Telegram Web Link
#ወግ_ብቻ
.
አያ ሙሌ ቁጭ ካለበት ሱቅ የተጋበዛትን ኮካ ኮላ ለባለሱቁ ትቀመጥልኝ ብሎ ይሰጠዋል። ባለሱቁም ኮካኮላዋን ወደ ሳጥኑ ሳይሆን መደርደሪያ ላይ ያስቀምጣታል።

አያ ሙሌ ከአንድ ወር በላይ ቆይቶ ወደዚህች ሱቅ ሲመለስ ባለሱቁ "አያ ሙሌ አስቀምጥልኝ ያልካት ኮካ ኮላ አለች በማለት ከመደርደሪያው ላይ አንስቶ ይሰጠዋል።

አያ ሙሌ ተገርሞ ብቻ ዝም አላለም። እንዲህ ሲል ነበር የልቡን ምኞት ጭምር የተናገረው:— " ለአንተ ነበር ሃገርን አደራ መስጠት "
.
©ሱራፌል አየለ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
''ሹሮ በአናት'' እና ''የመሬት ጥበት....''
ክፍል ፪

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የተገኘ ፁኹፍ ነዉ
ፀኀፊ :- ኤፍሬም እንዳለ
የፁኹፉ ድምፅ :- ሚኪያስ ልየዉ @Mykeyliyew


@Wegoch
@wegoch
@wegoch
#የሰኔ መቅሰፍቶች

  ክፍል - ፫

ህፃናቱ ከቤተሰቦቻቸው ቀድመው ተነስተዋል ማታ ቃል የተገባላቸውን ስጦታ ከአጎታቸው ለመቀበል በሩን እያንኳኩ ነው
አጎቴ አጎቴ....
በሩን በትናንሾቹ እጆቻቸው ይመታሉ ጉዞው አድክሟቸው ሿ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ነበሩ ፊያሜታ ድንገት ነቅታ በሩን ከፈተችላቸው አክስታቸው ተራ በተራ እያቀፉ ወደ አጎታቸው አልጋ ወጡ ስላልበቃቸው ግማሾቹ አልጋው ይዘው ቆመዋል
ፊንሀስ ተነስቷል እንዳልሰማ ለጥ አውቆ ሊያስጮኻቸው ነው
አጎቴ አጎቴ ተነስ ተነስ በትናንሽ እጆቻቸው ይነቀንቁታል ፊያሜታ በሩን ድግፍ ብላ በስስት አይን ትመለከታቸዋለች ልጅ የመውለድ ጉጉቷ ከሰሞኑ ጨምሯል ፍቅረኛዋን በሚያሳዝን ሁኔታ ነው የተሰናበተችው በዚ እርግማን ምክንያት እሱን ለዘለአለም ልታጣው እንደምትችል አምናለች ባሁኑ ብተርፍ እንኩዋ ሁሌ በአመት አመት ልቡን እየሰበረች ልታሳዝነው አልፈለገችም ለምን እንደራቀችው እንኳ ምክንያቷን ሳትነግረው የተለየችው አግኝታው ፍቅሯን እስከ ጥግ ገልፃለት ከአይኖቿ ሚወርዱትን እንባዎች መቆጣጠር ሲያቅጣት በቅጡ እንኳ አቅፋ ሳትሰናበተው መምጣቷ ክፉኛ ቆጭቷታል መልኩ ጠረኑ ሁሉ ነገሩ ናፍቋታል እውነቱን አስረድታ ሁሉን ብታጫውተው ሁሉም ጥሩ ሊሆን ይችል እንደ ነበረ ስታስብ ህመሙ ይሰማታ ነበር በጣም እንደሚጎዳ አውቃለች
ድንገት ፊንሀስ የለበሰውን ብርድ ልብስ ገልጦ ሲነሳ እሷም ከሀሳቧ ተመለሰች
ቆይ እናንተ ሰው አታስተኙም እንዴ ህፃናቱን እየተላፋ ያስቃቸው ጀመረ
እሺ አሁን ስጦታችን የት አለ አጎቴ ኤፍራታ ጠየቀች ህፃናቱን ምትመራው እሷ ናት ከሷ ቃል ውጪ ማንም ዝንፍ አይልም ይወዷታል ይፈሯታል አንዳንዴም ይጣሏታል
ቆይ እሺ ጠብቁኝ ላምጣላችሁ ፊንሀስ ከአልጋው ወርዶ ቦርሳውን ወደ አስቀመጠበት አመራ ቦርሳውን ከፍቶ በህፃናቱ ቁጥር ያመጣላቸው የብር መስቀል ይዞላቸው ሄደ surprise መስቀሉን እያሳያቸው
ህፃናቱ በጣም ተደሰቱ መኪና ኳስ ሌሎች መጫወቻዎችን ስላላመጣላቸው ምንም ቅር አልተሰኙበትም
እውነተኛ አዋቂዎች ትልቅ ሰዎች ፊያሜታ የመስቀሉ ነገር አዲስ ቢሆንባትም በነሱ ደስታ ግን ተገርማለች
በሉ እሺ ፊንሀስ ለሁሉም ልጆች አንገታቸውን እያዞረ መስቀሉን አደረገላቸው
እናመሰግናለን አጎቴ ሁሉም እኩል በሉ የተባሉ ይመስል አጎታቸውን ጮክ ብለው አመሰገኑት
አንገታቸው ላይ ያለው መስቀል እያዟዟሩ ተመለከቱት #ፊኮል የሚል ፅሁፍ አገኙበት
እንዴ አጎቴ ፊኮል የሚል ነገር ከመስቀሉ ላይ ምን ያደርጋል ከመካከላቸው አንዷ ልጅ ጠየቀች
ሁሉም ስሙን ለማየት ይበልጥ ያዟዙሩት ጀመሩ
ኑ እስቲ እኔጋ ከአልጋው ወርዶ ወደ መሬት ተቀመጠ ከፊቱ ደረደራቸው
አሁን ልብ ብላችሁ ስሙኝ ሁሌ በምትኖሩባት አለም ብዙ ነገሮች ታገኛላችሁ ብዙ ነገሮችን ታጣላችሁ ልክ ወደ ምድር ስትመጡ መጀመሪያ ምታገኙት ቤተሰባችሁን ሁሌም በምድር የእናንተ የመጀመሪያ ስጦታ ቤተሰቦቻችሁ ናቸው ግን ደሞ ሁሌም በዚች ምድር እስከ ዘለአለም አብሯችሁ ሚኖር ነገር ላታገኙ ትችላላችሁ ቤተሰቦቻችሁም ድንገች ትተዋችሁ ሊሄዱ ይችላሉ እዩን እስቲ እኔና ፊያሜታን ከኔ እና ከሷ በቀር ለእኛ ማንም የለንም  እናታችንን አባታችንንም አተናል ይሄ የምድር ህግ ነው ሁሉም ጊዜው ሲደርስ ያልፋል ይሄዳል በተለያየ ምክንያት ሊሆን ይችላል እንጂ
ነገር ግን ሁሌም ማታጡትና ከእናንተ እርቆ የማይሄድ ሁሌ የሚጠብቃችሁ አንድ ነገር አለ እሱም አባታችን እግዚአብሄር ነው አያችሁ እናንተን ለቤተሰቦቻችሁ እንደ ስጦታ ይሰጣችሉዋል እናንተም ከነሱ የቤተሰብ ስጦታ ትሰጣላችሁ ፍቅር ደግነት መልካምነት ሁሉንም በእነሱ ታገኛላችሁ ለቤተሰቦቻችሁ ፍቅር መስጠት ደግሞ እናንተ ምክንያት ትሆናላችሁ ማለት ነው
አያችሁ እግዚአብሄር ድንገት ከእናንተ ነጥሎ ቤተሰቦቻችሁን ቢወስድባችሁ ነገር ግን ቤተሰቦቻችሁን ለእናንተ የሰጣችሁ አምላክ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር አለ ማለት ነው ስለዚህ መከፋት ማዘን ማልቀስ የለባችሁም ሁሌም ቀና ብላችሁ የሰማዩ አባቴ አመሰግንሃለሁ እሺ ልትሉት ይገባል
በመስቀላችሁ ላይ ያለው ፅሁፍ #ፊኮል ይላል ፊኮል ማለት ንግግር አፈ ቃል ትእዛዝ ማለት ነው
ፊኮል ማለት በተዘዋዋሪው እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር ነው ማለት ነው ማለት ነው
ሁሌም አዝናችሁ ዝቅ ስትሉ መስቀላችሁን እዩ ፊኮል ሚለውን ስታነቡ ያኔ እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር እነደሆነ ታስባላችሁ ማለት ነው ለኔ አሁን እህቴ እናንተ እና መቼም የማይለኝ የሰማዩ አባቴ ከእኔ ጋር አለ ስለዚህ ምን እንለዋለን
የሰማዩ አባቴ አመሰግንሃለሁ እሺ አስቲ አንዴ በሉት
የሰማዩ አባቴ አመሰግንሃለሁ እሺ ህፃናቱ ደስ በሚል ድምፃቸው አመሰገኑ
እርግማኑን ስለ ፈራ ወላጆቻቸውን ድንገት ቢያጡ እንኳ ብዙ እንዳያዝኑ የተጠቀመበት መንገድ ነው
የእሱንና የእህቱን እጣ በህፃናቱ ላይ እንዲያድር አልፈለገም
በሉ ተነሱ ቁርስ እንብላ እንጂ ህፃናቱ መስቀሎቻቸውን ለወላጆቻቸው ሊያሳዩ ተፈትልከው ወጡ
ፊንሐስ በእጁ የቀረችውን አንድ መስቀል ለፊያሜታ አሰረላት
ፍርሀቱ ዘልቆ  ተሰማት......

ይቀጥላል....
ብላቴናው በእርግማን ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
........ሁለት ጋብሮቮ ሾፌሮች ጠባብ ድልድይ ላይ ስለተገናኙ አንደኛው መኪናውን ወደኀላ አንቀሳቅሶ ሌላውን ማሳለፍ ሊኖርበት ሆነ። ግን ወደኀላ በመንቀሳቀስ ነዳጅ ማቃጠልን ሁለቱም አልፈቀዱም።

ስለዚህም አንደኛው ቮፌር "አሁን ቁርጡን ሲያውቅ ያሳልፈኝ የለ?" ብሎ ጋዜጣውን ዘርግቶ ማንበብ ጀመረ።

ይኸኔ ሁለተኛው ሾፌር ከመኪናው ወጣና ኮፈኑ ላይ ተንጋሎ ፀሐይ እየሞቀ " የኔ ወንድም ጋዜጣውን አንብበህ ስትጨርስ ታውሰኛለህ?" አለው ይባላል።

በነገራችን ላይ ጋቭሮቦች በአለማችን የሚገኙ ቋጣሪ የሆኑ የሰው ፍጡሮች ናቸው። ከቋጣሪነታቸው የተነሳ በምሽት መፅሀፍ ሲያነቡ አንዱን ገፅ ጨርሰው ወደሌላው ገፅ ሲሻገሩ መብራት እንዳይቆጥር አጥፍተው ነው ሚገልፁት ይባላል።😂
@wegoch
@wegoch
#የሰኔ መቅሰፍቶች

  ክፍል - ፬

ቀኑ ቀኑን እየወለደ የእርግማኑ ወርም ሊገባ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተዋል ፍርሀቱን የለመዱት ቢመስልም የለመዱት ፍርሀት ሌላ ፍርሀት እየወለደ ያስፈራቸዋል
ትንናትም ዛሬም ነገም የቤቱ ልዩ አለሞች ህፃናቱ ናቸው ከፊንሀስና ከፊያሜታ ጋ በጣም ተላምደዋል ምኝታ ቤቱ ወደ ሳሎን ተቀይሮ በሚነጠፈው ትልቅ ፍራሽ ሁሉም አንድ ላይ ይተኛሉ
እፍንፍን ጭንቅንቅ ሲሉ ፍርሀቱ በትንሹም ቢሆን ይቀላቸዋል ሁሉም በአንድነት የሞቀ ጨዋታ ውስጥ ይገባሉ ምንም እንዳልተፈጠረ ሀሴት ይሰማቸዋል
ዛሬም በምሽቱ ሰብሰብ ብለው የተፈላውን ሻይ እየተጎነጩ ብርዱን ከኩባያው በሚወጣው ሙቀት በእጃቸው እየሳቡ የፊንሀስን ጣፈፋጭና ደስ የሚሉ ታሪኮችንና የመጽሐፍ ቅዱስ ወንጌሎችን ይሰማሉ
ህፃናቱ እሰከ ልባቸው ዘልቀው ያዳምጡታል ሁሉን እና እያንዳንዷነን ነገር በፅሞና ይከታተሉታል
ወላጆቹም አብረው ከታሪኮቹ ጋር ይተማሉ ቤቱ በፊንሀስ ሞቅ በህፃናቱ ደመቅ ብሏል
ዛሬም አሰፍስፈው እየጠበቁት ነው ፊንሀስ ዛሬ የሱን ጭንቀት አስወግዶ የነሱንም ጭንቀት ከላያቸው ላይ ለማጥፋት ወስኗል
ልጀምር አይደል አላቸው ያዘጋጀላቸውን መፅሀፍ ቅዱስ እያደላቸው አዎ አጎቴ ሁሉም በአንድ ድምፅ
እሺ ዛሬ ምነግራችሁ በህይወታችን ውስጥ ጭንቀት ስለ ተባለ አደገኛ ነገር ነው
መጽሀፍ ቅዱስ ላይ የተጨነቁ ሰዎች ምን ምን አድርገዋል የሚለውን እናያለን
ግን በመጀመሪያ እናንተ ለምን ትጨነቃላችሁ ህፃናቱን በአይኖቹ እየቃኘ ጠየቃቸው
እኔ ማሚ ካመማት እጨነቃለሁ እኔ ደሞ ትምህርት ቤት ዝቅተኛ ውጤጥ ሳመጣ አባዬ እንዳይቆጣኝ እጨነቃለሁ እኔ ደሞ ካመመኝ እጨነቃለሁ ሁሉም ህፃናት ጭንቀቶቻቸው ከየት እንደሚመጡ ነገሩት
ወላጆች ደሞ በአፋቸው ነግረው ባያስረዱትም ይሄ እርግማን የሚባል ነገር በነሱ ጭንቅላት ውስጥ ትልቅ ቦታ እንዳለው በውስጣቸው ያነበንባሉ
እሺ እስቲ እግዚአብሄር የልቤ ስላለው ስለ ዳዊት ልንገራቼሁ እናንተም ትናንሽ መላእክት የእግዚአብሔር የልቡ ሰዎች ናችሁ እሺ ...
እሺ አጎቴ ህፃናቱ በአንድ ድምፅ
ንጉሥ ዳዊት “ልቤ በየዕለቱ በሐዘን እየተደቆሰ፣ በጭንቀት ተውጬ የምኖረው እስከ መቼ ነውሲል በመዝሙር 13:2 ፅፏል ህፃናቱ በወላጆቻቸው ታግዘው ምዕራፉን ገልጠው አነበቡት
 ታድያ ዳዊት ይህን ሁኔታ እንዲቋቋም የረዳው ምንድን ነው ብለን መጠየቅ አለብን እናንተም ልክ እንደ ዳዊት ሲጨንቃችሁ ምን ማድረግ አለብን ልትሉ ይገባል
ታድያ ዳዊት በጸሎት አማካኝነት የልቡን ለአምላክ ያፈሰሰ ከመሆኑም ሌላ በአምላክ ታማኝ ፍቅር ሙሉ በሙሉ ይተማመን ነበር አያችሁ ዳዊት በጭንቀቱ በፍርሀቱ ጊዜ ሁሌም በአምላኩ ጠባቂነት እና ገደብ የሌለው ፍቅር ይተማመን ስለ ነበረ ጭንቀቱ በሱ አካል ላይ ሀይል እንዳይኖረው ያደርጋል
ሌላው በዳዊት መዝሙር 13:5፤ 62:8 አምላክም የከበደንን ነገር በእሱ ላይ እንድንጥል ጋብዞናል ይላል ዳዊት የጨነቀውን የከበደውን ሁሉ በአምላኩ ላይ ይጥል ነበር ማለት ነው ክንዱ ያልቻለውን መከራ በአምላኩ ረዳትነት ያልፈው ነበር ማለት ነው እናንተም ፍርሀታችሁን ጭንቀታችሁን ለአምላካችሁ መስጠት ለሱ መንገር ነው አለባችሁ ማለት ነው ምክንያቱም ሁሌም ለልጆቹ የሚያስብ አባት ስላለ
መከራና ጭንቀት ከእኛ ፊት ቢቆሙም ሁሌ በአምላክ ረዳትነት ማለፍ እንደምንችል ንጉስ  ዳዊት ይነግረናል
ህፃናቱ ልባቸው ተሞላ ሚነገራቸውን ነገር ሁሉ ይረዱታል
ቁጭ ብለው ፊንሀስን ሚሰሙት ሌሎቹ ሰዎች የሆነ ነገር ገሸሽ ሲልላቸው ታወቀ
ፍርሀቱ በአምላክ ይወገዳል..... እርግማኑስ

                  ይቀጥላል..
    ብላቴናው በእርግማን ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ስለ_ፎቶ
(በእውቀቱ ስዩም)
(ክፍል አንድ)
.
.
ልጅ እያለሁ ፎቶ ብርቅ ነበር ፤ ከእናቴ ጋራ የሆነ ግብዣ እሄዳለሁ፤ የቤት እመቤቲቱ ቡናው እስኪፈላ ከግድግዳው ላይ መስኮት የሚያህል ባለፍሬም ፎቶ መስቀያ አውርዳ በዳንቴል ወልወል አድርጋ ትጋብዘናለች:: በፎቶው ውስጥ ሚስት ጥበብ ቀሚስ ለብሳ ፤ገብረክርስቶስ ጫማ አድርጋ ቁጢጥ ብላ ትታያለች ፤ ባል ሱፉን ግጥም አድርጎ አጠገቧ ቆሞ ይታያል ፤ በሰሌዳው ውስጥ ያለውን ብዙ ቦታ የሚቆጣጠረው የባልና ሚስቱ ፎቶ ነው ፤ ቴምብር የሚያካክሉ የልጆች ፎቶዎች ፍሬሙን ተጠግተው ጣል ጣል ይደረጋሉ ፤ አንዳንዴ እናቴና ጋባዧ ሳያዩኝ መስታውቱን ከፍቼ እበረብራለሁ ፤ ያልተዋጣላቸው ፎቶዎች ከጀርባ ተደብቀው አገኛለሁ፤ በጊዜው ዴሊት ማድረግ እሚባል ነገር ስላልነበረ ያለሽ አማራጭ የከሸፉ ፎቶዎችሽን ሰብስቦ መደበቅ ነው፤ አስራሁለተኛ ክፍል ስደርስ የፎቶ አልበም መጣ፤ ግን በጊዜው የነበሩት አልበሞች ከአምሳ ገፆች በላይ አልነበራቸውም ፤ ከዚያ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሆነው ቦታ፤ ያገለገለ የሰርግ ጥሪ ካርድ ፤ የከሸፈ ሎተሪ እና የመፅሄት ቅዳጅ ይቀመጥበታል ፤የፎቶ አልበም ሲቀርብልን የምናየው በታላቅ ተመስጦ እንደነበር ትዝ ይለኛል ፤ ያኔ የጎረቤት ፎቶ በምናይበት ጥሞና ዛሬ ፊልም የምናይ አይመስለኝም ፤ እያንዳንዱ ፎቶ ደግሞ የራሱ ታሪክ ነበረው፤፤ በከተማችን የነበረው ብቸኛ ፎቶ ቤት እነማይ ፎቶ ቤት ይባላል ፤ የስቱዲዮዋ ባክግራውንድ ሁሌም የዘንባባ ዛፍ ነው፤ ካሜራው የቅየሳ መሳርያ ይመስላል፤ ከጎኑና ከጎኑ ሁለት ትልልቅ ባለ ባርኔጣ አምፕሎች ያጅቡታል፤ አንዱ አምፖል ብቻ የሚለቀው ጨረር ድፍን ጎጃምን ራት ሊያበላ ይችላል፤ ሲመስለኝ ከተማው መብራት ሃይል የለህዝቡ የሚያከፋፍለው ከነማይ ፎቶ ቤት የተረፈውን መብራት ሳይሆን አይቀርም ፤ በጊዜው “ ፊትዎትን በሳሙና በመታጠብ አይንዎን ከትራኮማ ይጠብቁ” የሚል መፈክር በሬድዮ ይነገር ነበር፤ የእነማይ ፎቶ ቤት አምፖል ባጨናበሰው አይን፤ ትራኮማ ተጠያቂ መሆኑ ያሳዝነኛል፤ ብዙ ጊዜ የተነሳነው ፎቶ ለመድረስ በትንሹ አምስት ቀን ይፈጃል፤ ጉጉታችን አይጣል ነበር:: በተለይ ሴቶች የቀጠሮ ቀናቸው እስኪደርስ ድረስ እየተቁነጠነጡ ፎቱዋቸውን ቢያንስ ሁለቴ በህልማቸው ያዩታል፤ ሲኒማ ወደ ከተማው ከመግባቱ በፊት ቅዳሜ ከሰአትን የምናሳልፈው እነማይ ፎቶ ቤት በር ላይ የተለጠፉትን የሳምንቱን ፎቶዎች በማየት ነበር ፤ አልፎሂያጁ የከተማዋ ቆንጆ ሴት የተነሳችውን ፎቶ ከብቦ እያየ “ እዩዋትማ!! እመብርሃንንኮ ነው እምትመስል ” እያለ ያደንቃል ”፤ አንዳንዱ ጎረምሳ በማየትና በማድነቅ ብቻ አይወሰንም፤ ፤ ለፎቶ አንሽው ጉርሻ ሰጥቶ የቆንጆይቱን ፎቶ አጥቦ እንዲሸጥላት ያግባባዋል፤ ከዚያ ፎቶዋን በኪሱ ይዞ በከተማው በመዞር 'ገርሌኮ ' ናት እያለ ጉራውን ይነሰንሳል ፤ ማርክ ዙከርበርግ የሰው ፎቶን Share የማድረግ ሀሳብ የወሰደው ከነማይ ፎቶ ቤት ይሆን
.
@wegoch
@wegoch
@wegoch
#የሰኔ መቅሰፍቶች

  ክፍል - ፭

ፍርሀቱ የቀነሰ ይመስላል ውጥረት ቀንሶ ጭንቀቱንም ለማስወገድ እየሞከሩ ነው ፊንሀስ ትልቅ ነገር በቤተሰቡ ላይ እየሰራ ነው ደረቁ ሳቅ ወደ ለዛ ተሸጋግሯል ህፃናቱ ብሶባቸዋል ቤቱን ደስታ በደስታ እያደረጉት ነው አሁን አሁን እርግማን የተባለ ነገር እየተረሳ ይመስላል በእስከዛሬው የቤተሰቡ ታሪክ እንዲህ ያለ መሰባሰብና ደስታ ታይቶ አይታወቅም እርግማኑ ብዙ አስከፊ ጎኖች ቢኖሩትም ቤተሰቡን አሰባስቦ አንድ ስላደረገ ደስ አሰኝቷቸዋል
በህፃናቱ የማያልቅ ደስታ ወላጆቻቸው ሀሴት ያደርጋሉ ምንም ነገር ላለማሰብና ሁሉን ነገር ለመርሳት እየሞከሩ ነው እርግማኑንም ቢሆን በአንድነት ለማለፍ ተዘጋጅተዋል ወይ አምላክ እራርቶ የህፃናቱ ሳቅ እንዳይቀየር ሲል ይሄን አመት እንዲዘላቸው እየተማፀኑ ነው
ዛሬ ቤቱ ሞቅ ብሏል ምሽቱ ደመቅ ብሏል የህፃናቱ ጨዋታ ብርዱን አስረስቷቸዋል አካባቢያቸው ላይ ምንም ነገር የለም ከእናት እና ከአባታቸው የወረሱት የተንጣለለው መሬት ላይ ያሉባት መካከለኛ ቤት ተሰርታለች አልፎ አልፎ ከሚታዩት ደሳሳ ጎጆዎች በቀር ቀና ሲሉ ሰፊው ሰማይ ዝቅ ሲሉ ቢሄዱበት የማያልቅ ሰፊ መሬት ነው የሚታያቸው
ፍርሀቱን የጨመረባቸው አንዱ ነገርም ይሄ ብቸኝነታቸው ሳይሆን አልቀረም
በምሽቱም አለፍ አለፍ እያሉ ከሚሰሙት የውሾች ድምፅ በቀር ሌላ ምንም የለም ጨዋታው ደርቷል ሳቁ ጦፋል ልዩ ምሽት ሆኖላቸዋል
ህፃናቱ ይዘምራሉ ይታገላሉ በሚኮላተፉት ትናንሽ አፋቸው ተሰምተው የማይታወቁ አስቂኝ ተረቶችን ያወራሉ ቤቱ በነሱና በፊንሀስ አማካኝነት ነፍሰ ተዘርቶበታል ዛሬም አንድ ነገር ሊናገር ድምፁን ጠረግ ጠረግ አደረገ  ውብ ነገሮችን ለማግኘት ፈልጋችሁ ታውቃላችሁ ልጆችዬ የነገዋንስ ፀሀይ ጀንበሯን ጮራዋን ለማየት ተመኝታችሁ ታውቃላችሁ
ሁሌም የሆነ ነገርን ለማግኘት በፈለግን ቁጥር ብዙ ፈተናዎች ከኛ ጋር ይጋጠማሉ ተስፋ ሳንቆርጥ ሁሉን ፈተና ከተጋፋን የወደድነውን ነገር ከማየት የሚያግደን የለም በጨለማው ሰአት የጨረቃን ብርሀን የናፈቀ እስክትወጣ ድረስ ብርዱን ቁሩን ጨለማውን ተቋቁሞ መጠበቅ አለበት
 ውብ ነገሮችን ለማግኘት ሰው ፍርሃቱን አልፎ መሄድ አለበት፤ በምንፈግልጋቸው ነገሮችና በእኛ መካከል የቆመው ትልቁ ግድግዳ ካለማውቅ የሚመነጨው ፍርሃት ነው
ፍርሀታችንን ሁሌም የምናጠፋው ለምን እንፈራለን ብለን መጠየቅ የጀመርን ሰአት ነው
ሁሌም ላሰባችሁት ላለማችሁት ለወደዳችሁት ነገር ወደ ፊት ብቻ
ህፃናቱ እጆቻቸውን ከፍ አርገው ወደ ፊት ሌላ ሳቅ
ፊንሀስ በሩን ከፍቶ ወጣ ቅድም ስለ ብርሀኗ ሲያወራላት የነበረችው ጨረቃ ዛሬ መልኳ ጠፍቶ ደም ለብሳለች
ደሟ ጨረቃ ለዚ ቤተሰብ ትልቅ ምልክት ናት የጭንቁ ቀን መቀራቡን ማብሰሪያ ምልክት
ያየውን ወደ ቤቱ ገብቶ አንሾካሾከ ሙቀቱ በብርዱ ተተካ ሳቁም ጠፍቶ የበፊቱ የቤተሰቡ መልክ ተመለስ
ጨረቃዋ ነገ ወደ ቀድሞ መልኳ ትመለሳለች
ቤተሰቡስ.....

ይቀጥላል...
     ብላቴናው በእርግማን ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ትዝታየ በፎቶ ዙርያ
(የመጨረሻው ክፍል)
( በእውቀቱ ስዩም)
.
በልጅነቴ ትዝ ከሚሉኝ መፈክሮች አንዱ “ ያልሰራ አይብላ” የሚል ነው፤ ስራ ብሄራዊ ሀይማኖት ሆኖ ነበር፤ ይሄ ደግሞ በጊዜው ፎቶ አነሳስ ላይ ሳይቀር ይንፀባረቃል ፤ አንድ ሰው ፎቶ ሲነሳ የሆነ ሰርቶ ማሳያ ነገር ፎቶው ውስጥ ማካተት ነበረበት፤ የቤት እመቤት ከሆነች ጥጥ እየፈተለች ወይም ምስር እየለቀመች ትነሳለች፤ ገበሬ ከሆነ የማሽላ እሸት አንጠልጥሎ ፤ የእንጨት መሰንጠቂያ ያለው ወጣት ደግሞ የሰራውን ቁምሳጥን ተሸክሞ ይነሳል ፤ አንድ ቀን ከአባቴ ጋር ፖሊስ ጎረቤታችን ቤት ሄድን:: በቤቱ ግድግዳ ላይ አራት ሰዎች ጎን ለጎን ቆመው የሚታዩበት ትልቅ ባለፍሬም የፎቶ መስታወት ተሰቅሏል:: “ ሽጉጥ ታጥቀህ የቆምከው አንተ ነህ ፤ቀሪዎች ወንድሞችህ ናቸው ልበል ?” ሲል ጠየቀ አባየ፤
“ አይደሉም! “ አለ ሰውየው” ይሄኛው ለመጀመርያ ጊዜ እጄ ላይ የወደቀው ሌባ ሲሆን እኒህ ደሞ ምስክሮች ናቸው ” በጊዜው ሰርቶ ማሳያም ሆነ ሰሮ ማሳያ የሌለን ልጆች ግን እጃችንን አንከፍርረን እንነሳለን፤ ከፎቶ መነሳት ውስጥ በጣም ከባዱ የእጅ ማስቀመጫ ማግኘት ነበር ፤ በተለይ ትምርት ቤት ውስጥ በቡድን በቡድን ስንነሳ- የነበረብን አበሳ- አይነሳ ! እጅህን ብድግ አድርገህ አጠገብህ የቆመቺው ልጅ ተከሻ ላይ ስታስቀምጠው አመናጭቃ ትወረውርብሃለች ፤ እጆችህን በወገብህ ላይ ብታስቀምጥ" ምነው ጠላ የቀጠነባት ኮማሪት መሰልህ" ይልሀል ፎቶ አንሺው፤ አሳርፍ በሚባለው ፈሊጥ ቆመህ ብትዘጋጅ “ እጅህ ቁርጭምጭሚትህ ላይ ደረሰኮ ፤ የጭላዳ ዝርያ አለብህ? ብሎ ያሸማቅቅሀል፤ እጅህን አገጭህ ስር ብታስደግፈው “ አቡሽ! አለሎውን እስክትወረውረው በጉጉት እየጠበቅንህ ነው” ብሎ ያላግጥብሀል፤ ያለህ አማራጭ እጅህን ኪስህ ውስጥ መክተት ነው፤ችግሩ እኛ የደሃ ልጆች የምንለብሰው ሱሪ ኪስ አልነበረውም፤ “ ሽልንግና ፀባይ ካለህ ከኮሌታህ ላይ ቀንሼ ኪስ ልስፋልህ እችላለሁ” ብሎኝ ነበር የመንደራችን መኪና ሰፊ፤ እኔ ደግሞ ከሁለቱ አንዱ አልነበረኝም፤አንዳንዴ ከስማርት ስልክ በፊት የነበረውን ህይወት ስታስቡት ይገርማል፤ እንደዛሬ ካሜራ በኪሳችን ይዘን ከመዞራችን በፊት ከምናደንቃቸው ዝነኞች ጋር ፎቶ የምንነሳው እንዴት ነበር? ፤ ሙሉቀን መለሰ ዝንጥ ብሎ ስታዲየም አካባቢ ሲናፈስ ታገኝዋለሽ እንበል ፤
“ ወይኔ ሙሌ እንዴት እኮ እንደማደንቅህ”
“ አመሰግናለሁ የኔ ቆንጆ"
“ ካላስቸገርኩህ ፒያሳ ፎቶ ቤት ሄደን ለማስታወሻ የሚሆን ፎቶ እንነሳ?”
ሙሉቀን መለሰ ዘፈኑን ትቶ ዘማሪ የሆነው እንዲህ አይነት ውጣ ውረድ አጋጥሞት ይመስለኛል፤ በነገራችን ላይ ፤በአዲሳባ ከተማ ውስጥ የመጀመርያውን ፎቶ ቤት የከፈተው የማንኩሳ ሰው ነው ፤ መቼም አታምኑኝም፤ ግን አንዴ ጀምሬዋለሁና ልቀጥል ፤ ጎሹ ይባላል፤ ማንኩሴው ከመላው ምስራቅ አፍሪካ የመጀመርያው የካሜራ ጥበብ ባለቤት እንዴት ሆነ እሚለውን አንድ ቀን እተርከዋለሁ :: አዲስአበባ ውስጥ አንድ አርመን የቡልዶዘርና የአውቶብስ ቅልቅል የሚመስል ባቡር ሰርቶ ነበር :: በምርቃቱ ላይ ተገኝቶ ባቡሩን አምስት ፎቶ እንዲያነሳው ለጎሹ ጥሪ ቀረበለት! ጎሹነት ጥሪውን ተቀብሎ አዲሳባ ሲገባ በጊዜው የነበሩት ከንቲባ ሃያ ጊዜ መድፍ አስተኩሰው ተቀበሉት፤ብቻ ስራውን ለመስራት ቀላል ሆኖ አላገኘውም፤ የከተማው ህዝብ በካሜራው ውስጥ ለመግባት ካለው ጉጉት የተነሳ ግልብጥ ብሎ ባቡሩ ጀርባ ላይ ወጣ ፤ ከዚያስ? ትሉኝ ይሆናል ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አካባቢው “ሰባራ ባቡር "ተብሎ ይጠራል፤

@wegoch
@wegoch
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew Tadesse)
እንደምን አደራቹ?

በአካባቢያችን ላይ እንዲኹም በእንቅስቃሴዎቻችን መኻከል ምናገኛቸዉ ''መስማት የተሳናቸዉ'' ሰዎች ምን ያህል ሊነግሩን 'ሚፈልጒትን ነገር እንረዳቸኋለን?

መልካም ቀን!
ግንቦት/ 2012
ሚኪያስ ልየው/Mikiyas Liyew


@Mykeyonthestreet
#ወግ_ብቻ
.
እ ግ ር በ እ ግ ር
አሌክስ አብርሃም

ክፍል - ፩ -

አንድ ቀን ሰይጣን በመንደሩ ወደሚፈሩትና ወደሚከበሩት አስር አለቃ ደባልቄ ግዛው ቤት ሄደና ተቀዳሚም ተከታይም ሳያደርግ፣ "ደባልቄ!!" ብሎ በስማቸው ጠራቸው።

አስር አለቃ ፊታቸውን በቁጣና በግርምት አኮማትረው ድምፁን ወደሰሙበት ዞር ቢሉ በአካባቢው ሰው የሚባል የለም። እዚህ ሰፈር አንድም ሰው የአስር አለቅነት ማዕረጋቸውን ሳያስቀድም፣ የአባታቸውን ስም ሳያስከትል እንዲህ ንፋስ እንዳነሳው ፌስታል ስማቸውን ለብቻው አንጠልጥሎ የሚያነሳ ሰው የለም። እንኳን ሰው የዚህ ሰፈር ሰይጣን ቢሆን ራሱ እንደዚህ አስር አለቃን አቃሎ እና አበሻቅጦ ይጠራቸዋል ተብሎ አይታሰብም። እንዴት ሆኖ! ምን ሲደረግ...!

እንግዲህ አስር አለቃ የተጣሉ ባልና ሚስት አስታርቀው ገና መመለሳቸው ነበር። ልክ በራቸው ላይ ሲደርሱ ነው ሰይጣን የጠራቸው። ምን ይጠራቸዋል፣ ያዋረዳቸው እንጂ! ቢሆንም 'ጆሮዬ ነው' ብለው ወደ ቤታቸው ግቢ ሊገቡ ርምጃ ሲጀምሩ፣

"አንተ ደባልቄ! የሚደባልቅ ይደባልቅህ! ሲጠሩህ አትሰማም!? ደንቆሮ!!" ብሏቸው እርፍ። በዚህ ቢበቃማ ጥሩ ነበር፣
"ምን ያሯሩጥኻል? ያች መንሽ እግር ሚስትህ እንደሆነች የትም አትሄድብህ፤ ተወዝፋ ነው የምትጠብቅህ" ሲል ዘለፋቸው።
አስር አለቃ መጀመሪያ በተናጋሪው ድፍረት ግርርርርርርርርርርም አላቸው፤ ቀጥሎ የንግግሩ ትርጉም አዕምሯቸው ውስጥ ሲተረጎም ደማቸው ፈላ። ላለፉት አርባ ዓመታት እንዲህ ተንቀውም፣ እንዲህ ደማቸው ፈልቶም አያውቅም። ከዘራቸውን ጠበቅ አድርገው ጨበጡና ድምፁን ወደሰሙበት ፎክረው ዞሩ።

"ያንበሳው ግልገል!" በአካባቢው የሰው ዘር የለም!!
"እንኳን ፊቴ ያላገኘሁት፤ ደመ-ከልብ አድርጌው ዘብጥያ መውረዴ ነበር።" አሉና ከዘራቸውን ወደ ግራ እጃቸው አጋብተው ከዘራ በያዙበት እጃቸው አማተቡ።

"ሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂ ... " የሰይጣን የሚያበሳጭ እና የሚሰቀጥጥ ሳቅ ጆሯቸው ስር ተቅጨለጨለ...

"ድሮም ከእግዜራችሁ በፊት ዱላችሁ ነው ትዝ የሚላችሁ... ነውጠኛ ሁሉ፤... የምትዠልጠው ስታጣ ታማትባለህ? አይ ሸፋፋው አስር አለቃ ... ሂሂሂሂሂ ሁሁሁሁ ቂቂቂቂቂቂ..." አለ ሰይጣን ቀድሟቸው ግቢያቸው ውስጥ ገብቶ ከጀርባቸው ከቆመ በኋላ። አስር አለቃ ግራ ተጋቡ። ንዴታቸውን ዋጥ አድርገው እየተጣደፉ በቁጣ ወደቤታቸው በር ገሰገሱ።
. . . . .
( ይቀጥላል
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
እ ግ ር በ እ ግ ር
.
ክፍል - ፪ -
.
አሌክስ አብርሃም
. . .
አስር አለቃ አቋማቸው እንደ ሰምበሌጥ ቀጥ ያለ ስፖርተኛ አቋም ነው፤ ሰው ሁሉ "አቤት ቁመና!!" ይላቸዋል። ሰይጣን ግን ወደ ቤታቸው ሲጣደፉ በሚያበሽቅ ንግግር፣
"ሸፋፋ ... ሸፈፍ ሸፈፍ ትላለህ! ሲራመዱ አይተህ... ደግሞ ወታደር ነኝ ይላል እንዴ? ይሄን ደጋን የመሰለ እግር ይዞ...፣ ሂሂሂሂሂሂሂ... እንኳን አገር ልትጠብቅ፣ በዚህ ሸፋፋ እግርህ ሚስትህንም አትጠብቅ፤... ተመልከት የእግርህን ክፍተት፤ በልጅነትህ ፀሐይ አላሞቀችህም ያች ጨብራራ እናትህ!! ኪኪኪኪኪኪ..."
አስር አለቃ ከሳቸው አልፎ እናታቸውን ማዋረዱ ቢያንገበግባቸውም የተናጋሪው ማንነት ስለገባቸው እንደገና አማተቡና፣

"የማርያምን ብቅል ፈጭቻለሁ! ቱ! ቱ! አንተ ፖለቲከኛ ሰይጣን!" ብለው አንዴ ወደ መሬት፣ አንዴ ወደ ሰማይ ትፍ! ትፍ! ቀጠል አድርገውም፣ "አንተ ክፉ አውቄኻለሁ፤ እንዲህ አቅልሎ የሚጠራኝ እንዳንተ ያለው ቀላል እንጂ ሌላ እንደማይሆን መች አጣሁት?" ካሉ በኋላ፣ ቆይ ላግኝህ በሚመስል ዛቻ ከዘራቸውን ነቀነቁና ነጠቅ ነጠቅ ብለው በመራመድ ወደ ቤታቸው ገቡ።

ሰይጣንም አጀንዳውን ከፍቶ፣ "አስር አለቃ ደባልቄ" በሚለው ፊት ለፊት በቀይ እስክርቢቶ 'ራይት' አደረገ። መንገዱንም ቀጠለ! እየሳቀ እና እያፏጨ...!
"ይሄ ሸፋፋ ለዛሬ ይበቃዋል ሲበሳጭ ይደር። ነገ ደሞ በተመቸኝ ሰዓት ብቅ ብዬ ነጅሸው እሄዳለሁ።" አለና እየሳቀ መንገዱን ቀጠለ። ከአስር አለቃ ቤት ግራና ቀኝ ባሉት ጫት ቤቶች ታኮልኩለው ጫት የሚቅሙትን ወጣቶች በኩራት እየተመለከተ፣
"ርስቴ እየተስፋፋ ነው!" ብሎ እየኮራ ቁልቁል ወደ ወንዙ!

፨ ፨ ፨

በእርግጥም ሰይጣን እንዳሰበው አስር አለቃ ሌሊቱን እንቅልፍ በዓይናቸው ሳይዞር ነበር ያደረው። እንደዛ ያበሻቀጣቸው ሰይጣን ነው ለማለት ጥርጣሬ ገባቸው፣
"እኔ የትኛው ቅድስና ኖሮኝ ሊፈትነኝ ይመጣል?" አሉ ለራሳቸው። እንደውም አንዱ ጎረቤታቸው ተደብቆ እንደሰደባቸው ጠረጠሩ። "ማን ሊሆን ይችላል?" ሌሊቱን ሙሉ ተብሰለሰሉ።

"ይች ጎረቤቴ የትነበርሽ ትሆን እንዴ? የለም ድምፁ የወንድ ነው። ግንበኛው አሰፋ መሆን አለበት፤ እሱ ለካ ለሥራ ክፍለ ሀገር ከሄደ ሁለት ወሩ፣ ...እና ማናባቱ ነው...።" ወደ ንጋቱ ላይ አንድ ሐሳብ ብልጭ አለላቸው። አረጋ!! ድንበር እየገፋ የበጠበጣቸው ጎረቤታቸው! አረጋ! ኧረ እሱስ ሚስታቸውንም በምኞት ዓይኑ የሚቃኝ ጥጋበኛ ነው፤ ድምፁም መጣላቸው፤ ራሱ ነው!

"አገኘሁት" ብለው ዘለው ከአልጋቸው ተነሱ።
. . . . .
(ይቀጥላል)
@wegoch
@wegoch
@wegoch
👆👆👆👆
አጭር፣አስተማሪና አዝናኝ ወግ ናት።

ምንጭ
ደራሲ አሌክስ አብርሀም
ከ "ዙቤይዳ " መፅሐፍ
ገፅ 201 የተወሰደ
ርዕስ ፡-"እግር በእግር"
ተራኪ፡-ስንታየሁ አዲሱ ሳንታ

(@san2w)
10/5/2011 Woldia Yniversity

@wegoch
@wegoch
አውራጅ
(ቡሩክ ካሳሁን)
ጥንት…ከጥቂት አመታት በፊት አያቶቻችን ከገበያ እቃ ጠልጠል አድርገው ሲመጡ ተሯሩጦ ተቀብሎ መመረቅ ወግ ነበር፡፡ እንደው ከበድ ያለ እቃ ገዝተው አልያም ቤት ቀይረው ከሆነ ተባብሮ አግዞ “እቺን ያዙ” (ያው ለወጉ ነው) ሲባል ኸረ ግዴለም ተብሎ፤ ውስጥ እየፈለገም ቢሆን በአፍ ተፎጋግሮ፤ “በቃ እንደዚያ ከሆነ ቤት ያፈራውን ቅመሱ” ብለው እቤት አስገብተው ጋብዘው መሸኘት ልማድ ነበር፡፡ ‹‹ነበር ለካ እንደዚ ቅርብ ነው›› አሉ፤ አሉ የአባይ ግድብን በ5 ዓመት እንጨርሰዋለን ብላቹ ነበር ተብለው ከ7 አመት በኋላ የተጠየቁት የሜቴክ ሹማምንት፡፡ ወደቀደመው ነገራችን ስንመለስ ያ ወግ ልማዳችን ሞቷል ብቻ ሳይሆን ግብዓተ መሬቱ ራሱ የት እንደተፈፀመ እንኳን ያየ ሰማሁ የሚል ሰው በከተማው(አ.አ) የለም፡፡ የኔ ጌታ ዘንድሮ ሶፋ ገዝቼ እቤቴ አስገባለው፤ እንደው ቁምሳጥን ነገር ብገዛ ብለህ ካሰብክ “ብሰርቅ” ብሎ እንዳሰበ ሰው በሌሊት ወጥተህ፣ በሌሊት ገዝተህ፣ በሌሊት ማስገባት ይኖርብሀል፡፡ እንቢ ብለህ ቀይ መስመሯን አልፈህ በቀን ገዝተህ የመጣህ እንደሆነ ግን 3ሺ ብር ለገዛኸው ቁምሳጥ 4ሺ ብር ማውረጃ ተጠይቀህ፤ ልብስ አስቀምጥበታለው ያልከው ሳጥን ደም ግፊትህ ገንፍሎ መቀበሪያህ ነው የሚሆንልህ፡፡ ችግሩ ደግሞ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ የምታውቀው፤ ሰፈር ውስጥ በስራ እጦት ተስፋ የቆረጡ ወጠምሾች መጥተው ለሚተምኑልህ ዋጋ ድርድሩን በዲፐሎማሲያዊ መንገድ ለማድረግ ‹‹ወገን እስኪ መጀመሪያ 30 ፑሽ አፕ እንወረድና ነገሩን በተረጋጋ ህሊና እንመርምረው›› ስትላቸው ‹በል ተነስ እዛው ወገብህን ረግጬህ ተሳቢ እንስሳ እንዳላረግህ› ብሎ አንዱ ያፈጥብሀል፡፡ የነገሩን አዝማሚያ አይተህ ‹‹ሀቅ ነው! የእናንተ ጉልበት 4ሺ ያወጣል ግን የኔ ቁምሳጥን 3ሺ ብቻ ስለሚያወጣ እኔው እራሴ ቁምሳጥኔን አስገባለው›› ብለህ አስታራቂ ሀሳብ ብታቀርብ ያቀረብከው አስታራቂ ሀሳብ እነሱ ጆሮ ጋር ሲደርስ አተናናቂ ይሆንና 32 እጆች በድንገት አንገትህ ላይ ሲያርፉ የአንዱ እጅ የአንዱን ጣት ይሰብርና ዋጋውን አስተካክለው 14ሺ ብር እንዳይጠይቁህ ፈርተህ ‹‹በቃ ዋጋ አስተካክሉልኝ ሚስቴ እርጉዝ ናት›› ስትላቸው ‹በእውነት?› ብለው ሲጠይቁህ፤ ሊምሩኝ ነው ብለህ ሰፍ ብለህ ‹‹በእወነት..ገብርኤልን…ሚካኤል…›› እያልክ መሀላ ስትደረድር ‹እና የታለች› ይልሀል አንዱ፤ ቀልጠፍ ብለህ አንተም ‹ያው መኪና ውስጥ ናት› ስትላቸው ‹በቃ እሷንም እኛ ነን ምናወርዳት፤ እሷን በአስተያየት 2ሺ እናወርድልሀለን› ብለውህ ደም ግፊትና ደም ማነስ በእኩል ሰዓት ታስተናግዳለህ፡፡ በጣም በጣም ሚያሳዝነው ደግሞ ፀጥታ እና ሰላም እንዲያስጠብቁ ሀላፊነት ያለባቸው የመንግስ አካላት ለዚህ አይነት ጋጠወጥነት መፍትሄ መስጠት አለመቻላቸው ነው፡፡ ‹‹እንዴዴዴ… መንግስት ባለበት ሀገር በጠራራ ፀሀይ ማጅራታችንን እንመታ እንዴ…›› እያልክ እየጦፍክ ፖሊስ ጣቢያ ሄደህ ለአንዱ ፖሊስ ስትነግረው፤ ‹ቆይ ስንት ብለውህ ነው?› ሲል ይጠይቅሀል ‹‹አይገርምህም 4ሺ አላሉኝም መሰለህ›› ስትለው ‹የኔ ጌታ እታች ሰፈር 6ሺ ነው ሚያወርዱት እነሱም መጥተው ተደምረው 10ሺ ብር ሳይጠይቁህ ቶሎ አስወርድ ሂድና› ብሎ የምክር አገልግሎት ይሰጥሀል፡፡ ‹‹እንደዚማ አይደረግም ለበላይ ክፍል አመለክታለው›› ብለህ ከቢሮው ተንደርድረህ ልትወጣ ስትል ‹ወዳጄ እንኳን አንተ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከቤተመንግስት ወጥተው ቤት ሲቀይሩ ለማን አቤት እንደሚሉ ቸግሯቸው በ8ሺ ደሞዛቸው 10ሺ ከፍለው ነው እቃቸውን በሰፈሩ ልጆች ያስወረዱት፤ እና አንተ ማነኝ ነው ምትው?› ብሎ የማንነት ጥያቄ ይጠይቅሀል፡፡ ነገሩ ወደ ብሄር ግጭት እያደገ መሄዱን ስትረዳ እቃህን በ4ሺ ብር አስወርደህ የሻይ ትልና 5ሺ ብር ሰጥህ ‹ታዲያ የሻይ ማሽን ግዙበት› ብለህ እንደ አቅሚቲ ኮምከህ ወጠምሾቹን በተቻለ ፍጥነት ከበርህ ላይ ድራሻቸውን ታጠፋዋለህ፡፡
“እኔ እንደውም ማጋነን ስለማልወድ ነው እንጂ…” ብለው እንደሚያጋንኑ ሰዎች የሀሳቤን መጠቅለያ በዚህ ሀረግ ባልጀምርም ይህ አይነቱ ተግባር ግን በተለይ አሁን አሁን እጅግ በጣም እየተበራከተ ስለመጣ መንግስት 4ኪሎ ቤተ መንግስት ገብተው “እኛ ነን የምናወርደው” እስኪሉት ድረስ መጠበቅ ያለበት አይመስለኝ፡፡ መንግስት ሆይ! 4ኪሎ ቤተ-መንግስት ከገቡ ደግሞ በጣም ብዙ የሚወርድ ነገር ስላለ በጊዜ ከሰፈር ብታስታግሳቸው መልካም ነው!!!

ነሀሴ 2011 ዓ.ም


😉      @wegoch
👕👉 @wegoch
👖      @burukassahunc
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (ልዑል)
ሰርጂካል ማስክ

500 እና ከዛ በላይ ለሚገዛ የአንዱ ዋጋ 11 ብር

250ዉን(5ፓክ) ለሚገዛ የአንዱ ዋጋ 13 ብር

150ውን (እስከ 3ፓክ) የአንዱ ዋጋ 15 ብር

ለመግዛት በ +251901927999 ይደውሉ

🛑ብዛት እስከሚፈልጉት ማዘዝ ይቻላል
አድምጡ ለቅዳሚታችኹ
መፅሐፍም ላስተዋውቃችኹ


@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
#የሰኔ መቅሰፍቶች

  ክፍል - ፮

የትናቷ ጨረቃ ከሰማዩ ብጠፋም ከቤተሰቡ አእምሮ ላይ ልጠፋ አልቻለችም ለሀገሩ ነግቷል ለቤተሰቡ ግን ክፉኛ ጨልሟል ከዛሬዋ ጠዋት ጀምሮ ቤተሰቡ አንድ ነገር ይጠባበቃል
ዘንድሮ ከቤተሰቡ አልፎ ለሀገሩም ጭንቅ ነው ሰኔ ሰኞ ሲባል ሁሌም ክፉ እንደሚሆን የሀገሬው ሰው ያውቃል
ይህን የሰኔ ወር ቤተሰቡ ብቻውን አይተክዝም ሀገሬው አብሮ ስለሚጨነቅ ሰኔ ለዚህ ቤተሰብ የምጥ ወር ነው በዘንድሮው ደሞ ችግሩን ሚካፈለው ብዙ ቤተሰብ አግኝቷል
ህፃናቱ በወላጆቻቸው መተከዝ እነሱም ተክዘዋል ዝምታው ይባላል
ወሩን ይወቁ እንጂ ሚመጣባቸውን ነገር አያውቁትም እንቅልፍ የለ ተፋጦ ማደር ሚመገቡትን ምግብ አያምኑትም በእርግማኑ ምክንያት በትንታ ሊሞቱ እንደሚችሉ ያስባሉ
የትናንቷ ጨረቃ ደም ለብሳ በመታየቷ የቤተሰቡን ትንሽ ደስታ ደም አልብሳዋለች
ህፃናቱ ሞክረው ሞክረው አሁን እርስ በራሳቸው ደስታ የሌለበት ጨዋታ ይዘዋል
በሚያዝን አንጀታቸው ለቤተሰቡ እራርተዋል ለምን እንዲህ እንደሆኑ ባይገባቸው
አባዬ እማዬ እናቴ የኔ አባት አቤት በሌለው አቤት ውስጥ ያዘነ ፊቶቻቸውን ይሰዱላቸዋል
ምን ሆንሽ እናቴ ምን ሆነሀል አባቴ ምንም በሚለው መልስ ውስጥ ሞትን መጋፈጥ ፈርተው
ፊንሀስ ምን አለ ጨረቃን ባላያት አይቼስ ባልነግራቸው ኖሮ እያለ ይብሰለሰላል በትንሹም ቢሆን ለቤተሰቡ መልሶት የነበረው ደስታ በሱ በሪሱ ምክንያት ሲንደው ሲያይ በጣም አዘነ
ምንም ቢል ሲያሞግሳት በነበረችው ጨረቃ ምክንያት የቤተሰቡ ደስታ በመጥፋቱ ከእንግዲህ በተስፋ የተሞሉ ቃላትን ለቤተሰቡ ቢያወራ ሰሚ እንደማያገኝ አውቆታል
ተከፍቷል ትኩረቱን ከህፃናቱ ቢያረገም አብሯቸው እያለ በሀሰብ መንጎዱን ተያይዞታል እያለ እንደ ሌለ ሲሆን ህፃናቱም ተከፍተዋል
ፊያሜታም በፊንሀስ እቅፍ ውስጥ መዋል ጀምራለች ፍርሀቷ አይሎ ባጣው ወይስ ቢያጣኝ እያለች ትብሰለሰላለች
ተስፋ ሚያስቆርጡ አስተያየቶችን እያየችው ሆዱን ታባባዋለች
ፊንሀስ መቅሰፍቱን ባያጠፋ እንኳ ይሄን ስሜት እንዴት ሊያጠፋ እንደሚችል ያሰላስላል ሞትን መፍራት በሕይወትህ ደስታ እንዳታገኝ እንቅፋት ይሆንብሃል ዕብራውያን 2:15 ብሎ ያነበበውን እያስታወሰ ነገሩ በሙሉ ዞሮበታል ህይወት ህይወት የሆነው በሞት እንደሆነ ስለሚያስብ እሱ ሞትን አይፈራም ይልቁንስ አጠገቡ ያሉትን በሞት ሲነጠቅ ነው ህይወት ለእሱ ትርጉም አልባ ምትሆነው
ቤተሰቡ አሁንም በሀሳብ እያለቀ ነው

ይቀጥላል...
 ብላቴናው በእርግማን ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
አመፅ!!
(በእውቀቱ ስዩም)
በለው! በለው! ዛሬ ታሪክ ተሰራ! ከተማውን ባንድ እግሩ አቆምነው!!
“ሽጉጥ መትረይሱን አንግቶታል
ያ ጥቁር ግስላ ደም ሽቶታል”
የሚለውን የአለማየሁ እሼቴን ዘፈን በአለማየሁ ፋንታ ድምፅ እያንጎራጎርሁ ከቤቴ ወጣሁ ፤ ፓርኩ ላይ ስደርስ አንዲት ደርባባ ኤሽያዊት ሰልፈኛ ተዋወቅሁ፤
ከኢትዮጵያ እንደሆንኩ ስነግራት አይኗ በደስታና ባድናቆት ብዛት ተጨፈነ ፤ባጠቃላይ ፊቷ ግንባር ሆነ ፤
“ እኔ ከደቡብ ኮርያ ነኝ “
“ አያቴ ስለ አገርሽ ብዙ ይነግረኝ ነበር ፤ በነገርሽ ላይ አያቴ እናንተ አገር ዘምተው ከነበሩት ዘማቾች አንዱ ነው ” ብየ ቀደድኩ፤
“የምርህን ነው?”
“ አያቴ ይሙት”
‘ ኦ ማይ ጋድ ! “ ልትጠመጠምብኝ እጆቿን ዘርግታ ስትንደረደር ገለል አልኩ፤ ከፊት ለፊቷ ከቆመው ዘንባባ ላይ ተጠመጠመች፤
“ ዛሬ በተቃውሞ ላይ ለመሳተፍ መወሰንህ ያያትህን ጀግንነት መውረስህን ያሳያል” አለችኝ::
“ነው ብለሽ ነው?” አልኩና እየተሽኮረመምሁ ወደ ለበሰቺው ቁምጣ ተመለከትኩ::
እሷ በቁምጣ እኔ በቁጣ ተሞልተን መራመድ ጀመርን!! የኦሃዮን ወንዝ የሚያሻግረውን ብጫ ድልድይ አልፈን ዳውንታውን የሚያስገባ አውራ ጎዳና ላይ ስንደርስ የተቆጣው ሰልፈኛ ቁጥር እየጨመረ ሄደ ፤ ጥቁር፤ ነጭ፤ ላቲኖ ኤሽያ የቀረ የለም፤ ዳውንታውን ስንደርስ የቤት መዝጊያ የሚያካክል የመስታወት ጋሻ የያዙ ፖሊሶች ተሰልፈው ጠበቁን ፤ ካጠገባቸው ፤ አድማ በታኝ መኪና ፤ ብረት ለበስ መኪና ፤ ታንክ እና ያየር መቃወሚያ ሳይቀር ያየሁ መስሎኛል፤ ሰልፉ በሰላም እየተካሄደ እያለ አንድ የተረገመ ጎረምሳ ጋዝ የተሞላ የሄኒከን የቢራ ጠርሙስ ወደ ፕሊሶች ወረወረ! (ሄኒከን ቢራ የሚቀጥለውን ፅሁፌን ስፖንሰር እንደሚያደርግ ተስፋ አደርጋለሁ )፤
ወድያው ከፊት ያለው ፖሊስ ሰልፈኛውን የፕላስቲክ ጥይት ተኩሶ ጠነበሰው ’፤ አየሩ በስጋትና በቁጣ ተሞላ፤፤ ji young ( የኮሪያይቱ ስም ነው) መፈክሯን አንከርፍፋ አይን አይኔን ታየኛለች፤
“ ጥግሽን ይዘሽ ጠብቂኝ “ አልኩና ጃኬቴን አውልቄ አቀበልኳት
“በጨበጣ ልትገጥማቸው ባልሆነ” አለችኝ ባድናቆት ጮሃ ::
“ በጨበጣ ካልሆነማ በርቀት በፕላስቲክ ጥይት ለቅመው ይጨርሱናል” ስል መለስኩላት፤
“ ስማኝ ሃኒ “ አለችኝ “ በጣም ከተጠጋኻቸው pepper spray ይረጩሀል አለቺኝ”
“ አታስቢ ! በርበሬ ስታጠን ስላደግሁ ችግር የለም፤ “
ወደ ፖሊሶች መራመድ ጀመርኩ፤ ተቃዋሚው ሰልፈኛ ፀጥ አለ! ፖሊሶች አይናቸውን ማመን አልቻሉም፤ ቶሎ ብለው አንድ ቁና ጭስ ለቀቁብኝ፤ በልጅነቴ፤ የጎረቤታችን ጠላ ሻጭ ሴትዮ የጠላ ቂጣ ሲጋግሩ ያለ ፍላጎታችን ጭስ ሲያካፍሉን ስለኖሩ አይኔ ለምዶታል ፤ እንዲያውም ቤት ውስጥ መለስተኛ ጭስ ከሌለ አይኔ በቅጡ አያይልኝም፤
ፖሊሶች ሁለተኛ ዙር ጭስ ለቀቁብኝ ፤ ይሄኛው ጭስ አፕል ፍሌቨር እንዳለው ልብ አልኩ!
ከፊት ለፊት ከቆመው ፖሊስ ልደርስ ሁለት ጫማ ሲቀረኝ ስልኬን አውጥቼ ፎቶ አነሳሁት፤
ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ ወደ ነበርኩበት ተመልሼ ስቆም::
“ ለመሆኑ አያትህ ኮርያ የዘመቱት በምን ዘርፍ ነበር ?” አለቺን ጂ ያንግ !
“ በጋዜጠኝነት”

@wegoch
@wegoch
ጓዶች በምሽጋችሁ ሆናችሁ ስለሰዓት ሽግሽጉ አድምጡ!

ወደ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ደወልን እንዲህም አልናቸው

<< አብዮተኞች መታገስ አልቻሉም ቶሎ አፍጥኑትና ፕሮግራማችን ይተላለፍ ፡ አለበለዚያ ሽምቅ ተዋጊ ገጣምያን የሰላ ብዕራቸውን ያነሳሉ በቃላት ወጋ ወጋ ማረጋቸውም አይቀርም >>

እነሱም << መቼስ አብዮቱ ካዘዘ የማይሆንለት የለም ብለው ዛሬ ምሽት 2:30 አይናችሁን ETV መዝናኛ ላይ አርጉ>> ብለውናል

እናመሰግናለን!!!

ከሁሉ የናፈቀኝ እኔና ጋዜጠኛዋ የተወዛወዝናትን ነገር

ሚካኤል አስጨናቂ ሳኒታይዘር አረጋለሁ ብሎ ሲነሳ ሆዱ አከባቢ ያለችዋ ቁልፍ ተስፈንጥራ ስለመወደቋ

#ማየት ! 2:30 እንገናኝ ETV መዝናኛ

አብዮተኞች ብትችሉ ይቺን ፎቶ እየወሰዳችሁ ራሳችሁ ጋር አስተዋውቁ፡፡

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወንዶቹን ምን ነካቸው?
<<ሚካኤል አስጨናቂ>>
የሆቴሉ በረንዳ ላይ ያለን የአዳም ዘሮች ሁሉ ፊታችን በጀርባችን አቅጣጫ እስኪደርስ ድረስ ተሽከረከርን :)
ድምቅ ያለው ጨዋታ ከየት መጣ ባልተባለ ምትሀታዊ ውበት ረጭ አለ !
ለካ የሴት ልጅ ውበት ጥይት ነው አልኩኝ።
አማፂ ተሰብስቦ እየወከበ ሳለ ድብልቅ ብሎ እንደጮኸ ጥይት ከየት መጣ ያልተባለ ፀጥታን አጥለቅልቃን ሄደች።
እሷ መታጠፊያው ዘንድ እስክትደርስ ድረስ ከልጅ አባቶች ጀምሮ እስከኛ አፍላ ወጣቶቹ ድረስ ትንፍሽ ያለ የለም።
የቤታቸው ሸለቆ ጋር ደርሳ እጥፍ ስትል ።
"ፓ !" አለ አቡሻ እየተቅበዘበዘ.. .
እውነትም ፓ !
ፓ ዳሌ ...ፓ ጠጉር ...ፓ የእግር ጣት ...ፓ ፈገግታ ።
ወንዶች ላይ መዓት ወረደብን....መብረቅ ተላከብን...ወጀብ አንገላታን ...ማዕበል ናጠን....የሁላችንም ምናብ በዝሙት ጦር ተወጋ ።
ይህች ሴት ማናት ?
ዳዊት ማብራራቱን ያዘው....ይህችን ልጅ እንዴት እስከዛሬ አታውቋትም? የእትዬ ዓለም ልጅ እኮ ነች...ቂጥ የዘራቸው ነው...ቤቱ እንዳለ በቂጥ ደኖች የተሞላ ነው አለን ...
መስፍኔ ቀጠለ ..."ይህችን ሴት ማን ወንድ ደፍሮ ይናገራታል? ባለ መኪና ነሽ...ባለ ህንፃ ነሽ...ባለ ድርጅት ነሽ ሁሉ ይፈሯታል....ውበቷን ይፈሩታል....ሁሉም ይመኟታል አንዳቸውም አይጠይቋትም" አለ..
እውነት ነው !
ልጅቷን እኔም የመጀመርያ ጊዜ ሳያት
"ይህች ልጅ ታውቃታለህ?" የሚል ቃል ከአንደበቴ እንዴት እንዳመለጠኝ አላውቅም...
ያኔ በግዜው አጠገቤ ተቀምጦ የነበረው ስምረት.. .
"ተው ! ተው ! ይሄ እቃ ገራሚ ባሉካ አለው። ባሉካው አሜሪካ ነው ያለው...ቀላል ገንዘብ አይበጭቅም አልኩህ...በቀን ብቻ ሶስት ጊዜ ነው ልብሷን የምትቀይረው" ብሎ ሙቁ ስሜቴ ላይ በረዶውን ወረወረ ።
ዝም አልኩኝ...ከዛ ቀን በኋላ ዛሬ ያቺን ሴት ደግሜ እስካያት ዘንግቻት ሰንብቻለሁ ....
ይህን ጊዜ ታድያ የሁሉንም አዳም ሀሳብና ግምት በፅሞና ሲከታተል የነበረው ፍቅሩ ይግረማቸው ብሎ እስካሁን አምቆት የነበረው ጉድን አፈነዳው።
"ልጅቷ የባቢ ቺክ ናት።" አለን!
......ገረመን ....
ባቢ ያ ቺስታው ?
ባቢ ያ ገራጅ ቤት በቡትቶ ቱታ የሚወላገደው?
ያ ጥራዝ ነጠቁ ቀለም የማይዘልቀው ባቢ
ያ ጥርሰ ብልዝ ጫታም...ሲጃራም...አረቄያም እውነት ይህችን ሴት ጠብሷታል?
.
"አዎ !ድብን አድርጎ ... ድንግልናዋ ሁሉ ለሱ ነው ሰፈፉ የደረሰው ..."
እርፍ!
"ያ አሜሪካ አለ የተባለ ባሏስ?
ያ ገንዘብ በየወሩ እየላከ የሚይፕብነሸንሻት ሸበላ ልጅስ?" ...ጠየኩት
"ማነው ይሄን ያለው?...ሰው እኮ ወሬ እየፈጠረ ነው የሚያወራው...ምንም ባል የላትም :) ...እንደውም ባቢ እሷን ለፍቅር የጠየቃት የመጀመርያ ወንድ እንደሆነ ነው የነገረችው ።"
"እርግጠኛ ነህ ?"
"ድብን አድርጌ !...ባቢ ደባሌ እኮ ነው...ፍቅራቸው ከተጀመረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያለውን ሂደት ከኔ በላይ የሚያውቀው ማን አለ ?"
ከጥግ በኩል ያ ነፍሰ ሰላላ ው አቡሻ እየተቅበጠበጠ አንድ ቃል አወጣ ።
"ፓ !...እውነትም ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም !
ባቢ ይመቸው :) "

@wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/09/24 23:21:56
Back to Top
HTML Embed Code: