምን ብለው ያወሩታል ይሄን ብለው ጥያቄ መልሰው አቀረቡልኝ። "እኔ እንኳን የድሮ ሰው ራስቸውንና ቤተሰባቸውን ከፍ ያደረጉና ያገነኑ ስለሚመስላቸው ይሆናል ብየ እገምታለሁ!" አልኳቸውና በተቀመጥንበት ትተውን ሄዱ።

በዚህ መሀል አንዱ ጓደኛችን ይሄ ጊዜን የኋሊት የሚመልሱት ሰውየ ጋ ለምን ሄደን አንጠይቅም ግን የምር እንደዛ የሚያደርግ አለ ግን? እውነት ይመስላችኋል? የሚል ሀሳብ አነሳ።
ጊዜ የሚመልሱ ሰውየ በአካባቢያችን አሉ " የጊዜ አለቃ " ይሏቸዋል። የኋሊት ዘመንን ጎትተው በዛ ዘመን የነበሩ ሰዎችን አነዋወር ሁሉ እንድትጠይቅ እና እንድታይ ያደርጉሃል ይባላል። ሄደን ባናውቅም። ሁላችንም በዝምታ የተስማማን መሆኑ ያስታውቃል። ልንሄድ ቀጠሮ ይዘን በዛ ቀን ከዛ ሰው ጋ ሄድን፡

የመጣንበትን ነገርናቸውና ማንን እንደምንፈልግ ሲጠይቁን ሃይሌ ቀደም ብሎ የእኔን ፥ ቅድመ አያቶች፥ ቅመ አያቶችና ቅማቶች የሰሩትን ማየት ነው ምንፈልገው፡፡ ከዛ መጡ መደዳውን ተደረደሩ ቅድመ አያቴን "ልጃችሁ ስትሞት ብቻዋን እንዳትሆን ሰው አብራችሁ ቀብራችሁላታል እንደ" ሲላቸው። አዎና ! አሉ በኩራት። እኔ ግን ወሽመጤ ስብር ብሎ ትንፋሽ መተንፈስም ተሳነኝ፡፡

እንደ መቸ ደሞ ሰው በነፍሱ ይቀበራል እንደ አላቸው። " አይ እኛ ሳንሆን ይሄን ያደረጉት አያቶቻችን ናቸው አሉ እኛ አልደረስንባቸውም አሉ! ይህን ሲናገሩ ትንፋሸ ተመለሰች። ኡፍፍ እንደት ይጨንቃል ሆሆ። ሌላውን ተወው የሳቸውን አያት ፈልጋቸው ስለው ዞር ዞር አለና አኛኛቸው። ከፊታችን አምጥቶም ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡

" እሳቸው ቆፍጠን ብለው፡ ይገርምሃል ዘራችን የባለአባት ዘር ነበር፡ እና ግን ዘራቸውን መተካት አልችል ብለው ፈጣሪያቸውን ቢማጸኑም አልሰማ አላቸው፡፡ ወይ ሰምቶ ዘገየባቸው፡ በእድሜያቸው የማታ የማታ ምን የመሰለች ቆንጅየ ሴት ልጅ በእቅፋቸው ሰጣቸው፡ አይናቸውን በአይናቸው አዩ፥ ወልደው ሳሙ፡፡ በንጉስ ስርዓት ያደገችው ልጃቸው ታድያ ለአቅመ ሄዋን በደረሰች ጊዜ የነገስታት ዘር ለሆነ ኮበሌ ታጭታ ሳለች፥ ይሄ ነው የማይባል ነገር ነፍሷን ከስጋዋ ለየው፥ ይህች ብቸኛ ልጃቸውን ሞት ነጠቃቸው። ከዛማ የናትና አባቷን ነገር አታውራው እናትና እና አባት እንደዛ ሲያዝንም ታይቶ አይታወቅም፡ ፊታቸውን ነጩትልባቸውን በጥቁር ድንጋይ ወገሩት ጸጉራቸውን ተላጩት። ግን ያችን ለአፍታ ጨለማ ዉስጥ ቆይታ የማታውቅ ልጅ ከመሬት በታች አፈር ሊያለብሷት መሆኑ ሲታወሳቸው 9 ወር የተሸከመ የእናት ማህጸን አልችል አለ፥ እንባቸው አባይን ሆነ። በዚህ መሀል አባት ብድግ ብለው ጓዶቻቸውን ጠቀስ አድርገው ጠሩና 'ልጀ ብቻዋን ቀብር አትወርድም 3 ቀን እንኳን የምታላምዳት አንዷን አብራችሁ አስገቡልኝ፥ የኔ ልጅማ ብቻዋን እዛ ጨለማ አትቀመጥም' አሏቸው። ጓዶቻቸውም ተስማምተው ከባሪያዎቻቸው አንዷን መርጠው ለ 3ቀን መቃብር እንደምትቆይ በ3ኛው ቀን ሲመለሱ ካልሞተች እንደምትወጣ ተስማምተው ጨረሱ፥ ለነገሩ መስማማት የለውም ያሏትን ነው ምታደርገው፡፡
®®®®®®®
ይሄን ሁሉ ሲያወሩ ራሴ አየር እንደሚሞላ ኳስ ሲወጠር ይታወቀኛል፥ ግን እውነቱን ልናውቅ ነውና የመጣነው ማዳመጡ ግድ ነው። " ከ. .ዛ ብለው ነገሩን ቀጠሉ፥ ከዛ ልጂቷም ተቀበረች ያች ባሪያም አብራ ትቀበረች በሶስተኛው ቀን ግን ባሪያይቱም ሞታ ተገኘች" ብለው አያቶችችን እንደ ተረት ንግረውናል። እንዲህ ያለው የባላባት ዘር ነበርን። አሉ።
®®®®®®
በጣም ተበሳጭቸ "እንደ ተረት ሳይሆን ይሄ በትክክል ተረት ተረት ነው፡ እንደ ተረት የተነገረ አይደለም፡፡ ሄይ ተነሱ እንሂድ ባክህ በዚህ አያያዝ አያቶቻችን እየተባለ አዳምና ሄዋን ጋ መድረሳችን አይቀርም። ብየ ቀድሜያቸው ወጣሁ። ስንቱ ተረት ይሆን ታሪካችን ሆኖ የተጻፈልን?ወይ ዘመን ብየ " አይ አያቶቻችን አልኩኝ"

@wegoch
@wegoch
@paappii
'የመንፈስ ችግር'
እጓለ ገ/ዮሐንስ
.
.
ነገራችን ሁሉ የእንባይ ካብ ሆነ፡፡ ታጥቦ ጭቃ መሆናችን ያስፈራኝ ከጀመረ ቆየ፡፡ ከተስፋ ይልቅ ፍርሃት ካሸነፈኝም ጊዜ ነጎደ፡፡ የእኛ ነገር ጉም እንደመጨበጥ ነው፡፡ በሀሳባችን፣ በተግባራችን የሽንፈት ሙሽሮች ሁነናል፡፡ ደንቆሮነታችን አብቦ፤ አለማወቅ ገሎናል፡፡ እንደው አለመዳናችን ለምንኖርበት ትውልድ መለያ ምልክቱ ነው፡፡
ሊቁ እጓለ ገ/ዩሐንስ ከአውሮፓ ትምህርታቸው ተመልሰው ሀገር ቤት ተገኙ፡፡ በ1953 ሲመለሱ ተስፋ ካደሩት ነገር በላይ ክፉ ያረገዘው የሀገራቸው ባህሪ እና የሰማይ ምጡ አስፈራቸው፡፡ ይህንን ጉዳይም 'የመንፈስ ችግር' አሉት፡፡
የመንፈስ ችግር ያሉት ነገር ምንድን ነው? ትናንት የመንፈስ ችግር ያሉት ደዌአችን ዛሬስ ላይ ተጣብቆብን የለም ወይ!? የትናንት ህመማችን ዛሬም ድረስ ተሻግሮ የህመምተኞች ሀገር ፈጥረናል? የመንፈስ ችግር ተብለው ከጠቀሳቸው ጉዳዬች ውስጥ አንዱ ይህ ነው፡፡
''አንድ ሰው የማይመስለውን ነገር ለማፍረስ ብቻ ይሰለፋል'' ይላሉ፡፡
ትናንት ይህ ባህሪያችን በየአምዱ ተስተውላል፡፡ ዛሬም ይህ ደዌአችን የመገናኛ መንገድን ቀይሶ እንታመምበታለን፡፡ የኛ ነው ከምንለው ሀሳብ ውጪ ለመስማት ጆሮ የለንም፡፡ መርምረን ክፉና ደጉን አንለይም፡፡ ፊደል ቆጥረናል ያሉትም አይደማመጡም፡፡ ብዙዎች ማፍረስን እንጂ መገንባትን አልተለማመድንም፡፡ የአፍራሽ ግብረ ሀይል ብዙ ነው፡፡ ሀገሪታም በዚህ ምክንያት ምጥ ውስጥ ገብታለች፡፡
ሁለተኛው የሚያነሱት የመንፈስ ችግራችን ስለ ትምህርት ነው፡፡ ''ሰው ከሙሉ የሰውነት ደረጃ የሚደርሰው በትምህርት ነው፡፡ ሰው ትክክለኛውን ትምህርት ካገኘ ለስላሳና (ኖብል) እግዚአብሄርን የሚመስል ፍጥረት ነው፡፡ ትምህርት ያላገኘ እንደሆነ ግን በምድር ካሉት አራዊት ሁሉ የባሰ ነው ብለው አበክረው ይናገራሉ፡፡''
የትውፊታዊው ትምህርት በሀገራችን የረጅም ዘመን ታሪክ አለው፡፡ በምግባር፣ በስራ ተተርጉሞ በአለማዊውም፤ በመንፈሳዊውም አለም ምስጉን ነበርን፡፡ የዘመናዊው ትምህርት መምጣት ግን የራሳችንን ውበት አስጥሎናል የሰው ወርቅ የምንናፍቅና፤ የራሳችንን ችግር በሌሎች እውቀት ለመሸንገል ዋጋ ከፍለናል፡፡ (ዘመናዊው እውቀት አልጠቀምንም እያልኩኝ አይደለም፡፡))
የትምህርት መንገዳችን ስለሌሎች የሚነግር እንጂ ለራስ የተፃፈ አይደለም፡፡ በስነ ህይወት፣ በህዝብ አስተዳደር፣ በህግ፣ በከዋክብት ጥናት፣ በህክምና የነበረንን ፅድቅ ትተን ከሰው ጓዳ ውለናል፡፡ ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ተረቱ በኛ ላይ ደረሰ፡፡ ከፈረንሳውያኑ፣ ከእንግሊዚያውያኑ፣ ከአሜሪካውያኑ የተማርነው ፈቀቅም አላደረገንም፡፡ እንደውም ጥራዝ ነጠቅ አደረገን፡፡ የራሳችን የህይወት መላ ከማበጀት ይልቅ ሌሎችን ለመምሰል በረታን፡፡ ትምህርቱ ሳይሰርፅብን፤ እውቀት ሳይደላደልብን ሌሎችን መሰልን፡፡ የራስን ጥለን የሰው አንጠልጥለን፡፡ የሀገር ቤት ትውፊታዊ እሴትን ረስተን እኔን ብቻ አልን፡፡ እኔን ብቻ ስሙ የሚለው ሀሳብም ከማህበራዊ ህይወት፣ ከፖለቲካው ተዛምቶ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነ ነገራችን፡፡ ነገራችንን አድካሚ፣ አሰልቺ ሆኖ ለስላሳ ፍጥረት ከመሆን ይልቅ ወንድም፤ በወንድሙ ላይ ተነስቶ የአውሬ ባህሪያችን በተደጋጋሚ ጊዜ ታየ፡፡ መሪር እንባን የእለት ውሎአችን ሆነ፡፡ እውቀት ሳይሰርፅብን በአብዬታውያን ወንድሞች ሀገር ጉድ ፈላባት፡፡
በሀገራችን በኢትዮጵያ ከሚያደክሙን የህይወት ህመማችን አንዱ የብሄር ትርክትና እና የዘረኝነት መንፈስ ነው፡፡ ክፉ መንፈስ ነው፡፡ ይህ የዘውጌ ሀሳብ ተመሳሳይ አእምሮ ያላቸው ሰዎች፣ ለተፎካካሪነትን እድል የማይሰጥ የሀሳብ ጭራን ይዘው ይኖራሉ፡፡ ዘረኝነት እና ብሄር ተኮር ሀሳቦች ከሌላው ወገን የሚመጣውን ሀሳብ አይሰሙም፡፡ አሸናፊ ሀሳብ ከሌላው ወገን የሚመጣ እንደሆነ አያምኑም፡፡ በንስር አይን ከማየት ይልቅ እንደ ጋሪው ፈረስ ሁናል ጉዛቸው፡፡ ይህንን በሽታችንን እጓለ ገብረዩሐንስ ''ዮሐንስ ጠምቆ ዮሐንስ ጠጣ ይሉታል፡፡'' ሀሳብ ሀገር የለውም፣ ምክንያታዊነት እና የህሊና ጉዞ ሁሉን በማከለ መንገድ የሚጋዝ አቃፊ ማንነት ነው፡፡ እከሌን የተሻገረ የሰውነት ጉዞ ነው፡፡
የመንፈስ ህመማችን ስላሳመማቻቸው መዘርዘሩን ገፍተውበታል፡፡ ነገር በብርሌ ከሆነልን ብለው ቀጥለዋል፡፡ ህሊናን እንደ አኩፋዳ ይስሉታል፡፡ በአኩፋዳ ውስጥ ጥሬውም፣ ብስሉም ይገኝበታል፡፡ ይህንን መደበላለቅ የሚያስተካክለው ደግሞ ሕግ ስነስርአት ነው፡፡ ስለ ህግና ስነስርአት ትናንትም ዛሬም ድኩማን ነን፡፡ ''ለህሊና ዋና ጠላቱ ድብልቅልቅ ዝብርቅርቅ ነገር ብቻ ነው፡፡''
የህሊናችን ዋና ጠላቶች እኛው ነን፡፡ በህግ፣ በደንብ፣ በስርአት ከመኖር ይልቅ በጉልበት፤ በማን አለብኝነት እንነዳለን፡፡ በዚህ ውስጥ በሚደርሰው ጉዳት ራሳችን እስካልተነካን ድረስ አፋችን አይከፈትም፤ እጃችን አይሰራም፡፡ እኔ ምን አገባኝ እንላለን፡፡ የወንድማችን፣ የእህታችን መነካት ግድ አይሰጠንም፡፡ የለበጣ ኑሮ አሸንፎናል፡፡ ከአንገት በላይ ኑሮን ይዘነዋል፡፡ እኔ ብቻ የሚለው ምርጫችን የዘወትር ጉዛችን እስረኞች አድርጎናል፡፡ የተረጋጋ፣ የተስተካከለ፣ ዜማ ያለው ኑሮ ያስፈራናል፡፡ በሬ ወለደ፣ ታይታ ኑሮ አሸንፎናል፡፡ ስርአትና ህግ ለሁላችን ጌጥ ይሆን ነበር፡፡
አንድ ሰው አሻግሮ ሳያይ ሲቀር፣ እስከ አፍንጫው ሲያስብ ችግር እንዳለ እናውቃለን፡፡ የኔ ትውልድ የዚህ ቀይ መብራት ነዋሪ ነው፡፡ ሀሳባችን፣ አለማችን ከአፍንጫችን አይዘልም፡፡ ድርጊታችን፣ ውሳኔአችን፣ የምንፅፈው ጉዳይ፣ ስድድባችን፣ አፀያፊ ምርጫችን የታሪካችን አንድ ክፍል እንደሆነ ረስተናል፡፡ እንደ ንፋሱ አመጣጥ ነው ጉዛችን፡፡ ህልም ያለን አንመስልም፡፡ የመንገድ፤ የመንገዱን ነው የምናስበው፡፡ ሊቁ እጓለ እንዳሉትም የመንፈስ ችግራችን ''ጎልማሳ ጦርም ሆነ ሽመል አርቆ ይወረውራል፡፡ ዓላማውን ሳይመታ ቢቀር ከክንዱ መድከም ብቻ ሳይሆን ከዓላማው ወላዋይነት ሊሆን ይችላል'' ብለዋል፡፡
እኛ እዚህ ውስጥ አናልምም፣ ለኢላማችን አንተኩስም፣ አቅሙም፣ ክህሎቱም የለንም፡፡ የእኛን የህይወት ጉዞ የሚያውቀው የነገው ንፋስ ነው፡፡ (በእውቀቱ እንዳለው!))
እነዚህ የመንፈስ ችግሮች በህይወት እኛን፤ በታሪክ ውስጥ ደግሞ ሀገር እየጎዱ ነው፡፡ እኛም ዘመናችንን እንድንባርክ፣ የታሪክ ሸክማችንን ለማቃለል ብርቱ የሆነ ጥሪ አለብን፡፡ ሊቁ እጓለ የመንፈስ ችግራችን ብቻ ሳይሆን፤ የመውጫ መንዱን አመላክተዋል፡፡ አንደኛው የመፍትሄ ሀሳባቸው ''በአሮጌ ቤት የሚኖረውን ሰው ተጠግተህ ቤትህ የማይረባ ነው ማለት አይገባም፡፡ ከበረቱ አጠገብ አዲስ ቤት መሥራት ነው ይላሉ፡፡ ይህ ሀሳብ በድርጊት ገላጭነትን ይነግረናል፡፡ ባለጌ ከማለት ይልቅ፣ ጨዋ የሆነውን ነገር አድርጎ ማሳየት፡፡ ዘረኝነት ከማስፋፋት ይልቅ፤ ሰውነትን ማበረታታትን በማሳየት አስተማሪነትን ማስፋፋት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስለ ውይይት ፈዋሽነት፤ የመንፈስ ችግርን አዳኝነት ተናግረዋል፡፡ ''አንድም ሀሳብ የመጨረሻ ነገር ነው ብሎ በተረጋገጠ መልክ አያቀርብም፡፡ በጥያቄ መልክ አቅርቦ ከተነጋጋሪው ጋር በመከራከር አብሮ ወደ እውነት ለመድረስ ይጣጣራል፡፡ እውነት በእንዲህ ያለ ዲያሎጋዊ ማህበራዊ ጥረት ብቻ የምትገኝ ነች ብለዋል፡፡''
ማህበራዊ ጥረታችን ወደ እውነት ጉዞ የሚያደርግ አይመስልም፡፡ እውነት ከተራራው ጫፍ ናት፡፡ እርስ በርሳችን ወደ ገድል ለመገፋፋት የምንጥር እንጂ፡፡ የመንፈስ ችግራችንን ተረድተን፣ በማህበራዊ ውይይት ከእውነት ታዛ ለመኖር የምንጥር ከሆነ
2024/09/24 14:30:10
Back to Top
HTML Embed Code: