Telegram Web Link
(በእውቀቱ ስዮም)
.
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አገሪቱን በልምላሜ ለማላበስ የሚያደርገው ጥረት እሚደነቅ ነው፤ ይህንን አረንጉዋዴ ዘመቻ ደግፌ መዳፌ ወንፊት እስኪሆን ሳጨበጭብ ቆይቻለሁ!!
የሰሞኑ አልገባኝም! ህልውናችን ክንብል ድፍት ሊል ጫፍ ላይ በሆነበት ጊዜ ላይ ለችግኝ ተከላ ዘመቻ ህዝብን መጥራት አስፈላጊ ነው?
አገራችን ማንም ያላገኘውን እድል አግኝታ በማባከን የሚደርስባት የለም ! ታሪኳ እንደዚያ ነው! ለኮሮና ያሳየነው ንቀት አንዱ ማሳያ ይመስለኛል፤ ባለፈ ነገር ላይ መወቃቀስ ስለማይጠቅም ነው እንጂ ብዙ እምለው ነበረኝ!
ለማንኛውም አሁን መንግስት፤
1)ለህክምና አርበኞች የሚያስፈልጋቸውን ስንቅ እና ትጥቅ እያቀረበ ነው?
2) የምግብ እጥረት በሚከሰትበት ጊዜ ለህዝቡ የሚነዛው ምግብ በጎተራው እያጠራቀመ ነው ?
3. ለኮሮና ቫይረስ መዳኒት ወይም ክትባት ቢገኝ ኢትዮጵያ የምታገኝበት መንገድ አስቦበታል? ‘፤ በቸርነቱ የሚደርስልን የአለም የጤና ድርጅት በትራምፕ ንፍገት ምክንያት ቺስታ ሆኗል! መንግስት ይሄንን ጉድለት የሚሞላበት ነገር አዘጋጅቷል?
መልሱ አዎ ከሆነ ይመቸው! ካልሆነ ግን ለዚህ ጣጣ መፍትሄ ሳያገኙ የችግኝ ዘመቻ ላይ ጉልበት መጨረስ አያዋጣም እላለሁ:: ወይራ ተከላው ከስምንት ወር በሁዋላ ይደረስበታል ! እስከዚያ ግን በህይወት መቆየት አለብን ‘ እህል የሚደርስ የፍልሰታ እኔ እምሞት ዛሬ ማታ “ ይላሉ ባልቴቶች ሲተርቱ!
በመጨረሻም፤ ድሮ በዘመነ ወረሼህ የነበረች አንዲት አሚና ከዙረት ወደ አገሯ ስትመለስ ያንጎራጎረችው እንዳይደርስብን እመኛለሁ!
“አስቲ ወደ አገሬ ልዝለቅ ወደ አፋፉ
ሰውስ አልቋልና እንደምነው ዛፉ “

@wegoch
@wegoch
Cyborea: The Mother of Judas
(Pp76)

የይሁዳ እናት Kahlil Gibran በፃፈው "Jesus The Son of Man " ውስጥ ስለ ልጇ ቀጣዩን ያናግራታል

"ልጄ ይሁዳ ትሁትና ፃድቅ ሰው ነበር። ለኔ ለእናቱ የነበረው አዘኔታና ርህራሄ መቼም ልረሳው አልችልም።

…ሮማውያን ያልዘሩትን የሚያጭዱ፣ በአይሁድ ሃብትም የከበሩ መሆናቸውን ዘወትር ሲናገር እሰማ ነበር።
ልጄ በአንድ አይሁዳዊ ወታደር ላይ ቀስቱን በመወርወር አቁስሎት እንደነበር ትዝ ይለኛል። ይሄም ወንጀል ሆኖ ሲታሰር ዕድሜው 17 ነበር።
በዚያ እድሜው የአይሁዳዊያንን ወጣቶች ልብ ሲያነቃቃና ሲያደፋፍር ይውላል። የእስራኤልንም ክብር በየአደባባዩ ይመሰክር ነበር።


የልጄን ሞት አውቃለሁ በዚያው ልክ ግን ማንንም እንዳልከዳ እና እንዳላታለለም ጭምር አውቃለሁ።
ልጄ የዘወትር ፍላጎቱ የእስራኤልን ከፍታ ማየት ነበር፣ በአፉም ይሄ አይለየውም ፣ በተግባሩም አሳይቷል።

አንድ ቀን በጎዳና ላይ ስንሄድ ይሄ አሁን ከዳው የሚባለውን ኢየሱስን አገኘነውና እኔን ጥሎ እሱን ተከትሎ ሄደ። ልቤ ግን ይህን ማድረግ እንደማይገባው ያውቅ ነበር።
ተመልሶ ሰላም ሁኚ በማለት ሲሰናበተኝ መሳሳቱን ነግሬው ነበር ግና አላደመጠኝም።


ከእንግዲህ ስለልጄ አትጠይቁኝ

ከይሁዳ እናት በላይ ክብር ወዳገኙት እናቶች ሂዱና እነሱን ጠይቁ።
ወደ ኢየሱስ እናት ሂዱ። በእኔ ልብ ያለፈው ልጅን የማጣት ሰይፍ በእርሷም አልፏልና የሚሰማኝን በሚገባ ልትገልፅላችሁ ይቻላታል፣ ያንጊዜ ትረዱኝ ይሆናል።"

ንባብ- Jesus The Son of Man by Kahlil Gibran
ትርጉም - በሱራፌል አየለ
@wegoch
@wegoch
Forwarded from Mikiyas Liyew Tadesse
ከጀመርነዉ 'ሚቀጥል
አድምጡማ
@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
የጀመርነዉ ኹሉ መባቻ ሲበጅለት
@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
#ወግ_ብቻ
.
ኔልሰን ማንዴላ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የህግ ትምህርት በሚማሩበት ጊዜ ነጭ
ፕሮፌሰር አስተማሪ ነበራቸው። ስሙም ፒተር

አንድ ቀን ፕሮፌሰር ፒተር በአንድ ምግብ ቤት ምግባቸውን እየበሉ ሳለ
ማንዴላ
በአጋጣሚ ምግብ ይዘው ከአጠገባቸው ይቀመጣሉ። ዘረኛው ፒተርም "አቶ
ማንዴላ! አሳማና 'ርግብ ለመብል አብረው አይቀመጡም!" ሲላቸው ብልሁ
ማንዴላም
"አይጨነቁ ፕሮፌሰር በርሬ እሄዳለሁ" ብሏቸው ሌላ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ።

በዚህ የተናደደው ፒተር በሌላ ቀን ቂሙን ሊወጣበት ያስባል። አንድ ቀንም
ፕሮፌሰሩ ክላስ ውስጥ እያስተማሩ

" ማንዴላ በመንገድ ላይ እየሄድክ ሁለት ቦርሳዎችን ብታገኝና በአንደኛው
ቦርሳ
'ገንዘብ' በሌላኛው ቦርሳ ደግሞ 'ጥበብ' ቢኖር የትኛውን ትወስዳለህ?" ብሎ
ማንዴላን ሲጠይቀው

ማንዴላም"ገንዘቡን እወስደዋለሁ" …ብሎ መለሰለት። ፕሮፌሰሩም በድል
አድራጊነት
"አንተ ሞኝ ነህ እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ጥበብ ያለበትን ቦርሳ እወስድ ነበር"
ሲለው ማንዴላ ፈገግ እያለ
"ልክ ነህ ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው" አለው።
በዚህ ሁሉ ነገር የተበሳጨው ፕሮፌሰር ፒተር የማንዴላ የፈተና ወረቀት ላይ
'ደደብ' ብሎ ይፅፋል። ሌሎች ተማሪዎች የታረመላቸውን የፈተና ወረቀት
ሲያዩ
ማንዴላ ደደብ
የሚለውን ፅሁፍ ከወረቀቱ ላይ አየና ተገረመ ከዛም ወደ ፕሮፌሰሩ ሄዶ

"ይቅርታ ቲቸር ፊርማህን ብቻ ነው ያስቀመጥክልኝ ውጤቴን ረስተኸዋል"
ብሎት እርፍ ፡፡

ካነበብኩት
@Wegoch
@Wegoch

Creadit yeneta
Forwarded from ወግ ብቻ (ልዑል) via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ወግ_ብቻ
ሥጋ ነፍስን ሲያሸንፍ ኃጢአተኛ፤
ነፍስ ደግሞ ሥጋን ሲያሸንፍ ፃድቅ ትሆናለህ።
----------------------
የሚስቲሲዝም እምነት አራማጆች አንድን ነገር በጥልቀት ማሰብ፣ ማሰላሰል ከዚያም በነገሩ ውስጥ መዋሐድ ነው ይላሉ።
ጠቢቡ ሰለሞን ‹‹ሰው በልቡ እንዳሰበ እንደዚያው ነው... /As the man thinks, so is he...›› ይላል። የምታስበውን፣ የምታሰላስለውን ትሆነዋለህ፤ ለምን ቢሉ ከማሰብ ማመን ይመጣልና፤ በአመኑት ነገር መኖር ደግሞ የሰው ባህርይ ነው።

ሚስቲሲዝም ጅማሬው ሃይማኖት ነው። በጥልቅ የምታሰላስለው አንድ ነገር አለ። በዚያ ነገር ልብህን ታፀዳለህ፤ ዕውቀትን ትቀስማለህ፤ ራስህን ወደ ሌላ ዓለም ታሸጋግራለህ። በዚህም ግብህ አንድ ነው። የምታሰላስለው ነገር ላይ መድረስ። ያ ነገርም ፈጣሪ ነው ይላሉ።
. . . . .
--------
አንድ የቻይና መነኩሴ ከፍተኛውን የሚስቲሲዝም ደረጃ ይጨብጥ ዘንድ ወደ ታዋቂው የዜን መምህር ሄደ። በዚያም ጥሩ አቀባበል ተደርጎለት በነጋታው ወደ ልምምዱ ገባ። በጥልቀትና በፀጥታ ማሰላሰልን ተነግሮትም ይህንኑ ጀመረ።

በመጀመሪያዎቹ አስራ ሁለት ዓመታት ከአንደበቱ የወጣ ቃል ቢኖር፦ ‹‹የምተኛበት አልጋ አልተመቸኝም...›› በማለት ለመምህሩ መናገሩ ነበር።
መምህሩ አሁንም መነኩሴው በተመስጦ ማሰላሰሉን እንዲቀጥል ነገሩትና አስራ ሁለት ዓመት ጨመረ።

በእነዚህ ቀጣይ አስራ ሁለት ዓመታት ደግሞ አሁንም መነኩሴው ከአንደበቱ የወጣ ቃል ቢኖር አንድ ብቻ ሲሆን ይኸውም ‹‹ምግቡ አልተስማማኝም›› የሚል ነበር። መምህሩ ሌላ አስራ ሁለት ዓመት አዘዙለት።

በእነዚህ አስራ ሁለት ዓመታት ደግሞ ይበልጥ ፀጥታና ማሰላሰልን ቢያጠናክርም በመጨረሻው ዓመት ግን አንዲት ቃል ወጣው፦ ‹‹በቃኝ!›› የሚል ነበር።

መምህሩም ይኽን ሲሰሙ፦ ‹‹እውነትህን ነው። እዚህ ባሳለፍካቸው ሰላሳ ስድስት ዓመታት ውስጥ የኖርከው በማጉረምረም ነው። በዚህም ምክንያት የመጀመሪያውን ደረጃ እንኳን ማለፍ አልቻልክምና ቢበቃህ ጥሩ ነው...›› በማለት አሰናበቱት።
. . . . .
በሌላ ጊዜ አንድ ወጣት መነኩሴ ወደ ዜኑ መምህር መጣና በተመስጦ ለማሰላሰልና የእውነትን ጫፍ ለመጨበጥ ያደረበትን ፍላጎት ነገራቸው። ከመምህሩ ያገኘው መልስ ግን ጩኸት የተቀላቀለበት ሳቅ ነበር።

በዚህም ተደናግጦ ወደ ቤቱ በሐዘን አመራ። በነጋታው ተመልሶ ወደ መምህሩ በመሄድ፦
‹‹መምህር ሆይ፤ ትናንት መጥቼ ስለ ሚስቲሲዝም በምጠይቅዎ ሰዓት በሳቅዎ አባረሩኝ። ጥፋቴን ሊነግሩኝ ይችላሉ?›› አለ።

መምህሩም መሳቃቸውን ጀመሩ። ቢሆንም እንደ ትናንቱ አልገፉበትም። ሳቃቸውን አቋርጠው፦
‹‹አንተ ከጥጃ አትሻልም›› አሉት። መነኩሴው ከትናንቱ ይልቅ ዛሬ ደነገጠ።
‹‹እንዴት ከጥጃ አልሻልም?›› አላቸው።
‹‹የእኔን ሳቅ ጥጃ ብትሰማ እየቦረቀች ትዘል ነበር፤ አብራም ትስቅ ነበር ... አንተ ግን ከመደንገጥህ የማዘንህ...›› አሉት።

መነኩሴው ከጥጃ የማነሱን ጉዳይ በዚሁ ማሰላሰል ጀመረ። መምህሩም አስራ ሁለት የማሰላሰያ ዓመት አዘዙለት።
-----------------------------
📓 "ጥ በ ብ"
🖌 ከ ጲ ላ ጦ ስ
(ኃይለጊዮርጊስ ማሞ)
📖 📖 📖 📖 📖 📖
#ወግ_ብቻ
.
የጠቢቧ ሴት ድንጋይ
——
ጠቢቧ ሴት በተራሮች መካከል ስትጓዝ ወንዙ ላይ አንድ የከበረ ድንጋይ አገኘች። በቀጣዩ ቀን ደግሞ አንድ የተራበ ሌላ ተጓዥ አገኘች፡፡ ጠቢቧ ሴትም የያዘችውን ስንቅ ከፍታ እንዲመገብ አደረገችው፡፡

የተራበው መንገደኛም ምግቡ ይብቃኝ ብሎ ከመሄድ ይልቅ ያገኘችውን የከበረ ድንጋይ ተመለከተውና የከበረውን ድንጋይ እንድትሰጠው ጠየቃት፡፡ የከበረውን ድንጋይም ያለምንም ማቅማማት ሰጠችው፡፡

ተጓዡም ዕድል ፋንታውን እያሰበ እያመሰገነ ጉዞውን ቀጠለ። የከበረው ድንጋይ ሙሉ ሕይወቱን ያለምንም ሥራ በተድላ እና በደስታ ማሳለፍ እንዲችል እንደሚያደርገው ያውቅ ነበር፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን ድንጋዩን ለመመለስ ወደ ጠቢቧ ሴት ተመልሶ መጣ፡፡

"እያሰብኩበት ነበር" አለ "ድንጋዩ ምን ያህል የከበረ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ከዚህ የበለጠ የከበረ ነገር ትሰጭኛለሽ ብዬ ተስፋ ስላደረኩ ለመመለስ ወስኛለሁ፡፡ እጅግ የከበሩ ነገሮችን ለመስጠት የሚያስችልሽን የበለጠ የከበረ ነገር እንድትሰጭኝ እሻለሁ፡፡ ይህን ክቡር ድንጋይ እንድትሰጭኝ ያደረገሽን የከበረ ነገር ስጭኝ፡፡"
***
በምድር ላይ የጥበብ ሁሉ ጥበብ ራስን መግዛት ነው፡፡ ራሳችንን መግዛት የሚያስችለንን የከበረውን ጥበብ ከከበሩ ቁሶች በላይ አንሻ፡፡ ደስታ የሚገኘው በከበሩ ቁሶች ሳይሆን በከበረ ማንነት እንጂ።
የከበረ ማንነት ደግሞ ራስን መግዛት ነው፡፡
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
አንድ ወፍ ዛፍ ላይ አለች። አንተ ደግሞ ርቦሀል። ወፏን ገድለህ መመገብ ወይንም ሌላ አማራጭ መፈለግ አለብህ? ይህንን ምርጫህን ለመወሰን ሳይንስ አያገለግልህም። ወፏን ለመብላት ከፈለክ ወንጭፍ ወይም ባላ ለመስራት ከወሰንክ ግን... ሳይንስ ወደፍላጎትህ ለመድረስ ጣልቃ ይገባል።

ወፏን ከዛፍ ላይ በወንጭፍ አማካይነት ከመታሃት በኋላ አሳዘነችህ እንበል። ልታድናት ፈለክ። ማዳን መወሰንህ ምርጫ ነው። ምርጫህ የሚወሰነው እንደ እምነትህ ነው። እምነትህ ከሀይማኖት ጋር የተሳሰረም የተፋታም ሊሆን ይችላል። እንደመሰለህ የምትወስነው ነው። ወፏን ለማዳን ከፈለግህ የእንስሳት ሀኪም ዘንድ ጠአቅፈህ ትወስዳታለህ። የእንስሳት ሀኪሙ ሳይንስን ነው በአንተ ውሳኔ ላይ ጣልቃ የሚያስገባው። ሳይንስ ለመግደል ስትወስን የጦር መሳሪያን በመስራት፣ ለማዳን ስትፈልግ ሀኪምን ተመስሎ ይመጣል። ወደ ምርጫህ ማቋረጫውን እንጂ የቅድመ ምርጫ ሚዛንህ አይሆንም። ሚዛንህ እምነትህ ነው። ስሜትህ ነው። ስሜትህ እንጂ... ተጠባጩ እውነታ አይደለም ግብረ ገባዊ እሴትህን (moral value) የሚሰራልህ።


ከሌሊሳ ግርማ ነፀብራቅ ገፅ 79 የተቀነጨበ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
መገናኛ ጋር ነው። ለታክሲ ሰልፍ ተሰልፌያለሁ። ከፊቴ እናትና ልጅ ቆመዋል። በመሐል አንዱ መፅሀፍ አዟሪ መጣ። በእጁ ብዙ መፅሀፍት ይዟል።

"የልጆች መፅሀፍ በ20 ብር ብቻ" አለ ጮክ ብሎ።

"ግዢልኝ ግዢልኝ" አለች ትንሿ ልጅ እናቷን።

"አታርፊም አንቺ!" አለች እናቷ ኮስትር ብላ።

"የልጆች መፅሀፍ በ20 ብር ብቻ" አለ በድጋሚ።

ልጅቷ "እማዬ ተይ ግዢልኝ" ስትል በቁንጥጫ ልምዝግ አደረገቻት። ልጅቷ ማልቀስ ስትጀምር መፅሀፍ አዟሪውን ጠራሁት። የተረት መፅሀፉን ተቀብዬ 20 ብር ከፈልኩኝ። መፅሀፉን ስሰጣት ልጅቷ በፈገግታ ስትቀበለኝ እናትየው በግልምጫ አነሳችኝ። እኔ ግን በልቤ ለራሴ እንዲህ አልኩ፦

"ይኼኔ መጫወቻ ቢሆን አስር ትገዛላት ነበር። ለልጆቻችን ለምን "ቁምነገር" አንገዛም?! ቢያንስ የአርቴፊሻል ሽጉጥን ያህል ስነልቡናዊ ቀውስ አያስከትሉም"

ሱራፌል አየለ
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
ፈላስስፎችና የተፈጥሮ መልስ

ሾፐንሃወር የተባለው ፈላስፋ ለሴቶች የተንሸዋረረ አመለካከት ነበረው። እንደውም በፍልስፍና ፅሁፉ ሴት ሰው አይደለችም እስከማለት ደርሷል። ታዲያ ከዚህ ፍልስፍናው በኋላ አንዲት ሴት ይወዳል። ይሁን እንጂ ሰው አይደለችም ብሎ የፈረጃት ሴት ፊት ነሳችው። ሴት ሰው ናት ወይ የሚለውን ጥያቄ ተፈጥሮ ራሷ መለሰችው።

ኒቼ ታላቅ ፈላስፋ ነው። የእግዚአብሔርን ሞት ያረዳን ኒቼ ነበር። በእርግጥ ኒቼ ወፈፍ ያደርገው ነበር። እናም እግዚአብሔርም በተራው የኒቼን ሞት አረዳን። ከተፈጥሮ ጋር ታግሎ ያሸነፈ የለም። ከተፈጥሮ የበለጠ ጠቢብ የለም። የአዋቂዎች ጥበብ ከንቱ ነው።

ዲዎጋን ተፈጥሮ ባይሆንም የሱን ልጨምርላችሁ፦

ፕሌቶ(አፍላጦን) ለተማሪዎቹ ሰው ማለት ሁለት እግር ያለው ክንፍ አልባ እንስሳ ነው ብሎ አስተማረ። በማግስቱ ዲዎጋን ክንፉ የተነቀለ ዶሮ ይዞ መጥቶ "ይኸውላችሁ የፕሌቶ ሰው" ብሎ በተማሪዎቹ አስቆበታል።

ምንም ያህል ብልህ ብትሆኑ የበለጠ ብልህ አለ!
ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
አንድ ቀን ጋሽ ስብሐት በጠና ታሞ ልንጠይቀው ሄድን። የጠያቂዎች ጋጋት በዝቶበት ስልችት ብሎት ኖራሯል። ከመሃከላችን አንዱ በጥያቄ ያጣድፈዋል። ጋሽ ስብሐት ብስጭት አለ። ስሙን ጠራው ፣ "እባክህ በሩን ከውጭ ትዘጋልኝ ...

*

ጋሽ ስብሐትን ቃለመጠይቅ ለማድረግ አንድ ጋዜጠኛ ወደ ቤቱ ሄደ። ጋሽ ስብሐትም እንግዳውን ተቀብሎ ሻይ ጣደ።
ጋዜጠኛው ስለ ስራዎቹና ስለ ጋሽ ስብሐት አንተ እኮ እንዲህ ነህ እያለ መለፍለፍ ጀመረ። ሻዩ ፈላ። ጋሽ ስብሐት ሁለት ብርጭቆ አቅርቦ ሻዩን መቅዳት ጀመረ።

የጋዜጠኛው ብርጭቆ ሞልቶ መፍሰስ ጀመረ። " እንዴ ጋሽ ስብሐት እየፈሰሰ እኮ ነው። "
" አንተም በኔ መረጃ ሞልተህ እየፈሰስክ ነው። ታዲያ ምንድን ነው ልጠይቀኝ የመጣኸው? "

*

ጋዜጠኛ:- ጋሽ ስብሐት በዓሉ ግርማን እንዴት ትገልጸዋለህ?
በዓሉ ግርማ ዛሬ ቢኖር የኔን ስም አታውቀውም ነበር። እግዜርም ይሄን አውቆ በጊዜ ቀጨልኝ።
@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለጊዜ ተዋቸው!


በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። ታዲያ ይህ ሰው፣ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በኑሮው ከሚገጥመው ችግር የተነሳ፣ ሁልጊዜም በህይወቱ ደስተኛ አልነበረም። አንድ ቀን ግን ከሚኖርበት ሥፍራ በቅርብ ርቀት የምትገኝ ከተማ ዘንድ፣ አንድ ታላቅ የኃይማኖት አባት ከአጃቢዎቻቸው ጋር እንደመጡ ይሰማል። ይህን ጊዜም እኚህን አባት ማግኘት አለብኝ ብሎ ይወስናል።

በመሸም ጊዜ እኚህ አባት ያሉበት ሥፍራ ይደርስና፡ እሳቸውን ለማግኘት ቁጭ ብሎ መጠባበቁን ይይዛል። ከረጅም ቆይታ በኋላም እኒያን አባት ያገኝና ጥያቄውን ይጀምራል። "አባቴ ሆይ፥ በህይወቴ ፍፁም ደስተኛ አይደለሁም፤ በቃ ሁሌም በችግር የተከበብኩኝ ሰው ነኝ... በዚህ በኩል የሥራ ጭንቀት፣ በዚህ ደግሞ የጤና ቀውስ፣ በዛላይ የቤቴ ውስጥ ችግር... ብቻ ተደማምሮ እረፍት ነስቶኛል፣ ደስታም ርቆኛል፤ እባክዎትን አንዳች የመፍትሄ ሀሳብ ይስጡኝና፡ ደስተኛና የሰላም ኑሮ እንድኖር ይርዱኝ!"

ሽማግሌውም ፈገግ ብለው፤ "ልጄ፥ ለችግርህ ነገ ጠዋት ላይ መፍትሄ እሰጥሃለሁ፤ ነገር ግን አሁን ባዝህ፣ ጥቂት የኔን ሥራ ልትሠራልኝ ትችላለህን?፤ ሰውዬውም በዚህ ይስማማል። እሳቸውም ቀጥለው፦ "በጉዞአችን የያዝናቸው መቶ ግመሎች በዚህ ይገኛሉ፤ እናም ዛሬ ምሽት የነርሱን ነገር፡ አደራውን ላንተ ሰጥቻለሁ፤ ሁሉንም ግመሎች እመሬት ላይ ካስቀመጥክ በኋላ ወደ መኝታ መሄድ ትችላለህ"። ይህንንም ብለው ወደ ድንኳናቸው ሲያቀኑ፣ ሰውዬውም የታዘዘውን ሊያደርግ ምሽቱን ግመሎቹ ዘንድ አመራ።

በቀጣይ ቀንም ሽማግሌው ማልደው ወደ ሰውዬው በማቅናት "ልጄ፥ ሌሊቱን ጥሩ ተኝተህ አደርክ?" ብለው ይጠይቁታል። ሰውዬው ግን ኅዘን በተሞላበት ስሜት ሆኖ "አባቴ፥ ለዐፍታ እንኳን እንቅልፍ ሳይወስደኝ ነው ሌሊቱ የነጋው። ብዙ ለፋሁ፣ ብዙም ጣርኩኝ፡ ይሁንና በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች እንዲቀመጡ ማድረግ አልቻልኩም። አንዳንዶቹ ራሳቸው ይቀመጣሉ፤ አንዳንዶቹ ግን ላስቀምጣቸው ብሞክርም እንኳን አይቀመጡም፤ አንዱ በዚህ በኩል ሲቀመጥ፡ በሌላ በኩል ያሉት ይነሣሉ"።

ይህን ጊዜ ሽማግሌው ፈገግ እያሉ እንዲህ አሉ፦ "ካልተሳሳትኩኝ፡ ይህ የሆነው ትላንት ማታ ነው አይደል?"

- ራሳቸውን በራሳቸው ያስቀመጡ ብዙ ግመሎች ነበሩ!?

- ብዙዎቹ ደግሞ በአንተ ጥረት ሊቀመጡ ችለዋል!?

- ቀሪዎቹ ልታስቀምጣቸው ሞክረህ እንኳን አልተቀመጡም፤ ከቆይታ በኋላ ግን በጊዜ ውስጥ ራሳቸውን አስቀምጠው አግኝተሃቸዋል!?

ሰውዬውም፦ "አዎ! አዎ!...ትክክል!" ብሎ መለሰ።

ሽማግሌውም ቀጠሉና፦ "ስለዚህ አሁን አንድ ነገር ተረዳህን?፤ በህይወት ያሉም ችግሮች እንዲሁ ናቸው...

- አንዳንዶቹ በራሳቸው መፍትሄ ያገኛሉ።

- አንዳንዶቹ በአንተ ጥረት መፍትሄ ያገኛሉ።

- አንዳንዶቹ ደግሞ በአንተ ጥረት እንኳን አይፈቱም፤ እነዚህን ችግሮች ለጊዜ ተዋቸው። ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ በራሳቸው ይፈታሉና/መፍትሄ ያገኛሉና/።

ትላንት ማታ፣ ምን ያህል ብትሞክር በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች ማስቀመጥ እንዳልቻልክ ትምህርት ወስደሃል። አንዱን ግመል በዚህ ጋር ስታስቀምጥ በሌላ በኩል ያሉት ይነሣሉ። ልክ እንዲሁ፤ እዚህ ጋር አንዱን ችግር ፈታሁ/ተፈታ ስትል እዛ ደግሞ ሌላ ችግር ተነስቶ ይጠብቅሃል። ህይወት እንዲህ ነውና!። ችግሮች የህይወት አካል ናቸው፤ አንዳንድ ጊዜ ጥቂት፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ በርካታ ችግሮች ይኖራሉ። ይሄ ማለት ግን ስለነሱ ሁሌ ማሰብ አለብህ ማለት አይደለም። እነሱን ለጊዜ እየተወክ ወደፊት ተጓዝ። በእያንዳንዱ እርምጃም ወደ ዓላማ-ህይወት (Purpose of life/self- realization/) ማደግን ተማር።

ልብ በል፤

• አንዳንድ ጊዜ፤ ደስታን ለማወቅ በኅዘን፣ ዝምታን ለማድነቅ በጩኸት፣ የመኖርን ዋጋ ለማወቅ ባለመኖር መንገድ ልታልፍ ግድ ነው።

ይኸውልህ፤ ህይወት በተቃርኖ የተሞላች ነች። እያንዳንዱ ስኬት ከሸክም ጋር ነው የሚመጣው። ትልቅ ቤት ማግኘት ስኬት ሲሆን፣ ብዙ የሚጸዳ መኖሩ ሸክም ነው። ልጅ መውለድ ስኬት ሲሆን፣ በእኩለ ሌሊት መነሳቱ ሸክም ነው። ባለስልጣን መሆን ስኬት ሲሆን፣ የህዝብን ጩኸት ማስተናገዱ ሸክም ነው።

ብዙ ጊዜ የምንሠራው ስህተት- ስኬቱን ያለ ሸክም ከመፈለግ የሚመጣ ነው። ይህ ግን እውነታው አይደለም። የሚመጡት በጥቅል (package) ነው። ዋናው ነገር፣ ሸክሙም እያለ በስኬቱ/በበረከቱ መደሰትን መማሩ ላይ ነው!!
@wegoch
@wegoch
@wegoch
መፅሐፍትን መቅዳት ትጉህነት ነው

ስለ ቅኔ ሳስብ በዘመኔ ማንበብ ከቻልኩዋቸዉ ጥቂት መፅሐፍት መኀከል አንዱን ላንሳ ''ኀሠሣ'' ይሠኛል ፀኀፍትዋ ሕይወት ተፈራ ናት። ቀድሞ ነገር ''Mine to Win'' ብላ በ እንግሊዝኛ ቋንቋ ነበረ የፃፈቸዉ ፥ ኃላ ላይ ታድያ ሕይወት ታደሰ የተባለች ሰዉ ይኽንኑ መፅሐፍ ወደ አማርኛ ቋንቋ ተርጒማ በድጋሚ ለንባብ አብቅታው ነበረ። ስለ መፅሐፉ ለማለት ብዙ ይፈልጋል እና እሱን እንመለስበታለን አኹን ግን እንደዉ ከመፅሐፉ ላይ ከተለያዩ ገፆች ያገኘዋቸዉን ፁኹፎች እቀዳለኹ ትጒህም ነኝና ፥ ለማነሳቸዉ ኹለት ገፆች ላይ የሰፈሩ ሐሳቦች ይረዳን ከኾነ ዘንድ ይኽ መፅሐፍ ባንድ ቅኔን ለመማር ከፍተኛ ፍላጎት ስላሳየ ተዋነይ ስለተባለ ወጣት ያተኩራል ስለ ቅኔ ህይወቱ ብቻም ሳይኾን እንዴት የፈለገዉን ነገር ማግኘት ስለመቻሉ ፣ ቀድሞ ነገር ፍላጎቱ የት ድረስ እንደነበረ ፣ ፈተናዎቹን እንዴት ባስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ  ቢኾን እንኳን ማለፍ ስለመቻሉ ከኹሉም ከኹሉም ደግሞ ቅኔን ለመማር ለማወቅም ያለዉን ውጣ ውረድ እና ኹናቴ በጉልህ አድርጋ ሕይወት ተፈራ ያሳየችበት መፅሐፍ ነው። እንዳልኳቹ ይኽ ከመፅሐፉ ስለምኖስደዉ ኀሳብ እንደ መኳተኛ ነውና ወደ ፁኹፉ ላዝግም

ገፅ 26 ላይ ያገኘኹትን ላስቀድም
 ( ተዋነይ'ን አጎቱ ዐወቀ በሚመክረዉ ጊዜ )

'' ገና ስትፀነስ በህይወት ዘመንኽ ትልቅ ቦታ የመድረስ ምርጫ ተመነሻዉም የተሰጠኽ መኾኑን ተገንዘብ። ፈጣሪ ሕይወት ሰጥቶኻል ፥ ሕይወትህን ደርዝ እምታስይዘዉ ግን አንተ ነኽ። ቢያንስ መሞከር አለብኽ። ወኔ ማለት መለወጥ 'ምትችለዉን ነገር መለወጥ መቻል ነው።

ገፅ 110 ላይ ደግሞ ተዋነይ ይኽን ይለናል

ቅኔ ለመቁጠር ግብዓት የኾኑትን ማኀበራዊ ደንቦች ፣ ልማዶች ፣ የሰዉ ልጅ ባህርይ እንዲኹም ተፈጥሯዊውን ዓለም በተመለከተ ጥልቅ ዕውቀት አቀበለኝ።
    የወንድ ልጅ ቁንጮ ፣ የልጃገረድ ጋሜ ፣ የአበባ መዓዛ ፣ የሴት ልጅ ውበት ፣ የመነኩሴ ብፅዕና ፣ ሞፈርና ቀንበር ፣ የጨቅላ ሞት ፣ የሴት ለጋስነት ፣ የወደቀ ዛፍ ፣ እሾኻማ ጽጌ ፣ ተፍለቅላቂ ኮከብ ፣ ብራ ቀን ፣ የማለዳ ንፋስ ሽውታ ፣ የወፍ ላባ ኩሽኩሽታ እንዲኹም ነጎድጓዳማ ሰማይ ኹሉ ጥልቅ ትርጉም ያዘሉ ተምሳሌቶች ናቸው።
      __________//_____

ኸዚኹ ገፅ ላይ የተቀረዉን እቀዳለኹ መቅዳት ትጒህነት ነውና።

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
ይህቺን የካህሊል ጂብራንን ጽሑፍ አንብቡና በፍቅር ውደቁ ::

የተሰበሩ አክናፍ (The Broken Wings)
( ካህሊል ጂብራን )


የፍቅር ምትሃታዊ ጨረር መንፈሴን በመዳበስ ዐይኖቼን የከፈተልኝ በ18 ዓመት ዕድሜዬ ነበር፡፡ መንፈሴን በውበቷ ያነቃቃችውና ወደ ፍቅር አፀድ የመራችኝ ሴት ደግሞ ሰልማ ካራሚ ነበረች፡፡

ውበትን አመልክ ዘንድ ራሷን ምሳሌ በማድረግ የፍቅርን ሀሁ ያስተማረችኝ ሰልማ ካራሚ ናት፡፡ የእውነተኛ ሕይወትን ግጥም ለመጀመሪያ ጊዜ ያዜመችልኝም እርሷ ነበረች፡፡

ማንም ወንድ የመጀመሪያ ፍቅሩን አይረሳም፡፡ የትውስታው ሕመም ልቡን እየጐዳው እንኳን የመጀመሪያ ፍቅሩን መላልሶ ያስታውሳል፡፡ የእያንዳንዱን ወንድ ብቸኝነት ወደሙሉ ሐሴት የምትቀይር ‹‹ሰልማ›› በሁሉም ሕይወት ውስጥ አለች፡፡ የወጣቱን ቀዝቃዛ ልብ በፍቅሯ በማሞቅ የደነዘዘ ምሽቱን በሙዚቃ የምትቀይር ‘ሰልማ' በሁሉም ሕይወት ውስጥ አንዴ ትከሰታለች፡፡


የቅዱስ መጽሐፍትን ምሥጢር ለመረዳት አእምሮዬ በተወጣጠረበት ወቅት ነበረ የሰልማ ውብ ከናፍር ለጆሮዬ ፍቅርን ሹክ ያሉት፡፡ ሕይወቴ ባዶ ነበር - ልክ አዳም በገነት እንደነበረው! ከዚያም ሰልማን እንደ ብርሃን ማማ ከርቀት አየኋት፡፡ እርሷ የልቤ ሄዋን ናት፡፡ ልቤን በአስደናቂ መረዳት ሞልታ የሕይወትን ትርጉም አሳየችኝ፡፡


የመጀመሪያዋ ሄዋን በራሷ ፍላጐት አዳምን ከገነት አስወጥታዋለች፡፡ የእኔዋ ሰልማ ግን በጣፋጭ ፍቅሯ አማካኝነት በራሴ ፍላጐት ወደገነት እንድገባ አደረገችኝ፡፡ ሆኖም የመጀመሪያውን ሰው የገጠመው እኔንም ገጥሞኛል፡፡ አዳምን ከገነት ያስወጣው እሳት የሆነ ቃል እኔንም ሳላጠፋና የተከለከለውን ፍሬ ሳልቀምስ ከገነት አባረረኝ፡፡

ዛሬ - ከዓመታት በኋላ - የቀረኝ ነገር ቢኖር የዚያ ውብ ሕይወት የሚያሳምም ትውስታ ብቻ ነው፡፡ ልቤን በሃዘን ፤ ዐይኖቼን በእንባ እየሞላ ያሰቃየኛል፡፡ የእኔዋ ውድ ሰልማ ሞታለች፡፡ የተሰበረ ልቤና በጥድ ዛፍ የተከበበ መቃብሯ ብቸኛዎቹ መታወሻዎቿ ሆነዋል፡፡ የሰልማ ምስክር ሆነው የቀሩትም ባዶው ልቤና መቃብሯ ናቸው፡፡


መቃብሯን የሚጠብቀው አስፈሪ ፀጥታ የሳጥኗን ውስጥ ምሥጢር ለፈጣሪ እንኳን አሳልፎ አይሰጥም፡፡ በሥራቸው አካሏን መጠው የሚመገቡት የዛፍ ቅርንጫፎችም ምሥጢሯን አይተነፍሱትም፡፡ የልቤ ሲቃ ብቻ ነው ፍቅር ፣ ውበትና ሞት የሠሩትን ድራማ የሚገልፀው፡፡

በቤሩት የምትኖሩ ወጣት ጓደኞቼ ሆይ - በመቃብሩ ሥፍራ ስታልፉ የእግራችሁ ዳና እንዳይረብሻት በዝግታ ተራመዱ፡፡ የሰልማ መቃብር ጋር ስትደርሱም አቅፎ ላስተኛት መሬት እንዲህ በሉልኝ፡- ‹‹በባህር ማዶ የፍቅር እሥረኛ የሆነው የጂብራን ተስፋዎች በሙሉ እዚህ አርፈዋል፡፡ እዚች ቦታ ላይ ደስታውን አጣ ፤ እንባውን አደረቀ ፤ ፈገግታውንም ረሳው፡፡››

የጂብራን ሃዘን ከመቃብሩ ጐን ካሉት ዛፎች ጋር ያድጋል፡፡ መንፈሱም ከፍ ብሎ ከዛፎቹ በላይ የሰልማን መሞት በሃዘን ያስታውሳል፡፡ ትናንትና ውበትን የዘፈኑት የሰልማ ከናፍር ዛሬ ከምድር በታች የተሸሸጉ ምሥጢራት ሆነዋል፡፡


‹‹ኦ - ወዳጆቼ! ባፈቀራችኋቸው ደናግል ስም እለምናችኋለሁ፡፡ በዚህ ስታልፉ ለተረሳችው ፍቅሬ አበባ አስቀምጡላት፡፡ አንድ አበባ ማኖር በፅጌሬዳ ላይ እንደምትፈጠር የማለዳ ጤዛ የንጋት አብሳሪ ነውና፡፡›


( ' መናፍቁ ካህሊል ጂብራን ' ከተሰኘው መጽሐፍ የተቀነጨበ )

@wegoch
@wegoch
@paappii
[' #Every_onE_has_a_storY ']
.
(#አሌክስ_ይህ )
.
.
.
ታቅዶ : በሚሖነውና : ያለ : እቅድ : በሚከሰተው : ገጠመኝ : መሓል : ደስታ : የሚባለው : ተወዳጅ : የስሜት : እንክብል : በተስፋ : ቅጠል : ተጠቅልሎ : ይገኛል :: መውደቅ : መነሳቱ : ማጣት : ማግኜቱ : ውሎን : ኣሪፍ : ህይወትን : ጣፋጭ : ያደርጋል : ጥሩ : የሚመስለው : ሑሉ : ጥሩ : ብቻ : ዐይደለም : መጥፎ : የሚመስለው : ኁሉም : መጥፎ : ብቻ : ኣይደለም
. . .
በህይወት : ውስጥ : ሑሉም : ነገር : የታቀደና : ቀድሞ : የሚታወቅ : ቢሖን : ኖሮ : ህዪወት : ሲበዛ : ኣሰልች : እና : ብዙም : የማትጣፍጥ : ትሖን : ነበር . . . በህይወት : ውስጥ : ምንም : ኣይነት : በእቅድ : የሚሖን : ነገር : ባይኖር : ኖሮ : ኣብዛኛው : የሕይወት : ገጠመኝ : ኣደጋ : የበዛበትና : ከባድ : ይሖን : ነበር . . .
. . .
ሑሉም : የራሱ : ታሪክ : ሑሉም : የራሱ : ገደል : ዐለዉ : ስለዚሕ : ሰዎችን : ኣትናቅ : ከማይገባቸው : ያለፈ : ቦታም : ኣትስጣቸው : ክፉ : ተግባርን : ሑሉ : ዐውግዝ : ከክፉ : ነገሮች : ኁሉ : ራቅ : ሰው : ነሕና : በሰዎች : ላዪ : ግን : ኣትፍረድ : ክፉ : ኣስተሳሰብ : እንጂ : ክፉ : ሰው : ኣልነበረም : ሖኖም : ግን : ክፉ : ሃሳብ : ካላቼው : ሰዎች ጋር : መዋል : ክፉ : ከማድረግ : ኣይተናነስም : መቼቱ : ይለያዪ : እንጂ : ኁሉም : ሰው : የሚያስደስት : ገጠመኝ : የሚያሳምም : ትውስታ : ኣለዉ : ሑሉም : ሰው : የተነገረም : ያልተነገረም : ታሪክ : ዐለው : የተፃፈና : ያልተፃፈ : የሚያስደስት : የሚያሳዝን : ሌላም : ሌላም. . .
. . .
የጊዜ : መልክ : ዥንጉርጉር : ነው : ኣንዱ : ትናንት : ኣቀርቅሮ : በተራመደበት : ጎዳና : ዛሬ : በኩራት : ይራመድበታል : ኣንዱ : ትናንት : በልበ : ሙሉነት : በሄደበት : መንገድ : ዛሬ : ኣንገቱን : ደፍቶ : ያልፍበታል : ሑሉም : ኃይል : በጊዜ : ውስጥ : ነው : ጊዜ : ባንተ : ሲሖን : ሃዘንህን : በልክ : ላንተ : ሲኆንም : ደስታህ : ረብ : ይኑረው
. . .
ኁሉም : የደስታ : ስሜቶችህ : ዘላቂ : እንዳልሖኑ : ኁሉ : ሑሉም : ፈተናዎችህ : በጊዜ : ውስጥ : እንደ : ጤዛ : ተነው : ይጠፋሉ : ኣንዳንድ : ነገሮችን : ከጊዜ : ይልቅ : የኣንተ : ጥረትና : ውሳኔ : የሚፈታቸው : ሲሖኑ : ኣንዳንድ : ሑኔታዎች : ደግሞ : በጊዜ : ብቻ : የሚፈቱ : መሖናቸውን : መረዳት : ኣለብሕ : ስለዚህ : ነገሮች : ‘ለምን : ኣሑኑኑ : ኣልሖኑም’ : ብለሕ : ሙጥኝ : ኣትበል : ትናንት : ያስጨነቀሕ : ዛሬ : እንደሌለ : ሑሉ : ዛሬ : የሚፈትንህም : ነገ : ላዪ : ኣይኖርም : ኣብዝቶ : መጨነቅ : ህይወትን : ማባከን : ሲሖን : ኣብዝቶ : ግድየለሽ : መሖንም : ኅይወትን : ጣዕም : ኣልባ : ያደርጋል : ትናንት : ያልነበረህ : ጸጋ : ዛሬ : እንዳለኅ : ሑሉ : ዛሬ : ያለህ : ፀጋም : ነገ : ላይኖር : ስለሚችል : ባለህ : ነገር : ኣመስግን : ተደሰትም:: #GooD_EveninG
.
.
.
.
.
እና ደ`ሞ #Its_My_Dam

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ከዛሬ ጀምሮ ጥቁር ነኝ
ባንጋባም አብረን ሶስት አመት የኖርን ፣አንድ ልጅ የወለድኩለት ባለቤቴ እዚህ
ውጪ ሐገር ብዙ የኖረ: በአባቱ አፍሪካ በናቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነው። አቤት ፀባይ! ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስይዞ በጥሬው ካለወለድ ሊበደር የሚችልበት ወርቅ አመል አለው። ሌላውማ አይነሳ። --እና ትናንትና ለወንድሜ በዋትስ አፕ ደውየለት እናቴ በዝና የምታውቀውን ባሌን በካሜራ አየችው እና እጇን ማራገብ ጀመረች -- 'ወቸው ጉድ! ብለሽ ብለሽ ደሞ ቅዱስ ሚኻኤል ረግጦት : በጦሩ የሚያስፈራራው ሰው ጋር ትኖሪ ጀመር ? አለችኝ። (ወንድሜ ትከሻዋን በስሱ ገፋ እያደረገ ዝም በይ ነገር ይላታል ።) አብሬ የኖርኩትን ሰው እንደ አዲስ ዞር ብየ አየሁት ። ለሃያ ምናምን ጊዜ ገንዘብ ስንልክላት እኮ እንኳን ለእኛ ቤት ለክልሎች ሁሉ አዳርሰን ስናበቃ; ተርፎን ለጅቡቲ የደፋነው ምርቃት አሸክማን ነበር። ውለዱ ክበዱ አይለያችሁ ምናምን --- ብላን ነበር ። 'ወይ ሰው' አልኩ የገዛ እናቴን። ባለቤቴ ወደ ካሜራው ቀረብ አለ እና ፈገግ ብሎ በአክብሮት 'ሃው ዱዩ ዱ ' አላት 'ምን አለ ደግሞ ?' አቤት አቤት አፍንጫ! አቤት የአፍንጫ ገደል! አቤት አፈጣጠር! አይይ የኢትዮጵያ ሰው ጉዴን ስማ ! ጉዴን ስማልኝ የቶቢያ ሰው!--- አለች 'ባክሽ እማየ ደሞ ታበዥዋለሽ የኢትዮጵያ ሰው ምን ያርግሽ ? የኢትዮጵያ ጠላቶች በእሱ የአፍንጫ ቀዳዳ የሚገቡ መሰለሽ እንዴ ? ' ብግን ብያለሁ። ምንም ቢሆን አንድ ልጅ ወልጄለታለሁ ። ተስማምቶኝ ነው የምኖረው።
እናቴ እያበሸቀችኝ ነው።
"ኤዲያ ! ያገርሽን ሰው የወንዝሽን ሰው አጣሽ እና ነው ይሄንን ዘር የሚያበላሽ
ይይይይ ደግ አላረግሽም ። እናት ነኝ እኔ ካልነገርኩሽ ማን ይነግርሻል ? ለካ ባለፈው አቃዠኝ አባተተኝ የግብርኤል ፀበል ላኩልኝ የምትይው ለካ ከዚህ ጋር እየኖርሽ ነው ? " ብላኝ አረፈች ። መጮህ አማረኝ። እማ! አፍሪካዊ ነው እኮ ! በአንድ አህጉር በአንድ ካርታ ውስጥ ነን --- " የምለው ጠፋብኝ። "ተይ ተይ! የምን ካርታ ? " አለች በቁጣ። ይሄ ካርታ እና ቁማር ድሮም ትውልዱን ያበላሸው ። ስንቱ መሰለሽ በካርታ ሰበብ
መቅኖ አጥቶ የቀረው?" እያለች ተብከነከነች ሶፋው ላይ ጋደም ያለችው ልጄ ጭቅጭቃችንን ሰምታ ተነሳች ። ባለቤቴ ቢያባብላት ዝም እልል ስላለች በዛውም ለቤተሰብ እንዳሳይ ከእቅፌ ላይ አኖራት። 'እህእ የማን ልጅ ናት?' አለች ። እናቴ በግርምት። አንጀቴ ተንተከተከ ' የማን ትሆናለች? የእኛ ነቻ። ' አልኳት። 'እህእ የእናንተ ልጅ? የእ-ናን-ተ ልጅ ቱቱፍ ቱፍ ቱፍ ቱፍ--- አለች '
እየመረቀቻት መስሎኝ ተፅናናሁ።
'ስሟን ማን አልሻት?' ' ብርቱካን '
እናቴ በሳቅ ተንፈራፍራ ልትሞት፣ ወንድሜም ሳቅ ሲያፍነው ይሰማኛል።
ጥላቻ በነፍሴ ሲሰራጭ ተሰማኝ።
'እኔ ምልሽ ?' 'እ ' አልኳት 'እናንተ ምትኖሩበት እውጭ ሐገር : ጥቁር ብርቱካን አለ እንዴ? ' አለች። አዞረኝ ፣ አጥወለወለኝ ፣ ስልኩን ዘጋሁት ። ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና ! አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እና መተኛ ናት :- (ምነው ስብሰባ ተሰብስበው ብዙዎቹን ሲያንቀላፉ አይደል የምናያቸው?) መቀመጫ ላይ ተቀምጠን ካወጋን በሁዋላ ታዲያ: ስንግባባ ደግሞ አብረን ብንተኛ ምን ችግር አለው?' እንግዲህ ብር ን ወንዶ ብርቱካኔን መጥላት የለም። ሁለተኛም ለቤተሰቦቼ አልደውልም ። እኔ በጥቁርነቴ አምናለሁ እነሱ ደግሞ ፀይም እንደሆኑ ይቀጥሉ።
አዲዮስ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#abeba birhanu
#ወግ_ብቻ
.
......የዜን መሪ የነበረው ሪዮካን ተራ በተራራ ግርጌ ባለው አንድ
ትንሽ ጎጆ ውስጥ በጣም ቀለል ያለ ሕይወት ይመራ ነበር ፡፡ አንድ ቀን ምሽት አንድ ሌባ ጎጆውንለመዝረፍ ይመጣል። ነገር ግን ጓዳ ጎድጓዳው ውስጥ ምንም ነገር እንደሌለ ያያል ፡፡

ሪዮካን ከሄደበት ተመልሶ ሲመጣ ሌባውን ይይዘዋል፡፡ “እኔን ለመጎብኘት ረዥም መንገድ መጥተህ ሊሆን ይችላል ፣ እናም ባዶ እጅህንማ አትመለስም! እባክህ ልብሶቼን በስጦታ ውሰድ፡፡” በማለት ለሌባው ችሮታን ያደርግለታል። ሌባ ግራ ተጋብቶ ነበር ፡፡ የተቸረውን ልብሶች ወስዶም ይሸሻል ፡፡

ሪዮካን ደማቋን ጨረቃ እየተመለከተ ራቁቱን ተቀምጦ “ድሃ ነፍስ! ፣ ያቺን ውብ ጨረቃ ብሰጥህ እመኛለሁ” ሲል ጮክ ብሎ ተናገረ ፡፡

ሱራፌል አየለ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
መፅሐፍትን መቅዳት ትጉህነት ነዉና ተያይዤዋለዉ

የጨረቃና የፀሐይ ግርዶሽ
እንደ ሳይንስ ጥናት አንዳንድ ጊዜ ፣ ጨረቃ እና መሬት በአንድ መስመር ላይ ይገናኛሉ። ይህ በሚኾንበት ጊዜ የመሬት ጥላ ጨረቃ ላይ ያርፍና ጨረቃ ትጋረዳለች ወይም የጨረቃ ጥላ መሬት ላይ ያርፍና ፀሐይን እንዳናይ ትጋርድብናለች። እንዚህ ክስተቶች ግርዶሽ ይባላሉ።
 
አንድሮሜዳ መፅሐፍ ገፅ194



የፀሐይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ መጻሕፍት 
ኢትዮጵያውያን ስለ ፀሓይና ስለ ጨረቃ ግርዶሽ በተናገሩበት ትርጓሜ ሚጠነ ብርሃናት በተባለ መጽሐፋቸዉ ላይ ስለ ፀሓይ ግርዶሽ የራሳቸዉን የምርምር አመክንዮ አኹን ካለዉ ሳይንስ ለየት ባለ መልኩ እንዲህ ሲሉ አስቀምጠዋል:-

መፅሐፉ ላይ በግዕዝ ቋንቋ ከሰፈረዉ ፁኹፍ ስር የቀረበዉን የአማርኛ ትርጓሜ እቀዳለኹ

በእንዳንድ ሀገር እንጂ በዓለም ኹሉ የማይኾን የፀሓይ የመጨለም ልማድን ጨረቃ የልማዱን ጒድለት በማያደርግ ጊዜ ክበቡ ያለ ብርሃን ባዶ ጠፍ ይኾናል ፤ የፀሓይ ሠረገላዉ ከላይ ሲኾን የጨረቃ ሠረገላዉ ከታች በኩል ነው ፤ በየዘመኑ ወይም በብዙ ዓመታት የጨረቃ ክበቡ ከፀሓይ ጋር በቀጥታ ወደ ተያየበት የጨረቃው ዙሪያው እንደ ደመና ያጋረዳል ፤ ክበቡም ያለ ብርሃን ባዶ ይኾናል ፤ በሰማይ ላይ በተጋረደ ጊዜ በዚያ ሀገር በግልጽ የፀሓይ መጨለም ይኾናል ፤ በዚያ ሀገር ፀሓይ አይታይምና ከደመና ይልቅ ክበቡ ግዙፍ ናውና ብርሃን እንደማይሰውረው እንደ ዐየር ነፋስ ረቂቅ አይደለምና ፤ በፀሓይ ክበብ ልክ ታላቅና ሰፊ ነውና) ብለው ጽፈው ነበር።

አንድሮሜዳ መፅሐፍ ገፅ 200

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
2024/09/24 20:38:47
Back to Top
HTML Embed Code: