Telegram Web Link
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

  ክፍል - ፮

ስሙን እነደነገራቸው መብረቅ የወረደ ይመስል ሁሉም ደነገጡ ኤልያስ የሚለው ስም ከጆሮአቸው እነደገባ ሚበሉትነ እሀል ትን አስባላቸው
አዎ የሀገሪቱ ዋነኛ ዘራፊ ማፈፍያ ከመካከላቸው መገኘቱ አስደንግጧቸዋል
ዮቶር ከፊቱ ምንም አይነበብትም ታድያ ከእኛ ጋ ለምን ቀላቀሉህ
እሱን እኔም አላውቅም በወተት ያራሰውን አንባሻ ለፊያሜታ እያጎረሳት አይኖቹን ከአይኗ አልነቀለም ብዙ አመት ሚተዋወቁ ነው ሚመስሉት
ሁሉም የቀረበላቸውን አንባሻ በወተቱ እያወራረዱ ስልቅጥ አድርገው በሉ ሶስት ቀን ሙሉ ጠብ ያላለ አንጀት ዛሬ ተንፈስ ብሏል
በሉ ተነሱ ማሳያችሁ ነገር አለ መነጋገርም አለብን ለትልቅ ጉዳይ ታስፈልጉኛላችሁ  አባ ተስፋ ስላሴ ከቤቱ ቀድመው ወተው ቀደ ቆጧ አመሩ ሁሉም ተከተሏቸው ሌባው ኤልያስም ፊያሜታን ተከትሎ ደግፍ ተከተላቸው የቆጧን በር ከፍተው ከፊት ለፊታቸው ያለውን ፍርግርግ ብረት አንሸራተው ከፈቱት
ሁሉም ወደ በሩ ዘለቁ አባ ፍርግርጉን መልሰው ከረቸሙት ሳይተታሰብ ቁልቁል ተምዘገዘገ ከአባ በስተቀር ሁሉም ተደናግጠዋል አይዟችሁ አሉ በአባት አንደበታቸው
የገቡባት ቆጥ ባልተታወቀ ሁኔታ እንደ አሳንሰር ወደ ታች ተምዘግዝጋ ቆመች
ፍርግርጉን አንሸራተው ከፈቱት
ሁሉም ወደ ታች ወረዱ ድቅ ድቅ ጨለማ ውጧቸዋል አባ ከነሱ ነጠል ብለው የሆነ ነገር ሲያንሸራትቱ ጨለማው በደማቅ ብርሀን ተሞላ
ሁሉም የሚያዩትን ማመን አልቻሉም እንዴት ወደ ዚ እንደመጡም ምንም ሚያቁት ነገር የለም
አለም ላይ ብዙ እውቀትን ያሳደዱት ምሁራን እንዲህ ያለ ትልቅ ቤተ መጽሀፍት አይተው አያውቁም ቁስለኛዋ ህመሟን እረስታ በምታየው ነገር እየተደመመች ነው ሌባውም ምን ጉድ ነው ብሏል ሌሎችም እንደዛው
በትላልቅ ምሰሶዎች ላይ ከተሰሩት መደርደሪያዎች ላይ የታሪክ የስነ ፈለግ የህክምና የሳይኮሎጂ የሀይማኖት የመዳኒት ቅመማ የቴክኖሎጂ የመሳሰሉት በየዘርፉ ተሰንደው ተቀምጠዋል ከማማው ላይ ያሉትን ለማውረድ ትላልቅ መሳላሎች ቦታ ቦታ ይዘዋል
አፋቸውን ይዘው እያልጎመጎሙ  አንገቶቻቸወን እየሽከረከሩ አይኖቻቸውን እያርገበገቡ ወደ አዳራሹ መጠጋት ጀመሩ
ከሰፊው አዳራሽ መሀላ ላይ ካለው ትልቅ ግርግዳ ላይ #ሻርማይክ የሚል ፅሁፍ በሮዝ አበባ ላይ ተስሎ ይታያል
ሁለቱ ሰአልያን ከመፅፀፍቶቹ በላይ የስዕሉ አሳሳል መስጦ አስገርሟቸዋል
በዚ አዳራሽ ከገባንበት ጨለማ እንወጣለን ከጨለማው ያስገቡንን እኛ ወደ ጨለማ እንከታቸዋለን
እንኳን ደህና መጣችሁ አባ ተስፋ ስላሴ ደስ የሚል ፈገግታ ለገሷቸው
ውሎ እያደር ሁሉም ተግባቡ ቁስለኛዋም ቁስሏ ደርቋል ሰባቱም ውሎ አዳራቸውን ከመሬቱ ስር ካለው ቤተ መፅሀፍት አድርገዋል
ሌባውም አመሉ ለቆት ከመፅሀፍት እውቀት መስረቅ ጀምሯል
ሰባቱ እድለኞች ከመሬት ስር ካለው ቤተ መፅሀፍት ትልቅ ሀሳብ እያሳቡ ነው መንግስት በነሱና በተሰዉት ምሁራን ላይ ያደረሰውን በደል ዋጋ ለማስከፈል ተዘጋጅተዋል
የቤተሰቦቻቸውን ናፍቆት ዋጥ አርገው ለአላማቸው ቆመዋል
የሀገራቸውን ልዩ ልዩ ቅርሶች ከመንግስት እጅ እየነጠቁ ተቋሙን ወና ለማስቀረት ወስነዋል
ከቱሪዝም ሚመጣውን ገንዘብ በአፍንጫው ይውጣ ብለው ካዝናውን ለማራቆቶ ተዘጋጅተዋል
ከአንድ አመቱ ትውስታ ሁሉም ተመልሰዋል......
ያለፈውን አንድ አመት የሆኑትን እያስታወሱ ከሬዲዮ በሰሙት ዜና እየተዝናኑ ነው
ከጠረጴዛው ላይ ያለችውን ሬዲዮ ፊያሜታ ጠረቀመቻት የእግሯ ጠበሳ ቦታውን እንደያዘ ነው ህመሟን የልጇን ናፍቆተት እያሰበች ታዝናለች   ሌሎቹም እንደዛው
እሳቱ ፍም ሆኖ ቅዝቃዜውን እያመጣው ነው
የሻርማይክ ቡድን አባላት ከፍሙ ስር ሆነው የአንድ አመት ትውስታቸውን መልሰው እየቃኙት ነው ቀጣይ ለታሰበለት ትልቅ እቅድ ሁሉም ቆርጠው ተነስተዋል
አባ ተስፋ ስላሴ የእያንዳንዱ ቅርስ መገኛ ቦታ እና ምንነት በመንገር የስድስቱንም ህይወት በማትረፍ እንደመሪነ ይቆጠራሉ
ሴቷ ጠቢብ ፊያሜታ አብርሀም የእያንዳንዱን ድርጅት የቤት ካርታ ንድፍ በማውጣት የማምለጫ እና የመውጫ በሮችን ትጠቁማለች
ሰአሊው ስምኦን ካሳሁን እስከዛሬ የተሰረቁትን ውድ ስዕሎች ተመሳሳይ እየሳለ ትልቅ የማጭበርበር ስራ በመንግስት ተቋማት ላይ ይሰራል
ሁለቱ ወንድማማቾች ኢላማ የተደረጉትን ድርጅቶች በመሄድ በ የደህንነት ካሜራዎችን የደህንነት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች የተጠመዱ አላምሮች ጨረሮችን ፈልፍለው በማወቅ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ
የኮምፒውተር ባለሙያው ቢንያም ቃኘው የደህንነት ካሜራዎችን የተለያዩ መሳሪያዎች የባለስልጣናት ስልኮችን በመጥለፍ ጥበቃውን ያፀዳዋል
ኤልያስ ሽመልስ ወደ ተመረጡት ቦታዎች በመሄድ ያካበተውን የዝርፊያ ችሎታ በመጠቀም የኢላማውን መጨረሻ ያሳምረዋል
ሰባቱም ድርሻቸው ትልቅ ነው
የሚቀጥለው ኢላማ ምደነው ፊያሜታ ጥያቄዋን ወረወረች.....

      ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@Wegoch
@wegoch
@wegoch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

  ክፍል - ፯

በፊያሜታ ጥያቄ ሁሉም የተስማሙ ይመስላሉ ከእሳቱ ፊት ለፊት ወደ ተቀመጡት አባ ተስፋ ስላሴ አይኖቻቸውን ላኩ
ረጋ ብለው የነበሩት አባ ቡዙም ማሰብ አልፈለጉም
ይበቃናል .. ደገፍ ካሉበት ወንበር ወረድ ብለው እጆቻቸውን ጉልበታቸው ላይ ጣል አደረጉ
ምኑ ነው ሚበቃው መነፅሮቹን እያስተካከለ ቢንያም ጠየቀ
ከእንግዲህ በዚ መሸገግ ይበቃናል ንፁህ ብርሀን የቤተሰቦቻችን ፍቅር ያስፈልገናል ስለዚህ ሁላችንም ወደየ ቤተሰቦቻችን መመለስ አለብን
ማንም አልተቃወማቸውም ሁሉም በሀሳባቸው የተስማሙ ይመስላሉ
ቆይ ያቺ ደግ እናትህ አልናፈቀችህም ባንተ ናፍቆት ስትጎሳቆል አታሳዝንህም የአባ ንግግር የቢንያም አይኖችን ጠንቁለው ገብተው እንባ አስቀረሩት
እናንተስ አባታችሁን ማየት አትፈልጉም ለሁለቱ ወንድማማቾች ጥያቄያቸውን ወረወሩ ሁለቱም እርስ በእርስ በአይኖቻቸው ተያዩ
አንተስ ሰአሊው ከውድ ባለቤትህ እና ከልጆችህ ጋ ተመልሰህ መኖር አልፈለክም
ፊያሜታ አንቺስ ካለ አባት የሚያድገው ውብ ልጅሽ አልናፈቀሽም አቅፈሽ ግንባሩም ለመሳም አልጓጓሽም
አንተስ ከበፊቱ የተሻለ ህይወት የእርጋታ ኑር ቤተሰብ መስርተህ መኖር አልፈለከም ኤልያስ ከአባ ይህን ቃል እንደሰማ አይኖቹን ወደ ፊያሜታ ላካቸው
በፍቅሯ የወደቀው ገና እግሯን ተመታ ከእቅፉ የገባች ግዜ ነው ውበቷ አሳስሮ ይዞታል ብልሀቷ ቅልጥፍናዋ ሴትነቷ ገዝቶታል እሷም ለሱ ደስ የሚል ስሜት አላት ሁሌ ባከናወኑት ስራ ሲደሰቱ አብረው ከጨለማው ገብተው ያወጋሉ ይጫወታሉ ከእቅፉ ገብታ ከልቡ ላይ ትተኛለች ትርታውን እየሰማች የኔ ሌባ ትለዋለች
የመጨረሻ ምኞቱ እሷን አግብቶ መኖር ሆኑአል
አባ ዝቅ ካሉበት ጉልበታቸው ቀና ብለው ደገፍ አሉ ስለ እሳቸው ቤተሰቦች እያሰቡ ነው
ሁሉም በሀዘን በናፍቆት የሗሊት ሸመጠጡ
ግን.....         አባ ሁሉንም ከገቡበት ትካዜ አነቋቸው
ግን አንድ የመጨረሻ ስራ መስራት አለብን የእስከዛሬዎቹን መፃህፍት ቅርሶች ስእሎችም ከወሰድንባቸው ቦታዎች መልሰናቸዋል ከመንግስት እጅ ያወጣናቸውንም ቅርሶች ከዝርፊያ ስለሆነ ያዳነው በራሳችን ቦታ አስቀምጠናቸዋል
አሁን ግን ለህዝባችን ለሀገራችን ምንሰራው አንድ ስራ አለ በተለይ ህክምና አተው መዳኒት አተው ለሚጎሳቆለው የሀገራችን ህዝም መፍትሄ የሚሆን ስራ ነው
በባለፈው ሳምንት ከአንድ ገዳም የተሰረቀ #እፀ-ደብዳቤ የሚል የብራና መፅሀፍ በጀርመኖች እጅ ገብቷል እነሱም በኤንባሲያቸው በትላልቅ የደህንነት ባለሙያዎችና በተደራጀ የሴኩሪቲ መስመር እየተጠበቀ ነው ከሶስት ቀን በሁዋላ ነው ይዘውት ወደ ሀገራቸው ሚበሩት በዚች ትንሽ ቀን ከእጃቸው ወስደን በመፅሀፉ ላይ ትልቅ ምርምር አድርገን ህክምናና መድሀኒት ለሚሻው ህዝባችን በባህል ሀኪሞቻችን ታግዘን መድሀኒት እንሰጠዋለን
መቼም በፋብሪካ እንስራው ብለን ለመንግስት ተብዬው ብናመለክት መልሶ ወደ ናጋዚ ነው እንደማያጉረን ምንም ማረጋገጫ የለንም
ስለዚህ ይህን ትልቅ መፅሀፍ ከእጃቸው ላይ መውሰድ አለብን
ያው እንደለመዱት ከእኛ አፍ ወስደው በስማችን መፅደቁን ለምደውታል ከአለም በመዳኒት ቅመማ ቁንጮ የሆነችው ጀርመን ተብዬ መናጢ ከእኛ ዘርፋ በወሰደችው መፅሀፍት ነው አሁን ደሞ በዚ መፅሀፍ አሁን ላሉት በሽታዎች ወደ ፊት ለሚመጡት ጭምር ሙሉ የመድሀኒቱን ቅመማ በመፅሀፉ ላይ ሰፍሮ ይገኛል
ቢያንስ ለመዳኒት ምታወጣውን ገንዘብ በባህል ሀኪሞቻችን እናድንላት
ለህዝባችን ለእናት ኢትዮጵያችን......

        ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ልብ ሰባሪ የአለማችን 4 ንግግሮች

1 በሶሪያ ጦርነት የቆሰለው ህፃን ለዶክተሩ «እኔ ወደ ፈጣሪ መሄዴ ነው
የሆነውን ሁሉ እነግረዋለው»

2 ኢራቅ ሞሱል ውስጥ ቆስላ እየሮጠች ካሜራማኑ ሲቀርፃት «አጎቴ እባክህ
ቪዲዮ አትቅረጸኝ ምክንያቱም ሂጃብ አለበስኩም»

3 አንድ ህፃን በፍልስጤም እጅግ በጣም ይራብና «ፈጣሪ ሆይ እባክህ በቶሎ ወሰደኝ አንተ ከወሰድከኝ በገነት ውስጥ አልራብም እዛ እበላለሁ»

4 በአፍጋኒስታን ጦርነት እጁ ክፉኛ የቆሰለው ህፃን ለሕክምና ዶክተር ጋ
ወስደውት ለዶክተሩ «ዶ/ር እጄን ስትቆርጠው ልብሴን አትቂረጠው ተጠንቀቅ ምክንያቱም እኔ ሌላ ልብስ የለኝም እና» አለው ።

በጦርነት ምክንያት እጅግ ፈታኝ የሆነ ድህነት በሶሪያ፣ አፍጋኒስታን ፣ ፍልስጤም እና ኢራቅ በርትቷል። እንፀልይላቸው ከነሱም የጦርነት አስከፊነትን እንማር።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#afendi mutaki
በትዕግስት በሪሁን

፳፬-፰-፲፪

ለዘመናዊነቱ ወደር የማይገኝለት ሆስፒታል ውስጥ እገኛለው። የእንግዳ መቀበያው ጋር ተሠይሜያለው። በትክክል መረዳት ያልቻልኩት እዚህ ቦታ ምን እየሰራው እንደሆነ ነው። አጠገቤ የተቀመጡትን ሰዎች ገልመጥ ገልመጥ ብዬ ለመመልከት ሞከርኩ። የማውቀው ሰው አጣሁ። ሀኪሞቹም ቢሆኑ ከዚህ በፊት የማውቃቸው አይደሉም። ታዲያ ምን እየሰራሁ ነው? ጥያቄውን ለእራሴው ሠነዘርኩ። ዝምታ...... ግራ መጋባት.....
"ኧረ ዶክተር አልቻልኩም.... ኧረ ውይይይይ.." ከሃሳቤ ያነቃኝ በዊልቸር እየተገፋ በአጠገቤ ያለፈ ታካሚ ነበር። ትንሽ ስላስበረገገኝ ወደ ሰውየው አፈጠጥኩ። ወጣት ነው በ፳ዎቹ መጨረሻ ላይ የሚገመት። ጉዳቱ እንዳሰብኩት እንዳልሆነ ያወኩት ሙሉ የአካል ክፍሎቹ እንዳሉ ስረዳ ነው። ከጩኸቱ መግነን እሣት የለበለበው አሊያም ከባድ የመቆረጥ አደጋ የደረሰበት ነበር የመሰለኝ። ነገር ግን ጉዳዩ ሌላ ነው። ወጣቱ ሆዱ አካባቢ የተወጠረ ነገር ተመለከትኩ ከእግሮቹ መካከልም ፈሳሽ ይፈሳል። እንዴ ምንድንነው ነገሩ??.... አእምሮዬ ውስጥ የተፈጠረውን ሃሳብ ማመን አልፈለኩም። ሁኔታውን ወደጎን አድርጌ ሌላ ነገር ለማሰብ ሞከርኩ። ኮሪደሩ ላይ አንዲት ሴት በችኮላ እየተራመደች በአጠገቤ አለፈች። አነስ ያለ ዘመናዊ ዘንቢል አንጠልጥላለች ፔርሙዝ ይታየኛል።
" የደረሰ ወንድ አሁን በዚህ አለፈ?" አለች ጠደፍ እያለች
እንግዳ ተቀባይዋ እርጋታ ተላብሳ መለሰችላት
" ወደ ማዋላጃ ክፍል ገብቷል.... ነገር ግን ማንም ሰው መግባት አይችልም እባክሽ እዛ ጋር አረፍ በይ" በቀኝ እጇ እኔ ወደተቀመጥኩበት አመላከተቻት።

የፈጣሪ ያለህ!!!! ምንድነው የምሰማው? ቅድም ያየሁትን ተጠራጠርኩ። አይ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ ወንድ ስለመሆኑ። ምን እየተፈጠረ ነው? ከቀድሞው በባሰ ግራ ተጋባሁ። የምጠይቀው ሰው ለመፈለግ በድጋሚ ዙሪያገባዬን ቃኘው። ከንቱ ልፋት።

" የአቶ ዘሪሁን ቤተሰቦች..." አንዲት ነርስ እኛ ወዳለንበት እየተመለከተች ተጣራች
" አቤት... አ.ቤት እኔነኝ... ማለቴ ባለቤቱ ነኝ" አለች የቅድሟ ሴት ከመቀመጫዋ እየተነሳች ትንሽ መርበትበት ይታይባታል።
"እንኳን ደስ አለሽ ባለቤትሽ በሠላም ተገላግሏል" ረዘም ያለ እልልታ.... እልልልልልልል .. በዙሪያችን ያሉት ሁሉ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ የእንኳን ደስ አለሽ መልእክት አዘነቡላት።
' መእዛ ምን እየሰራሽ ነው?' አእምሮዬ ስሜን ጠርቶ የጠየቀኝ መሰለኝ። እውነትም ምን እየሰራሁ ነው? ውሉ ባልገባኝ እና ምን እየተከናወነ እንደሆነ በማላውቅበት ቦታ ምን እያረኩ ነው? ተነስቼ መውጣት እንዳለብኝ ወሠንኩ። ከቦታው በፍጥነት መልቀቅ ስለፈለኩ ወደ አሳንስሩ አመራሁ ብዙ አላስጠበቀኝም። በውስጡ ፪ ሰዎች ይዟል ከኔ በላይ ካለው ፎቅ እንደመጡ ተመለከትኩ።
" ...ጌች ግን ታድሏል ሲመኝ እንደነበረው ወንድ ልጅ ተገላገል አይደል?" አለ ጠቆር ረዘም ያለው ወጣት
" እንዴ በጣም እንጂ ትላንት እራሱ ድካሙን ረስቶ ደስታ በደስታ ነበር" አለ የሰውየው ደስታ ተጋብቶበት
" እንኳን አደረገለት.. በሠላም መገላገሉ በራሱ ትልቅ ነገር ነው ለነገሩ ሃኪም ቤቱም ለማዋለጃ ብቻ በመሆኑ ጥሩ ነገር ያቀርባሉ" አለ የመጀመሪያው ሰው
እየመጣሽ ተኚ... አለ ያገሬ ሰው... ጭራሽ? የቅድሙን ወላድ በስህተት አሊያም በስንት አንድ ጊዜ በሚከሰት ክስተት የተፈጠረ ነው ብዬ ላምን በደረስኩበት ጊዜ ሌላ መርዶ? ሌላ አእምሮዬን የሚወጥር ነገር?
" መአዚ በቃ አመኚ ወንዶች መውለድ ጀምረዋል" አለኝ ውስጤ በለሆሣስ። አማተብኩ " ደግሞስ እስከመቼ እናንተ ሴቶች ብቻ የዚህ ነገር ተሸካሚ ትሆናላችሁ? እኩልነቱም ቢሆን በሚታይ ነገር ያምራል" አእምሮዬን ዝም ማስባል አልቻልኩም። በሩጫ ከሆስፒታሉ ቅጥር ወጣሁ።

* * * * * * * * * * * * * * * * ረቂቅ እና አጋሮቿ ያዘግጁት ዝግጅት ላይ ዘግይተን ነበር የደረስነው። ረቂቅ የረዱ የአጎት ልጅ ናት። ' የሴቶች መብት አቀንቃኝ ከሚባሉት ዋነኛዋ ናት። የ 'feminism'(ሴቶች የወንዶች ያህል መብት ይኑራቸው) ፅንሰሃሳብም ከሚያራምዱ ሰዎች ቀንደኛዋም ናት። ረቂቅ የመክፈቻ ንግግር አድርጋ ከመድረክ ከመውረዷ ነበር የደረስነው። ሃሳቡን ባልደግፈውም በረዱ ውትወታ እዚህ ተገኝቻለው።
"በቅድሚያ አላማችንን ደግፋችሁ እዚህ ለተገኛችሁ በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለው.." ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተሠማ። ''ወይ መደገፍ" አልኩኝ በልቤ
ቀላ ያለችው ሴት ንግግሯን ቀጥላለች
".... እንደሚታወቀው ዓለም የወንዶች ሆና ኖራለች። ከዚህ በኋላ ግን ይህ ሁኔታ አይኖርም! በእኛ እና መሠል ሴቶች ይቀየራል!" አሁንም ጭብጨባ
"... ዛሬ ፩ ብለን የምንጀምርበት ቀን ቢሆንም ለረጅሙ ጉዞአችን ብዙ ስንቅ የምንቋጥርበት ነው። በወንዶች የተያዙብንን የበላይነቶች በሙሉ የምናስመልስበትን ስንቅ የምንቋጥርበት። መብታችንን የምናስከብርበትን መንገድ አሐዱ የምንልበት። የወንዶች ፈላጭ ቆራጭነት የሚያበቃበት፣ ከታዛዥነት የምንወጣበት ጊዜ ነው።" ጭብጨባው ቀጥሏል

" ስለ ምን ታዛዥነት ነው የምታወራው? ባል የቤት ራስ መሆኑ ምኑ ላይ ነው ክፋቱ? ልባም ሴት ሆኖ ባልን እንደሚፈልጉት አድርጎ መስራት ሲቻል..."

" እስከሚያልቅ መቆየት አለብን?" አልኳት ፊቴን ወደ ረዱ አዙሬ
" መአዚዬ የአዳራሹን ጉዳይ ስላስፈፀምኩላት መጨረሻ ላይ ለምስጋና ስለምትጠራኝ ነው ትንሽ ብቻ 'ፕሊስ' " አለችኝ ረዱ።

ሌሎች ብዙ ሰዎች መድረኩ ላይ እየተፈራረቁ ንግግር አደረጉ። የሚያስደነግጡ፣ ከተፈጥሮ ያፈነገጡ ሃሳቦችን አደመጥኩ። ቢቻል የማይለወጠውን የተፈጥሮ ትዕእዛዝ ለመለወጥም እቅዱ እንዳላቸው እየተፈራረቁ አሠሙን።
.
.
.
.
.
.
.
አዎ! እራሱ ነው። ይኼ የ 'ፌሜኒዝም' ስብሰባ የፈጠረብኝ ነገር ነው። አእምሮዬን ሳልሰጣችው እንዴት ይኼን ያህል ተቆጣጠሩኝ? የእቅዳቸው ደራሲ እስክመስል ድረስ፤ የህልማቸው አቀናባሪ እስክሆን ድረስ እንዴት ይህን ያህል ምስል አእምሮዬ ፈጠረ??? አማተብኩ። የትላንት ምሽቴን ቅዠት አስቤ ተሣለምኩ።
ጌታሆይ ተፈጥሮህን ጠብቅ።

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
ይህ የአብዮተኞች ድምፅ ነው፡፡

የባለቅኔው ልጅ ሜዳ ወድቆ እኛ ቤት ደፍተን ቤት መተን አንገጥምም!!!



አዳሜ እና ሄዋኔ ትሰሙ እንደሆነ ስሙ!!! እዚህ ጋር ያንተን ላይክና ኮሜንት ለመሰብሰብ የሚፃፍ ትርክት የለም! ይልቅዬ ኪስህን አስዳብስሃለሁ! መፍትሄ አፈላላጊ አድርጌ እሾምሃለሁ ፡ ከችግር ፈጣሪነት አረንቋ ትላቀቃለህ !!!

ዳይ ዳይ ዳይ ሙስሊም ነሽ ክርስቲያን ነሽ ጦማሩን በሚገባ ተከታትለሽ የሚጠበቅብሽን ታደርጊያለሽ /ውልፍት እንዳትይ!/

እንደው የማያገባህ ጉዳይ ውስጥ ገብቼ እዘላብዳለሁ የምትል ካለህም መሰነባበቻ ቆመጥ ይሳብብሃል ወደ ጥልቁ ፅልመትም ትወረወራለህ፡፡

°°°°°°°°°°°••••••••••°°°°°°°°°°

ይህ የማየው ሰው ማነው ካላችሁ የታላቁ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ /አያ ሙሌ/ ልጅ ዳንኤል ነው ሸህ አብዱ ፡፡

ስለ ሙሉጌታ ተስፋዬ በኔ አንደበት ለማውራት ይከብደኛል ፡ ይልቁኑ አዋቂ ዘያሪዎች ያወጉትን ከኮሜንት መስጫው ሳጥን ሊንኩን አኖራለሁ፡፡ ግን ይሄንን ብቻ ልንገርህ አንተ ካህሊል ጂብራን ትላለህ አንተ እነ ሩሚን ምናምን ጠቃቅሰህ ደረትህን ልትነፋብኝ ትችላለህ እኔ ግን እልሃለሁ ቅድሚያ ባለኝ የሃገሬ ምጡቅ ላይ ኩራቴ ያይላል ፡፡ የኛ ባለቅኔ ነው ሙሉጌታ ፡ አፍህን ሞልተህ መኩሪያዬ የምትለው ነፍስያው የምትጥም የከተበው የማይነትብ ባለ ብሩህ አዕምሮ ባለቤት! ( በሱ ስራዎች የዝናን ማማ የተቆናጠጣችሁ አርቲስቶቻችን እስኪ በሉ መስክሩ)


✿ እንግዲያው ወደ ቁም ነገሩ እንምጣ ✿

እርሱ ሳለ እንዳሻው ይቦርቅ የነበረ አባቴ መከታዬ ነህ እያለው ከእርሱ ጋር ቅኔውን ሲደረድር የቆየው ልጁ ዛሬ እንደቆሻሻ ተጥሎ ይገኛል፡፡ የባለቅኔውን ሙሉጌታ ተስፋዬን የአዕምሮ ጭማቂ ለህዝብ ያጠጡ አርቲስቶቻችንም በመከራ የሚጠቀማትን ዳቦ በሻሂ ሲምግ በሶ ብጥብጡን ሲጠቀም እያዩ ያልፋሉ!!!

☞ እሺ ስለማያውቁት ነው ብለን ቨቀናነት እናስብና እወቁልን ብለን እየጮህን ነው፡፡

☞ ይሄ አብዮት ስያሜው #የግጥም_አብዮት ሆኖ ሳለ የግጥም አባቶችን ውለታ አለመክፈል ይከብደዋልና ሊጮህ ተገዷል፡፡

☞ እርግጥ ነው ፡ የወደቀን የሚወድ እምብዛም የለም ( ብር ካልሆነ ለማንሳት ገድም አንል)

✿ ወድ አብዮተኞቻችን ሆይ አሁን ጥያቄው አጭር እና ግልፅ ነው ፡ ይህ ሰው ሶማሌ ተራ ላይ ድንጋይ ትራሴ ብሎ ተጎሳቁሎ ይገኛል ፡፡ የሚበላውን እህል የከፈተውን ጉሮሮ ከሚዘጋ ፈጣሪ ዘንድ እንጂ በራሱ የሚያገኝበት መንገድ የለውም፡፡ አባቱን በማጣቱ ምክንያት በደረሰበት ጫና ምክንያት ከጭንቀት አልፎ ድብርት ከድብርት አልፎ ድብታ ውስጥ ገብቷል፡፡ እውነት ለመናገር ያ በብዙ ሰዎች ይከበብ የነበረው የበርካታ ዝነኞችን ፊት ይቃኝ የነበረ አይን ዛሬ በብቸኝነት ሲከበብ የአዕምሮ ቀውስ ቢገጥመው አይገርምም!

✿ በልዩ ቀና ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ንቁ! እዚህ መንደር በርካታ ፈጣሪ ፀጋውን ያበዛላችሁ ሰዎች እንዳላችሁ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ እውነት ለመናገር የጥቂቶቻችሁ እገዛ ብቻ ይህን ምስኪን ይታደገዋል፡፡

✿ ይህ አብዮት የግጥም ልጅ ወድቆ ቤት አይደፋም ቤት አይመታም ! ይሄ የምታዩት ሰው መጠለያ አጥቶ እኛ ከፀጋዬ ቤት ወል ቤት ከወል ቤት ሰንጎ መገን እየዘለልን አንገጥምም!!!!

ወደን ሳይሆን በግዳችን ይሄን ግዳጅ እንወጣለን ፡ ያኔ ነው ከፍታችን! በሉ በሉ የምን መቆም ነው ለጊዜው ጥቂት ብር ወርውሩ ጊዚያዊ ማደሪያ ቤቱ ይሰራለት ዘንድ የሚበላው የሚለብሰው እንዳይቸግረው ጠግቦ ያድር ዘንድ ብቻ!!!


እንግዲህ በኔ ቅዱስ ታደሰ ንጉሴ እንዲሁም ፍቃዱ ስማቸው መኮንን ከእናንተ የሚገኘውን ሳንቲም በማሰባሰብ ከሌሎች አብዮተኛ ገጣሚ ጓዶች ጋር በመሆን ለጊዜው የሚያስፈልገውን ለማድረግ በሚል ብቻ እንቀሳቀሳለን ፡፡ ሳትሰስቱ በሚመቻችሁ በኩል አለሁ በሉ፡፡

➊ ቅዱስ ታደሰ ንጉሴ ☞ 1000160263664 /የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ/

➋ፍቃዱ ስማቸው መኮንን☞19859107 /አቢሲኒያ ባንክ/


አረ ቀስስስስስ አትሻሙ ፡ እዚህ ጋር እኛ አነስተኛ #ቤት ለማሰራት፣ የሚበላው እንዳይቸግረው እና የሚለብሰውን እንዳያጣ ለማድረግ ጥቂት ሰው ነው የምንፈልገው!


ወዳጄ #ዋናው ዋናው ዋናው ስራ በቀጥታ ጉዳዩ #ለሚመለከታቸው ሰዎች አሳውቁና #እንዲሰበስቡት ይሁን ፡፡ የባለቅኔው ውለታ ያለባችሁ ተፍ ተፍ በሉ ሳይካትሪስትም ያሻዋልና አለሁ አለሁ በሉ ፡፡

ወዳጄ አዳምጠኝ ይሄ የከፋ ነገር አይደለም እጅግ በጣም ቀላል ነገር ነው ፡ እጅህን አትሰብስብ ፡ ነገ ላይ ራሱን አቅንቶ ታላቅ ነገር የሚሰራ ሰው ሜዳ ላይ ወድቆ እጅህ ቆርሶ እንዳይበላ፡፡

★የፍቅር ዘማች ወለየዎች ከወዴት ናችሁ?!

★ኢትዮጵያውያን አርቲስቶቻችን ውለታው የለባችሁም ወይ? ትላንት ሙሉጌታ ሳይሞት እንዲህ ባረኩ ኖሮ የምትሉትን ጉዳይ ለምን በልጁ ክሳችሁት አዕምሯችሁ እረፍት አያገኝም?!!!

እዚህ አብዮት ውስጥ ሰው ልትገል ደም ልታፋስስ የገባህ ካለ አሁኑኑ ለቀህ ውጣ፡ እንሆ አብዮቱ ሰው ሰው የሚሸቱ ስራዎችን የሚሰራ ነውና ሰው ለማዳን የምትሻ አብረኀን ዝለቅ ፡ ጣፋጩን ፍሬ ትበላለህ 🙏

#ሼር/SHARE እያደረጋችሁ ለመላው ኢትዮጵያውያን የማድረስ ግዴታችሁን ተወጡ፡፡ እንደ ሜቄዶኒያ ያላችሁ #ግብረ_ሰናይ ተቋሞች እያያችሁ አትለፉ !



"በመዋረድ ቀን፣ የለም ዘመድ፥
ዘመድ እንኳ ቀን ሲጎድል፣ ይኾን የለም ወይ ባዕድ፣
የሥጋ ኑሮህ ሲሟላ፣ ሲትረፈረፍልህ ማዕድ፣
ከነገድህ ያልኾነው፣ ከዘርህ የማይወለድ፣
የሚዛመድህ ብዙ ነው፣ ባዳም ይኾንሃል ዘመድ፣

ቀን ሲጎድል ግን፣ እንዲህ ነው፤

ሐዋርያውን ቢጠይቁት፣ ዐላውቀውም ብሎ ካደ፣
ፈጣሪውን ተወና፣ ከባዕድ ጋር ተዛመደ፤
ዘመድስ ዮሐንስ ነው፣ የነጎድጓድ ልጅ ብርቱ፣
መቃብር እስኪወርድ ድረስ፣ አልተለየምና ከእናቱ፤

ግጥም(በግዕዝ)☞የቅኔ ሊቅ አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ
ትርጉም ☞ በመምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ዳይ ዳይ ዝም ብለህ አትይ ሼር እያደረክ የበኩልህን ተወጣ ይህን አስከፊ ጊዜ ተጋግዘን እንሻገር ፡፡

ሀሉም ቢተባበር __ የት ይደረስ ነበር 🙏🙏🙏
#የግጥም_አብዮት

@wegoch
@wegoch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

   ክፍል - ፰

ሁሉም ለትልቁ እና ለመጨረሻው አላማ ዝግጁ ሆነዋል ይሄ እንዳለቀ ከሚናፍቋቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር ሚገናኙበት ቀን እሩቅ እንደማይሆን ተስፋ አድርገዋል
እቅዱንም አሳክተው መድሀኒት ለሚሻው ህዝባቸው ትልቅ ነገርን ሊያደርጉለት እንደሆነ ወስነዋል
#ፊያሜታ በተዘረጋላት መረብ ከጀርመን ኤንባሲ አዲሷ ወጥ ቤት ሆና ተገኝታለት
#ዮቶር ከኤንባሲው ቢሮዎች ሰተት ብሎ ገብቶ አዲሱ የቢሮው የማሽኖች እና የኮምፒውተሮች ጠጋኝ በሚል የካሜራዎችን ሲስተም የደህንነት ሁኔታዎን በስሩ ተቆጣጥሯል
#ስምዖንም አዲስ ለተገነባው ህንፃ በቀረበለት ኮንትራት መሰረት ልዩ ልዩ ስዕሎችን ለኤንባሲው እያቀረበ ነው
#ዶክተር ናትናኤል በኤንባሲው ለሚደረጉት ካርኒቫሎችና የእራት ግብዣዎች ቆጃንጆ ኮረዳዎችን ከነጮቹ እቅፍ ይከታል
ሁሉም በተለያየ መንገድ ለአንድ አላማ ቆመዋል...
በልብሶቻቸው ላይ በተገጠሙት ካሜራዎችና ድምፀ መቅርፆች የኤንባሲውን ቅጥር ከእግር እስከ እራሱ እየቀረፁ ከመሬቱ ስር ላለው ቢንያም ያደርሱታል ይህ እቅድ ከበፊቶቹ ሚለየው ለመጨረሻው ተግባር ኤልያስ ብቻ አይደለም ወደ ቦታው የሚያመራው በዚ እቅድ ስድስቱም ሰዎች ከቦታው መገኘት አለባቸው
ጉጉታቸውን እንባቸውን ናፍቆታቸውን አዲሱ ሚጀምሩት ህየይወታቸውን ሁሉም በዚ እቅድ ላይ ተሳትፈው ሊያገባድዱት ወስነዋል በናጋዚ ሰማይ ምንም ከሞት ጋ ቢፋጠጡ ለዚ አላማ እንደተመረጡ አውቀዋል
#ስምኦን ዙሪያ ገባውን ባስጌጣቸው ስዕሎች አዲሱን ህንፃ በሙሉ ሞልተውታል በእያንዳንዱ ስዕሎች ላይ የተገጠሙት ካሜራዎች ሁሉንም እንቅስቃሴዎች ወደ መሬቱ ስር ያስተላልፋሉ
#ፊያሜታ የመግደሉም የማዳኑም ነገር በእጇ ገብቷል መርዢ የሚል ትዕዛዝ ካገኘች የኤንባሲውን በሊታዎች ጠቅልላ ታስተኛቸዋለች
#ደራሲው ዮቶር ገቢ ወጪውን ይከታተላል በሚሰራቸው ማሽኖች ላይ በሚገጥማቸው ድምፀ መቅርፆች የኤንባሲውን ጩኸቶች አስከ ትናንሽ ሹክሹክታዎች ወደ መሬቱ ስር ያስተላልፋል
#ናትናኤል በውቦቹ ሴቶች ታግዞ ቡዙ ነገሮችን ይሰበስባል
ዛሬም ለአዲሱ ህንፃ ምርቃት በሚል ብዙ ታዳሚዎቸች ከቦታው ተሰባስበዋል
ሻርማይኮችም ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል .....
ሰአሊው አስውቦ ለሳላቸው ስዕሎች ከኤንባሲው ሰዎች ትልቅ አድናቆት ተችሮታል
ወጥ ቤቷ ፊያሜታም ለዛሬው ምሽት የሚቀርበውን የምግብ አይነት አዘጋጅታ የቀደሙ ወጥ በረቶቹን አስንቃ ለዛሬው ማታ ጉድ ጉድ ትላለች
ዮቶርም በቅልጥፍናው ከብዙ የኤንባሲዎቹ ሰዎች ጋ ተግባብቷል
ዶክተሩም በሚያመጣቸው ውብ ሴቶች ምክንያት ከነጮቹ ጋ ወዳጅነት ፈጥሯል
ዛሬ ሁሉንም ነገር አከናውነው ወደ አለማቸው መመለስ አለባቸው..
ከመሬቱ ስር ያሉት ሰዎች የእኩለ ሌሊቱን ሰአት እየጠበቁ ይገኛሉ አይኖቻቸውን መረጃ ከሚያሳዩቸው እስክሪኖች ላይ አልነቀሉም
ከኤንባሲው ካሉት ሰዎች የሚላኩላቸውን ምስሎች ትኩረት ሰተው እየተከታተሉ ነው
አባ ተስፋ ስላሴም ናጋዚ የቀማቸውን አስኬማቸውን ዛሬም አልጫኑትም ከመሬቱ ስር ያለው ሙቀት ዛሬ በርትቷል በአስኬማ ይሸፈን የነበረው ውብ ፀጉራቸውን እየነኩ ላባቸውን ይጠርጉታል ሁሉም እንዳለቀ እሳቸው አስኬማቸውን መልሰው ለመድፋት ወስነዋል
አባ ከገዳሙ በደረሳቸው መረጃ መሰረት Mr isaac የተባለውን ነጭ በትኩረት ከእስክሪኖቹ ላይ እየፈለጉ ፎቶውን እያስተያዩት ነው......

                  ይቀጥላል..
      ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
. . .
ማነሽ ባለሳምንት

ሳቅ የጥዋ ማህበር ጠባይ አለው። በአንዱ ላይ ለአስራአንድ ተሆኖ ይሳቃል። ሌላው ይቀጥላል የጥዋ ማህበሩን ለማውጣት። ሲል ሲል ዙሩ እኔ ጋ ደረሰ።

የፌዙ መነሻ ቤቴ ሰርሳሪ መግባቱ ነው። ጫት ቃሚው ሁሉ "እኔ የሰማሁት" እያለ አወራ፤ አውካካ። ወሬው ስብጥርጥር ነው። ለያዥ ለገናዥ ያስቸገረ። እኔ እንዲመች አድርጌ ላቅርብላችሁ። (ለዚህ መምህርነቴ ጠቅሞኛል።)

አንድ
-------
መካሻ አጎት ቤት ሰርሳሪ ገባ። የሰረሰረበትን ድጅኖ እንደያዘ የቤቱን ዙሪያ ገባ ቢመለከት ምንም የረባ እቃ አጣ። እቃ ከጠፋ በልቼ ልሂድ ብሎ ሌማቱን ቢከፍት ባዶ ሆኖ አገኘው። ፓስታ ቀቅሎ ይሆናል ብሎ ድስቱን ቢከፍተው ሸረሪት አድርቶበት አየ። በዚህም፦
ሀ - በሀዘኔታ አለቀሰ ያሉ አሉ፤
ለ - ቀስቅሶ ይሄን ድጅኖ ሸጠህ ብላ ብሎ ሰጠው ያሉ አሉ።
ሐ - አምስት ብር ቀዳዳ ሰሀን ላይ አስቀምጦለት ወጣ ያሉ አሉ።

ሁለት
--------
መካሻ አጎት ቤት ሰርሳሪ ገባ። ሌሊቱን ሲለፋ አድሮ ሊነጋጋ ሲል ቀድዶ ገባ። በድካም እያለከለከ ቢመለከት እሱ ከቀደደው የማይተናነስ ሌላ ነባር ቀዳዳ በትይዩ ግድግዳ ላይ ተመለከተ። በልፋቱ ተናደደ። ይበልጥ ያናደደው ደግሞ ቤቱ ውስጥ ምንም ባለመኖሩ ነበር። ስለዚህ የመካሻን አጎት ቀስቅሶ፦
ሀ - መከረው ያሉ አሉ፤
ለ - ሰደበው ያሉ አሉ፤
ሐ - ገረፈው ያሉ አሉ።

በዚች ቀልድ ጥሎሽነት ከወሪሳዎች ጋር እንዳልለይ ሆኜ ተቀላቀልኩ። አንድ አካል አንድ አምሳል ሆንኩ። በብላ ተባላ ዘመን የብላ ተባላ ሠፈር ሠፈርተኛ ሆንኩ። . . .
---------------------
ዓለማየሁ ገላጋይ
ወሪሳ
ገፅ 21 - 22
@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (👋ገብርዬ)
በ +251934039346
ወይም @cher46 ላይ ፎቶ በመላክ ሦዕል ማሳል ይቻላል።

ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ ነው።
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ

@seiloch
@seiloch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

 ክፍል - ፱

ከመሬቱ ስር አትኩሮቱ ቀጥሏል ሁሉም ትኩረታቸው ከአባ እጅ ላይ ወደ ሚገኘው ፎቶ ላይ ሆኑአል
ከኤንባሲው ካሉት የሻርማይክ አባላት የሚላከት ምሰሎች አንዱም ከፎቶው ጋ ሊመሳሰል አልቻለም
ናትናኤል ያሰፈራቸው ሴቶች ዛሬ ይበልጥ ውበት ጨምረዋል ቀለበት ያሰረውንም አፈፍ እያደረጉ በውበት ማርከዋል
ጭፈራው ሙዚቃው ደስታው ቀጥሏል
ለሻርማይኮች ግን ገና ነው እንደተለመደው ከድል ሲመለሱ በእሳቱ ዙሪያ ሰብሰብ ብለው በአባ ጊቢ ካሉት ላሞች ትኩስ ወተት እየተጎነጩ አባ ሸክ አርገው በሚያርዱላቸው ጠቦቶች ጥብስ እየተዝናኑ ማክበር ናፍቀዋል
ከእግር እስከ እራሱ የኤንባሲውን ቅጥር ቢያካልሉትም ፎቶ ላይ ያለው ሰው በአካል አልተገኘም
ፊያሜታ ሰአቱአን እየጠበቀች ነው በጀርመኖች ስርአት ከምግብ በሗላ ወይን የመብላት ፕሮግራም ይዘጋጃል እሷም የወይኑን ሰአት በጉጉት እየጠበቀች ነው
በእያንዳንዱ የወይን ፍሬ ላይ በጥንቃቄ በስሪንጅ ወግታ ባስገባችው አድካሚ እፅ ለእቅዱ ትልቁን ሚና ተጫውታለች
ከመሬቱ ስር ያሉት አባላት አይኖቻቸውን ነቅለዋል ከኤንባሲው ያልተገኙ እንግዶች እንዳሉ ስለተረዱ አባ እና ኤልያስ ወደ ኤንባሲው ለመሄድ ተነስተዋል ቢንያም እነሱ እዛ እስኪደርሱ አዲስ መረጃ ካለ ለእነሱ እንዲያሳውቅ ከመሬቱ ስር ከእስክሪኖቹ ጋ ተፋጡአል
መንፈቀ ሌሊቱ እየተጋመሰ ነው ጨዋታው ሞቅታው እየጨመረ ነው የደከመው ከሳበችው አንዱአን እቅፍ አድርጎ ወደ መጋለቢያው ይወስዳታል
በድካም ላይ ሌላ ድካም........
አሁን ያልመጡትን እንግዶች ለመቀበል ተዘጋጅተዋል
አባ እና ኤልያስም ወደ ኤንባሲው በተከፈተላቸው በሮች ገብተዋል
መንፈቀ ሌሊት አለፈ አዳዲስ ፊቶች በኤንባሲው በዝተዋል ከደቂቃዎች በፊት ሁለት ሰዎች በክብር ሞቅ ባለ ጭብጨባ ወደ ኤንባሲው የክብር ቦታ ገብተዋል እነሱን ተከትለውም በዛ ያሉ ታጣቂ ጋርዶች ከኤንባሲው ዘልቀዋል
የሙዚቃው ድምፅ ቀነስ እያለ መጣ...
ወደ መድረኩ አንዲት ሴት ወጣች ማይካሮፎኑን መታ መታ አደረገች
ሰላም እንዴት አመሻችሁ    የተጋተችው መጠጥ አድክሟታል
ወደ ዚህ መድረክ አንድ ትልቅ እንግዳ ልጋብዝ እወዳለሁ ለሀገራቸን ትልቅ ስጦታ ይዘውላት ለሚሄዱት Mr isaac
ኤንባሲው በሰከሩ ነጮች እና በጥቂት ሀበሾች ጭብጨባ ተሞላ
ወደ መድረኩ Mr isaac የተባለው ሰው ወጣ በእጆቹ በቀይ ጨርቅ የተጠቀለለ ነገር ይዟል
ሻርማይኮች እርስ በእርሰ ተያዩ
እኔ እንኳን ብዙ ላወራ አይደለም እየተዝናናችሁ ስለሆነ ብዙም አልቆይም ድምፁን ጠረግ እያደረገ
ዛሬ አንድ ትልቅ ነገር ለሀገራችን ጀርመን ይዘን ልንሄድ ስለሆነ መርቃችሁን እንድትሸኙን ነው
ቀዩን ጨረቅ እየፈታ.....
በጣም የቆየ የሚመስለ የነተበ ብራና ከቀደ ጨርቁ አወጣ ቀጠለ...
ሀገራችን ካለችበት የህክምና ብቃት ወደ ተሻለ ደረጃና በመድሀኒቱ ቅመማ ከአለም ቁንጮ የሚያደርገንን ጥበብ
ዛሬ ከደጎቹ ከልዩዎቹ ኢትዮጵያውያን ለኛ በስጦታ መልክ ስለተሰጠን ደስታዬን ለመግለፅ ስለወደድኩና ለማመስገን ስለፈለኩ ነው
አመሰግናለሁ ....
አባ ዘለው ቢያንቁት ደስታቸው ነበር ሰርቆ እና ገዳም በርብሮ አስበርብሮ ያገኘውን ጥበብ በስጦታ አስመስሎ ሲያወራ ተበሳጭተዋል
ደጎችና ልዩ የሆኑት ኢትዮጵያውያንን ደሞ በሱ አፍ በመጥራቱ ጭራሽ ንዴታቸው ገነፈላበቸው
ሰአቱ መድረሱን ስላወቁ ለመረጋጋት ሞከሩ
የወይኑ ሰአት የደረሰ ይመስላል ፊያሜታ እና አጋር ሰራተኞች ለእራቱ ተብሎ በተዘጋጀላቸው ልብሶች ተውበዋል
ከወጥ ቤት እየወጡ ወይኖቹን ለእንግዶቹ ማዘገን ጀመሩ
ውቧ ፊያሜታ ለምሽቱ የታደሙትን ሴቶች ታስነንቅ ጀመር ወይኑን ከውብ ፈገግታዋ ጋ እየሰጠች ጋርዶቹን ጭምር አዘገነች
Mr isaac ከሚስቱ እጅ እየተወረወረለት ወይኑን ወደ አፉ ያስገባ ጀመር
ከሻርማይክ አባላት ውጪ አብዛኛው ሰው ወይኑን እያጣጣመ ነው.....

              ሊፈፀም ሰአቱ ደርሷል
       ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
የማለዳቹ ይቺን ስሙማ

''በሸርተቴ ሞራል ሰበራ''

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የተገኘ ፁኹፍ ነዉ።
ፀኀፊ :- ኤፍሬም እንዳለ
የፁኹፉ ድምፅ :- ሚኪያስ ልየዉ @Mykeyliyew

(በንባቡ ላይ ስለተጠቀሰዉ የፀኀፊዉ የስም ስህተት በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለኹ ፀኀፊዉ ''ኤፍሬም ስዩም'' ሳይኾን ''ኤፍሬም እንዳለ'' ነው)።

@Wegoch
@wegoch
@wegoch
የታጋቹ ማስታወሻ
(በእውቀቱ ስዩም)
ከፀሀይ በታች አሮጌ ነገር የለም ፤ ፀሃይ ራሷ በየሰኮንዱ ትታደሳለች፤
ከእንቅልፌ ተነሳሁ፤ ተንጠራራሁና አይኔን ባይበሉባየ ጠራርጌ ከእምብርቴ በታች ያለውን ቃኘሁት፤ አጅሬ ከኔ በፊት ቀድሞኝ ተነስቱዋል ፤ የዛሬው ደግሞ የተለየ ነው፤ እስክንድር ነጋ ንግግር ባደረገ ቁጥር ባንዲራ ይዞ ከጀርባ እሚቆመውን ሰውየ ራሱ እንዲህ አይቆምም ! ጠበቆ ጠብቆ ምንም የተዘጋጀለት ነገር እንደለሌለ ቁርጡን ሲያውቅ ተኛ! ምስኪን!
ያልጋ መውረጃ የለህም ? የሚል አንባቢ አይጠፋም!
ሲጀመር አልጋ ራሱ የለኝም ፤ በርግጥ እንደ ጎማ የሚነፋ ፍራሽ አለኝ ፤ የገዛሁት ሰሞን አንዴ ከተነፋ እስከ ሌሊት ሙሉ ያገለግል ነበር፤ አሁን ቀሳ ከወጣሁ በሗላ ግን ወፈርኩ፤” ወፈርኩ” የሚለው ቃል አነሰ ! ስጋየ ገነፈለ ብል ይሻላል ፤ ሁለት የቁም መስታውቶች ገጣጥሜ ካልሆነ በቀር ሙሉ ሰውነቴን ለማየት እያዳገተኝ ነው፤ ለሶስት ሰአት ያክል ከተኛሁበት ተንፍሶ ምንጣፍ ይሆናል ፤ እንደፈረደብኝ ተነስቼ እንደገና እነፋለሁ፤
ቁርስ መስራት ይጠበቅብኛል? ባለፈው “ አንድ ብርጭቆ ሩዝ በሁለት ብርጭቆ ውሃ ለሃያ ደቂቃ ከቀቀሉት ሁለት ብርጭቆ ሩዝ ያገኛሉ “ የሚል አነበብኩ፤ እንደዛ ከሆነ ለምን በደንብ አላባዛውም ብየ አንድ ብርጭቆ ሩዝ ባራት ብርጭቆ ውሃ ቀቀልኩ፤ ከሃያ ደቂቃ በሗላ ሩዝ ጣል ጣል ያለበት ሙቅ ውሃ ጠጣሁ፤
አንድ ቀን ደግሞ እንቁላል ጠበስኩ፤ከዛ ወደ አፍንጫየ አቅርቤ ባሸተው ምንም መአዛ የለውም፤ ትንሽ ቅመም ነሰነስኩበት፤ ይህም ሆኖ አፍንጫየ ላይ አቅርቤ ስምገው ምንም የለም ፤ ወድያው ሼፍ ዮሀንስ ጋ ደውየ የጠቆመኝ ቅመም ችግር እንዳለበት ነገርኩት ፤ “ ርግጠኛ ነኝ ፌስ ማስክህን ሳታወልቅ ነው ያሸተትከው? “ አለኝ፤ ውነቱን ነው ፤ ፌስማስኬን አድርጌ ከመዋል ማደሬ የተነሳ እንደ ፊት ቡግር ሁሉ ማውጣት ጀምሯል፤
ምግብን ሼፍ ዮሀንስ ይስራት! ሲወርድ ሲወራረድ የመጣው ምግብ ስለደበረው እማይሞክረው አዲስ ነገር የለም፤ ባለፈው ሰይፉ ሾው ላይ ከሞሪንጋ ዱቄት ምን የመሰለ ላዛኛ ሰርቶ አስደምሞኛል፤ ይሄ ልጅ በዚህ አይነት ምርምሩን ከቀጠለ ሳያስበው ክትባቱን ሁሉ ሊያገኘው ይችላል፤
ምግብ ሲነሳ የሆነ ነገር ትዝ አለኝ፤ ይዲዲያ የሚባል ዝነኛ ነቢይ ትዝ አላችሁ ? ሚያዝያ ላይ ኮሮና ይጠፋል ብሎ ተንቢዮ ነበር፤ ከዛ ወረርሽኙ እየባሰበት ሲመጣ ሚያዝያ እንዲራዘምለት ጌታን በፀሎት ጠየቀ ፤ በቀደም ቃለመጠይቅ ላይ ምን ሲል ሰማሁት “ መፅሀፍ ቅዱስን በጣም ከመውደዴ የተነሳ አንዱን ገፅ ቀድጄ በልቼ አውቃለሁ” ፤ እምደንቅ ነው ባክህ! እኔ በዚህ ምስክርነትህ ላይ የታየኝ ነገር ቢኖር ለመፅሀፍ ቅዱስ ያለህን ፍቅር ሳይሆን ለምግብ ያለህን ፍቅር ነው፤ ኪሎህ ራሱ ይሄንን ይመሰክራል፤ ለማንኛውም ክንዳችሁ ላይ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅስ የተነቀሳችሁ ሰዎች ይሄን ሰውየ ተጠንቀቁት !
ለነገሩ ምግብ ላይ እኔም የዋዛ አደለሁም፤ ይሄው ፤ ገና ከምኝታየ ከመነሳቴ የፍሪጁን በር ከፍቼ ቆሚያለሁ ፤ የሚሳዝን አጭሬ ከተፍ አለልኝ!
አንድ ስሃን ሩዝ
ሁለት ሱካር ድንች
ፍሪጄን የሞላው
ይሄን ሁሉ ሲሳይ፤ ከማን ጋራ ልብላው? ☹️

@wegoch
@wegoch
@paappii
ለምሽታቹ ይቺን ስሙማ

''በሸርተቴ ሞራል ሰበራ''
ክፍል ፪

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የተገኘ ፁኹፍ ነዉ
ፀኀፊ :- ኤፍሬም እንዳለ
የፁኹፉ ድምፅ :- ሚኪያስ ልየዉ @Mykeyliyew


@Wegoch
@wegoch
@wegoch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

  ክፍል - ፲

የወይኑ ፕሮግራም ያለቀ ይመስላል ሁሉም አጣጥሞ ጨረሰ ከብርጭቆአቸው የቀረችውን አልኮል ለወይኑ ማወራረጃ እንድትሆን እስከ መጨረሻው ጭላጭ ሁሉም ይጨልጥ ጀመር
ሻርማይኮች ከወይኑ ፍሬ ያልቀመሰ እንደማይኖር አምነዋል ከወጥ ቤት እስከ ተፈላጊው ነጭ እና ጋርዶቹ ወይኑን ቀምሰዋል  በቀዩ ጨርቅ የተጠቀለለውንም መጽሀፍ ከመሬት የሚወድቅበትን ሰአት እየጠበቁ ነው እንቅስቃሴዎች በረድ አሉ ጭፈራ የለሌለው ሙዚቃ ብቻውን በእኩለ ለሊቱ ያስተጋባል
ምድነው....
 አብዛኛው ሰው እራሱን እየያዘ ብቻውን ያወራ ጀመር 
ሰአቱ ደርሷል.....
አብዛኛው ታዳሚ ጭንቅላቱን እየያዘ ከመሬት ይወድቅ ጀመር ግማሹ በእንብርክኩ እየወደቀ ተንጋሎ ከመሬት ይወድቃል ሻርማይኮች እርስ በእርስ ተያዩ ኢላማቸው ግቡን እየመታ ነው
ዛሬ በዚች ምሽት የብዙ ሚሊዮኖች የመዳን ተስፋ መልስ ያገኛል
ኢትዮጵያውን ምን ያህል ላሰቡበትና ላቀዱት አላማ ጥበባቸውን ማስተዋላቸውን አዋቂነታቸውን እንደሚጠቀሙ በሰባቱ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አሳይተዋል ሻርማይኮች ከናጋዚ ሞት ተተፍተው ዛሬ ለብዙ መድሀኒት ፈላጊዎች መድሀኒቱን ለመስጠት 11ኛው ሰአት ላይ ቆመዋል
ከኛ ለቃቅመው ዋሻዎቻችን ገዳማትና አድባራቶቻችን በርብረው በሚለቅሙአቸው የጥበብ መፅሀፍት ዛሬ ካሉበት ደረጃ ደርሰዋል በመስረቅ ከኛ በመንጠቅ ከብረዋል ተዝቆ የማያልቅ የሀብት ማማ ላይ ተቀምጠዋል ማስተዋል ጥበብ እውቀት ብልሀት ሁሉን ከደብሮቻችንና ከገዳማቶቻችን ሰርቀው ወስደውብናል መጪውን ሗላውን አሁኑን ጭምር በእኛ አውቀዋል
ዛሬም ከኛ በወሰዱት መፅሀፍ አለምን አዲስ መድሀኒት በትላልቆቹ ላብራቶሪዎቻችን ሰርታናል ብለው ተራ ትርክቶችን ይቀደዱልናል
መፅሀፉን ገልጠው መርምረው እኛ አገኘነው እያሉ ያታልሉናል
ሁሉም ግን በኛ ነው..  ዛሬ አንድ ውሸት መልስ ያገኛል
ፊያሜታና ናትናኤል ከmr issac አይን ላይ ናቸው
ታዳሚው እየተልፈሰፈሰ ከመሬት ተዘርሯል መሬቱ ባማሩ ቆንጆዎች በነጫጭ ሰዎች ከእጆቻቸው ባመለጡት ጠርሙሶች ተሞልተዋል Mr isaac ሰአቱን ጠብቁ ከመሬቱ ተንጋለለ ቀዩ ጨርቅም የወይኑን ፍሬ የወሰደ ይመስል ከመሬት ተዘረጋ
ከወይኑ የገባው እፅ እንቅስቃሴያችንን አደንዝዞ እፁን ከተጠቀሙ  በሗላ ማስተዋላቸውን ያስታል ሁሉም ከሰመመኑ ሲነቃ ምን እንደተከናወነ አያስታውስም
አሁን ከኤንባሲው ቅጥር ከሻርማይኮች ውጪ ቆሞ ሚተነፍስ የለም
ፊያሜታ በፍጥነት ወደ ተንጋለለው ሰውዬ አመራች ብራናውን ለቅመ አድርጋ ወደ አባ አመራች አባ እንባ ቀረሽ ደስታ ከፊታቸው ታየ ጥርሶቻቸውን ከፍተው እጆቻቸውን ዘርግተው ተቀበሏት ሻርማይኮች ሁሉም አንድ ቦታ ተመለከቱ ወደ ተስፋይቱ ወደ ምድረ ገነቲቱ ወደ መፃኢዋ ኢትዮጵያ በሀሳብ ተመሙ
በዚ ብራና ስንት ትውልድ እንደ ሚድን ተመለከቱ ስድስቱም ሰዎች አንድ ላይ ተቃቀፉ ከናጋዚ የሞት ክልል አምልጠው ዛሬ ላይ ሞት ለከበባቸው ሰዎች ሞትን ሲያባርሩ ተመለከቱ ሀዘን ደስታ ናፍቆት ጀብደኝነት ከስሜቶቻቸው መካከል ናቸው
እንዳትንቀሳቀስ...
መተቃቀፉ ሳያልቅ የአንድ ሰው ድምፅ ተሰማ ሻርማይኮች ምን እየሆነ እንደሆነ ማመን አልቻሉም
የያዝከውን ቁጭ አድርገው ወደ አባ እያየ መሳሪያውን ከፊታቸው ደቀነው
ፋታ ሳይሰጣቸው የመጀመሪያውን ቃታ ሳበው አባ ከወደ ደረታቸው ደም ተፈጠረቀ ልክ በወይኑ እንደ ወደቁት እሳቸውም በጥይት ተመተው ወደቁ ፊያሜታ ጩኸቱአን ለቀቀች ኤልያስ ለመጠባበቂያ የያዘውን መሳሪያ አውጥቶ ወደ ተኳሹ ቃታውን ሳበ ወደ ትከሻው ጨረፈው
በፍጥነት መዘናጋቱን ያዩት ሻርማይኮች ምግብ ተደርድሮበት የነበረውን ጠረጴዛ በፊቱ ደፍተው ተከተቱበት
ኤልያስ አባን ከትከሻቸው አቅፎ ከጎኑ ወደ ነበረ ዛፍ አስተኛቸው
ከኤልያስ ጥይት የተረፈው ጋርድ የአቅሙን ተነስቶ የጥይት ዶፍ ወደ ጠረጴዛው ያርከፈክፍ ጀመር
ምድነው ከየት ነው የመጣው ፊያሜታ በአባ መመታት ደንግጣ እንባዋን ታዘራለች
ኤልያስ ሸሚዙን ተልትሎ ለአባ አጥብቆ አሰረላቸው ከደረታቸው የሚወርደውን ደም ሸሚዙ ሊያስቆመው አልቻለም
እጁን ወደ አንገታቸው ሰዶ ከተዘቀዘቁበት ቀና አደረጋቸው አይዞት አባቴ ይጠንክሩ ትንሽ ነው የቀረው ትንሽ
አባ አይኖቻቸው ደም ለብሰዋል የግንባራቸው ደም ስሮች ተገታትረዋል ከአይናቸው የምቶርደው እንባ እየደከሙ እንደመጡ ለኤልያስ ፍንጭ ሰጡት እጆቹን ቀስ አድርጎ ወደ ታች አስተኛቸው
ተኳሹ ተኩሱን አላቆመም ጠረጴዛውን ቦተራርፎታል በቀዳዳዎቹ ትይዩ እነ ፊያሜታ ላይ ያነጣጥር ጀመር  ሁሉም ፈርተዋል ተስፋቸው በአንድ ተልካሻ ነጭ ሲናድ ታያቸው ናትናኤል ለቢንያም መልእክት ይሰጣል ከቢንያም ዘንድ ምንም መልስ የለም
ከተቦተራረፈው ጠረጴዛ አልፋ የመጣች ጥይት ከዮቶር ትከሻ ተሰነቀረች ደሙ ቁሉቁል ከትከሻው ሲወርድ ተመለከቱ ጭንቀት ፍርሀት ነገሰ
ከናጋዚ በሗላ ዛሬም መልአከ ሞት ከቧቸዋል
ፊያሜታ ብራናውን አጥብቃዋለች ከዚ ውጥረት መውጫ የሚሆን ጥበብ ከመፅሀፉ እንዲኖር ተመኘች
የጥይቱ ድምፅ በረደ ዶፉ እስከ ጭራሹ አባራ
 አባ ... ቢንያም ከኤንባሲው ደርሶ ተኳሹን ግንባሩን ብሎ ጣለው
ፀሎቷ የሰመረ መሰላት ናትናኤል ወንድሙን ደግፎ ይዞት ተነሳ
7ቱ ሰዎች ወደ ከዛፉ ስር ተሰበሰቡ አባ ወደ ሞት እየገቡ ነው የናጋዚ የሞት መልአክ ዛሬ አባን አፈፍ አደረጋቸው እያጣጣሩ ከወደ ደረት ኪሳቸው አንድ ብራና አወጡ ይሄን ወረቀት ያዙ
ኤልያስ እንባዎቹ አመለጡት ከአባ ደረት ላይ ተንጠባጠቡ ፊያሜታ አባቴ ሳግ ነገሰባት
 አባ ቀጠሉ....
ወረቀቱ ካርታ ነው ስታቃጥሉት ባዶው ወረቀት በቁጥር የተሞላ መሀሉ ላይ በልዩ ጥበብ የተሳለ ካርታ  ታገኛላችሁ በካርታው ታግዛችሁ ይሄን ብራና ወስዳችሁ  ጥቅም ላይ አውሉት
ትልቁን የመድሀኒት ማምረቻ ተቋም በዚ ካርታ ታግዛችሁ ታገኙታላችሁ ብዙ የባህል ሀኪሞቻችንና ጠቢባን በዛ ከትመዋል ሻርማይክ ብላችሁ ግቡ ፀሀዮች ይቀበሉዋቹሀል ሻርማይክ ማለት ትርጉሙ ፀሀይ ማለት ነው ወደ ሻርማይክ ቤት ግቡ ለኢትዮጵያ እንደ ጀንበሯ አብሩ
               ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ
                  ኀበ እግዚአብሔር
                          አሜን

                       ተፈፀመ
        ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
★ቂም የሸፈነው እውነት★★
                  (ሜሪ ፈለቀ)

“መለያየት እፈልጋለሁ፡፡ ፍታኝ?” አልኩት በመኪናው መስኮት አሻግሬ ዓይኖቹን እየሸሸሁ፡፡

“እሺ!!” ነበር መልሱ:: ቢያንስ ‘ለምን?’ ብሎ እንዴት አይጠይቀኝም?

“መች ነው እንዲሆን የምትፈልጊው? አሁን? ነገ? ከሳምንት በኋላ? መቼ?” ቀለል አድርጎ ቀጠለ፡፡ ቀጥዬ የምለው ጠፋኝ፡፡ ለራሴ ምክንያት መስጠት እፈልጋለሁ፡፡ ተናዶ እንዲናገረኝ እሱ ላይ እንከን ማግኘት አጥብቄ እፈልጋለሁ፡፡’ፈታችው’ ከመባል ሌላ ቅጥያ ተጨምሮበት ‘ስላናደዳት ፈታችው’፣ ‘ስለመታት ፈታችው’……… ብቻ ምክንያቱ ከሱ ቢመጣ ደስ ይለኛል፡፡

“ካለቀልን ዛሬም ብንፋታ ደስ ይለኛል፡፡”

“ከዛሬ በኋላ ተፋተናል፡፡ የግድ በህግ መፋታት የለብንም፡፡ እኔን መፍታት አይደል የፈለግሽው? ስለወደድኩሽ እንጂ ማንም ስለፈረመ  እና ምስክር ስለተጠራ አላገባሁሽም፡፡” ብሎኝ ከመኪናው ወረደ እና የኔን በር ከፈተልኝ፡፡ ቤታችን ደጅ ደርሰን ነበር፡፡ ተናደድኩ፡፡

“የንብረት ክፍፍሉ……..” አላስጨረሰኝም፡፡

“የትኛውን ንብረት ነው የምትፈልጊው?” የአጥሩን በር ከፍቶ በእጁ እንድገባ አሳየኝ፡፡

“ድርሻዬን::”

“ህምምምም…….. ቅር ካላለሽ ትንሿን መኪና ልውሰዳት ሌላውን ንብረት አልፈልገውም፡፡ ከዛሬ በኋላ ባልሽ አይደለሁም፡፡ ምንም ንብረትም የለኝም፡፡” ብሎኝ ‘ትንሿ’ ያላት መኪናው ውስጥ ገብቶ ተመልሶ ሄደ፡፡

ምን እንደምፈልግ ግራ ገባኝ፡፡ ካሳሁንን ሳላገባው  በፊት ነበር የምፈታው ቀን የሚናፍቀኝ፡፡ ሳላገባው ፈትቼዋለሁ፡፡ እሱ ያገባኝ የመሰለው ቀን እኔ አግብቼም ፈትቼዋለሁ፡፡ታዲያ ለምን አገባሁት? እሱን አላገባሁትም፡፡ ገንዘቡን እንጂ። ወንዶች ‘ሴት ልጅ ገንዘብ ያለው ወንድ ትወዳለች’ ሲሉ ሳቄ ያመልጠኛል፡፡ ወይ ሰውየው ማርኳታል ወይ ገንዘቡ ማርኳታል፡፡ ለአንዳቸው ቅድሚያ ትሰጣለች፡፡ለገንዘቡ ብላ ከሆነ ገንዘቡን እንጂ እሱን አትወደውም። ገንዘቡ እስካለ ወይም የምትፈልገውን እስክታገኝ ድረስ አለች፡፡ እነሱ ግን ራሳቸውን ሳይሆን ገንዘባቸውን ያቀርቡላታል፡፡ ምክንያቱም የቁስን ያህል ራሳቸውን አያምኑትም፡፡ ስለዚህ ከቁሳቸው ይልቅ ራሳቸውን ተወዳጅ አድርገው ማቅረብ ሲሳናቸው ለገንዘቤ ብላ ነው የወደደችኝ ይላሉ እንጂ ገንዘቤን ነው የወደደችው አይሉም፡፡ ሰውየውን ከወደደችው ለገንዘቡ ብላ፣ ለቁመናው ብላ፣ ለወዙ ብላ…. የሚሉት ቀልድ አይጥመኝም፡፡ በቃ ሰውየውን ነው የወደደችው፡፡

የዛን ቀን ምሽት አልመጣም፡፡ ጠበቅኩት፡፡ እውነቱን እንደሆነ ገባኝ፡፡ ካሳሁን ፈቶኛል፡፡ ሁለተኛው ቀን መሸ ።አልመጣም፡፡ አልደወለም፡፡ ሶስተኛ ቀን ሆነ……… አራተኛ ቀን መጣ… … አስር ቀን ሞላው። አልመጣምም። አልደወለምም። የገባኝ ግን ቢመጣ ደስ እንደሚለኝ ነው፡፡እሱን መፍታት ያስደስተኛል ብዬ ያሰብኩትን ያህል አልነበረም የደስታዬ መጠን፡፡

“አልወደውም፡፡ ከሀብቱ እንጂ ከእርሱ ጉዳይ የለኝም።” ለራሴ ብቻዬን አነበነብኩ። ስልኬን እልፍ ጊዜ ልደውልለት አነሳሁ። እልፍ ጊዜ ተውኩት፡፡ በአስራአንደኛው ቀን ስልኬ ጠራ። እሱ ነበረ። ለምን ደስ አለኝ? አብሬው መኖር የማልፈልገው ሰው ድምፁን መስማቴ እንዴት አስደሰተኝ?

“ደህና አደርሽ ሰብሊ? …… ላግኝሽ?”

“እሺ:: የት እንገናኝ?”

“ስራ ቦታ:: አራት ሰዓት ላይ መጥቼ ወስድሻለሁ፡፡”

ስራ የመግባት ፍላጎት አልነበረኝም፡፡ቁምሳጥኑን ከፍቼ ሊያቆነጀኝ ይችላል ብዬ ያሰብኩትን ሁሉ ልብስ ሞከርኩ፡፡ ላማልለው? ወይስ ከሱ በመለየቴ አለመከፋቴን ለማሳየት? ለራሴ የምሰጠው ምክንያት ባይኖረኝም በሱ ፊት ቆንጆ ሆኜ መታየት ፈለግኩኝ፡፡ አምስት ዓመት በትዳር አብሬው ስኖር ይሄ ግድ ሰጥቶኝ አያውቅም ነበር። በጥንቃቄ ስዋብ ብዙ ሰዓት ፈጅቼ ደረስኩ፡፡ ተጋብተን ብዙም ሳንቆይ ነበር ካሳሁን እቤት ከምትውዪ ብሎ ለንግድ ተስማሚ የሆነ ቦታ ላይ ትልቅ የሴቶች ፀጉር ቤት የከፈተልኝ ፡፡ በሩ ላይ ሲደርስ የት ይዞኝ ሊሄድ እንደሆነ እያሰብኩ ነበር፡፡ ብዙም ግድ ያልሰጠው ሰላምታ ሰጥቶኝ የመኪናውን በር ከፍቶ አስገባኝ፡፡ በሚከብድ ዝምታ መኪናውን መንዳት ጀመረ፡፡ ላገኘው እንዳልቸኮልኩ፡፡ ተጨነቅኩኝ፡፡

“የት ነው የምንሄደው?” አፌ ይሄን ይበል እንጂ የትም ብንሄድ ግድ አልነበረኝም፡፡

“የምንጨርሰው ጉዳይ አለን፡፡”

ባንክ ቤት በር ጋ ስንደርስ በሁለታችን ስም የነበረውን የባንክ አካውንት ሊያዛውርልኝ መሆኑን ነገረኝ፡፡ በተዘባረቀ ስሜት ውስጥ ሆኜ የሚጠበቅብኝን ፈፀምኩ፡፡ እድሜውን ሙሉ የሰራው ገንዘብ መሆኑን እያወቅኩ ‘አንተስ?’ ብዬ እንኳን አልጠየቅኩትም፡፡ ነገር ዓለሙ ዞረብኝ፡፡ ምንም ሳንነጋገር ፀጉር ቤቱ በር ጋር ደርሰን፡፡በር ሊከፍትልኝ ከመድረሱ ዘልዬ ከመኪናው ወረድኩ፡፡ በሌላ ትህትናው መቁሰል አልፈለኩም፡፡

“የት ነው ያለኸው?” አልኩት

“ቤት እስካገኝ ሆቴል ነው ያረፍኩት::”

“ለጊዜው እኮ እቤት መሆን ትችላህ::”

"በሚቀጥለው ሳምንት በአንዱ ቀን የቤት ባለቤትነቱን ስም አዛውርልሻለሁ:: ሰሞኑን ስራ ስለሚበዛብኝ የምችል አይመስለኝም፡፡” ብሎኝ መኪናው ውስጥ ገብቶ ሄደ፡፡ ራሴ የሚፈነዳ መሰለኝ፡፡የማብድ የማብድ መስሎ ተሰማኝ፡፡ ወደቤቴ ሄድኩ።

…… አልጨረስንም…

@wegoch
@wegoch
@paappii

#meri_feleke
#የሰኔ መቅሰፍቶች

     ክፍል - ፩

አመት ሊሞላው ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተዋል ቤተሰቡ እየተሰባሰበ ነው ዳር እስከ ዳር ያሉት የቤተሰቡ ሰዎች ከእናትና አባታቸው ቤት ከትመዋል
ቤተሰቡ ውስጥ ትልቅ ፍርሀት ነግሷል ቀን ቀንን እየወለደ ከጭንቆቹ ቀናት ሊደርሱ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተዋል
ቤተሰቡ መሰባሰብ ከጀመረ ሶስት ሳምንታት ተቆጥረዋል አንድ አንድ እያሉ ቤቱን ሞልተውታል
ይህን አመት ካለፉባቸው አመታቶች ውስጥ ልዩ ለማድረግ አስበዋል
ከአመት አመት የሚያጋጥማቸውን የክፉ እጣ ፈንታ ገጠመኝ ይህን አመት አንድ ላይ ለመጋፈጥ አስበዋል
ካለቁም አንድ ላይ ለማለቅ.....
በባለፈው አመት ከቤተሰቦቻቸው አባላት ስድስቱ በከፉው እጣ ፈንታ ተወስደዋል ጥቂት የሚባሉት ከሞት አምልጠዋል
ይህን አመት ደሞ ማን የእጣ ፈንታው ሰለባ እንደሚሆን አይታወቅም
ትናንሾቹ መልአክቶች ቤቱን ደመቅ አድርገውታል ቤተሰቡም ለህፃናቱ ፈርቷል
ምንም በማያውቁትና ባልገባቸው ነገር ተጠቂ እንዲሆኑ አልፈለጉም
ከአመት አመት ብቻ ትልቅ ዱብዳ ከቤተሰቡ ዘንድ ይወርዳል የትም ያለ የቤተሰቡ አካል በእኩል ሰአት በእኩል ቀን በእኩል ደቂቃ አንድ አይነት ነገር ያጋጥመዋል
በዚ አመት ክፉው እጣ ፈንታ ብዙ ሚደክም አይመስልም ሁሉም ቤተሰብ አንድ ቦታ ተሰብስቦለታል
እንዴት እና ለምን እንደሆነ ባይገባቸውም ከአያት ቅድም አያት እየተወራ የተነገራቸው ትልቅ የእርግማን መንፈስ በቤተሰቡ ላይ እንዳለ እና ከልጅ ልጅ እየተላለፈ ብዙ ሰው እንደሚጨርስ ተነግሮቸዋል ምንም ይሁን ምን ትልቅ ዱብዳ ቢሆንም እርግማኑ እያደጉ ያሉ ህፃናትን እንደማይነካ ስለተነገራቸው በትንሹም ቢሆን ተረጋግተዋል
አሁን ወልዶ የሳመ እሱም ተወልዶ ሲሳም ይሄ ነገር እንዳላጋጠመው ተነግሮታል
ካለፉት የቤተሰቡ አባላት በሌሎች ምክንያቶች የሞቱ ሰዎች ጥቂት ናቸው ይህ የእርግማን መንፈስ ቤተሰቡን ጨርሶታል
ይህ አመት አንድ ሆኖ የመጋፈጥ ነው ስንሰበሰብ ፈርቶን ቢቀር ብለው የተመኙት ብዙዎቹ ናቸው
ዛሬ ቤቱ በህፃናቱ ቡረቀና ሳቅ ተሞልቷል ትንሽ ከሀሳባቸው መልስ የሚያደርጋቸው የልጆቹ ሳቅና እከን አልባ ደስታ ነው
እኔ ነኝ ምሞተው እኔጋ ይሆን ያሁኑ አመት እጣ ሚደርሰው
ጭንቅላት በጣሽ ሀሳብ በፍርሀት ውስጥ ሆነው ያስባሉ
ሀሳባቸውን አንድ አርገው እነሱም ስለተሰባሰቡ ትንሽ ፍርሀታቸውን አቅሎላቸዋል
ምን አልባት ከመቶ ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ይሄ እጣ ለነሱ ብቻ የተፃፈ እንደሆነ አምነዋል
ለምን ......        ቤተሰቡን አንድ የሚያደርግ ጥያቄ
ሰኔ የነሱ የምጥ ወር ነው ሰአቱን ጊዜውን በማያቁበት አንዱ የሰኔ ቀን የእርግማኑ ቃል ይፈፀማል
ሁሌ ለዚ ቤተሰብ ሰኔ እና ሰኞ ይጋጠምበታል
በባለፈው አመት በዛው በሰኔ ወር በእያንዳንዱ ቤተሰብ በእኩል ሰአት በወረደው መብረቅ ስድስት ሰዎች ከቤተሰቡ ተነጥለዋል  
በዚ አመት ደሞ ምን ይወርድ ይሆን....
ግንቦት ሊያልቅ ጥቂት ቀኖች ቀርተዋል ከአያቶቻቸው በተሰጣቸው ምልክት እርግማኑ ሲቀርብ ከአመት አመት የግንቦት ወር ጨረቃ ቀይ ትለብሳለች
ቤተሰቡ ጨረቃን እየጠበቀ ነው ምልክቱ ሲታይ ሁሉም ወደ ፈተና ይገባል
ዛሬ የቤተሰቡ ተወዳጅ ልጆች ፊንሀስና ፊያሜታ ከመሸ ከቤተሰቡ ተቀላቅለዋል በባለፈው አመት ያጡት አባታቸውን ሀዘን ሳይጨርሱ ለዚ አመት የሰኔው መቅሰፍት ደሞ ተዘጋጅተዋል
ማንም የትም ቢሄድ በምድር ላይ እስካለ ድረስ ከዚ ፈተና አያመልጥም ብቸኛው ማምለጫ ከምድር ላይ መጥፋት ነው
ከቤቱ ሚቦርቁት ትናንሽ ህፃናት በትናንሽ እጆቻቸው ከእናቶቻቸው ጋር የሰሩትን እራት ከጠረጴዛው እያቀረቡ
ቤቱ በምግቡ መዓዛ ታውዷል ምን አልባት ይሄ መዓዛ ፍርሀቱን እንደሚቀንስ ተስፋ አድርገዋል.....

      ብላቴናው በእርግማን ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#የሰኔ መቅሰፍቶች

   ክፍል - ፪

እራቱ ተሰናድቷል ለቤተሰቡ አንድ ጠረጴዛ በይበቃም ህፃናቱ አንድ  ላይ ሊበሉ ተሰብስበዋል
ፀልዩ እሺ መጀመሪያ ፊያሜታ ዛሬ እነሱን በማግኘቷ በጣም ተደስታለች ከና ከመግባቷ ብዙ ነገር እያስረሱአት ነው
አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖል ሽምህ ይቀደስ መንትዝትህ ትምጥ  ፈቀድህ በሸማያት እንዲሁም...
ህፃናቱ በሚኮላተፉ አፋቸው ፀሎታቸውን አዳረሱ
ንፁህ ልብ ንፁህ ደስታ ምንም የማይሽረው ልዩ ፍቅር
ምን አለ እግዚአብሄ ለኚ ህፃናት ብሎ ከዚ መከራ ቢያወጣን እናት እና አባትን በዚ እርግማን ምን ያህል ማጣት እንደሚከብድ ፊያሜታ ታውቃለች
እራቱ አለቀ ....
ህፃናቱ እናትና አባታቸው ጋር ሄደው ተሸጉጠዋል ቤተሰቡ እነሱ ባይኖሩ ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ከባድ ነው
ቤተሰቡ በዝምታ ህፃናቱ በቡረቃ ሁለት አለም ሆናዋል
ምሽቱን ግን በሁሉም ዘንድ ዝምታ ነግሱአል ቤተሰቡ በመርገሙ ህፃናቱ ደሞ የቀኑ ውሏቸው አድክሟቸዋል
ምን ያህል ካለነሱ ይበልጥ ጭንቀቱ እንደሚገዝፍ ዛሬ በደንብ ተረዱ
አይ ህፃናት ትናንሽ ትልቅ አለሞች ናቸው የሀዘንን የጨለማን በፍቅር ያለመኖርን መንፈስ አባራው ሚጥሉ ሀዋርያት ናቸው....    ፊንሐስ በአፉ ያልጎመጉማል
አጎቴ ምን ይዘህልኝ ነው ግን የመጣኸው ኤፍራታ የፊንሀስና የፊያሜታ የአክስት ልጅ ናት ፊንሐስ ማለት ስለሚከብዳት ነው አጎቴ የምትለው
አሁን አይነገርም ጠዋት ለሁላችሁም ይሰጣችሁዋል እሺ ኤፊዬ ፊንሐስ አይኑን ከአይኗ ሳይነቅል
ሁሉም ልጆች እሺ አጎቴ ድምፃቸው የሆነ ልዩ ነገር ያመጣል ፍርሀት ይሰብራል
ምሽቱ ደሞ ነግቶ ይሄን ቀን ያሳልፈዋል የጭንቁም ቀን ይቀርባል
ይሄን ምሽት ሳይነጋ እየተኙ እየተነሱ ቢኖሩት ደስታቸው ነው ነግቶ አዲስ ቀን ሳያዩ ሰኔን በዚች ምሽት ቢያሳልፏት የሁሉም ደስታ ነው
ወደ ጭንቁ ቀን ብዙ ወደ ሚያስቡበት ሌሊት ሁሉም ተነሱ ወደ አልጋቸው አመሩ በዚ ሰአት ልጅ ያለው ሰው እድለኛ ነው ከልጁ ጋ እየተጫወተ ሌሊቱን ያጋምሳል
ልጅ የሌለው ከሀሳቡ ከጭንቁ ከፍርሀቱ ጋ እየተጣላ ሌሊቱን በፍርሀት ያድራል
ፊያሜታና ፊንሐስ ወደ ተዘጋጀላቸው መተኛ አመሩ
እህት ካለ ወንድም ወንድምም ካለ እህቱ ማንም የላቸውም
ዛሬም ተደጋግፈው ወደ አልጋቸው አመሩ ፊያሜታ እናቷን ካጣች አመት ሳይሞላት አባቷ ስለተለዩአት ሀዘኑ አጎሳቅሏታል ውበቷ ግን አሁንም እንዳለ ነው
ወንድሟ ፊንሀስ አጠገቧ ባይሆን ኖሮ ምን ሊውጣት እንደሚችል ለአፍታ ማሰብም አፈልግም....
ዛሬ ድካሙ ለነሱ እረፍ ሰቷቸዋል ምንም ሳያስቡ ወደ እንቅልፍ ገቡ
ፍርሀትን አቅፎ .......

     ብላቴናው በእርግማን ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ !
(ሚካኤል አስጨናቂ )
ምሽቱን በሙሉ የቋመጠለትን ገላ ያለ ከልካይ በእቅፉ ስር አድርጎታል ። በቀዩ የክለብ መብራት እና በሞንታርቦ ድንፋት ከደመቀው ክለብ ውስጥ እንኳን እንደ ሳሌም አይነት የመላዕክት እህት የመሰለች ሴት አይደለችም ስንቱ ጎራዳ ተውቦ ቀልብን ያማልላል ።
ሳሌም ውበቷ ምትሀታዊ ነው ። የሳሌምን ውበት በቅጡ ለመግለፅ የነ በዓሉ ግርማ አይነት የደራሲያን ህብረት በጋራ የሚያዘጋጁት መፅሀፍ ያስፈልጋል ፤ አለ አይደል የአይኖቿን ጉልላትነት በዓሉ ግርማ በ አራት መቶ ገፅ ፅፎት ሲያበቃ ስብሀት ለአብ ደግሞ አፈፍ አድርጎ የሳሌምን ከንፈር በሳሙ ቅፅበት በወንድ ልጅ ልብ ውስጥ እንደ መብረቅ ብልጭ ስለሚሉ አንድ ሺህ አይነት ስሜቶች በአንድ ሺህ ገፅ ከትቦ የሚገልፅበት !
ሄርሞን ደግሞ ለሴት ልጅ ውበት ልቡ ስስ ነው። እዚህ መቶ ሚሊየን አይነት መዓት በየሳምንቱ በሚወራበት ሀገር ውስጥ እየኖርኩኝ ሴቶች ባይኖሩ ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር ? ሲል ያስባል ።
ደባሪ በሆነው የመገናኛ ግርግር ፣ በሺህ የታክሲ ፈስ እና ጩኸት በተከበበው ሜክሲኮ ሰፈር እንዲሁም ኪስ ውስጥ ከሚገባ የገንዘብ በረከት ውጭ ለአይን ደስ የማይል ክርፋት በሚታይበት መርካቶ እየተመላለሰ ነው የሚሰራው ። የሚያየው ነገር ሁሉ ደስ አይለውም ።
ዘወትር የመኪናውን መስኮት ዝቅ አድርጎ አዲስ አበባ ከስሟ ውጭ አበባ ሊያስብላት የሚያበቁ ነገሮች የሉም ብሎ በጥላቻ አይን ሰፈሮቹን ይገላምጣል ። ወዲያው ግልምጫው ላይ እያለ ተረከዝ የሚያሳይ ጠፍጣፋ ቡኒ ጫማ ያደረገች ሙስሊም ሴት ያይና ልቡ አታሞዋን ትደልቃለች ።
በቄንጠኛ ቡኒ ጫማ ጎን አፈትልኮ የሚታይ ጠይም ውብ ተረከዝ ሲያይ መላ ሰውነቱን ይነዝረዋል ። የሴስ አጋንንቶቹ ሄርሞን ያርገበገበውን የወሲብ እሳት የበለጠ እፍ እያሉ ያቀጣጥሉታል ። አጋንንቶቹ ለአቦል ይጠራራሉ ። የወሲብ ቡና ይፈላል ፣ የቅንዝር ፈንዲሻ ይፈነዳል ፣ ተረከዝ ቡና ቁርስ ሆኖ ይቀርባል ። ያኔ አይኑ መንገዱ ላይ በሚርመሰመሱ ሴቶች እግር እና ቂጥ ላይ እየተመላለሰ የከተማውን ክርፋት ይረሳበታል ። በጭኖቹ መሀል ቆሞ ሱሪውን ድንኳን ያሰራው ማገሩ ጥቂት የእንባ ዘለላዎችን ያወርዳል ።
“ሄርሞን ወንድሜ ሆይ ስራህን በጊዜ ጨራርስና አመሻሹ ላይ ዋና ውሰደኝ!” እያለ ይጮህበታል ። ከዛም ቀኑን እያስታመመው ይውልና ምሽት ሲደርስ አንድ ሁለት ለማለት ቦሌ ይሄዳል ። ቀልቡ ወደፈቀደለት መሸታ ቤት ይገባና ሬድ ሌብል ውስኪው ውስጥ በረዶ ጨምሮ ይጎነጫል ።
መጠጥ ሲጀማምር ረጋ ያለ ቤት ውስጥ ይቆይና ትንሽ ሞቅ ሲለው አይኖቹ ይንከራተታሉ ። ያኔ የእመቤት እና የገረድ እቃ ልዩነት ይጠፋበታል ፣ የሙስሊም ሴት እና የክርስትያን ሴት ተረከዝ ይምታታበታል ። ሴቶች ሁሉ ለእሱ ተፈጥረው በዙሪያው የሚበሩ ቢራቢሮዎች ይመስሉታል ። ከሁሉም ሴት ጭን ውስጥ ማዕድን ለማውጣት ፍቃድ የተሰጠው ብቸኛ ሰው አድርጎ ራሱን ይቆጥራል ።
ተረከዝ ባይነት ባይነት !
ጠይም ፣ ቀይ ፣ ቀይ ዳማ
በቡኒ ጫማ ፣ በጥቁር ጫማ
ጭን ባይነት ባይነት !
《ጥቁር ፣ ጠይም ፣ ቀይ ፣ ቀይ ዳማ 》 ሁሉም ለሱ ስምሙ ናቸው ። ሽንቱ እንደመጣበት ሰው እመር ብሎ ይነሳና በክለቡ ጓሮ ሆኖ አይኑ ውስጥ የገባችውን ሴት ጠርቶ ይደራደራታል ።
ልጅቷን ከወደዳት የሚያስቆመው ሀይል የለም ። የቅንዝር አጋንንቶቹ የፈቀዳት ሴትን እንኳን ምድራዊው የሰው ልጅ ሀይል አይደለም የሰማይ መላዕክት የሚነፉት መለከት እንኳ ሊያስቆመው አይችልም ።
የወደዳትን አጋንንቶቹ የፈቀደላት ሴት ቀዳዳ ውስጥ ሲገባ ቀልቡን ስቶ ይውረገረጋል ። በአዕምሮው ጓዳ የሚያውቃቸውን ሴቶች ሁሉ እየሳለ በአንዲቷ ሴት ገላ ዓለም ላይ ያሉትን ሴቶች ሁሉ ያወጣል ።
ከዛም ተልፈስፍሶ አልጋው ላይ ዘፍ እያለ ለቆት ወደነበረው ምድር ይመለሳል !
አጋንንቶቹ አቦል ቡናቸውን ጠጥተው ካበቁ በኋላ እሱን ለመጀመርያው ፀፀት ጥለው ወደ ጎጆዎቻቸው ይሰደዳሉ ።
ያኔ ድሮ በልጅነቱ ቤተክርስትያን ሲመላለስ ከሰማቸው የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርቶች መሀከል አታመንዝር የሚለውን ትዕዛዝ ቀድሞ ሹክ ያሉት ካህን ፊቱ ድቅን ይላሉ !
አባ መልዓከ ፀሀይ ከበላይ ጣል ያደረጉትን ሸማ እያስተካከሉ …..
“ልጆቼ ከዝሙት ሽሹ ! ዝሙትን ከሌሎች ሀጥያቶች ይልቅ የከፋ የሚያደርገው በራስ ገላ ላይ በእግዚሀር ቤተመቅደስ ላይ የሚደረግ እርኩሰት በመሆኑ ነው ። ሰው መግደል ፣ መስረቅ ፣ መዋሸት የሚባሉ በደሎች ከራስ ገላ ውጭ የሚደረጉ ሀጥያቶች ናቸው ። እነርሱም ያረክሳሉ ፣ ከዝሙት በላይ ግን ሰውነትን የሚያረክስ ሀጥያት የለም ።
ስሙኝ ልጆቼ ከዝሙት ሽሹ ። እናንተን የሚያሰናክል ነገር ባያችሁ ቁጥር አምልጡ ፣ ሩጡ ፣ ጥፉ ….. !”
ሄርሞን ራሱን ካረከሰበት ክፍል ጠፍቶ ሲሮጥ ወደ መሸታ ቤቱ አቅጣጫ ይንደረደራል ። በሩጫው መሀከል ሰረቅ አድርጎ ሲማትር የባንኮኒው መደርደሪያ ላይ በግርማ ሞገስ ተደርድረው ከሚታዩት ኩራተኛ ጠርሙሶች መሀከል አንዱ ጠልፎ ይጥለዋል ።
አረፍ ይላል !
ተጨማሪ መጠጥ ያዛል ። እሱን እየተጎነጨ ራሱን ይወቅሳል ። ሀጥያት በደሉን ያስባል ። ከዝሙት እሳት ፈልቅቆ የሚያወጣውን ሌላ ምትሀተኛ ሀይል መለማመን ይጀምራል ። ፀሎቱን አስኪዶ አሜን ይላል ። ሶስት ጊዜ አሜን ያልተባለ ነገር እንደማይፀና ስለሚሰማው ደግሞ አሜን ይላል ።
ከዛም ፀሎቱን ሊያሳርግ ለሶስተኛው አሜን አ ...... ማለት ሲጀምር እንደ አቦሉ ሁሉ ሁለተኛው ቶና የቅንዝር ቡና እንዳይቀርባቸው የሚፈልጉት አጋንንቶቹ ስስ ልቡን ስለሚያውቁ መረብ ይዘረጉበታል ።
አንድ አይኑን ገለጥ ያደርጋል ። ለሰማይ ለምድር የሚከብድ ውበት ፣ መፅሀፈ ሄኖክ ውስጥ እንዳለው ታሪክ መልዓክትን ካሳቱ የሴት ልጅ ውበቶች መሀከል አፈንግጦ ዛሬ የደረሰ ውበት ላይ አይኑ ይተከላል ።
ሌላ ተረከዝ ፣ ሌላ ዳሌ ፣ ሌላ ጭን ፣ ሌላ ሳቅ ፣ ሌላ አይን ፣ ሌላ ፀጉር ፣ ሌላ ድምፅ ፣ ሌላ መዓዛ ።
እዛው ቆዳውን ያሸልትና አዲስ ማንነት ይፈጥራል። በሌላ የወሲብ ጠኔ ይመታል ፣ በሌላ የሴት ተረከዝ ጣዕም ጉሮሮው ይደርቃል ።
አዲስ ጉጉቱ ፍሬ አፍርቶ ይጎመራል ። ያን ጊዜ አጋንንቶቹ በሳቅ ያውካካሉ ። ሄርሞን በድጋሚ በቁጥጥራቸው ስር ይውላል ።
ጆግናው የአጋንንን ሰራዊት አንባገነኑን ሄርሞን በአንዲት ውብ ተረከዝ ጥይት መትቶ ተቆጣጥሮታል ።
ሄርሞን ወደቀ !
ሄርሞን አለቀ !
ሄርሞን ደቀቀ !
ማልዶ ሲነቃ ሳሌም ስሩ ተኝታለች ። ከዛሬ በፊት ለአጭር ጥሙ አልጋ ክፍል ከመግባት ውጭ ማደር አይወድም ነበር ። ዛሬ ግን አድሯል ። እንደው ቀን ከፍቶበት ፣ ስህተት ሰፍቶበት አድሮ ቢሆን እንኳ በለሊት ከአልጋ ክፍል መውጣት ነው የሚፈልገው ።
ተነሳ !
አብሯት ያደራት ሴት ሂል ጫማ ን አየው ። እንደሌሎቹ ብዙ ሴቶች ድፍን ሸራ ጫማ አድርጋ ስላልነበር ደስ አለችው ።
እሷ ያለችበት ክፍል መዓዛ በኮንዶም ክርፋት አልተበከለም ፣ ጡት ማስያዣ ና ፓንቶቿን አያቸው ።
አልቻለም ዞር አለ ። ሲዞር ከምትሀተኛ ውበት ጋር በአይኑ ተላተመ ።
ይሄን መሳይ ገላ አቅፌ ነው ያደርኩት ? ሲል አሰበና በልቡ ኮራ ።
“ደስ ትላለህ ሄርሞን ” የሚሰማውን ድምፅ አላመነውም ። ሄርሞን ? ጭራሽ ስሜን ነግሬያታለሁ ? ድምፅዋ ደግሞ መረዋ ነው ።
ይህቺ ሴት ማናት ?
“ማን ልበል ?”
“ሃሃሃሃሃሃ ምሽቱን እንደዛ ስሜን እየጠራህ ስታሞካሸኝ አድረህ ማንልበል አልከኝ ?”
“እኔ አንቺን በስምሽ ጠርቼ አሞካሸሁሽ ?”
“ድብን አድርገህ !እንዳንቺ አይነት ሴት አይቼ አላውቅም ምናምን እያልክ ስትለፋደድ አይደል እንዴ ያመሸኸው?”
“በርግጥ ቆንጆ ነሽ ። ”
“ባትልስ ? ምንም የማይወጣልኝ ቆንጆ ነኛ ”
“ግን መልክሽ አዲስ አልሆነብኝም ?”
“ያው እዚህ ስትመላለስ አይተኸኝ ይሆናላ ”
ቀስ ብሎ ፊት ለፊቱ ካየው ወንበር ላይ አረፍ አለ ። ማንን መሰለችኝ ?
አዎ ሰርካለም ራሷ !
ሰርካለምን ትመስላለች ። ሰርካለም አብረው ስምንተኛ ክፍል ሲማሩ የሚያውቃት ልጅ ነበረች። እሷና ሳምራዊት ተወልዶ ባደገባት ጠባብ ከተማ ውስጥ ከሚማሩ የአብዮት ልጆች ትምህርት ቤት ውስጥ የተለዩ ነበሩ ።
ሰርካለም ጠይም ሆና አሳ መሳይ ውብ ነች ። ጠጉሯ ያለምንም ቅጥያ የተንዠረገገ ነው ። በዛ ላይ ሱሪ እንደነውር በሚቆጠርበት ወቅት ላይ ከሳምራዊት እኩል ሱሪ ትለብሳለች ። እንደውም ሸገር ብዙ ጊዜ ኖራ ከመጣችው ሳምራዊት ይልቅ ሰርካለም ሱሪ ያምርባታል ።
ዳሌዋ ያለምንም ከልካይ ይንጎማለላል ።
“አይ የታምራት ልጅ ተበላሸችበት !” የሚሉ የባልቴት ድምፆች ከዚህም ከዛም ይሰማሉ ።
ውበቷ ን እየተመኙ የሚነቅፏት መምህራኖች በግራም በቀኝም በነገር እየጠዘጠዙ ያብጠለጥሏታል ። የሚቀኑባት ሴት ተማሪዎች ቀሚሷን የትም የምትገልብ ሸርሙጣ እያሉ መረን በለቀቀ አፋቸው መረን የለቀቀ ስድብ ይሰድቧታል ።
ግን ሁሉም የማይክዱት አንድ እውነታ ደግሞ አለ ።
ሰርካለም አድጋለች ። እድገቷም ፈጣን ነው ። እሷ በዚህ ሰዓት እንደ ፈለገችው በፈለገችው አቅጣጫ የሚሾሩላት ወንዶች እያሉ እንደሌሎቹ ሴት ልጆች ገመድ መዝለል እየተጫወተች እግሯ አቧራ የሚቅምበት ምክንያት የለም ።
የስንት መጋዘን ባለቤት ሀብታም ነጋዴ ጭራውን እየቆላ እግሯ ስር እየተርመሰመሰ ባለበት ወቅት ላይ ሂሳብ የቤት ስራ መስራት ለምኗ ነው ?
የሀበሻ ተማሪ ትምህርት የሚማረው ለየትኛው የፈጠራ ስራ እራሱን ለማዘጋጀት ነው ? ለመኖር ገንዘብ ለማግኘት ደህና መስሪያቤት ለመቀጠር አይደለምን ? ከዛ ተንቀባሮ ለመኖር ቤተሰብን ለመርዳት ...
ሰርካለም ደግሞ ሁሉንም አሁን መሆን ትችላለች ። ቁንጅናዋ ሁሉን አሸናፊ ነው። እሷን ከሰፈር ውሪ እስከ አስተማሪ
ከችጋራም እስከ ሀብታም ድረስ የሚመኛት አሸን ናቸው ። ሳትማር ፊደል ሳትቆጥር ፣ ለአስተማሪ ሳታሸረግድ ፣ ለሰፈሩ ባልቴት ምላሽ ሳትሰጥ ከሁሉም በላይ መሆን ትችላለች ።
ለዛም በራስ መተማመኗ ጥግ ድረስ ነው ።
ለብዙ ዘመናት ያህል ወንዶች በሷ ስለመጣላታቸው ፣ መምህራን በፍቅሯ ስለመደንዘዛቸው ፣ ሀብታሞች እሷን የነሱ ለማድረግ በገንዘብ መወራረዳቸውን ያውቀዋል ።
ደግሞም የሰርካለም ሀጥያት በጓደኞቿ ዘንድ ምንም ታህል አልነበረችም ። የሰርካለም ብቸኛ ስህተት ከእኛ ቀድማ መደጓ ብቻ ነው ሲል ሄርሞን አሰበ ።
ሰርካለም ዱርዬ የተባለችው ክፍል ስለፎረፈች ፣ ጀላቲ በአደባባይ ስለመጠጠች ፣ ሱሪ ስለለበሰች ፣ ጠጉሯን ስለተተኮሰች ፣ ከፍ ብላ የበቀለች ማሽላ ሆና አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ ሆና በእድሏ ስለተፈረጀች ፣ በግድ አብረንሽ እንሂድ ከሚሏት ደረቅ ወንዶች ጋር አብራ መንገድ ስለሄደች እንጂ አሁን ካለው ሄርሞን በላይ በደለኛ ሆና አይደለም ። ብሎ ወደራሱ ተመለከተ !
በዚህ ሳምንት ብቻ ከሀያ ሴቶች ጋር ወቷል ፣ አለቅጥ ጠጥቷል ፣ ቅሟል ፣ አጭሷል ።
ወደ ስራው ኮቱን ለብሶ ሲሄድ ግን ሀገር ምድሩ የተከበሩ ሲል ያሞካሸዋል ።
ሰርካለም የት ሆና ይሆን ? ውጭ ወታ ይሆን ? ሀብታም ሆና ይሆን ? ልጅ ወልዳ ከብዳ ይሆን ?
“ሰርካለም የምትባል አብራኝ የተማረች ልጅ አለች ። የደጀን ከተማ ልጅ ነኝ ”
“እንዴ ሄርሞን ባልሆንክ ?”
ቀና አለ !
“አንቺ ማነሽ ?”
“ሰርካለም። እዚህ መጠሪያዬ ሳሌም ነው ማለትም ማታ እየጠራህ ስታሞካሸው የነበረው ስም ቂ ቂ ቂ !”
ደነገጠ ። ከሁሉም በላይ ያስደነገጠው ነገር ግን ”ያቺ የውቦች ሁሉ ውቧ ሰርካለም እንዴት ያንን በራስ መተማመኗን አጥታ የቡና ቤት ሴት ሆነች የሚለው ጥያቄ ብቻ ነው ። “
ለሊቱን ስታስል ማደሯ ትዝ አለው ። ኮንዶም አለመጠቀሙም ታወሰው ።
አጋንንቶቹ የቅንዝሩን በረካ በፀፀት ፣ መላዕክት በቅስፈት እንዳይደመድሙት ፈራ ።

@wegoch
@wegoch
@paappii
🌙🌙🌙🌙🌙
ዉድ የቻናላችን የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦች እንኳን ለታላቁና ለተከበረው ለረመዳን በአል አደረሳቹ!!!

#ኢድ_ሙባረክ
መልካም በአል እንመኛለን

@wegoch
@wegoch
''ሹሮ በአናት'' እና ''የመሬት ጥበት....''
ክፍል ፩

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የተገኘ ፁኹፍ ነዉ
ፀኀፊ :- ኤፍሬም እንዳለ
የፁኹፉ ድምፅ :- ሚኪያስ ልየዉ @Mykeyliyew


@Wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/09/24 21:30:18
Back to Top
HTML Embed Code: