Telegram Web Link
''ደቦ''
የጉዞ ማስታወሻ
በ ''ሄኖክ ስዩም''
ክፍል ፫
(፷ ደራሲያን ከተሳተፉበት መፅሐፍ ዘንድ ያገኘነው ፁኹፍ ነው)
''በአፅንኦት የተተረከ''
የኋላውን ዝምታ ለማስከን ያኽል :- የጋሽ ሙላቱ አስታጥቄ ጃዝ ስራዎች
አቅራቢ @Mykey21

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
ታጋቹ ማስታወሻ
( በእውቀቱ ስዩም)
ቀሳ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ቤቴ ውስጥ ያገኘሁት ምግብ ሩዝ ብቻ ነው ፤ ሰኞ ሩዝ በቲማቲም- ማክሰኞ ሩዝ በጅንጅብል- ረቡእ ሩዝ እንደወረደ፤ ወዘተ…ባጭሩ በሩዝና በሪዝ ተከብቤ ሰነበትሁ ማለት ይቻላል፤ አንዳንዴ ምግብ የቀየርኩ እንዲመስለኝ የምበላበትን ቦታ እቀያይራለሁ፤ ሳሎን ውስጥ ሁለት ማንኪያ እጎርስና የተረፈውን በረንዳው ላይ ተቀምጨ እጨርሰዋለሁ፤
ሩዝ ጠዋት ማታ ከመብላቴ የተነሳ ወደ ማጅራቴ ሲሸሽ የነበረው ፀጉሬ ተመልሶ ቅንድቤ ድረስ ግጥ—ም አለ ፤ የህንድ አክተር ለመምሰል የቀረኝ በሱሪ ላይ ቀሚስ መደረብና ባየር ላይ የሚበር ሞተር ሳይክል መንዳት ነው፡ ፡
የሆነ ግልገል ጉንዳን ጠረጴዛየ እምብርት ላይ ከተበተኑት የሩዝ ቅንጣቶች መካከል አንዲቱን መርጦ ተሸክሞ ሲያዘግም ተመለከትኩ ፤ኩንታል መሸከሙ ነው፤ አይ ጉንዳን! አሁን ጉንዳንን የመሰለ ታታሪ ፍጡር በሚኖርበት አለም የሰው ልጅ የላባደሮችን ቀን ያከብራል ? ልይዘው ሞከርኩ ፤የጣቶቼን ጥላ ሲያይ ኩንታሉን እንደተሸከመ መሮጥ ጀመረ፤ አምልጠህ ሞተህል ባክህ! !ባውራ ጣቴና በነገረኛ ጣቴ መካከል አጣብቄ ያዝኩት ፤ የሞተ መስሎ ፀጥ አለ፤ ለካ አስመሳይነት የሰው ልጆች ባህርይ ብቻ አይደለም፤ ትወናውን አድንቄ በተሸከመው የሩዝ ቅንጣት ላይ አንዲት የቲማቲም ፍሬ መርቄለት ለቀቅሁት፤
ባለፈው ለለውጥ ያክል የሱካር ድንች ለመቀቀል ሞከርኩ፤ የአሜሪካ የሱካር ድንች አንዱ ፍሬ የድሮ ካውያ ያህላል ፤ ችግሩ በቀላሉ አይበስልም፤ እንዲያውም ካሜሪካ ሱካር ድንች፤ የኢትዮጵያ በሬ ሸኮና ቀድሞ ይበስላል፤ ቤት ጠርጌ ፤ምንጣፍ ቀይሬ፤ ኮርኔስ ራሱ ቀይሬ ተመልሼ መጥቼ ሳየው፤ አልበሰለም፤ ምን ጉድ ነው! ከዛ ገላየን ተታጥቤ፤ ብብቴንና በስተራስጌ የሚገኘውን ሁሉ ተላጭቼ ለባብሼ ሳበቃ ብረትድስቱን ከፈትኩት፤ ድንቼ መብሰሉን ለማረጋገጥ በሹካየ ወጋ አደረግሁት፤ እንዴየየየየ! የሹካው ጥርስ ተጣመመ፤ በጣም ተናደድሁና አውጥቼ በመስኮት በኩል ወረወርኩት፤ ድው! የሆነ ሰውየ oh Fuck! ብሎ ሲወድቅ አየሁት፤ ልጅ እያለሁ እናቴ “ ምግብ መወርወር ጡር ነው “ ትለኝ ነበር፤ እረ ጦርም ነው እማየ ፤ ይሄው አንድ ምስኪን ፖስታ አመላላሽ ፈረንጅ ለትንሽ ገድየ ነበር!
በክቡር ዳኛ Frank Caprio ፊት ቀርቤ ፤የፈነከትኩት ሰውየ እስኪሻለው ድረስ አልጋው አጠገብ ተቀምጨ በእንግሊዝኛ እንዳስታምመው ፈረዱብኝ! ሁለት ወር ሙሉ ተጎድቼ እንደከረምኩ ያወቅሁት በሆስፒታሉ ውስጥ የሚቀርበልኝን መኖ ሳይ ነው-ቆስጣ፤ የወይን ዘለላ፤ በማር የተጠበሰ ዳቦ! ግሪክ ሳላድ! እረ ወገን! ላስታማሚው እንዲህ አይነት ምግብ ከቀረበ ለታማሚው ምን እንደሚቀርብ ኢማጂን እንግዲህ!
ባልተያያዘ ዜና ፤
እንደ ዶክተር አቢይ አህመድ ያለ ብልጥ ሰው ግን አለ? ፤ ሰልስትና (ከሶስት ቀን በፊት) ተቃዋሚዎችን ፓርላማ ውስጥ ሰብስቦ ሲያወራ ማስኩን ካፍንጫው ሸርተት አድርጎ ከንፈሩ ላይ አስቀምጦት አየሁ ፤ ብዙ ሰው ስትራቴጂ መሆኑ የገባው አልመሰለኝም ፤የተፎካካሪ ፓርቲ ሊቀመንበሮች " አንተ ብቻ ነህ እንዴ አፍንጫህን የማናፈስ ነፃነት ያለህ ?ብለው በእልህ ማሳካቸውን ገለቡት ፤ አብቹየም ሁሉም አፍንጫውን ማጋለጡን ከተመለከተ በሁዋላ ፈገግ ብሎ በልቡ፤ “ጎበዝ! እንግዲህ ይቺን ቫይረስ እንቃመሳታ ፤ እኔ ጎልማሳ ስለሆንኩ አገግሜ እነሳለሁ ፤ ለእናንተም ደግሞ አካላዊ ርቀቱን ያስጠበቀ ቀብር አስከባሪ ይዘጋጃል” ካለ በሁዋላ የምትከተለዋን ዘለሰኛ ማስታወሻው ላይ አሰፈረ፤
ጎልማሶች ከመከራ ስንማር ፤
ለሼባዎች ነፍስ ይማር !

@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew Mykey)
ጣዕም ያላቸው ወዞች!
ኹሌም ቀኑን ለምታከብሩት ለእናንተ ይኹን

ከእነእርሱስ ፕሮጀክት © Mikiyas Liyew
@Mykeyonthestreet
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

      ክፍል - ፪

የት ነን ...
የምሁራኖቹ ድምፅ በናጋዚ ሰማይ ላይ ያስተጋባል እንባ ቀረሽ ልመና ከምሁራኖቹ ልሳን ይወጣል
ልጅ ያለው አረ ልጆቼን እናቱን ትቶ የመጣ አረ ለእናቴ እኔ ነኝ ያለሁዋት ሚስቱን ከእቅፉ ያጣ አረ ባለቤቴ ብቻዋን ናት
አባቱን ሳያቅፍ የመጣ አረ ድምፃቸውን እንኳ እንስማ
ከኚ ሁሉ ድምፆች የአንዲት ሴት ድምፅ ተለይቶ ይሰማል በናጋዚ ቤት ውስጥ ያለችው በቸኛዋ ሴት ሳትሆን አትቀርም
አረ ልጄ ብቻውን አረ ስለፈጠራችሁ በእናት አንጀቷ ታነባለች የተዘጋባትን በር ትደበድባለች
አይዞሽ እህቴ እንዲ አቱኚ ተረጋጊ ከጎኗ ካለው ክፍል አንድ ወጣት ያፅናናት ገባ
የናጋዚ ሰማይ በወንዶች እንባ በአንዲት እናት ጩኸት አሰቃቂ ቤት ሆኗል
ድሮም ለአዋቂ ከሁሉም የሚበልጥበት ስቃይ ከቤተሰቡ ከሀገሩ የተለየ ጊዜ ነው
ሌላ ነገር ለሱ ስቃይ አደለም ሀገሩና ቤተሰቡ ሰላም ከሆኑ ገሀነምም ገብቶ ስቃይ ይቀበላል
መንግስት ለምን የሀገሪቱን ወሳኝና የሀገር ባለውለታዎችን ወደ ናጋዚ አምጥቶ እንደከረቸመባቸው አልታወቀም
ሰሞኑን የእያንዳንዱ ምሁራኖች ቤተሰብ ከፖሊስ ቤት ይልቅ የመገናኛ ብዙሀንን ቤት ማንኳኳት ጀምረዋል
ስንት የሀገር ሰው አክሞ ያዳነውን ልጇን ፎቶ ይዛ በሰው ፊት ልጄ ትላለች በቴሌቪሽኑ መስኮት ታነባለች
የስንቱን አእምሮ በእውቀት የሞላው የጠፋውን ደራሲ ወንድሟን መፅሀፍ ይዛ እህት እንባዋን ትረጫለች
ታሪኳን ማንም ሳያይ ቆፍሮ ያወጣውን ልጃቸውን እያሰቡ አባት ልጄ ልጄ ይላሉ
በናጋዚ ሰማይ ልጄን ቤተሰቤን እየተባለ ዋይ ዋይታ በዝቷል
በቴሌቪሽኑና በሬዲዮው መስኮት ልጄን ወንድሜን የሚል ጩኸት በርክቷል
የሁለት ስጋዎች ወግ በሀዘን ተሞልቷል በሁለቱም ዘንድ ፍርሀት በርትቷል
በናጋዚ ሰማይ ያሉባትን ትንሽዬ ክፍል በአይናቸው ይዩ እንጂ ከየት በየት እንዴት እንደመጡ የሚያውቁት ነገር የለም
በናጋዚ ሰማይ ከቤቱ መከርቸም ውጪ ምንም አይነት ቅጣት የለም እያንዳንዷ አስፈላጊ ነገር በተዘጋጀላቸው ቀዳዳ ይሰጣቸዋል
ለነሱ ግን ሁሉም ባዶ ነው ለአዋቂ መሰረቱ ቤተሰቡ ነውና
በቀዳዳው ከቀረበላቸው የእንቁላል ሳንዱዊች የቁርስ ሰነ ስርአት በሁዋላ የተከረቸሙት በሮች በራሳቸው መከፈት ጀመሩ
አፍነው የያዙአቸውን ምሁራን ከአፋቸው ይተፉ ጀመር
እድሉን ያገኘ ሁሉ በመቅፅበት እየወጣ ወደ አገኘው ቦታ ይፍጨረጨራል
በመቅፅበት ከበሩ እየዘለለ መውጫውን ይፈልጋል
በእኩል መደዳ ከተደረደሩት በሮች ፊት ሙሉ ነጭ ቅብ ባዶ አዳራሽ አለ
ከማማው ላይ ጠመንጃቸውን ይዘው ወዲ ወዲያ ሚሉ ናጋዚ ብሎ የታተመበት የደንብ ልብስ የለበሱ የናጋዚ ሰማይ ዘቦች ቆመዋል
መፍጨርጨሩ ቀጥሏል የት ነን በሰፊው አዳራሽ የብዙ ምሁራን ላንቃዎች ተከፈቱ ድምፃቸው ካሉበት አዳራሽ ግርግዳ ጋ ተመልሶ እየተጋጨ መልሶ የት ነን የሚል መልስ ይሰጣቸዋል
ሌላ አንድም ያለበት አይመስልም
ከጩኸቱ ጀርባ ሁሉም እርስ በእርስ መተያየት ጀምሯል የሚተዋወቀው ምሁር እየተቃቀፈ እንባውን ያራጫል
ላቡን ጠብ አርጎ ሀገር ያቀና ጀግና ዛሬ ታፍኖ እንባውን ይረጫል
ፍርሀት አግራሞት ድንጋጤ በናጋዚ ሰማይ እየተስተዋሉ ነው
የናጋዚ ሰማይ ጩኸቱ በረድ ብሎ ጉርምርምታው ቀጥሏል
        ሰላም የሀገሬ ውድ ልጆች የአንዲት ሴት ድምፅ ከማማው ላይ ከሚገኝ ሰፊ ድምፅ ማጉያ ውስጥ ተሰማ ጉርምርምታው በአንዴ ፀጥ አለ
እንኳን ወደ ናጋዚ በሰላም መጣቹ
የወደፊቷ  የኢትዮጵያችን ተስፋ ወደ ሆነው ድርጅት በሰላም ተቀላቀላቹ
እራሳችሁን ትልቅ ለሆነ አላማ አዘጋጁ
ንግግሩ ቀጥ አለ
ጉርምርምታው ጨመረ ተከርችመው በራሳቸው የተከፈቱት በሮች አሁንም ምሁራኖቹን ለመዋጥ ሰተት ብለው ተከፈቱ
የናጋዚ ዘቦች ከማማው ወርደው ምሁራኖቹን ለመዋጥ ወደ ተዘጋጀው በር እየጎተቱ አስገቡ በሮቹም መዋጣቸውን ቀጠሉ ሁሉም የተከፈቱት በሮች መዋጣቸውን አቆሙ
ሁሉም በሮች ተከረቸሙ
ጩኸቱ በረከተ .....

     ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
በዚህ አዝግሙልኝ

''ባህላዊ ምሽት'' የተሰኘ ፁኹፍ ላንብብላቹማ
ሌሊሳ ግርማ ነው ፀሃፊው
ክፍል ፩
አቅራቢ:- @Mykey21

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

       ክፍል - ፫

ከተዘጉት በሮች ውስጥ ብዙ ጩኸቶች እየተሰሙ ነው ሁሉም በአንድ ነገር ተስማምተዋል የመጡበት ነገር አደለም ለሀገራቸው ለማንም እንደማይጠቅም ተረድተዋል
ከዚ በፊትም አፋኙን መንግስት ያውቁታል
 ተስፋ ቆርጦ በዝምታ ከዝምታ ገዳም የገባ አለ
እጁን ዘርግቶ ልመናውን ወደ ላይ አድርጓል
ከተዘጋው በር ውስጥ አነስተኛ የምሁራን በአት የገዳም ኑሮ መስሏል
የዘጉ ምሁራኖች በፀሎት ላይ ናቸው
ቀናቶች እየተቆጠሩ ሄዱ....
አሁን በናጋዚ ሰማይ ምንም አይነት ጩኸት የለም የዝምታ ሰማይ ከምሁራኑ ፀሎት ጋር ተደምሮ ናጋዚ የምሁራኖች ገዳም ተብሎ መሰየም ነው የቀረው
ከናጋዚ ሰማይ ውጪ የቤተሰቦቻቸውም ዝምታ በርትቷል የመገናኛ ብዙሀኖቹም በደረሳቸው ከባድ ማስጠንቀቂያ የማናቸውንም ቤተሰቦች መቀበል አቁመዋል
ቤተሰብም ከበአቱ ተቀላቅሎ ከቤቱ አነስተኛ ገዳም ገድሟል
እጁን ዘርግቶ ለጠፉበት ሰዎች ፍለጋውን ለአምላክ ሰቷል
በናጋዚ የምሁራን ገዳም ለቤተሰብ ይፀለያል በቤቱ የገደመው ልጄን ባይ ቤተሰብ ለልጁ ይጸልያል
የሁለት ስጋዎች ወግ ከአንድ የመንፈስ ገዳም ተገናኝቷል
እራሳችሁን ለትልቅ ነገር አዘጁ ለመጨረሻ ጊዜ የሰሙት ድምፅ ከጆሮአቸው ያቃጭላል ያ ትልቅ ነገር መጨረሻው ሞት እንደሆነ ተረድተዋል
ሁሉም አንድ ነገር ይጠብቃል ምክንያቱን ለመስማት ጓጉቷል ቋምጧል ተጨንቋል ተጠቧል
በናጋዚ ሰማይ ነገሮች የተለመዱ ይመስላሉ
ከገዳምያኑ ፀሎት ቀጥሎ በትልቅ ፀጥታ ውስጥ ትልቅ ነገር እየተነደፈ ነው
ዘቦቹ የሚያስፈልጋቸውን እየጠየቁ ከበአቱ ላሉ ምሁራን ያቀብላሉ
ግማሹ መጽሀፍ ቅዱስ ግማሹ መዝሙረ ዳዊቱን ግማሹ ዝምታው ሲውጠው ማስተንፈሻ ወረቀት መጽሀፍት
የሁሉም ተመሳሳይ ጥያቄ ፂም መላጫና እስኪርፒቶ ሆኑአል
ከሚቀርብላቸው ምግብ ጀርባ የሚሰጣቸውን ሹካና ማንኪያ መመለስ ካቆሙ ሰንበት በት ብለዋል
ፀሎታቸው ሰመረ መሰል የዘቦቹ ልቦና ተሰውሯል አስተዋይ በሌለበት አለም የነጋዚ ገዳማውየን በጥልቅ ዝምታ ትልቅ ነገር አስበዋል
አፋቸውን ከፍተው የተቀበሏቸው በሮች መቼ ሰተት ብለው እንደሚከፈቱ ናፍቀዋል
የተኙበትን አልጋዎች ብረት ፈታተዋል ከወለል እያደሩ ለአላማቸው ቁመዋል
ከፀሎቱ ቀጥሎ በሚገናኙበት ግንብ  ባለው ሽንቁር መልእክት ያስተላልፋሉ ሁሉም ለሚጠብቁት ቀን ተዘጋጅተዋል ሳይተዋወቁ በመንፈስ አንድ ሆነዋል በወኔ ተሞልተዋል
ዛሬ ቀናቸው ትመስላለች የቁርስ ስነ ስርአት እንዳለቀ የተዘጉት በሮች ሰተት ብለው ተከፈቱ
ከልብሶቻቸው ውሰጥ ብዙ ነገሮች ተከማችተዋል አንድ ነገር እየጠበቁ ነው በገደሙበት አለም ከአምላክ አንድ ነገር የተላከላቸው እስኪመስል ድረስ በራስ መተማመናቸው ጨምሯል ቀስ እያሉ ከበሮቻቸው ወደ ነጩ አዳራሽ ተመሙ
ዛሬ እንደ ቀድሞ ጩኸት የለም ሁሉም በትኩረት ሚደረገውን እየተመለከቱ ነው
የናጋዚ ዘቦች ከማማው ቦታቸውን ይዘዋል ሁለት አልሞ ተኳሾች ከማማው በላይ ተሰድረዋል
አይኖች ወዲያ ወዲያ ይላሉ የዝምታ ንግግሮች በሁሉም ጆሮዎች ገብተዋል
ከመላእክት የመጣው የማምለጫ ስልት ዛሬ ሊተገበር ከጫፍ ደርሷል
ከገደሙበት አለም መልስ ስለተላከላቸው ዛሬ ደሞ ነፍስ የማዳን የጀግና ተልእኮ ውስጥ ገብተዋል
ከምሁርነት ወደ ብህትውና ከብትህውና ወደ ጦር ዘመቻ ለመግባት አሰፍስፈዋል
ልጄን ስትል የነበረችው ሴት ዛሬ ልጇን ለማቀፍ የሚያስችላትን ነገር ለማድረግ ወስናለች
ያ እንባ ዛሬ የለም ወኔዋ ልቧን ሞልቶ ሊፈነዳ ደቂቃዎች ቀርተውታል
ሁሉም በአንድ ልብ
በስጋ መሪ የሌለበት ጦርነት በመንፈስ ግን መሪው ሲለምኑት የነበረው አምላካቸው እንደቆመላቸው አምነው ተዘጋጅተዋል
      ሰላም የሀገሬ ልጆች ትኩረታቸው ከድምጽ ማጉያው ላይ ተተከለ የባለፈዋ ሴት ደግማ መታለች
       እንዴት ከረማችሁ  መልስ የለም
ዛሬ ለምን ሁላችን ከዚ ከናጋዚ እንደተገናኘን እንነጋገራለን
ትልቁ አላማ ዛሬ ግልፅ ይደረግላቸዋል መልሳ ድምጿ እስከወዲያኛው ሄደ
የናጋዚ ገዳማውያን ለመጨረሻ ጊዜ ይሆናል ይሄን ድምፅ የሚሰሙት
     ሰአቱ ደርሷል.......
ሹካዎች የመመገቢያ ሳህኖች ከፂም መላጫ ውስጥ የወጡ በብዕር ላይ የታሰሩ ምላጮች
ከአልጋ የተነቀሉ ጠንካራ ብረቶች ከሁሉም በላይ በመሪያቸው ላይ ያላቸው እምነትን ይዘው ተዘጋጅተዋል
አዎ ሰአቱ እየተሽከረከረ ነው የሞት ትግል ሽረት በናጋዚ ሰማይ...

      ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ
    
@wegoch
@wegoch
@wegoch
ሰከን ብላ ከዋለችው ቅዳሜ ለምሽታችኹ ትኾን ዘንድ ይቺን ስሙማ!

''ባህላዊ ምሽት'' የተሰኘ ፁኹፍ ላንብብላቹ
ክፍል ፪
ሌሊሳ ግርማ ነው ፀሃፊው
@Mykey21

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
Audio
የሶስተ ሲኖትራክ ወገ
#እሱባለው_የኔነህ

@wegoch
@wegoch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች
 
     ክፍል - ፬

ከድምፅ ማጉያው መታ ከጠፋችው ሴት በሁዋላ ሁሉም አይኖቹን ወደ በሩ አማትሯል በሮች ሊውጧቸው እንዳልተዘጋጁ ባለመከፈታቸው ፍንጭ ሰጡ ዘቦቹም ከማማው ላይ አልተንቀሳቀሱም ቀጣይ ነገር እንዳለ ተረድተዋል
የጠቢብ ቅኔው ዝምታው ነው በዝምታ ሁሉን በአይኖቻቸው እየተከታተሉ  ነው
  ሰላም ውድ የሀገሬ ልጆች እንኳን ወደ ናጋዚ በሰላም መጣችሁ ጎርነን ያለ የወንድ ደምፅ ተሰማ
ቆይታችሁ ጥሩ እንደሆነ አልጠራጠርም አወራሩ የቀልድ ንግግር እንጂ ለቁም ነገር የመጣ አይመስልም
አሁን እዚ ምን እንዳገናኘን ለምን እንደተገናኘን ምነግራችሁ ይሆናል
የናጋዚ ድርጅት የኢትዮጵያ የመጪው ተስፋ ለልጅቿ ለህዝቧ ለወደፊት እጣዋ ለወደቀው ጥበቧ ለተራበው ህዝቧ መዳኒት ለሚሻው ህመምተኛዋ ለሰላሟ ትልቅ አሻራ ለመጣል የተቋቋመ ድርጅት ነው
እናንተም ለመጪዋ ኢትዮጵየያ የየራሳችሁን አሻራ እንድታስቀምጡ ነው ወደዚ የመጣችሁት ከዚች ቀን ጀምሮ ሁላችሁም በየድርሻችሁ በናጋዚ ስር ሆናችሁ ታገለግላላችሁ ማለት ነው
አጥንታችሁን ከስክሳችሁ ደማችሁንም ቢሆን አፍሳችሁ ላብችሁን አንጠፍጥፋችሁ ኢትዮጵያን አንድ እርምጃ ከፍ የማድረግ ሀላፊነት በእናንተ ላይ ተጥሏል
 በእናንተ ዋጋ የኢትዮጵያ ህዝብ እጁን ወደ ላይ በተስፋ ብቻ መዘርጋት አቆሙ ወደ ናጋዚ ይዘረጋል ተስፋ ብቻ አሳይተንም አንነሳውም የጠየቀውን ስለምንሰጥ እናንተም ሀሳብ አይግባችሁ እዛ መጸሀፍ አሳትማችሁ ሸጣችሁ በተራ ሆስፒታል የማይደን  በሽተኛ ከሚያደክማችሁ በምታስተምሩበት የማይገባው ከሚያደነቁራችሁ እዚ ሆናችሁ ሁሉንም ብታደርጉ ነው ሚሻላችሁ እዛ ከምትለቃቅሙት ገንዘብ በላይ እዚ ሆናችሁ ብዙ ነገሮች ታገኛላችሁ ከእንግዲህ ጀምሮ ለራስ መኖር አቁማችሁ ለሀገርና ለወገን ስለምትኖሩ እኛ ደሞ ለቤተሰቦቻችሁ ትልቅ ነገር እናደርግላቸዋለን እንከባከባቸዋለን የምፀት ሳቅ ከድምፅ ሚጉያው ተሰማ ድምፁም ወዲያ ተቋረጠ
የንግግሩ ነገር እንዳለቀ ከማማው ላይ ደረጃዎቹን እየደሰቁ ዘቦቹ መውረድ ጀመሩ ሰአቱ መድረሱን ልቦናቸው ነገራቸው ሁሉም እርስ በእርስ ተያየ
የማምለጥ ሰአት ደርሳለችና የሞት ሽረት ትግል ለማድረግ ተዘጋጁ
የእስከ ዛሬው የናጋዚ የምሁራን ገዳም ሱባኤ ዛሬ መልስ ያገኛል
ሁሉም ተስፋውን በለመነው አምላክ ላይ አድርጓል ሀይሉንም በሹካዎች በምላጮቹ በተገነጠሉት ብረቶች ላይ እንዲሆን ተማፅኗል
ሀገር በማቅናት የተልፈሰፈሰ እጅ ዛሬ ሲቀለብ ከኖረ ፈርጣማ ጋ ሊጋጭ ነው
በሮቹም እንደተለመዱት ሰተት ብለው ለመዋጥ አፎቻቸውን ከፈቱ
ዘቦቹ በማማው እስኪወርዱ ምሁራኑ ሁለት ሁለት ሆነው ተጠባብቀው ቆሙ
ቀጥል አለ ቀድሞ ወደ አዳራሹ የወረደው የናጋዚ ዘብ
ከፊቱ የሚገኘውን አንዱን ገፍተር እያደረገ
በመቅፅበት  ከሰውነቱ መዞ ያወታውን ሹካ በአይኖቹ ትክክል ሰካቸው
የጦርነቱ ማብሰሪያ ጩኸት በዘቡ እሪታ ተጀመረ
ከየት መጣ ሰይባል ዘቦቹ ላይ ጥቃት መፈፀም ተጀመረ
በያዙት ምላጭ አንገቶቻቸውን ይተለትሉ ጀመር ለመመገቢያ በተሰጣቸው ሹካ አይኖቻቸውን ይጠነቁሉ ገቡ ከአልጋው ባወረዱት ብረት የዶመዶመው ጭንቅላታቸው ላይ ማሳረፍ ቀጠሉ ዘቦቹም የዋዛ አደሉም ከማማው ያሉት ተኳሾች በፍጥነት መልስ ሰጡ በኢላማቸው የገባውን ምሁር ይለቅሙ ጀመር ጊዜው ስላልነበር እንጂ ለምሁራኖቹ የተዘጋጁ ነፍሰ በላዎች ነበሩ በትንቅንቁ ፈተና የሆነባቸው ምሁራኖቸቹን ለቅሞ መጣል ነበር
ጠመኔ የያዘ እጅ ዛሬ ስለት ይዞ ነፃነቱን የቀማውን ሰው ይተለትል ጀምሯል በጠመኔ ብናኝ የነጣው እጅ ዛሬ በደም ተጨማልቋል
በብዕር ቀለም ጠቅሶ ስንቱን እንዳልፃፈ ዛሬ በስለት ደም እየጠቀሰ ከመሬት ይጥል ጀምሯል
በጥይት እየተበሳሱ የሚወድቁ ምሁራን እየበዙ መጡ
አልሞ ተኳሾቹ መሳሪያውን ያንጣጡት ጀመር
ይተጋተጉት ገቡ
በጀርባው እየወደቀ በደረቱ እየተሳበ የሞት ትግል ሽረት ማድረጉ አልቆመም
ተኳሾቹ ያልጠበቁት ዱብዳ ስለወረደባቸው የራሳቸውንም ሰዎች ይልጡ ገቡ
ከዘቦቹ የተረፉት ወደ ማማው አመሩ አንዱን ተኳሽ ጉሮሮውን ቀደው ጣሉት
የናጋዚ ሰማይ የጦርነት ሜዳ ሆነ ብዙ ምሁራኖች ከመሬት ወድቀዋል የከፈሉት ውለታ ሳይመለስ በሞት ብድራቸው ተከፍሏል
ሌላኛውን ተኳሽ ዘለው ሰፈሩበት በያዘው ስናይፐር ከአፈር ደባለቁት መፅሀፍ ይዞ እድሜውን የጨረሰ ምሁር ዛሬ ለነፃነቱ ስናይፐሩን ታጥቋል
ከረፈደ የደረሱ ይመስላሉ የሚያቃስት ደምፅ ፊቱ የተተለተለ ለሞት የሚያጣር ድምፅ ከልቡ በገባው ጥይት እስትንፋስ ያቆመ እሬሳ ነጩ አዳራሽ በደም ተሞልቷል 7 ምሁራን ብቻ በህይወት መትረፍ ቻሉ በህይወት ያሉትን ዘቦች ከተኳሾቹ በቀሙት ስናይፐር ወደ ሞት መላክ ጀመሩ 
በፀሎት የተላከው የማምለጫ ስልት ለ7 ሰዎች ብቻ ሰርቷል ከሁሉ በላይ የፀለዩት እነሱ ናቸው መሰል
በደም የተጨማለቀ ሰውነታቸውን ይዘው የተዘጋውን በር በያዙት መሳሪያ እየከፈቱ መውጣት ጀመሩ ከሰባቱ ሰዎች ልጄ ስትል የነበረችው ሴት እግሯን ተመታ በአንድ ወጣት ተደግፋ እያፈገፈገች ነው     ተርፋለች
ዞሮ ማየት የለም የናጋዚ ሰማይ በሞት መልአኮች ተከቧል ወደሱ የገባ አፈፍ እየተደረገ ይወሰዳል
የዘቦቹ ደም ከምሁራኖቹ ደም ጋ ተቀላቅሎ አንድ ነን የሚል ምልክት የሰራ ይመስላል
በጦርነት የተጀመረ ልዩነት በሞት አንድ ሆኗል...

       ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
..........በድሮ ጊዜ አንድ አግኝቶ ያጣ ባለፀጋ ሰውዬ በአገሪቱ አሉ የተባሉ ባለሀብት ሰው ጋር ይሄድና

"ጌታዬ አግኝቼ ያጣው ነኝ፤ በደጉ ዘመን ከቤቴ ምንም ጠፍቶ አያውቅም፡፡ አሁን ክፉ ዘመን መጣና ከነቤተሰቤ የምልሰው የምቀምሰው አጣው ይርዱኝ" አላቸው፡፡

ባለጠጋው ሰውም እውነት አግኝተክ ያጣህ ከሆነ ይሄን ጥያቄ መልስ "ከዶሮ ብልቶች የሚጣፍጠው የቱ ነው?" አሉት፡፡

ነዳያኑም "ቆዳዋ" አለ፡፡

ባለጠጋውም "እውነትም አግኝተክ ያጣክ ነህ፤ በሉ ከእህሉ ስፈሩለት፤ ከከብቶቹም የሚበቃውን ያህል ስጡት ብሎ አሰናበተው፡፡

ይህ ሰው ወደ ቀየው ሲመለስ አንድ ወዳጁ ይሄን ሁላ ሀብት ከየት እንዳገኘ ይጠይቀዋል፡፡ ተመፅዋቹም ሁሉን ነገር ነገረው፡፡ ከዛ ባልንጀራው እንደሱ ሀብት ለመቀበል ወደ ባለጠጋው ሰው ሄደ፡፡

እዛም እንደደረሰ "ጌታዬ አግኝቼ ያጣው ነኝ፤ በደጉ ዘመን ከቤቴ ምንም ጠፍቶ አያውቅም፡፡ አሁን ክፉ ዘመን መጣና ከነቤተሰቤ የምልሰው የምቀምሰው አጣው ይርዱኝ" አላቸው፡፡


ባለጠጋው ሰውም እውነት አግኝተክ ያጣህ ከሆነ ይሄን ጥያቄ መልስ "ከበሬ ብልቶች የሚጣፍጠው የቱ ነው?" አሉት፡፡

ነዳያኑም "ቆዳው" አለ፡፡

ባለጠጋውም አንተ አጭበርባሪ ነክ ብሎ በባዶ ሰደደው፡፡

የፈለገ ብንቸገር መዋሸት ግን አይሆኑ ውድቀት ላይ ይጥለናል፡፡
#ሰናይ_ቀን_ና_ሌሊት
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
ፍርፋሪ ታሪክ
¤¤¤¤¤¤¤
"ከጅምሩ ማን ፍጠር አለህ እንዲህ ያለ ነገር?ይሄ ነው ፍርድህ? ዛሬስ አትወርድም፣አትጽፍም ከግንባሩ ላይ ኃጢያቱን የሚያጽፍ ድፍን የቆዬ ጎረምሳ ተሰልፏል..."
"ተው አርዮስ! ተው! ከፈጣሪ አትጋፋ!...አዋቂ ነው...ተው"
"ድንቄም አዋቂ! ሲታወቅ እንዲህ ከሆነ እውቀት በአፍንጫዬ ይውጣ።አይገርምህም!"
"ለአንዲት ጋለሞታ ፈጣሪህን...ትክዳለህን!"

"ጋለሞታ? ጋለሞታ አልህ?...የት አየህ ስትዘሙት?...የት?...አዘሟች ከሌለ ዘማዊት ትፈጠር ይመስል።እንደወይራ፣እንደቀጋ አትበቅል ዘማዊት..."
"ይወራል።...ድፍን መቂ እሱኑ ነው የሚያወራው"
"እና አመንህ አንተ?"
"ምን አማራጭ ይኖራል? ሰው ተኩኖ።...ሁሉ አምኗል እኔ ማነኝና ሰው ያመነውን አላምን የምለው?"
"አልገባኝም?"
"አይገባህም።አንተ ብቻ ከሰው፣ከቀየው ተነጥለህ፣ለዘማዊት ሴት ጥብቅና የሚያስቆምህ ነገር።ብቻህን ከአድባር ትጋጫለህ?...ሴት ጠፋ?ከሸርሙጣ?"
"ዝም በል አንተ!!...ምፅዋ ሸርሙጣ አይደለችም።"
"ነች!"
"አይደለችም! ምፅዋ ሸ...ር...ሙ...ጣ... አይደለችም!! ትሰማኛለህ...አንተ ካላባለግኃት አንዲት ምስኪን ሯጭ ከመሬት ተነስታ ሸርሙጣ አትሆንም።"
"ትጠረጥረኛለህ?"
"አላምንህም"
"አሕመድንስ ትጠረጥራለህ? ከእርሳቸው አፍ ነው ቀድሜ የሰማሁት።"
"እሳቸው ቅዱስ ገብርኤል ናቸው? የማልጠረጥራቸው?"
"እና እርሳቸውንም ጠርጥረህ?"
"እንክት! ምፅዋዬ እኮ ናት!"
"በል ወግድልኝ ልሂድበት መንገዴን!እውነትም አሪወስ!...ያሳደጉህ የእናትህ ጡትሽ ሳይሆን ስምህ እንደሆነ ገና ዛሬ ገባኝ!"
"የምን መንገድ?...የሰው መንገድ አበላሽቶ ...ወዴት?"
"የማን መንገድ ተበላሸ? አንተ ኩሩሩ ወግድልኝ!"
"የምፅዋ።የምስኪኗ...በወሬ ገፍታችሁ የጣላችኋት።...ህልሟ መንገዷ አልነበረም? እ!"
"የምን ህልም አላት ደግሞ ሸርሙጣ? ምን ትሰራበታለች ቢኖራትስ?"
"አንተም አለህ አይደል፤አይደል እሷ? ሯጭ ነበረች ታውቃለህ።... አቦ ሸማኔ የሚያሳድድ ፍጥነት ነበራት።...የጥንቸል ሳንባ ምታስተፋ ነበረች ይህን አንተም ታውቃለህ....ምን ያረጋል!"
"ጋለሞቶች።"
"አልገለሞተችም።....አንተ ውሻ እንዳልዘነጥልህ በዚህ ከዘራ!"
"ኧረ በህግ...በህግ አምላክ!...ምን ታረግበት ነው እሱ...ኧረ ኡ!...ኡ!...ኧረ በህግ!..."
"ልጄን!...አይኔን!...በማህፀኗ...እንደያዘች...አስኮበለላችኋት...ምፅዋዬን አሸሻችኋት"
"ተው አሪዎስ!...ተው አንተ ከሐዲ!...ባለውለታህን?"
"የት ብዬ ልፈልጋት እሺ አሁን?...ንገረኝ!...እ!..."
"እንካ ቅመስ ይችን ለምፅዋዬ!!...እ!...ይህችን ደግሞ በማህፀኗ ይዛ ለተሰደደችው ልጄ...እንካ!!"
"ኡ!...ኡ!...ኡ!...ኧረ የሰው ያለህ!!!"
"የት ብዬ ነው የምፈልጋት አሁን?...እ!...ምፅዋዬ...የበኩር ልጄን እናት?"
*
*
*
*
*
*
ዘንባባ
©ምግባር ሲራጅ
ከገፅ 133-134
©ከጥበብ ማረፊያ የቴሌግራም ገፅ
@wegoch
@wegoch
'' ስለ ኀዳር በሽታ ''
(የሐያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ከተሠኘው እና መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ እንደፃፉት)


@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

   ክፍል - ፭

ከሞት መንጋጋ ጫፍ ያመለጡት ምሁራን እያፈገፈጉ ነው
ሞትን ሰላም ብለውት ሊያቅፋቸው ሲል ነው ለትንሽ ያመለጡት በእውቀት ከድህነት ከላዋቂነት ጋር ይፋጁ የነበሩ ዛሬ ለነፃት ተዋግተው በእድል ተርፈዋል
ከሞት ለአንድ ስንዝር ታክል አምልጠው ወተዋል
የሳምንታቱ ሱባኤ ለሰባቱ ሰዎች ብቻ ነው የሰራው ሌሎቹ መሰዋትነትን ተቀብለው አልፈዋል
በናጋዚ ሰማይ ትተዋቸው በሞት የተለዩአቸውን ጓዶቻቸውን እያሰቡ ማምለጡን ተያይዘውታል
ለምን የሚለው ጥያቄ ሙታኖቹንም ጨምሮ ሰባቱ ሰዎችን አንድ ያደረገ ጥያቄ ሆኑአል
ወደ ሗላ ማየት የለም
 ቁስለኛዋን በየተራ እየተቀባበሉ ይደግፏታል በጣም ውብ ናት ውበቷም ሳይሆን አይቀርም እንዲ እንዲሳሱላት ያደረገው
የሷ ቁስል ከሁሉም ባሰ እንጂ ፊቱ የበለዘ አፍንጫው በዘቦቹ ቡጢ የተሰበረ
ጥርሱ የወለቀ ሰውነቱ የተገሸለጠ አለ
አይዟችሁ እንደርሳለን የአንድ ሰው ድምፅ ብቻ ነው ሚሰማው
ማን የት ከየት ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም ከመካከላቸው በእድሜ ከሁሉም ሚበልጡ ሰው መንገዱን ያወቁት ይመስላል በራስ መተማመናቸው ለሁሉም ደስታ ፈጥሯል
ወደ የት እንደሚሄዱ በአባ ተስፋ ስላሴ መሪነት ይነገራቸዋል
አባ ተስፋ ስላሴ በኢትዮጵያ ታዋቂ ሊቅ ናቸው በታሪክ በስነ ፈለገ ትልቅ ቦታ ይሰጣቸዋል ወደ ናጋዚ ሲገቡ አስኬማቸው በዘቦቹ ወድቆ አሁን የክህነት ስልጣናቸውን ለጊዜውም ቢሆን አተዋል
ሁለቱ ወንድማማቾች ዶክተር ናትናኤል ታምሩ እና ደራሲ ዮቶር ታምሩ ከ7 እደለኞች መካከል ናቸው
እግሯን በጥይት ተመታ ደሟን እያዘራች ምታፈገፍገው ፊያሜታ አብርሀም ትባላለች ሚስጥራዊ ምልክቶችን ፈቺ እና ሰአሊ ናት
ጥበበኛው ሰአሊ ስምኦን ካሳሁንም ሰባቱን ተቀላቅሏል የኮምፒውተር ባለሙያው ቢንያም ቃኘው ስር ስራቸውን እየተከተለ ነው
ሁሉም ይተዋወቃሉ በተለያዩ መድረኮች የጥበብ ዝግጅቶች የስነ ፅሁፍ ምሽቶች የስዕል አውደርዮች ላይ ተገናኝተው ያውቃሉ ለዛም ነው እርስ በእርስ በመተማመን በጋራ ማምለጡን የተያያዙት
ከሰባቱ ሰዎች የማይታወቅ አንድ ሰው አለ ሁሉም እርስ በእርስ ይተዋወቃሉ ይሄን ሰው ግን አያውቁትም ኤልያስ ሽመልስ ይባላል በአዲስ አበባ ብዙ ባንኮችንና ድርጅቶችን በመዝረፍ ይታወቃል ስሙን መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጆሮ አስገብቶታል መልኩን ግን ማንም አያውቀውም
እርሱም ማን ይሁኑ ማን ለምን ከነሱ ጋር አብሮ እንደሚሮጥ እራሱ አያውቀውም
እሩጫው ቀጥሏል ማፈግፈጉ አይሏል
ድካም ውሀ ጥም እረሀብ ...
ሞት ሁሉን ያስረሳቸው ይመስል ምንም ነገር አይሰማቸውም
አባ ተስፋ ስላሴ ከፊት ሆነው ይመራሉ ስድስቱ እድለኞች ይከተላሉ
ካገኙት ወንዝ ውሀ እየተጎነጩ ሳር ቅጠሉን እየበሉ ከሶስት ቀን በሁዋላ ጉዞአቸው ተገታ
ደርሰናል አሉ አባ ተስፋ ስላሴ ማምለጡ ማቆሙንና ዋስታና ያለው ቦታ እንደ ደረሱ ከፊታቸው እየተነበበ
በቆርቆሮ ከታጠረው ጊቢ ውስጥ አንዲት የቆጥ ቤት ትታያለች  ነው ምትታየው
የከብቶች ጩኸት የወፎች ዝማሬ የኩሬ መንፎልፎሎች ብቻ ነው ሚሰማው
ሶስት ቀን ሙሉ በዝምታ ነው ያሳለፉት
አባ ቀድመው ወደ በሩ አመሩ አንዲት ትንሽዬ ልጅ መታ በሩን ከፈተችው የይግቡ ፈገግታ ከፊቷ እየተነበበ
ሁሉም ወደ ግቢው ዘለቁ
ከግቢው ካለው የቆጥ ባሻገር ወደ አምስት የሚጠጉ ቤቶች በግቢው ውስጥ አሉ ከአንደኛው ቤት ሁሉም ተከተቱ
ቁስለኛዋን ከመደብ አስተኟት አባ ለቁስለኛዋ እርዳታ ማድረጊያ ብዙ መሰርያዎችን ይዘው መጡ
ዶክተር ናትናኤል ስራውን በአግባቡ ሰራ ከቁስለኛዋ ባሻገር የራሱን ቁስል ጨምሮ የሁሉንም ቁስሎች አከማቸው
ማምለጣቸውን ሲያረጋግጡ ረሀቡ ጠናባቸው
ትኩስ ወተት ከአንባሻ ጋር ቀረበላቸው
ያጣድፉት ጀመር ቁስለኛዋን ኤልያስ እየመገባት ነው
ትኩረት ሁሉ ወደ አዲሱ ሰው ነው
ስምህን ማን ልበል አለ ደራሲ ዮቶር ለአዲሱ ሰው ጥያቄውን ወረወረለት ከረጅም ጊዜ በሁዋላ ወደ ጆሮ የተወረወረች ድምፅ ተሰማ
ኤልያስ ሽመልስ እባላለሁ ......

      ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ወግ ብቻ pinned a voice message
2024/09/24 23:25:42
Back to Top
HTML Embed Code: