Telegram Web Link
እነ አባ አይቼው
( በእውቀቱ ስዩም)
እኛ የድርሰት ስራ እምንሞክር ሰዎች ስራችን ቅጥፈት ነው፤ ስንቀጥፍ ደግሞ ቅጥፈት መሆኑን አንደብቅም፤ ግን ቅጥፈቱን ስታነቢው ፤እየተዝናናሽ እግረመንገድሺን ደሞ ቄስ ወይም ፈላስፋ የማይነግርሽን የህይወት ሀቅ ልታገኚበት ትችያለሽ’! ድርሰት ማለት እውነትን እነግራለሁ ብለው ቃል ሳይገቡ እውነት መናገር ነው!
ይህ ወግ ስለ ድርሰት አይደለም! ሀቅ እናገራለን ብለው ሚድያ ላይ ስለሚያጭበረብሩ ሰዎች ነው ፤
ባገራችን ሶስት ዋና ዋና ያጭበርባሪ መደበቂያ ዋሻዎች አሉ፤ ያገር( ወይም የብሄር)ፍቅር ስሜት ፤ ሃይማኖት እና የእድሜ ባለፀግነት!
የሌለ እየተተረተርህ ፤ ቀዳዳነትህ ላይ ትንሽ ያገር ፍቅር ነስነስ ካደረግክበት ማንም አይናገርህም፤ ለምሳሌ አንዱ ብድግ ብሎ “የጥንት አባቶቻችን ጆቢራ ተፈናጠው ጨረቃ ላይ ወጥተው እንደነበር ጥንታዊ መዛግብት ያረጋግጣሉ “ ብሎ ቢቀድ አብዛኛው እድምተኛ እልል ብሎ ይቀበለዋል፤ ላርመው ወይም ልሞግተው ብለህ ብትነሳ ባልተወለደ አንጀታቸው ያበራዩሃል ፤
የፈጣሪን ስም አብዝተህ ካነሳህ ፤ አሁንም አሁንም ከማልህ፤ ጆሮ ጭው እሚያረግ ውሸት ብትናገር የሚሞግትህ የለም፤
እንዲሁም አረጋዊ ከሆንክ፤ ጋቢ ለብሶ ደጅ ላይ ቁጭ ማለት ደረጃ ላይ ከደረስህ እንደመጣልህ መበርነን ትችላለህ ! በደንብ ተተርትረህ ከመሸበት ታድራለህ! የሆነ ሰውየ አለ ፤ በያ ትውልድ ታሪክ ውስጥ እዚህ ግባ እሚባል ሚና የለውም፤ ዋለልኝ አይሮፕላን ሲጠልፍ እሱ ካፌ ቡሌ ሲጠልፍ ነበር! አሁን መቸም ሙታን ተነስተው፤ አይመሰክሩኝም ብሎ ነው መሰል በየሚድያው ቻክኖሪስን የሚያስንቅ ገድሉን ሲቀድ አየዋለሁ !
ድሮ በልጅነታችን ወላጆቻችን አደብ ሊያስገዙን ሲፈልጉ “ አባ ጅቦ መጣልህ “ ይሉን ነበር፤ ከዚያ ጎለመስን ! አያጅቦ መጣልህ በadult version “ ኢሉምናቲ እና 666” ሆኖ ከች አለልን ! ባለፈው አንዱ ጉድ፤ ቻናሉ ላይ ላይቭ ተጎልቶ “ ላይቭ ላይ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ሰዎች ትታዩኛላችሁ ፤ ወይ አንድ ሰው ይቀነስ ! ወይ አንድ ሰው ይጨመር! አለበለዚያ ልቀጥል አልችልም”፤ ሲል አየሁት !
ሰፊው ህዝብ ደሞ ኑሮው የፈጠረበት ፍርሃት ሳያንሰው እኒህ ፍሪኮች የፈበረኩትን ፍርሃት እየተበደረ ይቦካል! ኮሮና በቢልጌትስ የተፈጠረው በክትባት ሰበብ አእምሮአችን ውስጥ ቺፕስ ለማስቀመጥ ነው ይልሃል ደሞ ! ባለቺፕሱ ምን አጠምድ ብሎ ነው አንተ አእምሮ ውስጥ ቺፕስ እሚያስቀምጠው? ለቺፕሱም ይታዘንለት እንጂ!
ደብረ ማርቆስ ውስጥ፤ ድሮ፤ አንድ ሰው አገር እሚያስለቅቅ ውሸት ከተበረነነ “ አባ አይቼው “ የሚል ቅፅል ይሰጠው ነበር ፤ አባ አይቼው በቀዳዳነት ክብረወሰን የሰበረ ሰው ነበር ፤ ” አንድ ቀን ቀዳማዊ ሃይለስላሴ በመኪና ሲሄዱ አዩኝና መኪና አቁመው ሊፍት ሰጡኝ፤” ብሎ ላንድ ጠላ አጣጩ ነገረው ፤ እዚህ ላይ ቢያቆም ጥሩ ነበር ፤ “ የሁዋላ በር ከፍቼ ልገባ ስል “ ቀጠለ አባ አይቼው “ ጃንሆይ አጠገባቸው ወደ ተቀመጠችው ምሽታቸው እየተመለከቱ ፤አይቼው ጋቢና! መነን ወደ ሁዋላ ብለው ትዛዝ ሰጡ፤”
ሀሰት የሚወገዝበት ዘመን ነበርና የአባ አይቼው ተወግዘው ቀልለው ሞቱ፤ ዛሬ ቢኖሩ ኖሮ በየቻናሉ እየቀረቡ እንደ ልባቸው ተረርር እያደረጉ ከብረውና ተከብረው ይኖሩ ነበር
.
@wegoch
@wegoch
#የሰኔ መቅሰፍቶች

ክፍል -፯

የሰኔ ወር ሊያልቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል ከሰምኑ ትልቅ ሰላም ቢሰማቸውም አሁን የመጨረሻዎቹ ቀናቶች ሙሉ በሙሉ መቅሰፍቱን ይዘው እንደሚመጡ ገምተዋል
ሰውነታቸው መንምኗል ፊታቸው ገርጥቷል
ከቤተሰቡ ሁሉን የረሳችው ፊያሜታ ትመስላለች የሆነ አካል ሹክ ብሎ እንደነገራት ልቧ አምኗል
መቅሰፍቱ አልፏል
ካላለፈም ያው እንደተለመደው.....
ዛሬም ቤተሰቡ ሰብሰብ እንዳለ ነው
ዜናው ወሬው ሁሉ ጨረቃ ስልጣኗን ስላሳየችበት ግርዶሽ ሆኑዋል
ዛሬም ነግቶ መጨለሙ ከንደ አዲስ ይወራ
ቤተሰቡም ነግቶ ሲጨልም የኛም ነገር አከተመ ብለው ከሽብር ገብተው ነበረ
ጨረቃዋ ፀሀይን ጋርዳ ቀስ ብላ ቦታዋን ስትለቅ ቤተሰቡም ባልጠበቀው ደስታ ውስጥ እራሱን አጊቶታል
ያቺ እንደ ሶስት አመት የረዘመችው ሶስት ሰአት ግን ከማንም ሰው ትዝታ ውስጥ አጠፋም
ፊንሀስ የግርዶሹ ለት ከመፈጸሙ ከአንድ ቀን በፊት የነበረውን ሁኔታ እያስታወሰ ስቅቅ እስኪለው ይረብሸዋል የህይወት ነገረም ምን ያህል አስፈሪ ነገር እንደሆነ ሲያስብና ጭንቀቱ ምን ያህል እንደ ነበረ ሲያስብ ፈገግ ይሰኛል ሰውነቱን ለቀቅ አድርጎ ተመልስ ያስታውሰው ጀመር
ቤተሰቡ ሙሉ በሙሉ የመቅሰፍቱ ቀን መድረሱና ከግርዶሹ ጋ በቀጠሮ መምጣቱን አምነው ተቀብለዋል
ነገ ተመልስ ጨልሞ ይበራል ያንን ብርሀን በአይኔ አየው ይሆን....
ጭንቅላቷን እግሮቿ ውስጥ ከታ እግሮቿን በእጆቿ ጥብቅ አድርጋ ቆልፋቸዋለች
በቃ ሊያልቅ ነው ሊያበቃ ነው...
የተደፋችበት ሰአት ከመርዘሙ የተነሳ ሰውነቷ እርስ በራሱ ተሳስሯል ፀጉሯ ተነቃቅሎል የፊቷ ንዳድ እራሶን እየሰበቀ ይለበልበው ጀምሯል
ሲነጋ ያበቃል ነገ ከጨለመ ለኛ ቤተሰብ አይነጋም ያበቃል ፊያሜታ ከአልጋው ጀርባ ተጣብቃ ምሽቱን በእንባ እያሳለፈችው ነው
ቤተሰቡም ልጆቹን ይዞ ከነሱ ጋር የመጨረሻውን ምሽት ለማሳለፍ ወስኗል
የሁሉም ልብ በአንድ ሆኖ ለነገው ይመታል
በግድ የሚከፈቱ ጥርሶች ህፃናቱን በትንሹም ቢሆን ደስ አሰኝቷቸዋል
ፊንሀሴ በሀሳብ አለም ውስጥ ያለበትን ቦታ እረሴቶታል
ከእግሮቹ በላይ ሀሳቦቹ ስለፈጠኑበት እግሮቹኔ ማቆም አልቻለም
ዛሬ ከቤቴ ብወጣ ምንም አልሆንም ነገ ናት የኔ ቀን ዛሬን በምንም አልሆንም ተስፋ ከቤቱ ወጥት ጉዞውን ጀምሯል
አሁንም ይሄዳል አንገቱን ከግራ ወደቀኝ እየመለሰ በመስኩ መሀል ይራመዳል
ነገ የሚወዳት ጨለማ ፀሀይን ስትጋርድ ለቤተሰቡሜ ትልቅ ፅልመት ይዛ እንደምትመጣ አውቋል
አሁንም ግን ይወዳታል ከመስኩ አይኖቹን አንስቶ ጨረቃን ከሰማዩ ፈለጋት በዳመናው የጠቆረው ሰማይ መጣው መጣው ሚለው ዝናብ በመብረቁ መምጣቱን ሲያስገመግም ፊንሀስንም ከሀሳቡ አነቃው
ትንፋሹን ሀሳቡ የያዘበት ይመስል ወደ ውስጥ አየር ስቦ በረጅሙ ተነፈሰ
ብዙ እንደተጓዘ አውቋል ምሽቱሜ ለአይን መያዝ ጀምሯል
ተመልሶ ዞሮ ወደ ቤተሰቡ ገሰገሰ
ምን አልባት የሚራመድባት መስክ ለመጨረሻ ጊዜ የሚጓዝባት መንገድ ትሆናለች
ዝቅ ብሎ የመስኩኔ ሳር በእጁ ዳበስ አደረገው ስንብት መሆኑን ሳሩም ሳያውቀው አልቀረም
ነገ ነግቶ ሲጨልም ለቤተሰ በእርግማኑ ለተመረጡ ሰዎች የዘላለም ፅልመትን ያለብሳል
ፊያሜታ ባለችበት ዘንበል ብላ ከወለሉ ላይ ጋደም ብላለች
ፊንሀስም ከጉዞው ሲመለስ ያልጠበቀው ፀጥታ አስገርሞታል
ሁሉም ለትልቁ ሞት ልምምድ እንዲሆነው በትንሹ ሞት ውስጥ መቆየትን መርጧል
ፊንሀስም ወደ አልጋው ሄደ
የእህቱ እግሮች የአልገረውን ጫፎች አልፈው ተመለከታቸው
እሱም ከወለሉ ጋደም ብል ትንፋሿን ይቆጥረው ጀመር
አይንቹ ክድን ሲሉ ቁጥሮቹም አቆሙ

ይቀጥላል.....
ብላቴናው በእርግማን ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ምንምነት ውስጥ ምንም ነገር አለ።


ሀሳብ አለ።
… እሚታሰብ እሚንሰለሰል ። ሳትፈልገው ሚፈልግህ…… ሳታልመው
እሚያልምህ…… በአንተ ዙሪያ እየዘወረ እሚዘውረወህ…… ሀሳቡን
ተረድተህ ለመሰደር ብትባዝንም ምንጩንና ፍንጩ የማይገለጥልህ
ግዜ አለ……… ታወጣ ታወርድና ይህን ሀሳብህን ለሚካፈልህ ጓደኛ
ትሻለህ… …ለመረዳት ሀሳብህን ለመካፈል የመጣው ጓድህ " ምን
ገጠመህ ጓዴ? " ይልሀል። የገጠመህ እክል አታውቀውም ግን
ጨንቆሀል……ግን ደብቶሀል…… ግን ያባዝንሀል…… የተምታታ ስሜት
ውስጥህ ሰርፇል። እንዲህ ነው ብለህ ተንፍሰህ ነገሩን ሀሳቡን
ማቅለል ያዳግትሀል።

……ያሳለፍካቸውን ቀናት እየተመለስክ ውሎህን አዳርህን
እያስታወስክ የተገበርካቸውን ትሰልላለህ ። ምንም አታገኝም ወይም
ከስሜቱ ጋር እየታገልክ መንስኤው ይጠፋሀል። ዝም ብሎ ውስጥህ
ይነጫነጫል ንጭንጭህን ተባዕት ወይም እንስት በታገኝ
አግኝተውህ የውስጥህን ስላልተነፈስክ ይከብዳቸዋል።እንዲህ
ይገጥማል ሀቅ ነው ። መንስኤ አለው ወይም ደርሰህ ተደብተሀል።፤

☞ ………ምንም ባልነው ነገር ምንም ያላልነው ነገር ይፈተላል።
ምንም ማለት ባዶ አይደለም ባዶ ያልነውም ምንም አይደለም ማለት
አይደለም። ባዶነትም አንድ ምንነት ነውና።ግን ምን ሆኛለሁ? ምንም
አልሆንኩም አልልም ባዶ ሆኛለሁና።

እናም
☞ ማንኛውም ሀሳብ ሀሳብ ሆኖ… ሀሳብነቱ ገዝፎ ሀሳብን አጨንግፎ
እሱ ሲያንሰራራ… …አንሰራርቶ ሀሳብ ሀሳብነቱን የሚረዳ ሀሳቡ
ደርሶበት ያረፈበት ሰው ላይ ነው።

ደግሞም
ምንም ነገር ውስጥ ምንም ነገር አለ
ምንም ነገር ያለምንም ነገር አይነሳምና።

@wegoch
@wegoch
አንድ ቀን አንድ ወጣት ወደ አንድ አገር ለመሄድ በጉዞ ላይ ሳለ
ምሽት አሸነፈውና በጅብ ከመበላት ብሎ ከፊት ለፊቱ
የምትታየው ትንሽ መንደር አመራ ከመንደሩ ደርሶ "የመሸብኝ
እንግዳ ነኝ አሳድሩኝ?" ሲል ይማፀናል።
የቤቱን ባለቤት አብርሃምን መሆን የሚጥር እንግዳ ተቀባይ
ነበርና "ይግቡ" በማለት እንግዳውን ወደ ጠባብ እልፍኙ
ይጋብዘዋል። ወጣቱም ወደ ቤት ገብቶ ትንሽ እንዳረፈ ለእግሩ ውሀ
ተሰጥቶት ከታጠበ ብኋላ እራት ይቀርብለትና ይበላል።
የቤቱ ጌታ ለወጣቱ ልጅ መኝታ ሲያስብ የመኝታ ቦታ ስለሌለ ትንሽ ጊዜ
ያስብና አንድ ሀሳብ ይመጣለታል። ይህም ሃሳብ ሌላ አማራጭ ስለሌለው
ከልጃገረድ ልጁ ጋር እንዲተኛ ይወስናል። "እንግዳው ልጄ እዚህ አልጋ
ላይ ከልጄ ጋር ተኛ" ይለውና አልጋውን ሁለት ቦታ በትራስ ይከፋፍልና
ያስተኛዋል።
እንግዳው ልጅም በተመደበለት ቦታ አንድ ጊዜ እንኳን ሳይንቀሳቀስ ለሊቱ
ነጋ። ጠዋት ቁርስ በልቶ ከቤት ተሰናብቶ መንገዱን ሲቀጥል
ማታ አብሯት የተኛችው ልጅ አበባ ስትኮተኩት በአጥር ያያታትና
"እህት መሄዴ ስለሆነ በአጥር ዘልየ ልሰናበትሽ" ሲላት
ትሰበራለህ ስትለው "ግድ የለሽም አልሰበርም" ይላታል።
ልጅቱም "እህ.... ማታ ትራስ መዝለል ያቃተህ አሁን እንዴት
አጥር ልዝለል ትላለህ?" ትለዋለች
:
አንዳንድ ሰዎች አለመቻልና መተው ሲደባለቅባቸው አያለሁ።
መተው አለመቻል አይደለም። ሰው የቻለውን ሁሉ አያደርግም
ማድረግ ያለበትን ብቻ ነው ማድረግ ያለበት። የሚችለው ነገር
ቢሆን እንኳ ማድረግ ከሌለበት ይተወዋል። ያቅተዋል ሳይሆን
ይተወዋል ብሎ ይመልስላታል።
.
ምን ለማለት ፈልጌ ነው
:
:
:
ያ እንግዳ አክባሪ ሰው ያሰመረው ትራስ የእምነት መስመር
ነው። የመታመን አጥር ነው። አጥሩ ይርዘምም ይጠር ብቻ
ታጥሯል። ያንን አጥር ማክበር የእምነት ወሰንን አለማለፍ እንጂ
አለመቻል አይደለም።
.
ሰው መጮህ ስለቻለ ዝም ብሎ አይጮህም፣ሰው መሳቅ ስለቻለ
ያለ ምክንያት አይስቅም፣ሰው መልበስ ስለቻለ ያገኜውን
አይለብስም . . . ለራሱ በተረዳውና ባመነበት መንገድ መስመር
ያበጃል። ካሰመረው መስመር ላለማለፍ የሚችለውንም
ይተዋል።
ማድረግ ስላልቻለ አይደለም መስመር ማለፍ ስላልፈለገ ነው
እንጂ ! ! !

@wegoch
@wegoch
@wegoch
🏹🏹🏹🏹🤺🤺🤺🐅🐅🐅🐅🐅

🔱አንድ ንጉስ ከ አጃቢው ጋር በመሆን ለ አደን ይወጣል። ለ አደን ሲወጡ ንጉሱ ወጥመድ እያጠመደ እያለ ወጥመዱ አምልጦት እጁን ቆረጠው።
በዚህም አጃቢው በማዘን "አይዞህ ንጉስ ሆይ ሁሉ ነገር ለበጎ ነው!" ይለዋል።
በዚህም ንጉሱ በንዴት እየጦፈ "የኔ እጅ መቆረጥ ነው ለበጎ?" ይለውና እስር ቤት ያሳሰረዋል።
ከብዙ ጊዜ በሗላ ንጉሱ ብቻውን ለአደን እራቅ ብሎ ወደሚገኝ ጫካ ሄዶ በአደን ላይ ሳለ ሰው አርደው ለጣዖት መሰዋት የሚያደርጉ ጨካኝ ሰዎች ይይዙትና አርደው ለጣኦታቸው መሰዋት ሊያደርጉት ሲሉ ቆራጣ እጁን አዩት።

በእነሱ ህግ መሰረት መሰዋት የሚያደርጉት ሰዉ ሙሉ ጤነኛ መሆን አለበት፡፡ በዚህም እየተናደዱ ለቀቁት።
ንጉሱ አጃቢው ያኔ 'ሁሉ ነገር ለበጎ ነው! ያለው ትዝ አለው' እየሮጠም ወደ አጃቢው እስር ቤት ሄዶ ስላሰርኩክ ይቅርታ አርግልኝ!.......... ብሎ ታሪኩን አጫወተው።
አጃቢውም "ማሰርክ ለበጎ ነበር! እኔም መታሰሬ ጠቅሞኛል።" አለው።
ንጉሱ-"እንዴት?"
አጃቢ-"ባልታሰር ኖሮ ከአንተ ጋር እሄድ ነበር ከዛ የያዙክ ሰዎች አንተ ቆራጣ መሆንህን ሲያውቁ ይለቁህና አኔን አርደው መሰዋት ያረጉኝ ነበር"አለው።

ባለን አመስግነን የተሻለ ለማግኘት ስንጥር የሚገጥሙንን ውጣ ውረዶች ይበረቱብን ይሆናል። ይሄ ደግሞ ያለ እና ለእና ብቻ የሚሆን አይደለም። ስለሆነም በማማረር ፈንታ 'ነገር ሁሉ ለበጎ ነው' ብለን ውጣ ውረዱን በፅናት እንለፍ።
😊😊😊 ፅኑአን እንሁን😊😊😊

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ከስራ በሁዋላ አየሁዋት ሄድኩና"
(በእውቀቱ ስዩም)
ኢትዮጵያ ውስጥ ስራ እንዲከበር ያደረገ ደርግ ነው፤ ከዛ በፊት ስራ የተናቀ
ተግባር ነበር፤
“ዋይ ዋይ ባላባት
እንግዲህ ቀረ ሳይሰሩ መብላት “ ይሉ ነበር የዩኒቨርስቲ ፋኖዎች!
ደርግ ስራን አስከበረ፤ አንዳንዶች እንደውም ባንድ ጊዜ ሁለት ስራ ደርበው
እሚሰሩ ነበሩ ! ለምሳሌ አትሌት ምሩፅ ይፈጠር ሩጫ ልምምድ ሲያደርግ
እግረመንገዱን በየቤቱ ፖስታ ያድል ነበር! በደርግ ብር ኖቶች ላይ ያሉትን
ምስሎች ተመልከቷቸው ! ሰፌድ የምትሰፋ ሴት፤ የሚመራመር ሳይንቲስት ! ቡና
የሚለቅም ገበሬ! የቦዘነ የለም!
መንግስቱ ሃይለማርያም እልል ያለ አምባገነን ነበር ፤ በስራ ግን ቀልድ
አያውቅም! የሆነ ጊዜ ላይ መንጌ፤ አለማየሁ እሸቴንና ጥላሁን ገሰሰን ወደ ቢሮው
አስጠራቸው !
“ ወጣት አለማየሁ! “
“አቤት ጓድ ሊቀመንበር “
“እጅ እግሩ ተቆርጦ አከላቱ ጎሎ
ይኑር አባብየ እየበላን ቆሎ
አርባራቱን ታቦት ጠርቶና ለምኖ
ብለው የዘፈንከው ምን አስበህ ነው? አባትህ ካልሰራ ማን የቆላውን ቆሎ ነው
የሚበላው?"
“ ጓድ ሊቀመንበር ይሄን ዘፈን የዘፈንኩት ካብዮቱ በፊት ባድሃሪው ስርአት ውስጥ
ነው! አሁን ንቃቴ ከጨመረ በሁዋላ የገዛ ዘፈኔን ሳደምጠው ሼም
ይጨመድደኛል” አለ አሌክስ ዞማ ፀጉሩን በጣቶቹ እየቆፈረ !
“ ሂስህን ከዋጥህ ላይቀር፤ ነገሮችን አስተካክለህ ብትዘፍነው ምን
ይመስልሃል?”
“ ጥሩ አሳብ ነው ጓድ ሊቀመንበር ! ምኑጋ ላስተካክለው? ”
መንጌ በመስኮቱ አሻግሮ ትንሽ ሲያስብ ከቆየ በሁዋላ ፤” እጅ እግሩ ተቆርጦ
የሚለው ስንኝ በጣም ዘግናኝ ነው ! የምር አባትህ ከሆነ ትንሽ አስተያየት
አድርግለት ! ወይ እጁን ወይ እግሩን አስቀርለት ! "
“ የትኛውን ላስቀርለት?” አለ አሌክስ !
“ እንደኔ እንደኔ እጁን ብታስቀርለት ጥሩ ነው፤” ቀጠለ መንጌ
” የለመነውን ቆሎ ለመያዝ ራሱኮ እጅ ያስፈልገዋል፤ እንደ ሁኔታው አይተን፤
ብሄራዊ ውትድርና ላይም ልናሳትፈው እንችላለን ፤ ሻእቢያ ናቅፋ ላይ የረፈረፈችን
እግር የሌላቸው ሸሽተው እማያመልጡ ወንበዴዎችን የቀበሮ ጉድጏድ ውስጥ
ወትፋ ነው፤ ‘ ይገርምሃል መጀመርያ ፈንጅ በእግራቸው ያስጠርጏቸዋል! ከዛ
ደግሞ በባሊ ተሸክመው ወስደው ሽምቅ ውጊያ ላይ ያሰማሯቸዋል! አገር
መገንጠል የተለማመዱት የገዛ ወንድሞቻቸውን እግር በመገንጠል ነው!
ርጉሞች!"
ቀጥሎ መንጌ ወደ ጥላሁን ገሰሰ ዞር ብሎ " እሺ ጃል ጥላሁን! ወዳንተ
ስመለስ፤
" ያላየሁሽለታ በማዘን፤ በጭንቀት በድቀት ተክዤ
ሌሊቱን ሳልተኛ እያደርኩኝ፤ ቀኑን እውላለሁ ፈዝዤ "
ብለህ የዘፈንከውን አዳምጫለሁ! አሁን ያለንበት ሁኔታ የሙሉ ጊዜ አፍቃሪነትን
የምናበረታታበት አይደለም!! ወጣቱ ቀን በስራ ተስማርቶ ማታ ላይ በሃሳብ
መፍዘዝ መብቱ ነው! በተረፈ ኢትዮጵያ ሌትም ቀንም በፍቅር የሚጃጃል ወጣት
የምትሸከምበት ጫንቃ የላትም! የወዝ አደር እንጂ የውዝዋዜ አደር ፓርቲ
ለመገንባት አልተነሳንም! ተግባባን?”
ከጥቂት ሳምንታት በሁዋላ ጥላሁን ገሰሰ “ ፈልጌ አስፈልጌ “ የሚለውን ዘፈን
ሰራ! ዘፈኑ የመንጌ ተፅእኖ እንዳለበት ለማወቅ እኒህን ስንኞች ብቻ ማየት
ይበቃል!
“ አየሁዋት መርካቶ ሲሉኝ ትናንትና
ከስራ በሁዋላ አየሁዋት ሄድኩና
ከስራ በሁዋላ ብቅ ብል በማታ
የለችም ካዛንችስ እሱዋ የት ተገኝታ
እሷ የት ተገኝታ

@wegoch
@wegoch
@paappii
ከየት እንጀምር ?
#ዳንኤል ክብረት)
.
ወዳጄ ሆይ ለምን ከሌለህ ነገር ትጅምራለህ? በሰው ላይ ኀዘን የሚጨምረው፣ ተስፋ መቁረጥም የሚያደርሰው፣ የበታችነትንም የሚያመጣው፣ ቅዠትንም የሚያባብሰው ከሌለ ነገር መጀመር ነው፡፡ እስኪ ራስህን አስበው? ስላላገኘሃቸውና ስላልደረስክባቸው፤ ስላመለጡህና ስላልተደረጉልህ ነገሮች ከማሰብ በእጅህ ስላለውና ስለደረስክበት ነገር ለምን አታስብም፡፡
በአንተ እጅ ያለው ነገር በአንተ እጅ ከሌለው ነገር ይበልጣል ወይስ ያንሳል? በእጄ ያለው ትንሽ ነገር ነው፣ በእጄ የሌለው ግን ዓለም በሙሉ ነው፤ ታድያ እንዴት በእጄ ያለው በእጄ ከሌለው ነገር ሊበልጥ ይችላል? እንደምትል አይጠረጠርም፡፡ ሲገመትም እንደዚያው ነው፡፡
እንደ እውነቱ ግን በእጅህ ያለው ነገር በእጅህ ከሌለው ነገር ይበልጣል፡፡ እንዴት? አልክ፡፡ በመጀመርያ ደረጃ በእጅህ ያለው ነገር ያንተ ነው፡፡ በእጅህ የሌለው ግን ገና ያንተ አይደለም፡፡ ያንተ የሆነው ያንተ ካልሆነው ነገር ይበልጣል፡፡ ምክንያቱም ያንተ በሆነው ነገር መጠቀም ትችላለህ ያንተ ባልሆነው ነገር ግን ልትጠቀም አትችልም፡፡ ያንተ በሆነው ነገር ልታዝዝ ትችላለህ፤ ያንተ ባልሆነው ነገር ግን ልታዝ አትችልም፡፡ ያንተ የሆነውን ነገር ማግኘትህን ርግጠኛ ሆነሃል፡፡ ያንተ ያልሆነውን ማግኘትህን ግን ርግጠኛ መሆን አትችልም፡፡ ያንተ በሆነው ነገር ልትወስንበት ትችላለህ፤ ያንተ ባልሆነው ነገር ግን ልትወስን አትችልም፡፡ ያንተ የሆነውን ነገር ለሌላው መስጠት ትችላለህ፤ ያንተ ያልሆነውን ግን መስጠት አትችልም፡፡ ካለህ ነገር ላይ ቆመህ የሌለህን ማየት ትችላለህ፤ ከሌለህ ነገር ላይ ቆመህ ግን ያለሀን ነገር ማየት አትችልም፡፡
እናም ወዳጄ ስትቆጥር ካገኘኸውና ከሆነልህ ነገር ጀምረህ ቁጠር፡፡ ባላገኘኸው ነገር ከምትበሳጭ ባገኘኸው ነገር ተደሰት፡፡ ባልሆንከው ነገር ከምታዝን በሆንከው ነገር ሐሴት አድርግ፡፡ ባልያዝከው ነገር ከመበሳጨት በያዝከው ነገር ሥራበት፡፡ ባልሆንከው ማንነት ከመቃዠት በሆንከው ማንነት መኖር ጀምር፡፡
ይህ ማለት ምን ይመስልሃል?
ስትጓዝ እያረጋገጠክ ተጓዝ፡፡ መጀመርያ ያለህን ዕወቀው፣ ከዚያም ባለህ ነገር ምን ያህል እንደ ተጠቀምክበት ርግጠኛ ሁን፡፡ ላለህ ነገር ዋጋ ስጠው፡፡ ያንተ የሆነውን ነገር አክብረው፡፡ ያን ጊዜ የሌለህን ታገኘዋለህ፡፡ የሌላውን ሰው ትዳር አይተህ፣ እርሱን ተመኝተህ፣ እንደዚያ በሆንኩ እያልክ በሌለህ ነገር ከማዘን፤ እስኪ በአንተ ትዳር ውስጥ ምን መልካም ነገሮች አሉ? የትኞቹን ተጠቅመህባቸዋል? የትኞቹን አድንቀሃቸዋል? ለየትኞቹስ ዋጋ ሰጥተሃቸዋል፡፡ የሌለህን ብቻ የምታይ ከሆነ ያለህን ማወቅ አትችልም፡፡ ስለ ሌለህ ነገር ብቻ የምታስብ ከሆነ ባለህ ነገር መጠቀም አትችልም፡፡ አሁን የምትሠ ራበትን ሞያ ወይም ቢሮ ወይንም መስክ በሚገባ ተጠቅመህበታል? ሠርተህበታል? ከዚያስ ማግኘት ያለብህን አግኝተሃል? ወይስ ሌላ ሞያ የምትፈልገው፣ ሌላ ቦታ መቀጠርም የምትመኘው፣ ሌላስ መስክ ላይ መዋል የምትጓጓው ሰዎች አደረግነው ሲሉ ስለሰማህ ነው፡፡
ብዙ ሰዎች ታች ከፍል በተማሩት ምንም ሳይሠሩበት ወደ ላይ ይወጣሉ፡፡ በመጀመርያ ዲግሪያቸው አንዳች ሳይፈይዱ ሁለተኛና ሦስተኛ ይይዛሉ፡፡ አኗኗራቸውንና አስተሳሰባቸውን ስታየው ግን ታች ክፍል ናቸው፡፡ ለምን ይመስልሃል? መጀመርያ በያዙት ነገር ሳይረኩና ሳይጠቀሙ፣ የያዙትን ነገር ፈጽመው ማወቃቸውን ሳያረጋግጡ ሰው ስላደረገው ብቻ ሌላውን አደረጉ፡፡
በቤታችን ውስጥ ይህኮ የለንም ብለን የገዛናቸው የማንጠቀምባቸው አያሌ ዕቃዎች አሉ፡፡ በየቁም ሳጥናችን ውስጥ ስለሌለን ብቻ የገዛናቸው የማንለብሳቸው ብዙ ልብሶች አሉ፡፡ ምናልባት ግን እነርሱን ከመግዛታችን በፊት ምን እንዳለን ብናስብ ኖሮ እነርሱን የሚተካ ወይንም የሚያስከነዳ ነገር በቤታችን ነበረ፡፡ እስኪ ሰዎችን ስማቸው፡፡ እዚህ መሥሪያ ቤት የተቀጠሩ የሚሠሩበትን እያማረሩ ያኛውን መሥሪያ ቤት ያደንቃሉ፡፡ እዚያ ያሉት ደግሞ ያሉበትን እየረገሙ እዚህ ያለውን ያመሰግናሉ፡፡ ለምን? ሁሉም ሌላ ያያሉ እንጂ ያላቸውን አያዩም፡፡
የት እንደምትሄድ ሳታውቅ አትሂድ፡፡ የት እንደምትሄድ ለመወሰን ደግሞ ከየት እንደተነሳህ ማወቅ የግድ ነው፡፡ ምናልባትምኮ አለመሄዱ ከመሄዱ የተሻለ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዴት መሄድ ብቻውን ዓላማህ ይሆናል? ለአንዳንዶች መማር ብቻ ዓላማቸው ነው፡፡ ለአንዳንዶች ደግሞ ማግባት፡፡ ለአንዳንዶች መነገድ፡፡ ለአንዳንዶች ውጭ ሀገር መሄድ፡፡ ለአንዳንዶች ቤተ ክርስቲያን መሄድ፤ እነዚህ መንገዶች እንጂ መድ ረሻዎች አይደሉም፡፡ ሰውዬው መንገድ ሲሄድ አንድ ሽማግሌ ያገኛል፡፡
«አባቴ ይኼ መንገድ ይወስዳል?» ይላቸዋል፡፡
«የት ለመሄድ ፈልገህ ነው» አሉት ሽማግሌው፡፡
«የምሄድበትን አላውቀውም» አላቸው፡፡
«የምትሄድበትን ካላወቅከውማ የትኛውም መንገድ ይወስድሃልኮ» አሉት ይባላል፡፡

@wegoch
@wegoch
በእንተ ዲያስፖራ
(በእውቀቱ ስዩም)
ዲያስፖራ አይደለሁም፤ተመላላሽ ነኝ፤ “ ሲራራ “ የሚለው መጠርያ ይገልፀኛል::
እኔ እንደታዘብኩት ፤ዲያስፖራ ሁሉ አንድ አይነት አይደለም፤ መአት አይነት
ዲያስፖራ አለ! ለዛሬ ዋና ዋናዎቹን ላስታዋውቃችሁ !
የመጀመርያው ክፍል አድፋጭ ዲያስፖራ ነው፤ አሳምሮ የተማረ፤ ዘናጭ ስራ
ያለው፤ ፖለቲካን የሚያውቅ ግን በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ ውቃቤው
የማይፈቅድለት ! ወይ በእምየ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ተስፋ የቆረጠ ! የራሱን እና
ያገር ቤት ዘመዶቹን ኑሮ ከማቃናት የዘለለ አላማ የለውም ፤ ሰልፍ ላይ
ብትጠሪው አይመጣልሽም ! አበሻ ሬስቶራንት ብዙ አይታይም! እንጀራ ሲያምረው
ተራርቆ ያዝዛል ! ደፋሮች መድረክ ላይ አንፈራጥጠው ፤ ማይክ አንቀው ሲቀደዱ
ጥግ ይዞ እያየ ይስቃል፤ወይም ያሽሟጥጣል ! ለትምርት ቤት ፤ ለላይብራሪ
ወይም ለመጠጥ ውሃ ማሰርያ ካልሆነ በቀር መዋጮ አይሳተፍም ! ቁጥሩ ብዙ
ነው፤ግን በቀላሉ አይታይም!
ሁለተኛው መደብ የቱግ ቱግ መደብ ልንለው እንችላለን ! አልተማረም ! ወይ
ተምሮም ትምርት አልዘለቀውም! ግንባሩ ላይ ነጥሮ ተመልሷል! እድል፤
ከውልደት ወደ ስደት በቀጥታ የገፈተረችው ነው ! አዲሳባን እንኳን በቅጡ
አያውቅም! ፤ በቀጥታ ከይፋትና ጥሙጋ ወይም ከጭላሎ አሜሪካ ወይም
አውሮፓ የገባ ሊሆን ይችላል ! ከሩቢላ እንደወረደ የሰፈሩ ሰዎች ወይም ዘመዶቹ
ይቀበሉታል፤ እዛው ሰፈራቸው ውስጥ ማደርያ ይፈልጉለታል፤ ከዛ እዛው ሰፈሩ
ውስጥ ሲጥር ሲግር ኖሮ አርጅቶ ይሞታል! ሰፊውንና ውስብስቡን የኢትዮጵያ
ማህበረሰብ የማወቅ እድል አልነበረውም ! ስለዚህ ስለሌላው ህብረተሰብ
ያለው እውቀት ካሉባልታና ከሚድያዎች ቀደዳ የተቃረመ ነው !
በኑሮ ቺስታ ሊሆን ይችላል! ቤቱ ገብቶ “ ምን ይዤ ልመለስ ወደ ናቴ ቤት “
የሚለውን በድብቅ ያንጎራጉራል! አገሩ መግባት እንደማይችል ስለሚያውቅ አገር
ቤት ያለውን ሰው ሲያስብ ደሙ ይፈላል! አገር ቤት ያለው ሰው ድርሻውን
የወሰደበት ይመስለዋል! ፤ከእሱ ቡድን ውጭ ያለውን ከማርስ እንደወረደ እንግዳ
ፍጡር ይመለከታል ! የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ስትጠራው ሁለት ሰአት ቀድሞ
ይደርሳል፤ ! ባንዲራ በየአይነቱ- በጨርቅ መልክ፤ በፈሳሽ መልክ ሳይቀር
ሊኖረው ይችላል! ኑሮው እሮሮ አንደበቱ ተናዳፊ ነው! ዲያስፖራ ከሚባል”
ዳሞትራ “ ቢባል በደንብ ይገልፀዋል!
ብዙ ጊዜ ሚድያዎችን የሚያጣብበው በዚህ ምድብ ውስጥ ያለው ነው !
እንግዲህ ሁኔታውን አይተህ፤ ፍረድበት ፤ወረድበት፤ ወይም እዘንለት!
ምራቂ፤
ያገር ቤት ነዋሪ በዲያስፖራ ሲናደድ “ እዛ በርገርህን እየገመጥህ እኛን
ታፋጀናለህ ይላል! የማፋጀቱን ምንጭ ከላይ ጠቅሻለሁ:: አሁን የበርገሩን ነገር
ልናገር!
ብዙ ተመላልሻለሁ ! በርገር የሚበላ ዲያስፖራ አንድ ቀን አይቸ አላውቅም፤
እንዲያውም ከዲሲ ከቶሮንቶና ከአምስተርዳም በላይ በርገር የምትቀለብ ከተማ
ብትኖር አዲሳባ ናት
ኮረና ጭር ሳያደርጋቸው በፊት፤ ውሃ ልማት ፤ ቦሌ መድሀኒያለም እና ገርጂ
ውስጥ የተከፈቱ ቀያይ በርገር ቤቶች በደንበኛ ተጨናንቀው ጠጠር መጣያ
እንኳን አልነበራቸውም ! ዲያስፖራው ግን እንጀራን በያይነቱ አማርጦ የሚበላበት
ገበያ ዘርግቷል ! አበሻ እንደ ልብ በማይገኝበት ከተማ የተቀረቀርን ሰዎች እንኳን
ቢያንስ በወር አንዴ አገር አቆራርጠን ሄደን እንቀምሳለን!
ሚኒስቶታ ውስጥ አቶ ገረመውንና ኦቦ ጋሩማ በፖለቲካ ምክንያት ሊደባደቡ
ይችላሉ! ዲላ ሬስቶራንት ውስጥ ስታገኛቸው ግን አንድ ናቸው ! ሁለቱም የጤፍ
ምርኮኞች ናቸው ! ሁሉን አሰባሳቢ ባንዲራ ካለ እንጀራ መሆን አለበት !

@wegoch
@wegoch
@paappii
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
#ቅንነት_ድል_ያደርጋል!

ቅንነት ይነገራል ፣ ቅኖች ይመሰገናሉ ፣ ምክንያታዊ ዳሰሳዎች በሀገርና በአለም ትዕይንቶች ላይ ይቀርባሉ፡፡
መነሻችንም መድረሻችንም ቅንነትን ያነገበ በምክንያታዊነት የሚመራ በሀገር ፍቅር የተሞላ ትውልድ ማፍራት ነው፡፡

# ቅንድል_ኢትዮጲያ

https://bit.ly/3f3uU57
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቅንድል_መፅሔት_ቅፅ_2_ቁጥር_3_KendelM_edited70.pdf
6.2 MB
#ቅንድል _ዲጂታል_መፅሔት

★ቅፅ-፪ ቁጥር-፫

ወቅታዊና ትኩስ እውነቶች በሀገሬ ዐምድ

አጃኢብ ያስባለው የሀይማኖት አባት

ኢትዮጲያዊ ቅኖች ይመሰገኑበታል፡፡

አሸላሚ ጥያቄዏች የተካተቱበት

ያንብቡትና ብዙ ያትርፉበት


የበፊት ዕትሞችን ለማግኘት ይሄን ይጫኑ
ከክልሎቻችን የሚሻለው እስር ቤታችን
(አሳዬ ደርቤ)
ባንዲት አገር ውስጥ ተቻችለው ለመኖር የተቸገሩ ፖለቲከኞች በገባቸውና ባልገባቸው ምክንያት በቁጥጥር ስር ውለው በአንድ ክፍል ውስጥ ታድመዋል፡፡ ከእነዚህም መሃከል እስክንድር ነጋ፣ በቀለ ገርባ፣ ጃዋር መሃመድ፣ ኢንጂነር ይልቃልና ስንታየሁ ቸኮል ይገኙበታል፡፡ (መንግሥት አቀላቅሎ ያሰራቸው ሁለቱ ሕዝቦች በአንድ አገርና ክልል ቀርቶ በአንድ ክፍል ውስጥም መኖር እንደሚችሉ ለማሳየት ሳይሆን አይቀርም፡፡)
.
የሆነው ሆኖ እስረኞቹ ከተከላካይነትና ከአጥቂነት ስሜት ጸድተው፣ ተረኛና ነፍጠኛ መባባላቸውን ትተው… ለአንዱ የመጣውን ምግብ በጋራ ይበላሉ፡፡ እርስ በእርስ እየተቀላለዱ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ስቀውት በማያውቁትን ሳቅ እስር
ቤቱን ያደምቁታል፡፡ ከጃዋር ውጭ ያሉት አብዛኞቹ ተጠርጣሪዎች ሲታሰሩና ሲፈቱ የኖሩ በመሆናቸው ያሉበትን ሁኔታ ለመበቀል አላዳገታቸውም፡፡ በተለይ ደግሞ እስክንድር ለተወሰነ ጊዜ ያህል ባለቤቱን እና ልጆቹን ጎብኝቶ ከመመለስ ባለፈ ተፈትቶ አያውቅም፡፡ እሱ ግን በዚህ አባባል አይስማማም፡፡ ‹‹መቼ ታስሬ ነው የምፈታው?›› በማለት የእሥራትን ትርጓሜ ከፍርሐት ጋር ያዛምደዋል፡፡
.
እስረኞቹ የሚተኙት ተደራራቢ በሆኑ አልጋዎች ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ይሄን ቀደዳ ልጽፍ ወደ ክፍላቸው ስገባ ከጃዋር ስር ካለው አልጋ ላይ እስክንድር ተኝቶ ነበር፡፡ ከይልቃል ስር ካለው አልጋ ደግሞ በቀለ ገርባ ጋደም ብሏል፡፡ በቄ አብሮ ለመኖር እንጂ አብሮ ለመታሰር የሚመች ሰው በመሆኑ በየደቂቃው የሆነ ቀልድ እያወራ ያዝናናቸዋል፡፡ በዚያን ቀንም ናፕ ለመውሰድ አስበው አረፍ ከማለታቸው ‹‹የአማራ የበላይነት እዚህ ድረስ ተከትሎን መምጣቱ ያሳዝናል›› ማለት ጀመረ፡፡ ‹‹እኮ እንዴት?›› ተብሎ ሲጠየቅም ‹‹ከእኔ በላይ ያለውን አልጋ የተቆጣጠረውን ሰው አታዩም እንዴ?›› በማለት ወደ ኢንጂነር ይልቃል አልጋ ሲያመለክታቸው መተኛታቸውን ትተው መሳቅ ጀመሩ፡፡ በሳቁ መሃከልም እስክንድር ጣልቃ ገባና ‹‹እኔስ ምን ልበል?›› የሚል ጥያቄ ሲያቀርብ ‹‹አንተ ደግሞ ምን ሆንክ?›› በማለት በቀለ ጠየቀው፡፡ ‹‹አትላስ ከተሸከማት መሬት በላይ የሚከብድ መንግሥት ተሸክሜ ነው እኮ የማድረገው›› ብሎ ወደ ጃዋር አልጋ በጣቱ ባሳያቸው ጊዜም የቀዘቀዘው ሳቃቸው እንደ አዲስ ተሟሟቀ፡፡ ጃዋርም በእስክንድር ወሬ ሲስቅ ከቆየ በኋላ ‹‹እስኬው ለካ እንዲህ ተጫዋች ነህ እንዴ?›› በማለት ሲጠይቀው ‹‹ታዲያስ! ተከትየህ የመጣሁት እኮ ጨዋታ አዋቂ መሆኔን የሚያውቀው መንግሥት ጃዋርን አጫውትልኝ ስላለኝ ነው›› የሚል መልስ በመስጠት እያሳቃቸው ሳለ የክፍላቸው በር ተከፈተና አዲስ እንግዳ ገባ፡፡ የእንግዳውን ማንነት ሲመለከቱም ሁሉም ከአልጋቸው ላይ ተነስተው በጭብጨባና በጩኸት ተቀበሉት፡፡
.
ይሄም እንግዳ አቶ ልደቱ አያሌው ሲሆን ከክፍሉ በር ላይ ቆሞ በጭብጭባና በፈገግታ የተቀበሉትን ጓዶች ሲመለከት እሥር ቤት ሳይሆን ቤተ- መንግሥት
የገባ መሰለው፡፡ ከሰላምታ በኋላም ‹‹በምን ጥፋት ተጠርጥረህ ነው?›› አለ ጃዋር ለመሳቅ እየተዘጋጀ፡፡ ‹‹ደብረ ዘይት ላይ ቄሮዎችን አደራጅቼ ብጥብጥ ላስነሳ ስል…›› በሳቃቸው አቋረጡት፡፡ ‹‹ለሁለት ወራት ያህል አብረን ልንከርም ነዋ?›› እስክንድር ተናገረ፡፡ ‹‹ከዚያ በኋላስ?›› ጃዋር ጠየቀ፡፡ እስኬውም ‹‹ከዚያ በኋላማ መስከረም ሰላሳ ስለሚደርስ በመንግሥት የማይታዘዙትን ፖሊሶች ተከትለን ወደ ቤታችን እንሄዳለን›› የሚል መልስ በመስጠት ጃዋርና ልደቱን ሲተርባቸው በቄ ሳቁን አቋርጦ ‹‹ወደ ቤታችን ሳይሆን ወደ ቤተ-መንግሥታችን ተብሎ ይስተካከል›› የሚል እርማት ሰጠ፡.በተደረገለት አቀባበል የመዝናናት ስሜት የተሰማው አቶ ልደቱም ‹‹በሉ አልጋየን አሳዩኝና አረፍ ልበል›› ብሏቸው ወደ ውስጥ ሊገባ ሲል ‹‹የሻማ ሳትከፍል አትገባም›› በማለት በቀለ አስቆመው፡፡ በዚህም ጥያቄ ልደቱ ግር እየተሰኘ ‹‹መብራት የለም እንዴ?›› የሚል ጥያቄ ሲያቀርብ ‹‹ሰውዬ ፖለቲካ እያወራህ ከመንግሥት ጋር አታነካካን›› እያሉ ኪሱን ይዳብሱት ጀመር፡፡

@wegoch
@wegoch
@paappii
የባለቅኔው (የገጣሚው) ድምፅ
#ክፍል አንድ
ለጋስነት በልቤ ውስጥ ተዘርታለች፡፡ ክምር ስንዴ አመረትኩ፤ ለተራቡም አካፈልኩ፡፡
ነብሴ ለወይን ፍሬ ሕይወት ትሰጣለች፡፡ ወይኑን ጨምቄ ለተጠሙ አጠጣሁ፡፡
ፋኖሴን ዘይት ሞልቼ መስኮቴ ላይ አኖርኩ፡፡ በጭለማ ለሚጓዙ እንግዶችም መንገዱን አበራሁ፡፡
ይህንን ሁሉ የማደርገው በእነዚህ ድርጊቶቼ ውስጥ ስለምኖር ነው፡፡ የህይወት እጣ ለጋስ እጆቼን ብታስርብኝ ሞትን እመርጣለሁ፡፡ ገጣሚ ነኝና መለገስ ካልቻልኩ ፈፅሞ አልቀበልም፡፡

የሰው ልጅ ቁጣ እንደ አውሎ ነፋስ ያጓራል፡፡ እኔ ግን በዝምታ እተነፍሳለሁ፡፡ ምክንያቱም ትንፋሼ ፈጣሪ ጋር ሲደርስ ወጀቡ በሙሉ ይቆማልና፡፡
ሰዎች ምድራዊ ነገሮች ላይ ይንጠለጠላሉ፡፡ የእኔ መሻት ግን የፍቅር ችቦ ናት፡፡ በብርሃኗ የልቤን ኢ-ሰብአዊነት ታነፃልኛለች፡፡
ሰዎች በዘር፣ በቀለምና በሃይማኖት ተከፋፍለዋል፡፡ እኔ ደግሞ በሁሉም አገር እንግዳ ነኝ - ከየትኛውም ወገን አይደለሁም፡፡
ሥነ-ፍጥረት( ዩኒቨርስ) አገሬ ስትሆን ጎሳዬ ደግሞ ሁሉም የሰው ልጅ ነው፡፡
የሰው ልጆች አቅመ-ቢስ ሆነውም የተከፋፈሉ ናቸው፡፡ በየጊዜው የምትጠበውን ምድር በግዛትና አገራት መሰነጣጠቅ አላዋቂነት ነው፡፡
የሰው ልጆች እጅ ለእጅ የሚያያዙት የነብስን ቤተ-መቅደስ ለማፍረስና ምድራዊ ድልድይ ለመገንባት ብቻ ነው፡፡ ብቻዬን ቆሜ እንዲህ የሚል የውስጥ ድምፄ ተሰማኝ "ፍቅር በህመም ለሰው ልብ ሕይወት እንደምትሰጥ ሁሉ ድንቁርና ደግሞ የእውቀትን መንገድ ያሳየዋል፡፡" ሕመምና ድንቁርና ወደ ታላቅ ደስታ ይመራሉ:- ምክንያቱም ፈጣሪ ከፀሀይ በታች ለሰው ልጅ መከራን አልፈጠረም፡፡

ይቀጥላል.........
#መናፍቁ ካህሊል እና ሌሎችም

@wegoch
@wegoch
@paappii
የባለቅኔው...........

#ክፍል ሁለት

ውቧ አገሬ ዘወትር ትናፍቀኛለች፡፡ ጎስቋላ ሕዝቧንም ከልቤ እወዳቸዋለሁ፡፡ ሆኖም ግን የአገሬ ሰዎች "የአገር ፍቅር" በሚሉት የአብዮተኝነት ስሜት ተገፋፍተው ጎረቤት አገር በመውረር በሰዎች ላይ ግፍ ቢፈፅሙ ሕዝቤንና አገሬን ለመጥላት እገደዳለሁ፡፡

የትውልድ መንደሬንና ያደግሁበትን ቤት እናፍቃለሁ፡፡ ሆኖም የአገሬ ሰዎች ለምስኪን መንገደኛ መጠለያ ቢከለክሉ ናፍቆቴን በመተው እረሳቸዋለሁ፡፡ ለመንገደኛ መጠለያ ያልሆነ ቤት ቢፈርስ ይሻላል፡፡ የትውልድ መንደሬን አገሬን በምወድበት ኃይል እወዳታለሁ፡፡ አገሬን ደሞ ከምዶር እኩል እወዳታለሁ፡፡

የሰው ልጅ የፈጣሪ መንፈስ ምድር ላይ የሚወከልባቸው ፍጡራን ናቸው፡፡ እነዚያ የመንፈስ ልጆች ዛሬ በፈረስ መንደር ላይ ቆመው እያለቀሱ ለልጆቻቸው የድረሱልኝ ጩኸት ያሰማሉ፡፡ ልጆቻቸው ግን የጎሰኝነት መዝሙር በመዘመርና ጎረቤቶቻቸውን መግደያ ሰይፍ በመሳል ሥራ ተወጥረው የእናቶቻቸውን የለቅሶ ጥሪ አይሰሙም፡፡

ሰብአዊነት ልጆቿን ትጠራለች፤ ሆኖም ድምጿን የሰማት የለም፡፡ አንድ ሰው የእናቱን ጥሪ ሰምቶ እንባዋን ቢያብስላት ሌሎች "ደካማ ፤ ቡቡ!" ሲሉ ይሰድቡታል፡፡

የሰው ልጅ የፈጣሪ መንፈስ መገለጫ ነው፡፡ ፈጣሪ ደግሞ ፍቅርና በጎነትን ይሰብካል፡፡ ሆኖም ይህ ትምህርት የሰዎች ማሾፊያ ብቻ ነው፡፡ የናዝሬቱ እየሱስ ያንን ስብከት በማድመጡ ተሰቀለ ፤ ሶቅራጥስ ድምፁን ሰምቶ በመከተሉ መከራ ደረሰበት፡፡ የእየሱና የሶቅራጥስ ተከታዮች በአምላክ ያምናሉ፡፡ የነርሱ አማልክት በሰው እንደማይገደሉ ስለሚያምኑ በሁለቱ ስብከት ላይ አፌዘ፡፡ ፌዝ ደግሞ ከግድያ የበለጠ መራራ ናት፡፡

ሆኖም ግን እየሩሳሌም እየሱስን፤ አቴንስ ደግሞ ሶቅራጥስን መግደል አይችሉም፡፡ ሁለቱም ለዘላለም ይኖራሉ፡፡ በአምላክ የሚያምኑ ሁሉ በፌዝ አይሸነፉም፡፡
ለዘላለም ይኖራሉ ፤ ያድጋሉ፡፡

ይቀጥላል........

#መናፍቁ ካህሊል እና ሌሎች

@wegoch
@wegoch
@paappii
የባለቅኔው........

#ክፍል ሦሥት

የሰው ልጅ በመሆንህ ወንድሜ ነህ፡፡ ሁለታችንም የቅዱስ መንፈስ ልጆች ነን፡፡ ከአንዲት ምድር የተሰራን ፍጡራን፡፡

በሕይወት ጎዳና አብረኸኝ ትጓዝ ዘንድና የእውነታን ምሥጢር እንድረዳ ታግዘኝ ዘንድ ጓደኛዬ ነህ፡፡ 'የሰው ልጅ ነህ' ይህ ለኔ በቂዬ ነው፡፡ እንደ ወንድሜ እወድሃለሁ፡፡ አንተ እንደፈቀድህ ልትናገረኝ ትችላለህ፡፡ ነገ ሲደርስ ንግግርህን እንደማስረጃ ቆጥሮ ይፈርድብሃል፡፡

ንብረቴን ልትቀማኝ ትችላለህ፡፡ ስግብግብ በመሆኔ ያካበትኩት ሀብት ካስደሰተህ ውሰደው፡፡ የፈቀድከውን ልታደርገን ትችላለህ፡፡ ነገር ግን 'እውነቴን' ልትነካት አትችልም ፡፡ ደሜን ማፍሰስ ፤ ስጋዬን ማቃጠል ትችላለህ፡፡ ሆኖም መንፈሴን መጉዳት አትችልም፡፡

እግርና እጄን በሰንሰለት አስረህ ጭለማ ውስጥ ልታሥረኝ ትችላለህ፡፡ ሆኖም ግን ነፃ አስተሳሰቤ በሰፊው ሰማይ ላይ ትንሳፈፋለችና ማን ሊያስራት ይችላል?

ወንድሜ ነህና እወድሃለሁ፡፡ ባንተ ቤተ-ክርስቲያን አመልካለሁ ፤ በመቅደስህ እንበረከካለሁ ፤ በመስኪድህ እሰግዳለሁ፡፡ እኔና አንተ የአንድ ሃይማኖት ልጆች ነን፡፡ የሃይማኖት መንገዳችን ቢለያይም መንገዶቻችን በሙሉ የአንድ ፈጣሪ እጅ ጣቶች ናቸው፡፡ የፈጣሪ እጅ ለሁላችን ሙላትና የመንፈስ ስጦታ የተዘረጋ ነው፡፡

በእውቀት ዐይኔ ባላየውም ስለ እውነታህ ስል እወድሃለሁ፡፡ የሁለታችን እውነቶች በሚመጣው ዓለም እጅ ለእጅ ተያይዘው አንድ ዘላለማዊ እውነት በመሆን ይጣመራሉ፡፡ በፍቅርና በውበት ለዘላለም ይኖራሉ፡፡

በጨቋኝህ ፊት ደካማ ፤ በስግብግብ ባለፀጋ ፊት ደግሞ ደሃ በመሆንህ እወድሃለሁ፡፡ በዚህ ምክንያት እያነባሁ አቅፍሀለሁ፡፡ ከእንባዬ ጀርባ የፍትህን እጅ አቅፈህ የፈረዱብህን ይቅር ስትል አይሃለሁ፡፡ ወንድሜ ነህና እወድሃለሁ፡፡

ይቀጥላል...........

#መናፍቁ ካህሊል እና ሌሎች

@wegoch
@wegoch
@paappii
ታድለህ
(በእውቀቱ ስዩም)
.
’ስለኢትዮጵያ ዝም አንልም “ የተባለው ድርጅት ሊቀመንበር በቀደምለት በዝነኛ ተዋናይቶች ታጅቦ ባወጣው ያቋም መግለጫ እንዲህ አለ:-
“ አርቴፊሻል የወንድ ብልት መጠቀም፤ ራስን በራስ ማርካት እና የአፍ ዝሙት በወንጀል ህግ እንዲካተት (መንግስትን ) እንጠይቃለን “
ገራሚ ነው!
“ ራስን በራስ ማጥፋትም ፤ ራስን በራስ ማርካትም ተከልክሎ እንዴት ነው የሚኖረው? አለ ጉዋደኛየ በየነ ይህንን መግለጫ የሰማ ቀን::
እኔ እምለው! አንዲት ላጤ ሴት ፤ ብቸኝነት ሲቀፈድዳት ኳረንቲን ሲያዝጋት : አልፎ አልፎ ራሷን ብታረካ ምን ጣጣ አለው? ! በርግጥ በወንዱ ጉዳይ ላይ በስሱም ቢሆን እስማማለሁ!! በየቀኑ ደከመኝ ስለቸኝ ሳይል “የሚመታ “ ጎረምሳ፤ በዘር ማጥፋት ወንጀል ቢከሰስ ችግር የለብኝም ! አንዲሁም፤ ራሱን በራሱ ለማርካት አንድ ደርዘን ሳሙና የሚፈጅ ጎልማሳ ያገር ሃብትን አላግባብ በማባከን ቢከሰስ ሲያንሰው ነው!
ግን አንድ ሰው ምኝታቤቱን ዘግቶ ብቻውን ለሚሰራው ስራ ከሳሹ ማን ሊሆን ነው? ምናልባት፤ጎረቤቱ?
ከገዛ እጁ ጋራ ሲዳራ ፤ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ልደታ ፍርድ ቤት የሚቀርብ ተጠርጣሪ በአእምሮዋችሁ ሳሉት ፤
ዳኛው “ ጎረቤትህ ሴጋ ሲመታ በቀዳዳ አይቸዋለሁ ብሎ መስክሮብሃል፤ በዚህ ጉዳይ ምን ትላለህ?’
“ ክብር ፍርድቤት! ሽንቴን ከሸናሁ በሁዋላ ዘለግ ላለ ጊዜ ሳራግፍ አይቶኝ ይሆናል እንጂ እንዲህ አይነት ድርጊት ለመፈፀም አስተዳደጌ አይፈቅድልኝም" አርቴፊሻል የወንድ ብልትን አቅርቦትንስ መንግስት በምን መንገድ ነው መቆጣጠር የሚችለው?!
ማህበሩ በዚህ ጉዳይ ላይ ከወዲሁ ቢያስብበት ጥሩ ነው! ምናልባት ፤ፌዴራል ፖሊስ በላጤ ሴቶች መኖርያ ቤት ውስጥ ድንገተኛ ብርበራ ሊያደርግ ይችላል!
ከዚያ ፖሊሱ ከተጠርጣሪዋ ሴት ራስጌ የሆነ ነገር ጎትቶ እያወጣ
“ አንቺ ይሄ ምንድነው?
“ ያልጋው አምስተኛ እግር ነው!! ኮንስታብል"
" ካልጋው ጋር እንዴት አልተገናኘም ታድያ?"
" በ wirelessም ይሰራል"
ሌላው በወንጀል ህግ እንዲካተት የታጨው ተግባር “ኦራል ሴክስ “ ወይም በማህበሩ አጠራር "ያፍ ዝሙት" ነው!
ወደፊት የሚሆነውን አስቡት! ማለዳ ላይ አንድ ጨዋ ዜጋ ባቅራቢያው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ጎራ ይልና፤
“ ወንጀል ፈፅሜ ፤ በፈቃዴ እጄ ልሰጥ ነው የመጣሁት” ይላል፤
ተረኛው ፖሊስ ;-“ የሰራኸው ወንጀል ምንድነው?”
ወጣቱ “ ትናንት ማታ ፍቅረኛየን አስዘፍኛለሁ "
ይሄኔ ፖሊሱ ምን ይላል

@wegoch
@wegoch
@wegoch
የባለቅኔው........

#ክፍል አራት

ወንድሜ ሆነህ ሳለህ ለምን ትጣላኛለህ? ክብር የሚሹ አለቆችህን ለማስደሰት ብለህ ለምን አገሬን በመውረር ታንበረክከኛለህ? ሚስትና ልጆችህን ጥለህ በደምህና በእናትህ እንባ ክብርና ሥልጣን ለሚገነቡ ሰዎች ስትል ስለምን ደምህን ለማፍሰስ ወደሩቅ አገር ትሄዳለህ?

ወንድም ወንድሙን ቢገድል ክብር ይሆንለታል? ከሆነ ደግሞ ወንድሙን ሊገድለው ቃዬል ሃውልት ሊቆምለት ይገባል ማለት ነው፡፡

"የመኖር ጉጉት የሌሎችን መብት እንድንነጥቅ አስገድዶናል" በማለት የምታምን መሪ ወንድሜ ሆይ ስማ፡፡ የሌሎችን መብት ማስከበር እጅግ ታላቅ ተግባር ነው፡፡ የእኔ መኖር ሌሎችን በመግደል ላይ የተመሰረተ ከሆነ ሞቴን እመርጣለሁ፡፡ የሚገድለኝ እንኳን ባጣ ከዘላለማዊነት መምጣት በፊት ለዘላለማዊነት ስል ራሴን አጠፋለሁ፡፡

ወንድሜ ሆይ #ራስ-ወዳድነት የበላይነትን ትፈጥራለች፡፡ የበላይነት ደግሞ በተራዋ ጎሰኝነትን ስትፈጥር ከጎሰኝነት ደግሞ ሌሎችን የማንበርከክ የሥልጣን ጥማት ትመጣለች፡፡

ነብስ በእውቀትና በፍትህ ታምናለች፡፡ ድንቁርናና ብዝበዛን የሚያመጣ ሥልጣንን ደግሞ ትክዳለች፡፡ ባቢሎንን ያፈረሳት ፤ የእየሩሳሌምን መሠረት ያናጋውና ሮምን ያወደማት ይኸው ሥልጣን ነበር፡፡ እኔ የማከብረው ብቸኛው ሥልጣን የተፈጥሮን ፍትህ የሚጠብቅና የሚያከብር ዕውቀትን ነው፡፡

ገዳይን በመግደልና ዘራፊን በማሰር ምን ዐይነት ፍትህ እናመጣለን? ጎረቤትን በመውረር ሕዝብን መግደልስ ምን ዐይነት ፍትህ ነው? አንድ ገዳይ ሌላውን ገዳይ የሚቀጣበትን ሥልጣን ፍትህ ምን ትለው ይሆን? ሌባ ሌላው ሌባ ላይ የሚፈርድበትንስ?

ወንድሜ ነህ እወድሃለሁ፡፡ የምወድህም በሙሉ ክብርና ፍቅር በምትገለፅ በፍትህ ስም ነው፡፡ ዘርህንና ማህበረሰብህን ሳልመለከት እወድሃለሁ፡፡ ይህንን ውዴታዬን ፍትህ ባትደግፍልኝ በውስጤ አስቀያሚ ራስ-ወዳድነት ደብቄያለሁና ከሃዲ ነኝ፡፡

@wegoch
@wegoch
@paappii
እስልምና ለምን ደስ ይልሀል ? ያላችሁኝ እንደሆን.. .
(ሚካኤል አስጨናቂ)
በእምነቴ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታይ ነኝ።
ሀይማኖቴን ብዙ በመረመርኩት ቁጥር የበለጠ የእድለኝነት ስሜት ይሰማኛል።.
ያደግሁት አንድ መስጂድ እና ጥቂት ሙስሊሞች በነበሩባት ሰላሌ ፍቼ ከተማ ውስጥ ነው።
እንደውም ለረመዳንም ይሁን ለአረፋ ክብለ በዓል ጊዜ ነጭ በነጩን ለብሶ ጎልቶ የሚታየን አብድል የሚባል የዳቦ ቤት ባለቤት ብቻ ነበር። ስለ ሙስሊሞች ማወቅ እና ህይወታቸውን መከታተል የጀመርሁት ጅማ ዩንቨርስቲ ተማሪ በነበርሁበት ጊዜ ነው።
የጅማ ሙስሊሞች አክራሪ ተብለው ቢወነጀሉም እኔ በቅርበት አውቃቸው ስለነበር ትክክለኛ ማንነታቸውን እረዳው ነበር። የጅማ ሙስሊሞች እንግዳ ተቀባይና ፍቅሮች ናቸው። ከማንም ሰው ጋር ተቻችሎ ሳይሆን ተፋቅሮ ለመኖር ሀጃ የለባቸውም (አክራሪነት ህዝብ ጋር ሳይሆን መሀይማን ምሁሮች ባሉበት ብቻ የነገሰ ጣዖት ነው።
ብዙ የግቢ ጓደኞቼ ከቤት ቀርተን በበዓል ወቅቶቻችን ቅንጣት ሳይከፋን ራሳችን አርደን ባዘጋጀነው ስጋ ዘና ብለን አክብረን እናውቃለን ።
ዶሮ ወጥ ሰርተው ያበሉንን እትዬ ን ማን ይረሳቸዋል? (Wing 5 ቡና እንጠጣባት የነበረችውን ቤት ባለቤት አንድም የኪቶ ፉርዲሳ የኢንጂነሪንግ ተማሪዎች አንረሳቸውም)
እንደውም.. .
እዚህ ጋር አንዴ ታክሲ ውስጥ ያጋጠመኝን ሌላ እውነት ላጨዋውታችሁማ :)
ወሩ ታህሳስ ነበር...የጌታ ልደትን ለማክበር ሽር ጉዱ ጦፏል... ጅማ ከተማዋ በአሪቲና ጉዝጓዝ መዓዛዎች ታውዳለች። ብዙው ተማሪ ወደ ሀገሩ ተጉዞ በዓልን ሊያከብር መንቀሳቀስ ጀምሯል። ከአንድ ቀን በዓል ወከባ የማይወዱ የእኔ ቢጤዎች ደግሞ እዛ ጭር ባለ ግቢ ውስጥ ቀርተናል ...
ታክሲ ውስጥ ተሳፋሪው ሞልቶ ሊንቀሳቀስ ሲል ጀማል የሚባል ግለሰብ ገባ። በእጁ የገዛትን ዶሮ ይዟል።
"ጀማል " አለው...አንድ የአካባቢው ነዋሪ..
"ሀዬ " ብሎ ዞር አለ ...
"ዶሮዋ ምንድናት? "
ጀማል ፈገግ አለ ... (የድዱ ውቅራት ደስ የሚል ውበት አጎናፅፎታል )
"በዓል አይደል እንዴ? "
የታክሲዋ ተሳፋሪ ሁሉ በአግራሞት ጀማልን አየነው።
"እና ታድያ የክርስትያን በዓል እኮ ነው "
ጀማል ፈርጠም ብሎ መለሰ...
"አቦ ተዋ ! ፍቅር ካለ የወንድሜ በዓል ለኔ የማይተርፍበት ምክንያት የለም። ዶሮዬን ሸፍ አድርጌ ረሀ ሆኜ ማሳለፍ ነው የምፈልገው።
ገናን እወደዋለሁ ። አቦ አንተም ከቻልክ በኋላ ቤት መተህ ዱአ እያደረግን እንዋል ።"
የሰማሁትን ማመን አልቻልኩም ነበር...ድሮውንም የጅማ ሙስሊሞች ይመቹኝ ነበር...ፍቅሬ የበለጠ ጨመረብኝ።
ሙስሊሞችን ሳያቸው ነጠላ አጣፍቶ ቤተክርስትያን የሚሄዱ ክርስትያኖች ያህል ይቀሉኛል።
ሀይማኖታቸው ...ስርዓት አለው። ስርዓትና ምግባር በኦርቶዶክስ ቤት ብቻ ሳይሆን ሙስሊሞችም ጋር ያለ ስለሆነ እወዳቸዋለሁ ። አብዛኛው ሴቶቻቸው እንደ እሳት ሰንሰለት የሚጋረፍ ውበት ቢኖራቸውም ለማንም የማይገለጥ ምትሀት እንደሆነ አውቃለሁ። እንደው ለአንድ ቀን ፊትን ሸፍኖ መንቀሳቀስ ቢታገዱና ብናያቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የህንድ ሴቶች ሊወሩን መተዋል የምንል ይመስለኛል 😃
ባሎቻቸው ያንን ለህዝብ የተሸሸገ ውበት ቤታቸው ውስጥ ገላልጠው እያዩ ሚስታቸውን ከጎናቸው ሸጉጠው ጋደም ሲሉ ምን ይሰማቸው ይሆን?
እኔ በግሌ ለአንድ የኦርቶዶክስ ቤተመቅደስ ያለኝ ክብርን ያህል ለሙስሊም መስጂዶችም ክብር አለኝ። እንደው ለአመል ያህል በአፌ ቧልት እያወራሁ የምጓዝ እንኳ ቢሆን መስጂድ ደጆች ላይ ስደርስ ሀፍረት ይሸብበኛል።
ሰዎች በስሜታችን የከፋፈልነው ነገር እንጂ ፈጣሪ ለሁላችንም ፀሎትና እምነት ዋጋ እንደሚሰጥ ይሰማኛል።
አቦ በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
‹‹እንደትዳር ደባሪ ነገር የለም ››
(አሌክስ አብርሃም)
‹‹በእኔና አንተ መሃል ይቅር እንጅ እንደትዳር ደባሪ ነገር የለም ›› ትለኛለች!
ድንገት በአጋጣሚ ደውላ እያወራንኮ ነው! ድል ባለ ሰርግ ካገባች ገና አንድ
ዓመቷ !
‹‹ምነው ባለቤትሽ ጋር ሰላም አይደላችሁም እንዴ ?››
‹‹አንዱ የትዳር ደባሪ ነገሩኮ እሱ ነው …ሰላም ሁን አትሁን አታውቀውም ፀብ
የለም ግን ትበሳጫለህ ›› ትነጫነጫለች !
‹‹ምን ሆንሽ አሪፍ ልጅ ነው ያገባሽው... ማለቴ አይጠጣም ፣አያጨስም ፣
አይቅምም ፣ ፌስቡክ አይጠቀምም፣ እና ሌላ ሴት ቀና ብሎ አያይም
ይወድሻል.... ››
‹‹ኡፍፍፍ ባልቴቶች እንደሚያወሩት ነው የምታፅናናኝ! …ታውቃለህ ?
….መጀመሪያ ልትጋባ ስትወስን የሆነ በቃ ግርግር ነው ….ሚስት መሆን የሆነ
አስማት ነገር ይመስልሃል ፣በምድር ላይ ካሉ ሴቶች ሁሉ በሆነ ተዓምር ተለይተህ
የተመረጥክ ነገር … ትዳር ከውጭ ሁነህ ስታስበው ውስጡ እንጀሆቫ ዊትነስ
መፅሄት አበባ ወንዝ ልጅህን ቸቸ ብለው የሚያጫውቱ አንበሶች… ቁርስ
የሚያቀርቡ ነብሮች ምናምን ያሉበት ይመስልሃል ! …
ከዛ ሰርግ አለ …ግርግሩ ድግሱ ልብስ መግዛቱ ሰው መጥራቱ በቃ የሰማው
ሰው ሁሉ ልታገባ ነው ምናምን ለወግ ማረግ በቃች እያለ ማውራቱ … ቬሎው
ፎቶው ፍሸናው …ሚዜው አጀቡ ልእልት የሆንክ ነው የሚመስልህ …ከዛ ደግሞ
ምላሹ አለ …ባህላዊ ቅራቅምቦው ቅሉ ፎሌው ሞሰቡ ሹርባው … ስትመላለስ
የምትኖር ነው የሚመስልህ… ከዛ በኋላ በቃ ራት የትም ስትጠራ መድረክ
የሚዘጋጅልህ ነገር ….ጫጉላ አለ … ከተሳካልህ ወጣ ብለህ ምናምን ቱሪስት
የሆንክ መስሎ እስኪሰማህ …ቀለበት መንገድ ላይ መኪና ኮፈን ላይ ቁመህ
እንደታይታኒክ ተቃቅፈህ እጅህን መዘርጋት ሁሉ ይቃጠሃል... ያገኙህ ሁሉ አዲስ
ተጋቢ መሆንህን ሲያውቁ ፈገግ ይሉልሃል …
ተጋብተህ በመጀመሪያወቹ ሳምንቶች ገና ከማሸጊያቸው የወጡ አዳዲስ
ፒጃማዎች ፣ ሽቶዎች ከቤትህ አይጠፉም …ጧት ስትነሳ ፈገግታው …በቃ
ስትወጣ አዲስ ተጋቢዎች ናቸውኮ ምናምን መባሉ …ፊልም ላይ ያየሀቸውን
ፊክሽን ላይ ያነበብካቸውን የፍቅር ሲኖች የምትደግም ነው የሚመስልህ …ጧት
ቁርስ መስራቱ … የስጦታ አዲስ ሰሃን ፣ የስጦታ አዲስ ብርጭቆ ፣ የስጦታ
አዲስ ማንኪያ …ሁሉ ነገር አዲስ ነው …ሲም ካርድህ ሁሉ አዲስ ሊሆን
ይችላል ! መሸት ሲል የስጦታ አዲስ ጋቢ ጣል አድርገህ ሶፋ ላይ ….ባል ከውጭ
ሲመጣ ለማስደመም ምናምን ቡና ማፍላት … ያሳለፍከውን ታሪክ ማውራት
ከዛስ በለኝ ….
ከዛስ?
በቃ ትዳር ማለት.... ጭርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር
ርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር
ርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር
ርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር
ርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር
ርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርርር
ጓደኞችህ ራሱ የታባታቸው እንደሚጠፉ ግራ ይገበሃል …የሆነ ባል ሳይሆን
የሚናከስ ውሻ ያገባህ ይመስል እነዛ በቀን ስድስት ጊዜ የሚደውሉ ጓደኞችህ
ድራሻቸው ነው የሚጠፋው ‹‹ስፔስ እንስጣችሁ ብለን ›› ምናምን ይሉሃል !
ስፔስ አባታቸው ይውጣ !… ባገባና ባላገባ መካከል ክላስ መፈጠሩ ነው እንጅ …
በእውነት መገፋት ሁሉ ነው የሚሰማህ ! ባንዴ ያረጀህ እስኪመስልህ !
‹‹ፍቅር ካለ …››
‹‹ኦፋ …ፍቅር ትላለህ እንዴ? ቀለበቱ ጣትህ ላይ ሲገባ ፍቅር ከልብህ ላይ ክንፍ
አውጥቶ ነው የሚበረው መሰል …ባልህ ራሱ ታላቅ ወንድምህ ነው
የሚመስልህ ! በቃ የሆነ ስልችት ይልሃል …‹‹ሃኒ ከረቫቴ የት ነው …ሃኒ
ሰማያዊው ሸሚዜን የት አደረግሽው …ሃኒ እስኪ ደውይልኝ ስለኬን የት አደረኩት
…. ሃኒ ቻርጀር ወሰድሽ እንዴ ….ሃኒ ዛሬ ያየሁት ህልም …ሰፊፊፊፊፊፊፊፊ ባህር
ይመስለኛል …..በቃ ህልም ፈች ሁሉ ትሆናለህ! አልጋ ላይ ራሱ እንደበፊቱ
አትሆንም … መሄጃ ስለሌለህና አንድ አልጋ ላይ ስለምትገናኝ ስራ ከምፍታት
ምናምን ብለህ እንጅ ይሰለችሀል …ደግሞ ሙቀቱ …ባል ጋር ሲሆን ሰሀራ ነው
የሚሆነው አልጋው !
ከቤት ስትወጣ ‹‹ዋው ትዳር ተስማምቶሻል›› ለመባል እንደበፊቱ ብድግ ብለህ
አትወጣም! ለማማር ፍዳህን ትበላለህ ! ቁርስ ፣ ምሳ ፣ራት …መተኛት …ከዛ
ቁርስ ምሳ ራት …ከዛ ቁርስ ምሳ ራት … ወክ ! ከዛ ቁም ነገር ቁም ነገር
ማውራት …ሶፋ ብንቀይር …ሌላ ቤት ብንከራይ …ዕቁብ ገብተን የሆነች ከከተማ
ወጣ ያለች ቦታ ብንገዛና ሰርቪስ ነገር ብንቀልስ …አይ እዳው ያለቀ
ኮንዶሚኒየም ብንገዛ …ምናምን ማለት ትጀምራለህ …ስትወጣ ቦርሳና ጥላ
መያዝ ትጀምራለህ ! ወይ ታረግዛለህ እርፍ !! ሌላ ረዥም የገንፎና የዳይፐር ወሬ
….
‹‹እና ምን ተሻለ… ?››
በቃ የሆነ ጊዜ ላይ ድንገት በደረቅ ሌሊት ተነስተህ የድሮ ቦይ ፍሬንድህን ቀልድ
እያስታወስክ መሳቅ ትጀምራለህ …ወይ ደግሞ ያበሳጨህን እያስታወስክ
ትረግመዋለህ ! ‹‹እግዜር የኔን ቀን ይስጠው ,,,አዳልጦት ትዳር ውስጥ ይግባ
፣አልጋው ሰሀራ ይሁንበት›› እያልክ ! እንዲህም እያልክ ግን አሁን ማን ጋር ይሆን
እያልክ መቅናት ልትጀምር ሁሉ ትችላለህ … በቃ እዚህ ፌዝ ላይ ስትደርስ
ፌስቡክ ላይ መጀመሪያ ሰርች የምታደርገው የድሮ ቦይፍሬንድህንና ጓደኞችህን
ስታተስ ነው …
እኔ የምልህ አንተ ግን እንዴት ነህ ?… ያሳለፍነው ጊዜ ትዝ ይልሃል ወይስ
ረስተኸዋል …?
‹‹አሁን ነው ማምለጥ! ›› እላለሁ !

@wegoch
@wegoch
@paappii
2024/09/24 18:34:07
Back to Top
HTML Embed Code: