Telegram Web Link
#ማጠቃለያ

ነብሴ በሃዘኔ ወቅት አፅናኝ የልብ ወዳጄ ነው፡፡ ነብሱን ወዳጁ ማድረግ የማይችል ሁሉ የሰብአዊነት ጠላት ነው፡፡ የሰብአዊነትን መሪነት ያላገኘ ደግሞ ይጠፋል፡፡ ህይወት የምትፈጠረው ከውስጣችን እንጂ ከአካባቢያችን አይደለም፡፡

አንዲት ቃል ለመናገር መጥቻለሁ፡፡ ሆኖም ግን ሞት እስትንፋሴን ቢያቋርጣት ቃሌ ነገ ትናገራለች፡፡ ምክንያቱም ነገ ምሥጢርን በዘላለማዊነት መፅሐፍ ላይ አትተውምና፡፡

የፈጣሪ ነፀብራቅ በሆነ ብርሃንና ፍቅር ሥር ለመኖር መጥቻለሁ፡፡ ሰዎች ሕይወቴን ሊያጠፏት አይችሉምና እየኖርኩ ነው፡፡ ዐይኖቼን ቢያወጧቸው እንኳን የፍቅርና የውበትን ዜማ ጆሮዎቼ ይሰማሉ፡፡
ጆሮዎቼን ቢደፍኗቸው ደግሞ የተፈጥሮን ውብ ልስላሴ በመዳሰስና መዓዛውን በማሽተት እደሰታለሁ፡፡

ባዶ ቤት ውስጥ ቢያስሩኝ እንኳን የፍቅርና የውበት ልጅ ከሆነችው ነብሴ ጋር እኖራለሁ፡፡

እዚህ የመጣሁት ለሁሉምና ከሁሉም ጋር ለመሆን ነው፡፡ ዛሬ በብቸኝነት የማደርገው ነገር ሁሉ ነገ ደግሞ ለሁሉም ሰው ያስተጋባል፡፡

<< ዛሬ በአንድ ልብ የምንናገር ነገ በብዙ ልቦች ይነገራል>>


📯📜📯📜አለቀ📯📜📯📜

#መናፍቁ ካህሊል እና ሌሎች

@wegoch
@wegoch
@paappii
አምስት ሆነን እራት እየበላን ሳለ ከቀጠሮው ሰአት አርፍዶ ስድስተኛው መጣ።
ከመቀመጡ ቢራ እያዘዘ ስላረፈደበት ሁኔታ ማስረዳት ጀመረ።
"አታምኑኝም ከማን ጋር እንደነበርኩ" ሲል ጀመረ።
ከዚያም ማስታወሻ ደብተሩን አወጣና "እከሊት ናት የፃፈችልኝ" ብሎ በሚያምር
የእጅ ፅሁፍ የተፃፈ አንድ ገፅ ፅሁፍ አሳየን። ፅሁፉ ላይ ልጅቷ ምን ያህል
እንደምትወደው የሚገልፅ ሃተታ ይገኛል። ልጅቷን በስምና በመልክ ሁላችንም
እናውቃታለን።
"ጓደኛ ነበራችሁ?" አልነው።
"አዎ ተጣብሰን ነበር። ግን የቁምነገር አይደለም። ሴክስ ላይ በጣም ጎበዝ ናት
ሞክሯት" አለን።
ወዲያውም ስልክ ተደወለለትና ወጣ። ከዚያን ቀን በኋላ ባለው ሶስት አመት
ውስጥ አይቼው አላውቅም።
በተለያየ ጊዜ ስንገናኝ ከአምስታችን አራቱ መሞከራቸውን እና የተወራው
ጉብዝናዋ እውነት እንደሆነ እና ለማንም እንደማትከለክል ተናገሩ። የቀረሁት
እኔም እድሌን እንድሞክር ተነገረኝ። የማውቃቸው ሰዎች የደረሱበት መድረስ
እንደሚደብረኝ ስለሚያውቁ የተጫነኝ አልነበረም።
ይህ ከተፈጠረና ያ የጓደኞች ስብስብ ከተበተነ ከረጅም ጊዜ በኋላ ልጀቷ በስራ
ጉዳይ እኛ ሰፈር እንደምትመላለስ አወቅሁ። ተዋወቅን እና ቀስ በቀስ ተግባባን።
ፍቅረኛሞችም ሆንን።
ነግራኝ ያላመንኩት በኋላ ሳውቅ የገረመኝ ግን ልጅቷ ወንድ ያላወቃት ነበረች።
እሷ ራሱ ሁል ጊዜ የምትተርተው ተረት አላት " ብዙ የሚበላው ልጅ ስለ መብላቱ
የማይናገረው ነው " የሚል።
በቅርቡ ልንጋባ ነው።

@wegoch
@wegoch
@wegoch

#by_Haileleul_Aph
ቦይንግ 747-8፣ ለመገጣጠም ብቻ 4 ወር የፈጀ አውሮፕላን ነው፡፡ ስድስት
ሚሊዮን የሚገጣጠሙ ክፍሎች አሉት፡፡ በተለያየ የዓለም ክፍሎች ሆነው
ከጥቃቅን እስከ ግዙፍ፣ ከመካኒካል እስከ ኤሌክትሪካል የሚያመርቱ ከ30 ሺ
በላይ ሠራተኞች ይሳተፉበታል፡፡ ከእነዚህ መካከል የሚተዋወቁት ጥቂቶች
ናቸው፡፡ ብዙዎቹ የአንዱን መኖር ሌላው አያውቀውም፡፡ በእድሜ፣ በዜግነት፣
በጾታ፣ በእምነት፣ በመልክና በዘር ይለያያሉ፡፡ የሚከፈላቸው ክፍያ ይለያያል፡፡
የሚያመርቱትም የአውሮፕላኑን አንድ ክፍል እንጂ ጠቅላላውን አውሮፕላን
አይደለም፡፡
ሁሉንም አንድ የሚያደርጓቸው ሁለት ነገሮች ናቸው፡፡ የሚሠሩት ለአንድ ኩባንያ
መሆኑና የሚሠሩበት ዓላማ አንድ መሆኑ፡፡ እነዚህን ሁሉ ስድስት ሚሊዮን
ተገጣጣሚ አካላት የሚያመርቱት ባለሞያዎች ቦይንግ ለሚባል ኩባንያ የሚሠሩ
ናቸው፡፡ ንኡስ ኮንትራት ወስደው የሚሠሩት እንኳን ለዚሁ ኩባንያ እንደሚሠሩ
ያውቃሉ፡፡ ሁለተኛው ነገር ደግሞ የሁሉም ዓላማ አውሮፕላን መሥራት መሆኑ
ነው፡፡ በዓይን ለማየት አስቸጋሪ የሆነቺው ብሎን ከሚሠራ ጀምሮ ትልልቁን አካል
እስከሚያመርተው ድረስ ዓላማቸው ብሎን፣ ክንፍ፣ በር፣ ሞተር፣ ጎማ፣ ወንበር፣
መሥራት አይደለም፡፡ አውሮፕላን መሥራት ነው፡፡ ያ በሰማይ ሲበር የሚያዩት
አውሮፕላን እንደየዐቅማቸው ተሳትፈው እነርሱ የሠሩት አንድ አውሮፕላን ነው፡፡
ምናልባትም የመጨረሻውን ቅርጽ ሲይዝ ብዙዎቹ ላይገኙ ይችላሉ፡፡ ይህ
የሚፈጸመው ሲያትል ፓይነ በተባለው ሜዳ በሚገኘው የቦይንግ ኤቨረት ፋብሪካ
ነው፡፡ 13.4 ሚሊዮን ኪውቢክ ሜትር የሚጠጋው ይህ መገጣጠሚያ
በፕላኔታችን ላይ ለአውሮፕላን ከተሠሩ መገጣጠሚያዎች ሁሉ መሰል የሌለው
ነው፡፡ እዚህ ቦታ አውሮፕላኑ ተገጣጥሞ የመጨረሻውን ቅርጽ ሲይዝ ብዙዎቹ
ሠራተኞቹ የሉም፡፡ በአንድ ነገር ግን ርግጠኞች ናቸው፡፡ እነርሱ ያመረቱት አካል
ተገጣጥሞ አስደናቂውን የቦይንግ አውሮፕላን እንደሚፈጥረው፡፡
ሀገር የምትገነባው እንደዚህ ነው፡፡ በየዘመናቱ፣ በተለያየ ድርሻ፣ ሞያና
አስተዋጽዖ የሚችሉትን በሚያበረክቱ ዜጎች፡፡ በአሜሪካም ይሁኑ በጃፓን፣
በአውስትራልያም ይሁኑ በካናዳ፣ በአውሮፓም ይሁኑ በእስያ፣ በአፍሪካም ይሁኑ
በዐረቡ ዓለም ለአንዲት ኢትዮጵያ በሚሠሩ ዜጎች፡፡ የሚሠሩት ሥራ እጅግ
አነስተኛ መስሎ ይታይ ይሆናል፤ ወይም ደግሞ ገዝፎ የሚታይ ጉልሕ ይመስላል፡፡
ግን ኢትዮጵያ ለምትባል አንዲት ዓላማ፣ ኢትዮጵያዊነት በሚባል አንድ ኩባንያ
ውስጥ ሆነው የሚያመርቱ ዜጎች ናቸው ኢትዮጵያን የሚገነቧት፡፡ ምናልባትም
አንዳንዶች የእነርሱ አስተዋጽዖ የመጨረሻው ሥዕል ምን እንደሆነ አላዩም፣
ወደፊት አያዩ ይሆናል፡፡ ግን በአንድ ነገር ርግጠኞች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በሁሉም
አስተዋጽዖ ትገነባለች፡፡
የእያንዳንዱ ቅንጣት በጥራትና በብቃት መመረት ለአውሮፕላኑ ጥራትና ብቃት
ወሳኝ ነው፡፡ እያንዳንዳችን በተሠማራንበት ቦታ የምንሠራው፣ የምናስበው፣
የምንጽፈው፣ የምንወስነው፣ የምናካሂደው ነገር ጥራትና ብቃት እንዲኖረው
ከተደረገ ሀገራችን የጠራችና የበቃች ትሆናለች፡፡ እያንዳንዱ የቦይንግ
አውሮፕላን ቅንጣቶችን አምራች ባለሞያ የሚሠራው ነገር ከሌሎች ጋር
ተጋጥሞ፣ ተስማምቶና ተዋድዶ አንድ አውሮፕላን ካልፈጠረ ሥራው ዋጋ
የለውም፡፡ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በየቦታውና በየዘመናቱ የሚሠራው ሥራ
ከሌላው ጋር ተጋጥሞ፣ ተስማምቶና ተዋድዶ አንዲት ኢትዮጵያን ካልፈጠረ
ትርፉ ድካም ነው፡፡
ኢትዮጵያን በጋራ ለመገንባት ሁላችንም መተዋወቅ የለብንም፡፡ ለአንድ ዓላማ
እስከሠራን ድረስ የትም ሆነን፣ ማንም ሆነን በግንባታው ላይ መሳተፍ
እንችላለን፡፡ አንድ ዓይነት መሆንም የለብንም፡፡ የተለያየ እምነት፣ ዘርና ፖለቲካ
ይዘን፣ በተለያየ ዘመንና ቦታ ሆነን መገንባት እንችላለን፡፡ ብቻ ለአንድ ዓላማ
እንሰለፍ፡፡ ለማፍረስ ያይደለ፣ ለመገንባት፡፡
ማንም ብቻውን አውሮፕላኑን አያመርተውም፡፡ እያንዳንዱ ባለሞያ ለአንድ ዓላማ
ተሠማርቶ በሚቻለውና በተሰጠው መጠን ይገነባል እንጂ፡፡ ኢትዮጵያም እንዲሁ
ናት፡፡ ማንም ብቻውን አይገነባትም፡፡ ሁላችንም በተሰጠን መጠንና በቻልነው
ያህል አሻራችንን እያሳረፍን እንገነባታለን፡፡
ኑ፣ በጋራ አገር እንገንባ፣ አኮብኩባ ስትበርም እንያት፡፡

@wegoch
@wegoch
@paappii

#ዳንኤል ክብረት
ምክር እስከመቃብር
(ከኣልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ)

እንደምነሽ ሸገር
እንደምነሽ ሸገር
የቤት ኣከራየ የጋሽ ጣሰው ኣገር
እየመጣሁ ነው፡፡ወደ ኣዲስ ኣበባ እየመጣሁ ነው፡፡እናቶች
ኣባቶች ልጆች ኦርጅናሎች ሰልቫጆች! እኔ ሳልመጣ ውጊያውን
እንዳትጀምሩት ኣደራ፡፡ ኣጭርና ጣፋጭ ይሁን እንጂ
በማንኛውም ትግል ላይ ለመሳተፍ ዝገጁ ነኝ፡፡የጥይት መከላከያ
ቆብ ሹራብና ሱሪ እንዲሁም ፈንጅ የማይበትነው ጫማ
ከተሰጠኝ ኣንድ ሻለቃ እመራለሁ፡፡ኣነሰ ከተባለ ኣንዲት ኮረብታ
እቆጣጠራለሁ፡፡ በጦር ምህንድስና ላይ እሳተፋለሁ፡፡ ባሩድ
ኣገነፋለሁ፡፡ የታንክ ጎማ እነፋለሁ፡፡በሰላሙ ቀን ለሞባይል፤
በቀውጢው ቀን ለሽጉጥ ማስቀመጫ የሚሆን ሰገባ እሰፋለሁ፡፡
ይሄም ኣላዋጣ ካለ የኤፍሬም ይሳቅን ቡድን የሚፎካከር
ኣስታራቂ ቡድን ኣቋቁሜ” ኣንተም ተው ኣንተም ተው፤
ያስታረቅሁበትን ኪሴ ውስጥ ክተተው” የሚል ኣገልግሎት
እሰጣለሁ፡፡ቃሌ ነው፡፡የተናገርኩት ከሚጠፋ በቅርቡ የገዛሁት
ጋላክሲ ሙባይል ይጥፋ(በዝች ንግግር ውስጥ የተደበቀ ጉራ
እንዳለ እናንተ ሳትሉኝ ኣውቀዋለሁ)
ገና ለገና ካሜሪካ ሊመጣነው በማለት ማጅራቴን ለመመታት
እያሟሟቃችሁ ያላችሁ ዱርየዎች እንዲሁም ከዱላ የተረፈች
ማጅራቴን በማሸት ትርፍ ለማጋበስ የተሰናዳችሁ ወጌሻዎች
ተስፋ ቁረጡ ፡፡ ቤሳቢስትን የለኝም፡፡(ማጅራት መምታት ሲነሳ
ፋሲል ደመወዝ ትዝ ኣለኝ፡፡እንኳን እግዜር ማረህ ልለው ብደውል
ከዲሲ በርሮ ኣትላንታ እንደገባ ነገረኝ፡፡ለኮንሰርት ይሁን
ለስልታዊ ማፈግፈግ ኣልነገረኝም፡፡ ወይ ኣበሳ!እኛ
ኢትዮጵያውያንኮ ምስኪን ነን ፤ ኣገር በቀል- ዱላ ሸሽተን ስንሄድ
የውጭ ኣገር ዱላ ይጠብቀናል፡፡
ኣሜሪካ ሁለት ወር ስቆይ ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ግብዣና ምክር
ነው፡፡ዲታው ቢራ ጋብዞ ወደ ኣገርቤት ይዣት የምመለስ ቦርጭ
ያወጣልኛል፡፡ቺስታው ቦርጬ እንዴት እንደምቀንስ ይመክረኛል፡፡
ኣሜሪካ ፍሪሽ የሆነ ሰው ኑሮው ምክር እስከመቃብር ነው፡፡
ከኢትዮጵያ ወደ ኣሜሪካ ገንዘብ የተላከለት የመጀመርያው ሰው
ሳልሆን እቀራለሁ?
ለምሳሌ ጺም ለመቆረጥ ኣስር ዶላር መከስከስ ነበረብኝ፡፡
ፈርዶብኝ ኣሜሪካ ስገባ ጺሜ ያለወትሮው ቶሎቶሎ ማደግ
ጀመረ፡፡ኣዲኣበባ እያለሁ ጺም ኣልነበረኝም፡፡እንዲያውም” ይሄ
ልጅ ጺሚ የሚባል ነገር የለውም ስልብ ነው እንዴ?” የሚል
ኣሜት በመንደራችን ይናፈስ ነበር፡፡ስልብ ኣለመሆኔን ለማሳየት
ኣንድ ሁለት ቀን መንገድ ዳር ሸንቻለሁ፡፡
እንደልማዴ ከቀናኝ የሚጋብዘኝ ከፈረደብኝ የሚመክረኝ ኣላጣም
በማለት Fenton መንገድ ላይ ወደሚገኝ ያበሻ ምግብ ቤት
ጎራ ኣልኩ፡፡ ኣንዱ መድረክ ላይ የሱዳን ዘፈን ይዘፍናል፡፡
ከተስተናጋጆች ውስጥ ኣንድም የሚያዳምጠው የለም፡፡ሁሉም
ሙባይሉ ላይ ኣቀርቅሯል፡፡የታደለው ከፍቅረኛው በቫይበር
የተላከለትን የክንፈር ምስል እያየ በደስታ ይዋኛል ፡፡
ያልታደለው”የትምርት ቤት ክፍያ እየደረሰብኝ ስለሆነ ቶሎ
ላክልኝ እንጅ”የሚል ካገር ቤት የተላከ መልክት እያነበበ
ተክዟል፡፡ ሌላው ግድግዳው ላይ በተንጠለጠለው ቲቪ ላይ
የሚተላለፈውን ያሜሪካ እግርኳስ እየተመለከተ ምድር ጠቦታል፡፡
ያሜሪካ እግርኳስ ቢሏችሁ እንደ ዋናው እግርኳስ እንዳይ
መስላችሁ፡፡ ኣንዱ ጠብደል ጥቁር ሙልሙል ኳስ ይዞ
ይሮጣል፡፡ሌላው ኣሳድዶ ይደርስበትና ዘርጥጦ ይጥለዋል፡፡ ለኔ
ይህ ጨዋታ ሳይሆን ህጋዊ እውቅና ያለው ኣምባጓሮ ነው፡፡
በዚህ መሃል ዘፋኙ “ከ እኔ ጋ ናችሁ?” እያለ ኣስሬ ቢጣራም
ማንም ተጉዳይ ኣልጣፈውም፡፡ ልምምድ ላይ ያለ ይመስል
ለራሱ ዘፍኖ ወረደ ፡፡ስላሳዘነኝ ባንኮኒውን እንደመቋሚያ ተደግፌ
በጥሞና ኣዳመጥሁት፡፡ድምጹ ከዛፍ ላይ ኣምፖል ያረግፋል፡፡ ቢሆንም ዘፈኑን ኣለቅጥ ያስረዝመዋል፡፡የሱን የሱዳን ዘፈን ታግሶ
መጨረስ ሱዳንን በእግር እንደማቋረጥ ነው፡፡
ጥግ ላይ ክበበው ገዳ ተቀምጧል፡፡ ወንበር ስቤ ኣጠገቡ
ተሰየምሁ፡፡ ራት ይጋብዘኛል ብየ ስጠብቅ ከራት ጋር የተያያዘ
ገጠመኝ ጋበዘኝ፡፡
ክበበው ገዳ ጎረምሳ እያለ የለቅሶ ቤት እራት ኣያመልጠው
ነበር፡፡ እንድያውም እንዲያባላኝ እያለ ቃሪያ በኪሱ ይዞ መዞር
ጀምሮ ነበር፡፡ ኣንድ ለቅሶ ላይ ታድያ እራት ሲቀርብ ክበበው
ከቤቱ ይዞት የመጣውን ቃርያ ከኪሱ ኣውጥቶ ኮርሸም ሲያደርግ
የተመለከተ የሰፈር ልጅ ወደ ኣስተናጋጆች እያጨበጨበ “እዚህ
ጋ ቃርያ ኣልደረሰኝም” ብሎ ጮከ፡፡
ኣለፍ ብሎ፤ የጃንሆይ ኣምባሳደር ዘውዴ ረታና ያሬድ ጥበቡ
ቁጭ ብለዋል፡፡ያሬድ ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ ሲሆን
ዘውዴ የተንቀጠቀጠው ተራራ ነው፡፡ኣሁን ዲማሚቱና ተራራውም
ባንድ ጠረጴዛ ዙርያ ተቀምው ሳያቸው ገረመኝ፡፡
ከማጅራቴ ኣካባቢ “ልትጽፍ ነው የመጣህ ኣይደል”የሚል
ሹክሽክታ ሰማሁ፡፡ወይንሸት ናት፡፡ ባለፈው ኣመት ከባህል
ቡድናችን ጋር ስትመጣ ኮከብ ድምጻዊ ነበረች፡፡ኣሁን እዚሁ
ቀርታ ኮከብ ኣስተናጋጅ ሆናለች፡፡ኣፍንጫዋ ላይ የወርቅ ቡግር
የመሰለ ሎቲ ለጥፋለች፡፡እዚህ ኣገር ሴቶች ሎቲ
የሚያንጠለጥሉት ጆሮኣቸው ላይ ሳይሆን ኣፍንጫቸው ላይ ነው፡፡
ስለወይንሸት በሌላ ምእራፍ እተርካለሁ፡፡
በሩ ኣጠገብ ተኬን ኣየሁት፡፡ ተኬ በደርግ ዘመን ካይሮ ላይ
ከጠፋው የብሄራዊ ቡድናችን ገንዘብ- ያዥ ነበር፡፡ኢትዮጵያ
ከግብጽ ጋር ባደረገችው በግጥምያ ዋዜማ ላይ በረኛውን
ጨምሮ ብዙ ተጫዋቾች ስለኮበለሉ እሱ የበረኛውን ቦታ ተክቶ
ተሰልፏል፡፡ ከተቃራኒ ቡድን የተለጋች ኳስ ወደእሱ ኣቅጣጫ
ስትመጣ በገንዘብ ቆጠራው ለምዶበት ጣቱን በምላሱ እያጣቀሰ
ሲርበደበድ ፤ ኣስራ ሰባት ጎል ገበቶበታል፡፡ (ምንጭ፡
የይድነቃቸው ተሰማ ሪፖርት)ተኬ ጉዳዩ ሲነሳበት
ያማርራል፤“ይሄ ውለታ ቢስ ህዝብ የገባብኝን ኣስራ ሰባት ጎል
እንጂ ያዳንሁትን ሰባት መቶ ጎል ኣላሰበልኝም” ይላል፡፡ካገሩ
ወጥቶ መቅረት ኣሳብ ፈጽሞ ኣልነበረውም፡፡ይሁን እንጅ ይህን
ሽንፈት ይዞ ጓድ መንግስቱ ፊት መቆም የሚያመጣውን ነገር
ኣስቦ በዛው” ነካው“፡፡
ኣሁን በሩ ኣጠገብ ቁጭ ብሎ ”ብሉ ሙን“ ቢራ ይጠጣል፡፡
የቢራ ጠርሙሱን በጥርሱ ከፍቶ ቆርኪውን ጠረጴዛ ልይ ተፋው፡፡
ቢራ መክፈቻ ቢቀርብለትም ተጠቅሞበት ኣያውቅም፡፡እግዜር
መንጋጋን የፈጠረው ሲርብህ ኣጥንት እንድትቆረጥምበት
ሲጠማህ የቢራ ጠርሙስ እንድትከፍትበት ነው ይላል፡፡ ————በበእውቀቱ ሥዩም————

@wegoch @wegoch @wegoch
ሽምቅ ውጊያ ማ ነው !

(ሚካኤል አስጨናቂ)

ዝግጅቱ ተጧጡፎ ነበር ። እኔን ጨምሮ ሁሉም የሰፈር ጓደኞቼ ከቄሮ የሚያስንቅ አጣና አዘጋጅተን ሽር ጉድ እያልን ነው። 

ደፌ ፣ ኩሜ ፣ ታሪኩ እና ይርጋለም ሽመላቸውን አስውበው ያወዳድራሉ። ከእኔ ሽመል በስተቀር የሁሉም ጓደኞቼ ዱላ በቆርኪ አክሊል ተውበው ቀጭን ልዑል መስለዋል ። ጭራሽ ደፌና ኩሜማ በሽቦ የተሰራ ፅናፅል ተሸክመው ደንበኛ የደብር ዳቆን መስለዋል :) ከሁሉም የእኔ ዱላ ብቻ ተጣሞ የአዝማሪ ማሲንቆ ይመስል የነበረው። 

ስብሰባው ተጀመረ ...

ይርጋለም ገንዘብ ያዥ... እኔ ድምፅ ባይኖረኝም የተሻለ ግጥም ይችላል በሚል እምነት ዘፈን አውራጅ...ታሪኩ ተጠባባቂ ዘፋኝ ...ደፌ የስንዴ ሽልጦ ተሸካሚ.. .ኩሜ ደግሞ የፍርኖዱቄት ዳቦ ተቀባይ😊 ሆነን ተሿሿምን ። የሹመቱ መቀያየር ፍጥነት ከብልፅግና ፓርቲ ቢያስንቅ እንጅ የሚተናነስ እንኳ አልነበረም 😂

ጭፈራው ተጀመረ.. . ጭፈራውን ደግሞ የጀመርነው ማልደን ስለነበር ብዙ ቤት ሰዓት ገና 9 ሰዓት አልሆነም በሚል ሰበብ ኩም አድርገው መለሱን። እስከ ስድስት ሰዓት በነበረው ጭፈራ ጥቂት ገንዘብና ሁለት የፍርኖ ዱቄት ዳቦዎችን አተረፍን። በጭፈራው የመክሰር ስሜት ቢሰማንም ሁለቱን ሽሌ ተከፋፍለን ስንገምጥ ወድያው ሀሳባችንን ቀይረን ፊታችን በደስታ በራ።

ጎን ለጎን እስከ ዘጠኝ ስንፆም የነበርነውን የፍስለታ ፆም ወደ ስድስት ሰዓት አዙረን ከእግዜር ተኳረፍን ።

የከሰዓቱ ፕሮግራም ላይ ከገንዘብ ያዡ ይርጋለም በስተቀር የሁላችንም ሹመት ተቀያየረ /ብልፅግና ስታይል 😉/

የከሰዓቱ የመጀመርያ ዙር ጭፈራ ላይ ...

እዛ ማዶ

 ሆ 

አንድ ትሪ

ሆ 

እዚህ ማዶ 

ሆ 

ሌላ ትሪ

የኔማ ደጀኔ 

ሆ 

ባለ ማስተርስ ድግሪ የሚል ግጥም ያዘለ ሙገሳ ያደረስነው ቀን ሰራተኛው ደጀኔ በደስታ ሰክሮ አምስት ብር ለቀቀብን። 

ይሄ ብር ነዳጅ ሆኖን ፍጥነት ጨምረን ተርገበገብን...እስከ 10 ሰዓትም ድረስ ዜማና ግጥም እያሰናኘን የማህበረሰቡን የሙገሳ ጥም ስለቆረጥን በገንዘብና ሽልጦ ናዳ ተመተን በድሎት ተሰቃየን።

10 ሰዓት ላይ እኔን ጨምሮ የጓደኞቼም ጉሮሮ የካሴት ክር እንደነከሰ ቴፕ መነፋነፍ ያዘ። 

ጥቂቶች ሁኔታችንን ሲያዩ ስላዘኑልን.. .ዘፈን በቅጡ ባናወርድም እርጥባን ሲቸሩን ቆዩ ...ከ ጣሰው ቤት በስተቀር ።

ጣሰው የቀረችንን እንጥፍጣፊ ጉልበት አሟጦ ከሰለቀጠ በኋላ በዘመኑ ቋንቋ ላሽ አለን...

እዛ ማዶ



አንድ ከረባት 

ሆ 

እዚህ ማዶ



አንድ ከረባት 



የኔማ ጣሰው 



ክቡር ባላባት 

ሆ.... 

ብር ወፍ የለም :) ..... ሁሉም ማጉረምረም ያዘ ... በተለይ ከሁላችንም የተንኮል ሊቅ የነበረው ይርጋለም ጣሰውን እንስደበው የሚል ሴራ ጠነሰሰ ...

እዛ ማዶ .... ብሎ አስጀመረን.. .

ሆ ብለን ተቀበልነው

አንድ ገበያ 

ሆ 

እዚ ማዶ

ሆ 

አንድ አህያ

ሆ ..

የኔማ ጣሰው ...

ሆ ...

ደደብ አህያ !

(ከዚህ ግጥም በኋላ በቅፅበት ከየት መጣ ያልተባለ የጥፊ ድምፅ ተሰማ...ገንዘብ ሊሰጠን እየመጣ የነበረው ጣሰው ...በገንዘቡ ፈንታ በካልቾ እየጠለዘ እንደ ኳስ አንጥሮን ተበታተንን)

...

ሁላችንም ላባችን ጠብ እስከሚል ሮጠን ካበቃን በኋላ.. . እያለከለክን ተሰበሰብን...ሁላችንም ብንሰበሰብም ይርጋለም ግን በመሀከላችን አልነበረም። ቆይቶ እያለከለከ ስራችን ተከሰተ ...ፊቱን ዘፍዝፎ አንድ ከባድ መርዶ አረዳን...

ጣሰው የሰበሰብነውን ብር በሙሉ ተቀብሎታል።

ሀዘኑ እንደዚህ በቃላት የሚነገር አልነበረም...የሁላችንም ልብ ክፉኛ ቆሰለ ።

አዘንን ...ተከዝን....

ህመሙ ና ስብራቱ ቀኑ አልፎ አድረን እንኳ አልፋታ ብሎን በፅኑ ቆዘምን። በተለይ ታሪኩ ነጠላ አዘቅዝቆ ገቢው ውስጥ የለቅሶ ድንኳን ማስተከል ብቻ ነበር የቀረው።

ይሁንና ... ከቀናት በኋላ ይርጋለም ከስራችን ብን ብሎ ጠፋ ... ዘወትር ቸኮሌትና ፓስቲ እየገዛ እንደሚዝናና የሚጠቁሙ የወሬ ፍንጣሪዎች ደረሱን ። 

በርግጥም ይርጋለም ጣሰው ገንዘብ ተቀብሎኛል በሚል ሙድ የቀኑን ገንዘብ ለራሱ መደበርያ አውሎት ነበር :)

@wegoch
@wegoch
@paappii
#ከግድግዳው_ባሻገር

#በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰርቶ #የተፃፈ

“ደንበል..ሸዋ ዳቦ…ስቴዲየም…ሜክሲኮ…ኸ..ትሔዳላቹ….?”
ወትሮም በእዚህ ሰዓት የታክሲው ግፊያ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሰዉ ተገፋፍቶ ከጠባቧ የታክሲ በር ሾልኮ ተሰገሰገ፡፡ ከወንበሮቹ መካከል አራት ሰዎችን ከሚያስቀምጠው የመጨረሻ ረድፍ ላይ በቀኝ ጥግ ተቀመጥኩኝ፡፡ በተከፈተው የታክሲው መስኮት አልፎ የሚመጣው ቀዝቀዝ ያለ የጠዋት አየር ከፊቴ ደርሶ ሲጎበኘኝ ፊቴ ፈካ አለ፡፡
አፍታም ሳይቆይ ቁመቷ መካከለኛ የሆነ፣ ቀጠን ያለች ወጣት ሴት “ልትጠጋልኝ ትችላለህ?” አለችኝ፡፡ ሰምቻታለው ነገር ግን አይኔ ከመስታወቱ ባሻገር ስለነበረ መልስ ሳልሰጥ ወደ መስኮት ጥግ ሰውነቴን ሰብሰብ አድርጌ ተቀመጥኩኝ፡፡ የተቀባችው ሽቶ የታክሲውን አየር ተቆጣጥሮታል፡፡ ዘወር ብዬ የግርፍት እይታ ገረመምኳት፡፡ የተተኮሰው ፀጉሯ እዚህም እዛም ተበታትኗል፡፡ ደግሜ በጥልቀት ተመለከትኳት፡፡ ፊቷ የተረበሸ ከተማ ይመስላል፡፡ ጉንጮቿ ከፊቷ መቅላት ጋር አብሮ የቀላ ፍም ምድጃ ሆነዋል፡፡ የቀጠለችው ሰው ሰራሽ አልያም የሌላ ሰው ፀጉር ስፌት ከተተከለበት አናቷ ላይ በግልጥ ይታያል፡፡ ከንፈሯ ውሀ እንደተጠማ የደረቁ፡፡ በተደጋጋሚ ጣቶቿን እየሰደደች የቀሉ አይኖቿን ታሻቸዋለች፡፡ የደረቁት የኩል ፍርፋሪዎች ከአይኗ ሽፋሽፍት ላይ ከተጣበቁት አይናሮች ጋር እየተቀላቀሉ በጣቶቿ ከፊቷ ቆዳ ላይ ትዳምጣቸዋለች፡፡ በስራ አልያም በአንዳች ምክኒያት እንደተዳከመች ገብቶኛል፡፡
ታክሲው ደንበል ጋር እንደደረሰ ከተናገረ በኋላ ወራጅ መኖር አለመኖሩን በመጠየቅ የላይኛውን የቀለበት መንገድ በጎን ትቶ የውስጠኛውን የቀለበት መንገድ ቁልቁል ይዞ ከነፈ፡፡ ስልኬን ከፍቼ ቁጥሮቹን ከጎነቆልኳቸው በኋላ ወደ ቀኙ ጆሮዬ አስጠግቼ ጥሪውን እስኪያነሳ መጠባበቅ ጀመርኩኝ፡፡ ሁለት ሶስቴ ከጠራ በኋላ አነሳው፡፡ ሰላምታ ተለዋውጠን እዛው ስታዲየም እንደምጠብቀው ነገርኩት፡፡
“ትንሽ ስለማረፍድብህ ትንሽ ታገሰኝ ሻይ ቡና እያልክ፡፡” አለኝ በሰዐቱ መድረስ የተሳነው አንድ ጓደኛዬ፡፡
“መቼ ይሆን አንተም በሰዓትህ ምትገኘው?”
“ጥሩ ትኮምካለህ ባክህ! በል ዲዛይኖቹን በፍላሽ ሬዲ አርግልኝ እና ፕሪንት እናረጋቸዋለን እንደመጣው፡፡”
“አንተ ብቻ ቶሎ ና እሱን እቤት ገልብጬዋለው፡፡” ሰላምታ ተለዋውጠን ስልኩን ዘጋሁት፡፡ በግራ ትከሻዬ ከበድ ሲለኝ ተሰማኝ፡፡ ዘወር አልኩ፡፡ እኔ ላይ ደገፍ ብላ እንቅልፍ ሸለብ አድርጓታል፡፡ ደንገጥ አልኩኝ፡፡ ምናልባት ነቃ እንድትል በማሰብ ሰውነቴን ነቅነቅ አድርጌ ጠጋ ብዬ ተቀመጥኩኝ፡፡ ትንሽ እንደ መንቃት ብላ መልሳ ተኛችብኝ፡፡
አሳዘነችኝ፡፡ ታክሲው የአብዮት ትራፊክ መበራት ይዞት ቆሟል፡፡ ከቀዩ የትራፊክ መብራት የአንድ ደቂቃ ተኩል ቆይታ በኋላ ተንቀሳቀስን፡፡ መውረጃዬ ተቃርቧል፡፡ እንደተሸገረ የስታድየም ታክሲዎች ከተኮሉበት የታክሲ ማውረጃ እና መጫኛ ደረስን፡፡
“ስታድየም መጨረሻ፡፡” የታክሲው ረዳት ለፈፈ፡፡ ጥቂት የታክሲው ተሳፋሪዎች ወረዱ፡፡ እኔም አንደኛው ወራጅ ነበርኩኝ፡፡ አልወረድኩም፡፡ ልጅቷ ከትከሻዬ ጭንቅላቷን ሸብረክ አድርጋ እንደተኛች ነች፡፡ ከበስተ መጨረሻው ረድፍ ከተቀመጥነው አንዳችንም አልወረድንም፡፡ ረዳቱ የታክሲውን ጠባብ በር በክንዱ ገፍቶ አጋጠመው፡፡ ታክሲው ተንቀሳቀሰ፡፡ ከመውረጃዬ አለፍኩኝ፡፡ የይሉንታ ግዞተኛ መሆኔን ስረዳው አበሸቀኝ፡፡ ዘወር ብዬ ተመለከትኳት፡፡ የተከደኑ አይኖቿን በተበታተኑት ፀጉሮቿ መሀከል ስመለከታቸው አሳዘኑኝ፡፡ ምነኛ እንደደከማት ከደረቁት ከንፈሮቿ መሀከል የሚወጣው የሞቀ ትንፋሽ ልጆሮዬ ሹክ አሉት፡፡ እጆቿ በጭኖቿ መሀከል ተሸንቁረዋል፡፡
#ይቀጥላል
ስለሺ ሳልስ ዑመር
©SVC2017

@wegoch
@wegoch
@wegoch
እዛ ማዶ ጭስ ይጨሳል
አብዮተኛ ይደግሳል😊
ነሐሴ ➋➌
#የግጥም_አብዮት 🙏

ቦታ ☞ አ.አ ደምበል ህንፃ ጀርባ ወረዳ 9 የወጣቶች ማዕከል አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡

⭕️ 400 ሰው ብቻ!

📍100 ብር 👌
ተቃርኖ ((ጆኒ ሀብቴ))



ወጥቷል፡፡
ወደዓለም፡፡ለዓለም፡፡
ሊኖር ነው፡፡
ከዓለመኞች ጋር፡፡
ዓለመኞች ቆንጆ መሳይ ናቸው፡፡ተጣዳፊዎች፡፡ለሁሉ የሚሮጡ፡፡የሞላላቸው መሳዮች ግን በማብቂያው ፥ ምንም ያልያዙ መናጢዎች፡፡
ያፈቅራሉ፡፡
ቸኩለው ልብ ይሰጣሉ፡፡ተጣድፈው ሁሉን ተሰጣጥተው ይጨርሳሉ፡፡በንጥቀት ይሰለቻቻሉ፡፡
ደሞ ወደሌላ ይሮጣሉ፡፡መሬት ላይ ይሮጣሉ፡፡አልጋ ላይ ይሮጣሉ፡፡አየር ላይ ይሮጣሉ፡፡ፍቅር ላይ ፥ ጥላቻ ላይ ይሮጣሉ፡፡ሳቅ እንባ ላይ ይሮጣሉ፡፡
ሁሉ ላይ ይሮጣሉ፡፡ረግተው ካየሀቸው ለሌላ እሩጫ እያደቡ እንጂ እርጋታን አውቀውት አይደለም፡፡በዚህ ሁሉ ጥድፈታቸው ውሸታሞች ፥ ቀጣፊዎች ፥ አጭበርባሪዎች ሆነው ይታዩታል፡፡
"አትሩጥ፡፡ለምንም ነገር አትፍጠን፡፡ያንተ ያንተ ነው፡፡ላንተ ያለው እንጀራ ሻግቶ ይወድቃል እንጂ ማንም አይበላው" ይለው ነበረ እረኛ እያለ የሚያግደው በጉ፡፡
የታደለ ረኛ ነበረ፡፡የሚያወራ በግ የነበረው፡፡ይሄ ከሚሊዮን እረኛ አንዱ ብቻ የሚያገኘው እጣ ነው፡፡ወርቅ እንቁላል እንደምትጥለው ዶሮ ነው ይሄ በግ፡፡አይገኝም፡፡ሲገኝም በዘመን አንዴ ነው፡፡
አዋቂ ነው፡፡ልሳን አለው፡፡የጣፈጠ አንደበቱ እውቀቱን አሳምሮ ይናገራል፡፡
" ዛሬ ዛሬ ሁሉ ይሮጣል፡፡አንተ ግን ዝግ በል፡፡የሮጠውን ያህል ማንም አያገኝም፡፡በማብቂያው ሁሉ በሮጠው መጠን እርካታ የለውም....." ይለዋል ተናጋሪ በጉ፡፡
" እኔና አንተ ያለነው እልም ያለ ገጠር ፥ ለምን ስለከተሜው ታወራኛለህ?የት ታውቀዋለህ?"
ሳቅ ይልና " ዝም ብዬ የምታረድ በግ አልምሰልህ፡፡እሱ የአብርሐም በግ ነው፡፡እኔ ብታረድም አዋቂ በግ ነኝ " ይለዋል፡፡
" እሺ ይሄ ወሬ ለኔ ምን ይረባኛል!?"
"ቀንህ ሲደርስ ከተሜ ነህ፡፡በጊዜህ ከተሜኛ ነህ፡፡ለዛ ጊዜ የሚሆንህን ነው ዛሬ የምነግርህ፡፡"
ወጥቷል፡፡
ያየው ደነቀው፡፡ግራ ገባው፡፡
ይሄ ሕይወት እንቀልፍ አልባ ነው፡፡ንቃት ግን የለውም፡፡ረፍት አልባ ነው፡፡ስራው ግን አጥጋቢ አይደለም፡፡ይኳኳላል፡፡ግን ውብ አይደለም፡፡ያነጣጥራል፡፡ኢላማ ግን ይስታል፡፡ደስተኛ ነኝ ይላል፡፡ግን ብስክስክ ብሶቱን ታቅፎ ነዋሪ ነው፡፡ይብለጨለጫል፡፡ግን አያበራም፡፡
መጥታ ያቀፈችው ማን ነበረች!?
አዎ!!
ሔርሜላ ነች፡፡
ብዙ ሳቅ ያላት ሔርሜላ፡፡ብዙ ድምፅ ፥ ምንም ዝምታ የሌላት ሔርሜላ፡፡እየሳቀች እዛው የምታለቅስ፡፡እኩል በእኩል ሳቋም እንባዋም የበዙ፡፡
እንዴት ወደሱ መጣች!?
ከየት ወደሱ መጣች!?
ለምን እሱን አቀፈችው!?
ሁሉ ተሳከረበት፡፡ብብብብብብብብዥዥዥዥዥዥዥዥዥዥዥዥዥ ያለ ሆነበት፡፡አልጠራ ያለ መደፍረስ፡፡አያጥቡት ግን የሁሌ ጭቃ፡፡ተወቅጦ የላመ ፥ የደቀቀ ውሃ፡፡
" የኔ ፍቅር !?" አለች ሔርሜላ፡፡
እ!?
" ወይዬ " አለ እሱም፡፡
እ!?
" ልሄድ ነው በቃ፡፡ "
ከአይኑ የእንባ ኳሶች አንከባለለ፡፡ጉንጩን አብዶ ሰርቶ ፥ አፍንጫውን በሎጬ አታልሎ ፥ ሪዙን አብዶ ሰርቶ የእንባ ኳሶቹን ቁልቁል ወደመሬት ጎሉ በሹት ጠለዘው፡፡
" እሺ በቃ ሂጂ " አለ እንደምንም ብሎ፡፡
መቼ መጥታ!?
መቼ ልትሄድ!?
አሁን አቀፈችው አልተባለም እንዴ!?
አሁን ሳቀች ሲባል አልነበረ እንዴ!?
ምን ጉድ ነው ይሄ!?
እያለቀሰ ፥ እያለቀሰች ተቋጨች፡፡አከተመች፡፡ተቋጩ፡፡አከተሙ፡፡
" አለህልኝ የኔ ፍቅር!?" እያለች ከንፈሯን ከንፈሩ ላይ አተመች፡፡
" የኔ ኮኪዬ " አለ ከንፈሯን እያጣጣመ፡፡
ኮኪ ማን ነች ደሞ!?
የኔ የኔ ከተባባሉ የእነሱ የራሳቸው ናቸው፡፡እሱ የእሷ ፥ እሷ የእሱ፡፡
ፍቅረኛሞች ናቸው፡፡
ሽቅርቅር ያለች፡፡የሽቅርቅሯ መርቀቅ ከአጠገቧ ያለን ሁሉ አፈር ድሜ አስበልቶ የሚያስረሳ፡፡ሁሉ ነገሯ አይን ይጠራል፡፡አይን ማራኪ ጀግና መሽቀርቅር ፥ አይን ጎታች ማግኔት መሽቀርቀር ፥ አይን ጋባዥ ለጋስ መሽቀርቀር ነው ያላት፡፡
ያያት ሁሉ ይስቃል፡፡እሷን እያየ አብሯት ያለን ይረሳል፡፡ሲያያት ይደሰታል፡፡ከተሜ ቅብ ደስታ፡፡ጥድፊያ ውስዋስ ደስታ፡፡
" በጣም ነው የማዝነው የኔ ፍቅር፡፡"
" ይገባኛል፡፡"
" ግዴታ ስለሆነብኝ ነው፡፡መሄድ አለብኝ፡፡"
የእንባ ኳሱ.....የለቅሶ ግጥሚያው....የእንባ ሊጉ.....የዚህ ዘመኑ ውድድር ኮኪ ነበረች፡፡የመለየት ዋንጫውን አብልታውና ሸልማው ሄደች፡፡
ያ በጉ ታውሰው፡፡ሊያወራው ፈለገ፡፡
እንዲህ አይነት ወሬ....
"የማዝነው...
ክፉዎች ባሸነፉበት ዓለም ላይ በመኖሬ አይደለም!!!
"ቅዱሳኖቹ ተለይተው ስላልታወቁ እንጂ!!!
የሚከፋኝ...
"ዋናው እርኩስ ታውቆ ፥ ታላቁ ቅዱስ በማይታወቅበት ዓለም ላይ ስላለሁ ነው
የሚያስጠላኝ...
"እኔ ለማን ፥ ማን ለኔ እንደቆምን አለማወቃችን ነው...." ሊለው ፈለገ፡፡
ግን አይለውም፡፡ሊለው አይችልም፡፡ሰንቆታላ፡፡ከገጠር ወደከተማ ሲገባ፡፡
" እረደኝ፡፡ግን ፈጥነህ አትግፈፈኝ፡፡ቃሌን ለማቋረጥ በጥድፊያ ካራ አትሳል...." እያለው ከሚሊዮን አንድ እጣውን በፈጥነት ፈጣጥሞት ከተማ መግቢያ ስንቁ አድርጎታል፡፡
ምን አይነት ዓለም ላይ ነው የወጣው!?
ሰውዬው ከእንስሳው የሚያንስበት ፥ እረኛውን ከብቱ በሚያግድበት ፥ ጠባቂውን ተጠባቂው ተግቶ ዘብ የሚቆምለት ዓለም ላይ ነው የወጣው፡፡

@wegoch
@wegoch
#ከግድግው_ባሻገር
በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተፃፈ
ክፍል ሁለት
ጥቂት ደቂቃዎች አልፈዋል፡፡ ቡናና ሻይ እንደደረስን ሜክሲኮ ከመድረሳችን በፊት መቀስቀስ እንዳለብኝ አሰብኩኝ፡፡ ባልቀሰቅሳት፣ ቀኑን ሙሉ ብታርፍብኝ ምነኛ ደስ ባለኝ፡፡ ምናልባት አዳሯ ከባድ ሆኖ ይሆናል፡፡ ምናልባት እንቅልፍ የተጠማች የእንቅልፍ ባዳ ትሆን ይሆናል፡፡ ምናልባት ህይወትም ምትም ትርጉም አልባ ሆነውባት በተኛውበት ብሞት ብላ በመመኘት የተኛች ይሆናል፡፡ ምናልባት የተመቸው የቤቷ ፍራሽ ሳይመቻት የደረቀውን የኔን ትከሻ መርጣ ይሆናል፡፡ መቋጫ የሌላቸው የትየለሌ ምናልባቶች በህሊናዬ እየተንሸራሸሩ ከትከሻዬ ሸርተት ማለት ጀመረች፡፡ ወደ ጥልቅ የእንቅልፍ ባህር እየቀዘፈች ነበር፡፡ ነገር ግን የእኔ ትከሻ እሷ በምናቧ እንደተመለከተችው የውቅያኖስ ያክል አይሰፋም ነበር፤ ቢመቻትም አይበቃትም፤ ቢበቃትም አያዛልቃትም፡፡ ለደቂቃዎችም ቢሆን እረፍት ውስጥ ነበረች፡፡ ጭንቅላቷ ከነበረበት ትከሻ ቁልቁል ተንሸራቶ አየር ቀዝፎ እንደገና ሽቅብ ተመለሰ፡፡ ነቃች፡፡
ዘወር ብላ ተመለከተችኝ፡፡ ደንግጣለች፡፡ እንደ ማፈር አረጋት፤ ከነበረችበት ሰፊ የነፃነት አለም ወደ ጠባቧ፣ ጎርባጯና አስቀያሚዋ አለም መመለስዋ አላስደሰታትም፡፡
“ይቅርታ! አስቸገርኩህ፡፡” በተስለመለመ አንደበት አንገቷን ሸብረክ አድርጋ ይቅርታዋን አቀረበች፡፡
“የቤርጎ አላስከፍልም፡፡ ትከሻዬን ግን ስብርብሩን ነው ያወጣሽው፡፡ ያገር ወጌሻ ቢያሸኝ ሚመለስም አይመስለኝም፡፡” ፊቴን አጨማድጄ በማስመሰል መለስኩላት፡፡
“ዖ ማይ ጋድ! አንተ ላይ ነበር የተኛውት? ወይኔ በጣም ይቅርታ አላወኩም ነበር፡፡” የእጆቿን መዳፍ በአፏ ላይ አድርጋ የጨረፍታ ተመለከተችኝ፡፡
“ገና ጠዋት ነው፤ ከባድ ለሊት ነበር መሰለኝ ያሳለፍሺው፡፡”
ቀና ብላ አየችኝ፡፡ መልስ አልሰጠችኝም፡፡ “ሜክሲኮ መጨረሻ፡፡” ረዳቱ ጠባቧን በር እየበረገደ እንድንወርድ ጋበዘን፡፡ ውስጤ ምን እንደምትሰራ ለማወቅ በጣም ጓጉቷል፡፡ ቀደም ብዬ ከታክሲው የወረድኩት እኔ ነበርኩኝ፡፡ ከአፈታ በኋላ ወረደች፡፡
“በጠዋቱ እኔ ላይ ከተኛሽ ቀኑን ሙሉማ ስንቱ ላይ እንደምተኚ ሳስበው እቺ ልጅ ቡና ያስፈልጋታል አለበለዚያ የሰውን ትከሻ ሰባብራ ነው ምጨርሰው ብዬ አሰብኩኝ፡፡ ለምን ቡና አንጠጣም፡፡” ድፍረት የተሞላበት ግብዣ ነበር፡፡
“መተኛት አለብኝ ገብቼ…ግን ውለታህን እዚሁ ለመክፈል እዚሁ አካባቢ መጠጣት እንችላለን፡፡” እያንገራገረች እሺታዋን ገለፀችልኝ፡፡
እዛው አካባቢ አንድ ካፌ ከተምን፡፡ ካፌው ግርግር ያልበዛበት በጥሩ ቅንብር ሙዚቃ የታጀበ ጥሩ ድባብ ያለው ቤት ነው፡፡ ክብ ሰርተው ከተደረደሩት ወንበር እና ጠረጴዛ መሀከል ከአንዱ ተቀመጥን፡፡ ምርጫዋን ጥቁር ማኪያቶ እና ለኔም ሻይ አዘን ወደ ጨዋታችን ተመለስን፡፡
“መቀስቀስ ትችል ነበር እኮ ስተኛብህ፡፡”
“አይ እኔ እንኳን የሰውን የመተኛት ሰበዊ መብት አልጋፋም ብዬ ነው፡፡” ፈገግ አለች፡፡
“ከመቼ ወዲህ ነው መተኛት ሰባዊ መብት የሆነው አንተ?” የግርምት እየተመለከተችኝ ጠየቀች፡፡
“መኖር ሰባዊ መብት እንደሆነ እንደዛው ሁሉ በመተኛት ውስጥም ሌላ መኖር አለ፡፡”
“ውይ ፍልስፍና ላይ ብዙም አይደለሁም፡፡ ከስራ ግን አስፈታሁ፤ ስራ እየገባህ ነው እንዴ?”
“በእርግጥ ለስራ ነው የወጣሁት፡፡ ግን ጓደኛዬ ትንሽ አርፋጅ ስለሆነ ችግር የለውም፡፡”
“እዚሁ ነው ምትገናኙት ወይስ ሌላ ቦታ?” ትንሽ ፈገግ አልኩኝ፤ ይሉኝታ ይዞኝ እንደመጣው ባላወቀች፡፡
“መውረጃዬ ስታዲየም ነበር፡፡ ያው…ግን ሳይሽ ከባድ እንቅልፍ ላይ ነበርሽ፤ መቀስቀስ አልፈለኩኝም፡፡ ለሊት አልተኛሽም ነበር?” ጥያቄው ጠጠር እንዳለባት ከፊቷ መቀያየር በቀላሉ ማንበብ ይቻላል፡፡ አንድ ሁለቴ ማኪያቶዋን ማግ ካደረገች በኋላ ትንሽ ተከዝ አለች፡፡ ጥቂት በዝምታ ተዋጠች፡፡ አንዳችም አልተናገርኩም፡፡ ቀጣዩን ንግግር ለማዳመጥ ግን ጓጉቻለው፡፡
“ከስራ ነው ምመጣው፡፡” ፊቷ ኮሶ የጠጣች ያክል ተጨማደደ፡፡ አሁንም በትካዜ ውስጥ ነች፡፡
“በደለኛነት ተሰምቶህ ያውቃል?” ከምናወራው ነገር ጋር ጭራሽ የማይገናኝ ጥያቄ፡፡
“አዎ! አንዳንድ ጊዜ እኔ የማይገባኝን ነገር ሳደርግ አልያም በማይገባኝ አከሔድ ስኖር በደለኛነት ይሰማኛል፡፡ ለምን ጠየቅሽኝ?”
“እኔ እየተሰማኝ ስለሆነ፡፡ አየህ በህይወት ስትኖር ሶስት ነገሮች የህይወት ባላንስህን ይጠብቁልሀል፡፡ ያመንከው ፈጣሪ ውይም የምታምነው ነገር፣ ህሊናህ እና በዙሪያ ያሉት ሰዎች፡፡ ለእነዚህ ነገሮች ያለህ ቦታ የተዛባ ከሆነ የበደለኝነት ስሜት ይኖርሀል፡፡”
“ታዲያ የምትሰሪው ስራ እነኚህን ነገሮች አዛባቸው?” አይኖቿ እንባን አቅረዋል፡፡
“አዎ! አሁን ግን የፀፀተኝነቱም ስሜቴ የሞተ ይመስለኛል፡፡”
“ስራሽን ማወቅ እችላለው?”
ይቀጥላል….
ስለሺ ሳልስ ዑመር
©SVC2017

@wegoch
@wegoch
#ከግድግው_ባሻገር
በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተፃፈ
ክፍል ሶስት
“ስራሽን ማወቅ እችላለው?” ያልጠበቀችው ጥያቄ ስለነበር የግንባሯን ቆዳ ሸብሽባ አይኗን አፍጣ የንዴት ተመለከተችኝ፡፡
“ለምን ማወቅ ፈለክ?”
“አይ ያን ያህል አስፈልጎኝ አይደለም፡፡ ግን አንቺ እየተሰማሽ ያለውን ስሜት በጥልቀት ለመረዳት እና በምንነጋገርበት ሀሳብ ላይ የጋራ ነጥብ እንዲኖረን በማሰብ ነው፡፡ መናገር ካልፈለክሽ ግን አስገዳጅ አይደለም፡፡”
“ማሳጅ ቤት ነው ምሰራው፡፡ በማሳጅ ቤት ውስጥ በሴክስ ቢዝነስ እተዳደራለው፡፡” እምባዋ ግጥም አለ፡፡ እኔም ያልጠበኩት መልስ ነበር፡፡
“ማሳጅ ቤት ገብተህ ታውቃለህ?”
“እዚህ ሀገር አንድ ሁለቴ ቦስተን ገብቻለው፡፡ ነገር ግን ታይላንድ በነበርኩበት ወቅት በደንብ እገባ ነበር፡፡”
“ስለዚህ አንተ ዋነኛ ደንበኛ ነሀ የታይላንዱንማ ካወቅህ፡፡”
“አይ ታይላንድ እያለው በአብዛኛው የምጠቀመው የማሳጅ አይነት ታይ ካልቸራል ማሳጅ እና ፉት ማሳጅ ነው፡፡ በእርግጥ ሌሎች ከእኛ ወግ እና ስርዐት ያፈነገጡትን ባልጠቀማቸውም እንዳሉ ግን እውቀቱ አለኝ፡፡” ጭንቅላቷን ነቅነቅ አድርጋ በዝምታ ጠረጴዛው ላይ አይኖቿን ተከለች፡፡ በእጆቿ የማኪያቶውን ብርጭቆ ከማስቀመጫው ሳታነሳ ታሽከረክራለች፡፡ የፊትዋ ገፅታ ፍም እሳት ይመስላል፡፡
“ከማሳጅ ቤት ግድግዳ ባሻገር ሰው ይቸረቸራል፡፡ ትዳር ይፈርሳል፡፡ ሴት ክብር ታጣለች፤ ከእዛ ግድግዳ ባሻገር የሰው ብርሀን እየጨለመ ይመጣል…..” እንባዋን መሸከም ያቃቱት አይኖቿ ቁልቁል በጉንጯ ላይ መንታ እያደረገ እንባዋን ይወረውራል፡፡
“ዛሬ እንቅልፍ አልተኛውም፡፡ በጣም ስራ በዝቶብን ነበር፡፡ ማንነታቸውን ከማላውቃቸው 5 ወንዶች ጋር ወጥቻለው፡፡ ሁለቱ በእድሜ አርባዎች ውስጥ የሚገመቱ ናቸው፡፡ ቀለበት አድርገዋል፡፡ አንደኛው ሴክስ አድርጎ ሲጨርስ ገንዘብ ሊሰጠኝ የብር ዋሌቱን ሲያወጣው ሁለት የሚያማምሩ ልጆች ያሉበት ፎቶ ወደቀበት፡፡ ‘ልጆቼ ናቸው፡፡’ አለኝ በድፍረት፡፡ በእዛ ስረበሽ ቆየው በኋላ ላይ ከመጡት ወጣቶች መሀከል አንደኛው ከሌላ ጓደኛው ጋር እንደ መጣ አወቅሁ፡፡ አንደኛው ጓደኛው በሌላ ክፍል እየተሰራ ነበር፡፡ ይኼኛው ደግም ከእኔ ጋር፡፡ በጣም ትንሽ ልጅ እንደሆነ ገምቼ ነበር፡፡ መጨረሻ ላይ ብር ሲሰጠኝ ስንት አመቱ እንደሆነ ጠየኩት፡፡ 17 አመቱ ነበር፡፡ ጠጥቶ ስለነበር 2000 ብር እንደሚከፍለኝ እና ያለ ኮንዶም መውጣት እንደሚፈልግ ነግሮኝ ነበር፡፡”
“ምን አልሽው ታዲያ?”
“እሱ ቢያብድም እኔ አብሬ አላብድም፡፡ በደንብ እንደማስደስተው እና ያለ ኮንዶም ማድረግ እንደማልፈልግ ነግሬው ተስማምተን ነው ያደረግነው፡፡ እሱ ለሊት ከሰራኋቸው አምስተኛ ሰው ነበር፡፡ ከእሱ በኋላ ሌላ ሰው መስራት አልቻልኩም፡፡ በ17 አመቱ ራሱን አደጋ ውስጥ መጣሉን ሳስብ ስራው አቅለሸለሸኝ፡፡ በተዘጋ ግድግዳ የተሰባበረ ህይወት ነው ያለው፡፡ በስራው ጥሩ ገንዘብ አገኝበታለው፡፡ ሁሌም ህይወቴ ሙሉና ደስተኛ ሆኖ ግን አያውቅም፡፡ ወግ እና መዕረግ የእኔ ባዳ ናቸው፡፡” እንባዋ ዝም ብሎ መፍሰሱን ያየች የካፌው አስተናጋጅ ናብኪን አቀረበችላት፡፡
“አልቃሻ ሆንኩኝ እንዴ?” የውሸት ፈገግታ ለአስተናጋጇ አሳይታ አንድ ናብኪን አንስታ ፊቷን ጠራረገች፡፡
“ወንድሜ የኔ ጉድ ተነግሮ አያልቅም ቢቀርብህ ነው ሚሻለው፡፡” አይኖቼ አይኖቿ ላይ ናቸው፡፡ ድርቅ እንዳለ ሰው ትንፋሼም አይሰማም፡፡
“ደነገጥክ እንዴ? ወይስ ደበርኩክ? መልስ አልሰጥ አልክ..”
“ይቅርታ ዝም አልኩኝ? እንዴት ግን ወደዚህ ስራ ገባሽ?”
“ታሪኩ ብዙ ነው፡፡ ከአጎቴ ጋር ሳንጣላ የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ሳይመጣልኝ በፊት ቲያትሪካል አርት መማር እፈልግ ነበር፡፡ ስለዚህ ግጥም እና ቲያትር እሰራ ነበር፡፡ ሀ…ሃ.ሃ…ሃ….ሃ…ነበር ብቻ፡፡ በኋላም ማትሪክ ስላልመጣልኝ ህልሜን ባላሳካም የውበት አጠባበቅ እና ማሳጅ ተማርኩኝ፡፡ አጎቴ የመሰለው ፀጉር ስራ ነበር፡፡ በጊዜው ከአጎቴ ጋር በጣም እንጣላ ነበር፡፡ እናም ልንመረቅ አካባቢ አንድ ጓደኛዬ ማሳጅ ስራ አትራፊ እና ብንሰራው የራሳችንን ህይወት የሚያስችለንን ነገር እንደምናገኝበት ነገረችኝ፡፡ ያኔ ይህን ስራ ሀ ብዬ ጀመርኩኝ፡፡ አስታውሳለው 22 ከሚገኝ አንድ ማሳጅ ቤት ነበር የጀመርኩት፡፡ አንድ ቀን ከሰዐት አካባቢ አንድ አረብ ሊሰራ መጥቶ እየሰራሁት ሴክስ እንድናረግ ጠየቀኝ፡፡ ደነገጥኩኝ፡፡ ማረግ እንደማልፈልግም አስረግጬ ነገርኩት፡፡ ወዲውም ከሻንጣ ውስጥ አንድ የታሸገ የ10,000 ብር እስር አወጣ፡፡…
የመጨረሻውን ክፍል ነገ ይጠብቁ፡፡
ይቀጥላል….
ስለሺ ሳልስ ዑመር
©SVC2017

@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from Ribka Sisay
Forwarded from Ribka Sisay
#ከግድግው_ባሻገር
በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተፃፈ ክፍል አራት (የመጨረሻውን ክፍል) .........................................................
“የታሸገ የ10,000 ብር እስር አወጣ፡፡ በ10,000 የሚቆጠር ገንዘብ ቆጥሬ አላውቅም፡፡ ሴክስ ካረግን ይህንን ገንዘብ እንደሚሰጠኝና በሚሰራበት የሳውዲ ኤምባሲ ስራ እንደሚያስቀጥረኝ ነገረኝ፡፡ በዛን ቅፅፈት የአጎቴ ንትርክ ትዝ አለኝ፡፡ እንደማንኛውም ሴት ልጅ የተሻለ ህይወትን እፈልጋለው፡፡ ድህነቴ ግን ያንን ላይፍ እንድሆነው አልፈቀደልኝም፡፡ ትምህርት ደግም ስላልተሳካልኝ ከአጎቴም ሆነ ከአጎቴ ሚስት ጋር ትልቅ ቁርሾ ላይ ነን፡፡ እነኚህ ሁሉ ነገሮች ተደማምረው ለደቂቃዎች ክብሬን አጥቼ ህይወቴን የሚቀይረውን መንገድ ባመቻች የተሻለ ሆኖ ተሰማኝ፡፡ ወሰንኩኝ፡፡ አንዳንዴ መራራውን ፅዋ ጠጥተህ ህይወትን ማሸነፍ አለብህ፡፡ ያ ከሰዐት ሁለት የተደበላለቀ ስሜት የተሰማኝ ወቅት ነበር፡፡ ብዙ የሚመስል ብር እና ክብርን አጥቶ ከማያውቁት ሽማግሌ አረብ ጋር መተኛት፡፡”
“ቃል እንደገባው ታዲያ የኤምባሲውን ስራ አገኘልሽ?”
“የዛን ሰሞን በተደጋጋሚ ይመጣ ነበር፡፡ እንደ መጀመሪያው ቀን 10,000 ባይሆንም 1,000 ወይም 2,000 ብር ይሰጠኝ ነበር፡፡ እንደገናም በመኪና ከስራ ስወጣ ፒክ እያረገኝ አብረን ሺሻ ቤት እና መጠጥ ቤት እንዞር ነበር፡፡ በኋላ ግን ሳይነግረኝ ከሀገር ጠፋ፡፡ ብደውልም ስልኩ አይሰራም ነበር፡፡ ምንም ማረግ አልቻልኩም፡፡ ነገር ግን የሴክስ ቢዝነሱን አዋጪ የሆነ ስለመሰለኝ ተያያዝኩት፡፡ ከአጎቴም ጋር ተጣልቼ የራሴን ቤት ተከራይቼ መኖር ጀመርኩኝ፡፡ ይህ ደግሞ የማታም ሺፍት እየገባው እንድሰራ እድሉን አመቻቸልኝ፡፡”
እምባዋ በፊቷ ላይ ደርቆ ቁልቁል መስመር ሰርቷል፡፡ አይኖቿ ልክ እንደ ፀሐይ አድማሷን በምሽት ስትዘረጋ በሰማይ ላይ እንደምትለቀው ቀይ ቀለም ቀልተዋል፤ ከንፈሯ ዝናብ እንደናፈቁ የሰሀራ በረሀ ስንጥቅጥቅ መሬቶች ደርቀው ተሰነጣጥቀዋል፡፡
“ታዲያ በእዚህ ስራ የመቀጠል ሀሳብ አለሽ?”
“አሁንስ አንገሽግሾኛል፡፡ አንድም ቀን የሰላም እንቅልፍ ተኝቼ አላውቅም፡፡ ሁሌ ነጭናጫና በቀላሉ ተናዳጅ ሆኛለው፡፡ ለነገሮች ግደ የለሽ ቁብ የማይሰጠው ሆኛለው፡፡ በስራው ምክኒያት ሰውነቴም በጣም ተጎድቷል፡፡ ሁሌ ይደክመኛል፡፡ የምግብ ፍላጎቴም በጣም ወርዷል፡፡”
“እንደነገርሺኝ ያኔ ህልምሽ ቲያትሪካል አርት መማር ነበር፡፡ እንዴት ነው አሁንስ እሱ ነገር አለ ውስጥሽ?”
“ህልሜ አይደል እንዴ? መቼ ይጠፋና፤ ሁሌም አስባለው፡፡ አንድ ቀን ከዚህ ሰውበላ ከሆነ ስራ ተላቅቄ ትምህርቴን እንደምጀምር ተስፋ አለኝ፡፡ ሲከፋኝም ሆነ ውስጤ ሲሰማኝ ግጥም እፅፋለው፡፡”
“ቅርብ ጊዜ የፃፍሽው ግጥም ወይም ሌላ ፅሑፍ አለ?”
“አንድ ቀን ስራ ቦታ ግጥም ፅፌያለው ላንብብላቹ ብዬ ስለምኞቴ እና ስለወደፊት ቤቴ እና ኑሮዬ ግጥም አነበብኩላቸው፡፡ ከዛም ‘ምትበላው የላትም ምትከናነበው አማራት!’ ብለው ተረቱብኝ፡፡ ከዛን ቀን በኋላ አንድም ቀን ለሰው የምፅፋቸውን ነገሮች አንብቤያቸው አላውቅም፡፡”
“ግድ የለም እኔ ተረት አላውቅም ለኔ ልታነቢልኝ ትችያለሽ እንደነሱ አልተርትብሽም፡፡” ከግዚያት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እውነተኛ ፈገግታ ፈገግ አለች፡፡ ፊቷም ከቅድሞ የተሻለ ገፅታ ነበረው፡፡
“ግጥም ትወዳለህ?” ቦርሳዋን በቀኝ እጇ እየከፈተች ጠየቀችኝ፡፡
“በጣም ነው ምወደው፡፡ ግን ገጣሚ አይደለሁም፡፡” ብጣሽ ወረቀት ከቦርሳዋ አውጥታ መፈታታት ጀመረች፡፡
“ትናንት በጣም በተከፋው ሰዐት የፃፍኩት ግጥም ነው ላንብብልህ?”
“እባክሽ! ግን ፍቃደኛ ከሆንሽ ልቀዳው እፈልጋለው፡፡”
“ምን በራዲዮ ልታስተላልፈው ነው እንዴ? መብትህ ነው፡፡” ፊቷ በፈገግታ ሲታጀብ፣ የተቋጠረ ግንባሯ ሲፍታታ፣ ጥርሶቿ እንደደረሰ የጥጥ ፍሬ ሲገሸለጥ፣ ጉንጮቿ በሳቅ ተወጥሮ እንደ በለስ ፍሬ ሲፈረጥም ውበቷ ከከሳው ህይወቷ አፈትልኮ ይወጣል፡፡
“ምን ይታወቃል የወደፊቷ እውቅ ገጣሚት አንቺ ብትሆኚስ? በይ ቀጥይ ጓጉቻለው እስካዳምጠው፡፡” የሞባይሌን መቅጃ አስተካክዬ ወደ እሷ ሸርተት አድርጌ አስቀመጥኩት፡፡
“እሺ ተስፋ ይሰኛል ርዕሱ…
የሚመጣው ሁሉ የሚገኘው ከፊት
ጨለማ ከሆነ ከለበሰ ፅልመት
አሁን ያየሁትን ነገር ባላየሁት ነበር
ባዘን ፋንታ ደስታ
ውጥረት ቀሎ ፋታ
ችግር አልፎ ምቾት
ውድቀት ቀርቶ ዕድገት
ይተካል ባይባል መሻል ነበረበት
ህይወት ትርጉም አልባ ተስፋ ባይኖር ኖሮ
ሰው የሚለው ፍጡር የደስ ደስ እንዲለው
ቆይታው እንዲያምር ጥረቱ ልፋቱ ልቆ እንዲሰምር
ተስማምቶና አብሮ በፍቅር እንዲኖር
መታገስ ያሻዋል በተስፋ መነፅር
የነገን እያየ የዛሬን እንዲኖር
ተስፋ ሀይል ነገር ህይወትን ቀማሚ
ሰውና ኑሮውን አንድ አርጎ አስማሚ
የዘንድሮውን አልፎ እንዲያስብ ለከርሞ
ተስፋ በጥበብህ ብልሀት ለግሰው
ቻል አርጎ እንዲኖር ‘ሰውን ልጅ አበርታው::
ይሔን ይመስላል እንግዲህ” ድስ ብሏታል፡፡ ያስታውቅባታል፡፡ ደስተኛ ነች፡፡
“በጣም ግሩም ግጥም! በጣም ሊጨበጨብልሽ ይገባል፡፡”
“ኸረ ባክህ? እንዲህማ አታካብደውም፡፡ ስምህ ማነው ግን? ሳንተዋወቅ ብዙ አወራን እኮ፤ አትፍረድብኝ ስራ ቦታ ስም ሳንጠይቅ ነው ወደ ስራ ምንገባው፡፡ በዛ ለምዶብኝ ነው፡፡” ከት ብለን ተሳሳቅን፡፡
“ስለሺ እባላለው፡፡ ሳልስ ብለሽ መጥራት ትችያለሽ፡፡”
“ኦኬ ሳልስ! ለየት ያለ ስም ነው፡፡ እኔ ፍሬዘር (ለባለ ታሪኳ ደህንነት የተለወጠ ስም) እባላለው፡፡”
“ስልክሽን ማግኘት እችላለው? ምን አልባት አንዳንድ ጊዜ ተገናኝተን ሻይ እንጠጣለን፡፡”
“ያንተን ስጠኝ እኔ ብዙ ስራ ላይ ስለምሆን ሲመቸኝ እኔ እደውላለው፡፡”
ስልኬን ወሰደች፡፡ ፍሬዘር አልፎ አልፎ በተለያዩ ቁጥሮች ትደውልልኛለች፡፡ ከዛን ቀን በኋላ ግን በአካል ተገናኝተን አናውቅም፡፡ በደወለችበት ስልኮች መልሼ ብደውልም አንዳቸውም አይሰሩም፡፡ አንዳንዴ በሞባይሌ የቀዳሁትን ግጥም ደግሜ ደጋግሜ አዳምጠዋለው፡፡ የፍሬዘር ህልም ትልቅ ነው፡፡ በተስፋ ሁሌም ህልሟ ጋር ለመድረስ ዛሬን ትኖራለች፡፡ ብዙ የፍሬዘር አይነት ህይወት የሚኖሩ ሴት እህቶቻችን በሀገራችን አሉ፡፡ ሁላችንም ከግድግዳው ባሻገር ያለውን ከባድ ህይወት ልንረዳና ልንረዳቸው ይገባል፡፡ ለፍሬዘር መልካሙን ሁሉ እመኝላታለው፡፡
እናንተም ይህንን ከግድግዳው ባሻገር የተሰኘውን ባለ አራት ክፍል ታሪክ ስላነበባቹ ከልብ አመሰግናለው፡፡ ህይወት ትቀጥላለች፡፡ እኔ ከፍሬዘር ብዙ ተምሬያለው፡፡ እናንተም ስሜቴን እንደምትጋሩ ተስፋ አደርጋለው፡፡
ስለሺ ሳልስ ዑመር ©SVC2017 @wegoch @wegoch
የማስተጋባት ክፉ ደዌ
.
ደብረ ሊባኖሳዊው ባለ ቅኔ ካህሊል ጅብራን እንዲህ ይላል:-"አንዱ ሰው በውስጡ ሁለት ሰዎችን ነው፤አንዱ በብርሃን ሲተኛ ሌላው በጨለማ ይነቃል" ይላል ይህቺን ይዘን ሌላ ከፈለጋችን እንጭለፍ። ሳንሞቀው የጠለቀው ፀሀያች አያ ሙሌ ሙሉ -ጌታ ተስፋዬ(አያዬ) ደግሞ " ለካ ሰው ጥንድ ነው የአንድ ራስ መንትያ
አንድ ነው ሲካፈል" ይለናል እያወዳደርኩ አይደለም። ግን ቢያንስ ያለንን እንወቅ። ማንም ማንንም አልቀደመም አልበለጠምም ራሱን እስካልቀደመ በቀር።ነገ ስም ያለው ተነስቶ ስለ አያ ሙሌ ቢያወራ አሽቃብጠን እና አለ ልክ አውርተን ዝም ነን። አድናቂ ከማድነቁ በፊት የሚያደንቀውን ሰው እና ግብሩን ቢያንስ በአረዳዳችን መጠን እንኳን እንወቀው ግድ የለም ጥበብ መንጋነት አትደግፍም። የሚገርመው ግን የሀገራችን የስነ ፅሁፍ አለም በመንጋ የሀሳብ ዳራ ተተብትቧል።አንድ ጫፍ ይዞ ስለ አንድ ሰው ብቻ መለፈፍ ታሪክ ገደላ ነው።
ምን አይነት የዘመኑ ዘዴ አለ መሰላችሁ የባዕድ ቋንቋ በንግግር መሃል መደብለቅ የአዋቂነት ልክ እንደሆነው ሁሉ በስነ ፅሁፍ ችሎታቸው ገዘፍ ያሉትን ስም እየጠቀሱ ገሳ መጠለል ደግሞ አዋቂነት ሆኗል።እኔ ግን አይመስለኝም። ቀድሞ ነገር የገባን ራሱ አልገባንም።የጥበብ ሰው ደግሞ ጣዎስ ወይም ኮፒ ማሽን አይደለም ከሌላው የሰማውን ለማሰማት በስማ በለው አይጋልብም።ኢትዮጵያዬ ሆይ ጥበበኞችን ስንጠራ ብቅ የሚሉትን አንድ በይልኝ እኛ ጥበበኞችን እንጂ የቡና ወረኞችን አልጠራንም።ለማንኛውም ይህን ያልኩት በማያቸው መደጋገሞች ነው። ስጋ ቤት ሲከፈት መደዳውን ስጋ ቤት መክፈት ንግድ ነው። ስጋ ቤት ሲከፈት ከጎኑ እንጀራ ቤት ፣ ቢላ መሞረጃ ቤት እና የመሳሰሉትን መክፈት ደግሞ ጥበብ ነው።
በረሃ ላይ ውሃ ፍለጋ አንዲት ቦታ ላይ ቆፍረህ ውሃ ስታገኝ ኩባያ ይዞ ከሚመጣው ሰው ይልቅ የተገኘውን ምንጭ ደግሞ ለመቆፈር የሚመጣው ይበዛል። የገጠመን ይህ ነው። ወይ ለመጠጣት ኩባያ ይዘህ ና ወይም ፈቅ ብለህ ቆፍር። ብዙዎቻችን ሰው ከሚተቸን ተኩሶ ቢገድለን እንመርጣለን እና በማወቅም ባለማወቅም የተቀየመ ካለ ይቅር ይበለኝ። እኔም ይቅርታን ጠይቄያለሁ። ቸር ሰንብቱማ
ያለንን እንወቅ!!
አድናቂነት በግርድፉ ሳይሆን ሰርፆ ይግባን!!
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
©ሲራክ
@wegoch
@wegoch
ሙትና ሐውልት
#አለማየሁ ገላጋይ

ፕሮፌሰር ጤና'ዳም ጥያቄ ምልክቱን መስለዋል(እሱ በድን ሲሆን እሳቸው ግን ፕሮፌሰር ናቸው) ከቢሮአቸው ከወዲያ ወዲህ ይላሉ፡፡ ሚዛናቸውን ለመጠበቅ እንዲረዳቸው እጃቸውን ወደ ኃላቸው ልከው አጣመሩ፡፡

ፕሮፌሰር የረበሻቸው በህይወታቸው ገጥሟቸው የማያውቅ ሁኔታ ስላፋጠጣቸው ነበር፡፡ ሁለት ሰዎች (አንድ ወጣትና አዛውንት አያቱ) በመኪና አደጋ ተጎድተው ከሞላ ጎደል የአንድ ሰው አካል ብቻ ቀርቷቸው መጡ፡፡ ለሁለቱ፡፡ ከሁለቱ ሰዎች የተገኘው አካል በዝርዝር (ማስታወሻቸውን ገለጡ) አዎ - ሁለት አይን (አንድ አንድ ማለት ነው) አሁንም ሁለት እግር፣ አንድ ልብና አንድ ሙሉ አንጎል (ልቡ የወጣቱ ሲሆን አንጎሉ የአዛውንቱ ነው፡፡) በዚህ ላይ የወጣቱ ቀሪ የላይኛው ማቀፊያ አካል ሊገጣጠም በማይችልበት ሁኔታ ተፈረካክሷል፡፡

ፕሮፌሰር ያስጨነቃቸው የቁስለኞቹ አካል ጉዳይ ሳይሆን የሀሳባቸው አለመገጣጠም ነበር፡፡ ወጣቱና አዛውንቱ የተለያየ የማይጣጣም አመለካከት አላቸው፡፡ ሁለቱም በቅዠት ላይ ሆነው ወጣቱ "ቴክኖሎጂ" ሲል "ባፍንጫክ ይትከላ'ባክ" ይላሉ፡፡ ይኸውም አደጋው ከመድረሱ በፊት ሲነጋገሩበት የነበረ ርዕሰ-ጉዳይ እንደሆነ ፕሮፌሰር ገምተዋል፡፡

"አካል የአንድ ሰው፤ ሐሳብ የሁለት ሰው እንዴት ይሆናል?" ፕሮፌሰር አሁንም ራሳቸውን ጠየቁ፡፡ በተደጋጋሚ የሁለት ሰዎች አካል በአደጋ ምክንያት የአንድ ሰው እየሆነ ይመጣል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አብረው የሚውሉት በእድሜና በሀሳብ የተቀራረቡ ሰዎች በመሆናቸው አንድ አድርጎ በመተሳሰብ እንዲኖሩ ለሚደረገው ሳንካ አልተፈጠረባቸውም ነበር ፤ ከዛሬው ክስተት ሌላ፡፡ ወጣቱ ለዘመናዊ ትምህርት እውጭ ቆይቶ የመጣ ሲሆን አያቱ ግን ከእምነት ሌላ የማያውቁ ምስኪን በብህትውና የሚኖሩ አዛውንት ነበሩ፡፡

"ሁለቱንም ከማጣት አንድ ሆነው እንዲኖሩ ማድረግ ተገቢ ይመስለኛል" አሉ ፕሮፌሰር በሀሳባቸው ወሰኑም፡፡

ፕሮፌሰር ጫት ሳይቃም፣ ዕጣን ሳይጨስ፣ ሀድራው ሳይወርድ፤ እንደው በሌጣው በሚጠነቁሉበት ምናምን ነገር ላይ አንድ ዓይናቸውን አጨንቁረው፣ አቀርቅረው በመመልከት ትንሽ ከቆዩ በኃላ በሽተኞቹ ወደተኙበት ክፍል " ደፋ - ደፋ - ደፋ" እያሉ አመሩ፡፡ አመራር የሚጠብቁትም ሐኪሞች በአክብሮት ተቀበሉዋቸው፡፡

"እህሳ? ለውጥ አለ?"
ዶክተር ችግኝ ቀልጠፍ ብሎ "እርሶ የወሰኑበት ከሆነ......" አለ
"እኔ ወስኛለሁ"
" ጥሩ ሲበዛ እድለኞች ነን ለማለት እደፍራለሁ፤ ምክንያቱም የሁለቱም ጉዳተኞች አካል ከግማሽ በላይ ቢጎዳም የሁለቱም ምላስበጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ሐሳባቸውን ልንጠይቃቸው እንችላለን ብዬ አምናለሁ፡፡

"ምላስ ብቻ ምን ሊረባ?" አሉና ፕሮፌሰር ወደ ፊታቸው ዘንበል ስላሉ ለሚዛን መጠበቂያ እጃቸውን ወደኃላ አጣምረው "የወጣቱ አንጎልና የአዛውንቱ ልብ የለም -- አይደለም?"

" አዎ ግን ከእርሶ እኔ ባላውቅም ምላሶቻቸውን፣ የወጣቱን ከልቡ ጋር ፤ የአዛውንቱን ካንጎላቸው ጋር በጊዜያዊ መልክ አያይዘን አንድ የመሆናቸውን ሀሳብ ብንጠይቃቸው ተገቢ ይመስለኛል" አለ ዶክተር ችግኝ፡፡

" ጥሩ ሐሳብ ነው፣ አንዳንድ እጅ አላቸው አይደለም?"

" አዎ"
"እንግዲያው ከውሳኔያቸው ስር አስፈርመህ አምጣልኝ" አሉና "ደፋ ደፋ" እያሉ ወደ ቢሮአቸው ተመለሱ፡፡

★ ★ ★

ሁሉም ነገር ተሳካ - የመዋጮ ኑሮውም፡፡ ፕሮፌሰር በስራቸው ዘጠነኛ ኩራት ተሰማቸው፡፡ ምክያቱም ስምንቱን ኩራት አንድ ባንድ ከዚህ በፊት በሌሎች ላይ ኮርተዋልና፡፡ ትንሽም ቅር የሚያሰኘው የአሁኑ ድበላ በአካልም ሆነ በአስተሳሰብ እኩል አለመሆኑ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ጉዳተኞቹን ሊያስማማቸው ያልቻለ የነበረው የምላስ ጉዳይ ነበር፤ ምክንያቱም የሁለቱም ምላስ ደህና ሲሆን <የኔ ይሁን፣ የኔ > የሚለው ክርክር ፕሮፌሰር ቢያስጨንቃቸውም በመጨረሻ ዘዴ ዘይደውለት በአንድ ጭንቅላት ሁለት ምላስ ተዋህዶ እንዲቀመጥ አድረገዋል፡፡ የመጨረሻ ሥራ የሚተዳደሩበትን ደንብ ማርቀቅና የሁለት አንድ የሆነ ስም እንዲኖራቸው ማድረግ ነበር፡፡ ይህም በዶክተር ችግኝ ተጠናቆ ቀረበ፡፡ "ሁሉም የጋራ ነው" ይላል ረቂቁ አፉን ሲከፍት "እግሮች የጋራ ናቸው፣ እጆች የጋራ ናቸው፣ ዓይኖች የጋራ ናቸው፣ ልብና አንጎልም የጋራ ናቸው፣ እንዲሁም ችግሮች የጋራ ናቸው.......... ደስታዎችም"

ስማቸውም <ሙትና ሐውልት> ተባለ

ሙትና ሐውልት ከተዋሄዱበት ከመውጣታቸው በፊት የመሄድ ጥምረት እንዲኖራቸው እንዲሁም የመብላት ልምምድን ተያያዙት፡፡ የሙት እግር <ነጠር> ሲል...... በመናዊነት፣ የሐውልት እግር ደግሞ <ኮሰስ> ይላል፡፡

<ነጠር - ጠር - ጠር፣ ኮሰስ - ስስ - ስስ፣ ነጠር - ጠር፣ ኮሰስ - ስስ፣ ነጠር -- ኮሰስ፣ ነጠኮስ፣ ነጠ - ኮስ፣ ነጠኮስ፣ ነጠኮስ> እያሉ ልምምዳቸውን በ <ነጠኮስ> ቅንጅት ጨረሱ፡፡ ከመዋሃጃው በደማቅ አሸኛኘት ወጡ፡፡

"ሙትዬ" አለ ሐውልት

"ሀውልትዬ" አለ ሙት

"ምነው አላምን አልኩ? ፍርሃት፣ ፍርሃት ይለኛል"

"ልብህ ስለሌለ ነዋ፣ ይልቅዬ እኔ ደስ ደስ ይለኛል፤ እመን እመን ይለኛል"

"አንጎልህ ስለሌለ ነዋ፣ አንጎል ፍርሃት ነው"

"አንጎል አለመኖሩ እንዴትጥሩ ነው ጃል"

"ልብ አለመኖሩስ፣ ዓለም ነው"

" በፊት አንስማማም ነበር - - - ሐውልትዬ"

"አሁን ተሰማማን - - ሙትዬ" አለና <ነጠኮስ> እያሉ መንገዳቸውን ተያያዙት፡፡

"ሁለት ልብ፣ ሁለት አንጎል እንዴት መጥፎ ነገር ነው ባክህ ......... ያጣላል"

"አንድ ልብ፣ አንድ አንጎል እንዴት ጥሩ ነው ............. ያፋቅራል"

"ሐውልትዬ"

"ሙትዬ"

"እኔ ምንህ ነኝ?"

"ሕይወቴ............ እኔስ ምንህ ነኝ?"

"ነፍሴ"


ልብና አንጎል፣ ነፍስና ሕይወት፣ አንድና አንድ ............... ሁለትና ሁለት ............... አራትና አራት ................... ብዙና ብ ዙ = #ሕዝብ!!!

@wegoch
@wegoch
@paappii
#ወግ_ብቻ
.
አንድ ወጣት መጥቶ << ጋሽ ስብሐት >> ይለዋል።
.
<<እ- ደህና ነህ?>> ይላል ስብሐት
.
<<ደህና ነኝ - ግን አውቀከኛል?>> ይጠይቃል ወጣቱ።
.
<<አውቄሃለሁ>>
.
<<በእውነት አውቀውኛል?>>
.
<<አውቄሃለሁ >>
.
<<አልመሰለኝም አውቀውኛል?>>
.
<<አውቄሃለሁ አልኩኮ>>
.
<<ያወቁኝ አልመሰለኝም ፤ አውቀውኛል ?>>
.
<<አዎ! >>
.
<<እሺ ማነኝ? >>
.
<<ችኮ መንቻኮ >>

@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
ትንሽ ብታስብበት መብላት እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ነው። ቄራ ውረድና አንድ ሰዓት ያህል አስተውል።
በሬውን አምገቱን ገዝግዘው ሲያርዱት ፣ ቆዳውን ሲገፉት ፣ ብልቱን ሲለያዩት ፈርሱን ሲጎለጉሉት ተመልከት።
ሆቴል ግባና አይንህን ጨፍነህ ህዝቡ ሲያኝክ ፣ አጥንት ሲቆረጣጥም ስማ። አክ! ምን አይነት መጨማለቅ! ይሄ ሁሉ ያቺን የግማት ስልቻ ለመሙላት! ቀበቶህን ባጣበቅክ ቁጥር ፈርስ እንደምትጨፈልቅ አስበህበታል? ልክ የጎለጎሉትን የበሬውን ፈርሰ የሚመስል።
ለመሆኑ በሬን ሲያርዱት በስመ አብ ብሎ ማረድ የጀመረው ቀልደኛ ቄስ መሆን አለበት እላለሁ። ቀልድ ካልሆነ እንዴት የአብን ፍጡር በአብ ስም ትገድለዋለህ??
.
ሌቱም አይነጋልኝ ገፅ 6 ደራሲ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
ሽማግሌው የከተማ አውቶብስ መጠበቂያ ስፍራ ቆመው አውቶብስ እየጠበቁ ነው። አከባቢው እንደሳቸው ሁሉ አውቶብስ የሚጠብቀውና በወጪ ወራጅ መንገደኛው ተጨናንቋል።
በይኽ መሃል በኪሳቸው ያለው ተንቀሳቃሽ ስልካቸው (ሞባይላቸው) መጮህ ጀመረ። ጥሪ ነበር። ሽማግሌው የስልካቸውን ጥሪ ቢሰሙትም በይኽ ግር ግር መኻል ስልክ ቢያነጋግሩ የቀማኞች ሲሳይ መሆናቸው ስለገባቸው ዝም አሉ።
የ "ሞባይሉ"ን ድምፅ የሰማው አንድ ጩሉሌ ሌባ ከኃላቸው አድፍጦ ሽማግሌው ስልካቸውን ከወሸቁበት ሲያወጡ መንትፎ ለመሮጥ ቋምጧል።
ሽማግሌው ግን የዋዛ አልነበሩም። ስልኩ ይጮኻል እሳቸው ግን እንኳንስ አውጥተው ሃሎ ሊሉ ድንግጥም አላሉ።
ይሄኔ ሌባው ወደ ሽማግሌው ብሎ " አባቴ ስልክዎ እየጮኸ ነው እኮ ያንሱት እንጂ"አላቸው። ውስጠ ዘ ው (ምስጢሩ) የገባቸው ጠንቃቃው ሽማግሌ ተወው ልጄ እኔ ኃላ ከምጮህ እሱ አሁን ይጩኽ "አሉት።
@wegoch
@wegoch
2024/09/24 20:29:30
Back to Top
HTML Embed Code: